Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

Archive for the month “December, 2012”

የምርጫ ቦርድ ባለስልጣን ወ/ሮ የሺ ፈቃደ የብኣዴን/ኢሕኣዴግ አባል ሲሆኑ የደብረብርሃን ተወዳዳሪ ነበሩ

የምርጫ ቦርድ ባለስልጣንወ/ሮ የሺ ፈቃደ የብኣዴን/ኢሕኣዴግ አባል ሲሆኑ የደብረብርሃን ተወዳዳሪ ነበሩ::የቦርዱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ የሺ ፈቃደ በተለያዩ ሚዲያዎች እንደ ኢሕአዴግ ሆነው ሲከራከሩዋቸው ቆይተው አሁን የኢሕአዴግ አባል የሆኑበት ማስረጃ መገኘቱን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሚስጥራዊ ያሉዋቸውን ሰነዶች ይፋ አደረጉ::

 “በወይዘሮ የሺ ላይ ግላዊ ጥላቻ ኖሮን አይደለም፡፡ ነገር ግን የኢሕአዴግ አባላት ሥራ አስፈጻሚ የሆኑበት ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ሆኖ ምርጫ ማከናወን አይችልም፤” ብለዋል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች  በኃላፊዋ ላይ ለምን እንዳተኮሩ ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፣ ማስረጃውን ይዘዋል የተባሉት የኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አቶ ወንድማገኝ ደነቀ ንግግራቸውን የጀመሩት በእጃቸው አንድ ሰነድ ከፍ አድርገው በማመልከት ነበር፡፡ በ1997 ዓ.ም. በተካሄደው አገራዊ ምርጫ “የክልል ምክር ቤት አባላት የምርጫ ጣቢያ የድምፅ ቆጠራ ውጤት መተማመኛ” በሚል የምርጫ ቦርድ ዓርማ ያለበት ሰነድ የዕጩ ተወዳዳሪዋ የወይዘሮዋ የሺ ፈቃደ ስም የሚገኝበት፣ በብአዴን ፓርቲ በንብ ምልክት ያገኙት የድምፅ ብዛትና ደረጃቸው የሰፈረበትና ለአማራ ክልል ምክር ቤት የደብረ ብርሃን ዕጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረባቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

ወይዘሮ የሺ በቀረበው ማስረጃ ላይ አስተያየት እንዲሰጡን ጠይቀናቸው፣ “ይህ ማስረጃ ለምርጫ ቦርድ አልቀረበም፡፡ የምሠራው ለቦርዱ ነው፡፡ ቦርዱ ይህ ማስረጃ ቀርቦለት ጥያቄ ሲያቀርብልኝ ብቻ ምላሽ የምሰጥበት ይሆናል፤” በማለት የቀረበው ማስረጃ እውነተኛ ነው አይደለም ሳይሉ ለጥያቄው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡

http://www.ethiosun.com

posted by Tseday Getachew

Advertisements

Over 40 killed in army infighting

(ESAT New) Dec. 30–Over 40 members of the Ethiopia’s defense forces deployed in Bore front, Afar region, were reportedly killed in deadly clashes that erupted among divided soldiers. ESAT’s defense sources said that the infighting started Tuesday night in a place called Ali Funi, Manda.

According to the well-informed sources, the infighting between the two factions continued until Wednesday. So many residents of Manda who mistook the infighting for a resumption of fighting between Ethiopia and Eritrea fled their homes. Eyewitnesses told ESAT that senior military officials flew to the area in helicopters tried to stop the infighting.

Information obtained from Manda hospital indicated that over 40 soldiers were killed and 39 others were injured during the fighting. Some of the seriously injured soldiers and officers were transported to Mekele for treatment, it was learned.

The cause of the fighting between the two factions is still not clear. But some allege that the fighting started between divided TPLF military officers while others are say that the infighting was between domineering TPLF members and other Ethiopians in the army who feel being discriminated against.

The Bure front is under the command of Saere Mekonnen, the Commander of the Northern Front Command.. Tension is still high in the area despite efforts to defuse the explosive situation, ESAT sources said.

 

posted by Tseday Getachew

ሰበር ዜና `ከአሜሪካን የሚመጣው ሲኖዶስ መፈንቅለ መንግስት ሊያደርግ እንጂ ቤተክርስቲያን ሊመራ አይደለም!!` በረከት ስምኦን

ሰበር ዜና`ከአሜሪካን የሚመጣው ሲኖዶስ መፈንቅለ መንግስት ሊያደርግ እንጂ ቤተክርስቲያን ሊመራ አይደለም!!` በረከት ስምኦን

የወያኔው የህዝብ ግንኙነት ሰው ወይም ራሳቸዉን ምኒስትር ብለው የሚያስጠሩት አቶ በረከት ስምኦን ዛሬ ማምሻውን የኦርቶዶክስ ቤ/ክ አስመልክቶ ከወዳጆቻቸው ጋር ባደረጉት ዉይይት ቤተ ክርስቲያኒትዋን በመከፋፈል የጽንፈኛ ዲያስፖራዎችን ፖለቲካዊ አላማ በማንገብ አገር በት ከገቡ በሁዋላ ሽብር በመንዛት መንግስትን እና ህዝብን ለማጋጨት የተሸረበ ሴራ ነው ብለዋል:ሲሉ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ገለጡ::

የአሜሪካው ሲኖዶስ ነኝ የሚለው የፖለቲካ ቡድን በኢትዮጵያ ዉስት መረጋጋት እንዲኖር የሚሰራ እና ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን የተረጋጋ መንግስት ለመገልበጥ የተዘጋጀ ቡድን ነው ሲሉ ወቅሰዋል::

አቶ በረከት እንዳሉት የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው ሰላም እና ዲሞክራሲ በልማት አውህዶ ማደግ እንጂ በበርገር የጠገቡ ጳጳሳትን አይደለም ብለው ተወያይ ወዳጆቻችውን  ፈገግ አሰኝተዋል:: እንደ አቶ በረከት አባባል ለእርቀ ሰላም ከመጡት ሰዎቻቸው አንደኛው (ሃይለስላሴ አለማየሁ) ከተቃዋሚ መሪዎች ጋር በተለያየ ጊዜ በመንግስት ደህንነቶች በመታየቱ የህን ጉዳይ ከአቡነ ናትናኤል ጋር ተወያይተንበት ከምታስሩት ከሃገር እንዲወጣ አድርጉት ..አለም አቀፍ ተቃውሞው እንዳይበረታ …የሚል ነገር ስለነገሩን ከሃገር አባረነዋል ሲሉ አቶ በረከት ተንፍሰዋል:እንደ ምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች::

አቶ በረከት የሙስሊሞች እንቅስቃሴ በተመለከተ በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ መሆኑ ገልጠው አንዳንድ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ዲፕሎማቶች ይረዱዋቸዋል እንዲሁም ወደ ፖለቲካ ሽብር ለመቀየር እየለፉ ነው ሲሉ የሚለፉትን ሰዎች ሲም ከመጥከስ ተቆጥበዋል…የሚረዱትንም እንዲሁ…ዲያስፖራው ጽንፈኝነትን ለማስፋፋት እየሮጠ እንደሆን ሳያወሩ አላለፉም::

አሕባሽ የተባለዉን ነገር አንስተው የህ የሃይማኖት ሴክት /ሃራጥቃ / ነው ያሉት አቶ በረከት በህገ መንግስቱ መሰረት መስራት ይችላል ሆኖም ዘየቤው ሽብርተኛ አይደለም እንደለላው ብለዋል::
አቶ በረከት ይህን ሁላ ሲያወሩ የተቀዳላቸው ሻይ በርዶ ነበር::እንደ ምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ዘገባ::

http://www.ethiosun.com

posted by Tseday Getachew

ፓርላማው የአቶ ጁነዲን ሳዶን ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ ነው በዮሐንስ አንበርብር

 

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) በቅርቡ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸው የተነሱትን የአቶ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ መሆኑን ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡

የምክር ቤቱ አባል የሆኑ ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አቶ ጁነዲን በፓርላማ የሥነ ሥርዓት ደንብ መሠረት ሊጠየቁበት የሚችል የሕግ ጉዳይ ሊኖር ስለሚችል፣ በምክር ቤት አባልነታቸው ያገኙትን ያለመከሰስ መብት ምክር ቤቱ እንዲያነሳ የሚጠይቅ ደብዳቤ በመንግሥት ቀርቧል፡፡ ጥያቄው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ ወይም በፍትሕ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ በኩል መቅረብ ያለበት መሆኑን የምክር ቤቱ ደንብ ያዛል የሚሉት እነዚሁ ምንጮች፣ ጥያቄው በየትኛው አካል መቅረቡን ለመረዳት እንዳልቻሉ አስረድተዋል፡፡

ባለፈው ሐሙስ የዓመቱን ዘጠነኛ ስብሰባውን ያካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአምስት አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት ፕሮግራም ይዞ የነበረ ቢሆንም፣ በአራቱ ላይ ብቻ ተወያይቶ የቀረውን ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፎታል፡፡

የስምንተኛ መደበኛ ስብሰባውን ቃለ ጉባዔ፣ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅ፣ እንዲሁም ሁለት የተለያዩ ዓለም አቀፍ የብድርና የትብብር ስምምነቶችን ማፅደቅ በዕለቱ የተወያየባቸውና ውሳኔ ያሳለፈባቸው አጀንዳዎች ናቸው፡፡ በአምስተኛ አጀንዳነት ተይዞ የነበረው “የአንድ የምክር ቤት አባልን የሕግ ከለላ ስለማንሳት የቀረበ የውሳኔ ሐሳብን መርምሮ ማፅደቅ” የሚል ቢሆንም፣ የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ ይህንን አጀንዳ በቀጣይ ስብሰባ ለመመልከት ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፈውታል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት ለጉባዔው የሚቀርቡ አጀንዳዎችን ቀደም ብለው በማወቅ በጉዳዩ ላይ የሚቀርቡ ሰነዶች ካሉ ደግሞ ሰነዶቹ ከውይይቱ ሦስት ቀናት በፊት እንዲደርሳቸው የምክር ቤቱ የአሠራር ደንብ ቢደነግግም፣ የሕግ ከለላን ስለማንሳት ቀርቦ ስለነበረው አጀንዳ የቀረበላቸው ምንም ዓይነት ሰነድ እንደሌለ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

የሕግ ከለላው እንዲነሳ ጥያቄ የቀረበበት የምክር ቤት አባል ማንነት በይፋ ባይገለጽም፣ ይፋዊ ባልሆነ መንገድ የአቶ ጁነዲን ሳዶ ጉዳይ መሆኑን እንደተረዱ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

አቶ ጁነዲን ሳዶ በአሁኑ ወቅት በሽብር ተግባር ተጠርጥረው በእስር ላይ ከሚገኙት ባለቤታቸው ወ/ሮ ሐቢባ መሐመድ ጋር በተያያዘ፣ በድርጅታቸው ኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተገምግመው ከፓርቲው ከፍተኛ አመራርነት ወደ ተራ አባልነት ዝቅ መደረጋቸው ይታወሳል፡፡

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በፓርላማ በፀደቀላቸው የሚኒስትሮች ሹመት ደግሞ ከሲቪል ሚኒስትርነታቸው መነሳታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

ethiopianreporter.com

posted by Tseday Getachew

 

በሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ከአገር መባረር ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ቁጣቸውን እየገለጹ ነው

ሐራ ዘተዋሕዶ

December 29, 2012

ሊቀ ካህናት ለጉባኤው መግለጫ ይቅርታ እንዲጠይቁ ለሰዓታት ጫና ተደርጎባቸዋል
‹‹አጀንዳዬ ሃይማኖታዊ ነው፤ የሠራኹት ስሕተት ይኹን የምጠይቀው ይቅርታ የለም !!››
የሰላምና አንድነት ጉባኤው መግለጫ እንደሚያወጣ ይጠበቃል
መንግሥት በወሰደው ርምጃ የመንበረ ፕትርክና ዓላሚዎቹ ጳጳሳት እጅ እንዳለበት ታምኖበታል
ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ከብፁዓን አበው ጋር

በተወሰኑ ጳጳሳት ግፊትና በመንግሥት የደኅንነት ኀይሎች ርምጃ ትላንት ምሽት ከኢትዮጵያ ተገደው እንዲወጡ የተደረጉት ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ከጥቂት ሰዓታት በፊት አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ደርሰዋል፤ በሰላምና አንድነት ጉባኤው አባልም አቀባበል እንደተደረገላቸው ታውቋል፡፡ በሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ላይ ስለተፈጸመው ተግባር መረጃው የደረሳቸው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአሁኑ ወቅት በጉዳዩ ላይ እየመከሩበት ሲኾን ርምጃውን አነሣስተዋል፤ ግፊት አሳድረዋል በተባሉ ግለሰቦችና ጳጳሳት ላይ ጠንካራ አቋም ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል፤ጳጳሳቱን ያሳተፈውና ለመንግሥት ጣልቃ ገብነት ማረጋገጫ ተደርጎ የተወሰደው ይኸው ርምጃ የማክሰኞውን የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ እንዳያጋግለው ተፈርቷል፡፡

በቀዳሚው የዜና ዘገባችን እንዳስነበብነው÷ ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ትላንት ከሰዓት በኋላ ፒያሳ ከሚገኘው ቤታቸው ወደ ቦሌ ለስብሰባ ቀጠሮ ብለው ከወጡ በኋላ ነበር ታግተው ቆይተው በዚያው ‹‹ትኬት ተቆርጦላቸው›› ተገደው እንዲወጡ የተደረገው፡፡ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ዋነኛው ሰው የኾኑት ልኡኩ በግዳጅ እንዲወጡ ከመደረጋቸው በፊት እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ድረስ ባገቷቸው የደኅንነት ኀይሎች በተለያዩ ጥያቄዎችና ተጽዕኖዎች ሲዋከቡ እንደነበር ተገልጧል፡፡ ረቡዕ ዕለት አዲስ አበባ በደረሱበት ወቅትም ሊቀ ካህናትና አብረዋቸው የነበሩት ሌላው ልኡክ በልዩ ክፍል እንዲገቡ ተደርጎ ጥብቅ ፍተሻ እንደተካሄደባቸው ታውቋል፡፡

ሊቀ ካህናት በደኅንነት ኀይሎች ቁጥጥር ሥር በቆዩባቸው ሰዓታት የሰላምና አንድነት ጉባኤው ታኅሣሥ 12 ቀን 2005 ዓ.ም ላወጣው ‹‹በዘለፋ የተሞላ፣ የቅዱስ ሲኖዶስን ሉዓላዊነት የተዳፈረ፣ የአስታራቂነትን መርሕ የጣሰ ነው›› ለተባለው መግለጫ ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠይቁ ከፍተኛ ጫና ተደርጎባቸው እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ ቅ/ሲኖዶሱ የዕርቀ ሰላም ልኡካኑን ማሳሰቢያ ችላ ብሎ አስመራጭ ኮሚቴ በመሠየሙ ሳቢያ በዳላሱ የሰላም ጉባኤ የተደረሰበትን ስምምነት ለማስከበርና የዕርቀ ሰላም ሂደቱን ከዕንቅፋት ለመጠበቅ የወጣ ነው የተባለውን መግለጫ እንደሚያምኑበት በማስረገጥ በአቋማቸው የጸኑት ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ÷ ‹‹አጀንዳዬ ሃይማኖታዊ ነው፤ የሠራኹት ስሕተት ይኹን የምጠይቀው ይቅርታ የለም፤ ያሻችኹን ርምጃ መውሰድ ትችላላችኹ!!›› ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

‹‹በዕርቀ ሰላም ስም የፓትርያሪክ ምርጫውን ጊዜ በማራዘም የፖሊቲካ ዓላማን የማራመድ፣ ብጥብጥ የመፍጠር የተቃውሞ ኀይሎች አጀንዳ አለ፤›› ብሎ የሚያምነው መንግሥት ‹‹ዕርቀ ሰላሙን እደግፋለኹ›› ቢልም ምርጫውን አስቀድሞ በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ የዕርቅና ሰላም ሂደቱ በተጓዳኝ ወይም ከምርጫው በኋላ ሊካሄድ እንደሚችል አቋም መያዙ ይነገራል፡፡ በመንግሥት እምነት ‹‹ዕርቁ ይቅደም›› የሚሉ ወገኖች ‹‹የሥልጣን ተሻሚዎችና ጥቅመኞች››እንጂ የሰላምና አንድነት ወዳዶች አይደሉም፡፡ ይህን የመንግሥት አቋም የተቀበሉና በዚህ አቋም ሥር ተግነው የመንግሥትን አካላት የሚገፋፉ ግለሰቦችና በመንበሩ ለመቀመጥ የሚያልሙ ጳጳሳት በሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ላይ ለተወሰደው ርምጃ የበኩላቸውን ሚና መጫወታቸው ነው የተገለጸው፡፡

ከመንግሥት ጋራ ያላቸውን የጠበቀ ትስስር በመጠቀም ለርምጃው ግንባር ቀደም ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ሁለት ጳጳሳት በዋናነት የተቀሩት ሦስቱ በደጋፊነት ተጠቅሰው ስማቸው የደረሰን ቢኾንም ለጊዜው ከመግለጽ ተቆጥበናል፡፡ ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ከአገር እንዲወጡ ከመደረጉ በፊት በሰላም ልኡክነታቸው ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ እንዳይገቡ የተላለፈባቸው እገዳ በቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ይኹን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ እንደማይታወቅ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ዕርቀ ሰላሙን በሚመለከት የሚታየው ተጽዕኖ ዙሪያ መለስ ነው፡፡ የቅ/ሲኖዶሱ የዕርቀ ሰላም ልኡካን በብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ ተወክለው የአስመራጭ ኮሚቴውን መቋቋም በመቃወም በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ መግለጫ መስጠታቸው ለማስጠንቀቂያ ዳርጓቸዋል፡፡ ልኡካኑ ወደ አገር ቤት ከመመለሳቸው ሦስት ቀናት በፊት በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተጠርተው ከተጨማሪ መግለጫ እንዲቆጠቡ ጫና የተደረገባቸው ሲኾን ለልኡካን ቡድኑ በጸሐፊነት የተመደቡት ንቡረ እድ ኤልያስ ከኤምባሲው ሰዎች ጋራ ያረቀቁት ነው በተባለው የተቃውሞ መግለጫ ላይም እንዲፈርሙ መገደዳቸው ተገልጧል፡፡ በተመሳሳይ ኹኔታ ‹‹ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም›› በማለት የሚዲያ መግለጫ የሰጡና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ የሚታወቁ አገልጋዮችም በደኅንነት ወከባ ውስጥ መሰንበታቸው በየጊዜው ስንዘግብ ቆይተናል፡፡

ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ወይም የሰላምና አንድነት ጉባኤው በተፈጸመው ተግባር ላይ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡

http://www.ecadforum.com/

posted by Tseday Getachew

ብሶት የወለደኝ እያለ የሚመጻደቀው ወያኔ ብሶተኞችን እየፈለፈለ ነው

በአገራችን ውስጥ የነበረው ብልሹ አስተዳደር በፈጠረው ኢፍትሃዊነት ብሶት አርግዞ ለድል ያበቃውን ጠመንጃ እንደመዘዘ በኩራት የሚደሰኩረው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ፡ የመንግሥት ሥልጣንን የሙጥኝ በማለት በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ባለው ሰቆቃ ተማርረው በተራቸው ብሶት አርግዘው ጠመንጃ ለማንሳት የሚገደዱ ሃይሎችን በየቀኑ እየፈለፈለ መሆኑ በተግባር እየታየ ነው።

ወያኔ የድጋፍ መሠረቴ ነው ከሚለው የትግራይ ክልል ውስጥ የወጣው የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ወይም ዴሚት በሚል ምህጻረ ቃል ከሚጠራውና በርካታ የትግራይ ወጣቶችን ማሰባሰብ ከቻለ ድርጅት ጀምሮ “በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የብሄር እኩልነት ካባ አከናንቤያችኃለሁ” ብሎ ወያኔ ከሚመጻደቅባቸው ህዝቦች አብራክ የወጡ የኦሮሞ፣ የኦጋዴን፣የቤነሻንጉል፣ የጋምቤላ፣ የአፋርና የደቡብ ህዝቦች የዚህን ዘረኛ ሥርዓት እብሪትና ጥጋብ አስተንፍሰው የተዋረደውን ክብራቸውን ለማስመለስ  መሳሪያ አንስተው መፋለም ከጀመሩ ውለው አድረዋል።

በወያኔ የዘር ፖለቲካ ከማለዳው ጀምሮ የጥቃት ሰለባ የሆነውና እንደ ባዕድ ወራሪ በሰላም ከየሚኖርባቸው ክልሎች ታድኖ የሚባረረው አማራም “በዘር መደራጀት ከጥቃት የሚያድን” ከሆነ በሚል ቁጭት ተደራጅቶ የትጥቅ ትግሉን ጎራ መቀላቀሉን አስታዉቋል። በብሄር እኩልነት ስም በየክልሉ ለተሾሙ ምስለኔዎች በታኮነት የተመደቡ ዘረኞች በህዝባችን ስም እየማሉና እየተገዘቱ የሚያደርሱት ግፍ አስመርሯቸው ጠመንጃ ካነሱ ከነዚህ የብሄር ድርጅቶች በተጨማሪ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ላለፉት 12 አመታት ከወያኔ ጋር የሽምቅ ውጊያ እያካሄደ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርም የተፈጠረው ወያኔ በህዝባችንና በአገራችን ላይ በሚፈጽማቸው ወንጀሎች ብሶት ባረገዙ ዜጎች መሆኑን የማያውቅ ኢትዮጵያዊ የለም።

ሰሞኑን ደግሞ የወያኔን ዘረኛና አምባገነናዊ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ በትጥቅ ትግል ለማስወገድ በአገር ወዳድና ለህዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ዜጎች ስብስብ፤ ወጣቶችና፣ ምሁራን የተሞላ ድርጅት ማቋቋሙን ለህዝብ ይፋ ያደረገው “የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል” ካሰራጨው መግለጫ መረዳት እንደተቻለው፤ ወያኔ ድርድርና እርቅ የማይገባው፣ ትዕግስትን እንደፍራቻ፣ አርቆ አሳቢነትን ደግሞ እንደ ሞኝነት የሚቆጥር በዚህም ስሌት ሕዝብን ለዘላላም እየረገጠና እየዘረፈ ለመግዛት ቆርጦ የተነሳ እኩይ ኃይል በመሆኑ ወያኔን ሊገባው በሚችል ብቸኛ ቋንቋ በማነጋገር የአገዛዝ ዕድሜውን ለማሳጠር ቆርጦ ብረት ያነሳ ሃይል ተፈጥሯል።

ግንቦት7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ሲያስጠነቅቅ እንደኖረው ፋሽስት ጣሊያን ሞክራ ባልተሳካላት የመንገድና የህንጻ ግንባታዎች ተደልሎ ወይም ከግማሽ በላይ የሆነውን ህዝባችንን ለረሃብ በዳረገ ወያኔ ግን ልማትና እድገት ብሎ በሚጠራው ለውጥ ተታልሎ ክብሩንና ነጻነቱን አሳልፎ በመስጠት እስከወዲያኛው ለወያኔ ባሪያ ሆኖ ለመገዛት የተዘጋጀ ህዝብ የለም ብሎ ያምናል።

ወያኔ ጥጋብ በወለደው እብሪቱ በማንአለብኝነት የህዝብን መብትና ነጻነት ረግጦ በአፈና ሥልጣን ላይ ለመቆየት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች አለኝታየ በሚላቸው የፖሊስ፣ የደህንነትና ወታደራዊ ኃይሎች እስከ መጨረሻው አጠናክር ለመቀጠል የሚችል አድርጎ ያስባል። በዚህም ምክንያት እስካፍንጫው ባስታጠቀው ወታደር ብዛትና በነዋሪው ቁጥር ልክ ህዝብ መሃል ባሰማራው ሰላዮች የተገነባው የፍርሃት ግምብ የሚናድም መስሎ አይታየውም። ሃቁ ግን በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተሰባሰቡ ወጣቶችም ሆኑ ወያኔን በአራቱም የአገራችን ማዕዘናት ለመግጠም ጠመንጃ ያነሱ ሃይሎች ወያኔ ህዝባችንን ሊያስፈራራ የሚችልበትን ሁሉ በጣጥሰው ለመውጣት ምንም ችግር የሌለባቸው መሆኑን ነው።

ንቅናቄያችን ግንቦት 7 ወያኔ ገንብቻለሁ ብሎ የሚኮፈስበትን የፍርሃት ግምብ ደርምሰው ለነጻነታቸው ሲሉ ውድ የህይወት ዋጋ ለመክፈል በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ዙሪያ መሰባሰባቸውን ይፋ ያደረጉ ወጣቶች የተነሱለትን ክቡር አላማ ያደንቃል። በዚህም ምክንያት ለነጻነቱ ቀናኢ ለሆነው ህዝባችን ያቀረቡትን የትግል ጥሪ ወቅታዊነት ሁሉም እንዲረዳው የበኩሉን አሰተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

posted by Tseday Getachew

 

ሰንበት ምሳ፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ልጆች ደቡብ አፍሪካ ምን አላቸው!?

ዛሬም “ለአዲስ ታይምስ” (ፍትህ) አዲሳባ ተልካ የነበረችቱን ወግ ለሰንበት ምሳ እዚህ ተለጥፋለች፤ ይቋደሱልኝ እውነት ግን የደቡብ ኢትዮጵያ ልጆች ደቡብ አፍሪካ ምን አላቸው!?

ሰላም ወዳጄ እንዴት ሰነበቱ…

የመንገድ ቁፋሮው ነገር እንዴት አድርጎታል? በአሁኑ ሰዓት አዲሳባ ውስጥ ትራንስፖርት ከማግኘት “ፖርት” ማግኘት ይቀላል ሲሉ የሚያሽሟጥጡ ሰዎች መበራከታቸውን እየሰማን ነው።

ኧረ “ፖርት” ብል ጊዜ ምን ትዝ አለኝ፤ ኢትዮጵያ ለጅቡቲ አዲስ ወደብ ግንባታ እያደረገችላት መሆኑን ሰምተን ደስታችን ጨምሯል። እሰይ እንዲህ ነው እንጂ ልግስና! በዚሁ አይነት ፤ ሌሎቹ ጎረቤቶቻችንም እንዳይቀየሙ ብንገነባላቸው ምን አለበት…? ለነ ሱዳን ፤ለነ ሱማሌ ኤርትራዬ እና ኬኒያስ ቢሆኑ ካለኛ ማን አላቸው…? እና ይታሰብበት… “ያስቀኛል ገንፎ ከራቴ ላይ ተርፎ” አሉ አበው!

እና ታድያ የትራንስፖርቱ ነገር እንዴት አደርጎታል? እንደውም እንደሰማሁት ከሆነማ “ፒያሳ መሀሙድጋ ጠብቂኝ” ከሚለው የታላቁ ወዳጃችን መሃመድ ሰልማን መፅሐፍ በኋላ “ቦሌ ፒኮክ ጋ ጠብቂኝ” “መርካቶ ምዕራብ ሆቴል ጋ ጠብቂኝ” የሚሉ ተደጋጋሚ የቀጠሮ ፅሁፎች ሲወጡ የነበረውን ያህል… አሁን በቅርቡ ከወዳጆቻችን እንደ አንዱ የሆነው በሀይሉ ገብረ እግዚአብሔር “የትም አትጠብቂኝ” ብሎ መፃፉን ሰምተናል።

ወዳጃችን ይህንን ሲፅፍ እንደሌሎቹ መቀጣጠሪያ ቦታ አጥቶ ሳይሆን፤ ብቀጥራት በምን ትራንስፖርት ትመጣለች? ብሎ ይመስለኛል። እርግጥ ይሄ የኔ ግምት ነው እንጂ፤ ሙሉ ፅሁፉን ገና አላነበብኩትም። (የት አግኝቼው…)

የምር ግን የትራንስፖርቱ ነገር “የትም አትጠብቂኝ” የሚያስብል መሆኑን ብዙ ወዳጆቼ እያማረሩ ነግረውኛል። እኔ የምለው ግን መንገድ ገንቢው አካል ገንቢ አስተያየቶችን ለምን አይቀበልም? መንገዶቹን እስኪሰሩ ድረስ ወይ አማራጭ መንገድ መስራት ወይ ደግሞ የስራ ማቆም አድማ መጥራት አለበትኮ! አለበለዛ ሰዉ ከአለቃውና ከቀጠራት ጋር እየተጣላ ከተማዋ የድብድብ “ሪንግ” እንዳትሆን ያሰጋል…!

ለማንኛውም ወዳጄ ዛሬም ኬኒያ እንሄዳለን… ሻንጣዎትን መያዝ አይጠበቅብዎም እንደው ደረስ ብለን መለስ ነው የምንለው።

በነገራችን ላይ ከአዲሳባ ኬኒያ አንድ ሰዓት ከሃምሳ ደቂቃ የበረራ ሰዓት ብቻ ነው የሚወስደው። በአሁኑ ሰዓት ከሽሮሜዳ ቦሌ ለመድረስ እንኳ ስንት ሰዓት ይፈጃል? አሁን አሁንማ ምን ሰዓት “ሰው ነው የሚፈጀው እንጂ!” ብለው በጣም አያማሩ…

እንደምንም ብለው ቦሌ ይድረሱ። ከዛም አንድ ሰአት ከሃምሳ ደቂቃ በሰማይ ላይ ተንሳፈው፤ ናይሮቢ ኬኒያ እንኳን ደህና መጡ ብላ ትቀበልዎታለች።

በኬኒያ በተናጠል ከሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ በአንድ ጊዜ አርባ ሰላሳ እየሆኑ እየተቧደኑ የሚሰደዱ የደበብ ኢትዮጵያ ልጆችን ማየት በጣም የተለመደ ነገር ነው። እነዚህ “ደቡቤዎች” ኬኒያ የሚመጡት ካናዳ፣ አሜሪካ፣ እና አውሮፓን ናፍቀው አይደለም። ወይ ደግሞ ፖለቲካን ነክተው መንግስት “ንኩት” (ውጡልኝ ከዚህ ቤት) ብሏቸውም አይደለም።

በቃ ከሆነ ጊዜ በኋላ በደቡብ ኢትዮጵያ የመጣ አንድ ፋሽን አለ። አንድ ሰው ጎርመስ ካለ፤ “ደርሷል ይባላል” ለአቅመ አዳም አይደለም። ለአቅመ ስራም አይደለም። ለአቅመ ጉዞ ደበብ አፍሪካ እንጂ…!

አንድ ሰሞን ግራ ገብቶኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ልጆች ደቡብ አፍሪካ ምን አላቸው? ብዬ አንድ ወዳጄን ጠይቄው ነበር።

እርሱም ሲነግረኝ፤ በአንድ ወቅት አንድ የደቡብ ክልል ሰውዬ ስማቸው ጠፋኝ (በቅንፍ እርሳቸውም ጠፍተዋል መሰለኝ። (በሌላ ቅንፍ ዘንድሮ አንደሆነ እግር ኳስ ተጫዋች ሳይሆን እንደወጣ የሚቀረው የመንግስት ባለስልጣን ሆኗል። ሁለቱም ቅንፋችን ዘግተን ስንወጣ))

እናልዎ እኒህ የደቡቤ ባለስልጣን በደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ተደርገው ተሹመው ነበር አሉ። ታድያ ያኔ ሰውዬው በርካታ ዘመዶቻቸውን ከደቡብ ክልል ወደ ደቡብ አፍሪካ ማስወጣት ጀመሩ። ዘመዶቻቸው ደግሞ በ “ሳውዝ” እንደምንም ብለው ተፍጨርጭረው ውጤት ላይ ሲደርሱ ሌላ ዘመዳቸውን መጥራት ጀመሩ። ከዛ እያለ እያለ አሁን አሁን የደቡብ ኢትዮጵያ ልጆች ታላቅ የተስፋ ምድር አድርገው የሚያዩዋት ደቡብ አፍሪካ ሆነች።

ወደዛ ለመድረስ ደግሞ ኬኒያን መርገጥ፤ በኬኒያም መረገጥ ግድ ነው። እንዴት የሚለው ብዙ ነው… ዛሬ እንደው መንደርደሪያውን እንቃመሰውና እንቀጥልበታለን…

አብዛኛዎቹ የደቡቤ ስደተኞች የሚመጡት በግሩፕ ነው ተባብለን የለ! ኬኒያ ድረስ በእግርም በአውቶብስም በምንም በምንም ተብሎ ይገባል። ከዛ በኬኒያ አንድ ቤት ውስጥ ቁጭ ብለው አርባ ወይም ሰላሳ እስኪሞሉ ይጠባበቃሉ። ምክንያቱም ለቀጣዩ የደቡብ አፍሪካ ጉዞ ትራንስፖርታቸውም የትልልቅ መኪና እቃ ማጠራቀሚያ “ኮንቴይነር” ነው። “ኮንቴይነሩ” ከሰላሳ እስከ አርባ የሚሆኑ ሰዎችን በአንዴ ይይዛል። ዋጋውም ከሌሎች መጓጓዣዎች ቀነስ ያደርጋል። ስለዚህ ብዙዎች ይመርጡታል።

በኮንቴይነር ሲጓዙ ታድያ፤ ዋጋው ብቻ ሳይሆን ስቃዩም እርካሽ ነው። ሞቱም በሽ ነው። ምነው እንኳ ባለፈው ኬኒያን አልፈው ታንዛንያ ሲደርሱ ስንት ወጣቶች ናቸው አየር አጥሯቸው በኮንቴይነር ውስጥ የሞቱት…? እረሱት እንዴ፤ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሁሉ ዜናውን ሰምተን አልነበር እንዴ! (ወይስ እርስዎ ያኔም ዲሽ ገዝተው ነበር…!? ትንሽ ኢቲቪን ሏሽሟጥ ብዬ እንጂ ዜናው በአለም አቀፍ ማሰራጫዎችም ተሰራጭቶ ነበር። እና በርግጠኝነት ሰምተውታል)

ኬኒያ ቁጭ ካሉ ደግሞ እንደዚህ አይነት ዜና ብርቅ አይደለም። በተለይ ታንዛንያ ላይ በርካታ ወገኖቻችን በታጨቁበት ኮንቴይነር ውስጥ ፍፃሜያቸው ሆኗል።

ነገር ግን እንዲህም ሆኖ ጉዞው አያቋርጥም። መጓጓዣውም አይቀየርም። ኬኒያ ለ12 አመታት የኖረው አዲስ እንደነገረኝ ከሆነ “እነኳን ሌላው ቀርቶ አጠገባቸው ጓደኞቻቸው በኮንቴይነር ውስጥ አየር አጥሯቸው ሞተው በእግዜር ታምር ተርፈው ደቡብ አፍሪካ የገቡ ሰዎች ራሳቸው፤ ሌላ ዘመዳቸውን የሚያስመጡት በኮንቴይነር ነው።” ብሎኛል።

ደቡቤ ወዳጆቻችንም እንትና ሞተ የሚለውን ወሬ ቢሰሙትም ከልባቸው አይፅፉትም። በጣም ያስገረመችኝን አንድ ወሬ ቀጥሎ ልንገርዎትማ፤

በደቡብ ኢትዮጵያ በተለይ ከንባታ እና ሃድያ አካባቢ የተለያዩ ቪዲዮ ቤቶች አሉ። ቪዲዮ ቤቶቹ ፊልም ያሳያሉ። የሚያሳዩት ፊልም የ “ጄኪ ቻን” ካራቴ እንዳይመስልዎ… የ “ጆቴ ጃና ህይወት በደቡብ አፍሪካ” የሚል ነው።

እንግዲህ “ጆቴ” በአካባቢው የሚታወቅ የደቡብ ልጅ ነው አሉ። (ስሙ አፌ ላይ መጥቶ ነው አንጂ ማስታወሻ ደብተሬ ላይ ያለው እውነተኛው ስም አይደለም) እና ከደቡብ ሲወጣ “ስንጥር ነበር የሚያክለው ቀጫጫ፤ አሁን ወፍሮ ባላባት መስሏል። እቤቱ ሶፋ ላይ ሲቀመጥ፣ በሪሞት ቴሌቪዥኑን ሲያበራ እና ሲያጠፋ፤ የሆነች ነጭ የምታምር መኪና ተደግፎ፣ ደግሞ ሌላ ቀይ መኪና ውስጥ ቁጭ ብሎ “ሾፌር” ሆኖ… ብቻ በጥቅሉ የአካባቢው ወጣቶች በቅርብ የሚያውቁት “ጆቴ ጃና” ሆኗል የሚያስቀና…!

ይህንን ቪዲዮ የአካባቢው ወጣቶች ከፍለው ነው የሚያዩት። ከዛ የስቃይ እና የሞት ወሬ ትዝ አይላቸውም። ቁጭ ብለው ያስባሉ እንደ “ጆቴ ጃና” መሆን የሚቻለው እንዴት ነው? ብዙውን ጊዜ ቪዲዮውን የሚያሳየው ሰውዬ ራሱ አማካሪ ነው። እንደውም ሳስበው ቪዲዮውን ካሳያቸው በኋላ “እንደ ጆቴ ጃና መሆን ይፈልጋሉ… እንግዲያስ መላው ቀላል ነው!” ብሎ ማስታወቂያ ሳይሰራ አይቀርም።

ታድያ የድለላ ስራ ይራና ጠርቀምቀም ያሉ ጎረምሶችን ከመንገድ መሪ ጋር አድርጎ ኬኒያ ያደርሳቸዋል። ከኬኒያ ደግሞ ጠርቀምቀም ሲሉ በኮንቴይነር መኪና ውስጥ ተጭነው በሰላም ከገቡ “ጆቴ ጃና” ደቡብ አፍሪካ ይቀበላቸዋል።

“መሃሉ አይነገርም” እንዲል ሰባኪው መሃሉ ግን ብዙ ጣጣ አለው። በደቡብ ኢትዮጵያ እና በደቡብ አፍሪካ መሃል ካሉት የመሃል ላይ አበሳዎች አንዱ ኬኒያ ውስጥ ያለው አበሳ ነው… በሚቀጥለው ጊዜ ቅንጭብጫቢ አበሳዎችን እናነሳለን!

ለዛሬ ይብቃን…

እስቲ አማን ያሰንብተን!

http://www.abetokichaw.com

posted by Tseday Getachew

[ሻዕቢያ] በየቀኑ እየሞተ ነው”/ፕሬዚዳንቱ ግን “በልማት” ተግባራት ተጠምጃለሁ ይላሉ

 

ኤርትራ ከውጪና ከውስጥ ተዥጎርጉራለች። ከውጪ ደግሞ “በየቀኑ ትንሽ ትንሽ እየሞተች ነው፤ በቅርቡም የሚፈነዳ ነገር አለ” በሚል ግምት ከየአካባቢው እየተሰጠ ነው። ከውስጥ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የኢንቨስትመንት ጥያቄና ግብዣ ላይ ናቸው። የተበላሸባቸውን ዲፕሎማሲ ለማቃናት ላይ ታች እያሉ ነው።

“ኤርትራን በተመለከተ የሚወጡት መረጃዎች የችግሮቿን መወሳሰብና የፕሬዚዳንት ኢሳያስ እጣ ፈንታ መገባደጃው ላይ ለመድረሱ አመላካች ነው” የሚሉ ያሉትን ያህል “ኢሳያስ በውጪ ግንኙነታቸው ላይ የሰሩትን ስህተት በማረም ከበፊት ይልቅ አሁን ወደ ተሻለ መረጋጋትና የኢኮኖሚ ተሃድሶ ተሸጋግራለች” በሚል የሚከራከሩም አሉ። እንደውም ከህወሃት/ኢህአዴግ ይልቅ ሻዕቢያ ከስጋት የራቀ እንደሆነ አድርገው የሚከራከሩ አሉ።

በኤርትራ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ፣ መንግስት ከያዘው ሞኖፖሊ አስተሳሰብ እንደሚወጣና ቃል በመግባት ተወላጆቹንና ውጪ ባለሃብቶችን የሚወተውተው ሻዕቢያ “እየተንፈራገጠ ነው” በሚል ከመሸ የሚያደርገውን ጥረት ኑዛዜ አድርገው የሚመለከቱ አገሪቱ በለውጥ መብላላት ውስጥ እንደምትገኝ ነው የሚናገሩት። ይህንኑ የሚያጠናክር ዘገባ ቪኦኤ አሰምቶ ነበር።

ፈረንሳዊው የመገናኛ ብዙሃን ተመራማሪና ጋዜጠኛ ሊዮናል ቫንሶ ከምስራቅ አፍሪቃ የቪኦኤ ዘጋቢ ፒተር ሃይን ላየን ጋር ባካሄደው ጥያቄና መልስ ሊበጠስ የደረሰ የሚመስል ጉዳይ መድረሱን የሚያመላክት መረጃ አስተላልፏል። ስለ ኤርትራ መንግስት የተደራጀ መረጃ እንዳለው የሚያስታውቀው ጋዜጠኛ ቃለ መጠይቅ ያካሄደው “ተሰወሩ” የተባሉትን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ አሊ አብዶን አስመልክቶ ነው።

አቶ አሊ ለህክምና ጀርመን እንደነበሩና በታህሳስ ወር አገራቸው መመለስ ሲገባቸው እስካሁን ኤርትራ እንዳልገቡ ከቅርብ የመረጃ ምንጩ ማረጋገጡን የገለጸው ጋዜጠኛ፤ አጋጣሚውን በ2006 ከተሰወሩት የኤርትራ የወጣቶች ንቅናቄ መሪና የቀድሞ የአቶ አሊ አለቃ ጋር አገናኝቶታል። ለጉብኝት ኢሲያ ከሄዱ በኋላ ሲመለሱ ኢሳያስ እንደሚያስሯቸው መረጃ ስለደረሳቸው አገራቸው አልገቡም። እስካሁን ያሉበት አይታወቅም።

አቶ አሊም አውሮፓ ስዊድንና ጀርመን ከመታየታቸው ውጪ የት እንዳሉ መረጃ ማግኘት እንዳልቻለ የጠቆመው ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ፣ የአቶ አሊን መሰወር “በየቀኑ ትንሽ ትንሽ እየሞተ ካለው መንግስት ራሳቸውን ማግለላቸው ይሆናል” ሲል ግምቱን ሰጥቷል። ፒተር ሃይን አቶ አሊ አገራቸውን የሚከዱ ሰው እንዳልሆኑና አሁን የት እንዳሉ ስለማወቁ ላቀረበው ጥያቄ “የት እንደሆኑ አናውቅም። የምናውቀው በተቀነባበረ ደረጃ መሰወራቸውን ነው” በሚል ፈረንሳዊው ተጠያቂ ጋዜጠኛ መልስ ሰጥቷል።

ጋዜጠኛ ሊዮናል የአቶ አሊን በተቀነባበረ ደረጃ መሰወር ተከትሎ ያሉትን መረጃዎች ሲያብራራ ሴት ልጃቸው የሳቸውን ዱካ ተከትላ ወደ ሱዳን ማምራቷን፣ ባለቤታቸው ከሁለት ወንድሞቻቸው ጋር ካናዳ የሚኖሩ መሆኑና አስመራ መኖሪያ ቤታቸው በደህንነት ሰዎች መከበቡን አቶ አሊ አገር ውስጥ እንደሌሉ ማረጋገጫ አድርጎ ያቀርባል። በማያያዝም ቤተሰቦቻቸውን ተለይተው ብቻቸውን አስመራ በመኖራቸው ደስተኛ እንዳልነበሩ ተናግሯል።

በኤርትራ ውስጥ የሚታየው ሁኔታ የተካረረ መሆኑንን ያመለከተው ጋዜጠኛ አቶ አሊ በፖለቲካና በግል ጉዳይ በተጠና መንገድ እንደ ተሰወሩ ግምቱን አስቀምጦ፣ “ነገሮች አንድ ቀን ይፈነዳሉ። መንግስትም በአንድ ሰው የመተዳደሩና የመመራቱ እድል ያከትማል” ብሏል።በኤርትራ በጀኔራሎችና በሲቪል ባለስልጣናት መካከል አለመተማመን መንገሱንም አመልክቷል። የቅርብ መረጃ እንዳለው የተናገረው ጋዜጠኛ አቶ አሊ “አገራቸውን ከዱ” እንደማይባል፣ “ከዱ” የሚባለው ካሉበት ሆነው መንግስታቸው የሚያካሂደውን በሙሉ እንደማያምኑበትና እንደማይቀበሉት በገሃድ ሲያስታውቁ ብቻ መሆኑንን እንደሆነ ተናግሯል።አቶ አሊን አስመልክቶ “የኢሳያስ ልጅ አይከዳም! አናምንም” በሚል በስደት የሚኖሩ የኤርትራ  ተወላጆችን በማነጋገር ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ መዘገቡ ይታወሳል።

አቶ አሊ ኢሳያስን ወደ ማምለክ የደረሱ፣ በሽፍትነት ዘመናቸው የሬዲዮ መገናኛቸውን የሚያንቀሳቅሱ ታማቸውና የአቶ ኢሳያስን በርካታ ምስጢር የሚያውቁ የስርዓቱ ተጠቃሚ ስለሆኑ አገር ከድተው እንደማይጠፉ አሁን ድረስ የሚከራከሩ አሉ። እነዚህ ክፍሎች ኢሳያስ ታመዋል የተባሉበትን ወቅትና የርሳቸውም ምላሽ ያስታውሳሉ።

በኤርትራ ያለውን የፕሬስ ነፃነት ለማመጣጠን ጁላይ 15/2009 ከኤርትራ በተሰደዱ ጋዜጠኞች የተቋቋመና በድንበር የለሽ ዘጋቢዎች (Reporters Without Borders) የሚታገዘው ኤሬና /ERENA/ ሬዲዮ በሚያዚያ (April) ወር 2012 በኤርትራ ጄኔራሎች አስቸኳይ ስብሰባ “ኤርትራ እንዴት ትቀጥል?” በሚል መምከራቸውን ከፈረንሳይ መዘገቡን ተከትሎ ኢሳያስ አበቃላቸው ተብሎ እንደነበር ይታወሳል።

በኢትዮጵያ የስደት መንግስት ያቋቋሙትን የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚዎች ስብስብ “የኤርትራን ነፃ አገርነት አሳልፈው የሸጡ ከዳተኞች” በማለት የሚጠራው ይህ ሬዲዮ፣ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በጠና መታመማቸውን ተከትሎ “… ጄኔራሎቹ ቀጣዩን የኤርትራ ጉዳይ ‘አገራዊ መግባባት’ በሚሰፍንበት መልኩ ለማስቀጠል ይቻል ዘንድ በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ላይ መፈንቅለመንግሥት ለማካሄድ ሲያሴሩ ተደርሶባቸዋል በሚል በእስር ላይ ያሉት ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲፈቱ ወስኗል። የሞቱም ካሉ ለቤተሰቦቻቸው እንዲነገር ከስምምነት ላይ ተደርሷል” የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር።

በዛው ወር ቀለል ባለ አለባበስ ነጠላ ጫማ ተጫምተው በብቸኛዋ ኤሪ-ቲቪ (ERITV) ብቅ በማለት ነገሩን ሁሉ አፈር ያስገቡት አቶ ኢሳያስ ለተወራው ሁሉ መልስ መስጠት እንደሚያስቸግር በማስታወስ፣ በልማት ስራ ተጠምደው ከመክረማቸው ውጪ በጤናቸውም ሆነ በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ አንዳችም ነገር እንዳልተፈጠረ ተናግረው ነበር።

የልማት ስራዎችን ሲጎበኙ አስራ አራት ሰዓት ያህል ያለማቋረጥ ስለተጓዙ ረዥም እንቅልፍ መተኛታቸውን፣ እንቅልፉ ሳይለቃቸው ወደ ቢሮ ሲገቡ የፕሬስ ፀሃፊያቸው ከሰጠቻቸው ወረቀቶች ላይ ስለእርሳቸው ሲወራ የነበረውን  መመልከታቸውን ተናግረዋል። “ሞባይል የለኝም፤ ኢንተርኔትም አልጠቀምም” የሚሉት አቶ ኢሳያስ የተወራውን ሁሉ እንደንፋስ እንደሚቆጥሩት አስምረውበታል። ውሸት በተወራ ቁጥር ቴሌቪዥን ላይ በመውጣት ማስተባበያ መስጠት እንደማይቻል በመጠቆም የተወራባቸውን ክፉ ወሬ በማምከን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ “እኛ ተመስገን ብለን አስራ ሁለት ሰዓት ስንተኛ፣ ውሸታሞቹ ሃያ ሶስት ሰዓት ከሃምሳ ዘጠኝ ደቂቃ እንቅልፍ የላቸውም” ሲሉ ድምጻቸውና አድራሻቸው ሳይታወቅ ለከረሙበት ጊዜያት መልስ ሰጥተዋል። አሜሪካንና ሲ.አይ.ኤንም ወቅሰዋል።

የእርሳቸው መግለጫ እንዳበቃ፣ ኢሳያስ ከጠፉበት ብቅ ብለው ኢንተርቪው መስጠታቸውን ያላጤነው በህወሃት/ኢህአዴግ የሚደገፈውና ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ሰዓት ተጋርቶ ዝግጅት የሚያቀርበው ዳሃይ ኤርትራ በፕሮግራም የፕሬዚዳንት ኢሳያስን የጤና መጓደል በተመለከተ “አጋጣሚውን በመጠቀም አዲሲቷን ኤርትራ ለመመስረት እንነሳ” ሲል ለወታደሮችና ለህዝቡ ጥሪ አሰምቶ ነበር። እስካሁን ግን ምንም የለም።

ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ “አጉራ ዘለል፣ ተናካሽ ውሻ፣ አተራማሽ …” እያሉ የሚሰድቡትን የበረሃ ባለውለታቸውን ሻዕቢያን አስፈንጥረው እንደሚወረውሩት ለዓመታት መዛታቸው አይዘነጋም።

http://www.goolgule.com

posted by Tseday Getachew

የኢትዮጵያ መንግሥት ሊ/ካ ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁን በግድ ወደ አሜሪካ መለሳቸው

by Deje Selam on Saturday, 29 December 2012 at 19:01 ·
 

ዲፖርት አደረጋቸው፤
ጉዳዩን ያቀነባበሩት የአዲስ አበባው ልዑክ አባል የሆኑት ን/ዕድ ኤልያስ ናቸው ተብሏል፤
ሊ/ካ ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁ
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 20/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 29/2012)፦ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ አልገባኹም በሚል ሰሞኑን መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግሥት ለዕርቁ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋር ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ የሄዱትን የሰላምና አንድነት ጉባኤውን አባል ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን አስሮ ወደ አሜሪካ መለሳቸው። እዚያው አስሮ ያላስቀራቸው አሜሪካዊ ዜግነት ስላላቸው ነው ተብሏል። ከእርሳቸው ጋር ለዚሁ ጉዳይ ወደ ኢትዮጵያ የሄደው የሰላምና አንድነት ጉባኤው ሌላ አባል ዲ/ን አንዱዓለም ዳግማዊ ስላለበት ሁኔታ አልታወቀም። ዝርዝሩን እንደደረሰልን እናቀርባለን።

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።

posted by Tseday Getachew

 

በቡሬ ግንባር የሚገኙ እና በግጭቱ ታስትፈዋል የተባሉ ወታደሮች መሳሪያቸውን እንዲያስረክቡ ታዘዙ

ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢሳት ወታደራዊ ምንጮች እንደገለጹት ባለፈው ማክሰኞ ሌሊት በሰራዊቱ መካከል የተፈጠረውን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ከሆኑ በሁዋላ ባለፈው ሀሙስ ከመቀሌ እ   ከአፍዴራ የተንቀሳቀሱ ወታደራዊ አዛዦች በግጭቱ የተሳተፉት ሁሉ ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ማድረጋቸው ታውቋል። በእለቱ ከፍተኛ ግምገማ መካሄዱንም ለማወቅ ተችሎአል።

በአሁኑ ሰአት አንጻራዊ ሰላም መስፈሩን በአካባቢው የሚኖሩ የአፋር ተወላጆች ለኢሳት ገልጸዋል።

በቡሬ ግንባር በሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት  አባላት መካከል ማንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ማክሰኞ ሌሊት የእርስ በርስ ግጭት ተፈጥሮ እንደነበርና ቁጥሩ ከ12 እሰከ 40 የሚደረስ የሰራዊት አባለት መሞታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። 15 ወታደሮች በማንዳ ሆስፒታል የሞቱ ሲሆን፣ 12ቱ ደግሞ በሞትና በህይወት መካከል እንደነበሩ መዘገባችን ይታወቃል። በጽኑ የቆሰሉ አዛዦችም ወደ መቀሌ ሆስፒታል ተወስደዋል።

የግጭቱን መንስኤ እስካሁን በትክክል ለማወቅ አልተቻለም። በአካባቢው የተመደቡ የሰራዊት አባላትን ለማናገር ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም ሊሳካልን አልቻለም። በቡሬ ግንባር አካባቢ የሞባል ስልክ ኔት ወርክ ለማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን መረጃዎን ያደረሱን ምንጮች ገልጸዋል።

ማንዳ ከቡሬ ግንባር 21 ኪሎሜትር የሚርቅ ሲሆን፣ ግጭቱ በትክክል የተነሰባት ቦታ አሊ ፉኑ ዳባ እየተባለ በሚጠራው የጎሳ መሪ ስም በተሰየመ አሊ ፉኒ አካባቢ ነው።

posted by Tseday Getachew

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት መተማ ወረዳ አለንጌ በተባለ ቦታ ጥቃት ፈፀመ

ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ታህሳስ 18 ቀን 2005.ዓ.ም በመተማ ወረዳ ልዩ ስሙ አለንጌ በተባለው አካባቢ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በተካሄደው ውጊያ 8 የጠላት ወታደሮችን ገድሎ 11 በማቁሰል ከፍተኛ የህይወትና የንብረት ኪሳራ ማድረሱን ግንባሩ ገልጿል።

ግንባሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን መማረኩንም ገልጿል።

መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው መልስ የለም። ዜናውንም ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ አልተቻለም።

posted by Tseday Getachew

Breaking NewsReplace Samora yenuse-New head of Armed Forces L/G. Taddesse werede

ሰበር ዜና
ሌፍተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደ ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስን ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል::

በ2008 ከሜ/ጄ ወደ ሌ/ጄ የተሸጋገሩት ታደሰ ወረደ የጦር ሃይሎች ኢታማጆር ሹም የነበሩትን ሌ/ጀኔራል ሳሞራ የኑስን ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ዉስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጡ::በኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስቴር ቅድመ ተከተል መሰረት ጄኔራል ሳሞራ የኑስን ይተኩዋቸዋል የሚባሉ 4የበታች ጄኔራሎች አሉ ብለዋል ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ…
http://minilik-salsawi.blogspot.com/2012/12/blog-post_29.html

 
 
posted by Tseday Getachew
 
 
 
 
 
 

Gen. Samora Yenus in a German hospital – update

Elias Kifle

UPDATE – December 28, 2012: Ethiopian Review sources are reporting that armed forces chief of staff Gen. Samora Yenus is back in a Germany hospital. In August, we reported that Samora, looking frail, returned to Addis Ababa to attend dictator Meles Zenawi’s funeral, and that he will return to the hospital.

UPDATE – August 21, 2012: Samora Yenus has been observed at Bole Airport today along with other TPLF junta officials receiving Meles Zenawi’s body. Our sources have verified that he returned to Addis Ababa two days ago from Germany, but he will return to continue his medical treatment.

Samora YenusThe late Ethiopian dictator Meles Zenawi’s military chief of staff, Gen. Samora Yenus, is currently in Essen, Germany, receiving medical treatment.

Doctors at Essen University Hospital have diagnosed Samora with Pneumocystis Carinii Pneumonia, which is a symptom of AIDS, according to Ethiopian Review Intelligence Unit sources.

Samora was taken to Bole Airport by ambulance after he collapsed following a TPLF meeting last week, and flown to Germany.

Lt. General Seare Mekonnen is now in charge of the armed forces in Ethiopia, Ethiopian Review sources in Addis Ababa reported.

[Source: Ethiopian Review]

posted by Tseday Getachew

6ኛውን ፓትሪያክ ለማስመረጥ ለተሾሙት የተጻፈ ምስጢራዊ ደብዳቤ

6ኛውን ፓትርያርክ ለማስመረጥ ለተሾሙት ሰዎች ከሲኖዶስ የተጻፈላቸው ምስጢራዊ ደብዳቤ

Read more http://ethioforum.org/6%e1%8a%9b%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%8d%93%e1%89%b5%e1%88%aa%e1%8b%ab%e1%8a%ad-%e1%88%88%e1%88%9b%e1%88%b5%e1%88%98%e1%88%a8%e1%8c%a5-%e1%88%88%e1%89%b0%e1%88%be%e1%88%99%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%89%b0/

 

posted by Tseday Getachew

መንግሰት የኢንተርኔት ድረገጾችን እና ብሎጎችን እንደሚያፍን በይፋ አመነ

ታህሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አንዳንድ የኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች በኢትዮጽያ እንደሚታገዱ የኢንፎርሜሽን ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ በይፋ አረጋገጡ፡፡
ብ/ጄኔራሉ ሰሞኑን ለንባብ ከበቃው መንግስታዊው “ዘመን” መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንዳረጋገጡት አንዳንድ አስጊ ናቸው ያሏቸውን የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን ማገድ የኤጀንሲው ዋንኛ ስራ አለመሆኑን፤ ነገር ግን በመርህ ደረጃ መደረግ አለባቸው ብሎ ማስቀመጡን ጠቅሰዋል፡፡“ለዚህ ደግሞ ቴሌ እንዲያጣራቸው አቅም
የመገንባት ስራ እንሰራለን፡፡ከተቻለ ደግሞ ከሃይማኖት፣ከዘር፣ከሽብርተኝነት፣ከሕዝብ ሞራል ጋር የተያያዙ ድረገጾች ወደ ኢትዮጽያ እንዳይገቡ ጥረት ይደረጋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
“የሃይማኖት አክራሪነት አንድ ስጋት ነው፡፡ከዚያ አልፎ ሽብርተኝነት አለ፡፡ሕዝቡ በስነልቦና እንዲሸበር ፍርሃት፣ጭንቀት፣አለመተማመን እንዲሰፋ፣ ወጣቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ እንዳይገባ የሚያደርጉ ኃይሎች አሉ ” ያሉት ብ/ጄኔራሉ  ”ይህን ለመቆጣጠር ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የመከላከያ አቅም መገንባት
ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ብ/ጄኔራሉ በዚሁ ቃለምልልሳቸው መረር ብለው “የኢትዮጽያ ቴሌኮምኒኬሽን የኀብረተሰቡን ሰላም የሚያጠፉ ዌብሳይቶችን የመቆጣጠር አቅም ሊኖረው ይገባል፡፡መርሁ ይህ ነው፡፡ለኀብረተሰቡ የሰላምና የልማት አጀንዳ እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ የመቆጣጠር ብቃት አስፈላጊ ነው” ብለዋል፡፡

“ስርዓት ያልተበጀለት ኢንተርኔት ጉዳቱ ሰፊ ነው” የሚሉት ብ/ጄኔራል ተክለብርሃን “ሕገመንግስቱን ም ሆነ የሕዝቡን ሰላም የሚጻረሩ እንቅስቃሴዎች ሊፈቀድላቸው አይገባም” ብሎ አስቀምጧል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጽያ መንግስት በኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች ላይ አፈና በማድረግ የዜጎችን ኀሳብን በነጻ የመግለጽ ነጻነት የሚጻረሩ ሕገወጥ እርምጃዎችን ይወስዳል በሚል የሚቀርብበትን ተደጋጋሚ ክሶች፤ መሰረተ ቢስ ናቸው በሚል ሲያጣጥል መቆየቱ አይዘነጋም፡፡

posted by Tseday Getachew

Post Navigation

%d bloggers like this: