Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

Archive for the month “August, 2013”

የ“አምላካችሁ ባሮች” የሆናችሁ “ሰላማዊ ሰልፈኞች” ቅድሚ የምትሰጡት ለማን ነው?

religious leaders in addis

እርቅን፣ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ መቻቻልን ለማውረድ የሃይማኖት አባቶችና ሽማግሌዎች ቁልፍ ሚና አላቸው። በር ዘግተው ይጸልያሉ። ያስታርቃሉ። ይገስጻሉ። ያስጠነቅቃሉ። እንዲህ አይነት ለሌሎች ብርሃን ለመሆን የሚቃጠሉ የሃይማኖት አባቶች ያሏቸው ምንኛ የታደሉ ናቸው?

በተቃራኒው የአምላክ ባሪያዎች፣ የየእምነታቸው ባሪያዎች፣ የምዕመናን መንፈስ መጋቢዎችና ጠባቂዎች፣ ወዘተ አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚወጡ በይፋ ተነገረን። “በተገንጣይ ነጻ አውጪ” ስም እየተጠራጠረና እየተጸየፈ አገራችንን ከሚመራ ከሃዲ ድርጅት ጎን ለመቆም የሃይማኖት መሪዎች መነሳታቸው ለፈረደባት ኢትዮጵያና ለህዝቧ ከዚህ በላይ ሃፍረት የለም!! ችግሩ በውስጥም በውጭም ያለውን ይመለከታል። ይህንን ስንል ምክንያታችንን ህዝብ ይረዳዋል ብለን እናምናለን።

በሰማያዊውም ሆነ በምድራዊው ዓለም “መተፋት” አለ። የሃይማኖት አባቶችና መሪዎች ከዚህ አስደንጋጭ /ለሚደነግጡት ነው/ የፈጣሪ ቅጣት ይጠበቁ ዘንድ ምን ማድረግ እንደሚገባችሁ በወጉ ታውቁታላችሁና ዝርዝር ማብራሪያና ስብከት ውስጥ አንገባም። ተግባራችንም አይደለም። ግን ልብ ያለው ልብ ይበል! ለማለት እንወዳለን። ከመተፋትና ከመናቅ፣ ብሎም ተጠቅመው እንደሚጥሉት እቃ ከመጣል ይጠብቃችሁ!!

ሰሞኑን የሃይማኖት መሪዎችን ኢህአዴግ ሰብስቧቸው ድርጅታዊ ሥራ እንዴት መሥራት እንዳለባቸው ሲያሰለጥናቸው ነበር። በግልጽ ቋንቋ “ሃይማኖታዊ ካድሬነትን” ሲያስተምራቸው ሰንብቷል ማለት ነው፡፡ ስልጠናው “ጽንፈኝነትን ተቃወሙ” የሚል ነው። የተማሩትን በተግባር ለመፈጸምና ያላቸውን ልዩ ብቃት ለመገምገም እሁድ የሰርቶ ማሳያ ሰልፍ እንዲወጡ ተጠይቀዋል፡፡ በኢህአዴግ ቋንቋ ሰልፉ “ተሞክሮ ማስፋት፣ ማስፋፋት፣ ማስረጽ፣ ማሳለጥ … ” መሆኑ ነው።

ጽንፈኝነትን መቃወምም ሆነ በሃይማኖቶች መካከል ተቻችሎ ለመኖር በህብረት መነሳት ይሁን የሚባልለትና በመርህ ደረጃ ሊደገፍም የሚገባው ጉዳይ ነው። በየትኛውም ደረጃ፣ ማህበር፣ ተቋምና የሃይማኖት ቤቶች ውስጥ የሚጠነሰስን “ጽንፈኛነት” ባግባቡ መቃወም ሃጢያትም የለውም። ዓለም በሙሉ ባንድነት በሰላማዊ ሰልፍ ጽንፈኛነትን ማስወገድ ቢችልና ሰላም ለማውረድ ባንድነት ቢሰሩ ክፋት የለውም። ወደ ኢህአዴግ ሰራሹ የተቃውሞ ሰልፍ ስንመጣ ግን ለሁሉም ወገኖች ጥያቄም፣ ማሳሰቢያም፣ ፍርሃቻም አንዳለን ለመግለጽ እንወዳለን።

የሃይማኖት መሪዎች በሙሉ ኢህአዴግ ራሱ ለፈጠረው በሽታ “ክትባት አለኝና ኑ ልክተባችሁ” ከሚለው ድብቅ አስተሳሰቡ በተለየ እንዴት በነጻ አስተሳሰብ ላይ ይቆማሉ? ብለን ስንጠይቅ መልሳችን ” አይታስብም” የሚል ይሆናል። ምክንያቱን በውጪም በውስጥም ያሉ የሃይማኖት ተቋማት በሙሉ ነጻና “ፈሪሃ አምላክ” የነገሰባቸው እንዳልሆኑ እንረዳለንና!! ከዚያም በላይ የሁሉም ወገን ስጋት ይኸው የሃይማኖት መሪዎች መገሸብ ይመስለናል። ኢህአዴግም እንዳሻው የሚነዳቸው አፈጣጠራቸውንና ጽናታቸውን ስለሚገነዘብ ነው።

ሃይማኖቶች የሰላምና የፍቅር መስበኪያ ቦታዎች ናቸው ቢባልም አንዳንድ ሰዎች በጣም ሃይማኖታቸውን ከመውደዳቸው የተነሳ ዓለም በሙሉ የእነርሱ ሃይማኖት እንዲወድላቸው ከመፈለግ የተነሳ በፍቅር የጀመሩትን እምነት አክርረው የጥላቻ መነሃሪያ ያደርጉታል፡፡ ይህ ደግሞ በተለያዩ ሃይማኖቶች ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ሲንጸባረቅ የኖረ እውነታ ነው።

ሰሞኑን ኢህአዴግ የሰበሰባቸው የሃይማኖት ድርጅቶችም መስመር ሊወጣ የሚችለውን የአክራሪነት አቋም እንዲያወግዙ ነቅተዋል፤ ሠልጥነዋል፡፡ በጉባዔው ላይ ሼክ ከድር ሙሐመድ “ሃይማኖት ሰላም ነው። አገራችን ሰላም ትፈልጋለች፤ አገራችን ስትታመም መድኃኒቷ እኛ ነን” ብለዋል። ግሩም አባባል ነው።

አቡነ ማትያስ በበኩላቸውም “የኢትዮጵያን ሰላምና ዕድገት የሚፈታተኑ የሁላችንም ተቃራኒ ናቸው፤ ይህንን የመቋቋም ኃላፊነትና ግዴታ አለብን፤ … የየእምነታችንን ተከታዮች የአገራችሁን ሰላም ጠብቁ ብለን መስበክ የምንችልበት ሰፊ መድረክ አለን” በማለት ሃሳባቸውን በመሰንዘር ሌሎቹም የሃይማኖት ተቋማት ምን ማድረግ እንዳለባቸው መክረዋል፡፡

ለሃይማኖት መሪዎቹ የምናስተላልፈው መልዕክት ቢኖር ይህንኑ ለአገር ተቆርቋሪነታችሁን እና ሰላም ወዳድነታችሁን “ያልተጠኑት ገጾች” ላይ አስፍሯቸው ነው፡፡ ላለፉት 22ዓመታት ሰላም ሲነፍግና ህዝብን ሲጨቁን፤ ዜጎችን በግፍ እስርቤት ሲከትና በቃላት ሊነገር በማይቻል ሁኔታ ሲያሰቃይ፤ ሲገድል፣ በጅምላ ሲጨፈጭፍ፣ ከመኖሪ ቦታ ሲያፈናቅል፣ ዜጎቹን ለአረብ አገር ለግርድና ሲሸጥና ሲያሻሽጥ፣ ህጻናትን (ወንድ ህጻናትን ጨምሮ) ለወሲብ ንግድ ሲሸቅጥ፤ የአገር ድንግል መሬትን የተፈጥሮ ደን እየጨፈጨፈ በሳንቲም ሲሸጥ፣ የመናገር፣ የመሰብሰብ፣ ሃሳብን በነጻ የመግለጽ፣ … መብትን ሲነፍግ፣ የመናገርና ሃሳብ የመስጠት መብታችን ይከበር ያሉትን ሁሉ እንደ ወራሪ ኃይል ደረትና ግምባራቸውን በጥይት ሲበሳ፣ የኢትዮጵያ እናቶችን ለዘመናት ሲያስለቅስ፣ … የኖረውን ኢህአዴግን በነካ እጃችሁ “ተው ተመከር፤ ይብቃህ፤ እረፍ!” ስትሉና ስትገዝቱት ባለመሰማታችሁ ምመናን አዝነውባኋል። አሁንም ግን ጊዜ አለና በነካ እጃችሁ ኢህአዴግንም አስጠንቅቁ፣ አውግዙ።

የሃይማኖት አክራሪነትንና ጽንፈኝነትን ብቻ ሳይሆን በነጻ አውጪ ስም የመንግሥት ሥልጣን ይዞ አገርን ላለፉት 22ዓመታት ሲያሸብር የኖረውን አክራሪውና ጽንፈኛውን ህወሃትን ራሱን “እስካሁን የረገጥከው ሰብዓዊ መብት ይበቃሃል” በማለት ሃይማኖታዊ ድርሻችሁን ተወጡ፡፡ የሰላም አስጠባቂ፣ የፍትህና የሰብዓዊ መብት አስከባሪ ካድሬ ሁኑ፡፡ በምድር ላለው ኑሮና ተድላ ሳይሆን ለመጪው ዓለም አማኞች እንዲያስቡ የምትሰብኩትን እስቲ ለአንድ ጊዜ ራሳችሁ ኑሩበትና ይህንን የሕዝብ እሮሮ በማሳወቅ ከዚህ ምድር አስተሳሰብ የላቃችሁ መሆናችሁን አሳዩ፡፡ መስዋዕትነት የሚያስከፍል ከሆነም ምዕመኖቻችሁን እንዳስተማራችሁት እናንተም ለተግባራዊነቱ በዝግጅት ቁሙ!

እሁድ በሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የአክራሪነትና ጽንፈኝነትን ብቻ ሳይሆን የሰብዓዊ መብቶች ረገጣንም አብራችሁ ተቃወሙ፤ ይህን የማይገኝ ዕድል ተጠቀሙና ድምጻቸው የታፈነውን ዜጎች ድምጽ አሰሙ፡፡

የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ መግለጫ በእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ሕዝቡ አክራሪዎችንና ጽንፈኞችን “እረፉ” በማለት ያውግዛቸው ብሎ እንዳወጀው ሁሉ፣ በዚያውም ህወሃትንና ኢህአዴግን እንዲሁም ተላላኪዎቻቸውንና ጉዳይ አስፈጻሚ አሽከሮቻቸውን “የእስካሁኑ ይበቃችኋል፤ እረፉ፤ በነጻ አውጪ ስም አገርና ወገን ላይ የምታደርሱትን ግፍ አቁሙ” በሏቸው። እስኪ የሃይማኖት አባትነት ወግ አሳዩን!! እስኪ በታሪክ የሚዘከር ተግባር ፈጽሙ። ከኮሚኒስቶች ጉያና ትዕዛዝ ውጡና በምትሰብኩት አምላክ ፊት ስትቆሙ የማታፍሩ ሁኑ። የ”አምላካችሁ ባሮች” ቅድሚያ ለማን እንደምትሰጡ እወቁ። በሰማያዊውም ሆነ በምድራዊው ዓለም በቁም “መተፋትም” አለና!!

http://www.goolgule.com/

posted by Tseday Getachew

Advertisements

ነሐሴ 26 የመንግስት ድጋፍ ያለው የሀይማኖቶች ጉባኤ በአዲስ አበባ የጠራው ሰልፍ ያልተጠበቁ ነገሮችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።

መንግሥት ለተፈጠረው ችግር በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ እንጠይቃለን! ሰማያዊ ፓርቲ

 ኢሳት ዜና :-  በመንግስት የሚደገፈው የሐማኖቶች ጉባኤ  በመጪው እሁድ አክራሪነት እናወግዛለን በሚል አላማ በጠራው ሰልፍ ላይ የአዲስ አበባ እና እስከ 100 ኪሎሜትር በሚደርስ ርቅት ላይ  በአጎራባች የክልል ከተሞች የሚገኙ ዜጎች በብዛት እንዲገኙ የኢህአዴግ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ሰንብተዋል።  የመንግስት ሰራተኞች ፣ በግል ስራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ እንዲገኙ ካልተገኙ ግን አክራሪነትን እንደደገፉ እንደሚቆጠርባቸው ሲነገራቸው መሰንበቱን ወኪሎቻችንን ዘግበዋል።

መንግስት ለፖለቲካ ትርፍ ብሎ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ፣ መንግስትም ራሱ ያልጠበቀውን ነገር ይዞበት ሊመጣ እንደሚችል ምልክቶች እየታዩ ነው። ድምጻችን ይሰማ የተባለው አካል ከአመት ከመንፈቅ በላይ ያካሄደውን ተቃውሞ ኢህአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ ተገኝቶ ተመሳሳይ ተቃውሞ እንደሚያሰማ መግለጫ ማውጣቱ እሁድ ምን ይፈጠር ይሆን የሚል ጥያቄ አስነስቷል።

ድምጻችን ይሰማ ባወጠው መርሀግብር ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሀይማኖት አባቶች ንግግር ካደረጉ በሁዋላ ነጭ ወረቀት ወይም የጨርቅ ማህረም እንዲያውለበልቡ፣  የመጅሊስ ሹሞች ንግግር ሲያደርጉ ጆሮን በመድፈን፣ ያለምንም ድምጽ ሁለት እጅን ወደ ላይ በማንሳትና በማጠላለፍ የታሰሩት የኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል።

ድምጻችን ይሰማ ይህን መርሀግብሩን በተግባር ካዋለ፣ አንድ መንግስት ለድጋፍ በማለት በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞ ሲስተናገድበት በታሪክ የመጀመሪያው ይሆናል። ምናልባትም ለኢህአዴግ ታላቅ የፖለቲካ ክስረት ሊያመታበት እንደሚችል አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

ኢህአዴግ ከውርደት ለመዳን የጸጥታ ሀይሎችን በብዛት ከማሰማራት ጀምሮ የክልል ደህንነቶች ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ እያደረገ ነው።

ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ ሊቀጥል እንደሚችል መታወቁ ሌላ ድራማ ሊፈጥር እንደሚችልም ይጠበቃል።

ሰሞኑን በተደረገው የሀይማኖት ጉባኤ አቶ በረከት ችግሩ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑን ሲናገሩ አቶ ሀይለማርያም ደግሞ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።

ESAT

 

posted by Tseday Ghetachew

ድምፃችን ይሰማ ኢሕአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ በመገኘት አክራሪነትን እንደማይደግፍ በመግለጽ ኢሕአዴግን ሊያሳፍረው ነው

ከድምጻችን ይሰማ

የትኛውንም አይነት አክራሪነት ሙስሊሙ ህብረተሰብ እንደሚያወግዝ በእሁዱ ሰልፍ በአደባባይ ያስመሰክራል!
ጁምአ ነሐሴ 24/2005

‹‹አክራሪነትን ሕገ-መንግስቱ ቢፈቅድ እንኳን አንቀበለውም!›› ኮሚቴዎቻችን

ለዚህች አገር ሰላም እና ደህንነት መንግስትን ጨምሮ ሁሉም ወገን ከአክራሪነት ሊርቅ ይገባዋል!

አክራሪነት ማለት ድንበር ማለፍ ማለት ነው፡፡ አክራሪነት ዜግነት የለውም፣ በእምነት አይወሰንም፣ በቦታ አይከለልም፣ በሐገር አይለይም፡፡ በግል፣ በህብረት፣ በመንግስት ደረጃ ሊከሰት የሚችል ነው፡፡ አክራሪነትን ከማንም በፊት ያወገዙት ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) ስለሆኑና የጥፋት አቅጣጫ መሆኑን ስለጠቆሙን አክራሪነትን ለመቃወም ከማንም በፊት ቀድመን የምንገኘው እኛው ነን፡፡ አክራሪነትን የምንቃወመው መሰረታችን ለአክራሪነት የሚመች ስላልሆነ ነው፡፡ ተቻችሎ መኖርም ቋሚ አጀንዳችን ስለሆነ ነው፡፡ ለዚህች አገር በሰላም መኖር ሁሉም ወገን ከሁሉም አይነት አክራሪነት ርቆና እውነተኛ የሰላም ፈላጊ ሆኖ መኖር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ ህዝቦች በጋራ በተግባቡበት ህግ በሰላም የመኖር፣ በሃይማኖቶች መካከል መከባበር የአስተምህሮታችን መሰረት ሲሆን በሚሊዮኖች ፊርማ ወክለን በግፍ የታሰሩትን ኮሚቴዎቻችንን ጨምሮ መስዋእትነት የምንከፍልለት ሰላማዊ ትግላችን በኢትዮጵያ የሃይማኖት ነፃነት እና የሃይማኖቶች ተከባብሮ የመኖር ሂደት አካል ነው፡፡ አክራሪነት ማለት ግን ዛሬ ፖለቲከኞች እንደሚጠቀሙት ተለክቶ እንደሚሰፋ ልብስ ሊያጠቁት የሚፈልጉትን አካል ሁሉ በልክ በልኩ አሰፍተው አልብሰው የሚያጠቁበት መቆመሪያ አይደለም፡፡

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለሁለት አመታት ስንቃወም የኖርነውም መንግስታዊ ሃይማኖት (አህባሽ) በመንግስት ሙሉ እቅድ እና ትግበራ አማኞችን ለመከፋፈልና የእርስበርስ ፀብ ለመፍጠር ከሌሎች ሃይማኖቶችም ጋር አብሮ የመኖር ገመድን ሊበጥስ ‹‹ከመንግስት የወረደ ነውና ተቀበሉት›› ተብሎ ስለተጫነብን ነው፡፡ መሪዎቻችንም ሆኑ በሺ የሚቆጠሩ ንፁሃን በእስር የሚማምቅቁት ብሎም በርካቶች የሞቱትና የተደበደቡት ‹‹እኔ ከመረጥኩላችሁ ውጭ ትክክለኛ እምነት የለም›› የሚልን አክራሪነት በመቃወም እንጂ በሌላ አይደለም፡፡ መንግስት የእምነት መብት መጠየቃችንን አክራሪት ሲል ፈርጆታል፡፡ ይህ መብት መጠየቅን በአክራሪነት የሚፈርጅ ፖለቲካዊ አክራሪነትን በፅኑ እናወግዛለን፡፡ በሃገራችን ተጨባጭ ፅንፈኛ የፖለቲካ አካሄድ የትክክለኛው አክራሪነት መፈልፈያ መሆኑን እያየን ነው፡፡ በዚህ አክራሪነት ከማንም በላይ የተጠቃነው እኛ ነንና አክራሪነትን በፅኑ እናወግዘዋለን፡፡ ይህንንም ለማሳየት ነው የእሁዱን ሰልፍ የምንሳተፈው፡፡

የነሃሴ 26 ሰልፍ ህዝበ ሙስሊሙ ከሌላ ሃይማኖት ተከታይ ወንድሞቹ ጋር የሚገናኝበት፣ ስለሃገሩ ስላም ያለውን ቀናዒነት የሚያሳይበት መድረክ በመሆኑ ሙስሊሙ ከሌሎች ሃይማኖት ተከታይ ወንድሞቹ ጋር ሰላምታ በመለዋወጥ አድራሻ በመለዋወጥ ጠንካራ አብሮነትን የሚያጠናክርበት ነው፡፡ ትናንት የጥምቀት በዓሉን ታሳቢ በማድረግ የተቃውሞ መርሃግብሩን የከለሰለትና ቦታ ከቀየረለት ህዝበ ክርስቲያን ጋር ነሃሴ 26 በአንድነት ቆሞ አክራሪነትን በጋራ እያወገዘ ሰላማዊነቱን ያስመሰክራል፡፡ በተጨማሪም የነሃሴ 26 የቅዋሜ መድረክ ከሁሉም እምነት ተከታዮች ጋር ያለንን ትስስር የምናጠናክርበትና ሰላማዊ የመብት ጥያቄአችንን ይበልጥ የምናስረዳበት መልካም አጋጣሚ ነው፡፡ ሰልፉን እንደጠራው የሚነገርለት የሃይማኖት ጉባኤ ውስጥ ያሉ የሃይማኖት አባቶች ለዚህች ሃገር እውነተኛ የሰላም አስተማሪና ተጠሪ መሆናቸውን፣ ለችግሮች መፍትሄ በማፈላለግ በመሰለፍ ሃገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አደራ የምንልበትም ዕለት ነው፡፡

ሰልፉ የሃይማኖቶች ጉባኤ ከሚባለው ተቋም ጋር ህዝብ የሚኖረው የመጀመሪያ የአደባባይ ግንኙነት በመሆኑ የተቋሙን አሰላለፍ በተግባር ለማየት ምቹ አጋጣሚ ነው፡፡ በመሰረቱ የሃይማኖቶች ጉባኤ መንፈሳዊ መሪዎች ያሉበት በመሆኑ ‹‹አክራሪነትን እናወግዛለን›› በሚል መሪ ቃል በጠሩት ሰልፍ የአደባባይ ውንብድና ቢፈፀም በወከላቸው አማኝ እና በተወከሉለት እምነት ላይ ታላቅ ክህደትን መፈፀም ነው የሚሆነው፡፡ መንግስትም ይህንን ሰልፍ ለርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማዋል ከተሯሯጠ በሃገሪቱ እምነት የሚጣልበት ነፃ ተቋም ፈፅሞ አለመኖሩን ማስመስከር ሲሆን በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ደግሞ ያለ እፍረት መደበኛ ተግባሩ እንዳደረገው ለመላው ኢትዮጵያዊ በገሃድ የሚያውጅበት አጋጣሚ ይሆናል፡፡ በዚህ አጋጣሚም መንግስት ሰልፉን ለሃገራዊ መግባባት እንዲያውለው አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ ዜጎች በሃይማኖታቸው ተከብረው መብት በመጠየቃቸው ሳይሸማቀቁና ሳይበደሉ የሚኖሩባትን ኢትዮጵያ ለቀጣዩ ትውልድ ለማቆየት መልካም አጋጣሚ በመሆኑ መንግስት እድሉን በአወንታዊ መልኩ ሊጠቀምበት ይገባል እንላለን፡፡

ከዚህ ውጭ ግን ‹‹የሃይማኖቶች ጉባኤ ጠርቶታል›› ለተባለው ሰልፍ ተሳትፎ መንግስት የህዝብን ጓዳ ማስጨነቁ፣ ሰልፉን በማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ በማስፈፀም በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ ገብነቱን በግልፅ እያሳየ ነው፡፡ መንግስት ‹‹አክራሪነትን እዋጋለሁ›› በሚል ሽፋን እምነታችንን ክፉኛ ጣልቃ ገብቶበታል፡፡ አሁን ደግሞ ‹‹አክራሪነትን እናወግዛለን›› በሚል ሽፋን ህዝብን በግዳጅ ጭምር በማስወጣት ይህን ሰልፍ ከሃገራዊ መግባባት ይልቅ ለእኩይ አላማ ሊጠቀምበት አስቦ ከሆነ ተግባሩን በፅኑ እናወግዛለን፡፡ ይህ ተግባር የመንግስት መዋቅር ከዚህ ቀደም ፖለቲካን ሽፋን አድርገው የሃይማኖት እና የቡድን አጀንዳን ለማስፈፀም ለሚሯሯጡ አመራሮች እንደተጋለጠ ሁሉ፤ አሁን ደግሞ በሙሉ መዋቅሩ በሃይማኖት ሽፋን ፖለቲካዊ ቁማር ለመጫወት አስቦ ከሆነ በፅኑ እናወግዘዋለን፡፡

በመሆኑም ይሄን ሽፋን ገልጠን በማውጣትና መንግስት ሊደበቅበት ያሰበበትን ካባ በማውለቅ ‹‹አክራሪነትን አዎ እናወግዛለን!››፣ ‹‹በአክራሪነት ሽፋን ግን በእምነታችን ጣልቃ መግባትንም በተመሳሳይ እናወግዛለን›› ልንል ወደ ሰልፉ እንተማለን፡፡ በሰልፉ ላይ በመገኘት መንግስት ሰልፉን ከተቀመጠለት ስያሜ ውጪ ለህገ ወጥ ተግባሩና ፖለቲካዊ ትርፍ ማጋበዣው መጠቀሚያ እንዳያደርገው እናደርጋለን፡፡ ሃላፊነት በጎደለውና ከልክ ባለፈ ንቀት የሙስሊሙን እምነት ለመበረዝ ሲሞክርና አማኙን በማንገላታት ለመፍጠር የታለመው ሀገራዊ ትርምስ አልሳካ ሲል ዛሬ አሰላለፍን በመቀየር በሃይማኖቶች ሽፋን ህዝብን በህዝብ ላይ ለማነሳሳት የተቀመረ ስሌት ካለ እንደማይሳካ የፊታችን እሁድ በተግባር እናስመሰክራለን፡፡ ይህን ክፉ ራዕይ ዳግም መና ለማስቀረት ዛሬም ከሃገር ወንድምና እህቶቻችን ጋር እምነትና አስተሳሰብ ሳይለየን እጅ ለእጅ በመያያዝ ለዘመናት በገዢዎች ያልተናደውን አንድነታችንን እናጠናክራለን፡፡

የነሃሴ 26 ሰልፍን ስንሳተፍ አክራሪነትን በመቃወም እና አብሮነትና ተቻችሎ መኖርን በተግባር እናሰይበታለን፡፡ ሆኖም አክራሪነትን ከመቃወም ውጭ በሰልፉ ላይ የሚስተናገዱ ማንኛውንም አይነት አፍራሽ መርሃ ግብሮች ካሉ በፅኑ እናወግዛለን፡፡ ሁሌም ደጋግመን ስንገልጸው እንደነበረው ሁሉ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ጥያቄም ሆነ እንቅስቃሴ ሰላማዊ፣ አገራዊ እና ህዝባዊ መሆኑን እንዲሁም ይምነት እንጂ የፖለቲካ ጉዳይ አለመሆኑን እና ከመብት እና የፍትህ ጥያቄ ውጭ የተለየ መልክ እና ይዘት እንደሌለው ለሁሉም ኢትዮጵያውያን አሁንም ደግመን ማስረገጥ እንሻለን:: በመሆኑም ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በሙሉ ከእነ ቤተሰቡ ነቅሎ በመውጣት በእሁዱ የተቃውሞ መርሐ ግብር ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ ተላልፏል፡፡ ሁላችንም እዛው እንገናኛለን፡፡ ለእለቱ ከሚቀመጠው መርሐግብር ክንውን ሳንላቀቀ የተቀመጠውን ብቻ በመፈጸም አክራሪነትን ከሌሎች ኢትዮጵያውን እህቶችና ወንድሞች ጋር በመሆን በተግባር እናወግዛለን፡፡

የነሀሴ 26 መርሐግብር አፈጻጸም በተመለከተ
ጁምአ ነሐሴ 24/2005

በዕለቱ መደበኛውን የሰልፍ መርሃግብር ሙሉ በሙሉ በቋሚነት የምንከተል ሲሆን በተጨማሪ ግን

* ሁሉም የሃይማኖት አባቶች ሰላምን፣ ፍቅርን እና መቻቻልን እንደሚሰብኩ፣ እኩይ ተግባራትን እና አክራሪነትን እንደሚቃወሙና የሰላም እንደራሴዎች እንደሆኑ ለማሳየት እንዲሁም የሃይማኖት አባቶቹ ለወከሉት እምነትና በእምነቱ ስር ላሉ አማኞች ያለንን ክብር ለማሳየት ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት የማናምንበትን ወይም ሞራላችንን የሚነካ ንግግር ቢያደርጉ እንኳ በጥሞና ንግግራቸውን እናደምጣለን፡፡ በምንም መልኩ የሃይማኖት አባቶቹ ንግግር ሲያደርጉ ንግግራቸው እንዲቋረጥ አናደርግም፡፡ ንግግራቸውን እንዳጠናቀቁም የሰላም መገለጫ የሆነ ነጭ ነገር እናውለበልባለን፡፡ ለዚህም መሃረብ፣ ነጭ ወረቀት፣ ሶፍት እና መሰል ቀላል ነገሮችን መጠቀም እንችላለን፡፡

* ህዝብ በይፋ ባወረደው ህገ-ወጥ የቀበሌ ሹመት የመጡ የመጅሊስ ሹመኞች ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ንግግራቸውን እስኪጨርሱ ያለምንም ድምፅ ሁለቱንም ጆሯችንን በመዳፋችን ደፍነን እንቆያለን፡፡

* ንግግር የሚያደርጉ የመንግስት ባለስልጣናት ካሉ በሚሊዮኖች ፊርማ የወከልናቸው ኮሚቴዎቻችንን በማሰር መላውን መብት ጠያቂ ህዝበ ሙስሊም ያሰሩ መሆናቸውን ለመግለጽና የነጠቁንን መብታችንን በመመለስ ሕዝቡን ከእስራት እንዲፈቱት ለመጠየቅ ንግግራቸውን እስኪጨርሱ ያለምንም ድምፅ ሁለት እጃችንን ወደላይ ከፍ አድርጎ በማንሳትና በማጠላለፍ ምልክት ብቻ እናሳያለን፡፡

ማስታወሻ፡-

– ወደሰልፉ የምንሄደውም ሆነ የምንመለሰው ሌሎች የሰልፉ ተሳታፊዎች በሚሄዱበት ሁኔታ ሲሆን በዋናው መርሐግብር ላይም ሆነ ከዚያ በፊት እና በኋላ ከተጠቀሱት ውጭ ሌላ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ በጭራሽ የለብንም፡፡

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=6915

posted by Tseday Getachew

 

ማኀበረ ቅዱሳን በዌብሳይቱ ላወጣው ርዕሠ አንቀጽ የተሰጠ ምላሽ

እውነት መስካሪ – ከሚኒስታ

ማቅ፡ ‘‘ ማኅበረ ቅዱሳን ከዚህ ቀደምም ከማንም በፊት በሀገራችን የአክራሪነት ዝንባሌዎች እንዳሉ በማመልከት በኩል ግንባር ቀደም ሚና ተጫውቷል፡፡ “አክራሪዎች” በተለያዩ አካባቢዎች አብያተክርስቲያናትን ሲያቃጥሉ ክርስቲያኖችን ሲያርዱ አካሔዱ መልካም አለመሆኑን በመጠቆም እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ በማሳሰብ ሀገራዊ ሓላፊነቱን ለመወጣት ሞክሯል፡፡ የሃይማኖቶች መከባበር በመላው ሀገሪቱ እንዲሰፍን ያለውን ቁርጥ አቋምም አንጸባርቋል፡፡’’

መልስ፦ ለመሆኑ ከዚህ ቀደም በቤተክርስቲያንና በካህናት በምእመናንና በንዋይተ ቅዱሳን ላይ የደረሰውን ውድመት በርግጥ የፈጸመው ክፍል ማን እንደሆነ በምርመራ ተረጋግጦ ነው ‘አክራሪዎች’ ናቸው ብላችሁ ርምጃ እንዲወሰድ የተናገራችሁት? ድርጊቱ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት ካልቻለም ለማደከም የተነሳውን በቤተመንግስት ያለው ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ኦርቶዶክስ ኃይል እንዳላደረገው ምን ማረጋገጫ አላችሁ? አንዱን ብሔረሰብ ከሌላው ለማጋጨት ከላይ እታች ሲል የኖረና ያልተሳካለት አጥፊ ቡድን ዛሬ ደግሞ አንዱን ኃይማኖት ከሌላው ጋር ለማጋጨት የሚያደርገውን ታላቅ ሴራ እንዲሳካለት የሚያግዝ የእንካ በእንካ የቤት ስራችሁ እንዳልሆነ በምን ማረጋገጥ ይቻላል?

 ሙሉውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=6911

posted by Tseday Getachew

የኛ ነገር፡ ከኔ ማዕዘን፡- በብርሀኑ ተበሳጨሁ፤ በሰማያዊ ተጽናናሁ፡ በአንድነት ደግሞ ተስፋ አደረግሁ (ከተ/ሚካኤል አበበ)

ከተክለ ሚካኤል አበበ

1-      ይህ ጽሁፍ ዓላማው አድናቆት፡ ትችትና ግብዣ ነው። የአንድነት ምሽት በቶሮንቶ ግብዣ። ከአድናቆትና ከግብዣው በፊት ስለፖለቲካ መሪዎችና ስለፖለቲካ ተንታኞች አትቶ፤ የብርሀኑ ነጋን (ዲባቶ) አቀራረብ ይተቻል። የሰማያዊ ፓርቲን ርምጃ ያደንቃል። የአንድነት ዘመቻን ስለማገዝ ያሳስባል። እንደው ተገጣጥሞ ነው እንጂ፤ አንዱን ለማሞገስ ሌላው መኮሰስም መከሰስም የለበትም። ግን አንዳንዴ ደግሞ፤ በጊዜ ያልተተቸ፤ ይለመዳል። አጉል ልማድ ይሆናል። ሁሉንም ለያይቶ ለመጻፍ ደግሞ፤ ጊዜ የለም። ስለዚህ ባንድ ወንጭፍ ሶስት ወፍ ነው ለመማረክ የምጥረው። ከሀተታ ልጀምር።

የፖለቲካ ተንታኝና የፖለቲካ መሪ

2-      የፖለቲካ መሪ ከፖለቲካ ተንታኝ መለየት አለበት። የፖለቲካ መሪ የፖለቲካ ተንታኝ ሲሆን፤ የጋዜጠኞችንና የፖለቲካ ተንታኞችን/የምሁራንን ስራ ይጋፋል። ያ ብቻም አይደለም። መምራት አቅቶት፤ ወይም መምራት ጠፍቶት፡ በአካልና በስም የፖለቲካ መሪነቱን ወንበር ተቆናጦ፤ በግብር ግን የፖለቲካ ተንታኝነትን ቦታ ይዞ፤ የፖለቲካ መሪነትን ስራ በፖለቲካ ትንታኔ ሊያካክስ ይሞክራል። ያም ብቻ አይደለም፡ የፖለቲካ መሪነት ሚናን ከፖለቲካ ተንታኝ ጋር ያደባለቀ መሪ፤ የያዘውን የፖለቲካ መሪነት ሀላፊነት ከተንታኝነት ሲለሚቀይጠው፤ ትንታኔው ንጹህ አይሆንም። ስለዚህ የፖለቲካ ትንታኔውን መቀበል ይከብዳል። ባይከብድም ትንታኔው ጎዶሎና ወደሁዋላ የሚጎትት፤ ወይንም ወደፊት የማያራምድ ይሆናል። ወይም ትንታኔው ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ የሚደረግ ጥልቅ ያልሆነ ትንታኔ ይሆናል።

3-      ለምሳሌ ብርሀኑ ነጋ ባለፈው የኢሳት ስብሰባ ላይ ያቀረበውን የንግግሩን ገጽ 16 መጨረሻና ገጽ 17 መጀመሪያ ብንመለከት ሀሳቡ ጥልቅ ወይም ሀቀኛ አለመሆኑን በቀላሉ ለመረዳት ይቻላል። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/6563 ለዚህም ነው ምሁር ፖለቲከኛ መሆንን ከመረጠ፤ ምሁርነቱን ቀንሶ መሪነቱን እንዲያጠብቅ ግድ ነው የምንለው። ኦባማን ውሰዱ። ኦባማ ሲመረጥ ምሁር ነበር። ከአራት አመት በሁዋላ ግን ምሁርነቱ እየቀነሰ፤ ወደቡሽነት እየተጠጋ መጥቷል። የኦባማ የሶሪያ አቋም፤ ከቡሽ የኢራቅ አቋም ብዙ አይለይም። አሳድን እንበለው ወይም እንብላው እያለ ነው። ኢሳት ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ብርሀኑ ነጋ (ዲባቶ) ያንን መለየት ነው የተሳነው። በፖለቲካ መሪነት መጥቶ (በግንቦት ሰባት ሊቀመንበርነት) የፖለቲካ መሪነቱን ግን ትቶ፤ ምሁር ለመሆን ሞከረ። ተንታኝ። የፖለቲካ ተንታኝ በመሆን የጋዜጠኞችንና የምሁራንን ስራ መሻማት ብቻ ሳይሆን፤ ሁለቱንም ሳይሆን ቀረ። በዚህ ረገድ ጃዋር ይሻላል። እንደተንታኝ በደንብ ይተነትን ነበር። የተንታኝነቱን ሚና ትቶ ባለፈው ሰሞን የራሱን የፖለቲካ አቋም ሲያንጸባርቅም፤ ብዙ ሰዎችን ቢያበሳጭም፤ እቅጩን ነው ያስቀመጠው። ብሬ አድበሰበሰው። በእስር ላይ የሚገኙትም ይሁኑ በነሱ የተተኩትን ከነሱም የቀደሙትን ሙስሊሞች አካሄድና እንቅስቃሴ የሚጠራጠሩ ካሉ፤ ጥርጣሬያቸው በወያኔ ፕሮፓጋንዳ ነው የተፈጠረው ለማለት ይከብዳል። በወያኔ ፕሮፓጋንዳ የማይበገሩም ከተጠራጣሪዎቹ ተርታ ውስጥ አሉበትና።

4-      የዲባቶ ብርሀኑ ነጋ ያልጠራ ትንታኔ የመነጨው፤ ፖለቲካዊ መሪ መሆንና ፖለቲካዊ ምሁር/ተንታኝ መሆንን አጣምሮ ለመሄድ ከመሞከር ነው። የፖለቲካ ተንታኝ የምለው፤ በፖለቲካ ውስጥ በቀጥታ በአድራጊ-ፈጣሪነት ሳይሳተፍ ወይም መሳተፍ ሳይጠበቅበት፤ የአንድን ፖለቲካዊ ስብስብ/ማህበረሰብእ ፖለቲካዊ ሁኔታ እየቃኝ፤ ከአካባቢያዊና አለማቀፋዊ ሁነቶች ጋር እያጣቀሰ፡ የሁነቶቹን ምክንያት የሚያብራራ፤ ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮችን የሚጠቁም፤ አደጋዎችን የሚተነብይ፡ ተመልካችና ተናጋሪ ማለት ነው። የፖለቲካ መሪ የፖለቲካ ተንታኝ ሲሆን፤ አደናጋሪ ነው የሚሆነው። የፖለቲካ መሪዎች የፖለቲካ ተንታኝ መሆን የለባቸውም እያልኩ አይደለም። እኔ የምለው፤ አንደኛ ፖለቲካ መሪዎች የፖለቲካ ትንታኔ ችሎታቸው የሚገለጸው በፖለቲካዊ አመራራቸው በሚወስዱት ፖለቲካዊ እርምጃ ውስጥ መሆን አለበት ነው። ሁለተኛ፡ ፖለቲካን መተንተን የፖለቲካ መሪዎች ዋና የአደባባይ ስራ መሆን የለበትም ነው። እዚያው ድርጅታቸው ውስጥ እንደፍጥርጥራቸው። ይፋዊ ፖለቲካዊ ስራቸው ግን፤ መምራት እንጂ መተንተን አይደለም። አቶ መለስ ከሞቱ በሁዋላ ብቻ ያለውን ሁኔታ እንኳን ብንለመከት ግን፤ የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ብርሀኑ ነጋ፤ ከሲሳይ አጌና ጋር ያደረጋቸውን ቃለምልልሶች ወይንም ያለፈው ሰሞንን የኢሳት መድረክ ጨምሮ፤ በቀረበባቸው መድረኮች ላይ የሚናገራቸወን ስንለመከት አድራጊ የፖለቲካ መሪ ሳይሆን፤ ተንታኝ ጋዜጠኛ ወይንም እዚህ አገር እንደሚሉት ጠቢብ ምስክር ለመሆን ነው የጣረው።

5-      ያ ብቻም አይደለም፤ አሁን በእመ-ብርሀን፤ ሰላሳ ድርጅቶች የኢትዮጵያን እጣፈንታ ከህዝብ ጋር ሊመክሩ በተሰበሰቡበት መድረክ ላይ ለመነሻ የሚሆን የአስር ደቂቃ ንግግር አድርጎ የተቀረውን ሰዓት ለህዝብ ውይይት መተው እንጂ፤ የ55 ደቂቃ ድርሳን ማንበብ ምን የሚፈይደው ነገር አለ? ብርሀኑ ነጋ ባለፉት ሶስት ወራት በኢሳትም ይሁን በተለያዩ መድረኮች ያገኘውን እድልና ሰዓት ስንመለከተው ደግሞ የንግግሩ መርዘም ስህተትነትና አበሳጭነት ይጎላል። ያ ብቻም አይደለም፤ ሶስት ሺህ ምናምን አመት፤ መጀመሪያ በጸሀዩም በጨረቃውም በማምለክ፤ ከዚያ ብሉይን በመቀበል፤ ከዚያ ክርስትናን፤ ከዚያ እስልምናን፤ ከዚያ ካቶሊክን፤ ከዚያ ፕሮቴስታነንስዝምን፤ በመቀበልና በማቻቻል ለኖረች አገር፤ የሊበራሊዝምና ዴሞክራሲ መፍትሄ ለሀይማኖት ነጻነት የሚል የአንድ ሰዓት ስብከት ያስፈልጋታል? ቢቀርብንስ?

6-      በዚህ ኢሳት ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ፤ ግንቦት ሰባትን ወክሎ ንግግር ካቀረበው ብርሀኑ ነጋ ይልቅ፤ የሽግግር ምክርቤቱ እጥር ምጥን ባለች ባለአራት ገጽ ወረቀቱ፤ የተሻሉ የሽግግር ሀሳቦችን አቅርቧል። http://etntc.org/ENTC/wp/wp-content/uploads/ESAT-Presentation-0818.pdf። እነሱ የሚመኟት ኢትዮጵያ ምን መምሰል እንዳለበት፤ ሽግግሩ ምን እንደሚመስል፤ የሽግግር ሰነድ የሚያረቅ ኮሚቴ ስለማዋቀራቸው፤ አለማቀፍና አገርአቀፍ የእምቢተኝነት ቡድን ስለማቋቀም፤ ድርጅታቸው ምን እየሰራ እንደሆነ ተናግሯል። ከሽግግር ምክርቤቱ አራት አመት ቀደም ብሎ የተቋቋመው ግንቦት ሰባት ግን ጥምረት ከተቋቋመ ከሶስት አመት በሁዋላ፤ የከማል ገልቹ ኦነግ ከተመለሰ ከሁለት አመት በሁዋላ፤ ገና ስለድርጅቶች አንድነት፤ በጋራ ትግል ወያኔን ስለማስወገድ አጣዳፊነት ይሰብካል። የዛሬ አመት፡ የዛሬ ሁለት አመት፡ የዛሬ ሶስት አመት ከነበርንበት ብዙም ፈቀቅ አላልንም።

7-      ኢሳት ይሄንን ስብሰባ ማዘጋጀቱ ይደነቃል። ይሁን እንጂ፤ የኢሳት አስተዳዳር የሆነው ወዳጄ ነአምን ዘለቀ የዛሬ አመት አካባቢ እንዲህ ያለው ተመሳሳይ ስብሰባ ሲዘጋጅ፤ (ያኔ ስብሰባው የተዘጋጀው በኢሳት ሳይሆን በግንቦት ሰባትና በነኑሮ ደደፎ (ዲባቶ)/ከማል ገልቹ ኦነግ ነበር)፤ እባክህን መሪዎቹ ንግግር ያሳጥሩና ለሰዉ እንዲተነፍስ ግዜ ይስጡት ብዬ አሳስቤው ነበር። ነአምን አንዳንዴ አይሰማም። ወይም ቢሰማም አያደምጥም። እነሆ፤ ባመቱ፤ ሌላ ውድ መድረክ ባከነ። የብርሀኑ ነጋ ጽሁፍ፤ የመጀመሪያው አስራሶስት ገጽ ለዚያ መድረክ አስፈላጊ አልነበረም። ነገር መቁረጥና ማሰጠር፤ እንዲሁም መድረክ ላይና ምድር ላይ የምናቀርበውን መምረጥ አለብን። ያለበለዚያ ትክክለኛና ውጤታማ ሚናችንን መለየት አለብን።

ተስፋ፡ አድናቆትና፤ ግብዣ

8-      መቼም ተቃጥላችሁ አትሙቱ ያለን ፈጣሪ መጽናኛ አያሳጣንም፤ በግንቦት ሰባት ሊቀመንበር አቀራረብ ብንበሳችም፤ አላህ የሚያጽናናን አላሳጣንም። የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ እኛ በምናደርገው ነገር ምንም ቀስቀስ በማይልበት፤ ፖለቲካዊ አየሩ ጸጥ ረጭ ባለበት ሁኔታ ነው፤ የዛሬ ሶስት ወር አካባቢ፤ ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የተሳካ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ። ላለፉት ስምንት አመታት ሰልፍ አይታ ለማታውቀው አዲስ አበባ ሀያ መቶም የሁን ሀያ ሺህ ሰው ያስወጣ ሰልፍ ተከሰተ። ያ ያጽናናል። እነሆ ያኔ በያዙት ቀጠሮ መሰረት፤ ሁለተኛው የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በመጪው እሁድ ይቀጥላል። መቼም ብዙዎቻችን ፈሪዎችና ሸሺዎች በሆንበት ሁኔታ፤ ጥቂት ዠግኖች አልጠፉምና፤ የሰማያዊ ፓርቲዎች ድፍረትና ቁርጠኝነት የሚያስደንቅ ነው። የህወሀት ኢህአዴግ መንግስት ባለስልጣናት፤ በአዲስ አበባ መስተዳድር በኩል ሰልፉ ህገወጥ ነው ቢሉም፤ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች ግን ሰልፉ ህጋዊ ነው፤ እንገፋበታለንም እያሉ ነው። የመጪው እሁድ ትልቅ ተጋድሎ ዋዜማ ላይ ነን።

9-      እንዲህ ያለውን ትእይነት ቆሞ መመልከት ብቻ ግን ነውር ነው። መቼም አንዴ ሸሸተን ወጥተናል፤ በወጣንበትም ቢሆን ግን፤ የምንችለውን እንኳን በማድረግ ተዋናይ መሆንም አለብን። የኛ የተቀናቃኙ/ተፎካካሪው/ተቃዋሚው ጎራ፤ በተለይ በውጪ የምንኖረው ተቃዋሚዎች ትልቁ ችግር፤ ማድረግ የምንችለውን እንኳን ማድረግ አለመቻላችን ነው። በሰላማዊም ይሁን ደማዊ መንገድ፤ በአመጽም ይሁን በጸሎት ለሚታገሉት ስንቅና ትጥቅ ማቀበል። ስንቅና ትጥቅ ላለማቀበል ብዙ ምክንያት መደርደር ይቻላል። ምንም ምክንያት ግን አጥጋቢ አይሆንም። ቅዳሜና እሁድ የዱለትና የቁርጥ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን ጉዳይ እያብራራ የሚተነትነው፤ የምእራባዊያንን ሴራ የሚመሰጥረው ወዳጄ፤ የኢሳት ዝግጅትን የ20 ብር ትኬት ስሰጠው ፊቱን እንዳጨፈገገው መሆን የለብንም። ለሰማያዊ ፓርቲ ሁለተኛ ሰልፍ መሳካት እንጸልያለን። በጸሎት ብቻ አናበቃም። በግብርም እንከተላለን።

10-   መቼም በየከተማው ብዙ የማይደክማቸው ሰዎች አሉ። እነሆ በመጪው ቅዳሜ ማታ፤ በዚህ በኛ ከተማ ትንሽ ተንፈስ እንላለን። ተሰብስበን ኢህአዴግን ከመዘልዘል ባሻገር፡ የትግሉ በረከት እንጥፍጣፊ ይደርሰን ዘንድ የአንድነት ምሽት ያዘጋጁ አሉ። “የአእላፋት ድምጽ ለነጻነት” የተሰኘውን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ዘመቻ በመደገፍ እዚህ ቶሮንቶ ከተማ፤ እንደፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር፤ ቅዳሜ ኦገስት 31 ማታ ከ6ሰኣት ጀምሮ’፤ 2050 ዳንፎርዝ ጎዳና በሂሩት ሬስቶራንት የቤተሰብ አዳራሽ የእራት ምሽት ተዘጋጅቷል። በሰሀን $ 50 ብቻ። ለጥንዶች $ 60። ለኔቢጤው ደሀ ደግሞ $ 30 ብቻ። ገቢው፤ ከወጪ ምላሽ ለአንድነት ፓርቲ የሚሄድ ነው።

11-   እነሆ፤ በአካል ከግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሀይል ጋር ላንዘምት እንችላለን። በአካል ከሰማያዊ ፓርቲም ጋር አንሰለፍ ይሆናል። ከአንድነት የነጻነት ድምጾች ጋር ለመጮህ ግን አይሳነንም።ለሚጮሁት ጉልበት፤ ለሚሰለፉት ብርታት፤ ለሚዘምቱትም ጽናት ልንለግስ እንችላለን። በያለንበት አካባቢ ያሉትን የፖለቲካ ድርጅቶች እንርዳ። እዚህ ቶሮንቶ ያለን፤ ቅዳሜ ሂሩት ሬስቶራንት ብቅ እንበል። ቅዳሜ እንኩዋን፤ ላሊበላና ብሉናይል፤ ዞብልና ራንዴቩ ይቅሩብን። ቅዳሜ ማታ፤ ሂሩት ጋር እንገናኝ።

እኛው ነን። ከቶሮንቶ። ነሀሴ፡ 2005/2013።

የኛ ነገር፡ ከኔ ማዕዘን፡ ክፍል 13

በብርሀኑ ተበሳጨሁ፤ በሰማያዊ ተጽናናሁ፡ በአንድነት ደግሞ ተስፋ አደረግሁ

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=6908

posted by Tseday Getachew

 

የደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣን በቁጥጥር ስር ዋለ

ethiowaga.gif

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

ህወሓት በሁለት ቡድኖች መከፈሉ ይታወቃል። የደህንነት ሓላፊዎችም እንዲሁ በሁለት የተከፈሉ ናቸው። ሁለቱ የደህንነት ሓላፊዎች አቶ ጌታቸው አሰፋና አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ናቸው። በሁለቱም ከፍተኛ ጠብ አለ። አቶ ጌታቸው የነ አርከበ ቡድን ሲሆን አቶ ወልደስላሴ ግን የነ አባይ ወልዱ ሁኖ የወይዘሮ አዜብ መስፍን የቀኝ እጅ ነው።

ሁለቱም የደህንነት ተጠሪዎች በደም የሚፈላለጉ ናቸው። ባለፈው የህወሓት ጉባኤ አቶ ወልደስላሴ ለማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ተጠቁሞ አቶ ጌታቸው ጠንከር ያለ ትችት በማቅረቡ ሳይሳካለት ቀርተዋል። መለስ በህይወት እያለ (በአዜብ ምክር መሰረት) አቶ ጌታቸውን በአቶ ወልደስላሴ ለመተካት አቅዶ ነበር (ሞት ቀደመው እንጂ)።

አቶ ጌታቸው ለመለስ ከማይታዘዙ የህወሓት መሪዎች አንዱና ዋነኛው ነው። ከመለስ ጋር በብዙ ነጥቦች ላይ አይስማሙም፤ የተባለውን ሁሉ የሚሰማ አይደለም። ጠንካራ ነው። ከሙስና የፀዳ የህወሓት ባለስልጣን አቶ ጌታቸው አሰፋ ነው።

የትግራይ ቡድን የአዲስ አበባውን ለማሸነፍ በመለስ ራእይ ስም ከህዝብ መነጠል ችላል። የአዲስ አበባው ደግሞ በሙስና ሰበብ የትግራይ ቡድኑን እያሰረ ይገኛል።

ዛሬ የኢህአዴጉ ሚድያ ‘ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት’ የሃገር ውስጥ የደህንነት መምሪያ ሃላፊው አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነግሮናል። ጥሩ መጠላለፍ መሆኑ ነው። አቶ ወልደስላሴ የነ አቶ ገብረዋህድ ጓደኛ ነው። አቶ ወልደስላሴ ከታሰረ ወይዘሮ አዜብ መስፍንስ?

ለማንኛውም ቸር ያሰማን!

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=6903

posted by Tseday Getachew

ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ

  የETvው ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ ድብደባ እንደደረሰበት ሰማሁ፤ አዘንኩም። አንድ የዘነጋነው ነገር አለ። እውነት ነው፣ የገዢው ፓርቲ ተግባራት አንደግፍም። ገዢው ፓርቲ ስለማንደግፍ በመ

  ንግስት መስርያቤቶች ተቀጥረን አንሰራም ማለት ግን አይደለም። ልክ ነው፤ ኢቲቪ የመንግስት ሚድያ ሳይሆን የገዢው ፓርቲ የፕሮፓጋንዳ መሳርያ ነው።

  ብዙዎቻችን ድሆች ነን። ስራ እንፈልጋለን። የእንጀራ ጉዳይ ሁኖ በመንግስት ቢሮዎች እንሰራለን። በመንግስት ስንቀጠር መንግስትን ስለምንወድ ወይ ስለማንወድ አይደለም። ምግብ ስለሚያስፈልገን ነው። ምግብ ለማግኘት ሳንቲም ያስፈል…ጋል። ሳንቲም ለማግኘት ስራ ያስፈልጋል። የመንግስት ቢሮዎች ደግሞ ለብዙዎቻችን የስራ ምንጮች ናቸው።

  በመንግስት የተቀጠረ ሁሉ ገዢው ፓርቲ ይደግፋል ማለት አይደለም፤ ይቃወማል ማለትም አይደለም። የሚፈልገውን ገንዘብ ለማግኘት ግን እነሱ (ቀጣሪዎቹ) የፈለጉትን ነገር ወይ ስራ እንዲሰራ ግድ ይላል። የታዘዘውን ካላደረገ የሚፈልገውን አያገኝም። የሚፈልገውን ካላገኘ መኖር አይችልም። ስለዚህ የመንግስት ስራ የህይወት ጉዳይ ነው።

  ጋዜጠኛ ተመስገን የታዘዘውን ስላደረገ (የተፃፈለትን ስላነበበ) የድብደባ ሰለባ መሆን አልነበረበትም። የመንግስት ሰራተኞች ኮ ሓላፊዎች አሏቸው። የስራ ዕድገትና የደመወዝ ጭማሪ ለማግኘት የአለቆቻቸው ትእዛዝ ማክበር አለባቸው። ስለዚህ በመንግስት ሰራተኛ ላይ ጣት መቀሰር የመንግስት ሰራተኞች ሁኔታ ካለመረዳት የሚመነጭ ይመስለኛል።

  ስለዚህ ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች (እንደሚናገሩት ወይ እንደሚሰሩት) የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች አይደሉም። ደሞ … የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ቢሆኑስ? ኢህአዴግን የመደገፍ መብት የላቸውምን? የመንግስት ሰራተኞች እንደማንኛውም ዜጋ የፈለጉትን ድርጅት የመደገፍና የመቃወም መብት አላቸው።

  የምንታገለው ማንም ሰው በየፍላጎቱና በየምርጫው እንዲኖር እንጂ ከኛ ጋር ተመሳሳይ አመለካከት እንዲኖረው ለማስገደድ አይደለም።

  ስለዚህ በጋዜጠኛ ተመስገን በየነ ላይ የደረሰ ጥቃት እቃወማለሁ።

  It is so!!!See more

  posted by Tseday Getachew

ፓሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርን ነገ ሊያነጋግር ነው

ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ፓሊስ የፓርቲውን አመራሮች በመጥራት ለነገ ሊያነጋግራቸው ቀጠሮ መያዙን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ፡፡

ፓርቲው በበኩሉ ሊካሄድ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ በምንም አስገዳጅ ሁኔታ ሊሰርዝ እንደማይችል በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፓርቲው አመራሮች ተናግረዋል፡፡

ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ከሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ፀሐፊን፣ ሊቀመንበሩንና የሰልፍ አስተባባሪዎችን ለማነጋገር ጥሪ እንዳቀረበላቸው ታውቋል፡፡

በፀጥታ ዙሪያ ልናነጋግራችሁ እንፈልጋለን የሚለው የፖሊስ መጥሪያ ፓርቲው የእሁዱን ስብሰባ እንዲሰርዝ ለማግባባት ያለመ እንደሆነ ታውቋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ፓርቲያቸው የእሁዱን ስብሰባ ለማካሄድ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ እንደሆነ ተናግረው፤ ምንም አስገዳጅ ሁኔታ ከያዙት አቋም እንደማያስቆማቸው ለኢሳት ተናግረዋል፡፡
በታሪክ፣ በሞራልም ሆነ በህግ ተጠያቂ የሚያስደርገን ነገር ስለሌለ ሰላማዊ ሰልፉ የማይቀር መሆኑን የፓርቲው አመራር ተናግረዋል፡፡

በትላንትናው እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማህበራት ፍቃድ ጽ/ቤት የፓርቲውን ሰልፍ ህገወጥ ነው ማለቱን አስመልክቶ የተጠየቁት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ‹ሕጋዊ ወይም ህገ ወጥ› የሚባል ሰልፍ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡

የፓርቲው የሰልፍ አስተባባሪ ዝግጅት ክፍል ለእሁድ ሰልፍ የሚያደርገው ዝግጅት ከገዥው ፓርቲ የተለያየ ወከባ እየደረሰበት እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

መብራት በተደጋጋሚ የመጥፋት ተግባርና በመኪና ቅስቀሳ ለማድረግ የተደረገ እንቅስቃሴ በፀጥታ ሀይሎች ጫና እየተደረገበት እንደሆነ ፓርቲው አስታውቋል፡፡

የኢህአዴግ አባላት ቤት ለቤት በመሄድ ህዝቡ ለእሁድ የሀይማኖቶች ጉባኤ ሰልፍ እንዲወጣ ቅስቀሳ ማድረግ ላይ እንደሚገኙ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

መንግስት እያስተባበረ የሚገኘው የሀይማኖቶች ጉባኤ ሰልፍ ህዝቡ አክራሪነትን እና ጽንፈኝነትን ለማውገዝ በሚል የተጠራ ቢሆንም እየተካሄደ ያለውን የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ሌላ አቅጣጫ ለማስያዝ ያለመ እንደሆነ የተለያዩ አካላት በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

ሁለት ቀን ብቻ የቀረው የእሁዱ የመንግስትና የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ በሀገሪቱ የፖለቲካ አካሄድ ከብዙ ዓመታት በኋላ ያጋጠመ ክስተት ተደርጎ ታይቷል፡፡

ESAT

posted by Tseday Getachew

ኢቲቪው ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ ተደበደበ

በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ዜናዎችንና መንግስታዊ መግለጫዎችን በማንበብ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ መደብደቡን ጓደኛው ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ አረጋገጠ። ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ “ኤዲቶሪያል ፖሊሲና ዜና አንባቢ ለየቅል ናቸው – ጥቂት ስለ ተመስገን በየነ ጉዳይ” በሚል በፌስቡክ ባሰራጨው መግለጫ የጋዜጠኛውን መደብደብ ማረጋገጡን ገልጾ መደብደቡን ግን አውግዟል።

ጽሑፉ ለግንዛቤ እንዲረዳችሁ በሚል ዘ-ሐበሻ እንደወረደ እንዲህ አቅርባዋለች፦

ኤዲቶሪያል ፖሊሲና ዜና አንባቢ ለየቅል ናቸው –
ጥቂት ነገር ስለ ተመስገን በየነ ጉዳይ

(ከደመቀ ከበደ)

ከትናንት በስቲያ አንድ ወዳጄ ‹‹ተመስገን በየነ ተደበደበ የተባለው እውነት ነወይ›› ሲል ኢንቦክስ አደረገኝ፡፡ ላጣራና እነግርሀለሁ ብዬው ተለያየን፡፡

****** **** ***** *****
ተመስገንን በቅርበት አውቀዋለሁ፡፡ በጣም ሰላምተኛ፣ ትሁትና ስራውን አክባሪ ነው፡፡ ከውድነህ ክፍሌ ጋር በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ላይ የአየር ሰአት ወስደው ይሰሩ በነበረበትና እኔም ከመልቀቄ በፊት ወደ ስቱዲዮ በመጣ ቁጥር የበዛ ትህትናውን እየለመድኩት መጣሁ፡፡ ከዚያ በኋላም ሜሮን ጌትነት፣ አንሙት አብርሀም፣ እሱ /ተመስገን/ እና ሌሎች አምባሳደር ለሆኑለት የልመና ማስወገድ ጉዳይ የተቻለውን ሲያደርግ በዘገባ ጉዳይ ብዙ ተረዳድተናል፡፡ በቃ ስራውን ያከብራል፤ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈፀም ትጉህና አርአያ ነው – አሁንም ከትህትና ጋር፡፡

ሰሞኑን ስለ እሱ የሰማሁትን በሁለት መልኩ ለማጣራት ጣርኩ፡፡ አንደኛው ከእሱ ከራሱ እና ከባለቤቱ /የቀድሞ ባልደረባዬ እምርታ አስፋው / ጋር ደወልኩ፡፡ የሁለቱም ስልኮች ኦፍ ናቸው በተደጋጋሚ ብሞክርም፡፡ / እስካሁን ድረስ/

ሁለተኛው ከቅርብ ወዳጆቼ እውነቱን ለማጣራት ደወልኩ፤ /ከባለቤቱ ወዳጆችና ከ‹‹አምባሳደርነት›› ወዳጆቹ ማለት ነው፡፡ ከላይ የጠቀስኳቸው ናቸው/
‹‹ጉዳት መድረሱንና ህክምና በመከታተል ላይ›› መሆኑን ነገሩኝ፡፡
‹‹ማን እና ለምን›› ለሚለው ግን መልስ አልነበራቸውም፡፡ ሊኖራቸውም አይችልም፡፡

ከተደጋጋሚ ሙከራዬ በኋላ የባለቤቱ /ከደቂቀቃወች በፈት/ እምርታ ስልክ ጠራ – አነሳችው፡፡
‹‹አሁን በመልካም ጤነነት ላይ ይገኛል፡፡ ትንሽ ቆይተህ ደውልለትና ራሱን አናግረው፤ አሁን ደክሞት ሰለተኛ ነው እንጅ እየተሸለው ነው፡፡›› አለችኝ፡፡
‹‹ምክንያቱ ግን ምንድን ነው›› ስል ደገምኩ ጥያቄዬን፡፡
‹‹አላወቅንም፤ ጉዳዩን ፖሊስ ይዞታል፡፡ ከተጣራ በኋላ እንነግርሃለን›› ብላኝ ‹‹እግዜር ይማረው ብዬ›› ተለያየን፡፡

የሆነውን እስኪ ከሰብአዊነት ብቻ እየመዘንን ‹‹እየተወሩ ያሉ›› ምክንያቶችን እንይ፡፡ ሰብአዊነትን ሰው ከመሆን ጋር ብቻ ሚዛናችን ነው!!

‹‹ተመስገን የተደበደበው በኢቴቪ ዜና የተነሳ ነው›› – እንበል፡፡ ‹‹ማን ደበደበው›› የሚለውን ማጣራቱ ለኔ ፅሁፍ ጠቃሚ አይደለምና ብዙ አልዘላብድም፡፡ ግን ‹‹በኢቴቪ ዜና የተቆጡና የተበሳጩ አካላት ወይም ግለሰቦች ነናቸወው ከተባለ ይሀህ መታየት አለበት፡፡

በሚዲያ ህግ አንድ የሚዲያ ተቋም የሚተዳደረው ‹‹በኤዲቶሪያል ፖሊሲው›› ነው፡፡ የሚዲያ ህገ መንግስት ይባላል፡፡ ይህ ‹‹ኤዲቶሪያል›› እንደየ ሚዲያው ፍላጎት፣ እንደየ ሚዲያው ማሰራጫ አገር፣ እንደየሚዲያው ገዥዎች እሳቤና እውቀት የሚወሰን ነው፡፡ እንደኛ አገር ባሉ ታዳጊ አገራት የሚዲያዎች ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ከአገሪቱ ህገ – መንግስት ጋር የተቆራኜ ነው፡፡ የመንግስት ጣልቃ ገብነት ይበዛበታል፡፡ ኢቴቪም ከዚህ የወጣ እንዳልሆነ መንገር ለቀባሪ ማርዳት ይሆናል ፡፡

ታዲያ በማንኛውም ሚዲያ ተቀጥሮ የሚሰራ ሁሉ / ይህ የግል ሚዲያዎችንም ይጨምራል/ ኤዲቶሪያሉን አክብረው የመስራት ግዴታ አለባቸው፡፡ በኤዲቶሪያሉ ያልተስማማ መልቀቅ ብቻ ነው ምርጫው፡፡ ጋዜጠኞች የቤቱ ኤዲቶሪያል ፈፃሚ ሲሆኑ አለቆች ደግሞ አስፈፃሚ ናቸው፡፡
ወደ ዜና አንባቢዎች ስንመጣ ደግሞ፤ ዜና አንባቢዎች የተሰፃቻን ዜናች ያላንዳች መነካካት የሚያነቡ ናቸው – ፖስተኛ ማለት ነው ዜና አንባቢነት፡፡ የተሰጠህን መቀበል ብቻ!!

የሙሉ ጊዜ ዜና አንባቢ / የሚዲያው ቋሚ ተቀጣሪ/ እና የፍሪላንስ ዜና አንባቢዎች አሉ፡፡

ተመስገን በየነ የፍሪላንስ ዜና አንባቢ ነው፡፡ የኢቴቪ ጋዜጠኞች የሰሩትን ዘገባ ከማንበብ የዘለለ ምንም ሚና የሌለው፡፡ እንደ ጋዜጠኛ ወጥቶ መረጃ ቃርሞ ወይ ኤዲት አድርጎ የማቅረብ አንዳች ተልዕኮ የለውም፡፡
ይህን ነው ‹‹ለምን›› እንድል ያደረገኝም ፤ ብዬም ወደእናንተ ያስፃፈኝም ‹‹ይኸወ የአንባቢነት እንጅ የመረጃ ቃራሚነት ወይም ሃያሲነት›› ሚና የሌለው መሆኑ ነው፡፡

አሁንም ‹‹ተደባዳቢው›› አካል ማንም ሆነ ምንም ድርጊቱ ትክክል ነው ብዬ አላምንም፡፡ ‹‹ድብደባ›› በሰው ልጅ ላይ ተገቢ አለመሆኑን የማልደግፈው ሰው በመሆኔ ብቻ ነው፡፡ ምናልባት ያነበባቸው ዜናዎች ያስቆጡት ‹‹አካል›› ወይም ‹‹ግለሰብ›. የፈፀመው ከሆነ ለኔ ‹‹አህያውን ፈርቶ ዳውላውን›› ይሆንብኛል፡፡ አሁንም እደግመዋለሁ ፤ ተመስገን በዜና አንባቢነቱ ከሆነ የተደበደበው ነውር ነው – ፖስተኛ ሳይሆን ፖስታውን የፃፈው ነው መጠየቅ ካለበት መጠየቅ ያለበት፡፡ / መደብደብ ያለበት አላልኩም/

እህስ ሌላ ጉዳይ አስደብድቦት ከሆነስ ብለን እንጨምር፤

ዘረፋ የሚፈፅሙ ማጅራት መቺዎች ከሆኑም ‹‹ህግና እግዜር›› መፍትሄ ይሰጡት ዘንድ እመኝለታለሁ፡፡

በማንኛውም ምክንያት ‹‹በቂም ተነሳስቶ›› ተፈፅሞ ከሆነም ‹‹ከድብድብና ስድብ›› ወደ ቅርርብና ፍቅር መምጣት ይቻላል ባይ ነኝ፡፡ በእኔ እምነት ሰውን ከማያግባባው የሚያግባባው ነገር ይበልጣል፡፡ ፍቅር ያሸንፋል!!

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=6888

posted by Tseday Getachew

 

የኢሕአዴግ ወታደራዊ ትጥቅ ማምረቻ ፋብሪካ ተቃጠለ

(ይህን የሚሊተሪ ልብስ የሚያመርተው ፋብሪካ ነው የተቃጠለው)

(ይህን የሚሊተሪ ልብስ የሚያመርተው ፋብሪካ ነው የተቃጠለው)

በመከላከያ ሚኒስትር የትጥቅና ወታደራዊ ልብስ ስፌት ፋብሪካ ህንጻ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ማስታወቃቸውን ኢሳት ራድዮ ዛሬ ዘገበ። የእሳት አደጋ ቃጠሎ በሕንፃው ላይ ጉዳት እንዳደረሰና እንዳወደመ የዘገበው ኢሳት ራድዮ የአደጋውን ምንጭ እያጣራሁ ነው ብሏል።

ከአዳማ ከተማ ወደ ወንጂ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው ወታደራዊ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ በፋብሪካው ላይ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት መድረሱን የዘገበው ራድዮው በ18 ሚሊዮን ብር ወጪ በቅርቡ የተገነባው ፋብሪካው የተለያዩ ወታደራዊ ዩኒፎርሞችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ሲሆን የደረሰው አደጋ መንስኤ ሊታወቅ አልቻለም ብሏል።

እንደ ራድዮው ዘገባ ከሆነ በፋብሪካው ላይ የደረሰውን ቃጠሎ ለማጥፋት ከአዳማ ከተማ የእሳት ማጥፊያ ባለመኖሩ ደብረ ዘይት ከሚገኘው አየር ሀይል እሳት ማጥፊያ እስከሚደርስ ድረስ የተነሳውን እሳት ማጥፋት አለመቻሉን የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ ለአንድ ሰዓት ያህል በቆየው የእሳት አደጋ ግምታቸው ከፍተኛ የሆነ ማሽኖች ላይ ጉዳት እንደደረሰ የታወቀ ሲሆን ከአራት ቀናት በፊት መንግስት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የገዛቸው ማሽኖች በፋብሪካው ገብተው እንደነበረ ታውቋል ሲል ኢሳት ራድዮ ዘገባውን አጠናቋል።

ከአደጋው በስተጀርባ ሊደበቅ የተፈለገ የሙስና ወንጀል ይኖር ይሆን?

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=6881

posted by Tseday Getachew

እኛ “መንግስት” (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

 

Journalist Temasegan Dasaleg

“በእያንዳንዱም መንግስት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ስለ ሆነ መንግስት አንዱን ነገድ አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይደለም፡፡ አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡ ለአንዱ ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግስት የሚገባ ሥራው አይደለም” ይህንን መግቢያ የወሰድኩት በልዑል የኢትዮጵያ መንግስት አልጋ ወራሽ ተፈሪመኮንን ማተሚያ ቤት የካቲት 1 ቀን 1917 ዓ.ም ከታተመው የነጋ ድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ‹‹መንግስትና የሕዝብ አስተዳደር›› መፅሀፍ ነው፤ ዛሬም ያለንበትን ዘመን ይዋጃልና፤ በተለይ ስለ‹‹ነገድ›› የተጠቀሰውን አርቀን ሰቅለን፣ ‹‹ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት›› የምትለዋን ሀረግ በወጉ ካጤንናት ለጊዜያችን በልክ የተሰፋች መሆኗን ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡

እናም የስርዓቱን የአስተዳደር ዘይቤ ያለፍርሃት አደባባይ ካዋልነው የቀድሞ ገዥዎቻችን የተጓዙበትን ጎዳና እየተከተለ መሆኑን ለመተንተን የምሁራንን ጥናት መጠበቅ ግድ አይለም፤ ምክንያቱም ለዓመታት የተመለከትነው እውነታ የሚነግረን የአመራሩን እና በዙሪያው የሠፈሩ የጥቅም ተጋሪ ግለሰቦችን ብልፅግና ታሳቢ ያደረገ፣ ከታግሎ መጣል ህግ የተቀዳ፣ የራስ ሀገርንና የራስ ሕዝብን በምርኮ ያስገበረ ፖለቲካ መንበሩን ነው፤ ገብር፣ ገብር፣ ገብር…!!

ዛሬ መንገድ ዳር ረሀብ አዙሮ የጣለው ወንድምህ ስቃይ እንደ ጥላ የሚከተልህ፤ ህፃናት በትምህርት ገበታቸው ላይ በጠኔ ተሸንፈው መመልከቱ የሰርክ አሳዛኝ ክስተት የሆነብህ ከሰው ሰራሽ ችጋር፣ ከሰው ሰራሽ የቀዬ ፍንቀላ፣ ከሰው ሰራሽ እርዛት… የመነጨ መርገምት እንጂ የሰማይ ቁጣ አይምሰልህ፤ እመነኝ መለስም ሆነ ተተኪዎቹ ስኬት አድርገው የሚሰብኩትም ይህንን ነው፤ ‹ሀገር አቀናን!› የሚሉትም ይህንን ነው፤ ሰሞኑን የሚያሰለቹህ ተረኛ ምሁራንም ‹‹ትምህርትና ጤናን በተመለከተ መለስ ‹እልል› የሚያስብል ሥራ ሰርቷል›› የሚሉህ ጣራና ግድግዳ እየቆጠሩ ነው፤ ይህ አይነቱ መደዴ ሙገሳም ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን ሪፖርት ለማዘጋጀት ከሚረዳ ቁጥር የዘለለ አበርክቶ አንደማይኖረው አትዘንጋ፡፡

እውነት እውነት እልሀለሁ፡- ይህ የሆነበት ብቸኛው ምክንያት መንግስት በስልጣን ላይ ስለሚቆይበትመንገድ ብቻ መጨነቅን ግዴታው በማድረጉ ነው፤ ይህንን ለመረዳትም እያገባደድን ባለው ክረምት የመንግስት ትኩረት በምን ላይ አንደሆነ የሚያሳይ ማስረጃን ጨርፌ ላሳይህ፡፡

ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የእስልምና እምነት ተከታዮች መንግስት በሃይማኖታቸው ጣልቃ መግባቱን በመቃወም እና የታሰሩ ኮሚቴዎቻቸው እንዲፈቱ በመጠየቅ እያደረጉ ያለውን ትግል በሰላማዊ መንገድ አጠንክረው ሲቀጥሉ፤በተቃራኒው ‹‹ፀጥታ አስከባሪዎች›› አንዳንዴ በጥይት፣ አንዳንዴ በአስለቃሽ ጢስ፣ አንዳንዴ በማጋዝ…ምላሽ ሲሰጡ…

በርግጥ መንግስት ከኃይል እርምጃው በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎችን (በምን አግባብቶ ወይም በምን አስፈራርቶ እንደሆነ ባይታወቅም) ወደ አደባባይ በማስወጣት መብት ጠያቂዎቹን ከ‹‹አክራሪ››ነት እና ‹‹ወሃቢዝም››ነት ጋር አያይዘው የውግዘት በረዶ እንዲያዘንቡባቸው እያደረገ ነው፡፡ ኢቲቪም ይህንን ኩነት እየተከታተለ ማራገቡን ቀጥሎበታል፤ ‹‹የቲፒ ከተማ ነዋሪዎች ‹አክራሪዎችን አወገዙ››፤ ‹‹በደቡብ ወሎ ኩታ በር ዞን አንድነት ፓርቲ ህገ-ወጥ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰልፍ ተካሄደ››፤ ‹‹የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ‹የሼሁ ግድያ ድራማ አይደለም› አሉ፣ ‹የሼህ ኑሩ ኢልም ነው፣ የአሸባሪዎች ብር ነውም›ብለዋል››፤‹‹የመርሀቤቴ ነዋሪዎች ፅንፈኞችን በመቃወም የአቋም መግለጫ አወጡ››፤…

ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- አንድነት ፓርቲ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የ‹‹ፀረ-ሽብር ሕጉ›› እንዲሰረዝና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ እና የአዳራሽ ስብሰባዎችን እያካሄደ ነው፤ መንግስትም አንዳንዴ የአፀፋ የድጋፍ ሰልፍ ሲያካሄድ፤አንዳንዴ የአዳራሽ ስብሰባዎች ከመካሄዳቸው አስቀድሞ ‹መጋኛ› ሲሆንባቸው፤ አንዳንዴም የአስተባባሪዎቹን መኪና ጎማ ሲያፈነዳ፤ አንዳንዴም አዳራሽ ከልክሎ ሲያደናቅፋቸው… መዋሉ ፋታ የነሳው ይመስላል፤ በወላይታ የተጠራውን የአዳራሽ ስብሰባም ‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ የትውልድ ቦታ እንዴት ተደርጎ!›› ያሉ ካድሬዎች የአንድነት ሰዎችን አዋክበው ስብሰባውን አክሽፈዋል፤

ክረምቱእንዲህእየተገባደደነው፡-ገዥው ፓርቲ ‹የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ አንደኛ ሙት ዓመት አከብራለሁ› በሚል መላ ኢትዮጵያን ችግኝ መትከያ፣ መላ ዜጎቿን ደግሞ ወደ አርሶ አደርነት በአስማት የቀየራቸው አስመስሏቸዋል፤ቴሊቪዥንና ራዲዮንም አስፈላጊነታቸው በየመንደሩ ችግኝ መተከሉን እየተከታተሉ መዘገብ ብቻ እስኪመስል ድረስ እንዲህ ሲሉ ጀምበር ወጥታ ትጠልቃለች፡- ‹‹የላይ አርማጮህ ነዋሪዎች ችግኝ ተከሉ››፣ ‹‹በመቀሌ ከተማ ‹ዘመቻ መለስ› በሚል የችግኝ ተከላ ተካሄደ››፣ ‹‹አቃቂ ኮረብታ ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር ችግኝ በኦሮሚያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ተተከለ፤ ቦታውም ‹መለስዜናዊ ኮረብታ› ተብሎ ተሰይሟል››፣ ‹‹በምዕራብ ሀረርጌ አስራ ሰባት ሚሊዮን፣ በወልበራ አስራ አራት ሚሊዮን ችግኝተ ተክሏል››፣ ‹‹በመንዝ ላሎ ወረዳ ተቆጥሮ የማያልቅ ችግኝ ተከላ ተደርጓል››፣ ‹‹የብአዴን አመራርና ካድሬ በባህር ዳር ከተማ በቢሊዮን የሚቆጠር ችግኝ ተከሉ፤ በፕሮግራሙ ላይ ጓድ አዲሱ ለገሰ ‹ችግኝ የምንተክለው አገሪቱ በአረንጓዴው ልማት በአለማችን ማግኘት የሚገባትን ቦታ እንድታገኝ ለማድረግ ነው› ሲል፣ ጓድ በረከት ስምዖን ደግሞ ‹ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአለማችን በአንድ ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ችግኝ እየተከሉ ያሉባት ብቸኛ ሀገር ናት› ብሏል››፤‹‹ዝክረ መለስ 1ኛ ዓመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ ከሐምሌ አስራ አምስት ቀን ጀምሮ ሁሉም ቀበሌዎች በስሙ ‹ፓርክ› ሰይመው ችግኝ ተከላ እያካሄዱ›› መሆኑን ደግሞ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ መግለፁን የአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ ዘግቧል፤ ‹‹በወልቂጤ ከተማ በተደረገው ችግኝ ተከላ ላይም አንዲት ወጣት ‹መለስ ለሴቶች የተለየ አመለካከት ነበረው›› ማለቷም በዘገባው ተጠቅሷል፤ …ማን ነበር የመለስ ራዕይ ‹ችግኝ መትከል ነው› ያለው? …ኢህአዴግ ይሆን?

ከዚሁ ጎን ለጎን (አሁንም ሙት ዓመቱን ለማሰብ) በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የእግር ጉዞ ተደርጓል፣ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓትም ተካሄዷል፤መነሻውን መቀሌ፣ መድረሻውን አዲስ አበባ ያደረገ ‹‹የመለስ ቱር አረንጓዴ ልማት›› የብስክሌት ውድድርም ሊጠናቀቅ ገና አንድ ሳምንት ይቀረዋል፤ በብሄራዊና ሀይማኖታዊ በዓላት ቀንለሃያ አንድ ጊዜ ይሰማ የነበረው የመድፍ ድምፅም፣ የመለስን አንደኛ ሙት ዓመት ለማብሰር ተተኩሷል፤ …በግድ አልቅሱ፣ በግድ ተዝካር አውጡ፣ በግድ ችግኝ ትከሉ፣ በግድ ተወያዩ፣ በግድ አደባባይ ውጡ፣ በግድ የፎቶ ግራፍ ኤግዚቢሽን ጎብኙ፣ በግድ.. ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ እና የትምህርት ሚኒስትሩ ሽፈራው ሽጉጤ ከአንድ ሺህ ሰባት መቶ በላይ ለሚሆኑ የዩኒቨርስቲ ከፍተኛ መምህራን ‹የአቅም ግንባታ ስልጠና› እየሰጡ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምሁራኖቹን ማሰልጠን ያስፈለገበት ምክንያት ‹‹ብቃት ያለው ምርጥ የተማረ ኃይል ለማፍራት››መሆኑን ቢነግርህ አይግረምህ፤ ይህ ኢትዮጵያ ነውና የዐዋቂነት ማረጋገጫው መማር፣ ማንበብ፣ መመራመር… አይደለም፣ የፖለቲካውን ኃይል መያዝ እንጂ፤ ‹ስልጣን ላለው ሁሉምሚስጥረ-ጥበብይገለፅለታል› እንዲል አብዮታዊ ዲሞክራሲ መለስ ዜናዊም በሁሉም መስክ ‹አስተማሪ› ነበር፤ የህግ ባለሙያዎችን ሰብስቦ የሀገሪቱን ወንጀለኛ መቅጫ ህግ ትርጓሜ ሲተነትን ደጋግመህ ሰምተኸዋል፤ በቀጣዩ ቀን ደግሞ ለግብርና ባለሙያዎች ከውሃ ማቆር እስከ በላብራቶሪ የሚዳቀል ምርጥ ዘር ድረስ ባሉጉዳዮችዙሪያ የሁለት ቀን ማብራሪያ መስጠቱን ታስታውሳለህ፤ እመነኝ ተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህንኑ ነው እያደረገ ያለው፤ የሆነ ሆኖ ኃ/ማርያም ለምሁራኖች ከሙያቸው ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ጭምር በሰጣቸው ስልጠና ላይ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር ‹‹የኢንዱስትሪዎች በበቂ ሁኔታ አለመኖሩ፣ በክፍል ውስጥ የምናስተምረውን ንድፈ ሃሳብ በተግባር ለማሳየት እንቅፋት ሆኖብናል››፤ በርግጥጠቅላይ ሚንስትሩ‹‹መፍትሄ››ያለውን የተናገረው ብዙም ሳይጨነቅ ‹‹እኔ ኢንዱስትሪን ‹ዲፋይን› የማደርገው ግብርናም ኢንዱስትሪ ነው ብዬ ነው››በማለት ነበር፤…ግና!ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል በተጨባጭ አላብራራም፡፡ለምሳሌ ህክምና የሚያጠና ተማሪ በምን መልኩ በሞፈርና ቀንበር የተግባር ልምምድ ማድረግ እንደሚችል፤ወይም ፖለቲካ ሳይንስ የሚያጠና ተማሪ የተግባር ልምምዱን በግብርና ኢንዱስትሪ እንዴት ሊወጣው እንደሚችል? ማለቴ ነው፡፡

ለዓመታት በርካታ ምሁራን ብቃት አልባ ተማሪዎች እንደ ሰማይ ከዋክብት የመብዛታቸው መንስኤን ከትምህርት ፖለሲው ጋር የሚያነፃፅሩበትን ሀቲት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ባገኘው የሀገር መሪነት ስልጣን ገልብጦ በዩንቨርስቲ ቆይታው መምህራኖቹ የነበሩትንም ጭምር ‹‹አቅም አንሷችኋልና-እገነባችኋለሁ›› ሲል ከመስማት የከፋ እንደ ሀገር ክሽፈት የለም (በነገራችን ላይ ከወራት በፊት ለኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በረከት ስምዖን፣ ቴውድሮስ አዳህኖም፣ ሶፍያን አህመድ በአጠቃላይ ሁሉም የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት አንድ ህንዳዊ ፕሮፌሰር በኢህአዴግ ጽ/ቤት ‹‹ልማታዊ መንግስት›› እንዴት ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ሲተነትንላቸው፣ እነርሱም ደብተርና እስክርቢቶ ይዘው በንቃት ሲከታተሉ የቴሌቪዥ ዋና ዜና ሆኖ የቀረበበትን ምክንያት ዛሬም ድረስ ሊገለፅልኝ አልቻለም፤ በተለይም ፕሮፈሰር እንድርያስ እሸቴ ‹‹በቃሉ የፀና…›› በሚል ርዕስ መለስን አስመልክቶ በተዘጋጀ ዶክመንተሪ ፊልም ላይ ‹‹በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ ልማታዊ ስርዓተ መንግስት ‹ዴሞክራሲያዊ ሊሆን ይችላል፤ መሆንም አለበት› ብሎ በአደባባይ የተከራከረው እኔ እስከማውቀው ድረስ መለስ ነበር›› ማለቱን፣ ተተኪዎቹ ፍልስፍናውን ገና እየተማሩት ከመሆኑ አንፃር ስናየውሀገራችን ያለችበት ሁኔታ ጉዞው ወዴት ነው? ያስብላል፡፡ …ከቶስ በተማሪ ፖለቲከኛ የሚተዳደር ሕዝብ ከኢትዮጵያ በቀር ወዴት ይኖራል?)

ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የህዳሴውን ግድብ ከዳር ለማድረስ በቂ ገንዘብ ስላልተገኘ ተደጋጋሚ የቦንድ ሽያጭ እየተካሄደ ነው፤ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞችም በካድሬ ባልደረቦቻቸው ጫና በድጋሚ ቦንድ ለመግዛት መወሰናቸው ተሰምቷል፤ በርግጥ ከፍተኛ የኢህአዴግ የአመራር አባላት በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቦንድ እንዲገዙ ለመቀስቀስ የአዘጋጇቸው ስብሰባዎች ‹‹ቅድሚያ የዜጎች መብት ይከበር›› ባሉ የሀገራችን ልጆች መክሸፉም የክረምቱ የመንግስት ዋና ሥራ ነው፤ ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- በነቢብ የኢትዮጵያ፣ በገቢር የገዥው ፓርቲ የግል ንብረት የሆነው ቴሌቪዥን ጣቢያ ባለፉት ሶስት ወር ብቻ ከሃያ በላይ ‹‹ዶክመንተሪ ፊልም›› አሳይቷል (ገና ይቀጥላልም) በርዕሳቸው እንደሚከተለው እንዘርዝራቸው፡- ‹‹ኢፍቲን›› በሶማሊያ ላይ የሚያጠነጥን፣ ‹‹የጥቁር ህዝቦች ልሳን (መለስ በአፍሪካ)››፣ ‹‹ከፓን አፍሪካ እስከ አፍሪካ ህዳሴ›› የጠቅላይ ሚንስትር መለስን ህይወት የሚዳስስ፣ ‹‹ዘመነ አፍሪካ››፣ ‹‹የአፍሪካ ልሳን-መለስ››፣ ‹‹መለስ ማን ነው?››፣ ‹‹ሀገሬ-ቤቴ››፣ ‹‹ባለራዕዮቹ›› ስራ ፈጠራ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ደውል›› እና ‹‹ደውል 2›› ህገወጥ-የሰዎች ዝውውርን በተመለከተ (በተለያያ ጊዜ የተላለፉ)፣ ‹‹የዲያስፖራ የልማት እንቅስቃሴ››፣ የካርታ ስራ ድርጅትን በተመለከተ፣ ‹‹የጥልቅ አስተሳሰብ ባለቤት›› በፕ/ር እንድርያስ እሸቴ ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን፣ ምድር ባቡር ኮርፕሬሽንን በተመለከተ፣ ‹‹ያልተለመደ ጉብኝት›› የአዲስ አበባ አስተዳደር የአምስት ዓመት የመንግስት ግንባታዎችን በተመለከተ፣ ‹‹ሼህ ኑር ለምን ሞቱ?›› የደሴውን ሼህ ኑር ይማምን ግድያ በተመለከተ፣ ‹‹የተስፋ ስንቅ››፣‹‹በቃሉ የፀና›› በድህረ መለስ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ያልተጠኑ ገፆች›› በመለስ ዜናዊ ህይወት ዙሪያ (በርግጥ በዚህ ፊልም እህቱ ጠላ፣ ወንድሙ አንባሻ በመሸጥ መተዳደራቸውን በምስልም በድምፅም ማቅረቡ ምን የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ እንደሆነ ለማወቅ ግራ ያጋባል፤ …ምናልባት እንዲያ እየዘረፈ ለቤተሰቦቹ ‹ሶልዲን› የማይሰጥ ‹ቆነቋና› ነበር ለማለት ይሆን? ወይስ ለአዜብ መስፍን ‹የወር ቀለባችንን እንቸገራለን› የአንድ ሰሞን ማስተዛዘኛ ምስክር ፍለጋ ነው?

በጥቅሉ ለኢህአዴግ ሕዝብን የማስተዳደር፣ ሀገርን የመምራት መገለጫ ይህ ነው፤ ሌላ አይደለም፤ ግና! ለዘመናት ያልተመለሱ ጥያቄዎቻችን ዛሬም መጮኻቸውን አላቋረጡምና እነሆ እንዲህ ቀጥለዋል፡- ሀገር ማስተዳደር ‹መለስ ጀግና ነበር› እያሉ ማሰልቸት ነውን? የመንግስትስ ስራ (ግዴታ) ምንድር ነው? ሀገሪቱን ‹‹መለስ-ፓርክ›› ወደሚል ስያሜ ከመቀየራችሁ በፊት፣ ለጤፍ ዋጋ አለቅጥ መናር ምክንያቱን ስለምን መመርመር ተሳናቸው? ሀገሪቱን በ‹አራጣ› እንደያዘ ስግብግብ ነጋዴ በሚሊዮኖች ህይወት ላይ የማይሞላ ‹ሳፋ› ደቅኖ አዋጣ፣ ግዛ፣ ክፈል፣ ገብር… እያለ የሚያስጨንቀው ማን ነው? ስለመለስ ‹የሃሳብ ምጡቅነት› መስካሪ ምሁራኖቻችን ለጎዳና ኑሮ የተዳረጉ ኢትዮጵያውያን ስንት ሚሊዮን እንደደረሱ እና እልፍ አላፍት ታዳጊዎቻችን በሴተኛ አዳሪነት እንደተሰማሩ የምትነግሩን መቼ ነው?እንዲህ የመሆኑ ምክንያትስ በማን ይሆን? ‹የሁለት ዲጂቱ›ዕድገት ሸክምን የማለዘብ አቅም ከሌለውፋይዳው ምንድር ነው? ‹ሳቅ ትዝታ› ስለሆነባቸው ጎጆዎች ለምን አትነግሩንም? መለስ ‹ያለመለማት› ኢትዮጵያ ወዴት ትሆን? ‹ፖለቲካ› ማለትስ ይህ ነውን? …ነጋ ድራስ ገ/ህይወት እንዳሉት ‹‹…መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡›› የመተራረሚያው ጊዜም በጣም ያለፈ ይመስለኛል፡፡ አገዛዙን ‹እንደ መንግስት› መቀበሉም እንዲሁ፡፡

http://ecadforum.com/

posted by Tseday Getachew

የሕወሐት ባለስልጣናት የአሜሪካ ቆይታ፤ የከዱ አሉ

 

ከኢየሩሳሌም አርአያ

በአባይ ወልዱ የሚመራውና ሰባት ከፍተኛ የሕወሐት ባለስልጣናት የተካተቱበት ቡድን በአሜሪካ አራት ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ እንደገጠመው በስፍራው የተገኙ ምንጮች አስታወቁ። ቡድኑ በዋሽንግተን ኢትዮጲያ ኤምባሲ በጀመረውና በመቀጠል በላስቬጋስ፣ ሲያትልና ካሊፎርኒያ ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ “አላማ” አድርጎ የያዛቸው ጉዳዮች እንደነበሩ የጠቆሙት ምንጮች፣ እነሱም፥ “የመለስ ፋውንዴሽን፣ የአባይ ግድብና የ40/60 የቤቶች ግንባታ.” ሲሆኑ፣ ለነዚህ ማስፈፀሚያ “ገንዘብ አዋጡ” የሚለው ዋናው ግብ እንደነበር አስረድተዋል። በተለይ ደግሞ « በትግራይ ተወላጁ ዘንድ ሕወሐት የለም፣ ተከፋፍሏል፣ ተዳክሟል፣ ፓርቲው ሰው የለውም፤» የሚለውን እራሱ ቡድኑ በማንሳት ለገዛ ጥያቄው መልስ ሲሰጥ « ሕወሐት አሁንም ሃይል አለው፤ አልተዳከመም» በማለት አድራጊ- ፈጣሪ በመሆን ስልጣኑን በበላይነት ተቆጣጥሮ እንደያዘና ቡድኑ የመጣውም “አይዟችሁ” ለማለት እንደሆነ መገለፁን በቅርብ የተከታተሉት ምንጮች አስታውቀዋል። ቡድኑ በተጨማሪም ፥ « ልማት አልምተናል፤ ትግራይ እየለማ ነው፤ ህዝቡን ተጠቃሚ እያደረገነው ነው» ከማለቱ ባሻገር « በትግራይ ተወላጁ ላይ አደጋ ተደቅኗል፤ የሙስሊሙ፣ የትምክህተኞችና የሽብርተኞች አደገኛ እንቅስቃሴ እያንዣበበ መሆኑን፣…የተደቀነብህን አደጋ ከጎናችን ሆነህ ተከላከል፤ ያለበለዚያ ግን ሊያጠፉህ ነው፤» ሲሉ መናገራቸውን የገለፁት ምንጮች አክለውም፣ « አባላት የሆናችሁ ተወደደም ተጠላ መሬትና መኖሪያ ቤት እንሰጣችኋለን፤ ለዚህም ከእኛ ጎን መሰለፍ አለባችሁ» በማለት ሊሸነግሉ መሞከራቸውን ጠቁመዋል።

ከዋሽንግተን ስብሰባ (ለሁለት ተከፍሎ ነው የተካሄደው) በኋላ ወደ ሶስቱ ከተሞች ተከፋፍለው እንደሄዱ ሲታወቅ፥ ሲያትል አቶ ብርሃነ ማረት፣ እንዲሁም ላስቬስጋስ አባይ ወልዱና ተክለወይኒ አሰፋ መሄዳቸው ታውቋል። በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ የገጠማቸው እነአባይ ስብሰባው ከቀኑ 2፡00 ሰዓት ይጀመራል ተብሎ ከአራት ሰዓት በኋላ ዘግይቶ አመሻሽ ላይ መጀመሩን ምንጮች ገልፀዋል። ስብሰባው ሲጀመር ከላይ የተገለፁትን ጉዳዮች ያደመጠው ተሰብሳቢ ተከታዮቹን ጥያቄ አቀረበ፤ « ዴሞክራሲ አለ ትላላችሁ፣ ነገር ግን ዴሞክራሲ የለም፤ በሃሳብ የሚቃወማችሁን ታስራላችሁ፣ ታንገላታላችሁ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ ታካሂዳላችሁ፤ ከእናንተ የተለየ ሃሳብ ያለውን ትፈራላችሁ፤ ለምንድነው ይህን ሁሉ የምታደርጉት?….በማ.ረ.ት.(ማህበር ረድኤት ትግራይ) በትግራይ ሕዝብ ስም የምትሰበስቡትን ገንዘብ ለአራጣ ብድር እና ለፖለቲካ መጠቀሚያ በመሳሪያነት እያዋላችሁት ነው። ለምን?….ትእምት (ኤፈርት) ማነው ባለቤቱ?..በማን ነው የሚመራው?..ማነው የሚቆጣጠረው?..ለመሆኑ ኦዲት ተደርጎ ያውቃል ወይ?..እነማናቸው እየተጠቀሙበት ያለው?» የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ጥያቄዎች እንደነበሩ ምንጮቹ የጠቆሙ ሲሆን፣ አባይ ወልዱ « እኔ አልመልስም፣ ተ/ወይኒ መልስ ይስጥበት» ቢሉም ነገር ግን ግልፅና አግባብ ያለው ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ወደ ማመናጨቅና ቁጣ ያመሩት ተ/ወይኒ በዚህ ድርጊታቸው በርካታ ተሰብሳቢዎችን እንዳሳዘኑ አስረድተዋል። በዚህ የተበሳጨው ተሰብሳቢ « ጥያቄያችን አልተመለሰም» በማለቱና ሁከትና ያለመደማመጥ በማየሉ ስብሰባው እንዲቋረጥ መደረጉን የጠቆሙት ምንጮች፣ የጥያቄና ተቃውሞው መብዛት ያስደነገጣቸው ባለስልጣናቱ የመረጡት ማምለጫ በላስቬጋስ ተወካያቸው በሆነውና መድረክ ሲመራ በነበረው አቶ ተወልደ በኩል፥ « አዳራሹን የተከራየንበት ሰአት አብቅቷል፤ ስለዚህም ስብሰባው አብቅቷል » በማለት በአስቂኝ ሰበብ መቋረጡን አያይዘው ገልፀዋል። እነአባይ ከአዳራሹ ሲወጡ ቀድሞ ውጭ ሆኖ ይጠብቃቸው በነበረው ተሰብሳቢ ውግዘትና ስድብ እንደደረሰባቸው ያስታወቁት ምንጮች « ሌባ..ሌባ…ሙሰኞች..» የሚሉ ተቃውሞዎች ጎላ ብለው እንደተሰሙ አመልክተዋል።

ስብሰባዎቹን የታዘቡ ወገኖች በሰጡት አስተያየት እንዲህ ብለዋል፤ « በአንድ በኩል ልማት እያካሄድን ነው፤ እያሉና ገንዘብ እየጠየቁ በሌላ በኩል “ትግራዋይ አደጋ ተደቅኖብሃል፣ ከጎናችን ሆነህ ተከላከል፤” ማለት እርስ በርሱ የሚጋጭና ድጋፍ የማግኛ የፖለቲካ የፖለቲካ ቁማር ነው። ያልተጠየቁትን የፓርቲውን ህልውና (ስለ ሕወሐት) አንስቶ መነገሩም አስገራሚና አጠያያቂ ነው።» ሲሉ ትዝብታቸውን የጀመሩት እነዚህ ወገኖች በማያያዝም፥ « እነዚህ ሰባት ባለስልጣናት ወደ አሜሪካ የመጡት ከነዘመዶቻቸው፣ ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ሲሆን፣ ባለስልጣናቱ የመንግስት ወኪሎች እንደመሆናቸው – በማን ገንዝብ ነው የሚንቀሳቀሱት?..የሚለው መጠየቅ አለበት። በሕዝብ ገንዝብ እየተንፈላሰሱ እንደሆነ ግልፅ ነው። የትግራይ ተወላጁን ብቻ ለይተው ስብሰባ የሚጠሩት ለምንድነው?…በእርግጥ ስላሰቡለት ነው?…የሚሉት ሲፈተሹ .መልሱ በጭራሽ አይደለም ነው። አላማቸውና ትኩረት የሰጡት የትግራይ ተወላጁን እየተንከባከቡት እንደሆነና ተጠቃሚ መሆኑን ለማሳየት በመፈለግ፣ እግረ-መንገዳቸውን ከቀሪው ኢትዮጲያዊ ወገኑ ጋር በመነጠል..ድጋፍ ለማግኘትና በውስጣቸው የተፈጠረውን ቀውስ በዚህ በኩል ቀዳዳውን ለመድፈን የሚደረግ የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ ስልት ነው። ..ደግሞስ ሕወሐት “አጋር” ከሚላቸው ብ.አ.ዴ.ን፣ ኦ.ህ.ዴ.ድ.፣ ደቡብ ሕዝቦች ተለይቶ፣ በሕዝብ ገንዘብ ስብሰባ የሚጠራበትና ያሻውን የሚያደርግበት አግባብ ምንድነው?..የሚለው ከዚህ ጋር መታየት ያለብት ነው። ፖለቲካዊ ፍጆታና ማንአለብኝነት በፓርቲው በመነገሱ እንደሆነ ደግሞ ግልፅ ነው።» ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ አሜሪካ ከመጡት ሰባት የሕወሐት ባለስልጣናት መካከል- ማለትም አባይ ወልዱ፣ ብርሃነ ኪ/ማሪያም፣ ተ/ወይኒ አሰፋና ዳንኤል አሰፋ በዋነኛነት ሲጠቀሱ፣ ከሰባቱ ሶስቱ ስብሰባውን ሳያካሂዱ ከቡድኑ ተገንጥለው በአሜሪካ መቅረታቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል። ቤተሰቦቻቸውን ይዘው (ልጆቻቸውን ጭምር) በመምጣት አሜሪካ ጥገኝነት ጠይቀው መቅረትን የመረጡት ባለስልጣናት ውስጥ የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባላት እንዳሉ ያረጋገጡት ምንጮች በቅርቡ ዝርዝሩን ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

ግልጽ ደብዳቤ ለሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት (አማኑኤል ዘሰላም)

 

ለተከበሩ ኢንጂነር ይልቃል፣  ለክቡራን ከፍተኛ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት፣ በቅድሚያ ሰላምታዬ ባላችሁበት ቦታ  ይድረሳችሁ!  ጤና ይስጥልኝ።

ለሰማያዊ ፓርቲ አድናቆት አለኝ። የግራዚያኒ ሃዉልትን በመቃወም ያደረጋችሁት ሰልፍን ተከታትያለሁ።  በብዛት ግን ሰው ያወቃችሁ፣ በአዲስ አበባ በጠራችሁት ሰላማዊ ሰልፍ ነዉ። ያኔ ትልቅ ሥራ ነው የሰራችሁት። አኩርታችሁኛል። ብዙ ደጋፊዎችም በአጭር ጊዜ ዉስጥ አግኝታቹሃል።

ያኔ የጠራችሁትን ሰልፍ አብዛኞቻችን ብንደግፈውም፣ ሌሎች ድርጅቶችን ሳታማክሩ ፣ ሰልፉን በችኮላ መጥራታችሁ ግን ብዙዎችን ደስ አላሰኝም ነበር። ነገር ግን «ማንም ይጥራዉ፣ ማንም ፣ ትግሉን እስከጠቀመ ድረስ መተባበር ያስፈልጋል» የሚል አቋም በርካታ የአንድነት ፓርቲና መኢአድ አመራር አባላት በመያዝ ድጋፍ ሰጧችሁ። መኢአድ በመግለጫ ድጋፉን ገልጸ። በፓርቲ ደረጃ፣ የሥራ አስፈጸማዊ፣ ምክር ቤቱ ተነጋግሮበት ዉሳኔ ለመወሰን 15 ቀናት በቂ ስላልነበረ፣ በኦፈሴል የአንድነት ፓርቲ ድጋፍ ባይሰጥም፣ የፓርቲዉ አመራር አባላት ግን እንደ ኢሳት በመሳሰሉ ሜዲያዎች በመቅረብ፣ የአንድነት አባላትን ደጋፊዎች በሰልፉ እንዲገኙ፣ ሰማያዊ ፓርቲ ለጠራዉ ሰልፍ ድጋፍ እንዲሰጡ ጥሪ አቀረቡ። በአዲስ አበባ 23ቱም ወረዳዎች የሚገኙ የአንድነት አስተባባሪዎች፣ «የሰማያዊ ፓርቲ የጠራዉ ሰልፍ፣ የኛም ሰልፍ ነው» በሚል በየወረዳዎቻቸዉ ቅስቀሳ ሲያደርጉ፣ መፈክሮችን ሲያዘጋጁ እንደነበረም ታውቃላችሁ። የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላትም በሰልፉ ተገኝተዋል። አንድነት ፓርቲ፣ እንዲሁም መኢአድ ለሰማያዊ ፓርቲ ሙሉ ድጋፉቸውን በዚህ መልኩ መስጠታቸው ተገቢና አስፈላጊ ነበር።

የአዲስ አበባዉን ሰልፍ ተከትሎ፣ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ እንቅስቃሴ ጀመረ። በጎንደርና በደሴ ቅስቀሳ ይደረግ በነበረበት ጊዜ፣  የሰማያዊ ፓርቲ፣ ድጋፉን እንዲሰጥና ከጎንደርና ከደሴ ሕዝብ ጎን እንዲሰልፍ  አንዳንዶቻችን  ጠይቀን።  ከአዲስ አበባ ዉጭ ድርጅታዊ አቅም እንደሌላችሁ እናውቃለን። ነገር ግን ቢያንስ ቢያንስ፣ በመግለጫ ደረጃ ሰላማዊና ህዝባዊን ንቅናቄ በመደገፍ ከጎንደርና ከደሴ ሕዝብ ጎን መቆም ይገባችሁ ነበር። ያንን ግን፣ ተጠይቃችሁም እንኳን፣ አላደረጋችሁም። አንድነት ፓርቲ ከእናንተ ጋር አጋር እንደነበረዉ፣ እናንተ ግን ወገናዊ ምላሽ መስጠት ተሳናችሁ። ከጎንደሩና ከደሴዉ ሰል በኋላ በጂንካ፣ በአርባ ምንጭ፣ በባህር ዳር፣ በፍቼ ሰላምዊ ሰልፎች የተደረጉ ሲሆን፣  በመጨረሻዉ ሰዓት ላይ የአንድነት አመራር አባላትን በማሰርና በማንገላታት ከፍተኛ ጫና ሕወሃትና ኦሕድድ በማድረጋቸው ሰልፎቹ ተላለፉ እንጂ፣ በመቀሌና በባሌ/ሮቢ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል። በነዚህ ሁሉ ከተሞች የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምጹን ለሰላም፣ ለዲሞክራሲን አለነጻነት ሲያሰማ ድርጅታችሁ ድምጹን አጥፍቶ ነበር። በዚህ እዝኜባቹሃለሁ።

የጎንደሩን እና የደሴዉን ሰልፍ ተከትሎ የአንድነት ፓርቲ አዲስ አበባ ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ሊያደርጋቸው ያቀዳቸውን ሰልፎችና ህዝባዊ ስብሰባዎች ለሕዝብ አሳወቀ። በፕሮግራሙ መሰረት፣ ከበርካታ ሰልፎች መካከል ፣ በአዲስ አበባ መስከረም 5 ቀን፣ በአሶሳና ጋምቤላ ነሐሴ 26 ቀን  ሊደረጉ የታሰቡ ሰልፎች ይገኙበታል።

ብዙዎቻችንን  የገረመን  የአንድነት ፓርቲ ሰልፍ እንደሚጠራ ባሳወቀ በሁለት ቀኑ ፣ በችኮላ  ነሐሴ 26 ቀን በአዲስ አበባ ሰልፍ እንደምትጠሩ መግለጻችሁ ነበር። እየተደረገ ያለው፣  ትግል እንጂ ጨዋታ እንዳልሆነ በማስመር፣  ሰልፉን ከአንድነት ፓርቲ ጋር እንድታደረጉ ጥያቄ አቀረብንላችሁ። ያ ብቻ አይደለም፣  የፖለቲካ ፕሮግራም ልዩነቶችን ባለመኖራቸው፣  ከአንድነትና ከመኢአድ ጋር መዋሃድ የሚቻልበትን ሁኔታ እንድታመቻቹ አበረታታን።

አንድ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባልን፣  በዚህ ጉዳይ ላይ ሳነጋገር «እንኳን ሰልፍ ከነርሱ ጋር ለማድረግ፣ እንደዉም የፖለቲካ ፕሮግራሞቻችን አንድ ናቸው። እንዋሃድ ብለን ጠይቀናቸው ፍቃደኛ አልሆኑም» የሚል መልስ ነው የሰጡኝ። በአጭሩ፣ በአንድነት ፓርቲ ዘንድ፣  ከማንም ድርጅት ጋር፣ በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ አብሮ ለመስራት፣ ሰላማዊ ሰልፎችን  ለማስተባበር ፣ ፍቃደኝነት እንዳለ ነዉ የተረጋገጠልኝ።

ነገር ግን ከእናንተ አዎንታዊ ምላሽ ልናገኝ አልቻልንም። «የሚጠየቁት ጥያቄዎች አንድ አይነት ሆነው፣ ለሰልፍ የሚጠራዉ ህዝብ አንድ ሆኖ፣ በሁለት ሳምንት ጊዜዉስጥ፣ ሁለት ሰላማዊ ሰልፎች መጥራት ምን ይባላል ?  ገንዘብና ጊዜ ማባከን ነዉ» በሚል ብትችሉ አብራችሁ  ከአንድነት ጋር መስክረም 5 ቀን ሰልፍእንድታደርጉ፣ ካልተቻለ ደግሞ የሰልፉን ቀን ትንሽ ራቅ እንዲል ተማጸንን።

በነሐሴ 26 ቀን በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራት፣ በጋምቤላና በአሶሶ፣ ነሐሴ 26 ቀን  የአንድነት ፓርቲ ሊያደርጋቸው ያቀዳቸውን  ሰላማዊ ሰልፎችና በዚያም የሚኖረው ሕዝብ ጥያቄ በስፋት እንዳይዘገብና ትኩረት እንዳያገኝ የሚያደርግ መሆኑን በማስገንዘብ፣ ለጋምቤላና ለአሶስ ሕዝብ ክብር እንድትሰጡም ጠየቅናችሁ።

ነገር ግን «አልሰማም፣ እምቢ አሻፈረን» አላችሁ። ግትር ሆናችሁ።  በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ የድርጅታችሁ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል «ለምን ከሌሎች ድርጅቶች ጋር አብራችሁ አትሰሩም ? » ተብለው ሲጠየቁ «ምን የሚረባ ድርጅት አለህ ብለህ ነዉ ? » የሚል አሳዛኝና አሳፋሪ ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት መሪ የማይጠበቅ ምላሽ ነበር የሰጡት። በአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ፣  ከማንም ድርጅት ጋር ግንባር፣ ቅንጅት፣ ዉህደት ለመፍጠር  ሰማያዊ ፓርቲ ፍላጎት እንደሌለውም አቶ ይልቃል በድጋሚ አስምረዉበታል። በአጭሩ ሰማያዊ ፓርቲ ለብቻው መጓዝ የመረጠ ይመስላል። በዚህም ምክንያት ሰማያዊ ፓርቲ ከሰላሳ ስምንቶቹ ዉጭ ሊሆን ችሏል።

የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት፣ «ሰማያዊም ሆነ ማንም ድርጅት፣  ድርጅታዊ ነጻነትና፣ ባመነበትና ባቀደው መንገድ የመንቀሳቀስ መብት አለዉ» በሚል የሰማያዊም ሆነ የሌሎችን ሥራ ላይ አስተያየት መስጠት አልፈልጉም። ሌሎች የሚያደርጉትን  ለነርሱ ትተው፣  በኦሮሚያ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በመቀጠል በሮቤና በአዳማ፣ እንዲሁም በመቀሌ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላእንዲሁም አዲስ አበባ  ሰላማዊ ስለፎችን ለማድረግ እየተዘጋጁ  ነዉ። የኢትዮጵያን ሕዝብ፣  በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በደቡብ፣ በትግራይ፣ በአማራዉ ክልል፣ በኦሮሚያ ፣ በጋምቤላ፣ በቤኔሻንጉል …እያንቀሳቀሱት ነዉ። ጸጥ ብለው ስራቸውን እየሰሩ ነዉ። በዚህ በርቱ፣ ቀጥሉበት እንላቸዋለን።

ድርጅታችሁ በሕዝብ ካልተደገፈ የትም ሊደርስ አይችልም። እንደከዚህ በፊትም  ሕዝቡ በቀላሉ ለፖለቲካ ድርጅቶች ድጋፍ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለም። ሕዝቡከፖለቲካ ድርጅቶች የሚጠብቀዉ ነገር አለ። «አንድ የተቃዋሚ ድርጅት ኢሕአዴግን ተክቶ፣ በኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ ልዩነቶችን አጣቦ፣ ያገሪቷን አንድነት ጠብቆ፣በአገሪቷ ሁሉ ሰላምና መረጋጋትን አስፍኖ አገር ማስተዳደር ይችላል ወይ ?» የሚል ጥያቄ ይጠይቃል። ሕዝቡ «ምን ያህል ኢሕአዴግን ይቃወማል ?» የሚል ጥያቄአይደለም የሚጠይቀው። «ከኢሕአዴግ ይሻላል ወይ ? » የሚል ጥያቄ ነዉ የሚጠይቀዉ። ሕዝብን ለማሰባሰብ የሚችል ድርጅት ደግሞ ሌሎችን የሚያከብር፣ ትሁት መሪዎች ያሉት ድርጅት መሆን ይኖርበታል።

እንግዲህ ትህትና ይኑራችሁ እላለሁ። ከአሁን ለአሁን አንድ ሰልፍ ጠራችሁና እራሳችሁን እንደ ግዙፍ ማየታችሁን አቁማችሁ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎትና ጥያቄ እራሳችሁን አስገዙ እላለሁ። በነሐሴ 26 የጠራችሁትሰላማዊሰልፍንሰርዙ። የአዲስ አበባ ሕዝብ በአስራ አምስት ቀናት ዉስጥ ሁለት ጊዜ ሰልፍ ሊወጣ አይገባም። ሰልፍ ለማዘጋጀትትልቅ የገንዘብ አቅም ይጠይቃል። በመሆኑም ሰልፉን መስክረም 5 ቀን ከአንድነት ፓርቲ ጋር አብራችሁ አድርጉ። በአንድነት ፓርቲና በሰማያዊ ፓርቲ  ካስፈለገምሌሎች ድርጅቶችን ያቀፈ ግብረ ኃይል ተቋቋሞ የመስከረም 5ቱን ሰልፍ ያስተባብር። ይሄን ለማድረግ ትንሽ ጊዜ ካስፈለገም የመስከረም 5 ቱን ሰልፍ በአንድ ወይንም 2ሳምንታት እልፍ እንዲል ማድረግም ይቻላል።

እግርጥ ነዉ ለኢሕአዴግ የሶስት ወራት ጊዜ ሰጥታችሁታል። «ጥያቄያችንን ስላልመለሰ በገባነው ቃል መሰረት በሶስት ወሩ ሰልፍ መዉጣት አለብን» የሚል አስተያየት ሊኖራችሁ ይችላል። እስቲ ልጠይቃችሁ …ከመጀመሪያዉ ሰልፍ በኋላ ያልሰማችሁ ኢሕአዴግ፣ አሁን ለምን ይሰማቹሃል ? እንዳለፈው ጊዜ የአንድነት/መኢአድ አባላትና ደጋፊዎች አይተባበሯችሁም ።  ለምን ለመስክረም 5 ዝግጅት ስለሚያደርጉ። ለሰልፍ የሚመጣዉ ሕዝብም ቁጥሩ ሊያንስ ይችላል። ያ ደግሞ የበለጠ ተቀባይነታችሁን ይሸረሽርዋል እንጂ የሚፈይደው አንዳች ፋይዳ የለም።

ይልቅስ  በኢሕአዴግ ላይ የበለጠ ጫና ማሳደር ከፈለጋችሁ፣ በሚቀጥለው ሰልፍ ኢሕአዴግ እንዲሰማ ከፈለጋችሁ፣ ከአንድነት ፓርቲ፣ ከመኢአድ ከመሳሰሉ ጋር እጅና ጓንት ሆናችሁ መስራት ይኖርባቹሃል። የአንድነት ፓርቲ ያለ አንዳች ቅደመ ሁኔታ ከናንተ ጋር ለመነጋገር፣ ሕብረት ለመፍጠር ዝግጁ ነዉ። ከእናንተ ጋር ብቻ አይደለም ከማንም ድርጅቶች ጋር አብሮ መስራት ይፈልጋል። ለዚህም ነዉ ከአምስት አመት በላይ በመድርክ ዉስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረዉ። (ይሄን ያህል ዉጤት ባይገኝም)  ለዚህም ነዉ ከመድረክ አልፎ፣ መድረክን ተክቶ፣ ድርጅቶችን በሚስማሙበት ጉዳይ አሰባስቦ ጥሩ ሥራ ሊሰራ ይችላል ብዬ በማስበው፣  በሰላሳ ሰምንቶቹ ዉስጥ ፣ ድርጅቶች በአንድ ላይ ሆነው በአገዛዙ ላይ ጫና እንዲያሳድሩ እየሰራ ያለዉ። ለዚህ ነዉ ዘሃበሻ እንደዘገበዉ ከመኢአድ ጋር ለመዋሃድ እንቅስቃሴ የሚያደርገዉ።

እዚህ ላይ አብቃ። ተስፋ አደርጋለሁ ምክሬን እንደምትሰሙ። ሕዝቡ ይከታተላል። ሕዝቡ ሁሉንም ይመዝናል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ትልቅ ሚና ልትጫወቱ ከፈለጋችሁ ጉዟችሁን በጥንቃቄና በማስተዋል አድርጉ። ትላንት ግዙፍና ተወዳጅ የነበሩ፣ አሁን ግን የተተፉ የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችና ድርጅቶች እንደነበሩና እንዳሉም አትርሱ።

(ዘግይቶ የደረሰኝ መረጃ የአንድነት ፓርቲ፣  ነሐሴ 26 ቀን ፣ ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ከመጥራቱ በፊት፣ አስቀድሞ በጋምቤልና በአሶሳ ያቀዳቸዉን ሰልፎችን እንዲሁም በድረደዋ በመሳሰሉ ከተሞች  ሊደረጉ የታቀዱ ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ሰርዟል። ይመስለኛል ሰማያዊ ፓርቲ ተገቢዉን የሜዲያ ትኩረት እንዲያገኝ ታስቦ ሳይሆን አይቀርም። ለሌሎች ድርጅቶች ከበሬታ ማሳየት ማለት ይሄ ነው)

አማኑኤል ዘሰላም
amanuelzeselam@gmail.com

ነሐሴ  21 ቀን 2005 ዓ.ም

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=6770

posted by Tseday Getachew

 

የኢህአዴግ ስውር ሴራ በሮቤ ከተማ ተጋለጠ!!! ሐገሪቷን የሚያስተዳድራት ማነው? የባሌ ሮቤ ሰላማዊ ሰልፍ ለምን ተደናቀፈ?

 

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ማብራሪያ

የሚሊየኖች ድምፅ ለነፃነት ንቅናቄ በአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት የነፃነት ድምፅ ማስተጋባት ከጀመረ እንሆ ዛሬ ስልሳ ሰባተኛ(67) ቀኑን ይዟል፡፡ ፓርቲያችን በእዚህ ታላቅ ሕዝባዊ የነፃነት ንቅናቄ መሪር የሆነ ውድ ዋጋ እየከፈለ ድምፅ አልባ ለሆኑት ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ድምፅ በመሆኑ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡

ላለፋት ስምንት ዓመታት ሰቆቃ እና ግፍ በገዢዎቻችን ሲፈፀምበት የኖረው የገጠሩም ሆነ የከተማው ታላቁ ህዝባችን ‹አንድነት ፓርቲአችን አስትንፋሳችን› በማለት  አንድነት ፓርቲ ባመቻቸለት ህዝባዊ ስብሰባዎች እና ሠላማዊ ሠልፎች በነቂስ በመውጣት የታፈነ ብሶቱን በግልፅ በአደባባይ ላይ በማሰማቱ ኢህአዴግ እና ህዝቡ ዛሬም ድረስ ተለያይተው እንዳሉ አንድነት ፓርቲ በማያወላዳ ሁኔታ በሚሊዮኖች ድምፅ ንቅናቄ በህዝባችን መሀል በመገኘት አረጋግጧል፡፡

ኢህአዴግ የቀረው በውሸት እና በሴራ የተሞላ የቅጥፈት ፕሮፖጋንዳ ብቻ መሆኑን ይበልጥ ያረጋገጠልን የባሌ ዞን አስተዳደር እና የሮቤ ከተማ አስተዳደር ያዘጋጁት በሀገር ሽማግሌዎች ስም የተቀነባበረው የእናደራድራችሁ አሳፋሪ ድራማ ለኦሆዴድም ሆነ ለኢህአዴግ ታላቅ ውድቀት ነው፡፡

አንድነት ፓርቲ በባሌ ሮቤ ከተማ ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ህጉ በሚያዘው መሰረት ነሐሴ 13/2005 የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ደብዳቤ ለከተማዋ አስተዳደር አስገባ፡፡ ጉዳዩን የሚከታተሉት የፓርቲው ተወካዮች ደብዳቤው ከገባ ከ48 ሠዓት በኋላ ወደ መደበኛ ቅስቀሳቸው መግባት እንደሚችሉ ህጉ እንደሚፈቅድላቸው የተረዱት የፓርቲያችን ትንታግ ታጋዮች ጊዜ ሳያባክኑ የተዘጋጀውን የቅስቀሳ በራሪ ወረቀት በከተማ ውስጥ ማሰራጨት ጀመሩ፡፡

ሁኔታውን በቅርብ ሲከታተሉት የነበሩት የፌደራል መንግስት እና የክልሉ መንግስት ከሮቤ ከተማ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት አንድነት ፓርቲ ላይ ያጠመዱት ሴራ ለመተግበር የከተማው ከንቲባ አቶ አብዱል ላጥፍ ነሓሴ 13/2005 ለገባላቸው የፓርቲው ደብዳቤ መልስ ያሉትን ነሓሴ 13/2005 ቀን እንደ ተፃፈ ተደርጎ ፓርቲው አላማ ያሉትን ዘርዝረው ነሓሴ 17/2005 ዓ.ም ደብዳቤ ለፓርቲው ተወካዮች ሰጡ፡፡ የተባሉትን ሰበቦች እና ምክንያቶችን በሙሉ አሟልቶ ፓርቲው የእዚያኑ ዕለት በደብዳቤ ምላሽ ቢሰጥም የከተማው አስተዳደር ባለስልጣኖች ከንቲባውም ጭምር ቢሮአቸውን ዘግተው ጠፉ፡፡ መዝገብቤትም ለማስገባት የተደረገው ጥረት በመዝገብ ቤት ሰራተኞች እምቢ ባይነት ሳይሳካ ቀረ፡፡ የአምባ ገነኑን የኢህአድግ ባለስልጣኖችን ነውረኛ ስራ ቀድሞ የሚያውቀው የአንድነት ፓርቲ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በሪኮማንዴ በፓስታ ቤት በኩል አንዲደርሳቸው በማድረግ ምንም መፈናፈኛ ሰበብ እንዳያገኙ አደረገ፡፡                                                                                                                            ግራ የገባቸው የከተማው አስተዳዳሪዎች ተሰባስበው ከላይ በተሰጣቸው ትእዛዝ መሰረት አንድነትን የማጥቅያ ሌላ ሴራ ተጠቅመው መጥታችሁ የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያውን ቅፅ ሙሉ በማለት ለተወካዮቻችን ጥሪ አደረጉ፡፡ የፓርቲው ተወካዮች ስራቸውን እየሰሩ ቅፁን የሚሞሉ እና የሚፈርሙ አባላትን በመመደብ ተወካይ ብቻ ወደ ወስተዳድሩ ፅ/ቤት ላኩ፡፡ የጠበቃቸው ግን የተቀናጀ ሴራ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲን በህግ የሚያስጠይቅ እንዲሁም ያዘጋጁትን የሀይል ርምጃ ህጋዊ የሚያደርግ፤ ደብዳቤ ካስገባን 48 ሰዓታት ባነሰ ጊዜ ሰልፍ እወጣለሁ ብሎ ፓርቲው ነሓሴ 17/2005 ደብዳቤ እንዳስገባ ተደርጎ ይህንኑ ቀን የጠቀሰ ቅፅ አዘጋጅተው የአንድነትን ተወካዮች አንዲፈርሙ ተጠየቁ፡፡ ቀድሞውኑ ሴራው የገባው የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር በሰጠው መመርያ መሰረት ቅፁ ላይ የምንፈርመው ደብዳቤአችንን ያስገባንበትን ነሐሴ 13/2005 ቀን ከጠቀሰ ብቻ ነው በማለት የአንድነት ተወካዮች አንፈርምም አሉ፡፡

አንድነት ፓርቲን በጉልበትም በህግም ለማኮላሸት ኢህአድግ ያዘጋጀውን ሴራ በጥበብ ማክሸፍ ተቻለ፡፡ ኢህአዴግ ለሌላ ሴራ ማቀንቀኑን ወድያውኑ ተያያዘው፡፡

የፓርቲው ቀስቃሽ ቡድን በ50.000 የሚገመት በራሪ ወረቀት መበተኑን እና ከ5.000 በላይ ፖስተር በእለቱ በመለጠፍ የፓርቲውን መልእክት ለታፈነው የሮቤ ከተማ ህዝብ አደረሰ፡፡ በሁለት መኪና መጠነኛ ቅስቀሳ ካደረገ ከ 1፡00 ሰዓት በኋላ መኪናዎቹ ከነቀስቃሽ ቡድኑ ከነሀሴ 18/2005 እስከ እሁድ ነሀሴ 19/2005 ድረስ በታጣቂዎች ከቆሙበት አንዳይንቀሳቀሱ ታገቱ፡፡ የትራፊክ ፖሊሶችም መኪናዎቻችንን በማገት ያለቆቻቸውን ትዕዛዝ ተግባራዊ አደረጉ፡፡ በዚህ መሀል ነው በሽማግሌ ስም ያደራጃቸውን 15 የሚሆኑ የኦህዴድ ካድሬዎች ‹‹ነገ የሚከሰተው ደም መፋሰስ አሳስቦን ነው የመጣነው እናወያያችሁ›› በማለት ከምሽቱ 1፡30 ባረፍንበተ ሆቴል ተሰባስበው የመጡት፡፡ ለሀገር ሽማግሌ ክብር የሚሰጠው አንድነት ፓርቲ ሽማግሌዎች የተላኩበትን ዝርዝር መልእክት ካዳመጠ በኋላ የእሁዱን ሰላማዊ ሰልፍ በምንም ተአምር እንደማንሰርዘው፤ ይልቁንም የከተማው መስተዳድር ለፖሊስ የሀይል እርምጃ ውሰዱ ብሎ ያስተላለፈውን መመሪያ እንዲስብና ህገመንግስቱን እንዲያከብር ሽማግሌዎቹ ምክራቸውን ለገዢው ፓርቲ ባለ ስልጣኖች እንዲለግሱ መልእክት በመንገር ውይይቱ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ተጠናቀቀ፡፡ በኢህአድግ የተለመደ ቀመር የቅስቀሳ ጊዜያችንን በጉልበት እና በማስመሰል ለመስረቅ የተደረገውን የተለመደ ቅንብር አንድነት ፓርቲ ቀድሞ የሚያውቀው ጉዳይ በመሆኑ ሁለት ተደራዳሪዎችን ብቻ በመመደቡ ሌላው ግብረኃይል ሳይዘናጋ የቅስቀሳ ወረቀቱን በማሰራጨቱ ኢህአዴግ ያሰበውን አንድነትን የመነጠል ሴራ ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡

እነዚያው የሀገር ሽማግሌዎች የተባሉ ግለሰቦች ‹‹መስተዳድሩ አሁን ሊያነጋግራችሁ ዝግጁ ነው፡፡ ቢሮ ድረስ ኑ እና ተወያዩ›› በማለት በሰላማዊ ሰልፉ ቀን እሁድ ከጥዋቱ 1፡00 ሰዓት እኛን ቀጥረውን በሰዓቱ ስንደርስ የኦሆዴድ ባለስልጣኖች ግን የጠዋቱ የቅስቀሳ ስዓታችንን ለመስረቅ ከጠዋቱ 1፡40 በሁለት ኮብራ መኪና እና ታርጋ በሌላት በአንድ መኪና በደህንነት ባለ ስልጣኖች ታጅበው መጡ፡፡

ውይይቱ በዞኑ ም/አስተዳዳሪ አቶ ሰሎሞን አወያይነት የከተማው ከንቲባ፣ የኦሆዴድ ተጠሪ የኮምኒኬሽን ሀላፊ ሌሎችም ከ15 ያላነሱ ባለ ስልጣኖች እንዲሁም በርካታ የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ሦስት የመንግስት ካሜራዎች ተጠምደው ውይይቱ ተጀመረ፡፡

የሽማግሌ ካባ የለበሱት የኦሆዴድ ካድሬ የሆኑት የሀገር ሽማግሌዎች ተወካይ ነኝ ያሉት ግለሰብ ውይይቱን በንግግር ሲጀምሩ ‹‹እናንተ የነፍጠኛን ስርዓት ልታመጡብን ነው፡፡ እኛን ሳታነጋግሩ ሳንፈቅድላችሁ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንዴት አሰባችሁ? አሁንም ይህንን ሰላማዊ ሰልፍ አታደርጓትም፡፡ የሮቤ ህዝብ እኛን ዎክሎናል መንግስት እንኳን ቢፈቅድላችሁ እኛ ሽማግሌዎች አይደረግም ብለናል አቁሙ›› በማለት የተጫኑትን ዉሳኔ በሚደንቅ ሁኔታ አስተላለፉ፡፡ በእዚያው መድረክ የኢህአዴግ/ኦህዴድ ማንነት እና ጭንብል ለዓለም ህዝብ ተጋለጠ፡፡ አንድነት ፓርቲም ይህንን ከላይ እስከታች ባሉ ባለስልጣኖች የተቀነባበረውን ድራማ በካሜራ ቀርፆ ያስቀረ በመሆኑ በእጃችን የሚገኘውን የውይይቱን ይዘት የያዘውን ቨድዮ እንድትመለከቱ በአክብሮት  እየጋበዝን አንድነት ፓርቲ የኢህአዴግን እውነተኛ ገፅታ በመረጃ ማጋለጡን  አጠናክሮ ዛሬም ነገም ይቀጥላል፡፡

በሮቤ ከተማ ለቅስቀሳ የተላከው ቡድን በመስተዳድሩ ባለስልጣናት ትእዛዝ ከምሽቱ 4፡00 ስዓት አልጋ ከያዙበት ታይታኒክ ሆቴል በግፍ ተባረው፤ የያዙትን ቦርሳ እንኳን ከመኝታ ክፍላችው ሳያወጡ በግፍ አውላላ ሜዳ ላይ ወንጀል እንዲፈፀምባቻው የከተማው መስተዳድር የፍፀመውን መንግስታዊ ውንብድና ፓርቲአችን በዝምታ የሚያልፈው ጉዳይ አይደለም፡፡ የመኪና ሹፊሮቻችንን በውድቅት ሌሊት ጭንብል ባጠለቁ ከ 20 በላይ ታጣቂዎችን በማሰማራት በማስወረር በጉልበት ክፍላቸው ውስጥ በመግባት ስለተፈፀመው ወንጀል አንድነት ፓርቲ በህግ የሚጠይቅ ሲሆን ታላቁ የሮቤ ከተማ ነዋሪ ህዝብ መብቱን ለማስከበር ያደረገውን ትንቅንቅ አንድነት ፓርቲ ከልብ ያደንቃል፡፡ ምስጋናውንም በእዚህ አጋጣሚ ያቀርባል፡፡

ድል ለታፈነው የኢትዮጵያ ህዝብ!!!

   አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ

ነሐሴ 21 ቀን 2005 .

አዲስ አባባ

 

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=6772

posted by Tseday Getachew

መንግሥት ለተፈጠረው ችግር በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ እንጠይቃለን! ሰማያዊ ፓርቲ

semayawi party's protest call in Addis Ababa

ፓርቲያችን ሰማያዊ በህገ መንግሥቱ በተደነገገው ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱን ተጠቅሞ ለመንግሥት ጥያቄዎችን በማቅረብ ግንቦት 25/2ዐዐ5 ዓ/ም. ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ አድርጓል፡፡

መንግሥት ላቀረብናቸው ጥያቄዎች በሦስት ወር ውስጥ መልስ የማይሠጥ ከሆነ በተጠናከረና በተደራጀ መልኩ ጥያቄያችንን በድጋሚ በህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ እንደምናቀርብ በግንቦት 25/2ዐዐ5 ዓ/ም. በተደረገው ሠልፍ ላይ ለህዝብ ቃል በገባነው መሠረት ነሃሴ 26/2ዐዐ5 ዓ/ም. በድጋሚ ሰልፍ ጠርተን አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረግን መሆኑን ለህዝብ በልዩ ልዩ መገናኛ ዘዴዎች ገልፀናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ለሰልፉ በሰላም መጠናቀቅ አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግልን አዋጁ በሚጠይቀው መሠረት ለአዲስ አበባ መስተዳድር ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሰወቂያ ክፍል ጉዳዩን እንዲያውቀው አድርገናል፡፡

ይሁን እንጂ ፓርቲያችን ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ በጠራበት ግዜና ቦታ ላይ በሌላ አካል ሰልፉ መጠራቱን በትናንትናው ዕለት ነሀሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በመንግሥት ቴሌቪዥን ዜና ሰምተናል፡፡ በተጨማሪም ለመንግሥት መዋቅር ዜጐች በዚህ ሰልፍ እንዲወጡ በግድ እንዲፈርሙ እየተደረገ መሆኑን ከአዲስ አበባ ኑዋሪዎች አረጋግጠናል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ አስፈላጊውን የህግ ቅድመ ሁኔታ አሟልቶ ነሐሴ 26/2ዐዐ5 ዓ/ም. በመስቀል አደባባይ የጠራውን ተቃውሞ ሰልፍ ለህዝብ ያሳወቀና አስፈላጊውን ዝግጅት ያጠናቀቀ በመሆኑ ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በጠራበት ቀንና ሠዓት በሌሎች አካላት የተጠራው ሰልፍ ከመረጃ እጥረት ከሆነ እንዲሠረዝ እየጠየቅን ይህ ካልሆነ ግን ሰማያዊ ፓርቲ በህጋዊ መብቱ የሚያደርገውን የተቃውሞ ሰልፍ ሆን ብሎ ለመረበሽና አቅጣጫውን ለማስቀየስና በዜጐች መካከል ግጭት ለመፍጠር የታቀደ ስለሆነ ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ መንግሥት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብና የሚመለከታቸው አካላት እንዲያውቁት በአፅንዖት እንገልፃለን፡፡

በመጨረሻም መንግስት ዜጐችን ያለፈቃዳቸው በማስፈረም ተገደው ሰልፍ እንዲወጡ ማድረግ ህገ ወጥ ስለሆነ፣ በአስቸኳይ እንዲያቆም እንጠይቃለን፡

Post Navigation

%d bloggers like this: