Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

Archive for the month “May, 2013”

የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን በተጠርጣሪዎች 60 የክስ መዝገቦች መቋረጣቸውን አስታወቀ

court

 
– የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት

– ሁለት ተጠርጣሪዎች በምርመራ ወቅት መደብደባቸውን ተናገሩ

‹‹ተያዘ የተባለው ሰነድ ሁሉ በሀብት ምዝገባ ያስመዘገብኩት ነው›› አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ምርመራ ቡድን፣ በተለያዩ የሙስና ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር በዋሉ ተጠርጣሪዎች እንዲቋረጡ ከተደረጉት 60 የክስ መዝገቦች ውስጥ 28 ያህሉን መሰብሰቡን ግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ለፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

መርማሪ ቡድኑ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ እንዳስረዳው፣ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ባለፉት 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ላይ የሠራውን የምርመራ ሥራ እንዳብራራው፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሥራዎች ጋር ግንኙነት ያላቸውን የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ሰብስቧል፡፡ ከተለያዩ ባንኮች በተወሰኑ ተጠርጣሪዎች ላይ ከአራጣ ብድር ጋር የተያያዙ ማስረጃዎችን፣ በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ (መኒ ላውንድሪንግ) መጠቀምን የሚያሳዩ ሰነዶችን መሰብሰቡን ገልጿል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ጨምሮ እንደገለጸው፣ ተጠርጣሪዎቹ በአራጣ ብድር የተከሰሱ ሰዎችን ክስ ያቋረጡባቸውን የክርክር መዝገቦችን መሰብሰቡንና በኮንትሮባንዲስቶች ላይ በፍርድ ቤት ተጀምረው ከነበሩትና በሕገወጥ ጥቅም ከተቋረጡት 60 የክስ መዝገቦች ውስጥ 28 የሚሆኑት መሰብሰቡንም ገልጿል፡፡

በአንድ የንግድ ድርጅት ላይ ተወስኖ የነበረን ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ግብር ወደ ሦስት ሚሊዮን ብር የተቀነሰበትን ሰነድ፣ እንዲሁም 87 ሚሊዮን ብር ግብር እንዲከፍል ተወስኖበት የነበረን ድርጅት፣ በሕገወጥ መንገድ ወደ ስምንት ሚሊዮን ብር ዝቅ የተደረገበትን ሰነድም መሰብሰቡን ቡድኑ ለችሎቱ ተናግሯል፡፡

ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኦዲት ሊያደርጋቸው የሚገቡ ስምንት ኩባንያዎች መኖራቸውን ማረጋገጡን የገለጸው መርማሪ ቡድኑ፣ ኦዲት የሚደረጉትን ለይቶ መጨረሱንና ለመሥሪያ ቤቱ ደብዳቤ መጻፉን አሳውቋል፡፡ መርማሪ ቡድኑ የምስክሮችን ቃል በከፊል መቀበሉንና የንብረት ጥናትም በከፊል መሥራቱን ገልጾ፣ የቀሩትንም የምርመራ ሥራዎች ጠቁሟል፡፡

ያላግባብ ክሳቸው የተቋረጡ 40 የክስ መዝገቦችን መሰብሰብ፣ በሕገወጥ መንገድ ግብር እንዲቀነስ የተደረገባቸውን ሰነዶች፣ ሕጋዊ በማስመሰል ሕገወጥ ገንዘብን ለመጠቀም የተዘጋጁ ሰነዶችን መሰብሰብ፣ የስምንት ኩባንያዎችን ግብር ማጣራት፣ የኦዲተሮችን ቃልና የቀሪ ምስክሮችን ቃል መቀበል እንደሚቀረው በመግለጽ፣ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ላለፉት 14 ቀናት በተጠርጣሪዎቹ ላይ የሠራቸውንና የሚቀሩትን ሥራዎች ለችሎቱ ካሳወቀ በኋላ፣ በጠየቀው ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜን በሚመለከት አስተያየታቸውን እንዲሰጡ በችሎቱ የተፈቀደላቸው፣ በኢትዮጵያ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ኃላፊ የምርመራ መዝገብ ሥር ያሉ 12 ተጠርጣሪዎች ናቸው፡፡

መርማሪ ቡድኑ በጥቅል ከመግለጽ ባለፈ እያንዳንዱ ተጠርጣሪ ምን እንደሠራ፣ ተጠርጣሪው ከሠራው ወይም ካጠፋው ነገር አንድም እንኳን እንዳልተነገረው፣ ምን ሠርቶ ምን እንደቀረው እስካሁን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለፍርድ ቤቱ ያስረዱት፣ የአቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር ጠበቃ ናቸው፡፡ ደንበኛቸው ተጠርጥረው የታሰሩት ክስ በማቋረጥና ባልተፈቀደ የፍራንኮቫሉታ ፈቃድ ሲሚንቶ ማስገባት እንደነበር ያስታወሱት ጠበቃው፣ መርማሪ ቡድኑ 14 ቀናት የምርመራ ተጨማሪ ጊዜ ሲጠይቅ ያልተናገራቸውና ለደንበኛቸው ያልተገለጹላቸው ሰነዶችን ማሸሽ፣ ንብረት ከተገቢው በላይ ማፍራትና ከባለሥልጣናት ጋር መመሳጠር፣ ሕገወጥ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ መጠቀም፣ አራጣ ማበደርና ግብር ያላግባብ መቀነስ የሚሉት የሕገ መንግሥቱን ድንጋጌ የሚጥስና ያላግባብ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡

በሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ መሠረት ስለተጠረጠሩበት ወንጀል በተያዙበት ወቅት ሊነገራቸው ይገባ እንደነበር የገለጹት ጠበቃው፣ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ መርማሪ ቡድኑ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ሲጠይቅ ያስመዘገባቸው፣ ‹‹የሲሚንቶው ጉዳይ ምን ሆነ? ሰነድ ጠፋ ወይስ ምን ሆነ? ሊገለጽልን ይገባል፤›› ካሉ በኋላ፣ በወቅቱ ያልተገለጹና እንደ አዲስ ክስ የቀረቡት ጉዳዮች ተገቢ ጥያቄዎች ባለመሆናቸው የ14 ቀናት ተጨማሪው የጊዜ ጥያቄው ውድቅ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡

አቶ ገብረ እግዚአብሔር እንዲናገሩ ችሎቱን ጠይቀው ሲፈቀድላቸው እንደተናገሩት፣ በምን ተጠርጥረው እንደታሰሩ አያውቁም፡፡ ለምርመራ ሲቀርቡ በተደጋጋሚ የሚቀርብላቸው ጥያቄ ስለንብረታቸው ነው፡፡ የልብ ሕመምተኛ መሆናቸውንና ንብረታቸውም የተመዘገበ መሆኑን በመግለጽ፣ ማወቅ የሚፈልገው አካል በፈለገ ጊዜ ሊያውቅ እንደሚችል ገልጸው፣ እሳቸው ግን በአንድ በተዘጋ ክፍል ውስጥ መሆናቸው አግባብ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

እምባና ሳግ እየተናነቃቸው ዝቅ ባለ ድምፅ መናገር የቀጠሉት አቶ ነጋ፣ በታሰሩበት ክፍል ውስጥ ሁለት ጊዜ ራሳቸውን ስተው ወድቀው እንደነበርና መደብደባቸውንም ገልጸዋል፡፡

ነጋዴ በመሆናቸው ሀብት ማፍራት እንደሚችሉ የተናገሩት ተጠርጣሪው፣ ምርጥ ታክስ ከፋይ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ መሆናቸውን፣ ለአገራቸው 33 ሚሊዮን ብር መድበው በ23 ሚሊዮን ብር ያስገነቧቸውን ፖሊ ቴክኒክ ትምህርት ቤቶችን ለሕዝብና ለመንግሥት ማስረከባቸውን ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡

‹‹አገሬን ያወቅኋት አሁን ነው፤ ዜጋ ነኝ ለማለት አይቻልም፤›› ያሉት አቶ ነጋ፣ ሲደበደቡ ራሳቸውን ስተው እንደሚወድቁ አስታውቀው፣ ኢሰብዓዊ ድርጊት እንደተፈጸመባቸው ጠቁመዋል፡፡ የደም ግፊትና የስኳር ሕመምተኛ መሆናቸውንና የልብ ቱቦ ተገጥሞላቸው ያሉ ታማሚ በመሆናቸው ክትትል ካልተደረገላቸው ለሕይወታቸው አስጊ መሆኑን ጠበቃቸው አክለዋል፡፡

የመርማሪ ቡድኑን በጥቅል የመግለጽ ሁኔታ እንደ አቶ ነጋ እሳቸውም እንደሚቃወሙት የተናገሩት የባለሥልጣኑ ሠራተኛ አቶ ጥሩነህ በርታ ሲሆኑ፣ መርማሪዎች ወደ ምርመራ ክፍል በመውሰድ የሚጠይቋቸው ከሥራቸው ጋር የማይገናኝ፣ መረጃ እንደሚያውቁ ተደጋጋሚ ጥያቄ እንደሚቀርብላቸውና በማያውቁት ጉዳይ ላይ መረጃ ሰብስበው ክስ ለመፍጠር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እሳቸው ተጠርጥረዋል በተባሉበት ክስ የማቋረጥ ወንጀል መጠየቅ ያለባቸው እሳቸው ሳይሆኑ ከእሳቸው በላይ ያሉ ኃላፊዎች እንደሆኑ የተናገሩት ተጠርጣሪው፣ እነሱ ሳይጠረጠሩ እሳቸውን አስሮ ማሰቃየት ኢሰብዓዊ ድርጊት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ሱሪያቸውን ከፍ በማድረግ እግራቸውን ለችሎቱ እያሳዩ መደብደባቸውን የገለጹት ተጠርጣሪው፣ ውኃ እየተደፋባቸው እንደተገረፉ ለበላይ ኃላፊ ቢያመለክቱም፣ መርማሪዎቹ በድጋሚ ሲያገኟቸው ‹‹እንኳን ለኃላፊ ለማንም ብትናገር አንተውህም›› እንዳሏቸው ሲገልጹ መርማሪ ቡድኑ አቤቱታቸውን ተቃውሟል፡፡ የተቃወመበትን ምክንያት እንዲያስረዳ ፍር ቤቱ ሲፈቅድለት፣ ተጠርጠሪው የሚያነሱት ጉዳይ አስተዳደራዊ መሆኑን በመጠቆም፣ ፍርድ ቤት ሊቀርብ እንደማይገባ አመልክቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ምላሽ፣ ‹‹አስተያየታቸው ሊደመጥ ይገባል፡፡ ኮሚሽኑ ከሰብዓዊ መብቶች ጋር በተያያዘ የሚነሱ አቤቱታዎችን እንዲያስተካክል በተደጋጋሚ ቢታዘዝም ሊታረም አልቻለም፤›› በማለት ተጠርጣሪው አቤቱታቸውን እንዲቀጥሉ አዟል፡፡

ተጠርጣሪው ቃላቸውን እስካሁን የተቀበላቸው እንደሌለ በመግለጽ፣ ቢሮአቸውንም ሆነ ቤታቸውን ቡድኑ በርብሮ ምንም አለማግኘቱን፣ እያንገላታቸው ያለው አዲስ ማስረጃ ለማሰባሰብ እንጂ በእሳቸው ላይ ምንም ዓይነት ጭብጥ እንደሌለው ፍርድ ቤቱ እንዲገነዘብላቸው አመልክተዋል፡፡

የባለሥልጣኑ ኦዲተር መሆናቸውንና ደመወዛቸው ከአሥር ሺሕ ብር በላይ መሆኑን፣ የተጣራ 5,600 ብር አካባቢ እንደሚያገኙና ሥራ የሌላቸውን ባለቤታቸውን ጨምሮ፣ ልጆቻቸውንና የእህታቸውን ልጅ ጭምር የሚያስተዳድሩት እሳቸው መሆኑን የተናገሩት አቶ በላቸው በየነ ሲሆኑ፣ መርማሪ ቡድኑ የልጃቸው ላፕቶፕ ጨምሮ በመሥሪያ ቤታቸውና በቤታቸው ያለውን ሁሉንም ሰነድ ስለወሰደ በዋስ እንዲለቃቸው ጠይቀዋል፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን በጥቅሉ ሳይሆን እያንዳንዱ ተጠርጣሪ የተጠረጠረበትን ወንጀል ለይቶ ማቅረብ እንደሚገባው የገለጹት ተጠርጣሪው፣ መንግሥት በመደባቸው በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ ለ27 ዓመታት መሥራታቸውን፣ አብዛኛው ሥራዎቻቸውን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ጭምር ያውቁት እንደነበር፣ ቤተሰብንም ሆነ ሌላ አካል ወይም ማንንም ለመጥቀም በሚል ሕገወጥ ሥራ ሠርተው እንደማያውቁ አስረድተዋል፡፡

በቅርቡ ለዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኃላፊዎች ሥልጠና ለመስጠት እሳቸውና ሌላ አንድ ሰው ተመርጠው እንደነበር የተናገሩት ተጠርጣሪው፣ መርማሪ ቡድኑ ኩባንያዎችን ኦዲት እንዲያደርጉለት ለዋና ኦዲተሩ ደብዳቤ መጻፉን አስታውሰው፣ ‹‹ኦዲት የሚያደርጉት ሠልጥነው ነው ወይስ?›› ሲሉ ፍርድ ቤቱ ‹‹ይኼ በማስረጃ ጊዜ የሚታይ ነው፤›› በማለት አስቁሟቸዋል፡፡

አቶ ገብረ ዋህድ ወልደጊዮርጊስ ሁለት ሕፃናት ልጆቻቸው እስካሁን ድረስ የት እንዳሉ እንደማያውቁ፣ የሚረዳቸው ወይም የሚቀልባቸው ሰው ባለመኖሩ ሥጋት ላይ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት፣ ባለቤታቸው ኮሎኔል ሃይማኖት ተስፋይና እህታቸው ወ/ሮ ንግስቲ ተስፋይ፣ እንዲሁም በውጭ አገር ለሰባት ዓመታት ቆይቶ ከመጣ አራት ወራት ብቻ የሆነው የወ/ሮ ንግስቲ ልጅ አቶ ሀብቶም ገብረመድኅን በዋስ እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

እሳቸው የተጠረጠሩበትን የወንጀል ሰነድ አሽሽተዋል በሚል ቤተሰቦቻቸው መታሰራቸው አግባብ አለመሆኑን የገለጹት አቶ ገብረ ዋህድ፣ ሸሽቷል የተባለው ሰነድ ኮሚሽኑ ባወጣው የሀብት ማስመዝገብ አዋጅ የተመዘገበና ኮሚሽኑ የሚያውቀው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የባለቤታቸው እህት የ60 ዓመታት አዛውንት መሆናቸውን፣ ከአቅም በላይ በሆነ ውፍረት ክብደታቸው ከፍተኛ በመሆኑ ዕርዳታ እንደሚፈልጉና የደም ብዛትና የስኳር ሕመምተኛም ስለሆኑ ከተቻለ በነፃ ካልሆነም በዋስ አንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡

ኮሚሽኑ የቀረው መደበኛ ሥራው መሆኑን የገለጹት አቶ ገብረ ዋህድ፣ ከእሳቸውና ከቤተሰባቸው ጋር የሚያገናኘው ነገር ስለሌለ በዋስ እንዲለቀቁ ወይም የምርመራ ጊዜው አንዲያጥር አመልክተዋል፡፡

የአቶ ስዬ አብርሃ ወንድም አቶ ምሕረተ አብ አብርሃ ባቀረቡት አቤቱታ እንደገለጹት፣ የሚተዳደሩት በንግድ ነው፡፡ ከ1993 ዓ.ም. እስከ 1999 ዓ.ም. ድረስ በታሰሩበት ወቅት ንብረታቸውን ያስተዳድር የነበረው ኮሜት የሚባል ድርጅት ነበር፡፡ ንብረታቸውን በሚመለከት ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ጋር አለመግባባት ላይ ደርሰው፣ መብታቸውን ያስከበሩት በፍርድ ቤት ነው፡፡ በመሆኑም አሁን ‹‹ተጠርጥረሃል›› ከተባሉበት ክስ ማቋረጥ፣ ኮንትሮባንድ፣ አራጣና ሌሎች ጉዳዮች ጋር እንደማይገናኙ ተናግረዋል፡፡ ከነበሯቸው ከ15 በላይ ተሽከርካሪዎች ልጆቻቸውን እያስተዳደሩ ያሉት በሁለት ተሽከርካሪዎች በሚያገኙት ገቢ ብቻ መሆኑን የገለጹት አቶ ምህረተ አብ፣ ባለሥልጣኑ ከፍተኛ ግብር ጭኖባቸው ከ1999 ዓ.ም. እስከ 2003 ዓ.ም. ድረስ በፍርድ ቤት ባደረጉት ክርክር መብታቸውን ማስከበራቸውን ገልጸው፣ አሁን የተጠረጠሩበትን ምክንያት ስለማያውቁት ዋስትና እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡

ሁሉም ተጠርጣሪዎች በአጠቃላይ መርማሪ ቡድኑ ያቀረበው የምርመራ ውጤት ወንጀሉ ጥቅል መሆኑን፣ በተያዙበት ወቅት ያልተነገራቸው የወንጀል ክስተት እየቀረበባቸው መሆኑን፣ ማስረጃ ተሰብስቦ ቢያልቅም መብታቸው አለመከበሩን፣ ጥርጣሬዎቹ ከሰነድ ጋር የተገናኙ በመሆናቸው ታስረው ሊቆዩ እንደማይገባና ዋስትና ሊፈቀድላቸው እንደሚገባ፣ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንደማያስፈልግ የሚሉትን ሐሳቦች ሁሉም ያነሱ ሲሆን፣ በተናጠል ደግሞ የቤተሰብ ኃላፊ መሆናቸውን፣ የጤና ችግር እንዳለባቸው፣ የመብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑን፣ ከተያዙ ጀምሮ ቃላቸውን አለመስጠታቸውን ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል፡፡ በምርመራ መዝገቡ የቀረቡት 12 ተጠርጣሪዎች ናቸው፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን ተጠርጣሪዎቹ ላነሷቸው ጥያቄዎች በሰጠው ምላሽ፣ የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈጸመው በተናጠል ሳይሆን በቡድንና ውስብስብ በሆነ መንገድ መሆኑን ገልጿል፡፡ ጉዳዩ አገራዊ በመሆኑ በቀላሉ የሚታይ አለመሆኑንም አስገንዝቧል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከፍተኛ ኃላፊዎችና ባለሀብቶች መሆናቸውን በመጠቆም፣ ሥልጣንንና ገንዘብን ተገን በማድረግ ውስብስብ በሆነና በጥቅም በመመሳጠር በአገር ገቢ ላይና በሌሎች የሕዝብ ጥቅሞች ላይ የተፈጸመ ወንጀል መሆኑን አስረድቷል፡፡ ክስ እንዲቋረጥና ከውጭ የሚገቡ የንግድ ዕቃዎች ቀረጥ እንዳይከፈልባቸው ሲደረግ፣ ለጠቋሚዎች የሚከፈል አበል ለራስ ጥቅም ሲደረግ፣ አንድ ተጠርጣሪ ብቻ የሚሠራው ሳይሆን በቡድንና በመመሳጠር የሚሠራ መሆኑን መርማሪ ቡድኑ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡ ድርጊቱ በአጠቃላይ በትብብር የተሠራ መሆኑንና ለቀሪ የምርመራ ጊዜ ተጨማሪ 14 ቀናት ጊዜ እንዲፈቀድለት በድጋሚ አመልክቷል፡፡

ቃል አልሰጠንም ያሉት ተጠርጣሪዎች ቃላቸውን መስጠታቸውን በተለያየ መንገድ መግለጻቸውን፣ ሰብዓዊ የመብት ረገጣ ደርሶብናል ያሉት ተጠርጣሪዎችም በማስረጃ የቀረበ ባለመሆኑ ሊታመን እንደማይችል መርማሪ ቡድኑ ገልጾ፣ ዋስትና ቢፈቀድ የሰነድና የምስክሮች ቃል ሊያጠፉበት እንደሚችሉ በመናገር ዋስትናውን ተቃውሟል፡፡

መርማሪ ቡድኑ በተሰጠው ጊዜ በማን ላይ ምን እንደተሠራ፣ በማን ላይ ምን እንደቀረው በግልጽ አለማስቀመጡን፣ ይኼም ለክርክር በር መክፈቱን፣ በርካታ ምስክሮች የቀሩት በማን ላይ እንደሆነና ሰነድም ሆነ ሌላ መረጃ ለማጣራት የተፈለገው በማን ላይ እንደሆነ ግልጽ አለመደረጉ አግባብ አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ ገልጾ፣ በቀጣይ ቀጠሮ በእያንዳንዱ ተጠርጣሪ ላይ በተናጠል የተሠራው ተዘርዝሮ እንዲቀርብ አዟል፡፡

በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ ከድርጊቱ ውስብስብነት አንፃር የተጠርጣሪዎች ዋስትና ጥያቄን አለመቀበሉን፣ የመርማሪ ቡድኑን 14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜያት መፍቀዱን አስታውቆ፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን አቤቱታ ኮሚሽኑ አጣርቶ እንዲያቀርብ በማዘዝ ለሰኔ 3 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በዕለቱ መቅረብ የነበረበት የእነ አቶ መላኩ ፈንታ የምርመራ መዝገብና የእነ አቶ መሐመድ ኢሳ የምርመራ መዝገብ በመሆኑ፣ መዝገቡ የቀረበ ቢሆንም ቀኑ በመምሸቱ ለግንቦት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. በይደር ተቀጥሯል፡፡ በእነ መሐመድ ኢሳ የምርመራ መዝገብ ፍሬሕይወት ጌታቸው የተባሉ ተጠርጣሪ በመካተታቸው ጠቅላላ የተጠርጣሪዎች ቁጥር 55 ደርሷል፡፡

ግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሹማምንት፣ ታዋቂ ነጋዴዎችና ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ችሎት ለመታደም በፍርድ ቤት የተገኙ ታዳሚዎች ከችሎቱ አቅም በላይ ስለነበሩ በርካቶች ችሎቱን መከታተል አልቻሉም፡፡ (ምንጭ: ሪፖርተር)

http://www.goolgule.com

posted by Tseday Getachew

Advertisements

የግንቦት 7 ንቅናቄ 4ኛ ጉባኤ ህዝቡ ወደ ትግሉ እንዲቀላቀል ጥሪ አቀረበ

የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነት፣ የዲሞክራሲ ንቅናቄ 4ኛ ጉባኤ ከግንቦት 11 – 19/2005 አ/ም በበርካታ ወቅታዊ፣ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየት እና የድርጅቱን አዲስ ም/ቤት በመምረጥ ወያኔን በማስወገድ ረገድ ሊከተል የሚገባውን ጠቋሚ አቅጣጫዎችንና ውሳኔዎችን ከተሳታፊው በመውሰድ ወሳኝ የሆነ ውይይት አድርጓል።

ንቅናቄው ከተለያዩ አለማት በአባላት የተወከሉ ጉባኤተኞች እና በተለያዩ የስራ ክፍል የሚገኙትን የድርጅቱን አባላት ያሳተፈ፤ ከዚህ በፊት ከተደረጉትም ጉባኤዎች እጅግ የላቀ አባላት የተገኙበት ነበር።

ጉባኤው የነበረውን የም/ቤት ሪፖርት፣ የስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የኦዲትና ማናጅመንት ኮሚሽን፣ የግልግልና ዳኝነት ኮሚቴን እና የፋይናንስ ሪፖርቶችን በማዳመጥ ጥልቅ የሆነ ወይይቶች አደርጓል።

የግንቦት 7 ንቅናቄ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች፤ ደርጅቱ የጀመረውን ወያኔን የማስወገድ ትግል በየትኛውም አቅጣጫ አስፈላጊ ሆኖ የታመነበትን ማናቸውም መንገድ ሁሉ በመጠቀም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የዘረኝነትን ስርአት ድባቅ መምታት፤ አልፎም ዘላቂ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት አስቸኳይና ማንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ግዴታው አድርጎ መውሰድ ያለበት አጣዳፊ ስራ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰላም አየርና የዲሞክራሲ ጮራ ሁሌም የሚፈነጥቅባት፣ ህዝብ ካለፍርሃትና ሰቀቀን ወጥቶ የሚገባባት፣ ህዝብ በነጻነት የፈለገውን ፓርቲ የሚመርጥበት፣ የሚያወርድበት፣ ስልጣን የህዝብ መሆኑን የሚረጋገጥበት፣ የመንግስት አካላት ለህዝብ ተጠያቂ የሚሆኑበት፣ ነጻ ሚዲያ ለመልካም አስተዳደር ግንባታ የሚያገለግልበት፣ ፍትህ ለሁሉም በእኩል የሚሰጥበት፣ ዜጎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክልሎች የመኖር፣ ሀብት የማፍራት፣ ቤተሰብ የመመስረት፤ ከቦታ ወደ ቦታ ያለምንም ገደብ የሚንቀሳቀሱበት መብት እንዲኖራቸው፣ እና የሃይማኖት ነጻነት ይኖረን ዘንድ የድርጅቱ ጉባኤተኞች ሙሉ መሰዋእት ለመክፈል ዝግጁዎች ነን ሲሉ በድጋሚ ቃል በመግባት መራራ የሆነውን ትግል እጅ ለእጅ ተያይዞ ተራራውን ለመውጣት እና ለማቋረጥ ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።

ከ4ኛ ጉባኤ ጋር በተያያዘ ጉባኤተኛው የግንቦት 7ን 5ኛ አመት ምስረታ ታሪካዊ ቀን አስቦ ውሏል። በዚህ በግንቦት 7, 1997 ቀን የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ተሳትፎ ፍትህ፣ ነጻነትና ዲሞክራሲ በሀገሪቱ ይሰፍን ዘንድ ለዘመናት ተጭኖት የነበረውን ጫና ተቋቁሞ የወያኔን ስርአት በድምጹ የጣለበት ልዩ ቀን ነበር። ግንቦት 7, ሁሌም በታሪክ የሚዘከር ልዩ እለት ነው።

ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያዊ ትውልድ በግንቦት 7 ያሳየውን ልበሙሉነት፣ ጀግንነት፣ መሰዋእትነት፣ አንድነትና ወንድማማችነት ለዘለአለም ሲታወስ ይኖራል። ይህንኑ በ97 የተጀመረው የትግል ፍሬ፤ ውጤት ያፈራ ዘንድ አስፈላጊ ያላቸውን ትግሎችን እያደረገ እንደሆነ ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነት፣ የዲሞክራሲ ንቅናቄ 5ኛ አመቱን ከአባላቱ ጋር ሆኖ ሲዘክር ተወያይቷል። ይህም ታሪካዊ የህዝብ ድል ቀን፤ በጠመንጃ ሃይል የነጠቀውን ወያኔን ለማስወገድ እና የህዝብን ድምጽ ለማስመለስ ድርጅታችን ማናቸውንም መንገድ በመጠቀም የሚያደርገውን የትግል ጅማሮ ግብ ለመምታት አሁን ከአለንበት በተሻለ በመጠናከር መሆኑንም ስምምነት ተደርሷል። ድርጅታችን ካለፈው ጉባኤ ጀምሮ ድርጅቱ ያደረገውን እንቅስቃሴ በስፋት ገምግሞ፤ በስራ ሂደት የታዩ ድክመቶችን አፍረጥርጦ ተወያይቶ፤ የታዩትን ጠንካራ ጎኖች ይበልጥ የሚጎለብቱበትን ሁኔታ ተመልክቶ፤ በድርጅቱ የእስትራቴጂ አካሄድ ላይ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን አድርጎ፤ እነኝህን የእስትራቴጂ አቅጣጫዎች በተቀላጠፈ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ወሳኝ የመዋቅር ለውጦችን አጽድቆና ይህን አዲስ መዋቅር የሚያስፈጽሙ ያመራር አባላትን መርጦ፤ በከፍተኛ የጓዳዊ መንፈስና ልዩ በሆነ የትግል ወኔ ጉባኤውን በድል አጠናቋል::

በመሆኑም ግንቦት 7፣ በግንቦት 7 የገባውን ቃል ኪዳን ዛሬም ህያው መሆኑን ሲያረጋግጥና ትግሉ ከመቼውም በበለጠ ጽናትና ቁርጠኛነት እንደሚገፋበት ቃል ሲገባ፣ የሀገራችን ህዝብ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ; አዛውንት፣ ወጣት፣ ጾታ፣ ሃይማኖት፣ ዘር ቀለም ሳይለያችሁ በግንቦት 7/ 1997 የተሰረቀውን፣ የተነጠቅነውን የህዝብ መንበረ-ድምጽ ስልጣን ወደ ትክክለኛ ባለቤቱ እንዲመለስ የምናደረግውን የትግል ጉዞ ትቀላቀሉ ዘንድ ጥሪያችን ይድረሳችሁ!

የሀገራችን ወጣቶች ሆይ፡ ለነጻነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ቱርፋቶች መሰዋእት ሆናችሁ መሰዋእትነታችሁ በጥቁር ህዝብ የኢትዮጵያ ታሪክ ገድል ውስጥ ለዘላለም ተከትቦ ይቀመጥ ዘንድ ኢትዮጵያዊ የሞራል ግዴታ አለባችሁ፡፡ ግንቦት 7 ትግሉን ጀምሯል። ኑ ተቀላቀሉ!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

posted by  Tseday Getachew

 

መኢአድ አንድነት ከሰማያዊ ጎን ቆሙ – ግርማ ካሳ

ዜጎች ሃሳባቸዉን በነጻነት የመግለጽ፣ የመሰባሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ሙሉ መብት አላቸው። ይሄንን መብት በመጠቀም አገር ቤት የሚንቀሳቀሰው የሰማያዊ ፓርቲ፣ በአፍሪካ ሕብረት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ይጠራል። ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት፣ ለባለስልጣናት ሰልፍ እንደተጠራ ማሳወቅ ብቻ ስለሚያስፈልግ፣ የፓርቲዉ አመራር አባላት ማስታወቂያ ለማስገባት ወደ አዲስ አበባ አስተዳደር ይሄዳሉ። የአስተዳደሩ ሃላፊዎች ግን ሊያናግሯቸውም ሆነ ማስታወቂያዉን ሊቀበሏቸው ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀረ። ተደጋግሞ ሙከራ ቢደረግም፣ በሕጉ መሰረት የሰማያዊ ፓርቲን ማስታወቂያ ተቀብለው፣  አስፈላጊዉን ትብብር ማድረግ የነበረባቸው የኩማ ደመቅሳ ሰራተኞች ግን ዜጎችን ማንገላታት መረጡ። Read full story in PDF.

posted by Tseday Getachew

ጎንደር ታምሷል፤ አዲስ አበባ ህዝቡ ተነሳስቷል!

EMF – በመተማ ገንዳውሃ ከተማ ግንቦት 20 ቀን 2005 ዓ. ም የእርሻ መሬታቸው የተነጠቁ በርካታ ሰዎች በተገኙበት ስብሰባ ተካሄደ፡፡ በስብሰባው የ‹ክልሉ› ም/ አስተዳደር እንደሚገኝ ቢነገርም የተገኙት የሰ/ ጎንደር አስተዳደር ሀላፊ አቶ ግዛት አብዩ ናቸው፡፡

Blue party logo

Blue party logo

ስብሰባው የእርሻ መሬታቸውን በተነጠቁት አርሶ አደሮች ጉዳይ ሲሆን ከፍተኛ ክርክር ተካሂዶ ስምምነት ያልተደረሰ ሲሆን አቶ ግዛት ‹‹ መሬቱን መልቀቅ አለባችሁ..›› ሲሉ ተሰብሳቢዎች ተቃውሞ አድርገዋል፡፡
አያይዘውም አቶ ግዛት ‹‹…እስከ አፍንጫው የታጠቀ መከላከያ ሰራዊት ነው ያለን ሜዳው ያውላችሁ….›› በማለት ዛቻ አሰምተዋል፡፡ አርሶ አደሮችም ‹‹ መሬቱን አንለቅም መከላከያ እገላለሁ ካለም ይግደለን፡፡›› በሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ከስብሰባው በኋላ የኢህአዴግ አባላትን ይዘው እስከ ምሽቱ 6፡00 በመሰብሰብ ችግር ይፈጥራሉ ባሏቸው ሰዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዶልተው ሂደዋል፡፡

በተመሳሳይ በጎንደር ከተማ የሚገኙ ባለኀብቶችና ነጋዴዎችን የቀበሌ ሹማምንት ‹‹የመለስ ራእይ›› የሚለው ‹‹መፃህፍን›› ከ2000.00- 5000.00 ብር ግዙ በማለት ከፍተኛ ጫና እየፈጠሩ መሆኑን ነጋዴዎች በምሬት ገለፁ፡፡ እያንዳንዱ ቀበሌ ‹‹መፅሀፉን›› ሽጦ ከ400.000.00- 500.000.00 ብር ገቢ እንዲያደርግ ታዟል፡፡

በሌላ መልኩ ቁጥቸው 500 የሚደርሱ ሚሊሻዎች ከደባርቅ ወረዳ በመሰብሰብ ለልዩ ስልጠና ከ21/ 09/ 2005 ዓ. ም ጀምሮ በድብ ባህር ልምምድ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ የስልጠናው ምክንያት በአካባቢው ባሉ የታጠቁ ኃይሎች ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ አበባ ላይ የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ የሰሞኑ የአገር ቤት አቢይ ዜና መሆኑ ተገልጿል። ከዚሁ ጋር የደረሰን መእክት እንዳስተላለፈው፤ የህዝባዊ ስብሰባው አጀንዳ ሀገራዊ በመሆኑ ቀደም ሲል ሁሉም ኅብረተሰብ ‹‹ተቃዋሚ የለም፣ ማን ያስተባብረን፣ ሚጠራን የለም፣…ወዘተ. ›› ጉንጭ አልፋ ወሬዎችን የሰበረ ነው፡፡ ይኸው ‹‹ና›› ተነስ ተቃውሞህን ግለጽ ተብለናል፡፡ በየጓዳው፣ በየካፌው፣ በየባንኮኒው፣ በየወረቀቱ፣ በየ…፣በየ…፣ መትመክመክ ዋጋ የለውም፡፡

ስለዚህ በዚህ ምቹ አጋጣሚ ሁላችንም ተነስተን ‹‹ሆ›› ብለን ተቃውሟችን እንግለፅ፡፡
በስብሰባው መገኘት የግድ የሰማያዊ ፓርቲ አባል መሆን አይደለም፣
ስብሰባው ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ይጋብዛል፣
ሁሉንም ተቃዋሚዎች ይጋብዛል፣
ሁሉንም እምነቶች ያካትታል፣
ከቤት ውጭ በመሆኑ በጣም አመችና ገላጭ ነው፣
መፈክር ይዞ ለመውጣት ያመቻል፣
ለረዥም ቀናት/ድል ለመጨበጥ/ ያመቻል፣
ከሁሉም በላይ ወሩ ግንቦት ነው፣
ጥንካሬ፣ ድፍረት፣ ቆራጥነት፣ ፅናት፣ ….ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡

የዘገባው መጨረሻ፤ ራሳችን ነፃ ወጥተን ሀገራችንን ነፃ እናውጣ!!!
…..ቱኒዝያ፣ ግብፅ፣ ሊብያ፣ የመኒያ፣……ኢትዮጵያ፣……” ብሏል ርእየ- ሁለንተና – አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ

http://ethioforum.org

 posted by Tseday Getachew

የአሜሪካ የህግ ባለሙያዎችና አኢጋን በኅብረት ስራ ጀመሩ!

ዓርብ የፖለቲካና የሙስሊም እስረኛ ጠበቆችን ያነጋግራሉ

aba nsmne

 

በኢትዮጵያ በግፍ የታሰሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን በተመለከተ የአሜሪካን የህግ ባለሙያዎች ማህበር (ABA – American Bar Association) ሙሉ በሙሉ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ስራ አርብ እንደሚጀምር ተገለጸ። አዲስ አበባ ካሉ የፖለቲካና የሙስሊም ወገን እስረኞች ጠበቆች ጋር የመጀመሪያ ስብሰባ አርብግንቦት 23፤2005ዓም ያደርጋሉ። አቶ ኦባንግ ሜቶ የተረሱ እስረኞች ጉዳይም እንደሚካተት ጠቅሰው በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ለታሰሩ ዜጎች ጥብቅና የቆሙ ካሉ የአዲሲቷን ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ በቀጥታ እንዲገናኙ ጥሪ አቅርበዋል።

(ABA) በሚል ስያሜ የሚታወቀውና ከተቋቋመ 135ዓመታትን ያስቆጠረው የአሜሪካ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ከ400 ሺህ በላይ የህግ ባለሙያ አባላት አሉት። ይህ በአሜሪካ ትልቅ የተባለ ማህበር በግፍ ለሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ድጋፍ ለማድረግ የወሰነው የአኢጋን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ በይፋ የድጋፍ ጥያቄ ባቀረቡ በቀናት ውስጥ ሲሆን፣ በጋራ በተከናወኑ ንግግሮችና የሰነድ ውይይቶች በወርጊዜ ውስጥ ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት እንደተቻለ ለማወቅ ተችሏል።

ከወር በፊት በተካሄደ የማህበሩ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ንግግር እንዲያደርጉላቸው በተጋበዙት መሰረት አቶ ኦባንግ ህግን እየተንተራሰ ዜጎችን በቁም እስርና በወህኒ ቤት እያሰቃየ ስላለው የኢህአዴግ አገዛዝ በስፋት ባስረዱበት ወቅት ማህበሩ እሳቸው ከሚመሩት ድርጅት ጋር በትብብር ለመስራት ፈቃዱን አሳይቶ እንደ ነበር አቶ ኦባንግ ለጎልጉል ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ኢህአዴግ ህግን ከለላ በማድረግ በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ግፍና ወንጀል፣ ለአፈና ተግባሩ ማስፈጸሚያም የጸረ ሽብርተኝነትን፣ የመያዶችን፣ ወዘተ ህጎችን በማውጣት ዜጎችን ለወህኒ ቤትና ለቁም እስር፣ ለስደት፣ ለስቃይ መዳረጉን፣ የፍትህ አካላቱን ህግን በሚያከብሩና ፍትህ በሚያስፈጽሙ ገለልተኛ አካሎች ሳይሆን ራሱ በመሠረተው ተቋም እያመረተ የሚጠቀምባቸው የፖለቲካው መሳሪያዎቹ ስለመሆናቸው፣ በመዘርዘርና ማስረጃ በማጣቀስ አቶ ኦባንግ ለጉባኤው መናገራቸውን አመልክተዋል።

ቀደም ሲል ጀምሮ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የስራ አስፈጻሚዎች የሚታወቁትም ሆነ ሚዲያው የዘነጋቸው ዜጎች ጉዳያቸው ዓለም ዓቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ በያቅጣጫው እየተደረገ ካለው የተለያየ  ጥረት በተጨማሪ ሲመክርበት የነበረው ጉዳይ እንደሆነ በመግለጽ አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ኦባንግ “ተጽዕኖ ሊፈጥሩ የሚችሉት አካላት በራሳቸው ሰዎች በቂ መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ ታላቅ ተግባር ነው። ድርጅታችን እንደ ስኬት ይቆጥረዋል። ዓርብ በዝርዝራችን ካገኘናቸው የታዋቂ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪ ጠበቆች ጋር የስካይፕ ስብሰባ ይካሄዳል። በቀጣይ አገር ቤት በመሄድ ባመቻቸው መንገድ ስራቸውን ያከናውናሉ” ብለዋል።

በአሁኑጊዜ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የሙስሊሙን ህብረተሰብ ጥያቄ በማንሳታቸው የታሰሩት ወገኖች፣ ወዘተ ጠበቆች ጋር በስካይፕ ንግግር እንደሚደረግ አቶ ኦባንግ አስታውቀዋል። እስከዛሬ ጆሮ ያልተሰጣቸው ወገኖች ጉዳይ አደባባይ ከማውጣት በተጨማሪ የጋራ ንቅናቄው ባቋቋማቸው ግብረኃይሎች አማካይነት ወደ ህግ የሚሄዱ፣ ሌሎች አብረው መስራት የሚፈልጉ አካላት የሚያቀርቧቸውን አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ጉዳዮች በአገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ክስ መስርቶ ለመሟገት ማህበሩ ዝግጁ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አስፈላጊውን የህግ ድጋፍ የሚፈልጉ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች ጥያቄያቸውን ለጋራ ንቅናቄው ማቅረብ ይችላሉ” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ማህበሩ መንግስትን የሚያማክሩ፣ የሚመክሩ፣ ፖሊሲ በማርቀቅ ስራ ላይ የተሰማሩ ታዋቂ የህግ ባለሙያዎች፣ ለዓለም ዓቀፍ ሚዲያና ኔትወርኮች ቅርበት ያላቸውና ተሰሚነታቸው የጎላ በመሆኑ እንዲህ ካሉ አካላት ጋር በጨዋነት መስራት በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ለማስተጋባት መልካም አጋጣሚ ማመቻቸት እንደሆነም አቶ ኦባንግ አመልክተዋል።

“…ኢህአዴግ በስደተኛነት ስም ደጋፊዎቹን በስርዓቱ የተገፉ በማስመሰል የሃሰት ማስረጃ እያስጨበጠ  በአሜሪካ፣ በካናዳና በተለያዩ የምዕራብ አገራት ያሰማራቸውና በተቀነባበረላቸው መረጃ የስደት መኖሪያ ፈቃድ ካገኙ በኋላ ስደተኛውን እንዲሰልሉና ለሥርዓቱ እንዲሰሩ እያደረገ መሆኑ፤ በተለያዩ አገራት በገቢር የተያዙ መረጃዎችና ዋቢ ክስተቶች መኖራቸውን የተረዳው የባለሙያዎቹ ማኅበር ጉዳዩን በጥልቀት እንደሚያየውና ያለውን ከፍተኛ የሰው ኃይል በመጠቀም ከአኢጋን ጋር እንደሚሰራ ከሌሎች ማኀበራት ጋር በመሆንም በተለይ በምዕራቡ ዓለም የተሰገሰጉትን አስመሳይ ስደተኞች ወደ ፍትህ የማምጣቱ ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ለድርጅታቸው አረጋግጠዋል” በማለት ከዚህ ቀደም ለጎልጉል ስለተናገሩት አስተያየት እንዲሰጡ አቶ ኦባንግ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

“ኢህአዴግን የሚደግፉ ዜጎችም ቢሆኑ ለጋራ ንቅናቄያችን ልጆቹ ናቸው” በማለት አስተያየታቸውን የጀመሩት አቶ ኦባንግ “ለመጀመሪያጊዜ በዚህ ጉዳይ ላይ ምስጢረኛ ለመሆን እገደዳለሁ። አንድ ነገር ለማስታወስ ያህል ግን ምዕራባውያን አሠራራቸው መጭበርበሩን ካረጋገጡ ምህረት የላቸውም። ከሰብአዊነትም አንጻር ቢሆን አገሩ መኖር ያልቻለን ዜጋ ስደት አገር ድረስ እየተከታተሉ ማሳደድ በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የለውም። በህግም አይፈቀድም። እንደዚህ ካሉት ጋር የሚተባበሩ አገሮችን ህግ ፊት በማቆም በህግ ስለፍትህ እንከራከራል” የሚል መልስ ሰጥተዋል።

ABA የሚባለው የህግ ባለሙያዎች ማህበር ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ከሁለት ሳምንት በፊት ሲያከብር ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙት አቶ ኦባንግ ሜቶ በርካታ ጉዳዮችን በማንሳት ድጋፍ ጠይቀው አዎንታዊ ምላሽ እንዳገኙ፣ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። አቶ ኦባንግ እንደሚሉት አርብ የሚደረገው ንግግር የድጋፉና አብሮ የመስራቱ ሂደት መጀመሪያ ነው። ሥራውጊዜ የሚወስድና እልህ የሚያስጨርስ መሆኑን ሁሉም እንዲያስተውለውና ፈጣን ውጤት በመጠበቅ ቶሎ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ሁሉም ዜጋ አለኝ የሚለውን መረጃ ለጋራ ንቅናቄው በመላክ ትብብሩን እንዲቀጥል ጨምረው ገልጸዋል፡፡

aba

http://www.goolgule.com/

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

posted by Tseday Getachew

ኢህአዴግ ደብሮታል!

 

575707_555196677856268_1202584028_n

ባለፈው ጊዜ ግንቦት 17 ሰማያዊ ፓርቲ በአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ አቅርቦ መነግስት እንደተለመደው ዝም ብሎ ደብዳቤ አንቀበልም በማለት አላየንም አልሰማንም ብሎ የአራዳ ሰፈር ልጆች (ባላየ ባልሰማ ሙድ) እንደሚሉት አይነት ሊያልፈው ነበር፡፡ ነገር ግን ሰማያዊዎቹ ፈቃድ አንጠይቅም ካሳወቅናችሁ ይበቃችኋል ሰልፉን ባልነው ሰዓት እና ቦታ ከማድረግ አንቦዝንም እና አስቡበት ብለው ለበላይ አቤት አሉ፡፡ ያኔም የበላዩ የኦቦ ኩማ ደመቅሳ ቢሮ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ አጉል ግርግር ከሚፈጠር መደራደር ይሻላል ብሎ ዘየደ፡፡ ተደራደረ ለግንቦት 25ም ሰልፉ እውቅና ተሰጠው፡፡ እኛም የሰማያዊን አስጨናቂነት፤ የከንቲባውንም ተጨናቂነት አደነቅን፡፡

ሳስበው ሳስበው ኢህአዴግ የዛን ጊዜ አጣብቂኝ ውስጥ ሆኖ ለሰልፉ እውቅና ከሰጠ በኋላ ደብሮታል፡፡ እንደውም ቀፈፈኝ ብሎ እውቅናውን ቢያነሳ ራሱ ደስ የሚለው ይመስለኛል፡፡ በተለያየ ማህበራዊ ድረ ገጾች ሰልፉ እንዲደነቃቀፍ ስልታዊ እንቅስቃሴ የሚያደረጉ ምልምሎችን እየተመለከትን ነው፡፡ እነዚህ ምልምሎች አንድ ጊዜ “የሰልፉ ቀን ተቀይሯል” ሲሉ ሌላ ጊዜ ደግሞ “ቦታው ተለውጧል” እያሉ የተለያዩ የሚያምታቱ መረጃዎችን እያቀበሉን ነው፡፡ እነዚህ መረጃዎች ከሚያበጁት የሚያፈርሱት ይበልጣልና መረጃ ሳሆኑ “መራጃ” ናቸው ብያቸዋለሁ፡፡ (በቅንፍም የግንበኛ ልጅ መሆን ጥቅሟ ይቺ ናትኮ በእውኑ፤ “መራጃ” ማለት ምን እንደሆነ ከእኛ ውጪ የሚያውቁ ጥቂቶች አይደሉምን… “መራጃ” ድንጋ ለመፈረካከስ የሚያገለግል አንዳች ብረት ነው)

ለማንኛውም አስከ አሁን ድረስ እንደሰማነው ሰላማዊ ሰልፉ በዕለቱ እና በሰዓቱ ይከናወናል፡፡ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎችም በሰልፉ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በዚህም ኢህአዴግ ደብሮታል፡፡ ኢህአዴግ ቀፎታል፡፡ ኢህአዴግ ሙዱ “ተከንቷል”!

http://www.abetokichaw.com/

posted by Tseday Getachew

ሊደመጥ የሚገባው እና ጥልቅ የሆነ ቃለ መጠይቅ ከአቶ አብርሃም ያየህ

ዳዊት ከበደን አውራምባ ታይምስን ለዚህ ጥልቅ ቃለ መጠይቅ ከልብ እናመሰግናለን

 

http://www.maledatimes.com/

posted by Tseday Getachew

 

ኮለኔል ጎሹ ወልዴ እና ዶር ታዬ ወ/ሰማያት ወዴት ገቡ?

https://i2.wp.com/www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2013/05/goshu-welde.jpg

ኮለኔል ጎሹ ወልዴ እና ዶር ታዬ ወ/ሰማያት ወዴት ገቡ?

ዛሬ ካልወጡሰ መቼ?        

ከሎሚ ተራ

ዝነኛውና የማይጠገበው ድምጻዊ (ዶ/ር) ጥላሁን ገሠሠ፤ ሲያንጎራጉር፤ እንዲህ ብሎ ነበር፤

“ጩኸቴን ብትሰሙኝ ፤ ይኸው አቤት አቤት እላለሁ በደል ደርሦብኝ እጮሃለሁ ብያለሁ”

ኮለኔል ጎሹ ወልዴ

እያለ ያንጎራጎረውን  እኔም አቤት አቤት የ ( የመሪ ያለህ!!! ) በዪ እኔም እጮሀለሁ። ምንም እንኳን ሰለኮነሬል ጎሹም ሆነ ሰለ ዶክተር ታዬ ታላቅ ሰራና አገር ወዳድነታቸው አገር የሚያወቀው ያደባባይ ሚሰጥር ቢሆንም  ቅሉ፤ ሰሞኑን ግን የተለያዩ የሀገርኛ ጉዳይን የሚያሳዩ ቪዲዩዎችን ሰመለከት ድንገት የኮነሬል ጎሹን ብዙዎችን ያሰደነቀና ያኮራ ሃገር አቀፍ የጥብቅና ንግግር (On the fate of Ethiopia and Eritrea’s Referendum) አየሁና  በቁጭት ምን ተብሎ፤ ማን አሰከፍቶት ይሆን ኮነሬሉ ጥግ የያዙት ? ዶክተር ታዬ ወልደሰማያትሰ ? የት ገቡ ? በማለት በቁጭት ለመጠየቅ ብዕሬን አነሳሁ።

መቼም እንዲህ ያለውን አንገብጋቢ ሃገራዊ ጥያቄ የሚጠይቁ በርካታዎች እንደሚሆኑ ባምንም ጥቂቶች ደግሞ  የ ምርጫ 97 ቱን ምሳሌ በማድረግ የሞተ ዘመድ የለውም ወይ?  ይኸ ሰው ምን ነካው የሚሉ እንደማይጠፉም አምናለሁ። መልሴ ግን የሞቱ ዘመዶች በርካቷች አሉኛ፤ ተሰፋዪ ግን አይሞትም።ተሰፋ ላንድም ሰከንድ አጥቼ አላውቅም ነው ።

እንዲህ አይነቱ ጥያቄ አገራችን የምትገኝበትን የፖሎቲካ ሂደትና ቀውሰ በሰፊው እንድንጠይቅና ከሰኸተታችንም ታርመን ይቅርም ተባብለን፤ በሃገር ጉዳይ እኔ ማን ነኝ ? ምንሰ ማድረግ ይጠበቅብኛል ? የሚለውን ጥያቄ በቅንነት በመጠየቅ አንተ ትብሰ፤ አንቺ ትብሸ በመባባል እንደገና እጅ ለእጅ ተያይዝን አገራችን እንድትገባበት ከተቆፈረላት ጥልቁ ጉድጓድ የማውጣት አገራዊ ግዴታ አለብን በዬ አምናለሁ።

ከገጠመን እና ከተጋረጠብን የፖሎቲካ ውጥንቅጥ አኳያሰ እባክህ፤ እባክሽ ያሰፈልጋል ወይ ? ብቃት ያላቸው የፖሎቲካ መሪዎችሰ እባካችሁ እሰኪባሉ መጠበቅ አለባችው ወይ ? በሚል የተለያዩ እሣት የሚተፉ እንጉርጉሮዎች ከየጎራው ሊነሱ እንደሚችሉ የሚጠበቅ ቢሆንም ከተጋረጠብን ከፍተኛ አደጋ ባሻገር ምንሰ ብናደርግ አገር ትዳን እንጂ ነው መልሴ።

ሥለዚህ  ሰለጠንካራ የፖሎቲካ አመራር ብቃታቸውና፤  ሰራቸው በርካታ አገር ወዳዶች የሚመሰክሩላቸውን ጠንካራ መሪዎች ዳግም ወደ ፈጠጠው የትግል ጎዳና እንዲመጡ የማይደረግበት ምክነያት ምንም ሊኖር አይችልም።  እነ ኮነሬል ጎሹንም እነ ዶክተር ታዬ ወ/ሰማያትንም ሌሎችም አሉ የሚባሉትን ከየ አካባቢያችን ውጡ፤ አገራችን ኢትዮጲያ ትጮሃለች፣ የመሪ የለኸ እያለችም ትጣራለች ብለን የማውጣት ሃገራዊ ግዴታ አለበን። እከሌ ከከሌ ሳንል ጩኸታችንን እናሰማና አገራችንን ተባብረን ከውድቀት እናድን።

“ይሄ – መሪ ትግሉ ይወልዳል የሚለውም ባዶ ጩኸታችን ለ 22 አመት ወልዶ አላሳየንም እና ሁላችንም ቆም ብለን እናስብ፡

የሚዲያ ክፍሎችም በሙሉ፤-  እነ ቪ. ኦ. ኤም፣ ዶቼ ቬሌም ፤ እሣትም፣ ሌሎች ሚዲያዎች ሁሉ ካሜራችሁን ወደ አራቱም ማዕዘናት አዟዙሩት ፤ምክነያታቸውንም አሰሙን እያልኩ ጩኸቴን ብትሰሙኛ እላለሁ። በቸር ይግጠመን!!

ሎሚ ተራ፦Tuesday, May-28-13

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=3754

posted by Tseday Getachew

ከሙስና ተጠርጣሪዎች እሥር በኋላ የጥቆማ ቁጥር በእጥፍ ጨመረ፤ ሕጉ ይሻሻላል ተባለ

 

ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ

አዲስ እየተዘጋጀ ባለው ረቂቅ ሕግ በዋናነት የግል ዘርፍ አካላትን በሙስና ወንጀል ተጠያቂ የሚያደርግ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። በተለይም በመቶ ሚሊዮኖች ገንዘብ የሚገመት ሀብት እያንቀሳቀሱ ያሉ፣ የሕዝብ ሀብት የሚያስተዳድሩ የግል ዘርፍ አካላት ላይ ረቂቅ ሕጉ አተኩሯል። እነዚህ አካላት በማንኛውም አግባብ ከአባላቶቻቸው ወይም ከሕዝብ የተሰበሰበ ወይም ለሕዝባዊ አገልግሎት እንዲውል የተሰበሰበ ገንዘብ፤ ንብረት ወይም ሌላ ሀብትን የሚያስተዳድሩ ወይም የሚያንቀሳቅሱ አክሲዮን ማኅበራት በማኑፋክቸሪንግ፣ በእርሻ፣ በንግድ፣ በኮንስትራክሽን፣ በትራንስፖርት፣ በፋይናንስ እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት መካከል በአክሲዮን የተቋቋሙ ባንኮች፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሐዋላ ተቋማት የሙያና የብዙሃን ማኅበራት ፌዴሬሽኖችና ኮንፌዴሬሽኖች፣ የኅብረት ሥራ ማኅበራትና ዩኒየኖች፣ ኢንዶውመንቶችና የልማት ማኅበራት (ለምሳሌ አልማ፣ ኦልማ፣ ወዘተን) ያካትታል።

ሕጉን እንደገና ለማሻሻል ያስፈለገው ሙስናን የሚፀየፍ ኅብረተሰብ እንዲፈጠር የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር፣ በዓለም አቀፍ ደረጃም፤ በግል ዘርፍ የሚፈፀም ጉቦኝነትና ምዝበራ በሙስና ወንጀል የሚያስቀጣ በመሆኑ ሲሆን፤ አዲሱ ረቂቅ ሕግም ከሲንጋፖር፣ ከስዊዲንና ከደቡብ አፍሪካ ተመሳሳይ ሕጎች በመቀመር መዘጋጀቱም ታውቋል።

በአዲሱ ሕግ መሠረት ለሕዝብ ተብሎ የተሰበሰበ ሀብት የሚያንቀሳቅሱ እና የሚያስተዳድሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና የዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በሙስና ወንጀል እንዲጠየቁ ማድረጉ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝን በሕጉ ያልተካተቱ ሲሆን፤ ሌሎች የሕዝብን ገንዘብና ሀብት የሚያስተዳድሩ ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት፣ እድር እና ተመሳሳይ ባህላዊ ወይም ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ማኅበራት አባላቱ እርስ በርስ የሚተማመኑና ለሙስና የመጋለጥ ዕድላቸው ዝቅተኛ በመሆኑ፣ በሙስናውም ቀጥተኛ ተጠቂ የሚሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጥቂቶች በመሆናቸውና ከሚያንቀሳቅሱት ሀብት አነስተኛነት የተነሳ በሙስና ተጠያቂ በማድረግ ከሚድነው ሀብት ይልቅ ተጠያቂ ለማድረግ የሚባክነው ሀብት ከፍተኛ በመሆኑ ከሕጉ ውጪ ተደርገዋል።

በአዲሱ የሙስና ወንጀል ረቂቅ ሕግ በግለሰብ ባለሀብት ወይም ባለሀብቶች የተቋቋመ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በሙስና ወንጀል አይጠየቅም።¾

በእነ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ መዝገብ ስር የተዘረዘሩት 12 ተጠርጣሪዎች ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው

–    በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ ያሉ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ዛሬ ይታያል

–    አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሔር ድብደባ ተፈፅሞብኛል አሉ

በአሸናፊ ደምሴ

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ቡድን ተጨማሪ ጊዜ በተጠየቀባቸው በእነ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ መዝገብ ስር የሚገኙ አስራሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀኑ ጊዜ ቀጠሮ ሲፀናባቸው፤ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ በሦስት የተለያዩ መዝገቦች የተዘረዘሩትን 22 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ለመመርመር ደግሞ ዛሬን ጨምሮ ሐሙስና አርብ ተለዋጭ ቀጠሮዎችን ሰጥቷል።

ችሎቱ በዕለቱ ሲሰየም ኮሚሽኑ የደረሰበትን የምርመራ ውጤት ለመስማት እንደሆነ ፍርድ ቤቱ አስታውሶ፤ ለፌዴራሉ ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ቡድን ተወካዮች ሀሳባቸውን እንዲያስረዱ ዕድል በመስጠት ጀምሯል። በችሎቱ የተገኙት የመርማሪ ቡድኑ ተወካይም ቡድኑ ያሳካቸውንና ያላሳካቸውን የምርመራ ውጤቶች በሁለት ከፍለው ለፍርድ ቤቱ አሰምተዋል። በዚህም በዘጠኝ ተጠርጣሪዎች መኖሪያ ቤት በመድረስ የኤሌክትሮኒስ መሳሪያዎችን፣ የተደበቁ ሰነዶችንና በህገወጥ መንገድ የተገኙ ገንዘቦችን (መኒ ላውንደሪ) መሰብሰቡን ጭምር ገልጿል። አክሎም የ28 ተጠርጣሪዎች ክስ መቋረጡን የሚያስረዱ ሰነዶችን፣ ስምንት በቫት ማጭበርበር ተጀምረው የተቋረጡ ክሶችን፣ ኦዲት ያልተደረጉ ሰነዶችን እና የ15 ምስክሮችን ቃል ስለመቀበሉ ካጠናቀቃቸው ውጤቶች አንኳሮቹ ናቸው ሲል አስረድቷል።

በአንፃሩ ደግሞ የኮሚሽኑ የምርመራ ቡድን አላጠናቀኳቸውምና ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ጥያቄ ያቀረበባቸው ጉዳዮች መካከል፤ ተጨማሪ የሙስና ወንጀሎች የታገዱባቸው ሰነዶች፣ የታገዱ ንብረቶችን ማጣራት፣ ከአራጣ ብድር ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ማጥራት፣ የምርመራ ስራው ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ቦታዎች የሚካሄድም ጭምር መሆኑን እና በምርመራ ቡድኑ አማካኝነት የተገኙ ሰነዶችን መርምሮ ከክስ መዝገቡ ጋር እንዲያያዙ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ ተጨማሪ 14 ቀናትን ፍርድ ቤቱ እንዲፈቅድ ጠይቀዋል።

ሰኞ ከሰዓት በኋላ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት በቀዳሚነት ጉዳያቸው በችሎቱ መሰማት የጀመረው በሁለተኛ የክስ መዝገብ ስር የተዘረዘሩት 12 ተጠርጣሪዎች ሲሆን፤ በዚህም ስር የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ ጨምሮ ሌሎችም ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች በሙስና ወንጀሉ ተሳታፊ ሆነዋል የተባሉ ቤተሰቦች በችሎት ቀርበው በጠበቆቻቸው በኩል ጉዳያቸውን አስረድተዋል።

አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች በጠበቆቻቸው በኩል ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት ጥያቄና አቤቱታ መሠረት፣ መርማሪ ቡድኑ በቂ ማስረጃዎችን ሰብስቤያለሁ ያለ መሆኑን በመጥቀስ፤ አንዳንድ ተጠርጣሪዎችም አሁን ድረስ የተጠረጠሩበትን ወንጀል ክስ አለማወቃቸውን እና በጤናና በቤተሰብ ጉዳይ ላይ ተንተርሶ የዋስትና መብታቸው እንዲከብር ጥያቄ አቅርበዋል።

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ በጠበቃቸው አማካኝነት የምርመራ ቡድኑ አገኘሁት ያለው መረጃ በቂ ሆኖ ሳለ ሁለት ህፃናት ልጆቼ በችግር ላይ ስለሚገኙ የዋስ መብቴ ተጠብቆ ከእስር ልለቀቅ ይገባል የሚል ሀሳብ አቅርበዋል።

አቶ ገብረዋህድ አክለውም፤ ሁለት ህፃናት ልጆቼ የሚንከባከባቸው በሌለበት መልኩ እንዲኖሩ ተገደዋል። ባለቤቴም ሆነች እህቷ የተመሠረተባቸው ክስ ሰነድ መደበቅ ቢሆንም ተደብቋል የተባለው ሰነድ ግን ቀድሞም በኮሚሽኑ እጅ የገባ መሆኑን በማስታወስ፤ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች በዚህ ክስ ስር መጠቃለላቸው አግባብ አይደለም ብለዋል። ይህም በመሆኑ ፍ/ቤቱ ሁለቱን የቤተሰብ አባላት በዋስ መብታቸው ተጠቅሞ እንዲያሰናብታቸው ጠይቀዋል።

በሌላም በኩል በተለይም በሁለተኛው የክስ መዝገብ ስር 5ኛ ተከሳሽ ሆነው የቀረቡት የነፃ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሔር በምርመራ ወቅት ከፍተኛ ድበደባ እንደተፈፀመባቸውና ለሁለት ጊዜያት ያክል ራሳቸውን ስተው እንደነበር በማስታወስ፤ “በእስር ቆይታዬ አገሬ ምን እንደምትመስል አውቄያለሁ” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሔር የልብ፣ የደምና የስኳር ህመምተኛ መሆናቸውን ጭምር በማስረዳት የዋስትና መብት ጠይቀዋል። በዚሁ መዝገብ 3ኛ ተጠርጣሪ ሆነው የቀረቡት አቶ ጥሩነህ ባልቻ በበኩላቸው ሕገመንግስቱንና ሰብዓዊ መብትን በሚቃረን መልኩ በዱላ የታገዘ ምርመራ ተፈፅሞብኛል ሲሉ ቅሬታቸውን ለፍርድ ቤቱ አሰምተዋል።

በመዝገቡ ስር ሁለተኛ ተጠርጣሪ ሆነው የቀረቡት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣና ዋና ኦዲተር አቶ በላቸው በየነ፤ በጠበቃቸው አማካኝነት በቂ ማስረጃና ኤግዚቢት ይዘናል፤ ሠነድ ሰብስበናል ካሉ በኋላ የደንበኛዬን የዋስትና መብት በመገደብ ተጨማሪ የ14 ቀናት ቀጠሮ ሊጠይቅ አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል። ለ27 ዓመታት በመንግስት መስሪያ ቤት ማገልገላቸውን ያስረዱት ተጠርጣሪው፤ እኔ የምተዳደረው በወርሐዊ ደመወዜ ነው ሲሉ በእርሳቸው መታሰር ምክንያት ቤተሰባቸው ችግር እንደገጠመው በመጥቀስ ፍርድ ቤቱን የዋስትና መብት ይከበርልኝ ሲሉ ጠይቀዋል።

በድምሩም በችሎቱ ለመርማሪ ቡድኑ ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል ፍርድ ቤቱ አፅንኦት የሰጡባቸው ሦስት አበይት ጉዳዮች ሲኖሩ፤ ይኸውም ቡድኑ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜን ሲጠይቅ ምንን እንደሚጠይቅ ቢታወቅም ማንን እንደሚጠይቅ በግልፅ አለመቀመጡን፣ የሚሰሙት ምስክሮች በማን ላይ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ስለመሆናቸውና የትኛው ተከሳሽ በየትኛው ክስ ስር ተጠያቂ እንደሆነ በግልፅ አለመስፈሩ ተጠቁሟል።

የምርመራ ቡድኑ ተወካዮች በበኩላቸው ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዱ፤ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የተጠየቀው ወንጀሉ እጅግ ውስብስብና ሰንሰለታማ መሆኑን በመጥቀስ፤ ተጠርጣሪዎቹ ባለስልጣናትና ባለሃብቶች ከመሆናቸው አንፃር ከእስር በዋስ ቢለቀቁ ማስረጃዎችን ከማጥፋትም በላይ ምስክሮችን ሊያሸማቅቁ አሊያም ሊያግባቡ የሚችሉ ናቸው ሲል አስረድቷል።

በምርመራ ሂደት ውስጥ ተፈፅሟል ለተባለው ሕገ-መንግስቱን የጣሰ የሰብዓዊ መብት ችግር አስመልክቶ በሰጡት ምላሽ፣ ጉዳዩ ለፍርድ ቤት ሲደርስ ተጠርጣሪዎቹ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ነገር ግን እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ችግሮች ካሉ እናርማለን የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የህክምናና የቤተሰብ ጉዳዮችን አስመልክቶ ለተነሱት ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡም፤ ታማሚዎች ካሉ ማረሚያ ቤቱ የራሱ የሆነ ክሊኒክ መኖሩን በመጥቀስ ከክሊኒኩ በላይ ለሆኑ ህመሞች በሪፈራል ደረጃና ከዚያም በላይ ለማሳከም የሚያስችል አቅም መኖሩን ጠቅሰዋል። ቤተሰብን በተመለከተ በተለይም 1ኛ ተጠርጣሪ በሰጡት አስተያየት ላይ ተመርኩዘው ሲያስረዱ ከቤተሰቡ የተገኘው ሰነድ እንዳለ ሆኖ መርማሪ ቡድኑ የሚፈልጋቸው ሌሎች ሰነዶችም ስለመኖራቸው በመግለፅ ተጠርጣሪዎቹ በዋስ መብት ከእስር ቢለቀቁ አስቸጋሪ ይሆንብናል ብለዋል።

በጥቅሉም ለተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት መስጠትን በሚመለከት በወንጀለኛ ሕጉ ላይ፤ የተፈፀመው ወንጀል በሀገር ሀብት ላይ ከሆነና ከ10 ዓመት በላይ ሊያስቀጣ የሚችል መሆኑ ከግምት ከገባ ዋስትና እንደማይሰጥ ይደነግጋል ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ችሎቱም፤ ተከሳሾቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል ከባድና ውስብስብ መሆኑን በመጠቆም የዋስትና መብታቸውን ውድቅ አድርጐ ለመርማሪ ቡድኑ ተጨማሪ የ14 ቀናትን የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል። አያይዞም በሰጠው ትዕዛዝ፤ የተጠርጣሪዎችን ሰብዓዊ መብት በሚመለከት ጥንቃቄ መደረግ እንደሚገባው አሳስቦ የምርመራ ሂደቱም ግልፅ ይሁን ሲል ትዕዛዝ በመስጠት ለሰኔ 3 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በተያያዘ ዜና በሙስና ወንጀል የተጠርጣሪዎቹን ቁጥር ወደ 54፤ የክስ መዝገቡን ደግሞ ወደ ሰባት ያደረሰው የእነመልካሙ እንድርያስ ጉዳይ በመርማሪ ቡድኑ የተጨማሪ ቀነ ቀጠሮ በመጠየቁ ለግንቦት 23 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል። በዚህ መዝገብ የተዘረዘሩት ግለሰቦች መልካሙ እንድርያስ የናዝሬት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ሰራተኛ፣ ወ/ሮ አልማዝ ከበደ የባሕር ትራንዚት ስራ አስኪያጅ፣ አቶ ዳዊት መኮንን ደላላ እና አቶ ዳዊት አብተው ሠራተኛ ናቸው። እነዚህ ግለሰቦች የተጠረጠሩት ከትራንዚት ድርጅቶች ጋር በመመሳጠር እቃዎች የጉምሩክን ስርዓት ባልጠበቀ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግና ያልተገባ ሀብትን ማካበት በሚሉ ወንጀሎች ነው።¾

ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ የረቡዕ ሚርይ 29 ዕትም አዲስ አበባ

http://www.zehabesha.com/amharic/

 posted by Tseday Getachew

ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ በሚጠራው ሰልፍ ላይ 100ሺህ ሰው ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል

 

በመስከረም አያሌው

የፊታችን ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም በሚካሄደው እና ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፁት፤ ፓርቲው ባለፈው ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያራዝም መንግስት በጠየቀው መሰረት የፊታችን እሁድ ያካሂዳል። መንግስት በፀጥታ እና ሰላም ማስከበር ሂደት ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥመው ሰልፉን ለሌላ ጊዜ እንዲዛወር መጠየቅ ይችላል የሚል ህግ በመኖሩ ሰልፉ ከአንድ ሳምንት በኋላ እንዲደረግ መወሰኑን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

ሰላማዊ ሰልፉን በአፍሪካ ህብረት በዓል ወቅት ማካሄድ የተፈለገው ኢትዮጵያ በአሉን ስለምታዘጋጅ እና መንግስት ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራው ስራ በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብና ሚዲያው እንዲሁም አለም አቀፍ ሚዲያዎች ስለሚሰሙት ጥያቄው ከፍ ብሎ ይሰማል ከሚል አስተሳሰብ መሆኑን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፤ የሰላማዊ ሰልፉ ቀን መራዘም ምንም የተለየ ነገር እንደማይፈጥር ገልፀዋል። “የችግሩ ባለቤትም ሆነ መፍትሔ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። የሚጨቁነንም መንግስት እዚህ ነው ያለው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ ሰልፉ በታሰበለት ቀን ቢካሄድ ጥሩ እንደነበር ገልፀው ቀኑ መቀየሩም ያን ያህል ለውጥ እንደሌለው ተናግረዋል።

የሰላማዊ ሰልፉ በመራዘሙ በፊት ይሳተፋል ተብሎ ከታሰበው በላይ ሰው ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ሰላማዊ ሰልፉን በህጉ መሰረት ማስፈቀዱ እና ህዝቡም ጊዜ ወስዶ እንዲወያይበት በመደረጉ ከ100ሺ በላይ ሰዎች በሰልፉ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሰልፉ የሚነሱት አራት ጥያቄዎች በመሆናቸው ህዝቡ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እና የተነሱ ጥያቄዎችን የተመለከተ ብቻ እንዲሆንም ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል። በሰላማዊ ሰልፉ ወቅትም የታሰሩ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ፣ የእስልምናን እምነት ነፃነት በመጠየቃቸው የታሰሩት የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ፣ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደሚኖሩበት አካባቢ በሰላም ተመልሰው ካሳ እና ድጎማ ተደርጎላቸው ህይወታቸውን እንዲቀጥሉ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ እና በስራ አጥነት እና በሙስና ላይ መንግስት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲፈልግ የሚሉ ጥያቄዎችን አንግበው ሰላማዊ ሰልፉን እንደሚያካሂዱም ተገልጿል።

ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፉ መነሻውን ግንፍሌ አካባቢ ከሚገኘው የፓርቲው ጽ/ቤት በማድረግ በአራት ኪሎ፣ ፒያሳ እና ቸርቸል ጎዳና አልፎ እስከ ድላችን አደባባይ ወይም ኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት አደባባይ የሚደረግ ሲሆን፤ በእለቱም አጠቃላይ የሀገሪቱን ሁኔታ የሚገልፁ ንግግሮች እና መፈክሮች ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።¾

(ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የረቡዕ ሜይ 29 ዕትም)

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=3746

posted by Tseday Getachew

የሻብዕያው ተላላኪ ተስፋዬ ገ/አብ « ኤርትራዊ ነኝ» ሲል አስመራ ለሚታተም መፅሄት የሰጠው መረጃ ይኸው።

 

ተስፋየ ገብረዕባብ ማነው ?? ለሚለው ባጭሩ እኔ ኤርትራዊ ብሆንም በኢትዮጵያዊነቴ ነው የማምነው እያለ የሚያምታታ የሻቢያ ትግሬ ነው [ ኤርትራውያኖች ራሳቸውን ትግርኛ ነን ብለው የጠራሉ ]።
ኤርትራ ነጻነቷን [ባርነት ??] መርጣ ዛሬ በችግር ማቅ ውስጥ ስላለች ሀገር አንድ ዜጋ ለምን መጻፍ አስፈለገኝ ?? ነገሩ እንዲህ ነው ይህ ሰው ኤርትራዊም ቢሆን ዛሬ የሚይዙት የሚጨብጡት ያጡ የሃገራችን ፖለቲከኞች [ግራ ዘመም ?? ]እንደ አማካሪ አድርገው ይዘውት በኤርትራ በኩል ታጥቃችሑ ነጻ ትወጣላችሑ የሚል አሉቧልታ ሲደሰኩርላቸው የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ይሉ ዘንድ “ይህን ሃሳብ ተስፋየ ገብረዕባብ አመጣልን” እያሉ እምቧ ዘራፍ የሚሉ አልጠፉም ። በሌላ በኩል ደግሞ ተስፋየ እንዲህ አለ እየተባለ ሜድያ ተሰቶት ዛሬ በየድረገጹ ሲጨበጨብለት እናያል ።
ግን ይሄ ሰው የሚጨበጨብለት ነው ወይ ?? እስኪ ከጻፋቸው ጽሁፎች አንድ አንድ ነገር እንይ ….
ተስፋየ የቡርቃ ዝምት ብሎ በኦሮምኛ በጻፈው መጽሃፍ እንዲህ ይለናል

“ቡርቃ ሲገኣ የሮን ጌሴ ጂራ ቡርቃ፤
ዋቀዮ መራንፍራ ዲኒ ኬኛ አርባ ጉጉ ጂራ፤
አማሪ ቡርቃ ጂራ ቆንጨራ ካስኔ ጪራ”።

ይህ ከላይ ያሰፈርኩት የተስፋዬ ገብረአብ ጽሁፍ ወደ አማርኛ ሲተረጎም የሚከተልውን መልእክት ያስተላልፋል።

“ጊዜው ደርሶአል ቡርቃ በቃህ
ጠላታችን አርባ ጉጉ ላይ ነው ያለው
አማራ ቡርቃ ነው ያለው
ቆንጮራ አንስተን እንቆራርጠዋለን”።

የቡርቃ ዝምታ ማለት ምን ማለት ነው ?? ብሎ አንድ ሰው ይጠይቅ ይሆናል ተስፋየ እንዲህ ይለናል “ምንሊክ አርሲን ሲወርና የገዳውን ስርዐት ሲያጠፋው ግን የቡርቃ ወንዞች በኦሮሞወች ተንበርካኪነት አዝኖና አፍሮ መሬታችሑን በጃችሑ ካላገባችሑ እኔንም አታዩኝም ብሎ አካላቱን ሁሉ እንደዘንዶ ስቦ ከመሬት ቀበረ” ይለናል እንግዲህ ቡርቃ የሚባለው ወንዝ አኩርፎ አልታያችሑም አላቸው ነው የሚለን ።
በመሰረቱ ተስፋየ ይሄን ነገር ሰርቢያወች ህዝባቸውን በኮሶቮ ላይ አነሳስተው ለዛ ሁሉ እልቂት ከዳረጋቸው የተኮረጀ ሲሆን ልዩነቱ ተስፋየ ሰርቢያወች አበቦች አኮረፉ የሚለዉን ወንዝ አኮረፈ ማለቱ ብቻ ነው ። በዚህ ጉዳይ ላይ ዶክተር አሰፋ ነጋሽ የስነልቦና ሙህር ከሙያቸው አኳያ የሰጡትን ገለጻ እዚህ ሊንክ ላይ ያዳምጡ [Dr. Assefa Negash Part 7 Of 17 on Youtubehttp://www.facebook.com/l.php?u=http%3A%2F%2Fwww.youtube.com%2Fwatch%3Fv%3DSlBFP5qjRKc&h=MAQEeg2I7&s=1

በምን አይነት መለኪያ ነው በምን አይነት ፖለቲካ ነው ይህን ሰውየ በጭፍን አትጥላው የምባለው ። እኔ ተዉት ሰው መሆንን !! እንደ አንድ አማራ ይሄን ሰው ልውደደው ብል አልችልም ።
ይህን ሰው “ሌሎች የጻፋቸው መጽሃፎች ላይ ስለ ወያኔ ጽፎልናል ለዛም ነው የምንደግፈው ” ይሉናል ከወያኔ ያልተናነሰ ያማራ ጥላቻ ያላቸው ግለሰቦች ። ወያኔን ተስፋየ ሳይሆን የሚያሳውቀኝ ወያኔ በገባ ሁለት አመት እስከሚሆነው ድረስ ምን ምን አደረገ የሚሉትን ነገሮች ልብ ብየ ካየሁ የበቂየ ነው ። ልብ ላለው ሰው ጉዳዩ ያገባኛል ላለ ሰው የተስፋየ ልብ ወለድ መጽሃፍ ሳይሆን ወያኔ በተግባር ያሳየን ስለወያኔ ምንነት ይነግረናል ። ባማርኛ በጻፈው መጽሃፉ ላይ እንዲህ ይለናል …
“መሬታችን ጥቁር ቅቤ ነው ። ምንሊክ የሚባለው ስግብግብ ሲያየው ጎመዠ እኛን ማክበር አቃተው ። እንደፈረስ ልጋልባችሑ አለን አሻፈረን አልነው በመሳርያ ብቃት ተማምኖ ጨፈጨፈን ። የሴቶችንም ጡት ጥሬ ስጋ እንደሚበላ ሰው እየተስገበገቡ ቆረጡት የሰቶቻችን ጡት እኛ ከበግ ላይ ጸጉር እንደምንሸልተው እንዲያ ነበር የሚቆርጡት እነኝህ ሰወች በግ ሲያርዱ በስመዐብ ብለው ይጀምራሉ የሴቶችን ጡት ሲቆርጡ ግን በስመ አብ አይሉም ግን ሃይማኖት አለን ይላሉ … “።

ይህን መጽሃፍ ዶክተር ነጋሱ ጊዳዳና ሎሬት ጸጋየ ገብረመድህን ያወገዙት ሲሆን ሎሬት ጸጋየ እንዲህ ብለዋል “ይህ መጽሃፍና ጽሃፊው ከኢትዮጵያ መወገድ አለባቸው” ነበር ያሉት ።

ጀግኖች ኢትዮጵያ ነጻ ስትወጣ ተስፋየን ኢትዮጵያ ውስጥ ባገኘነው ይላሉ ። ወራዳ ከንቱወች ደግሞ ኧረ እሱ ቢጠላን ጥላቻ መልስ አይሆንም ይላሉ ።
ከጀግኖቹ ወይም ከወራዶቹ ጎራ ለመሆን የዕያንዳንዱ ሰው ምርጫ ነው ።
በተስፋየ ገብረዕባብ የሚመሩ ከንቱወች [ ሃሳብ የሚወስዱ ] ኢትዮጵያን ነጻ ከማውታታቸው በፊት ለራሳቸው ነጻ ይውጡ ።
አመሰግናለሁ ።

እየሩሳሌም አራያ

All Amhara መላው አማራ

posted by Tseday Getachew

! …. ትንሽ ስለ ዳንኤል ብርሃነ …! – ኣብርሃ ደስታ

abc
ዳንኤል (Daniel Berhane) የፌስቡክ ጓደኛዬ ነው። የኢህኣዴግ መንግስት ደግፈው ከሚፅፉ ሰዎች የተሻለ መከራከርያ ሓሳብ ማንሳት የሚችል ነው። ሞያው ራሱ እንደነገረን ጋዜጠኛ ነው። ከኢህኣዴግ ባለስልጣናት በቅርብ እንደሚገኝ (የአብዛኞቹ የግል ስልክ ቁጥር እንዳለው) እገሌ ጋ ደውዬ ነበር፣ እገሌ ስልኩ አያነሳም … ገለመሌ እያለ ከሚፅፋቸው ነገሮች መረዳት ይቻላል።
 
የሆነ ሁኖ ጥረቱ የሚመሰገን ነው።
 
እኔ ስለ ዳንኤል የሰማሁት የደህንነት (የሳይበር ሰላይ) መሆኑ፣ በበረከት ስምኦን ፍቃድ የተሰጠውና ድጋፍ የሚደረግለት (ስራው የግል ጋዜጠኝነት ሁኖ ወይ በማስመሰል የመንግስት አፈ ቀላጤ ተደርጎ ደመወዙ ከመንግስት ካዝና እንደሚከፈለው)ና ኢህኣዴጎች እንደሚተማመኑበት ነበር። ይህን መረጃ ግን እስካሁን አላመንኩትም ነበር (ደሞ አመንኩ አላመንኩ ምን ያደርግልኛል? እንደማንኛውም ዜጋ ሓሳቡ በነፃነት የመግለፅ መብት አለው’ኮ)። በዚህም ስለ ማንነቱ ጉዳዬን አላደርገውም።
እስቲ ዛሬ ስለ ሰው እናውራ። (ጓደኞቼ ሰለ ‘አንድ ግለሰብ’ ማውራት ትክክል አይደለም እንደምትሉኝ አልጠራጠርም። የሰውየው ማንነት ማወቅ ግን ለብዙ ሰዎች ደህንነት ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም ሰውዬው በትክክል የኢህኣዴግ የስለያ አባል ከሆነ ዳንኤል አንድ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን ‘ተቋም’ ነው ማለት ነው።)
በዛሬው ቀን በፌስቡክ ዎሉ ተለጥፎ ያየሁት (በአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ለመሳተፍ የሚያስችለው ባች) ዳንኤል የኢህኣዴግ የደህንነት (ወይ ስለያ) ባልደርባ እንደሆነ የሚጠቁም ነገር አለ (ወይስ ማንኛውም ጋዜጠኛ ወደ የመሪዎች ስብሰባ ሲጋበዝ ፍቃድ የሚሰጠው በደህንነት ቢሮ በኩል ነው? መረጃ የለኝም። ስለዚህ እንድታስረዱኝ በትህትና ልጠይቅ።)
ስለዚ ዳንኤል (እንደ ጓደኛ) በጋዜጠኛ ወይስ በሰላይ እንወቅ ህ? (መቼም ቅር እንደማይልህ ተስፋ አደርጋለሁ፣ ምክንያቱም ጥያቄው አስፈላጊ ባይሆንም ሰው ስለ ጓደኛው ስራና ማንነት ለማወቅ ቢጠይቅ ነውር አይደለም።)
ወባና ሰላዮችን በጋራ እንከላከል።

 It is so!!!

posted by Tseday Getachew

“ኢትዮጵያ የሻለቃ ጉዊንን የወሰን መሥመር ተቀብላ አታውቅም፤ ልትቀበልም አይገባትም” – አቶ አገኘሁ መኮንን (የታሪክ ባለሙያ)

ኢትዮጵያ ዛሬ የያዘችውን ቅርጿንና ስፋቷን ከመያዟ በፊት ጥንታዊ ግዛቷ እንደ ንጉሥ ኢዛናና ካሌብን የመሳሰሉ ጠንካራ ነግሥታት በነበሯት ጊዜ የት ድረስ ይደርስ እንደነበረና ደካማ
መሪዎች በነበሯት ጊዜ ደግሞ ምን ያህል ይሸበሸብ እንደነበር በማስረጃ አስደግፈው በማቅረብ የንግግራቸው መንደርደሪያ አደርገውታል። በማከልም ግብጽ ዘላለማዊ ህልሟን ማለትም አባይን ከምንጩና ቤኒ ሻንጉል አካባቢ አለ የሚባለውን የወርቅ ማዕድን ለመቆጠጠር ስትል ታደርግ በነበረው ተደጋጋሚ ሙከራና በኋላም በድርቡሾች የበቀል ወረራ የሰሜንና የሰሜን ምዕራቡ ድንበራችን ምን ያህል በተደጋጋሚ ይታወክ እንደነበር አብራርተዋል።

Read more: http://www.ethiomedia.com/abc_text/ethiopia_never_accepted_gwynn_demarcation.pdf

(ከኢትዮሚድያ ዝግጅት ክፍል)

posted by Tseday Getachew

ሙስናን የተመለከተው የፍርድ ቤት ውሎ

የኢትዮጵያ ፌዴራል የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በሙስና ጠርጥሮ ከሁለት ሣምንታት ገደማ በፊት ያሰራቸው የግምሩክ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የባለሀብቶች የምርመራ የጊዜ

ገደብ ጉዳይ ዛሬ እንደገና በፍርድ ቤት ሲደመጥ ዋለ። ስለፍርድ ቤቱ ውሎ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ያነጋገርኩት ወኪላችንን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ቀጣዩን ማብራሪያ ሰጥቶዋል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC :  http://www.dw.de/popups/mediaplayer/contentId_

16840060_mediaId_16839895

DW

posted by Tseday Getachew

Hiber Radio: አማራው ተደራጅቶ ራሱን ከህወሃት ጥቃት እንዲከላከል ጥሪ ቀረበ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ  ግንቦት 18  ቀን 2005 ፕሮግራም

<<…በደቡብ አፍሪካ ፣በአንጎላ፣ በሞዛምቢክ እነዚህ ወንድሞቻችን ካሉበት የባርነት ቀንበርነጻ እስኪወጡ ድረስ መላው አፍሪካና  ኢትዮጵያዊያኖች በዓለም ሸኝጎ በዕኩልነት ድምጻቸው እንዲሰማ …የአፍሪካ አገሮች የአዲስ አበባ ጉባዔ…>>ቀዳማዊ አጼ ሀይለስላሴ እ.አ.አ በ1963 ካደረጉት ንግግር የተወሰደ

<<ህወሃት ጣሊያን የሰራውን ነው በአማራ ህዝብ ላይ እያደረገ ያለው። የፋሺስቱ ጣሊያንና አሁን ያለው የህወሃት አገዛዝ ጸረ አማራ አቁዋም አንድ ነው። አማራው ራሱን ማደራጀትና ከዚህ ሊያቀጠፋው ከተነሳ ድርጅት ጥቃት መከላከል አለበት። አማራ ልደራጅ ሲል ለምን ተቃውሞ ይቀርባል?…>>

አቶ ተክሌ የሻው የሞረሽ ወገኔ ሊቀ መንበር በቬጋስ ተገኝተው ካደረጉት ንግግር የተወሰደ

<<… አማራው እየተረገጠ ለመብትህ አትደራጅ ብትለው ማን ይሰማሃል? ማርቲን ሉተርን አትደራጅ ትለዋለህ? ማህተመ ጋንዲን እንግሊዞችን አትታገል ትለው ነበር? ህወሃት ከዚህ የባሰ ነው። አማራው በፖለቲካውም ሆነ በወታደራዊ መስክ ተደራጅቶ ራሱን መከላከል አለበት። አማራ ተደራጅቼ …ልግደል ቢል ግን እንታገለዋለን። ዛሬ ዘመኑ ሰልጥኗል ሰው ልግደል ብለህ ፓርቲ ብታቋቁም ሰው አይከተልህም።ለመብት ተደራጅቶ መታገሉን ግን እደግፋለሁ…>>ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን በቬጋስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ራዕይ ማህበር የቀድሞ ሊቀመንበር ስለ አማራ መደራጀት ከተናገሩት

<<…ወ/ሮ ትግስት ከሲና በረሃ ለሽፍቶቹ ገንዘቡ ተከፍሎ ተለቃለች።ዛሬ ካይሮ ግብጽ ነች።እዚያ ያሉ ግፍ የሚፈጸምባቸው ወገኖቻችንን በተመለከተ እያንዳንዳችን ሀላፊነት አለብን…>> ወ/ሮ ሰብለ ደምሴ ከሱዳን ታፍነው ተሽጠው በሲና በረሃ ሲሰቃዩ የቆዩትን ሴት ለማስለቀቅ ዕርዳታ ማሰባሰቡን ካስተባበሩት አንዷ ለህብር እንደተናገሩት

የአፍሪካ ህብረት እና የ50 ዓመት ክብረ በዓሉ ዳሰሳ  

ሌሎች ቃለ መጠይቆችም አሉን

ዜናዎቻችን

– የግብጹ ፕሬዜዳንት ሙርሲ አዲስ አበባ ላይ በአባይ ግድብ ዙሪያ መከሩ

– አንድነት የሰኔ አንድ ሰማዕታትን በሕዝባዊ ንቅናቄ አከብራሉ አለ

– አማራው ተደራጅቶ ራሱን ከህወሃት ጥቃት እንዲከላከል ጥሪ ቀረበ

– በጉዲፌቻ መልክ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የመጣች ህጻን ልጅ በአደጋ ሞተች

– የኤርትራ ጳጳሳት ለተመድ ዋና ጸሃፊ አቤቱታ አቀረቡ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን     

AUDIOS: https://soundcloud.com/user468591803/hiber-radio-052613

http://www.zehabesha.com/ 

posted by Tseday Getachew

Post Navigation

%d bloggers like this: