Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

Archive for the month “November, 2013”

በሳውዲ አገር የተፈጸመው የኢትዮጵያውያን ውርዴት ያተስተናገደው ማን እንደሆን የማያውቅ ወይም የሚጠራጠር ካለ መልሱ (ተ.ሀ.ሕ.ት.) ነው።

ከጎሹ ገብሩ

በመጀመርያ የወገናችሁ ሥቃይና መከራ አንገብግቧችሁ ሲያለቅሱ አልቅሳችሁ፣ሲከፉ አብሮ ለምከፋት፣ሲቸገሩ ችግራቸውን አብሮ ለመጋራትና በደላቸው የናንተ በደል መሆኑን ለማሳዬት በዓለም ዙርያ ለምትገኙ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች በሙሉ በጣም ኮርቸባችሁ አለሁ። ወሳኙ ሰላም፣ፈቅርና አንድነታችን ማረጋገጥ የምንችለው በጋራ ሥናብር ብቻ ለመሆኑ እሩቅ ሳንሄድ የወያኔው ድራማ በጌቶቻቸው አገር ሽፋንና ከለላ በመጠቀም ያደረጉትን እኩይ የመሃይሞች ድርጊት ውስጡ ለቄስ መሆኑን እርቃኑን በማውጣት ዓይንና ጀሮ ኑሮት ማየትና መስማት ለሚችል ከማስጠንቄቃው ጋር የተላለፈው መልዕክት የመጨረሻው የኢትዮጵያውያን የበቃን ኑዛዜ ነው። ወላጆቻችን አሟሟቴን አሳምርልኝ ብለው ሲፅልዩ ሰንሰማ ለሞት ምን ጌጥ አለውና ብለው ነው እንዲህ የሚሉት እያልን የአባባሉ ትርጉም ሳይረዳን የምናነዉር ወይም የምናሽሟጥጥ ነበርን።

ይሄውና ሲሉት የነበረዉ አባባል ፍልትው ብሎ ለማየት በቅተናል።እነዚህ በሳውዲ አረብያ ሬሳቸው በጎዳና ላይ እንደ በድን ውሻ ሲጎተቱ ፣የሚያምረው ምስላቸው እንደ ከሰል ጠቁሮ ያየነው፣በአረቦች የሰላ ጎራዴ የሰራ አካላታቸው ተዘልዝሎ ያየነው፣እጅና እግሮቻቸው አስረውና አዘቅዝቀው እየተረዳዱ በአኮርማጆ ሲደበደቡ ድምጻቸው ከፍ አድርገው በእግዚያብሄር ሥም ማሩን የሚሉት እህት ወንድሞቻችን ለነጻነትና እንጀራ ፍለጋ የመጡ እንጅ የፈጸሙት በደል ወይም የሚያውቁት ሌላ መንም ነገር እንደለለ የማያውቅ ይኖራል ብየ አልገምትም። ሥለዚህ በማያውቁት አገርና ህዝብ እንደ ረከሰ እንሰሳ ተወርውሮ መቅረትን ስላስጠላቸው ነው ወላጆቻችን ይህን ብለው ሊፅልዩ የቻሉት። ሞት የማይቀር ለሁሉም ፍጡር ግዜው ጠብቆ በቀጠሮው ቀን ከተፍ የሚል አድሎ የማይታይበት  የእግዚአብሄር  ስጦታ ነው።

ስደት ጥንትም የነበረ አሁንም ያለ ለወደፊትም የሚኖር ነው አሁን በኛ  አልተጀመረም። ከ1400 ዓመት በፊት የነብዩ መሐመድ ተከታዮች ከአገራቸው ሸሽተው የኢትዮጵያን አፈር ሲረግጡ  መጠግያ ሰጥተን ያስተናገድን እንግዳ ተቀባዮቹ ኢትዮጵያውያኖች ውለታችን ተዘንግቶ በሳውዲ ቅልብ ወታደሮች አጥንታችን ከስክሰው ደማችን ያፈሰሱት በቅዱስነቱ ከሚታወቀው ከተማ መሃል ላይ ነው።ግን ትእዛዙ የሰጣቸው አካል ከመጋረጃው በኋላ መሆኑ ብንግነዘብም ቅሉ ይህ ዓይነት ድርጊት ለመፈጸም ያደፋፈሯቸው ሁለት መክንያቶች ጠቅሼ ማለፍ እፈልጋለሁ፦

  1. አንደኛና ዋናው ምክንያት ብየ የምገልጸው በኢትዮጵያውያን መካከል የነበረው መተሳሰር፣ህብረትና ጠንካራው አንድነታችን ለ23 ዓመታት ያህል ለህልውናችን ተፈታታኝ በሆነ መልኩ በመላልቱ ምክንያት በደል እያደረሱብን ያሉት ጠላቶቻችን በቅርብ ሆነው ስላጤኑት አሁን የፈለግነው ብንሰራ ሊያቆመን የሚችል ሃይል  የለምና ትዕቢታቸውን አፈንድተን  የባርነት ቀንበር ልንጭንባቸው የምንችለው ወቅቱ አሁን ነው በማለት ይሄውና በ21ኛው ክፍለዘምን የባርያን ሥራአት አድሰው በኛ ላይ ለመጫን እየተደረገ ያለ የሂልና ጦርነትና ሰጥ ረጭ አድርጎ ለመግዛት የተተበተበ የኋላ ቀሮች ቅዠት ሲሆን።

 

  1. ሌላው አብይ መክንያት ደግሞ ወገኖቻችንን ማሰቃዬት የለብህም በሎ የሚገላምጥና የሚያፈጥ የኛ የምንለው መንግስት የለለን፣አለ የሚባልለት የተጋድሎ ሀርነት ህዝብ ትግራይ(ተሀህት)መንግስትም በቱጃሮች ሳምባ የሚተነፍስና የሚሽከረከር በጥቅም አይኑ የታወረ ለነሱ የቆመ በመሆኑ በኢትዮጵያውያን አይሰሩ ግፍ ቢሰራም ደንታ የለለው በመሆኑ የተነሳ የንጹሃን ኢትዮጵያውያን ደም በስውዲ መናገሻ እንደ ጎርፍ ሲፈስ እያየ ብዙ ምክንያቶች በመደርደር አድበስብሶ ከማለፍ በቀር የሰራው ምነም ነገር የለም። ከሁሉ በላይ የሚያሳዘነው የተሀህት ተውካይ ተብየው ትእቢት በተሞላው አንደበቱ ሳውዲ የወሰደችው እርምጃ አግባብነት ያለው ነው ብሎ የምስክርነት ቃሉ ሲሰጥ ተሀህት ለማን እንደቆመ ግልጽ አድርጎ የሚያሳይ ማስረጃ ነው።ጥቂት ለወያኔ ያደሩ ግለሰቦች ለፖለቲካ ፍጆታ ሲል በአፋጣኝ ቢያጓጉዝ ነገር ግን ግምቱ 23000 የሚጠጉት ወገኖቻችን ግን በስቃይ ላይ ለምሆናቸው የምናየው የምንሰማው ሃቅ ነው። መንግስት ያላቸው ሀገሮችማ ዜጎቻቸውን ለማዳን ምክንያት ሲለግቡ አይታዩም።

 

ለምሳሌ ያህል ለመጥቀስ፦ መንግስት የላትም የምትባለው ሶማሊያ እንኳ በቅርብ ወራታት ውስጥ አንድ የሶማሊ ዜጋ በመገደሉ የተነሳ ለደቡብ አፍሪካ መንግስት የወገኔን ገዳይ ለፍርድ ካላቀረባችሁ ከናንተ ጋር የሚኖረን የዲፕሎማሲ ግንኙነት አቋርጣለሁ በማለቷ የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናትም ለጉዳዩ ተኩረት በመስጠት በነገሩ ለመተባበር ተስማምተዋል። ሌላው ከ20ና ከ25 ዓመት በፊት የናይጀርያ ዜጎች በሱዳኗ መናገሻ ከተማ ካርቱም ላይ ችግር ቢከሰትባቸው የናይጀርያው መንግስት ስድስት ስዓት በማይበልጥ ግዜ ዜጎቹን በሙሉ ወደ አገራቸው በማጓጓዝ አደጋውን ሊከላከል ችሏል።አገር ቤት ያለው ወገናችን በወገኖቹ ላይ የተፈጸመውን በደልና ሥቃይ ለመቃወምና ብሶቱን ለሳውዲ መንግስት ለማሰማት በህገ ደንባቸው ያሰፈሩትን መብት ተጠቅሞ ቢወጣ በወያኔው የፌደራል ቅልብ ወታደር የደረሰበት በደል፣ሥቃይና ድብደባ ያላዬ ይኖራል ብዬ አልገምትም።

ይህ በኢትዮጵያውያን ያንዣበበው አደጋ ለመከላከልና ቀርፈን መጣል የምንችለው በኢትዮጵያዊነት ሥም ተባብረን ስንመክት ብቻ ነው። በጎሳ፣በዘር፣በጎጥና በሃይማኖት መለያየቱ ምንኛ እንደጎዳን ለቀባሪ እንደ ማስረዳት ስለሚሆንብኝ መልሱ ለናንተ ልተወው።

ነገር ግን አንድ ተልቅና ብሩህ ተስፋ ሰጭ ሆኖ ያገኘሁትና የታዘብኩት ነገር ቢኖር በተለያዩ ምክንያቶች በየ ማእዘኑ አንገቱን አጎንብሶ የነበርው ኢትዮጵያዊው ወገናችን ከጠርዝ አስከ ጠርዝ ተቆጥቶ በመነሳት ያሳየው ህብረት ለጠላቶቻችን ያርበደበደ ትልቅ የህልውናችን መለያ የሆነውን አንለያይም አንድ ነን ማለቱን ነው።

ወያኔ ባይገፋኝ ከተወለድኩበት

ሰደትን መምረጡ መች ወደድኩት

መብቴ ተረግጦ ነው የተዋረድኩት

እህቶቼም ተደፈሩ ሳይወዱ በግድ

ደሜም አጨቀየው የሳዉዲ አስፓልት

ከባህር ማዶ ላለነው ከአገር ቤት

እረ-ፍርዱ ሰጠን የሰማዩ አባት።

ኦ-ሳውዲ በስመ ገናና

ወራዳ ልበልሽ የድሃ ደመኛ

ህጻናት የሚረሽኑብሽ ከአውላላው ጎዳና።

 

በቅድሱ ስፍራ በሁሉ የሚከበር

የንጹሃን አካል ተዘልዝሎ ሲመተር

ፍጡርን የሚያሰቃይ በሚዘገንን

ያውም በሰለጠነው በአሁኑ ዘመን

በጣም ያሳፍራል እንዲህ ለመናገር።

ኩላሊቱን ለማዘረፍ የሰራ አካላቱ

ከቶ ለምን ይሆን ወደ አረብ መሰደዱ

እንዲህ ለማይቀረው ተዋርዶ መሞቱ

ተከብሮ ለመቀበር በወገን ዘመዱ

ከባድማችን ላይ ይሻላል መሞቱ።

መሳለቅያ ሆነናል በሞላው ዓለም ላይ

ይብቃን ውርዴት እንግልት ስቃይ

በክብር እንሙት ከአፈራችን ላይ።

 

በወገኖቻችን ላይ የተፈፅመው በደል

ውጤቱ ይታያል ሳይውል ሳያድር

እንዲህ ያለ ግፍ እንዴት  ይረሳል

በሰፈርይት ቁና መሰፈር አይቀር።

አጼ ተዎድሮስ ቢኖሩ በሕይወት

ምን ይሉ ይሆን በውንት

አብደላ ሳውዲን በኢትዮጵያውያን ደም ሲያጨቀያት።

መስዋእትነት የከፈሉትን ወገኖቻችን መንግስተ ሰማያት ያዋርሳቸው

 

Ze-Habesha

posted by Tseday Getachew

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በውጭ ስርአቱ ጥሩ ነው ይበሉ እንጅ በግል ሳናግራቸው ለውጥ እንደሚፈልጉ ገልጸውልኛል ሲሉ ወ/ሮ አና ጎሜዝ ተናገሩ

Ana Gmes Speaks: Addis Standard’s exclusive interview 

ኢሳት ዜና :-የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባል እና የኢትዮጵያን የ1997 ምርጫ የታዘቡት ወ/ሮ አና ጎሜዝ ይህን የተናገሩት አዲስ ስታንዳርድ ለተባለ የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ነው።

በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው የአውሮፓ፣ አፍሪካና ካረቢያን አገሮች የፓርላማ ጉባኤ ላይ የተገኙት ወ/ሮ አና የአምባገነን ምንጭ የሆነው መለስ ዜናዊ ቢሞትም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካዊ ለውጥ አለመምጣቱን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ተለውጣለች በማለት በአደባባይ የሚናገሩት ባለስልጣናት በግል ሳነጋግራቸው በኢትዮጵያ ፈጣን ለውጥ መደረግ አለበት ብለው ይላሉ ያሉት ወ/ሮ አና፣ አቶ ሀይለማርያም  ከሙስና ጋር በተያያዘ አንዳንድ መጠነኛ እርምጃዎችን ቢወስዱም፣ የትግራይ ተወላጅ ባለመሆናቸው ስልጣናቸውን ለማቆየት እየተቸገሩ መሆኑን ገልጸዋል። ቀደም ብለው እስክንድር ነጋንና ርእዮት አለሙን ለመጎብኘት በጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ትእዛዝ ወደ ቃሊቲ የተጓዙት የአውሮፓ ህብረት ልኡካን፣ በእስር ቤቱ ሀላፊዎች መከልከላቸው በአገሪቱ ውስጥ ያለውን እውነታ የሚያሳይ ነው ያሉት ወ/ሮ አና በኢህአዴግ ውስጥ ከፍተኛ የስልጣን ሽኩቻ እንዳለ እንደሚያውቁም ተናግረዋል።

የመለስ ዜናዊ መንግስት ስልጣኑን ለማቆየት ሲል ሙስሊምና ክርስቲያኑን ለማጋጨት ጥረት ሲያደርግ እንደነበርም የፓርላማ አባሉዋ ተናግረዋል። የኢትዮጵያን ወጣቶች አፍኖ መያዝ አይቻልም ያሉት ወ/ሮ አና የፖለቲካ ሜዳውን ለዲሞክራሲ መክፈት ኢትዮጵያን ከውድቀት እንደሚታደጋት ገልጸዋል።

ESAT

posted by Tseday Getachew

ከኢትዮጵያ ዜጎች ጋር በተያያዘ በሳውድ አረቢያ ከፍተኛ የሆነ አደጋ ማንዣበቡን ኢትዮጵያውያን ተናገሩ

 ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ የሚታየው ሁኔታ እጅግ አስፈሪ ነው ይላሉ ያነጋገርናቸው ዜጎች። ከ40 ሺ በላይ ኢትዮጵያን በእስር ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ። ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቀናቸውን ይጠባባቃሉ። የኢትዮጵያ መንግስት በመቶ ሺ የሚቆጠረውን ስደተኛ ለማስተናገድ የመደበው የሰው ሀይል 40 ብቻ ነው። የሳውድ አረቢያ መንግስት ደግሞ በተዘዋዋሪ መንገድ ኢትዮጵያውያን ከአገሪቱ ምድር ተጠራርገው እንዲወጡ እየቀሰቀሰ ነው። ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አደጋ ሊፈጠር ይችላል ብሏል  አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ ጋዜጠኛ።

በዛሬው እለት በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች የተበተነው የኤስ ኤም ኤስ መልዕክት  ህጋዊ ለተባሉትም ሆነ ህገወጥ ለሚባሉት ኢትዮጵያውያን የማስጠንቀቂያ ደወል ነው ይላሉ እኝህ ጋዜጠኛ።

በሞባይል ስልኮች የተበተነው ኤስ ኤም ኤስ ኢትዮጵያውያንን ቀጥራችሁ የምታሰሩ እንዲሁም መኖሪያ ቤት ያከራያችሁ ሁሉ በአስቸኳይ እንድታስወጡ፣ ይህን ባታደርጉ ግን 100 ሺ ረያል ትከፍላለችሁ የሚል እንደሆነ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል። ይህን መልእክት ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከተከራዩበት ቤት ተባረዋል። 9 ኢትዮጵያውያንን ወደ አስጠጋው ኢትዮጵያዊ በመደወል መታሰቢያ ቀጸላ አነጋግራቸዋለች። እርሱ እንደሚለው መልክቱ መተላለፉን ተከትሎ ጓደኞቹ ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርጎ በእርሱ ቤት ተጠልለዋል

ከቤታቸው ከተባረሩት መካከል አንዱ ከ8 ወራት በፊት አባቱ ቤታቸውን ሸጠው ፣ በኪራይ ቤት እየኖሩ በህጋዊ መንገድ እንደላኩት ይናገራል። አሁን ቤትክን ለቀህ ውጣ ተብሎ ህይወቱ አደጋ ላይ ወድቋል

የሳውዲ መንግስት በኦፊሴል እንዲህ አይነት መልክት ያስተላልፍ እንደሆነ የጠየቅነው ጋዜጠኛ፣ መንግስት በቀጥታ እንዲህ አያደርግም ነገር ግን እርሱ ባሰማራቸው ሰዎች አማካኝነት መልክቶችን እንደሚሰድ ይታወቃል ብሎአል።

የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ዘመቻ በማድረግ በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ህይወት መታደግ ሲችል በቀን ይህን ያክል ሰው አስመጣሁ በማለት ፕሮፓጋንዳ ይነዛል የሚለው ጋዜጠኛው፣ በሳውዲ የቀረው ኢትዮጵያዊ ወደ አገር ቤት የተመለሰውን በብዙ እጥፍ ይበልጣል ሲል በአገሪቱ ያለውን እውነታ አስረድቷል።

በሌላ በኩል ከሳውድ አረቢያ ወደ የመን የገቡ 3 ሺ ያክል ኢትዮጵያውያን በምግብ እጥረት ተጎሳቁለው እንደሚገኙ እስር ቤት ድረስ በመሄድ ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሀይማኖት ጎብኝቷቸዋል።

ESAT

posted by Tseday Getachew

ከሳዑዲ አረቢያ ወደ የመን የገቡ ስደተኞች እና እስከ ትላንትና ወዲያ ከጅቡቲ በባህር ወደ የመ የገቡ እስረኞች በግሩም ተ/ ሀይማኖት

ዛሬ አርብ ሰነዓ የሚገኝው የኢሚግሬሽን እስር ቤት ያሉትን እስረኞች ለማየት (ለመጠየቅ) ሄድን፡፡ እንደተለመደው ምግብ፣ የልብስ ሳሙና፣ የገላ ሳሙና፣ ከየሰዉ ያሰባሰብኩትን ልባሽ ልብስ፣ ባዝሊን፣ ሲጋራ..የሚመሳስሉትን በአቅሜ ለማዳረስ የምችለውን ያህል አዘጋጅቼ በማደሉ የሚያግዙኝ ሰዎች ጨምሬ ሄድኩ፡፡ ያሉት የእስር ክፍሎች ሞልተው ሜዳው ሁሉ በኢትዮጵያዊያ ተሞልቷል፡፡ ህጻናት ሳይቀር ጊቢውን አጨናንቀውታል፡፡ ከሳዑዲ አረቢያ ሸሽተው ወደ የመን የመጡ በግምት ከሶስት ሺህ በላይ ናቸው፡፡ ባሉት ሰዎች ልክ ለማዳረስ አልችልም፡፡ በሌላ በኩል ሌሎችም ሁለት ሴቶች እንዲሁ የአቅማቸውን መጠነኛ ነገር አዘጋጅተው ነበር፡፡ ያንን ለማዳረስ ስላልቻልን ሁሉን ነገር ለሁለት ለሁለት እያጣመድን መስጠት ተገደን ነበር፡፡ በየክፍሉ ካሉት ተጨማሪ ከእስር ክፍል ውጭ ያሉትን ስናድል ነው ቪዲዬው ላይ የሚያሳየው፡፡ የሚገርመው ነገር በባህር መሻገሩ ቢቀንስም አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ በባህር ሲመጡ ተይዘው ትላንት ኢሚግሬሽን እስር ቤት የገቡ ሁለት ልጆች አግኝተናል፡፡ የአግዙን ጥሪ የመን ሰነዓ ነዋሪ የሆናችሁ ወንድም እህቶች እባካችሁ የአቅማችሁን በማድረግ ልብስም በማሰባሰብ እንርዳቸው፡፡ አሁን ያሉበትን ሁኔታ ጉስቁልቁለ

posted by Tseday Getachew

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!

በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንምመከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው።

ወያኔ ስላልቻለ ነው እንጂ ይህንን ከአለም አጽናፍ እስከ አለም አጽናፍ ያስተጋባ የወገን ደራሽ ድምጻችንን አዲስ አበባ ላይ እንደ አደረገው በሃይል ለማፈን ወደኋላ አይልም ነበር።

ሀፍረት የለሾቹ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች ይህን የተጋለጠ ሀገርና ህዝብ አዋራጅ ተግባራቸውን እና በውሸት የተበከለ ገመናቸውን ለመሸፈን ከዚያም አልፈው የዋሆችን በማታለል የፖለቲካ ትርፍ ለማትረፍ የተለመደ ቲያትር መስራቱን ተያይዘውታል። ቴዎድሮስ አድሃኖም ችግሩ ባለበት በሳውዲ መሬት ላይ ሳይሆን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በራሱ ወጪ አሳፍሮ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ባፈሰሳቸው ኢትዮጵያውያን መሃል እየተጎማለለ ያዛኝ ቅቤ አንጓች ቲያትሩን ሲሰራ ትንሽ እንኳን ሀፍረት አይታይበትም።

እነዚሁኑ ወደ ሀገር የተመለሱ አእምሯቸው በችግር የተመሰቃቀለ ዜጎች ወደ ካሜራ እየገፉ ስለ ሳውዲ ኤምባሲያቸውና ስለመንግስታቸው ‘ድንቅ” አገልግሎት እንዲናገሩ ያስጠኗቸውን ተመሳሳይ አረፍተ ነገር መስማት የሚያሳዝን ባይሆን ኖሮ ተወዳዳሪ የሌለው ኮሜዲ ይወጣው ነበር።

እውነቱ ዛሬ በሀገራችን የሰፈነው ስደትና አብሮት የሚመጣው መከራ ሁሉ ዋናው አምራች ፋብሪካ ወያኔ መሆኑ ነው። ወያኔ የገነባው ጥቂት ጀሌዎቹንና ሎሌዎችን ተጠቃሚ ያደረገና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በተለይ ወጣቱ በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ያደረገው ስርአት ነው። የስደታችንና የመከራችን ምንጭ ስደት የሚመጣው በሀገር ተስፋ መቁረጥ ነው። እንጀራ ፍለጋና ጭቆናና አፈና ሽሽት አምልጠን በየባዕድ ሀገሩ እንድንከራተት የሚያደርገን የወያኔ ስርአት ነው። በታሪካችን ውስጥ ተሰደን በባዕድ የተዋረድነው በወያኔ ምክንያት ነው።

በሀገር ውስጥ በአፈና ስር ሆናችሁ፣ በውጪው አለምም በየኢምባሲው የምታሰሙት ጩኸትና የምታፈሱት እምባ እብሪትና ትእቢት ያደነደነውን፣ ዝርፊያ ያደነዘዘውን የወያኔን ልብ እንደማያሸብረው ማወቅ አለብን።

የወያኔ ሹማምንቶች ይግረማችሁ ብለው ከአላንዳች ሀፍረት ያውም በሳውዲ አረቢያ ወጪ ተጓጉዘው ሀገር የገቡትን ግራ የተጋቡ ስደተኞች ለፖለቲካቸው ማሳመሪያ በቴሌቪዥን ስእልና ፎቶግራፍ መነሻ ሲያደርጉትና ለፖለቲካ ስራ መሳሪያ ሲያውሉት እያየን ነው። በነሱ ቤት ብልጥ ፖለቲከኞች መሆናቸው ይሆናል። በኛ ቁስል ላይ እንጨት እየሰደዱ መሆናቸውን ግን ፈጽሞ አይሰማቸውም።

ወያኔ በመካከለኛው ምስራቅ ተሰደው ለፍተው የሚኖሩት ወገኖቻችን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ያውቃል። ቢያንስ በየኢምባሲው ያስቀመጣቸው ነጋዴዎች ይነግሩታል። ችግሩን እንዳላየና እንዳልሰማ የሚያየው ከዜጎች ይልቅ እነሱ አፈር ግጠው ለፍተው ለሚያመጧት የውጪ ምንዛሬ የበለጠ ፍቅር ስላለው ነው። በዚህ ተግባሩ ወያኔ ወገኑን የሸጠ ባሪያ ፈንጋይ ነጋዴ እንጂ የመንግስት መሪ መሆኑ ያጠራጥራል።

ግንቦት 7 የፍትህና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ዘወትር እንደሚለው ሁሉ ይህ የዜግነትና የሀገር ውርደት፣ ይህ ሁሉ የወገን መከራ የሚቆመው የዚህ ሁሉ መሰረት የሆነው ወያኔና ስርአቱ ከመሰረቱ ሲነቀልና ሲወገድ መሆኑን ላፍታም አይዘነጋውም።

እንባችን የሚደርቀው ደማችን በየቦታው መፍሰሱ የሚቆመው መብታችን እንደዜጋ ተከብሮ ቀና ብለን የምንሄድበት ሀገር በትግላችን የተቀዳጀን ጊዜ ብቻ ነው።

ግንቦት 7ን ተቀላቀሉ በያላችሁበት ግንቦት 7 ሁኑ!! እኛ ከዚህ ውርደት ሞቶ የሚገኘው ነጻነት ይሻላል ብለን የተነሳን ልጆቻችሁ ነን። እርሰዎስ?

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

posted by Tseday Getachew

ከቤሩት የተሰማ አሰቃቂ መረጃ (ይህን ቪድዮ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ እንዲያዩት አይመከርም)

ወደ ዘ-ሐበሻ ዝግጅት ክፍል በፌስቡክ የግል መልዕክት አንድ እህት ብታነጋግሩኝ አሳዛኝና ማንም ያልዘገበው መረጃ ቤሩት ውስጥ የተፈጸመ አቀብላችኋለሁ አለችን። ፈቃዳችንን ገልጸን ስልኳን ተቀብለን ወደ ቤሩት ደወልንላት። አነጋግርናት። ሌሎችንም እንዲሁ አንጋገርን። ከዚያም የሚከተለው አሳዛኝ መረጃ እንዲህ ተቀናበረ።

http://www.zehabesha.com/

posted by Tseday Getachew

ቴዎድሮስ አድሃኖም ቢያጥቡት የማይጠራ ወያኔ ነዉ (ኤፍሬም ማዴቦ)

ኤፍሬም ማዴቦ

የኢትዮጵያ ህዝብና እናስተዳድረዋለን የሚሉት አምባገነን ገዢዎቹ ተስማምተዉና አንዱ ሌላዉን አክብሮ የኖረበት አንድም የታሪክ አጋጣሚ የለም። የእስከዛሬዉ ታሪካችን ምዕራፍ በጥቅሉ ሲታይ ታሪካችን የሚቋጨዉ ህዝብ ተረገጠ፤ ተጋዘ፤ ገዢዎች ደግሞ ረገጡ፤ገዙ፤ አሰሩ፤ አጋዙ እየተባለ ነዉ። አዎ! የኢትዮጵያ ህዝብ እስከዛሬ ባለዉ ታሪኩ ተግዟል፤ ተረግጧል፤ ተንቋል፤ ተንቋሿል። የዘንድሮዉ በተለይ ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት እየደረሰብን ያለዉ ብሄራዊ ዉርደትና ንቀት ግን ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ልዩ ከልዩም ልዩ ነዉ። በቀዳማዊ ኃ/ሥላሤ ዘመን የኢትዮጵያ ህዝብ ልክ እንደዛሬዉ ሰብዓዊ መብቱ ተረግጧል፤ ፍትህ ተነፍጓል፤ ነጻነቱን ተገፍፏል፤ ሆኖም አገር ዉስጥም ከአገር ዉጭም ፈላጊና ባለቤት አንደሌለዉ የቤት ዉስጥ እንስሳ የወገንም የባዳም እጅ አልተረባረበበትም። አንገፍግፎን አንፈልግም በቃ ብለን ያስወገድነዉ የቀዳማዊ ኃ/ሥላሤ ስርዐት በስልጣን ላይ በነበረበት ግዜ “ኢትዮጵያ” የሚለዉ ስምና “ኢትዮጵያዊነት” አገር ዉስጥም ሆነ አዉሮፓ፤ አሜሪካና አፍሪካ ዉስጥ እጅግ በጣም የተወደደና የተከበረ ስም ነበር። ዛሬ ወያኔ ነጻ አወጣኋችሁ፤ እኩልነት አመጣሁላችሁ እያለ በሚሰብክበት ዘመን ግን የኢትዮጵያ ሀዝብ አገር ዉስጥም በዉጭ አገሮችም ባለቤት አንደሌለዉ ፈረስ ማንም የሚጋልብበት ፈላጊ እንደሌለዉ  ዕቃ ያገኘ ሁሉ እንዳሰኘዉ እጁን የሚያሳርፍበት የተናቀ ሀዝብ ሆኗል። ለመሆኑ ለምንድነዉ ኢትዮጵያዊነት እንደዚህ  እንደ ተራ ዕቃ የቀለለዉ? ኢትዮጵያዉያንስ ለምንድነዉ በየሄዱበት እንዲህ አይነት ዉርደትና ስቃይ የሚደርስባቸዉ? መልሱ ቀላል ነዉ። “ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ” ወይም  “ባለቤቱ ያቀለለዉን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለዉም” ነዉ።

የወያኔ አገዛዝ እኛ ኢትዮጵያዉያን “ኢትዮጵያዊነት” እያልን ስለምንሳሳለትና ስለምንከባከብለት ትልቅና ክቡር ሀሳብ በፍጹም ግድ የለዉም። እንዲያዉም ወያኔ ሽንጡን ገትሮ ከሚታገላቸዉ ዋና ዋና ብሄራዊ እሴቶቻችን ዉስጥ “ኢትዮጵያዊነት” የመጀመሪያዉ ነዉ። ስለዚህም ነዉ ባለፉት ሃያ ሁለት አመታት በግልጽ እንደተመለከትነዉ “ኢትዮጵያዊነት”  ብለዉ የተጣሩ፤የጮሁ፤ ህዝብን ያስተማሩና የታገሉ ግለሰቦች በወያኔ እየተለቀሙ የታሰሩትና የተገደሉት። ከአገር ዉጭም ቢሆን በየዉጭ አገሩ የሚገኙት የወያኔ ኤምባሲዎች ኢትዮጵያዉያን ከአገራቸዉ ዉጭ ማግኘት የሚገባቸዉን የዜግነት አገልግሎት የሚሰጡት ዜግነታቸዉን እያዩ ሳይሆን ቦንድ የገዛ ያልገዛ፤ “ልማታዊዉን መንግስት” የደገፈ ያልደገፈ እያሉ ወይም “የወርቃማዉ ዘር” አባልነቱን እያጣሩ ነዉ። እነዚህንና ሌሎችም እነዚህን የመሳሰሉ ሰንካላ የወያኔ መስፈርቶች ያላሟሉ ኢትዮጵያዉያን አገር ዉስጥም ከአገር ዉጭም ወያኔ በዜግነት ሳይሆነ በጠላትነት የሚመለከታቸዉ ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃ ዜጎች ናቸዉ። ዛሬ ከአፍሪካ፤ ከኢሲያና ከላቲን አሜሪካ አገሮች ስራ ፍለጋ ሳዑዲ አረቢያ ከሄዱ ዜጎች ዉስጥ እንደ ኢትዮጵዉያን እጁንና እግሩን ታስሮ የተገረፈ፤ እንደሴቶቻችን በሳዑዲ ጎረምሶች የተደፈረና እንደ ኢትዮጵዉያን በየአደባባዩ የተገደለ የሌላ አገር ዜጋ የለም። ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ የሚገኙ የሌሎች አገሮች ኤምባሲዎች የዜጎቻቸዉ መብት በሳዑዲ መንግስትና ህዝብ ሲደፈር ለምን ብለዉ ይጠይቃሉ ወይም ለዜጎቻቸዉ ግዜያዊ መጠለያ፤ የህክምና እርዳታና የህግ ሽፋን ይሰጣሉ እንጂ ኤምባሲያቸዉ በራፍ ላይ “ዝግ ነዉ” የሚል ጽሁፍ አይለጥፉም።

የወያኔ ኤምባሲ ግን ከስረ መሠረቱ የተቋቋመዉ የወያኔን የራሱን እንጂ የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ስላልሆነ ይህንን የሌሎች አገሮች ኤምባሲዎች ለዜጎቻቸዉ የሚያደርጉትን ጥበቃና እንክብካቤ ለወገኖቹ ለማድረግ አልታደለም፤ ፍላጎቱም የለዉም።  ይህንን ቅሌትና ዉርደት ደግሞ ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት በግልጽ ተመልክተናል። ጂዳና ሪያድ ዉስጥ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰዉን መከራና በደል ተቃዉመዉ ሠልፍ የወጡ ኢትዮጵያዉያን በሳዑዲ ፖሊሶች ታድነዉ እንደታሰሩ ሁሉ አዲስ አበባ ዉስጥም በወንድሞቻችንና እህቶቻች ላይ እንዴት እንዲህ አይነት በደል ይፈፀማል ብለዉ ሳዑዲ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሠላማዊ ሠልፍ የወጡ ኢትዮጵያዉያን በአረመኔዎቹ የወያኔ ፖሊሶች ታድነዉ ታስረዋል፤ተደብድበዋል። አዎ! ኢትዮጵያዉያን ሳዑዲ ዉስጥም ኢትዮጵያ ዉስጥም ለምን የሳዑዲን መንግስት ተቃወማችሁ ተብለዉ በሁለቱም አገር ፖሊሶች እየታደኑ ታስረዋል ተደብድበዋል።

ከወያኔና ከጥቂት ሆድ አምላኪ ደጋፊዎቹ ዉጭ በአገር ዉስጥና በመላዉ ዓለም የሚገኘዉ ኢትዮጵያዊ በአንድ አላማ ዙሪያ የተሰባሰበበትና አንድ ሳምንት ሙሉ አንድ ቃል በአንድ ትንፋሽ የተነፈሰበት ግዜ ቢኖር ወርሃ ህዳር 2006 የመጀመረያዉ ነዉ ማለት ይቻላል። የአንድ አገር ህዝብ በአንድ አላማ ስር ሲሰባሰብና በአንድነት ሲቆም ከማንም ከምንም በላይ በዚህ አንድነት መጠቀምም መደሰትም ያለበት መንግስት ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ የወያኔ አገዛዝ ግን ዕቅዱና ስራዉ ሁሉ የኢትዮጵያን ህዝብ ማስጨነቅና ማበሳጨት ነዉ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ በሚሰራዉ ስራ ተደስቶ አያዉቅም፤ ለወደፊትም የሚደሰት አይመስልም። ከሰሞኑ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰዉ ልክ የሌለዉ ስቃይና መከራ መላዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ቀፎዉ እንደተነካ ንብ ከዳር ዳር ሲያስቆጣ ወያኔና ሞራለ ብልሹ ሹማምንቶቹ ግን ከዚህ ወገኖቻችንን በባዕድ አገር ለከፍተኛ ጥቃት ካጋለጠና ብሄራዊ ዉርደት ካከናነበን ክስተት ትርፍ ለማግኘት የፖለቲካ ቁማር እየተጫወቱ ነዉ። ኢትዮጵያዉያን ሳዑዲ ዉስጥ በአሰሪዎቻቸዉ፤ በመንደር ዉስጥ ጎረምሶችና በፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ፤ እንግልትና ዉርደት ሲደርስባቸዉ ኤምባሲዉ በራፍ ላይ “ኤምባሲዉ ዝግ ነዉ” የሚል ጽሁፍ በመለጠፍ ይበላችሁ እያለ አፉን ዘግቶ የተመለከተዉ የወያኔ አገዛዝ ዛሬ የወገን አሳቢና ተቆርቋሪ ለመመሰል የጭቃ ዉስጥ እሾኩን ቴዎድሮስ አድሀኖምንና የአገዛዙን የዉሸትና የቅጥፈት ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲን በግምባር ቀደምትነት በማሰለፍ የፖለቲካዉን ገደል ቁልቁል ተያይዞታል።

ቴዎድሮስ አድሃኖም ቢከፋም ቢለማም የአገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነዉ፤ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የስራ ሀላፊነት ደግሞ አገሪቱንና ዜጎቿን ከዉጭ አገሮች ጋር በሚያገኛኙ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ነዉ እንጂ በአገር ዉስጥ የሚሰራዉ ይህ ነዉ ተብሎ የሚነገር ስራም ሀላፊነትም የለዉም። አንዴ ወዳጅ አንዴ ጠላት እየመሰለ እንደ እስስት መልኩን የሚቀያይረዉ ቴዎድሮስ አድሀኖም ግን ሳዑዲ ዉስጥ ድረስልን ብለዉ ሲጣሩት ፊቱን ያዞረባቸዉ ኢትዮጵያዉያን አዲስ አበባ ሲመለሱ ያሉበት ቦታ ድረስ በመሄድ እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት ሲሞክር ይታያል።  ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆንስላ ጽ/ቤቶች ቅርቅር አድርጎ ዘግቶ የወገን ያለህ ብለዉ የመጡትን ኢትዮጵያዉያን እንጃላችሁ ብሎ ፊቱን ያዞረባቸዉ የአዛኝ ቅቤ አንጓቹ ቴዎድሮስ አድሃኖም እነዚሁኑ እንደ ባዳ ፊቱን ያዞረባቸዉን ኢትዮጵያዉያን አገር ቤት ሲመጡ “እንኳን ደህና መጣችሁ” ማለቱ የገደለዉን ወታደር ለማከም ከሞከረዉ የናዚ ጀርመን ወታደር ተለይቶ የሚታይ አይደለም። ቴዎድሮስ አድሀኖም እንደ ፈረስ ገርተዉ ለዚህ ባደረሱት በነመለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ ጭቅላት ሳይሆን በራሱ ጭንቅላት የሚያስብ ሰዉ ቢሆን ኖሮ የሱ የስራ ድርሻና ሀላፊነት ዜጎቻችን አገር ቤት ከገቡ በኋላ ሳይሆን ሳዑዲ ዉስጥ እያሉ ነበር።

ዛሬ ቴዎድሮስ አድሃኖምም ሆነ ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች ከሳዑዲ በሚመለሱት ወገኖቻችን ዙሪያ የሚያደርጉት ልታይ ልታይ የፎቶ እሽቅድምድም ወገኖቻችንን ለመርዳት ሳይሆን ዘረኛ መሪያቸዉ መለስ ዜናዊ ሲሞት ሳያስቡት በድንገት ከእጃቸዉ የወጣዉን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ መልሰዉ እጃቸዉ ለማስገባት ወይም በሚቀጥለዉ አመት በሚደረገዉና ወያኔ ከወያኔ ጋር በሚወዳደርበት ትርጉም የለሽ ምርጫ የፈረደበት ኃ/ማሪያም ደሳለኝን በቴዎድሮስ አድሃኖም ለመተካት ነዉ። አዎ! ለመተካት  . . . ለመተካካት። ወያኔ መተካካት እያለ አንዱን ጌኛ በሌላ ጌኛ በልቶ የጠገበዉን አህያ በተራበ አህያ መተካት ከጀመረ ዉሎ አድሯል። የአሁኑም ሩጫቸዉ ቢጭኑት አልሸከም ቢቀመጡበት አልመች ያላቸዉን ኃ/ማረሪያም ደሳለኝን የራሳችን ሰዉ ብለዉ በሚጠሩት በቴዎድሮስ አድሃኖም ለመተካት ነዉ (ኃይለማሪያምማ አሁንስ ቢሆን በቁሙ አልተተካም ብላችሁ ነዉ . . . ድፍን አበሻ ዉጭ አገርም አገር ዉስጥም ሲተራመስ ኃ/ማሪያም አንዲት ቃል አልተነፈሰምኮ)   ሳዑዲ ዉስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቻችን ፓስፖርታቸዉን ሲቀሙ፤ ሲደበደቡ፤ሲታሰሩና ሲገደሉ ቴዎድሮስ አድሀኖም የሰጠዉ ምላሽ ቢኖር  የኤምባሲዉንና የቆንስላ ጽ/ቤቶችን በር መዝጋት ነበር።  አዎ መዝጋት። ልክ ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ ከመለስ ዜናዊና ከአግዓዚ ነብሰ ገዳዮች የጥይት እሩምታ ለማምለጥ ወደ ቤተክህነት ጽ/ቤት ግቢ ሸሽተዉ ለመግባት በሞከሩ ወጣቶችና ህፃናት ላይ አባ ጳዉሎስ በሩን እንደዘጉባቸዉ ዛሬም የአባ ጳዉሎስ ታናሽ ወንድም የሆነዉ ቴዎድሮስ አድሃኖም በባዕድ አገር ዉስጥ አድነን ብለዉ በተጠጉት ወገኖቻችን ላይ የኤምባሲን በር ቀርቅሮባቸዋል።

ለመሆኑ ቴዎድሮስ አድሃኖም በየአመቱ ከ40ሺ በላይ ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በለጋ ዕድሜያቸዉ ከወላጆቻቸዉ ተለይተዉና ትምህርታቸዉን ትተዉ ስራ ፍለጋ ወደ አረቡ አለም የሚጎርፉት እሱ ሊነግረን እንደሚፈልገዉ  በአትራፊ ደላላዎች ተታልለዉ ወይም የአረብ አገር ኑሮ ጥሟቸዉ ሳይሆን ወያኔ በሚከተለዉ የዘረኝነት ፖሊሲና የተበላሸ የኤኮኖሚ ስርዐት የተነሳ መሆኑን ያዉቅ ይሆን? በተለይ ወጣት ሴቶቻችን በአረቡ አለም የሚደርስባቸዉን ዉርደትና መከራ እያወቁ በነጋ በጠባ አረብ አገር የሚሄዱት አገራቸዉ ዉስጥ ሰርተዉ መኖር ስላልቻሉ ከወያኔ ጋር ከመኖር አረብ አገር ሄዶ መሰንበት ይሻላል ብለዉ ነዉ አይናቸዉ እያየ የሞት ወጥመድ ዉስጥ የሚገቡት። ወያኔ በእጥፍ ድርብ አሳደግኩት የሚለዉ የአለማችን ፈጣኑ ታዳጊ ኤኮኖሚ ለእነዚህ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሮ ቢሆንና ዜጎች ስራ የሚያገኙት ችሎታቸዉ ብቻ እየታየ ቢሆን ኖሮ ይህ ዛሬ የምናየዉ ብሄራዊ ችግርና ዉርደት አይኖርም ነበር። ይሉኝታና እፍረት የሚባል ነገር አብሮት ያልተፈጠረዉ ቴዎድሮስ አድሃኖም የዜጎቻችንን ወደ አረብ አገር መጉረፍ በደላሎችም ሊያሳብብ ሞክሯል። አሱ ለሚከስሳቸዉ ደላሎች የስራና የንግድ ፈቃድ ሰጥቶ በዜጎች ንግድ እንዲከብሩ መንገዱን ያመቻቸዉና የከፈተዉ የራሱ የቴዎድሮስ ፓረቲ ነዉ፤ ብዙዎቹ አትራፊ ደላላዎችም የራሱ የቴዎድሮስ ጓደኞች ናቸዉ። የቴዎድሮስ አድሃኖም ጉድ ብዙ ነዉ፤ ተዘርዝሮ አያልቅም።

ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ሳዑዲ ዉስጥ ሲጋዙና ሲገደሉ ቁጥሩ ተገኗል እያለ በወገኖቻችን ላይ ያፌዝ የነበረዉ ቴዎድሮስ አድሃኖም ነበር፤ ኢትዮጵያዉያን ወገንና ረዳት አለን ብለዉ ወደ ኤምባሲዉ በብዛት ሲመጡ ኤምባሲዉና ቆስንላ ጽ/ቤቶች በራፍ ላይ “ዝግ ነዉ” የሚል ጽሁፍ ለጥፎ ወገኖቻችንን ለባዕዳን ጥቃት አሳልፎ የሰጠዉ ቴዎድሮስ አድሀኖም ነዉ፤የሳዑዲ መንግስት በአገሩ ዉስጥ ወንጀል ሲፈጸም ህጋዊ እርምጃ መዉስድ መብቱ ነዉ ብሎ የወገኖቻችንን መገደልና የሴቶች እህቶቻችንን መደፈር ህጋዊ ለማድረግ የሞከረዉም ቴዎድሮስ አድሃኖም ነዉ። የሚገርመዉ ይህ ወገኖቻችንን በባዕድ አገር “አይናችሁን ለአፈር” ብሎ በሩን የዘገባቸዉ ከሃዲ ሰዉ ነዉ ዛሬ የወገን አሳቢና ደራሽ መስሎ ቀልዱ እንዳማረለት የመድረክ ላይ ኮሜዲያን እዚህም እዚያም ሽርጉድ የሚለዉ። ሳዑዲ ዉስጥ በወገኖቻችን ላይ ለደረሰዉ ይህ ነዉ የማይባል ትልቅ በደልና ጥፋት የኢትዮጵያ ህዝብ በዋናነት ተጠያቂ ከሚያደርጋቸዉ የወያኔ ባለስልጣኖች ዉስጥ ቴዎድሮስ አድሃኖምና ተላላኪዉ ዲና ሙፍቲ የመጀመሪያዎቹ ናቸዉ።

ከሰሞኑ ፊቱን እያሳመረ በየደቂቃዉ ኢቲቪ ላይ መቅረብ የጀመረዉ ቴዎድሮስ አድሃኖም  “ሳዑዲ ዉስጥ ለደረሰዉ ጥፋት መንግስት ተመጣጣኝ እርምጃ ይወስዳል” እያለ ሲዘለብድ ተሰምቷል፤ የሱ ተላላኪ የሆነዉ ዲና ሙፍቲ ደግሞ “በዜጎች ላይ ምን ግዜም ድርድር የለም” ብሎ ሲናገር ተደምጧል። ይህንን በሁለት ባዶዎች የተነገረ ባዶ ንግግር ያዳመጠ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን “ጽድቁ ቀርቶበኝ በወጉ በኮነንከኝ” እያለ የቴዎድሮስንና የዲና ሙፍቲን “ጅብ ከሄደ ዉሻ ጮኸ” ንግግር ሰምቶ እንዳልሰማ አልፎታል። የሚገርመዉ ይህ ወገኖቻችንን በክፉ ቀን ወግዱ ብሎ ፊቱን ያዞረባቸዉ ቴዎድሮስ አድሀኖም ነዉ ዛሬ የሳዑዲ መንግስት በራሱ ወጪ አዲስ አበባ የሚልካቸዉን ዜጎች ዘመድ መስሎ ለመጠየቅ የሚሄደዉ። ደግሞኮ እስከዛሬ ድረስ አዲሰ አበባ ገብተዋል የሚባሉት በጣት የሚቆጠሩ ሰዎችም ቢሆኑ በተለመደዉ የወያኔ የዘመድ አሰራር እየተመረጡ የመጡ እንጂ ዜግነታቸዉ፤ ዕድሜያቸዉና የጤንነት ሁኔታቸዉ እየታየ የተመረጡ ሰዎች አይደሉም። ባጠቃላይ የተጣለበትን አገራዊ አደራና የተሰጠዉን ህዝባዊ ሀላፊነት መወጣት የተሳነዉን ቴዎድሮስ አድሀኖምን በየሜድያዉና በተገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ እያሽሞነሞኑ ለማቅረብ የሚደረገዉ ጥረት እንደ ህፃን ልጅ ሽንት መቀበያ የቆሸሸዉን የወያኔ ፊት በቆሻሻ ዉኃ ከማጠብ ተለይቶ የሚታይ አይደለም። ወያኔ ከአሳማ አሳማ እየመረጠ ለማሳመርና ለማሽቀርቀር የሚያደርገዉ ጥረት አሳማዉን ወደ ለመደዉ ወደ ጭቃዉ ዉስጥ ይበልጥ ይስበዋል እንጂ በፍጹም አያሳምረዉም፤ ምክንያቱም አሳማ አጌጥነዉ አላጌጥነዉ ምን ግዜም አሳማ ነዉ። የቴዎድሮስ አድሃኖም ነገርም እንደዚሁ ነዉ ፤ ወያኔ ያሻዉን ያክል ቢቀባዉና ቢያሳምረዉ ቴዎድሮስ አድሃኖም ወያኔነቱን አይለቅም! ወያኔ ደግሞ በልቶ የማይጠግብ ታጥቦ የማይነጻ አሳማ ነዉ።

ebini23@yahoo.com

posted by Tseday Getachew

መፍትሔው (አበራ ሽፈራው ከጀርመን)

አበራ ሽፈራው ከጀርመን

በተለይም ባለፉት 22 ዓመታት በሀገራችን ለተከናውኑት አበይት ችግሮች ሁላችንም እጆቻችንን ወደ ህወሓት እየቀሰርን ለችግሮቻችን መፍትሔ መስጠት አቅቶን ይባሱኑ ለከፍተኛ ስቃይና መከራ መዳረጋችንና፤ መፍትሔውን ከህወሓት እየጠበቅን ለችግራችን መባባስ አስተዋጽኦ በማድረጋችን ችግራችን እየተባባሰ ቀጥሏል። በምን መልኩ ነው አስተዋጽኦ አደረግነው?

በምን መልኩ አስተዋጽኦ አደረግን? ለምንል ደግሞ በተደጋጋሚ የህወሓትን ማንነት አይናችን እያየና እየተመለከት መስዋዕትነት ለመክፈል መወሰን ባለመቻላችንና የሀገራችንን እጣፋንታና የወደፊት እድላችንንም ጭምር በህወሓት እጅ አስቀምጠን አሁንም ለህወሓት ባርነት እራሳችንንና ሀገራችንን አሳልፈን መስጠታችን መቀጠሉ አስገራሚ ጉዳይ መሆኑና እኛም ለዚህ ውርደታችን መባባስ ለህወሓት ከፍተኛ እድል በመስጠታችንም ጭምር ነው።

ለችግራችን መፍትሔ ፈጣሪ ለመሆን እስካልቻልንና መፍትሔ የመፈለጉ ጉዳይ በራሱ በኢትዮጵያ ህዝብ እጅ እስካልገባ ድረስ አሁንም የህወሓት ጥቂት ጨቋኝ ቡድን የባርነት ቀንበር ተጭኖብን ለመኖር በመፍቀዳችን መፍትሔ አልባ ህዝቦች ሆነን ለመኖር መፍቀዳችንን ልንገነዘብ ይገባናል።

ባለፉት ዓመታት ህወሓት በሀገርቷና በህዝቧ ላይ መጠነ ሰፊ ግፍን ሲፈጽም ዝም ተብሎ ዛሬ እዚህ ደርሰናል። ሀገር እየተቆረሰ ለሌላ ሀገር ሲሰጥ፣ ህዝብ በጅምላ ሲገደል፣ ህዝብ እያፈናቀሉ ወደመጣህበት ዘር ሂድ ሲሉና የሰውን ልጅ ከደን ውድመት ጋር እያዛመዱ ሲሳለቁብን፣ በታጋይነት ሰበብ የአገሪቷን ጠቅላላ ወታደራዊ ሥልጣንን በቁጥጥር ውስጥ አስገብተው ጥቂቶች በህዝብ ሃብትና ንብረት ሲሳለቁ ፣ ጠቅላላውን የአገሪቷን የንግድ እንቅስቃሴ በመቆጣጠር የራሳቸውን የፓርቲ ንግድ ሲያስፋፉና ሌላውን የንግድ እንቅስቃሴ ሲያቀጭጩ እየተመለከትን፣ የአገሪቷ ህዝቦች በስደትና በመከራ ላይ ሆነው እነሱ የአገሪቷን መሬትች በመኖሪያ ቤት፣ በንግድ ቦታና በእርሻ ቦታነት እየተከፋፈሉ የራሳቸውን መስፋፋት ሲያጠናክሩ እየተመለከትን፣ በተለይም ላለፉት 22 ዓመታት የአገሪቷን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ያሉትን ጠቅልለው ይዘው የንግድና የራሳቸው የኑሮና የመስፋፋት ዓላማን ለማስፈጸም ከፍተኛ እድልን ፈጠረው ሲቀልዱብን አይናችን እያየ እየተመለከትን ለመሆኑ እኛ ማን ነን? ምንስ እንጠብቃለን?

ስለሆነም ህወሓት አሁን ካለበት ሁኔታ አንጻር በምን አይነት ሁኔታ እንዳለና ምን መፍትሔ መፍጠር እንደሚቻል ትንሽ ነገር ልበል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ህወሓት/ ኢህአዴግ አሁን ያለበት ሁኔታ በእኔ እይታ

ህወሓት ለአለፉት 22 ዓመታት ህዝቡን ሲረግጥ፣ ሲጨቁንና ሲከፋፍል የኖረ ከመሆኑ አንጻርና በህዝቡ ላይ ከመቼውም ጊዜያት ባልታየ ሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብን ለመከራ፣ለረሃብ፣ ለስደትና ለብዝበዛ ከበዳረጉም በላይ ጥቂቶች ባልተጠበቀ ሁኔታ በሃብት ጣራ የነኩበት ሀገር ከመሆኗ አንጻርና ከሌሎችም ተያያዝ ጉዳዮች ጋር ሲታይ ህወሓት ኢትዮጵያን ለመምራት ሃላፊነት በህዝቡ ሊሰጠው የማይችል መሆኑን ህዝቡና እራሱ ህወሓትና ባለሟሎቹ ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ ይሁንና በጉልበትና በአንባገነነነት፣ እንዲሁም ህዝብን በማሸበር የመንግስትን ስልጣን ተቆጣጥረው ለመቀጠል ቆርጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን እየደረሰበት ካለበት መከራ አኳያ ሲታይ ህወሓት ሁኔታዎች እንደከዚህ በፊቱ ሁሉም አልጋ ባልጋ ይሆኑለታል ማለት ግን አይደለም። ምክንያቱም ህወሓት እኩይ የሆነው ተግባሩ ሰፊ ጠላትን አፍርቶለታልና ነው። ስለሆነም ህወሓትን ከዚህ አንጻር ልንገመግመው እንችላለን።

1. ህወሓት በራሱ በህወሓት ውስጥ ሲታይ

በነገራችን ላይ ህወሓት ህዝባዊ መሰረት እንዳለው የሚነገረው ትክክለኛ አለመሆኑን የተለያዩ ማስረጃዎች ማሳየት ይቻላል። ህወሓት በመሰሪነትና በገዳይነት የሚታውቅ ድርጅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በትግራይ ውስጥም ሆነ በራሱ በታጋዮች መካከልም ለዓመታት ታጋዮችን ጭምር በመግደል፣ በማሰቃየት፣ በማሰር፣ በማጥፋት እና መሰል የሽብር ተግባርን በመፍጠር ፍርሃትን በማንገሱ ፣እንዲፈራ በማድረግ በፍርሃት የተፈጠረ ድጋፍ እንጅ ሰው አምኖበት የደገፈው ድርጅት አልነበረም አሁንም አይደለምም። ህወሓት አሁንም በትግራይ ህዝብም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ እየፈጠረ ያለው አንባገነናዊ ሥርዓት በህዝቡ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ህዝብን በመንግስታዊ ሽብርተነት በማስገደድ እንዲሰገድለት ማድረግ ትልቁ አላማ አድርጎ ያለ ድርጅት እንጂ በፍጹም በዲሞክራሲያዊ ግባቶች እንደማያምን የራሱ የፓርቲው አፈጣጠርና አመጣጥ በግልጽ ያሳየናል።

እነዚህ ሁኔታዎች ህወሓት በራሱ ፓርቲ ውስጥ ሰፊ የሆነን ጥላቻን ይዞና፤ ቂም በቀልን የያዞ መሆኑና ብዙዎቹ ሁኔታዎችንና ጊዜዎች እየተጠባበቁ ያሉ መሆናቸውንም ጭምር ሊገባን ይገባል። በተወሰነ አጋጣሚ ሁኔታዎች ቢለወጡ ብዙዎቹ ለመበቃቀል የሚፈላለጉ መሆናቸውን በግልጽ እናያለን፤ ከዚህም በላይ አሁንም ቢሆን በመሃከላቸው ትልልቅ ልዩነቶች ያሉባቸው ከመሆናቸው አንጻር ለአደጋ የተጋለጡም መሆናቸውንም በቀላሉ መረዳት እንችላለን።

2. ህወሓት በኢህአዴግ ውስጥ ካለው ቦታ አንጻር ሲታይ

  • ህወሓት ሌሎችን የኢህአዴግን ፓርቲዎች በማስፈራራትና የሚፈልገውን እየሾመባቸው ለመኖር የሚሻ መሆኑ
  • ሁሌም የበላይነትን ይዞ ለመቆየት ሲል ሌሎችን በማሰር፣ በመግደል፣ በማስፈራራትና የመብትና የዲሞክራሲያዊ መብት ጥያቄዎችን እንዳያነሱ በማድረግ ጥቂቶች በበላይነት እንዲቀጥሉ በማድረግ
  • ዋና ዋና የአገሪቷን ሥልጣኖች በሙሉ በራሱ ቁጥጥር ውስጥ ከማስገባቱ ጋር ተያይዞ በሌሎች ፓርቲዎች ውስጥ ተቀባይነቱ እየተሸረሸረ መሆኑና፤ በተለይም ከ1997 ምርጫ በኋላ አይን ያወጣ አንባገነንነቱን ይዞ መቀጠሉ ችግሩን በይበልጥ እየጎላ መምጣቱና በፓርቲዎቹ መካከል አለመተማመን እየተፈጠረ መምጣቱ
  • ጥቂቶች በመቀያየር እየተሽከረከሩ የሚያስተዳድሩት መሆኑና ለዘለቄታ የሚሆን መሰረት የሌለው መሆኑ
  • በራሱ አባላት ጭምር የተጠላ አንባገነን ፓርቲ መሆኑ

3. ህወሓት በኢትዮጵያ ህዝብ አንጻር

  • ጥቂቶች ይባስም ብለው በቤተሰብ ደረጃ የተሰባሰቡበት ቡድን መሆኑ መታወቁ
  • ኢትዮጵያን የማይወክል ቡድን መሆኑ መታወቁ
  • ጥቂቶች እስከ እድሜ ልካቸው ድረስ በዚህ ቡድን ውስጥ ተሸሽገው የኢትዮጵያ ህዝብ ደም እስከ ጡረታቸው ድረስ የሚፈልጉትን ለማደረግ እንዲችሉ የተዋቀረ የማፍያ ቡድን መሆኑ መታወቁ
  • ወታደራዊ ሃይሉን የሚያስተዳድሩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክሉ ሳይሆኑ ጥቂቶች አንድን አካባቢ ብቻ የሚወክሉ ተሰባስበው አገሪቷንና ህዝቧን እያስፈራሩ ለመኖር የተዋቀሩ የማፍያ ቡድን አባላት መሆናቸው መታወቁ
  • በሙስና የተጨማለቁ መሆናቸው ህዝቡ ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑ
  • ለህይማኖት ነጻነት ክብር የማይሰጥ መሆኑና የነጻነት አምልኮ መገደቡ መታወቁ
  • በአጠቃላይ በየትኛውም መለኪያ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ የተጠላ ቡድን መሆኑ

4. ህወሓት በመከላከያ፣ በፖሊስና በልዩ ልዩ ወታደራዊና የደህንነት መስሪያ ቤት ሲታይ

  • ኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊቷና ሌሎች ወታደራዊ አደረጃጀቶቿ እጅግ በሚገርም መልኩ የአገሪቷ ሳይሆኑ የጥቂት ይልቁንም የአንድ አካባቢ ሰዎች ተሰባስበው የሚያስተዳድሩት መስሪያ ቤት ከመሆኑም በላይ በየትኛውም የአገሪቷ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አገሪቷ ለትልቅ የብዝበዛ መዋቅርነት እንዲያገለግል ተደርጎ የተደራጀ መሆኑ፤ ይህ ተቋም የአገሪቷ ተቋም ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ ለወደፊቱም ቢሆን ለአገሪቷም ሆነ ለህዝቦቿ ነጻነት ትልቅ አደጋ መሆኑ
  • ብዙዎች የመከላከያ ሰራዊት አባላትም የአገሪቷ የመከላከያ አወቃቀር መስተካከል እንዳለበት በመጠየቅ ላይ መሆናቸው
  • ወታደሩ ለኢትዮጵያ ከማገልገል ይልቅ የእነዚህን ጥቂት ዘረኞች የብዝበዛ መዋቅር እያስጠበቁ መሆናቸውን እያወቁ መምጣታቸው።
  • በአጠቃላይ ወታደሩ በልዩ ልዩ ጭቆና ውስጥ ያለ መሆኑና ጥቂት ነገር የሚፈልግ መሆኑ

ከላይ እንደተመለከትነው ህወሓት በአጠቃላይ ባለፉት ዓመታት ህዝቡን ባስመረረ መልኩ መጠነ ሰፊ ግፍን በህዝቡ ላይ ፈጽሟል ከዚህ በላይ ምን እስከምንሆን እንደምንጠብቅ አላውቅምም ወይም አልገባኝም። አንድ ነገር ግን ይገባኛል፤ እሱም እያንዳንዳችን ለራሳችን፣ ለህዝባችንና፤ ለሀገራችን የሚጠቅመውን ባለማድረግ፣ በመፍራት፣ እራስን በመውደድ፣ ለግል ጥቅም በመራራጥ፣ በግድየለሽነት፣ ነግበዕኔ ባለማለት፣ ህወሓት ለአቀረበልን ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞች እየተገዛን በመንበርከካችንና በጋራ ባለመታገላችን፣ ከጋራ ጠላታችን ከህወሓት ይልቅ ሌሎች ተቃዋሚዎችን ለመተቸት በመሽቀዳደማችንና በሌሎችም ምክንያቶች አሁን እየደረሰብን ላሉ ሀገራዊ ውርደቶች እንድንዳረግ ሆነናል። እነዚህን ነገሮች ለመቀየር እንችል ዘንድ ቆም ብለን ማሰብ መቻል ያለብን ጊዜ ግን አሁን መሆኑ ግልጽ እየሆነ መጥቶልናልና እስኪ እናስብ።

ህወሓት አሁን ለምናየው እኩይ ተግባሩ ታግሎ መጥቶ በምስጊን ህዝብ ደም በነጻነትና በእኩልነት ሰበብ ይህንን ተግባሩን ሲፈጽም እንዴት እኛ ለእውነተኛው እኩልነት መነሳትና የራሳችንን መብት ለማስጠበቅ እንዴት ያቅተናል? ለዚህስ መስዋዕት ለመሆን ለምን ተቸገርን? ማን መስዋዕት እንዲሆን እንጠብቃለን? ግንቦት ሰባት ታግሎ ነጻ እዲያወጣን፣ አርበኞች ነጻ እንዲያወጣን፣ ኦነግ ነጻ እንዲያወጣን ወይስ ሌሎች ነጻ እንዲያወጡን እንደኔ ድርጅት ነጻ አያወጣንም። መጀመሪያ እራሳችን በግል እራስን ነጻ ለማውጣት መቁረጣችንን ማረጋገጥ አለብን። ከዚያ በኋላ ነው ድርጅቶችን መፈለግ ያለብን፣ከዚያ በኋላ ነው በመረጥነው የትግል መንገድ ከጠላታችን ጋር መፋለም የምንችለው፣ በመጀመሪያ ነጻነት ያስፈልገናል ወይስ አያስፈልገንም የሚለው ጉዳይ ሊያግባባን ይገባል፤ ከዚያም ነጻነትን እንዴት እናገኛለን ካልን የመጀመርያው መልስ ድርጅትን መምረጥ ሳይሆን ለመታገልና መስዋዕትነት ለመክፈል መነሳትና መቁረጥ ያስፈልጋል፤ ከዚያም ከቆረጡ ታጋዮች ጋር መደራጀት ይጠብቅብናል። መስዋዕትነት ለመክፈል መቁረጥ ይኖርብናል ሲባል ግን መስዋዕትነት የህይወት መሰዋዕትነት ብቻ አይደለም የጊዜ፣ የገንዘብ፣የእውቀት ማካፈል፣ የመረጃ መስጠት፣ ሌሎችም እንዳሉ ማመንና በአንደኛው ወይም በሌላኛው የትግል መስክ ተሰማርቶና የትግሉ አካል በመሆን ወደትግሉ በመቀላቀል የጋራ ጠላታችንን ዓላማ መቀልበስ ጊዜ የሚሰጠው አይደለምና እሁን እናስብበት! ግዜው አሁን ነው! ያለንም መፍትሔም ይኸው ብቻ ነው።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

ሀገራዊ ውርደት ይብቃን!

አበራ ሽፈራው ከጀርመን
aberay12@googlemail.com  

 posted by Tseday Getachew

በአ.አ የታላቁ ሩጫ ተሳታፊዎች የሳዑዲን እና የኢትዮጵያን መንግስት ሲቃወሙ (Video)

ከቀናት በፊት ዘ-ሐበሻ በአዲስ አበባ ታላቁ ሩጫ ውድድር ላይ ሕዝቡ ተቃውሞውን ማሰማቱን መዘገባችን ይታወሳል። “ታላቁ ሩጫ የብሶት መግለጫ” እያሉ ነበር የዘመሩት የታላቁ ሩጫ ተሳታፊዎች። የኢትዮጵያ ቲቪን ካሜራ ማን ሲያዩ ደግሞ “Shame on u.. Shame on u” ሲሉ ነበር። “ታላቁ ሩጫ… ታላቁ ሩጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሶት መግለጫ..” ሲሉ ባለፈው እሁድ በአዲስ አበባ በተደረገው የታላቁ ሩጫ ተሳታፊዎች ድምጻቸውን ሲያሰሙ ነበር።

posted by Tseday Getachew

ከሳኡዲአረቢያ በተመለሱ ዜጎች ላይ የሚፈፀመው በደል አገር ዉስጥም እንደቀጠለ መሆኑን የኢህአዴግ አባላት አጋለጹ

ከተመላሾቹ መካከል የአክራሪ የኦነግና የግንቦት 7 አባላቶች ስላሉ መዝግባችሁ በአይነ ቁራኛ ተከታተሉዋቸው’’

                                                 የመንግስት አመራር አካላት

ዋሽንግተን ዲሲ፤ ህዳር 19/2006 (ቢቢኤንሳኡዲ አረቢያ ህጋዊ የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውን ዜጎች ማስወጣትዋን ተክትሎ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውን ከእንግልትና ከስቃይ በሗላ ወደ ገራቸው ገብተዋል በማለት የኢትዮጵያ መንግስት ቢገልጽም ተመላሾቹ በገዛ አገራቸዉ ይሸማቀቁ ዘንድ በመንግስት ዘመቻ እንደተከፈተባቸዉም ለማወቅ ተችሏል።

በአማራ ክልል በኦሮሚያ ዞን ያሉ የመንግስት የአመራር አካላት ከተለያዩ ቀበሌዎች ለመጡ ካድሬዎች በሰጡት መመሪያ ከሳኡዲ አረቢያ የሚመጡ ዜጎችን በመመዝገብ ጥብቅ ክትትል እንዲደረግባቸዉና በአይነ-ቁራኛ እንዲመለከቷቸዉ ትዕዛዝ መተላለፉ ታዉቋል፡፡ከታማኝ የመንግስት ምንጮች ለማረጋገጥ እንደተቻለዉ ከተመላሶቹ መካካል የኦነግ የግንቦት 7 እና የአክራሪነት ዝንባሌ ያላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ወደ ትዉልድ ቀዬአችዉ ይመለሳሉ በሚል ስጋት ነዉ-ክትትል እንዲደረግባቸዉ የታዘዘዉ።

መንግስት ባንድ በኩል ዜጎቹን ለማስመለስና በአገራቸው እንዲቋቋሙ ከፍተኛ ጥረት እያደረኩ ነው እያለ

ወደ አገራቸው በመመለስ ላይ ያሉ ዜጎች ተጠቃለዉ እንኳ ሳይገቡ ይህን መሰሉን ትእዛዝ በአመራር አካላት እንዲተላለፍ ማድረጉ መንግስት ለስልጣኑንጅ ለህዝቡ ደንታ እንደሌለው ያሳያል ሲሉ የገለጹም አሉ፡፡

በሰው አገር እንግልትና መከራ የደረሰባቸው ዜጎች ከደረሰባቸው የስነ-ልቦና ቀውስ ሳያገግሙ፣ቁስላቸው ሳይሽር እና የቤተሰብ ናፍቆትን ሳይወጡ ባይነ ቁራኛ ተከታተሉዋቸው አክራሪ ናቸው፣የኦነግ-ግንቦት 7 አባላት ናቸው በማለት መጠነ ሰፊ ዘመቻ ለመክፈትና ለማሸማቀቅ ከሚያደርገዉ የፕሮፓጋንዳ ስራ መንግስት ሊታቀብ ይገባል ሲሉ ቅሬታቸዉንም የሚያሰሙ ወገኖች አሉ።

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከሳኡዲ የሚገቡ ዜጎችን በአክብሮት ተቀበልን ዜጎቻችንን መልሶ ለማቋቋም ጥረታችን እንደቀጠለ ነዉ በማለት እጃቸዉን ለሳኡዲ ፖሊስ ያልሰጡ ኢትዮጵያዉያንን ወደ አገር እንዲመጡ መገፋፋታቸዉ መሬት ላይ ካለዉ ሁናቴ ጋር አለመመሳሰሉ አጠያያቂ ነዉ የሚሉም አሉ። ሚኒስቴሩ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም እራሳቸዉን በመላዉ አለም ከሚገኘዉ ኢትዮጵያዊ ጋር በፌስቡክና በትዊተር በማስተዋወቅና ገጽታቸዉን በማሳመር በቀጣዩ ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስቴር የመሆን ህልማቸዉን ለማሳካት የምርጫ ቅስቀሳ (campaign) የጀመሩ ይመስላል በማለት አንዳንድ ተንታኞች ይገልጻሉ።

በሙስና የተራቆተ አመራርን የያዘዉ ኢህአዴግ፤ የዜጎች ሁለንተናዊ መብት ነፍጎ፣የ አገሪቱን ኢኮኖሚ አራቁቶ፣የፖለቲካ ተቀናቃኞችን አመናምኖ፣ በመቶሺዎች የሚቆጥሩ ዜጎችን ከአገር እንዲሰዱ አርጎ፣ኢትዮጵያዉያን በገዛ አገራቸዉ እንዲፈናቀሉ ሆኖ፣መሬት ለዉጪ ኢንቬስተሮች እየተሸጠ፤ ስርዓቱ ከህዝባዊ እንቢተኝነትና አመጽ ድኖ እንደተለምደዉ ተሸንፎ የሚያሸንፍበት ምርጫ ይከሰታል የሚለዉ በሒደት የሚታይ ቢሆንም፤ ከሳኡዲ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ጉዳተኞች ግንቦት7 ፣ኦነግ ወይም  አክራሪ ሊሆኑ ይችላሉ በሚል ግምት እንደየ-ዘራቸዉና እንደየ-ሐይማኖታቸዉ ክትትል እንዲደረግባቸዉ መደረጉን በሁናቴዉ ደስተኛ ያልሆኑ የኢህአዴግ አባልት ለቢቢኤን ገልጸዋል።

http://www.zehabesha.com/

posted by Tseday Getachew

 

 

የወያኔ በዲሞክራሲ ቁማር እስከመቼ? -በአሸናፊ ንጋቱ

በአሸናፊ ንጋቱ

በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ መንግስት የዛሬ 22 ዓመት አንግቦት የነበረውን የዲሞክራሲ መፈክር በማየት ዲሞክራሲ የጠማው የኢትዮጵያ ህዝብ የደስታ ጮቤ በመርገጥ ነበር የተቀበለው፡፡ ነገር ግን ይህ መፈክር ድራማ መሆኑ እየዋል እያደረ ነበር እየተጋለጠ የመጣው። ጮቤ እየረገጠ፤ ትግሉን ተቀላቅሎ መስዋት የከፈለውን ህዝብ የቁልቁል ወደ ባሰ የመከራ ማጥ ከቶታል።
ወያኔ እራሱ ህግ አውጥቶ እራሱ የማፍረስና በህጉ ያለመገዛት አባዜ የተጠናዎተው አንባገነን ስርአት መሆኑ በሃያ ሁለት አመታት የስልጣን ጉዞው አስመስክሯል፡፡ በትክክል እንደ ህገ-መንግስቱ ቢሆን ኖሮ ህገ-መንግስት የህጎች ሁለ የበላይ ህግ ነው፡፡ነግር ግን ወያኔ ያለምንም ከልካይ እንዳሻው ያለ ህዝብ ተሳትፎ ለስልጣናቸው እርዝማኔ ይመች ዘንድ ሲዘርዙትና ሲደልዙት ይስተዋላል፡፡ ሲፈልግ ስልጣን መብት ሲሰጥህ/ሽ ሳይፈልግ ደግሞ ሲከለክልህ/ሽ በስመ ዲሞክራሲ እየነገደ የሚኖር የማፍያ ስርአት ነው፡፡ የአምባገነን መንግስታት መለዬ በሆነው ሃይልን እየተጠቀመ በመግደል፤ በእስር፣ በመሳርያ እና በዱላ እያስጨነቀ የህዝቡን ስነ ልቦና በማድከም የስልጣን ቆይታውን ማርዘምም የስርአቱ ዋና አላማ፡፡ እንዲህ አይነቱ አምባገነንና በዲሞክራሲ ስም ህዝባችን ላይ ቁማር የሚጫዎት ስርአት ለኢትዮጵያውያችን አያስፈልግም፡፡ ስለዚህ ይህንን በጨካኝኔ የተሞላ ስርአት ከሃገራችንና ከህዝባችን ጫንቃ የምናስወግድበት ሰአት አሁንና አሁን ብቻ ነው።

በዲሞክራሲ ቸነፈር መመታታችን ሳያንሰን አገር አልባ ለመሆን በተቃረብንበት እና ማንነታችን ጥያቄ ውስጥ በገባበት በዚህ ጊዜ ዲሞክራሲን መናፈቃችን ብቻ ተፈጥሮአዊ አያደርገንም፡፡ በተፈጥሮ ያገኘነውን ነፃነት በተግባር ስናስጠብቅ ብቻ ነው፡፡ ይህ ሁሌ ፍዳና መከራ የሆነው በሃገራችን ላይ በጣም ገኖ ከእኔ በላይ ላሳር በማለት በሃይል በጉልበት በስልጣን ላይ በተቀመጠው የወያኔ ስርአት ነው፡፡ የወያኔ ስርአት ስልጣን ከያዘ ቀን ቀንን እየተካ፤ ሳምንት ሳምንታትን እየተካ፤ ወር ወራትን እየተካ፤ አመት አመታትን እየተካ ይኸው እነሆ 22 አመታችንን አስቆጠርን፡፡ በዚህ 22 ዓመት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ለዲሞክራሲ፤ ፍትና ነፃነት የዘመሩ ዜጎች አልቀዋል፤ ለስደትም ተዳርገው የድራማው ሰለባ ሆነዋል፡፡ አሁንም ዝም ካልነው ሌላ ብዙ አስርት የመከራ አመታትን መጋፈጥ ሊኖርብን ነው፡፡ እስከመቼ ዝም እንደ ምንለው ግን ወገን አይገባኝም፡፡ አሁንም ህፃን፤ ወጣት፤ ጐለምሳና አዛውንት ወገኖቻችን ሲረግፍ፤ ሲሰደዱ ማየት ከሆነ ህልማችን መልካም! ግን ይህንን የሚያልምም ሆነ የሚመኝ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም፤ ከራሳቸው ከወያኔ ሆዳደር ካድሬዎች በስተቀር፡፡ ስለዚህ ወገኔ ሆይ ይህንን መንግስት ዝም ብለን ልናየው አይገባም፡፡ ወይም እንደ ፈለገ ሊፈነጭብን ቦታ መስጠት የለብንም፡፡ እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሰው ጭቆናና በደል ይበቃል ልንለው የግድ ነው፡፡

በዲሞክራሲ እጦት ሃገራችንን ማስጨነቁ አልበቃው ያለው ይህ ክፉ ስርአት በአሁኑ ጊዜ የህዝባችንን ኑሮ ከድጡ ወደ ማጡ አድርጎት ይገኛል፡፡ ህዝባችን በኑሮ ውጣ ውረድ ህይወቱ ሰላም አጥቷል። ወያኔ ስርአቱን የሚቃወሙትን ብሎም የዲሞክራሲ ጥያቄን ያነሱ ንፁሃን ዜጐችን መግደል፤ ማሰርና ማሰቃየት መለዬው ነው። ወያኔ ይህን ስትራቴጂ የሚጠቀመው ለሃገራቸው መልካም የሚመኙትን እና ለሃገር ይሰራሉ ተብለው የሚገመቱትን ሃገር ወዳድ ዜጐች ማጥፋት ከመፈለጉ የተነሳ ነው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ሁሌም ለሃገራቸው ደህንነት ለህዝባቸው ኑሮ የሚጨነቁ ስለሆኑ ስርአቱን የመደገፍ ፍላጎት ስለማይኖራቸውና እየፈፀመ ያለውን አረመኔ ተግባር ለህዝብ ሊያጋልጡብኝ ይችላሉ ብሎ ስለሚፈራም ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ሁኔታ የሚቀጠለው እንዴት ነው? ውድ ኢትጵያውያን በአሁኑ ጊዜ ህዝባችን ስቃይ ላይ ነው፡፡ ልንደርስለትና ከህዝባችን ጐን ተሰልፈን ነፃነታችን ማፋጠን ይገባናል፡፡

በስተመጨረሻም መጠየቅ የምፈልገው በዲሞክራሲ እየነገደ ያለው ይህ የወያኔ ስርአት በሃገራችን ገነባሁት፤ እያበበም ነው የሚለው የዲሞክራሲ ስርአት የቱ ይሆን?

በየትኛው ዲሞክራሲ፡ ነፃነትና ፍትህ ያለበት ሃገር ላይ ነው አንድ መንግስት ለ22 አመታት ሲገዛ ያየነው? ዲሞክራሲ፡ ነፃነት እና ፍትህ አሰፍናለሁ ብሎ ቃል የገባላትን እናት ሃገር ዛሬ ግን ድንበሯን በመሸራረፍ እየሸጧት፣ እየለወጧት ብሎም ህዝባችንን በኑሮ እሳት ረመጥ እያቃጠሉት፤ ነፃነቱ ቀርቶ የሃገራችንን ህዝቧን እየከፋፈሉ የብሄር ብሄረሰብ መብትን አስከብራለሁ እያሉ እርስ በእርስ ህዝቡን ማጋጨትና ማጨፋጨፉ ይሆን የሃገራችን ዲሞክራሲ መገለጫው?

ነው ወይስ ዲሞክራሲ ለወያኔ ህዝቡን መከፋፈል፣ እንደልብ እንዳይናገር ማፈን፣ መሬትን ያለባለቤቱ ፈቃድ እየነጠቁ መሸጥ፣ ሙስናን ተዋጋሁ እያሉ በሙስና ተጨማልቆ መገኘት፡፡ ይሄ ነው የወያኔ ዲሞክራሲና እና ፍትህ? የቆሰለችውን ኢትዮጵያ አድንሻለሁ ብሎ ለባሰ ህመም መዳረግስ ለምን!? እውነት ግን በተቃራኒው በቁስሉ ላይ እየሸነቆሩ ማድማት ነበር እንዴ አላማቸው? የተራባችሁትን ሰላም እና ዲሞክራሲ እሰጣችኋለሁ ብሎ ቃል የገቡለትን ህዝብ እልል ብሎ ሲቀበል፣ በታሪኩ አይቶት የማያውቀው የመከራ ጦስ መክተት ነበር እንዴ የወያኔ አላማ!? ስራቸውና ተንኮላቸው የገባው/ት ለምን ብሎ ሲጠይቅ/ ስትጠይቅ ወደ ወህኒ እና ወደ ሞት መጣል መሆን አለበት እንዴ የዚያ የምስኪን ህዝብ ለሰራው ውለታ መልሱ? ታዲያ የወያኔ ዲሞክራሲያዊ ግዛት ይኼ ነው?

ዛሬ ህዝባችን የተወለደበትን ምድርና ቀየ በሃይል በማስለቀቅ መሬቱን በኢንቨስትመንት ስም እየተሸነሸነ እየተሸጠ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ታዲያ ይሄ ጭቁን ህዝብ ምድሩን ለቆ ወዴት ይሂድ የትስ ይድረስ? ነው ወይስ ስርአቱ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ነው ቆርጦ የተነሳው? ወገኔ ሆይ ሃገር አለን ብለን የምንኮራው መቼ ይሆን? እስኪ መልሱልኝ፤ የቀን ከሌት ጥያቄየና በራሴ መልስም ለማግኘት ባለመቻሌ አንድ ብትሉኝና ለአምሮየና ለመንፈሰይ ሰላምን ባገኝ ነው ለዘመናት የሚመላለስብኝን ጥያቄዎች መሰንዘሬ፡፡ በእኔ በኩል ይህንን አፋኝና አምባገነን ስርአት ያለምንም ልዩነት በአንድ ልብ በቃ ልንለውና፤ በቁርጠኝነት ልንታገለው ይገባል ባይ ነኝ።

ድል ለጭቁኑ ኢትዮጵያ ህዝብ!!!

በአሸናፊ ንጋቱ

ለአስተያየትዎ: andethiopia16@gmail.com የኢሜል አድራሻየ ነው።

posted by Tseday Getachew

 

 

ዶክተር ቴወድሮስ አድህኖም በእውነት አዝነው ወይስ መስታወቂያ እየሰሩ !!

Gebregziabher Lema /Kitzingen/

የኢትዮጽያ ህዝብ  የሞተበት፤ ያዘነበት፤ ፍትህ ያጣበት ፤የተራበበትና የተሰደደበት ግዜአቶች ቢኖሩም   አሁን ግን እራሳቸው ከሚያደርሱብን ግፍና በደል  በተጨማሪ በባእዳን ሀገራት    ተደፍሮና ተነክቶ የማያውቀው ህዝብ   አሁን ባለው  ስርአት  ታሪካችንንና መንነታችንን  ለመጥፋት መጠነ ሰፊ ዘመቻ እየተካካሄደብን ነው። ይህ የማንነታችን መደፈር ዛሬ በገሀድ ወጥቶ ሁላችንም እንስማው እንጅ  ቀደም ሲል ከእኛ በታች በነበሩ የጎረቤት ሀገራት በነጂቡቲ ፤ሱዳን ና ኬንያ ተዋርደንና ተጠቅተን  እንድንኖር ከተደረገ  ውሎ አድሮአል  ። ዛሬ በኢትዮጽያ ህዝብ ጀርባ  ህልውናዋ የቆመው በጂቡቲ እንኮ ኢተዮጺያዊነት ተወርዶ  በነሱ ስንገደል ፤ስንታሰር፤ ሴት እህቶቻችን የነሱ መጫወቻ ሲሆኑ፤ ሹፌር ወንድሞቻችን በራሳቸው ላይ በደል ተፈጽሞባቸው እራሳቸው ተቀጭ ፤በንብረቶቻቸው ላይ አደጋ ተፈጽሞባቸው እራሳቸው ከፋይ ፤ግመሎቻቸውና ፍየሎቻቸው ላይ አደጋ ቢደርስ  ገና ውደፊት እሰከምትወልደው የልጅ ልጅ እዲከፍሉ በማድረግ  ለሚደረገው ህገወጥ ስራወች ሁሉ ለወያኔ አቤት ያልተባለበት ግዜ የለም  የገንዘብ ኪሳቸውን  ለመሙላት ሲሉ ህዝብን  ለባርነት ዳርገውት ይገኛሉ።

ታዲያ ዛሬ ቴወድሮስ አድህኖም ያዞ እንባውን ከየት አመጡት  ምን አልበት በሳውዲ መንግስት ከወገኖቻችን  አላግባብ የፈሰሰው ደም ፤  በቃየል ላይ እንደ መሰከረበት የአቤል ደም ሆኖባቸው ይሆን ? ወይስ  ለሚቀጥለው  ምርጫ  የቢል ቦርድ  ማስታወቂያ  ፎቶ  እያዘጋጁ ? አዎ ይህ ነው እንጂ ካልሆነማ  በስደት  በመንገድ ላይ በየኮንተቴይነሩ ለሚያልቁት ፤በሱዳን፤በጂቡቲ፤በየምን ና ኬንያ በባርነት ያሉ ወገኖች ፤ በሀገራቸው በክልላችሁ ሂዱ ተብለው   ሀብት ንብረት ካፈሩበትና ወልደው ከዳሩበት አያት ቅድምአያቶቻቸው  ለነጻነት አጥትና ደማቸውን ከገበሩበት ሀገርና ቀየ ያንተ አይደለም ተብሎ ሲፈናቀሉ ሌሎች ዘመዶቻቸው እንደጀብድ ሲያወሩት እንደነበር አያውቁም ? ስለዚህ ይህ የውሸት እንባ የኛን አንጀት ያጠነክራል እንጂ የሚያለሰልሰው ፈጽሞ አይሆንም።

http://www.zehabesha.com/

posted by Tseday Getachew

[የሳዑዲው ጉዳይ] ተዋርደን አንቀርም – ከኢንጂነር ይልቃል ጌትነት

ከኢንጂነር ይልቃል ጌትነት

ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡

ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡

አቶ ሽመልስ ከማል ለሚዲያወች የሰጡትን ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላና ሰበብ አዳምጨዋለው፡፡ “ሰላማዊ ሰልፉን ያገድንበት ምክንያት ጸረ-አረብ መፈክሮች ስለነበሩ ነው“ብለዋል፡፡መጀመሪያ ደረጃ ሰልፉ ገና ከግቢው ፈቅ ሳይል ነው ያፈኑት፣ሆኖም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አንድ በአንድ እየሆንን ወደ ሰላማዊ ሰልፉ መዳረሻ ለመሄድ ስንሞክር የተወሰኑ አመራሮችን አራት ኪሎ አካባቢ ያዙን፣እነሱ ቀድሞውኑ ሰልፉ እንዳይካሄድ ስለወሰኑ ነው እንጅ ትንሽ እንኳ ተንቀሳቅሶ የሰልፉን ባህሪ ለመገምገም ምንም እድል አልሰጡንም፡፡

ለምሳሌ ሰልፉን እንደምናደርግ ይፋ ባደረግን ማግስት ከራዲዮ ፋና ተደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎች ተጠይቄ ነበር፡፡በቃለ-መጠይቁ ሰላማው ሰልፉ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም እንደምናደርግ ተናግረናል፡፡ጋዜጠኛው ለሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች መልዕክት ካለ ብሎ በጠየቀኝ ወቅት የሳውዲ አረቢያ ሰንደቅ አላማ ላይ ያለው ምልክትና ጽሁፍ ሀይማኖትን የሚመለከት በመሆኑ ዜጎች በስሜታዊነት ባንዲራ እንዳያቃጥሉ፣እነሱ ቢያዋርዱንም እኛ ግን ክብር ያለን ዜጎች ስለሆንን ተቃውሟችንን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ማካሄድ እንዳለብን ተናግሬ ነበር፡፡ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት በዚህና በተለያየ መንገድ በማያሻማ ሁኔታ መልዕክት ባስተላልፍም እነሱ ግን ይህን በመቁረጥ አላስተላለፉትም፡፡እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ሲደመሩ የአቶ ሽመልስ ከማል ንግግር ነጭ ውሸት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡

ሁለተኛ የአንድ ሀገር መንግስት ዜጎቹ እየተደፈሩ፣በማጎሪያ ካምፕ በረሀብና በውሃ ጥም፣ሌላው ቢቀር መጸዳጃ ቤት እንኳ ተከልክለው ፍጹም ከሰውነት ክብራቸው ወርደው እየተበደሉ፣እየተገደሉ ባለበት ወቅት ገና ለገና ተቃዋሚ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በሚንጸባረቅ ጥላቻና ተቃውሞ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ይበላሽብኛል ብለን መናገር እንችላለን?ሌላው ይቅር አንድ ክፉና ደጉን የለየ ሰው የሚያስበው ጤነኛ ሃሳብ ነው ማለትስ ይቻላል?

ከእገዳው ባሻገር የሚደንቀው ነገር ደግሞ በፓርቲያችን አመራሮችና አባላት ላይ የተደረገው ድብደባ ነው፣የሆነ ማስተላለፍ የፈለጉት ነገር ያለ ይመስላል፡፡የጭካኔያቸውን መጠን እንድናውቅ የሚደበድቡት አቅመ-ደካሞችን፣ሽማግሌወችንና ሴቶችን እየመረጡ በፍጹም አረመኔነት ነበር፡፡ይህን ተግባራቸውን ስመለከት የደረሱበትን የዝቅጠት ደረጃ መታዘብ ችያለው፡፡ከፖለቲካ ልዩነትም፣ከአምባገነንነትም በላይ ሰወቹ እንደታመሙ ነው ለመረዳት የቻልኩት፣ስር የሰደደ የቁስ ሰቀቀንና የስልጣን ጥም የተጣባቸው፣ለዚያ ሲሉም የትኛውንም አይነት ውርደት ለመቀበል የቆረጡና የሞራል ልዕልናቸውን ሙሉ በሙሉ ያጡ ሰዎች ናቸው፡፡ስነ-ልቦናቸው ክፉኛ ተቃውሷል እንጂ ሀገር እመራለው የሚል ቡድን እንዲህ ያለ ተግባር ይፈጽማል ለማለት እቸገራለው፡፡በአባላቶቻችን ላይ ክፍኛ ድብደባ ተፈጽሟል፣እስከዛሬም እግሮቻቸው መራመድ የማያስችላቸው፣የሚያነክሱ ሰዎች አሉ፡፡እውነት ለመናገር ይሄ እብደት ነው፡፡አንዲት እራሷን መከላከል የማትችል ሴትን ለሶስት መደብደብን ከዚህ በተሸለ ልገልጸው አልችልም፡፡

አንድ ማስገንዘብ የምፈልገው ነገር ለኛ ዋነው ጉዳይ የዜጎቹ ህጋዊነት ወይም ህጋዊ ያለመሆን ጉዳይ አይደለም፡፡በምንም አይነት መንገድ ሴቶች እየተደፈሩ፣ወንዶች በየስርቻው እንደ ውሻ ተቀጥቅጠው እየተገደሉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ታጉረው ይህን ሁሉ መከራ መቀበላቸውን ልንታገሰው፣ወይም ከህጋዊነት አንጻር እየተራቀቅን ልንመለከተው አንችልም፣ስለ ህግም ከተወራ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ጭፍጨፋው ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ባላቸው ላይ ጭምር ሲፈጸም እንደነበር አምኗል፡፡

ባለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን የአንዱ ሀገር ዜጋ ካለ ሀገሩ መገኘት አገር ይያዝ የሚያስብል አይደለም፡፡መውጣት ካለባቸው ጊዜ በመስጠት፣ከመንግስታቸው ጋር በመነጋገር በዘዴ ነገሩን መከዎን እየተቻለ አንድ ሀገርና መንግስት በሰዎች ላይ እንዲህ የጭካኔ ጥግ የሆነን አቋም ይዘው መንቀሳቀሳቸው ፍጹም ኢ-ሰብአዊነት ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን እንዲህ ያለ አስከፊ ጊዜ የለም፣እውነቱን ለመናገር ለአገዛዙ ሰዎች የነበረኝ ጭላንጭል ተስፋም አፈር ተደፍቶባታል፣እንዲህ ግልጽ የሆነ ጭፍጨፋ እየደረሰብን እንኳ በድፍረት ለመናገር አልፈለጉም፡፡ስለ ኢትዮጵያውያን መገደል ለማውራት ሲፈልጉ ሌላ ሀገር ይጠቅሱና እነሱም እኮ እየተገደሉ ነው ይላሉ፣ወገን ከምንለው የማህበረሰባችን አካል ይሄን መስማቱ ከጥቃቱ ይበልጥ ያማል፡፡

ለምሳሌ ኢቲቪ ስጉዳዩ ሲያወራ ህገ ውጥ ሊባል የሚችል ድርጊት ተፈጽሟል በማለት ነው፡፡ተመልከቱ! እንዴት ያለ ባዕድነት ነው?ኢትዮጵያውያን በድህነትም ውስጥ እንኳ ለክብራችን የመሞት ባህሪ አለን፣ይሄ ከቀደሙት አንጡራ ኢትዮጵያውያን የወረስነውና ዛሬም ያለን ሀብታችን ነው፡፡

ትናንት ፍየል ጠባቂ የነበረ በረኸኛ ይህን ክብራችንን ገፍፎ እንደውሻ ቀጥቅጦ ስርቻ ሲጥለን ያልተቆጣ መንግስት ኢትዮጵያዊ ነው?ከዜጎቹ የወጣና ለህዝቡ የቆመ እውነተኛ መንግስት ከዚህ የበለጠ የሚቆጣበት ጉዳይ ከወዴት ይመጣል? እውነተኛ መንግስት ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሳውዲ ካምፓኒዎችን በሰአታት ውስጥ ማባረር፣ኢምባሲውን ዘግቶ አምባሳደሩን ማሰናበትን የመሳሰሉ ውሳኔዎችን ያሳልፉ ነበር፡፡የሆነው ግን በተቃራኒው ነው፣የድፕሎማሲ ግንኙነቴ ሊበላሽ ይችላል ብሎ እኛ ድምጻችን እንዳናሰማ ደበደበን፣አፈነን፡፡በግልጽ እንደሚታየው የጥቅም ትስስሩ ነው አፋቸውን ያዘጋቸው፣ይህች ጥቅማቸው እንዳትቋረጥ በዜጎች ህይዎት መደራደርን መርጠዋል፡፡

ስነ ልቦናቸው የተቃወሰ በመሆኑና ተራ ስስታሞች በመሆናቸው እንጂ ኢንቨስትመንትም ሆነ ዲፕሎማሲ ግብአትነታቸው ለሰው ልጅ ነው፣እንደ አህያ ሲያፈጋ ከርሞ ሬሳቸውን ለላከ መንግስት እንዴት ተመጣጣኝ ምላሽ ለመመለስ ይገዳል?እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ታሪካዊትና ለአፍሪካ የነጻነትና የኩራት ተምሳሌት የሆነች ሀገርን እየመሩ እንዴት ትናንት የነዳጅ ዘይት ባቆማቸው እረኞች ስትዋረድ ዝም ይላሉ?!::

እንዴት!በዜጎች ህይወት የተደራደረው አገዛዝ ማለፉ አይቀርም፣ለዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ታሪክ ለመጥቀስ ብዙ ርቀት መሄድ አያስፈልግኝም፡፡የቅርብ የሰሜን አፍሪካ አምባገነኖች የከፋ ፍጻሜ አለና፡፡ኢትዮጵያውያን ፍቅርም ጸብም እናውቃለን፣ሳውዲወችም የፈጸሙትን ግፍ ማወራረዳቸው አይቀርም፡፡በዚህ ክፉ ጊዜ ስለስብአዊ መብት ቆመናል የሚሉ አለም አቀፍ ተቋማት ዝምታን መምረጣቸው እውነተኝነታቸውን ለመመርመር ጥሩ እድል ይሰጠናል፡፡

መንግስት ቢኖረን ኖሮ ይሄ ሁሉ ውርደት ይፈጸምብን ነበር ብየ አላስብም፡፡በዚህ ሰአት ርዕሰ-መንግስት ብሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ድርጅት እንደመሆኑ፣ወደየትኛውም ሀገር የሚደረገውን ጉዞ አቋርጨ ዜጎቸን ማስወጣትን አስቀድም ነበር፡፡ያሄ ጥቂት ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ሊያመጣብን ቢችልም ከከፋው የዜጎች ስቃይ ጋር ግን በአንድ ሚዛን ላይ አይቀመጥም፡፡የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ኮሚሽን የሚባል ድርጅት አለ፡፡በዜጎቻችን ላይ ጎርፍና ድርቅ ሲመጣ ብቻ ነው የሚንቀሳቀሰው? ይሄም ሰው ሰራሽ አደጋ ነው ሙሉ ሀይሉን ወደዚህ አዙሮ ሊንቀሳቀስ ይገባው ነበር፡፡

እርግጥ ነው ባቀድነው መሰረት ሰላማዊ ሰልፉ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡ጩኸቱ ግን ይቀጥላል……ባለን አቅም ሁሉ አፈናውንም፣ወከባውንም ተቋቁመን ለዜጎቻችንና ለኢትዮጵያዊነት እንታገላለን፡፡

አገዛዙ ይሄን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያፍን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንድ መልእክት አስተላልፏል፣ይህን መልእክት እንዲያስትላልፍ ማስገደዳችንም ለኛ ትልቅ ስኬት ነው፡፡የሳውዲ መንግስት ያሻውን ያደርግ ዘንድ የፈቀድኩት እኔ ነኝ፣በመሆኑም እሱን በመቃወም ግንኙነቴን አታበላሹ ብሎ እርምጃ በመውሰዱ ህዝቡ የነገሩ ቁልፍ የት እንዳለ፣የአጥቂወቹ በራስ መተማመን ምን ላይ እንደቆመ በጠራ ሁኔታ ለመመልከት እንዲችል ሆኗል፡፡

ይሄ ሁሉ ነገር እየተፈጸመ የተስተዋለ አንድ ነገር አለ፡፡የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ እውነተኛ ማንነታቸው፣እውነተኛ በአገዛዙ ውስጥ ያላቸውን ቦታ ያሳየን ክስተት ነው፡፡እንደሚታወቀው እሳቸው በኢህአዲግ እንጂ በኢትዮጵያ ህዝብ የተመረጡ አይደሉም፡፡ኢህአዲግ የሚናገረው ከሌለ እርሳቸው የሚሉት አይኖርም፡፡እንደ አንድ ሀገርና ህዝብ መሪ ግን የመኮነንም ሆነ የማጽናናት ቃል ይጠበቅባቸው ነበር፡፡

ባሉበት ቦታ ያስቀመጣቸው ህወሀት ነው፤ድርጅቱ ደግሞ ይሄን አቋም አልወሰደም፡፡ስለዚህ እንደሚቆጣቸው ስለሚያውቁ ዝምታን መረጡ፣ቸልታንም አስበለጡ፡፡በሀገርም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ከዚህ በላይ ሽንፈት ያለ አይመስለኝም፡፡

(ይህ ጽሁፍ በፋክት መጽሄት ተስተናግዷል፣ነገር ግን መጽሄቱ ላልደረሳቸው ሰዎች ይደርስ ዘንድ እዚህ ለማስተናገድ ወደድኩ፡፡)

posted by Tseday Getachew

በሽብርተኝነት ስም የህዝብ መብቶችን ማፈን ይቁም!

ከቅዱስ ዬሃንስ

ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ሁለት ጥቅም ያስገኝላቸዋል፡፡ አንደኛ በፀረ- ሽብርተኝነት ስም ከምዕራባውያን ኃያላን ጎን በአጋርነት በመቆማቸው በጥሬ ገንዘብም ሆነ በዓይነት (ለምሳሌ በመሣሪያ፣ በፖለቲካ ድጋፍ) ዳጎስ ያለ ጥቅም ያገኛሉ፡፡ ሁለተኛ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ስም የሚያወጡት ሕግ የውስጥ የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን ለማጥቃት የሚያስችላቸውን ሕጋዊ ሽፋን ይሰጣቸዋል፡፡ ስለዚህ ነው ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ከሰማይ የወረደ የተቀናቃኝ ማጥቂያ መሣሪያ ነው የሚባለው፡፡ ይህንን ያልኩበት አብይ ጉዳይ ዛሬ ሃገራችንንና ህዝቧን እያስጨነቀ ያለው የወያኔ አገዛዝ የፀረ ሽብርተኝነት ህግን ከለላ በማድረግ በሰላማዊ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው የመብት ረገጣ፤ እጅግ የከፋ ደረጃ በመድረሱ ነው።

በሰላማዊ ትግል ዴሞክራሲያዊ የመንግስት ለዉጥ ለማምጣት የሚታገሉ ሰላማዊ ዜጎችን አግባብ ባልሆነና ባልተጨበጠ ክስና ዉንጀላ ማሰር፣ አፍኖ መሰወር፣ ንብረትን ማዉደምና መዉረስ እንዲሁም የአደባባይ ግድያ ባለፉት 22 የወያኔ የአገዛዝ ዘመናት የተለመዱ ተግባሮች ሆነዉ ቆይተዋል። አሁን ደግሞ ይህ አምባገነናዊና ኢፍትሀዊ ተግባር በህግ ሽፋን ተጠናክሮ ቀጥሏል። ለገዥዉ ስርአት የአፈናና የጥርነፋ መዋቅር ተባባሪ ያልሆኑና ለመብታቸዉ መከበር የሚታገሉ ዜጎች በአሸባሪነት ስም በጅምላ እየታፈሱና እየታሰሩ ይገኛሉ። ታፍነዉ የተወሰዱና ያሉበት ቦታ የማይታወቀዉም ጥቂቶች አይደሉም። ባለፉት ጥቂት አመታት ብቻ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሽብርተኝነት ተወንጅለዉ ታስረዋል። ሰብአዊ መብታቸዉም በማንአለብኝነት እየተረገጠ ይገኛል። ከነዚህ ንፁሀን ዜጎች ዉስጥ ብዙዎቹ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላቶች፤ የእምነት መሪዎችና ለሞያቸዉ ታማኝ የሆኑ ጋዜጠኞች መሆናቸዉን ስናይ ደግሞ ዘመቻዉ በሀገራችን ተጠናክሮ የህዝብን የስልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚደረገዉን ሰላማዊ ትግል ለመጨፍለቅና ህዝብን ከትክክለኛ መረጃ አርቆና አፍኖ ለመግዛት ታስቦበትና ሆነ ተብሎ የተያዘ ስልት መሆኑን ግልፅ ነው።

በሽብርትኝነት ያለመከሰስ መብቱን በጠመንጃ ያስከበረው ወያኔ ግን ሰላማዊውን ህዝቡ በተለያዩ መንገዶች እያሸበረ የስልጣን ቆይታውን ለማርዘም ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል። ዜጐችን በማፈናቀል፤ በእምነት ውስጥ ጣልቃ በመግባትና የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት በመከፋፈል እያፋጀ የሽብር ሴራውን እየፈፀመ ይገኛል። ሰላማዊ ዜጋውን ፣አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን በልማት ስም ተወልዶ ባደገበት እትብቱ ከተቀበረበት ሃገር እያፈናቀለ ለስደት እየዳረገው ይገኛል፡፡ ለዚህም የሽብር ሴራው ሰለባ የሆኑት፤ የሚበሉት፤ የሚጠጡት እና በመጠለያ እጦት በየአደባባዩ ሰፍረው የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ የሚገኙት የአማራ ብሔረሰብ ወገኖቻችን ናቸው፤ እነዚህ ወገኖቻችን በሃገሪቱ አራቱም ማዕዘናት እየተፈናቀሉና እየተዋከቡ ይገኛሉ። ማፈናቀለ አልበቃ ያለው የወያኔ የሽብር መረብ ወደ እምነት ቦታዎችም በመዛመት ዋልድባን እና የተለያዩ የሃይማኖት ቦታዎችን በማፈራረስ በአለም ደረጃ እውቅና እና አድናቆት የተሰጣቸውን የሃገሪቱን የሃይማኖት፤ የታሪክ ቅርሶች በማውደም፤ ኢትዮጵያውያን በቀደምትነት በምንታወቅበት እምነታችን ላይ አደጋ በመፍጠር፤ አዋራጅ ድርጊቶችን በንቀት እና በጥላቻ እየፈፀሙ ይገኛሉ፡፡ ከእምነት ቦታዎች ባሻገር በአለም ደረጃ እውቅናን ካገኙት ታሪካዊ ቦታዎች ውስጥ ተጠቃሹ የታችኛው አዋሽ እና ኦሞ ሸለቆዎች አንዱ ነው፡፡ ይህ ታሪካዊ ቦታ ያራዊቶች እና የተለያዩ የደኖች ስብስብ ያለበት ሰፊ የሃገራችን ቅርስ የነበረው ሲሆን ዛሬ ላይ ግን ወያኔዎች በልማት ስም ለውጭ ባለሃብቶች አስረክበውት ድብዛው እየጠፋ ነው፡፡ አምባገነኑ ወያኔ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ያነሱትን የመብት ጥያቄ ወደ ጎን በመተው በእኔ አውቅላችኋለሁ እብሪት የተሞላ አስተሳሰብ በማፈን ንፁሃኑን ሙስሊም እየገደሉ ብሎም በሽብርተኝነት በመወንጀል እያሰቃዩት ይገኛሉ። ሙስሊሙ ህብረተሰብ የተቃውሞ ድምፁን ያሰማበትን አላማ ምንድነው? ችግሩስ ከምን የመነጨ ነው? ብሎ እልባት ከመስጠት ይልቅ ጥያቄአቸውን በማንቋሸሽ እና በማጥላላት በጠመንጃ አፈ ሙዝ የሚመልሱት ይመስል ህዝበሙስሊሙን ለከፋ መከራና ስቃይ ዳርገውታል። ለዚህ ድርጊታቸው ደግሞ ሚስጥሩ ንፁሃኑ ህዝበ ሙስሊም ላይ የሃሰት ታርጋ በመለጠፍ አሸባሪነትንና አክራሪነትን እየተዋጋው ነው በሚል የማስመሰልና የማታለል ስራው የምዕራባውያን ሃገራትንና የአሜሪካ ቀልብ ለመሳብና እርዳታ ለማጋበስ ነው። ቢያውቁት ግን ይህ ድርጊታቸው አውሬ እንጅ ሰው አለመሆናቸውን ቁልጭ አድርጐ ያሳያል። ለገንዘብ ሲባል ሰውን ያክል ፍጡር መግደል፤ ማሰርና ማሰቃየት ከአንድ ሰው የሆነ ሰብአዊ ፍጡር አይጠበቅምና።

ሌላው ወያኔዎች 22 ዓመታት በጠመንጃ ስልጣን ላይ ከወጡበት ጊዜ አንስቶ ሲጠነስሱት የነበረው ሽብር የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት በመከፋፈልና በማፋጀት የኢትዮጵያን ህልውና አንድነትን፣ ማንነትን በማናወጥ፤ የስልጣን እድሜያቸውን ማርዘም ነው። ይህ ስራቸው ከምን ጊዜውም በላይ በአሁኑ ሰአት እያፋፋሙትና፤ ሰላማዊውን ህዝብ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት በማጋጨት የሽብር ሴራቸውን እያስፋፉ ይገኛሉ። ዳሩ ግን ለወያኔዎች ህዝብን መከፋፈል የሚበጅ ቢመስላቸውም የዚህ የሽብር ድራማቸው ተጠቂዎች ግን በፍፁም ልንሆን አልቻልንም፤ ወደፊትም ልንሆን አንችልምም። ምክንያቱም መቻቻል እና በፍቅር አብሮ መኖር መለዬ ባህላችንን በፍፁም ይህ ሰይጣናዊ ድርጊታቸው ሊያመክነው ስለማይችል ነው። ይህንን አንድነታችንን፤ ፍቅራችንን የመቻቻል ባህላችንን የበለጠ በማጎልበት፤ ባህላችንን፣ አንድነታችንን፣ ሃይማኖታችንን እየተፈታተነ ያለው የወያኔን የሽብር ስልት በማክሸፍ፤ ለበለጠ ድል እስክንበቃ ትግላችንን ማጠናከር ይኖርብናል።

በመጨረሻም የወያኔ ባለስልጣናት በፈረጠመ አምባገነናዊ ክንድ ህዝብን በማሸበርና በማፈን የስልጣን ዘመንን ለማራዘም መሞከር አወዳደቅን ማክፋት መሆኑን ካለፉት አምባገነናዊ ስርአቶች ሊማሩ ይገባል! አሁንም በድጋሚ ወያኔዎች ጠንቅቀው ሊያውቁት የሚገባ እውነት የኢትዮጵያ ህዝብ ሽብኝነትን በጽናትና በቁርጠኝነት ይቃወማል፤ ያወግዛልም፡፡ በፀረ -ሽብርተኝነት ሽፋን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን እየጣሰ ያለውን የወያኔ አገዛዝንም በተመሳሳይ ጽናትና ቁርጠኝነት ይቃወማል፤ ይታገላልም!!!

ድል ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!

ያለዎትን አስተያየት በፀሃፊው አድራሻ: kiduszethiopia@gmail.com ይላኩ።

posted by Tseday Getachew

 

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ሰራዊት በጋራ ወታደራዊ ጥቃት መፈጸማቸውን አስታወቁ

Arbegnoch

 

(ዘ-ሐበሻ) የጋራ ትግል አስፈላጊ መሆኑን በፅኑ እንደሚያምኑ የሚገልጹት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢሕአግ/ እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ /ጋሕነን/ በሕዳር 13/2006 ዓ.ም በሁመራ ሉግዲ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ለሶስት ሰዓት ያህል በወሰደው ውጊያ የወያኔው 24ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ መመታቱን የአርበኞች ግንባር ቃል አቀባይ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ አስታወቀ። “ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በ24ኛው ክፍለ/ ጦር ላይ በተመሳሳይ ሥፍራ ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል” ያለው ዘገባው ” በሕዳር 13/2006 ዓ.ም የኢሕአግና የጋህነን ሰራዊት በወሰዱት ድንገተኛ ወታደራዊ ጥቃት 66 /ስልሳ ስድስት/ ገድለው 113 /አንድ መቶ አስራ ሶስት/ በማቁሰል እንዲሁም ቁጥራቸው የበዛ የጦር መሳሪያዎችን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ማርከዋል።” ብሏል።

“ሁለቱ ድርጅቶች በጋራ በተለያየ የትግል መስክ ሲተጋገዙና ሲተባበሩ ቆይተዋል” ያለው የአርበኞች ግንባር ቃል አቀባይ ይህ “የግንኙነታቸውን እድገትና ለውጥ የሚያሳይ ወታደራዊ ጥቃትም ፈፅመዋል። ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘውና የሚፈልገው የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ስምምነትና አንድነት መገለጫ ሊሆን የሚችል አኩሪ ጥቃት መሆኑ ይታመንበታል።” ሲል የትብብሩን አስፈላጊነት ገልጾታል።

“በጥቃቱ የተካፈሉ የሁለቱ ድርጅቶች ታጋዮች እንዳብራሩት ዛሬ በጋራ የጀመርነው ወታደራዊ ጥቃት በዚሁ የሚያበቃ ሳይሆን የጋራ ዓላማና ራዕይ እስካለን ድረስ ወደኋላ የማይቀለበስ ነው ሲሉ ተናግረዋል።” ያለው የግንባሩ ቃል አቀባይ “ከዚህም አክለው የዚህ ወታደራዊ ዘመቻ ዓላማ አገር እንደሌለው ሁሉ በሰው አገር ፍዳውን እያየና እየተሰቃየ እንዲሁም ለሞት እየተዳረገ የሚገኙውን በሳውዲ አርቢያ ለተፈፀመው በደል ለመበቀልና ሕዝባዊ ወገንተኝነታችንን ለማሳየት ታስቦ የተወሰደ ወገናዊ እርምጃ ነው በማለት አብራርተዋል። በውጊያው ከሞት ተርፎ ለከባድ ቁስልና የአካል ጉዳት የተዳረገው የወያኔው ቅጥረኛ የ24ኛ ክፈለ ጦር አባላትን ከሁመራ አንስቶ እስከ ትግራይ የሕክምና ማዕከሎች ማጋጋዝ ዋነኛ ተግባሩ ሆኗል።” ብሏል።

የአርበኞች ግንባር ቃል አቀባይ ለዘ-ሐበሻ የላከውን መግለጫ ሲያጠቃልልም “ይህንን የጀግና ጥቃትና ድል የተመለከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ሰራዊቱን እንኳን ደህና መጣችሁ ብሎ በመቀበልና ስንቅና ትጥቅ በማቅረብ አጋርነቱን ያስመሰከረ ሲሆን የተጀመረው ወታደራዊ ጥቃት በተለያዩ አካባቢዎች ላይ እንዲደገም ያላቸውን ልባዊ ምኞት ገልፀው በንፁሃን ላይ ያለ አግባብ ሲወሰድ የነበረው የቅጥረኞች እርምጃ አንጀቱ ላረረው ሕዝብ እምባ ያበሰ እንደሆነም ተናግረዋል። በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር/ ኢሕአግ/ እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ /ጋህነን/ ወያኔ ለ22 ዓመት ያህል አገሪቷን ሲበዘብዝና ሕዝቡ የዲሞክራሲያዊ መብቱ ተጠቃሚ እንዳይሆን በሃይል የመግዛቱ ሂደት እንዲያከትም የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ ቆርጠው መነሳታቸውን አስታውቀዋል።” ብሏል።

አርበኞች ግንባር እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ሰነዘርን ባሉት ወታደራዊ ንቅናቄ ዙሪያ ከመንግስት አካባቢ የተገኘ ምላሽ የለም።

http://www.zehabesha.com/

posted by Tseday Getachew

Post Navigation