Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

Archive for the month “December, 2013”

በስዑዲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይዞታ

በስዑዲ ዐረቢያ መዲና በሪያድ፤ በተለይም ማንፉህ በተባለው ቀበሌ ከሁለት ወር በፊት እንደሆነው ሁሉ፤ አሠሳ ፤ ከትናንት በስቲያ በጦር ሠራዊቱ ልዩ ኃይል የተጀመረ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆንስላ ጽ/ቤት ሕጋዊ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ የሌላቸው

የኢትዮጵያ ተወላጆች ፤ በሰላም እጃቸውን ለፖሊስ እንዲሰጡ በተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ማቅረባቸው ተነግሯል።መጀመሪያ ሥራ ካሠጣቸው ተያዥ ጋር ግንኙነት የሌላቸው እንደ ሕገ ወጥ ሠራተኞች እንደሚታዩ የስዑዲ መንግሥት አስታውቋል ተብሏል። በዚህ ሁኔታ ቁጥራቸው ከ 80 ሺ እስከ 100ሺ የሚገመት ኢትዮጵያውያን ፣ ሕገ-ወጥ ተብለው አገር እንዲለቁ ሊገደዱ ይችላሉ ቢባልም ፣ አብዛኞቹ ፣ ከተያዥዎቻቸው እውቅና ውጭ ሥራ አግኝተው እየሠሩ የሚኖሩ እንዲባረሩ የሚያደርግ እርምጃ ይወሰዳል ብለው እንደማይገምቱ ነው የሚነገረው። ይሁንና ፣ በሚመጡት ቀናት ሊወሰድ የሚችለው እርምጃ እጅግ አሳሳቢ ሊሆን እንደሚችል ግምት አለ። በዚህ ጉዳይ ላይ ነቢዩ ሲራክ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሮ ልኮልናል።

ነቢዩ ሲራክ

Advertisements

በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መንግስት እንዲታደጋቸው እየተማጸኑ ነው

 

96 ኢትዮጵያውያን ታንዛንያ ላይ ተያዙ!!! ታህሳስ ፲፰ አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዩኒቲ በሚባለው ግዛት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያን በጦርነት አጣብቂኝ ውስጥ መገኘታቸውንና ህይወታቸው አደጋ ውስጥ መውደቁን ተናግረዋል።

በግዛቱ ውስጥ በአንድ የመንገድ ስራ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ 6 ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩት በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የሚደረገውን የተኩስ ልውውጥ ለማምለጥ ያለፉትን ሁለት ቀናት በከባድ ማሽነሪዎች ውስጥ በመደበቅ ለማሳለፍ ተገደዋል። በአካባቢያቸው 2 ኢትዮጵያውያን መገደላቸውንና 3ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን ተናግረዋል።

እስካሁን ድረስ ምን ያክል ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ ባይታወቅም፣ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በማነጋገር እንደዘገበው የሞቱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እስከ ታህሳስ 17፣ 2006 ዓም ድረስ ቢያንስ 30 ይደርሳል።

ኢሳት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደሚሉት መንግስት እስካሁን ድረስ ዜጎቹን ለመሰብሰብ ጥረት እያደረገ አይደለም። ጎረቤት አገሮች ኬንያና ኡጋንዳ ዜጎቻቸውን ሲያስወጡ የኢትዮጵያ መንግስት ምንም አይነት እርምጃ ለመውሰድ አለመፈለጉ ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኗል። ኢትዮጵያውያን አሁንም መንግስት እንዲደርስላቸው ጥሪ አቅርበዋል

በጆንግሌ ግዛት የተደፈሩ 4 ኢትዮጵያውያን ጁባ ውስጥ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እንዲያገኙ ተድርጓል።x

ይህ በእንዲህ እንዳለ የምስራቅ አፍሪካ መንግስታት በናይሮቢ ኬንያ ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በግላቸው ተኩስ እንደሚያቆሙ አስታውቀዋል። አገራቱ የመንግስትን እርምጃ የደገፉ ሲሆን፣ የኬንያው መሪ ኡሁሩ ኬንያታ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን መሪ በሀይል ለማውረድ የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንደማይደግፉ ገልጸዋል።

የተቃዋሚዎች መሪ የሆኑት ሪክ ማቻርም በተመሳሳይ መንገድ ተኩስ እንዲያቆሙ የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች ተማጽኖ አሰምተዋል። መሪዎቹ በሚቀጥሉት 4 ቀናት ፊት ለፊት ተገናኝተው እንዲወያዩ ኢጋድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።እስካሁን በተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት ከ1 ሺ በላይ ሰዎች መገደላቸውን አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል;፡

ESAT

posted by Tseday Getachew

እኔ ጃዋርን ብሆን ኖሮ (ክፍል 2)

Jawar Mohamed Muslim fundamentalist

ከዓለማየሁ መሀመድ (ክፍል 2)

በትላንቱ ጽሁፌ ጃዋርና ህወሀት የፈጸሙትን ለጊዜው መረጃው ብቻ ስላለኝ ያጋብቻ ጉዳይ አንስቼ በቀጠሮ ነበር የተለያየነው። ማስረጃው በቅርቡ እጄ እንደገባ ሰማንያ ተፈራርመው የሰሞኑን የፌስቡክ ግርግር እንዴት እንደገቡ ይፋ አደርጋለሁ። እስከዚያው ታገሰኙ።

ለአሁን ጃዋርን ብሆን አማረኝ

አዎ! ጃዋርን ብሆን ይሄን ጊዜ እነዚህን ነገሮች አደርጋለሁ

1. የኬንያና የህወሀት መንግስታት ተስማምተው የኦሮሞ ልጆችን እያደኑ ነው። ሰሞኑን ከወደ ኬኒያ እንደሚሰማው ከ 500 በላይ የወያኔን መንግስት ሸሽተው ኬኒያ የተጠለሉ ኦሮሞዎችን ኬኒያ አሳልፋ እየሰጠች ነው። በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ስም ኦሮሞች ተለቅመው ለወያኔ መንግስት እየተሰጡ ነው። ይህ ዘመቻ አሁንም ቀጥሏል። እናም እኔ ጃዋርን ብሆን ኬኒያ እያደረገች ያለችው ድርጊት ዓለም ዓቀፉን የስደተኞች መርህ የሚጣረስ በመሆኑ ለመንግስታቱ ድርጅት፡ ለዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት፡ ለኬኒያ ፓርላማ እና ለሌሎች ድርጅቶችና መንግስታት አቤቱታ እንዲቀርብ አስተባብራለሁ። ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ ባለመሆኑ ያለኝን ማህበራዊ ቦታና ተቀባይነት ተጠቅሜ፡ ሰፊ የቅስቀሳ ስራ በማከናወን ኬኒያ ላይ ጫና እንዲፈጠር አደርጋለሁ።

2. በምስራቅ ሀረርጌ ከሶማሌ ክልል ድንበርተኛ በሆኑ ወረዳዎች ላለፉት ሶስት ዓመታት በልዩ የሶማሌ ክልል ታጣቂዎች እየተፈጸመ ያለው መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሰሞኑን ተባብሶ መቀጠሉ እየተነገረ ነው። የሶማሌ ልዩ ሃይሎች የኦሮሞ ሴቶች እየደፈሩ፡ናቸው። ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በተለያዩ አጎራባች አከባቢዎች የተሰደዱት ወገኖች ቁጥር ከፍተኛ ነው። የሚበሉት ያጡ ህጻናት እየረገፉ ናቸው። እናም እኔ ጃዋርን ብሆን ተመሳሳይ የቅስቀሳ ዘመቻ በመክፈት ጉዳዩ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ሰሚ እንዲያገኝና ወገኖቼ ከስቃይ እንዲድኑ የሚቻለኝን አደርጋለሁ። የገቢ ማሰባሰቢያ መድረኮች እንዲዘጋጅ እየቀሰቀስኩ ገንዘብ አሰባስቤ ለእነዚያ እየረገፉ ላሉት ህጻናት፡ መሄጃ መድረሻ ላጡት ወገኖቼ እደርስላቸው ነበር።

3. የወያኔ እስር ቤቶች በኦሮሞዎች ተጥለቅልቋል። በቅርቡ ኢንጅነር ተስፋሁንን ጨምሮ በርካታ ኦሮሞዎች በወያኔ የጭካኔ ተግባር በእስር ቤት እያሉ ህይወታቸውን አጥተዋል። ከሰሞኑ ሁለቱ የኦሮሞ መብት ታጋዮች አቶ በቀለ ገርባና አቶ ኦልባና ሌሊሳ በአንድ ዓይነት ህመም እየተሰቃዩ ነው። ህክምና ተነፍገው በከፍተኛ ስቃይ ላይ እንዳሉ ተሰምቷል። እናም እኔ ጃዋርን ብሆን ለእነ አምንስቲ ኢንተርናሽናል፡ ሂውማን ራይትስ ዎች እና ተጽእኖ ለሚፈጥሩ አካላት ጉዳዩን በማሳወቅ እስረኞቹን ከሞት እታደጋለሁ። ገንዘብ እንዲሰባሰብ በማድረግ ለእስረኞቹ ቤተሰቦች እርዳታ እንዲደረግ እቀሰቅሳለሁ።

ሌላም…. ሌላም…..

ግን ጃዋርን አይደለሁም። ባለኝ አቅም ጥረት እያደረኩ መሆኔን ግን መግለጽ እፈልጋለሁ። ጃዋር ካለው ማህበረሰባዊ ተቀባይነት አንጻር ከእኔ የተሻለ ውጤት ሊያስመዘግብ ይችላል ከሚል መነሻነት ነው ጃዋርን መሆን ያማረኝ።

ጃዋር ጆሮው ላይ የሚያቃጭለው የሙታን ድምጽ ነው። በዓይነ ህሊናው የሚሽከረከረው የሙት መንፈስ ነው። እየተላፋ ያለው ከማይጨበጥ ከማይዳሰሰው ጋር ነው። በህይወት ስላሉት ከንፈር እንኳን መምጠጪያ ጊዜ አላገኘም። ጠዋት ተነስቶ  እስኪመሽ በኮምፒውተሩ ቂጥ ስር ተወሽቆ ኦሮሞ ፈርስት እያለ ማላዘኑ ተመችቶታል። የኬኒያዎቹ ኦሮሞዎችን ስቃይ የሚሰማበት ጆሮ የለውም። ለምስራቅ ሀረርጌዎቹ ህጻናት ሲቃ ጊዜም ሊሰጥ አልፈቀደም። በየእስር ቤቱ ለሚሰቃዩ የኦሮሞ ልጆች የሚያዝን ልቦና አልሰጠውም። ጸሀይ ወጥታ እስክትጠልቅ ከታሪክ ተራራ ጋር ይላፋል። ይቸከችካል። መሰሎቹ ጃስ ሲሉት ደስ ይለውና አሁንም ይቸከችካል። ሙቀቱ ተመችቶታል። ጭብጨባው ልቡን ላይ የትዕቢት ተራራ ቆልሎለታል። ድሮውንስ የኦሮሞ ህዝብ ስቃይ ለሱ የግል ዝና መሸመቺያ እንጂ መቼ መቆርቆር ከአጠገቡ ደርሳ?

ለማንኛውም በቅርቡ የጃዋርንና የህወሃትን ጋብቻ የተመለከተውን ማስረጃ ይዤ እመለሳለሁ። ለዘነጋችሁ;  ጃዋር የወያኔ አሻንጉሊት የሆነው ኦህዴድ ልጅ ነው። ውለታ አለበት። ለአቅመ ፖለቲካ እንዲደርስ ያበቃውን ኦህዴድን(ህወሀትን) ቢረሳ አምላክም ደስ አይለውም። ወደፊት የማካፍላችሁ ዕውነትም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው።

በመጨረሻም ለፈርስቶች መልካም የጩኧት ጊዜ። ሙቀቱ ሲለቃችሁ እንገናኝ።

posred by Tseday Getachew

 

 

በጎንደር ዳባት ሕጻን ሰለሞን ላይ ማን የጥይት እሩምታ አወረደበት?

ከዳዊት ሰለሞን

ሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ነዋሪ የነበሩት የ55 ዓመቱ አቶ ማስረሻ ጥላሁን የተመሰከረላቸው አርሶ አደር ገበሬ በመሆናቸው የክልሉ ግብርና ጽ/ቤት ሞዴል አርሶ አደር በማለት ሸልሟቸዋል፡፡የሁለት ወንድና የአምስት ሴት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ማስረሻ ወሰኔን ገፍተሃል የሚል ክስ ቀርቦባቸው በዳባት ፍርድ ቤት 300 ብር መቀጮ ተጥሎባቸው በመክፈል ወደ እርሻቸው ቢመለሱም የገበሬ ቀበሌ ማህበሩ ሊያስቀምጣቸው አልቻለም፡፡

ጥቅምት 15/2006ዓ.ም ከሁለተኛ ልጃቸው ሰለሞን ማስረሻ ጋር አትክልት ተክለው አመሻሹ ለይ ተዳክመው መኖሪያ ቤታቸው ገብተዋል፡፡ማለዳ 12፡00 ከመኝታው ባላቋረጠው የውሾች ጩህት ከእንቅልፉ ተነሳው ሰለሞን በሩን ከፍቶ ሲወጣ የጥይት እሩምታ ይወርድበታል፡፡አባት ልጄን ብለው የሌሊት ልብሳቸውን እንደለበሱ ወደ ውጪ ሲወጡ የጥይቶቹ አቅጣጫ ወደ እርሳቸው በመዞሩ ማን እንደተኮሰባቸውና ማን እንደመታቸው ለማየት እንኳን ሳይታደሉ ይህችን ጨካኝ አለም ተሰናበቱ፡፡

መኖሪያ ቤቱ ላይ በሚወርደው የጥይት እሩምታ የተነሳ ሁለት ላሞችና አንዲት ጊደር ተገደሉ፡፡የስምንት አመቷ ስለእናት ማስረሻ ቀኝ እጇ ላይ በጥይት ተመታች፡፡ባለቤታቸውን በሞት የተነጠቁትና ምንም የማታውቀውን ህጻን ልጃቸውን አካለ ጎደሎ ያደረገባቸውን ጥይት ማን እንደተኮሰው ለማወቅ ለዳባት ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ አቤት ሲሉ ‹‹ባለቤትዎ ሽፍታ መረጃ ስለደረሰን ግድያውን የፈጸመው የጸረ ሽብር ግብር ሃይል ነው››ተብለዋል፡፡‹‹ሽፍታ እንዴት ባለ80 ቆርቆሮ ቤት ይሰራል?ልጆቹን ያስተምራል?ሞዴል አርሶ አደር ተብሎ ይሸለለማል?በየት አገር በብአዴን ስብሰባ ላይ እንድትገኝ ተብሎ በደብዳቤ ይጠራል?እንዴት ሽፍታ የመለስ ዜናዊን አደራ ለመወጣት በምንችልበት ሁኔታ ለመወያያት እንድንነጋገር ይባላል? ›› ጥያቄዎቹን ፖሊሶቹ ሊመልሱላቸው ባለመቻላቸው ወደ ክልሉ አስተዳደር አምርተዋል፡፡ክልሉ ለዞኑ ዞኑ ለወረዳው ደብዳቤ እየጻፈ እስካሁን ድረስ የአቶ ማስረሻ እውነተኛ የግድያ መንስኤ መታወቅ አልቻለም፡፡

 

posted by Tseday Getachew

ትንሽ ስለጃዋር መሀመድ

ከዓለማየሁ መሀመድ

ሁለት ነገሮችን ላንሳ።

1.  የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል መሬት አንቀጥቅጥ ሆኖ ለሁለት ዓመት ገደማ ዘልቋል። በዚህ ትግል ውስጥ በሀገር ቤት ከስርዓቱ ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው ደም ህይወታቸውን ገብረው ትግሉ በማይናወጥ ጽናት ላይ እንዲቆም ያደረጉት ብዙሃኑ ሙስሊሞች ዋጋቸው በክብር መዝገብ ላይ ምንጊዜም ወርቃማ በሆነ ቀለም ተመዝግቦ ይቀመጣል። ከእነሱ ባሻገር በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትግሉ መሬት ይዞ  በሰከነ መልኩ እንዲጓዝ ያደረጉት አስተዋጽኦም የሚዘነጋ አይደለም። ጃዋር በዚህ ውስጥ ስሙ ሲጠቀስ ነበር። የሙስሊሞች ትግል ላይ ትንሽም ብትሆን አሻራው አርፎበታል። ያኔ ነው። በፊት። አሁንስ?Jawar Mohamed Muslim fundamentalist

2.  የኦሮሞ ህዝብ ጭቆና ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የተለየ ነው- አይደለም -የሚለው ክርክር ለጊዜው ይቆይና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ለ40 ዓመታት ሲያቀነቅነው የነበረውና ውጤት ሳይኖረው ዘመናት የቆየው ትግሉ አሁን ‘’የኦሮሞን ህዝብ ትግል በኢትዮጵያ ጥላ ስር’’ የሚለው ሀሳብ አሸንፎ ሲወጣ ጃዋር ብቅ አለ። መጀመሪያ ላይ በሳል በሆኑ፡ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ፡ የሰውን ልጅ በአንድ መነጽር የሚመለከቱ የሚመስሉ ሀሳቦች በጃዋር አፍ ውስጥ ይዋኙ ነበር። ይህም በተቀረው ኢትዮጵያውያን ዘንድም ጃዋር ምናልባት ያረጀውን የኦነግ ጠባብ ብሄርተኝነት ከመቃብር አስቀመጦ የኦሮሞን ህዝብ ከዕውነተኛ ድል የሚያቀርብ አዲስ መንገድ ይጀምራል የሚል ብጣቂ ተስፋ ውስጣቸው የነበሩ ጥቂቶች አልነበሩም። ከመነሻውም የተጠራጠሩት፡ የተደበቀው ማንነቱ አንድ ቀን ይወጣል ብለው በጥርጣሬ ሲመለከተቱት የነበሩት ቁጥራቸው የትየለሌ ነበር። ሆኖም እኔም ሆንክ ጥቂቶች ጃዋርን እንደ አብሪ ኮከብ መመልከታችን አልቀረም። አሁንስ?

ጃዋር አሁን አይሰማም። መስማት የሚፈልገው የፈለገውን ብቻ ነው። በየአዳራሹ የሚሰማው ጭብጨባ ሰርቆታል። ቀልቡ አሁን ከሚኒሶታ እስከ ለንደን በተዘረጋው የ’ኦሮሞ ፈርስት’ ቅልጥ ያለ የወቅቱ ነጠላ ዜማ ላይ ሆኑዋል።

1. የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል በእፎይታ ጊዜ ላይ ቢሆንም የጃዋር ‘ኦሮሞ ፈርስት’ በይፋ ከታወጀችና ‘ሜንጫ’ዋ በሚኒሶታ መድረክ ከተስተጋባች በኋላ የሙስሊሞች ትግል ላይ መጠነኛ ተጽእኖ መፈጠሩ አልቀረም። የሙስሊሙን ትግል የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል አድርገው የተሰለፉ ወገኖች በጥቂቱ ማፈግፈጋቸው በመጠኑ ይታያል። ሜንጫ የሚለውን ቃል ጃዋር ሚኒሶታ ላይ ካፈነዳት ወዲህ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ እንኳን ውዥንብር ተፈጥሯል። እናም የሟችዋ ሚካያ በሃይሉ ዜማን ልዋሰው- “ሸማመተው”::  ህወሀት ሸመተ:: ትግሉ እንዲደበዝዝ ቀን ከሌት ይመኝ የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ- ሸማመተው!!

2.  ከምንጊዜውም በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነቱን ለማሳየት፡ በጋራ ወደ ምር ነጻነት ለመምጣት እጅ ለእጅ እየተያያዘ ያለበት ወቅት ላይ እነጃዋር የኦሮሞ ብሄርተኝነትን ወደ ጠባቡ ጽንፍ ወስደውት ዘራፍ ማለት መጀመራቸው በተወሰነ ደረጃ ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ከሰማይ የወረደ አዱኛ ሆነለት:: አሁንም ሚካያ ትላለች -“ሸማመተው” – ህወሀት ሸመተ::

እነ ጃዋር እየተናገሩ ነው:: ‘ኦሮሞ  ፈርስት’-‘ ማይ ካንትሪ ኢዝ ኦሮሚያ’ ::  የህወሀት የፌስቡክና ትዊተር ሰራዊቶች ስማቸውን በኦሮምኛ ለማድረግ ከብርሃን ነበር የፈጠኑት:: እናም ‘ኦሮሞ  ፈርስት’  መፈክራቸው ሆኖ አጼ ሚኒሊክ ላይ እርግማናቸውን ውእግዝ ከማርዮሱን እያዘነቡት ነው።

ጭብጨባው ቀልጧል። ነጠላ ዜማው ሰማይ ምድሩን አድምቆታል፡፡ እነጃዋር በህወሀት ነጠላ ዜማ ዳንሱን እያቀለጡት ነው። የሚሰማ ጆሮ የላቸውም። ልባቸው ሸፍቷል። አውቀው ይሁን ሳያውቁት ከህወሀት መንደር ዘልቀው የልፊያ ፖለቲካውን ተያይዘውታል። ጭብጨባ ክፉ ነው። ላላወቀበት ስካር ነው።

ሰሞኑን ከጨፌ ኦሮሚያ አንድ መረጃ ደርሶኛል። ሳይላመጥ አይቀርብም በሚል ለጊዜው ይዤዋለሁ። እነጃዋርን የተመለከተ ነው። ምናልባት መረጃውን በማስረጃ ማስደገፍ ከቻልኩኝ በድብቅ የተፈጸመውን የእነጃዋርንና ህወሀትን ጋብቻ ይፋ አደርጋለሁ።

እስከዚያው ጩኧቱን እየሰማን እንቆይ። መልካም ጋብቻ የምንልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።

 

posted by Tseday Getachew

ልጓሙን የበጠሰው የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የስድብ ፈረስ

December 27, 2013

ከዳኛቸው ቢያድግልኝ

ፕሮፌሰሩ በጽሁፎቻቸው እንዲህ ብለውናል

“…በዓለም ሕዝቦች መሀከል ውድድር ቢደረግ ያለጥርጥር አበሻ አንደኛከሚወጣባቸው ነገሮች አንዱ ልመና ሳይሆን አይቀርም፤ ለአበሻ፣ ልመናየኑሮ ዘዴ ነው……”  http://www.goolgule.com/abesha-and-begging-1/

             “…አዳም አበሻ ሳይሆን አይቀርም፤ ሁሉንም ነገር ብላ ከተከለከለው በቀር ብሎ ያስቀመጠው ይመስላል፤ በላባችሁ ወዝ ብሉ ተብለው አዳምና ሔዋን መረገማቸውን አበሻ ገና አልሰማም፤ አበሻ የተፈጠረው ገነት ውስጥ ቁጭ ብለህ ያለውን ሁሉ ብላ በተባለበት ጊዜ ነው፤ እግዚአብሄር አበሻን ሁሉንም ብላ ሲለው ምናልባትም በጆሮው ጭራሽ አታስብ ብሎት ይሆናል …….” (ሰረዝ የተጨመረ)

                 እስከናካቴው “ሆድ” የሚባል ቃል ከአበሻ ቋንቋ ፈጽሞ ቢሰረዝ ቋንቋው ብቻ ሳይሆን አበሻም ጉድ ይፈላበታል።  አዕምሮ ፣ ሕሊና የሚባሉትን ቃላት አበሻ አያውቃቸውም፤ ተግባራቸውንም ሁሉ ለሆድ ሰጥቶታል።   (ሰረዝ የተጨመረ)http://www.zehabesha.com/amharic/archives/9015

ልጻፍ ልተው… ምናልባት… እንዲያው ምናልባት በዚሁ የሚያበቁ ከሆኑ አይቶ እንዳላየ ማለፍ ይሻል ይሆናል ስል ልጓሙን የበጠሰው የስድብ ፈረሳቸው በማንአለብኝነት ጋለበብን። ባእዳን አበሽ እያሉና እየሰደቡ ይገድሉናል። የራሳቸው ታሪክ በረሀብ ቸነፈርና ስደት የተሞላ እንዳልሆነ ሁሉ በመዝገበቃላታቸው ውስጥ ኢትዮጵያን የረሀብ ምልክት አድረገው የሚያዋርዱን በርካታዎች ናቸው። ፕሮፌሰሩ በአንድ ወቅት ሲሉ እንደሰማሁዋቸው  ወያኔዎች ከዱር ወደከተማ ሲገቡ ህዝቡን ፈሪ ለማድረግና የሚያከብረው ምልክት ለማሳጣት በየቀዬው በህብረተሰቡ ዘንድ የሚከበሩትን እያፈላለጉ በአደባባይ ፂማቸውን ይዘው በመጎተት ያዋርዱዋቸው ነበር። ይህን መሰሉ የወያኔዎች ተግባር በሚያሳዝን ሁኔታ በፕሮፌሰሩም ላይ በተደጋጋሚ ደርሶባቸዋል። የወያኔዎች ኢትዮጵያዊነትንና ኢትዮጵያን የማዋረድ ዘመቻ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ታዲያ ይህ ባለበት ሁኔታ የእውቀት ጣርያ ላይ ደርሰዋል የሚባሉት አዛውንቱ ፕሮፌሰር መስፍንም  በአሮጌና ያለአግባብ በተደረደረ ምሳሌ ይህን መከራ የበዛበትን ህዝባችንን በሚሸነቁጥ የጅምላ ስድብ መቀጥቀጣቸው ግር የሚያሰኝ ሆነብኝ። ይህ ወቅትና ሁኔታን ያላገናዘበ መፍትሄ የመጠቆም፣ የማስተማር አቅምም የሌለው ኢትዮጵያዊነትን የሚያዋርድ ጅምላ ስድብና ሽሙጥ በተከታታይ ሲወርድብን አይቶ እንዳላየ ማለፉ ክብራችንን ለማጉደፍና ለማዋረድ ኢትዮጵያችንን ለማንቋሸሽ ለሚተጉት ዱላ ማቀበል ይሆናል። እናም ይህ ጥያቄ ይከነክነኝ ገባ። እውን አበሻ ሥራ ጠል፣ ለማኝና ሆዳም ነውን? በምን ጥናት በማንስ ትንታኔ?

Prof. Mesfin Woldemariam : is an Ethiopian Human Rights activist and philosopher

እድሜአቸውን ሙሉ ሀገራችንን አገልግለዋል ሲባል መስማቴ ብቻ ሳይሆን በባህላችን አዛውንት ይከበራልና  ክብራቸውን የሚያጎድፍ  ትችት ማቅረብ አልፈልግም።  ቢሆንም ታድያ የሰሞኑ ማቆሚያ ያጣው የስድብ ጅራፍ ዘላቂ ጉዳቱ ከፍተኛ ነውና አክብሮቴን ሳላጎድል እባክዎን የስድብ ፈረስዎን ልጓም ያዝ አድርጉልን እላለሁ።

በሀገራችን አዋቂ ነን የሚሉ ሰዎች  ከነሱ የተለየ ሃሳብ ይዞ የሚመጣን ተወያይቶ የተሻለውን ሃሳብ ከመደገፍ ይልቅ ለየት ያለ ሃሳብ ያቀረበውን አንገት የሚያስደፋ የስድብ ናዳ ማውረድ ይቀላቸዋል። ይህንን በመፍራት አዋቂዎቹ ግዙፍ ስህተት ሲፈጽሙ በዝምታ ማለፍ ለሌላ  ስህተት በር መክፈት ይሆናል። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ጽሁፍን በይዞታው ሳይሆን በጸሃፊው ማንነት እየመዘኑ ጸሀፊው በግልጽ ያስቀመጠውን ሃሳብ ወደጎን ትተው  ያልተባለውን መልካም ሃሳብ ፍለጋ እየማሰኑ የራሳቸውን ትርጓሜ ይሰጣሉ። ሰአሊ በስህተት የረጨውን ቀለም “አብስትራክት” ነው ብለው በምናባቸው ውብ ስዕል እንደሚሰሩት አይነት ከስድብ ጀርባ ሙገሳ መፈለጉ ከንቱ  ነው።

የፕሮፌሰር ተከታታይ ጽሁፎች የተጻፉት ኢትዮጵያን በስፋት በማያውቅ ሰው፣ ሀሳብን ለህዝብ ለማቅረብ ምን አይነት ጥንቃቄ የተመላበት የምርምር ጥበብ አስፈላጊ እንደሆነ በማያውቅ ሰው ቢሆን፣ ሀሳብን የማስፈር ዓላማና ግብን መረዳት በማይችል የእውቀት አድማሱ ያልሰፋ፣ በሌሎች ሀገራት የሚኖሩ ሰዎችን አኗኗር በተመለከተ ምንም ግንዛቤ በሌለው ሰው ወይም እንዲያው ለፌዘኛ የመሸታ ቤት ቀልድ ሲባል ለተወሰኑ ታዳሚዎች የቀረበ ቢሆን ምንም  ትኩረት መስጠት ባላስፈለገ ነበር።  ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ግን አለምን ተዘዋውረው የጎበኙና ያልኖሩበትን ዘመንና ያልጎበኙትን አገር ህዝብ አኗኗር በምርምርና በንባብ ጠንቅቀው የተረዱ እድሜ የጠገቡ ምሁር ናቸውና በምንም ጥናታዊ መረጃ ባልተደገፈ መንገድ የአንድን ጥንታዊና ታሪካዊ ሀገር ሕዝብ በዚህ መልኩ ማሳነስና ከሌላ ፕላኔት የመጣ ሰንካላ ፍጡር ማስመሰል እድሜያቸውንና እውቀታቸውን አይመጥነውም። የአንድ ሀገር 90 ሚሊየን ሕዝብ በአንድ ቅንፍ ውስጥ “አበሻ” ብለው ከተው እንኳን የሰው ልጅ ቀርቶ ማንኛውም ማህበራዊ እንስሳ የሚያደርገውን ተሳስቦ፣ ተዛዝኖ፣ ተካፍሎ መኖርን በዚህ መልክ አሳንሶ ኢትዮጵያዊነትን ማዋረድ ታላቅ ስህተት ነው።

ኢትዮጵያዊነትን እያዋረዱ አገር አልባ ሊያደርጉን አዲስ ታሪክ ሊጽፉልን ያሰፈሰፉ ጠላቶች አራት ኪሎ በተቀመጡበት ሰዓት፤ ከልመና ግርድና ይሻላል ብለው የፕሮፌሰሩ የልጅ ልጆች በመላው አለም ተበትነው ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው ቢያልፍልን  ብለው በሰው ሀገር እየተደፈሩ፣ እየተዋረዱ በሚዳክሩበት በዚህ ዘመን፣ በርካታ እናቶች አራስ ልጆቻቸውን ታቅፈው ትንሽ ሳንቲም ለማግኘት በየመንገዱ ዳር ጥቂት የተቀቀለ ድንችና ንፍሮ ለመሸጥ ጸሀይና ብርድ ሲፈራረቅባቸው ውሎ በሚመሽበት ዘመን፣ ደካማ እናቶች ወገባቸው እስኪጎብጥ ቅጠልና ጭራጭሮ ተሸክመው የእለት ጉርሳቸውን በሚያገኙበት ሀገር፣ ተራራ የሚያክል ሸቀጥ በጭንቅላታቸው ተሸክመው የሚሮጡ ወገኖች በሚርመሰመሱበት ሀገር፣ ህጻን አዛውንቱ ትንሽ ባገኝ ብሎ ሊስትሮና ማስቲካ ነጋዴ በሆነበት ሀገር ፕሮፌሰሩ ኢትዮጵያውያን ሥራ-ጠል ሆዳምና ለማኝ መሆናችንን አስረግጠው ሲነግሩን  መስማት እጅጉን ያማል።

ሀገር በሞታቸው ያቆዩልን ተዋርደው አጽማቸው ከመቃብር ሀውልታቸው ከቆመበት እየፈረሰ ባለበት፣ የኢትዮጵያን ገጽታ ማቆሸሽ የመንግስት ፖሊሲ በሆነበትና ግፈኞችና ጎጠኞች ሰው በሀገሩ ሰርቶ ሰው መሆን እንዳይችል በየማዕዘናቱ እየበተኑት ባሉበት የመከራ ጊዜ የኛው የተማሩ አዛውንት ዋናው ተሳዳቢ መሆናቸው ያሳዝናል። አብረን ስለበላን ሆዳም፣ ተቸግሬአለሁ ብሎ ድጋፍ ለጠየቀ ወገን ስለለገስን ኅሊና ቢሶች አሉን። ሰውን ከመዝረፍ መለመንን ስለመረጠ ፈሪና ጅል፣ ስላመነ ሞኝና ተላላ አድርጎ መመልከት ነውር ነው። ይህ መተዛዘንና ተካፍሎ መብላት ቀለም ያልቆጠረው ኢትዮጵያዊ ያቆመውን መሰረትና  ያቆየውን ባህላዊ እሴት ልናከብረውና ልንከባከበው ይገባል።  በተከታታይ በፕሮፌሰሩ የተጻፉት ጽሁፎች የሚደመድሙት አበሻ ስራ ጠል መሆኑን፣ ሆዳምነቱንና፣ ለማኝነቱን ነው። በሚቀጥለው ጽሁፋቸው ደግሞ ሌላም ሊያስከብሩን የሚገባቸውን ባህሪያችንን ልናፍርባቸው የሚገቡ አጉል ገጽታዎች አድርገው ይጽፉልን ይሆናል። ይህ ወይ እራስን ከፍ ከፍ ለማድረግ ሌላውን ዝቅ ዝቅ ማድረግ በመፈለግ አለዚያም ተስፋ የቆረጠ ሰው አገርን በጅምላው ሊያስነውር የሚያደርገው ድርጊት ይመስላል።

ለመሆኑ ፕሮፌሰሩ ሆድ መውደድን እንዴት ይገልጹታል? ምግብ መውደድ፣ መውደድ ብቻ አይደለም አጣፍጦና አስውቦ መብላት አንደምንስ ያስወቅሳል? በውጪው አለም የምግብ ስራ ጥበብ ምንኛ የተከበረ ሙያ መሆኑን፣ ቴሌቪዥኑ በሙሉ በምግብ ስራ ፕሮግራም መጨናነቁንና የምግብ ስራ ጥበብ መጻህፍት ጸሀፊዎች ምንኛ የተከበሩ መሆናቸውን እንዴት ዘነጉት? ምግብ እኮ የህልውና መሰረት ነው በአካል ለመዳበር፣ አእምሮን ለማጎልበት፣ የማስታወስና የማሰብ አቅምን ከፍ ለማድረግ የታመቀውን የተፈጥሮ አቅም ለማውጣት የሚያግዝ ነው። በጣም የሚገርመው ደግሞ ቢወደውም ጥቅሙን ቢረዳውም እንኳ አልሚ ምግብ አግኝቶ ሳይሆን በተገኘው ምግብ ሆዱን ሞልቶ የሚያድር እንኳን በሌለበት ሀገር ውስጥ ለሚገኝ ሕዝብ በረሀቡ ላይ ሆዳም የሚል የስድብ ምርቃት ማከሉ አሳዛኝ ነገር ነው። ምክርም ይሁን ግልጽ ዓላማ የሌላቸው ጽሁፎች መጻፉ ግቡ ኢትዮጵያን ለሚያዋርዱት ‘ምሁራዊ’ ድጋፍ መስጠት ብቻ ይመስለኛል።

በምግብ አብዝቶ መብላትና ሲያመነዥጉ በመዋል የሚታወቁት የሌሎች አገሮች ዜጎች ናቸው።  ይህንን የማያውቅ ከመንደሩ አለፍ ብሎ የማየት እድል ያልገጠመው ሰው እንጂ እንደ ፕሮፌሰር አውሮፓ ኤዥያና ሰሜን አሜሪካን ያሰሰ ሊሆን አይችልም። ለዚያውም ባንድ ወገን ሆዳምና አይነቱና ብዛቱ ወደር የማይገኝለት ምግብ ስለመብላቱ የሚነገርለት ሕዝብ በሌላው የፕሮፌሰሩ ፅሁፍ ለማኝነቱንና አምላክ ደድብ ያለው ሥራ-ጠልነቱ ይበሰርለታል። አንዱን ፅሁፋቸውን ከሌላኛው ማገናኛ ድልድዩ ምን ይሆን ያሰኛል። ለማኝ እኮ አጣጥሞና አማርጦ ለመብላት ያልታደለ ምርጫ አጥ ነው። ሥራ ጠልቶና ለምኖ አማርጦ መብላት ከተቻለማ ኢትዮጵያችን መና ከሰማይ የሚዘንብባት ሁናለች ማለት ነው።

ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላው በገበታ ዙሪያ የሚሰባሰበው ለመብላት ምክንያት በመፈለግ አይደለም፤ ምግቡ የመገናኛው ማጣፈጫ እንጂ። ሰርግም ሆነ መልስ፣ ልደትም ሆነ ተዝካር፣ ፋሲካም ሆነ እንቁጣጣሽ በጋራ ገበታ መቀመጥ መሰረታዊ ምክንያቶቹ ማህበራዊ ግንኙነቶች ናቸው። የሰው ልጅ ማህበራዊ እንስሳ ነው። አብሮነቱን ካላዳበረ ተነጣጥሎ ይሞታልና የትኛውም ማህበረሰብ በየትኛውም የዓለም ጫፍ ቢኖር በራሱ መንገድ ይሰባሰባል። አብሮ ያድናል፣ ተጋግዞ ያርሳል፣ ፈረቃ ገብቶ ያመርታል። ያንን ውበት ለመስጠትና አብሮነቱን ለማሳመር ደግሞ በጋራ ገበታ ይቁዋደሳል። ታዲያ ለምንድን ነው ኢትዮጵያውያን አብረው መብላታቸው ልዩ እንከን ተደርጎ የሚቀርበው? እንዲያውም ኢትዮጵያውያንን ሰብስቦ የያዘው ጠንካራ ድር ቢኖር እንዲህ ያለው በደስታና በሀዘን አብሮ መሆኑ ነው።  አብሮ ያቆመን ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ባህላዊ እሴት እንደ ሁዋላ ቀርነትና ሆዳምነት ሲቆጠር ስቆ ማለፉ የሚያስከትለውን እራስን የማዋረድን ጣጣ ልብ ያለማለት ነው። ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የቆዩ በአብዛኛው ከሀይማኖት ጋር የተገናኙ አሰባሳቢና አገናኝ በዐላት አሏቸው። በለጸጉ የሚባሉት አገሮች ደግሞ ከሀይማኖታዊ በአላት በተጨማሪ ለንግድ የሚመቹ አዳዲስ በዐላት እየፈጠሩ  አብሮነታቸውን የሚያጠናክሩበትን መንገድ ፈጥረዋል።  የእናት ቀን፣ የአባት ቀን፣ የፍቅር ቀን፣ የምስጋና ቀን እያሉ አብረው ይበላሉ ይጠጣሉ። ስለዚህም ኢትዮጵያውያንን አብረው በመብላታቸው ሆዳም የሚላቸው በርዕሰ ጉዳዩ  ላይ ትንሽም ቢሆን ጥናት ያላደረገ ብቻ ነው።

ከዚህ ቀደም እንደ ጻፍኩት ኢትዮጵያውያንን ‘አበሻ’ ባልል እመርጣለሁ ምክንያቱም ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ለማሳነስ በርካቶች አበሻ የሚል ስያሜ ላይ በመንጠልጠል መጥፎና ደካማ የሆነውን ነገር ሲያጎሉ ማየት እየበዛ ነው። ‘አበሽ’ የሚለውን የንቀት መሰል አጠራር የሚጠቀሙትም እነማን እንደሆኑ እናውቃለንና ኢትዮጵያ እያልኩ እቀጥላለሁ። እናም ክቡር ፕሮፌሰር የአለም ሕዝብ ከእንቅልፉ ተነስቶ ማዛጋት ሲጀምር ነቃ የሚያደርገውን ቡና…. ፓስታና ማኮሮኒ እያማረጠ የሚበላበትን ስንዴ…. ‘ግሉቲን’ ሆዱን እየነፋው ፊቱን እያዠጎረጎረ የሚያስቸግረውን ሕዝብ ጤናማ የሆነ እሹኝ ፈትጉኝ የማይለውን ጤፍ ጠገብ ሲል ደግሞ የበላውን የሚያወራርድበትን ጥሙን የሚያስታግስበትን ገብስ ለአለም ያበረከተው “ሰነፍ፣ ሆዳምና ለማኝ” እየተባለ የሚዘለፈው የኢትዮጵያ ገበሬ ነው። የሀገሬ ገበሬ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ የሚተጋ ጠዋት ያሟሸውን አፉን ማታ ባገኛት እፍኝ እህል እየዘጋ የሚኖር ነው። ይህ ደግሞ ከሰማንያ በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያንን ይወክላል። ይህ ወገንዎ ክብር እንጂ ስድብ፣ ሙገሳ እንጂ ውርደት አይገባውም። በምንም መልኩ ኢትዮጵያውያንን እርሶንም ጨምሮ እግዜር በጆሮአችንን አታስቡ ብሎ መርጦ አላደደበንም። ያንን ስድብ ተቀብለው የሚኖሩ ደደቦች ካሉ ምህረቱን ያውርድላቸው። ሀገራችንን ለማጥፋት የሚያዋርዱን በቂ ጠላቶች አሉንና እራሳችንን በማዋረድ ለጠላት ስራውን አናቅልለት።

ኢትዮጵያውያንን ከሀገራቸው ውጪ የሚያሳዩትን የስራ ፍላጎትና መነሳሳት ለመመልከት እድል ላገኙ ሁሉ ኢትዮጵያውያን ሀገሬውንም ሆነ ሌሎቹን መጤዎች በልጠው ሲተጉና ውጤትም ሲያመጡ እንጂ ሰነፍ በመሆን ከሌላው አንሰው አያዩም። ስለዚህ በጅምላ ኢትዮጵያውያንን ስራጠል ሰነፍ አድርጎ መኮነኑ ውሃ አያነሳም። ኢትዮጵያውያን ስራጠል ከሆኑ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች ስለምን ወደ አረብ አገር ሊሄዱ ቻሉ? ለልመና ነበር? ለመሆኑ ኢትዮጵያውያን በተሰደዱባቸው ሀገራት በአውሮፓና አሜሪካ በአፍሪካ ሀገራትም እንኳን የሚታወቁት በስራ አይደለምን? ባዶ እጃቸውን ከሀገር ወጥተው አዲስ ሀገር ውስጥ ኑሮ መስርተው ከብረው ለመኖር የቻሉት በአስማት ነውን? ስለዚህ ፕሮፌሰሩ እነዚህ በአንዲት ጀንበር ዘርፈው የከበሩ ነጣቂዎችን መንግስት ብለው መንግስት አንደተቀበለው ቻይና እንዳረጋገጠው ብለው ስንፍናችንን ሲደመድሙ የፌዘኛ እንጂ ምሁራዊ ትችት አይመስልም። አንድን በይሉኝታና በፈሪሃ እግዚአብሄር (አምላክ) የሚኖርን  ሕዝብ አዕምሮና ሕሊና ቢስ የሚል ሰው እውን ሕሊናና አእምሮ አለው ብሎ መገመትስ ይቻላልን?

ኢትዮጵያውያንስ እንዴት ሁኖ ነው በሆዳቸው ነው የሚታወቁት የተባለው? ኢትዮጵያውያን ተጋብዘው ድግስ እንኳን ሲሄዱ “ቤታቸው ምግብ የለም እንዴ” ላለመባል እቤታቸው በልተው የሚሄዱ ናቸው። ነፃ ምግብ አለ ሲባሉ ለሳምንት የሚበቃ ቀለብ በሆዳቸው ለመጫን የሚዳዳቸው ሌሎች አንጂ ኢትዮጵያውያን አይደሉም። ኢትዮጵያዊውማ ከሆዴ ይልቅ ክብሬ በማለት እርቦትም አሁን በላሁ ነው የሚለው።

ሰዎች ይህንን ስራ ከምሰራ ለምኜ እበላለሁ የሚሉበት ዘመንም ከነበረ በትንሹ ግማሽ ምዕተ አመትን አሳልፏል። ይህም ክስ እውነት እንኩዋን ቢሆን ኢትዮጵያውያንን ለይቶ ከንቱና ርካሽ የሚያደርግበት ምንም ሚዛን የለም። በየትኛውም የአለም ክፍል ቢሆን በአንድ ወቅት የተናቀ ስራ ነበር። ዛሬም ቢሆን ይህን ከምሰራ ዌልፌር ምን አለኝ ብሎ እጁን አጣጥፎ የሚቀመጥ ስንት ፈረንጅ በየሀገሩ አለ። ሌላም አንድ እውነት አለ፣ ሰዎች ከልምዳቸው ውጪ የሚመጣን ነገር የመቀበል ፍላጎታቸው ውሱን ነው። ለምሳሌ ከብት አርቢዎች እርሻን በንቀት ይመለከታሉ። አንዳንድ ከብት አርቢዎች ለምን እነደዚህ ያለ ስራ አትሰሩም የሚባል ከአካባቢው ሁኔታ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ሲቀርብላቸው የኛ ዘሮች ይህንን አይሰሩም ይህን የሚሰሩት ሌሎች ናቸው ይላሉ። አንጥረኞች፣ አዝማሪዎች፣ ነጋዴዎች ሁሉም የለመደውን ስራ አጥብቆ መያዝ የኢትዮጵያውያን ብቻ ባህሪይ አይደለም። እንዲያም ሆኖ ኢንጅነሮች፣ የሙዚቃ ጠበብቶች፣ ዶክተሮች የመንግስት ተጡዋሪ ላለመሆንና ለቤተሰባቸው የተሻለ ህይወት ለመስጠት ስራ ሳይንቁ ከጠዋት እስከማታ መኪና በመጠበቅ፣ ታክሲ በመንዳት፣ ዘበኛ በመሆን፣ ጽዳት ሰራተኛ በመሆን ይዳክራሉ። እንዴት ነው ይህን ህዝብ ስራጠል አድርጎ መኮነን የተቻለው?

በሀገራችን ያለጥናትና በቂ መረጃ በምሁሩ ምክር የሰው ንብረት መውረስና ማህበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ጥፋት በስመ ሶሻሊዝም በተፈጸመበት ጊዜ የተመለከትነው አንድ እውነት አለ። ሁለት ስራ መስራት አድሃሪነት ነበር ገንዘብ መያዝና ፈጠራ ወንጀል ነበር። ሶሻሊዝምን ያመጣውና መስራትንና መክበርን ወንጀል ያደረገው ተማርኩ ያለው ወገን የመረጠው የሶሻሊዝም መንገድ ነበር። እንዲያም ሆኖ በአዋጅ ሰዎች ድህነትን እንዲቀበሉ በተደረገበት ጊዜ እንደ አቅምቲ ከበርቴ ተብለው ሀብት ንብረታቸው እየተዘረፈ ሰዎች ወደ እስርቤት በተጋዙበት ጊዜ አዲስ አበባ የተከፈቱ ምግብ ቤቶች (ኢድዩ ቤቶች)፣ ባልትና ቤቶች ሁሉ ሕዝባችን ችግሩን ለማሸነፍ ምን ያህል የሚፍጨረጨር እንደነበረ የሚያስመሰክር ታሪካዊ ወቅት ነበር። እነዚያ “እመቤቶችና ወይዛዝርቶች” ሆቴል ቤት ከፍቼ ለማንም ከማስተናግድ ልመና እመርጣለሁ አላሉም።

ኢትዮጵያውያኖች ለማኞች መሆናችንን ፕሮፌሰር በተለያየ ምሳሌም አስቀምጠዋል። መንግስትን መጠየቅን፣ ሰውን መማለድን (ድርድርን)፣ ትህትናንና ሰላማዊነትን ፕሮፌሰር በልመናነት መድበውታል። እውነታው ግን እነኚህ ባህሪያት አስተዋይነትንና ህግ አክባሪነትን ነው የሚያመለክቱት። ሁሉንም በጉልበት የሚያስፈጽም ማህበረሰብ በሰላም መኖርም አይችልም። በርካታ ታጋዮች የኔ መንገድ ብቻ ነው ትክክል በማለት የተለየ አመለካከት ባሳየው ላይ ተከታታይ በደልን በመፈጸማቸው ሰዉ ክፉኛ እንዲሸማቀቅ ተደርጎአል። ነገርግን ሕዝቡ የለማኝ ባህሪ ተጠናውቶታል ብሎ መደምደም ከባድ ስህተት ነው። ፕሮፌሰር ደግሞ ሰላማዊ ትግል ብቻ የሚሉ እንደመሆናቸው መጠን ዘራፍ ብሎ ለዱላ ከመጋበዝ ይልቅ መንግስትን በጥሞና መማለድን የሚደግፉ ኢንጂ እንዴት የሚኮንኑ ሊሆኑ ይቻላቸዋል?

የመጽዋችና የተመጽዋች ግንኙነት ያለው ደግሞ በኢትዮጵያ ብቻ አይደለም። ምክንያቱም ያለውና የሌለው በየሀገሩ ነው ያለው። ያለው ደግሞ ለተቸገረው መቸርን የማያውቅ ከሆነ በሰላም ወጥቶ መግባትም አይቻልም። ከመለመን ይልቅ በጉልበት ቀምተው የሚወስዱ ነጣቂዎች የበረከቱበት ሀገር ይሻላል የምንል ካለን የማሰብ አቅማችን ተናግቶአል ማለት ነው።  ኢትዮጵያውያን ካላቸው ላይ ቀንሰው ለሌላው መስጠታቸው የስነምግባርና የሞራል ባለጸጋ መሆናቸውን ያመለክታል እንጂ ልመናን የሚያበረታቱ ሰነፍ ማምረቻዎች አያሰኛቸውም። ጧሪ ያጡ አዛውንቶች፣ የአካል ጉዳተኞችና ህመምተኞች በመሆናቸው ስራ ማግኘት የማይችሉና ጤነኛም ሆነው ስራ ማግኘት ያልቻሉ መለመን ሊገደዱ ይችላሉ። ይህ ሰነፍ አያስብላቸውም። ባደጉት ሀገራትም የ ‘ዌልፌር/ድጎማ’ አሰራር አላቸውና ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የተለያዩ እርዳታዎችን ይለግሳሉ። ይህ መንግስታዊ ድጋፍ በሌለባት ኢትዮጵያ ወገን ወገኑን መርዳቱ አስፈላጊና የሚደነቅ እንጂ የሚያስወቅስ አይደለም። ኢትዮጵያውያን ይህንን የመረዳዳት ባህል ባያሳድጉ ኖሮ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በተበተነ ጊዜ መሳርያውን ተሸክሞ ሰለ እግዚአብሄር ውሀ ስጡኝ ብሎ ባልጠየቀ ነበር። ተደራጅቶ መዝረፍ ሲችል ወርቅ ቤት ተደግፎ የሚለምን በዲሲፕሊን የታነጸ ጦር ኢትዮጵያ ብቻ በመኖሩ ጨዋና ህግ አክባሪ ያደረገንን ባህል ልናመሰግን ይገባል። ከዚህም ባሻገር  ‘ልመና’ የሌለበት አገር የለም። አሜሪካም ሆነ አውሮፓ ወይም ኤዥያ በውበቱ ከሚያፈዝ ህንጻ ስር  ቆቡን ዘርግቶም የሚለምን ሆነ ፕሮፌሰር እንደጠቅሱት የድሬዳዋ ለማኝ ብር ስጠኝ እያለ እንደማዘዝ የሚያደርገው ለማኝ ሞልቶዋል።

ልመናና ጸሎት ተመሳሳይ ትርጉም ከተሰጣቸው ደግሞ ሁሉም አገሮች ውስጥ ጸሎት አለና ልመናው አለምን አስጨንቆአል ማለት ነው።  ድርድርም ልመና ከተባለ በትህትና የቀረቡ ጥያቄዎች ሁሉ ልመና ይደረጋሉና ጨዋነት እንደክፉ ባህሪ ሊታይ ነው ማለት ነው። ላሊበላነትም የልመና መስክ ሆኖ ተተችቷል። ነገር ግን ዘፋኝ ሲዲ አሳትሞ ለገበያ ሲያቀርብ ለማኝ አንለውም። አዝማሪዎችና ላሊበላዎች ደግሞ ዛሬ ላለው ኪነታዊ ጥበብ መሰረቶች ናቸው። ስለምን የቀድሞውን ነገር ሁዋላ ቀርና እርባና ቢስ እንደምናደርግ አይገባኝም።

የቆሎ ተማሪ በልመና ስለተለከፈ አይደለም የሚቀፍፈው። የሀገሬ ባላገርም የትምህርትን አስፈላገነት ስለተረዳ ካለችው ቆንጥሮ ያካፍላቸዋል።  ፕሮፌሰርም ሲማሩ የተሰጣቸው መማርያ፣ የጠጡት ወተትና  ልብሳቸውን ያጠቡበት ሳሙና እንደ ቆሎ ተማሪዎች ሰለ ማርያም ብለው ቆዳ ለብሰው ቀፈፋ ባይዞሩም ያው ከንጉሱና ከህዝቡ ቀፈፋ ነበር። እኛ ካልቻልንበት ያልቻልነውን በመጠቆም ማሻሻል እንጂ ያለፈው ትውልድ በቻለውና ባወቀበት መንገድ ሰርቶ ያቆመልንን  አገር ማዋረድ ወንጀል ነው።

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የቆመችው ባሉን ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶቻችን ነው። የድሮውን አሳድጎ ዘመናዊ ማድረግ ወይም የተኮረጀውን ከሀገር አስማምቶ ጥቅም ላይ ማዋል ስላቃተን የነበረውን ስንወነጅል ልንኖር አይገባም። አገርን በጅምላ ስንወነጅል ራሳችን የምናበረክተውን እንገምግም። ራስን እያዋረዱ ክብር መሻት ሞኝነት ነው። ከልመና ለመውጣትና ገበና ለመሸፈን አስፈላጊ የሆኑ ተቋማት እንዲፈጠሩ ማበረታት ያሉትንም ማጠናከር እንጂ ወገን በሀዘኔታ ካለችው ላይ ስለሰጠ የተቸገረም ስለለመነ ማውገዙና በሽሙጥ መውገር ምን ይረባናል? ማንም በእርግጠኛነት ሊናገር የሚችለው ኢትዮጵያውያን ለማኝ፣ ሆዳምና ሥራ-ጠል ሳይሆኑ ዘመናትን የሚሻገር ባህልን ያሳደጉ ሲቸገሩ ተረዳድተው ሲመቻቸው አብረው ተደስተው የሚያኖራቸውን ባህል ያቆዩ ታታሪ ሰራተኞችና የሚረዳዱ መሆናቸውን ነው። የእውቀት መነጽራችን ይህንን ላላስመለከተን መቃወምና መንቀፍ ብቻ የእውቀት ምልክት የሚመስለን ህዝብን ከመስደቡ ብንታቀብና  የማስተዋል አቅማችንን ብናዳብረው ይበጃል።

ሀገር አዋራጅ መሰረተቢስና ውልየለሽ ጅምላ ስድብን እውነት ነው ብሎ መቀበል ተቀብሎም ስድቡ ይገባናል በማለት እየተቀባበሉ መሰዳደብ ትክክል አይደለም። ስለዚህም በተከበሩ ፕሮፌሰር ስለተጻፈ ብቻ እንደታላቅ ግኝት በየሚዲያው ማሰራጨቱም “ሞኝን አንዴ ስደበው እራሱን ሲሰድብ ይኖራል” የሚለውን ብሂል በተግባር ማዋል ይሆናል። ኢትዮጵያንና በልጆቿ እየተሸረሸረ ያለውን ኢትዮጵያዊነትን እናድን ዘንድ እንትጋ።

biyadegelgne@hotmail.com

posted by Tseday Getachew

ለኢትዮጵያ ሰማያዊ ፓርቲ ምስክርነት

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

ሰማያዊ ፓርቲን እንደፖለቲካ ድርጅት/ፓርቲ ለምን እንደምደግፈው፣

እ.ኤ.አ ዴሴምበር 15/2013 ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብላ በምትገኘው አርሊንግተን ከተማ የስብሰባ አዳራሽ በተዘጋጀው የሰማያዊ ፓርቲ የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ ተገኝቼ  ንግግር እስካደረግሁባት ዕለት ድረስ በበርካታ ጥያቄዎች እወጠር ነበር፡፡ አንደኛው ተደጋግሞ የሚጠየቀው ጥያቄ ለበርካታ ዓመታት ገለልተኛ ሆኘ እና ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ቡድን ጋር ሳልወግን ከቆየሁ በኋላ በአሁኑ ጊዜ ለሰማያዊ ፓርቲ ለምን ያልተቋረጠ ድጋፍ በመስጠት ላይ እንደምገኝ በሚቀርብ ጥያቄ ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡

በኢትዮቱብ ድረገጽ/ethiotube.com በሰጠሁት ቃለ ምልልስ በግልጽ እንዳስቀመጥኩት ለሰማያዊ ፓርቲ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ የምሰጥበት ዋና ምክንያት የኢትዮጵያ ትኩስ ወጣት ኃይል የሀገሩን መጻኢ ዕድል የመወሰን እና በሰላማዊ የትግል ሂደት በመሳተፍ ለውጥ ለማምጣት ዝግጁ ነው የሚል ሙሉ እምነት ያለኝ በመሆኑ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ከ35 ዓመት የዕድሜ ክልል በታች የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል 70 በመቶ ይሸፍናል፡፡ እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በአብዛኛው የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ሰለባ ሆኖ የሚገኘው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ አብዛኛው የወጣት ህብረተሰብ ክፍል የኢትዮጵያ የማጎሪያ እስር ቤቶች የፖለቲካ ጭቆና እና ማስፈራራት፣ ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር የመዋል እና እስራት፣ የስቃይ፣ የመብት እረገጣ እና ከህግ አግባብ ውጭ የእስር ቤት አያያዝ ሰለባ ዒላማ ሆኖ ይገኛል፡፡ አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስር በሰደደ የስራ አጥነት ወጥመድ ተጠፍረው እና ጥራት ያለው የትምህርት ዕድል እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት መብታቸውን ተነፍገው በሀገራቸው ላይ የበይ ተመልካች ሆነው ይገኛሉ፡፡ እዚህ ላይ የእኔን “አስረጅ” ምሰክርነት ለማስመዝገብ እንዲሁም ለሰማያዊ ፓርቲ ‘ምስክርነት’ ለመስጠት ያህል  በማያወላውል መልኩ የኢትዮጵያ ወጣቶች የቆሸሸውን የጎሳ ፖለቲካ፣ አስፈሪውን የኃይማኖት ጥላቻ  እና በውሸት ድር እና ማግ የተደወረውን የቅጥፈት ተምኔታዊ ፖለቲካ በጣጥሰው በመጣል “ፍቅር የነገሰበት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ” የሚባል አንጸባራቂ ከተማ ከተራራው አናት ላይ እንደሚገነቡ ያለኝን የማይታጠፍ እምነት ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ ይህ የተቀደሰ ተግባር የዛሬው ወጣት ትውልድ ቋሚ ታሪካዊ ዕጣ ፈንታ ነው የሚል ጽኑ እምነት አለኝ፡፡

የእኔ “አስረጅ” ሆኖ መቅረብ የእራሴን ሀሳብ እና አስተያየት ከመግለጽ ባለፈ በምንም ዓይነት መልኩ የሰማያዊ ፓርቲን፣ የአመራሩን ወይም የአባላቱን ያለፈውን፣ የአሁኑን እና የወደፊቱን ድርጅታዊ እና ድርጅታዊ ያልሆነ አቋም አይወክልም፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ምንም ዓይነት ሚና የለኝም፡፡ ያለኝ ብቸኛ ሚና ቢኖር “የሰማያዊ ፓርቲ ቁጥር 1 አድናቂ” መሆኔን በኩራት መግለጼ ብቻ ነው፡፡ እዚህ ላይ የእኔ ለሰማያዊ ፓርቲ ‘በአስረጅነት’ በጽናት መቆም ቅንድቦችን ከፍ ሊያደርግ ይችላል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ጠንካራ ደጋፊ በመሆኔ ከአንዳንድ ወገኖች ህብረተሰቡን በእድሜ እየለያየ የሚል ትችት ሲሰነዘር ሰምቻለሁ፡፡ እኔ በእድሜ በመከፋፈል መረጃ የመስጠት ጨዋታ ተጫወትኩ እንጅ በስልጣን ላይ ያለው ገዥው አካል እንደሚያደርገው ሁሉ በዘር ወገኔን በመከፋፈል የቁማር ጨዋታ አልተጫወትኩም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ወጣቱ ኃይል ብይን እንዲሰጥበት በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ ጆርጅ ኦርዌል እንዳሉት ‘ዓለም አቀፋዊ ማጭበርበር ተንሰራፍቶ በሚገኝበት በዚህ ዘመን ስለእውነት መናገር አብዮታዊ ድርጊት ነው‘፡፡ በአሁኑ ጊዜ የፖለቲካ አጭበርባሪነት፣ የሞራል ዝቅጠት እና አታላይነት ተንሰራፍቶ በሚገኝበት ሁኔታ እኔ ስለሰማያዊ ፓርቲ እየሰጠሁት ያለው ‘አስረጅነት’ እንደ ‘አብዮታዊ ድርጊት’ ይቆጠራል የሚል ዘርፈ ብዙ አመለካከት አለኝ፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ቁጥር: 1  አድናቂ ለምን ሆንኩ?

በመጀመሪያ ደረጃ ሰማያዊ ፓርቲን የምደግፍበት ምክንያት ከወጣቶች፣ በወጣቶች፣ ለወጣቶች፣ የተቋቋመ የፖለቲካ ፓርቲ ስለሆነ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የአብዛኛውን የኢትዮጵያን ህብረተሰብ ፍላጎት እና ጥቅም ሊወክል የሚችል ፓርቲ ስለሆነ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ ህዝብ ከ35 ዓመት የዕድሜ ክልል በታች ያለው የህብረተሰብ ክፍል 70 በመቶውን ይሸፍናል የሚለውን ሀቅ ላሰምርበት እፈልጋለሁ፡፡ (የሚቀርበውን መረጃ ታሳቢ በማድረግ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ አማካይ የህይወት እድሜ ከ49 – 59 ዓመት ነው፡፡)

የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው ትውልድ (ወጣቱ ትውልድ) ብዙሀኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ለመወከል የሚያስችል የራሱን የፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋም ይፈልጋል፡፡ የአቦሸማኔው ትውልድ ለራሱ/ሷ መናገር፣ ለራሱ/ሷ መቆም፣ ለሴቶች፣ ለወንዶች መቆምን ይፈልጋሉ፡፡ የእራሳቸውን እና የአገራቸውን ዕጣ ፈንታ ሊወስኑ የሚችሉት እራሳቸው ወጣቶቹ ብቻ ናቸው፡፡

የጉማሬዎቹ ትውልድ (የእኔ ትውልድ) የፖለቲካ ፓርቲዎች በጉማሬዎቹ፣ ለጉማሬዎቹ የተቀመሩ እና በእነርሱ የአስተሳሰብ ንፍቀ ክበብ ውስጥ የታጠሩ ፍልስፍናዎች ስለሆኑ ከእረፍትየለሾቹ የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች (የወጣቱ ትውልድ) ህልሞች፣ ውስጣዊ ፍላጎቶች፣ ዓላማዎች እና የጋሉ ስሜቶች የስምምነት እምነቶች ንፍቀ ክበብ ውጭ ናቸው፡፡ እኛ የኢትዮጵያ የጉማሬዎች ትውልድ (የእኔ ትውልድ) የአቦሸማኔዎችን ትውልድ (የወጣቱን ትውልድ) ፍልስፍናአና አስተያየት አንረዳውም፡፡ ይህም በመሆኑ ብዙዎቻችን በጎሳ እና በክልል (“ባንቱስታን” ወይም “ክልላዊ”) የፖለቲካ ጭቃ፣ በሚያጣብቅ የጎሰኝነት ዝቃጭ ቆሻሻ፣ እና በታሪካዊ ምክንያተቢስ ጥላቻ  ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ተዘፍቀን ስንዋኝ የቆዬን ስለሆነ ለስኬታማነት የማንበቃ የተሽመደመድን የህበረተሰብ ክፍል ነን፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ትውልዶች (የወጣቶች ትውልድ) የጥንቱ ወይም የኋላቀር ፋሽን የጎሳ ማንነት ፖለቲካ እስረኛ መሆን አይፈልጉም፣ እንዲሁም ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ከእራሳቸው ጋር በጥብቅ ተቆራኝቶ በታሰረ የታሪክ ክስተት መንገድ ላይ ለመራመድ አይፈልጉም፡፡ እንዲሁም ነጻነታቸውን በማወጅ እና የእራሳቸውን ዕጣ ፈንታ ለመምረጥ በመወሰን የእራሳቸው የሆነቸውን ኢትዮጵያ መፍጠር ይፈልጋሉ፡፡

“የኢትዮጵያ የጉማሬ ቡድን” ታማኝ አባል እንዳለመሆኔ መጠን የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ትውልድ ከኢትዮጵያ የጉማሬ ትውልድ በጣም ልዩነት አለው የሚለውን እውነታ ለመቀበል እቸገራለሁ፡፡ ለእኔ እና ለእኔው የጉማሬ ትውልድ የዱላ ቅብብሎሹን ለአቦሸማኔው ትውልድ በማቀበል ከጎን ሆነን የአቦሸማኔውን ትውልድ በትህትና የምናግዝበት የመጨረሻው ጊዜ እየደረሰ መሆኑን ለመቀበል እቸገራለሁ፡፡ ለዚህም ነው እራሴን ከጉማሬ ትውልድ ወደ “አቦ -ጉማሬ” ትውልድ ያሸጋገርኩት፡፡ ይህንን ሽግግር “የአቦ – ጉማሬ ትውልድ መነሳሳት” በሚለው ትችቴ ላይ መዝግቤ ማስቀመጤ የሚታወስ ነው፡፡

በሁለተኛ ደረጃ የወደፊቱ የኢትዮጵያ ወጣት ዕጣ ፈንታ በጥልቅ ያሳስበኛል፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት ለማስታወስ እንደሞከርኩት ሁሉ “ደስታ የራቀው እና በመጥፎ ሁኔታ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ወጣት በጊዜ ቀመር ተሞልቶ ለመፈንዳት በመጠባበቅ ላይ የሚገኝ የሰው ቦምብ የመሁኑን ሀቅ ያመለክታል፡፡ የወጣቱ ተስፋ መቁረጥ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ደስታ እየራቀው መሄድ፣ በቅዠት ህይወት ውስጥ መኖር እና ለብዙ ጊዜ በሚቆይ የኢኮኖሚ ቀውስ በመደቆስ ጥንካሬን ማጣት፣ የኢኮኖሚ ዕድሎችን እና ተጠቃሚነትን ያለማግኘት እና የፖለቲካ ጭቆና በገፍ ተንሰራፍቶ መገኘት ሊፋቅ የማይችል አስተማማኝ መረጃ ነው፡፡ ወጣቱ ለነጻነት ያለው ጥልቅ ፍላጎት እና የለውጥ ፈላጊነት ስሜት በእራሱ ማረጋገጫ ነው፡፡ እዚህ ላይ ሊነሳ የሚችለው ብቸኛ ጥያቄ የሀገሪቱ ወጣቶች ለውጥን ሊያመጡ የሚችሉት እየጨመረ በመጣው ወይም በሌላ በሰላማዊ የለውጥ አማራጮች…የሚለው ነው፡፡” ሰማያዊ ፓርቲ ተስፋ ያጣውን የወጣት ኃይል ወደ ሰላማዊ ሽግግር በማምጣት በኢትዮጵያ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል የሚል እምነት አለኝ፡፡

ሦስተኛ በወጣት ኃይል አድራጊ እና ፈጣሪነት ላይ በሙሉ ልቤ እተማመናለሁ፡፡ የወጣት ሀሳብ እና ጥልቅ የለውጥ ፈላጊነት ስሜት ልብን፣ አዕምሮን እና ሀገርን የመለወጥ ኃይል አለው፡፡ የወጣት ኃይል በዓለም ላይ ከሚገኙ ጠብመንጃዎች፣ ታንኮች እና የጦር አውሮፕላኖች በላይ የበለጠ ኃይል አለው፡፡ የአሜሪካ የሲቪል መብቶች እንቅስቃሴ የተካሄደው በወጣቶች ኃይል በተከፈለ የጉልበት መስዕዋትነት አማካይነት ነው፡፡ አብዛኞቹ በአመራር ቦታ ላይ የነበሩት እና የመብት ተሟጋቾች ወጣቶቹ የህብረተሰብ ክፍሎች ነበሩ፡፡ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በቢርሚንግሀም አላባማ የተካሄደውን የሲቪል መብቶች ሰላማዊ እንቅስቃሴ ሲመሩ የ26 ዓመት ወጣት ነበሩ፡፡ በዚያን ጊዜ ጆን ሌዊስ የ23 ዓመት ወጣት የነበሩ ሲሆን 24 ጊዚያት ታስረዋል፣ እንዲሁም ድርጊቱን ሊያስታውሱት በማይችሉት መልኩ በብዙ አጋጣሚዎች ሰውነታቸው ድቅቅ እስከሚል ድረስ ተደብድበዋል፡፡ እ.ኤ.አ በሜይ 6/1963 በበርሚንግሃም ከ2000 በላይ የሚሆኑ አፍሪካ አሜሪካውያን የሁለተኛ፣ የመለስተኛ ሁለተኛ እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች የዘር መድልኦን በመቃወም ሰልፍ በመውጣታቸው ብቻ ለአሰቃቂው እስር ተዳርገዋል፡፡

ወጣት አሜሪካውያን በቬትናም ላይ በእብሪት በመነሳሳት የተካሄደውን ጦርነት እንዲቆም አድርገዋል፡፡ በካሊፎርኒያ የዩኒቨርስቲ የተጀመረው የመናገር ነጻነት እንቅስቃሴ በአሜሪካ የመናገር ነጻነትን እና የዩኒቨርስቲ አካዳሚ ነጻነትን አጎናጽፏል፡፡ ያለወጣቱ ድምጽ መስጠት ባራክ አቦማ ለፕሬዚዳንትነት መመረጥ አይችሉም ነበር፡፡ ኮሚኒስታዊ ገዥዎችን እና በቅርቡም በሰሜን አፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ለመለወጥ አስቸጋሪ ናቸው ተብለው ይታሰቡ የነበሩትን ርህራሄየለሽ አምባገነኖች በሰላማዊ ትግል አንኮታኩቶ በመጣሉ እረገድ ወጣቱ ኃይል ወሳኝ የሆነ ሚና ተጫውቷል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተፈናጥጠው የሚገኙት ገዥዎች የንጉሳዊውን አገዛዝ እና አምባገነናዊውን የወታደራዊ መንግስት በትጥቅ ትግል ለማንበርከክ ሲፋለሙ የነበሩ ወጣት “አብዮተኞች” ነበሩ፡፡ በእርጅና የእድሜ ጊዚያቸው ግን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ምድር ለማስወገድ ሲፋለሙት የነበረውን ጭራቅ ሆነው ተቀምጠዋል፡፡ ከዚህ አንጻር በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ህብረተሰብ ለመመስረት ለበርካታ ዘመናት መስዕዋትነትን በመክፈል የእራሳቸውን ድርሻ በመወጣት ላይ ባሉት የኢትዮጵያ ወጣቶች ኃይል ላይ ሙሉ እምነት አለኝ፡፡ እ.ኤ.አ በ2005 አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ ገዥ አካል ታጣቂዎች እንደ አበደ ውሻ በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ በመክለፍለፍ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን በጥይት ጨፍጭፈዋል ገድለዋል፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ ለእስራት ዳርገዋል፡፡ (በዚያን ጊዜ በሰው ልጅ ህይወት ላይ በጣም አስደንጋጭ እና አስፈሪ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ወንጀል በማየቴ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ተሟጋችነት አንደቀላቀል ተገድጃለሁ፡፡) በአሁኑ ጊዜም እንኳ የኢትዮጵያ ወጣቶች ለዴሞክራሲ፣ ለህግ ልዕልና፣ ለነጻነት እና ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ሲባል የደም፣ የላብ እና የእንባ መስዕዋትነት በመክፈል ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ምርጡ እና ብሩህ አዕምሮ ያለው ወጣት እየተቀጣ፣ ፍርደገምድል ፍርድ እየተበየነበት፣ እየታሰረ፣ እና ጸጥ እረጭ ብሎ እንዲገዛ እየተደረገ ነው፡፡ ከእነዚህ የወጣት ዝርዝር የመጀመሪያው እረድፍ ላይ የሚገኙት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ በቀለ ገርባ፣ አቡበካር አህመድ፣ ውብሸት ታዬ፣ ኦልባና ሌሊሳ፣ አህመዲን ጀቤል፣ አህመድ ሙስጣፋ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ በቅርቡ ከህይወት የተለየው የኔሰው ገብሬ እና ሌሎች ለቁጥር የሚያታክቱ ትንታግ የኢትዮጵያ ወጣቶች ናቸው፡፡

በመጨረሻ ሆኖም ግን አስተዋጽኦው ቀላል ካልሆነው ከሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራም ጋር ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በደንብ አስቦበት እና የሀገሪቱን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል ተግባራዊ ፕሮግራም ነድፎ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ ነው፡፡ ከእኔ ልዩ አተያይ እና ስጋት አንጻር በፍትሀዊ አስተዳደር፣ በሰብአዊ መብቶች እና በህግ የበላይነት አተገባበር ላይ ትኩረት በማድረግ የፓርቲውን ፕሮግራም ስገመግመው በጠንካራ መሰረት ላይ የተዋቀረ ልዩ ፓርቲ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ፓርቲው ሙሉ በሙሉ ነጻ የሆነ እንዲሁም ከፖለቲካ ተጽዕኖ እና ጣልቃገብነት ፍጹም ነጻ የሆነ እና ብቃት ያለው የፍትህ ስርዓት በሀገሪቱ እንዲመሰረት ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ዳኞች ሲያጠፉ መከሰስ ያለባቸው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በሙያቸው በቋሚነት ጡረታ እስከሚወጡበት ጊዜ ድረስ ተቀጥረው እንዲሰሩ ያደርጋል፡፡ ፓርቲው ህገመንግስታዊ ፍርድ ቤት ከነሙሉ ስልጣኑ ጋር እንዲቋቋም ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ኢትዮጵያ ፈርማ ባጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ውሎች እና ስምምነቶች ለመገዛት እና ለተግባራዊነታቸውም ዕውን መሆን ፓርቲው ጠንክሮ እንደሚሰራ ቃል ገብቷል፡፡ የግለሰብ መብቶችን ጥበቃ የመናገር እና የእምነት ነጻነቶችን ጨምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ፓርቲው ቃል ገብቷል፡፡ መንግስት እና ኃይማኖት በግልጽ መለያየት እንዳለባቸው ፓርቲው በጽኑ ያምናል፡፡ ፓርቲው ማንኛውንም በብዙሀን መገናኛ ዘዴዎች ላይ የሚደረግን ቅድመ ምርመራ አጥብቆ ይቃወማል፣ እንዲሁም ከህግ አግባብ ውጭ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ማህበራት እንዳይዘጉ ያደርጋል፡፡ የሀገሪቱ የጦር እና የደህንነት ኃይል ታማኝነቱ ለሀገሪቱ ህገመንግስት መሆን እንዳለበት እና በምንም ዓይነት መልኩ ለፖለቲካ ፓርቲ፣ ለጎሳ ቡድን፣ ለክልል ወይም ለሌላ አካል ታማኝ መሆን እንደሌለበት ፓርቲው በፕሮግራሙ ላይ አጽንኦ በመስጠት አስፍሮታል፡፡ የፓርቲው የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ እና የባህል ጉዳዮችም እንደዚሁ በተመሳሳይ መልኩ ትኩረትን በጣም የሚስቡ ናቸው፡፡

ሰማያዊ ፓርቲን  እንደ  ንቅናቄ እና የኢትዮጵያ የአቦሸማኔዎች (ወጣቶች) ትውልድን እውነተኛ ድምጽ ለምን እንደምደግፍ፣

እንደ እራሴ ሀሳብ ሰማያዊ ፓርቲ እንደማንኛውም ተወዳድሮ ስልጣን በመያዝ ወደ ስልጣን ቢሮ ከሚገባ  የፖለቲካ ድርጅት የበለጠ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንደፖለቲካ ድርጅት እራሱን ቢያዘጋጅ እና በተለመደው መልክ ምርጫ ቢያሸንፍ እና የፓርላማ ወንበር ቢይዝ ምንም አዲስ የማገኘው ነገር የለም፡፡ ከ80 በላይ “የተመዘገቡ ፓርቲዎች” ባሉባት ሀገር (በጣም አብዛኞቹ ለይስሙላ የተቋቋሙ የጎሳ የፖለቲካ ፓርቲዎች) እና ገዥው “ፓርቲ” በ99.6 በመቶ በሚያሸንፍበት ሁኔታ ከግማሽ ነጥብ በመቶ ያነሰ ድምጽ ለማግኘት እንደሰማያዊ ፓርቲ ሁሉ ሌላ ፓርቲ ተመዝግቦ ለዚህች በጣም በጣም ትንሽ ለሆነችው ድምጽ ለመወዳደር የመሞከሩን አስፈላጊነት ትርጉምየለሽ ያደርገዋል፡፡ ለዚህም ነው ሰማያዊ ፓርቲን በኢትዮጵያ ከወጣቶች፣ ለወጣቶች፣ በወጣቶች የተቋቋመ የወጣቶች ንቅናቄ ነው የሚል እምነት ያለኝ፡፡

“የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄን” የኢትዮጵያ ወጣቶች ለእራሳቸው እና ለወደፊቱ ትውልድ የሚተላለፍ ህልማቸውን እና ሀሳቦቻቸውን የሚተገብር ድርጅታዊ ተቋም አድርጌ እወስወደዋለሁ፡፡ እንደ ንቅናቄ ሰማያዊ ፓርቲ በብዙ የአቅም ደረጃዎች ላይ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያን ወጣቶች ስለብዙው የሀገራቸው ታሪክ፣ ልማዶች እና ባህሎች እንዲያውቁ የሚያደርግ “የትምህርት” ተቋም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች የማትከፋፈል የአንዲት ኢትዮጵያ፣ ኃያል ወራሪውን የአውሮፓ ኃይል አሸንፋ እና አሳፍራ የመለሰች የኩሩ አርበኞች ዘር የትውልድ ሀረግ መሆናቸውን ያስተምራል፡፡ እንደ አሁኑ ሳይሆን በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ በዓለም እና በአፍሪካ ለሚኖሩ ጥቁር ህዝቦች የኩራት ፈርጥ ነበረች፡፡ የአሁኑ የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ የቀደመውን ኩራታችንን እንደገና መልሶ ለኢትዮጵያውያን ህዝቦች የማጎናጸፍ ዓላማን ሰንቆ ተነስቷል፡፡

“የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄን” ዋና ዋና ዕሴቶች እጋራለሁ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ገዥዎችን እና ኢፍትሀዊነትን በሰላማዊ የትግል ስልት መንገዶች የማስወገድ እምነት አለው፡፡ በዓለም ላይ በየትኛውም ቦታ ገዥዎችን እና ኢፍትሀዊነትን በሰላማዊ የትግል ስልቶች በመጠቀም ለማስወገድ እሰብካለሁ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ ወጣቶች የሽግግር ኃይል ላይ እምነት አለው፡፡ ባለፉት ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያ “እና በአፍሪካ” ላይ ወጣቶች የጻፍኳቸውን የሰኞ ዕለታዊ ትችቶች በሙሉ መልክ በማስያዝ በጥራዝ ቢዘጋጁ የኢትዮጵያ ወጣቶችን የሽግግር ኃይል በተጨባጭ የሚያመላክት ማስረጃ ይሆናልሉ፡፡ የእኔ መፈክርአሁንም በፊትም ወደፊትም ፣ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ተባበሩ፣ በፍጹም እጅ እንዳትሰጡ፣ ኃይል ለኢትዮጵያ ወጣቶች!” ነው፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ አንድ ግብ ብቻ አለው፣ “ፍቅር የነገሰበትን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ” መፍጠር፣ ልክ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በረዥሙ የትግል ጉዟቸው በአሜሪካ የሰብአዊ እና የሲቪል መብቶችን በማለም “ፍቅር የነገሰበት ማህበረሰብን” ለመመስረት እንዳደረጉት ተጋድሎ ሁሉ፡፡ ዶ/ር ኪንግ እንዲህ ብለው አስተማሩ፣ “የሰላማዊ ትግል ማህበራዊ ለውጥ መጨረሻው ዕርቅ ነው፣ መጨረሻው ኃጢያትን ተናዝዞ ንስሀ መግባት ነው፣ መጨረሻው ፍቅር የነገሰበትን ማህበረሰብ መመስረት ነው፣ እንግዲህ ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ እና ፍቅር ነው በባላንጣነት የሚተያዩትን ወገኖች ወደ ጓደኝነት የሚያመጣው፡፡” “ፍቅር የነገሰበት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ“ ከክልላዊነት (ባንቱስታን) አመድነት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚወጣ እምነቴ የጸና ነው፡፡

“ፍቅር የነገሰበት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ” የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ መሰረቱ አንድነት፣ ሰላም እና ተስፋ ነው፡፡ “ፍቅር የነገሰበት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ” ሰው በመሆኑ ብቻ አንድ ይሆናል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከከፋፋይ የጎሰኝነት እና ከአፍቅሮ የጎሰኝነት ስሜት ነጻ ይሆናል፡፡ ይህ ዓይነቱ ማህበረሰብ እኩልነት፣ ፍትሀዊነት እና ተጠያቂነት ያለው ህብረተሰብ ለመመስረት ጥረት ያደርጋል፡፡ “ፍቅር የነገሰበት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ“ ከእራሱ እና ከጎረቤቱ ጋር ሰላም ፈጥሮ የሚኖር ህብረተሰብ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከጎሳ አለመቻቻል እና ጥላቻ ነጻ የሆነ እንዲሁም ከፍርሃት፣ ጥልቅ ጥላቻ እና ከገዥዎች እና ከጨቋኞች ነጻ የሆነ ማህበረሰብ ይፈጥራል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ደኃ እና ሀብታም፣ ወጣት እና ሽማግሌ፣ ወንድ እና ሴት፣ ክርስቲያን እና ሙስሊም… ለማለም ነጻ፣ ለማሰብ ነጻ፣ ለመናገር፣ ለመስማት እና ለመጻፍ ነጻ፣ ከጣልቃገብነት ነጻ ሆኖ ለማምለክ፣ ለመፍጠር ነጻ፣ ለመስራት ነጻ እና ነጻ ለመሆን ነጻ የሆነ ዓላማ ይዞ ነው የተነሳው፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ ሰላምን በአግባቡ በመጠቀም ጥላቻን፣ የጥላቻ መንፈስን፣ ለመጣላት መቸኮልን፣ ወደ ጓደኝነት፣ መተሳሰብ እና መከባበር በማሻጋገር ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምን ያመጣል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ንቅናቄው ከመራራ ትችት በውይይት፣ ከመቃረን በስምምነት፣ ከጥላቻ በፍቅር፣ እና ጭካኔን፣ ወንጀለኝነትን እና ታጋሽየለሽነትን ለማሸነፍ የሰው ልጅን ክብር ከፍ የሚያደርጉትን መርሆዎች እንደሚከተል እምነቴ የጸና ነው፡፡ “ፍቅር የነገሰበት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ“ “የተስፋ እና የህልሞች መሬት” ነው፡፡ ይህ ማህበረሰብ ወጣቶች ለእኩል ዕድሎች፣ ለእኩል መብት እና ፍትህ እንዲያስቡ የሚያደርግ ነው፡፡ ይህ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ ወጣቶች ነጻ ሆነው ተስፋዎቻቸውን እና ህልሞቻቸውን በጋራ መካፈል እንዲችሉ የሚያበቃ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ወጣቶች የማይገታ ተስፋ አንዳላቸው ጽኑ እምነት አለኝ፡፡

ለሰማያዊ ፓርቲ ምን ማድረግ እንዳለብን እንጠይቅ፣

ሁሉም ኢትዮጵዊ በተለይም የእኔ የጉማሬው ትውልድ ከሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ ጎን እንድንቆም  አበረታታለሁ፣ እማጸናለሁም፡፡ አውቃለሁ፣ ብዙዎቻችሁ ቀደም ሲል ድጋፋችሁን ለመስጠት በሞከራችሁበት ጊዜ በተፈጠረው ያልተሳካ የትግል ውጤት ምክንያት ተገቢነት ያላቸው ጥያቄዎች፣ ብዥታዎች፣ እና ጥርጣሬዎች ሊኖሯቹህ እንደሚችሉ እገነዘባለሁ፡፡ “እነዚህ ወጣት እና የአመራር ልምድ የሌላቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር የሚሰሩ ለመሆናቸው ምን ማስተማመኛ አለን?“ በማለት ተጠይቂያሁ፡፡ እኔም እንዲህ የሚል መልስ ሰጠሁ፣ “ልምድ ያለን እና እምነት የሚጣልብን የጉማሬው ትውልድ አመራሮች የሆንነው ከዚህ ቀደም እንዴት ሰራን?“ አፍሪካ በማያቋርጥ አምባገነናዊ የአገዛዝ መዳፍ ስር ወድቃ ስለምትገኝ የወጣቱን የህብረተሰብ ትኩረት የሚስቡ በርካታ ነገሮች እየተፈጠሩ ነው፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች ስብዕናዎቻቸው ከምን ከምን ነገሮች እንደተዋቀሩ አሳይተውናል፡፡ የተዋቀሩባቸው የመሰረት ድንጋዮች በዝርዝር ሲታዩ የሚከተሉትን ያካትታል፡ ድፍረት፣ የሞራል ጽናት፣ ስነስርዓት፣ ብስለት፣ ጀግንነት፣ ክብር፣ የመንፈስ ጽናት፣ ፈጣሪነት፣ ትህትና፣ ሀሳብ አፍላቂነት እና እራስን ለመስዋዕትነት ማዘጋጀት ናቸው፡፡ ስብዕናዎቻቸውን በማክበር ላለመንበርከክ ሲሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል፣ ታስረዋል፣ እንዲሁም ተደብድበዋል፡፡ ሰላማዊ ትግሎቻቸውን አላቋረጡም፡፡ እኛን በማሳመን ሙሉ ድጋፋችንን ከማግኘታቸው በፊት ሌላ ምን ተጨማሪ መስዕዋትነት መክፈል ይኖርባቸዋል? ወጣቶች እና አዲስ ነገር ለማምጣት ጥልቅ ፍላጎት ያላቸው ናቸው፣ በሰላማዊ ትግል ለውጥ ለማምጣት ተገቢው ልምድ ያላቸው ሲሆን ይህንኑ ልምዳቸውን እስከመጨረሻው ይቀጥሉበታል፡፡

አንዳንድ ሰዎች ሰማያዊ ፓርቲ ለገዥው አካል ወይም ለሌላ ድብቅ ዓላማ ላላቸው ኃይሎች ተቀጣሪዎች ላለመሆናቸው ምን ማረጋገጫ አለ በማለት ይጠይቃሉ፡፡ ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ የምለው ነገር ቢኖር የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች የገዥው አካል ታማኝ ሎሌዎች ናቸው ብለን የምናስብ ከሆነ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም፣ ፕሮፌሰር ያዕቆብ ኃይለማርያም እና ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያምም ሊጠቀሱ የሚችሉ ታማኝ ሎሌዎች ናቸው ማለት ነው፡፡ ገዥው አካል ብልህ ከሆነ ሰማያዊ ፓርቲ ስለየህግ የበላይነት እና ስለዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ያሉትን ፕሮግራሞች በመገናኛ ብዙሀን ለማስተላለፍ እንዲችል መፍቀድ ይኖርበታል፣ ይህን ካደረገ እኔ ለዚህ ደጋፊ ነኝ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ገዥው አካል ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች (በሚስጥር እስር ቤቶች የሚገኙትን ጨምሮ) የሚለቅ ከሆነ፣ ጨቋኝ ህጎችን የሚሰርዝ ከሆነ፣ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎችን እና ምርጫ ማጭበርበርን የሚያቋም ከሆነ ከመንገድ በመውጣት የመጀመሪያ በመሆን እነሱን በማሞገስ የምዘምር እሆናለሁ፡፡ ጉዳዩ በስልጣን ላይ ስላሉት ሰዎች አይደለም፣ ሆኖም ግን ጉዳዩ በስልጣን ላይ ስላሉት ጭራቃዊ ድርጊት ስለሚፈጽሙት ሰዎች እንጅ፡፡

ባለፉት አስርት ወይም ከዚያ በላይ ዓመታት ተመስርተው በመንቀሳቀስ ላይ የነበሩት እና በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት የፖለቲካ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ስኬታማ ሳይሆኑ እንደቀሩ አንዳንድ ሰዎች ይነግሩኛል፡፡ እንዲህ በማለትም ይጠይቁኛል፣ “ሰማያዊ ፓርቲም ስኬታማ ሳይሆን የሚወድቅ ላለመሆኑ ምን ዋስትና አለህ?“ ሰማያዊ ፓርቲ ላለመውደቁ ምንም ዓይነት ዋስትናዎች የሉም፡፡ ስኬታማ ሳይሆን የሚወድቅ ከሆነ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት ጽናት እና እራስን ለስነስርዓት ያለማስገዛት፣ የዓላማ ጽናት እና እራስን መስዕዋት ለማድረግ ያለመቻል ጉድለት ሊሆን አይችልም፡፡ በዋናነት ለውድቀቱ ምክንያት ሊሆን የሚችለው ድጋፍ ያለማግኘት፣ ቅን መንፈስ ያለመኖር፣ በእራስ የመተማመን ጉድለት፣ የለጋሽነት እጥረት እና በአገር ውስጥ ካለው ኢትዮጵያውያን/ት ወገኖች እና ከዲያስፖራው ማህበረሰብ የማቴሪያል እና የሞራል ድጋፍ ለማግኘት ያለመቻል ነው፡፡ ፓርቲው ስኬታማ ባይሆን እና ለውድቀት ቢዳረግ በእብሪትነት ተነሳስተን፣ የሌባ ጣታችንን ወደ ፓርቲው በመቀሰር፣ “ተናግሬ አልነበረም!“ ስንል ሦስቱ ጣቶቻችን ደግሞ ቀስ ብለው ወደ እኛ እያመለከቱ መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም፡፡ ኔልሰን ማንዴላ እንዲህ ሲሉ ተማጽነዋል፣ “እኔን በማስመዘግባቸው ስኬቶች አትገምግሙኝ፣ይልቁንም ምን ያህል ጊዜ እንደወደቅሁ እና ከውድቀቶች ተመልሸ እንደተነሳሁ እንጅ” ብለዋል፡፡ ከዚህ አንጻር ሰማያዊ ፓርቲ ወደፊት ምን ያህል ጊዜ አዳልጦት ይወድቃል ብለን ከመገምገም ይልቅ ፓርቲው በእኛ እገዛ እና ድጋፍ ከውድቀቱ እንደገና ለመነሳት ምን ያህል ጊዜ ጥረት ያደርጋል የሚለውን ነው መገምገም የሚኖርብን፡፡

ባለፉት በርካታ ጊዚያት እንደታየው የሚያዋጡት የገንዘብ ድጋፍ አላግባብ ሊባክን ይችላል የሚል ስጋታቸውን አንዳንድ ሰዎች ገልጸውልኛል፡፡ ጠንካራ የሆኑ የተጠያቂነት እና ግልጸኝነት ዋስትናዎችን ማግኘት ይፈልጋሉ፡፡ እንዲህ ብለውም ይጠይቁኛል፣ “ባለፉት ጊዚያት ሌሎች እንዳደረጉት ሁሉ ሰማያዊ ፓርቲም በእርሱ ላይ ያለንን እምነት ላለመሸርሸሩ በምን ሁኔታ ማረጋገጥ እንችላለን?”

በሰሜን አሜሪካ ያለው የሰማያዊ ፓርቲ የድጋፍ ስብስብ በጣም ጠንካራ እና በስነስርዓት የታነጸ የኢትዮጵያ ወጣት ኃይል ስለሆነ ከዚህ ስብስብ ጋር መተዋወቄ እና አብሬም መስራቴ ታላቅ ክብር እና ደስታ ይሰጠኛል፡፡ እነዚህ ወጣት ኢትዮጵያውያን/ት የኢትዮጵያን ወጣቶች ትግል ለመደገፍ ከኪሳቸው በርካታ ገንዘብ በማውጣት በስራ ላይ እንዲውል በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ የሙያ ስብጥራቸውን ስንመለከት ወጣት ፕሮፌሽናሎች፣ በንግድ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ወንዶች እና ሴቶች እንዲሁም የኢትዮጵያን የጎሳ፣ የጾታ እና የባህል ህብረ ብሄር የሚወክሉ ናቸው፡፡ የተያቂነትን እና ግልጸኝነትን ዋጋ በሚገባ የተገነዘቡ ናቸው፡፡ እርስ በእርሳቸው በመተማመን እና ለእሴቶቻቸው ተገዥ በመሆን ድጋፋቸውን የሚሰጡ ናቸው፡፡ ለወጣቶቹ ዕድሎችን በመስጠት መሞከር እና ለምሰጠው የድጋፍ ገንዘብ ችግር የለብኝም፣ ምክንያቱም ወጣቶቹ የዚህ አይነት ዉርደት ላይ መውደቅ አንደማይሹ ተገንዝበአለሁ፡፡ መርህን በሚያከብሩት የኢትዮጵያ ወጣቶች እና ህዝቦች ታላቅ እምነት አለኝ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች ትክክለኛውን ነገር ይሰራሉ የሚል እምነት የእኔ ዋስትና ነው፡፡

እ.ኤ.አ ዴሴምበር 15/2013  በኣርሊንግቶን ከተማ አዳራሽ ለመጀመሪያ ጊዜ በተጠራው የሰማያዊ ፓርቲ ስብሰባ ላይ በመገኘት ባደረግሁት ንግግር የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ይልቃል ጌትነት እርዳታ ለመሰብሰብ እና ለኑስ አምስት ሳንቲም ልመና ወደ አሜሪካ አልመጣም በማለት ለተሰበሰበው ታዳሚ ተናግሬ ነበር፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከእኛ በሰሜን አሜሪካ ከምንኖር ኢትዮጵያውያን/ት እርዳታ ወይም የገንዘብ ልገሳ አይፈልግም፡፡ ይልቁንም ይልቃል ወደ አሜሪካ የመጣው ገዥው አካል በሰማያዊ ፓርቲ ላይ እያደረሰ ያለውን አስቸጋሪ ሁኔታ፣ የህግ ስርዓት ሂደቱን፣ በአባላቱ ላይ የሚደርሱባቸውን ችግሮች፣ ጨካኝ አምባገነናዊ ስርዓት ባለበት ሁኔታ ፓርቲው ዓላማዎቹን ለማሳካት እንዴት እየሰራ እንዳለ እና የኢትዮጵያ ወጣቶች ነጻ እና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ትግል ላይ ያሏቸውን ህልሞች እና ተስፋዎች ለእኛ ለወገኖቹ ለማካፈል ነው፡፡

በአሜሪካ ከተሞች ለሰማያዊ ፓርቲ ስብሰባዎች በተያዙ ፕሮግራሞች ሁሉ በመገኘት በኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እንዲመጣ ለሚታገሉት ባለራዕይ ወጣቶች ለይልቃል፣ ለሰማያዊ ፓርቲ አባላት እና ለንቅናቄው ድጋፍ ሰጭ ጀግኖች ወጣቶች አቀባበል ማድረግ እንዳለብን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ በከተማው የስብሰባ አዳራሽ የሚካሄዱትን ስብሰባዎች ወጣት መሪዎች እንደእነ ይልቃል፣ እስክንድር፣ አንዷለም፣ ርዕዮት እና ሌሎች ብዙዎቹ በግል ያደረጓቸውን የጀግንነት ስራዎች በማወደስ ብቻ የምናልፈው ሳይሆን በአዳራሹ ማክበር ያለብን ሌሎችም ወጣት ጀግኖች በአደባባይ በመንገዶች በመውጣት ተቃውሟቸውን እንዲህ እያሉ ላሰሙት ጭምር ነው፣ “አንለያይም! አንለያይም!“ (እንደተባበርን እንኖራለን!) ወይም ኢትዮጵያ፣ አገራችን! ኢትዮጵያ፣ አገራችን! (ኢትዮጵያ፣ የእኛ አገር!)፡፡ (አንለያይም! አገራችን፣ ኢትዮጵያ! በማለት ወጣቶቹ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ሲጮኹ ስሰማ ሁልጊዜ ይነሽጠኛል፡፡)

የሰማያዊ ፓርቲ መሪ ይልቃል እዚህ በመካከላችን መገኘቱ ለእኔ እ.ኤ.አ በ2005 በተደረገው ምርጫ የተጭበረበረውን ድምጽ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው በአምባገነኑ መሪ ትዕዛዝ በታጣቂዎች በግፍ ያለቁት ወጣቶች እንዳልሞቱ የሚያደርግ ኩራትን በመፍጠር እለቱን እንድናስታውሰው ያደርገናል፡፡ ይህ ዕለት የህግ የበላይነት ምንም ይሁን ምን መቀጠል እንዳለበት እና ለነጻ እና ለፍትሀዊ ምርጫ ዕውን መሆን በሰላማዊ ትግል ሲፋለሙ ለነበሩት እና በግፍ ለተገደሉት ወጣቶች መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የይልቃል በመካከላችን መገኘት ሕያው ምስክር ነው፡፡

ለሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ ምን ማድረግ እንችላለን? የተሸለ ጥያቄ ሊሆን የሚችለው ለወጣት ጀግኖቻችን፣ ሲፋለሙ ህይወታቸውን ላጡት፣ በእስር ቤት በመማቀቅ ላይ ለሚገኙት፣ የግርፋት ስቃይ እየተፈጸመባቸው ላሉት፣ በየዕለቱ ማስፈራራት ለሚፈጸምባቸው፣ ስቃይ እና ውርደት ለሚፈጸምባቸው  ምስጋናችንን፣ ክብር መስጠታችንን እና አድናቆታችንን እንዴት ነው መግለጽ የምንችለው? የሚል ይሆናል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ማግኘት የሚችለውን ማንኛውንም ድጋፍ ማግኘት ይፈልጋል፡፡ የሞራል ድጋፋችንን ይፈልጋሉ፡፡ የእኛን ማበረታታት ይፈልጋሉ፣ እኛ በእነርሱ ላይ እምነት ያለን መሆኑን ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡ ከሁሉም በላይ ወጣቶችን በሙሉ ለመድረስ እንዲችሉ፣ ለትምህርት እና ለግንዛቤ መፍጠሪያ ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ ሊውሉ የሚችሉ ከእኛ የማቴሪያል ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡ ድርጅታዊ ህልውናቸውን ለማጠናከር እና በመላ አገሪቱ ቀጣይነት ባለው መልኩ መንቀሳቀስ እንዲችሉ የእኛን የማቴሪያል ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡ ጠንካራ የህግ መከላከያ ገንዘብ ለማግኘት የእኛን ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡ በአፍሪካ አህጉር አላግባብ በበለጸጉ፣ ሙስናን በሚያራምዱ እና ምህረትየለሽ አምባገነኖች ላይ ትግል ለማድረግ የማቴሪያል ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡

ለሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ የምናደርገው የገንዘብ ድጋፍ በሰላማዊ ትግል ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለዴሞክራሲ እና ለሰብአዊ መብቶች መጠበቅ የሚያደርጉትን በቅርብ በመደገፍ ምስጋናቸንን በማቅረብ ከጎናቸው መሆናችንን ለመግለጽ ነው፡፡ ለሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ ያለን ስጦታ ሰላሟ በእራሷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለማየት ሀብትን ማፍሰስ ነው፡፡ እንሰጣለን፣ እንለግሳለን፣ በዚህም መሰረት ቀጣዩ የኢትዮጵያ ትውልድ በእኛ ስህተት እና ድንቁርና በተፈጠረው ሁኔታ ሳይቸገር በአዲሲቱ ኢትዮጵያ በሰላም ይኖራል፡፡ የእኛን ወጣት ትውልድ መደገፍ የእያንዳንዳችን እና እንደሀገርም የማህበረሰባችን ኃላፊነት ነው፡፡ እኛ ልጆቻችንን፣ ሁሉንም በኢትዮጵያ ያሉ ወጣቶችን ካልረዳን… ማን እንዲረዳ ይፈለጋል?

ሰማያዊ ፓርቲ ለእኛ ምን እንደሚያደርግልን እንጠይቅ፣

እ.ኤ.አ በኦገስት 2012 በአንድ ትችቴ ላይ “የአቦሸማኔው ትውልድ፣ የጉማሬው ትውልድ” በሚል ርዕስ እንዲህ ስል ጠየቅሁ፣ “ኢትዮጵያን ሊጠብቅ ሊያድን የሚችል ማን ነው?“ በሰላማዊ መንገድ በኢትዮጵያ ለውጥ ለማምጣት መከተል ያለብን መንገድ አገራዊ ውይይት ማድረግ እንደሆነ የኢትዮጵን ወጣቶች ተማጽኛለሁ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አቤቱታዬን ለበርካታ ጊዚያት በተደጋጋሚ ሳቀርብ ቆይቻለሁ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄን በመጀመሪያ በተጠናከረ መልኩ በእራሳቸው በፓርቲው አባላት ላይ በቀጣይም በመላው የኢትዮጵያ ወጣት ማህበረሰብ ላይ የዕርቅ ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የዕርቅ ውይይት በኢትዮጵያ የወጣቱ ህብረተሰብ ውይይት መጀመር ቀጥሎ የሚፈጸም ይሆናል የሚል እምነት አለኝ፡፡

የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ትውልድ እራሳቸውን ማጠናከር አለባቸው፣ የእራሳቸውን የፖለቲካ እና የማህበራዊ ቦታ መፍጠር አለባቸው፡፡ አገራቸው ከአምባገነንነት ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በሰላማዊ መንገድ ሽግግር ማድረግ እንድትችል የእራሳቸውን አጀንዳ በመቅረጽ ወጣቶቹ ዘርፈ ብዙ ውይይቶችን መጀመር አለባቸው፡፡ የቋንቋ፣ የኃይማኖት፣ የጎሳ፣ የጾታ፣ የክልል እና ወዘተ ገደብ ሳይኖር ወጣቶች የእራሳቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ የዘመቻ እቅድ ማዘጋጀት እና በወጣቱ ማህበረሰብ ዘንድ ንግግሮችን ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ውይይቶቻቸው ግልጽ በሆኑ መርሆዎች፣ በእውነት፣ በዴሞክራሲያዊ ተግባሮች እና በነጻነት እና በሰብአዊ መብቶች መከበር ላይ የተመሰረቱ መሆን አለባቸው፡፡ ከፍርሃት እና ከጭፍን ጥላቻ ነጻ ሆነው መወያየት አለባቸው፡፡ ሆኖም ግን በመከባበር እና በሰለጠነ መንገድ መከናወን ይኖርበታል፡፡ ከሁሉም በላይ የአቦሸማኔው ትውልድ የውይይት ሂደቱን “የእራሱ” ማድረግ አለበት፡፡ የአቦሸማኔው ትውልድ በሚሰበሰብበት ጊዜ የጉማሬው ትውልድም ይገኛል፣ ነገር ግን በዝምታ  ማዳመጥ ነው ያለባቸው:: ወጣቱን የህብረተሰብ ክፍል በቀላሉ ለማታለል የሚችሉ መሰሪ የጉማሬው ትውልድ አበጋዞች ስለሚኖሩ ምንጊዜም ቢሆን የአቦሸማኔው ትውልድ ነቅቶ ባይነ ቁራኛ ሊጠብቃቸው ይገባል፡፡ በአረብ የለውጥ አመጾች/Arab Spring እንደታየው ሁሉ ወጣቶች በወጥመድ ተይዘው የታዩባቸው ሁኔታዎች ስለነበሩ የኢትዮጵያ ወጣቶችም በወጥመዶች እንዳይጠለፉ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው፡፡ በመጨረሻም በማታለል የተካኑት የጉማሬው ትውልድ አባላት ወጣቶችን ከጨዋታ ውጭ እንዲሆኑ፣ እንዲጭበረበሩ፣ እንዲደለሉ ያደርጓቸዋል፡፡ መጠንቀቅ ተገቢ ነው::

የዕርቅ ወይይቶች በድንገት እና ተራ በሆነ መልኩ በወጣት የመብት ተሟጋቾች መካከል መጀመር እንዳለባቸው አምናለሁ፡፡ ለምሳሌ እንደዚህ ያሉ ውይይቶች በሚግባቡ እና ተመሳሳይነት አስተሳሰብ ባላቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ወጣቶች መካከል በመንደር ወይም በጎረቤት ደረጃ መካሄድ ይችላሉ፡፡ ወጣት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ወጣቶች አቅማቸውን፣ ያላቸውን እምቅ ኃይል፣ ዕድሎችን እና ችግሮችን ለይተው በማውጣት ዕቅድ ነድፈው ትናንሽ ህብረተሰብ አቀፍ የዕርቅ ውይይቶችን ማካሄድ ይችላሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ያሉትን ድርጅቶች፣ ተቋሞች፣ ማህበራትን እና መድረኮችን በመጠቀም ወጣት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የዕርቅ ውይይቶችን በማካሄድ የወጣቶችን ግንዛቤ ማሳደግ  ይችላሉ፡፡

የዕርቅ ወይይት መነጋገርን ብቻ አይደለም የሚያካትተው ነገር ግን እርስ በእርስ በንቃት መደማመጥን ጭምር እንጅ፡፡ ወጣቶች ከኢትዮጵያ ብሄረሰቦች እርስ በእርስ በመማማር የእራሳቸውን ብዙሀንነት ማጠናከር ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ትውልድ ከጉማሬው ትውልድ ስህተቶች እና ከሌሎች አገሮች ወጣቶች ልምዶችም ለመማር ይችላሉ፡፡ የኢትዮጵያ አቦሸመኔ ትውልድ የሚያደርጓቸው የዕርቅ ውይይቶች በመርህ ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ አጥብቄ እማጸናለሁ፡፡ ወጣቶች ደስተኛ ባልሆኑባቸው ነገሮች ላይ መቃወም መቻል አለባቸው፡፡ በነገሮች ላይ አለመስማማት ማለት የዕድሜ ልክ ጠላት መሆን ማለት አይደለም፡፡ የሰለጠነ ውይይት ማድረግ ለጉማሬው ትውልድ ከባድ ቢሆንም ለአቦሸማኔው ትውልድ ግን በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡

ምነው ዝምታ?

“ዓለም አቀፍ ማጭበርበር በተንሰራፋባት ምድር ላይ“ ዝምታ ከቃላት እና ከስዕል የበለጠ ይናገራል፡፡ ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዲህ አሉ፣ “በመጨረሻ የምናስታውሰው የጠላቶቻችንን ቃላት አይደለም፣ ነገር ግን የጓደኞቻችንን ዝምታ እንጅ“፡፡ ይህንን ትችት ካጠናቀቅሁ በኋላ “ስለጓደኞቻችን” “ዝምታ” መናገር አለብኝ፣ ምክንያቱም አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ከመናገር የበለጠ የመግለጽ ችሎታ አለው፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች ፓርቲ መሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በመጡበት ጊዜ እና እስከ አሁን ድረስ ለበርካታ ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን ታዳሚዎች በተገኙበት ስብሰባ ላይ የወጣቶቹ መሪ ንግግር በሚያሰሙበት ጊዜ ትኩረትን በሚስብ መልኩ የአሜሪካ ድምጽ ወኪል ጋዜጠኛ ሳይገኝ ቀርቷል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ድርጊቱን ለመዘገብ አንድም ጋዜጠኛ ሳይልክ ቀርቷል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ዜናውን ለመዘገብ ለምን እንዳልተገኘ የማውቀው ነገር የለም፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ስብሰባ ግን ከተለያዩ የኢትዮጵያ ስፖርቶች፣ ባህላዊ፣ አካዳሚያዊ እና የማህበረሰብ ስብሰባዎች እንዲሁም የመጽሀፍት ርክክብ ፊርማ ስነስርዓት ሲኖር የአሜሪካ ድምጽ በሳምንቱ መጀመራያ እና በሳምንቱ ማጠቃለያ በዋሽንግተን ዙሪያ አካባቢ ሰፊ ሽፋን ሰጥቶ ከሚዘግበው የሚያንስ አለመሆኑን በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፡፡ ምናልባትም ሰማያዊ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ወጣቶች ለአሜሪካ ድምጽ ምንም ያልሆኑ ቀላል ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ለወጣቶቹ ግድ ላይኖረው ይችላል፣ የኢትዮጵያ ወጣቶችም ለአሜሪካ ድምጽ ጉዳያቸው አይደለም፡፡

የአሜሪካ ድምጽ እንዲገነዘበው የምፈልገው ነገር ግን በሟቹ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዝናዊ “ኢትዮጵያ  ላይ ዘር ማጥፋት” ፕሮፓጋንዳ አካሂደዋል የሚል ክስ በይፋ ባስታወቀበት ጊዜና ሌላም ጊዜ ወንጭፋቸውን ሲያነጣጥሩባቸው እና ቀስቶቻቸውን ሲቀስሩባቸው በነበረበት ወቅት ከእነርሱ ጎን ቆሜ ነበር፡፡ በዚያ ውንጀላ ጊዜ የአሜሪካ ድምጽ በጽናት ለመርህ የቆሙ መሆናቸውን፣ ለሙያው ክብር ሰጥተው ይዘግቡ እንደነበር፣ ያለአድልኦ እንደሚሰሩ ጊዜን አክብረው ደግመው እና ደጋግመው እንደሚዘግቡ ሽንጤን ገትሬ ተከራክሪያለሁ፡፡ የአሜሪካ ድምጽ በሰማያዊ ፓርቲ ጉባኤ ላይ በመገኘት እንደ ድሮው ሁሉ በጽናት ለመርህ ቆመው፣ ለሙያው ክብር ሰጥተው እና ያለአድልኦ የጉባኤውን ሂደት እንደሚዘግቡ እጠብቅ ነበር፡፡ ምናልባትም ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ጊዜ የአሜሪካ ድምጽ የሚለውን ስያሜ የዝምታ ድምጽ ተብሎ መጠራት ጀመረ ወይ ብለው እየጠየቁ ይሆናል፡፡ የዝምታ ድምጹን ለመስማት እንቀጥላለን፣ ሆኖም ግን በዝምታ አይደለም የምንሰማው፡፡

ከዚህ በኋላ ዝምታ መኖር የለበትም፣ ድምጻችንን ከፍ አድርገን እንጩህ እና ለሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ ድጋፋችንን እናሳይ፣ ዝምታን ከዚህ በኋላ እናቁም፡፡ ለሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ ድጋፋችንን በይፋ እናውጅ፡፡ ቀጥ ብለን እንቁም እና በእነርሱ እንኩራ፡፡ ለሚያካሂዱት ሰላማዊ እና ግጭት አልባ የስርዓት ለውጥ ትግል አድናቆታችንን በመግለጽ ድጋፋችንን እንስጥ፡፡ ወደ ነጻነት የሚወስደው መንገድ የቱንም ያህል ረዥም ጉዞ ቢፈጅ ከእነርሱ ጋር መሆናችንን እናረጋግጥላቸው፡፡ ወጣቶቹ በመጨረሻም ድልአድራጊዎች ይሆናሉ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ አባላትን እንደምንወዳቸው በተግባር እናረጋግጥላቸው!

የኢትዮጵያ ወጣቶች ተባበሩ፣ በፍጹም እጅ እንዳትሰጡ፡፡ ኃይል ለኢትዮጵያውያን/ት ወጣቶች!

ታህሳስ 15 ቀን 2006 ዓ.ም

EMF

Professor Alemayehu G. Mariam

posted by Tseday Getachew

በአረና መጠናከር የሰጉት ህወሓቶች ‘ዕርቅ’ ፈፀሙ – አብረሃ ደስታ ከመቀሌ

 

ህወሓቶች ለሁለት ተከፍሎው የደብረፅዮን (የአዲስ አበባ) ና የአባይ ወልዱ (የትግራይ) ቡድን ተሰይመው ሲነታረኩ መቆየታቸው ይታወቃል። ከወራት በፊት ጀምሮ ደግሞ ሁለቱም ቡድኖች ‘ለማስታረቅ’ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ጠቅሼ ነበር።

ትንቅንቅ

አሁን አቶ ስብሃት ነጋ (ከቢተው በላይ ጋር በመሆን) ሁለቱም ባላንጣ ቡድኖች ‘ማስታረቅ’ ችለዋል። ዕርቁ የተፈፀመው በነ ደብረፅዮን ቡድን አሸናፊነት ነው። የነ አባይ ወልዱ ቡድን በመሸነፉ ምክንያት አቶ አባይ ወልዱ ከነ ስብሃት ነጋ ጋር እንዲስማማ ምክንያት ሁነዋል። የነ አባይ ቡድን የተዳከመበት ምክንያት ለሁለት በመከፈሉ ነው። አቶ አባይ ወልዱ ከአቶ ቴድሮስ ሐጎስ፣ ኢያሱ ተስፋይ፣ ተክለወይኒ አሰፋ፣ ኪሮስ ቢተው፣ በየነ መክሩ ወዘተ መግባባት ባለመቻሉ ከአዲስ አበባዎቹ ጋር ለመስማማት ተገደዋል።

 

በስምምነቱ መሰረት ህወሓት በአዲስ አበባዎቹ ፕላን ይጓዛል። በ’መለስ ራእይ’ ስም ህዝብ መጀንጀን ይቀራል። በሙስና ሰበብ ባለስልጣናት ማሳሰርም ይቀራል። ከአሁኑ በኋል ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣናት በሙስና ሰበብ አይታሰሩም። በቀጣዩ የኢህአዴግ ጉባኤ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ከህወሓት እንዲሆን ጥረት ይደረጋል (ዶር ቴድሮስ አድሐኖም)።

ይህ የህወሓቶች የ’ዕርቅ ሂደት’ ባብዛኛው የብአዴን አመራር አባላትና በተወሰኑ የኦህዴድ መሪዎች ቅሬታ አስነስተዋል። ህወሓቶች ለመታረቅ የተገደዱበት ምክንያት በተቃዋሚዎች ስልጣን እንዳይነጠቁ በመስጋት ነው። ዓረና ፓርቲ ለህወሓቶች ትልቅ ስጋት በመፍጠሩ ነው። የፀጥታ ሃይሉ መፈራረስም ሌላ ህወሓቶች ያስደነገጠ ጉዳይ ነው። በዕርቁ ሂደት ከፍተኛ ሚና የተጫወተው አቶ ስብሃት ነጋ ነው።

የዕርቅ ሂደቱ በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ከፍተኛ አለመግባባት ሊፈጥር ይችላል። ኢህአዴግ በዉስጥ ለውስጥ የስልጣን ሹክቻ ምክንያት የሚዳከምበት አጋጣሚ መፈጠሩ አይቀርም። ዕርቁ ግዝያዊና ስትራተጂካዊ ብቻ ነው። የታረቁት መግባባት ስለ ፈጠሩ ሳይሆን የጋራ ጠላትን ለመከላከል ብቻ ነው።

https://www.zehabesha.com/

posted by Tseday Getachew

ሰበር ዜና ከሳውዲ አረቢያ ! ሮብ ምሽት በመንፈሃ ዙሪያ መጠነ ሰፊ ጥብቅ ፍተሻ ተጀመረ !

ነቢዩ ሲራክ

* በሪያድ የኢትዮጵያ ኢንባሲ የተጀመረውን ፍተሻ በማረጋገጥ ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ዜጎች በሰላማዊ መንገድ በአስቸኳይ ለጸጥታ አስከባሪዎች እጅ በመስጠት ወደ መጠለያ በመግባት ወደ ሃገር እንዲገቡ ማምሻውን ባወጣው ማስታወቂያ አሳስቧል ። ካለፉት ሳምንታት ወዲህ በሪያድ መንፉሃ በኢንባሲውና በሃገር ሽማግሌዎች የተቋቋሙ የመረጋጋት ኮሚቴ አባላት ወደ መንፉሃና ኢትዮጵያውያን በሚበዙባቸው ምንደሮች በመንቀሳቀስ ዜጎች ያለ ምንም ጉዳት እጃቸውን ሰጥተው ወደ ሃገር ለመግባት እንዲዘጋጁ የመከረ ቢሆንም ጥረቱ አልተሳካም ነበር ።  የሪያድ ኢናባሲ የሽማግሌዎች ኮሚቴ አባላት ባደረጉት ቅስቀሳ ወደ ሃገር ለመግባት ባልተጨበጠ ተስፋ የተዘናጉ ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ ያልያዙ ወደ ሃገር በመግባቱ ላይ እንዳያቅማሙ መምከራቸው ይጠቀሳል !

* አሁን በተጀመረው የመንፉሃ ፍተሻ ማዋከብ የለበትም ። ህጋዊ መኖርያ ፍቃድ የሌለውን ብቻ እንደሚይዙና ከአሰሪው (ከከፊሉ) ጋር ይሰራል አይሰራም የሚባል ማጣራትም ሲካሔድ አልተስተዋለም ተብሏል ።

* ከአሰሪው ጋር የማይሰራ እንደ ህገ ወጥ እንደሚቆጠር የሳውዲ ህግ በግልጽ ያሳወቀ ሲሆን የጅዳና የሪያድ ኢንባሲ ይህ ህግ እንደሚጸና ተደጋጋሚ ማስታወቂያ በማውጣት “በሰላም ወደ ሃገራችሁ ግቡ!” በማለት ሲመክሩና ሲወተውቱ ሰንብተዋል።

* በቀጣዩ መጠነ ሰፊ የማጣራት ዘመቻም ከአሰሪው (ከከፊሉ) ጋር የማይሰራ እንደ ህጋዊ ስለሚቆጠር የሳውዲ መንግስት በፈቃደኝነት እጃቸውን የሚሰጡት ወገኖች ወደ ሃገር መስደድ እንደተጠናቀቀ አንወጣም ባሉት ላይ ፍተሻ በማድረግ በእስራትና በገንዘብ እንደሚቀጣ በኢንባሲና በቆንስል መስሪያ ቤቶች በኩል ባስተላለፈው ማስጠንቀቂያ አስታውቋል ።

*  ቁጥራቸው በሽዎች የሚገመቱ ዜጎች እስካሁንም ድረስ ወደ ሃገር ግቡ የሚለውን ጥሪ ባለመቀበል የተዘናጉበት ሁኔታ ይስተዋላል ። ይሁን እንጅ ካለፉት ሁለት ቀናት ወዲህ መንቀሳቀስ  ያልጀመረው የጅዳ አካባቢ በርካታ ነዋሪዎች ወደ ሃገር ቤት ለመግባት ወደ ተዘጋጀው መጠለያ በመግባት ላይ ናቸው ። ከአሰሪያቸው ጋር ስለማይሰሩ ህገ ወጥ የተባሉት ግን አሁንም እንቅስቃሴ አለማሳየታቸው ይመለከታል ።

* የጅዳ ቆንስልና የወገን ለወገን ደራሽ ኮሚቴውም አውቶቡስን በአፋጣኝ እንዲቀርብ በማድረጉ ረገድ ከቆንሰሉ ሃላፊዎች ጋር በመተባበር ለነዋሪው ድጋፍ በማድረግ ላይ ናቸው ። ህጋዊ ሰነድ የሌላችሁ አስፈላጊውን ውሳኔ መውሰድና በእድሉ መጠቀም ይጠበቅችኋል። እድሉን መጠቀም መቻል ብልህነት ነው !

ጀሮ ያለው ይስማ

ነቢዩ ሲራክ

 

posted by Tseday Getachew

ሚሊየነሩ ኒቆዲሞስ ዜናዊ (ከእየሩሳሌም አርአያ)

bfa6c-images1

ኒቆዲሞስ ዜናዊ የአቶ መለስ ዜናዊ ወንድም ነው። ከወ/ሮ አለማሽ ገ/ልኡልና ከአቶ ዜናዊ አስረሳኸኝ የተወለዱ ወንድማማቾች ናቸው። ኒቆዲሞስ በደርግ ስርአት በክብሪት ፋብሪካ ተቀጥሮ በተራ ሰራተኝነት ይሰራ ነበር። የአካል ጉዳተኛ (አንድ እግሩ) የሆነው ኒቆዲሞስ ከተራ ወዝአደርነት ወጥቶ ሚሊየነር ለመሆን የበቃው ደርግ ወድቆ ሕወሐት/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ነበር። የፋብሪካ ስራውን በግንቦት 1983ዓ.ም ማግስት የለቀቀው የአቶ መለስ ወንድም ኒቆዲሞስ ከአሜሪካ በ25ሺህ ዶላር የተገዛች አዲስ አውቶማቲክ ማርሽ አውቶሞቢል እንዲይዝ ተደረገ። ተራ ወዛደር የነበረ ሰው 25ሺህ ዶላር የሚያወጣ መኪና ሊገዛበት የሚችል የገንዘብ አቅም እንደሌለው ግልፅ ቢሆንም ነገር ግን ይህን ያክል የገንዘብ መጠን በማውጣት ለኒቆዲሞስ የተበረከተለት ስጦታ ወንድሙ አቶ መለስ ዜናዊ የሚመሩት ሕወሐት እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነበር። ይህም ብቻ አይደለም፤ ኒቆዲሞስ አካል ጉዳተኛ ነው በሚል ሰበብ አውቶሞቢሉ የጉምሩክ ቀረጥ ሳይከፈልበት ነበር አገር ውስጥ የገባው። ይህን ጉዳይ በተመለከተ “ወጋህታ” የተባለች በትግርኛ ቋንቋ በአገር ውስጥ ትታተም የነበረች የነፃው ፕሬስ ጋዜጣ ከጉምሩክ ለኒቆዲሞስ ዜናዊ ያለቀረጥ መኪናው እንዲገባ የተሰጠውን፣ በስሙ ተፅፎ ከነመኪናው ሻንሲ ቁጥር ጭምር የተገለፀበትን ደረሰኝ ማስረጃ በማውጣት ጋዜጣዋ አጋልጣለች። ከዜና ዘገባው ጋር በተያያዘ በወቅቱ በተለያዩ ጋዜጦችና ሌሎች ወገኖች ከተነሱት አስተያየት አዘል ጥያቄዎች ተከታዩ ዋናው ነበር፤ « ..ኒቆዲሞስ ዜናዊ ያለቀረጥ አውቶሞቢል እንዲገባለት የተደረገው ከበላይ አካል በተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ ነው። የገንዘብ ምንጩ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት እንደሆኑ ግልፅ ነው። ከመኪናው ግዢ እስከ ጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ፍቃድ ድረስ ሙስና ተፈፅሟል። ኒቆዲሞስ ይህን ህገ-ወጥ ጥቅም እንዲያገኝ ሲደረግ የአገሪቱ መሪ አቶ መለስ ወንድም በመሆኑ ነው። ስለዚህም በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ አቶ መለስ ከሙስናው ጋር በተያያዘ ሊጠየቁ ግድ ነው። ለምሳሌ በሙስና እንዲከሰሱ ከተደረጉት ባለስልጣናት አንዱ አቶ ስዬ አብርሃ የቀረበባቸው ክስ በቂ ማስረጃ ወይም ማመሳከሪያ ነው። አቶ ስዬ ለወንድማቸው ምህረተአብ አብርሃ ሰባት መኪኖች ያለቀረጥ እንዲገቡ አድርገዋል የሚለው ክስ ይጠቀሳል። አንድ መኪና ሆነ ሰባት አሊያም ሰባት መቶ..ቀረጥ እስካልተከፈለባቸው ድረስ ሙስና ለመሆኑ አያጠያይቅም። ስለዚህም የኒቆዲሞስ ጉዳይ ሙስና መሆኑ ግልፅ ነው። ከተፈፀመው ቀረጥ ያለመክፈል ክስ ጋር ኒቆዲሞስና ወንድሙ አቶ መለስ በሙስና ሊከሰሱ ይገባ ነበር። » የሚሉ ነጥቦች ነበሩ ከተለያዩ ወገኖች ይነሱ የነበረው። ይህ ጉዳይ በተለይ በስፋት አነጋጋሪ ሆኖ የነበረው በዘጠናዎቹ የመጀመሪያ አመታት ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ተከታዩ ነው።

ኒቆዲሞስ ዜናዊ ከተራ ወዝአድርነት ወጥቶ በአንድ ግዜ ሚሊየነር የሆነበት ሚስጥሩ በ1988 ዓ.ም አንድ የኤርትራና ጣልያን ዘር ያለው ግለሰብ ከሮም አዲስ አበባ ይመጣል። ከዚያም ከኒቆዲሞስ ዜናዊ በጋራ « ጃክሮስ ኢትዮጲያ » የተባለ ድርጅት ያቋቁማሉ። ኒቆዲሞስ የጃክሮስ ግማሽ (50%) ባለድርሻ ሆኖ ነበር ድርጅቱ የተመሰረተው። “ጃክሮስ” በተቋቋመ ማግስት የመንግስት ሚዲያ የሆኑትን የኢትዮጲያ ቴሌቪዥንና ራዲዮ እንዲሁም ፋና ራዲዮ በማስታወቂያ ተቆጣጠረው። በተጨማሪ የአማረ አረጋዊ « ሪፖርተር » ጋዜጣ ማስታወቂያ በተጋነነ መልኩ ከማውጣት ባለፈ ስለ ድርጅቱ (ጃክሮስ) ሰፊ የዜና ዘገባና ትንታኔ በመስራት ተከታታይ ሽፋን መስጠት ያዘ። በጋዜጣውና በመንግስት መገናኛ ይቀርቡ የነበሩት ማስታወቂያዎችና ዘገባዎች ፥ « ..ጃክሮስ ኢትዮጲያ, በአገራችን የመጀመሪያው የመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚያካሂድ፤ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ ቪላዎችን በመገንባት ለደንበኞቹ በአጭር ግዜ ውስጥ ሰርቶ የሚያስረክብ ነው፤ ለግንባታ ከሚጠቀማቸው ቁሳ-ቁሶች መካከል በተለይ ለቪላው ማሳማሪያ የሚጠቀማቸው ከውጭ አገር የመጡና ዘመናዊ ናቸው፤ እንደ ደንበኛው ፍላጎትና ምርጫ የሚገነባው በቂ የዋስትና ሽፋን በድርጅቱ የሚሰጠው ሲሆን፣ ጃክሮስን የተለየ የሚያደርገው የሚገነቡት ቪላዎች ስታንዳርዳቸውን የጠበቁና የውጭ አገር ዘመናዊ ቪላዎች አይነት መሆናቸው ጭምር ነው። ደንበኛው ሙሉ ክፍያ የሚከፍል ከሆነ በአንድ አመት ግዜ ውስጥ መኖሪያውን አጠናቆ ያስረክባል፤ ከደንበኛው ጋር በሚደረግ ስምምነት ክፍያው ተፈፃሚ ይሆናል፤ ይህ ማለት የረጅም አመት ክፍያ ድርጅቱ ይሰጣል።…» የሚሉት በተጋነነ መልክ ይቀርቡ ከነበሩት ይጠቀሳሉ።

ድርጅቱ እንደ ሽፋን የተጠቀመበትና የተጠቀሱት ሚዲያዎች ያራግቡ የነበረበት አንድ አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር። በ1988ዓ.ም የአትላንታ ኦሎምፒክ የሚካሄድበት አመት ነበር። እነ ሃይሌ ገ/ስላሴ ለመጀመሪያ ጊዜ ኦሎምፒክ የሚሳተፉበት፣ እነ ፋጡማ ሮባና ደራርቱ ቱሉ የተካተቱበት ጭምር ነበር። ሁሉም ኢትዮጲያዊ ማለት ይቻላል ከወራቶች ቀደም ብሎ ውድድሩን በጉጉት እንዲጠብቅ የተገደደበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። “ጃክሮስ” ይህን አጋጣሚ ለመጠቀም ኢላማ አድርጎ የተነሳው የአንጋፋው አትሌት ሻለቃ ዋሚ ቢራቱን ቤት በነፃ እገነባለሁ በሚል ነበር። በቀድሞ ወረዳ 12 ቀበሌ 07 የሚገኘውን የዋሚ ቢራቱ መኖሪያ በሁለት ወር ውስጥ ሰርቶ እንደጨረሰ ተናገረ። ቀደም ሲል የነበረውን የዋሚ ቤት በማደስ የሰራውና በከፍተኛ ደረጃ የተራገበለት መኖሪያ በቲቪ መስኮት የታየውና ተጨባጩ እውነታ ለየቅል ነበሩ። ለቤቱ ግንባታ ተብሎ ዙሪያውን የዋለው ለተለያዩ ቁሳቁሶች ማሸጊያነት (ለምሳሌ ከውጭ የሚገቡ ፍሪጆችና ቴፕ..ወዘተ ጉዳት እንዳይገጥማቸው ከውስጥ በማሸጊያነት ) የሚውለው ፎም ነበር። ከዚያ በቀለም እንዲያሸበርቅ ከተደረገ በኋላ « 2 ሚሊዮን ብርበማውጣት ጃክሮስ ለዋሚ ቢራቱ ቤት ገንብቶ አስረከበ..» ተብሎ በጋዜጣውና በሚዲያ አስነገረ። አንጋፋው አትሌት በወቅቱ ከአሜሪካለመጣውና ቀበሌ 11 ለሚኖረው እስክንድር አሰፋ ስለቤቱ ሲናገር በሃዘን ጭምር ነበር፤ « የበፊቱ መኖሪያዬ ይሻለኝ ነበር። እንኳን 2 ሚሊዮን ብር 1ሺህ ብር አልወጣበትም። እኔን መነገጃ ማድረጋቸው ለምን እንደሆነ አልገባኝም።» ነበር ያለው ዋሚ። በእርግጥም እነኒቆዲሞስ በዋሚ ነግደዋል።

ከአሜሪካ የመጡ መኖሪያ ቤት ፈላጊዎች ጃክሮስን አምነው 70ሚሊዮን አስረከቡ። ሌሎች ወገኖችም ቀለጡ። አንድ አመት ቢጠብቁ ምንም ነገር የለም። ከአሜሪካ የመጡ ወገኖች ከብዙ መንከራተት በኋላ የደረሰባቸውን በደል በኢ.ቲ.ቪ “አይናችን” ፕሮግራም ቀርበው « ለአመታት ሰሃን አጥበን፣ ደም ተፍተን ሰርተን ያጠራቀምነውን ገንዘብ በአደባባይ ተዘረፍን። ህግና መንግስት ባለበት አገር እንዴት እንዘረፋለን?..መንግስት ይፍረደን!.» በማለት በእንባ እየተራጩ አቤቱታቸውን አሰሙ። እነ ኒቆዲሞስ ከህብረት ኢንሹራንስ ጋር የዋስትና ውል አለን ብለው ያሉትም በጭራሽ ከተገለፀው ድርጅት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው የህብረት ኢንሹራንስ ዋና ሃላፊ አቶ ኢየሱስወርቅ ዛፉ በወቅቱ አጋለጡ። ኤርትራዊው የጃክሮስ ባለድርሻ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በወረዳ 12 ፖሊስ ጣቢያ እንዲታሰር ተደረገ። የሚገርመው ከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል መሆኑ እየታወቀ፣ ጉዳዩ በማእከላዊ ምርመራ መያዝ ሲገባው ወይም የጃክሮስ ቢሮ ይገኝበት በነበረው ቦሌ አካባቢ ባለ ፖሊስ ጣቢያ መታየት ሲገባው…ከድርጊቱ ጋር ግንኙነት በሌለው ወረዳ 12 የፖሊስ ጣቢያ ጉዳዩ መያዙና መታሰሩ እንቆቅልሽ ነበር። ሶስት ቀን ብቻ ከታሰረ በኋላ ፍ/ቤት ሳይቀርብ “በ2ሺህ ብር ዋስ” ተፈታ። በተፈታ ማግስት በቦሌ እንዲወጣ ተደረገ። ከፍተኛውን ሚና የተጫወተው ኒቆዲሞስ ነበር። የተዘረፉት ወገኖች በድጋሚ ወደ ኢ.ቲ.ቪ ቢሄዱም መስተናገድ አልቻሉም። ምክንያቱ ደግሞ ግልፅ ነበር።

የዘረፋው ጉዳይ በነፃው ፕሬስ በየግዜው ቢነሳም ሰሚ ግን አልነበረም። ነሐሴ 1993ዓ.ም አቶ መለስ ዜናዊ ከጋዜጠኛ ሴኮቱሬ ስለጉዳዩ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ አስገራሚ ነበር። ሴኮ « ከወንድሞ ጋር በተያያዘ የሚነሳ ነገር አለ፤ ስለጉዳዩ የሚሉት ነገር ይኖራል?» ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ « በመጀመሪያ ደረጃ ወንድሜን ያገኘሁት ከአስር አመት በኋላ በእናታችን የቀብር ስነስርአት ላይ ነው። አዲስ አበባ እንደገባን ካገኘሁት በኋላ አግኝቼው አላውቅም። የተባለውን ጉዳይ በተመለከተ እነደሰማሁ ከዚህ ተግባር እንዲታቀብ ነግሬው ነበር» አሉ። የአቶ መለስ ምላሽ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነበር፤ “አግኝቼው አላውቅም” ካሉ በኋላ መልሰው ደግሞ “ከዚህ ተግባር እንዲታቀብ ነግሬው ነበር” አሉ። ሌላው ነጥብ ወንድማቸው ኒቆዲሞስ በዘረፋ ወንጀል ተሰማርቶ እንደነበር ማመናቸውን በግልፅ አስቀምጠዋል።

ኒቆዲሞስ ዜናዊ በአቋራጭ ዘርፎ ሚሊየነር ሆነ። እጅግ አምባገነን ባህርይ የተጠናወተው ሰው ነው። ማን እንዳስታጠቀው የማይታወቅ ማካሮቭ ሽጉጥ አለው። በቅሎ ቤት አካባቢ በሚገኘው “ሃረግ” መዝናኛ ያዘወትር ነበር። በሴተኛ አዳሪዎች ላይ ሽጉጥ እየመዘዘ ፍዳቸውን ያሳይ ነበር። ማንም አይጠይቀውም።

ሲጠቃለል፥ ከጥቂት ወራት በፊት በመለስ ዜናዊ ቤተሰብ ዙሪያ በኢ.ቲ.ቪ አንድ ፕሮግራም ተሰርቶ ነበር። «ጠላ ሻጭ» ወዘተ ተብለው የቀረቡት ከአቶ መለስ ጋር በአባት የሚገናኙ ናቸው። ኒቆዲሞስና መለስ ግን የአንድ እናትና አባት ልጆች ናቸው። ስለሚሊየነሩ ኒቆዲሞስ ምንም የተባለ ነገር የለም። ለምን እሱ በፕሮግራሙ አልተካተተም?…ምክንያቱ ደግሞ ግልፅ ነው። ዘርፎ ሃብታም እንደሆነ በማስረጃ ስለተጋለጠና ህብረተሰቡ ጉዳዩን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ነው።

ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com

posted by Tseday Getachew

Opportunity for TPLF/EPRDF to right the wrong and for Ethiopia to reclaim its legal and historic rights

By Eneh LeHaggareh

On December 6, 2013, a number of media reports includingAljazeera and Africa Review have all indicated that the ruling party in Ethiopia (TPLF/EPRDF) and the  Isayas led EPLF in Eritrea are currently negotiating through a mediator, Omar AlBashir of the Sudan.

On December 16, 2013, in an opinion that appeared on the online publication African Argument: Herman Cohen, the former Assistant Secretary of State for Africa, also alluded to the same rapprochement  stating that “in recent months, positive signals have been coming from both countries. “

In principle, this writer is not against the idea of resolving conflict and differences through peaceful negotiation. However, I believe, a meaningful conflict resolution requires addressing the unspoken but true concerns of the Ethiopian people. In my opinion, any attempt to move forward without addressing these outstanding issues will only aggravate the sense of injustice thereby sawing the seed for continued conflict.

I am an Ethiopian therefore; first and foremost my focus is safeguarding the current and future interest of Ethiopia.

First and foremost, any attempt to resolve this outstanding issue should weigh-in the fact that Ethiopians have been betrayed by the ruling TPLF/EPRDF regime when it comes to some of the cardinal  decisions made about the unity and territorial integrity of their country. Here are some of the highlights:-

The “referendums” of 1993 was conducted in a way that did not represent the interest of Ethiopians. Ethiopians were completely excluded from having a say in that highly important decision.  Such a decision of monumental consequence was made in a closed door away from the people of Ethiopia.  At the time, the government was only transitional and with no such mandate whatsoever from the general public.

 • Ethiopia’s historical and legal rights were completely ignored. Instead, ill-conceived political calculation and ideological gimmick dictated the ruling group’s extremely short sighted decisions. Thanks largely to Mr. Zenawi’s and his small circle’s decision, Ethiopia’s right of access to the sea was completely denied. It is noteworthy to mention here that even the so-called outside negotiators like Herman Cohen were baffled by Meles’s disregard of this distinct and less controversial possibility.
 • Following the 1998-2000 war that killed over 70 thousand people, once again, the ruling group in Addis failed to protect the best interests of the Ethiopian people. The possibility for a military solution was sabotaged by the order of none other than the PM Meles Zenawi .
 • The so called “Algers agreement “basically does not take into account, the historical, legal and strategic interests of Ethiopia. The Algers agreement hands Badme over to Eritrea and does not even contemplate providing Ethiopia with access to its historic and legal port of Assab.  As a number of prominent legal scholars have documented, the Algers agreement was a tragic miscarriage of justice. The “lawyers” representing Ethiopia were arguing in favour of Eritrea, not Ethiopia (see Asseb Yeman Nat, by Dr Yakob H.Mariam , 2004 Et Calendar).   As Leo Tolstoy, once wrote “Wrong does not cease to be wrong because the majority share in it.” ― Leo TolstoyA Confession . The unfairness of using colonial references to disadvantage Ethiopia was wrong and should not have been accepted as a legal base to settle such disputes. Assab and Bademe have and should always belong to Ethiopia. Anything less would be a betrayal of the inhabitants of these regions.
 • Many of the then key decision makers within the TPLF/EPRDF now acknowledge that these were historical wrongs of the ruling TPLF/ EPRDF when it comes to issues related to Eritrea. Chief among those who have publicly declared their positions are the then President Negaso Gidada, PM Tamrat Layne, Defence Minsiter Seye Abraha, and Mr Gebru Asrat (then then Governor of Kilil One -Tigray Region).
 • Even today, issues related to Eritrea are not yet fully settled. At this point, the ruling TPLF/ EPRDF has an opportunity to right some of the wrongs of the past. Hence, It should stand firm and demonstrate that it stands for the best interests of Ethiopia. The interest of 97 million people should not be in any way compromised. The involved world knows how misguided and lopsided both Eritrean referendum of 1993 and the Algers Agreement of post war 1998-2000 have been. There is nothing wrong to take measures to address the injustice done to Ethiopia.

Action matters

The current leaders of TPLF/EPRDF have to understand that they cannot and should not continue to disadvantage and disregard their own country. The government of PM Hailemariam Desalegn should learn from the bad and fatalistic practices of the past  and conduct business by being loyal to the will and desire of Ethiopians and Ethiopia’s own sovereign interest – not to the will of some foreign power. This government should not surrender the right of Ethiopia to have full access to the sea port. Ethiopia cannot continue to pay tens of millions of dollars to others to use their port and put our national interest in jeopardy.

Until such time that EPRDF/TPLF shows its commitment to Ethiopian Unity, it will continue to pay dearly and suffer from lack of trust by Ethiopians.  One can not buy trust with money, by intimidation or through misleading propaganda.  It has to be earned by traveling through painstaking process.  As the saying goes, show clearly that you love the people and the people will in turn love you and/or at least respect you. Clearly, everyone understands that there is no easy way to right all the wrongs committed in the last several years. However, now is the time for the ruling group in Ethiopia to do the right thing and set the country in the right direction. Ethiopia cannot afford to miss yet another opportunity to reclaim its legal and historical rights and assert itself. Action matters.  There is no justification whatsoever to continue on the path that has disadvantaged Ethiopia and relegated her to a dependent country on states like Djibouti.

What needs to be done now?

The government

 • To start with, the ruling party should stop being obsessed about the opposition and holding to power forever. It should stop the desire to accommodate Issayas to cajole him in order to stop supporting the opposition. The government should trust the Ethiopian public not Issayas. Issayas is not trust worthy and there is no way one can satisfy his insatiable appetite for domination.
 • The government should commit itself to find a way to right the wrong of the past 22 years when it comes to Issayas.  Clearly, this should inform all activities of the government moving forward.
 • The right of the Afar, the Erob etc people to remain Ethiopians and Ethiopia’s historical as well as legal right to Assab should be fully asserted.  The government has to be committed to act on the best interests of Ethiopia not the interest of any foreign power.
 • The border issue should be resolved without splitting Ethiopians in Tigray, Saho, the people of Erob and Afar into different countries. The government must protect the right of those who rightly claim their Ethiopianness. Badme belongs to Ethiopia as does Assab.
 • Herman Cohens recommendation that “Ethiopia offer to accept a symbolic initial takeover by Eritrea of territory awarded by the EEBC, followed by the same day opening of dialogue with a totally open agenda”.  Should be fully rejected. Ethiopia cannot be tricked twice.
 • The government should work with the opposition in order to develop a strong “Ethiopian position” for any negotiation or eventuality with Esayiyas Afewerki and his regime.
 • The government should use this opportunity to develop a national dialogue and to build national consensus among all Ethiopian political forces. This opportunity should be used to bring lasting peace through national dialogue and by building national consensus and reconciliation.

The opposition

 • Just like the ruling party, everyone in the Ethiopian opposition should also clarify   its position when it comes to the issue of Eritrea. Saying nothing on such important matter is tantamount to endorsing the statusquo. And the statusquo is not in the best interest of Ethiopia.
 • Engage EPRDF/TPLF in order to develop a strong Ethiopian position vis-à-vis the   Isayas/Shabia position.
 • Use this opportunity to develop trust for national dialogue and to build national consensus and reconciliation among all Ethiopian stakeholders.
 • Discharge its/their responsibility to the public faithfully by providing  timely and accurate information about the status of any “negotiation” or rapprochement  with Isayas and Shabiya

The Ethiopian public

 • Be vigilant and follow diligently any action related to negotiation/ dialogue with Issays / Shabiya.  An informed public is an empowered public.
 • Speak to the politicians both within the government and the opposition to pressure them to stand up for a strong Ethiopian interest and to redress past mistakes. An engaged public is the key to influencing political decisions and the future of our collective destiny.
 • Use this opportunity to pursue a national dialogue and to build national consensus among all Ethiopians. Our future is intertwined and we cannot afford to leave any one behind or exclude any Ethiopian.
 • Members of the Ethiopian media, both diaspora based and locally, should also discharge their professional obligation by reporting without any biases and by holding politicians accountable. Media biases have become the centre of our political life and that has to change.

Ethiopia is bigger than the political ambition of any single politician or political party. The interstate of Ethiopia goes beyond the interest of one party.  Ethiopia has room for all of its citizens. The party that reflects the interest of Ethiopia will always be the winner of the hearts and minds of the Ethiopian people during election times.

Now Ethiopians have an opportunity to reclaim our collective destiny and to jump start our bright future through a national consensus. TPLF/EPRDF too has yet another opportunity to demonstrate that it has learnt from its mistakes. Let us not spoil this opportunity.

Ethiopia does not have to be bound by the defective Algers Agreement and the decisions of the Ethiopia-Eritrea Border Commission (EEBC). The new leadership in Addis should not be bound by the meaningless Algers Agreement and simplistic and outdated ideological gimmick. Just like the treaty of Wuchale that favored Italy’s interest over Ethiopia, we should reject the Algers agreement; because the Algers agreement too is unfair to Ethiopia. Anything less will be unacceptable to Ethiopians everywhere.

It is important to note that foreign governments (weak or strong) have their own interest. And when they recommend solutions, it is first and foremost to protect their own national interests.

Ethiopia has no one but its sons and daughters to protect it. The sons and daughters include the politicians within the ruling party as well as in the opposition. Better late than never, the politicians in the ruling party and its supporters need to stand up for Ethiopians interest now.

I urge the public to engage actively on this issue, make your voices heard by writing, discussing in all pal talk rooms, radio programs etc. Not doing so could have a colossal consequence for our beloved country both today and in the future too.

May God bless Ethiopia

 

posted by Tseday Getachew

የአማራ ዴ/ኃ/ን ለሱዳን ተላልፎ በተሰጠው መሬት ዙሪያ “ዳሩ ካልተጠበቀ መሃሉ ዳር ይሆናል” የሚል መግለጫ አወጣ

ጋዜጣዊ መግለጫ

“ዳሩ ካልተጠበቀ መሃሉ ዳር ይሆናል”!!

ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) የተሰጠ መግለጫ

ታህሣሥ 10 ቀን 2006 ዓ.ም.

በዓለም ላይ እስከአሁን የተከሰቱ መንግሥታት (ቅኝ ገዥዎችን ጨምሮ) ጨቋኝ (አምባገነን)፣ በዝበዥ፣ ዘራፊ (በሙስና የተዘፈቀ) … ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ። አሁን ኢትዮጵያን በመግዛት ላይ እንዳለው የትግሬ ዘረኛ ቡድን የሚገዛትን ሀገርና ሕዝብ የሚጠላና ሀገሩንም ለማጥፋት 24 ሰዓት የሚሠራ መንግሥት ግን እስከ አሁን በታሪክ አልታየም። ወደፊትም ከወያኔ በስተቀር የሚገዛትን ሀገር፣ ታሪኳንና ሕዝቧን የሚጠላና ሆን ብሎ ለማጥፋትም ቀን – ተሌት የሚጥር መንግሥት በምድር ላይ ይከሰታል ብለን አናምንም። ይህ የትግሬ ዘረኛ ቡድን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን መጥላቱን የሚያሳይ የድርጊቱን ሥንክሣር መዘርዘር ቢቻልም፣ በአሁኑ ሰዓት የተከሰቱ ሁለት ታላላቅ ብሔራዊ ጉዳዮችን ብቻ እንኳ ብናይ ዘረኛው ቡድን ምን ያህል የሚገዛትን ሀገርና ሕዝቧን አምርሮ እንደሚጠላ ፍንትው አድርገው ያሳያሉ፦

 1. በሣዑዲ አረቢያ የወገኖቻችን ደም  በግፍ ሲፈስስ፣ እህቶቻችን ያለርህራሄ በቡድን ሲደፈሩ፣ በ21ኛው ክ/ዘመን በሰው ልጅ ላይ የፈፀማል ተብሎ የማይታሰብ ኢሰብአዊ ግፍ ሲፈፀምባቸውና በአጠቃላይ በሀገሪቱ ላይ ብሔራዊ ውርደት ሲደርስ የትግሬው ዘረኛ ቡድን “የሣዑዲ አረቢያ መንግሥት በሀገሩ ላይ ይህንን ማድረግ መብቱ ነው” ነበር ያለው።
 2. በዚህ ሰቅጣጭ ሐዘን ውስጥ ተውጠንና በስቃይ ላይ ያሉ ወገኖቻችንን ለመርዳት ላይ ታች በምንልበት ጊዜ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ታጥቆ የተነሳው የትግሬው ዘረኛ ቡድን አባቶቻችን ደማቸውን በማፍሰስና አጥንታቸውን በመከስከስ ጠብቀው ያቆዩትን 1600 ኪ/ሜ ርዝመትና ከ20-60 ኪ/ሜ ወደ ኢትዮጵያ ጥልቆ የሚገባውን ከሱዳን የሚያዋስነውን ድንበራችንን በሕገወጥነት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ፈርሞ ለሱዳን አስረከበ። ምንም እንኳን በሚስጥር ሊይዘው ቢሞክርም የድንምበር ማካለሉ ከጥር ወር 2006 እስከ መስከረም 2007 ችካል በመቸከል እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) ይህንን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ የሚደረግ ሕገወጥ የድንበር ክለላ አጥብቆ መቃወምና ማውገዝ ብቻ ሳይሆን እንዳባቶቹ ደሙን አፍስሶና አጥንቱን ከስክሶ ታሪካዊ ድንበሩን ለማስከበር ቆርጦ ተነስቷል። ባንዳ የባንዳ ልጆች ከአባቶቻቸው የወረሱትን ሀገር የማጥፋትና የመሸጥ ውርስ ተግባራዊ ሲያደርጉ እኛ የአርበኛ ልጆች ነን የመንል ይህንን ደባ ዝም ብለን ብንመለከት ድንበር ላይ የተከሰከሰው የአባቶቻችን አጥንት እሾህ ሆኖ ይዎጋናል። በመሆኑም በአካባቢው ያላችሁ ታጋይ ኃይሎችና የገፈቱ ቀማሽ የሆንከው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በርስቱና በሚስቱ ያልሞተ ወንድ ልጅ ወንድ አይደለምና ወንድ ልጅ ነኝ ያልክ ሁሉ ተባበረን፣ ከዚህ በላይ የሞት ሞት የለምና።

አዴኃን ይህንን ድርጊት አምርሮ የሚቃወመው እንዲያው በጭፍኑ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ሕጋዊ የሆነ ድንበር አይኑራት ብሎ አይደለም። የድንበር ስምምነቱ ኢትዮጵያን ጎድቶ ሱዳንን የሚጠቅም፣ ከ110 ዓመታት በፊት የፈረሰና ሕጋዊ ያልሆነ ውልን መሠረት ያደረገ፣ በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ጥናት ያደረጉ ኢትዮጵያውያንን ጥናትና ውትወታ ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባና በአጠቃላይ ከኢትዮጵያ  ሕዝብ ጀርባ በደባና በሕገወጥነት የተፈረመ ውል በመሆኑ እንጅ።

በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ጥናት ያደረገው የኢትዮጵያ የድንበር ኮሚቴና ከዚያ በፊትም ጥናት ያደረጉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሑራን እንደሚሉን ከሆነ ይህ ዛሬ የትግሬው ዘረኛ ቡድን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ለተፈራረመው ውል ዋቢ የሚያደርገው ውል በዳግማዊ አፄ ምኒልክና በጊዜው የሱዳን ቅኝ ገዥ በነበረችው እንግሊዝ መካከል የተፈረመው እ.አ.አ 1902 ነበር። አፄ ምኒልክ ይህንን ውል የፈረሙት በኃይል ተገድደውና በይዞታቸው ሥር የነበሩ ብዙ መሬቶችን ለቀው ነበር። በዓመቱ በ1903 የእንግሊዙ የጦር መኮንን ሻለቃ ጉዊን ድንበሩን ከስምምነቱ ውጭ ብቻውን ሄዶ ከመከለሉም በላይ አፄ ምኒልክ ተገድደውም ቢሆን የፈረሙትን ካርታ አዛብቶ ኢትዮጵያን እየጎዳ ችካል ቸከለ። ይህንንም ሻለቃ ጉዊን ከተሰጠው ሥልጣን በላይ ሄዶ መሥመሩን በማዛባት ከኢትዮጵያ መሬት እንደወሰደ በራሱ ሪፖረት ላይ በግልፅ ሳይደብቅ ጽፏል። እንግሊዞችም በ1902 የተፈረመበትን ካርታ ጥለው በችካሉ መሠረት በ1903 አዲስ ካርታ በመሥራት እነርሱ ከፈረሙበት በኋላ አፄ ምኒልክን ለማስፈረም ቢሞክሩም ከስምምነት ውጭ ለተቸከለው የጉዊን ክለላ ዕውቅና በመንፈግ ሳይፈርሙበት ቀርተዋል። የትግሬው ዘረኛ ቡድን አፄ ምኒልክ፣ አፄ ኃይለሥላሴና ደርግ የጉዊንን መሥመር ተቀብለዋል እያለ የሚያላዝነው ይህንን የመሰለውን ሐቅ በመካድ ነው። ይህንንም ዓይን ያወጣ የወያኔን ቅጥፈት አዴኃን ብቻ ሳይሆን ሰኞ 19 ኖቬምበር 2007 (እ.አ.አ.) ሱዳን ትሪቢዩን የተባለ ጋዜጣም “ድንበሩን አስመልክቶ የሱዳን መንግሥት ከቀደምት የኢትዮጵያ መንግሥታት ጋር የነበረው ግንኙነት ቀና አልነበረም። በድንበሩ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር የመጀመሪያው ፈቃደኛ መንግሥት ገዥው የኢሕአዴግ መንግሥት ብቻ ነው”በማለት መሥክሮበታል።

ጥሪ፦     

ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራትም ጭምር፣ ይህ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ በሀገር ከሃዲው የትግሬ ዘረኛ ቡድ ከጎንደር፣ ከጎጃም፣ ከወለጋና ከኢሊባቡር ክፍለ ሀገሮች ተቆርሶ ለሱዳን የሚሰጠው ለም መሬት የክፍለ ሀገራት ተወላጆቹ መሬት ብቻ አይደለም፤ የአንተም የኢትዮጵያዊው መሬት እንጅ። በመሆኑም አዴኃን ይህንን በባንዳ ልጆች የተጋረጥብንን ኢትዮጵያን የማጥፋት ታላቅ አደጋ ለመቀልበስ ስንል ያሉንን ጥቃቅን ልዩነቶች ወደጎን በመተው፣ ከምንጊዜውም በላይ እጅ ለእጅ ተያይዘንና ያለንን አቅም ሁሉ አስተባብረን በመነሳት የዜግነት ግዴታችን እንድንወጣ አስቸኳይ ጥሪውን ያስተላልፋል። “ዳሩ ክልተጠበቀ፣ መሀሉ ዳር ይሆናል” እንደሚባለው የትግሬውን ዘረኛ ቡድን በተባበረ ክንድ ዛሬውኑ ካላስወገድነው በስተቀር እናት ሀገራችን ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዕኩይ ተልዕኮው የድንበር መሬቶችን እየቆረሰ ለጎረቤት ሀገራት በመስጠት ብቻ ያቆማል ብሎ ማሰብ ፍፁም የዋህነት ነው።

ለመከላከያ ሠራዊት፣ የፖሊስ ኃይልና የኢሕአዴግ ደጋፊዎች፣ እናንተ የምትደግፉት ሀገር አጥፊው የትግሬ ዘረኛ ቡድን አባቶቻችን ደረታቸውን ለጦር፣ እግራቸውን ለጠጠር ሰጥተው በደማቸው ያቆዩአትን ይህችን ጥንታዊትና ታሪካዊት ሀገራችንን እያጠፋት እንደሆነ ለእናነተ የተሠወረ አይደለም። ይህንን ሀገር የማጥፋት ወንጀል የሚፈፅመው ደግሞ እናንተን በመሣሪያነት በመጠቀም ስለሆነ ይህንን ተገንዝባችሁ አሁኑኑ ከሕዝባችንና አደጋውን ለመቀልበስ ከሚታገሉ ኃይሎች ጎን በመቆም ሀገራችሁን እንድትታደጉ ስናሳስብ፣ ጥሪያችን ችላ በማለት ለሀገር አጥፊው ቡድን ተባባሪነታችሁን ከቀጠላችሁበት ግን ታሪክና ሕዝብ ይቅር እንደማይላችሁ በጥብቅ ልናስጠነቅቃችሁ እንወዳለን።

ለብአዴን አባላት፦ “እሣት አመድ ይወልዳል” እንደተባለው ካልሆነ በስተቀር፣ አባቶቻችሁ ኢትዮጵያን ከሚያጠፋ ጠላት ጋር ተባብረው እናት ሀገራቸውን አላጠፉም፤ ይልቁንም ደማቸውን አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው የታፈረችና አንድነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለእናንተ አስረከቧችሁ እንጅ። እናንተ ግን የጀግኖች አባቶቻችሁ የባሕሪ ልጆች መሆን አቅቷችሁና አደራቸውን በልታችሁ ኢትዮጵያን ለማፈራረስና አማራን ለማጥፋት ቆርጦ ለተነሳው የትግሬ ዘረኛ ቡድን አሽከር ሆናችሁ እናት ሀገራችሁንና ወገናችሁን እያጠፋችሁ ነው። “ለእንጀራየ፣ ለልጆቼና ለቤተሰቦቼ ስል ወይም ተገድጀ ነው ይህንን የማደርገው” የሚለው ውሃ የማይቋጥር ምክንያት እንደማያዋጣችሁ አውቃችሁ የጋራ ሀገራችንንና ወገናችንን ለመታደግ አብራችሁት እንደትቆሙ አዴኃን ከልብ የመነጨ የሀገር አድን ጥሪ ያቀርብላችኋል።

ወንድም ለሆነው የሱዳን ሕዝብ፦ የኢትዮጵያና የሱዳን ሕዝብ ለብዙ ሺህ ዘመናት ከአንድ ወንዝ ከተቀዳ ውሃ እየጠጣ፣ በመከባበር ላይ በተመሠረተና በመልካም ጉርብትና አንዱ ለሌላው የችግር ጊዜ ደራሽ ሆኖ የኖረ ወንድማማች ሕዝብ ነው። ነገር ግን ዛሬ የትግሬው ዘረኛ ቡድን በሀገር ውስጥ የሚገኙ ነገዶችን እርስ በእርሳቸው ከማናከስ አልፎ የኢትዮጵያን ሕዝብ በተለይም የአማራውን ነገድ ወንድም ከሆነው የሱዳን ሕዝብም ለማናከስ ቆርጦ የተነሳ በመሆኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕውቅና ውጭ የተፈረመን የድንበር ስምምነት እንዳይቀበል በጥብቅ እናሳስባለን።

በመጨረሻም የዓለም ምንግሥታትና ዓለም – አቀፍ ሠላም ወዳድ ሕብረተሰብም የወያኔ ዘረኛ ቡድን ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ፈፅሞ እንደማይወክልና አሁን ከሱዳን መንግሥት ጋር በድብቅ የተፈራረመውንም የድንበር ስምምነት ንቅናቄያችን አዴኃን እና የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደማያውቁት ተገንዝበው ስምምነቱ አሁንም ይሁን ወደፊት በሁለቱ ሀገራት ሕዝብ መካከል የሚፈጠረውን ቀውስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለስምምነቱ ዕውቅና እንዳይሰጡና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን ይህንን ሤራ እንዲቃወሙ አዴኃን ጥሪውን ያስተላልፋል።

በደም የተረከብናትን ሀገር በደም እንጠብቃታለን!!

 

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ

posted by Tseday Getachew

Hiber Radio: በደቡብ ሱዳን የተከሰተው የጎሳ ግጭት በኢትዮጵያ እንዳይከሰት የሚመለከታቸው ሁሉ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ተጠየቀ

Hiber Radio 122213-122913

 

የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 13 ቀን 2006 ፕሮግራም

 

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

<… ሻምበል ፍቅረ ስላሴ ወግደረስ አዳዲስና ከዚህ በፊት የማናውቃቸውን ጉዳዮች በመጽሐፋቸው አንስተዋል …ራሳቸው ሁለት ጊዜ ሕይወታቸው አጣብቂኝ ውስጥ የገባበት ሁኔታን ጨምሮ የተለያዩ ወሳኝ መረጃዎችን አንስተዋል። ይህም መጽሐፍ ለታሪካችን አንድ ማስረጃ ነው…>

 

አቶ ኤልያስ ወንድሙ የጸሐይ አሳታሚ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ከሶስት ቀን በሁዋላ ለገበያ ስለሚቀርበው የሻምበል ፍቅረ ስላሴ <<እኛና አብዮቱ>> መጽሐፍ ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ማብራሪያ የተወሰደ ሙሉውን ያዳምጡት

<<… በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በዘር ላይ የተመሰረተ የአፓርታይድ ስርዓት ነው። …በኢትዮጵያ ያለው የጎሳ ችግር ከደቡብ ሱዳን የበለጠ ነው። ተቃዋሚዎች ብቻ ሳይሆኑ ሚዲያው፣የሐይማኖት አባቶች በአጠቃላይ ሁሉም ዜጋ በሱዳን የተከሰተው የዘር ግጭት እንደ ትልቅ ማስተማሪአ ወስደን በኢትዮጵያ እንዳይከሰት መስራት አለብን…>> አቶ ኦባንግ ሜቶ ስለ ደቡብ ሱዳን የሰሞኑ ግጭት ለህብር ከሰጡት የተወሰደ

የሱዳኑ አልበሽር ኢትዮጵያና ኤርትራን በእርግጥ ለማስማማት ወይስ ሁለቱ መንግስታት በተቃዋሚዎቻቸው የሚደርስባቸውን ለመከላከል? እውነት ይስማማሉ? አቶ መለስ የሰጉበትን የጓዶአኤርትራን ፍላጎት ዕውን ሕወሃት ማሟላት ይችላል ? የተቃዋሚዎቹስ ሚና(ትንታኔ)

የኦባማ ኬር የመጀመሮያ ዙር ምዝገባ ሰኞ(ከአቶ ተካ ከለለ ጋር ከአትላኢታ ቲኪ ዲሴምበር 23 ይጠናቀቃል።…ኢንሹራንስ ያለውም ተመዝግቦ የገበያ አማራጩን ማየት አለበት? (ስለ ኦባማ ኬር ከአቶ ተካ ከለለ ጋር )

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

– በደቡብ ሱዳን የተከሰተው የጎሳ ግጭት በኢትዮጵያ እንዳይከሰት የሚመለከታቸው ሁሉ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ተጠየቀ

– ማንዴላን ያሰለጠኑት ኢትዮጵያዊ መኮንን ለቀብሩ ለመሔድ ቪዛ መከልከላቸውን በምሬት ገለጹ

– ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን ጉዳይ እጇን እንዳታስገባ ተጠየቀ

– በጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ ላይ የተሰጠው የፍርድ ውሳኔ የዳኛው የእጅ ጽሑፍ ሳይሆን የሌላ ሰው መሆኑ ተገለጸ

– ምስጢሩ ሰኞ በርዮት የ30ኛ ወራት እስራት ይፋ ይሆናል

– በሳውዲ በሸሚሴ መጠለያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አቀረቡ

– ከሳውዲ የመጡ እና በአገር ቤት ያሉ ወጣቶች ተፋጠዋል

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Audio https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-122213-122913

posted by Tseday Getachew

የኢህአዴግ አዲሱ አሰላለፍ ፪ – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

 

በድህረ-መለስ ኢትዮጵያ የፖለቲካው ሥልጣን በስርዓቱ ልሂቃን መካከል ከሚደረገው የኃይል መተናነቅ አንጻር፣ ዛሬም ከመፈራረቅ ጣጣው የተላቀቀ የማይመስልባቸው ምልክቶች መታየታቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ ከአራት ወር በፊት በዚህ መፅሄት ላይ ‹‹አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ›› በሚል ባቀረብኩት ፅሁፍ በገዥው ፓርቲ ውስጥ ተፈጥሮ ከነበረው ክፍፍል የትኛው ቡድን የበለጠ ጉልበት አግኝቶ በአሸናፊነት መውጣት እንደቻለ ከገለፅኩ በኋላ ፅሁፉን የቋጨሁት እንዲህ በማለት ነበር፡- ‹‹የፓርቲው የታሪክ ድርሳን እንደሚነግረን ‹ይሆናሉ› የተባሉት ተቀልብሰው፣ ባልተጠበቁ ሁነቶች (የኃይል መገለባበጥ ተከስቶ) ፖለቲካው የሚመራበት አጋጣሚ ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል ሊኖር እንደሚችልም መዘንጋት አያስፈልግም፡፡››

እነሆ በዚህ ፅሁፍ ደግሞ በቅርቡ በተጨባጭ የታዩትን አዳዲስ ኩነቶች እና ይህንኑ ተከትለው ሊመጡ ይችላሉ ብዬ የምገምታቸውን ‹የቢሆን ዕድሎች› (Scenarios) ለማየት እሞክራለሁ፡፡  ሰላም የራቀው-ኢህአዴግ  በግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል ዛሬም ድረስ ሙሉ በሙሉ የተረጋጋ ፖለቲካ አልሰፈነም፤ የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ፣ ቁልፍ የሥልጣን ቦታዎችን ጠቅልሎ ይዞ በነበረው በቀድሞ ሊቀ-መንበሩ ህልፈት ሳቢያ የተፈጠረው የአመራር ክፍተት እና እርሱን ሊተካ የሚችል መሪ ማግኘት ባለመቻሉ ይመስለኛል፡፡ እንዲህ አይነት አጋጣሚዎችም በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ከሕግ ይልቅ የጠመንጃ ኃይልና የግለሰብ አምባገነናዊነት በገነነበት ሀገር ‹የማይገመቱ ክስተቶች› (Unpredictable Event) ማምጣታቸው የሚጠበቅ ነው፡፡

የሆነው ሆኖ በዚህ አጀንዳ ለመመልከት የምሞክረው ጉዳይ፣ በአሁኑ ጊዜ ሀገር እየመራ ያለው ኃይል ለሁለት የተከፈለ ቢሆንም፣ በአንፃራዊነት በጥምር የሚሰራ መሆኑን በማስረገጥ ነው፡፡ የእነዚህ ሁለት ቡድኖች የጉልበት ምንጭም የታጠቀውን ኃይል በመቆጣጠር እና የፖለቲካውን ሥልጣን በመያዝ ላይ የተመሰረተ ነው፤ ይኸውም ሠራዊቱ እና የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሙሉ በሙሉ በህወሓት ሰዎች ሲንቀሳቀሱ፣ ፖለቲካውን ደግሞ የብአዴን መሪዎች፣ ከተወሰኑ የኦህዴድና ደህአዴን የአመራር አባላት ጋር ተባብረው መያዛቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች መኖራቸው ነው፡፡

የህወሓት ኃይል

ህወሓት የቀድሞው ፍፁማዊ የበላይነቱን ለመመለስ ዋና ችግር የሆነበት በውስጡ ለተፈጠረው መከፋፈል እስካሁን መፍትሄው ተለይቶ አለመታወቁ ነው፤ ከዚህ ቀደም በዚሁ መፅሄት፣ አንዱ ኃይል የተሻለ ጉልበት በማግኘቱ ሌላኛውን (እነአዜብ መስፍንን ጨምሮ አባይ ወልዱና ቴዎድሮስ ሀጎስን የመሳሰሉ ከፍተኛ ካድሬዎች የተሰባሰቡበትን) በመብለጥ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን እንቅስቃሴያቸውን መገደቡ ተሳክቶለት እንደነበረ ማስነበቤ ይታወሳል፡፡ ይህ ክፍፍል ምንም እንኳ እንደ 1993ቱ ከፓርቲ እስከ ማስወጣት የሚደርስ አለመሆኑ ቢታወቅም፣ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና ጌታቸው አሰፋ የተሰለፉበት ቡድን ተፅእኖ ፈጣሪ ሆኖ መውጣት ችሏል፤ ይህም ሆኖ ውስጥ ውስጡን የሚገመደው ተንኮልም ሆነ ሽኩቻ ገና መቋጫ አለማግኘቱ ግልፅ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍ ጠመንጃ የታጠቀውን ክፍል ‹የህወሓት ኃይል› እያልኩ የምገልፀበት ዓብይ ምክንያት፣ በጄነራል ሳሞራ የኑስ ኤታ ማዦር ሹምነት የሚመራው የመከላከያ ሠራዊት እና በማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጌታቸው አሰፋ ስር ያለው የደህንነት ኃይል ለሚደግፉት ቡድን መጠናከር እያበረከቱት ያለውን አስተዋፅኦ ከግምት በመክተት ነው፡፡ ሁለቱም ሰዎች ለመለስ ፍፁም ታማኝ የነበሩ ቢሆንም፣ ከህልፈቱ በኋላ እንደእርሱ ተጭኖ ሊቆጣጠራቸው የሚችል ጉልበታም ህወሓትን ጨምሮ በሁሉም የግንባሩ አባል ፓርቲ ውስጥ አለመኖሩ፣ በፖለቲካው ‹ቼዝ› የ‹ዘመነ መሳፍንቱ›ን ሚካኤል ስሁል አይነት ሚና እንዲጫወቱ አስችሏቸዋል፤ ሁለቱም ከስራቸው የነበሩትንና ‹ስልጣን ሊጋፉ ይችላሉ› ብለው የጠረጠሯቸውን ባልደረቦቻቸውን አስቀድሞ ገለል ማድረጉ ከሞላ ጎደል የተሳካላቸው ይመስለኛል፡፡ በተለይም ጌታቸው አሰፋ ከራሱ ወንበር አልፎ ከእነአዜብ መስፍንና አባይ ወልዱ ጋር በመተባበር አንድ ቀን በጠቅላላው የመንግስት የሥልጣን እርከን ላይ ‹ናቡቴ ሊሆን ይችላል› የሚል ስጋት ያሳደረበትን እና ‹መለስ ዜናዊ ሞት ባይቀድመው በእርሱ ቦታ ሊተካው ነበር› እየተባለ የሚነገርለትን የመረጃ ኃላፊ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና የሚወነጀልበትን መንገድ አመቻችቶ ለእስር ባይዳርገው ኖሮ ‹‹ለቁርስ ያሰቡንን…›› አይነት ታሪክ ራሱን መድገሙ አይቀሬ ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡ ጄነራል ሳሞራ የኑስ በበኩሉ ተቀናቃኙ አድርጎ ይመለከታቸው የነበረው ሶስቱ ከፍተኛ መኮንኖች እንደ ወልደስላሴ ‹ፍንቀላ መሳይ ነገር ሊሞክሩ ይችላሉ› ተብለው አይደለም፡፡ የእነርሱ የመጀመሪያው ችግር ከወታደራዊ ዲሲፕሊን በማፈንገጥ አለቃቸውን አለማክበራቸው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሳሞራ ‹በየትኛውም ምክንያት ከኃላፊነቴ ብነሳ የቆየ ፋይል አገላብጠው አደጋ ላይ ሊጥሉኝ ይችላሉ› በሚል ስለሚጠረጥራቸው ነው፡፡ እነዚህ መኮንኖች የሰሜን ዕዝ አዛዥ ሌፍተናንት ጄነራል ሰዓረ መኮንን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ መልካም ግንኙነታቸው እንደቀድሞው እንዳልሆነ የሚነገረው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌፍተናንት ጄነራል አበባው ታደሰ እና የአየር ኃይሉ አዛዥ ሜጀር ጄነራል ሞላ ኃይለማርያም ናቸው፡፡ እናም ሰዓረ እና አበባው በቀጥታ ሠራዊት ከሚያዙበት ቦታ ተነስተው በመከላከያ ሚኒስትር ውስጥ በቢሮ ስራ ላይ ሲመደቡ፣ ሞላም ከነበረበት ኃላፊነት አኳያ ብዙም ይመጥነዋል የማይባል የቢሮ ስራ ተሰጥቶታል፤ በእርሱም ቦታ ሜጀር ጄነራል አደም መሀመድ ተተክቷል፡፡ የሳሞራ እና የሞላ ልዩነት በመለስ ዘመንም በአደባባይ የሚታወቅ እንደነበረ ሰምቻለሁ፡፡ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆነ የመረጃ ምንጬ እንዳረጋገጥኩት የአስተዳደር ዘይቤውን በማኪያቬሊያዊ አስተሳሰብ (ከፋፍለህ ግዛ) የሚያሳልጠው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ ለሞላ ትዕዛዝ የሚሰጠውም ሆነ ማንኛውንም ጉዳይ በተመለከተ የሚያነጋግረው የዕዝ ተዋረዱን ጠብቆ በኤታ ማዦሩ በኩል ሳይሆን፣ በቀጥታ በመገናኘት መሆኑ፣ አየር ኃይሉን ከመከላከያ ሚኒስቴር የተገነጠለ አስመስሎት ነበር፤ ይህ ሁኔታም በሁለቱ መኮንኖች መካከል ያለው ግንኙነት የሥልጣን ተዋረድን የጠበቀ እንዳይሆን በማሰናከሉ በጄነራሉ ላይ ደፍሮ የማይናገረው ቅሬታ ሊያሳድርበት ችሏል፤ ከመለስ ህልፈት በኋላም ሳሞራ ሂደቱን ለማስተካከል መሞከሩ፣ በየግምገማው ላይ እስከ መዘላለፍ አድርሷቸው ነበር (በነገራችን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ እንደ ጦር ኃይሎች አዛዥነቱ፣ ከጄነራሎቹ ጋር መደበኛ /Official/ በሆነ መንገድ ትውውቅ አላደረገም፤ እነዚህ ሶስት ጄነራሎችም ለዚህ አይነቱ የአሰራር መፋለስ ጥፋተኛ የሚያደርጉት አለቃቸውን ሳሞራ የኑስን ነው፤ ከምንጮቼ እንደሰማሁት ከሆነም ከወራት በፊት ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኘበት ‹ጎልፍ ክለብ› በሚባለው የጄነራሎቹ መዝናኛ በተዘጋጀ ፕሮግራም ማጠናቀቂያ ላይ ሳሞራ አንድ ጠረጴዛ ከበው ወደ ተቀመጡት እነዚህ ጄነራሎች ጋ ሄዶ ‹ኑ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ላስተዋውቃችሁ› ማለቱን እና እነርሱም በጥያቄው ተበሳጭተው ቢሮ ያላቸው መሆኑን እና ክብራቸውን በሚመጥን መልኩ መተዋወቅ እንደነበረባቸው በኃይለ ቃል መመለሳቸውን ነው)

የሳሞራ የኑስ እና ሰዓረ መኮንን መነቋቆር ከትግሉ ዘመን ጀምሮ የመጣ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ሳሞራ ከማንም በላይ የሚፎካከረውም ሆነ መበለጥ የማይፈልገው በሟቹ ጄነራል ኃየሎም አርአያ እንደ ነበር የቀድሞ ጓዶቻቸው ያስታውሳሉ፤ ይህ ሁኔታ ዛሬም ድረስ በስራ ላይ ያሉ መኮንኖችን ‹የሳሞራ› ወይም ‹የኃየሎም ተከታይ› በማለት መከፋፈሉ በጓዶቻቸው እና በፓርቲው መሪዎች አካባቢ የሚታወቅ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለማዕረግ እድገት የተለየ የድጋፍ አስተያየት የሚያገኙት በዛን ዘመን ‹የሳሞራ ተከታይ› የሚባሉት እየተመረጡ እንደነበረ በወሬ ደረጃ ይናፈሳል (በነገራችን ላይ ጄነራል ሳሞራ ከጤንነት ጋር በተያያዘ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጡረታ ይሰናበታል በተባለበት ጉዳይ ላይ እያንገራገረ እንደሆነ ከመከላከያ አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ፤ እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ ‹ለእኔ በጎ አመለካከት የላቸውም› በሚል የሚጠራጠራቸው ጄነራሎች በሥራ ላይ እያሉ የእሱ ጡረታ መውጣት ከመስሪያ ቤቱ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ያደሩ የሙስና ካርዶች የሚመዘዙበትን ዕድል ያሰፋዋል የሚል ነው፤ በተለይም በግዙፍ የቢዝነስ ሥራዎች ላይ በታላቅ ተፎካካሪነት እየተሳተፈ የሚገኘው ‹መቴክ› ምንም እንኳ ማረጋገጫዎች ባይቀርቡበትም በመከላከያ ሥር ከነበረበት ዘመን እስከ 2002 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ከግዥዎች ጋር ተያይዘው የሚነሱ በርካታ የሙስና ሁኔታዎች በመኖራቸው ነው፡፡ መቴክ ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ በአዋጅ የልማት ድርጅት እንዲሆን ቢደረግም፣ ዛሬም ዳይሬክተሩ የሠራዊቱ አባል ብርጋዴር ጄነራል ክንፈ ሲሆን፣ መከላከያ ደሞዝ የሚከፍላቸው ጥቂት የማይባሉ ሠራተኞችንም እንዳቀፈ ይታወቃል፡፡ እናም ሳሞራ ሃሳቡ ከተሳካለት ለጥቂት ተጨማሪ ዓመታት በሥልጣኑ ላይ ሲቀጥል፣ አሊያም ‹የወንድ በር› ለማግኘት በትግሉ ዘመን የእርሱ ሰልጣኝ እንደነበረ የሚነገርለትን እና በቅርቡ ብቸኛው ከሜጀር ወደ ሌፍተናት ጄነራል ማዕረግ ያደገው ዮሀንስ ገ/መስቀል እንዲተካው መንገድ ጠረጋውን ማመቻቸቱ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት ጉዳይ ይመስለኛል) ይህም ሆኖ የተኮረኮርን ያህል የምንስቀው ጄነራል ሳሞራ የኑስ በቅርቡ ለታተመው ‹‹ህብረ ብሔር›› መፅሄት ሙስና ለሠራዊቱ አደገኛ መሆኑን እንዲህ በማለት መግለፁን ስናነብ ነው፡- ‹‹ሙስና ሠራዊቱን ሊያበላሸው ይችላል፡፡ ሙስና ፀረ-ልማት ነው፤ ሠራዊቱን ሊበትነው እና ሕዝባዊ ባህሪውን እንዲያጠፋ ሊያደርገው ይችላል፤ አንድ ሠራዊት ሠራዊት ነው የሚባለው እንደ ወታደር እንደ አንድ አካል ሲያስብ እንጂ ለግሉ ሲያስብ አይደለም፡፡ …በአጠቃላይ (ሠራዊቱ) በዚህ ነው የሚፈርሰው፡፡››  መቼም ጄነራሉ ይህንን የተናገረው እራሱን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ መኮንኖች እንደ እንግሊዝ ንጉሳውያን ቤተሰቦች በተንጣለለ ቪላ ቤት ውስጥ፣ የተቀማጠለ ኑሮ መኖራቸውን ረስቶት አይመስለኝም፤ ‹ይህ የተንዛዛ ወጪያቸውም የሚሸፈነው ከደሞዛቸው በሚያገኙት ገቢ ነው› ብሎ ቧልት መሳይ ክርክር ሊያመጣ አይችልም፡፡ ይሁንና እታች ያለው ጭቁን የኢትዮጵያ ሠራዊት ምንም እንኳ በአለቆቹ ‹ቴክሳስ›ነት ላይ ለመቆጣት ባይደፍርም፣ እንደማንኛውም ዜጋ ለኑሮ ውድነትና አስከፊ ድህነት የተጋለጠ መሆኑን መካድ አይቻልም፡፡ የሆነው ሆኖ ተሰሚነታቸው እየተቀዛቀዘ የመጣው አቦይ ስብሃት ነጋ ከወራት በፊት ለ‹‹ውራይና›› መፅሔት ‹‹ህወሓት ትንሳኤ ያስፈልገዋል›› በማለት የሰጡትን ምክር ተከትሎ፣ ጄነራል ሳሞራ እና አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ከድርጅቱ ምክትል ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ጋር በመተባበር ህወሓትን ለማጠናከር እና በፖለቲካ ውስጥ የነበረውን የአንበሳውን ድርሻ ለማስከበር (ጉዳዩን ከለጠጥነው ደግሞ ‹ለማስመለስ›) እየሰሩ እንደሆነ ይነገራል (በነገራችን ላይ የሳሞራና ጌታቸው ተፅእኖ መጨመሩን ለመረዳት፣ መከላከያ ‹አገራዊ ጥቅምንና ደህንነትን ለመከላከል› በሚል ‹እጅግ ጥብቅ ሚስጢር ብሎ የሰየማቸውን የሰው ኃይል ፕሮፋይል፣ የሒሳብ መዝገቦችና ሰነዶች እና የክፍያ ማስረጃዎች ለማንም አካል እንዳይገለፅ› የሚያስችለውን ስልጣን፣ ደህንነቱ ደግሞ በስራ ላይ የሚፈፅማቸው ማንኛውም ጉዳዮች ወደፊት በህግ እንዳይጠይቅ እስከ መከላከል የሚደርሰውን አዲስ የተዘጋጁትን አዋጆች ማንበቡ በቂ ነው፡፡ በርግጥ እነዚህ ባለሥልጣናት እንዲህ ባለ ተመሳሳይ መንገድ እንዲጓዙ ያስተሳሰራቸው አንዱ ጉዳይ ‹ህወሓት ተዳከመ፣ ተሸነፈ፣ አበቃለት…› የሚለው የካድሬውና ደጋፊው ቁጭት እንጂ ወትሮም መልካም ግንኙነት ኖሯቸው አይመስለኝም)

ለማንኛውም በጥቅሉ ሲታይ የህወሓት ትልቁ ችግር ተብሎ በአመራር አባላቱ የሚጠቀሰው ‹በዚህ ወቅት ወደፊት መምጣት የሚችሉ ጠንካራ ቴክኖክራቶችን አለማፍራቱ፣ ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርግለትን የታጠቀውን ኃይል ተጠቅሞ የፖለቲካ ልዩነቱን ጨፍልቆ በአሸናፊነት ይዞት መውጣት የሚችል መሪ እንዳይኖረው አደረገ› የሚል ነው፡፡ በርካታ የላይኛ እና የታችኛው ካድሬዎችም ‹ለእንዲህ አይነቱ ክፉ ጊዜ ድርጅቱ የሚያስፈልገው፣ በትግሉ ዘመን ልምድ ያካበተ ታጋይ ብቻ ነው› የሚል አቋም እንዳላቸው ይነገራል፡፡ ስርዓቱ ከሚያራምደው ርዕዮተ-ዓለም ጋር ጠንካራ ትውውቅ ያሌለውን እና የትግሉን ዘመን በአሜሪካን ሀገር በማሳለፉ ‹የምዕራባውያን ድጋፍ አለው› ለሚባለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የሚሰጡት ዝቅተኛ አመለካከት መግፍኤም ይኸው ይመስለኛል፡፡ ለነገሩ እርሱም ቢሆን በጠንካራ ድርጅታዊ ዲሲፕሊን ካለመታነፁ እና መሰል ጉዳዮች ጋር በሚያያዙ ምክንያቶች ለትንፋሽ ጊዜ የማይሰጠውን የድርጅት ሊቀ-መንበርነትንም ሆነ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ የሚወራውን ያህል ይፈልገዋል ብሎ መደምደሙ አስቸጋሪ ነው ብዬ አስባለሁ፤ ከዚህ ይልቅ በተፈጥሮ ከታደለው የተግባቢነት ባህሪው አኳያ እንደ ሕዝብ ግንኙነት የመሳሰለ ብዙም የማያጨናንቅ ሥራን ይመርጣል፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ከሰለጠነበት ሙያ ጋር የቀጥታ ተያያዥነት ያለውን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በሚመራበት ዘመን፣ ከውጭ ሀገር በርካታ የተቋረጡ ፈንዶችን እንደገና ለማስለቀቅ መቻሉ እንደ ታላቅ ስኬት የሚወራለት፤ አልፎ ተርፎም ‹ወባን ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋት ብርቱ ትግል አደረገ› ተብሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሳይቀር እስከ መሸለም የደረሰው እዚህ መስሪያ ቤት እያለ እንደሆነም ይታወቃል፡፡

ትንቅንቅ
በሌላ በኩል ደግሞ በፓርቲውም ሆነ በመንግስት አስተዳደር ከህወሓት ሰዎች ትልቁን ስልጣን የያዘው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከምዕራባውያን ጋር የቆየ ቀረቤታ እንዳለው ሰምቻለሁ፤ እንደሚታወሰው ደብረፅዮን ከክፍፍሉ በፊት (የደህንነት መስሪያ ቤቱ እንዲህ እንደ ዛሬው እጅግ ዘመናዊ በሆነው የቻይና ቴክኖሎጂ ሳይጥለቀለቅ) ከነበረው ከፍተኛ የሥልጣን ቦታ ላይ ተነስቶ፣ ቁልቁል ወርዶ በሁመራ በአንድ ዞን እንዲሰራ የተመደበው (ሁላችንም ስንገምት እንደነበረው) የአንጃው አባል ወይም ደጋፊ ሆኖ አይደለም፤ ይልቁንም የእነስዬ-ተወልደ ቡድን በመባል የሚታወቀው (‹አፈንጋጩ› ኃይል) ደብረፅዮንን በሲ.አይ.ኤ እና ሞሳድ ወኪልነት የመክሰሱ ጉዳይ የድርጅቱን በርካታ አባላት ቀልብ በመሳቡ፣ መለስ ይህንን ተከትሎ ከሚመጣበት አደጋ ራሱን ለመከላከል የወሰደው እርምጃ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት እስከ 1998 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በሁመራና ራያ አካባቢዎች በዞን ደረጃ ለማገልገል ተገዷል፡፡ እናም እርሱን የምዕራቡ ዓለም ፊት-አውራሪ አሜሪካና ሸሪኮቿ ወዳጅ ነው የሚያስብለው በቀድሞ መስሪያ ቤቱ በኩል በነበረው ግንኙነት ይመስለኛል። 

የፖለቲካውን መዘውር የጨበጠው ኃይል

የዚህ ቡድን አምበል እንደ ድርጅት ብአዴን ቢሆንም፣ በቋሚ ተሰላፊነት ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ አባዱላ ገመዳ፣ ሙክታር ከድር እና ሬድዋን ሁሴን እንደሚገኙበት ይነገራል፤ ለብአዴን ‹በተሻለ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ ለመገኘቱ መደላድል ፈጥሮለታል› የሚለውን ሙግት ምክንያታዊ የሚያደርገው ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ጥናት ምርምር አማካሪ በረከት ስምዖን፣ የኢህአዴግን የካድሬ ማሰልጠኛ ማዕከል በዳይሬክተርነት የሚመራው አዲሱ ለገሰ፣ ደርቦ ይዞት የነበረውን የትምህርት ሚኒስትርነት ለሽፈራው ደሳለኝ በመልቀቅ፣ በአሁኑ ወቅት ሙሉ የስራ ጊዜውን በግንባሩ ፅ/ቤት የሚያውለው ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤው ካሳ ተክለብርሃን የያዙት ሥልጣን ያለውን የፖለቲካ አቅም መመዘኑ ይመስለኛል፡፡ በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥም ከሳሞራ አንድ እርከን ዝቅ ባለ ሥልጣን ከሌሎች ሁለት ጄነራሎች ጋር የሚገኘው አበባው ታደሰ እንደ ቀድሞው በዕዝ አዛዥነቱ (በቀጥታ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወታደሮችን ማንቀሳቀስ የሚችልበት) ላይ ቢሆን ኖሮ ጥንካሬውን የተሟላ ማድረጉ አይቀሬ እንደነበረ መገመት ይቻላል፡፡

ከዚህ ሌላ ለእነበረከት ቡድን ተጨማሪ የፖለቲካ ጉልበት እየሆናቸው ያለው የኃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ እና በአባዱላ ገመዳ አፈ-ጉባኤነት የሚመራው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ነው፡፡ አባዱላ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ለማቅረብም ሆነ ለመታዘዝ ፍቃደኛ ያልሆኑ አንዳንድ ባለስልጣናት፣ በውስጥ መስመር በሚተላለፍለት ‹ጥቅሻ› በምክር ቤቱ በኩል የሚመለከተው የቋሚ ኮሚቴ አባላት አስጠርቶ የተሰጠውን ኃላፊነት የሚገመግምበት ስልት እየተገበረ ነው፡፡ በአናቱም ምን ጊዜም የሳምንቱን የሥራ መጨረሻ ቀን አርብን ጠብቆ የሚሰበሰበው የሚኒስትሮች ም/ቤትን ከሞላ ጎደል ይህ ቡድን እየጠቀመበት ይመስለኛል፡፡ በርግጥ ሚኒስትሮቹ በሚገናኙበት አብዛኛውን ሰዓት ሳይግባቡ (በጭቅጭቅ) ማሳለፋቸው ይነገራል፤ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በአቶ መለስ ዘመን ም/ቤቱ የሚሰበሰበው የተለያዩ አጀንዳዎችን ለማቅረብ እና በቀረበው አጀንዳ ላይ ለመከራከር (ለመመካከር) ሳይሆን፣ መለስ ወስኖ የመጣበትን የሥራ ድርሻ ተቀብሎ ለመበተንና ሪፖርት ለመስማት የነበረው አሰራር፣ ዛሬ ተቀይሮ በርካታ የተነቃቁ ሚኒስትሮች የየራሳቸው ሃሳብ ተቀባይነት እንዲያገኝ (ለማንፀባረቅ) የሚታገሉበት መድረክ ወደ መሆን በመሸጋገሩ ነው፡፡ ይህም ሁናቴ ዋናውን የመንግስት ሥራ የመገምገም እና የማስፈፀም አቅምን ሳይቀር ከሚኒስትሮች ም/ቤት ወደ ኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ አሻግሮታል የሚያስብሉ ማሳያዎች አሉ፡፡ ይሁንና በዚህስብሰባ ላይም ቢሆን ደፈር ብሎ ከበረከት ስምዖን እና አባይ ፀሀዬ የተሻለ አዳዲስ ሃሳብ የሚያቀርብ ባለሥልጣን እንደሌለ ሰምቻለሁ (በነገራችን ላይ ምክንያቱን ባላውቅም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር አማካሪ› ተደርገው የተሾሙት በረከት ስምዖን፣ አባይ ፀሀዬ፣ ኩማ ደመቅሳ እና ዶ/ር ካሱ ኢላላ የሥራ ቦታቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ሳይሆን መገናኛ አካባቢ በሚገኝ አንድ ህንፃ ላይ ነው፡፡ የተሰጣቸው ኃላፊነት ኃይለማርያምን በቅርብ እንዲያገኙ ከማስገደዱ እና በግልፅ ከሚታወቀው የአማካሪ አስፈላጊነት አኳያ ካየነው ግን ግራ የሚያጋባ ይመስለኛል)

አቶ አባይ ጸሐዬ

 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ…

ኃይለማርያም ደሳለኝ ይህንን ቦታ ከያዘ በኋላ፣ ብዙዎች በስልጣኑ የማዘዝ አቅሙ ላይ አመኔታ እንደሌላቸው (አንጋፋ ታጋዮች እንደ ‹አሻንጉሊት› ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ) ደጋግመው መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ በግልባጩ ‹አፈንግጦ ለመውጣት መሞከሩ አይቀሬ ነው› የሚሉ ግምቶች ነበሩ፡፡ በርግጥ እነዚህ መላ-ምቶች ዛሬም ድረስ እልባት ባያገኙም፣ እዚህ ጋ ያልጠቀስኳቸው አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ያሳያቸው ወጣ ያሉ አቋሞቹን ሳስተውል ግን፣ አሁን ያለው አሰላለፍ (የአነበረከት እና አባዱላ ፖለቲካዊ መጠናከር) ለእርሱም የተረፈው ይመስለኛል፡፡ እንዲሁም ከቤንች ማጂ የተባረሩ አማርኛ ተናጋሪዎችን አስመልክቶ በድርጅቱ ውስጥ ባልተለመደ መልኩ ‹አጥፊዎቹ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ› ከማለት አንስቶ (በነገራችን ላይ በአማካሪ ብዛት እንዲከበብ ካደረገው ምክንያት አንዱ ጓዶቹ በዚህ ንግግሩ መበሳጨታቸው ነው) በቅርቡ ህወሓትን ለመሸምገል በተዘጋጀ መድረክ ላይ ‹ሁኔታዎች እንዲህ እየተካረሩ ከሄዱ ወደ ማሰሩ መግባታችን አይቀርም› በማለት ማስፈራራቱ እና በቴዎድሮስ አድህኖም የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ላይ የመቆጣቱ ጉዳይ ድረስ የሚካተቱ እውነታዎች ሰውየው የራሱን መንገድ ለመከተል እየሞከረ መሆኑን ያሳያሉ ብዬ አስባለሁ፡፡

የሆነው ሆኖ እነዚህ ሁናቴዎች የፖለቲካውን ጉልበት ሙሉ በሙሉ በብአዴንና በተባባሪነት በጠቀስኳቸው የኦህዴድና ደህአዴን የአመራር አባላት አካባቢ ቢያከማቻቸውም፣ በማንኛውም ሰዓት ያሻውን ማድረግ የሚችለው የታጠቀው ኃይል ደግሞ ከህወሓት ጎን እንደተሰለፈ ይገኛል፡፡ መጪውን ጊዜም አዲስ ክስተት እንድንጠብቅ ገፊ ምክንያት ይህ አይነቱ የኃይል አሰላለፍ ይመስለኛል፡፡

ምን እንጠብቅ?

ከረጅሙ የፓርቲ ፖለቲካና መንግስታዊ መንገራገጮች በኋላ፣ የሁለቱንም የኃይል መሰረቶች ጠቅልሎ በመዳፉ ሥር የከተተው መለስ ዜናዊ በሞተ ማግስት ‹የኃይል መገዳደሮች ሊከሰቱ ይችላሉ› የሚለው የብዙዎቹ ግምት ነበር፤ ከወራት በፊት አስነብቤ በነበረው ከላይ በተጠቀሰው ፅሁፍም ግምቶቹ እውን መሆን እንደ ጀመሩ ማሳያዎች ማቅረቤ ይታወሳል፡፡ ኢህአዴግ ውስጥ ራሳቸውን ያቧደኑት ኃይሎች ዋነኛ ግብ ከሥልጣን የሚነሱ ጥቅሞችና አነስተኛ የየራሳቸው ፓርቲ ፍላጎቶች የፈጠሩት በመሆኑ፣ እንደ ሟቹ ደመ-ቀዝቃዛ አምባገነን አይነት በጠንካራ መዳፍ ሥር የሚያሰባስባቸው ባለመገኘቱ በየጊዜው የኃይል መሸጋሸጎች ሊከሰቱ እንዲችሉ አድርጓቸዋል፤ አሁንም እየተስተዋለ ያለው ይኸው እውነታ ነው፡፡ በዚህ አውድ ላይ ቆመን ሊፈጠሩ የሚችሉ የቢሆን ሃሳቦችን ስናስቀምጥም በጠረጴዛው ላይ የምናገኘው ሁለት ዕድሎችን ይመስለኛል፡፡

የመጀመሪያ ሲናሪዮ የሚሆነው ከላይ የጠቀስኩት ቡድንተኝነት እንዳለ ሊቀጥል ይችላል የሚል ነው፤ ይህም የሚሆንበት ምክንያት ባለኝ መረጃዎች መሰረት የፖለቲካውን መስመር የያዘው ቡድን መሪ አባላት፣ አሁን ያላቸውን መንግስታዊ ሥልጣን ጠብቀው መቆየትን መሰረታዊ መሰባሰቢያ አጀንዳ ማድረጋቸው ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሳሞራና ጌታቸው ጥምረት ህወሓትን ወደ ቀደመው ዘመኑ ለመመለስ ቢሻም፣ ሊሄድበት የሚችልበት መንገድ አደገኛ መሆኑ (ወታደራዊ ላዕላይ መዋቅሩንና የደህንነት ኃይሉን ከመያዙ አኳያ) ሁኔታዎችን ባሉበት ይዞ መቀጠልን በትርፍ-ኪሳራ ስሌት የተሻለ አማራጭ አድርጎ ይወስደዋል ብዬ አስባለሁ፡፡ ሁለተኛው የቢሆን ዕድል፣ ዳግመኛ የኃይል መሸጋሸግ ሊፈጠር መቻሉ ነው፤ ሰዎቹ ጥቅመኛ በመሆናቸው የቋንቋ ተናጋሪነት ልዩነቶቻቸውንና የኋላ የመቆራቆስ ታሪኮቻቸውን ተሻግረው፣ አንዳቸው ከአንዳቸው ጋር ሌላ መልክ ያለው ስብስብ ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆናል፤ ይህ አይነቱ አዲስ የኃይል አሰላለፍም፣ ከቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ በፊት በማይታወቀው ተሰዊና ሰዊ ሊጠናቀቅም ይችላል፡፡ በመጨረሻም ምንም ይፈጠር ምን፤ እኛን ሊያግባባን የሚገባው ጭብጥ፣ የትኛውም ቡድን በግንባሩ ውስጥ ቢነሳ፣ የማዕከላዊ መንግስቱን ህልውና ወደሚበታትን ሂደት መግባቱ ሊሰካለት አለመቻሉ ነው፤ ምክንያቱም በዚህ መልኩ ሄዶ የሚጣሉበትን ጠረጴዛ መስበሩ ምን እንደሚያስከትል ያውቁታልና ወደዚህ ምዕራፍ እንደማይሻገሩ አምናለሁ፡፡ ይሁንና ከፓርቲው ዝግነት እና ከፖለቲከኞቹ አቋም የለሽነት አንፃር አሁንም ሆነ በቀጣይ ጊዜያት ከማንም ግምት ውጪ ያሉ ክስተቶች እንደ ደራሽ ውሃ ድንገት ሳይታሰብ ግንባሩን ሊያተራምሱት ይችላሉ ብሎ መገመቱ አግባብ ይመስለኛል፡፡

http://www.zehabesha.com/

posted by Tseday Getachew

በደም የተገነባ ተቋም ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል

 (ለዳግመኛ ክህደት እንዳይዳረግ) ግንቦት 83/91 ላይ የኢትዮጵያ ሰማይ ክፉኛ በሃዘን ሲመታ ፣ ደመናው ሲጠለሽ ፤ ወንዞች መደፈራረስ ሲጀምሩ ፤ የሰውን ልብ ባር ባር ሲለው …….. የክፉው ቀን ጅማሮ ፣ የውርደት ሃሌታ ፣ የሃገር አልባነት ስሜትና የዜግነት ውርደት ደጃፍ ላይ መውደቃችን እውነት ነበር ።

Read full story in PDF: በደም የተገነባ ተቋም …

 

posted by Tseday Getachew

Post Navigation

%d bloggers like this: