Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

Archive for the month “July, 2013”

አሣ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል (ክፍል 2)

ናደዉ፣ ከዋሽንግቶን ዲሲ

ባለፈዉ ሳምንት “እስቲ ቂማችን ጥቂት እናቆየዉ” በሚለዉ በዚህ አምድ የመጀመርያዉ ፅሁፌ በዳያስፖራዉ ዉስጥ ሰርገዉ ስለገቡ የወያኔ ጨካኝ አገዛዝ አባሎችና ሆድአደር ጀሌዎቻቸዉ ጥቂት በጣም ጥቂት ለማለት ሞክሬአለሁ።፦ምን ያለበት ምን አይችልም እንዲሉ ሆነና፣ ተላላኪዎቻቸዉ ተደፈርን ያዙኝ ልቀቁኝ ማለታቸዉን አንድ ወዳጄ ነገረኝ። ላለፉት አስራ አምስት አመታት ያህል እጅግ የተካኑበትን የተቃዋሚዉ ወገን አመራሮችን በስም እየጠቀሱ ጥላሸት መቀባት ዳያስፖራዉን ለመከፋፈል በወያኔ በጀት ተመድቦላቸዉ በሚያሰራጩት አጉራ ዘለል ራዲዮኖቻቸዉ ሲያላዝኑ ዉለዉ አደሩ ማለትንም ሰማሁ። የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ በተጠቀሱት የወያኔ ተላላኪዎችና ሆድ አደሮች ዉስጣቸዉ ሆኖ ለረጅም ጊዜያት መረጃዎችን ሲሰበስብ በመቆየቱ እነሆ አሁን እንደ መንደርደሪያ አይነት ባለፈዉ ፅሁፍ ዉስጥ ነካ ነካ ለማድረግና ተጠንቀቁ ማንነታችሁን እናዉቃለን አይናችሁን ሸፍኑና እናሞኛችሁ ማለት ከእንግዲህ ወዲያ አይሰራም ተመቸን ብሎ ከወያኔ በሚከፈላችሁ የመንደር ራዲዮ ሠዉን መዘርጠጥ ይቁም ለማለት ብጫ ካርድ ለማሣየት ሞክሬአለሁ፥ ይህ ግን እንደሞኝነት መቆጠሩን በዚህ ሰሞን ይህ ሆድ አደር መቶ አለቃ ያለፈዉን ፅሁፍ በመጥቀስ እንዳበደ ውሻ ግምታዊ ዘለፋውን ለማቅረብ መንገታገቱ ተመልክቻሁ፧Inside Washington Little Ethiopia

በዚህ ምክንያት የሆነዉን ሁሉ በማስጃ በተደገፈ ፅሁፍ ቁልጭ አድርጌ ለማቅረብ ወንኩ፧እኔ አሁንም አጠገባቸዉ ነኝ። በተለያዩ ማሕበራዊ ጉዳዮች እንገናኛለን። በሚገባም እንተዋወቃለን። ከአጋላጭ ፅሁፎቼ በኋላ በሕዝብ ፊት እዉነቱን በገሀድ ፍርጥ አድርጌ በራሳቸዉ ራዲዮ ላይ ከጋበዙኝ ለመቅረብ ዝግጁ ነኝ። ይህን ካልኩ በኋላ በቀጥታ ወደ ዛሬዉ የአጋላጭ ትኩረት አቅጣጫዪ ልዉሰዳችሁ።

ጓድ ምርጫዉ ስንሻዉ ማነዉ? ምክትል የመቶ አለቃ ምርጫዉ ስንሻዉ አሥመራ ከተማ ቃኘዉ ስቴሽን ይገኝ በነበረዉ የፖለቲካ መምሪያ ዉስጥ በካድሬነት ያገለግል የነበረ በዚያን ወቅት የሥራ ባልደረቦቹን መቆምያ መቀመጫ የሚያሳጣና ከፋፋይና ተንኮለኛ ስለነበር ከአጠቃላይ ባህርይው የተነሳ ትንኩሽ በሚል ቅፅል ስም የሚያዉቁት የሠራዊቱ አባሎች ዛሬ እዚህ ሰሜን አሜሪካ ይገኛሉ።ከዚያ በኋላ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘዉ በወቅቱ ከፍተኛ ፩ በሚባለዉ መስተዳድር የአራዳ የአኢወማ ሊቀመንበርና ካድሬ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በከፍተኛዉ መዝናኛ ክበብ እሱ በሚመጣበት ሰአት ብዙዎቻችን ወጣቶች ሹልክ ሹልክ እያልን ከቦታዉ የምንሰወርበትን የብሄራዊ ዉትድርና ጭፍን የምልመላን ሽሽት ወቅት አንደነበር ዛሬ ብዙዎቻችን በቁጭት እናስታዉሰዋለን፤ አሁን ደግሞ ይኸዉ ግለሰብ ማልያዉን ገልብጦ የሌላዉ ጨካኝ አምባገነን አገዛዝ ሰርጐ ገብ ተላላኪ መሆኑ ፧ቀደም ሲል ይህንን ግለሰብ የምናዉቀውን ብዙዎቻችንን አስገርሞናል።

ይህ ጓድ አይኑን በጨዉ አጥቦ ጅብ በማያዉቁት አገር ቁርበት አንጥፉልኝ አለ እንደሚባለዉ እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ መጣ።እኛም የሰፈሩ ወጣቶች የዛሬዎቹ ጎልማሶች አገኘነዉ አሁን ድረስ አንድ ጓደኛችን ባገኘዉ ቦታ ሁሉ ለዱላ ይጋበዝበታል እኛም ያለፈዉን እርሳዉ ብለን ገላጋይ መሆናችን አልቀረም። ያለፈዉ በደል ሳያንሰዉ አሁን ደግሞ ሌላ ቁማር ጀመረ፣ራዲዮ ጣቢያና ቤተክርስቲያን ከፈተ ።በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዮጵያዊነት ራዲዮ የሚልና ኡራኤል ቤተክርስቲያን፤ ራዲዮ ጣቢያዉን ራሱ ብቻዉን የሚያስተዳድረዉ ሲፈልግ የሚከፍተዉ ሲያሻዉ የሚዘጋዉ፤ ቤተክርስቲያኑንም እንዲሁ ቀዳሽ ቄስ ካገኘ አገኘ ካላገኘ ቅዳሴዉን በካሴት ያስነካዋል፧እሱ ማንን ፈርቶ አገሩ አሜሪካ አይደል!

እጅግ የሚያሳፍር ተግባር ይሏችኋል ይህ ነዉ!ጓድ መቶ አለቃ ምርጫዉ ስንሻዉ ዛሬም አለ ! በተመሳሳይ ተግባር ላይ፧ ይህ የወያኔ ተላላኪ የዋሽንግተን ዲሲንና የአካባቢዉን ኢትዮጵያዊ ይቅርታ ካልጠየቀ በተጨበጠ ማስረጃ አርጩሜዬን ማንሳቴ እዉነት ሊሆን ነዉ።

ዛሬ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ላለፉት ሀያሁለት አመታት እንደመዥገር ተጣብቆበት ደሙን በመምጠጥ ላይ ያለውን ፋሽስታዊ አምባገነን አገዛዝ ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ዜጎች በተለያየ አቅጣጫ በአንድነት ርብርብ በማድረግ ላይ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት ከእንደዚህ አይነት ሆድአደር እበላባይ ተርታ አጉራዘለል ግለሰብ ጋር እሰጥ አገባ መግጠሙ ደግ ባይሆንም የሱና የመሰሪ ጓደኞቹ አካሄድ በሕዝባዊዉ ትግል ላይ የሚያሳድረዉ ተፅእኖ ቀላል ባለመሆኑ ቀይ ካርድ ማሳየቱ ወቅቱ የሚጠይቀዉ ቁም ነገር ነዉ። ያለፈዉን የመንደርደርያ ፅሁፍ የተመለከቱ ወገኖች በተለይ ደግሞ በዚህ ግለሰብ ጥቃት የደረሰባቸው ኢትዮጵያዉያኖች ሀብት ንብረታቸውን ተቀምተዉ ያዘኑትን ጨምሮ ራዲዮ ጣቢያው ሲመሠረት አብረዉ አጋር የነበሩና በራዲዮኑ ስም የሚሰራዉ ተቃዋሚ ድርጅቶችን የማፍረስ ደባና የሚዘረፈዉ የየዋህ አገር ወዳዶች ገንዘብና ንብረት የተነሳ ጥለዉት የሄዱት አባሎቹ የሰጡት አጋላጭ የድምፅና የፅሁፍ ማስረጃ በጄ ገብቷል።ለዚህ ነው የዛሬዉን ርእሴን የመረጥኩበት ሁለተኛዉ ምክኒያቴ፧የንጉሴ ወልደማርያም ሀገር ፍቅር ራዲዮ፣የመቶ አለቃ ምርጫዉ ስንሻዉ ኢትዮጵያዊነት ራዲዮ፧የፀሀዬ ደባልቄ ሰላም ራዲዬ፤ልዩ ራዲዮና የዮሴፍ ግዛቸዉ አንዲት ኢትዮጵያ ራዲዮ ጣቢያዎች በዋሽንግተንና አካባቢዉ የሚገኘዉን ኢትዮጵያዊ ከወያኔ አምባገነን ስርዓት ምስረታ ማግሥት ጀምሮ ገንዘቡን በመዝረፍና የትግል ተነሳሽነት ወኔዉን በማኰላሸት የጨካኙን የወያኔ አምባገነን ሥርዓትእድሜ እያራዘሙለት ይገኛሉ።

በዚህ ጽሁፍ መደምደሚያ ላይ አንባቢዎቼን ላስገነዝብ የምፈልገዉ አንድ ቁምነገር ፧አለ ፧ይኸዉም መቶ አለቃዉ የወያኔን አምባገነን አገዛዝሥርአት ከማዉገዙ ጎን ለጎን የሚያስተላልፋቸዉ ከፋፋይ የተቃዋሚ መሪዎችንና ታዋቂ አገር ወዳድ ግለሰቦችን ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በጐደለዉ በአጉራዘለል ቋንቋ መዝለፍ ጥቅሙ ለማን ነዉ? የማንን ጡንቻ ነዉ የሚያፈረጥመዉ የየትኛዉስ የትግል ጎራ ነዉ የሚኮስሰዉ?! ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያኖች የህሊና ፍርድ እተወዋለሁ!የዚህ ግብዝ ማንነት የቆመለትንም አላማና ተልእኮ ማወቅ ያስችላል። ገንዘብ ሲያጣም ሆነ ሲያገኝም የሚያሳብደዉን የጓድ መቶ አለቃ ምርጫዉ ስንሻዉን አይን ያወጣ መሠሪ ከፋፋይ እንቅስቃሴዎች ከነማስረጃዎቼ በሚቀጥለዉ ፅሁፊ እመለስበታለሁ ፅሁፎቹም የሚያተኩሩት በሚከተሉት ነጥቦች ዙርያ ይሆናል፦

፩ኛ፦ቤተክርስቲያን በመክፈት ስለሚያገኘዉ ጥቅምና በዚህ ዙርያ የፈፀማቸዉን አስነዋሪ ተግባራት፣

፪ኛ፦ከስራ ጓደኞቹ ጋር በመሆን የተሰበሰበ የዕቁብ ገንዘብ ይዞ ስለመሰወሩ

፫ኛ፦በደርግ ዘመን በወገኖቻችን ላይ ያደርስ ስለነበረዉ በደል

፬ኛ፦በሚያሰራጨዉ ራዲዮ ላይ በአንድ ወቅት ሼክ መሐመድ አላሙህዲንን በመዝለፉ ምክንያት ስለተመሰረተበት ክስና አማላጅ ልኮና እግር ላይ ወድቆ ይቅርታ ስለመጠየቁ

፭ኛ፦ደራሽ ግብረሀይል ብለዉ በድርቅ በተጐዱ ወገኖቻችን ስም የተሰበሰበዉን ከሁለት መቶ ሺህ ዶላር በላይ ከንጉሤ ወልደማርያምጋርበመሆንዘርፈዉስለተሰወሩት ገንዘብ

፮ኛ፦በቅንጅት መሪዎች መፈታት ማግስት ኢንጅነር ኃይሉ ሻወልን በማጥመድ ይህንን ተትሎ ከመሠል ጓደኞቹ ጋር በመሆን ለቅንጅት መፍረስ ምክንያት የተጫወተዉ ከፍተኛ ሚና

፯ኛ፦ቀደም ሲል ከዋሽንግተን ዲሲ በአማርኛ ቋንቋ የሚተላለፈዉን የቪኦኤ ራዲዮ ጣቢያ ለማዘጋት የተቃዉሞ ሰልፍ በማደራጀት ስላስተባበዉ እንቅስቃሴ

፰ኛ፦እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ከቅርብ አመታት ወዲህ በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት ሕዝቡን ለትግል በማነሳሳት ላይ የሚገኙት የኢሕአፖ ወጣቶች ክንፍ ዉስጥ ሰርጎ በመግባት ከእናት ድርጅታቸዉ ለመነጠል የሚያደርገዉን እንቅስቃሴና መሰል ወያኔያዊ ተልዕዎቹን በዝርዝር እንመለከታለን

ዉድ ለአንባቢዎች፦ እነዚህን የመሳሰሉ የዳያስፖራውን አንድነትና ትግል በወያኔ የምፅዋት ገንዘብ ሽባ የሚያደርጉትን አረመኔ ሆድ አደር ተላላኪዎች በቃችሁ እንበላቸዉ!!!

ክፍል ፫ ይቀጥላል፦ ናደዉ።

http://ecadforum.com

posted by Tseday Getachew

Advertisements

ከቤንሻንጉል ተፈናቅለው ከነበሩት የአማራ ተወላጆች ከፍተኝ ድብደባ ተፈፀመባቸው – ፍኖተ ነጻነት

ከተደበደቡት ዘጠኝ ሰዎች መካከል ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሶስት ተጎጅዎች ወደ አማራ ክልል ቻግኒ ከተማ መጥተው በግል ክሊኒኮች እየታከሙ መሆናቸውን አስታማሚዎች የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ከስፍራው ዘግበዋል፡፡ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸው ቻግኒ ከተማ እየታከሙት የሚገኙት ግለሰቦች አቶ በለጠ መንግስቴ፣ አቶ ጥላሁን ገበየሁ፣ አቶ …

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ወይም ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።

http://www.ethiopianreview.info

posted by Tseday Getachew

መኢአድና አንድነትን ለማዋሐድ እየተሞከረ ነው

ውህደቱ ከሰመረ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ
(መኢአፓ) የተባለ አዲስ ፓርቲ ሊፈጠር ይችላል

በዘሪሁን ሙሉጌታ

የመኢአድ ፕሬዚዳንትነቱን ለወጣት አስረክበው የወረዱት ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል

የመኢአድ ፕሬዚዳንትነቱን ለወጣት አስረክበው የወረዱት ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)ን ለማዋሐድ ተቋርጦ የነበረው ውይይት ለመጀመር እየተሞከረ ነው። የውህደቱን ሂደት የሚመሩ ከየፓርቲዎቹ ሦስት ሦስት አባላት ያሉበት የውህደት አመቻች ኮሚቴ እንዲቋቋም በመርህ ደረጃ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

ቀደም ሲል ሁለቱ ፓርቲዎች ለማዋሐድ አመራሮቹ የተለያዩ ጥረቶች ሲያደርጉ ቆይተዋል። ሌሎች ሀገር ወዳድ ምሁራን ጋር በመሆን በኢንጂነር ኃይሉ መኖሪያ ቤት ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ምክክር ሲደረግ መቆየቱን አንድ የአንድነት ከፍተኛ አመራር በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልፀዋል። ነገር ግን የሁለቱ ፓርቲዎች ድርድር አንድነት በመድረክ ውስጥ በመሳተፍና መኢአድ መድረክ በጎሳ የተደራጁ ፓርቲዎች ስብስብ በመሆኑ መኢአድ ከፓርቲዎቹ ጋር የፕሮግራም ልዩነት እንዳለው በመግለፁ ድርድሩ ሳይሳካ መቅረቱ ይታወቃል። በመቀጠልም ባለፉት ሁለት አመታት መኢአድ በውስጥ ችግር በመቆየቱ ሁለቱን ፓርቲዎች የመዋሐድ ሐሳቡ ሳይንቀሳቀስ ቆይቷል።

ሆኖም ሰሞኑን መኢአድ ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ አዲስ ፕሬዝዳንት ከመረጠ በኋላ ተቋርጦ የነበረው ፓርቲዎቹን የማዋሐድ ኀሳብ እንደገና መንቀሳቀስ መጀመሩን ለሁለቱም ፓርቲዎች ቅርበት ያላቸው ምንጮች አረጋግጠዋል።

ቀደም ሲል ‘‘33ቱ ፓርቲዎች’’ ጋር አብሮ ለመስራት የነበረው ሂደትን ሰማያዊ ፓርቲ ለብቻው ሰላማዊ ሰልፍ በመጥራቱ በሌሎች ፓርቲዎች በኩል መጠነኛ ቅሬታ በመፍጠሩ አሁን ሁለቱን ፓርቲዎች በማዋሐድ ትግሉን ለማጠናከር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ምንጫችን ጠቁሟል።

አንድ የመኢአድ ከፍተኛ አመራር ሁለቱ ፓርቲዎች በቅንነት ከተንቀሳቀሱ አዲስ ውህድ ፓርቲ መፍጠር እንደሚችሉና ከሁለት አመት በኋላ በሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ ጠንካራ ሆነው ሊወጡ እንደሚችሉ ገልፀዋል። ውህደቱ ከሰመረ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ (መኢአፓ) የተባለ አዲስና ጠንካራ፣ ፓርቲ መመስረት እንደሚቻልም ግምታቸውን ገልፀዋል።

 

አስራት ጣሴ

አስራት ጣሴ

የአንድነት ፓርቲ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስራት ጣሴ ጉዳዩን በተመለከተ ከሰንደቅ ጋዜጣ ጥያቄ ቀርቦላቸው ‘‘ጉዳዩን ማንም የነካካው የለም’’ ካሉ በኋላ በመርህ ደረጃ ፓርቲዎቹን ለመዋሐድ የተጀመረው ጥረት እንደሚቀጥል ግን ተስፋቸውን ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ አቶ አስራት ‘‘ጉዳዩን የነካካው የለም’’ ቢሉም ሰሞኑን በመኢአድ ጽ/ቤት መገኘታቸውን በተመለከተ ተጠይቀው በቀጣይ 33ቱ ፓርቲዎች ስለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ከመኢአድ አዲሱ አመራር ጋር ለመወያየትና አዲሱን የመኢአድ ፕሬዝዳንት እንኳን ደስ አለህ ከማለት ባለፈ በጉዳዩ ላይ በኮሚቴ ደረጃ ውይይት አለመጀመሩን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የመኢአድ አዲሱ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሓሪ ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አቶ አስራት ጣሴ በፓርቲው ጽ/ቤት ተገኝተው ሁለቱ ፓርቲዎች በሚዋሐዱበት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ውይይት ማድረጋቸውን አረጋግጠዋል።n

ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ የረቡዕ ጁላይ 30 ቀን 2013

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=5758

posted by Tseday Getachew

 

የአማራ ብሔር ተወላጆች ዳግም ከጉራፈርዳ እየተፈናቀሉ ናቸው ተባለ

  በደቡብ ክልል በቤንቺ ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ እየሩሳሌም ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የአማራ ብሔር ተወላጆች፣ ዳግም እየተፈናቀሉ መሆኑን ሰማያዊ ፓርቲና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አስታወቁ፡፡

ሁለቱ ፓርቲዎች ሐምሌ 18 ቀን 2005 ዓ.ም. በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት መንግሥት ቀደም ብሎ በጉራፈርዳ ወረዳ፣ በሸፒ ቀበሌና በተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ነዋሪ የነበሩት የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች መፈናቀላቸውን ተከትሎ፣ መንግሥት በአፈናቃዮቹ ላይ ዕርምጃ እንደሚወስድ ቢያሳውቅም፣ ዜጐቹ ግን እስካሁን እየተፈናቀሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ተወካይ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ፣ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው ለዓለም ሕዝብ ጭምር በሰጡት ማብራሪያ፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እንዲፈናቀሉ የተደረጉ የአማራና የኦሮሞ (የዘር ማጥራት ወንጀል እንዳይመስል) ተወላጆችን ያፈናቀሉ ኪራይ ሰብሳቢዎች ላይ፣ መንግሥት ዕርምጃ እንደሚወስድና ተፈናቃዮችም ወደ ቀያቸው በአስቸኳይ እንደሚመለሱ የተናገሩ ቢሆንም ተግባራዊ አልሆነም፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡

Source: reporter.

http://ethioforum.org

posted by Tseday Getachew

አንድነት ፓርቲ – በአምስት የክልል ከተሞች ለሚያደርጋቸው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎችና ህዝባዊ ስብሰባዎች ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል

አንድነት ፓርቲ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም በአምስት የክልል ከተሞች ለሚያደርጋቸው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎችና ህዝባዊ ስብሰባዎች ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አስፈላጊውን የማሳወቅ ተግባር እንደጨረሰ አስታወቀ፡፡ ፓርቲው በመጪዎቹ ቀናት በባህር ዳር፣ በጅንካ፣ በመቀሌ፣ በአርባ ምንጭና በወላይታ ሶዶ ቅስቀሳ ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ከዋናው …

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ወይም ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።

http://www.ethiopianreview.info

posted by Tseday Getachew

Hiber Radio: በአቶ መለስ ልጅ ስም በኒዮርክ ባንክ አለ የተባለውን 5 ቢሊዮን ዶላር የሚያሳየው ቼክ ጉዳይ እንዲጣራ ለአሜሪካ መንግስት ሊቀርብ መሆኑ ተገለጸ

 

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ሐምሌ 21 ቀን 2005 ፕሮግራም

< <…በግብጽ አዲሱን ሕዝባዊ አብዮት ያስነሱት ሻይ ቤት እንደ ቀልድ የመከሩ፤ ከኮምፒዩተር በስተቀር መሳሪያ የሌላቸው፤ በዕምነታቸው ሙስሊም የሆኑ የሙርሲ መራጮች ነበሩ። በአንድ ዓመት አገዛዙ የተማረሩ ናቸው። እነዚህ ወጣቶች ሚሊዮኖችን አደባባይ አውጥተው እንዴት መንግስት ሊቀይሩ ቻሉ? …>

የግብጽን አብዮት በአብነት ከወቅታዊ ጉዳይ ጋር ቃኝተነዋል(ሙሉውን ያዳምጡት)

< <…ሽማግሌዎቹ ለእኛ ያመጡት አዲስ ነገር የለም…>አቶ ሞገስ ሽፈራው በቬጋስ በስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉት አሽከርካሪዎች የሕግ ጉዳይ ኮሚቴ አባላት አንዱ

< <…ሃያ አንድ ዓመታት ያስቆጠረው የጎሳ ፌዴራሊዝም በኢትዮጵያ ውስጥ ያስከተለው ጉዳትና የፈጠረው ቀውስ ሲፈተሽ (ወቅታዊ ትንታኔ)

 

< <…እዚህ ጋር ቁምልኝ አለኝ። አደጋ ያስከትላል አይቻልም አልኩት። በግድ ታክሲውን ሊያቆም ሞከረ።አልቻለም። ሳላስበው መታኝ። ራሴን ሳየው ደምቻለሁ። ተጎድቼ ነበር።…>

በተሳፋሪ የተደበደበ ኢትዮጵያዊ የታክሲ አሽከርካሪ በቬጋስ …

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ወይም ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።

 
 
posted by Tseday Getachew

ግልፅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ (ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማሪያም)

Amhara Ethnic group members Ethiopia
የቤኒሻንጉል ተፈናቃዮች አሁንም በችግር ላይ ናቸው” (መኢአድና ሠማያዊ ፓርቲ) ከቤኒሻንጉል ክልል ተፈናቅለው ከነበሩት የአማራ ክልል ተወላጆች ጋር በተያያዘ የክልሉን የስራ ሃላፊዎችና መንግስትን ለመክሰስ….. ሰማያዊ ፓርቲና መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጥብቅና ያቆሟቸው አለም አቀፍ የህግ ባለሙያው ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማሪያም፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ግልፅ ደብዳቤ መፃፋቸው ተገለፀ፡፡ ሁለቱ ፓርቲዎች ከትናንት በስቲያ ከሠዓት በኋላ በሠማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በጋራ በሠጡት መግለጫ፤ ተፈናቃዮቹ አሁንም ችግር ላይ መሆናቸውን፣ ልጆቻቸው ትምህርት ማቋረጣቸውን፤ በሚዲያ እንደሚነገረው ወደ ቀድሞ ኑሯቸው አለመመለሳቸውንና በአጠቃላይ ችግር ላይ መሆናቸውን በማስረጃ በማስደገፍ፣ የጉራፈርዳንና የቤኒሻንጉል ተፈናቃዮችን በማነጋገርና በበርካታ መረጃዎች የተደገፉ ዶክሜንቶችን በማያያዝ ዶ/ር ያዕቆብ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የላኩትን ደብዳቤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ፈርሞ
መቀበሉንም ፓርቲዎቹ ገልፀዋል፡፡
የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት እንደተናገሩት፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ችግሩን በፓርላማ ቀርበው ማመናቸውን፣ ድርጊቱን ፈፅመዋል የተባሉት የክልልና የወረዳ ስራ አስፈፃሚዎች ከስራ መሰናበታቸውን፣ ተፈናቃዮቹ ወደነበሩበት ተመልሠው በሠላም እየኖሩ እንደሆነ የገለፁ ቢሆንም እውነታው ግን ከዚህ በተቃራኒው መሆኑን ዶ/ር ያዕቆብ ከተፈናቃዮች ጋር በመነጋገር ማረጋገጣቸውን ጠቁመው፣ ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት ከመሄዱ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሠጡ ዶ/ር ያዕቆብ ለጠ/ሚኒስትሩ በላኩት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡ ዶ/ር ያዕቆብ፤ አፋጣኝ ምላሽ ያሻቸዋል ያሏቸውን አራት ዋና ዋና ነጥቦች በደብዳቤያቸው ላይ ያሰፈሩ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ተፈናቃዮቹ
ወደ ቀድሞ ቦታቸው በመንግስት ወጪ ተመልሠው መሬታቸው፣ የንግድ ተቋሞቻቸውና ቤት ንብረታቸው በአስቸኳይ እንዲመለስላቸው፣ ተፈናቃዮቹ ለደረሰባቸው ቁሳዊ ጉዳት፣ አካላዊና ሞራላዊ እንግልት መንግስት ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፍላቸው የሚመለከታቸውን አካላት እንዲያዝዙ፣ በቤኒሻንጉል የሚኖሩ የማንኛውም ብሄር ተወላጆች ተመሳሳይ ወንጀል እንዳይፈፀምባቸው ጥበቃ እንዲደረግላቸው እና ተዋዶና ተፋቅሮ የሚኖረውን ህዝብ በመከፋፈል የማፈናቀል ድርጊት የፈፀሙ የመንግስት ባለስልጣናት ህግ ፊት ቀርበው ቅጣት እንዲያገኙ ውሳኔ እንዲያሳልፉ የሚሉት ነጥቦች ተቀምጠዋል፡፡

መንግስት ወንጀለኞች ያላቸውን የወረዳ ስራ አስፈፃሚዎች ከስራ ማሠናበቱንና ጉዳያቸው በፍ/ቤት እየታዩ ያለ ባለስልጣናት እንዳሉ፣ ተፈናቃዮቹም ወደ ቀድሞ ህይወታቸው ተመልሠዋል እየተባለ ነው የተፈናቃዮቹን ጉዳይ ለምን በተደጋጋሚ ማንሳት ፈለጋችሁ በሚል ከጋዜጠኞች ለተነሳው ጥያቄ “ኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲከኛ ለመሆን በርካታ ምክንያቶች አሉ” ያሉት ኢ/ር ይልቃል፤ ነገር ግን ተፈናቃዮች አሁንም በችግር ላይ ናቸው ቤት ንብረታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ተቀራምተውት በክረምት ሜዳ ላይ የወደቁ አሉ፣ በፋሲካ በዓል ቤታቸው የተቃጠለባቸው ተፈናቃዮች አሉ፣ ወደ ቀድሞ ቦታቸው ያልተመለሱትም በርካቶች ናቸው ካሉ በኋላ “ጠበቃችን ዶ/ር ያዕቆብ ይህንን ጉዳይ ከተፈናቃዮቹ በተጨባጭ አረጋግጠዋል” ሲሉም አክለዋል፡፡ የመኢአድ ዋና ፀሀፊ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ በበኩላቸው፤ የጉራፈርዳ ተፈናቃዮች በችግር ላይ ለመሆናቸው ጋዜጣዊ መግለጫውን እስከሠጡበት ሰዓት እንኳን መረጃዎች እየደረሷቸው እንደሆነ ገልፀው፣ በጠበቃው ዶ/ር ያዕቆብ በኩል ደብዳቤ መፃፋችን ጉዳዩ በፍ/ቤት እልባት እስኪያገኝ አስቸኳይ መፍትሄ  እንዲሠጣቸው ነው ብለዋል፡፡

ችግሩ መቆም ያልቻለው ከመረጃ እጥረት ይሆናል በሚል ምን ያህል ሰዎች በችግር ላይ እንዳሉ፣ ቤት ንብረታቸውን ቆጥረው የተመዘገቡበት መረጃ ከየምርጫ ጣቢያው የወሠዱትን ካርድ መልሠውና ንብረታቸውን አስመዝግበው እንዲወጡ በሀላፊዎች ፊርማና በመንግስት ማህተም የታዘዙበት ደብዳቤና በርካታ ዶክሜንቶችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከደብዳቤው ጋር አያይዘው መላካቸውም ተገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአገሪቱ መሪ እንደመሆናቸው ችግሩንም በፓርላማ ቀርበው ማመናቸው እንደ ማስረጃ ተቆጥሮ የአገሪቱ የስራ አስፈፃሚ ከፍተኛ አካል በመሆናቸው ስለሚከሰሱ “መረጃው የለኝም አላየሁም” እንዳይሉ ታስቦ፣ ዶክሜንቱ እንደተላከላቸውም በፓርቲዎቹ ተገልጿል፡፡ ወደ ክስ ከሄዳችሁ ደብዳቤው ለምን አስፈለገ? ጠ/ሚኒስትሩ ምላሽ ከሠጡስ ክሱ ይቆማል ተብሎ ከጋዜጠኞች ለተነሳው ጥያቄ “ችግሮች መፍትሄ ካገኙ ክሱ ቀድሞውኑ ለምን ያስፈልጋል” ያሉት ኢ/ር ይልቃል፤ “መንግስት ይህን ወንጀል የፈፀሙትን አስሬያለሁ ከስራ አሠናብቻለሁ” የሚለው ጉዳዩ አለም አቀፍ ስለሆነበት ውጥረቱን ለማርገብ ነው ብለዋል፡፡ ምላሽ ካላገኛችሁ በትክክል ክስ መቼ ትጀምራላችሁ ለሚለውም፤

ወንጀሉ የይርጋ ጊዜ ስለሌለው ዶ/ር ያዕቆብ ለህክምና ከሄዱበት አሜሪካ ሲመለሱ ይጀመራል፣ በአገር ውስጥ ፍ/ቤት ካልተሳካ ጉዳዩ ወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች ያመራል ብለዋል – የመኢአድ ዋና ፀሀፊ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ፡፡ እስካሁንም በጉራፈርዳ ከሚኖሩ 78ሺህ የአማራ ተወላጆች መካከል 21ሺህ ያህሉ መፈናቀላቸውንና በቤኒሻንጉልም ከአምስት ሺህ በላይ ተፈናቃዮች አፋጣኝ መፍትሔ እንደሚሹ የፓርቲው አመራሮች ተናግረዋል፡፡

http://www.maledatimes.com/

posted by Tseday Getachew

! …. የህወሓት የድሮ ታጋይ ‘አሸባሪ’ ተባለ ….! ~ በአብርሃ ደስታ

 7c196-1001168_485348238212789_1719160956_n

ስዒድ አሕመድ ይባላል። የድሮ የህወሓት ታጋይ ነው። በትጥቅ ትግሉ ወቅት የትግራይ ህዝብ ለትግሉ በማነሳሳትና ትግሉ በመምራት ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ግንባር ቀደም ሚና ተጫውቷል። የደርግ ስርዓት ከተገረሰሰ በኋላ እንደሌሎች ታጋዮች ከውትድርና ተቀንሶ በግል ስራ ተሰማርቶ ህይወቱ ሲመራ ቆየ። ባለፈው ሓሙስ (ሓምሌ 18) የፌደራል ፖሊሶች የትጥቅ መሳርያው እንዲያስረክብ ይጠይቁታል። ስዒድ ደግሞ አሁን ምንም ዓይነት መሳርያ እንደሌለውና የድሮ ትጥቁ ደግሞ ከዓስር ዓመት በፊት በሕጋዊ መንገድ ለመንግስት አካላት ማስረከቡ በማስረጃ ያስረዳል። ፖሊሶቹም ‘በሽብር ተጠርጥረሃል’ በሚል ሰበብ ዓፍነው ይወስዱታል።

የስዒድ ቤተሰቦች ከስራ ቦታው በፖሊሶች ታፍኖ መወሰዱ እንጂ ወዴት እንደወሰዱት (የት እንደታሰረ) ስላላወቁ ከሦስት ቀናት ፍለጋ በኋላ ትናንት (ቅዳሜ) ማታ በኲሓ ታስሮ እንደሚገኝ ለማወቅ ቻሉ። ስዒድ በምን ይሆን የታሰረው?

ስዒድ በትጥቅ ትግሉ የነበረውን ድፍረት ተጠቅሞ ባለፈው የሙስሊሞች የመጅሊስ ምርጫ በቀበሌ ሳይሆን በመስጊድ መከናወን እንዳለበት ጠንከር ያለ አስተያየት ሰጥቶ ነበር። ከዛ በኋላ የመንግስት አካላት ስዒድን ለማሰር ምክንያት ሲያፈላልጉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

ስዒድ ለምን ነበር የታገለው? ወይ ወላዲት ትግራይ ዝረከብክዮ መዓት!

It is so!!!

 
posted by Tseday Getachew
 

ሰበር ዜና፣ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ቤት በፖሊሶች እየተበረበረ ነው

ብርበራው ቀኑን ሙሉ እንደሚደረግ ታውቋል

በደቡብ ወሎ ዞን በሀይቅ ከተማ የሚገኙ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ቤት ላይ ዛሬ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ብርበራ እንደተጀመረ የዞኑ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡

የአንድነት ፓርቲ የወረባቡ ወረዳ ሰብሳቢ አቶ እድሪስ ሰኢድ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት ዛሬ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ “የጦር መሳሪያ ሰውራችኋል” በሚል ፖሊሶችና ሚኒሻዎች በሀይቅ ከተማ ባሉ ከ16 በላይ በሚሆኑ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት መኖሪያ ቤት ውስጥ ብርበራ አካሂደዋል፡፡ ብርበራው ከተካሄደባቸው አመራሮች መሀከል አንዱ የሆኑት የወረዳው የአንድነት ፓርቲ የፋይናንስ ኃላፊ አቶ አራጌ ሑሴን ለሪፖርተራችን እንደገለፁት 5 ፖሊሶችና 1 ሚሊሻ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምረው መኖሪያ ቤታቸውን ፈትሸዋል፡፡ አቶ አራጌ ሁሴን አክለውም “እኔ ሰላማዊ ሰው ነኝ ምንም አታገኙም አልኳቸው፤እንዳልኩትም 2 ሰዓት የፈጀ ብርበራ አድርገውም አንዳች ሳያገኙ ወጥተዋል” በማለት ገልፀዋል፡፡

“ብርበራው መንግስት በአንድነት አባላት ቤት ውስጥ የጦር መሳሪያ አገኘሁ በሚል የተለመደ ድራማ ለመስራት እንደተዘጋጀ የሚያስረዳ ነው” ያሉት የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ወሎ ዞን ሰብሳቢ አቶ ብስራት አቢ ኢህአዴግ የደቡብ ወሎ ህዝብ በግዳጅ አንድነት ፓርቲን እንዲያወግዝ በተለያዩ ከተሞች ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፎችን እንደጠራ አስረድተዋል፡፡ በአንድነት አባላት ቤት የሚደረገው ብርበራ እስከ ምሽት ሊቀጥል እንደሚችልም ለፍኖተ ነፃነት የደረሱ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

http://ecadforum.com

posted by Tseday  Getachew

ለሰነበተ የዶ/ር ፈቃደ አዘዘ ጥያቄ መልስ – በክፍሉ ሁሴን

The Ethiopian Air Force is the air arm of the Ethiopian National Defense Forces

አፍቃሪ ወያኔ የፌስቡክ ወዳጄ “ሰላማዊት ስዮም”በጣለችልኝ የፍልሚያ ሸማ መሰረት ምላሹን ልሰጥ ለዛሬ ቃል ገብቼ ነበር።ሰላማዊት “እስቲ ስለዘንድሮ ፓይለቶች (ወያኔ የአየር ሃይል ፓይለት ይሁኑልኝ ብሎ በትዕዛዝ ወይም በአብዮታዊ ዴሞክራሲ አግባብ “ፓይለት” የሆኑትን ማለቷ ነው) አውቃለሁ የምትለውን ያህል ስለድሮዎቹ በሐውዜንና በመሳሰሉ ቦታዎች በገበያ ላይ ቦምብ እየጣሉ ሰላማዊ ሕዝብ ስለፈጁት ፓይለቶች ደም ከውሃ ይወፍራል በሚለው አይነት ሳትደብቅ ንገረን፤ለልጆችህም ንገራቸው (አባቴ የኢትዮጲያ ንጉሰ ነገሥት መንግስት አየር ሃይል ቆፍጣና መኮንንና ፓይለት የነበረ መሆኑን ዘወትር በኩራት የማነሳውን ተሸማቅቆ ሁለተኛ አያነሳውም በሚል የተወረወረ ወያኔያዊ አሽሙር መሆኑ ነው) ስትል “ተፈታተነችኝ።” ለእሷም ሆነ የታሪክን ሚዛን ለመጠበቅ ሲባል ምላሹን ለዛሬ ይዤ ለመቅረብ ቃል ስገባ እስከዚያው የዶ/ር ፈቃደ አዘዘን “ዲሞክራት ፓይለቶች”የሚለውን ግጥሙን ‘አያ ጎሽሜ’በሚል ርዕስ ካሰተመው መድብሉ እያነበባችሁ ጠብቁኝ ማለትን ዘነጋሁ።ግድየለም ይህ ምላሽ ካልተንዛዛ እዚሁ ላነሳው እሞክራለሁ።አሁንወደ ጭብጡ።

የአንድ ደቂቃ አርምሞ (A minute of silence) ለኢትዮጲያውያን የጦርነት ሰለባዎች

ስለሐውዜን እልቂት ነገሩ በዝርዝር ሳይገባኝ መጀመሪያ የሰማሁት በ1982 ዓ.ም ግንቦት ወር መጨረሻ አካባቢ ነው።በዚያን ጊዜ ኢትዮ-ሊቢያ የጋራ የማዕድን ኩባንያ የሚባል መ/ቤት እሰራ ነበር።አብረውኝ ከሚሰሩ ሁለት የኩባንያው ፀሃፊዎች ጋር ከምሳ በኋላ ቡና ጠጥተን እየዘቀጠ በመሄድ ላይ ያለውንና ከሃያ ሶስት አመት በኋላም ምንም መሻሻል ያልታየበትን የአገራችንን ፖለቲካ በሹክሹክታ እንደተለመደው አንስተን መውቀጥ ጀመርን።ከእነዚሁ ከትግሪኛ ተናጋሪ (አንዷ ራሷን ከአድዋ አንዷ ራሷን ከኤርትራ የሚያጣቅሱ ነበሩ) ወገን ከሆኑ ጓደኞቼ ከአድዋ የሆነችውና በእድሜም ላቅ ያለችው በድንገትወደኔ አተኩራ “እናንተ ጄኔራሎች ሲሞቱ ብቻ ነው የደርግ ክፋት የሚታያችሁ የትግራይ ሕዝብ በአውሮፕላን ሲጨፈጨፍ ግን ደንታ አይሰጣችሁም።”ጭውውታችንን በምናደርግበት ጊዜ በግንቦት ስምንት 1981 ዓ.ም መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ሳቢያ የኢትዮጲያን ጦር ሃይል  ከአረመኔነትና ከፈርጣጭነት ጋር ስሙ ዘላለም በክፉ እንዲነሳ ያደረገው ፈርጣጩ “ቆራጡ የአብዮታዊ ጦር ጠቅላይ አዛዥ”በቁጥጥር ስር ካዋላቸው ቀሪዎቹ ከፍተኛ መኮንኖቹ ውስጥ ከአንድ ዓመት በኋላ በዚያው በገፊነት በሚታወቀው ግንቦት ወር አስራ ሁለቱን የፈጀበት ጊዜ ነበር።ለአድዋዋ መልሴ በመፈንቅለ መንግስቱ ያለቁት ጄኔራሎች አብዛኞቹ በመንግስቱ ኃ/ማሪያም ደደብ አመራር እየተንዛዛ የሄደውንና አላስፈላጊ ከፍተኛ እልቂትና የንብረት ወድመት ያደረሰውን የርስ በርስ ጦርነት ለመግታት እንጂ በግልማ ከሰው የተለየ ችግር እንደሌለባቸው እንዲያውም የተንደላቀቀ ኑሮ ሊገፉ ይችሉ እንደነበር ላመላክታት ሞከርኩ።ይህ አይነቱ ሚዛናዊ ክርክር ያኔም ብዙ ዋጋ እንደሌለው ዛሬም ብዙ ዋጋ የለውም።ያም ሆኖ እንደወያኔ፣ሻዕቢያና ደርግ የመሳሰሉ እኩይ ድርጅቶች በጫሯቸውና ሆነው ብለው እሳቱን ለረጅም ጊዜ እንዲቀጣጠል በማድረግ ላለቁት ሲቪሎችም ሆነ የኢትዮጲያ ጦር መለዮ ለባሾችና የተገንጣይ አስገንጣይ ቡድን ጀሌዎች የአንድ ደቂቃ የአርምሞ ጊዜ ባለሁበት ወስጄያለሁ።

መንግስቱ ፈረጠጠ፤መለስ ነገሰ፤የሐውዜን ድራማ በቴሌቪዥን ቀረበ

አሰቃቂው ድራማ በቴሌቪዥን በቀረበ ማግስት ከአድዋ የሆነችው ባልደረባዬ ሰላምታ ሳታቀርብልኝ በፊት ይህ ነው ሊሉት በማይችሉት ከፍተኛ ስሜት ተውጣ እየተፍነከነከች “ትናንት ማታ አየህ የሐውዜንን ጭፍጨፋ?”ስትል ጠየቀችኝ።”ህፃናትን ሳይቀር  በጀሌነት አሰልፎ ሆነ ብሎ ሲቪሉ ስር ተጠልሎ የሚዋጋ አጋሚዶ እንዲህ ያለ እልቂት ያስከትላል።”ነበር መልሴ።ለነገሩ ፊልሙን ከሁለት ደቂቃ በላይ አላየሁትም፤ምን ሊያደርግልኝ ከፊልሙ አቀራረፅ ተልዕኮው ግልፅ ሆኖ ሳለ!ተልዕኮውን ገብረመድህን አርአያ ኋላ ላይ ግልፅ እንዳደረገልን ሁሌም ስንጠረጥር እንደነበረው የወያኔ የለየለት የመሰሪነት ውጤት ነው።ገብረመድህን አርአያ ቀድሞ የወያኔ አባል የነበረና ወያኔ በረሃብተኞች ስም የመጣውን እርዳታ ቸብችቦ ከጦር መሳሪያ ግዢ በተጨማሪ እንዴት አመራሩ እንደደለበበት በሰጠው የማያወላዳ መረጃ መሰረት የቢቢሲው ማርቲን ፕሎት አንድ ሰሞን አለምን ያነጋገረና ቦብ ጊልዶፍ የሚባለውን “በጎ አድራጊ”የፈረንጅ አቀንቃኝ ጭምር ያበሳጨ ፕሮግራም እንዲሰራበት ያደረገ ውስጥ አዋቂ ነው።ገብረመድህን ስለሐውዜኑ እልቂት የሚከተለውንም ይለናል።

“ወያኔ ኤርትራን ለማስገንጠል ከሻዕቢያ ጋር በምታደርገው መሞዳሞድና በሌሎችም ምክንያቶች በትግራይ ሕዝብ የተጠላችበት ጊዜ ስለነበር ሰው አጣች፤የሚመለመል ጠፋ።ስለዚህ ተንኮል አሰቡ።በለገሰ አስፋው የትግራይ አስተዳዳሪነት ጊዜ አንድ ክፍለ ጦር ሐውዜን ገባ ወጣ እንዲል አደረጉ፤ወያኔ ትልቅ ስብሰባ ሐውዜን ላይ ሊያደርግ ነው የሚል የውሸት መረጃ ለለገሰ አስፋው እንዲደርሰው አደረጉ።በዚያን ጊዜ ይህን ያቀነባበረው ሃይሉ ሳንቲም የሚባል የወያኔ የወታደራዊ ደህንነት ነው።ቀደም ብለው ባሰቡበት መሰረትም ፊልም ቀረጻ እንዲሰለጥኑ ተክለወይን አስፍሃ፣ሱራፌል ምህረተአብ፣ኢያሱ በረሄ ወዘተ ሱዳን ተላኩ።ደርግ መረጃው እውነት እንዲመስለውም የተወሰኑ ታጋዮች በሐውዜን ገበያ ቦታ ውር ውር እንዲሉ ተደረገ።ደርግም ተጨማሪ ማጣራት ሳያደርግ ስድስት ሚጎች ልኮ አስደበደበ።ያ ሁሉ ድብደባ ሲደረግ እነኢያሱ በሰለጠኑት መሰረት ተራራ ላይ ቆመው ከሁሉም አቅጣጫ እያንዳንዱን ሚግ ቪዲዮ ይቀርጹ ነበር።”

ይህ ሊታመን የማይችል ነው የሚል ወያኔ ከሚነግድበት የሐውዜን ድብደባና በዚያን ጊዜ ከነበረው የፊልም ቀረጻ ቴክኖሎጂ ተነስቶ ወያኔ ደርግ ድብደባ እንደሚያደርግ አስቀድሞ መረጃ ካልደረሰው በቀር እንደዚያ ተንፈላሶ ገፅ በገፅ (footage by footage ) ሊቀርፅ እንደማይችል፤ይልቁንም ሕዝቡን ከአካባቢው እንዲወጣ ማስታወቂያ ከማስነገር ፈንታ ገብረመድህን እንዳለው ሕዝቡን በማስፈጀት ኢሰብዓዊ በሆነ ፕሮፖጋንዳ መዋጮና ምልምል መሰብሰብ ዋነኛ ግቡ እንደነበር ሲረዳ ለሐውዜን እልቂት ዋነኛው ተጠያቂ ወያኔ መሆኑን ይገነዘባል።ይህም ብቻ አይደለም።ገብረመድህን ሌላም ጉድ ይነግረናል።ለወያኔ ፀረ ኢትዮጲያ አላማ ተባባሪ አልሆን ያሉ በትግራይ ሕዝብ ዘንድ ከበሬታ ያላቸውን ሰዎችም ከጉልበት በስተቀር ዘዴ ላልፈጠረበት ደርግ የወያኔ አባል እንደሆኑ አስመስሎ ማህተሙን አሳርፎና በረቀቀ መረጃ እንደተገኘ አድርጎ ባሰረገለት መሰረት ትላልቅ ሰዎች እንዲገደሉና በዚህም የትግራይ ሕዝብ ተበሳጭቶ የወያኔ ተባባሪ እንዲሆን አድርጓል።ቀይ ሽብርን በመፍራትወደወያኔ የተቀላቀሉ የአስራ ሁለት የአስራ ሶስት አመት ሕጻናትንም በኋላ ላይ የበረሃ ሕይወትን መቋቋም ሲያቅታቸውና ወላጆቻቸውን ናፍቀው ፈቃድ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ፈቃዱን የሚሰጥ መስሎ “ወደትውልድ ቀዬያችሁ መሄድ የምትፈልጉ እጃችሁን አውጡ ብሎ አመራሩ ካታለላቸው” በኋላ እንሄዳለን ብለው ራሳቸውን ያጋለጡ ልጅ እግር ታጋዮች እየተለቀሙ ተረሽነዋል።ገብረመድህን “አረመኔው ወያኔ”እነዚህን በጥይት ደብድቦ የገደላቸውን ሕጻናት “ናብ እነይ”(ወደ እናቴ) በሚል ቅጽል ስም እየጠራ እንደሚያላግጥባቸውም ይናገራል።እጅ በሰጡና በተማረኩ የኢትዮጲያ ወታደሮች ላይም ወያኔ የፈጸመውንም ፍጅት በስፋት ገብረመድህን አውስቷል።ዝርዝሩን ከአንጀቱ ለሚፈልግ ብዙ ሳይደክም ያገኘዋል።አሁንወደሐውዜን ፍጅት እና ወታደር ከአለቃው የሚሰጠውን ትዕዛዝ ያላንዳች ጥያቄ መፈጸም ስላለበት ጉዳይ እንመለስ።

አላግባብ የተከሰሱና የተፈረደባቸው ኢትዮጲውያን ፓይለቶች ብቻ ስለመሆናቸው

ባንድ አጋጣሚ የተዋወኩት የቀድሞ የባህር ሃይል መኮንን የነበረና ወያኔ ሲገባ እንደማንኛውም የኢትዮጲያ የጦር ሃይል ባልደረባ ተይዞ ወያኔ “ተሐድሶ”በሚለው እስር የተንገላታ እንዳጫወተኝ ወያኔ ጦሩን በወያኔያዊ መሰሪነቱ እየከፋፈለና እርስ በርሱ እንዲወነጃጀልና እንዲሁም ለአገሩ በመዋጋቱ ወንጀል እንደሰራ ሊያሳምነው ሲሞክር አንዳንድ ቆራጦች “አዎ ወንጀል ሰርተናል!ወንጀላችን መሸነፋችን ነው!ለናንተም መሳሪያችንን አውርደን እጅ መስጠታችን ነው!ብለው ከመሸም በኋላም ቢሆን እንደተጋፈጡት አጫውቶኛል።እውነት ነው።ያ ሁኔታ በወቅቱ ብዙ ያላጤንኩትን ያንድ ባላገር አነጋገርንም አስታውሶኛል።”የወታደር ቁምነገረኛ ባመቱ ድሃ ነው።”ብሄራዊ እርቅ፤ኢትዮጲያዊነት ወዘተ ለማይገባው ወያኔና ሻዕቢያ ጦሩ መሳሪያውን አውርዶ እጁን ሰጠ፤በዚህም መታሰር፣ መጋዝ ብቻ ሳይሆን በጦር ሜዳ ውሎ ወያኔንና ሻዕቢያን ለረጅም ጊዜ እንዳላርበደበደ ከኢትዮጲያ ባህልና ልማድ ውጪ በበቀል ውርደትን እንዲሸከም ተደረገ። ሲመሩት የነበረው ጦር በከሃዲ የእረኛ ጦር እንዳይሆን ሆኖ መዘረሩ ያበሳጫቸው በወታደራዊ ብቃታቸውና አመራራቸው የሚታወቁት ሜጄር ጄኔራል ግዛው በላይነህ ከጡረታቸው ላይ ሆነው “ጦሩ መባረር ሲያንሰው ነው”ብለው በቁጭት ለጦቢያ መፅሄት ጻፉ።በዚያ ፅሁፋቸውም አቻቻው ጄኔራል ነጋ ተገኝ ተቃውመዋቸው ምልልስ እንዳደረጉ አስታውሳለሁ።ሁለቱም ትክክል የሆኑበትን ነጥብ በወቅቱ አንስተዋል።እዚህ ለማሳየት የተፈለገው በርስ በርሱ ጦርነት ለደረሰው እልቂት ሐውዜንንም ጨምሮ ተጠያቂዎቹ የሻዕቢያ፣የወያኔና የደርግ ከፍተኛ አመራር ናቸው።

ባጭሩ ለማስቀመጥ እስካሁን ባለኝ መረጃ በጦር ወንጀለኝነት ተከሶ የተፈረደበት የተዋጊ አውሮፕላን ወይም የአየር ሃይል ፓይለት ሄርማን ጎሪንግ የተባለ የናዚ ጊዜ የአየር ሃይል አዛዥ ነው።እሱም የተከሰሰውና የተፈረደበት በጦርነቱ ጊዜ ይመራው ለነበረው የጀርመን አየር ሃይል በሰጠው ትዕዛዝ ሳይሆን ይበልጡን በናዚ አባልነቱ ባሳየው የይሁዲዎች ፍጅት ነው።ከዚህ ውጭ በቅርቡ አንድ የአርጀንቲና የቀድሞ የባህር ሃይል ፓይለት (ከመርከብ የሚነሱ ወታደራዊ አውሮፕላኖችን የሚያበር) አርጀንቲና በአምባገነን ወታደራዊ አገዛዝ በነበረች ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙ ሲቪል ተቃዋሚዎችን በባህር ሃይሉ ከሚገኝ መደብ እያወጡ አይናቸውን እየሸፈኑ በአውሮፕላን ከጫኑ በኋላ ከሰማይወደባህር እየወረወሩ በመግደል የብዙ ጊዜ የበረራ ድርጊት ላይ ተሳትፏል ተብሎ አገር ቀይሮ ይሰራበት ከነበረው የሆላንድ አየር መንገድ ድርጅት ተይዞ ለፍርድ መቅረቡን አስታውሳለሁ።በተቀር ከሽምቅ ውጊያወደለየለት የፊት ለፊት ጦርነት በተለወጠ ትዕይንት ውስጥ የቅርብ አለቃውን ትዕዛዝ በተዋረድ አክብሮ የተዋጋንና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት የጦር ቀጠና ውስጥ የተሳተፈን እግረኛ ወታደር ሆነ የአየር ሃይል ፓይለት በጦር ወንጀለኝነት ከሶ የሚያንገላታ በቀለኛና አላጋጭ የቧልት ፍ/ቤት በወያኔ ቁጥጥር ስር ካለችው ኢትዮጲያ በስተቀር የትም የለም።ኢትዮጲያን በመዝረፍ ረገድ ስግግብነታቸው ወያኔንና ሻዕቢያን ባያጋጫቸው ኖሮ እንደግርማ ዋቅጅራ ባሉ ራሳቸውን የህግ ባለሙያ ብለው በሚጠሩ ቅጥረኞች አማካይነት ወያኔ ሊበቀል እስር ቤት አጉሯቸው የነበሩት የቀድሞ ቆፍጣና፣እውቅና በበረራ ሙያ የተካኑ የአየር ሃይል አብራሪዎች በሐውዜን ስም ለረጅም ጊዜ በእስር ላይ ቆይተው በቀል የተፈፀመባቸው እነኮሎኔል ብርሃነመስቀል ሃይሌ፣ኮሎኔል ግርማ አስፋው፣ሌተና ኮሎኔል ሰለሞን ከበደና ሻምበል ክፍሌ ውቤ ብቻ አይሆኑም ነበር።ሌላው ቀርቶ ወያኔ በ1970ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ከአየር ሃይል ተሰናብተው በሲቪል ፓይለትነት ኢትዮጲያ አየርመንገድ አገልግለውወደጡረታ በመግባት ላይ የነበሩትን እነኮሎኔል ተካ መኮንንን፣ኮሎኔል ጥግነህ ሃብተጊዮርጊስን ጭምር ኤርትራን ደብድባችኋል ብሎ አስሯል። የ”ባድሜ ሉዓላዊነት” ፉክቻ አስፈታቸው።ከላይ እንደተመለከተው መንግስቱ ኃ/ማሪያም እስከዛሬ ድረስ ለጦሩ መሸነፍ የራሱን ደደብ የ”አብዮታዊ ጦር ጠቅላይ አዛዥነትና” ፈርጣጭነት እንደማይቀበል ሁሉ በመሰሪነት የሚያስከነዳው ሟቹ መለስ ዜናዊና በአምሳሉ የፈጠረው ወያኔም በሐውዜንና በመሳሰሉት ለደረሰው እልቂት የራሳቸውን ሃላፊነት ትተው ሌሎችን ይበቀላሉ።አጋጣሚ ሆኖ በሐውዜን ጉዳይ ለረጅም ጊዜ ተከሶ ለአገሩ እጅግ ከፍተኛ ዋጋ የከፈለው ኮሎኔል ብርሃነመስቀል ሃይሌ ከአባቴ ጋር አንድ ላይ ተፈሪ መኮንን የተማረ በፓይለት 11ኛ ኮርስም አንድ ቅጥር ከመሆናቸውም በላይ ከአየር ሃይል ተመርጠው ገና በመቋቋም ላይ የነበረውን የምድር ጦር አየር ክፍል (Army Aviation ) እንዲያደራጁ ተልከው ጎን ለጎን ለረጅም ጊዜ አብረው አገልግለዋል።አባቴ በሚያዝያ 1966 ዓ/ም አካባቢ የአገልግሎት ህይወትን ቶት በሲቪል ፓይለትነትወደአየርመንገድ ሲዛወር በእነብርሃነመስቀል ላይ ከደረስባቸው እንግልት ሊተርፍ ችሏል።ለነገሩ ኮሎኔል ብርሃነመስቀልም ደርግ ከመወድቁ አንድ ሁለት አመት በፊት ከአየር ሃይል ለቆ አየርመንገድ መጀመሪያ በበረራ አስተማሪነት በኋላም ዳሽ 5 ወይም ባፋሎ (Buffalo) በሚባል ካናዳ ሰራሽ አውሮፕላን ላይ ሲያገለግል ከነበረበት ነው ወያኔወደኋላ ሄዶ ያሰረውና የተበቀለው።በሐውዜንና በመሳሰሉት ለደረሰው ጭፍጨፋ እንዲሁም የራሱን ወንጀል ለመሸፈን ከቅርብ አለቃቸው የተሰጣቸውን ጥብቅ ትዕዛዝ መከተል የነበረባቸውን ኢትዮጲያውን መኮንኖች በግፍ ላንገላታበትና ላሰቃየበት እንዲሁም ለፈጸመው የአገር ክህደት አንድ ቀን ወያኔን ለመፋረድ መረጃዎቻችንን እያጠራቀምን እንገኛለን።እዚህ ላይ የጠቀስኳቸው የአየር ሃይል መኮንኖች ሁሉ ስማቸው ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በዚያም ሆነ በዚህ ከዚህ ቀደም በአደባባይ ስለተጠቀሰ መረጃው ሙሉ እንዲሆን ፎቶግራፍም ጭምር አያይዤያለሁ።በመጨረሻም ለወዳጄ ሰላማዊት ስዩም የዶ/ር ፈቃደን “ዲሞክራት ፓይለቶች” የሚለውን ግጥም አለመጋበዝ “ወዳጅነታችንን”የሚያሻክረው ስለመስለኝ እነሆ ጀባ ብዬለሁ።

ዲሞክራት ፓይለቶች

ሲበርሩ–ምንድን ይጭናሉ?

ሲተኩሱ–ምን ይተኩሳሉ?

ሲጥሉ–ምን ያፈነዳሉ?

ካናት በሚያፈሱት ካናት በሚረጩት፤

ከአጤውና ከደርግ በምን ይለያሉ?

በፊት “ለእናት ሀገር”፤

“ለድንበር ነፃነት”ከተመሠረቱት

በይሁዳ አንበሳ መፈክር ካደጉት

ኋላም በደርግ ዓለም “በልዩ ሁኔታ በአዲስ ወኔ መንፈስ

ዳግም ከታነፁት”

“በሶሺያሊስት ምግባር፤ለሰው ልጅ ደህንነት ከተኮተኮቱት”

“ለዓለም ወዛደሮች፤ለምድር ጎስቆሎች”

“ለኢትዮፕ ሰፊ ሕዝቦች፤ቤዛ እንዲሆኑት”

“በእውቅ ተመልመለው፤በእውቅ ከተገነቡት”

“ከማይደፈሩት–ከማይገሰሱት”

“በዓለም ተደንቀው ባለም ከሚፈሩት”

ከአጤውና ከደርግ፤

“ጀግና አየር ኃይሎች”

“ቀይ-ብስል ፓይለቶች”

በምን ይለያሉ “ዲሞክራት ፓይለቶች”?

ቅንጨና ፍርፍሩን

የዶሮ ፍትፍቱን

ብሩንዶ ስጋውን

ጥብስና ክትፎውን

ደሃ የሚመኘውን

በልሙ የሚቆርጠውን

በኮዳ ውሃውን–ጠላውን ማርጠጁን

በቅርጫት ዳቦውን-ሸሚዝ-ኮትሱሬውን

የብርቱካንና የፓፓያ መዓት

ሊረጩ ነው ጧትጧት?

ከመና ፋብሪካ ሰማያ ሰማያት?

ፅጌረዳ አበባ እርግብ ይረጫሉ?

“አንቺ ሆዬ”ን እና “ትዝታ”ያዜማሉ?

ሕዋውን በ”ባቲ”በፍቅር ይሞላሉ?

ከአጤውና ከደርግ የአየር ላይ ሀይሎች

በምን ይለያሉ “ዲሞክራት ፓይለቶች”?

ዶ/ር ፈቃደ አዘዘ ሚያዝያ 01/1988 2:59 ማታ ላይ እንደገጠመው።ማለፊያ ጥያቄ ነው ዶ/ር ፈቃደ ያቀረበው።የአጤውና የደርግ ፓይለቶች ከ”ዲሞክራት”ፓይለቶች የሚለዩት ቢያንስ መሃል ከተማ ላይ አውሮፕላን ማብረር ሲያቅታቸው ገበያ ላይ ለቀው በጃንጥላ ለማምለጥ “ድፍረት” አልነበራቸውም።ማብረር ሳይችሉ ቦምብ ጭነው ለመሄድም የሚያስችል “ዲሞክራሲም”በአጤውና በደርግ ጊዜ ለነበሩት ፓይለቶችም አልነበረም።ልዩነቱ እሱ ነው።

Email: kiflukam@yahoo.com

http://ecadforum.com/

posted by Tseday Getachew

ጆሮ ያለው ይሰማል! አይን ያለው ይመለከታል! ጆሮ ኖሮት የማይሰማ፣ ዓይን ኖሮት የማያደምጥስ? – ከድምፃችን ይሰማ

የኢቴቪ ከ‹‹ጥቂቶች›› ወደ ‹‹የተወሰኑ›› የቃል ሽግግር!

እያንዳንዷ ጁምአ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪክ የሚጻፍባት ገጽ ከሆነች ቆይታለች። ጁምአ የፍትሕ፣ የነጻነትና የህዝብ ድምጽ ቀን ናት ለእኛ። የዛሬዋ ጁምአ ደግሞ በበኩሏ ታሪካዊ ሆና ውላለች። እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በአለም አቀፍ ደረጃ አገሪቱ ውስጥ እየተፈጸመ ላለው የሃይማኖት ጭቆና ድምጹን አሰምቷል። ዛሬ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በተጠራው አለም አቀፍ ተቃውሞ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እለቱን ስለ ፍትህ በመጣራት ሲያሳልፉት ውለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለው የሃይማኖት ነጻነት እጦት፣ ተደጋጋሚ ፖለቲካዊ ክሶችና እስሮች፣ ሙስሊሞች ላይ እየተፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት ረገጣ፣ የህገ መንግስት ጥሰት፣ የመስጊድ ቅሚያ እና መታሸግ፣ በመንግስት ሚዲያዎች ሙስሊሞች ላይ የሚሰነዘረው የፕሮፖጋንዳ ጦርነት፣ የመሪዎቻችን እስርና ወዘተ የመብት ጥሰቶችን በአንድ አንደበት ግን በተለያዩ አሕጉራት ሆኖ ለመቃወም የተጠራው የዛሬው ተቃውሞ እጅግ ባማረና ባስደነቀ ትእይንቶች ታጅቦ ተካሄዷል፡፡ በዚህ ሪፖርታዣችን በአገር ውስጥ ብቻ የተካሄዱትን የተቃውሞ መርሐ ግብሮች አፈጻጸም የምናስቃኛችሁ ሲሆን በነገው ሪፖርታዣችን ከአገር ውጪ የተካሄዱትንና ዛሬ ምሽት እንዲሁም ነገ ቀጥለው የሚካሄዱትን የቤት ውስጥና ከቤት ውጪ ተቃውሞዎች ሙሉ ዘገባ እናቀርባለን፡፡

አዲስ አበባ ገና ከማለዳው ነበር የተለመደ መንገዳቸውን ትተው ወደ ፒያሳው ኑር መስጂድ በሚፈሱ ሙስሊሞች መሞላት የጀመረው፡፡ ለወትሮው በአንዋር መስጂድ ጁምአን ለመፈጸም የሚሄደው ሙስሊም ህብረተሰብ በሚሊዮን ሆኖ የተቃጠረበትን ኑር መስጂድን በማሰብ ነበር ወደ ኑር መስጂድ የነጎደው፡፡ ኑር መስጂድ ከመርካቶ፣ ቦሌ፣ ልደታ ካዛንቺስ እና ፒያሳ አቅጣጫ የሚመጡ ሙስሊሞች ለመሞላት የጁምአ ሰላት መድረስ እንኳ አላስፈለገውም ነበር፡፡ ገና በጊዜ መስጂዱ ሞልቶ ጎዳና ላይ መፍሰስ የጀመረው ሙስሊም በፒያሳ፣ ተ/ሃይማኖት እና አንዋር መስጂድ አቅጣጫ መፍሰሱን ተያያዘው፡፡ ሕዝቡ እንደጉድ ይመጣል፤ ጎዳናውም መሙላቱን ቀጥላል፡፡ ከጁምአ ሁለተኛ አዛን በፊት ወደ ተ/ሃይማኖት የወረደው ሙስሊም በላይ ዋናውን ጎዳና ለመዳረስ ጥቂት ቀርቶት ነበር፡፡

የጁምአ ሰላት እንደተጠናቀቀም ሁሉም በየፊናው የያዘውን መፈክር ከፍ በማድረግ ‹‹አላሁ አክበር›› በማለትና አላህን በማተለቅ ተቃውሞውን አሀዱ አለ፡፡አንድ ሁለት እያሉ መፈክሮች ተከተሉ፡፡ የአካባቢው ድባብም ተቀየረ፡፡ መብቱ የተነካው ሙስሊም ‹‹ኢ-ፍትሃዊነትን የምሸከምበት ትከሻ የለኝም!›› በማለት እየተፈጸመበት ያለው በደል እንዲያከትም፣ የመንግስት ያልተገደበ ጣልቃ ገብነት እንዲያበቃ ደጋግሞ በመፈክሩ አስተጋባ፡፡ ደቂቃዎች እየነጎዱ፣ ጾመኛ የሆነው ሕዝብ ሀይልና ወኔ ግን እየጨመረ ነበር የሄደው – እስከ ተቃውሞው መጠናቀቂያ ወቅት ድረስ፡፡ ሙስሊሙ ተቃውሞውን አጠናቆም ዱአውን በማስከተል ወደየአካባቢው መመለስ ጀመረ፡፡ በአካባቢው የነበረው ሕዝብ ብዛት በታሪክ ያልታየና አካባቢውም ሆነ ኑር መስጂድ አስተናግዶት የማያውቅ እንደነበርም በብዙ የአይን እማኞች ምስክርነት ተሰጥቶታል፡፡ የአዲስ አበባውን የኑር መስጂድ ተቃውሞ ለታደመ መንግስት ባለበት ሃገር ዳግም ህዝባዊ ተቃውሞ መጥራት እንደማያስፈልግ ይረዳል። የህዝብ ሃላፊነት ድምፁን ማሰማቱ፣ የመንግስት ግዴታው ደግሞ የህዝቡን ድምፅ ማድመጡ ነውና። መቶ ሺዎች በአዲስ አበባ ብቻ ሲጠሩት ያልሰማ መንግስት የቱን ሃላፊነት በመወጣት ላይ ይሆን? ህዝብስ መብቱን እንዴት እንዲጠይቀው እየገፋፋ ይሆን?

በህብረተሰብ ስብጥር እና በማህበረ ፖለቲካው ረገድ ትልቅ ግምት የሚሰጣት ሻሸመኔ በልዩ ትኩረት የምትታይ ነች። በዚህች ከተማ የሚኖር መልካምም ሆነ መጥፎ ተሞክሮ እጅግ በርካታ በሆኑ የከተማና የገጠር ቀበሌዎች ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ አለው። እናም ሻሸመኔዎች ድምፃቸውን የወታደር ከበባ ጥሰው ሲያሰሙ የሃይል እርምጃ ፈፅሞ እንደማያዋጣ እና መዘዙም የከፋ መሆኑን በዙሪያቸው ባሉ ከተሞችና ቀበሌዎች ስም እያስደመጡ ነበር። በከተማዋ አል ሂከም መስጂድ ዛሬ የተደረገውን ተቃውሞ ተከትሎ ፌደራል ፖሊሶች መሰጂዱን ከበውት የቆዩ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ ያካሄደው ሰላማዊ ተቃውሞ ከተጠናቀቀ በኋላ መስጂዱን ለቆ ለመውጣት ሳይችል ቀርቷል፡፡ ወደ ቤቱ ለመመለስ የሚወጣውንም ሕዝብፖሊስ ሲያፍን የነበረ በመሆኑ ሙስሊሙ እስከ አስር ሰላት ድረስ በመስጂዱ ለመቆየት ተገዷል፡፡ ከአስር ሰላት መጠናቀቅ በኋላ ህዝበ ሙስሊሙ በጋራ በመሆን ከመስጂድ ቢወጣምፖሊስ ግለሰቦችን ነጥሎ ያስር እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡

በሂላል መስጂድ የተሰባሰቡ የአጋሮ ከተማ ሙስሊሞች አንደባለፈው ሳምንት ተቃውሞውን ለሴቶች ብቻ ከመተው ይልቅ በወንዶች በኩል የሳምንቱን በደል ለመካስ ሲሰባሰቡ ሴቶች ማንም ዝም ቢል ዝም ላይሉና ታሪክ ለመድገም ቃል ተግባብተዉ ነበር የመጡት፡፡ ዉጤቱ ወንዶች በደላቸዉን ሲክሱ ሴቶችም ወንዶችንአንድ እርምጃ በመቅደም በጀግንነት መዝገባቸዉ ላይ ስማቸዉን በደማቅ ቀለም ለሁለተኛ ግዜ አስመዝግበዋል፡፡ የመንግስት ኢማሞች ሕዝቡን ለማስፈራራት ቢሞክሩም ‹‹መብቴን ተነጥቄ ዝም አልልም›› ያለው የአጋሮ ሕዝብ ከሰላት መጠናቀቅ በኋላ በተክቢራ የጀመረውን ተቃውሞ በሌሎች መፈክሮች ታጅቦ በሰላም አጠናቆታል፡፡ የአጋሮ ድምፆች በመላው ሀገሪቱ የተሰሙ የመብት ጥያቄ ድምፆችን ተቀላቅለው ኢትዮጵያዊ ህብር ሰርተው ከተማው ደምቆ ውሏል።

በኦሮሚያዋ መቱ የነበረው የተቃውሞ ትእይንትም ልዩና የአገሬው ሕዝብ በሌሎች የአገሪቱ ክልሎች እንደሚገኙት ሙስሊሞች ፍትህ መነጠቁን የመሰከረበትና ለፍትህ እንደሚሟገት ያሳየበት ነበር፡፡ በከተማዋ ዋና መስጂድ ነጃሺ የተገኘው በርካታ ሕዝብ በእልህና በንዴት በተናጠ ገጽታ መሪዎቻችን እንዲፈቱ፣ መንግስት ሕገ መንግስቱን እንዲያከብር፣ ሙስሊሞችን መጨቆን እንዲያቆም ጠይቋል፡፡ በመቱ የነበረው ተቃውሞም የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድምፅ ሃገራዊ ጥሪ መሆኑን ለሚያስተባብሉ ሁሉ ተግባራዊ ምላሽ የሰጠ ደማቅ ተቃውሞ ነበር።

በደሌም ታላቅ ተቃውሞ አስተናግዳ ነበር፡፡ የኢሊባቡር ዞኗ በደሌ በረህማ መስጂድ ሲሆን በበደሌ ከተማ እስከዛሬ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እጅግ በጣም ብዛት ያላቸው በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ሰላማዊ ተቃውሞ አከናውነዋል፡፡ የዛሬው የበደሌ ተቃውሞ የተለያዩ መፈክሮች የተስተጋቡበት ሲሆን፤ ከግማሽ ሰዓታት በላይም ቆይቷል – እንደ ዘገባዎች፡፡ በኢሊባቡር ዞን በምትገኘውና ከበደሌ ከተማ 36 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ጮራ ከተማ ከረጅም ጊዜ ዝምታ በኋላ ተቃውሞ ተካሂዶባታል፡፡ የድምጽ ተቃውሞ በተካሄደባት በጮራ ከተማ ትዕይንቱ በሁለት ቀበሌዎች በሚገኙ በፈትህ እና በኑር መስጂዶች መካሄዱን ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

በኢሊባቦር ዞን በገቺ ከተማም እንዲሁ ከጁምአ ሰላት በኋላ ከባድ ተቃውሞ ተደርጓል:: የገቺ ከተማ ህዝበ ሙስሊም ተቃውሞውን እንዲያቆም የከተማው የፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎች የከተማውን ሽማግሌዎች እና የከተማዋን ህዝብ ለያይተው ስብሰባ በመጥራት ማስፈራራታቸው የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ጁምአ ግን ማስፈራሪያው ቦታ እንደሌለው በተግባር አሳይተዋል፡፡ በከተማዋ የፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎች የተደረገው ማስፈራራት ሳይበግረው የገቺ ከተማ ህዝበ ሙስሊም እልህ እና ወኔ በተሞላበት ሁኔታ ከበፊቱ ይበልጥ በነቂስ በመውጣት ድምፁን ሲያሰማ መዋሉን ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡ የጁምአ ሰላት ከመሰገዱ በፊትም ለኮሚቴዎቻችን ዱአ የተደረገ ሲሆን በመስጂዱ የተገኘው ህዝበ ሙስሊምም በለቅሶ እና በእምባ ‹‹አሚን›› ሲል እንደነበር ተሰምቷል፡፡ በተካሄደው ተቃውሞ የሴቶች ተሳትፎ ከፍተኛ የነበረ ሲሆን የተለያዩ መፈክሮችም ተብለዋል፡፡

ጅማዎች በፖሊስ ተከበው በዋሉበት በዛሬው ጁምአ የፈጸሙት ጀግንነት በቃላት ብቻ የሚገለጽ አይደለም፡፡ በከተማዋ ፈትህ መስጂድ ከረፋዱ ጀምሮ ከቧቸው የነበረውን ታጣቂ ሀይል ሳይሰጉ ወደ መስጂድ አል ፈትህ ያመሩት ጅማዎች የሰላት መጠናቀቅን ተከትሎ በነፍስ ወከፍ ያዘጋጁትን መፈክር ከፍ አድርገው የድምጽ ተቃውሞአቸውን ጀመሩ፡፡ ‹‹ድምጻችን ይሰማ!›› ከሚለው መፈክር ተነስተው ‹‹አሻእቡ ዩሪድ ኢስቃጠል መጅሊስ›› የሚለውን መፈክር አቋርጠው ለታሳሪ ኮሚቴዎቻችን ጥብቅና እንደሚቆሙ ከፍ ባለ ድምጽ መስክረዋል፡፡ ‹‹መብትን በማሰር መንጠቅ አይቻልም!›› እያሉም ለመንግስት ግልጽ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የጅማ የመብት ታጋዮች የእነሱን፣ በዙሪያቸው ያሉ ከተማ እና ገጠር ቀበሌዎችን ድምፅ ይዘው ሲወጡ ድምፃቸው ሃገራዊውን ተቃውሞ በሚደንቅ ውበት ተቀላቅሎ ውሏል።

ብዙዎች ‹‹ያልተጠበቀ ጀግንነት ነው›› ያሉት የወልቂጤው አስደማሚ ተቃውሞ ደግሞ እጅግ ውጥረት በሞላበትና የጦር ቀጠና በመሰለ ከባቢ ውስጥ በድምቀት ተካሂዷል። ወልቂጤዎች በዲናቸው የማይደራደሩ መሆናቸውን ለሚያውቅ ግን ‹‹ታሪክ ራሱን ደገመ›› እንጂ ሌላ አይልም፡፡ ውጥረት ነግሶበት የተከናወነው የወልቂጤው ተቃውሞ ባልተጠበቀው የህዝብ ማዕበል የበድረዲን መስጂድ ሜዳ በከተማው ሙስሊም ተጨናንቆ የጁመዓን አለም አቀፍ ተቃውሞ በከፍተኛ ድምቀት አከናውኗል፡፡ የጁመዓ ሰላት እንደተጠናቀቀ በተክቢራ የደመቀው በድረዲን መስጂድ ወዲያው ነበር ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ልዩ ሀይሎችና ፖሊሶች የተከበበው፡፡ ከበባውን ተከትሎ የተቃውሞው ድምፅ ከመቼው ጊዜ በበለጠ ከፍ ብሎ መሰማት ቀጠለ፡፡ ‹‹ጥያቄው ይመለስ!››፣ ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!››፣ ‹‹ድምጻችን ይሰማ!››፣ ‹‹በአቋማችን እንፀናለን!›› እና ሌሎች መፈክሮች ተስተጋቡ፡፡ በስተመጨረሻ ህዝቡ ተቃውሞውን አጠናቆ አካባቢውን ከበውት የነበሩትን ልዩ ሀይሎችና ፖሊሶችን በመሀል ሰንጥቆ በማለፍ ከመስጂዱ ወጥቷል፡፡ ሆኖም ወደ 10 የሚጠጉ ሙስሊሞች መታሰራቸው የተሰማ ሲሆን ከፊሎቹም ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ተዘግቧል፡፡

ምእራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ በዶዶላ ወረዳ ስር በሚገኘው ሄረሮ ከተማ በሦስት መስጂዶች ዛሬ ከጁምዓ ሰላት በኋላ ከፍተኛ የሆነ የድምፅ ተቃውሞ መደረጉና በሰላም መጠናቀቁም ተነግሯል፡፡ ተቃውሞው የተደረገው በኡሙ ቱርኪ ትልቁ መስጊድ፣ በቢላል መስጊድና በሳፊ መስጊድ ሲሆን በተቃውሞው ላይ ጎልተው ከተሰሙት መፈክሮች መካከል ‹‹አላሁ አክበር!››፣ ‹‹ድምፃችን ይሰማ!››፣ ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!››፣ ‹‹መጅሊስ አይወክለንም!››፣ ‹‹ድራማው ይብቃ!››፣ ‹‹ህገ-መንግስቱ ይከበር!›› እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ ሕዝቡ በተያዘው መርሀ ግብር መሰረት ተቃውሞውን አሰምቶም በሰላም ወደ መጣበት ተመልሷል፡፡

የሰሞኑ የፓሊስ እስር፣ ፍተሻ፣ ማስፈራራት፣ ዘመቻ እና የመንግስታዊው እስልምና ተከታታይ ፕሮፓጋንዳ ያልገደበው የወራቤ ሙስሊም የተቃውሞ መርሃ ግብሩን በብቃት አሳክቶ በድል ወደቤቱ ተመልሷል፡፡ በወራቤው ተቃውሞ ህጻን፣ አዋቂ፣ ሴት፣ ወንድ ሳይለይ በጋራ ‹‹ፍትህ ይከበር!›› ድምጹን ያስተጋባ ሲሆን የአካባቢው አስተዳደሮችም ሁከት በመፍጠር የተወሰኑ ሙስሊሞችን ለመያዝ ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡ ነቀምቴዎችም በአለም አቀፉ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ እለት ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ጋር በዱዓ ተቃውሞ ተቀላቅለዋል። ከእነዚህ ከተጠቀሱት ከተሞች በተጨማሪ በሌሎች በርካታ ከተሞች ከበር መልስ የዱአ እና የመሰባሰብ ተቃውሞዎች ተደርገዋል፡፡

ይህ ህዝብ ድምጹን እንክን የለሽ በሆነና በሰለጠነ ሰላማዊ መንገድ እያሰማ ቢሆንም እስካሁንም ግን በመንግስት ባለስልጣናት ‹‹ጥቂት›› እየተባለ ከመሸርደድ፣ ‹‹አክራሪ›› እየተባለ ከመሸንቆጥ አለማለፉ ለብዙዎች የሚያሳዝናቸው እውነታ ሆኗል። ‹‹ጥቂት›› የሚለው ቃል ሌላ አዲስ ትርጉም የተበጀለት ይመስላል። በቀበሌ ካድሬዎች ማስፈራሪያ ተገደው ለሰልፍ የሚወጡአንድ እፍኝ የማይሞሉ ሰዎችን ‹‹የእገሌ ከተማ ሙስሊም ህዝብ›› እያለ የሚያጭበረብረው ኢቲቪ የአዲስ አበባንና የሌሎች ከተሞችን ጎዳናዎች ሞልተው የፈሰሱና በየሳምንቱ ድምጻቸውን የሚያሰሙ ሚሊዮኖችን ግን ‹‹ጥቂት አክራሪዎች›› ለማለት አያመነታም። ዛሬ ደግሞ ይሄ ቃል ‹‹የተወሰኑ›› ወደሚል ቃል ተለውጦ አይተነዋል፡፡

መንግስት ሁለት አመት ሙሉ የሄደበትን የሀሰት አዘጋገብ በመከተል ሕዝቡን የተወሰነ ከማለቱ በተጨማሪ ሕዝበ ሙስሊሙን በጸረ ሰላምነትና ኢትዮጵያዊነት የማይሰማቸው ዜጎች አድርጎ ለማቅረብ ጥረት አድርጓል፡፡ ዛሬ በአንዋር መስጂድ የተቃውሞ ፕሮግራም ያልነበረ ቢሆንም የተቃውሞ ፕሮግራም እንደነበርና ሰላማዊው ህዝብ የመንግስትን ንብረት አወደመ ብሎ እጅግ አሳፋሪ ዜና ለሕዝቡ አቅርቧል፡፡ ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ መሰሉ የሀሰት ዜና የማይደለል ቢሆንም መንግስት እውነታውን ከማውራት ይልቅ በዚህ አይነቱ ‹‹አልሰማም አላይም›› ሁኔታ መቀጠሉ እንደ አገሪቱ ዜግነታችን በጣም ያሳስበናል፡፡አንድ መንግስት የህዝቡን ልብ ትርታ በትክክል ለማዳመጥ ከዚህ የተሻለ ምን እድል ሊያገኝ ይችላል? የህዝበ ሙስሊሙን ፍላጎት በትክክል ለማወቅስ ከዚህ የተሻለ አጋጣሚ ይኖር ይሆን?

አዎን! የዛሬዋም ጁምአ ‹‹ህዝብን ማሸነፍ አይቻልም!›› የሚል መልእክቷን ነው ያስተላለፈችው! እናም ህዝብን ማሸነፍ አይቻልምና በከንቱ አትድከሙ። የሃይል እርምጃም ሆነ የግዳጅ ጠመቃ እንዳላዋጡ ለማየት የዛሬውን ተቃውሞ ብቻ ማየት ይበቃል። አዎን! እኛ ለምትወስዱብን የሃይል እርምጃ ምንዳችንን አናጣውም… ትግላችን ለፍትህና ለነጻነት እሴቶች ነውና! እናንተ ሰላማውያንን በመደብደብና በመግደል እያጣችሁት ያለው ተቀባይነትና እያተረፋችሁት ያለውን የህዝብ ቁጣ ግን በምን ታካክሱት ይሆን!?

አላሁ አክበር!

ታሪኩ ተፅፏል!
ጁምአ ሐምሌ 19/2005

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=5675

posted by Tseday Getachew

በአርሲ አንድ አድማ በታኝ ፖሊስ አዛዥ በጩቤ ተወግቶ ተገደለ

 ESAT
 

 

ሐምሌ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሻለቃ ማእረግ ያለው ፖሊስ አዛዥ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቹ ላይ በጩቤ ተወግቶ መገደሉን የደረሰን ዜና ያመለክታል። ግድያውን ተከትሎ ፖሊስ በትናንትናው እለት እና ዛሬ ከፍተኛ ፍተሻ ሲያካሂድ ውሎአል።

የገዳዮቹ ማንነት እስካሁን አልታወቀም። በዛሬው እለት በሻሸመኔ ከወትሮው በተለየ ቁጥር በየቦታው ፍተሻ ሲያኪዱ የታዩት የፌደራል ፖሊሶች፣ ምናልባትም ግድያውን ከሙስሊሞች ጥያቄ ጋር ሊያያይዙት እንደሚችሉ ፍንጮች መታየት መጀመራቸውን ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖች ለኢሳት  ገልጸዋል።

ከ 27 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ይጠይቃል የተባለ የቴሌኮሙኒኬሽን ማስፋፊያ ሥራ ለቻይና ኩባንያ ተሰጠ።

ሐምሌ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከስልክ ኔትወርክ ጥራት ጋር በተያያዘ በየጊዜው የሚነሳውን ቅሬታ ይፈታል የተባለ እና 1ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከ 27 ቢሊዮን ብር በላይ  ወጪ የጠየቀ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራ ”ሁዋዌ”ለተሰኘው  የቻይና ኩባንያ ትናንት ተሰጠ።

የፕሮጀክቱን ውል ስምምነት ትናንት ማምሻውን ኢትዮ ቴሌኮም  እና የቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ ጋር ተፈራርመዋል።

ፊርማውን የኢትዮ ቴሌኮም ተቀዳሚ ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም አድማሴ ፤ በሁዋዌ በኩል ደግሞ የኩባንያው ስራ አስፈፃሚ ሚስተር ጆኒዱኦን ያስቀመጡ ሲሆን ፥ በአጠቃላይ የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ላይም ከሁዋዌ በተጨማሪ የዜድ ቲ ኢ የቴሌኮም ኩባንያም የቴሌን ደህንነት በማስጠበቅ በኩል ተሳታፊ ይሆናል ተብሏል።

የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ  በዋናነት ለጥራት ትኩረት በመስጠቱ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ሲጠናቀቅ አሁን የሚስተዋለውን የኔት ወርክ ጥራት ችግር ይፈታል ተብሎ ተስፋ እንደተጣለበትም   ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል  ተናግረዋል።

የሁዋዌ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ጆንዱንግ በበኩላቸው ፥ ፕሮጀክቱን በፍጥነት በማጠናቀቅ የተሻለ የቴሌኮም አገልግሎት በቅርቡ ለማሰረከብ ቃል ገብተዋል።

ይሁንና የቻይናው ህዋዌ ኩባንያ ይህን ያህል ትልቅ ፕሮጀክት-ከ ኢትዮ ቴሌኮም የተረከበው በግልጽ ጨረታ ይሁን አለያም እንደተለመደው እንዲሁ ተሰጥቶት፤አቶ ደብረጽዮን ያሉት ነገር የለም።

ቻይና ለ ኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ያለው ብድር እየሰጠች ያለች አገር ነች።

ሁዋዌ የተባለው የቻይና ኩባንያ የአሜሪካን መንግስት ይሰልላል በሚል ክስ ቀርቦበት እንደነበር ይታወቃል። ኩባንያው ለኢትዮጵያ መንግስት የስለላ ሶፍትዌሮችን ሊሰጥ መስማማቱን በቅርቡ መዘገባችን ይታወሳል።

 
 

ፒያሳ የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን የተቃውሞ ድምጾች አስተናግዳ ዋለች

ሐምሌ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፒያሳ ከሚገኘው ኑር መስጊድ አንስቶ ዙሪያውን ባሉ መንገዶች ላይ ቆሞ የረመዳንን ጁመዓ ስግደት ሲሰግድ  የዋለው ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ ፣ ከአንድ አመት በላይ ሲያሰማው ነበረውን ድምጻችን ይሰማ የሚለውን ተቃውሞ በከፍተኛ ድምጽ በማሰማት የፒያሳን አየር ተቆጣጥሮት ውሎአል።

ድምጻችን ይሰማ፣ የተነጠቅነውን መስጂዶቻችን ለህዝቡ ይመለሱ፣ የተባረሩ ኢማሞች ይመለሱ፣ አሸባሪ አይደለንም፣ ኢማሞቻችን ይፈቱ፣ ጥያቄው ይመለስ፣ ህገ መንግስቱ ይከበር፣ መጅሊሱ አይወክለንም የሚሉትና ሌሎችም ጥያቄዎች ቀርበዋል።

የዛሬው ተቃውሞ ከአንዋር መስጊድ መውጣቱ ብቻ ሳይሆን በተቃውሞው ላይ የታየው የህዝብ ብዛትና የተሰማው ድምጽ ህዝብን ትኩረት ስቦአል።

ተቃውሞው ከአዲስ አበባ ውጭ በተለይም በሻሻመኔ የፌደራል ፖሊሶች  በብዛት በተገኙበት ሁኔታ ተካሂዷል።

መንግስት የሙስሊሙን  ጥያቄ የጥቂቶች ጥያቄ ነው ቢልም በተለያዩ አካባቢዎች በገሀድ የሚታየው እውነታ ይህን የሚያረጋግጥ አልሆነም።

የኢትዮጵያ መንግስት ሙስሊሙ ለሚያቀርበው ጥያቄ እስካሁን ድረስ ተገቢውን መልስ አልሰጠም።

በስፔን የደረሰውን አሰቃቂ የባቡር አደጋ ተከትሎ የባቡሩ ሾፌር በቁጥጥር ስር መዋሉን ቢቢሲ ዘገበ።

ሐምሌ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአገሪቱ ሰሜናዊ ምዕራብ ከተማ በሆነችው በሳንቲያጎ ደ-ኮምፖስቴላ  ረቡዕ እለት በደረሰው የባቡር አደጋ 78 ሰዎች ሲሞቱ 130 ሰዎች ተጎድተዋል።

ከ130ዎቹ ቁስለኞች መካከል 35 ቀላል እርዳታ ተደርጎላቸው ከሆስፒታል የወጡ ሲሆን ከበድ ያለ ጉዳት የደረሰባቸው 95 ሰዎች በሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ ይገኛሉ።

የባቡሩን ሾፌር ለአደጋው ተጠያቂ ያደረገው የስፔን ፖሊስ ፤አደጋው በሚደርስበት ጊዜ ባቡሩ ከተፈቀደው ፍጥነት ከእጥፍ በላይ እየከነፈ እንደነበር ጠቁሟል።

የመቁሰል አደጋ የደረሰበትና ላደጋው ተጠያቂ የሆነው ሾፌር በአሁኑ ጊዜ በ አጃቢዎች እየተጠበቀ ህክምናውን እየተከታተለ ነው።

ከተጎዱት መካከል 32ቱ ክፉኛ መቁሰላቸውን ያመለከተው ቢቢሲ፤ ከነዚህም ውስጥ ከተለያዩ የ ዓለማችን ክፍሎች የመጡ ዜጎችና ህፃናት ጭምር እንደሚገኙበት ዘግቧል።

አደጋውን ተከትሎ በስፔን መጪዎቹ ሦስት ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ጊዜ እንዲሆኑ ታውጇል።

በግብጽ የፕሬዚዳንት ሙርሲ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች የተቃውሞ እና የድጋፍ ሰልፎችን አደረጉ

ሐምሌ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲ ደጋፊዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት ፕሬዚዳንቱ ወደ ስልጣን እንዲመለሱ ሲጠይቁ ፣ የእርሳቸው ተቃዋሚዎች ደግሞ ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ላወረደው የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለመስጠት በታህሪር አደባባይ ተገኝተዋል።

ለፕሬዚዳንቱ ከስልጣን መወገድ ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱት ጄኔራል አብደል ፋታህ ኤል ሲሲ ሰሞኑን ህዝቡ ለወሰዱት እርምጃ ድጋፋቸውን እንዲሰጣቸው ተማጽነው ነበር።

በሌላ በኩል ደግሞ ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲ ከፍልስጤሙ ተዋጊ ድርጅት ሀማስ ጋር በመተባበር በግብጽ እስር ቤቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም አሲረው ነበር የሚል ክስ እንደሚቀርብባቸው ታውቋል።

አንዳንድ ተቺዎች ግን ክሱ ፕሬዚዳንቱ እንዲፈቱ ከተለያዩ ወገኖች ለሚሰነዘረው ተቃውሞ ሰበብ ነው በማለት አስተያየት ይሰጣሉ።

ግብጽ በፖለቲካው ምክንያት መከፋፈሉዋን ተከትሎ የእርስ በርስ ግጭት ሊፈጠር ይችላል የሚለው ስጋት እያየለ መጥቷል።

ESAT

posted by Tseday Getachew

ኢትዮጵያዊ-እስራኤላዊው ፈላሻ ጠበቃውንና የጠበቃውን ሴት ልጅ ገደለ

 

 

ማከሰኞ ጠዋት በፍች ጉዳይ ምክንያት በጠበቃው ክርክር የልረካው ኢትዮጵያዊ -እስራኤላዊ ጠበቃውንና የጠበቃውን ሴት ልጅ ገደለ፡፡
እስራኤላዊው የፖሊስ ቃል አቀባይ እንደተናገረው ተጠርጣሪው በአካባቢው በሚገኝ ህንፃ የጥበቃ ስራ ይሰራ እነደነበርና ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት አካባቢ ግድያውን እንደፈጸመ ተናግሯል፡፡
ጌታጎን ታደሰ የተባለው ኢትዮጵያዊ -እስራኤላዊ የጥበቃ ሰራተኛ በፍች ሂደት ውስጥ እንደነበርና ሟች ጠበቃን ቀጠሮ ይከራከር እንደነበር የፖሊች ዘገባ ያስረዳል፡፡ ሆኖም ግን በፍርድ ሂደቱ ያልረካ በመሆኑ ጠበቃው ጋር ሄዶ የከፈለውን ብር እንዲመልስለት ጠይቆት እንደነበርና ቀጥሎም በያዘው መሳሪያ ጠበቃውንና ሴት ልጁን ከቅርብ ርቀት ተኩሶ እንደገደላቸው ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያዊ -እስራኤላዊም ወንጀሉን እንደፈጸመ በፖሊስ እንደተያዘና እርስ በረሱ የተቃረነ ማስረጃ እንደሰጠ የተዘገበ ሲሆን በወንጀሉ ወቅት አእምሮው ነትክክል እንደማያስብ ተናግሯል፡፡
ኢትዮጵያዊ -እስራኤላዊው ምንም አይነት የአእምሮ ህመም እንደሌለበትና የጥበቃ ስራውን ሲጀምር የተሰጠውን የአእምር,ሮ ጤንነት ፈተና አልፎ መሳሪያ እንደተሰጠው ተጠቅሷል፡፡ ይህንን ተከትሎ ዳኛው ሮብለት የአእምሮ ህመም ምርመራ እንዲያደርግና ለስምንት ተጨማሪ ቀናት እንዲቆይ ትዛዝ ሰጥተዋል፡፡
የ49 ዓመቱ ጌታጎን ታደሰ የ4 ልጆች አባትና በ2004 ዓ. ም. ከኢትየጵያ ወደ እስራኤል የመጣ ፈላሻ እንደሆነ መረጃዎቹ የጠቁማሉ፡፡
ማከሰኞና ባለፈው ግንቦት ወር ላይ በተፈጸመው ክስተት ምክንያት የእስራኤል ቁጥጥር ቢሮ በመሳሪያ አያያዝ ላይ የተሻሻለ ህግ እንደሚያስፈልግ ረቡእ እለት አስታውቋል፡፡ የሟች ጠበቃና የሴት ልጁ የቀብር ስነ-ስርዓትም በተመሳሳይ ቀን ሮብለት ተፈጽሟል፡፡

http://sodere.com/

posted by Tseday Getachew

ሰለኮሎኔል ታደሰ ጥቂት ልበል፡

ከፍል2
ይታያል የሩቅሰው
ወደ እለቱ ተግባራዊ ቅኝቴ ለመግባት፡ ባለፈው ሳምንት በዚህ አርእዕስት የከተብሗትን፡ ጦማሪን ስደመድም፡ ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ፡ ወደአሜሪካን ባቀናበት ወቅት፡ በዚያው እንዲቀር ለቀረበለት ጥያቄ፡ የሰጠው መልስ፡ወያኔ ውሎ ካደረ ኢትዮጵያ የምትባል ሃአገር አትኖርም፡ እናም ቢሆን ከጥፋት አድናታለሁ፡ ካልሆነም ጥፋቷን ሳላይ ማንም ያጥፋኝ ማን ስከላከልላት እኔ ቀድሜያት፡ እጠፋለሁ፡ ሞት እንደሁ ፈራንም ደፈርን፡ የማይቀር የተፈጥሮ እዳችን ነው። የሚል እንደነበር በመጥቀስ ነበር፡፡ ወደዛሪው የምገባው ደግሞ የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ በመሞከር ነው።
2.1.የመሰወሩ ምክናያቶችስ ምንና እነማን ናቸው?
ነገሩ እንዲህ ነው፣በኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ፡ የሰከነና፡ በእውቀት ላይ የተመሰረተ አመራር፡ በእነ ቱሗት፣ በእነ ጁማ፣ በእነ ዮሴፍ፣ በእነተ ስፋዬ፡ ትጋትና የዓላማ ጽናት፡ ያልተለየው የሌት ከቀን እንቅስቃሴ፡ በክፍል አንድ ማብራሪያዬ፡ እንደጠቀስሁት፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፡ በአጭር ጊዜ ተጠናክሮ፡ ጥቃት መሰንዘር ከሚያስችለው ደረጃ ላይ እየደረሰ ሲመጣ፡ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ በርካታ፡ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን፡ እቦታው ድረስ በመሄድ ጎብኝተው፡ ትግሉን በማበረታታት ወደ እየመጡበት ሲመለሱ፡ ፕ/ር ሙሴ ተገኝ ግን፡ ጓዙን ጠቅልሎ አስመራ በመግባት፡ አይዟችሁ በማለት ፋንታ፡ ከተማ ቁጭ ብሎ፡ የግንባሩ መሪ ለመሆን ባለው ህልም፡ ይሁን በሌላ ልዩ ተልዕኮ፡ ባለየለት ምክናያት፡ በኤርትራ ባለስልጣናት ቢሮዎች እየዞረ፡ እነኮሎኔል ታደሰን፡ እነዚህን ደርጎች፡ እንዴት ታምኗቸውአላችሁ፡ በማለት ማጥላላትን ስራየ ብሎ ይይዛል፡ አመራሩ ግን፡ ከሗላው እየተለቀለቀበት ያለውን ጥላሽት፡ በማያውቅበት ሁኔታ ላይ ሆኖ፡ ብዙ ኩነቶችን ከዳሰሰና፡ ካጠና በሗላ የውጊያ እቅድ ሲነድፍ፡ አንድ መደምደሚያላይ ይደርሳል። እሱም የትግሉ መሰረት የጎረቤት ሀገር ሳይሆን ሃገር ቤት መሆን አለበት። የወደቀው ወድቆና ያለቀው አልቆ፡ ሀገራችን ላይ ነጻመሪት ሊኖረን ይገባል፡ የሚለው ተወስኖ ጠቅልሎ ለመግባት የ6ወር ጊዜ ገደብ ተቀምጦለት፡ ዝግጅት ይጀመራል፡ ጉዳዩም በሚስጥር እንዲያዝና ከስራ አመራሩ በቀር ለማንም እንዳይወራ፡ ተስማምተው በእየተመደቡበት የስራ ዘርፍ ደፋቀና በማለት ላይ እንዳሉ፡ ከ7ቱ አመራር አባለት መካከል አንዱና በገንዘብ ያዥነት፡ የተመደበው አበሩ አታላይ ማለት ዛሪ ስሙን ቀይሮ መስከረም ነኝ ያለውና፡ ጀርመን ሃገር የሚኖረው፡ ለህክምና ብሎ አስመራ በሄደበት ከፕ/ር ሙሴ ተገኝ ጋር ተገናኘቶ 2ቱ የተንኮል ሴራ ሽርበው፡ በጋራ ከአንድ የሻብያ ቱባ ባለስልጣን ቢሮ ቀጠሮ አስይዘው በመግባት፡ እነዚህ ደርጎች እነ ኮሎኔል ታደሰን ማለት ነው፡ ጓዛቸውን ጠቅልለው ሀገራቸው ሊገቡ ወስነው እየተዘጋጁ ነው ያሉት፡ እንዲያውም፡ በመጀሪያ፡ ወያኔን ቀጥለን ሻብያን፡ እንደመስሳለን፡ ሀገራችን ወደብ አልባ ሆና አትቀርም ነው የሚሉት፡ በማለትና ሌሎች ሻብያን ሊያበሳጭ ይችላል ያሉትን ውሽት በመደርደር፡ መረጃ ሰጥተውና ለቀጣይ መመሪያ ተቀብለው ይወጣሉ። ከዚያች እለት ጀምሮ እነ ኮሎኔል ታደሰ በሻብያ አይነ ቁራኛ መጠበቅ ይጀምራሉ፡፡ አበሩ አታላይም ወደግንባር ተመልሶ፡ የጎንደር አካባቢ ተወላጅ ሲያገኝ፡ ጎነደሬ፡ የትግራይ ካባቢ ተወላጅ ሲያገኝ፡ ትግሬ ነኝ በማለት፡አቅሙ በፈቀደ መጠን ሰራዊቱን፡ በመንደር መከፋፈሉን ያጧጡፋል።
ነገር ከስሩ ውሃ ከጥሩ እንዲሉ፡ ለአነባብያን፡ የበለጠ ግልጽ እንዲሆን፡ ትንሽ ወደሗላ ሄጄ፡ ሰለ አበሩ አታላይ፡ ማንነት በአጭሩ፡ አንድ ሁለት ልበል፡ ተጠቃሹ፡ ወልቃይት ውስጥ ነው ተወልዶ ያደገው፡ ትምህርት፣ የሚሉት ነገር ባህላዊዩም ሆነ ዘመናዊዩ አልነኩትም በፍጹም አይተዋወቁም፡ በማህበራዊ ኑሮውም በአካባቢው የተጠላ ነበር፡ ያነን ማንነቱን የፋቀልኝ መስሎት ሳይሆን አይቀርም ስሙን መቀየር ያስፈለገው። ይህ ግለሰብ የሚኖርባት መንደር የጎንደር ክፍለሀገር ክልል ሆና፡ የትግራይንና የኤርትራን ክፍላት ሀገራት በቅርብ እርቀት የምታዋስን በመሆኗ፡ በደርግ ዘመን፡ በሚፈጽማቸው አስነዋሪ ተግባራት፡ ምክናያት በፖሊስ፡ ጎንደር ሲፈለግ ትግራይ፣ ትግራይ ሲፈለግ ኤርትራ፡ እያለ በማስቸገር ሲኖር፡ በአንድ ወቅት ብልሁ የሀገሪ ሰው በዘዴ ለመገላገል፡ሲል ለአካባቢ ህዝባዊ ሰራዊትነት መልምሎ እንዲሰለጥን ይልከዋል፡ አበሩ ከተላከበት ጠፍቶ ወደመንደሩ ሲገሰግስ አዘዞ ላይ ተይዞ፡ በሀገር ክህዕደት ወንጀል ተፈርዶበት እስር ቤት ይገባል፡ ጨርሶ ሲወጣ፡ ወደመንደሩ ሄዶ የተለመደ ስራውን ሲያከናውን፡ ወያኔ ሀገሪቷን ይቆጣጠራል፡ ወያኔዎች እንደገቡ ሌባ ይገድሉ ስለነበር እንዳይገደል ፈርቶ፡ ወደሱዳን ይሸሻል፡ እዚያም ከፋኝን ተቀላቅሎ፡ እያለ የከፋኝ መስራችና ነባር አባላቱም ሆኑ መሪዎቹ በዩ.ኤ.ን. አማካኝነት፡ ወደተለያዩ ምእዕራባውያን ሀገራት ሲሄዱ፡ እሱ በመቀረቱ፡ በአቶ ዮሴፍ ያዘው የሚመራውን፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራሴያዊ ግንባርን፡ተቀላቅሎ ኤርትራ ይገባና፡ የትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪነቱን፡ እንደ ማንነት መገለጫ በማቅረብ፡ በድብቅ በአካባቢው፡ ላገኛቸው የኤርትራ ባለስልጣናት ኤርትራዊ እነቱን በመንገር፡ የሻብያ አባል ይሆንና፡ አብረውት የተሰደዱ ኢትዮጵያንን፡ እንዲሰልል ግዳጅ ተሰጥቶት እያለ ነው ተጨማሪ ሐይል ሙሴ ተገኝን ያገኘ።
ስለ መስከረም አታላይ፡ ከብዙው በጥቂቱ፡ ይህነን ያህል ካልሁ ወደ ኮሎኔል ታደሰ ልመለስ፡ እነኮሎኔል ታደሰ ባላወቁት ነገር በሻብያ ጥርስ ተነክሰው፡ የሚደነቀርባቸውን ሁሉ መሰናክል በትግስት እያለፉ፡ ስራቸውን በማፋጠን ላይ እንዳሉ፡ ከእለታት አንድ ቀን በሻብያ ሰራዊት ተከብበው፡ አመራሩ እንዲበተን ይደረጋል፡ ከዚህ በሗላ ኮሎኔል ታደሰ፡ ከአስመራ እንዳይወጣ ሲደረግ ቱሗት ፖልና ጁማ እሩፋኤል፡ ከኤርትራ እንዲወጡ፡ ዮሴፍ ያዘው ከተሰኔይ ከተማ እንዳይወጣ፡ ሲደረግ ተስፋዬ ጌታቸው፡ አዚያው ሃሪና በርሀውስጥ እንዲታሰር ተወሰነበት፡፡ይህ ከመከናወኑ ቀደም ብሎ ግን የግንባሩ አመራር ከነደፈው፡ መርሃግብር አንዱ የሆነውን አርበኛው፡ ከኤርትራ ነቅሎ ሲወጣ፡ መሰረቱን የሚጥልበትን ቦታ፡ አጥንቶ እንዲመለስ የተመደበውን ቃኝ ሃይል፡ በሃላፊነት መርቶ የሚሄድ አንድ ሰው ለመምረጥ፡ በተደረገ ውይይት ላይ፡ አበሩ ወይንም መስከረም አታላይ፡ በእራሱ ፈቃድ እኔ ልሂድ ስለአለ፡ በሃላፊነት መርቶ እንዲሄድ ይደረጋል፡ አበሩ ከፊሉን አስገድሎና ከፊሉን፡አስማርኮ፡ እሱ ብቻውን፡ ጥይት አይደለም እንቅፋት ሳይመታው፡ ከመመለሱም በላይ ኪሱ ውስጥ በርካታ ዶላር በመገኘቱ፡ ጉዳዩ አጠራጣሪ ሆኖ ስለተገኘ፡ እስኪጣራ አመራሩ አስሮት ከነበረበት፡ በሻብያ ትእዕዛዝ ተፈትቶ፡ አሁንም ያለምርጫ፡ በሻብያ ትእዛዝ የግንባሩ፡ አዛዥ እንዲሆን ሲመደብ፡ በአንድ በኩል የፕ/ር ሙሴ ተገኝ የመሪነት ህልምን ሲያከስም፡፡ በሌላበኩል ሰራዊቱን፡ አስቆጥቶ፡ ከመበታተን፡ ደረጃ አደረሰውና፡ የተበተነው የሰው ሐይል፡ ከፊሉ ሱዳን ሲገባ ከፊሉ ደግሞ ወደሀገሩ የተመለሰ ሲሆን፡ ሁለቱንም ማድረግ ያልቻለው፡ መሀይም አይመራንም፡ አበሩ አታላይ፡ ታደሰ ሙሉነህን ሊተካ አይችልም፡ በማለት፡ የደቡብ ህዝቦች፡ የሲዳማ ህዝቦች፣ የጋቤላ፣ የቤንሻንጉል ወ.ዘ.ተ. በሚል ተከፋፍሎ፡ እነሆ ዛሪ የምንሰማውን 8 የብሄረሰብና የቋንቋ ድርጅት አቋቁሞ፡ እዚያው ኤርትራ ውስጥ እየኖረ ይገኛል። አበሩ አታላይም፡ በጣም ጥቂትና በግንዛቤም ሆነ በአቅም የሚመሳሰሉተን፡ የመንደሩን ልጆች አሰባስቦ፡ የአርበኛ ግንባር የሚለውን ስም፡ እንደያዘ አዛዥ ነኝ በማለት፡ ተስፋዬ ጌታቸውን ጉድጓድ ውስጥ አስሮ እንደውሻ በዱላ ደብድቦ ገደለው። በዚያን ጊዜ በአበሩ አታላይ፡ የተጀመረው፡ ወያኔን የምንጠላበት፡ የመንደርተኝነት፡ አባዜ እረ ወያኔስ ቢያንስ ከፍ አድርጎ፡ በቋንቋ ነው የከፋፈለን፡ አበሩ ግን አውርዶ፡በቀበሌ ገነጣጥሎን፡ አርበኛ ግንባር ውስጥ አሁንም ድረስ ተጠናክሮ እየሰራ ሲሆን፡ አመራር አይደለም፡ የአርበኛ ግንባር ታማኝ አባል ለመሆን፡ ቢሆን ወልቃይት፣ ካልሆነም ጎንደር መወለድ የግድ ይላል፡፡ ባልተጻፈው በእነ መስከረም፣ ማእዛው መመሪያና ደንብ፡ መሰረት፡፡ ለዚህም ነው አረበኛ ግንባር በተለያየ ጊዜ ከገደላቸው፡ ሁሉ ምሁራን፡ መካከል ከካሳሁን ወንዴ በቀር ጎንደር ክፍለሀገር የተወለደ፡ ሌላ2ኛ ሰው የማይገኝበት።
ከእነ ታደሰ ሙሉነህ፡ በሗላ ያለው አርበኛ ግንባር፡ ተስፋዬ ጌታቸውን ብቻ አይደለም የገደለው ወደፊት ታሪክ የሚያወጣቸው፡ ለመታገል የገቡ በመቶወች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ምሁራንን፡ እንክት አድርጎ በልቷል፡ ለዚህ ድርጅት አመራር አካላት ፊደል የቆጠረ ሰው፡ ከወያኔ በላይ ያስፈራቸዋል፡፡
መስከረም አታላይ፡ እሱ በሻብያ እንደተሾመ ሁሉ ከ3 አመት ቆይታ በሗላ፡ ወደጀርመን ሲጓዝ በተራው ደገሞ፡ መጻፍና ማንበብ የማይችለውን፡ የታላቅ እሀቱን ልጅ፡ ማእዛው ጌቱን፡ ሾሞት ስለሄደ 9 አመት ሙሉ አርበኛ ግንባር፡ የሚመራው በእሱ ነው፡ ያሳያችሁ እንግዴህ በተራቀቀ ሳይንስና ቴክኖለጅ፡ የሚጠቀምን ጠላት ለማስወገድ እታገላለሁ የሚል ጦር አዛዡ፡ ይህ ሰው ነው፡ ታዲያ፡ ለምን አይዳከም? ለምንስ አይክሰም? በእውቀት የበሰሉ፣ በሙያው የተካኑ፣ ኢትዮጵያውያን ሲቀላቀሉት፡ ፈጥኖ
ይበላቸዋል፡ ለእነማዛው ስልጣን ስለሚያሰጉ። የኮሎኔል ታደሰ መሰወር መንስኤው ሌላ ምንም ሳይሆን ይኸው ነው፡ ለእነማእዛው ስልጣን እንዳያሰጋ ገለል ማለት አለበት። ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ፡ ከአስመራ እንዳይወጣ ተወስኖበት ሲኖር፡ ከዲያስፖራ አርበኛውን ለመጎብኘት የሚሄድ፡ ሁሉ ኢትዮጵያዊ የአመራሩን ደካማነት ሲያይ፡ በማዘንና ተስፋ በመቁረጥ፡ ምናለ ኮሎኔል ታደሰ አመራሩን እንዲረከባችሁ ብታደርጉ የሚል ከቅንነትና ከመቆርቆር የመነጨ፡ አስተያይት፡ ተደጋግሞ እየተሰነዘረ ስላስቸገራቸውና፡ኮሎኔል ታደሰ አመራሩን ተረክበ ማለት ደግሞ፡ በምርጫ የማይቀየረውና፡ በማእዛው፡ የሚመራው 7ቱ የስራአመራር፡ ኮሚቴ ከዲያስፖራ እየተዋጣ፡ የሚላክላቸውን ዶላር በማዘርዘር፡ ተሰነይና ጉልሽ ከተሞች ላስቀመጧቸው የኤርትራ ቆነጃጅት፡ አልባሳትና ከእግር ጥፍራቸው እስከ እራስ ጸጉራቸው፡ የሚንቀለቀሉበት ወርቅ፡ መግዛቱ የሚቆም ከመሆኑም በላይ፡ ያመራር ቦታው፡ ወልቃይት በመወለድ ሳይሆን፡ በብቃት በሹመት ሳይሆን በሰራዊቱ የተመረጡ ሰዎች የሚይዙት ስለሆነ፡ ከአዛዥነት ወደታዛዥነት ሊወርዱ ነው፡፡ ይህ እንዳይሆን ዘላቂ መፍትሄና፡ ስጋትን አስወጋጅ ነው ብለው ያሰቡት፡ ኮሎኔል ታደሰን፡ ወንጅሎ ቢሆን ተላልፎ ለእነሱ ተሰጥቷቸው፡ እንደተስፋዬ ጌታቸው፣ እንደ ካሳሁን ወንዴ እንደ ጌታቸው ብርሃኑ እንደ ወርቅነህ መበሩ፡ ወ.ዘ.ተ.ጉርጓድ ውስጥ አስረው በውሃጥምና በእራብ አሰቃይተው፣እንደውሻ ዱላ ደብድበው በመግደል፡ አለዚየም፡ እንደ ሌሎች በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን፡ ታጋዮች በጥይት መረሸን፡ ካልሆነም በማሳሰር፡ ብቻ በሆነ ነገር ኮሎኔሉን ከአካባቢው፡ በማጥፋት እሱ ይምራችሁ የሚለውን ጥያቄ፡ ማንም እንዳያነሳባቸው ማድረግ ስለሆነ፡ ለዚህ ግባቸው መሳካት ደግሞ ውሸት ፈብርኮ ለኤርትራ መንግስት ታደሰ ሊያሰራን አልቻለም፡ በማለት የማያቋርጥ አቤቱታ ማቅረብ፡ ስለነበረባቸው፡ ከእረጅም ጊዜ ጥረት በሗላ እርኩስ ዓላማቸው ተሳክቶላቸዋል።
እስካሁን ግልጽ ያልሆነው ግን ኮሎኔል ታደሰን፡ የኤርትራ መንግስት እራሱ አስሮታል? ወይንስ አሳልፎ ለዚህ ወልዶበላ ድርጅትና፡ ግብዝና መሀይም መሪዎች ሰጥቶታል? የሚለው ነው። ይህነን እርዕስ ለማጠቃለል መነሻዬን ማስታወሱ ተገቢ ይመስለኛልና፡ የመሰወሩ ምክናያቶችስ ምንና እነማን ናቸው፡ የሚለውን ከዚህ በላይ በዝርዝር ለማሳየት ሞክሪያለሁ፡ ጠቅለል አድርጌ ለማስቀመጥ፡ ደግሞ ለዚህ ጀግና እና እውነተኛ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ መሰወር፡ መነሻውም መድረሻውም፡ አንድና አንድ ብቻ ነው፡ እሱም በስሟ እየነገደ ከወያኔ ባልተናነሰ ሁኔታ ብርቅዬ ልጆቿን እንደምስጥ እንክት አድርጎ የበላውና እየበላ ያለው፡ ካልተነቃበት ለወደፊትም ከመብላት የማይገታው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ነው።
ለዛሬ በዚህ ላብቃ ቀሪውን ሳምንት በክፍል3 እመለስበታለሁ ለዚያ ሰው ይበለን ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅ አሜን

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=5632

posted by Tseday Getachew

 

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ በወባ ከሚሞተው ይልቅ በፖለቲካ ጦስ እና ችግር የሚጎዳው በቁጥር ይልቃል›› ተመስገን ደሳለኝ – [ጋዜጠኛ]

 

ኢትዮጵያን ማን ይታደጋትበተሰኘውና በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ታትሞ በገበያ ላይ በዋለው መፅሀፍ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ  የሰጠው ቃለ – ምልልስ የሚከተለውን ይመስላል፡፡ ዘ-ሐበሻ ድረገጽ ለግንዛቤ በሚል ለአንባቢዎቹ እንደወረደ አቅርቦታል

‹‹ተመስገን ደሳለኝ ጋዜጠኛ ሳይሆን የፀረ-ኢሕአዴግ ፖለቲካ አቀንቃኝ ነው›› ሲሉ ጋዜጠኛነቱ ላይ ጥያቄ የሚያቀርቡ ወገኖች የመኖራቸውን ያህል ከብዙ ፓርቲዎች በተሻለ ገዢው ፓርቲን በብዕሩ የታገለ፣ ጋዜጣ አንባቢው ኅብረተሰብ ከፖለቲካዊ ፍርሃት እንዲላቀቅ በጽናት የጣረ፣ የቁርጥ ቀን ጋዜጠኛ መሆኑን ምስክርነት የሚሰጡለትም አሉ። አራት ዓመት ገበያ ላይ በቆየችው ፍትሕ ጋዜጣ፣ ታይተው በጠፉት አዲስ ታይምስ መጽሔትና ልዕልና ጋዜጣ ላይ ባሰፈራቸው መጣጥፎቹ የመነጋገሪያ ርዕስ የነበረው ተመስገን ለእሱ በተሰጡ ቀጣይዎቹ ገጾች ላይ ከእዚህ መጽሐፍ አዘጋጆች የቀረቡለትን ሞጋች ጥያቄዎች በመመለስ የ‹‹ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት?›› አካል ሆኗል።

በልጅነትህ ምን መሆን ትፈልጋለህ ስትባል ምላሽህ ምን ነበር?

ያደግኩት ፊት በር አካባቢ ነው። ይህ ሰፈር ደግሞ በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ በርካታ የደሀ ሰፈሮች አንደኛው ነው። ያደግነውም ሆነ የምንጫወተው በቡድን ነበር። ልጅ ሆኜ ሁሌም ማታ ማታ አባቴ ጋዜጣ ገዝቶ ስለሚመጣ ቡና እየተፈላ ጋዜጣ እንዳነብላቸው ያበረታታኝ ነበር። ሁለተኛ እና ሦስተኛ ክፍል እያለሁ ለቤተሰቡ ጋዜጣ ማንበብ የዘወትር የማታ ተግባሬ ነበር። ታላቅ ወንድሜ ቢኖርም አባቴ የሚያስነብበኝ እኔን ነበር። ትምህርት ቤትም ክፍል ውስጥ አነብ ነበር።

አባትህ ማንበብ አይችሉም?

ይችላል። እስከ ዘጠነኛ ክፍል ተምሯል። በኃይለ ሥላሴ ጊዜ እስከ ዘጠነኛ ክፍል መማር ከአሁን ጋር ሲነፃፀር ያው እንደምታውቁት ነው። [ሳቅ]

ጋዜጣ ማንበቤ፣ ጋዜጠኛ እንድሆን አድርጎኛል እያልክ ነው?

አነብ ነበር እንጂ ጋዜጠኛ እሆናለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር። አድጌ መሆን እፈልግ የነበረው መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ገብቼ እስከ ጄኔራል ማዕረግ መድረስ ነበር።

የሆንከው የማትፈልገውን ነው ማለት ነው?

ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው ጋዜጠኛ በመሆኔ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ። ሁለትም፣ ሦስትም ሰዎች ቢሆኑ እኔ በምሠራው ሥራ ደስተኛ በመሆናቸው ደስ ይለኛል። በልጅነታቸው የተመኙትን ሲያድጉ የሚሆኑ ጥቂቶች ናቸው። የምንኖረው ደግሞ የተመኘነውን ሳይሆን የተጻፈልንን ነው። እናንተም ቢሆን ጋዜጠኛ እንሆናለን ብላችሁ ተመኝታችሁ እንደማታውቁ እገምታለሁ። [ጠያቂዎቹ የፈለጉትን እንደሆኑ ተናግረዋል።]

በልጅነትህ ቶሎ ደምህ የሚሞቅ፣ ከኪስህ ጩቤ የማይጠፋ የፍልውሃ እና የአራት ኪሎ የታወቅክ ተደባዳቢ መሆንህን ሰምተናል። ትክክል ነን?

[በጣም ሳቀ] አ… ማለት… እእእ… እንትን ነው… ወሬው ትንሽ ግነት አለው ብዬ አስባለሁ። እንደ ማንኛውም ልጅ ሰፈር ውስጥ ስትውል ‹‹ሰፈሬን አላስደፍርም›› ከሚል እሳቤ ፀብ አይጠፋም። በእኛ ጊዜ ደግሞ የቡድን ፀብ ፋሽን ነበር። ጩቤ ይዤ የምዞር ተደባዳቢ ግን አልነበርኩም።

ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በሰጠሀቸው ቃለ-ምልልሶች ላይ እንደተናገርከው ወደ ጋዜጠኝነቱ ያመጣህ የሙያው ፍላጎት ሳይሆን ከ1997 ዓ.ም. በኋላ መንግሥትን የሚሞግቱ ጠንካራ ጋዜጦች አለመኖር አስቆጭቶህ እንደሆነ ገልጸሀል። አመጣጥህ መንግሥትን ለመቃወም ወይም ተቺ ፖለቲካዊ ሀሳቦችን ለማንሸራሸር ብቻ አይመስልም?

አይመስልም ሳይሆን ነውም፤ ይህ ግምት ሳይሆን እውነታ ነው። ቅድም እንዳልኩት ጋዜጠኛ የሆንኩት ተጽፎልኝ አይደለም። የጋዜጠኝነት ስሜቱም እንደነበረኝ እርግጠኛ አይደለሁም። ያመጣኝ ጎርፉ ነው። እንደ ማንኛውም ሰው አገሬን እወዳለሁ። በማንኛውም ቀዳዳ፣ በምችለው መልኩ ለአገሬ የሆነ ነገር ማበርከትን አስብ ነበር። 1997 ዓ.ም. የተፈጠረው ማዕበል፣ ያመጣበት ጎርፍ ያደናገጠው ኢሕአዴግ በርካታ ጋዜጦችን ከጥቅም ውጪ አደረጋቸው። ከዚያ በኋላ የተፈጠሩት ጥቂት ጋዜጦች ደጋግሜ እንደምለው አቅሙ ቢኖራቸውም ከኢሕአዴግ ባሕሪ አኳያ ‹‹ዶማን ዶማ፣ አካፋን አካፋ›› ከማለት ይልቅ ቅኔ ለበስ ያደርጉት ነበር። ስለዚህም ይህን የፍርሃት ቆፈን ለመግፈፍ መሞከር አለብኝ በሚል እንጂ ጋዜጠኛ ለመሆን ስወድቅ ስነሣ ቆይቼ አልመጣሁም። የ97 ጎርፍ ባይመጣ ኖሮ እሆን የነበረው ጋዜጠኛ ሳይሆን ኦዲተር ነበር፤ ከ1999 ዓ.ም. ጀምሮ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ የውጪ ኦዲተር ነበርኩ።

ፍትሕ ምን ዓይነት ጋዜጣ ነበረች?

የፖለቲካ ጋዜጣ!

አንድ ጋዜጣ፣ ጋዜጣ ለመባል ሊያሟላቸው የሚገባቸው ነገሮች አሉ። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የዓምድ ስብጥር ነው። በሙሉ ወይም በከፊል ፍትሕ ይህን ይዛ ነበር ብለህ ታስባለህ?

አይ …. እንደሱ ብዬ ላስብ አልችልም። ምክንያቱም የአገራችን ሚዲያ ገና እያደገ ስለሆነ እኛም አንድ ጋዜጣ ሊያሟላ ያስፈልገዋል ወደሚባለው ደረጃ ለመድረስ ሌት ተቀን እየሠራን ባለንበት ሁኔታ ነው ጋዜጣዋ እንድትቆም የተደረገው እንጂ እጅግ በጣም ብዙ እንደሚቀረን እናውቃለን።

በአገራችን ያሉ ጋዜጦች አቋማቸው፣ የገጽ ብዛታቸውና የዓምድ መጠናቸው ቢለያይም የሚይዟቸው ነገሮች አሉ። ለምሣሌ ጤና የአገሪቷ ትልቅ ችግር ነው። በዚያ ዙሪያ የሚደረጉ ወንጀሎች፣ ሙስናዎች፣ በግል ሕክምና ተቋም የሚካሄዱ ሕጋዊ የሚመስሉ ዘረፋዎች… ብቻ ብዙ ናቸው። የምትሠሩት ለሕዝብ እስከሆነ ድረስ በቀጥታ ከመንግሥት ጋር የተገናኘው ፖለቲካ ላይ ከማተኮር ባለፈ ሌሎች ችግሮችን ወደ ማጋለጥ ለምን አታተኩሩም?

ኢትዮጵያ ውስጥ በወባ በሽታ ከሚሞተው ይልቅ በፖለቲካ ጦስና ችግር የሚጎዳው በቁጥር ይልቃል። ለዚህ ነው ከወባው ይልቅ ለፖለቲካው ቅድሚያ የሰጠነው።

[ሳቅ] ፍትሕ ጋዜጣ፣ አዲስ ታይምስ መጽሔት እና ልዕልና ጋዜጣ ላይ ከ12 ሰዎች በላይ የግል ሃሳባቸውን ይገልጹበታል፤ ከድርጅታችሁ ሠራተኞች ብዛት ይልቅ የዓምደኞቻችሁ ቁጥር ይልቃል። ይሄ ደግሞ የጋዜጣውን ኤዲቶርያል ሐሳብ ለማንሸራሸር ዕድል አይፈጥርም። ሁሉም አገሪቷ ላይ ያሉ ችግሮችን አስቦ መጥቶ ይተነፍሳል እንጂ ‹‹ሳምንታዊ አጀንዳችን እነዚህ ናቸው›› ተብለው የመሠራት ዕድላቸው አናሳ ነው።

ይሄ የሚታየው ከጋዜጣው አሠራር አኳያ ነው። ኤዲቶሪያላችን የሚያስቀምጠው ነገር አለ። ሃይማኖትን የተመለከቱ በጣም ስስ የሆኑ ነገሮች አሉ። ከዚያ በተረፈ ጋዜጣው ሙሉ በሙሉ ሐሳብን በነፃነት መግለጽ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት ስላልን ከርዕስ አንቀጻችን ውጪ ሁላችንም የተለያየ ሐሳብ የምናንፀባርቀው ከዚያ ተነሥተን ነው። ከላይ እንደገለጽኩት ፍትሕ የተመሠረተችው የጋዜጠኝነት ሙያ ባንገበገባቸው ወይም ባቃጠላቸው ሰዎች ሳይሆን ጭራሽ ጋዜጠኛ እንሆናለን ብለው ባላሰቡት ነው።

የሆነ ሆኖ ትልልቅ አገራዊ አጀንዳዎች ሲኖሩን ኤዲቶሪያል ቡድናችን ተነጋግሮ በጋራ የሚሠራበት አጋጣሚ አለ። አዲስ ታይምስ ላይ በ‹‹አባይ ግድብ›› ዙሪያ የሠራነውን መጥቀስ ይቻላል። ልዕልና ላይ ወቅታዊውን የሚዲያ ሁኔታ በተመለከተ ሠርተናል። ፍትሕ ላይም ደጋግመን ኤዲቶሪያላችን ወስኖ የሠራናቸው አጀንዳዎች አሉ። ስለዚህም ከሞላ ጎደል የጋዜጣዋን ኤዲቶሪያል ሐሳብ ማንሸራሸር ችለናል ብለን መናገር እንችላለን። አንዱን ሃይማኖት ከሌላው ሃይማኖት አናጣላም፤ በብሔርም እንደዚሁ ነው። ከእነዚያ ውጪ የሚከለክለን/የማይከለክለን ኤዲቶርያል አቋም አለን ብለን የምንራቀቅበት ሁኔታ የለም። የጋዜጣው ዋነኛ የማዕዘን ድንጋይ ፍርሃትን መግፈፍ ስለሆነ አሁን የምንከተለው ስልት ትክክል ነው ብዬ አስባለሁ።

ይህ ምን ያህል ተሳክቶልናል ብለህ ታስባለህ?

ይሄንንም የምናገረው በግምት ነው እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ የተደረገ ወይም ያካሄድነው ጥናት የለም። ነገር ግን የተሻለ ነገር አምጥተናል ብዬ አስባለሁ። ሌላ ሰው መጥቶ ‹‹ይሄን … ይሄን ፍትሕ የፈጠረችው አይደለምን?›› እስከሚል ድረስ ማለት ነው። የመምህራን ተቃውሞ፣ የፀረ- መጅሊስ እንቅስቃሴ የመሳሰሉት ‹‹ስትነጠቅ እምቢ በል›› የሚለው ፍትሕ የፈጠረችው ለውጥ እና መነቃቃት ነው ብዬ አስባለሁ። በሁለቱም በኩል ፍትሕን እንደሞዴል አንሥተው በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ጽፈው አይተናል።

ስትፅፍ ሐሳብን ገልጸህ መገላገልህን ነው ወይስ የሚያስከትለውን ውጤት (Consequence) ታሰላዋለህ?

ጋዜጠኝነት አርበኝነት አይደለም፤ ጦር ይዘህ ጠላትን ስታይ የምትወረውረውርበት/የምትሰካበት ተግባር አይደለም። ጋዜጠኛ ከሆንክ የምታነሣቸው ትችቶች እውነትን መሠረት ያደረጉ እና ሕዝብ ሊያውቃቸው ይገባል የምትላቸውን ነው። መፍትሄ ማግኘት አለባቸው ያልናቸውን ጉዳዮች እናነሣለን። ገዢው ፓርቲ እየሄደበት ያለውን ስሕተት መጠቆም እና የተሻለ መንገዶችን ማሳየት ላይ አተኩራለሁ። ኢሕአዴግ ብልጥ አምባገነን ነው። የእኛ ጋዜጣ (ፍትሕ) ታተኩር የነበረው የኢሕአዴግን የብልጠት ሴራዎችን ለሕዝብ በማሳየት እና በማጋለጥ ላይ ነው። የእኔም ጽሑፎች የሚቃኙት በዚሁ መልኩ ነው።

‹‹ተቃዋሚ›› ከሚባሉት ከአንዳንድ ፓርቲዎች በተሻለ መንግሥትን በጽሑፎችህ ለመገዳደር ትሞክራለህ። መጣጥፎችህም የጋዜጠኛ ሳይሆን የአርበኛ ወይም የተቃውሞ ፖለቲካ አቀንቃኝ ዓይነት ናቸው።

እንደምታውቁት አደባባያችን ጭር ብሏል። ጠንካራ ተቃዋሚ የለም፤ ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠት በዘለለ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ያሉ አማራጭ የትግል ስልቶችን አንዱንም አይጠቀሙም። ተቃዋሚዎች ትልቅ ነገር አደረጉ ከተባለ መግለጫ ማውጣት ነው። መሪያቸው ሲታሰር፣ አቧራ የሚያስነሣና ለትችት የሚዳርግ ፖሊሲ ሲወጣ የእነሱ ሥራ መግለጫ ማውጣት ነው እንጂ በሰላማዊ ትግል ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ አማራጮችን አይጠቀሙም። ወደ እኛ ስትመጣ አንድ ጋዜጠኛ ሊያደርጋቸው የሚገቡ አማራጮችን ሁሉ በመጠቀማችን ከፓርቲዎቹ የተሻለ ግምት አስይዞልን ‹‹አርበኛ›› ሊያስብለን ይችላል። ይህን የሚያመጣው የአርበኝነት ሚና መጫወት የነበረባቸው ፓርቲዎች ጭርታን በመፍጠራቸው እና አንተ የድርሻህን በመወጣትህ ነው። እኔ ግን ከጋዜጠኝነት የዘለለ ሚና አለኝ ብዬ አላስብም።

ፍትሕ ላይ አስፍረኸው የነበረውን ‹‹የፈራ ይመለስ›› የሚለውን ጽሑፍህን ለአብነት ማንሣት ይቻላል። [ጠያቂው ጋዜጣውን ገልጦ እያሳየው] በሰላማዊ መንገድ ቢሆንም ‹‹መብትህን ለማስከበር ውጣ፣ ተንቀሳቀስ›› የሚል ጥቅል ሐሳብ አለው። ይሄ የአንድ ጋዜጠኛ ተግባር ሊሆን ይገባዋል?

ከፖለቲካ ገለልተኛ የሆነ አገር የሌለው ብቻ ነው። አገር የሌለው ደግሞ ማን አለ? ማንም የለም። ጋዜጠኛ ብሆንም የራሴ የሆነ የፖለቲካ አቋም አለኝ። ጽሑፎቼ ላይ አቋሞቼ ሊንፀባረቁ ይችላሉ። ሥርዓቱ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለመተቸት ያልከውን ጽሑፍ ጽፌዋለሁ። አምስት ዓመት ያህል የጻፍኩት ግን ‹‹የፈራ ይመለስ›› ብቻ ብዬ አይደለም።

የአንድነት ፓርቲ ልሳን ከነበረችው እና ስትንፋስዋ ከተገታው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ፣ የፖለቲካ አቀንቃኝ (Political Activist) ስለ መሆንህ ጥያቄ ቀርቦልህ ‹‹አዝማሚያው ሊኖር ይችላል›› ብለህ ነበር። ታዲያ ይህ ከጋዜጠኝነት መርሕ ጋር በእጅጉ አይጋጭም?

‹‹የፖለቲካ አቀንቃኝ ነህ?›› ያለው ጠያቂው እንጂ እኔ አይደለሁም።

አንተም ግን ‹‹አክቲቪስት ነኝ ባልልም እስከ ዛሬ ፍትሕ ታደርግ የነበረው ከዚህ የዘለለ አይደለም›› ስትል ምላሽ ሰጥተሀል።

‹‹ጽሑፎቼ ያንን ስያሜ ለማሰጠት አጋድለው ሊሆን ይችላል›› ነው ያልኩት። አንባቢ ከጽሑፍህ ተነሥቶ አርበኛ ሊልህ፣ ፅንፈኛ ሊልህ፣ የተቃውሞ ፖለቲካ አቀንቃኝና ሌላም ሊልህ ይችላል። እነዚህ ሁሉ ምድቦች ግን እኔ ውስጥ የሉም። ራሴን የምቆጥረው በአገሩ ላይ የተሻለ ነገር እንዲፈጠር የሚጥር አንድ ጋዜጠኛ አድርጌ ነው።

ስለ ስደተኛ ጋዜጠኞች ያለህ አቋም ምንድን ነው?

ኧኧኧ… [ሳቅ… የቁጥብነት ስሜት እየታየበት] ማንም ሰው ‹‹ለምን የእኔን ፅዋ አልጠጣም?›› ብለህ ልትወቅሰው አይገባም። የራሱ መከራ የመቀበል አቅም የት ድረስ እንደሆነ ያውቀዋል። እዚያ ደረጃ ሲደርስ ማንም ሰው ይሰደዳል። ለእኔ ግን መሰደድ የሚወገዝ ተግባር ነው።

ጋዜጠኛ መፍራት/መሸሽ የለበትም እያልክ ነው?

የመፍራት ጉዳይ ብቻ ሆኖ ሳይሆን ችግሩ እኮ ያለ ነገር ነው። እናንተ ጋዜጣ ለመጀመር ፈቃድ ጠይቃችሁ የነበረው የአውራምባ ታይምስ ማኔጂንግ ኤዲተር ‹‹ልከሰስ ነው›› ብሎ በሸሸበት፣ አዲስ ነገሮች የተሰደዱበት ሁኔታን እያወቃችሁ ነው። እና ታዲያ ‹‹ይህ ጸበል ለእኛ አይደርሰንም›› ብላችሁ ታስባላችሁ? ታዲያ ልከሰስ ነው፣ ልታሰር ነውን ምን አመጣው?

ስለዚህ ለተሰደዱ ጋዜጦች ምንም ክሬዲት አትሰጥም ማለት ነው?

[እየሳቀ] ያው ገልጬዋለሁ ‹‹የተሰደዱ ጋዜጠኞች ለፍተዋል፣ ሠርተዋል›› ብዬ ላስተካክለው? [ሳቅ] የእውነት ሠርተዋል፤ ለፍተዋል። ሲሰደዱ መከራን የመቀበል አቅማችን እዚህ ድረስ ነው ብለው ነው። ባይሰደዱም ያሉት ነገር (እስር) ሊተገበርባቸው ይችል ነበር። የእኔ ቅሬታ ኢሕአዴግ የለየለት አፋኝ በመሆኑ የጋዜጣ ፈቃድ ሲወስዱ ይህ እንደሚሆን ስለሚያውቁት ከመሰደድ ይልቅ ፊት ለፊት መጋፈጡ የተሻለ ነው የሚል ነው። የምንፈልገውን ውጤት የምናመጣው መስዋዕትነት በመክፈል ነው። ጋዜጠኛ የሐሳብ ተዋጊ ነው፤ ምሽጉ ደግሞ ሚዲያው ነው። ስለዚህ መስዋዕትነቱን እየከፈለ ምሽጉን መልቀቅ አይገባውም። ከአገር የተሰደዱ ጋዜጠኞችን ግን በምንም መልኩ ጥፋተኛ ልናደርጋቸው አይገባም። የሸሹ ሰዎች ጥፋተኛ ናቸው አለማለቴ እንዲታወቅልኝ ግን እፈልጋለሁ።

አገር ውስጥ ሆነው የሰላ ትችት ለሚሰነዝሩት ክብር ሰጥቶ በተቃራኒው የተሰደዱትን ክሬዲት ማሳነስ ልክ ይሆናል? አገር ውስጥ ካሉት ከተሻለ በውጪ ወጥተውም አበርክቷቸው ያልተቋረጠ (እየሠሩ ያሉ ጋዜጠኞች) አሉ ብዬ ስለማስብ ነው። እንዳሉት የሚታሰሩ ከሆነስ ወጥተው የሚችሉትን ማበርከታቸው ተገቢ አይሆንም?

ግልፅ እንዲሆን የምሻው ስደተኛ ጋዜጠኞች ፈሪዎች፣ የማይሸሹ ጋዜጠኞች ደግሞ ደፋሮች ናቸው አላልኩም። ድፍረት እና ፍርሃትን ከዚህ ውስጥ እናውጣው! ነገር ግን የቁርጠኝነት ጉዳይ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። መከራ የመቀበል ደረጃ ልዩነት እና የስልት ጉዳይም ነው። እኛ (ፍትሖች) ‹‹እዚሁ ቆስለን፣ እዚሁ ደምተን እንሠራለን›› ስንል፣ ሌሎች ጋዜጠኞች ደግሞ ‹‹ከመታሰር ከአገር ውጪ ሆኖ አስተዋፅኦ ማድረግ የተሻለ ነው›› ይላሉ። ይሄ የምርጫ ጉዳይ ነው። በእኔ እምነት ግን ከአገር ውጪ ሆኖ መሥራት የተሻለ አይደለም፤ እዚህ ሆኖ የመጣውን በጸጋ መቀበሉ የለውጡን ቀን ያቀርበዋል። በተረፈ ትክክሉ ለየራሳችን የሚተው ነው።

የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን አስመልክቶ ‹‹ከጥቂት ቀናት በኋላ አንድ ነገር ይኖራል ጠብቁ›› ብለህ ፌስቡክ ላይ ገልጸህ ነበር። በሁለተኛው ቀን ማረፋቸው ተነገረ። የኢሕአዴግ የውስጥ ምንጮች አሉህ?

ምንም የማያከራክረው ፍትሕ በአገሪቷ ትልቅ ጋዜጣ ነበረች፤ ዋና መስፈርቱ የኅትመት ቁጥር በመሆኑ። የብዙ ሰዎችን ትኩረት ስለሚስብ መረጃዎች ወደ እኛ ይመጣሉ። ሥርዓቱ አገርን እየጎዳ እንደሆነ የሚገነዘቡ የሥርዓቱ ወሳኝ የሆኑም/ያልሆኑም ሰዎች አገርን ከማዳን አኳያ፣ እኛን በማመን አንዳንድ መረጃዎችን ያቀብሉናል።

ጽሑፎችህ ጥልቀት እንደሌላቸው እና ሰዉ ‹‹የእኔ›› ብሎ እንዲያነብ ሰሞነኛ ብሶታዊ ስሜትን ማንፀባረቅ ላይ እንደምታተኩር የሚተቹህ አሉ።

ሁሉም ጽሑፎቼ ላይ ባይሆንም ይሄ ዓይነት ነገር አለ ብዬ አስባለሁ። ፍርሃትን በመግፈፍ ሕዝብን ወደ አደባባይ መሰብሰብን ስለማልም፤ [አደባባይ ስል አብዮት አደባባይ አይደለም] ሕገ- ወጥነትን እምቢ እንዲል የማንቃት ባሕሪ ዋና ዓላማዬ ስለሆነ ሕዝባዊ እና ስሜታዊ ጉዳዮች ላይ አተኩራለሁ። በአገራችን ላይ የጠፋው ነገር የርዕዮተ ዓለም ዳሰሳ እና ትንተናዎች ሳይሆን [ይሄን በቂ ምሁራን ብለውታል] ፍርሃትን ማሸነፍ ነው። ለዚህ ደግሞ መፍትሄው አብዮታዊ ዲሞክራሲን ከሊበራል ዴሞክራሲ ጋር እያነፃፀርክ መተንተን አይደለም። የጠቀስካቸውን ጉዳዮች መዳሰስ ነው። ከዚህ አኳያ እንዳልከው ጥልቅ ትንታኔ ላይኖረኝ ይችላል። ‹‹የፈራ ይመለስ›› ለማለት ጥልቅ ትንታኔ አያስፈልግህም። አምስት ዓመት የተጻፉት ጽሑፎች ሁሉ ጥልቀት የሌላቸው ናቸው ብዬ ግን አላስብም።

ከሐሳብ ሙግት ይልቅ ግለሰቦችን ‹‹መጭረፍ›› ላይ ታተኩራለህ። መለስ ዜናዊ፣ ስብሀት ነጋ፣ ፕ/ር አንድሪያስ እሸቴ፣ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ፣ ሬድዋን ሁሴን፣ ፋሲል ናሆምና ሌሎችም ላይ ግላዊ መሠረት ያለው ትችት አቅርበሀል። ችግሮች ያሉት ግለሰቦቹ ጋ ነው ወይስ ተቋማዊ አሠራሩጋ?

ገበያ ላይ ከዋሉ 197 የፍትሕ ኅትመቶች ውስጥ ቢያንስ በሳምንት አንድ ጽሑፍ ላይ እኔ አለሁ። [በነገራችን ላይ የፍትሕ የመጀመሪያዎቹ ሕትመቶች ላይ ተመስገን በስሙም ሆነ በብዕር ስም የጋዜጣዋን ከግማሽ በላይ ገጾች ይሸፍን ነበር።] ከዚያ ውስጥ ግለሰብ ላይ ያተኮርኩት በጣም ጥቂት ጽሑፎች ላይ ነው። ግለሰቦች ላይ የጻፍኩት እኮ አምስት ጊዜ ብቻ ነው።

ልልህ የፈለግኩት ለውይይት የሚጋብዙ ሓሳቦች (Arguments) ላይ ከማተኮር ይልቅ የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር መለስን ጨምሮ በርካቶች ግላዊ ኹነት ላይ ትንተራሳለህ ነው። [የተቋምም ሆነ የሲስተም ፈጣሪ ሰው መሆኑ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው።]

በርዕዮተ ዓለሞች ላይ፣ በፍትሕ ሥርዓቱና በመሳሰሉት ላይ ለሁለት ዓመት ያህል ሀተታዎች (Features) ጽፌያለሁ። ስለዚህ ፍትሕ ከመግነኗም በፊት ያለውን ማሰብ/ማየት ያስፈልጋል።

‹‹እስኪ በስብሀት ሙድ እንያዝባቸው፣ ንዋይ ገብረ አምላክ በረሃ እንዳልገቡ አውቃለሁ ምናልባት ውቤ በረሃ ካልገቡ በስተቀር…›› መሰል ከሞራል እና መገናኛ ብዙኃን ከሚቀርብ ጽሑፍ አንፃር (በተለይ ኮስታራ ጽሑፍ ላይ) ተገቢ ያልሆኑ ቃላትን ትጠቀማለህና ይህ ሐሳብህን ወደ ስድብ ደረጃ አያወርደውም?

ኧ… ኧ… ኦኬ! ቃላቶቹን የተጠቀምኩት ትንሽ ዘና ለማድረግ ያህል ነው። ለምሳሌ ንዋይ ገብረ አምላክ የኢሕአዴግ ታጋይ አይደሉም፣ የደርግ ባለሥልጣን ነበሩ። ያንን ይበልጥ ለመግለጽ ‹‹ንዋይ ገብረ አምላክ በረሃ አልገባም፤ ምናልባት ውቤ በረሃ ካልሆነ›› ብያለሁ። ስድብ ነው ብዬ አላስብም ነበር። በዚያ መልኩ ተተርጉሞ ከሆነ በጣም አዝናለሁ። ምናልባት ቃላቶቹ ወደ ስድብ ወርደው ከሆነ በእጅጉ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ለመሳደብ አልነበረም፤ ከባሕሪም አኳያ የመሳደብ ነገር የለብኝም።

አፍሮጋዳ የሚል መጽሐፍ አንብበሀል? ‹‹ዘመኑ የሚወደው ጥልቀትን አለዝበህ ስሜቱን እንድትነግረው ነው። ቴዲ አፍሮ እና ይስማዕከ ወርቁ (ዴርቶጋዳ) የተወደዱት ለዚህ ነው›› ይላል፤ ታሪክ ሠሪው ከግልቡ እኩል አይታወቅም የሚል ይዘት አለው ጽሑፉ። ይሄንን በአንተ ላይ እንዴት ታየዋለህ?

የ‹‹ጥልቀት›› እና የ‹‹ግልብ›› መስፈርቱ ምንድን ነው? የሚለው አንድ ነገር አለ። በእኔ እምነት የቴዲ አፍሮም ሆነ የዴርቶጋዳ ሥራዎች ግልብ አይደሉም። እነዚህን ‹‹ግልብ›› እንበላቸውና የንዋይ ደበበን ወይም የሰለሞን ተካልኝን ሥራዎች ‹‹ጥልቀት›› አላቸው እንበል? [የአግራሞት ሳቅ] ጥያቄውን ለመመለስ ግን ምናልባት አገር እና ሕዝብን የመናቅ ነገር ይመስለኛል። ቴዲ አፍሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አድማጮች አሉት እነዚህን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አብረህ መተቸት ነው። እነዚህ ኢትዮጵያኖች የወደዱትን ሥራ አናንቀን የተሻለው የትኛው ነው?

ሕዝብ የወደደው ነገር ሁሉ ትክክል ነው ማለት ይቻላል?

እንደ ሕዝብ ስሕተት አለው ብዬ አላስብም። አንድ መጽሐፍ ጥልቅም ይሁን ግልብ ሆኖ ይውጣ፣ ገበያ ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥረው ጋዜጦች ላይ ከሚወጣው ማስታወቂያ ይልቅ ሕዝብ የሚያወራው ነው። የአንተን መጽሐፍ በጣም አሪፍ ነው እያለ የሚያወራው ከሆነ በቃ አከተመ፤ በጥሩ ሁኔታ ይሸጣል። ‹‹ኡ… የአቤል መጽሐፍ የሞተ ነው›› ብሎ ሕዝብ የሚያወራ ከሆነ ታቅፈኸው ትቀራለህ። ዴርቶጋዳ በእኔ እምነት ጥሩ መጽሐፍ ነው። ያንን ሁሉ ሰው ማሳማን የቻለ ሥራ ግልብ ነው? ይሄ ሁሉ ሰው ግልብ እና ጥልቀት መለየት አይችልም? የሚሉ ነገሮች አብሮ ሊታዩ ይገባል ባይ ነኝ።

ሁሌም መንግሥትን የሚያጠለሹ ጽሑፎችን ብቻ በመጻፍ ትተቻለህ። ይህ ሥርዓት ምንም አልሠራም ብለህ ታስባለህ?

ሩቅ ሳትሄድ ለምሳሌ አዲስ ነገር፣ አውራምባ ታይምስ፣ ፍትሕ ጥቂት ጊዜ ቢኖሩም የዚህ ሥርዓት ውጤት ናቸው፤ እንደ ድመት ራሱ ወልዶ በላቸው እንጂ። ምንም የምትክደው ነገር አይደለም። በደርግ ጊዜ ‹‹ሠርቶ አደር፣ አዲስ ዘመን፣ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ›› እያልክ ትሄዳለህ እንጂ የግል ሚዲያ ሽታውም አልነበረም። በዚህ 22 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚመስሉ ነገሮች ብዙ አሉ። ለምሳሌ እናንተ የአውራምባ ታይምስ ባልደረቦች ነበራችሁ። ምንም ይሁን ምን አውራምባ ታይምስ የተዘጋው በኢሕአዴግ ጫና ነው። ስለዚህ ስለ ፕሬስ ነፃነት የሚኖራችሁ ግንዛቤ እዚያ ላይ መሠረት ያደረገ ነው። አውራምባ ታይምስ አራት ዓመት ያህል ለመሥራትዋም ቢሆን ምንም ሳያከራክር ክሬዲቱን መውሰድ ያለበት ኢሕአዴግ ነው። ‹‹ነፃ ፕሬስ›› ብሎ፣ አዋጅ አቋቁሞ፣ ፈቃድ የሰጠው ኢሕአዴግ ነው። ፍትሕ ተዘግታለች ነገር ግን እስከ ነበረችበት ጊዜ ድረስ ፈቃድ የሰጣት ኢሕአዴግ ነው። እነዚህ እነዚህ በጎ ጎኖች በትልልቅ ጥፋቶች፣ ውድመቶችና ኪሳራዎች ስለሚጋረዱ ያንን ማየት የማትችልባቸው ሁኔታዎች አሉ።

ፍትሕ ከተዘጋችና አዲስ ታይምስ መጽሔት ላይ ተሻግራችሁ ሥራ ከመጀመራችሁ በፊት 300 ሺህ ብር ወጪ እንዳወጣህ ፌስቡክ ላይ ጽፈህ አንብበናል። የማስታወቂያ ገቢ አልነበረህምና ጋዜጣ ሸጦ ይሄንን ሁሉ ወጪ መሸፈን ይቻላል?

ጋዜጣ እየሸጥክ እያለህ ድርጅትን ልታሻሽል ትችላለህ። አቁመህ ግን ይሄን ያህል ትርፍ ወጪ መሸፈን አትችልም። እንደምታውቁት ባለፈው ዓመት (2004 ዓ.ም.) ግንቦት ወር ላይ ከወጣው መጽሐፌ (የመለስ አምልኮ) ብዙ ብር አግኝቼበታለሁ። ንገረኝ ካልከኝ መጠኑን ልነግርህ እችላለሁ።

ይቻላል!

እስካሁን ባለው ሁኔታ ከስድስት መቶ ሺህ (600,000) ብር በላይ አግኝቼበታለሁ። ጋዜጣው ቢዘጋም የደጎመኝ ይሄ ብር ነው። ‹‹300 ሺህ አወጣሁ›› ያልኩት ፍትሕ ማተሚያ ቤት ስትያዝብን 84 ሺህ ብር ከፍለን ነበር። በተጨማሪም ጋዜጣውን ለማዘጋጀት የከፈልናቸው ወጪዎች ነበሩ። በአዲስ ታይምስ እስክንመለስ ድረስ ማንም ሠራተኛ ስላልተባረረ ደመወዝ እንከፍል ነበር። 300 ሺህ ብር የደረሱት እነዚህ ወጪዎች ተደማምረው ነው። መቆየት የቻልነውም በመጽሐፉ ገቢ ነው።

ፍትሕ እንደቆመች በተሻለ ፍጥነት በአዲስ ታይምስ መጽሔት ተመለሳችሁ፣ ለስምንት እትም የሄደችው አዲስ ታይምስ ስትቆምም አራት እትም በሄደችው ልዕልና›› ለሦስተኛ ጊዜ መጥታችሁ ነበር። በዋነኝት ኦርኬስትራውን የምትመራው አንተ ነህና ይህ ትጋትህ ለፕሬስ ነፃነት ነው ወይስ ለገንዘብ ነፃነት? [የንግድ ሱቁ የተዘጋበት ሰው ገቢው እንዳይቆም በፍጥነት ሱቅ አፈላልጎ እንደሚይዘው ሁሉ የእናንተም ወደ ሌላ ፕሬስ የምትጓዙት በፍጥነት ስለሆነ ጥርጣሬ በመፍጠሩ ነው።]

ትልቁ ስሕተትህ የሚጀምረው [ጠያቂው አቤልን ቆጣ ብሎ እያየ] በኢትዮጵያ የጋዜጣ ንግድ ለገንዘብ ነፃነት ያበቃል ብለህ መገመትህ ነው። ሐሳቡ የአንተ ካልሆነም ‹‹ሐሳባችሁ ስሕተት ነው›› በልልኝ። በኢትዮጵያ ፕሬስ ውስጥ ያለህን ይዘህ ገብተህ፣ ባዶ እጅህን ትወጣለህ እንጂ እውነት አትራፊ የምትሆንበት ነው?

ፍትሕ አትራፊ አልነበረችም?

ፍትሕ አትራፊ ነበረች። ለአራት ዓመት ያህል ርምጃዋን ጠብቃ መጓዝ በመቻልዋ በሂደት አትራፊ መሆን ችላለች። ነገር ግን አዲስ ታይምስን ስምንት ጊዜ ስናሳትም እና ልዕልናን በከፍተኛ (በተጋነነ) ወጪ ንግድ ፈቃድዋን ከግለሰብ ላይ ስንገዛው ቁማር እንደሆነ እናውቃለን። ከኢሕአዴግ አፋኝ ባሕሪ አንፃር አንድ እትምም ሳንሄድ ሊዘጋት እንደሚችል እናውቃለን። በተለይ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሞት በኋላ ሥርዓቱ ሆደ ባሻ በመሆኑ ያገኘውን ነገር ሁሉ መርገጥ እና ማፈን ጀምሯል። ይህ ባለበት ሁኔታ ብዙ ወጪ አውጥቶ፣ በኪሳራ ምክንያት የቆመን ጋዜጣ ከግለሰብ ላይ በተጋነነ ገንዘብ መግዛቱ ለገንዘብ ያለህን ሐሳብ በፍጹም አያሳይም። ልናተርፍ ይቅርና ያወጣነውን ገንዘብ እንኳን ለማስመለስ ዋስትና የለንም። የሚገርመው ደግሞ የቃለ-ምልልሱን ተከታይ ክፍል በምታደርጉበት በዚህ ወቅት ልዕልና መቆሟን የምነግራችሁ የመጀመሪያ ሰዎች ሆናችኋል። ስለዚህ፣ ያወጣነውን ወጪ እንኳን ማስመለስ አልቻልንም ማለት ነው። እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ‹‹ለገንዘብ ነፃነት ነው የምትሠሩት›› መባል የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ አለማወቅ ይመስለኛል። ያለንን እያወጣን መቆመራችን፣ ለፕሬስ ነፃነት እንታገላለን ከሚል እሳቤ የመነጨ መሆኑን ያለጥርጥር እናገራለሁ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ራሳቸውን ሳያከብሩ ሌላውን ማክበር፣ ለራሳቸው አድናቆት ሳይኖራቸው ሌላውን ማድነቅና ጥቂት ግለሰቦች ላይ መንጠልጠል ይፈልጋሉ። መናገር እየቻሉ ‹‹ተመስገን በዚህ ጉዳይ ጻፍበት፣ ተችበት፣ ንገርልኝ›› ሲሉ በጎንዮሽ መልዕክት ማስተላለፍን ይመርጣሉ። ትቀበለዋለህ?

እንዳልኳችሁ እንደ እነዚህ ዓይነት ሰዎች እና ሁኔታ አገራችን ላይ በመኖሩ ነው እኔ ጋዜጠኛ የሆንኩት እንጂ ፍላጎቱ ኖሮኝ ከየትኛውም የጋዜጠኝነት ትምህርት ቤት ተመርቄ አይደለም። እንደዚህ ዓይነት ድባብና ፍርሃት ስላለ የግድ የተወሰንን ሰዎች ሰንደቅ ማንሳት አለብን፤ ሰዎቹ ቢሉም ትክክል ናቸው። የምንሠራው ለእነሱ፣ ለሌላው ሕዝባችንና ለአገራችን ነው። በዚህ ላይ ደግሞ ለአንድ አገር መስዋዕት ሊሆኑ የሚገቡት ጥቂት ሰዎች ናቸው እንጂ 80 ሚሊዮን ሕዝብ መስዋዕት ከሆነ ታዲያ ማን ነው በመስዋዕትነት በተገኘ ድል ላይ የሚረማመደው? የአረብ ዓለም አብዮት በተነሣ ጊዜ ሆን ብለው የመንግሥት የፀጥታ ሠራተኞች ‹‹ይሄ ሕዝብ አንተ ሞተህለት እንዲያልፍለት ነው የሚፈልገው›› የሚል አፍራሽ ቅስቀሳ ጀምረው ነበር። አገራችን የተሻለች ልትሆን የምትችለው፣ የተወሰንን ሰዎች መከራውን ከተቀብለን ነው። ፈረንጆቹ ‹‹ነጻ ምሳ የለም›› እንደሚሉት ሕዝቡ በሙሉ መከራና ችግር የሚቀበል እና የሚቸነከር ከሆነ ከትርፉ ይልቅ ኪሳራው ያመዝናል። ስለዚህ በጥቂቶች ላይ ቢንጠለጠሉም ተገቢ ነው።

ዱላውን የሚቀበል በሌለበት፣ ለእውነት መታገል እና መስዋዕትነት መክፈል ኪሳራ አይሆንም?

ፍትሕን የመሠረትኩትና እኔ ጋዜጠኛ የሆንኩበት ምክንያት የዚህ ዓይነት ዱላ የሚቀበሉ ዜጎችን ለማፍራት ነው። እቅዴ ፍርሃትን አሸንፈው እና ከቀንድ አውጣ ዛጎላቸው ውስጥ ወጥተው ዱላ ሊቀበሉ የሚችሉ የፍትሕ ቤተሰቦችን ማፍራት ነው።

ዱላ ተቀባይ ከሌለስ?

ማፍራት አለብን። እስኪፈራ ድረስ አቅም እስካለ እንሠራለን። እኛ ብናልፍ በርካታ ሰዎች ይቀጥሉታል። ቢያንስ በዚህ አራት ዓመታት ውስጥ ሁለትና ሦስት ማፍራት እንችላለን ብዬ አስባለሁ። በሂደት እንዲህ አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት እየተባለ ይቀጥላል።

‹‹ዱላ ተቀባዮችን በሂደት እናመጣለን›› ብለሀልና አሁን ዱላ ተቀባዮች ከሌሉ፣ ብዙዎች በፍርሃት ቆፈን ውስጥ ከባተቱ፣ አንተ ወይም ጥቂቶች ጠንካራ እና ሞጋች ሐሳቦችን መሰንዘራችሁ እናንተን እያገነነ ወደ ጀብደኝነት ደረጃ ከፍ ያደርጋችኋል እንጂ ተከታዮችን ለማግኘት ያስችላችኋል?

‹‹ተመስገን አርአያዬ ነው›› የሚሉ ሰዎች አሉ። እንዲህ ካሉ እኔ አናጢ፣ ግምበኛ ወይም አስተማሪ አይደለሁም። አርአያነቴ በጋዜጠኝነት ሥራዬ ነው። ስለዚህ ይህንን አርአያ ይከተላሉ ማለት ነው።

የሠራህባቸው የኅትመት ውጤቶች ከተቋማዊ አሠራር ይልቅ በአንተ ትከሻ ላይ መንጠልጠል ይታይባቸዋል። ጥናት ባንሠራም፣ ባለን መረጃ መሠረት ከጋዜጣችሁም ጥቅል ፍሬ ነገር ይልቅ አንተ ርዕስ ነህ። በሆነ አጋጣሚ ለአንድ ወይም ለሁለት ሳምንታት ተመስገን ባይጽፍ የጋዜጣችሁ ሽያጭ አደጋ ውስጥ የሚወድቅ አይመስልህም? [የፍትሕ/አዲስ ታይምስ/ልዕልና አንባቢያን ማዳመጥ የሚፈልጉት ያንተን ትኩሳት ነው ብዬ ነው።]

ይሄ ሁኔታ ተቋማዊ ሁኔታን ካለመገንባት የሚመጣ ሳይሆን ጋዜጣው ለረዥም ዓመት እንደ አሁኑ ‹‹በድል ጎዳና›› መራመድ ሳይጀምርና በቂ የሠራተኛ ኃይል ሳይኖረው፣ ለረዥም ዓመት በችግርና በብድር [አራጣ እስከ መበደር ደርሼ] ጋዜጣውን ይዤ የተጓዝኩት እኔ ስለሆንኩ ነው። በ2004 ዓ.ም. ሙሉ ዓመት ግን ጋዜጣው ተቋማዊ ሰውነት ይዞ እየተጓዘ ነበር። በእኔ እምነት ፍትሕ የተለያዩ ሐሳቦችን ታነሣለች፣ ታስተናግዳለች። አቅም ኖሮንም መክፈል ችለናል። ይሄ ጋዜጣዋ በድል ጎዳና መጓዝ ከጀመረች በኋላ የመጡ ለውጦች ናቸው። ይሄ ጥያቄ የተነሣው 2004 ዓ.ም. ሳይገባ በፊት ቢሆን ትክክል ነበር። ከስሜ ውጪ በብዕር ስም ስድስትና ሰባት ጽሑፍ በሳምንት የምጽፍበት ጊዜ ነበር።

‹‹ፍትሕ በድል ጎዳና…›› ካልከው ጋር ልንተራስና፣ በተደጋጋሚ ጊዜ በኅትመት መጠን ቀዳሚ መሆንን እንደ ብቃት ጥግ ማሳያ ትመለከተዋለህ። ፍትሕ ታብሎይድ ስለሆነች እና ስሜት ቀስቃሽ (Sensational) ጉዳዮችን ስለምታንፀባርቅ (ስለምታነሣ) እንጂ የጋዜጣዋን በደረጃ ቀዳሚነት እና ጥልቀት፣ ተነባቢነቷን ፈጽሞ አይገልጽም ብልህ ተሳስቻለሁ?

አዎን! ሙሉ በሙሉ ተሳስተሃል። ምክንያቱም ምንም የማያከራክረው ነገር 2004 ዓ.ም. ሙሉ ፍትሕ በኅትመት መጠን ቀዳሚ ነበረች። በታብሎይድ ስታይል ብትሄድ፤ አንድ ሳምንት ስሜት ቀስቃሽ ርዕሰ ጉዳይ ስታገኝ ሊሳካልህ፣ ሳታገኝ ደግሞ ላይሳካልህ ነው። ከሳምንት ሳምንት በቋሚነት አንባቢ አፍርተህ መጓዝ ማለት ግን የተሻለ አማራጭ ይዘህ መጥተሃል ማለት ነው። ስሜት ቀስቃሽ ነገሮች በጣም ውስን እና ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር የሚያያዙ ናቸው። ለምሳሌ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሞት ስሜት ቀስቃሽ አጀንዳ ሊሆን ይችላል። ጥሩ አድርገህ ልትሠራበት ትችላለህ። ሁልጊዜ ግን እሳቸው አይሞቱም። ዓመቱን ሙሉ በቀዳሚነት መጓዛችን የሚያሳየው ቋሚና ታማኝ አንባቢ ማግኘታችንን ነው። ታማኝ አንባቢ ማግኘት ደግሞ ቀዳሚ መሆን ማለት ነው።

በአገራችን ነፃ ፕሬስ ስሙ ነው እንጂ በአሁን ወቅት አለ ብለህ ታምናለህ?

የለም ብዬ አምናለሁ።

ማሳያህ ምንድን ነው?

ጋዜጠኛው በራሱ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቱ ምን ያህል ተከብሯል? እስክንድር ነጋ፣ መስፍን ነጋሽ፣ ዳዊት ከበደ፤ አቤል፣ ኤልያስ፣ ውብሸት ወይም አቤ ቶኪቻውን ምን ያህል ነፃ አድርገዋቸዋል? በሚል ነው የሚለካው እንጂ ‹‹ኢሕአዴግ አምባገነን ነው›› ብቻ ብሎ በመጻፍ የጋዜጣህ ነፃነት ወይም ነፃ ጋዜጠኝነት አይለካም። ከዚህ አኳያ አሁን ወዳሉት የኅትመት ውጤቶች ስትመጣ ‹‹ነፃ ጋዜጣ አለ›› ለማለት ይከብደኛል። [የቃለ ምልልሱን የመጀመሪያ ክፍል ያደረግነው ፍትሕ ጋዜጣ ከቆመች በኋላ በነሐሴ 2004 ዓ.ም. እንደነበር ልብ ይሏል።] ‹‹ከዚህ በኋላ በዚህ ርዕስ ላይ እንዳትሠራ›› የሚሉ የጋዜጣ ባለቤቶች ናቸው ያሉት። ዋና አዘጋጆቹም የባልደረቦቻቸውን ሸክም (መስቀል) መሸከም የማይችሉ ናቸው። በአገሪቱ የፕሬስ ሕግ መሠረት የሚጠየቀው ዋና አዘጋጁ ነው። ፍትሕ ላይ ሁሉም በሚጽፉት ጽሑፍ አንዳች ነገር እንደማይደርስባቸው ያውቁታል። ስለዚህ እነዚያ ጋዜጠኞች እንዳሻቸው በነፃ ሜዳ ላይ ይቦርቁበታል ማለት ነው። ማንኛውም ዋና አዘጋጅ ለባልደረቦቹ ያንን ያህል ኃላፊነት መውሰድ አለበት። በዋነኛነት ‹‹ነፃ ጋዜጣ የለም›› የምልህ አፈናው የሚጀምረው ከውስጥ፤ ከባለቤቱና ከዋና አዘጋጁ በመሆኑ ነው። ጋዜጦቹን በደንብ ተከታተሏቸው፤ የሚጮሁበትና የማይጮሁባቸው ጉዳዮች አሉ። የሚሠሩት ‹‹ይሄ ኢሕአዴግን ያስቆጣዋል/አያስቆጣውም›› እያሉ በማማረጥ ነው።

ነፃ ሚዲያ አለ ብለህ አታምንም ነገር ግን የኅትመት ውጤቶችህ/ቻችሁ ሲዘጉ እነዚህኑ የፕሬስ አካላት ሁኔታውን ይፋ እንዲያደርጉ እና አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ትጠይቃለህ። አይጣረስም?

ግልፅ እንዲሆን የምፈልገው ነገር… የሕወሃትን አጀንዳ የሚያራምዱ መገናኛ ብዙኃን እንዳሉ አምናለሁ። ሌሎቹ ግን ራሳቸው ላይ ቅድመ ቁጥጥር እያደረጉ ራሳቸውን በራሳቸው አዳክመዋል። አንድ ሚዲያ ራሱን ከገደበ፣ ኤዲቶሪያል ነፃነቱ ላይ ከተደራደረ፣ ‹‹ይዘጉብኛል›› ብሎ ራሱን ከቆጠበ ደካማ ነው። በርግጥ ይህ የሆነው በሥርዓቱ ጫና ፈጣሪነት ነው። ይህ ማለት ግን ሕወሃት ጠፍጥፎ ሠርቷቸዋል ማለቴ አይደለም። ስሕተታችንን ነግረኸናል በሚል ቅር ተሰኝተው፣ ከእናንተ ጎን አንቆምም የሚሉ ካሉ የአቶ መለስን አባባል ልዋስና [አቶ መለስ የሚነሡለት በጎ ነገር ባይኖርም፣ ተረቶቹ ይነሣሉ] ‹‹በሊማሊሞ ማቋረጥ ትችላላችሁ›› እላቸዋለሁ።

እኛ አገር ባለው ሁኔታ አሳታሚዎች ወይም ጋዜጠኞች የጋራ ችግር ሲመጣ፣ የማተሚያ ቤት ዋጋ ሲወደድና መሰል ችግሮች ሲፈጠሩ ለይምሰል ማኅበር ይቋቋማል፣ ‹‹ኅብረት›› ለመፍጠር ይጥራሉ እንጂ በጥቅሉ አጋርነት (Solidarity) አለ ለማለት ይቻላል?

እንዳልኳችሁ ምን ያህል ጋዜጦች ነፃ ናቸው? ከ2003 ዓ.ም. በኋላ ገበያ ላይ እስከነበርንብት ጊዜ ድረስ ከአውራምባ ታይምስ ውጪ ነፃና በራሱ ቆሟል ብዬ የማምነው ሌላ ጋዜጣ አልነበረም። ይሄ የአደባባይ ሃቅ ነው። ሌሎቹ የየራሳቸው ፍላጎት ያላቸው ናቸው። ራሳቸውን ነፃ ካላወጡ ሰዎች ጋር አብሬ፤ ነፃ ማኅበር መስርቼ እንቀሳቀሳለሁ፣ የፕሬስ ካውንስል መስርቼ እንቀሳቀሳለሁ ብትል አያስኬድም። የፕሬስ ካውንስል በየትኛውም አገር የሚታየው ከሥነ-ምግባር አኳያ ነው። አፍሪካ ውስጥ ትልቅ የፕሬስ ካውንስል ያለበት የመጀመሪያ አገር ዛምቢያ ትመስለኛለች። እዚያ ፕሬዝዳቱ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከፍተኛ ባለስልጣናት በአንድ ጋዜጣ የወጣ ዘገባ በደለን፣ ጎዳን፣ ስማችንን አጠፋው ብለው ሲያስቡ ወደ ፍ/ቤት አይሄዱም። ፕሬስ ካውንስሉ ጋ ሄደው መርምሮ የሥነ-ምግባር ጉድለት ካለበት ቅጣት ይወስናል። ‹‹ለሦስት ወር አትዘግብ›› ሊል ይችላል። ፕሬስ ካውንስል ይሄንን የሚያደርግ ትልቅ ኃላፊነት የተሸከመ ድርጅት ነው። ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ካውንስል አደራጅ ሊቀ-መንበር ሚሚ ስብሐቱ ትባላለች። የምናወራው ስለ ስነ-ምግባር ነው፤ ከግለሰቧ ጋር ምንም ችግር የለብኝም። አንዳንዴ ትራንስፖርት ውስጥ ድምጿን በሬድዮ ከመስማት ውጪ ስለእሷ ብዙም መረጃ የለኝም። በአካልም ተገናኝተን አናውቅም። ነገር ግን ከአሜሪካ ሬድዮ ጣቢያ በሥነ-ምግባር ጉድለት የተባረረች፣ በ1998 ዓ.ም. ጋዜጠኞች ሲታሰሩ ‹‹እነዚህ ጋዜጠኞች ሞት ሊፈረድባቸው ይገባል›› ብላ ስትከራከር የነበረች፣ ጋዜጠኞች በተሰደዱ ቁጥር ‹‹ከሥረው ነው፣ አሸባሪዎች ናቸው›› የምትል፣ ፍትሕ ሲዘጋም ‹‹መንግስት ዘገየ›› ያለች ሴትዮ ሌላውን ጋዜጠኛ እንዴት አድርጋ እንደ ምታስተምር እግዚአብሔር ነው የሚ ያውቀው።

እንደዚህ አይነት ካውንስልን ስለማታምነው እና ነፃነት እንደሌለው ስለምታውቅ አብረኸው ልትሠራ አትችልም። በሙሉ መልዕክተኞች ናቸው። በአብዛኛው የመንግሥት አስፈጻሚዎች ናቸው። እነሱ ነፃ መሆን ቢፈልጉም ኢሕአዴግ በባህሪው ምንም ነገር ነፃ እንዲሆን አይፈልግም። እነዚህ ሠዎች ደግሞ የሥርዓቱ ቀንደኛ አገልጋዮች እና ዋና ተጠሪዎች ናቸው። ስለዚህ ከእነዚህ ጋር ልትሠራ አትችልም። ይሄ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ አጋርነት እንዳይኖር ያደረገው።

ከመንግሥት ትዕግስት አልባነት አንፃር ብዙዎች ጋዜጣ ለመጀመር ፈቃድ ማግኘት ባልቻሉበት አገር እናንተ ሦስት ‹‹መለያ›› ቀያይራችሁ [አዲስ ታይምስ እና ልዕልና ላይ የቆያችሁት ለአጭር ጊዜም ቢሆን] ስትጫወቱ መታየቱ ጥርጣሬ የጫረባቸው ወገኖች አሉ። ‹‹የኢሕአዴግ አንድ ክንፍ “ነጻ ሚዲያ አለ” ለማስባል ከጀርባቸው ሆኖ ያግዛቸዋል›› የሚሉ ድምጾችም ይሰማሉና ምን ትላለህ?

እንዲህ እያሉ የሚያራግቡት ሕሊናቸው በጥቅም የታወሩ ሠዎች ናቸው። ምክንያቱም እኛ በ‹‹አዲስ ታይምስ››ም ሆነ በ‹‹ልዕልና›› ስንመለስ በሥርዓቱ (በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን) ፈቃድ አይደለም። ሁለቱንም ከባለቤቶቹ ጋር ተደራድረን ገዝተን ወደ እኛ ከዞረ በኋላ የአንድ ዓመት ፈቃድ ስለነበራቸው በሕጉ መሠረት ለብሮድካስት ባለስልጣን ያደረግነው ‹‹ዋና አዘጋጅ እና ሥራ አስኪያጅ መቀየራችንን ማስታወቅ እንጂ ማስፈቀድ አይደለም። በማስታወቅ እና በማስፈቀድ መሀከል ሰፊ ድልድይ አለ።

ስታሳውቁ እናንተ መሆናችሁን ሲረዱ እንዳትንቀሳቀሱ እንዴት አላደረጓችሁም?

ያው ዘጉት እኮ። ከታኅሳስ 30 በኋላ የሥራው ፈቃድ ስለሚቃጠል የአዲስ ታይምስን ፈቃድ ልናድስ ስንል ‹‹ሥም ያዞራችሁት በሕገ-ወጥ መንገድ ስለሆነ አናድስም›› ብለው ዘጉት። ልዕልናንም የጀመርነው አዲስ ፈቃድ አውጥተን አይደለም በውልና ማስረጃ ማድረግ የሚገባንን ከጨረስን በኋላ ጋዜጣው ነገ ሊወጣ እንደዛሬ ባለቀ ሰዓት ዋና አዘጋጅ መቀየራችንን በደብዳቤ አሳወቅን። ሦስት ዕትም ከሄድን በኋላ ብሮድካስት ላይ ያሉ የሥርዓቱ ሎሌዎች ‹‹በሕገ ወጥ መንገድ ነው ጋዜጣውን ወደ እናንተ ያዞራችሁት›› ብለው ደብዳቤ ጻፉልን። በጣም የሚገርመው ግን ከልዕልና ባለቤት ጋር ስምምነት ነው እንጂ የፈጸምነው ገና ሥም ወደ እኛ አልዞረም ነበር። አራተኛውን ዕትም ካወጣን በኋላ በንግድ ሚኒስቴር በኩል ‹‹የንግድ ፈቃዳችሁ ተሰርዟል›› የሚል ደብዳቤ ላኩልን።

እውነታው ይህ ስለሆነ የሚወራውን በማስተባበል ራሴን አላደክምም። እንዲህ ብለው የሚጽፉትም እውነታውን ያውቁታል። በሦስቱም የኅትመት ውጤቶች ላይ እኛ የምናነሳቸው ርዕሰ ጉዳዮች የእውነት ሥርዓቱ የሚፈልጋቸው ወይም ለማስተንፈሻነት የሚጠቀምባቸው ናቸው? አንባቢ ስለሚፈርድ ይህን በማስተባበል ጉልበቴን አላደክምም።

በነገራችን ላይ… ልዕልና ላይ ባሰፈርካቸው መጣጥፎች ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን  አንቱታን ትተህ ሁለተኛ መደብ ነጠላ ስም በመጠቀም ‹‹አንተ›› እያልክ ትገልፃቸው ነበር። ይህ ተገቢ ነው?

ተሳስቼ ሳይሆን ሆን ብዬ ያደረግኩት ነው። ፍትሕ ላይ እያለን ሥርዓቱ በተወሰነ መልኩ ሕግ እንደሚያከብር የማስመሰል አካሄድ ስለነበረው ለዚያች እውቅና ሰጥቼ ‹‹አንቱ›› እላቸው ነበር። አሁን የተፈጠረው ግን ጭልጥ ያለ አፈና እና ጉልበተኛነት ስለሆነ እነዚህን ሰዎች አንቱ ማለቱ አግባብ አይደለም ብዬ ስለማስብ ነው። የምታከብረው እኮ የሚከበርን ሠው ነው። አፋኝ፣ ሕገ ወጥና ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱ ጭፍን አምባገነን ስለሆኑ ‹‹አንተ›› ከማለት ባለፈ በአፋጣኝ ከሥልጣናቸው እንዲለቁም እፈልጋለሁ። ‹‹ከሥልጣንህ ውረድ›› እንጂ ‹‹ከሥልጣንዎ ይውረዱ›› አትልም። ጋዳፊ፣ ሙባረክ ‹‹ውረድ›› ነው የተባሉት።

ጋዜጠኛ ከሥልጣን ሲወርዱ ይዘግባል እንጂ ‹‹ከሥልጣን ውረድ›› ማለት ይገባዋል?

ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ የጋዜጠኝነትን መርህ አክብረህ የምትሠራበት ስላልሆነ ነው። ጋዜጠኝነት መታየት ያለበት ከአውዱ አኳያ ነው ብዬ አስባለሁ።

ባለፈው ነሐሴ 2004 ዓ.ም. በጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ላይ አንተ፣ አቶ አማረ አረጋዊ [የሪፖርተር ጋዜጣ ከፍተኛ ባለድርሻ እና ሥራ አስኪያጅ] እና ዶ/ር መሠረት ቸኮል [በዊስኮንሲን ሪቨር ፎልስ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ፕሮፌሰር የነበሩና በሕዳር/2005 ዓ.ም. በጉበት ካንሰር ሕይወታቸው ያለፈ] ለቃለ ምልልስ ቀርባችሁ ነበር። አቶ አማረ ‹‹ሚዲያ ካውንስሉ የፕሬስ ነፃነትን እየታገለ ነው መጓዝ ያለበት›› ሲሉ አንተ እና ዶ/ር መሠረት ደግሞ ‹‹መጀመሪያ የፕሬስ ነፃነቱ መቅደም አለበት›› ስትሉ ነበር።

ጋዜጠኞች ናችሁና ብዙ መረጃ አላችሁ። ለረዥም ጊዜያት አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ ‹‹አገሪቱ ላይ የቀሩት ሁለት ነፃ ጋዜጦች ናቸው›› ይሉ ነበር። አውራምባ ታይምስ ከተዘጋች በኋላ ደግሞ አንድ ጋዜጣ ብቻ መቅረቱን ተናግረዋል። አሁን ደግሞ ‹‹የቀረችው አንድ ጋዜጣ ተዘጋች›› ብለዋል፤ ፍትሕን። ስለዚህ መጀመሪያ የሚያስፈልገው ሚዲያው ነው። ካውንስሉ የሚያስፈልገው ሚዲያ ሲኖር ነው፤ ሚዲያ ከሌለ ደግሞ ካውንስሉ ምንም አይሠራም። ሚዲያ የሚኖረው ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሲረጋገጥ በመሆኑ፣ መጀመሪያ መታገል ያለብን ሚዲያ እንዲኖር ነው። እናንተ የጋዜጣ ፍቃድ ተከልክላችኋል። ታዲያ እንዴት ስለ ካውንስል ይወራል? ማውራት ያለብን [ቆጣ ብሎ] ፍቃድ ስለ መከልከል/አለመከልከል ነው። ፍቃድ ተከልክለህ ካውንስሉ ምን ያደርግልሀል? ካውንስሉ የሚያያዘው ከሥራ ጋር ነው፤ ስትሠራ፣ ስታጠፋ ካውንስሉ ያስፈልጋል። ‹‹የዐይንህ ቀለም አላማረኝም›› ተብለህ ፍቃድ በምትከለከልበት አገር ላይ እንዴት ስለ ካውንስል እናወራለን? ካውንስሉ አያስፈልግም ሳይሆን በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣ ነው። መጀመሪያ ሚዲያው በእግሩ መቆም አለበት። የእነ አማረ አረጋዊና የእነ ሚሚ ስብሐቱ የሚዲያ ካውንስል ዕቅድ ዝም ብሎ ተራ ቅዠት ነው። ዝም ብለው ድርጅት አቋቋምን ብለው መንፏለል ካልሆነ በስተቀር ግብዝነት ነው። እኔ አማረ አረጋዊን ከሚሚ ስብሐቱ ጋር አንድ ላይ ደርቤ አላየውም። አማረ የራሱ ፍላጎት ቢኖረውም፣ የራሱ ኤዲቶሪያል ነፃነት ያለው ጋዜጠኛ አለው። ሚሚን ግን እንደ ጋዜጠኛ ልወስዳት አልችልም፤ ጋዜጠኛ አይደለችምም። ‹‹ጋዜጠኛ አይደለሽም፤ አትችይም›› ተብላ የተባረረች ነች፤ እየሠራች ያለውንም የምታዩት ነገር ነው። ‹‹ካውንስል መሠረትን›› ብለው በየመድረኩ ለታይታ ለመቅረብ ካልሆነ በስተቀር የትም ሊደርስ እንደማይችል ከእኔ የበለጠ እነሱ ያውቁታል።

በአንድ ወቅት ላይ ከአንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ጋር ፖርላማ ስብሰባ ላይ ተገናኝተን ስናወራ ‹‹ተመስገንን አስረን አናጀግነውም›› ብለውኝ የነበረ ቢሆንም ለስድስት ቀንም ቢሆን መታሰርህ አልቀረም። ታስረህ ‹‹መጀገን››፣ መሸለም እንደምትፈልግ፣ ለመታሠር ጉጉ እንደሆንክ የሚደመጡ አስተያየቶች አሉ። ምን መልስ አለህ?

ይሄ እንደ ሰውየው የማሰብ መጠን ይወሰናል። ሲ.ፒ.ጄ. ከሸለማቸው ሰዎች ውስጥ [ከዳዊት ውጪ ያሉት] አብዛኛዎቹ ታስረው የማያውቁ ናቸው፣ እስር ቤት ሆነው የተሸለሙ በጣም ጥቂቶች ናቸው። በሲ.ፒ.ጄ ለመሸለም ትልቁ መስፈርቱ በአምባገነን መንግሥት ውስጥ ሳትሸሽ፣ በድፍረት መሥራት ብቻ ነው እንጂ ‹‹መታሰር›› የሚል ቅድመ ሁኔታ የለውም። ምናልባት መታሰርን እንደ ሁለተኛ መስፈርት ሊወስዱት ይችላሉ። አቶ ሽመልስ ከማል አንተ [ኤልያስ] በጥያቄህ ላይ እንዳነሳኸው ሁሉ እኔንም ቢሯቸው ጠርተው ‹‹የዳዊት ሽልማት አማልሎህ ከሆነ በጣም ተሳሰተሃል›› ብለውኛል። ንግግራቸው እና ከንግግራቸው ጀርባ ያለው እውነታ የሚያሳየው ‹‹አሳሪ፣ ጨፍላቂ፣ ደምሳሽ ነን›› የሚል ነው እንጂ አንድ ጋዜጠኛን ጠርተህ ‹‹ለመታሰር ፈልገሃል›› የምትልበት ምንም ምክንያት የለም። ጋዜጠኛ ካጠፋ መታሰር አለበት። ወንጀል የሠራ ሰው መመከር ሳይሆን መታሰር ነው ያለበት። የአቶ ሽመልስ ንግግር የሚገልጸው እሳቸው የሚያገለግሉት ሥርዓት ምን ያህል ጨቋኝ፣ አፋኝና የነፃውን ፕሬስ ምኅዳር አጥባቢ መሆኑን ነው።

… ታስሬ ጀግና መሆን የምፈልገው መቼ ስፈታ ነው? ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ውሰደው! 18 ዓመት ተፈርዶበታል። ከእነዚህ ዓመታት በኋላ 60 ዓመት ሲሆነው [አሁን አርባ ሁለት ዓመቱ ነው] ወጥቶ የሚያገኘውን የጀግንነት ክብር ፈልጎ ይታሰራል? ‹‹የማገኘው ክብር አለ›› ብለህ መታሰር፣ ሕይወትህን ልትበላበት የምትችለው ቁማር ነው። አሁን 34 ዓመቴ ነው። 15 ዓመት ቢፈረድብኝ ከእስር ቤት የምወጣው በ50 ዓመቴ ነው። በዚያ 15 ዓመታት ውስጥ የማጣቸው ብዙ ነገሮች አሉ። የማገኘው ክብር ምንድን ነው? ሁሉንም ነገር ከዜሮና ከአዲስ ነው የምትጀምረው። አቶ ሽመልስ የሚያንፀባርቁት ነፍሳቸውን ይማረውና የሟች ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ጉልበታም ሐሳብ ነው። ይሄ የአምባገነኖች ባሕሪ ነው።

(ዘ-ሐበሻ ድረገጽን በየቀኑ በማንበብ ራስዎን በመረጃ ከሰው እኩል ያድርጉ)
በቃሊቲ የስድስት ቀን አክራሞትህ እነማንን አገኘህ? ምንስ ተማርክ?

የታሰርኩት የቀድሞ መንግሥት ባለሥልጣናት ታስረው በነበረበት ‹‹ዞን አራት›› ነው። ዋና ዋናዎቹ ተፈትተዋል፣ ጥቂት ሚኒስትሮች ነበሩ። ለምሳሌ የኢኮኖሚ እና የጡረታ ዋስትና ሚኒስትር የነበሩት ኮሚሽነር ገሠሠ ወልደኪዳን ነበሩ። ሻለቃ መላኩ ተፈራ [የጎንደር አስተዳዳሪ] እነ ሻምበል በጋሻው አታላይ [የወሎ አስተዳዳሪ] ነበሩ። በርካታ እስረኞች አሉ። ዶ/ር ተስፋዬ ብሩ፣ የአዋሽ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ለይኩን ነበሩ፤ ብዙ ብትቆይ ከእነሱ ብዙ ትማራለህ።

የቀድሞ የቤንሻንጉል ጉምዝ ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ያረጋል አይሸሹምን አግኝቻቸዋለሁ። ከእሳቸው የምትማረው ነገር አለ ብዬ አላስብም፤ ሙስናን ካልተማርክ በስተቀር። [ሳቁ መጣበት] ከብዙዎቹ ጋር አውርተናል፤ ግን ለጊዜው ባልገልጻቸው ጥሩ ነው። የእስር ዘመንና ሰቆቃቸውን ማበርታት ይሆናል። ብዙዎቹ ከእኔ ጋር የሚያወሩት ስለ ዕድርና ዕቁብ አይደለም። አስቀድመው የፖለቲካ ጋዜጣ አዘጋጅ መሆኔን ስላወቁ፣ ያወጋነው ፖለቲካዊ ወሬ ስለሆነ፣ ይሄንን መናገር አስቸጋሪ ነው።

‹‹ለምን እንዳሰሩኝ፣ ለምን እንደፈቱኝ›› አላውቅም ብለህ ከወጣህ በኋላ ጽፈሀል። ዞን 4 ተስማምቶህ ነበር እንዴ?

[ከሳቀ በኋላ] አይደለም። በጥፊ አጩዬህ ይቅርታ መጠየቅ የለብኝም። ሲጀመር መማታት የለብኝም። ዝም ብለህ ማንንም ሰው እየጠራህ፣ ከቤቱ እየወሰድክ፣ እስር ቤት እየከተትክ፣ የምትፈታበት ሁኔታ መቆም አለበት። መብቴ ሊከበር ይገባል። የተለቀቅኩት ስድስት ቀን ያለአግባብ ታስረሀል ተብዬ አይደል? ለዚህ ካሳ ማግኘት ነበረብኝ፤ መንግሥትም በይፋ ይቅርታ ሊጠይቀኝ ይገባ ነበር።

ዳግመኛ ወደ እስር ቤት የምትመለስ አይመስልህም? [ይህ ጥያቄ የቀረበለት በድጋሚ በዚህ ጉዳይ ከመከሰሱ በፊት ነበር።]

በዚህ ጉዳይ ተመልሼ እገባለሁ ብዬ አላስብም።

በድህረ መለስ ኢትዮጵያ ምን ገጽታ የሚኖራት ይመስልሀል? ለኢትዮጵያ የሚጠቅማት ማን እና ምንድን ነው ብለህስ ታስባለህ?

ከፋፍለን እንየው፣ መጀመሪያ ከእውነታው እንነሣ። ስገምት ‹‹ድህረ-መለስ›› አስቸጋሪ ሁኔታ ይኖረዋል ብዬ አስባለሁ። አራቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሥልጣን ሲይዙ ባልተመጣጠነ ጉልበት ነው። ሕወሃት አስኳል ነው። ወሳኝ ወሳኝ ነገሮችን ይዟል። የመሪነት ባሕሪ አለው። ልክ በደርግ ጊዜ ስትመጣ መፈክሩ ሁሉ ‹‹በጓድ መንግሥቱ ኃይለማርያም ማዕከላዊነቱ ኢሠፓን እንመሠርታለን…›› ነበር የሚሉት። ኢሕአዴግም ሲመሠረት በሕወሃት ማዕከላዊነት ነው። ከ1993 ከሕወሃት መሰንጠቅ በኋላ ግለሰብ (አቶ መለስ) ማዕከላዊ ሆነዋል። ይሄ ሁኔታ ጉዳቱን በግልጽ ያመጣዋል። በተለይ ደግሞ አማራንና ኦሮሞን የሚወክሉ ሁለት ድርጅቶች አሉ። ኦሕዴድ እና ብአዴን ወክለውት ወደ ግንባር የመጡት የሕዝብ ቁጥር አለ። ከፍተኛ ሥልጣን ይዞ የነበረው ሕወሃት ይዞ የመጣው የሕዝብ ቁጥር አለው። ምናልባት አሁን የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ ‹‹በቁመታችን ልክ ግንባሩ (ኢሕአዴግ) ውስጥ ቦታ ልናገኝ ይገባል።›› የሚል ጥያቄ ያነሣሉ ብዬ አስባለሁ። አሁን የሥልጣን ትግል (Power Struggle) ይፈጠራልም፤ ተፈጥሯልም። በተለይ ደግሞ በትግሉ ላይ ተቀራራቢ ዕድሜ ያስቆጠሩ ፓርቲዎች አሉ፤ ሕወሃትና ብአዴን። ኦሕዴድ ከ1981፣ ደኢሕዴን ከ1983 ወዲህ ስለሆኑ፣ በዚሁ ልክ ነው ግንባሩ ውስጥም የእኔነት ስሜትና የበላይነት ቁመት የሚኖራቸው። አሁን ያለው የድህረ መለስ ክፍፍል በብአዴንና በሕወሃት መካከል ከፍተኛ ትንቅንቅ ፈጥሯል። ይሄ ትንቅንቅ የቱ ጋር ሄዶ ሄዶ ያቆማል ሌላ ጉዳይ ነው። ወይ ደግሞ ትንቅንቁ ወደ አደባባይ በወጣ ጊዜ የሥርዓቱ መጨረሻ ይሆናል። ጉልበት መለካካቱ አይቀርም።

በምኞት ደረጃ የምትለኝ ከሆነ፣ መንግሥት ብሔራዊ ዕርቅ መፍጠር አለበት። ለደርግ ባለሥልጣናት የተሰጠው ምሕረት ጥሩ ነው። ኢሕአዴግ ብዙውን ጊዜ ፈልጎ፣ የተወሰነ ጊዜ ደግሞ በስሕተት በርካታ ዜጎችን አሰቀይሟል፣ አስኮርፏል፣ በድሏል፣ ለስደት ዳርጓል። እነዚያን ለማምጣት ዕርቁ ያስፈልጋል። ከፖለቲካ ፓርቲዎች [ኦነግ እና ግንቦት 7ን ጨምሮ] ጋር ምሕረት ነግሦ፣ ‹‹አሸባሪ›› ለሚሉት ምሕረት አውርደው፣ የምርጫ ጊዜ ከመድረሱ በፊት ሁሉም ፓርቲዎች ፓርላማውን አፍርሠው፣ በእኩል ምኅዳር፣ በእኩል የሚዲያ አጠቃቀም የሚወዳደሩበትን ዕድል መንግሥት ፈጥሮ፣ ምርጫ እንዲደረግ ቢያደርግ የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ።

ስለ አንገት ልብስዋ እናውራ። ፍትሕ ላይ ፎቶህን ለጥፈህ መጻፍ ከጀመርክበት ጊዜ ጀምሮ አንገትህ ላይ የምትታየው የአንገት ልብስ (Scarf ) በተለያየ አጋጣሚ ስናገኝህም ወልቃ ተመልክተን አናውቅም። አንተ ብቻ ሳትሆን ባልደረቦችህና የፍትሕ ቤተሰቦችም የአንገት ልብስ አይለያቸውም። የአንገት ልብስዋ መልዕክት ምንድን ነው?

ሻርፑ ራሱን የቻለ መልዕክት አለው።

ልትነግረን ትችላለህ?

ጊዜው ገና በመሆኑ አሁን ልናገረው አልችልም።

‹‹የአንገት ልብስ አብዮት›› የማስነሳት ዓላማ አላችሁ?

በአገራችን ላይ ማንም የማይፈቅድልን፣ ማንም የማይነሳን የፈለግነውን ሕጋዊ እንቅስቃሴ የማድረግ ሙሉ መብት አለን። ይሄ ጥያቄ ከላይኛው ጋር ስለሚያያዝ ለጥቂት ወራት ቢቆይ የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን፣ የአንገት ልብሱ ለብርድ ወይም ለጌጥ የሚደረግ አለመሆኑን መናገር እችላለሁ።

ከዚህ በኋላ በሌላ የፕሬስ ውጤት ትመለሳለህ?

CNNን እንደ ሞዴል ወስደን ከሰዎች ጋር በሽርክና ግዙፍ የሆነ የኦን ላይን ሚዲያ (ድረ-ገጽ) ለመመሥረት ብዙ መንገዶችን ተጉዘናል። አራት የኢትዮጵያ ክልሎች ላይ ቢሮዎች ይኖሩናል። የምንመለሰው በዚህ መንገድ ነው።

ከመሰናበታችን በፊት በኪስህ ስንት ብር እንደያዝክ ልታሳየን ትችላለህ?

አደጋ ይደርስብኛል፣ አንድ ነገር ያጋጥመኛል ብዬ ስለማስብ ከአምስት ሺህ ብር በታች አልይዝም። ብሩን ላሳያችሁ እችላለሁ፤ ግን አንድ ነገር ላይ መግባባት አለብን። [ሳቅ] ‹‹አበድረን›› የሚል ነገር አልፈልግም። [ስድስት ሺህ አራት መቶ (6,400) ብር የታሰረ፣ ሦስት ሺህ (3,000) ብር ያልታሰረ መያዙን ፊታችን ቆጥሮ አረጋግጠናል] የሥርዓቱ ባሕሪ በፈጠረው የተለያዩ ምክንያቶች ከቤቴ ስወጣ ቀና ነገር ይገጥመኛል ብዬ አስቤ አላውቅም። በተወሰነ መልኩ ገንዘብ ያስፈልጋል ብዬ አስባለሁ።

ጨርሰናል። ስለ አብሮ ቆይታችን ከልብ እናመሰግናለን። መልካሙን ሁሉ እንመኝልሀለን።

እኔም አመሰግናለሁ። በእውነቱ ብዙ ጊዜ መናገር የማልፈልጋቸውን ነገሮች እንድናገር ስትገፋፉኝ ስታስገድዱኝ ነበር፤ አስገድዳችሁኛልም። ‹‹Hard Talk›› እንደማለት ነው። ቢሆንም እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ጨለማ በነገሠባቸው አገራት፣ ሕዝብ እንዲያውቅ የመረጣችሁበት መንገድ በእጅጉ የሚያስመሰግን እና ፈር ቀዳጅ ነው ብዬ አስባለሁ።

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=5649

posted by Tseday Getachew

 

Post Navigation

%d bloggers like this: