Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

Archive for the category “NEWS”

የታገደው ድፍረት ፊልም የይገባኛል ጥያቄ አስነሳ

አንጀሊና ጆሊ ኤግዚኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር የሆነችበትና ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ዲፕሎማቶችና የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት በብሔራዊ ቴአትር ሊመረቅ የነበረው ድፍረት ፊልም፣ በፍርድ ቤት እግድ ከተቋረጠ በኋላ የይገባኛል ጥያቄ ማስነሳቱ ታወቀ፡፡

ፊልሙ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ የሚያጠነጥነው አስገድዶ የደፈራትን የ29 ዓመት ወጣት በገደለችው የ14 ዓመት ታዳጊ አበራሽ በቀለ (በፊልሙ ሒሩት) ሕይወት ዙሪያ ነው፡፡ ደፋሪዋ ሕፃኗን በጠለፋ ሊያገባትም ሙከራ አድርጐ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር መሥራች የሆኑት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ጉዳዩን ሰምተው ጥብቅና ቆመውላት ራስን ለመከላከል በሚል በነፃ እስከተለቀቀችበት ጊዜ ድረስ፣ አበራሽ በግድያ ክስ ተመሥርቶባት ማረሚያ ቤት ነበረች፡፡

በአቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ መሐሪ የተጻፈውና ዳይሬክት የተደረገው ይህ ፊልም በዚህ ዓመት በሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫል ተሸላሚ መሆኑን ተከትሎ፣ የታሪኩ ባለቤት በሆነችውና ፈቃደኝነቷን እንዳልተጠየቀች በምትናገረው ወ/ሪት አበራሽና የወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ወንድምና የታሪኩ ጸሐፊ ነኝ በሚሉት አቶ ፍቅሩ አሸናፊ ጥያቄ ተነስቶበታል፡፡

የፍርድ ቤት እግዱ እንደሚያሳየው በከሳሽነት የቀረቡት አቶ ፍቅሩ አሸናፊና ወ/ሪት አበራሽ በቀለ ሲሆኑ፣ ተከሳሾቹ ደግሞ አቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ፣ ኃይሌ አዲስ ሥዕሎች ድርጅትና ትሩዝ ኤይድ ሚዲያ ድርጅት ናቸው፡፡

ክሱ እንደሚያስረዳው ድፍረት የተሰኘው ፊልም ተመርቆ ለሕዝብ ዕይታ ቢውል በከሳሾች ሞራላዊና ኢኮኖሚያዊ መብት ላይ የማይተካ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል በመገንዘብ፣ ፍርድ ቤቱ ፊልሙ ለሕዝብ ዕይታ እንዳይውል ወይም እንዳይመረቅ ጭምር እገዳ ጥሏል፡፡ በተጨማሪም በተከሳሾች ላይ ሊደርስ ለሚችል ኪሳራ ከሳሾች 50 ሺሕ ብር በዋስትና አስይዘዋል፡፡

ወ/ት አበራሽ እንደምትለው ፊልሙ በርሊን እስከተመረቀበት ጊዜ ድረስ ምንም ዓይነት መረጃ አልነበራትም፡፡ ከሰባት ወራት በፊት ግን አቶ ዘረሠናይን አግኝታው በፊልሙ ላይ ዕውቅና እንዲሰጣት፣ የተወሰነ ገንዘብም እንዲከፍላት እንደምትፈልግ ገልጻለት የነበረ ቢሆንም ይህ ሳይሆን ቀርቷል፡፡

የፊልሙ ሥራ የእሷን ደኅንነት ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ አይደለም በማለት የምትወቅሰው ወ/ት አበራሽ፣ ምንም እንኳ ሁኔታውን ለማስረዳት ብትሞክርም ከአቶ ዘረሠናይ በመጨረሻ ያገኘችው መልስ አዎንታዊ አለመሆኑን ትናገራለች፡፡ ‹‹ከተፈጠረው ነገር ጋር በተያያዘ የምኖረው ተደብቄ ነበር፡፡ ይኼ ፊልም ግን ታሪኩን እንደ አዲስ ቀስቅሶ የእኔንም የቤተሰቦቼንም ሕይወት አደጋ ላይ ጥሎታል፤›› ትላለች፡፡

ወ/ት አበራሽ የደፈራትን ሰው ከገደለች በኋላ በኦሮሞ የእርቅ ባህል ጉማ መሠረት ቤተሰቦቿ ካሳ ከፍለው ነገሩ ተቋጭቶ ነበር፡፡ በስምምነቱ መሠረት እሷም ቀዬዋን ጥላ ለመውጣት ተስማምታ እንደነበር የምትናገረው አበራሽ፣ ‹‹በባህሉ መሠረት ሴት ገድላ ካሳ መክፈል አትችልም፡፡ ስለዚህም ወደ አካባቢዬ እንዳልመለስ የሟች ቤተሰቦች ያስጠነቀቁኝን በመስማትና ለቤተሰቦቼ ደኅንነት ስል ለዓመታት እዚያ ሳልደርስ ቀረሁ፤›› ብላለች፡፡

በአሁኑ ወቅት ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችን ለማገዝ የሚሠራ ሀረም በተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ በመሥራት ላይ የምትገኘው ወ/ት አበራሽ፣ በሕይወቷ ብዙ ውጣ ውረዶችን እንዳሳለፈች ትናገራለች፡፡ የትውልድ ቦታዋ ቀርሳ አርሲን የለቀቀችው ወ/ት አበራሽ ሁለተኛ ደረጃ እስክትደርስ የኖረችው ቀጨኔ ሕፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ነበር፡፡ ታሪኳ ተካትቶ በተሠራ ዘጋቢ ፊልም አማካይነት ታገኝ የነበረው ገንዘብ ኮሌጅ ስትገባ መቋረጡን ታስታውሳለች፡፡ ስለዚህም በነበረባት የገንዘብ ችግር የኮሌጅ ትምህርቷን ለማቋረጥ መገደዷን፣ ከዚያም ወደ ዱባይ እስከሄደችበት ጊዜ ድረስ በአንድ ትንሽ የፊልም ሲዲ ማከራያ ሱቅ ውስጥ መሥራቷን ለሪፖርተር ገልጻለች፡፡

አቶ ዘረሠናይ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ላይ እንደተናገረውና አቶ ፍቅሩ እንደሚሉት ስለታሪኩ መጀመሪያ አቶ ዘረሠናይ የነገረው ለእርሳቸው ነው፡፡ ይህ የሆነው እ.ኤ.አ. በ2005 ሲሆን፣ አቶ ፍቅሩ እንደሚሉት የፊልሙ ሐሳብ የተወሰደው ከእሳቸው በመሆኑ ፊልሙን በጋራ ለመሥራት አስበው ነበር፡፡ ‹‹ከ2008 በኋላ አቶ ዘረሠናይ እኔን ለማናገር አልፈለገም፡፡ እንዲያውም ይደበቀኝ ጀመር፤›› ይላሉ፡፡

የፊልሙን መሠራት ሲጠባበቁና ነገሮችን ሲከታተሉ እንደነበር፣ የአበራሽን ይሁንታም እንዳገኙ አቶ ፍቅሩ ይናገራሉ፡፡ አቶ ዘረሠናይ ግን ለእሷም ለእሱም የታሪኩ ሐሳብ ባለቤት እንደመሆኑ ዕውቅና ሳይሰጥ መቅረቱን ያስረዳሉ፡፡ ‹‹ያለሷ ታሪክ ፊልሙ አይሠራም ነበር፡፡ ባትደፈር፣ በጥንካሬ ደፋሪዋን ባትገድለው ኖሮ ታሪክ አይኖርም ነበር፤›› ይላሉ አቶ ፍቅሩ፡፡

በፊልሙ ውስጥ ሌላ ባለታሪክ የሆኑትና በወቅቱ የ14 ዓመቷ ታዳጊ ጠበቃ የነበሩት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ለፊልሙ ዳይሬክተር ታሪካቸው በፊልሙ እንዲካተት ፈቃድ መስጠታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ይህንንም ያደረጉት ታሪኩ በፊልም መሠራቱ የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ጥያቄን ያራምዳል፣ ስለጠለፋና ስለጥቃት ግንዛቤ ለመፍጠር ያስችላል በሚል እንጂ ‹‹የእኔ ታሪክ ይነገር›› በሚል እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

ለአበራሽ ጥብቅና በቆሙላት ጊዜ ከዚያም በኋላ አበራሽ በመኖሪያ ቤታቸው ተቀምጣ እንደነበር ቅርበትም እንደነበራቸው የሚያስታውሱት ወ/ሮ መዓዛ፣ ለረዥም ዓመታት ግን ከአበራሽ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሳይኖራቸው እንደቆዩም ይናገራሉ፡፡

ከፊልሙ መሠራት በኋላ ግን የታሪካቸው በፊልም መሠራት ለአበራሽ የሚከፍተው የዕድል በር ይኖራል በሚል ማፈላለግ መጀመራቸው የሚናገሩት ወ/ሮ መዓዛ፣ ስለጉዳዩ በነገሯት መሠረት በመጨረሻ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኗ ደራርቱ ቱሉ የአበራሽን ስልክ ቁጥር እንደሰጠቻቸውና እንዳገኙዋት ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

‹‹ደውዬ ወደ አዲስ አበባ አስመጣኋት፡፡ አሁንም ያለችው እናቴ ቤት ነው፡፡ የእኔ ቤት ወጣ ስለሚል ነው እዚያ እንድትቀመጥ ያደረግኩት፡፡ ከመጣች ወደ ሰባት ወራት ገደማ ሆኗል፤›› የሚሉት ወ/ሮ መዓዛ፣ ወ/ት አበራሽን አሁን እየሠራችበት ያለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እንድትቀጠር ያደረጉት እሳቸው እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡

ወ/ሮ መዓዛ እንደገለጹት ወ/ት አበራሽ ወደ አዲስ አበባ እንድትመጣ ያደረጉት ፊልሙ ጀርመን በርሊን ውስጥ ሊመረቅ በተቃረበበት ጊዜ ነበር፡፡

ለታሪኳ ባለቤት ወ/ት አበራሽ በፊልሙ ሥራ ተሳታፊ ከሆኑት ግለሰቦች ሁሉ ቅርበት ያላት እርሷ እንደመሆኗ የታሪኳ ባለቤት ተጠቃሚነትን በሚመለከት ለወ/ሮ መዓዛ ጥያቄ ቀርቦላቸው በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹መጠቀም እንዳለባት አምናለሁ፡፡ አቶ ዘረሠናይም በዚህ ያምናል፡፡ ይህን ለማድረግም በጣም ፈቃደኛ ነው፡፡ እሷም የምትጠብቀው ነገር አለ፡፡ ችግር የፈጠረው እንዴት በሚለው ላይ አለመነጋገር ነው፤›› ብለዋል፡፡

ወንድማቸው አቶ ፍቅሩ አሸናፊም ፊልሙ ላይ ጥያቄ ማንሳታቸውን በሚመለከት፣ ወንድማቸውና የድፍረት ፊልም ዳይሬክተርና ከፕሮዲዩሰሮቹ መካከል አንዱ የሆነው አቶ ዘረሠናይ ምንም እንኳ የጓደኝነታቸውን ደረጃ መናገር ባይችሉም፣ ጓደኛማቾች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ ወንድማቸው ስለ እርሳቸው ለጓደኛው አቶ ዘረሠናይ ሲያወሩ የፊልም ባለሙያ የሆነው አቶ ዘረሠናይም ታሪኩን ወደ ፊልም ለመቀየር ትልቅ ፍላጐት እንዳደረበትና የፊልሙ መነሻ እንዲህ እንደነበር፣ ከዚህ ውጪ ግን በወንድማቸውና በአቶ ዘረሠናይ መካከል ሌላ ጉዳይ ይኑር አይኑር የሚያውቁት እንደሌለ አስረድተዋል፡፡ ግጭቱ ቀላል እንደሆነ ስለዚህም በጣት በሚቆጠሩ ቀናት ውስጥ ይፈታል የሚል እምነት እንዳላቸው አክለዋል፡፡

የፊልሙ ዳይሬክተር አቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ በእጁ ላይ ያለው የፍርድ ቤት እግድ ብቻ በመሆኑ ስለክሱ ዝርዝር ነገር ሳያውቅ በጉዳዩ ላይ ምንም ዓይነት አስተያየት መስጠት እንደማይፈልግ ለሪፖርተር አስታውቋል፡፡ የባለታሪኳ ወ/ሮ አበራሽ ፈቃድን ማግኘት አለማግኘቱን በተመለከተም አቶ ዘረሠናይ ምንም ማለት አለመፈለጉን ገልጿል፡፡ ጠበቃው ዓርብ ነሐሴ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ የክሱን ቻርጅ ለማግኘት ፍርድ ቤት እንደነበሩና የክሱን ዝርዝር እንዳወቁ ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጥ ገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ዓርብ እኩለ ሌሊት ድረስ ከእሱ በኩል የተሰማ ነገር አልነበረም፡፡

የፊልሙ እግድ ለብሔራዊ ቴአትር ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. አሥራ አንድ ሰዓት ላይ መድረሱን ከሳሾች ቢጠቁሙም፣ የቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሽመልስ እግዱ የደረሰው አሥራ አንድ ሰዓት ከሃያ አምስት ላይ እንደነበር ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

እሳቸው እንዳሉት እግዱ በደረሰበት ወቅት 1,200 ያህል እንግዶች አዳራሹ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አሥር ያህሉ አምባሳደሮችና ባለሥልጣናት ነበሩ፡፡ በአሳጋጆቹ በኩል የነበረው አቀራረብ አስቸጋሪ ስለነበርና በሌላኛውም በኩል ፊልሙን ለማቋረጥ ያለመፈለግ ነገር ስለነበር፣ በአጋጣሚው የአገር ገጽታ እንዳይበላሽ በጥንቃቄ ለመያዝ ቴአትር ቤቱ የተለያዩ ጥረቶችን አድርጓል ብለዋል፡፡

‹‹የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይከበራል፡፡ ይህ ምንም ዓይነት ጥያቄ የለውም፡፡ ነገር ግን በሁሉቱም በኩል የነበረው ነገር ወደ ግጭት የሚያመራ ዓይነት ስለነበር ነገሩ በሰላም እንዲፈታ ፖሊስ ጠርተናል፡፡ ምክንያቱም እኛ ያለን የፀጥታ ኃይል ያን ማድረግ አይችልም ነበር፤›› ሲሉ አቶ ተስፋዬ የነበረውን ሁኔታ አስረድተዋል፡፡

posted by Tseday  Getachew

http://satenaw.com

Advertisements

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ተጨማሪ አራት ቀን እስር ቤት እንዲቆዩ ተደረገ

Blue Party’s executives and female members

Semayawi Party- Ethiopia

ባለፈው ሰኞ ፖሊስ መረጃ ለማሰባሰብ በሚል ፍርድ ቤት የ14 ቀን ጊዜ ጠይቆ 5 ቀናት እንደተፈቀደለት ይታወቃል፡፡ ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ችሎት ቢቀርቡም ፖሊስ አሁንም ‹‹ምርምራውን አልጨረስኩም፣ ተጨማሪ የምይዛቸው ሰዎች አሉ፣ የተያዙትም ቢለቀቁ ሌላ ወንጀል ይሰራሉ›› በሚል ሰባት ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጡት ጠይቋል፡፡

በአንጻሩ የታሳሪዎቹ ጠበቃ ሆነው የቀረቡት የጋዜጠኛ ርዕት አለሙ አባት አቶ አለሙ ጌደቦ በበኩላቸው ፖሊስ ተሰጥቶት የነበሩት ሰባት ቀናት መረጃ ለማሰባሰብም ሆነ ሌሎች የምይዛቸው ተጨማሪ ሰዎች አሉ ያላቸውን ቢኖሩ ኖሮ ለመያዝ በቂ እንደነበር አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም ታሳሪዎቹ በኃላፊነት ቦታ ላይ የሚሰሩና ቋሚ አድራሻ ያላቸው በመሆኑ በዋስ ተለቀው ጉዳያቸውን መከታተል ስለሚችሉ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ተከራክረዋል፡፡Semayawi party activist court show up

በሌላ በኩል ታሳሪዎቹ በምርመራ ወቅት በፖሊስና ‹በደህንነቶች› እየተፈጸመብን ነው ያሉትን በደል ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል፡፡ ‹‹የታሰርነው በያዝነው አስተሳሰባችን ምክንያት ነው›› ያለው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ መታወቂያ ለማሳየት ፈቃደኛ ያልሆኑ ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች ‹‹ሰማያዊ ከሚባል አሸባሪ ወጥታችሁ ከእኛ ጋር ካልሰራችሁ መቼ እንደምንገላችሁ አታውቁም፡፡›› በሚል እንዳስፈራሩዋቸው ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ወንድ ፖሊሶች ሌሊት ሴቶች እስር ቤት ውስጥ በመግባት እንደሚያስፈራሩዋቸውም ተገልጻል፡፡ ሴቶቹ ታሳሪዎች ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ ወንድ ፖሊሶች ከታሰሩበት እያስወጡ እንደሚያስፈራሩዋቸውም የየራሳቸውን አጋጣሚዎች ለፍርድ ቤት አቅርበዋል፡፡ ወጣት አቤል ‹‹ከእኛ ጋር ከሰራህ የተሻለ እንከፍልሃለን›› ብለውኝ አልፈልግም በማለቴ እንገልሃለን ብለውኛል በማለት ገልጹዋል፡፡

በተቃራኒው ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ሌሎች ታሳሪዎች ላይ ቅስቀሳ እያደረጉ መሆኑን፣ በጋራ እንደሚዘምሩ፣ ቃል ለመስጠት ፈቃደኛ እንደማይሆኑ በመግለጽ ተጨማሪ 7 ቀን እንዲሰጠው በድጋሜ ጠይቋል፡፡ ዛሬ ጠዋት ወደ ችሎት ሲመጡ የታላቁን ሩጫ ቲሸርት ካለበስን አንሄድም ማለታቸውንም ታሳሪዎቹ በቀጣይነትም ወንጀል ሊሰሩ ይችላሉ ለሚለው መከራከሪያው እንደ ማስረጃ አቅርቧል፡፡ ዳኛው ፖሊስ በታሳሪዎቹ ላይ እንዳደረሰው የተገለጸውንና ታሳሪዎቹ ሌሎች ታሳሪዎችን በማቀስቀስና በመረበሽ ያቀረበውን ክስ ላይ ምክር አዘል መልዕክት ካስተላለፈ በኋላ ተጨማሪ 4 ቀን የምርመራ ጊዜ ሰጥቷል፡፡

ችሎቱ መደበኛ ስራውን ይጀምራል ከተባለበት አንድ ሰዓት ዘግይቶ ሊጀምር ችሏል፡፡ በክርክሩ ወቅት መረዳት እንደተቻለውም ጠዋት ታሳሪዎቹ ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡበት ጊዜ በሩጫው ዕለት ለብሰውት የነበረውን የታላቁን ሩጫ ቲሸርት መልበሳቸውን ፖሊስ በመቃወሙ በነበረው አለመግባባት መዘግየቱ እንደተከሰተ ታውቋል፡፡

ፖሊስ ሰኞ ዕለት ያስመዘገበው የክስ ጭብጥ እንደሚያመለክተው ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋለው ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ተንቀሳቅሰዋል፣ የጣይቱ ልጆች ነን፣ የምኒልክ ልጆች ነን፣ ዳቦ ራበን፣ ብለዋል በሚል ነው፡፡ በዛሬው የክርክር ሂደት እንደተስተዋለው ግን ፖሊስ የመጀመሪያዋን ጭብጥ ብቻ መዝዞ ተከራክሯል፡፡ መርማሪ ፖሊሱ በወቅቱ አሉኝ ያላቸውን የክርክር ነጥቦች በሚያስረዳበት ወቅት አለመረጋጋት ጎልቶ ይታይበት እንደነበር ተስተውሏል፡፡

http://ecadforum.com/

posted by Tseday Getachew

በንፋስ ስልክ ላፍቶ የመንግስት ታጣቂው የባለ3 ልጆች ባለትዳሮችን በጥይት ደብድቦ ገደለ

ምኒልክ ሳልሳዊ እንደዘገበው 

በንፋስ ስልክ ላፍቶ የመንግስት ታጣቂው የ3 ልጆችን ባልና ሚስትን በጥይት ደብድቦ መግደሉ ተሰማ። ድርጊቱ የተፈፀመው ትላንት ከቀኑ 9.30 አካባቢ ነው ተብሏል።

አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ውስጥ ልዩ ስሙ መካኒሳ አቦ ማዞሪያ በሚባል አካባቢ አንድ የመንግስት ታጣቂ የሶስት ልጆች ወላጆች የሆኑትን ባልና ሚስት በአውቶማቲክ መቺንገን በጥይት ደብድቦ ገድሏቸዋል።

የአካባቢው ሰዎች እና የሟች ዘመዶች በጋራ በመሆን የቀብሩን ስነ- ሥርዓት ለማስፈጸምና የመንግስት ታጣቂው የወሰደው እርምጃ ለማውገዝ እና በየጊዘው በአካባቢው የሚፈጸመውን የመንግስት ታጣቂዎች እርምጃ እና በህብረተሰቡ ላይ የደረሰውን ግፍ በጋራ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ለማጋለጥ በህብረት ድምጻቸውን ለማሰማት ሲሞክሩ በፈደራል ፖሊስ የተበተኑ ሲሆን በአካባቢው ላይ የአዲስ አበባ የፖሊስ ሃይሎች ተሰማርተዋል።

የፈደራል ፖሊስ አመራሮች የአከባቢውን ህዝብ የፖለቲካ አጀንዳ ያለው ሲሉት የፈረጁት ሲሆን ቀብሩ ሳይፈጸም ህዝቡን በማስፈራራት እና በዛቻ ያባረሩት ሲሆን የሟች ዘመዶች የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን ጉዳችንን ሳይሰማና ሳያውቅልን አንቀብርም ብለው አስከረኖቹ ወደ መኖሪያ ቤት ተመስልሷል።

ለዘ-ሐበሻ ዘግየት ብሎ በደረሰን መረጃ ቀብሩ በነገው እለት ይፈጸማል።

Ze-Habesha

posted by Tseday Getachew

የባህር ዳር ህዝብ ሆ ብሎ ወጣ!! ህዝቡ “ከባዶ ጭንቅላት… ባዶ እግር ይሻላል፡፡” አለ!

(ዜና ጥንቅር ዳዊት ከበደ ወየሳ)
የተቃውሞ ሰልፉ መነሻ የብአዴኑ ምክትል ሊቀመንበር አለምነው መኮንን የአማራውን ህዝብ በመናቅ እና በመሳደብ የተናገሩት ቃል ነው:: አማራውን… “በባዶ እግሩ እየሄደ ሌላውን ይንቃል” ካሉ በኋላ ለአማራው የሚቆረቆሩትን ደግሞ “ለሃጫቸውን…” እና የመሳሰሉትን እዚህ ላይ ለመጻፍ የምንጸየፋቸውን ቃላቶች ጭምር በመጠቀም አሽሙር አይሉት ስድብ ሰንዝረዋል:: ነገሩ ከአንድ የአማራን ህዝብ እወክላለሁ ወይም እመራለሁ ከሚል ሰው የሚጠበቅ ባለመሆኑ ብዙዎችን አሳዝኗል፣ አናዷልም::

በመሆኑም የአንድነት እና የመኢአድ ፓርቲዎች በጥምረት ሆነው በባህር ዳር ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ወሰኑ:: ምክትሉ ሊቀመንበሩ ከሰልፉ በፊት እንደበፊቱ በትእቢት ተወጥረው ሳይሆን ረጋ ብለው ምን ለማለት እንደፈለጉ ቢያስረዱም ህዝቡ ግን ተቃውሞውን ቀጠለበት:: ለነገሩ በዚህ አጋጣሚ ሌሎች የሚነሱ የህዝብ ብሶቶች እንዳይነሱ በመስጋት የክልሉ አስተዳዳሪዎች አንዳንድ እንቅፋቶችን ለመፍጠር መሞከራቸው አልቀረም:: እርግጥ ነው… ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የተቃውሞ ሰልፉን ለማድረግ ሲዘጋጁ ብዙ እክል ገጥሟቸው ነበር:: ከተማ ውስጥ በራሪ ወረቀት መስጠት እና ቅስቀሳ ማድረግ ጭምር ተክልክለዋል:: ሆኖም ህዝቡ ራሱ ከልካዮቹን በመቃወሙ የፖሊሶቹ እገታ እና ጫና በረድ አለ:: ተቃዋሚዎቹ በባዶ እግር መሄድ ማለት ምንም ማለት እንዳልሆነ ለማሳየት ቅስቀሳ ሲያደርጉም ሆነ ዛሬ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ… ጫማቸውን አውልቀው በባዶ እግራቸው ነበር የታዩት::

bahrdar demo13 2232014

ዛሬ እሁድ… እ.ኢ.አ የካቲት 16, 2006 ባህር ዳር ቀበሌ 12፣ ግሽ አባይ በሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ ሰልፉ ሲጀመር የተለያዩ መፈክሮች እየተደመጡ ነው፡፡ በሰልፉ የፊት ረድፍ ላይ የፓርቲው ሊቀ መንበር ኢንጂነር ግዛቸው፣ ዶ/ር ኃይሉ አርአያ እና ሌሎችም አመራሮች ከህዝቡ ጋር ሆነው ታይተዋል:: ከግሽ አባይ የተነሳው ሰልፈኛ ጉዞውን በባህር ዳር ጎዳናዎች ላይ ማድረግ ሲጀምር ሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ የከተማው ነዋሪዎች ሰልፈኛውን ተቀላቅለዋል:: የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የያዙ ወጣቶች ከፊት ሆነው መፈክር በማሰማት ከተማዋን ከጠዋት እንቅልፏ አባነኗት:: የባህር ዳሩን የተቃውሞ ሰልፍ የአንድነት ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ፣ የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ከፊት በመምራት ላይ ይገኙ ነበር::
bahrdar demo7 2232014

ከባህር ዳር በደረሰን ዘገባ መሰረት… ህጻናት ልጆቻቸውን በጀርባቸው ያዘሉ፣ በዊልቼይር የሚሄዱ፣ አዛውንቶች፣ ወጣቶች በአንድነት ሆነው በባህርዳር ከተማ የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡
bahrdar demo9 2232014
ሰልፉ ከመጠናቀቁ በፊት ቁጥራቸው 15 ሺህ ያህል ሰዎች እንደነበሩ ነው ከስፍራው የተዘገበው:: በወቅቱ ከተያዙት መፈክሮች የተወሰኑት…
“የመሬት ቅርምቱ ያብቃ!”
“ህዝብን ከርስቱ ማፈናቀል ይቁም”
“ገበሬው በገዛ መሬቱ ስደተኛ አይሆንም”
“የህዝብን ክብር የደፈሩት አቶ አለምነው ለፍርድ ይቅረቡ”
“ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል”
“ህዝብን እየሰደቡ መግዛት አይቻልም”
“ድል የህዝብ ነው”
“አቶ አለምነው የሰደቡት የአማራን ህዝብ ብቻ አይደለም”
“ብአዴን /ኢህአዴግ የአማራን ህዝብ የመምራት የሞራል ልእልና የለውም”

ከስፍራው ሁኔታውን እየተከታተለ በቀጥታ ሲዘግብ የነበረው ነብዩ ሃይሉ እንደገለጸው ከሆነ… በሰልፉ ላይ አቶ አለምነው በአማራ ህዝብ ላይ የተናገሩት የጥላቻ ንግግር ለሰልፈኛው ተለቆ ህዝቡ ንግግሩን በቁጭት በብአዴን ላይ ተቃውሞውን እያሰማ ነው፡፡
“ክብራችንን የደፈሩት የብአዴን አባላት ለፍርድ ይቅረቡ”
“ነፃነታችን በእጃችን ነው”
“ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል፡፡”
“ብአዴን የአማራን ህዝብ ለመምራት የሞራል ልዕልና የለውም”
“መተማ የኛ ነው፣ ቋራ የኛ ነው” በሰልፉ ላይ ከተስተጋቡ መፈክሮች መሀከል ይገኝበታል፡፡ ሰልፉ በህዝብ እንደታጀበ ቀጥሏል፡፡

በመጨረሻም የየፓርቲዎቹ ተጠሪዎች ለህዝቡ ንግግር አድርገዋል:: አቶ አበባው መሃሪ 1-አቶ አለምነው መኮንን በህግ እንዲጠየቅ
2- ብአዴን የአማራ ህዝባ ወኪል ነኝ ማለቱን እንዲያቆም
3-አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁ አሳስበዋል፡፡
የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ በንግግራቸው… አቶ አለምነው እንዲህ እንዲናገሩ ያደረገውን አምባገነን የኢህአዴግ ስርአት ለመቀየር እንስራ ብለዋል፡፡

የሰላማዊ ሰልፉን የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ፕሬዘዳንት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ናቸው፡፡ ኢንጂነሩ የመግቢያ ንግግራቸውን የከፈቱት በዛሬው እለት ደስ ካሰኙን መፈክሮች “ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል” የሚለውን በማለት ነበር፡፡ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው በንግግራቸው መጨረሻ ላይ አቶ አለምነው ይቅርታ ካልጠየቀና በህግ ፊት ካልቀረበ አንድነት በድጋሚ በባህርዳር የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚጠራ አሳውቀዋል፡፡

አሁን ሰልፉ ተጠናቆ ህዝቡ በሰላም እንደወጣ፣ በሰላም ወደ ቤቱ እየተመለሰ ነው:: የሰላማዊ ሰልፉ በሰላም መጠናቀቅ የህዝቡን ጨዋነትና የአመራሩን ብስለት ያሳያል:: እርግጥ ነው… ሰላማዊ ሰልፉ ተጠናቆ ህዝቡ በሰላም ወደቤቱ ቢያመራም… ባህር ዳር ላይ የተለኮሰው የመነቃቃት ስሜት ግን በቀላሉ የሚበርድ አይመስልም:: እኛም መልካሙን ሁሉ እየተመኘን ዘገባችንን እዚህ ላይ አጠናቀናል::

EMF

posted by Gheremew Araghaw

ኢትዮጵያውያን ረዳት ፓይለቱን በመደገፍ በዋሽንግተን ዲሲ የስዊዘርላንድ ኢምባሲ ደጃፍ የፊታችን ሰኞ ሰልፍ ሊወጡ ነው

(ዘ-ሐበሻ) ሰኞ ዕለት ሮም ላይ ማረፍ የነበረበትን አውሮፕላን ስዊዘርላንድ ላይ እንዲያርፍ ያደረገው ኢትዮጵያዊው ረዳት ፓይለት “የታፈነውን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጥሰት ለዓለም ያሳየ ጀግና ነው” የሚሉ ኢትዮጵያውያን የፊታችን ሰኞ ጠዋት ፌብሩዋሪ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ የስዊዘርላንድ ኢምባሲ ደጃፍ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ። የስዊዘርላንድ መንግስት ነገ ወይም ከነገ በስቲያ በረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

በዋሽንግተን ዲሲ የስዊዘርላንድ ኢምባሲ ደጃፍ የተጣራው ይኸው ሰልፍ ረዳት አብራሪው አውሮፕላን ጠላፊ አሸባሪ እንዳልሆነና ድርጊቱን የፈጸመው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ በስርዓቱ ውስጥ የሰፈነውን የአንድ ብሔር የበላይነትን ለዓለም ለማሳየት የተጠቀመበት ዘዴ በመሆኑ የስዊዘርላንድ መንግስት የጥገኝነት ጥያቄውን እንዲቀበለው እንደሚጠይቅ ከሰልፉ አስተባበሪዎች ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

“ለወገን ደራሽ ወገን ነውና ይህ ወንድማችን ለኛ ነፃነት የታፈነውን ያገራችንን ህዝብ በአለም አደባባይ ያንድ ዘር ብቻ የነገሰው የዘረኛው ወያኔን ስራ ለአለም ያጋለጠ ጀግና ወንድማችን አሸባሪ ሳይሆን የነፃነት ታጋይ ወንድማችን መሆኖን ለመግለጽ ይህን ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል” ያለው የዋሽንግተን ዲሲው ሰልፍ አስተባባሪዎች ጥሪ ፍላየር ለዘ-ሐበሻ ደርሷታል። ሰልፉ የሚደረገው Embassy of Switzerland in the United States of America ሲሆን አድራሻውም ፦ 2900 Cathedral Ave., NW, Washington, D.C. ነው።

ረዳት ፓይለቱን በመደገፍ ተመሳሳይ ሰልፍ በስዊዘርላንድና በሌሎች ሃገራት ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑ የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ይህ በ እንዲህ እንዳለ የስዊዘርላንድ መንግስት በረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራ ዙሪያ ነገ ወይም ከነገ በስቲያ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል። ይህንን ተከትሎም በርካቶች ጋዜጣዊ መግለጫውን በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው።

Ze-Habesha

posted by Tseday Getachew

በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ዙሪያ የቴሌኮንፍረንስ ጥሪ ለመላው ኢትዮጵያውያን

ሸንጎ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ዙሪያ ሕዝባዊ ውይይትና ገለጻ ለማድረግ የፊታችን እሁድ ፌብሩዋሪ 9 ቀን 2014 ቴሌኮንፈርንስ ጠርቶ ማንኛውም ስለድንበሩ ያገባኛል የሚል ኢትዮጵያዊ እንዲገኝ ጥሪውን አቅርቧል። የጥሪው ወረቀት የሚከተለው ነው፦

https://i1.wp.com/www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2014/02/shengo-forum.jpg

posted by Tseday Getachew

“ባለስልጣኑ ካልተባረረ ዳሽን ቢራን አንጠጣም” የሚል ማእቀብ ተጠራ

Share Button

በአማራ ሕዝብ ተቋቁሞ ሆኖም ግን የጥቂት ብአዴን ባለስልጣናት ከርስ መሙያ ሆኗል የሚባለው ዳሸን ቢራ ላይ ኢትዮጵያውያን የመጠጣት ማእቀብ (ቦይኮት) እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ። ጥሪው የቀረበው ሰሞኑን በተለያዩ የሶሻል ሚድያዎች የክልሉ ባለስልጣን የሆኑት አቶ አለምነህ መኮንን እመራዋለሁ የሚሉትን የአማራ ሕዝብ ለመጻፍ በሚከብዱ ጸያፍ ቃላት ሲሳደቡ የሚያስደምጥ ድምጽ ከተለቀቀ በኋላ በተቆጡ ኢትዮጵያውያን ነው።

የቦይኮት ጥሪው በፌስቡክ እና ትዊተርን በመሳሰሉ ታላላቅ የሶሻል ሚዲያዎች እየተሰራጨ ሲሆን በተለይም አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች በተለይም በአማራ ክልል የዳሽን ቢራን አንጠጣም የሚለው አድማ በሰፊው እንደተሰማ ነው። የቦይኮቱ እንስቃሴ መሪዎች በሶሻል ሚድያ እንደገለጹት ብአዴን የተባለው በአማራው ሕዝብ ስም የተቋቋመው የሕወሓት ተላላኪ ድርጅት እንደ አቶ አለምነህ መኮንን ያሉ ሰዎችን በስሩ ይዞ የሚቀጥል ከሆነ ይህ ዳሸን ቢራን ያለመጠጣት አድማ ይቀጥላል።

አቶ አለምነህ መኮንን ሕዝብን በመናቅ አንድን የተከበረ ሕዝብ በአጸያፊ ቃላት ሲናገሩ ማድመጥ በጣም የሚሰቀጥጥ መሆኑን የሚገልጹት እነዚሁ የቦይኮት ዳሸን ቢራ አስተባባሪዎች ሰውዬው ከስልጣናቸው ወርደው ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።

በሶሻል ሚድያዎች የተበተነውና ብዙዎች በየገጻቸው ላይ እያባዙት የሚገኘው የቦይኮት ዳሸን ቢራ መልዕክት የሚከተለው ነው፦

EMF

posted by Tseday Getachew

የ2014 የዓለም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ ኢትዮጵያ 25ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች

coup map

January 30, 2014 07:32 am By  Leave a Comment

በያዝነው የአውሮጳውያን ዓመት ሊከሰቱ የሚችሉ የመፈንቅለ መንግሥት አደጋዎች ይፋ ሆኑ፡፡ በርካታዎቹ በአፍሪካ አገራት ሲሆኑ አደጋው ካንዣበበባቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ 25ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

በአሜሪካ የፖለቲካ ሳይንቲስት የሆኑት ጄይ ዑልፌልደር የተለያዩ የሒሳብ ስሌቶችን በመጠቀም የ2014ዓም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያቸውን ሰጥተዋል፡፡ እንደ እርሳቸው ትንበያ ከሆነ 40 አገራት ቀይ የአደጋ ምልክት በርቶባቸዋል፡፡ ስለ ጉዳዩ ሲናገሩ መፈንቅለ መንግሥት እንዲሆን የሚመኙት ነገር ባይሆንም የመከሰቱ ጉዳይ ግን መነገር ያለበት ነው ይላሉ ምሁሩ፡፡

በተለያዩ የአሜሪካ አንጋፋ ጋዜጦች ላይ የተዘገበው ይኸው ጥናት እንደሚያመለክተው በዓለማችን ላይ 40 አገራት ከፍተኛ የመፈንቅለ መንግሥት አደጋ ያነጣጠረባቸው መሆናቸውን በጥናቱ ተገልጾዋል፡፡ አብዛኛዎቹም ከአፍሪካ መሆናቸው አሁንም አህጉሪቱ ለበለጠ ቀውስ የተጋለጠች መሆኗን የሚያሳይ ነው፡፡

በቀዳሚነት የመፈንቅለ መንግሥት የሚያሰጋቸው አገራት ጊኒ፣ ማዳጋስካር፣ ማሊ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኒጀር፣ ጊኒ ቢሳው እና ሱዳን፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክና ደቡብ ሱዳን ናቸው፡፡ ከአውሮጳ ምንም አገር በዝርዝሩ ውስጥ ያልገባ ሲሆን ዩክሬይን አደጋው ጥላ ካጠላባቸው በቀዳሚነት የምትጠቀስ ሆናለች፡፡ ከወደ አሜሪካ ዩኳዶርና ሃይቲ ቀዩ የአደጋ ምልክት የታየባቸው ሲሆን ከእስያ ታላንድ፣ አፍጋኒስታን እና ፓኪስታንን ጨምሮ ስድስት አገራት የመፈንቅለ መንግሥት የቀይ ምልክት አደጋ ካለባቸው 40 አገራት ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ከ40ዎቹ ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ 25ኛ ላይ ትገኛለች፡፡ በየጊዜው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ህወሃት/ኢህአዴግ ሥልጣኑን ለራሱ ታማኞች ብቻ በመከፋፈል እንዲያም ሲል በቤተሰብ ደረጃ በማውረድ እየሸነሸነው በመሆኑ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የበይ ተመልካች ሆኗል፡፡ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሰሞኑን ያወጣውን መረጃ ጠቅሶ አዲስ አድማስ ሲዘግብ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ መጥበቡን እና የነጻው ሚዲያ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን ገልጾ ነበር፡፡

አፋኝ ሕጎችን በማውጣትና ማንኛውንም ዓይነት የግለሰብ መብት በመንፈግ በአንጻሩ ሊኖር የማይችል የቡድን መብት አስከብራለሁ የሚለው ህወሃት/ኢህአዴግ በተመሳሳይ የሚወጡ መረጃዎችን በማጣጣል ዋጋ ቢስ ሲያደርግ መቆየቱን የተለያዩ የሲቪክ ማኅበራትና የፖለቲካ ፓርቲዎች በየጊዜው የሚያነሱት ነጥብ ነው፡፡ በተቀረው ደግሞ “ልማት፣ ህዳሴ፣ ውዳሴ፣ … ” በማለት የለውጥ ሃሳብ ከመጣ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ይስተጓጎላሉ በሚል በሕዝቡ ዘንድ ማደናገሪያ በመፍጠር በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን የፖለቲካ ፓርቲዎች “ጸረ ልማት” በማለት እንደሚወነጅላቸው ያማርራሉ፡፡ በምርጫ ማጭበርበርና ማንኛውንም ፖለቲካዊ ሆነ ማኅበራዊ እንዲሁም ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ በሙሉ ቁጥጥር ሥር ማዋል ኢህአዴግ በሥልጣን ለመቆየት የሚጠቀምባቸው ዓይነተኛ መንገዶቹ እንደሆኑ በስፋት ይጠቀሳል፡፡

ይህንን የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ የቀመሩት ምሁር ስሌታቸውን ለማቀናበር የተለያዩ መረጃዎችን መጠቀማቸውን ገልጸዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል የአገራቱ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ፣ በቅኝ ግዛት የመያዝ ሁኔታ፣ የአገራቱ ዕድሜ፣ ከነጻነት በኋላ የኖሩበት ዓመታት፣ የፖለቲካ መረጋጋት፣ የእርስበርስ ግጭት፣ የነጻ ምርጫ ሁኔታ፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ በየቀጣናው ያለ የመፈንቅለ መንግሥት እንቅስቃሴ፣ ወዘተ የተወሰኑት ናቸው፡፡ ይህንን አያይዘውም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ ማድረግ የግድ መፈንቅለ መንግሥት ይሆናል ማለት እንዳይደለ ነገር ግን አደጋውን ተመልክቶ አስፈላጊ እርምጃዎች በመውሰድ እንዳይሆን መከላከል ዓይነተኛ አማራጭ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ (ካርታዎቹ የተወሰዱት ከጄይ ዑልፌልደር ብሎግ ነው)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የዛሬ ዓመት የአሜሪካንን የደኅንነት ምክርቤት ጠቅሶ ባወጣው ዜና በ2030 እኤአ ከሚከሽፉ መንግሥታት (failed states) መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ዘግቦ ነበር፡፡ ዜናውን ከዚህ በታች በድጋሚ አትመነዋል፡፡


“በ2030 ከሚከሽፉ መንግሥታት አንዷ ኢትዮጵያ ነች”

ዘገባው የ15 አገራትን ዝርዝር አውጥቷል

የአሜሪካ የብሔራዊ የደኅንነት ምክርቤት እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2030 የሚከሽፉ 15 መንግሥታትን (failed states) ዝርዝር አውጥቷል፡፡ “በግጭት መብዛትና በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ምክንያት” ይከሽፋሉ ተብለው ከተተነበዩት የአፍሪካ፣ የእስያና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ነች፡፡

እጅግ የነጠረ፣ ያልተዛባና የተጠና ዘገባ ለአሜሪካ የስለላ ተቋማት፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አውጪዎችና ለዓለምዓቀፍ ግንኙነት ተመራማሪዎች በማውጣት የታወቀው የአሜሪካ ብሔራዊ የደኅንነት ምክርቤት ከተቋቋመ በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ምክርቤቱ በሚያወጣቸው ዘገባዎች የአሜሪካ መንግሥትም ሆነ የተለያዩ መ/ቤቶች ተጽዕኖ እንደማያደርጉበት የሚናገር ሲሆን፤ ዘገባዎቹንም ከአድልዎ እና ከአሜሪካ መንግሥት አቋም ነጻ በመሆን እንደሚያዘጋጃቸው ይናገራል፡፡

የም/ቤቱ ዘገባ በተለይ ምርጫ ከተካሄደ በኋላ ለመጪው ፕሬዚዳንት የወደፊቱን የዓለማችን መልክ ምን እንደሚመስል የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ አስተሳሰቦች እና ዓለምአቀፋዊ ዝንባሌዎች ላይ አቅጣጫ የሚጠቁም ትንበያ ያደርጋል፡፡ ለፕሬዚዳንቱ ዓለምአቀፋዊ የደኅንነት ዘገባ ያቀርባል፤ ለብሔራዊ የጸጥታ ምክርቤት እና ለአገር ውስጥ ደኅንነት መ/ቤት ምክር ያቀብላል፤ በአጠቃላይ የአሜሪካን የስለላና የደኅንነት ማኅበረሰብ ሊከተል በሚገባው ጉዳይ ላይ አቅጣጫ የሚያስይዝ ሃሳብ ያቀርባል፡፡

በዚሁም መሠረት ባለፈው የታህሳስ ወር “በ2030 የዓለም አቅጣጫ፡ አማራጭ አገራት” በሚል ርዕስ አንድ ዳጎስ ያለ ጥናት አቅርቧል፡፡ ይኸው 160ገጽ ያለው ዘገባ የዛሬ 17ዓመት የዓለማችን ገጽታ ምን እንደሚመስል ከየአገራቱ በተወሰደ ጥናትና እዚያው በሚገኙ ተመራማሪዎች የሰበሰበውን ያካተተ ነው፡፡ ዓለማችን የምታዘነብልባቸው ቀዳሚ ሁኔታዎች አንዱ ሰዎች በራሳቸው አነሳሽነት ድህነትን ለመቀነስ፣ በትምህርት ለማደግ፣ በቴክኖሎጂና በህክምና ለመራቀቅ እንዲሁም በገቢም የመካከለኛው መደብ ላይ ለመድረስ የሚያደርጉት ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ከተጠቀሱት አንዱ አቅጣጫ ጠቋሚ ነው፡፡

ሌሎቹ ዓለምን አንድ አድርጎ በመዳፉ ሥር የሚገዛ ኃይል የማይነሳ መሆኑ ከሚታዩት ከፍተኛ ዝንባሌዎች ተጠቃሽ ሲሆን አሜሪካ ምንም እንኳ “የዓለም ፖሊስ” የመሆኗ ሁኔታ የሚቀንስ ቢሆንም የዓለምን አቅጣጫ መቆጣጠሯ ይቀራል ማለት እንዳልሆነ ይጠቁማል፡፡ የዓለም የሕዝብ ቁጥር ከመጨመሩ አኳያ “እያረጁ” የሚሄዱ አገራት የኢኮኖሚ ዕድገታቸው እንደሚያሽቆለቁልና ከገጠር ወደከተማ ፍልሰት እንደሚጨምር፤ 60በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ሕዝብ በከተሞች አካባቢ ኑሮውን እንደሚያደርግ ይተነብያል፡፡ በዚህም ምክንያት የውሃ፣ የምግብና የኃይል (ኤነርጂ) ፍላጎት ከሕዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያድግ ይናገራል፡፡ የቴክኖሎጂ ምጥቀትና የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎትም የዓለማችንን አቅጣጫ እንደሚቀይር ያስረዳል፡፡

የቻይና እና የአሜሪካ ግንኙነት በስፋት እንደሚቀጥልና በበርካታ ፈርጆች ትብብርና ስምምነት እየፈጸሙ ሰፋ ያለ ዓለምአቀፋዊ ኅብረት እንደሚያደርጉ የሚናገረው ይህ ሪፖርት በየአገራቱ እየሰፋ የመጣው በድሃና በሃብታም መካከል ያለው ክፍተት የማኅበራዊ ቀውስ እንደሚያስከትል ይጠቁማል፡፡ ይህም ቀውስ በአንዳንድ አገራት ውስጥ እየሰፋ በመምጣት ለተባባሰ ግጭትና ክስረት እንደሚያጋልጥ የኑሮ ልዩነቱም የማኅበራዊ ቀውሱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንደሚያደርሰው ይተነትናል፡፡ የሃይማኖት ሚና እንደሚጨምር የጠቆመው ዘገባ ይህንኑ ተከትሎ መካረርና ግጭት እንዲሁም አሸባሪነት ለመስፋፋት ሃይማኖት ምክንያት እየሆነ እንደሚሄድ ይናገራል፡፡

በዘገባው ከተነገረው በተጻጻሪ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተጠናቀቀ ወዲህ እስካሁን በ44 አገራት ጉዳይ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ጣልቃ በመግባት ጦርነት ያካሄደችው አሜሪካ የዓለም ኃያል ሆና እንደምትቀጥል በመናገር ሪፖርቱን የሚያጣጥሉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ እንደማስረጃም አድርገው አሜሪካ በተለያዩ አገራት ያላትን 737 የወታደራዊ ተቋማት ይጠቅሳሉ፡፡ ስለሆነም ዘገባው የአሜሪካ የበላይነት የመቀነሱን ጉዳይ አንስቶ የተናገረውን አይቀበሉም፡፡

እኤአ በ2030 የሚክሽፉት 15ቱ መንግሥታት (ፎቶ: ጂአይ)

ዘገባው የዓለማችንን የወደፊት ሁኔታ ሲተነብይ በዋንኛነት ከጠቀሳቸው ጉዳዮች አንዱ በ2030 የሚከሽፉ መንግሥታትን ዝርዝር ሰጥቷል፡፡ “በግጭት መብዛትና በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ምክንያት” የሚከሽፉ መንግሥታት ተብለው ከተጠቀሱት 15 አገራት መካከል ኢትዮጵያ እንዷ ስትሆን አፍጋኒስታን፣ ፓኪስታን፣ ባንግላዴሽ፣ ቻድ፣ ኒጀር፣ ማሊ፣ ኬኒያ፣ ቡሩንዲ፣ ሩዋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ፣ ማላዊ፣ ሃይቲና የመን የተቀሩት ናቸው፡፡

ይሁንና ይኸው ም/ቤት እኤአ በ2015 ፓኪስታን የምትከሽፍ አገር ትሆናለች በማለት ትንቢት ሰጥቶ ይኸው እስካሁን አለች በማለት ዘገባውን የሚያጣጥሉ ክፍሎች ኢትዮጵያም ሆነ ሌሎቹ አገራት ለመክሸፋቸው በቂ ማስረጃ የለም በማለት የዘገባውን ጥቆማ ይቃረናሉ፡፡ በሌላ በኩል እንዲህ ያለው የመክሸፍ ሁኔታ ሊዋጥለት የማይችለው ኢህአዴግ “ህዳሴ፣ ውዳሴ” ከማለት ይልቅ ይህንን ጉዳይ አጥብቆ ሊያስብበት እንደሚገባና የሥርዓት መበስበስ አመላካች የሆነውን “የመንግሥት ሌቦች” መበራከት መፍትሔ ሊያበጅለት እንደሚገባ ደጋፊዎቹና አመራሩ በየጊዜው የሚያነሱት ነጥብ ነው፡፡

በዚሁ የኢትዮጵያ እንደ አገር የመክሸፍ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው አሁን ካላቸው ተግባር አኳያ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በአውሮጳ የሚገኙ የፖለቲካና ዓለምአቀፋዊ ግንኙነት ተመራማሪ “ችግሩ የኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን የተቃዋሚውም ነው” ይላሉ፡፡ “በአገር ውስጥ ያለው ተቃዋሚ ከውስጥ የሥልጣን ሽኩቻና ከስብሰባ/ውይይት ጋጋታ ባለፈ መልኩ ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ሊያደርግ የሚችል የተቀናጀና ውጤታማ ተግባር ሊፈጽሙ ይገባቸዋል” የሚሉት ምሁር በውጭ ያለውም “ከጊዜያዊና ጥቃቅን የራስ ክብር የመፈለግ አካሄድ በመላቀቅ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ ጡንቻውን በወያኔ ላይ ማሳረፍ ይጠበቅበታል” ብለዋል፡፡ “የደኅንነት ተቋሙ ባወጣው ዘገባ ላይ በግልጽ እንደተነበየው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ የመጨመሩ ያህል በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ይህንኑ ለውጥ ማምጣት የሚችል የዘመኑ ቴክኖሎጂ ለአሉባልታና ተራ የፖለቲካ ወሬ ከመጠቀም ይልቅ አገር ለማዳን ተግባር ሊጠቀምበት ይገባል” በማለት አስተያየታቸውን ደምድመዋል፡፡

የደኅንነት ምክርቤቱ ያወጣው ሙሉ ዘገባ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡

(http://www.goolgule.com/)

postd by Tseday Getachew


 

Prof. Mesfin W.Mariam speaks about the Ethio-Sudan Border issue (VIDEO)

EMF

poasted by Tseday Getachew

በሽብርተኝነት ህጉ ውይይት ስም የአዲስ አበባ ህዝብ እየተሸበረ ነው ሲሉ አንዳንድ ተወያዮች ገለጹ

 

ጥር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  :-በቅርቡ በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞችና በተዋረድም ከህዝቡ ጋር እተደረገ ባለው የሽብርተኝነት ህግ ውይይት፣  ነዋሪዎች ጥላቸውን እንኳን ማመን እንደሌለባቸው በአሰልጣኞች እየተነገራቸው ሲሆን፣ በስልጠናው ላይ የተካፈሉ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች፣ ስለሽብረተኝነት ልንማር ሂደን ተሸብረን መጣን ሲሉ ተናግረዋል።

በመንግስት  ከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀው የማሰልጠኛ ሰነድ ኢሳት እጅ የገባ ሲሆን፣ ሰነዱ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን ቆሞ ልማቱን እንዲጠብቅና እንዲያፋጥን ይጠይቃል። በመስተዳድሩ የሚገኙ  የቢሮ ሃላፊዎች፣ በአዲስ አበባ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር በሆኑት በአቶ ተወልደ ወ/ጻዲቅ መሪነት በሰነዱ ላይ ውይይት አድርገውበታል ። በሰነዱ ላይ የመስተዳድሩ የየደረጃው  አመራሮችና ሲቪል ሰራተኞች እንዲሁም የከተማው  ህዝብ እየተወያዩበት ነው።

እስካሁን ባተካሄደው ውይይት እንደታየው የመንግስት ሰራተኞች በስልጠናው ላይ የሚገኙት የስም ምዝገባ ስላለ  እንጅ በዝግጀቱ አምነውበት አይደለም ይላሉ ተሳታፊዎች።

በውይይቶች ወቅት የመንግስት ባለስልጣኖች ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጡት ከህዝቡ ስለሚጠበቀው ግዴታ መሆኑን የሚናገሩት ተሳታፊዎች ፣ የአገሪቷን ደህንነት ፖሊስና የደህንነት ሃይሉ ጠብቆ ስለማይችል፣ ህዝቡ ከኮሚኒቲ ፖሊስ ጋር በመተባበር ነቅቶ መጠበቅ እንዳለበት ባለስልጣኖች ማሳሰቢያ መስጠታቸውን ተሰታፊዎች ይገልጻሉ።

የፌደራል ፖሊስ ሽብርተኝነትን ለመከላከልና ወንጀለኛን ለመለየት የአፍና የጸጉር ምርመራ ሊያደርግ እንደሚችል፣ ምርምራው እንዲደረግበት የተጠረጠረ ሰው ፈቃደኛ ካልሆነ ተመጣጣኝ ሃይል በፖሊስ ሊወሰድበት እንደሚችል፣  በማንኛውም ጊዜ በድነገት በከተማ ባስና በታክሲ ላይ ፍተሻ ሊደረግ ስለሚችል ህዝቡ መተባበር እንዳለበት የመንግስት ባለስልጣናት ተናግረዋል።

የመንግስት ሰራተኞች  ቦርሳ፣ፌስታልና መሰል ቁሳቁሶችን ቢሮ ውስጥ ጥለው እንዳይሄዱ የተነገራቸው ሲሆን ፣ ቢሮ ውሰጥ የተገኙ ፌስታሎችና ቦርሳዎች ለአደጋ ከማጋለጣቸው በፊት በጥንቃቄ እንዲታዩ ምክር ተሰጥቷል።

ለማወያያነት በቀረበው ሰነድ ላይ በግልጽ እንደሚታየው “ከፍርድ ቤት ፈቃድ በመውሰድ በሽብርተኝነት የተጠረጠረን ሰው የስልክ፣ የሬዲዮ፣ የኢንተርኔት የኤሌክትሮኒክስ፣ የፋክስ፣ የፖስታ ግንኙነት እና የመሳሰሉ ግንኙነቶችን ለመጥለፍ ወይም ለመከታተል፣ ጠለፋውን ለማስፈፀም ወደ ማንኛውም ቤት በሚስጢር የመግባት ወይም ይህንኑ ለመፈጸም የሚያስችሉ መሳሪያዎችን ለማስቀመጥ ወይም ለማንሳት የፌደራል ፖሊስ ስልጣን ተሰጥቶታል።

እንዲሁም “ ማስረጃ ከሚሰበሰብባቸው የተለያዩ ዘዴዎች መካከል አንዱ በሽብርተኝነት ወንጀል ከተጠረጠረው ሠው ላይ ናሙናዎችን መውሰድ እና የህክምና ምርመራ እንዲያደርግ ማድረግ በመሆኑ ፣ ተጠርጣሪውም በምርመራ ሂደት ናሙናውን ለመስጠት ወይም የህክምና ምርመራ ለማድረግ ፍቃደኛ ካልሆነ ፖሊስ ተመጣጣኝ ኃይል ተጠቅሞ ናሙናውን የመውሰድ ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡

ሰነዱ “ የሀይማኖት አክራሪነትና አሸባሪነት ዋናው ምንጭ ድህነትና ተስፋ መቁረጥ ” መሆኑን ከገለጸ በሁዋላ ፣  ”ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ፈጣን ልማት ለማረጋገጥ በመንግስት የወጡ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና እቅዶች ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ሰፊ ርብርብ ማድረግ” ከህብረተሰቡ እንደሚጠበቅ ይገልጻል።

ኢሳት አስተያታቸውን የጠየቃቸው ሰልጣኞች እንዳሉት ውይይቱ ህዝቡን የበለጠ የሚያሽብር ቢሆንም መንግስትም ሽብር ውስጥ መግባቱን ያመለክታል።

በሰነዱ ላይ  ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት7፣ አልሸባብና አልቃይዳ አሸባሪ ድርጅቶች ተብለዋል

 

posted by Tseday Getachew

በቁጫ ከታሰሩት መካከል 13 ቱ ፍርድ አገኙ

በቁጫ ከታሰሩት መካከል 13 ቱ ፍርድ አገኙ

ጥር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  :-የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥር 16፣ 2006 ዓም ባስቻለው ችሎት በእነ አቶ ደፋሩ ዶሬ መዝገብ የተከሰሱ 13 ሰዎች በሙሉ በ2 አመት ከ9 ወራት እስር እንዲቀጡ ወስኗል። በውሳኔው መዝገብ ላይ እንደተመለከተው እስረኞቹ የተፈረደባቸው “ እኛ ወይም ቁጫ የጋሞ ብሄረሰብ አይደለንም በሚል ህዝብን አነሳስታችሁዋል፣ ህገወጥ ስብሰባ አድርጋችሁዋል፣ እንዲሁም የጸረ- ህዝብ አቋም አራምዳችሁዋል” በሚል ነው።

እነዚህ እስረኞቹ ቀደም ብሎ በቁጫ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት በዋስትና እንዲወጡ ከተደረገ በሁዋላ እንደገና ተመልሰው እንዲታሰሩ ተደርጎ ያለፉትን 6 ወራት በእስር ቤት አሳልፈዋል። ፍርዱ የተሰጣቸውም እስር ቤት ውስጥ እንዳሉ ነው።

እስረኞቹ በአካባቢው ህዝብ በሽማግሌነት ተመርጠው እስከ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ድረስ በመሄድ አቤት ብለው ነበር። በቁጫ አሁንም እስር እና ሰዎችን ማሰደድ እንደቀጠለ ሲሆን፣ መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጸረ ሰላም ሃይሎች እጅ አለበት በሚል በአካባቢው የጸጥታ ሃይሎች እንዲሰማሩ አድርጓል። ከቁጫ የማንነት ፣ የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከ200 እስከ 400 የሚደርሱ ሰዎች ታስረዋል።

 

 posted by Tseday Getachew

 

ሾልኮ የወጣ የጥምቀት የጭፍጨፋ ድግስ ሚስጥር

ቹቸቤ

ሾልኮ የወጣ የጥምቀት የጭፍጨፋ ድግስ ሚስጥር

በመጀመርያ ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ። እንዲያው ይሁን ብዬ እንጂ ጥምቀተ ባህር እንኳን ሙስሊም ጓደኞቻችንም አብረውን ይውሉ እንደነበር አስታውሳለሁ።የጥምቀተ ባህር ፀበል ብቻ ሳይሆን የፍቅር ፀበልም የሚረጭበት  የፍቅር በታ ነው።: በተለይ  ተረ … ተረረረ…. ረረረ የምትል ማንም ከደፈረ የሚጫወታት ሃርሞኒካ ተይዛ ከሚጨፈርበት እነ አብዱና እነ ሙስጠፋስ መች ይጠፉ ነበር። ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ ብለው ሜዳውን የሚሞሉት ኮረዶች መካከልስ ተቃቅፈው ወይ እጅ ለእጅ ተያይዘው ከሚሄዱት ሃሊማና ሩቅያስ መች ይታጡ ነበር። “ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስትያኑ…ተዘነጋሽ እንዴ ኢትዮጵያ መሆኑ”  ያለው ቴዲ ይህን በዐይኑ አይቶ እንጂ ተረት ሰምቶ አይደለም። ደግሞም ነገም ወደፊትም አብረን እንኖራለን የማያኖሩን አይኑሩ! አሜን አላችሁ?

አሁን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ድህረ ገጽ ላይ ሰውነት የሚያንቀጠቀጥ ዘግናኝ የሆነ ጉዳይ በእንግሊዝኛ ተጽፎ አነበብኩ።http://ecadforum.com/2014/01/17/terror-plot-to-turn-ethiopian-epiphany-celebration-into-an-inferno-uncovered/ በእንግሊዝኛ መጻፉ ብቻ ሳይሆን የመልዕክቱ አስቸኳይነት እጅግ አሳሰበኝ። ለነገ የሞት ድግስ መላምት ካልሆነ አለም ሊያውቀው እኛም ሕዝቡን ልናስጥነቅቅበት የሚገባ መሆን አለበት በሚል ስሜት በድጋሚ አነበብኩት። ከሆነ በሁዋላ ከማዘን የተወራውን ማሳወቅ የታሰበ ነገርም ካለ ተነቃብን እንዲሉ ካልሆነም አስፈላጊ ጥንቃቄ እንዲደረግ ስለሚረዳ መልዕክቱን ማጮህ ይሻላል ብዬ አሰብኩ።

በድህረ ገጹ ላይ የሚነበበው እነዚህ አረመኔዎች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሞት እንደ ጠበል ሊረጩት ተዘጋጅተዋል የሚል መልዕክት ነው። ይህም የሚሆነው ለጥምቀት ለዛሬ  መሆኑ ነው። ባለን አስተማማኝ መረጃ መሰረት ይላሉ የአፍሪካ ቀንድ ዘጋቢዎች (infohorntimes@gmail.com) በሚገባ የሰለጠኑት የትግራይ ተገንጣይ ወንበዴ ቅጥረኞች የሙስሊሞችን አለባበስ ተክነውበት በእለተ ጥምቀት አዲስ አበባን በቦምብ ሊያናውጧት መዘጋጀታቸውን ነው።

እድሜ አብዝቶ ይስጥልንና ለሀገር አሳቢና የሕዝብ አክባሪ የሆኑት አቶ ገብረመድህን አርአያ የትግራይ ተገንጣዮች አከርካሪያቸው ሊሰበር ሲቃረብ ወጣቱን በገፍ ለማፈስ በሀውዜን ላይ ልዩ ቅንብር አዘጋጅተው ወገኖቻችንን  በአውሮፕላን እንዲጨፈጨፉ በማድረግ ፊልም ሲቀርጹና ድጋፍ ሲያሰባስቡ እንደነበረ በአንደበታቸው ነግረውናል። እነዚህ ሰዎች መግደል ማስገደል ዞር በል የማለትን ያህል እንኳን አይከብዳቸውም። ከሞት ያዳኗቸውን ያስገድላሉ የደፈሯቸውን ነብሰ ጡር ወጣት ሴቶች ገድለው ጉድጓድ ይጨምራሉ። አሁን ደግሞ ሌሎች ወገኖች በመላው ኢትዮጵያ የደም ጎርፍ ሊያፈሱ ተዘጋጅተዋል ይሉናል።

“ከፍንዳታው ቀጥለው የሙስሊም ልብስ የለበሱ የግድያ ስልጡኖች በድንጋጤ የሚበታተነውን ሰው በጥይት ይቆሉታል” ብሎ ሚስጥር አሾላኪው ነግሮናል ነው የሚሉት። ቀደም ብሎ ትዕዛዝ የተሰጣቸው ቅጥረኞች ደግሞ ብቀላ በሚመስል መልኩ ከፍንዳታው በሁዋላ በአላባ ቁሊጦ ሁለት መስጊዶችን ዶግአመድ ያደርጋሉ። የዚህ ሁሉ እልቂት ድግስ ምክንያቱ መጪውን ምርጫ ፍራቻ መሆኑም ተሰምቷል። ወሎም የጥቃት ዒላማው ከተነጣጠረባቸው ስፍራዎች ወስጥ ይገኛል። በአርሲና በባሌም እንዲሁ ዘግናኝ ጭፍጨፋን ለማድረግ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ አረመኔዎች መኖራቸው ተጽፏል። በጅጅጋም እንዲሁ ይላል ጽሁፉ ….የሶማሌ ሙስሊሞችን አለባበስ ለብሰው ለጥምቀት እርድ የተዘጋጁ ቅጥረኞች ትዕዛዝ በመጠባበቅ ላይ ናቸው።

የዚህ ሁሉ የክፋት ጥንስስ ዓላማው የትግራይ ተገንጣይ ወንበዴዎች አገር አሸብረው እስከዘላለሙ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንበርክከው ለመግዛት የሚያስችላቸው ንድፍ አንደሆነ ነው የሚገለጸው። በዚህም መነሻ ተቃዋሚዎችን ሁሉ አሸባሪ የሚል ስም ለጥፎ ጭፍጨፋና እስር ከዚያም አፈናውን ለመቀጠል መሆኑ ይነገራል።

ይህ የእልቂት ድግስ ሊከሽፍ ይገባዋል። ከወዲሁ ድግሱ በሰፊው ሊነገርና ተጠያቂው ማን እንደሚሆን ሊነገር ይገባል። ሕዝባችንንም መረጃውን ልናደርሰው ይገባናል። ይህንን መረጃ ከውስጥ አዋቂ ተቀብለው ሪፖርቱን አቀናብረው ያቀረቡልንን ተቀማጭነታቸው በደቡብ አፍሪካ የሆኑት አቶ ጌታሁን መኩሪያን አመሰግናለሁ።

ecadforum.com/

posted by Tseday Getachew

በስዑዲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይዞታ

በስዑዲ ዐረቢያ መዲና በሪያድ፤ በተለይም ማንፉህ በተባለው ቀበሌ ከሁለት ወር በፊት እንደሆነው ሁሉ፤ አሠሳ ፤ ከትናንት በስቲያ በጦር ሠራዊቱ ልዩ ኃይል የተጀመረ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆንስላ ጽ/ቤት ሕጋዊ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ የሌላቸው

የኢትዮጵያ ተወላጆች ፤ በሰላም እጃቸውን ለፖሊስ እንዲሰጡ በተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ማቅረባቸው ተነግሯል።መጀመሪያ ሥራ ካሠጣቸው ተያዥ ጋር ግንኙነት የሌላቸው እንደ ሕገ ወጥ ሠራተኞች እንደሚታዩ የስዑዲ መንግሥት አስታውቋል ተብሏል። በዚህ ሁኔታ ቁጥራቸው ከ 80 ሺ እስከ 100ሺ የሚገመት ኢትዮጵያውያን ፣ ሕገ-ወጥ ተብለው አገር እንዲለቁ ሊገደዱ ይችላሉ ቢባልም ፣ አብዛኞቹ ፣ ከተያዥዎቻቸው እውቅና ውጭ ሥራ አግኝተው እየሠሩ የሚኖሩ እንዲባረሩ የሚያደርግ እርምጃ ይወሰዳል ብለው እንደማይገምቱ ነው የሚነገረው። ይሁንና ፣ በሚመጡት ቀናት ሊወሰድ የሚችለው እርምጃ እጅግ አሳሳቢ ሊሆን እንደሚችል ግምት አለ። በዚህ ጉዳይ ላይ ነቢዩ ሲራክ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሮ ልኮልናል።

ነቢዩ ሲራክ

በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መንግስት እንዲታደጋቸው እየተማጸኑ ነው

 

96 ኢትዮጵያውያን ታንዛንያ ላይ ተያዙ!!! ታህሳስ ፲፰ አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዩኒቲ በሚባለው ግዛት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያን በጦርነት አጣብቂኝ ውስጥ መገኘታቸውንና ህይወታቸው አደጋ ውስጥ መውደቁን ተናግረዋል።

በግዛቱ ውስጥ በአንድ የመንገድ ስራ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ 6 ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩት በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የሚደረገውን የተኩስ ልውውጥ ለማምለጥ ያለፉትን ሁለት ቀናት በከባድ ማሽነሪዎች ውስጥ በመደበቅ ለማሳለፍ ተገደዋል። በአካባቢያቸው 2 ኢትዮጵያውያን መገደላቸውንና 3ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን ተናግረዋል።

እስካሁን ድረስ ምን ያክል ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ ባይታወቅም፣ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በማነጋገር እንደዘገበው የሞቱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እስከ ታህሳስ 17፣ 2006 ዓም ድረስ ቢያንስ 30 ይደርሳል።

ኢሳት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደሚሉት መንግስት እስካሁን ድረስ ዜጎቹን ለመሰብሰብ ጥረት እያደረገ አይደለም። ጎረቤት አገሮች ኬንያና ኡጋንዳ ዜጎቻቸውን ሲያስወጡ የኢትዮጵያ መንግስት ምንም አይነት እርምጃ ለመውሰድ አለመፈለጉ ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኗል። ኢትዮጵያውያን አሁንም መንግስት እንዲደርስላቸው ጥሪ አቅርበዋል

በጆንግሌ ግዛት የተደፈሩ 4 ኢትዮጵያውያን ጁባ ውስጥ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እንዲያገኙ ተድርጓል።x

ይህ በእንዲህ እንዳለ የምስራቅ አፍሪካ መንግስታት በናይሮቢ ኬንያ ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በግላቸው ተኩስ እንደሚያቆሙ አስታውቀዋል። አገራቱ የመንግስትን እርምጃ የደገፉ ሲሆን፣ የኬንያው መሪ ኡሁሩ ኬንያታ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን መሪ በሀይል ለማውረድ የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንደማይደግፉ ገልጸዋል።

የተቃዋሚዎች መሪ የሆኑት ሪክ ማቻርም በተመሳሳይ መንገድ ተኩስ እንዲያቆሙ የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች ተማጽኖ አሰምተዋል። መሪዎቹ በሚቀጥሉት 4 ቀናት ፊት ለፊት ተገናኝተው እንዲወያዩ ኢጋድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።እስካሁን በተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት ከ1 ሺ በላይ ሰዎች መገደላቸውን አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል;፡

ESAT

posted by Tseday Getachew

በአረና መጠናከር የሰጉት ህወሓቶች ‘ዕርቅ’ ፈፀሙ – አብረሃ ደስታ ከመቀሌ

 

ህወሓቶች ለሁለት ተከፍሎው የደብረፅዮን (የአዲስ አበባ) ና የአባይ ወልዱ (የትግራይ) ቡድን ተሰይመው ሲነታረኩ መቆየታቸው ይታወቃል። ከወራት በፊት ጀምሮ ደግሞ ሁለቱም ቡድኖች ‘ለማስታረቅ’ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ጠቅሼ ነበር።

ትንቅንቅ

አሁን አቶ ስብሃት ነጋ (ከቢተው በላይ ጋር በመሆን) ሁለቱም ባላንጣ ቡድኖች ‘ማስታረቅ’ ችለዋል። ዕርቁ የተፈፀመው በነ ደብረፅዮን ቡድን አሸናፊነት ነው። የነ አባይ ወልዱ ቡድን በመሸነፉ ምክንያት አቶ አባይ ወልዱ ከነ ስብሃት ነጋ ጋር እንዲስማማ ምክንያት ሁነዋል። የነ አባይ ቡድን የተዳከመበት ምክንያት ለሁለት በመከፈሉ ነው። አቶ አባይ ወልዱ ከአቶ ቴድሮስ ሐጎስ፣ ኢያሱ ተስፋይ፣ ተክለወይኒ አሰፋ፣ ኪሮስ ቢተው፣ በየነ መክሩ ወዘተ መግባባት ባለመቻሉ ከአዲስ አበባዎቹ ጋር ለመስማማት ተገደዋል።

 

በስምምነቱ መሰረት ህወሓት በአዲስ አበባዎቹ ፕላን ይጓዛል። በ’መለስ ራእይ’ ስም ህዝብ መጀንጀን ይቀራል። በሙስና ሰበብ ባለስልጣናት ማሳሰርም ይቀራል። ከአሁኑ በኋል ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣናት በሙስና ሰበብ አይታሰሩም። በቀጣዩ የኢህአዴግ ጉባኤ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ከህወሓት እንዲሆን ጥረት ይደረጋል (ዶር ቴድሮስ አድሐኖም)።

ይህ የህወሓቶች የ’ዕርቅ ሂደት’ ባብዛኛው የብአዴን አመራር አባላትና በተወሰኑ የኦህዴድ መሪዎች ቅሬታ አስነስተዋል። ህወሓቶች ለመታረቅ የተገደዱበት ምክንያት በተቃዋሚዎች ስልጣን እንዳይነጠቁ በመስጋት ነው። ዓረና ፓርቲ ለህወሓቶች ትልቅ ስጋት በመፍጠሩ ነው። የፀጥታ ሃይሉ መፈራረስም ሌላ ህወሓቶች ያስደነገጠ ጉዳይ ነው። በዕርቁ ሂደት ከፍተኛ ሚና የተጫወተው አቶ ስብሃት ነጋ ነው።

የዕርቅ ሂደቱ በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ከፍተኛ አለመግባባት ሊፈጥር ይችላል። ኢህአዴግ በዉስጥ ለውስጥ የስልጣን ሹክቻ ምክንያት የሚዳከምበት አጋጣሚ መፈጠሩ አይቀርም። ዕርቁ ግዝያዊና ስትራተጂካዊ ብቻ ነው። የታረቁት መግባባት ስለ ፈጠሩ ሳይሆን የጋራ ጠላትን ለመከላከል ብቻ ነው።

https://www.zehabesha.com/

posted by Tseday Getachew

Post Navigation

%d bloggers like this: