Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

Archive for the month “January, 2013”

የኢትዮጵያዊነት ልዩ ውበትና አንድነት እስከ ፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ የመብት ጥያቄዎችና ተቃውሞዎች የተንጸባረቁበት 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ

 

በፍቅር ለይኩን

Ethiopian footballer adane girma

የ1998ቱ በፈረንሳይ አስተናጋጅነት የተካሄደው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ በዓለም አቀፉ የፖለቲካ መድረክ ስፖርት ለሰላም፣ ለወንድማማችነት፣ ለአንድነት… ወዘተ ያለው አዎንታዊ ፋይዳ በግልፅ የታየበት መድረክ ሆኖ ነበር ያለፈው፡፡ በአንድ ቡድን ተደልድለው የተገናኙት በጥንታዊ ስልጣኔዋኗ እስከ አስር ሺህ ዘመን በሚመዘዝ ግዙፍ ታሪኳ፣ ታላቅ የሆነ ብሔራዊ ኩራትና ስሜት ያላት ጥንታዊቷ ፋርስ የዛሬዋ ኢራን ብሔራዊ ቡድን፣ ከአሜሪካ አቻዋ ጋር በተፋጠጡበት መድረክ፣ የትናንትነዋ ኃያል ኢራንና የዘመናችን ልዕለ ኃያል አገር አሜሪካን ያገናኘ ልዩ አጋጣሚ ሆኖ ነበር ያለፈው፡፡

በእነዚህ ሁለት ባላንጣ አገሮች በአንድ ቡድን ተደልድለው የተገናኙበትን ጨዋታ/ፉክክር የአሜሪካው እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በአጭር ቃል እንዲህ ሲሉ ነበር የገለጹት፡- “the mother of all games” በወቅቱም ስለ ሁለቱ አገራት ጨዋታ የዘገቡ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን፣ የሁለቱ አገራት ፖለቲከኞች፣ ዲፕሎማቶች፣ የእግር ኳስ ባለሙያዎችና ተንታኞች ጨዋታው ከስፖርታዊ ውድድር ባለፈ ጠንከር ያለ ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳለው ነበር ሲዘግቡ የነበሩት፡፡

ይሁን እንጂ ከእግር ኳስ ፍክክሩ ባሻገር ፖለቲካዊ አንድምታው ጎልቶ በተነገረበት በዚህ የአሜሪካንና የኢራን ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ፣ ሁለቱ አገሮች በስፖርቱ መድረክ ለሰላምና ለመልካም ግንኙነት ያላቸውን አዎንታዊ ፍላጎትና ስሜት የገለጹበት መልካምና ልዩ አጋጣሚ ሆኖ ነበር ያለፈው፡፡

በተጨማሪም የሁለቱ አገሮች ደጋፊዎች በውድድሩ ወቅት ያሳዩት ሰላማዊነትና ጨዋነት፡- ‹‹ስፖርት ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለአንድነት፣ ለትብብር፣ ለወንድማማችነት…›› የሚለውን የስፖርት መርህ ከፍ አድርጎ ለዓለም ሕዝብ ያሳየ ነበር፡፡ ጥቂት የማይባሉ የሁለቱ አገራት እግር ኳስ አፍቃርያንና ደጋፊዎች አንድ ጉንጫቸውን በአሜሪካን አንድ ጉንጫቸውን ደግሞ በኢራን ሰንደቀ ዓላማ ቀለማት በማስዋብ የእግር ኳስ ስፖርት በአገሮችና በሕዝቦች መካከል መቀራረብና ሰላም እንዲፈጠር የሚያስችል መድረክ መሆኑን በተግባር ለዓለም አሳይተውበታል፡፡

ይህን የወቅቱን እውነታ ያስተዋለው የኢራኑ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆነው አፍሺህን የእግር ኳስ ስፖርት አገራትን በሰላምና በፍቅር መንፈስ ለማስተሳሰር ያለውን ጉልበት እንዲህ በማለት ነበር የገለጸው፡-

There are two things that can bring this planet closer together: love and football.

የተባበሩት መንግሥታት ድ/ት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ባንኪሙን በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እ.ኤ.አ ግንቦት 11/2011 ዓ.ም ስፖርት ለሰላምና ለልማት ያለው አስተዋጽዖ በሚል ባደረጉት ንግግራቸው እንዳረጋገጡትም፤ ስፖርት በዓለም አቀፍ ደረጃ የአገሮችን ድንበር ተሻግሮ የዘር፣ የጎሳና የሃይማኖት ልዩነቶች ሳይገድበው፣ የዓለም አቀፍ ቋንቋ መሆን እንደቻለና ስፖርታዊ ውድድሮች ለሰው ልጆች ሰላም፣ አንድነትና እድገት እየተጫወቱ ያለውን ቁልፍ ሚና እንዳለው እንዲህ በማለት ነበር የገለጹት፡-

“Sport has become a world language, a common denominator that breaks down all the walls, all the barriers. It is a worldwide industry whose practices can have a widespread impact. Most of all, it is a powerful tool for progress and development.”

የደቡብ አፍሪካው የነፃነት ታጋይና የሰላም አባት የሆኑት ኔልሰን ማንዴላም በዓለም አቀፉ የስፖርት መድረክ ለሰው ልጆች ነፃነትና መብት ባደረጉት ትግል፣ ስፖርታዊ ውድድሮች በረጅሙ ዘመን የእርሳቸውና ሕዝባቸው እልህ አስጨራሽ የፀረ-አፓርታይድ የነፃነት ተጋድሎአቸው ወቅት ‹‹ሰላማዊ የትግል ስልት›› መሆኑን ላሳዩበት ፖለቲካዊ ብቃታቸው በተሰጣቸው ዓለም አቀፍ ሽልማት ላይ በዳረጉት ንግግራቸው ስለ ስፖርት እንዲህ ነበር ያሉት፡-

Sports had the power to change the world … to inspire … to unite people.

ስፖርታዊ ውድድሮች የሰላም፣ የወንድማማችነትና የፍቅር መድረክ ናቸው ቢባሉም አልፎ አልፎም ቢሆን የዘረኝነት መንፈስ የሚንጸባረቅባቸው፣ የሌሎችን ክብርና ነፃነት የሚጋፋ ሃይማኖታዊ መልእክቶች፣ ፖለቲካዊ ተቃውሞችና እስከ ጠብና ግጭት የሚዘልቁ ክስተቶችን ማስተናገዳቸው አልቀረም፡፡

እንግሊዝና አርጀንቲና፣ የላቲን አሜሪካኖቹ የኤልሳልቫዶርና የሆንድራስ በእግር ኳስ ጨዋታ ምክንያት የተፋጠጡበትንና ጦር የተማዘዙበትን አጋጣሚዎች ስናስብ የስፖርቱ መድረክ አልፎ አልፎም ቢሆን ከፖለቲካዊ የሆኑ አጀንዳዎች እንደማያጣው ያስገነዝበናል፡፡

ለአብነትም ያህል በአንድ ወቅት ከናይጄሪያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ጋር ባደረግነው ጨዋታ ናይጄሪያዎቹ ‹‹ኢትዮጵያን ራብተኞች ናችሁ›› በሚል ክብርን በሚነካ መልኩ ለኢትዮጵያን ተጫዎቾችና ደጋፊዎች ዳቦ የወረወሩበት አጋጣሚ ስናስብም ስፖርት የሰላም፣ የፍቅር፣ የወንድማማችነት…ወዘተ መድረክ ነው የሚለው መርህን በጥቂቱም ቢሆን ጥያቄ ውስጥ ማስገባታችን አይቀርም፡፡

በዘንድሮው በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ባለው 29ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ በሆነ መልኩ ትላንትና የነበሩ፣ ዛሬም የቀጠሉና እንዲሁም ወቅታዊ የሆኑ አንዳንድ ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ አጀንዳዎችን ያነገቡ ወገኖቻችንን ተቃውሞዎችንና ጥያቄዎችን አስተውለናል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን/ዋልያዎቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ የገቡበትን አጋጣሚ ተከትሎ የታየው ፖለቲካዊ አጀንዳዎችና ተቃውሞዎች በመጠኑም ቢሆን በእኛም ሆነ በተጫዋቾቻችን መካከል አሉታዊ ስሜቶችን ፈጥሯል፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንም ሰላማዊ በሆነ የስፖርቱ መድረክ ለመንግሥት ያላቸውን ተቃውሞና ጥያቄዎቻቸውን በተለያየ መልክ ለመግለፅ ሲሞክሩም ታዝበናል፡፡

የኢትዮጵያውያኑ ተቃውሞው በዋነኝነት ያነጣጠረው መንግሥት ስፖርታዊ ውድድሩን ለራሱ ፖለቲካዊ አጀንዳ ሊጠቀምበት አቆብቁቧል ከሚል ፍራቻ የተወለደ ነው፡፡ በአንፃሩም ደግሞ የተቃውሞው ሌላ መልክ እንደቀድሞው ሁሉ ከባንዲራ እስከ ሃይማኖት ነፃነት፣ ከሰብአዊ መብቶች ረገጣ እስከ ዲሞክራሲና ፍትሃዊ ምርጫ፣ ከሕገ-መንግሥቱ ይከበር እስከ የራስን ዕድል በራስ ከመወሰን እስከ መገንጠል የመሳሰሉት ፖለቲካዊ አጀንዳዎችና ጥያቄዎች የተነሱበትና የተራገቡበት ነበር፡፡

South Africa Ethiopian fans

ለአፍሪካና ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነፃነትና የልዑላዊነት ምልክት ተደርጎ በሚቆጠረው በአረንጓዴ፣ ቢጫውና ቀዩ ባንዲራችን ላይ የኢህአዴግ መንግስት በአገራችን ያሉ ብሔር ብሔረሰቦች ነፃነትና መብት መከበር እንዲሁም ሕዝቦች እርስ በርሳቸው በወንድማማችነትና በእኩልነት ላይ ለተመሰረተ ግንኙነታቸው መገለጫ ይሆናል ብሎ ባስቀመጠው የኮከብ ምስል ላይ ተቃውሞ ያላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ይህንን ባንዲራ ላለመያዝና ሌሎችም እንዳይዙት ለማድረግ ሲያደርጉት የነበረውን ቅስቀሳ ሰምተናል፣ ተመልክተናልም፡፡ የዚህ የባንዲራችን ጉዳይ ውዝግብም በአገር ውስጥም ሆነ ኢትዮጵያን ባሉበት በውጭ ዓለምም መፍትሔ አልባ ሆኖ እንደቀጠለ ነው፡፡

በረጅሙ ዘመናት ታሪካችን በሰንደቀ ዓላማችን ላይ በአንድ ወቅት የአንበሳና የመስቀል ምልክቶችን የተካተቱበትን ጊዜያትም እናስታውሳለን፡፡ እስከ አሁንም ድረስ አንበሳ ያለበትን ባንዲራ የሚይዙ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን፣ አፍቃሪ ኢትዮጵያ የሆኑ ራስ ተፈሪያውያን፣ አፍሪካ አሜሪካውያንና ጃማይካዎችም መኖራቸውን አሳምረን እናውቃለን፡፡

በሰንደቀ ዓላማችን ዙሪያ ያለው ውዝግብ መፍትሔ አልባ ሆኖ በአንድ አገር ስም የተሰለፉ ሕዝቦች ባለ ምልክትና ምልክት አልባ ባንዲራ በሚል ሁለት ዓይነት ባንዲራዎችን ለማውለብለብ ተገደዋል ወይም ተገደናል፡፡ ብሔራዊ ቡድናችን በተጫወቱባቸው መድረኮችም ሁሉ ደጋፊዎች ይኸው ስሜታቸውን ሲያንጸባርቁ ነው ያስተዋልነው፡፡

ይኸው የባንዲራችን ውዝግብም በተደጋጋሚ በዚህ በአገራችንም ሲንፀባረቅ ታዝበናል፡፡ ምንም እንኳን መንግሥት በአዋጅና በሕግ አስደግፎ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከዚህ ባለ ኮከብ ከሆነው ባንዲራ ውጭ ማንም እንዳይጠቀም ቢወተውትም ያሰበውን ያህል አድማጭ ያገኘ አይመስልም፡፡

‹‹የኢህአዴግ ባንዲራ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን አይወክልም!›› በሚል ስሜት ምልክት አልባ የሆነውን ባንዲራ አንግበው ብሔራዊ ቡድናችንን ለመቀበል በጆሐንስበርግ ኦሊቨር ታምቦ ዓለም አቀፉ አየር መንገድ የተገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻን ዋልያዎቹን በቅርብ ርቀት አግኝተው ፍቅራቸውንና ስሜታቸውን ሊገልጹላቸው አልቻሉም፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ የብሔራዊ ቡድኑ መሪዎች ተጫዋቾቻችንን በሌላ በር ይዘዋቸው በመውጣታቸው መሆኑን በቅሬታ ውስጥ ሆነው ገልጸዋል፡፡

ይኽም ይላሉ እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖች፡- ‹‹መንግሥት ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት፣ ወንድማማችነት… በሚሰበክበት በስፖርቱ መድረክ እንኳን ሳይቀር የተለመደ የመከፋፈል፣ የጎሰኝነትና እኩይ ፖለቲካዊ አጀንዳውን እያራመደ መሆኑን ያስረገጠበት አሳፋሪና ተራ ፖለቲካዊ ቁማር ነው፡፡›› በማለት አስተያየታቸውንና ምሬታቸውን ሲሰጡ ተሰምተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሰንደቀ ዓላማ ላይ ገና የልተፈታ ጥያቄ ያላቸው ወገኖቻችን በአብዛኛው በስታዲዮም ውስጥ ይዘው የገቡት ምንም ምልክት የሌለበትን ባንዲራ ነበር፡፡ በአንፃሩም ደግም ባለ ኮከብ ምልክቱን ባንዲራ ሲያውለበልቡ የነበሩ በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በስታዲየሙ ውስጥ እንደነበሩም ተመልክተናል፡፡ ይኽ እውነታም በአገር ቤትም ጭምር በተደጋጋሚ የተስተዋለና የምናስተውለው ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በስታዲም ውስጥ የኦነግ አባላት የሆኑ ሰዎችም በተለየ ባንዲራ ራሳቸውን ለመግለጽ መሞከራቸውን በቴሌቪዥን መስኮታችን ታዝበናል፡፡ በደቡብ አፍሪካ ኦነግ ናችሁ በሚል ሰበብ ከምድራችን ተፈናቅለናል የሚሉ በርካታ ኦሮሞዎች አሉ፡፡ እነዚህ ኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ‹‹አቢሲኒያ የኦሮሚያ ቅኝ ግዢ ናት››፣ ከቅኝ ግዛት ለመውጣት የምናደርገውን ትግል መንግሥት ከሽብርተኝነት ፈርጆ እኛንና ነፃነት ፋላጊ የሆነውን ሕዝባችንን እያሰረ፣ እያንገላታና ሰብአዊ መብታቸውን እየገፈፈ ነው በሚል መንግስትን አጥበቀው ይከሳሉ፣ ይኮንናሉም፡፡

እነዚሁ የተለያየ አጀንዳና ጥያቄ ያላቸው የመንግሥት ተቃዋሚዎች በዚህ በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ይኸው ፖለቲካዊ ጥያቄያቸውን ይዘው በስታዲየሙ መገኘታቸው ግርምትን አጭሯል፡፡

በተመሳሳይም ደግሞ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም መንግሥት ከሃይማኖታችን ላይ እጁን ያንሳ በሚል Free our Leaders የሚል ቲ-ሸርት ለብሰውና በአበሽ አንጠመቅም፣ መሪዎቻችን ይፈቱ፣ ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ…ወዘተ የመሳሰሉትን መፈክሮች አንግበው በስታዲየም ውስጥ መታደማቸውንም በአግራሞት ውስጥ ሆነን ታዝበናል፡፡

የአገር ቤቱ ፖለቲካዊ ትኩሳትም ወደ ውጭ ዘልቆ በስፖርት መድረኩም እንኳን ሳይቀር ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ አጀንዳዎቻችን መንጸባረቃቸው የነገ ዕጣ ፈንታችን ምን ሊሆን ይችል ይሆን የሚል ጥያቄን እንዳነሳና በአንፃሩም ደግሞ የኢትዮያዊነት የአንድነት መንፈስና ውብ የሆነ አብሮነታችን የተጋረጠበትን አደጋ በስጋት ውስጥ ሆኜ እንዳስብ አስገድዶኛል፡፡

በዘንድሮው ከሰላሳ ዓመታት በኋላ ተሳታፊ በሆንበት በደቡብ አፍሪካ የእግር ኳስ ዋንጫ የሆነውና የታየው ነገር ገና በመካከላችን ሰላምን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን፣ እርቅንና መግባባትን ለማስፈን ረጅም ጉዞ እንደሚጠብቀን ያሳየ ነው ብል ብዙም ከእውነታው የራቅኹ አይመስለኝም፡፡

ለዚህ ጉዞአችን መሳካትና ውጤት ደግሞ ሀገራዊ/ብሔራዊ ራእይ፣ ጠንካራና በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑ የማይናወጽ ጽኑ መንፈስ ያላቸው፣ ከዘረኝነት፣ ከጥላቻና ከአድልዎ የጸዱ ኢትዮጵያውያን ማንዴላዎች፣ ጋንዲዎች፣ ሉተሮች… ወዘተ በእጅጉ እንደሚያስፈልጉን አስባለሁ፡፡  

በሌላ በኩል አዎንታዊ በሆነ መልኩ በዚህ በዘንድሮው በደቡብ አፍሪካው የ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ያስተዋልኳቸው በእጅጉ ደስ ያሰኙኝና ልቤን የነኩኝ አንዳንድ መልካም አጋጣሚዎችም ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በየአገራቸው ሰንደቀ ዓላማ በአንድነት ሆነው ለዋልያዎቹ ያላቸውን ድጋፍና መልካም ምኞታቸውን ለመግለፅ በስታዲየሙ ውስጥ በመገኘት ያሳዩት ፍቅርና የወንድማማችነት መንፈስ በእጅጉ ሊጠቀስና ሊመሰገን የሚገባው ነው፡፡

እነዚህ በባህል፣ በታሪክ፣ በሃይማኖት፣ በቋንቋና በደም የተሳሳሩ ሕዝቦች በመንግሥቶቻቸው መካከል ያለውን የጠላትነት መንፈስ ወደጎን ትተው በስፖርቱ መድረክ ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለአንድነትና ለወንድማማችነት… ያላቸውን አዎንታዊ ስሜትና ፍላጎት የገለጹበት ሁኔታ በእውነት ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡

በተቃራኒው እስካሁን ድረስ እያሰገረመኝ ያለው ነገር ደግሞ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፡- ‹‹ከኤርትራ ጋር ለመደራደርና ሰላምን ማውረድ አስመራም ድረስ ቢሆን እንኳን እሄዳለሁ፡፡›› ባሉ ማግስት፣ ‹‹በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሁለቱ አገራት የሚያድረጉትን ጨዋታ በሌላ ሦስተኛ አገር እንጂ በአስመራ ለማድረግ ፈቃደኛ አይደለንም›› የሚለውን መረር ያለውን መግለጫ ሳስብ ደግሞ የመንግሥታችን የሰላም አቋም ግራ ያጋባኛል፡፡

እናም ‹‹ሰፖርት ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለወንድማማችነትና ለአንድነት…›› የሚለው መርህ በመንግሥት ባለስልጣኖቻችንና በስፖርቱ ኃላፊዎች ዘንድ ትርጓሜው ምን እንደሆነ በግልፅ ያስረዱን ዘንድ እንድንጠይቃቸው እንደዳለን፤ ሊያውም ደግመን ደጋግመን ነዋ!

Ethiopian and Eritrean football fans in South Africaበተመሳሳይም ከሁለት አስርተ ዓመታት የእርስ በርስ ጦርነት፣ መፈራረስና ኹከት በኋላ ዳግም እንደ አገር በሁለት እግሯ ለመቆም ጉልበቴ በርታ በርታ እያለች ያለችው የቅርብ ጎረቤታችን የሆኑት ሶማሊያኑም ልክ እንደ ኤርትራውያኑ ሁሉ የዋልያዎቹን ማልያ ለስብሰው ብሔራዊ ቡድናችንን ለመደገፍ ከኢትዮጵያን ወገኖቻችን ጋር የተገኙበት አጋጣሚ ይኸው ስፖርቱ በዓለም አቀፍ መድረክ በአገራትና በሕዝቦች መካከል ሰላምን፣ አንድነትንና፣ ወንድማማችንትን በማሰፈን ረገድ ያለውን አዎንታዊ ተጽእኖ እንድንታዘብ ያደረገ ልዩና ተወዳጅ አጋጣሚ ነበር፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ በቀደመ ታሪኳ በስፖርቱ መድረክ አፍሪካውያን ነፃነታቸውን እንደዲቀዳጁና ከጭቆና ቀንበር እንዲላቀቁ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ ያሰማች አገር ናት፡፡ በዓለም አቀፉ መድረክም ስፖርት ከዘረኝነት፣ ከአድሎና ከጭቆና የፀዳ የሰላምና የወንድማማችነት መድረክ እንዲሆንም በብርቱ የታገለች አገር መሆኗን የታሪክ መዛግብት በሰፊው ይጠቁማሉ፡፡

እንደእነ ይድነቃቸው ተሰማ ያሉ የአፍሪካ የእግር ኳስ አባትና መስራች፤ ስፖርቱ የሰላም፣ የአንድነት፣ የወንድማማችነት፣ የትብብር… ወዘተ መድረክ እንዲሆን በብርቱ የሰሩና የታገሉ መሆናቸውንም ማስታወስ ይኖርብናል፡፡

በተደጋጋሚ በአፓርታይድ ዘረኝነት መዳፍ ስር ስትማቅቅ ለነበረችው ደቡብ አፍሪካ ነፃ መውጣት ከፖለቲካው መድረክ ባሻገር በስፖርቱ መድረክ ድምፅዋን ያሰማችውና በብርቱ የተሟገተቸው አገራችን ኢትዮጵያ፣ በዋልያዎቹ አማካኝነት ለአፍሪካ አገሮች ሁሉ ነፃነት ምልክት የሆነው አረንጓዴው፣ ቢጫና ቀዩ ሰንደቀ ዓላማችን በደቡብ አፍሪካ ሰማይ ላይ ከፍ ብሎ መውለብለቡ አገራችን ለአፍሪካ አገሮች ነፃነት ያደረገችውን ታላቅ አስተዋጽኦ ዳግም እንድናስታውስ የሚያደርገን ነው፡፡

ከግማሽ ምዕተ ዓመታት በፊት እምቢ ለነፃነቴ፣ እምቢኝ ለሕዝቤ፣ እምቢኝ ለእናት ምድሬ መከራና ግፍ፣ እምቢኝ ለዘረኝነትና ለጭቆና. . . በማለት እረ ጥራኝ ዱሩ፣ እረ ጥራኝ ጫካው በማለት በቀደሙ አባቶቻችን የኢትዮጵያዊነት ወኔና የአይደፈሬነት ጽኑ መንፈስ መንፈሳቸው የሸፈተባቸው፣ የአፍሪካ ብርቅዬ ልጅና ነፃነት አርበኛው ማንዴላ የከተሙባት ኢትዮጵያችን፤ ዛሬ ደግሞ በዋልያዎቹ አማካኝነት፣ በማንዴላና በሕዝቦቻቸው የአይበገሬነት መንፈስና ትግል ፍሬ ነፃነቷን ተጎናጽፋ በዓለም መድረክ Rainbow Nation በሚል ቅፅልን ባገኘችው በደቡብ አፍሪካ መገኘታቸው ልዩ የሆነ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ለማለት እደፍራለኹ፡፡

በዚህ ቡድናችን ከሰላሳ ዓመታት ልፋት፣ ድካም፣ ቁጭትና እልህ… በኋላ ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው የ29ኛው አፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ ለመሆን ልዩና ታሪካዊ የሆነ ዕድልን ላገኘው ብሔራዊ ቡድናችን፣ በአፍሪካም ሆነ በዓለም አቀፉ መድረክ የበለጠ ብቃቱን የሚያሳይበት መልካም ዕድል እንዲገጥመው እመኛለኹ፡፡

የስፖርቱ መርህ የሆነው ‹‹ሰላም፣ ፍቅር፣ ወንድማማችነት፣ አንድነት…›› ጽንፈኝነትና ጥላቻ በሚያይልበት በአገራችን የፖለቲካ ሜዳ ላይ የጥላቻ፣ የመወጋገዝና የጠላትነት አረምና ጭንገፋ ከስሩ ተንቅሎ የፍቅር፣ የሰላም፣ የአንድነትና የወንድማማችነት… ፍሬ አፍርቶ የምናይበት እውነተኛ የትንሳኤና የህዳሴ ዘመንን ለእናት ምድራችን ኢትዮጵያ ይሁን! አሜን! ይሁን!!

ሰላም! ሻሎም!

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/5895

posted by Tseday Getachew

Advertisements

በጉርዳፈርዳ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው የሰብአዊ መብት ረጋጣ ቀጥሏል

ጥር ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኢትዮጵያ ቤንች ማጂ ዞን በጉርዳፈርዳ ወረዳ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው የሰብአዊ መብት ረገጣ መቀጠሉ ተገለጸ።

በወረዳው ባለፈው ታህሳስ አንዲት የ8 ልጆች እናት በጥይት ሲገደሉ፣ ሁለት ህጻናት በመስተዳድሩ መኪና ተገጭተው መሞታቸውን የመኢአድ ም/ሊ/መንበር አቶ ወንድማገኝ ደነቀ ለኢሳት ገልጸዋል።

ታህሳስ 28/ 2005 ከምሽቱ 4 ሰአት ሲሆን 5 መሳሪያ የታጠቁ ወተዳሮች የ8 ልጆች እናት የሆኑትን ወ/ሮ አይቼሽ ስጦታውን በመኖሪያ ቤታቸው እንደገደሉዋቸው  ነው ም/ ሊቀመንበሩ የተናገሩት።

ጥር 15 ቀን 2005 ዓ/ም ደግሞ የ4 እና የ7 አመት ህጻናት በመስተዳድሩ መኪና ተገጭተው ህይወታቸው ማለፉን ከአቶ ወንድማገኝ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሎአል።

ሌሎች 23 የአማራ ተወላጆች በወህኒ ቤት በመሰቃየት ላይ መሆናቸውንም_ የመኢአድ ተቀዳሚ የፐም/ል ፕሬዚዳንቱ አክለዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማናገር ብንሞክርም አልተሳካልንም።

 posted by Tseday Getachew

ምርጫ ቦርድ እንደተጠበቀው ተጨማሪ የመመዝገቢያ ቀን ሰጠ

ጥር ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በተመዝጋቢዎች ድርቅ የተመታው መጪው የወረዳና የአካባቢ ምርጫ ምዝገባ ለሁለት ቀናት የተራዘመ ሲሆን፣ ኢህአዴግ ካድሬዎች በዩኒቨርስቲዎች ሳይቀር እየገቡ፣ ግለሰቦች እንዲመዘገቡ ካልሆነ ግን ችግር እንደሚደርስባቸው እየገለጡ ነው።

የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ካድሬዎቹ በዩኒቨርስቲዎች እየዞሩ ሰራተኞችን ተመዝግባችሁዋል አልተመዘገባችሁም እያሉ ሲጠይቁ ውለዋል።

የኢህአዴግ ካድሬዎች በምርጫው ያልተመዘገቡትን ” ከእኛ ጎን ናችሁ ወይስ ከአሸባሪዎች ” በማለት እያስፈራሩ እንደሚገኙ ኢሳት ያነጋገራቸው በርካታ ሰዎች መግለጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

33 የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ለኢህአዴግ ምርጫ አጃቢዎች አንሆንም በማለት ራሳቸውን ለማግለል መወሰናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።

ኢህአዴግ በበኩሉ ተቃዋሚዎች በምርጫው የማይሳተፉት ጥቅም ስለማያገኙበት ነው በማለት ተቃዋሚዎች ለወሰዱት እርምጃ መልስ ሰጥቷል።

ምርጫ ቦርድ የተመዝጋቢዎች ቁጥር በእቅዱ የተቀመጠውን ያሟላ ነው በማለት ቢገልጽም ፣ ኢሳት ያገኘው መረጃ እንደሚያሳየው እስካሁን የተመዘገበው ህዝብ ከታቀደውም ከግማሽ በታች ነው።

posted by Tseday Getachew

የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎችና አባ ዝምታዎች ትንሣኤ

 

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

በአቦሸማኔዎች ምድር የጉማሬዎች (አባ ዝምታዎች) ዓለም

በአዲስ ዓት መግቢያ ጦማሬ ላይ 2013ን ‹‹የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ዓመት››(የወጣቶቹ)  ብዬው ነበር፡፡ በዚህ ዓመትም የኢትዮጵያን ወጣቶች ለማስተማር፤ባሉበት ለመድረስ፤ለማሳሰብም ቃል ገብቼ ነበር:: የኢትዮጵያም የምሁራን አምባ ይህንኑ ለማድረግ ጥረት እንዲያደርጉ ተማጽኜ ነበር (በተለይም በከፍተኛው ጣርያ ላይ ያለነውን ምሁራን)፡፡ በተመሳሳይ ወጣቱን እንዲደርሱት አሳስቤም ነበር፡፡ ከዚህ ባለፈም ተማጽኖዬ ከሰፊው የጉማሬ ትውልድ ጋር (መንገዱ የጠፋው ትውልድ) እራሱን በማግኘት መስመሩን አስተካክሎ ጉዞውን እንዲያሳምርና ወጣቱን እንዲረዳ  ምኞቴን አስታዉቄ  ነበር፡፡

በጁን 2010 በግልጽ ባሰማሁት (የኢትዮጵያን ምሁራን ምን በላቸው?) የእንዳዳን ጥሪ (S.O.S)  እና አሁን ደሞ ‹‹የተሳካላቸውን ግድ የለሽ ምሁራን›› ጥሪው ጥሩ አቀባበል አላገኘም:: በተለይም በ‹‹ጉማሬያዊያን›› ላይ ያቀረብኩት ጥያቄ: በጨካኞች ሰው አጥፊዎች ላይ በሰብአዊ መብት ግፍ ፈጻሚዎች ላይ፤የአብረን እንሁን  እንስራ ተማጽኖዬ  በጣሙን የከረረ እምቢታና ጆሮ ዳባ ልበስ መልስ ነው የተሰጠው፡፡ ከአንዳንድ ጉማሬዎች ተረት መሰል አባባል እንደተረዳሁት እራሳቸውን በማመጻደቅ ከጳጳሱ ቄሱ እንዲሉ አይነት፤‹‹እከሳለሁ›› በሚል መልኩ ጣታቸውን ወደ ሌላው መቀሰርንነው፡፡ አንዳንዶች ሲተቹ እንዲያውም እራሴን በከፍተኛው ቦታ ላይ በማስቀመጥ፤ ለታይታ ብቻ በመጻፍ፤ እራሴን ለማስተዋወቅና ተወዳጅነትን ለማግኘት እንደምንቀሳቀስ አይነት ሃሳብ ሰንዘረዋል፡፡ በጉማሬዎች መሃል የተፈጠረው ድንጋጤና ስጋት፤እኔ ጉዳዩን ማንሳት እንዳልነበረብኝና ያደረግሁትም ሕዝባዊ ጥረቱን ክህደት፤ ስም ማጥፋትና የሚያሳፍር በመሆኑ፤ በራሳቸው የፈጠሩትን ሽባነትና ፍርሃት ጨርሶ ማንሳት እንዳልነበረብኝ አትተዋል፡፡ አንዳንዶችም ይህን አቦሸማኔና ጉማሬ የሚለውን  ዘይቤያዊ አነጋገር በመጠቀም፤ በወጣቱን በባለዕድሜው መሃል ልዩነትን ፈጠርክ ብለው ይኮንኑኛል፡፡ በኔ እምነት ግን ከሼክስፒር አባባል ልዋስና ‹‹ሁለቱም ወገኖች የምሬታቸው ሚዛን እኩልነው››::

የኔ እምነትና ፍላጎት ያንን ጥንታዊ የዝምታ ባህል ሽፋን ለመግለጥና አውነትን ብቻ ለገዢዎች ተብሎ ሳይወሰን፤እራሳቸውንም ለዝምታ መዳረግን ለመረጡትም ጭምር ነው፡፡ በዝምታ፤ ትክክለኛውን በስህተቱ መተካትም ትክክል አይደለም ብዬ አበክሬ አምናለሁ፡፡ በጸጥታ እኩይ ደባን እንደ ድል ማመንም፤በራሱ እኩይ ደባ መፈጸም ነው፡፡ ግፍን በዝምታ መመልከትም የለየለት የሞራል ሕገወጥነት ነው፡፡ ጥላቻን ተግባራቸው ካደረጉም ጋር መወገን በራሱ የጥላቻውአካል መሆን ነው፡፡ የሕግ ምሳሌያዊ አባባልም ‹‹ዝምታ ፈቃድ አለያም መስማማት ነው››፡፡ በይሉኝታ ብቻ

በዝምተኞች የሚረጨው ውሃ በተጨቋኞች ልብና ሕሊና ውስጥ የሚፈላውን መከራና ቁጣ የሚያቀዘቅዝ አይሆንም፡፡ ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ እንዳለው፤ ‹‹እንደ ዝምታ የባለስልጣናትን ጉልበት የሚያጠናክር ምንም የለም››፡፡ እኔ ደግሞ‹‹አምባገነናዊ አስተዳደርን እንደ ዝምታ የሚያጠናክረው የለም እላለሁ፡፡ ማንም ቢሆን ጨቋኞችን በዝምታ ቋንቋ ሊያነጋግራቸው አይሆንለትምና፤  እውነት በሆነ የእምቢተኛነት ቋንቋ ሊያነጋግራቸው ይገባል፡፡ ዝምታ በምንም መልኩ የግብዞችና የአጭበርባሪዎች የመጨረሻው መሸሸጊያ ሊሆን አይገባም፡፡

አንዳንድ አበረታች የእድገት አዝማሚያዎች ይታያሉ፡፡ ባለፉት ሳምንታት በርካታ የነጻነት ብርሃን የፈነጠቁ አስተዋጽኦዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ጨቋኝ ሥርአት ላይ እየታዩ ናቸው፡፡ ሙክታር ኦማር ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› በሚለው የሃሰት ጽነሰ ሃሳብ ላይ፤ አውዳሚ ወይም አጥፊ የሆነ ግን እውነት ሂስ አስነብቦን ነበር፡፡ ‹‹በወቅቱ በኢትዮጵያ ውስጥ አለ የሚባለው እድገት በተገቢው አስተሳሰብ ሲመዘን ከውጭ መንግሥታት በሚቸር ዳረጎት እንጂ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ በሚጮኸው የመፈክር ጋጋት አይደለም::በትክክለኛው አስተሳሰብ የማርክሲዝም ኮሚኒዝምን

ግንኙነት እና የአብዮታዊ ዴሞክራሲን ትስስር በሚገባ ያሳየናል፡፡” ሙክታር ሲያጠቃልል፤ “ከመለስ ዜናዊ  አስተሳሰብ ጋር ፍቅር ያላቸው ምሁራን ምክንያታዊ በማድረግ አስደንጋጫ የሆነውን የሰብአዊ መብት ሬኮርዱን ለመዘንጋት ካሰቡ እነሱም በፈቃደኝነት አለማወቅ ወንጀለኞች ናቸው፤ አለያም ከፕሮፌሰር ጆን ግሬይ ‹‹መሰራታዊ እኩይነት ከእድገት ክትትል ይወለዳል›› ከሚለው ምሁራዊ ማሳሰቢያ ጋር አይስማሙም፡፡

የኢትዮ ፎረም ድሕረ ገፅ  ዋና አዘጋጅ ‹‹ልማታዊው ኪስ አውላቂ ›› በሚል የአማርኛ ፅሁፍ፤ የአባይን ግድብ ለመጨረሻ ተብሎ በቢሊዮን ዶላር የሚሰበሰብለት፤በከንቱነት የሚነገርለት የሬኔሳንስ ቦንድ ግልባጭ መሆኑን በማስረጃ ያቀርብልናል፡፡ ሕዝቡ በችጋር እየተቆላና በጨቋኞች አለ አግባብ  እየተኮነነ የልማት ግድብ አለ ማለት ከንቱ ነው፡፡

ከእኔ በበለጠ ብልሆች የሆኑት የምከተለው ፍሬ ቢስ አቅጣጫ እንደሆነ ይነግሩኛል፡፡ ፊትህ ደም እስኪመስል መጮህ፤ማሳሰብ ትችላለህ፤ያም ሆኖም ግን ከኢትዮጵያ ጉማሬዎች ሰፋ ያለ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ፤ ጥብቅና፤ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ ብለህ ማመን ግን፤ ከቀይ ስር ደም አንደመጭመቅ የሚቆጠር ነው፡፡ ብልሆቹ እንደሚሉኝም፤ እነ አባ ዝምታን የዝምታ ዓለም ዝም ብሎ በአቦሸማኔዎች መሬት መጻፍ ይሻላል ነው::  እነሱን ከመጨቅጨቅ ዝም ብሎ ፤ እኩይነትን ላለመስማት ክፋትን ላለማየት፤ክፉ ላለመናገር በፈጠሩት የማስመሰያ አስደሳች መኖሪያቸው ዓለም እንዲኖሩ መተው ይሻላል ይሉኛል፡፡

እና እንደዚያ ላድርግ?

ከአቦሸማኔዎች ጋር ዕምንትን  መልሶ  መገንባት

ትልቅ ችግር አለን! በጣም ትልቅ፡፡ ‹‹እኛ›› ሁላችንም አቦሸማኔዎችና ጉማሬዎች ነን፡፡ እውነት እውነቱን እንነጋገር፡፡ ጉማሬዎች ከአቦ ሸማኔዎች ጋር የነበራቸውን እምነት አፍርሰዋል፡፡ አቦሸማኔዎች በጉማሬዎች ክህደትተፈጽሞብናል ይላሉ፡፡ አቦሸማኔዎች ተገፍተናል ጫና ተደርጎብናል ይላሉ፡፡ አቦሸማኔዎች ታማኝነታቸውና መስዋእትነታቸውበጉማሬዎች ተንኮል ተተክቶብናል ይላሉ፡፡ የአክብሮታችንና የታዛዥነታችን መልሱ ማንቋሸሽና ድፍረት ሆኗል ይላሉ፡፡ አቦሸማኔዎች፤ ጉማሬዎች ትህትናቸውን በአድርባይነት፤ ሃሳብ ተቀባይነታቸውን በግትርነት፤ ሰብአዊነታቸውን

በክብረነክነት መልሰውልናል ይላሉ፡፡ አቦሸማኔዎች፤ ክህደት፤ ለእስራት ፤ተንኮል፤ውሸት፤መደናገር በጉማሬዎችተፈጸመብን ይላሉ፡፡ አቦሸማኔዎች የጉማሬዎችን ተጠያቂነት በማንሳታችን ተኮንነናል ይላሉ፡፡ እራሳቸውን በነጻ በመግለጻቸው ሰበብ በጉማሬዎች ዝምታ ለግፍ ስራ ተዳርገናል ይላሉ፡፡ አቦሸማኔዎች በጉማሬዎች ላይ እምነታቸውን አጥተዋል፡፡ ከበርካታ ኢትዮጵያዊያን አቦሸማኔዎች የምሰማው የስሞታ መግለጫ ይህን የመሰለ ነው፡፡ አቦሸማኔዎችይህን ማንሳታቸው፤ ቅሬታቸው፤ ስሜታቸው ትክክል ነው? ጉማሬዎችስ ይህን ያህል ደባ ፈጽመዋል?

ስለ መተማመን መልሶ ግንባታ ከመነጋገራችን በፊት በቅድሚያ ወጣቱ ከባለእድሜዎቹ ጋር ስላለው አለመግባባት ትንሽ እናንሳ፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች በየቀኑ በግዴታ የንስሃ ጸሎት በሚሰሙበትና የሚመዘኑትም በተፈጥሮ ስብእናቸው ሳይሆን በዘራቸው እንዲሆን በሚገደዱበት ቦታ ነው፡፡ ግላዊነት፤ዜግነት፤ሰብአዊነት የሌላቸው ዘረኝነት ብቻ የነገሰበትነው፡፡ ለዚህም ነው ‹‹የዘር ፌዴራሊዝም›› የሚባል መኖርያ የፈጠሩላቸው፡፡ ወጣቶቹ በሕይወት የመኖርያቸው ጣቢያ የተወሰነው በአእምሮ ብስለታቸው ችሎታ ሳይሆን፤ በነዚያ ማሰብ በተሳናቸው የግፍ አምባ ገዢዎች ፈቃድ መሆኑን በሚገባ ተረድተዋል፡፡ከአጋሮቻቸው ጋር በእኩል ከሚያስተሳስራቸው ሁኔታ ጋር ሳይሆን በሚያለያያቸው ላይ በይበልጥ እንዲያተኩሩ ተገድደዋል፡፡በዚህ እጅጉን እኩይ በሆነ ሰይጣናዊ አስተሳሰብና አካሄድ የሚያዳምጡት ነገር ቢኖር በዝምታ ከታገዱት የሚወጣውን የዝምታ ዱለታ ብቻ ነው፡፡ ከኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ጋር አመኔታን መልሶ ለመገንባት በቅድሚያ ዝምታችንን በአምቢተኛነት በመለወጥ፤ እራሳችንን ከተለጎመበት በማላቀቅ፤ በማያወላውል ቆራጥ አቋም ላይ ማሰለፍ አለብን፡፡

ከወጣቶቹ ጋር እምንት ከመገንባታችን በፊት ከራሳችን ጋር መተማመን መቻል ይኖርብናል፡፡ ማለትም ወጣቱን ወገናችንን ከማዳናችን አስቀድሞ እራሳችንን ማዳን መቻል፡፡ ከራሳችን ጋር መተማመን ከመገንባታችን በፊት፤ ስለፈፀምነው ስህተትና ቸል ስላልነው ጉዳይ እራሳችንን ይቅር ማለት መቻል፡፡ በራሳችንና ትክክለኛነት በመተማመን፤ የነጻነትንና የሰብአዊ መብትን አስፈላጊነት አምነን መቀበል፡፡ ወጣቱ ወኔውን እንዲያጠናክር ከመንገራችን በፊት እኛ እራሳችንከፍርሃታችን መላቀቅ፡፡ ወጣቶቻችን እንደ አንድ እናት ኢትዮጵያ ልጆች መዋደድ እንዳለባቸው ከመንገራችን በፊትከውስጣችን ጥላቻን ማጥፋት፡፡ ከራሳችን ጋር መተማመን ለመፍጠር መቻል እንድንበቃ አስቀድመን ከምቾት ከልላችን፤ከምቾት ስብስባችን፤ ከምቾት አምባችንና ጎሳችን መላቀቅ፤ ቀደም ሲል ልናደርገው ሲገባን በችልታ ሳናደርገውየቀረውን ተግባር ለመፈጸም ዝግጁ መሆን አለብን፡፡  ማንኛቸውንም ጉዳይ ማድረግና መፈጸም የሚኖርብን እውነትና ትክክል ስለሆነ ብቻ እንጂ ከሌሎች ስለተፈቀደልን ወይም ስለተከለከልን ሊሆን ጨርሶ አይገባም፡፡ ጆርጅ ኦረዌል እንዳለው ‹‹በዓለም አቀፍ ማታለል ወቅት፤ እውነትን ገልጦ መናገር የእምቢታ ተግባር ተደርጎ ይታያል›› እንዲያ ከሆነም፤ ሁላችንም እምቢተኞች ሆነን ስልጣን ላይ ለተኮፈሱት፤ አቅመቢስ ለሆኑት፤ጉልበታቸውንና ሃይላቸውን

ለተነጠቁት፤ ለየእራሳችንም እውነቱን ልንናገር ይገባል፡፡

ለአቻ ጉማሬ ወገኖቼ ሚዛናዊ ለመሆን፤ ለግፈኞች እውነቱን መናገር አንዳችም ለውጥ አያስገኝም በሚል እምነት ዝምለማለት መምረጣቸውን ይናገራሉ፡፡ ለግፈኞች እውነትን መናገር ጊዜ ማጥፋት ነው ይላሉ፡፡ ግፈኞች የሚያዳምጡትምሆነ ለመስማት ፈቃደኛ የሚሆኑት የመሳርያ ጩኸትን ብቻ በመሆኑ፤ ከነሱ ጋር ስለእውነት መናገር መመከሩ ከንቱድካም ነው ይላሉ፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ እኔ ልዩነት አለኝ፡፡ ለነጻነት፤ ለዴሞክራሲ፤ለሰብአዊ መብት በሚደረግ ትግል፤ መናገር የሰዎችን ሕሊናና ልብ ከጠመንጃ፤ ከመድፍ፤ ከጦር አውሮፕላን በበለጠ ያሸንፋል፡፡ ለዚህም ታሪክ እራሱ ምስክር ነው፡፡አሜሪካ በቪየትናም ለሽንፈት የተዳረገው የጦር አውሮፕላን፤የጦር መሳርያ፤ ቴክኒካዊ ብቃት፤ ወይም የገንዘብ አቅም በማጣቱ አልነበረም፡፡ አሜሪካ በጦርነቱ ለሽንፈት የተዳረገው የቪየትናማዊያንን ልብን ሕሊና ለማሸነፍ ባለመብቃቱ ነው፡፡

ሕሊናንና ልብን ለማሸነፍ በሚካሄድ ጦርነት ቃላት በጣሙን የጠነከሩ መሳርያዎች ናቸው፡፡ቃላት እንደምንፈጥራቸውና ገጣጥመን እንደምንጠቀምባቸው ቀላል አይደሉም፡፡ቃላት እጅጉን ሃያል ናቸው፡፡ቃላት ጨለማውን ያበራሉ፤የተጨፈነን አይን፤ የታሸጉ ዓይኖችን፤የተደፈኑ ጆሮዎችን፤ የተለጎሙ አፎችን ይከፍታሉ፡፡ ቃላትያነሳሳሉ፤ያሳውቃሉ፤ ሕይወት ይዘራሉ፡፡ በታሪክ ከፍተኛ ቦታዎች ከተሰጡት አንዱ የሆነው የጦር መሪ ናፖሊዮን ቦናፓርቴ፤ከጠብመንጃ ይልቅ ቃላቶችን አምርሮ ይፈራ ነበር፡፡ ለዚህ ነው ‹‹ከአንድሺህ ጦር መሳርያዎች፤አራት የጠላት ጋዜጦች ሊፈሩ ይገባል›› (ወይም ከሺ ጦረኛ አንድ ጋዜጠኛ ይፈራል) ያለው፡፡ ለዚህ ነው እኔም፤ ውድ የተሳካላችሁ ምሁራን ወዳጆቼም ሆኑ ሌሎችምበምር የዴሞክራሲ፤ የነጻነት፤ የሰብአዊ መብት፤ የሕግ የበላይነት መከበር፤ ደጋፊዎች ነን የሚሉት ሁሉ መነጋር፤ደግሞም መናገር፤ መናገር አሁንም መናገር ያለባቸውና ከዝምታ መጋረጃ ጀርባ ተጠቅልለው መሸሸግ የለባቸውም የምለው፡፡ እኔ የምለው፤ ዕውነትን ለግፈኞች ተናገሩ ነው::   እምነትን በሰብአዊ  መብት መለኮትነት፤ በዘር አክራሪነት ክፉነት ላይ አሳምኑ፤በግፊት፤በወንጀል ድርጊት ፊት፤ስልጣናቸውን አላግባብ በሚጠቀሙና ሕዝባዊ መብቶችን በመግፈፍ ለእኩይ ምግባር በተሰለፉ ፊት ጨርሶ ለዝምታ ቦታ አትስጡ፡፡

ከአቦሸማኔዎች ጋር መተማመንን መገንባት በጣሙን አስፈላጊ ነው፡፡ በጉማሬዎችና በአቦሸማኔዎች መሃል ያለው የትውልድ ክፍተት ጉዳይ አይደለም፡፡ያለው የመተማመን ክፍተት ነው፡፡የግምት ክፍተት፤የመግባባት ክፍተት፤ ከፍ ያለ የርህራሄ ክፍተት አለ፡፡ አቦሸማኔዎችንና ጉማሬዎችን የሚከፋፍላቸውን ክፍተት ለመዝጋት በርካታ ድልድዮች መሰራትአለባቸው፡፡

የ ”አቦጉማሬ” ትውልድ ትንሳኤ

‹‹አዲስ›› የ “አቦጉማሬ” ትውልድ አየመጣ ነው:: “አቦጉማሬ” አስተሳሰቡን፤ድርጊቱን፤ ጸባዩን ሁሉ እንደ አቦሸማኔ ለማድረግ የሚጥር  ማናቸዉም ሰው ነው፡፡ የጉማሬዎችን ገደብ እያወቀ ግን ለአንድ ግብ በአንድ ዓላማ አብሮ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ አቦሸማኔም: አቦጉማሬ ነው፡፡ “አቦጉማሬዎች” ድልድይ ሰሪዎች ናቸው፡፡ትውልድን ለማቀላቀል ወጣቱን ከባለእድሜው ጋር ለማድረግ ድልድይ ይሰራሉ፡፡ዴሞክራሲን፤ነጻነትን፤ ሰብአዊ መብትን ለማስከበር የሚጥሩ ሰዎችን ለማገናኘት ድልድይ ይሰራሉ፡፡ በዘር ገደል  የተከፋፈሉትን ለማገናኘት አግድመት ድልድይ በመስራት ከታሰሩበት የዘር ወህኒ ቤት ደሴት ያሸጋገራሉ ያገናኛሉ፡፡ የቋንቋ ሰርጥን  ሃይማኖትን እና ክልልንን ያቀራርባሉ፡፡ ድሃውን ከሃብታሙ ለማቀራረብ ጥራሉ፡፡ የብሔራዊ አንድነትን ድልድይ በመገንባት ሁሉንም ያስማማሉ፡፡ በሃገር ውስጥ ያለውን ወጣት በዲያስፖራ ካለው ወጣት ጋር ለማስተሳሰር ድልድይ ይሰራሉ፡፡ “አቦጉማሬዎች” ማህበራዊና ፖለቲካዊ  አውታር በመፍጠር ለወጣቱ የፈረጠመ ጉልበት ይሰጡታል፡፡

አንተስ አቦጉማሬ ነህ ወይስ ጉማሬ?

አቦጉማሬ የምትሆነው እምንትህ፡-

ወጣቱ ትውልድ የሃገሪቱ የወደፊት ተስፋ መሆኑንና ባለእድሜዎች ደግሞ የሃገሪቱ ያለፈ ጊዜ መሆናቸውን ካመንክ፤

መጪው ትውልድም ጊዜም በጣም የተሻለና እጅጉንም አስፈላጊነቱን ካመንክ፤

የሰው ዋጋው የሚወሰነው ከስሙ/ስሟ ጋር በሚለጠፈው ተቀጥላ ሳይሆን ወገኑ ለሆነው ሰብአዊ ፍጡር ስለ ሰብአዊ

መብቱ መከበር ለመቆም ባለው ቆራጥ ወገናዊነት ፤ጥሩ ባህሪ፤ትህትና፤ ህዝባዊ ተግባር፤ ትብብር፤ የሰው ችግር

የሚገባው፤ይቅር ባይ፤ ታማኝነት፤ክብር፤ ሃሳባዊነት፤ተጣማሪነት፤ እና ግልጽነት ያለው በመሆኑ ሊሆን ይገባል የሚል

ከሆነ ነው::

አቦጉማሬ የምትሆነው ሁኔታህ

ግልጽ አእምሮ፤ተለዋጭ፤እና ትሁት ስትሆን፤

ከተለያዩ እድሜ ካላቸው፤ ከተለያዩ ዘር፤ ሃይማኖት፤ ጾታ፤ እና ቋንቋ ተናጋሪዎች ጋር አዲስ ሃሳቦችን

የምትቀበልና ለመግባባት የምትችል ከሆነ፤

ከምቾት አምባህ ወጥተህ አስቸጋሪ ምርጫ ውስጥ ለመቀላቀል ፈቃደኛ ከሆንክ፤

ያልከውን የምትሆንና የምትለውን ለመሆን በቆራጥነት የምትቆም እንጂ በመዘላበድና በአሉባልታ፤ በአገም ጠቀም ጊዜ የማታጠፋ ከሆንክ፤

ከነገ ይልቅ በዛሬው ለመጠቀም ፈቃደኛና ዝግጁ ከሆንክ፤

ወጣቱንም ሆነ ሌሎችን በጥፋታቸው ከመውቀስህ በፊት በፈጸምከው ድክመት እራስህን ለመውቀስ ዝግጁ ከሆንክ፤

ያለፈውን አጉል ትምህርት በመርሳት አዲስ ትምህርት ለመማር ጉጉ ከሆንክ፤

ምቹ ጊዜ በማጣት ከማማረር ምቹውን ጊዜ ለማግኘት የምትጥር ከሆንክ፤

ሁኔታዎችንና እምንት ለማዳበር የሚችለውን ለማንጸበራቅ እንጂ የማይቻለወን የማታማርር ከሆንክ፤

ዓለም በማያቋርጥና በፈጣን ለውጥ ላይ መሆኗን በመገንዘብ ለመለወጥ ባለመቻልህ ተወቃሹ አንተው ብቻ እንጂ ሌላ

አለመኖሩን ከተገነዘብክ ነው፡፡

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/5886

posted by Tseday Getachew

 

“የመበስበሱ በሽታ ሁሉም ዘንድ ነው”

ሻዕቢያው በረከት ህወሃትን ሊነዱት ይሆን?

bereket vs sebhat

የአቶ በረከት ስምዖንና የአቶ ስብሃት ነጋ የደፈጣ ውጊያ ገሃድ መውጣቱን የሚያመላክት መረጃ ይፋ መሆኑን ተከትሎ በህወሃት መንደር ውስጥ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል። ጉዳዩን የሚከታተሉ እንደሚሉት ልዩነቱን ለማርገብ በከፍተኛ ደረጃ ጥረት ቢደረግም ሊሳካ አልቻለም።

ከፍተኛ ስልጣን የያዙትንና አቶ መለስ ለመተካካት ያዘጋጇቸውን አዳዲስ አመራሮች፣ በቅርቡ ደንብና ህግ በመጣስ ሹመት የሰጡዋቸውን ጨምሮ የሰራዊቱን አዛዦችና ደህንነቱን ከጎናቸው ያሳተፉት ክፍሎች የተፈጠረው ልዩነት እልባት ማግኘት ይገባዋል የሚል አቋም መያዛቸውን የሚጠቁሙ ክፍሎች እነማን ተለይተው እንደሚመቱ ለመገመት አስቸጋሪ መሆኑንን ይገልጻሉ።

“ፓርቲያችን ከእንጥሉ በስብሷል” በማለት ከዛሬ አስራአንድ ዓመት በፊት በአገር ክህደት ሊያስወግዷቸው የተነሱትን ጓዶቻቸውን የረቱት መለስ የተጠቀሙበት ዋንኛ ስልት አባይ ጸሃዬን “ከውህዳኑ” ጋር በማሰለፍ ነበር። ዛሬ ለህወሃትና ለትግራይ ህዝብ በትግርኛ ቋንቋ ተጽፎ ተሰራጨ የተባለውና ይህንኑ መረጃ ዋቢ በማድረግ ኢየሩሳሌም አርአያ በተለያዩ ድረገጾች ይፋ እንዳደረጉት አቶ አባይ ጸሐዬ የተመደቡት ወጥመዱ ከተጠመደባቸው ዘንድ ነው።

“ድርጅትህ ኢህአዴግ እስከዛሬ ታግሎ እዚህ አድርሶሃል። በተለይም የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪ የሆነው ባለ ራዕዩን መሪህን በቅርቡ አጥተሃል” የሚል የአምልኮ መሪ ቃል ያለበት የጥሪ ወረቀት “ተቆርቋሪ ለሆናችሁ የትግራይ ተወላጆች በሙሉ” በማለት ጥሪ አቅርቧል። ኢየሩሳሌም አርአያ ቃል በቃል በትምህርተ ጥቅስ አኑረው ባሰራጩት በዚህ ጉልህ ዜና “እነ አቶ በረከት፣ ወ/ሮ አዜብ፣ ቴዎድሮስ ሃጎስ” ወረቀቱን አዘጋጅተው እንዳሰራጩ ያስረዳል።

በኢየሩሳሌም አርአያ ዜና ላይ እንደተመለከተው እነ አቶ ስዩም መስፍን፣ አባይ ጸሐዬ፣ አለቃ ጸጋዬ ከነባለቤታቸው የትግራይን ህዝብ ለጠላት ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ያወሳል።  “… የኔ የምትላቸው ጅቦች ተነስተውብህ ይገኛሉ” የተጠቀሱትንና ሌሎች ደጋፊዎቻቸውን “ጅቦች” ሲል የሚጠራው መልዕክት፣ “… ከእኛ ኋላ የተፈጠሩና ራሳችን ያሳደግናቸው ሲጠናከሩ ድርጅታችን ግን እየተዳከመ በመሄድ ላይ ነው” ሲል ያሳስባል። እነማን እንደሆኑ በግልጽ ሳይዘረዘር “የተወገዱ ግን በመጥፎ ጎዳና ያልተሰማሩን መልሰን ወደ ፓርቲው ማስገባት አለብን። ይህ ካልሆነ ግን የህዝብ ትግል አውላላ ሜዳ ላይ ጅብ በልቶት ሊቀር ነው ከጠላቶቻችን ጋር እንታረቅ እያሉን ነው” የሚል ማስጠንቀቂያ ያስቀምጣል። በስተመጨረሻ  “ከጀርባ ሆኖ የዚህ አፍራሽ ዋና ቀያሽ መሃንዲስ ስብሃት ነጋ መሆኑን ደርሰንበታል” ይላል።

“የኢህአዴግ ስኬት የመስመር እንጂ የግለሰብ አይደለም” በማለት የመለስን አምልኮ ለመቃወም ቀዳሚ የሆኑት አቶ ስብሃት ኤፈርትን ለወ/ሮ አዜብ ካስረከቡ በኋላ ከድርጅቱ ጋር ያላቸው ግንኙነት የላላ መሆኑን ለማሳየት እንደ ሩቅ ተመልካች አስተያየት ሲሰጡ ባብዛኛው ባልተለመደ መልክ ይዛለፉ ነበር። በተለይም አቶ በረከትን የማኮሰስና ምናምንቴ አድርጎ የማሳየት ስልት ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ይህ እንዳለ ሆኖ አለመግባባቱ ሊከሰት ግድ እንደሆነ አስቀድመው የተነበዩም ነበሩ።

“… መለስ ስለሌሉ የወንበር ቡቅሻው የማይቀር ነው። በድርጅቱ አመራሮች ዘንድ የሌባና ፖሊስ፣ የሃይል ሚዛንና ቅኝት፣ አሰላለፍን የማሳመር ሰልፍ እየታየ ነው፤ … የመለስ ማለፍ በድርጅቱ ውስጥ ታፍኖ የቆየውን ቁርሾ ማፈንዳቱ አይቀርም…” ሲሉ ኦክቶበር 25 ቀን 2012 ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ቃለ ምልልስ የሰጡት አሁን በትምህርት ላይ የሚገኙ የኢህአዴግ ሰው፣ የኢህአዴግ ድልድይ ተሰብሯል፤ የጋራ ነጥብም የለውም ብለው ነበር።

አውራምባ ታይምስ በበኩሉ ምንጩን አዲስ አበባ በማለት በተመሳሳይ የህወሃትን አደጋ ውስጥ መውደቅ ሲያበስር በስም ከዘረዘራቸው አመራሮች መካከል አቶ ስብሃት ነጋን አልጠቀሰም። ኢየሩሳሌም አርአያ አቶ በረከት የሚዘውሩትና የእነ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ወገን በዋናነት ለመምታት ያሰበው አቶ ስብሃት ነጋን እንደሆነ ለአባላት ተበተነ የተባለውን የማስጠንቀቂያ ወረቀት በመጥቀስ ይገልጻል።

አውራምባ ታይምስ “እያጣራሁ አቀርበዋለሁ” በማለት ያወጣው ትኩስ ዜና ለህወሃት አባላት ተሰራጨ የተባለውን ደብዳቤ “ማን እንደጻፈው አልታወቀም” በማለት ብዥታ የሚያጭር መልክት ሲያስተላልፍ፣ ኢየሩሳሌም አርአያ ከአውራምባ ድረገጽ ባለቤት አቶ ዳዊት ከበደ በተለየ መልኩ ዜናውን በትነው አስረድተዋል። በሁሉም በኩል እንደተጠቀሰው ህወሃት ቀውስ ውስጥ ተነክሯል።

በየካቲት ወር በሚደረግ ድርጅታዊ ግምገማ ጠራርገው እንደሚያስወግዷቸው እንደ ከባድ ሚዛን ቦክስ ቀጠሮ በመያዝ እነ አቶ ስብሃት፣ ስዩም፣ አባይና አለቃ ጸጋዬን በመጥቀስ የተሰራጨው  ወረቀት በስተመጨረሻ ስብሃት ነጋ ላይ ክርኑን አስደቁሶ እንደሚያበቃ የህዋሃትን ጓዳ አስመልክቶ በተደጋጋሚ ለየት ያለ ዜና የሚያስነብቡት ኢየሩሳሌም አርአያ ያበቃሉ።

ጎልጉል ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው የነበሩት የኢህአዴግ ሰው ይህንን ዜና አስመልክተው ምን አስተያየት እንዳላቸው ጠይቀናቸው ነበር። “በሌሎቹም አቻ ድርጅቶች ውስጥ በተመሳሳይ ይህ ሁኔታ ይከሰታል። የመበስበሱ በሽታ ሁሉም ዘንድ ነው” በማለት መልሳቸውን ይጀምራሉ። ለጊዜው ደኢህዴንና ብአዴን አንድ ላይ መሆናቸውን ያስታወቁት እኚሁ አስተያየት ሰጪ የኦህዴድ አቋም አለመጥራቱን ነው የሚናገሩት።

“የድጋፉ ጉዳይ የፎርሙላ ነው። ዶ/ር ደብረጽዮንና በረከት ስለላውን፣ ጦር ሃይሉን፣ የፖሊስና የልዩ ሃይሉን ሙሉ በሙሉ ስለተቆጣጠሩት በአሸናፊነት እንደሚወጡ ጥርጥር የለውም” ካሉ በኋላ አቶ ስብሃት ሰሞኑን “አማራውን ከሰደብኩ እኔ ታምሜያለሁ ማለት ነው ሆስፒታል መሔድ አለብኘኝ” በማለት የሰጡት መግለጫ ሲዘልፉትና ሲረግሙት የኖሩትን አማራና ብአዴንን ተለሳልሶ ለመቅረብ ያደረጉት እንደሆነ በተዋረድ ለብአዴን አባሎች መገለጹን እንደሚያውቁ አስረድተዋል።

“ምንም ተባለ ምን በመከላከያውና በደህንነቱ ሃይል ተጠቅመው የፈለጉትን መወሰንና የማስወሰን፣ ባላቸው በሚሰራው የፖለቲካ መዋቅር እስከታች መመሪያ በማውረድ የእነ በረከት ወገን ባለድል እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ቀድሞ ታጋይ የነበሩ፣ የደህንነት ሃይሉን እየረዱ ብር የሚያመርቱ ግርግሩ ስለማይመቻቸው ሃይል ካለው ወገን ጋር በመሆናቸው እነ ስብሃትን ያቀላጥፏቸዋል። ይህ ሁሉ የሚሆነው ግለሂስ አድርገው አርፈው ለመቀመጥ ካልተስማሙ ብቻ ነው” በማለት አስተያየታቸውን ይደመድማሉ፡፡

ይህንን መረጃ በሚያጠናክር መልኩ ከዚህ በፊት ከጻፍናቸው ዜናዎች መካከል አቶ በረከትና አቶ ሃይለማርያም የመለስ የቅርብ ሰዎች መሆናቸውንና አቶ መለስ ወደ ውጪ ሲወጡ የሥልጣኑን ቁልፍ የሚሰጡት ለአቶ በረከት እንደሆነ፤ የአቶ ሃይለማርያም ሹመት መነሻውም በዚሁ ቀደም ሲል በተፈጠረ “የቤተሰብ መሰል” ግንኙነት መሆኑን በመናገር ስማቸው ሳይጠቀስ ቃላቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የሰጡ የኦህዴድ ሰው ጠቅሰን መጻፋችን የሚታወስ ነው፡፡ አቶ መለስ በሞቱ ማግስት ከኢህአዴግ ምክርቤት እና ከፓርላማው ውሳኔ በፊት አቶ ሃይለማርያም ጠ/ሚ/ር ሆነው እንደሚቀጥሉ በመናገር የተጠባባቂ ጠ/ሚ/ርነት ሥልጣን ይዘው እንደሚሠሩ አቶ በረከት በወቅቱ በሰጡት ቃለምልልስ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡ አቶ ሃይለማርያም ለፎርማሊቲ በፓርላማ ፊት ቀርበው ምህላ እንደሚፈጽሙ አቶ በረከት በግላቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መናገራቸው ይህንኑ ቤተሰባዊ ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑን መዘገባችን የሚጠቀስ ነው፡፡

http://www.goolgule.com/the-future-of-tplf/

posted by Tseday Getachew

Ethiopia likely to miss top players in key match

RUSTENBURG, South Africa (AP) — Ethiopia’s chances at the African Cup of Nations have taken a hit with the team’s two top players expected to miss the decisive Group C match against Nigeria on Tuesday.

Ethiopia coach Sewnet Bishaw said Monday that midfielders Asrat Megersa and Adane Girma may not recover from the injuries they sustained in the first half of the team’s match against Burkina Faso.

Ethiopia is last in the group but will still have a chance of advancing if it beats Nigeria in Rustenburg.

In its first tournament appearance in more than 30 years, Ethiopia earned a surprising 1-1 draw with defending champion Zambia in the opener, then fell 4-0 to Burkina Faso after Asrat’s and Adane’s injuries.

“Two very important players were out and I’m afraid that they are not coming back,” Bishaw said. “Adane and Asrat are not in a good position right now. It will be up to the doctor’s decision before the match.”

Adane, who scored against Zambia for the team’s first African Cup goal in 37 years, left Friday’s match against Burkina Faso with a muscle injury in his right leg. Asrat had to leave the match just before halftime because of a right knee injury.

Neither player has been able to practice since the match at Mbombela Stadium and they are both undergoing intensive treatment. Bishaw said Asrat’s injury appears the more serious one and that he may have to be sidelined for up to 20 days.

Bishaw said losing the players early against Burkina Faso played a big part in the team’s 4-0 loss.

“We were dominating in the beginning and missed several opportunities and then our most important players get injured and go out. Our game was totally destroyed,” Bishaw said.

Ethiopia won the Cup of Nations in 1962 but last qualified for the final tournament in 1982. Players were promised more than $100,000 each if they win the competition in 2013.

The team arrived with few expectations, just hoping to gain experience, but the surprising draw against Zambia in the opener raised the team’s hopes of advancing to the second round.

“This is already a new chapter for this generation, playing after 31 years and scoring our first goal in 37 years,” Bishaw said. “We will be trying to make it to the quarterfinals, make history and make our people very happy. Our mission is to play football and to show Africa and the rest of the world that Ethiopia can play football.”

http://www.ethiomedia.com/addis/5098.html

posted by Tseday Getachew

 

ታደሰ በዛብህ የመርካቶው አይጥ

ከበልጅግ ዓሊ
Beljig.ali@gmail.com

Click here for PDF

ታደሰ በዛብህ በተወለደ በአስራ አንድ ዓመቱ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር – መስከረም 26/1981 ራሱን በማጥፋት ከዚህ ዓለም ተለየ።

Tadesse Bezabh Ethiopian adopted kid in Germany1ስለ ታደሰ በዛብህ ለመጻፍ ካሰብኩ ብዙ ጊዜ ነው። ቀን ሞልቶልኝ ተሳክቶልኝ አልጻፍኩትም። ሰሞኑን ሁለት ገጠመኞቼ ታደሰን እንደገና እንዳስበው አደረጉኝ። አንደኛው በጀርመን “ራይን ላንድ ፋልዝ” በሚባለው ክፍለ ሃገር ውስጥ ፋልዝ (PHALZ) በመባል በሚታወቅ ጋዜጣ ይታተማል። ይህ ጋዜጣ በ20.01.2013 እትሙ (Gestatten: Neger) በሚል ርዕስ ስለ <<ኒግር>> (“Neger” በእንግሊዘኛ ቋንቋ ደግሞ “Nigger”)በሚመለከት የተጻፈውን ካነበብኩ በኋላ ሲሆን በሁለተኛ ደግሞ እዛው ጀርመን ውስጥ በማደጎነት የተሰጠ አንድ አፍሪካዊ ሕጻን ከተገናኘሁ በኋላ ነው።

በዚህ ከላይ በጠቀስኩት ጋዜጣ ላይ የተጠቀሰው ጽሁፍ እንደሚያመለክትው በጀርመን ሃገር የሚታተሙ የሕጻናት መጽሐፍ ውስጥ ኒገር (Neger) የሚለው ቃል ስለሚገኝ ቃሉን ከመጽሐፍቶቹ ውስጥ መውጣት አለበት የሚል ነው።

ጋዜጣው ውስጥ ያለውን ዝባዝንኬ ትተን በተለይ በጀርመን የሕጻናት መጽሐፍ ውስጥ ያሉትን ዘረኛ ቃላት በምናስብበት ወቅት ከዛው ጋር ተያይዘው የሚመጡትን ችግሮች በቀላሉ ልናልፋቸው አንችልም። በጋዜጣው ላይ የተጠቀሰው የሕጻናት መጽሐፍ ለምሳሌ( Der NegerkÖnigin in Pipi Langstrumpf –) <<የኒግር>> ንግሥት ይባል የነበረው ከሚቀጥለው እትም በኋላ  (Südsee Kőnig-) የደቡብ ባሕር ንጉስ በሚል እንደሚጠራ ይገልጻል። በጀርመን ሃገር ያሉ ጥቁር ሕጻናት በዚህ  ቃል ምክንያት ብዙ ችግር ትምህርት ቤት ውስጥ እንደሚደርስባቸው ደግሞ የሚካድ አይደለም።

ከሁሉ የሚገርመው በጀርመን ሃገር “Neger” የሚለውን መጠርያ እንደ ቤተሰብ ስም (family name) የሚጠቀሙ ነበሩ። ስሙን እንዴት እንዳገኙት ባይታወቅም ይህንን የሚል መጠሪያ 470 ሰዎች የሚሆኑ ቤተሰቦች ይጠሩበት እንደነበር በ2008 ተገምቷል። ቢሆንም ብዙዎቹ በአካባቢያቸው በሚደርስባቸው ስድብ ምክንያት ስማቸውን ለመቀየር ተገደዋል። ከዚህ ተነስተን ያለውን ሁኔታ ስንገመግመው በጀርመን የሚገኙ ጥቁር ሕጻናት ላይ የሚደርሰውን መከራ መገንዘብ እንችላለን። በቅርብ ቀን በጀርመን ከፍራንክፈርት ከተማ አቅራቢያ በምትገኝ ሠፈር ያገኘሁት አንድ አፍሪካዊ ሕፃን ልጅ የዚህ አስከፊ የሆነ የዘር ችግር ሰለባ ሊሆን ይችላል።

ይህ ልጅ እድሜው አራት አመት አካባቢ ነው። ብርዱን ለመከላከል የለበሰው ልብስ ድቡልቡል አስመስሎታል። ክብ ፊቱ፣ ካደረገው ኮፍያና አንገቱ ላይ ከተጠቀለለት የአንገት ኩታ ማህል፣ በነጭ ጥርሱ ታጅባ ለተመለከታት ደስታን ትፈጥራለች። ከልጁ ፊት አንዲት የክረምቱ ብርዱ ሰውነቷን እንደ ወረቀት ነጭ ያደረጋት ጀርመናዊ ትራመዳለች። ልጁ ከኋላዋ እየተከተለ ፣ <<ማማ ፣ ማማ>> እያለ ይጠራታል። ሌሎች ጀርመኖች ልጆቻቸውን ከሕጻናት መዋያ እያደረሱ ሲመለሱ ገልመጥ እያሉ ይህንን ድርጊት እንደ አስደናቂ ትርዕይት ይመለከታሉ። ከምሄድበት መንገድ አሳብሬ ወደ እሱ አካባቢ ስሄድ፣ ልጁ በመቆም ወደ እኔ በመመልከት ያጠናኝ ጀመር። የእኔ ጥቁረት ከእሱ ጋር በመመሳሰሉ ይመስለኛል አተኩሮ ተመለከተኝ።

በጀርመንኛው(guten Morgen) ጉትን ሞርገን – መልካም ጠዋት ብዬ ሰላም አልኩት።

ትንሽ ተመልክቶኝ መልስ ሳይሰጠኝ ወደ እናቱ እየከነፈ ሄደ። እናቱም ሰላም አትለውም እንዴ? ብላ ጠየቀችው። የእናቱን እግር ጨምድዶ ይዞ እንደገና ያጠናኝ ጀመር። ለእናቱ ሰላምታ ሰጥቼ ። ቆንጆ ልጅ አለሽ በማለት ስለ ልጁ ለማወቅ ያለኝ ጉጉት ስለገፋፋኝ ወሬ ጀመርኩ። እናቱም ልጇ ቆንጆ ስለተባለ አመስግናኝ ልትሄድ ስትል ወሬዬን በመቀጠል የእኔ ልጅም እዚህ ሕጻናት መዋያ ነበረች። በጣም ጥሩ የሆነ የሕጻናት መዋያ ነው አልኳት።

– በመንገዱ ላይ ሌላ ሴት መጥታ ወደ እኔ በመመልከት እናትየዋን ሰላም ካለች በኋላ፣ ሁል ጊዜ ልጠይቅሽ እፈልጋለሁ “የልጁ አባት እሱ ነው?” ብላ እናቲቱን ጠየቀቻች።

– እናቲቱም “አይደለም” በማለት አጭር መልስ ስጥታት ጉዟችንን ቀጠልን።

– “መቼም እኛ ጀርመኖች ስንባል የማያገባንን ወሬ መሰብሰብ አንወዳለን አለችኝ?”

– “ጀርመኖች ብቻ ሳይሆኑ ወሬ መውደድ  የሰው ልጅ ተፈጥሮ ነው ብዬ መለስኩ።”

በተለይ የዘርን ጉዳይ በተመለከተ ብዙ ጀርመኖች ዘረኛ በመሆናቸው እንደዚህ ዓይነት ወሬ እንደሚጥማቸው አላጣሁትም ነበር።

ሕፃናት መዋያው ጋር ስንደርስ ጠብቀኝ ብላ ልጁን ልታደርስ ወደ ውስጥ ገባች። በራፉ ላይ የቆመችው አስተማሪ ልጁን ተቀብላት ተመለሰች።

– “ለመሆኑ ልጅህ ስንት ዓመቷ ነው ?”

– “አስራ ስምንት ሆኗታል።”

– “እኔ ደግሞ ትንሽ መስላኝ ለልጄ ጓደኛ እንድትሆን ልጠይቅህ ነበር።” አለችኝ።

– “ጓደኛ የለውም ወይ?” ብዬ ጠቅኋት።

– “አይ አፍሪካዊ የሆነ ጓደኛ ለማለት ነው።”

– “አዎ ችግር ነው። እዚህ አካባቢ አፍሪካውያን በብዛት ስለማይገኙ መሞከር ነው አልኳት።” በዚያውም አያይዤ። “የማደጎ ልጅሽ ነው?” ብዬ ጠየቅኋት።

– “አዎን። የዛሬ ሁለት ዓመት እኔና የሴት ፍቅረኛዬ ለእረፍት ምዕራብ አፍሪካ ሄደን መንገድ ላይ ሲለምን አገኘነውና በማደጎ ልጅነት ይዘነው መጣን።”

ሴትየዋ ከሌላ ሴት ጋር እንደ ባልና ሚስት እንደምትኖር ሳውቅ ደነገጥኩ። የደነገጥኩት ለእሷ ሳይሆን ይህ ልጅ ወደ ፊት ምን ችግር በትምህርት ቤትም ሆነ በአካባቢው እንደሚደርስበት ስለገመትኩ ነው። አሳዛኝ ነው። ይህ ልጅ ወደ ፊት ስለ ቤተሰቡ መጠየቁ አይቀርም። ስለሃገሩ መጠየቁ አይቀርም። እያደገ ሲሄድ በሁለት እንስት ቤት ውስጥ በማደጎ ማደጉ የሚፈጥረው ችግር ትንሽ አይደለም። ከሴትየዋ ጋር ትንሽ ተጨዋውተን ተለያየን። ግን የልጁ ሁኔታ ከጭንቅላቴ ሊጠፋ አልቻለም። ብዙ አወጣና አወርድ ጀመር።

በዚህ በጀርመን ሃገር ውስጥ አንድ አሳዛኝ ታሪክ ተፈጽሟል። ይህ ታሪክ በመጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል።  የመጽሐፉ ርዕስ “Tadesse Warum” – “ታደሰ ለምን” ማለት ነው።

Tadesse Bezabh Ethiopian adopted kid in Germany2

ታደሰ አዲስ አበባ በነበረበት ወቅት

ታደሰን ብዙ ጊዜ አስበዋለሁ። በሰው አገር የደረሰበት ስቃይ ትንሽ አይደለም። ዛሬ ይህንን ልጅ ሳይ ታደሰን ለምን ከሃገሩ ልጆች ጋር በትንሽ ጽሁፍ አላስተዋውቀውም ብዬ አሰብኩ። ሳይታወቅ ከሚቀር ይሻላል። Irmhild SÖhl – የምትባል ጀርመናዊት የታደሰ የማደጎ እናት ስለ ታደሰ ከፃፈችው መጽሐፍ ላይ የተወሰነው ለማቅረብና ታደሰ በወገኖቹ እንዲታሰብ ማድረግ አለብኝ ብዬጀመርኩ።  ታደሰ በዛብህ የተወለደው በሰሜን ኢትዮጵያ በወሎ ክፍለ ሃገር ነው። ታደሰ በተፈጥሮው የቋንቋ ስጦታ ሰለነበረው የጀርመን ቋንቋ አቀላጥፎ ይናገር ነበር። ታደሰ ምንም እንኳን የጽሁፍ መረጃ ተገኝቶ በየትኛው ቀን እንደተወለደ ባይታወቅም እድሜው ተሰልቶ በ1969 መወለዱ ታውቋል።

የታደሰ ሕይወት ገና ከመጀመሪው አስቃቂ ነበር። ገና የ5 ዓመት ልጅ እያለ አባቱ እፊቱ ሲገደሉ ተመከልክቷል። ከዛም እናቱ ወደ አዲስ አበባ ይዛው ተሰዳለች። አባቱ የተገደሉበት ምክንያት በውል ባይታወቅም ወቅቱ አብዩት የፈነዳበት ነበር። የመንግሥት ታጣቂዎች የፈለጋቸውን የሚያደርጉበት ወቅት ስለነበረ አባቱ በአብዮት ደጋፊዎች ሳይገደሉ እንዳልቀሩ ነው።

ታደሰ አባቱ ከተገደሉ በኋላ ከወሎ ክፍለሃገር ወደ አዲስ አበባ ከባዱንና አድካሚውን ጉዞ አድርጎ ከእህቱ ከኑኑ ጋር አዲስ አበባ እንዲመጣ ተገዷል። እናቱ አዲስ አበባ መርካቶ ውስጥ ከብዙ ችግር በኋላ እንጀራ እየጋገረች ልጆቿን ለማሳደግ ትጥር ነበር። በዚህ ወቅት ነበር ታደስ << የመርካቶው አይጥ >> የሚለው ስሙን ያገኘው። ታደሰ በዛብህ ከእህቱና ከእናቱ ጋር አዲስ አበባ ውስጥ ከነበሩበት(DED & Terre des  Hommes) የእርዳታ ድርጅቶች ጋር የተገኛኙት።

በዚህ ወቅት በደቡብ ጀርመን በባደን ቩተንበርግ ክፍለ ሃገር – የዞል ቤተሰቦች (Familie Sőhl) ከአምስት ልጆቻችው ጋር የገጠር ኑሮን የሚመስል ቤት ሠርተው በውስጡም( ውሻ Tadesse Bezabh, Ethiopian in Germany፣ ዶሮ ፣ ፈረስ ፣ . . .  ) የመሳሰሉትን እንስሳት በማካተት ለመኖር ይፈልጉ ነበር። የዞል ቤተሰቦች አንድ ልጅ ከሦስተኛው ዓለም ለማሳደግ በነበራቸው ጽኑ ፍላጎት ከብዙ ትግል በኋላ በግንቦት 1976 ታደሰ በዛብህን ከብዙ ትግል በኋላ  በማደጎ ልጅነት ተሰጣቸው።

ታደሰ በግንቦት ወር ፍራንክፈርት አውሮፕላን ጣቢያ ላይ ከአዲሱ ቤተሰቦቹ ተገናኝቶ የጀርመን ቋንቋ መማር ጀመረ። በነሃሴ ወር አዲሶቹ ወላጆቹ በሚደነቁበት ሁኔታ የጀርመን ቋንቋን ካለስህተት ይናገር ጀመር።

ታደሰ በዛብህ አርቆ አስተዋይ ነበር። ይህንን አርቆ አስተዋይነቱን በሚመለከት   ሕይወቱ ካለፈ 8 ዓመት በኋላ በሕይወት በነበረበት ጊዜ ይጽፋቸው ከነበሩት ደብዳቤዎች ውስጥ አንዱን “ZEIT” የሚባለው የጀርመን ታዋቂ ጋዜጣ 12.05.89 እትሙ ይዞ ወጥቷል።

Tadesse Bezabh letter

ትርጉሙም ፡ –

እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ። እድሜዬም አሥር ዓመት ነው። በአንድ ጀርመናዊ ቤተሰብ ውስጥ የማደጎ ልጅ ነኝ። እኔ እንደማውቀው ኢትዮጵያ ውስጥ አሁንም ፖሊሶች መንገድ ላይ ስለሚተኩሱ(ስለሚገድሉ) ፍርሃት አለብን። እናንተ ደግሞ አሁን እዚህ እናንተ ጥገኞችን ለመቀበል ካልፈለጋችሁ በስደተኞች ውስጥ ያለውን ፍራቻ  ለብዙ ጊዜ እንዲኖር ታደርጋላችሁ። ይህ ደግሞ በጣም መጥፎ ነው። አንድ ሰው በስደት ወደ እዚህ ከመጣና እናንተ መኖር ከከለከላችሁትና ሃገሩ ደግሞ መሄድ ካልቻለ መኖር አይችልም ማለት ነው። ይህ ደግሞ ትንሽም ቢሆን እንደ ይሁዳውያን ላይ እንደተፈጸመው ነው።በዚህ ምክንያት ነው ለመርዳት ዝግጁ መሆን ያለብን ።

ታደሰ ዞል ሚሸልባህ

ከዚህ ደብዳቤ እንደምንረዳው ይህ ልጅ ገና በአሥር ዓመቱ ከራሱ ችግር አልፎ የሃገሩ ልጆች ችግር ያሳስበው እንደ ነበር ነው።

ይቀጥላል

26 January 2013

http://www.ecadforum.com

posted by Tseday Getachew

 

ሕወሐት ለሁለት ተሰነጠቀ፤ ወረቀት ለአባለት ተበተነ

ከኢየሩሳሌም አርአያ

ዛሬ በመቀሌ ለአባላ ትና አልፎም ለህዝቡ በተበተነ የትግርኛ ፅሁፍ እነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ፀጋዬ በርሔ ከነባለቤታቸው እንዲሁም ሌሎች ከድርጅቱ እንዲባረሩTigray People Liberation Front Split በተበተነው መግለጫ ተጠቁሞዋል። በመግለጫው፥ ከጀርባ አሉ የተባሉትና « የዚህ መኅንዲስ» ተብለው የተፈረጁት ስብሃት ነጋ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከተባሉት መካከል በዋነኛነት ተፈርጀዋል። እነ ቴውድሮስ ሃጎስ፣አዜብ መስፍንና በረከት እጃቸው እንዳለበት የተነገረለት ይኸው መግለጫ ተከታዩን ይመስላል፤
«ተቆርቋሪ ለሆናችሁ የትግራይ ተወላጆ በሙሉ፤

«ድርጅትህ ሕወሐት እስከ ዛሬ ታግላ እዚህ ደረጃ አድርሰሃለች። በተለይም የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪ የነበረው ባለ ራዕይው መሪህ በቅርብ ጊዜ አጥተኽል።

ዛሬ እነዚህን ደካማ ጐኖች ተጠቅመው ለጠላት አሳልፈው ሊሰጡህ የሚፈልጉ ያውም ደግሞ የእኔ የምትላቸው ጅቦች ተነስተውብህ ይገኛሉ። ይህንን ግልፅ ለማቅድረግ አሁን በቅርብ ጊዜ በመቀሌ የድርጅቱ ማ/ኰሚቴ ስብሰባ አካሄደን ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ ነው እንግዲህ ተከታዩ ነገር የተነሳው። ይኽውም፥ እነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ፀጋዬ ከሚስቱ ጋርና ሌሎችም ያሉበት ይህን አሉ፤

«ድርጅታችን ጨርሶ ተዳክሞዋል። እኛ የኢትዮጲያ ሕዝብ ትግል መስራች ሆነን ሳለ ወደኋላ ተገፍትረን በአንፃሩ ሌሎች ከእኛ ኋላ የተፈጠሩና ራሳችን ያሳደግናቸው ሲጠናከሩ ድርጅታችን ግን እየተዳከመ በመሄድ ላይ ነው። ባዛው መጠን ሕዝባችን እየተጎዳ ነው። ስለዚህ አሁን ካጋጠመን አደጋ መውጣት ካለብን ከድርጅቱ -የተወገዱትን ግን በመጥፎ ጎዳና ያልተሰማሩትን መልሰን ወደ ፓርቲው ማስገባት አለብን። ይህ ካልሆነ ግን የሕዝብ ትግል አውላላ ሜዳ ላይ ጅብ በልቶት ሊቀር ነው።» በማለት ከጠላቶቻችን ጋር እንታረቅ እያሉን ነው።

“ሕዝባችን አስተውል። በዚህ አይነት ዳግመኛ በድርጅታችን ተኃድሶ እንደሚያስፈልገን ነው የተገነዘብነው። በሚቀጥለው የካቲት ወር በሚካሄደው ጉባኤያችን ይህንን ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶና አጥርቶ (ውሳኔ አሳልፎ) እንደሚወጣና እነዚህንና መሰሎቻቸው ከሚያራምዱት አቋም ጋር ጠራርጐ እንደሚያስወግድልን ተስፋ እናደርጋለን። በዚህም እያንዳንዱ እንደከዚህ ቀደሙ የተለመደ አስተዋፅኦ (ሚና) እንደሚያበረክት አንጠራጠርም።

በተጨማሪ ከጀርባ ሆኖ የዚህ አፍራሽ ዋና ቀያሽ መሃንዲስ ስብሃት ነጋ መሆኑን ደርሰንበታል።”

ከመቀሌ…

 
posted by Tseday Getachew

እግርኳሳችን የራሷን ሙሴ ትፈልጋለች

ስሜት ጎርፍ ነው፤ ያውም ደራሽ ጎርፍ፤ ብሄራዊ ቡድናችንን ስንደግፍም ሆነ ስናወድስ እንዲሁም ስንወቅስ በዚሁ ደራሽ ጎርፍ መወሰዳችን ይታያል። ይሄ ችግር ግን እንደ ሃገርም ችግራችን እየሆነ የመጣ ነገር ነው በስሜት መደገፍ በስሜት መቃወም፤ ዛሬ ያወደሱትን ነገ መርግም ሁሉንም ነገር በዘላቂ ጥቅም፤ በዘላቂ ስራ እና በዕውቀት መመዘን እያቃተን ነው። ከዚያም ዐልፎ ስሜታችን ጫፍ ላይ በሚደርስበት ጊዜ ሰከን ብሎ የሚያስብ ሰው ሲያጋጥመን እንደጭራቅ እንመለከተዋለን። ከእኛ በሓሳብ የተለየ አስተያየት የሰጠ እንደሆነማ በቃ ቤተክርስቲያን ውስጥ የገባ ውሻ እናደርገዋለን።…

የሰሞኑ የብሄራዊ ቡድናችን ውጤትም የዚህ ጎርፍ ሰለባዎች መሆናችን አንዱ ማሳያ ነው። መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አበባ ከቤኒን ብሄራዊ ቡድን ጋር ሲጫወት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የአሰላለፍ ስህተት ሰርቶአል መሃል ላይ ምንም ፈጣሪ /creative/ ተጫዋች አልነበረውም በሚል ከውጤቱ በኋላ ህዝቡም ጋዜጠኞችም ሲያወግዙት ከረሙ። ልብ አድርጉ እዚህ ጋር ሁሉም የሚያወራው በስሜት የዕለቱን ጨዋታ በተመለከተ የነበረውን ችግር እንጂ በዕውቀት የሃገራችን እግርኳስ ችግር ምንድን ነው? ብሎ ስለዘለቄታው የሚያወራ እና የሚያስብ የለም። ፌደሬሽኑም ቢሆን ህልውናውን ከጊዜያዊ ውጤት ጋር አጣብቆ የተቀመጠ ስለሆነ ዘለቄታዊ ስራ ሲሰራ አይታይም እናም አቶ ሰውነት ያቺን የተችት ፍላጻ እንደምንም ሽል ብለው አሳለፏት ። …

ቀጥሎም ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ሱዳንን አሸንፈን ለአፍሪካ ዋንጫ አላፊ መሆናችንን አረጋገጥን፤ ስሜት አሁንም እንደደራሽ ጎርፍ አጥለቀለቀን ህዝቡ ”ሳላዲን ጥቁር ሰው” ተባለ። ሲሰደብ የነበረው ሰውነት በየኤፍኤም ራዲዮው ጋሼ ጋሼ መባል ተጀመረ። አንዳንዶቹም ኢትዮጵያዊው ሞሪኖ ይሉት ጀመር። አሁንም እዚህ ጋር ረጋ ብሎ በዕውቀት ይሄ ውጤት ጊዜያዊ ነው፤ ዘለቄታዊ ውጤት የምንፈልግ ከሆነ ሰከን ብለን የእግርኳሱን ችግር እንመልከት በስሜት አንነዳ የሚል ሰው ሲገኝ እንደከሃዲ ሃገሩን እንደማይወድ ተቆጥሮ መወገዝ ጀመረ በስሜት! አቶ ሰውነትም ይህቺን ስለሚያውቅ በሴካፋ ውድድር መሳተፋችን አስፈላጊ አይደለም ብሎ ራሳችንን ከሴካፋ ውድድር እንድናገልል አደረገ። ለምን? ምክኒያቱም ስሜታዊ መሆናአችንን ስለሚያውቅ በሴካፋ ላይ የሚመጣው ውጤት የእርሱን ከብሄራዊ ቡድን ጋር ቆይታ ስለምትወስን ቁማሩን መቆመር አልፈለገም። አዎ ስራዎች በዕቅድ እና በዕውቀት ሳይሆን በስሜት በሚሰሩበት ሃገር ለምን ሪስክ ይወስዳል? …

የዛምቢያውን ጨዋታ አቻ ስንወጣማ ሁሉም ራሱን በስሜት አበደ፤ በደራሹ ውሃ እየተገፋ የሃገር ፍቅር ስሜት በሚል ሽፋን ተጫዋቾቹ ወኔ አላቸው ጀግና ናቸው ማለት ተጀመረ። በዚህ ወቅት እጅግ በጣም ጥቂት ሰዎች ናቸው ረጋ ብለው በስሜት ሳይነዱ እግርኳስ ጥበብ እንጂ ወኔ አይደለም ብለው ለመናገር ድፍረት የአገኙት እንደ Genene Mekuria Libro ያሉት ሰዎች፤ ግን ማን ያዳምጣል? ሁሉም በስሜት ባሉን እየተንሳፈፈ ነው ከጋዜጠኛ እስከ ፌደሬሽኑ ድረስ፤ እንደማይደርስ የለም ዐርብ ዕለት የቡርኪናፋሶ ውጤት የስሜት ባሉኑን ክፉኛ አስተንፍሶት ከነበርንበት ከፍታ በድንገት ከመሬት ወርደን ዝርግፍ አልን ፤ አሁን ደግሞ አሰልጣኙን ማውገዝ ተጀመረ በሳምንት ውስጥ ስናወድሰው የነበረውን ሰውዬ ወደተለመደው በስሜት ማውገዝ ተጀመረ ያሳዝናል ። …

በሃገር ፍቅር ስሜት ቢሆን በቁርጠኝነት ቢሆን ኖሮ የአፍሪካ ዋንጫን አይደለም የዓለም ዋንጫንም ቢሆን ከእኛ ልጆች የሚነጥቅ ሃገር አይኖርም ነበር፡፡ በነገራችን ላይ ለተጫዋቾቹ ያለኝ ክብር በጣም ከፍተኛ ነው የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል የቆጠቡትም አንዳች ነገር አልነበረም እናም ክብር ይገባቸዋል። መጪው ውጤት ምንም ቢሆን ቢያልፉም ባያልፉም ለእነሱ ያለኝ ክብር አይቀንስም … አሁንም ቢሆን ግን ከጊዜያዊ ውጤት ባሻገር ነገሮችን በዕውቀት የሚመለከት ጋዜጠኛ፤ በዕውቀት የሚሰራ ፌዴሬሽን እና ጊዜያዊ ውጤት ተመልክቶ ሳይሆን ዘላቂ ስራዎች እየተመለከተ የሚደግፍ ተመልካች ያስፈልገናል። እግርኳስ የስሜት ስፖርት መሆኑ ሳይረሳ ስሜቱም በሜዳ ላይ እንጂ ከሜዳ ጀርባ የሚሰራው ነገር በሙሉ በዕውቀት እና በጥበብ የሚሰራ መሆኑም ሳይዘነጋ …

አዎ እግርኳሳችን የእራሷን ሙሴ ትፈልጋለች!

http://www.ethiosun.com

posted by Tseday Getachew

የጎልጉል ቅምሻ/(ከዚህም ከዚያም)

 

“የድመት ጸጉር የመብላት ሱሰኛ ነኝ”

የሱሰኛነት ነገር ሲነሳ ሰሞኑን ከወደ ሚሽጋን ጠቅላይግዛት የተሰማው ጉድ የሚያሰኝ ነው፡፡ የ43ዓመቷ ሊሳ በቀን

ሦስት ሩብ መጠን ያለው የድመት ጸጉርጥቅል እንደምትበላ ተናግራለች፡፡

“የድመት ጸጉር የመብላት ሱሰኛ ነኝ” በማለት የምትናገረው ይህች ግለሰብ ሱሰኝነቱ የጀመራት የዛሬ 15ዓመት እነደሆነና እስካሁ 3200 ጥቅርል እንደበላች ታስረዳለች፡፡ ጥቅልሉን ከወለል፣ ከሶፋ፣ … እንደምታዘጋጅ ገልጻ በጣም አሪፍ የሆነው ግን በቀጥታ ከድመቷ የምታገኘው እንደሆነ ተናግራለች፡፡

ማርገዝ –› መጠጣት –› ጽንሱ ማበላሸት –› ዳረጎት ማግኘት

ከደቡብ አፍሪካ አስደንጋጭ ነገር ከተሰማ ጥቂት ቀናት ቢያልፉም የዜናው አስደንጋጭነት ግን እስካሁንም እውን ነው፡፡ ከመንግሥት የሚገኝ ጥቂት ዳረጎት ተጠቃሚ ለመሆን እርጉዞች ልጆቻቸውን በሽተኛ ሆነው እንዲወለዱ እያደረጉ ነው፤ በተለይ ችግረኛ በሆኑ ከተሞች የሚኖሩ፡፡

የደቡብ አፍሪካ ቤተሰቦች ከመንግሥት ከሚያገኙት ጥቂት ጥቅማጥሞች መካከል በአንድ ልጅ 250 ራንድ ወይም በዶላር 28.40 ያገኛሉ፡፡ ልጁ በሽተኛ ከሆነ ድጎማው 1200 ራንድ ወይም በዶላር 137.28 ይሆናል፡፡ ስለዚህ በእርግዝና ወቅት በሽተኛ ልጅ በመውለድ ከመጠን በላይ የሚጠጡ ሲሆን አንዳንዶቹ ከጠዋት ሦስት ሰዓት ጀምሮ በቀን ከአምስት እስከ ስድስት ጠርሙስ እንደሚጠጡ ተነግሯል፡፡

ጠ/ሚ/ር ሻሮን ሊነቁ ይሆን?

የዛሬ ሰባት ዓመት አካባቢ በድንገት ባጋጠማቸው የደም መርጋት በሽታ ራሳቸውን ስተው የሚገኙት የቀድሞው የእስራኤል ጠ/ሚ/ር ኤሪያል ሻሮን ሰሞኑን በጭንቅላታቸው ውስጥ ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ሁኔታ መመልከታቸውን ሐኪሞቻቸው ገልጸዋል፡፡

የ84ዓመቱ ሻሮን ተመልሰው ሊነቁ የሚችሉበት ሁኔታ እጅግ ዝቅተኛ እንደሆነ ሐኪሞች ቢናገሩም በአሁኑ ጊዜ ግን በጭንቅላታቸው ውስጥ የመስማትና አንዳንድ ክስተቶችን የማመላለስ ድርጊት እየተካሄደ እንደሆነ የሚጠቁም የምርመራ መረጃ ማግኘታቸውን ሐኪሞቹ ተናግረዋል፡፡

ለወራት ራሳቸውን ስተዋል፣ ሞተዋል፣ እያገገሙ ነው፣ ተመልሰው ሥራ ጀምረዋል፣ … ሲባልላቸው ቆይቶ በመጨረሻ ላይ የቀብር ሥነስርዓታቸው የተጠናቀቀው አቶ መለስ እንደ ሻሮን “አሉ እየተባሉ” በሞትና ሕይወት ውስጥ ቢቆዩላቸው ምኞታቸው መሆኑን በወቅቱ ወዳጆቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ተመኝተውላቸው ነበር፡፡

ካስወለድክ ትታሰራለህ!

ከተለያዩ ሴቶች የአራት ልጆች አባት የሆነው ሲም ቴይለር ከእንግዲህ ወዲህ አንድ ልጅ ቢጨምር ወደ እስር ቤት እንደሚወርድ ፍርድቤት ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡

ለልጆቹ ማሳደጊያ ባመክፈል ወደ 100ሺህ ዶላር ዕዳ ለበት የኦሃዮ ጠቅላይ ግዛት ነዋሪ የሆነው ይህ ግለሰብ የዳኛውን ውሳኔ የተቃወመ ሲሆን ለማሳደጊያ ገንዘብ ባይሰጥም ልጆቹንም እንደሚገባው ሲከባከብ እንደኖረ ተናግሯል፡፡ ጠበቃው በበኩላቸው “ፍርድቤቱ በደንበኛዬ መኝታቤት ጉዳይ ላይ ነው ውሳኔ የሰጠው” በማለት የዳኛውን ውሳኔ ተቃውመዋል፡፡ ግለሰቡ ገንዘቡን እንደሚከፍል ሁኔታዎችን ካመቻቸ የማስወለድ መብቱ እንደገና ሊታይ እንደሚችል ዳኛው ተናግረዋል፡፡

የፍቅራቸው ፊኛ ሲፈነዳ

ጥንዶቹ ለመጋባት ሲወስኑ ዕቅዱ አየር ላይ የጋብቻው ሥነስርዓት እንዲሆን ነበር፡፡ በያዝነው የአውሮጳውያን ወር መጀመሪያ አካባቢ የታሰበው የጋብቻ ሥነስርዓት እንደታሰበው አልተጠናቀቀም፡፡

በደቡብ ካሊፎርኒያ ጠቅላይ ግዛት ከነሙሽሮቹ ወደ 14የሚጠጉ ሰዎች የተጫኑበት የእሣት ፊኛ ሙሽሮቹ የጋብቻ ቃልኪዳናቸውን ከፈጸሙ በኋላ በአየር ላይ እንዳለ እክል ስለገጠመው ፓይለቱ ፊኛውን ባስቸኳይ ወደ ምድር እንዲወርድ ሲያደርግ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ግን እንደሌለ አብሮ ተዘግቧል፡፡ ሙሽሮቹ ግን አሁን ተስፋ አልቆረጡም – ገና አለ ገና – እንደግማለን ብለዋል፡፡

17 ቢሊዮን መሬት መሰል ፕላኔቶች

በቅርቡ ከአሜሪካው የጠፈር ምርምር ማዕከል (ናሳ) በተገኘው መረጃ እያንዳንዳችን ቢያንስ አንድ የግላችን ፕላኔት ሊኖረን እንደሚችል ነው፡፡

በኬፕለር የጠፈር አርቆ መመልከቻ የተገኙት ፕላኔቶች ምድርን የሚመስሉ ሲሆን ተንታኞች ባገኙት መረጃ መሠረት ምድርን የሚመስሉ 17 ቢሊዮን ፕላኔቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ነው፡፡ ምድርን መምሰላቸው ብቻ ሳይሆን በተመራማሪዎች አስተሳሰብ ህይወት ሊኖር ይችላል የሚል ግምትም አለ፡፡

የሳምንቱ ምርጥ ፎቶ

ከጥቂት ቀናት በፊት በፈረንሳይ የሚገኝ ድርጅት በየጊዜው የትዊተር መልዕክት ሲተላለፍ የብርሃን ብልጭታ በማሳየት የትዊተር እንቅስቃሴ የሚከታተል የዓለማችንን ካርታ ይፋ አድርጓል፡፡ ጨለማው አህጉር አሁም ጨለማ እንደወረሰው ነው፡፡

ዘገባውን ለማጠናቀር በየጽሁፉ ከጠቀስናቸው ምንጮች በተጨማሪ ሌሎችንም የሚዲያ ውጤቶች መጠቀማችንን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ ከዜናዎቹ ማነስ አኳያ በየጸሁፉ ለመግለጽ ባለመቻላችን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

http://www.goolgule.com

posted by Tseday Getachew

የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሀይል የነጻነት ተዋጊዎች ጋር ግምባር መፍጠሩ ታውቋል።

ጠቅላይ ሰፈሩን በኤርትራ እና ኢትዮጵያ ድበሮች ላይ አድርጎ ወደ ትግራይ እየዘለቀ ተደጋጋሚ ጥቃት በወያኔ ሎሌዎች ላይ በመፈጸም የሚታወቀው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (TPDM) በቅርቡ እራሱን ይፋ ካደረገው የግንቦት 7 ህዝባዊ ሀይልና ሌሎችም ባካባቢው ከሚንቀሳቀሱ የነጻነት ተዋጊዎች ጋር ግምባር መፍጠሩ ታውቋል።

 

 

http://ecadforum.com

posted by Tseday Getachew

በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ 13 ሚሊዮን ብር በማውጣት ፎርጅድ ቀለሞችን የገዙ ሰዎች ተያዙ

ጥር ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከዩኒቨርስቲው ምንጮች ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በዩኒቨርስቲው ፋይናንስና ሂውማን ሪሶርስ ክፍል ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች 13 ሚሊዮን ብር ዋጋ የሚያወጣ ፎርጅድ ( የተጭበረበረ)የፕሪንተር ቀለምና የኮምፒተር እቃዎችን ገዝተዋል ተብለው በፌደራል ፖሊሶች ቁጥጥር ስር ውለዋል። የተያዙት ግለሰቦች ከዚህ ቀደም በከፍተኛ የሀላፊነት ቦታዎች ላይ የነበሩና ላለፉት 20 አመታት በተለያዩ መንገዶች ለአካባቢው ህዝብ የሚላከውን ገንዘብ በመዝረፍ የሚታወቁ ናቸው።

አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ሰው እንደተናገሩት ገቢው በቀን አንድ ዶላር በሆነባት አገር ፣ ይህን ያክል የገንዘብ ዝርፊያ መካሄዱ አስገራሚ ነው ብለዋል። ግለሰቦቹ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በመሆናቸው ህዝቡን ለማስደሰት ተብለው ታሰሩ እንጅ በቅርቡ ሊለቀቁ ይችላሉ በማለት ግለሰቡ አክለው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው ሙስና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው።

posted by Tseday Getachew

የወያኔን ሰላዮችን ከውጭ አለም ማጽዳት

ከእስከ ነጻነት

Original flag of Ethiopiaኢትዮጵያ የነጻነት ቀንዲል ነች፡እንደ ስበሃት ነጋ ላሉ ባንዳ ወያኔዎች ግን ጣሊያንን አሸንፈን ለመላው የጥቁር ህዝብ የነጻነት ጎህ ቀዳጅ መሆናችን ኩራት ሳይሆን እፍረት ስለሚመስላቸው አገሪቷ ከነሰንደቅ አላማዋ ጥፍታ ማየት የዘወትር ጥረታቸው ነው፡ ሌት ተቅን የሚተጉትም ለዚህ ስለሆነ የኢትዮጵያዊነት ሰሜት ያላቸውን ሁሉ ማሰር፤ መግደል፤ ማጥፋት ዋና ትግባራቸው ነው፡ ይህም ተግባራቸው ከበረሃ እስከ አዲስ አበባ ከዛም ጎረቢት አገሮች ድረስ ዘልቆ አሁን ደግሞ ወደ ምእራብ ሐገራትም መጣሁ እያለ ነው።

ግን አገሪቷም ሆነ ባንዲራዋ ልትጠፋ አትችልም፡ ለጥቁር ህዝብ የነጻነት ጎህ የቀደደች መሆኗን ለማረጋገጥ በርካታ ሃገራት ከቅኝ ግዛት ነጻ ሲወጡ ባንዲራቸውን መሰረት ያደረጉት በኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ላይ ስለሆነ ባለም ዙሪያ ሲውለበለብ ይኖራል እንጂ ባንዳዎች እንደተመኙት ልትጠፋ አትችልም።

ባለፈው አበበ ገላው ላይ የተቃጣው የግድያ ሴራ ከወያኔ አድሎአዊ አገዛዝ፤ ሸሽተን በመጣነው ሁሉ ላይ የተቃጣ ዛቻ ነው በሚል አጠር ያለች ጽሑፍ በእንግሊዘኛ ቋንቋ አቅርቤ ነበር። በዛሬው ጽሁፌ ማተኮር የምፈልገው ወያኔ (ለኔ ወያኔ ማለት ለአላማም ይሁን ለጥቅም የዚህን አገዛዝ እድሜ የሚያራዝም ሁሉ ነው) እንዴት ተሰደን ባለንበት አገር ለማስፈራራት ብርታቱን አገኘ? እንዴትስ የወያኔ አባላት ሰላዮች እና እበላ ባዮች በውጭው አለም በዙ? እንዴትስ መመንጠር እንችላለን የሚሉትን ዝርዝር ጉዳዮች በተመለከተ ይሆናል።

ወደ ውጭ አገር መሰደጃ መንገዶች የታወቁ ናቸው፡ ከደርግ ጅምላ ፍጅት ሽሽት አገራቸውን ጥለው የተሰደዱ ብዙ ናቸው፡ በዘር የተደራጀው እና ዘር በማጥላላትና በማጥፋተ ላይ የተመሰረተው የወያኔ ቡድን ስርዓቱን በኢትዮጵያ ላይ ከጫነ ጀምሮ፡ ወያኔ በህዝቡ ላይ በሚያደርገው ጫና፤ ጭቆናና ግፍ አገራችንን ለቀን ተሰደናል፡ የተሳካልን ነጻው አለም ደርስናል ያልተሳካላቸው በበረሃ አሸዋ ተውጠው ቀርተዋል፡ ባህር ውጧቸዋል፡ ከቀይ ባህር እስከ ቬንዙዌላ የውሃ ጎርፍ ወስዷቸዋል፡ ከባህር እና ካሸዋ የተረፉት በየሀገራቱ እስር ቤቶች ተሰቃይተው ሞተዋል፡የውስጥ አካላቸው ተበልቶ ተወሰዷል፤ በእህቶቻችን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ግፍ እና ስቃይ መናገር አይቻልም፡ የሰው ህሊና ሊያስበውና ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ነው።

እኛስ በዚህ መልኩ ተሰደድን የወያኔ ደጋፊዎች፤ እና ሰላዮችስ እንዴት መጡ?

በስራ፤ በንግድ፤ ወይም በተለያየ መንገድ ከመጡት በተጨማሪ፡ እንደኛው ወያኔ ሊያኖረኝ አልቻለም፡ አሰረኝ፤ ገረፈኝ ብለው የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው ውጭ የሚኖሩ በጣም ብዙ ናቸው፡ በሌላም በኩል ኤርተራዊ ነኝ፡ ብለው በኤርትራውያን ስም፤ ሱማሌያዊ ነኝ ብለው በሱማሌ ስም ጥገኝነት ጠይቀው የተፈቀደላቸው እንዳሉም ይታወቃል፡ እንዳውም የኤርትራውያንን ስደተኞች ተቀብያለሁ እና ሶስተኛ አለም ተረከቡኝ ብሎ ሶስተኛ አገሮች ከተረከቧቸው አብዛኛዎቹ የወያኔ ደጋፊዎች እና የወያኔ ሰላይ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ስደተኞችን ተቀባይ አገሮች አይወቁት እንጂ የህን ጽሁፍ በማንበብ ላይ ያለኸው፤ ያለሽው፡ ጠንቅቀው ያውቁታል።

ለምን የወያኔ ደጋፊዎች፤ ወደ ነጻው አገር መጡ አደለም ጥያቄው፡ ይኸ መንግስት በድሎናል፤ ጨቁኖናል መኖር አልቻንም ብለው የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው፤ ጥያቄያቸው ተቀባይነት ካገኘ በሗላ ከዚሁ ጨቆነን ካሉት መንግስት ጋር አብሮ መስራት፤ የወያኔ ደጋፊዎች፤ ኢምባሲ ጭምር በሚያዘጋጁት ስብሰባ ላይ፤ የድጋፍ ሰልፍ ላይ እንዴት ሊገኙ ቻሉ?

ይህ ብቻ አደለም ከድጋፍ አልፈው የወያኔ አገዛዝ አስመርሯቸው የተሰደዱትን በኬንያ፤ በዩጋንዳ በሱዳን፤ በሶማሊያ፤ በጅቡቲ ሲገሉ እና ሲያሰገድሉ ኖረዋል፡ ያንን ተግበር አሜሪካ፤ ካናዳ እና አውሰትራሊያም ሊሞከሩ እንደሚችሉ፤ መገመት በቻ ሳይሆን አበበ ገላው ላይ የተጠነሰሰው ሴራና የአሜሪካው የፌዴራል ምርምራ ቢሮ (FBI) ማክሸፉ ያላቸውን ዕብሪት በግልጽ ያሳያል።

ይህ ደግሞ በአበበ ገላው ብቻ የሚቆም አደለም ለሌሎቻችንም የሚተርፍ የወያኔ ድግስ ነው ስለዚህ እንዴት ማስቆም አለብን የሚለው ነው ቁም ነገሩ።

ይህንን ለማሰቆም ወይም የወያኔ ሰላዮችን አጋልጦ ለፍርድ ለማቅረብ የፖለቲካ ድርጅቶች ወይም የሲቪክ ድርጅቶች አያስፈልጉም፡ እነሱ ወያኔን ከስሩ ለመንቀል ይንቀሳቀሱ፤ ለዚህ ተግባር ግን የሚያሰፈልገው፡ በወያኔ የዘረኛ አገዛዝ ተማረህ የተሰደድክ፡ ግፋዊ አሰተዳደሩን መቋቋም አቅቶሽ አገርሽን ጥለሽ የወጣሽ፡ በወያኔ የግፍ ቀንበር እህትህን ያጣህ፤ ወንድምሽ እህትሽ በስደት ላይ እያሉ ባህር የዋጠብሽ፡ አንተ ነህ፤ አንቺ ነሽ የምታስፈልጊው፤ የምታስፈልገው። በአንድ ከተማ ውስጥ አንድ ወይም ሁለት ቁርጠኛ ኢትዮጵያዊ ካለ በቂ ነው፡ በኢትዮጵያ የህግ የበላይነት መከበር ጽኑ አላማ ያለውና በጥቅም ያማይገዛ ህሊና ያላቸው አንድ ወይም ሁለት ባንድ ከተማ ካሉ በጣምበቂ ነው፡ የሚጠበቀው መደባደብ ወይም መሰዳደብ አደለም የሚያሰፈልገው ወያኔ በድሎኛል ብሎ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀ ሰው ከወያኔ ቡድን ጋር እየሰራ እና ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም ጥገኝነት የሰጠውን አገር አየስለለ መሆኑን ሪፖረት ማረግ ብቻ ነው።

ማንኛውም ሰው አንድ አገር የፖለቲካ ጥገኝነት ሲጠይቅ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በደለኝ ብሎ መኖር አልቻልኩም ካለና ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ በሗላ ያ መንግስት እስካልተቀየረ ድረስ ከዛ መንግሰት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ሊኖረው አይችልም፡ በምንም መልኩ ከዛ መንግስት ጋር ግንኙነቱን ከቀጠለ ከመንግስቱ ጋር ችግር የለበትም ማለት ነው ስለዚህ ወዳገሩ መመለስ አለበት፡ የኽ የኔ አስተያየት ሳይሆን የየሃገራቱ የስደተኛ ህጎች ናቸው።

ስለሆነም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ የተፈቀደለት፡ ወይም ኤርትራዊ፤ ሶማሊያዊ ነኝ ብሎ ጥገኝነት የተፈቅደለት (ወንድ ይሆን ሴት፤ አማራ ይሁን ኦሮሞ፤ ትገሬ ይሆን አደሬ፤ ማንም ይሁን ማ) የወያኔው ኢምባሲ በሚያዘጋጀው ፕሮገራም ላይ የሚሳተፍ፤ የወያኔ ባለስልጣናት በሚጠሩት ስብሰባ ላይ የሚገኝ፤ የወያኔ ደጋፊዎች ወይም ካደሬዎች በሚያዘጋጁት የወያኔ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የሚገኘን፡ ከወያኔ ጋር የንግድ ስራ ጀምሮ ኢትዮጵያ የሚመላለስን ሁሉ ለሚመለከተው ክፍል ሪፖርት ማደረግ ያስፈልጋል።

ባለፈው 21 አመት ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት አልተቀየረም ስለሆነም በነዚህ ጊዜያት የወያኔ መንግስት በድሎኛል፤ ሊያኖረኝ አለቻለም ብሎ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀ ሰው ሁሉ በምንም መልኩ ከወያኔ ጋር የሚሰራ፡ ወያኔ በሚያዘጋጀው ዝግጅት ላይ የሚገኝ ሁሉ ሪፖርት መደረግ አለበት።

እዚህ ላይ አደራ የምለው እና ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ የሚገባው ሪፖርት የሚደረገው ነገር እውነት ብቻ እንዲሆን፤ በግል ቂም በቀል፤ ወይም በተወሰነ ዘር ላይ ያነጣጠረ እንዳይሆን አደራ እላለሁ፡፡ ወያኔን ያጠናከረው፡ የተወሰነ ዘር ወይም የወያኔው አባላት ብቻ ሳይሆን እበላ ባይ አጃቢ ጭምር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡ ስለዚህ ሁሉም የወያኔን እድሜ እየለመነ የወያኔን ፍርፋሪ የሚለቃቅም ሁሉ ሪፖርት መደረግ አለበት።

ወያኔን ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ ከወያኔ ጋር መደባደብ መነታረክ ሳይሆን ሰማቸውን ቢቻል አድራሻና ፎቶገራፋቸውን መዝግቦ መያዝ ነው ከዛ ለሚመለከተው ረፖርት ማድረግ።

ሪፖርት ለማድረግ የግድ የግል ሰማችሁን መጠቀም አይኖርባችሁም፤ ሰሜ አይገለጽ ማለትም ትችላላችሁ፡ ከቤታችሁ ሪፖረት መላክ ካላመቻችሁ ወይም ካልፈለጋችሁ ከህዝብ መጻሕፍት ቤት ኮምፑተር ተጠቅማችሁ ሪፖርት ማድርግ ትችላላቸሁ፡ የህዝብ ቤተ መጻህፍት አባል ለመሆን ክፍያ አይጠይቅም ነጻ ነው፤ የሚጠይቀው መታወቂያ ወይም ባደራሻችሁ በስማችሁ የተላከ ደብዳቤ ብቻ በቂ ነው፡

መልክታችሁ አጭር ነው፡

“እገሌ የሚባል ሰው አዚህ አገር ሲገባ መንግስት ጨቆነኝ አላኖር አለኝ፤ ብሎ ነበር አሁን ግን ጨቆነኝ ከሚለው ከመንግስት ጋር በቀጥታ እየሰራ ስለሆነ ሰላይ ሊሆን ይችላል ወይም የጥገኝነት ጥያቄው የውነት አደለም ብዬ እጠራጠራለሁ ማጣራት ቢደረግ”

ማጣራቱ የናንተ ጉዳይ ሳይሆን የደህንነት ሰራተኞች ጉዳይ ይሆናል፡ ከማንም ሳትማከሩ፤ አዩኝ አላዩኝ ብላችሁ ሳትፈሩ፤ ሚስጥሬ ይባክናል የሚል ስጋት ሳይኖራችሁ ትክክለኛውን መረጃ ለሚመለከተው ክፍል መስጠት የህሊና ነጻነት መጎናጸፍ እና የዜግነት ድርሻን መወጣት ነው፡

ሪፖርት የምታደርጉባቸውም አድራሻዎች

1. በዩናይትድ ሰቴትስ FBI (Federal Bureau of Investigation) https://tips.fbi.gov
2. በካናዳ Canadian Security Intelligence Service: http://www.csis-scrs.gc.ca/cmmn/cntcts-eng.asp
3. በአውስትራሊያ Australian security Intelligence Organization: http://www.asio.gov.au/Contact-Us.html

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ::

http://www.ecadforum.com

posted by Tseday Getachew

 

ከእሁድ እስከ እሁድ/(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)

 

occupy london embassy

 

ሻማ ማብራት ኤምባሲ መውረር

በአብዛኛው የኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ሻማና ጧፍ ማብራት፣ በሰላማዊ ሰልፍ መጮህ፣ ፒቴሽን መፈራረም፣ በተለያዩ ማህበራዊ አውታሮችና ድሮች መሳደብና የመሳሰሉት ናቸው። ባለፈው ሳምንት የኤርትራ ተወላጆች ሎንዶን የሚገኘውን የኢሳያስ ኤምባሲ ጥሰው በመግባት የፈጸሙት የተቃውሞ ተግባር ከፍተኛ የሚዲያ ትኩረት ስቧል።

“ኤምባሲው የእኛ ነው። ከኤምባሲያችን ወደ የትም አንሄድም” ያሉት የኤርትራ ተወላጆች የሚፈሩትን ኢሳያስን ያገኙ ያህል ፎቷቸውን ከግድግዳ በማውረድ መሬት ላይ በመከስከስ ረጋግጠው ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ራሳቸው ፕሬዚዳንት ኢሳያስና ዓለም ተመልክቷል። ይህ ታላቅ የተቃውሞ መልዕክት ለሁሉም ባለስልጣናት መልዕክት ሲሆን በተለይም ስደት ልዩ መለያው ለሆነው የኤርትራ ህዝብ ባንድነት ይነሳሳ ዘንድ የሚቀሰቅስ ተግባር ሆኖ ተገኝቷል። የእኛ አገር ተቃዋሚዎችና ደጋፊዎችስ? ሻማና ጧፍ በማብራት እንቀጥላለን ወይስ ተቃውሞውን አንድ ደረጃ እናሳድገዋለን?

መለስ አልታደሉም

ጎል ካስቆጠሩ በኋላ አቶ መለስ የተለጠፉበትን ካኒቴራ በማሳየት ደስታቸውን እንዲገልጹ የታዘዙት የብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች የተባሉትን ማድረግ አቅቷቸዋል። ሁኔታውን ሲከታተሉ ነበሩ አሽሟጣጮች ትዕዛዙ ጎል ስናገባ ሳይሆን ጎል ሲገባብን የመለስን ፎቶ የሚያሳየውን ቲሸርት በማሳየት ሃዘንን መግለጽ ቢሆን ኖሮ አቶ መለስ በቡርኪናፋሶ ጨዋታ ወቅት አራት ጊዜ በሃዘን የመታወስ እድል ያገኙ ነበር ሲሉ ተደምጠዋል።

እነዚሁ ተረበኞች በናይጀሪያ ጨዋታ ላይ ትዕዛዙ ላይ ማስተካከያ እንዲደረግ መክረዋል። ቡድኑ ሜዳ ሲገባ በመጀመሪያ መለስ ያሉበትን ቲሸርት እንዲለብስ፣ ጨዋታው ሊጀመር ሲል ዳኛውን በማስፈቀድ የናይጄሪያ ተጨዋቾችም ቲሸርቱን ከውስጥ እንዲለብሱ እንዲያስገድዱላቸው ጥያቄ ማቅረብ፣ ከዚያም እኛ ካላገባን እንኳ ናይጀሪያዎች ሲያገቡ የመለስን ቲሸርት በማሳየት ደስታቸውን እንዲገልጹ፣ ይህንን ካደረጉ አላሙዲ እንደሚሸልሙ አስቀድሞ ለተጨዋቾቹ ማስታወቅ የሚሉትን ሃሳቦች ያቀረቡት ሸርዳጆች ሁሉም ተደርጎ ካልተሳካ መለስን በኳስ ሜዳ የማስታወሱ ጉዳይ በቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ይተገበር ዘንድ በአምስቱ ዓመት የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ እንዲያዝና ውድድሩን ኢትዮጵያ እንድታዘጋጀው በማድረግ ለስኬቱ መታገል እንደሚቻል መክረዋል። አቶ መለስ በህይወት በነበሩበት ወቅት ስለ ስታዲየም ግንባታ ተጠይቀው “እኔን የሚያሳስበን ማዳበሪያ ነው” ማለታቸው ይታወሳል።

በባንዲራ ብዛት የተሞሸረ ብሄራዊ ቡድን

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደቡብ አፍሪካ ላይ ለክብሩ የቀረበለት የባንዲራ ብዛት በሪኮርድነት ተመዝግቧል። ምናልባትም ይህ የዕድሜ ልክ ሪኮርድ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። አሁን ያለው ባለኮከቡ ባንዲራ፣ የቀድሞው ሰንደቅ ዓለማ፣ የኦሮሚያ መለያ፣ የሞአንበሳ ባለ አንበሳው ባንዲራ፣ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ባንዲራ፣ የኢህአዴግ አርማ …

ቡድኑን ለመደገፍ ወደ ስታዲየም የመጡት ደጋፊዎች ያሳዩት የተለያ ባንዲራ ሁሉም ኢትዮጵያን ለመደገፍ ቢሆንም የፖለቲካ መልዕክት ከማስተላለፍ አኳያ ሆን ተብሎ የተደረገ በመሆኑ አገሪቱ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት አመላካች ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም። ለወደፊቱ ቡድኑ የሚጫወትበት መለያ የሁሉንም ባንዲራ የሚወክል እንዲሆን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሊያስብበት ይገባል። ሁሉንም ብሄሮችና የነጻነት ጥያቄ ያላቸውን ክፍሎች መለያ እንዲያካትት ተደርጎ አዲስ መለያ ከተዘጋጀ ሁሉም የየራሳቸውን ባንዲራና አርማ ከመጎተት ይልቅ አዲሱን ማሊያ በመልበስ ውክልናቸውን ያሳያሉ። በመሆኑም አዲሱ የመጫወቻ ሹራብ ክንዱ የኦነግን አርማ፣ አንገቱ የኢህአዴግን፣ ጀርባው የቀድሞውን ባንዲራ፣ ፊትለፊቱ የኦብነግን፣ ቁምጣው የብአዴንን፣ ኪሱ የስልጤ፣ የእግር ሹራቡ የህወሃትን፣ አልበቃ ካለ ኮፊያና ስካርፕ አድርገው የተለያዩ ብሄሮችን እንዲወክሉና ሜዳ እንዲገቡ ቢደረግ የተሻለ ሳይሆን ይቀራል?

ብሄራዊ ቡድን ሬኮርድ ሰበረ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በደቡብ አፍሪካ ውድድር ብዙ የገባበት ቡድን በመሆን ሬኮርድ ተመዝግቦበታል። ቡድኑ ቡርኪና ፋሶ አስር ሰው ሆነው ቢጫወቱም አጋጣሚውን መጠቀም አልቻለም። በጉዳት የወጣው አዳነ ግርማ ጉዳቱ ከፍተኛ በመሆኑ ቶሎ እንደማያገግም የቡድኑ ዶክተር አስታውቀዋል።

ከሰላሳ አንድ ኣመት በኋላ አፍሪካ ዋንጫ የተቀላቀለው የኢትዮጵያ ቡድን መርሃ ግብሩን የሚያጠናቅቅበት የመጨረሻ ጨዋታውን ከናይጀሪያ ጋር ያከናውናል። ያለፈው ዓመት ባለድል ዛምቢያ ከቡርኪናፋሶ ጋር በምታደርገው ጨዋታ ከተሸነፈች ወይም እኩል ከወጣችና ኢትዮጵያ ናይጀሪያን ማሸነፍ ከቻለች ወደ ሁለተኛው ዙር ታልፋለች። አሁን ባለው የነጥብ ድምር ውጤት መሰረት ቡርኪና ፋሶ አራት፣ ዛምቢያ ሁለት፣ ናይጀሪያና ዛምቢያ ሁለት፣ ኢትዮጵያ አንድ ነጥብ አላቸው።

ሰውነት ቢሻው ተወቀሱ

በቀጣይ ያልተጠቀምኩባቸውን አሰልፋለሁ

በቡርኪና ፋሶ አራት ለባዶ የተሸነፈው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው እየተወቀሱ ነው። ሽንፈቱን አስመልከቶ የህዝብ አስተያየት ያሰባሰበው ኢቲቪ “በጨዋታው የአሰልጣኙ ደካማ ብቃት ተስተውሏል፣ እንቅስቃሴው ዝቅተኛ ነው። ምክንያቱ አልገባኝም። አሰልጣኙ አሰላለፍ ላይና አቀያየር ላይ ስህተት ሰርተዋል። አምስት ተመላላሽ ተጨዋቾችን አሰልፏል…” የሚሉ ነቀፌታዎች አሳይቷል።

አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውን “በድሉ” በማለት የሚጠሯቸውና በቅርብ የሚያውቋቸው ተጨዋቾች አሰልጣኙ አሁንም ችግሩ አልገባቸውም እያሉ ነው። “በራሳችን ሜዳ ኳስ በብዛት ማንከባለላችን ጎድቶናል” በማለት አቶ ሰውነት የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ የተሰጠው አስተያየት በናይጀሪያው ጨዋታ አሰልጣኙ ረጅም ኳስ የመጫወት እቅድ እንዳላቸው አመላካች ነው። ይበልጥ እንዳንከስር እንፈራለን ብለዋል። ምን ይደረግ? ለተባሉት ኳስ ይዞ ባላጋራን በመቁረጥና አማካዩን ክፍል ኳስ ለሚችሉ ልጆች በመፍቀድ እንዲጫወቱ መደረግ እንዳለበት ተናግረዋል። የባዮሎጂ መምህር የነበሩት ሰውነት ቢሻው ወኔ በማነሳሳት እንደሚታወቁ የሚገልጹት አስተያየት ሰጪዎች በዚህም በኩል ጥንቃቄ እንዲደረግ፣ ተጨዋቾቹ ሰክነው እንዲጫወቱ መደረግ እንዳለበት ይመክራሉ።

ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ኪራይ ሰብሰቢ ተባሉ

መንግስት ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጣቸው የሚነገርላቸው የጥቃቅን አነስተኛ ተቋማት በኪራይ ሰብሳቢነት ተፈረጁ። ኢንተርፕራይዞቹ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና የተግባር ማነቆ እንዳለባቸው ይፋ ያደረገው ኮንስትራክሽን ሚኒስትር እንደሆነ የዘገበው ሪፖርተር ነው።

የተበደሩትን ገንዘብ መመለስ እንዳልቻሉ ሪፖርት የቀረበባቸው ተቋማት በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት 1.6 ቢሊዮን ብር እዳ መክፈል ሲገባቸው 575 ሚሊዮን ብር ብቻ መክፈላቸው የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት የተጠናወታቸው አስብሏቸዋል።1.1 ቢሊዮን ብር መቆጠብ ሲገባቸው ተቋማቱ 540 ሚሊዮን ብር ብቻ ተቀማጭ ማድረጋቸው ሌላው ችግር እንደሆነ ሪፖርተር የጠቀሰው ዘገባ ያስረዳል።

ትርፍም ኪሳራም የለውም

ከአካባቢ ምርጫ ራሳቸውን ያገለሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኢህአዴግ ላይ ሊያስከትሉት የሚችሉት ጫና እንደሌለ ተሰማ። የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት የህዝብ አደረጃጀት ሃላፊ የሆኑትን አቶ ሬድዋንን ፎቶ በማስቀደም አዲስ አድማስና ሪፖርትር እንዳስነበቡት በኢህአዴግ እምነት “ትርፍም ኪሳራም የለም”።

አቶ ሬድዋን የተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው አለመሳተፋቸው “ለኢህአዴግ ትርፍም ኪሳራም የለውም” በማለት በሰጡት መግለጫ እንደተለመደው የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ዘልፈዋል። ለአካባቢ ምርጫ ደንታ ቢስ አድርገው ስለዋቸዋል። ኢህአዴግ ያቋቋማቸውና ተወዳዳሪ ሊሆኑ የማይችሉ ፓርቲዎች ምርጫውን በማድመቅና ኢህአዴግን በማጀብ የተለመደ ተግባራቸውን እንደሚጫወቱ በተለያዩ ሚዲያዎች መዘገቡ ይታወሳል።

 
posted by Tseday Getachew

ከብዕር ስም ጀርባ (ከብስራት ኢብሳ)

ይድረስ ለኢንተርኔት ድኅረ -ገጽ ሃላፊዎች

ከብስራት ኢብሳ (ሆላንድ) 26-01-2013

ድሮ የምደግፈው የነ አበበ ጉርሙ የመቻል እግር ኳስ ቡድን ከጠፋ ከዓመታት ቦኋላ በትላንቱ ምሽት ለመጀመርያ ጊዜ የተከታተልኩትን ፣ በደቡብ አፍሪካ ፣ ብሔራዊ ቡድናችን ባሳዛኝ ሁኔታ በቡርኪና ፋሶ ተሸንፎ ጨዋታው ሲያልቅ ፣ ተደብሬ የቴለቪዢኑን መስመር ከኢውሮ እስፖርት ወደ ደች የዜና መስመር ቀይሬ ከባለቤቴ ጋር የዓለም ዜና ማዳመጥ ጀመርን ፡፡

በአፍሪካ አህጉራችን ፣ ማሊ ውስጥ ፈረንሳይ “የአልካሂዳን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር“ በሚል ርዕስ ዙርያ ፣ ፈረንሳይ ሁሌ ለዚህ አይነተግባር የምታሰማራቸውን ፣ ቅጥረኛ (ፈረንጆቹ ሜርሲነሪ የሚሉት) ወታደሮቿን እንደላከች በምስል በተቀረጸ ፊልም ካሳዩ ቦኋላ ፣ አንድ ሆላንዳዊ ድሮ በእንደዚህ አይነት ውትድርና ተቀጥሮ የነበረ ፣ ስለ ቅጥረኛ ወታደር ልምዱን ለተመልካችና አዳማጭ እንዲያካፍል ጋዜጠኛው አቀረበው ፡፡

እንደ ጀብደኛው የቀድሞ ቅጥረኛ ወታደር አገላለጽ ፣ ለእንደዚህ አይነት ውትድርና  መቀጠር የሚፈልጉ ሰዎች ፣ የተለያየ የግል ችግር ያለባቸው ፣ ዓላማ የሌለው ጀብዱ መስራት የሚወዱ፣ ለገንዘብ የሚሞቱ…ወዘተ ዘርዝሮ ፣ የስልጠናው ክብደት፣ ያሰልጣኞቹን ኢ- ሰባዊ የጭካኔ አያያዝና ፣ ኮርሱን ጨርሰው ከተልዕኮዋቸው በህይወት የሚመለሱበት ዕድል ምን ያህል የጠበበ እንደሆነ በጣም ሰፋ አድርጎ ልምዱን አካፈለ፡፡

ከረዥም ልምዱ በተለይ ቀልቤን የሳበው፣ ሲቀጠሩ አዲስ የውሸት ስም እንደሚወጣላቸና ፣ ትክክለኛ ስማቸውን የያዘ ፓስፖርታቸውን፣ የባንክ ካርዳቸውን ፣ መንጃ ፍቃዳቸውን …ወዘተ ማንኛውም ከእውነተኛ  ማንነታቸው ጋር የተያያዘን ዶክሜንት እንደሚያቃጥሉና፣ አዲሱን  ስማቸውን ብቻ የሚገልጽ መታወቂያ ተሰርቶ እንደሚሰጣቸው  የተናገረው ነበር ፡፡

ይህንን የሚያደርጉበት ምክንያትም፣ ቅጥረኞቹ የሚላኩበት ሃገር እንዲሰሩ የሚታዘዙት፣ በሃገሩም ሆነ  በዓለም አቀፍ ሕግ የተከለከለና ፣ ኢ- ሰባዓዊ የሆነ ድርጊት እንደሆነ ቀድመው ስለሚያውቁት ፣ የግል ሃላፊነትን ላለመውሰድና ከተጠያቂነት ለመሸሽ እንደሆነ አስረዳ፡፡

ፕሮግራሙ ሲያልቅ ፣ ስለሰማሁት እያብሰለሰልኩኝ፣ ዘወትር ዓርብ ማታ ፣ ወደ ምኝታዬ ከመሄዴ በፊት ፣ እንደ ድሮ ካዛንቺስ ወይም ባንቢስ ፣ ሦስቱ በር ፣ አምስቱ በር ፣ አደዋ መደዳ የመዝናኛ ስፍራዎችን የሚያካክስልኝ ፣ አዲሱ የሽማግሌ የመዝናኛ ስፍራዬ የፓልቶክ መደዳ ጎራ ብዬ አንድ ሁለቱ ዘንድ ሃዘን ተቀምጠው ስለደረስኩኝ  ዘግቼ ፣ የኢሜል መልዕክት እንዳለኝ ስፈትሽ  አንድ በብዕር ስም የተጻፈ፣ በግለ ሰብ ስብዕና ላይ የሚያተኩር ዘገባ አየሁ፡፡ ፀሐፊ የራሳቸውን ስም ሸሽገው ፣ የሚወቅሱትን ግለሰብ ስም ፀሐይ ላይ አስጥተውታል፡፡ እኚህ ፀሃፊ እንደ አተናተናቸው ፣ ለሃገር ተቆርቋሪ ፣ እረዥም ዓመታት በሆላንድ የኖሩ ፣ ብዙ ውጣ ውረድ ያዩ ናቸው፡፡ ፀሃፊው ማን ሊሆን እንደሚችል ለማወቅ አልሞከርኩም ፡፡ ምክንያቱም ፀሃፊው ሲጽፉ ሊያስጠረጥሩ የፈለጉት ሰው ስላለ ፣ እሳቸውን መተባበር አልፈለኩም ፡፡ በትክክለኛ ስማቸው በማይጽፉ ተቺዎችም ይሁን አስተያየት ሰጪዎች ፣ እንኳን አቅዋም ለመውሰድ ፣ ላለማንበብ ከወሰንኩኝ ስለሰነበትኩኝ ፣ እንደዚህ አይነት ፣ ስም የለሽ ደብዳቤዎች ሲመጡ ፣ በቀጥታ የምልካቸው ወደ የቁሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ነበር ፡፡

በዚህ ምሽት ግን በኳሱ ብስጭትና ፣ በቅጥረኛው ወታደር ታሪክ እየተገረምኩኝ ሳላስበው የእኚህን የብዕር ስም ትችት ግማሹን አንብቤ ነው፣ ማንበብ እንዳልነበረብኝ ከሃሳቤ የነቃሁት፡፡ ግማሽ ቃሌንም ቢሆን ለማክበር ጽሁፉ  ማንበብ አቋርጬ ፣ እንደተለመደው ወደ ቆሻሻ ቅርጫት ስፍራው አስተናግጄው ወደ መኝታዬ ሄድኩኝ ፡፡

ነገር ግን እንደተመኘሁት ያቺ በስህተት ያነበብኳት እንደ አቦል ቡና እንቅልፍ ነስታኝ መገላበጥ ጀመርኩኝ ፡፡ ድሮ እኔም በስሜ መጻፍ ከመጀመሬ በፊት በግለሰብ ዙርያ ሳይሆን በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ እጽፍ ስለነበር ፣ የብዕር ወይም የውሸት ስም መቼና እንዴት? እንደተጀመረ ፣ ለምን ? ማን እንደጀመረው ለማወቅ ማሰላሰሌን ተያያዝኩት ፡፡ እኔን እንደዚህ በጨረፍታ ያነበብኩትን እንቅልፍ የነሳኝ ፣ የሚጻፍባቸው ግለሰቦችንና ፣ ፀሐፊው እራሱ እንቅልፍ አጥቶ በዚህ የእስፖርት ግር ግር ለዚህ ጉዳይ ጊዜውን ያጠፋው ምን ያህል የተጎዳና ፣ እርዳታ የሚያስፈልገው ሰው ይሆን ? ወይስ እንደተለመደው የወያኔ ተላላኪዎች ? እያልኩኝ እያሰላሰልኩኝ እንቅልፍ አሸለበኝ ፡፡

ይህንን እንቅልፍ የነሳኝን የብዕር ስም አመጣጥ ቅድመ ታሪክ ለማወቅ ዛሬ ጠዋት ከቁርስ ቦኋላ ባለቤተን ወደገበያ ብቻዋን ልኬ ፣ የተለመደ ጉግሌንና ፣ ዊኪፒዲያን አገላበጥኩኝ ፡፡ የደረስኩበትንም ማሰርያ ለአንባቢዎቼ አካፍዬ ለመገላገል ወሰንኩኝ ፡፡ስለዚህ ይህ መልዕክት በብዕር ስም ስለተላከልኝ መልዕክት  አስተያየት ለመስጠት ፣ ወይም የብዕር ስምን በደፈናው ለማውገዝ አይደለም፡፡

ከላይ እንደጠቀስኩት ፈረንሳዮች ለቅጥረኛ ወታደር ብቻ ሳይሆን ፣ ለመደበኛ ወታደሮቻቸውም ፣ ከፈረንሳይ አብዮት በፊት ጀምሮ ፣ ከሙሉ ስማቸው መጨረሻ ፣ ኒክ ኔም ፣ ተደጋጋሚ ስሞችን ለመለየት ፣ ወታደሩ ከመጣበት አካባቢ መንደር ፣ መንገድ ፣ ተራራ ስም ጋር የሚያያዝ ፣ ወይም በሰውየው ሰውነት ላይ ከሚታይ የተለየ ነገር በማያያዝ ተቀጥላ ስም ያወጡለት ነበር ፡፡ በሃገራችንም ጀብዱ የሰሩ ጀግናዎች ከፈረሳቸው ስም ጋር (ታጠቅ፣ ገስግስ፣ አባ ቦራ .ወዘተ.) እንደሚባለው ማለት ነው፡፡ በተረፈ ከተወሰነ ሙያቸው፣ ባህሪያቸው ፣ ከሚወዱት ነገር ፣ ከሚያዝወትሩት ፣ መርሳት ከማይፈልጉት ፣  ….ወዘተ ጋር በተያያዘ የሚወጡ ብዙ አይነት ፣ የብዕር ፣ የመድረክ ፣ የእስክሪን ፣ የሃይማኖት ፣ የተልዕኮ …መዘርዘር እስከሚሰለቸን ብዙ አይነት የተለያዩ   (ፔሱዶኒም ፣ ኒክ) ስሞች መጠቀም በዓለማችን የተለመደ ነው ፡፡

እንዲሁ በፖለቲካውም ዓለም ከአስራ ስምንተኛውና ፣ አስራዘጠነኛው ዘመን ጀምሮ ፣ ለህቡዕ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለቀስቃሽ ጋዜጦች፣ ለህቡዕ እንቅስቃሴዎች ፣ ለካድሬ ስሞች፣ የብዕር ወይም የድብቅ ስም ተጠቅመዋል ፡፡  ለምሳሌ ሌኒን ፣ እስታሊን ፣ ትሮትስኪ … ወዘተ የካድሬ (የፖለቲካ)ስማቸው እንጂ ፣ ትክክለኛ ስማቸው ሌላ ነው ፡፡ ብዙዎቹ ቀሪውን እድሜያቸውን ከትክክለኛ ስማቸው በላይ የሚታወቁበት ወይም የሚጠሩበት በአንድ ወቅት ፣ ለሆነ ምክንያት  ወይም ችግር ባወጡት ስማቸው ነው ፡፡ በኛም ሃገር በባህላችን በስማችን ላይ  ፣ እንደ ቅጽል ፣ ከምግባር ፣ ወይም ከድርጊት ጋር በተያያዘ ምክንያት እንጨምር ነበር ፡፡ ከዚህ ባሻገር ፣ በሃገራችን እንደ ውጪው ሃገር ፖለቲካ የብዕር ስም መጠቀም የተጀመረው ፣ ይኔ ትውልድ ሥርዓቱን መታገል ከጀመረና ፣ የግራው ፖለቲካ ወደ ሃገራችን ከገባ ቦኋላ ፣ እራስን ከአገዛዙ የፖሊስና የጸጥታ አፈና ላለማጋለጥና ፣ ፍልስፍናውን እንደፈጠሩት የቀደምት ፖለቲከኞችን መንገድ እንደፋሺንም ጭምር በመከተል ነበር ፡፡

ሆኖም በአንድ በተወሰነ ወቅት፣ ይህ እራስን ከአንባገነኖች አፈና ተደብቆ የማታገያና የመታገያ ዘዴ፣ ሌሎችም ፣ እንደ ማፍያ አይነት ወንጀለኛ ድርጅቶች ከምዕራቡ ዓለም ጀምሮ ለመጥፎ ተግባር መጠቀም ጀመሩ ፡፡ ከላይ ቅጥረኛው ወታደር እንደ ነገረን ፣ በፖለቲካውም ሆነ በማፍያው ዓለም ፣ ስማቸውን እየደበቁ በማስፈራራት በመዝረፍ ፣ ስም እያስጠፉ እራሳቸውን ለመጥቀም ፣ ለማበልጽግና ቦኋላም እራሳቸውን ከሃላፊነትና ፣ ከተጠያቂነት ለማምለጥ የብዕር ስምን መጠቀም  ቀጠሉ፡፡

ባጠቃላይ የብዕር ስም ሌላውን አጥቅቶ ለመደበቂያ ፣ ለወንጀል ተግባር ፣ ሌላውን ለማስጠርጠር ፣ ለመከፋፈል ፣ ስም ለማጥፋት አይሁን እንጂ ፣ ማንም የብዕር ወይም የውሸት ስም የመጠቀም መብትም አለው ፡፡ በሚወዳት ፍቅረኛው ፣ በምታደንቀው ጀግና ስም ፣ በምንወደው መፈክር  ….ወዘተ ፣ የብዕር ስም መጠቀም ተንኮልና ሴራ እስከሌለው ድረስ ፣ ችግር የለውም ፡፡ ወይም በአገዛዙ ላይ ለህይወታቸው የሚያሰጋ ትችት የሚያቀርቡና ፣ ሃገር ውስጥ መግባትና መውጣት የሚፈልጉ እስከሆኑ ድረስ ፣ በበኩሌ ችግራቸው ይገባኛል ፡፡

በተረፈ ተቺዎች አውሮፓና ፣ አሜሪካ ተቀምጠው ከሐገሩ እንደ ከሳሾቹ ለተሰደደ ፣ በግልጽ ማንነታቸውን አሳውቀው የመተቸትም ሆነ የመቃወም መብት የተጠበቀበት ነጻ ሃገር ቁጭ ብለው ፣ የሚጽፉትን በእውነት የሚያምኑበት ከሆነና ሌላ የተደበቀ ተንኮል ከሌለበት ?፣ ወይም ተገዶ በተጽዕኖ ፣ አሊያም ገንዘብና ስልጣን አታሎት  ካልሆነ በስተቀ ፣ የሚተቸውን ሰው ስም እየጠቀሰ የራሱን ስም የሚደብቅበት ምክንያት የለም፡፡

(በእርግጥ አንዳንድ የሌላውን ቀልብ ለመሳብ ፣ የውይይት ማዕከል ለመሆንና ለሚቀጥለው ተንኮላቸው ሽፋን ለመጠቀም ፣ ሌላ ሰው እንደጻፈ አስመስለው በራሳቸው ላይ የሚጽፉ እንዳሉ ፣ በተለያዩ መጻህፍት ያነበብናቸውና ፣ “ተደራራቢ ስብዕና “ፈረንጆቹ “መልቲፕል አይደንቲቲ“ የሚሏቸው የግለሰብ ባህሪዎች መኖራቸውን ስንዘነጋ ፡፡)

ወደ ጀመርኩት ልመለስና ፣ እንዲያውም በቅርቡ የተጀመረው ፣ “በአንድ ጠጠር ሦስት ወፍ“  እንደሚባለው ፣ ስምን መደበቅ ብቻ ሳይሆን ፣ ጸሃፈ አስመስለው  ለማሳጣት የሚፈልጉትንም ሰው   የአጻጻፍ ዘዴ ፣ የፊደሉ አመራረጣቸው ፣ የአርስት አሰጣጣቸው ፣ ቅንፍና ኮማ ሳይቀር ሊያስጠረጥሩ እንደሚፈልጉት ሰው አድርገው መጻፍ ጀምረዋል፡፡ በዚህ ዘዴ የሚፈጽሙት ደባ  ሊያጠቁ የሚፈልጉትን አስጠርጥርጥረው ያስነጥሉታል፣ ያስጠሉታል፡፡  የሚሰድቡትንም ግለሰብ  በዚህ አይነት ስሙን ያጠፋሉ ፡፡  በሁለቱ ግለሰብ ፣ ወይም ድርጅት ወይም ቡድን …ወዘተ መሃል ቅራኔ ፈጥረው ያተራምሳሉ ፡፡ ይህ አይነት የተቀነባበረ ሴራ ደግሞ ፣ በግለሰብ የሚሰራ ፣ ወይም አንድን ሰው  ብቻ ለመጉዳት ወይም ለመጥቀም ሳይሆን ፣ ከኋላው ወፍራም መዳፍ ያለበት ወያኔያዊ ወይም ሻቢያዊ ተልዕኮ ብቻ ሳይሆን ፣ አንዳንድ ሃላፊነት ከማይሰማቸው  ተቃዋሚም ሰፈር አካባቢ ከሆነ ? በጣም አደገኛና  በታታኝ  ሴራ ስለሆነ ፤ የድህረ -ገጽ ሃላፊዎች ፣ እንደዚህ አይነት ዝቅ ያለ ደረጃ ወርደው ለሚከፋፍሉን ፣ ትግሉንም ሆነ ታጋዮችን ስለሚያዳክም መተባበር የለባቸውም ፡፡

ትችት ተገቢ ነው፡፡ አንድ ተቺ ስለ ግለሰብ የሚጽፈውን የሚያምንበት ከሆነ እራሱን መደበቅ የለበትም፡፡ የማያምንበት ወይም የሚፈራ ከሆነ አርፎ መቀመጥ ይችላል ፡፡ ነገር ግን እሱ ማንነቱን ማሳወቅ ፈርቶ ፣ የሚከሰውን ሰው ስም እየጠቀሰ ፣ ያልጻፈን ሰው እያስጠረጠረ  የሚደበቅ ሰው የሚመሳሰለው ፣ ከኋላ አድፍጦ ከሚተኩስ ፈሪ ሰው ጋር ብቻ ነው ፡፡

ስለዚህ የኢንተርኔት ድህረገጽ ሃላፊዎች ፣ እንደነዚህ አይነት ሃላፊነት የማይሰማቸው ፣ እንደ ቅጥረኛው ወታደር ከተጠያቂነትና ፣ ከሃላፊነት ለማምለጥ ፣ ተደብቀው በብዕር ስም ደባ የሚሰሩትን ፣ ድህረ ገጾቻችሁ ላይ ለማውጣት አትተባበርዋቸው ፡፡ በማንኛውም ሃይማኖት፣ ሞራል፣ ኤቲክስ ፣ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ይህን አይነት አሰራር ፣ አይከተልም ፡፡( በእርግጥ በአንባቢ እጦትና ፣ በራሳቸው ምርጫ ስሜታዊ አሉባልታወችን በማስተናገድ ድህረ ገጾቻቸውን በዚህ አይነት ጽሁፍ ለማጨናነቅ ከወሰኑት በስተቀር)  ማንም ለፍትህና ለዲሞክራሲ የሚታገል ፣ የኢንተርኔት ድኅረ-ገጽ ሃላፊዎች ፣ ከአርዕስቱ ወጥቶ በግለሰቦች ስብዕና ላይ  በሃሰት ስም ጀርባ ተደብቀው የተንኮል ድራማ ዘመቻ ለማስነበብ የሚፈልጉትን ተንኮለኞች እንደማይተባበሩ ተስፋ አለን ፡፡

በተረፈ በኳሱ ጨዋታ ብንሸነፍም ፣ ከኳሱ ጀርባ ተከፋፍለን እንድንቆም ተዘጋጅቶ የነበረውን ድራማ ፣ አብዛኛው ወገናችን ነቅቶ ፣ ከብሔራዊ ቡድናችን ጎን በመሰለፍ የተዘጋጀውን ወጥመድ በማክሸፉና ፣ በአንድነት ቆሞ ለወገኑ ድጋፉን መስጠት በመቻሉ ፣ ሌላ የሕብረትና ፣ የጸባይ ድል ስለተጎናጸፍን ፣ በደቡብ ያጣነውን ኳስ ፣ ከደቡብ እንስከ ሰሜን ፣ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ተያይዘን አንድነታችንን ያደስንበትን አዲስ ክስተትና ፣ ድል ! ! እንደተፈጠረ ሳንረሳ፣ ይህንንም እያዳበርነው ፣ እያቀጣጠልነው ወደፊት እንቀጥል በማለት የሽማግሌ ምክሬን አስተላልፋለሁ፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ከከፋፋዮች ይጠብቃት ፣ እኛም እንተባበረው !!

http://www.ecadforum.com

Posted by Tseday Getachew

 

 

Post Navigation

%d bloggers like this: