Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

Archive for the month “February, 2013”

ምርጫው ተጠናቋል

በከፍተኛ ጉጉት ሲተበቅ የነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ በአሁኑ ሰዓት ተጠናቋ ፡፡ ከተመዘገቡት 870 መራጮች መካከል ከ800 በላይ ያህሎቹ  ድምጻቸውን መስጠታቸው ታውቋል ፡፡  ከአሁን በኋላ የሚቀረው ሂደት የካርዱን ብዛትና የመራቹን ቁጥር ማነጻጸር ፤ ድምጹን ቆጥሮ ቃለ ጉባኤ መፈራረም ፤ የመገናኛ ብዙሃንን በመጥራት ማን ምን ያህል እንዳገኝ መግለጽ እና ቀጣይ ፓትርያርኩን የማወጅ ስራ ብቻ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
 
 
ስድስተኛው ፓትርያርክ ብጹእ አቡነ…………… ሆነዋል የሚለውን ድምጽ እንጠብቃለን፡፡
 
 
posted by Tseday Getachew
Advertisements

ለ13 ዓመታት ገለልተኛ ሆና የቆየችው የኖርዝ ካሎራይና ቤተ ክርስቲያን ህጋዊውን ሲኖዶስ ተቀላቀለች

Ethiopian-Orthodox-Church-Holy-Synod

… በእኛ ዘመንም ቤተ ክርስቲያን በሶስት ጎራ የተመደበችበት ዘመን ነው። ይህን ክፍፍል ወደ አንድነት ለማምጣት የመካነብርሃን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የራሷን ድርሻ ተወጥታለች፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ሕግና ስርዓትም መጠበቅ ቅድሚያ ትሰጥታለች። ስለዚህም ስላሴን እናመሰግናለን። በሻርለት ኖርዝ ካሎራይና የምትገኘው መካነ ብርሃን ቅድስት ስላሴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 13 ዓመታት በገለልተኛነት መኖሯዋ የታወሳል። በገለልተኝነት እንድትቆይ ያስገደዳትም ዋናው ምክንያት ለአለፉት ሃያ አመታት ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ማዕከል በማድረግ የተፈጠረው ልዩነት ተወግዶ በተዋህዶ ይመለሳል በማለት ነበር። በተለይ ደግሞ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዘንድ ታላቅ ተስፋ የተጣለበትና ለአለፉት ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ሲካሄድ የቆዬው የሰላም ድርድር ከፍጻሜ ደርሶ ለማየት ምኞታችን ፍጹም ነበር። ሆኖም ከዛሬ 21 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያን የተቆጣጠረው አካል በቤተክርስቲያናችን ላይ ያስገባውን እጅ መሰብሰብ ባለመቻሉና ለፍላጎቱም መጠቀሚያ የሚሆኑ ለግል ጥቅምና ስልጣን እንጂ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት ደንታ የሌላቸውን አንዳንድ አባቶች ከጎኑ በማሰለፍ ብዙ የተደከመበትና ተስፋ የተጣለበት የሰላም ድርድር ያለውጤት እንዲቋጭ አድርጓል። ስለዚህ የመካነ ብርሃን ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያናችን በገለልተኛነት መቆየት የታሰበውን አንድነት የሚያመጣ ሳይሆን ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሳተ አካሄድ በማጠናከር ዕምነታችንንና የቤተ ክርስቲያን ስርዓታችን የሚያፋልስ በመሆኑ ለማስተካከል ተገዳለች። ይቀጥላል…

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/6328

posted by Tseday Getachew

 

የሕወሐት ፍጥጫ ቀጥሏል (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

 

“አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው” እነ ስብሃት
“የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን” እነ አባይና አዜብ

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም « መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ የለበትም?» ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም» የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።

በፓርቲው በተለኮሰው ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ፍጥጫ ካድሬው ለሁለት ተከፍሎ ሲነታረክ መሰንበቱን ምንጮች ጠቁመዋል። በፓርቲው አባላት « አደገኛ» የተባለውን ይህን ፍጥጫ መሰረት በማድረግ በቴውድሮስ አድሃኖምና ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የሚመራ ቡድን ራሱን « የአስታራቂ ሽማግሌዎች ቡድን» በሚል ሰይሞ ባለፉት ቀናት ሲነቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀዋል። ሆኖም ሁለቱን ጎራዎች አቀራርቦ ለማነጋገርና ለማስማማት የተጀመረው ጥረት በሁለቱም በኩል በሚታየው አክራሪ አቋም ምክንያት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እንደማይታይ ምንጮቹ አስታውቀዋል። አሁንም ድርድሩ መቀጠሉን ምንጮቹ አልሸሸጉም።

የሕወሐት ሕልውና አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት በአሁኑ ወቅት በሌላ ጐራ የተነሱ ወጣት የፓርቲው ካድሬዎች ባነሱት ጥያቄ ፥ ሁሉም አንጋፋ አመራሮች ከድርጅቱ እንዲለቁ ጥያቄ ማቅረባቸውንና ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ሕወሐት ሊፈርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ጭምር መስጠታቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።

በተያያዘም « ጉባኤ ይጠራ» በሚል በካድሬዎች የቀረበውን ጥሪ እነ አባይ ወልዱና አዜብ ያሉበት ቡድን ውድቅ እንዳደረገው ታውቋል። አባይና አዜብ የሚመሩት እንዲሁም ትርፉ ኪዳነማሪያም፣ ሃድሽ ዘነበ፣ አለም ገ/ዋህድ፣ በየነ ምክሩ፣ ተክለወይኒ አሰፋና ሳሞራ የኑስ የተካተቱበት ቡድን በጉባኤው አሸናፊ ሆነው እንደማይወጡ ከወዲሁ በማመናቸውና በነስብሃት በኩል ከፍተኛ ሃይል እንደተደራጀባቸው ጠንቅቀው ስለተረዱ ነው ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ሳሞራ በመከላከያ እጣ ፈንታቸው ተመሳሳይ መሆኑን በማመናቸው ከነአዜብ ጋር ተሰልፈው እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የበላይነትን እየያዘ ነው የሚባለውና በስብሃት የተደራጀው እንዲሁም በደብረፂዮን የሚመራው ቡድን አብዛኛውን የማ/ኮሚቴ አመራር በዙሪያው ያሰባሰበ ሲሆን ከነዚህም፥ አዲስአለም ባሌማ፣ አርከበ እቁባይ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ፈትለወርቅ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ አባዲ ዘሙ፣ ሃ/ኪሮስ ገሰሰ፣ ተ/ብርሃን…በዋንኛነት እንደሚገኙበት ምንጮቹ አመልክተዋል። የሽማግሌው ቡድን ስብስባ እንደቀጠለ ተጠቁሞዋል።

 
posted by Tseday Getachew
 

 

ሞት በምልጃ፤ የበረሃ ጣዕር!

ማስለቀቂያ ካልተከፈለ – ኩላሊት ለገበያ
 

“አቧራ ይጨሳል። ከዚያ ያፈኑትን ይዘው ይሰወራሉ” አስደንጋጩ ታሪክ ውስጥ ያለው ስዕላዊ ገለጻ ነው። አንድ ወቅት አዲስ አበባ የህጻናት ሌቦች ተበራክተው ነበር። በወቅቱ በርዳታ ስም ተመዝግበው የፈጣሪ ስም እየጠሩ ህጻናትን በመነገድ የከበሩ ወረበሎች በደንብ የተደራጁና የሚቀናቀናቸውን የማስወገድ አቅም ስለነበራቸው “አቧራው ጨሰ” የሚል ስያሜ የኮድ ስም ተሰጥቷቸው ነበር። አሁንም አሉ። “ህጻን እናሳድጋለን” እያሉ በዘረጉት ሰንሰለት የህጻናትን ደም የሚጠጡ “አንቱ” የተባሉ ሰዎች!! የውጪ አገር ዜጎች ጭምር …

በሱዳን ሰዎችን በማፈን ሲና በረሃ የሚሰውሯቸው ራሻይዳዎች የተደራጁ ናቸው። ከአረብ ምድር የፈለሱ ናቸው የሚባልላቸው እነዚህ ጎሣዎች በሱዳንና በኤርትራ የሚገኙ ሲሆን በተለይ በኤርትራ ያሉቱ ከዘጠኙ ጎሣዎች መካከል የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ አኗኗራቸው የዘላን በመሆኑ ከኤርትራ መንግሥት ቁጥጥር ውጪ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡ እነዚህ ጎሣዎች እጅግ አሰቃቂ የሆነ የአፈናና የጭከና ድርጊት ሲፈጽሙ በወጉ ታጥቀውና ዘመናዊ ተሽከርካሪ በመያዝ ነው። የሚታፈነውን ሰው ከተቆጣጠሩ በኋላ አዋራ ይነሳል። የሚከንፉበት ተሽከርካሪ አሸዋውን ተርትሮት ሲወረወር የሚነሳው ጭስ ሲበተን እነሱ የሉም። ቀሪው ተግባር “ሚስትህን፣ ወንድምህን፣ እህትሽን፣ ዘመድሽን ለሚያርዱ የሰውነት ክፍል ሌቦች አሳልፈን ሳንሰጥ ዶላር ክፈል ወይም ክፈይ” የሚለው ድርድር ነው። ይህ ድራማ መሰል ንግድ ሲከናወን ተገደው ይሁን የንግዱ ተባባሪ በመሆን በውል በማይታወቅ ሁኔታ የድርድሩ አስተርጓሚ ሆነው የሚሰሩት ኤርትራዊያን እንደሆኑ ተሰምቷል። ኢትዮጵያዊያኖችም አሉበት ይባላል። ማንም ይስራው ማን ድርጊቱ አሰቃቂ መሆኑ ብዙዎችን አስለቅሷል። አስጨንቋል።

በደላሎች እስራኤል ለመግባት ጉዞ ከጀመሩት ወገኖች መካከል ስንቶቹ በሲና በረሃ ሟምተው እንደቀሩ መረጃ የለም። ከሱዳን ምድር ወጥተው ግብጽ በመሻገር ሲና በረሃ እንደ ከብት ተበልተው የሚጣሉት ወገኖች ስቃይ ለሰሚው ግራ ነው። ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው አሰቃቂ መከራ ከቀን ቀን እየተባባሰ ነው። አሰቃቂ ዜናዎች መስማት ለየእለቱ የሚያስፈልገን መሰረታዊ ጉዳይ እስኪመስል ተለመዷል። ይህ አሳሳቢ ጉዳይ “እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል” የሚለው የሁሉም ወገን “ዳር ቋሚዎች” ጥያቄ ነው።

“ለጆሮ የሚሰለች ነው፣ እርዳታ መስጠት ታከተን፣ የሚል መልስ የሚሰጡ አጋጥመውኛል። ድርጊቱ ተደጋግሞ ለጆሮ የሚያሰለች ደረጃ እስኪደርስ እነዚህ ወገኖች የት ነበሩ? ቢያንስ ሌሎች ላይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይደርስ ምን ሰሩ? በውጪ አገር ያለን ወገኖች የሚረዳውንና የማይረዳውን መለየት የተሳነን ይመስለኛል” በማለት በሚኔሶታ የሚኖሩት ወ/ሮ ሰብለ አስተያየታቸውንና ተማጽኗቸውን ያሰማሉ።

የካቲት 3፤2005 (2/10/2013) የቪኦኤ አማርኛ ክፍለ ጊዜ ያሰማው እረፍት የሚነሳ ዜና እስካሁን አልተቋጨም። ሱዳን ሸገራብ በሚባለው ሰፊ የስደተኞች ጣቢያ ከባለቤታቸውና ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩ ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ ጥር 22 ቀን 2005 ዓ ም ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም ከቤታቸው ይወጣሉ። በካምፕ ውስጥ ከሚገኘው ቤታቸው ወጥተው በግምት ሰላሳ ሜትር ሳይርቁ ታፈኑ።

ባለቤታቸው አቶ መልካሙ ባዬ ለቪኦኤ እንደተናገሩት አፋኞቹ ራሻይዳዎች ናቸው። ራሻይዳ የቆዳቸው ቀለም ጠየም ያለ የሱዳን፣ የኤርትራና የግብጽ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ ቀደም ሲል ከሶስት እስከ አራት ሺህ ዶላር እየተቀበሉ በደላላ አማካይነት ስደተኞችን በሲና በረሃ ወደ ግብጽ ያሻግሩ ነበር። እስራኤል በሲና በረሃ ወደ ድንበሯን ዘልቀው የሚገቡበትን የስውር መንገድ ስትዘጋው ራሻይዳዎቹ የገቢ ምንጫቸው ተዘጋ። ገንዘብ የለመዱት ወንበዴዎች የንግዱ ስልት ቀየሩና ሰው ማፈን ጀመሩ። አፈናውንም ከሚያካሂዱባቸው መንገዶች ጥቂቶቹ ድንበር አቋርጠው የሚጓዙትን አድፍጠው በመያዝ፣ ስደተኞችን ከስደተኛ ካምፕ አፍኖ በመውሰድ፣ ከሌሎች አፋኞች ስደተኞችን በአነስተኛ ገንዘብ በመግዛት እንደሆነ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉት ሜሮን እስጢፋኖስ ይናገራሉ፡፡

ወ/ሮ ሰብለ ደምሴ ይህንን ዜና ሲሰሙ ደነገጡ። ዜናውን ካሰራጨው የቪኦኤ ዝግጅት ክፍል አድራሻ በመጠየቅ አቶ መልካሙን አገኟቸው። አቶ መልካሙ በቃለምላልሳቸው ወቅት እንደተናገሩት ሁሉ ለወ/ሮ ሰብለ የደረሰባቸውን ሁሉ አጫወቱ። ወ/ሮ ሰብለ “የሰማሁት ሁሉ እረፍት ነሳኝ። የማውቃቸውን ሰዎች ማስቸገር ጀመርኩ። ጊዚያዊ የባንክ ሂሳብ በመክፈት ገንዘብ ማሰባሰብ ጀመርኩ። ህይወት ለማትረፍ እየጣርኩ ነው” ሲሉ ጥሪ ያካተተ አስተያየት ሰነዘሩ።

ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ አሁን ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው። አፋኞቹ 35 ሺህ ዶላር ካልቀረበላቸው የሰውነት አካል ክፍል ለሚዘርፉት አራጆች ያስረክቧቸዋል። እዚያ ከደረሱ ድርድር የለም። የሰውነት ክፍላቸው የበለጠ ዋጋ ስለሚያወጣ ሌሎች ወገኖች ላይ እንደተፈጸመው እርሳቸውም ላይ ይከናወናል።

የ12 እና የ 1 ዓመት ከስምንት ወር ልጅ ያላቸው ወ/ሮ ትዕግስት ባለቤታቸውን በስልክ እንዲያነጋግሩ ይደረጋሉ። ባለቤታቸውም ይሰቃያሉ። እግራቸውና እግራቸው መካከል ብረት ተደርጎባቸዋል። ይደበደባሉ። ይህ ሁሉ የሚደረገው ባለቤታቸው የተጠየቁትን ገንዘብ ባስቸኳይ እንዲከፍሉላቸው ለማስጨነቅ ነው። ባለቤታቸው እንደተናገሩት “ምንም አማራጭ የለኝም። የተጠየቀውን ገንዘብ ማግኘት አልችልም። ልጆቼ ወደፊት ሲጠይቁኝ ለምኜ አቃተኝ ለማለት እየለመንኩ ነው። ባለቤቴ ግን ምንም ማድረግ እንደማልችል ታውቃለች፤ … ” ብለዋል።

የ 12 ዓመቷ ልጃቸው ሱፊ “እኛንም እንዳይወስዱን ስለምንፈራ ከቤት አንወጣም” በማለት ልብ የሚነካ መልስ ከቪኦኤ ለቀረበላት ጥያቄ መልስ ሰጥታለች፡፡ “እናቴን አፈኗት” ያለችው ህጻን የበርካታዎችን ልብ እረፍት ነስታለች። ወ/ሮ ሰብለ “እንደዚህ አይነት አሳዛኝ ሲቃ ተሞላበት ጉዳይ እየሰማን በውጪ ያለን ወገኖች እንዴት 30 ሺህ ዶላር ማዋጣት አቃተን” ሲሉ ይጠይቃሉ። ወ/ሮ ትዕግስት ጸሃይ ቢተርፉ ለሌሎች በማስተማር ተመሳሳይ ችግር በሌሎች ወገኖቻችን ላይ እንዳይደርስ የማድረግ ስራ ይሰራል የሚል እምነት እንዳላቸው አስታውቀዋል።

በሰብአዊ ተግባርም ሆነ በየትኛውም ዓይነት ማህበር ተመሳሳይ ስራ ተሳትፎ እንደሌላቸው ያስታወቁት ወ/ሮ ገነት፣ ይህን ጉዳይ የሳቸውን ልብና አእምሮ ዕረፍት ነስቶት ለዚህ ተግባር ራሳቸውን እንደሰጡ ሁሉ፣ ሌሎችም ይህንን ልብ ሰባሪ አደጋ ሌሎች ወገኖችም ሰምተው ተባባሪ እንዲሆኑ በሚል ለጎልጉል አስተያየት መስጠታቸውን ተናግረዋል።

ለመንግስት ስለማሳወቃቸው ተጠይቀው በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጸሐፊ ስልካቸውን በማፈላለግ ካገኙ በኋላ ማነጋገራቸውን ይገልጻሉ። በምላሹም “ይልቁኑ አፋኞቹ ስልካችሁን እንዳያውቁ ተጠንቀቁ። እየደወሉ ይጨቀጭቋችሁዋል” የሚል የማስፈራሪያ ማስጠንቀቂያ ማግኘታቸውን ይናገራሉ።

ቴዲ አፍሮ በፑንት ላንድ ሞት የተፈረደበትን የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ቀድሞ በመድረስ ህይወቱን እንደታደገው አቶ መልካሙ አስታውሰው በተመሳሳይ የባለቤታቸውን ህይወት ሊታደግ የሚችል ወገን ሊኖር እንደሚችል ተቁመው ለማንኛውም “መፍትሔው እግዚአብሔር ዘንድ ነው” የሚል መልዕክት በቪኦኤ በኩል አስተላልፈዋል።

ወ/ሮ ሰብለ በበኩላቸው “ፈቃደኛነቱ ካለ ሁሉንም ነገር ማድረግ እንችላለን” በማለት የጀመሩት የነብስ ማዳን ስራ በቅርብ ወዳጆቻቸው መደገፉን አስታውቀዋል። አያይዘውም ሩጫው ከጊዜ ጋር መሆኑንን አመልክተዋል።

ገንዘቡ ከተገኘ ለአፋኞቹ እንዴት ይደርሳል? ወ/ሮ ትዕግስትስ እንዴት ነጻ ይሆናሉ? በሚል ወ/ሮ ሰብለ የሰሙት ነገር እንዳለ ለተጠየቁት፣ ሰዎቹ እስራኤል አገር ወኪል አንዳላቸውና፣ ገንዘቡ ለወኪሎቻቸው ሲገባ ግብጽ ወስደው እንደሚለቋቸው፣ ይህንን ለማከናወን የሚችሉ ሴት አቶ መልካሙ ማዘጋጀታቸውን እንደነገሯቸው የሴትየዋን ስም በመጥቀስ ተናግረዋል።

“በድብደባና በስቃይ ደክሜያለሁ። አሁን ገንዘቡ ተከፍሎ ቢለቁኝም በረሃውን አቋርጬ ግብጽ የምደርስበት አቅም የለኝም። እሞታለሁ። አትክሰሩ። እኔ አልተርፍም። የምትችሉ ከሆነ ህይወቴን ይወስዳት ዘንድ ለፈጣሪ ጸልዩ” ይህ ሲና በረሃ ታፍኖ የቆየ ኤርትራዊ ወጣት ለወንድሞቹ የተናገረው የመጨረሻ ንግግር ነበር። ወንድሞቹ እስራኤል አገር በስደት ሃዘን ተቀመጡ። ከዚያ በኋላ ስልካቸውን ቀየሩ። ወንድማቸውን በስልክ ድምጽ ነፍሱ ሳይወጣ ሞቱን ተቀበሉ” ሲሉ የሰሙትን ወ/ሮ ሰብለ አጫውተውናል። በሌላም በኩል በተመሳሳይ ታፍና የነበረች አንድ ወጣት የሚከፈለው ተከፍሎ በቅርቡ ከግብጽ አዲስ አበባ እንደገባች አመልክተዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሙት የሲና በረሃ አሰቃቂ ስቃይ ሳቢያ የወ/ሮ ትዕግስት ገብሬን ህይወት ለማትረፍ ራሳቸውን ከፊትለፊት ያቆሙት ወ/ሮ ሰብለ ሊያነጋግራቸው ለሚፈልግ ሁሉ የኢሜል አድራሻቸውን  አስታውቀዋል።  yegetasew@yahoo.com

ዝግጅት ክፍሉ፦ በተመሳሳይ፣ በተለያዩ ስፍራዎች የሚፈጸሙትን የወገኖቻችንን ስቃይ አስመልክቶ ላልሰሙ ትምህርት ይሆን ዘንድ ጽሁፍ ለምትልኩልና ወገኖች ሁሉ ቅድሚያ እንደምንሰጥ ለመግለጽ እንወዳለን። በተለይም በሱዳን የስደተኞች ካምፕ ከ30- 40 ዓመት የኖሩ ስደተኛ ወገኖች ጉዳዩን አስመልክቶ የኢትዮጵያዊን ተሳትፎ ምን እንደሚመስል ብትጠቁሙን ጉዳዩን እንደምናጣራው ከወዲሁ እንገልጻለን።

ወ/ሮ ሰብለና ለተመሳሳይ አላማ የተነሱት እህቶች የሚከተለውን ደብዳቤ ለእምነት ባልደረቦቻቸውና ለቤተክርስቲያን ያቀረቡትን የተማጽኖና እንቅስቃሴያቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

የካቲት ፲፫/፳፻፬

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈሥ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

“እውነት እላችኋለሁ ከሁሉ የሚያንሱ ከነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳን ስላደረጋችሁ ለእኔ አደረጋችሁ” ማቴ ፳፭ ፥ ፴፱

ጉዳዩ፦ በስደት ላይ እያሉ በአጋቾች ለታገቱ እናት ማስፈቻ የሚሆን ገንዘብ ስለማሰባሰብ

የክርስቶስ ሰላም ይብዛላችሁ በማለት መንፈሳዊ ሰላምታችንን እያስቀደምን ወደ ጉዳዩ እንገባለን።

ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ በሱዳን አገር ሸገርአብ የስደተኞች ጣቢያ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊት ስደተኛ ሲሆኑ በ01/22/13 ጠዋት ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ በራሻይዳዎች ታግተው በህይወት ለመውጣት ገንዘብ እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል።

ባለቤታችው አቶ መልካሙ ባዬ በዛው በሸገርአብ የስደተኞች ጣቢያ ከአንድ ዓመት ከሰባት ወር ህፃን እና ከአስራ ሁለት ዓመት ታዳጊ ሴት ልጆቻቸው ጋር የሚኖሩ ሲሆኑ የተጠየቀውን ገንዘብ ለመክፈል ምንም አይነት አቅም ስለሌላቸው በ02/10/13/ በተላለፈው የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል የመስታወት ዝግጅት ላይ ወገን ይደርስላቸው ዘንድ ተማጽነዋል ።

/ሙሉ ቃለ-መጠይቁን በዚህአድራሻ ማግኘት ይቻላል?

http://amharic.voanews.com/audio/audio/257172.html

እኛም ሥማችን ከደብዳቤው መጨረሻ የተዘረዘረው ግለሰቦች ይህንን የተማጽኖ ድምጻቸውን ሰምተን ክርስቲያናዊ እና ወገናዊ ግዴታችንን ለመወጣት ከአሜሪካ ድምጽ/VOA / ጠይቀን በተሰጠን የስልክ ቁጥር በመደወል አቶ መልካሙን /የታጋቿ ባለቤት / አነጋግረን በምን ልንረዳቸው እንደምንችል እና አሁን ባለቤታቸው ያሉበትን ሁኔታ በዝርዝር አስረድተውናል።

በእኛ በኩል እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት፦

1. በለንደን የሚገኘውን የAmensity International Sudan Team ስልክ በመደወል በእርግጥም ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ ከላይ በተጠቀሰው ቀን በአጋቾች እንደተወሰዱ በሱዳን ያለው UNHCR እንዳሳወቃቸው ሰምተን ጉዳዩ እውነተኛ እንደሆነ አጣርተናል።

2. በሱዳን ካርቱም ላለው የኢትዮጵያ ኤንባሲ በአንባሳደሩ ጸሐፊ በኩል ጉዳዩ የሚመለከተው ቆንስላ ክፍል ክትትል እንዲያደርግ አሳውቀናል።

3. የምናውቃቸውን ሰዎች ቃለ ምልልሱን ሰምተው የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ ጥረት እያደረግን ነው።

4. ተጨማሪ የአየር ሰዓት አግኝተው እርዳታ ይጠይቁ ዘንድ በሸገር ሬድዮ የ‘ታድያስ አዲስ’ አዘጋጅ ከሆነው ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር ተነጋግረን ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ 02/16/13 ሌላ ቃለ-መጠይቅ እንዲደረግላቸው አድርገናል

5. በአሁኑ ሰዓትም በዚሁ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የተለያዩ የራድዮ ጣቢያዎች ይህንን አሳዛኝ ነገር ወደ ህዝብ ጆሮ እንዲያደርሱ እየጠየቅን ነው።

6. በተጠላፊዋ ስም የFacebook ገጽ ከፍተን ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች በPaypal እርዳታ የሚሰጡበትን መንገድ እያመቻቸን ነው

7. Tewahedo.org. የተባለው የቤተክርስቲያን ድህረ-ገጽ ይህንን አሰቃቂ ነገር በፊት ገፁ እንዲለጥፍ አስፈላጊ መረጃ ልከናል።

8. ለዚሁ አገልግሎት ብቻ የሚውል የባንክ አካውንት ከፍተናል

በአሁኑ ሰዓት ገንዘቡ በፍጥነት መከፈል ካለመቻሉ የተነሳ በወ/ሮ ትዕግስት ላይ በኤሌክትሪክ እና በእሳት መቃጠል፤ ድብደባ፤ ተዘቅዝቆ መታሰር፤ እንዲሁም የሞቱ ሰዎችን አጥንት እያሳዩ የሥነ-ልቦና ጥቃት ማድረስ እና ሌሎችም ኢ- ሰብአዊ ድርጊቶች እየተፈጸሙባቸው መሆኑን ባለቤታቸውን በስልክ ባገኟቸው ቁጥር ከሚነግሯቸው ነገር ለመረዳት ችለናል።

ይህንንም ደብዳቤ ለመላክ የተገደድነውም በእኛ አቅም የተጠየቀውን 25,000.00 USD ሰብስበን የእኝህን እናት ህይወት ለማትረፍ የማንችል መሆኑን በማመናችን እና ይህ ገንዘብ ካልተከፈለ ግን አጋቾቹ “ከፍለን ነው የገዛናት ቢያንስ ያንን ለመመለስ ኩላሊቷን አውጥተን እንሸጣለን ” በማለት በግልጽ በመናገራቸው ይህ አደገኛ ነገር ከመከሰቱ በፊት ህዝበ ክርስቲያኑ የሚችለውን አድርጎ እኝህን እናት ለልጆቻቸው እንዲያተርፍላቸው በእግዚአብሔር ሥም በመጠየቅ ነው።

በአሁኑ ሰዓት መዋጮ መጠየቅ እንዴት ከባድ እንደሆነ ለሁላችንም ግልጽ ነው። ጉዳዩ የህይወትና የሞት መሆኑ አስገድዶን እና ለወገን ደራሽ የሆነውን ኢትዮጵያዊ ወገናችንን ተስፋ አድርገን ይህንን ለህዝበ ክርስቲያኑ እንድታስተላልፉልን የተሰደዱት ሁሉ መከታ በሆነችው በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ሥም በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን። ከሁሉ በላይ ማህበረ ካህናቱም እና ምዕመኑ እኚህ እናት በህይወት ይወጡ ዘንድ ወለተማርያም እያሉ በፀሎት እንዲያሳስቡላቸው እንጠይቃለን።

ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር

እሴተ ህይወት/ኢየሩሳሌም ጸጋዬ/ እህተ ማርያም (አዜብ ሮባ) ሰብለ ወንጌል /ሰብለ ደምሴ/

To wire money:

Seble Demissie Asefa

Swift code for international money wiring :WFBIUS6FFX
Routing number : 121000248

Online or in person transfer in the USA routing number : 019000019.

Account number is 7728584504.

Bank name: Wells Fargo

ስልክ ፡ (612) 636 1266 ስልክ ፡ (651) 366 2310 ስልክ፡ (612) 232 8720
የግርጌ ማስታወሻ፦

የባለቤታቸው አቶ መልካሙ ስልክ ቁጥር 011 249 116 112 170 ሲሆን አስፈላጊውን ጥያቄ ሁሉ ለመመለስ በማናቸውም ሰዐት ዝግጁ እንደሆኑ ለመግለፅ እወዳለን።

http://www.goolgule.com/save-tigist-gebre/

posted by Tseday Getachew

ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለበት! አዎ ዕዳ አለበት!!

ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

እንደ ጉርሻ 
በሽብርተኝነት ተከሰው በወህኒ ቤት የሚገኙ በጣም በርካታ እስረኞች የይቅርታ ፎርም እንዲሞሉ እየተደረገ ነው (ምንአልባት የሀይለማርያም መንግስት ሪፎርም /ማሻሻያ/ የማድርግ ዕቅድ ካለው በዚሁ ሊጀምር አስቦ ሊሆን ይችላል፤ አሊያም እንደተለመደው እስረኛ በመልቀቅ የፖለቲካ ማሻሻያ እንደተደረገ ለማስመሰል ይሆናል)፡፡ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄርም በብዛት ከሚለቀቁት እስረኞች ጋር አብረው እንደሚፈቱ ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል፡፡
አጀንዳችን…
ዛሬ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የእነእስክንድር ነጋን ንብረት ለመውረስ ፍትህ ሚንስቴር የመሰረተው ክስ ሲታይ ውሎአል፡፡
እስክንድር ከዚህ ቀደም ‹‹የታሰርኩት በግፍ ስለሆነ ንብረቴን አትውረሱ ብዬ አልከራከርም፤ ዛሬውኑ ልትወስዱት ትችላላችሁ›› በማለት ያልተከራከረ ሲሆን፣ የአበበ በለውን ንብረት በሚመለከት በሌለበት ታይቷል፡፡ የአንዱአለም አራጌ ባለቤት ደግሞ በስሟ የተመዘገበው መኪና መወረሱ አግባብ እንዳልሆነ በጠበቃዋ አቶ ደርበው ተመስገን አማካኝነት ተከራክራለች፡፡ ፍርድ ቤቱም ለውሳኔ የፊታችን ሚያዚያ አስር ቀን ቀጠሮ ሰጥቷል (በእኔ ግምት ቀጠሮው እንዲህ የራቀው መጋቢት አስራ ስምንት ቀን እነእስክንድር የጠየቁት ይግባኝ የመጨረሻ ውሳኔ ስለሚሰጥበት ከዛ በኋላ የንብረቱን ጉዳይ ለመጨረስ ይመስለኛል)
የሆነ ሆኖ ዓቃቢ ህግ የእስክንድር ንብረት ተብለው ከቀረቡት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት፣ በባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ስም የተመዘገበ የቤት መኪና፣ እንዲሁም የእስክንድር እናት ንብረት የሆነ በአንድ ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤትን ለመውረስ ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም፣ በዛሬው ዕለት በእናቱ ስም የተመዘገበውን ቤት እንደተወው ገልጿል (አዲስ ታይምስ መፅሄት የእናቱ ቤት ዝርዝር ውስጥ መግባቱ ተገቢ አለመሆኑን ደጋግማ መግለጿ የሚታወስ ነው)፡፡
ይህንና ዓቃቢ ህግ በእስክንድር እናት ስም የተመዘገበውን መኖሪያ ቤት ከሚወርሳቸው ዝርዝር ውስጥ በማውጣቱ ምንም አይነት ምስጋና የለኝም፡፡ ምክንያቱም እንኳን ንብረታቸው ተከሳሾቹም ምንም ጥፋት ያላጠፉ ንፁሀን ናቸው ብዬ ስለማምን፡፡ ስለዚህም አሁንም እንዲህ እላለሁ፡- ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለብህ! አዎ እዳ አለብህ!! ንፁሀን ወንድሞቻችንን ይቅርታ ጠይቀህ እስክትለቅልን ድረስ!!!

* ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይህን ዘገባ በፌስቡክ ገጹ ካሰፈረው ነው ያገኘነው።

Ze-Habesha Website is not responsible for accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

  http://www.zehabesha.com
 
posted by Tseday Getachew

ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም!

በመቅደስ አበራ (ከጀርመን)

ትላንት የተናገሩትን ዛሬ፤ ዛሬ የተናገሩትን ነገ የማይደግሙ ከሀዲ አንባገነን እና ዘረኛ ቡድኖች የስልጣን ኮረቻ በሀይል ከተፈናጠቱበት እለት ጀምሮ የተለያዩ የማወናበጃ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ የበርካታ ንጹሀን ዜጎችን ህይወት ቀጥፈዋል አስቀጥፈዋል፡፡እንኳን እንደጠላት የሚቆጥሩትንና በመርሃ ግብራቸው ነድፈው መጥፋት አለበት ብለው የፈረጁትን ህዝብ ቀርቶ አርነት እናወጣሀለን እያሉ ክእናንተ በመፈጠራችን ኮራንባችሁ የሚሏቸውን የትግራይን ንጹሀን ዜጎች ሳይቀር  የራሳቸውን የስልጣን ዕድሜ ለማራዘም ውድ ህይወታቸውን እንዲገብሩ አድርገዋል፡፡ የሀውዚንን ጭፍጨፋ አቀናብረዋል፣በ1991ዓ.ም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተደረገው  ጦርነት ከ70000 በላይ የጠርነቱ ሰለባ ሁነዋል፡፡አልሻባብን ለመደምስስ በሚል በሶማሊያ በረሃ የረገፉትን ወታደሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ስልጣን ለወያኔ ከምንም ነገር በላይ ነው፡፡ ስልጣን ከሉአላዊነት፣ከባህር በር ፣ከሀገርና ከህዝብ እንደሚበልጥባቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ የወሰዷቸው እርምጃዎች ማሳያ ናቸው፡፡የገንዛ ሀገሩን ቆርሶ ለሱዳን የሚሰጥ፣የባህርበር አያስፈልገኝም የአሰብን ወደብ ውሰዱት፣ኤርትራ እንድትገነጠል ፈቅጃለሁና እውቅና ስጡልኝ እባካችሁ እያለ የአለም መንግትታትን  የተማጸነ፣የገንዛ ዞጎቹን አፈናቅሎ ለውጭ ባለ ሀብቶች መሬታቸውን የሚሰጥ፤የሀገሪቱን ሀብት ለተደራጁ ወንበዴወች የሚያስዘርፍና የሚዘርፍ፤ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችን አጥፍቼ  ታላቋን ትግራይን እመሰርታለሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ አንባገነን እንዴት ያለ ሀገራዊ ራዕይ ነው የሚኖረው፡፡

ዘረኛው መንግስት በተለያዩ ጊዜያት እንዱን ብሄር በሌላው ብሄር ላይ በማነሳሳት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ሀብትና ንብረታቸውን ተዘርፈው ለከፍተኛ ችግር ሲዳረጉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለእልፈት ተዳርገዋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጋዜጠኞችን  በሽብር ስም እያሰረ ንጹሀንን ሲያሸብር ቆይቷል፡፡በርካታ ፓርቲዎች በሰርጎ ገብ ሰላዮች የተነሳ ይዘውት የተነሱትን አላማ እና  የህዝብ አደራ እዳር ሳያደርሱ በጅምር ቀርተዋል፡፡በወያኔ መሰሪ ተንኮል በተቀነባበረ ሴራ ጦርነት ውስጥ ያልገባ ክልልና ብሄር ባይገኝም ውጤቱ እንደሚፈልጉት ስላልሆነላቸው እና የኢትዮጵያ ህዝቦችም ባላቸው አርቆ አስተዋይነትና ረጅም ጊዜ በሰላም አብሮ የመኖር ባህሉ በመታገዝ  የፕሮፖጋንዳቸው ሰለባ ባለመሆናቸው ለወያኔዎች ትልቅ ራስ ምታት ጥሮባቸዋል፡፡እስካሁን ሲጫወትበት የነበረውን ካርድም እንዲቀይርም ተገዷል፡፡ አዲሱ የመጫወቻ ካርድም ከብሄር ግጭት ወደ ሐይማኖታዊ ግጭት ለማሸጋገርም የሚያስችለውን “ጀሀዳዊ ሀረካት”የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም በመስራት ከ1500 አመት በላይ አብረው የኖሩትን ሁለቱን ታላላቅ እምነቶች ማለቂያ ወደሌለው ጦረነት በመማገድ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም ቢምክርም እናንተ ከመጣችሁት ገና 21 ዓመታችሁ ነው እኛ ደግም ለረጅም ጊዜ  በፍቅር አብረን ኑረናል፤  የጋራ ጠላታችን ዘረኛው ወያኔ ነው፡፡እኛ ከእነሱ እንሻላለን አንለያይም እያሉ በየአደባባዮ አንገት ላንገት ተቃቅፈው እየተላቀሱ ቁጭታቸውን ሲገልጹ መመልከት የተለመደ ተግባር ነው፡፡ሰሞኑን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕርግራም ሙኒክ ላይ የታየውም ህብረት የዚሁ አካል ነው፡፡

እንዴት እንደ  ኢትዮጵያ ያለች ታላቅ ሀገር እና እንደ ኢትዮጵያውያን ያሉ ቀደምት ህዝቦች እንደ ወያኔ ባሉ ትንሽ ሰዎች ይገዛሉ?እንዴት የአለም ማህበረሰብ በሀሰት የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ሲታለል ይኖራል?እስከመቼ ብቻቸውን በምርጫ ተወዳድረው አሸነፍን እያሉ ሲያላግጡ ይኖራሉ? ወያኔዎችስ በቀጣይ ምን የማደናገሪያ ስልት ያመጡ ይሆን? እኔ በበኩሌ በቃ ብያለሁ፡፡ ወያኔ ራዕይ የለውም ኑሮትም አያውቅም፤ ወደፊትም አይኖረውም፡፡የወያኔ  ሀገር እና ህዝብ የማውደም ቅዠት እንጂ ሀገራዊ ራዕይ ብሎ ነገር አያውቅም፡፡በጋራ ጠላታችን ላይ በጋራ እንነሳ!!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

 
 
posted by Tseday Getachew

ጋዜጠኛ ውብሸትና አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚአብሔር ሊፈቱ ነው

የካቲት ፩፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በሽብርተኝነት ተከሰው በወህኒ ቤት የሚገኙ በጣም በርካታ እስረኞች የይቅርታ ፎርም እንዲሞሉ እየተደረገ መሆኑን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ገለጸ።

ተመስገን ፦<<አቃቤ ህግ ዕዳ አለብህ >>በሚል ርዕስ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ  ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና አቶ ዘሪሁን ገብረ-እግዚአብሔር  በብዛት ከሚለቀቁት እስረኞች ጋር  አብረው እንደሚፈቱ ምንጮች አረጋግጠውለታል።

<<ይህ የሚደረገው ምንአልባት የሀይለማርያም መንግስት ሪፎርም /ማሻሻያ/ የማድርግ ዕቅድ ካለው በዚሁ ሊጀምር አስቦ

ሊሆን ይችላል፤ አሊያም እንደተለመደው እስረኛ በመልቀቅ የፖለቲካ ማሻሻያእንደተደረገ ለማስመሰል ይሆናል>> ብሏል ተመስገን።

በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት  በከፍተኛው ፍርድ ቤት የእነእስክንድር ነጋን ንብረት ለመውረስ ፍትህ ሚንስቴር የመሰረተው ክስ ሲታይ መዋሉን ጋዜጠኛ ተመስገን ጨምሮ ገልጿል።

እስክንድር  ቀደም  ሲል፦‹‹የታሰርኩት በግፍ ስለሆነ ንብረቴን አትውረሱ ብዬ አልከራከርም፤ ዛሬውኑ ልትወስዱት ትችላላችሁ›› በማለት ስለ ንብረቱ አለመከራከሩን ያወሳው ተመስገን፣ የአበበ በለውን ንብረት በተመለከተ የተመሰረተው ክስ ተከሳሹ በሌለበትመታዬቱን አመልክቷል፡፡

 እንደ ተመስገን ገለፃ የአንዱአለም አራጌ ባለቤት ደግሞ በስሟ የተመዘገበው መኪና መወረሱ አግባብ እንዳልሆነ በጠበቃዋ በአቶደርበው ተመስገን አማካኝነት ተከራክራለች፡፡

 ፍርድ ቤቱም በጉዳዩ ላይ  ውሳኔ ለመስጠት  ለመጪው ሚያዚያ አስር ቀን ቀጠሮ ሰጥቷል።
<<በእኔ ግምት ቀጠሮው እንዲህ የራቀው መጋቢት አስራ ስምንት ቀን እነእስክንድር የጠየቁት ይግባኝ የመጨረሻ ውሳኔ ስለሚሰጥበት ከዛ በኋላ የንብረቱን ጉዳይ ለመጨረስ ይመስለኛል>>ሲልም  ጋዜጠኛ ተመስገን ግምቱን አስቀምጧል።

 ዓቃቢ ህግ ቀደም ሲል የእስክንድር ንብረት ተብለው ከቀረቡት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት፣ በባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ስም የተመዘገበ የቤት መኪና፣ እንዲሁም የእስክንድር እናት ንብረት የሆነ በአንድ ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤትን ለመውረስ ጥያቄ አቅርቦ እንደነበር ያስታወሰው ተመስገን ፣ በዛሬው የችሎት ውሎ በእናቱ ስም የተመዘገበውን ቤት እንደተወው ገልጿል።

አዲስ ታይምስ መፅሄት የእናቱ ቤት  በንብረት ውርስ ዝርዝር ውስጥ መግባቱ ተገቢ እንዳልነበር  ደጋግማ መግለጿን ተመስገን አስታውሷል።
ተመስገን ጽሁፉን ሲያጠቃልልም፦<<ይህንና ዓቃቢ ህግ በእስክንድር እናት ስም የተመዘገበውን መኖሪያ ቤት ከሚወርሳቸው ዝርዝር ውስጥ በማውጣቱ ምንም አይነት ምስጋና የለኝም፡፡ ምክንያቱም እንኳን ንብረታቸው ሊወረስ ተከሳሾቹም ምንም ጥፋት ያላጠፉ ንፁሀን ናቸው ብዬ ስለማምን፡፡ስለዚህም አሁንም እንዲህ እላለሁ፡- ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለብህ! አዎ እዳ አለብህ!! ንፁሀን ወንድሞቻችንን ይቅርታ ጠይቀህ እስክትለቅልን ድረስ!!!>>ብሏል።

posted by Tseday Getachew

የ5ቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እጩ ፓትርያርኮች አጭር የሕይወት ታሪክ

 

ዲ/ን ኅሩይ ባየ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ አስመራጭ ኮሚቴ በመሠየም እጩ ፓትርያርኮችን ለመምረጥ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ ከካህናት፤ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች፤ ከማኅበረ ቅዱሳን፤ እንዲሁም ከምእመናን ጥቆማ እንዲያካሔዱ ተደርጓል፡፡ በተካሔደው ጥቆማ መሠረት አስመራጭ ኮሚቴው ጥቆማውን በግብአትነት በመጠቀም አምስት ሊቃነ ጳጳሳትን በእጩነት በማቅረብ የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም. ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቅርቧል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤም ከየካቲት 16 – 18 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ውይይት በማካሔድ አምስቱም ሊቃነ ጳጳሳት በእጩነት እንዲቀርቡ አጽድቋል፡፡ የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. ለሚካሔደው የ6ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የፓትርያርክ ምርጫ የቀረቡት ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፡-  ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዪጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ  የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ፤ የከፋ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የወላይታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት አጭር የሕይወት ታሪካቸውን እንደሚከተለው እናቀርባለን፡-

ብፁዕ አቡነ ማትያስ :- photo 4

የቀድሞው የአባ ተክለማርያም ዐሥራት የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ማትያስ በ1934 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ቅዳሴ፣ ዜማ፣ ቅኔ፣ ባሕረ ሐሳብ፣ የመጻሕፍተ ሐዲሳት ትርጓሜ ተምረዋል፡፡ በ1948 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ዲቁናን ጮኸ ገዳም ተቀብለዋል፡፡ ከመ/ር ዐሥራተ ጽዮን ኰኲሐ ሃይማኖት መአረገ ምንኩስናን አግኝተዋል፡፡ በ1955 ዓ.ም በ1969 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ መቃርዮስ መአረገ ቁምስናን ተቀብለዋል፡፡

 በጮኸ ገዳም በቄሰ ገበዝነት፣ በመጋቢነት በልዩ ልዩ ገዳማዊ ሥራ አገልግለዋል፡፡ በገዳሙ ውስጥ በነበራቸው ቆይታ ሐዲስ ኪዳንን አስተምረዋል፡፡ ከ1964 — 68 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በቅዳሴና በልዩ ልዩ አገልግሎቶች ተመድበው አገልግለዋል፡፡ ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ዓመታት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ ቀሲስና ምክትል ልዩ ጸሐፊ በመሆን ሠርተዋል፡፡ ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳም ኤጲስ ቆጶስ ሆነው ተሹመዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ገዳም ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡

 ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ :-

photo 1የቀድሞው አባ ኅሩይ ወልደ ሰንበት የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ በ1930 ዓ.ም ተወለዱ ጸዋትዎ ዜማ፣ ቅኔ፣ ትርጓሜ መጻሕፍት፣ ፍትሐ ነገሥት፣ ባሕረ ሐሳብና ሐዲስ ኪዳንን ተምረዋል፡፡ በ1945 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዲቁና በ1964 ዓ.ም ምንኩስናን በደብረ ሊባኖስ ገዳም ተቀብለዋል፡፡ በ1965 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል ቅስና በ1969 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ሰላማ ቁምስናን ተቀብለዋል፡፡ በደብረ ጽጌ ገዳም በመዘምርነትና በቅዳሴ አገልግለዋል፡፡ ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም  በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ የከፋ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ ተብለው ተሹመዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የሰሜን ጎንደር  ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡

 ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ :-

ነሐሴ  16  ቀን  1944  ዓ.ም  በሰሜን  ሸዋ  ክፍለ  ሀገር  በሸኖ አውራጃ  ልዩ  ስሙ  ጨቴ  ጊዮርጊስ  በተባለው  ቦታ ተወለዱ፡፡ የቀድሞ ስማቸው photo 2 ቆሞስ  አባ ኀይለጊዮርጊስ ኀይለ ሚካኤል ይባላል፡፡ ፊደል የቆጠሩት ዜማን የተማሩት ቅኔን የተቀኙት በሀፋፍ ማርያም በኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ ገዳም ነው፡፡ ቅዳሴን በዳግማዊ ምኒሊክ መታሰቢያ የቀሳውስት ማሠልጠኛ ት/ቤት ተምረዋል፡፡ በሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ት/ቤት ለ4 ዓመታት ተምረው በዲፕሎማ ተመርቀው ዘመናዊ ት/ርታቸውን እስከ 12ኛ ክፍል በማጠናቀቅ በምዕራብ ጀርመን እሸት ኬርከሌ መንፈሳዊ ት/ቤት ስለ ገዳማት አስተዳዳር አጥንተዋል፡፡

 ሐምሌ 5 ቀን 1991 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ እድ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ተብለው ተሹመዋል፡፡ በአሁኑ ሰአት የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡

ምንጭ፡- ዜና ቤተ ክርስቲያን 31ኛ የዓመት ቁ.3፣ ጥር 4 ቀን 1971 32ኛ ዓ.ም ቁ.4

 ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፡-

photoየቀድሞ ስማቸው መልአከ ምሕረት አባ ሀብተ ማርያም ይባላል፡፡ ግንቦት 7 ቀን 1946 ዓ.ም በደቡብ ወሎ አማራ  ሳይንት ልዩ ስሙ ደብረ ብርሃን ለንጓጥ ሥላሴ ተወለዱ፡፡ አባታቸው ግራ ጌታ መኮንን ኀይሉ እናታቸው ወ/ሮ አታላይ ደርሰህ ይባላል፡፡ ዜማ፣ አቋቋም፣ ቅኔ፣ ፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ ተምረዋል፤ የቅኔ መንገድ ከነአገባቡ ተምረው በመምህርነት ተመርቀዋል በ1956 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ገብርኤል ዲቁና ተቀብለዋል፡፡

 ጳጉሜን 3 ቀን 1981 ዓ.ም በደብረ ሊባኖስ ገዳም ሥርዓተ ምንኩስና ፈጽመዋል፡፡ ኅዳር 12 ቅን 1982 ዓ.ም የቅስና ማዕረግ ከብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፤ ከብፁዕ አቡነ ቄርሎስ መዓርገ ቁምስና ተቀብለዋል፡፡  ከ1982 – 87 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ በጽርሐ ጽዮን ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የመጽሐፍ መምህር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከሠኔ 20 ቀን 1987-1990 ዓ.ም በምሥራቅ ሐረርጌ ሐደሬ ጤቆ መካነ ሥላሴ ደብር፣

 ከየካቲት 1990-93 ዓ.ም የድሬዳዋ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፣ ከሠኔ 1 ቀን 1993 ዓ.ም – ሐምሌ 1 ቀን 1994 ዓ.ም ጀምሮ ለጵጵስና መአርግ እስከ በቁበት ዘመን በአዲስ አበባ ቦሌ ደብረ ምጽላል እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን አገልግለዋል፡፡ ከሐምሌ 1 ቀን 1994 ዓ.ም የሰሜን ወሎ ደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም አስተዳዳሪ ሆነው አገልግለዋል፡፡ ነሐሴ 22 ቀን 1997 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ እድ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የከፋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ተብለው ተሹመዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የምዕራብና ደቡብ አዲስ አበባ ፤ የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት  ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡

 ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፡-

photo 3 

በ1955 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ልዩ ስሙ ምንታምር ቀበሌ ከአቶ ጌታነህ የኋላሸትና ከወ/ሮ አምሳለ ወርቅ ማሞ ተወለዱ፡፡ አቋቋም፣ ቅኔ ከነአገባቡ ቅዳሴ ኪዳን አንድምታ፣ ዜማ፣ ሠለስት፣ አርያም፣ ጾመ ድጓ፣ ቁም ዜማ ተምረዋል፡፡ በ1969 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ዲቁና ተቀብለው ቅስና ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ተቀብለዋል፡፡ በ1975 ዓ.ም በደብረ ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ሥርዓተ ምንኩስና ፈጽመዋል፡፡ በሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ለ4 ዓመታት ያህል ተምረው በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡ በሆላንድ ሆህ እስኩለ የቲዎሎዲ ትምህርት ቤት ገብተው ለ4 ዓመታት ተምረው በቲኦሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ተቀብለዋል፡፡

 በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በሰበካ ጉባኤ አደራጅነት፣ በሰ/ት ቤት ሓላፊነት፣ አ/አ ሀገረ ስብከት ሸሮ ሜዳ መንበረ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በሰባኪነት፣ በሐረር ደብረ ገነት መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በአ/አ ሀገረ ስብከት በአቃቂ መድኀኔዓለም በአስተዳዳሪነት በቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል በሳሎ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ደብርና በሐረር ደብረ ገነት መድኀኔዓለም አብያተ ክርስቲያናት በአስሪተዳዳሪነት አገልግለዋል፡፡ በውጭ ሀገር በአሜሪካ ዳላስ ቅዱስ ሚካኤል በአውሮፓ ሲውዘርላንድ በጀኔሻ፣ በሎዛን፣ በዙሪክና በበርንባዝል ከተሞች ባሉ አድባራት በቀዳሽነትና በሰባኪነት አገልግለዋል፡፡

 ነሐሌ 22 ቀን 1997 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ እድ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የዋግ ሕምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተሾሙ፡፡ በአሁኑ ሰዓት የየወላይታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡

http://www.eotcmk.org

posted by Tseday Getachew

OLF faction led by Kemal Gelchu decimated

EthiopianReview.com | February 26th, 2013

The faction of Ethiopian armed opposition group, the Oromo Liberation Front (OLF), led by General Kemal Gelchu now survives only in name after the Eritrean government put Kemal and all his comrades under house arrest and disarmed the troops who were camped in eastern Eritrea near Assab, according to the latest information Ethiopian Review has received from reliable sources.

Recently, we had reported that Gen. Kemal Gelchu has been detained. Today we learned that Gen. Hailu Gonfa and all the other leaders of OLF under Kemal have been ordered not to leave Asmara. They are also prohibited from leaving Eritrea.

The fate of OLF troops is even worse. Ethiopian Review sources are reporting that the number of troops has declined from a few hundred to less than 80. Many have escaped and some of them died from disease and malnutrition.

The health condition of the remaining OLF troops is appalling, one of our sources said.

Gen. Kemal Gelchu and his OLF faction are now practically prisoners of the Eritrean government.

EthiopianReview.com

posted by Tseday Getachew

ፌስቡክን ለመታገል የቆረጠ የሚመስለው ታገል ሳይፉ!

 • በግምት ከአንድ ወር በፊት ይመስለኛል ታገል በግጥም መድብሉ ባሰፈረው “መታሰቢያ እና ምስጋና” ምክንያት በፌስቡክ ተቃውሞ የቀረበበት ታገል ከቁምነገር መፅሔት የየካቲት እትም ጋር ባደረገው ቃለምልልስ የ…ቀረበበትን አስተያየትና ተቃውሞ በሰከነ ሁኔታ በመሞገት ፋንታ ከመስመር በወጣ መልኩ አንድ ሚሊዮን እንኳን ያልሞላውን ኢትዮጵያዊ የፌስቡክ ተጠቃሚ በጅምላ ዘልፏል።በውኑ ታገል ፌስቡክን ያውቀዋል ተጠቃሚስ ነው? ወይንስ በሆድ አሳዳሪዎቹ የተሰጠው አጀንዳ አለ!?የታገል ፌስቡክን የማውገዝ ምክንያት ምን ይሆን!? እለት እለት እየተጠናከረ በመጣው አፈና ምክንያት ፌስቡክን እንደመተንፈሻ እና መንግስትን ለመታገል እንደዋነኛ መደራጃ እያገለገለ እንደሚገኝ ግልፅ ነው ታዲያ ሁሉንም ነገር ካላፈኑ እንቅልፍ የማይወስዳቸው ወያኔዎች የፌስቡክ ነገር ከቁጥጥራቸው እንደወጣ ስለተገነዘቡ ፌስቡክ የሚፈጠሩ ግሩፖቹን፥ገፆችንና የግለሰብ ፕሮፋየሎችን እየተከታተሉ ከመዝጋት ባሻገር ፀረ-ፌስቡክ የሆነ ዘመቻ ከጀመሩ ውለው አድረዋል እስከአሁን ፀረ-ፌስቡክ የሆኑ የፕሮፓጋንዳ ስራዎች በኢቲቪ፥ በሪፓርተር እና በዛሚ ኤ.ኤፍ.ኤም ቀርበዋል።ከሆድ አሳዳሪዎቹ ጋር እንዘጭ እንዘጭ ያበዛው “ታዋቂው” ታገል በወያኔ እየተካሄደ ያለው ፀረ-ፌስቡክ ዘመቻ እራሱን አካል ስለአደረገ ይመስለኛል ከመስመር በወጣ መልኩ ፌስቡክና ፌስቡካውያንን በአንድ ከረጢት አጭቆ የዘለፈው።=>>ሙሉውን ቃለምልልስ አያይዠዋለውና ያንብቡት

  ታገል ሳይፉ ከቁምነገር መፅሔት የየካቲት እትም ጋር ያደረገው ፀረ-ፌስቡክ ቃለምልልስ በከፊል።

  ታገል የሰጠውን ቃለምልልስ እንዳለ አላቀረብኩትም ነገር ግን በኔ እይታ የገረሙኝን ጥያቄና መልሶች እንዳለ አቅርቢያቸዋለሁ።

  ቁምነገር፦ አዲሱን መፅሐፍህን መታሰቢያነቱን ለመለስ ልጆች ማድረግህን ፖለቲካዊ ትርጉም የሰጡት ሰዎች ነበሩ ምን ትላቸዋለህ?

  ታገል፦ ብዙም የምልሽ ነገር የለም ማንኛውም ጤነኛ ሰው አንብቦ ሊረዳው የሚችለው ነገር ነው ።ራስሽ አስቢው መታሰቢያነቱ “አባታቸው ለሚወዳቸው ልጆቹ ፍቅር የሚሰጥበትን ጊዜ ያጣ ሙሉ እድሜውን ለሕዝብና ለሀገር የሰጠ ነበር” ይላል ። መቸም አባትየው ለሀገሩ ጊዜውን መስጠቱን ደጋፊውም ተቃዋሚውም የማይክደው ነገር ነው።አከራካሪው ጉዳይ ለሀገሩ በሰጠው ጊዜ ምን ያህል ጠቀማት ጎዳት የሚለው ይመስለኛል።እኔ እዚህ ውስጥ አልገባሁም።የኔ ጉዳይ ልጆቹ ናቸው ልጆቹ ደግሞ የፖለቲካ ምልክት የለባቸውም። ምን አልባትም እነኝህ ልጆች ከየትኛውም ተቃዋሚ ወገን በላይ የገዥው ፓርቲ ነገር አይጥማቸው ይሆናል። የአባታችንን ፍቅር ነጥቆናል ብለው ሊያስቡ ይችላሉ።እኔ እዚህ ውስጥ አልገባውም ነገር ግን እኔም አባትነኝና ባባታቸው የጊዜ እጥረት አባታዊ ፍቅሩን አጥተው መኖራቸው ብቻ ሳይሆን አጥተው መቅረታቸው እንደሰው ሊያሳዝነኝ ይችላል እናም መታሰቢያነቱን ለነዚህ ልጆች ለማድረግ አባትነት ውስጥ ያለው ሰብዓዊነት ብቻ በቂ ነው።ይሁን እንጅ እንደተባለው አይነት ፖለቲካዊ ትርጉም ያለው መታሰቢያ አድርጌ ቢሆን ኖሮ ስህተት ነበር ማለት አይደለም።ከፈለግኩ ለወሰንጋላ ለአዳልሞቲም መታሰቢያ ማድረግ መብቴ ነው።መፅሐፌን ለማን መታሰቢያ ማድረግ እንዳለብኝና እንደሌለብኝ የሚነግረኝ ካለ መልሸ የምነግረው “ልኩን የማያውቅ ደፋር” መሆኑን ብቻ ነው።

  ቁምነገር፦ በምስጋናው ገፅ ላይ ለአቶ በረከት ያቀረብከውን ምስጋና ያልወደዱልህ ሰዎች አሉ?

  ታገል፦ ቅድም እንዳልኩሽ ማንኛውም አንባቢ የአንድን ደራሲ መፅሐፍ ሲገመግም ጣልቃ ከማይገባባቸው ጉዳዮች አንዱ የመታሰቢያ ገፅ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የምስጋና ገፅ ነው።አንድ ደራሲ ለህሊናው ታማኝ ከሆነ የሚያመሰግነውን ሰው የሚመርጠው ሰውየው በሌሎች አይን የሚታይበትን ገፅታ ከግምት ውስጥ አስገብቶ መሆን የለበትም ይልቁንስ ሰውየው በእርሱና በስራው ላይ ካሳዳረው በጎ ተፅእኖ አንፃር ነው።በተረፈ በማይመለከተው ጉዳይ ገብቶ ማንን ማመስገን እንዳለብህና እንደሌለብህ እኔ ልንገርህ ማለት ትልቅ ጅልነት ይመስለኛል እንዲያውም (የአንድ ወዳጄን አባባል ልዋስና) ከዚህ አይነቱ ጅል ጋር ሲነፃፀር ቂሉ ማሞ አራዳ ነው ማለት ይቻላል።

  ቁምነገር፦ አንዳንድ ሀብታሞችን በሰፊው ማመስገነህን ያልወደዱልህ አስተያየት ሰጭዎች አሉ?

  ታገል፦ እውነቱን ለመናገር እዚህ ገፅ ላይ ደሀን የማመሰግንበት ምንም ምክንያት አልነበረም(ለዚህ አባባሌ ይቅርታ እጠይቃለው) ከሀብታሙም ቢሆን እኔን ሳይሆን ኪነጥበቡን ለማገዝ የጣሩት ተመርጠው ተመስግነዋል።(ታገል በሌሎች ሀገሮች መንግስት የጥበብ ሰዎችን በገንዘብ እንደሚረዳ እያስረዳ ይቀጥላል)

  ቁምነገር፦ ከግጥሞቹ መጨረሻ ላይ መታሰቢያነቱን ያበረክትላቸውን ሰዎች (ከተለመደው ውጭ) በጣም ታሞግግሳቸዋለህ ብለው የሚተቹህ አሉ።

  ታገል፦ ያልተለመደ ነገር ያልተለመደን ነገር ያስከትላል ልክ ነው በግጥሞቹ መጨረሻ ላይ እነ ልዑል ራስ መንገሻን የመሳሰሉ ታላላቅ የሀገር ባለውለታዎችን ደስ እያለኝ አመሰግናቸዋለው። በዚህ ዘመን ባለውለታን ማክበር ትልቅ ስቃይ ነው እንደ ጤናማ ነገር ተለምዶ የማይሰቀጥጠን ማንቋሸሽና ማዋረድ ነው።ከዚህ የተነሳ ሰው ሲሞገስ ለምን እንላለን ነገር ግን ዳገቱ የቁልቁለቱን ያክል ነው የሚባል ተረት አለ።ምን አልባት በየፌስቡኩና በየሚዲያው ታላላቅ የሀገር ባለውለታዎች የሚናገሩትን በማያውቁና የማያውቁትን በሚናገሩ ምላሶች ዝቅ ዝቅ መደረጋቸው ከፍ ከፍ እንዳደርጋቸው ያነሳሳኝ ይመስለኛል ።ስለዚህ ጀግኖችን ለማንሸራተት ያበጁት ቁልቁለት ካልሰቀጠጣቸው የቁልቁለቱን ያክል ብድግ ያለውም ዳገት ሊረብሻቸው አይገባም።ምክንያቱም የኔን ዳገት የፈጠረው የነሱ ቁልቁለት ነው።

  ቁምነገር፦ እስከአሁን ድረስ በፌስቡክ ላይ ለወረዱብህ ውግዘቶች ይኸን ሁሉ ምላሽ ይዘህ ድምፅህን ያጠፋኸው ለምንድን ነው?

  ታገል፦ ከመፅሐፍ ቅዱስ የምወደውና የሚመራኝ አባባል አለ።”የባልቴቶች ከሚመስል ወሬ እራቅ” ይላል። እኔ ድሮ የማውቀው የባልቴቶች ወሬ በረከቦት ዙሪያ እንደነበር ነው።አሁን ወጣት ባልቴቶቻችን የሚሰበሰቡበት ረከቦት ፌስቡክ ሆነ።ስለዚህ ከዚህ አካባቢ ወሬ /መልስ ባለመስጠት/ መራቅ ነበረብኝ።

  ቁምነገር፦ ከዚህ ሁሉ ውዥንብር አንፃር ፌስቡክ ጠቃሚ ነው ትላለህ?

  ታገል፦ ጠቃሚነቱ ምንም አያጠያይቅም ግን ይህን የሚወስነው አጠቃቀማችን ነው።እዚህ ላይ የማስታውሰውን ገጠመኝ ልንገርሽ ከአንድ አዛውንት ጋር ታክሲ ውስጥ ቁጭ ብያለሁ ከውጭ ጆሮው ላይ ሎቲ አንጠልጥሎ ጎዳናውን የሚያቋርጥ አንድ ወጣት ተመለከትኩና ወደ እኝህ አዛውንት ዘወር ብየ “አባቴ በእናንተ ዘመን ሰዎች አንበሳና ቀጭኔ ገድለው ነበር ሎቲ የሚያንጠለጥሉት ይህ ወጣት ምን ገድሎ ይመስሎታል ሎቲ ያንጠለጠለው?” ስል ጠየኳቸው አዛውንቱም አየት አድርገውት “እንግዲህ ይህ ደግሞ ጊዜ ገዳይ ይሆናል በዛ ፌስ ቡካችሁ” ነበር ያሉኝ። እንደኔ እንደኔ ፌስቡክ ላይ ችግር የሚፈጥሩት ለፌስቡክ ክብር የሌላቸውና ፋይዳውን በቅጡ ያልተገነዘቡት ወገኖች ናቸው።እነዚህ ወገኖች ድሮ ድሮ ስማቸውን ደብቀው በየሽንትቤቱ ግድግዳ ላይ ብዙ አይነት ሀሜቶችንና ነውሮችን ሲፅፉ የኖሩ ይመስለኛል።አሁን ደግሞ ፌስቡክን እንደሽታ አልባ የሽንት ቤት ግድግዳ ሳይቆጥሩት አልቀረም። ድሮ በሽንት ቤት ግድግዳ ላይ እንደሚያደርጉት ዛሬም ስማቸውን ደብቀው ያሻቸውን ነውር ይፅፋሉ ።ያም ሆኖ ፌስቡክ የሽንት ቤት ግድግዳ ሆኖ የቀረው በነዚህ ወገኖች ደካማ ግንዛቤ ብቻ እንጅ በአግባቡ የሚጠቀሙት ወገኖች አይደለም።

  05/06/05 ሀና መታሰቢያ

  posted by Tseday Getachew

ሳንሱር ዋጋ ያስከፍላል

Ethiopia #StopCensorship

From  Zone 9  blog

ለምዕራባዊያኑ የመጨረሻ  ወር በሆነው ዲሴምበር ወር መጀመርያ በሀገረ አሜሪካ ኢትዮጵያዊውን ጦማሪ እና እስክንድርነጋን ለማሰብ የተዘጋጀ መድረክ ነበር፡፡ በመድረኩ ላይ ስለ እስክንድር ነጋ የተናገሩት ተዋናይ ሊዬቭ ሽሬ የይበር እና ጸሐፊ ካርል በርንስቴይን ነበሩ፡፡ በርንስቴይን  ከ40 ዓመታት በፊት የዋሽንግተን ፖስት ዘጋቢ ሆኖ በሚሠራት ወቅት ከባልደረባው ቦብ ዉድወርድ ጋር በመሆ ን በአሜሪካ መንግስት ታሪክ ትልቅ የተባለውን እና የዋተርገቱ ቅሌት በመባል ሚታወቀውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ያሳተፈ የሙስና ቅሌት አጋልጠዋል፡፡ በነዚህ ሁለት ዘጋቢዎች ታሪካዊ ማጋለጥ ምክንያት በወቅቱ አሜሪካን በፕሬዝዳንትነት ይመሩ የነበሩት ሪቻርድ ኒክሰን ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንዲለቁ ሆኗል፡፡

የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ምሳሌ ተደርጋ የምተጠቀሰው አሜሪካ በወቅቱ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ አቅም የሚያንሳት ሀገር አልነበረችም፡፡ የፖለቲካ ባህሏም (በጥቅሉ) ተጠያቂነትን የሚያበረታታ እና ሙስናን የመሰሉ ተግባራትን አፀያፊ አድርጎ የሚቆጥር ነበር/ነው ማለት ይቻላል፡፡ በዚህም ሥርዓት መሐከል ግን እንክርዳድ አይጠፋውም፡፡ እናም መደበኛው የተጠያቂነት ሥርዓት ያልደረሰበትን ማማ አራተኛው የመንግሥት ክንፍ  (fourth organ of government) በመባል የሚታወቀው ሚዲያ አጋለጠው፡፡

ነጻ የሆኑ መገናኛ ብዙኃን መኖር እና ዜጎች ሐሳባቸውን መግለጽ እና መወያየት መቻላቸው የመንግሥትን እና የባለሥልጣናቱን ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ሕዝብን ከአደጋ ለመጠበቅ ቁልፍ መሣሪያዎች ናቸው፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ደሃ ሀገራት እያንዳንዱ የመንግሥት መዋለ ነዋይ ለሚፈለግለት ዓላማ መዋል አጥብቆ የሚፈለግ ነገር ነው፡፡ እውነታው ግን ይሄ አይደለም፡፡ በደሃ ሀገራት FreddomofSpeech.phpስልጣን የሚይዙት ሰዎች/የፖለቲካ ፓርቲዎች ግን አንድም የራሳቸውን ግለሰባዊ ችግር ከሀገሪቱ ችግር በማስቀደም ወይንም በስግብግብነት አልፎ አልፎም ደግሞ ከብቃት ማነስ ሀገራቸው እጅግ አድርጋ የምትፈልገውን መዋለ ነዋይ ያባክናሉ፡፡ ይባስ ብሎም አብዛኞቹ ደሃ ሀገራት የሚመሩት ሁሉንም ነገር መቆጣጠር በሚፈልጉ እና ለምንም አይነት ነጻነት እና መብት ደንታ በማይሰጣቸው መሪዎች  (totalitarian) ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የሀገር ሃብት ሲመዘበር እና አለአግባብ ጥቅም ላይ ሲውል ለምን ብሎ የሚጠይቅ አካል አይኖርም፡፡ ካለምፍዳው እጅግ ብዙ ይሆናል፡፡

የሕዝብ ውክልና የሌላቸው/የሚጎላቸው የድሃ ሀገራት መሪዎች ስልጣን ላይ በሕይወት እስካሉ ድረስ ለመቆየት ሀገራቸው ላለባት ምጣኔ-ሃብታዊ እና ሌሎችም ችግሮች እራሳቸውን ብቸኛ አማራጭ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ ይህንን ለማድረግ አብዛኛዎቹ መሪዎች ሕዝብ በከፈለው ግብር የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙኃንን የራሳቸውን ተረክ ለመፍጠር ይጠቀሙበታል፡፡ እነሱ ከሌሉ ሀገሪቷ የምትገባበትን ‹ሲኦል›  ይሰብኩበታል፡፡ ይህ ብቻ አይበቃቸውም፡፡ ምንም ዓይነት የተለየ ተረክ ለሕዝብ እንዲደርስ አይፈቅዱም፡፡ የሐሳብ አሀዳዊነትን በሕዝብ ላይ ለመጫን ይመቻቸው ዘንድ የበይነ-መረብ ማጥለል፣ የተለየ ሐሳብ ያላቸውን ጋዜጦች፣  መጽሔቶች ይዘጋሉ፤ ጋዜጠኞችን ያዋክባሉ፣  ያስራሉ፡፡ በዚህም የተነሳ ስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ሀገርን የሚጠቅም ነው ብለው የሚያወጧቸው ምጣኔ-ሀብታዊ (ሌሎችም) ፖሊሲዎችን የተለየ ምልከታ ሰጥቶ ጥቅሞቹን እና ጉድለቶቹን ተንትኖ እና ከሕዝብ ፍላጎት ጋር ያላቸውን መጣጣም አመዛዝኖ ለሕዝብ የሚያቀርብ አማራጭ እንዳይኖር ያደርጋሉ፡፡ እናም ፖሊሲዎች መታረም ከሚችሉት ህፀፆቻቸው ጋር በሰሠሯቸው ሰዎች ተደጋግመው ከተወደሱ በኋላ ወደሥራ ይገባሉ፡፡

እነዚህ መሪዎች አንድ መሠረታዊ የሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮን ዘንግተዋል፡፡ ማንኛውም ጤነኛ ሰው የሚቀበለውን መረጃ እንደተሰጠው አይውጠውም፡፡ ሁልግዜም ባይሆን ባመዛኙ፣  የሰው ልጆች የሚሰጣቸውን መረጃ ማመዛዘን ይፈልጋሉ –  በተለይም ድጋፍ መስጠት/አቋም ሊይዙበት ለሚፈልጉት ጉዳይ ሲሆን፡፡ አማራጭ ትንተና ያጡ ዜጎ ችአንድ አንዳንዶቹ (ጥቂቶቹ) የራሳቸውን ትንተና በመስጠት አቋም ሲወስዱ አብዛኞቹ ለድጋፍም ሆነ ለተቃውሞ የሚበቃ አቋም ለመውሰድ በቂ ትንተና ለማግኘት ይቸገራሉ፡፡በመጨረሻም ፖሊሲውን ተፈፃሚ ለማድረግ የሕዝብ ተሳትፎ/ድጋፍ አጥሮናል ብለው የሚያማርሩ የመንግሥት ድምፆችን መስማት እንጀምራለን፡፡

ምጣኔ ሃብት እና ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት

እ.አ.አ 1989 ድሬዝ እና ሴን የተባሉ የምጣኔ ሀብት ተመራማሪዎች ባያደረጉት ጥናት ነጻ መገናኛ ብዙኃን ባለበት ሀገር አንድም ግዜ ረሀብ ተከስቶ እንደማያውቅ ጠቁመዋል፡፡ ይህንንም ሲደግፉ ነጻ የሆነ የመረጃ ፍሰት ባለባቸው ሀገራት መንግሥታትን (ዴሞክራሲያዊ ባይሆኑም እንኳን) ከሕዝብ የሚመጣ ጫና ውስጥ ስለሚከታቸው እና ይህንንም ለማስወገድ ሲሉ ቀድመው የሕዝብን ጥያቄ የሚመልስ እርምጃ ስለሚወስዱ እንደሆነ ይተነትናሉ፡፡ ኢሻም፣ ካፍ ማን እና ፕሪቼት የተባሉ ምሁራን እ.አ.አ  1997 ባደረጉት ጥናት መሠረት ደግሞ ግለሰባዊ ነጻነቶች  (ሐሳብን የመግለፅን ጨምሮ) ማክበር በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን ምጣኔ-ሃብታዊ ውጤት  (Project’s Rate of return) እስከ 20 በመቶ ያክል ድረስ ይጨምረዋል፡፡ እንደነዚሁ አጥኚዎች ትንተና መሠረት ግለሰባዊ መብቶችን  (ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ/የመሰብሰብ ነፃነት፣ ሐሳብን በነፃነት የመያዝ እና የመግለጽ፣ ሕዝባዊ ጉዳዮች ላይ በነፃነት የመሳተፍ እና ነፃ ማኅበር ማቋቋም) አለማክበር በእኩል መጠን ከሚከሰት የዓመታዊ ምርት መቀነስ፣ የበጀት እጥረት ወይንም የወጪ እና ገቢ ንግድ ላይ ከሚያጋጥም ንዝረት ባልተናነሰ ሁኔታ በመንግስት የሚካሄዱ ፕሮጀክቶች ውጤታነት ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡

እንደ በመንግስት የሚተዳደሩ ፕሮጀክቶች ባይሆንም በግል ባለሀብቶች እና ተቋማት የሚካሄዱ ንግዶች ሐሳብን በነጻነት መግለጽ በሚቻልበት ሀገር ለገበያ የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች እና አገልግሎቶች የኅብረተሰቡን ደኅንነት ወይንም ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል እንዳይሆኑ ከፍ አድርገው ይጠነቀቃሉ፡፡ በግድየለሽነት ወይንም በአጭር ጊዜ ለመክበር በሚያደርጉት ሙከራ የህብረተሰቡን ደህንነት ወይንም ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል ዕቃ ወይንም አገልግሎት ቢያቀርቡ ነፃ መገናኛ ብዙሃን ሁኔታውን በማጋለጥ ህብረተሰቡን ከጉዳት ይጠብቃሉ፡፡

የሳንሱርዋጋ

የሐሳብ ብዝኃነትን በመቆጣጠር ሕዝብ እነሱ የሚሉትን ብቻ እየሰማ እንዲነዳ የሚፈልጉ መንግሥታት ሐሳብን ለማፈን ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ሐሳብ ለማፈን ከከሚጠቀሙባቸው መንገዶች በይነ መረብን ማጥለል እና ጦማሮች እዳይከፈቱ ማገድ፣ በይነመረብን በመጠቀም ዜጎች ላይ መሰለል እና በሳተላይት የሚተላለፉ የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ስርጭቶች ሞገዶችን መከልከል ይጠቀሳል፡፡

የአውስትራሊያ መንግስት  በ2009 ዓ.ም ሊተገብረው ያሰበው የበይነ መረብ ማጥለልን በተመለከተ ዴቪድ በርድ የተባለ ጦማሪ እንደጻፈው በበይነ መረብ የሚተላለፉ መረጃዎችን ለማጥለል ጥቅም ላይ የሚውሉት ቴክኖሎጂዎች የበይነ መረብ አገልግሎት ፍጥነትን ከ2 በመቶ እስከ 70 በመቶ ይቀንሳሉ፡፡ የማጥለል ሥራውን  ‹በውጤታማነት የሚያከናውኑት› ቴክኖሎጂዎች ደግሞ ፍጥነቱን በደንብ የሚቀንሱት ናቸው፡፡

ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ደግሞ ኒውዮርክ ታይምስ አንድዜና ለኢትዮጵያዊያን ይዞልን ወጥቶ ነበር፡፡ ፊንፊሸር የተባለ በይነ መረብን በመጠቀም ዜጎች ላይ ስለላ ለማድረግ የሚያስችል የረቀቀ ቴክኖሎጂን እንደሚጠቀሙ ከታወቁት  10 ሀገራት አንዷ ሀገራችን መሆኗን፡፡ እንደዘገባው ቴክኖሎጂውን ለመግዛት ከ350ሺህ  በላይ የአሜሪካን ዶላር ወጪ ማድረግ ይጠይቃል፡፡ ቁጥር አንድ ጠላቷ ድህነት ለሆነ ሀገር ሕገ-መንግሥቱን ጥሶ ዜጎች ላይ ለመሰለል ይህን ያህል ወጪ ማውጣት እውነትም አሀዳዊ ተረክ ለመፍጠር ምን ያህል ርቀት እንደሚኬድ ማሳያ ነው፡፡

በሳተላይት የሚተላለፉትን ሬዲዮ እና የቴልቪዥን ስርጭትን ለመደገፍ ምን ያህል የተወሳሰበ ቴክኖሎጂ እንደሚያስፈልግ እና እሱም ምን ያህል ወጪ እንደሚያስወጣ መገመትም ቀላል ነው፡፡

ምንም እንኳን አከራካሪ ቢሆንም ዜጎች በነጻነት ሲያስቡ እና ሐሳባቸውን በነጻነት መግለጽ ሲችሉ አዳዲስ እና ውጤታማ የንግድ ሐሳቦች ማፍለቅ ቀላል ይሆንላቸዋል፡፡ ይህም ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት መንፈግ ከሚያስከፍሉት ቀጥተኛ ያልሆኑት ዋጋዎች ውስጥ ሊካተት ይችላል፡፡

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/6302

posted by Tseday Getachew

የአዲሱ ፓትርያርክ ምርጫ እና የቅዱስ ሲኖዶስ የውስጥ ውዝግብ

ቤተ ክርስቲያን ስትጠራኝ እምቢ እላለኹ ወይ ! ! !›› /ብፁዕ አቡነ ማትያስ/

 • ‹‹አጃቢ ነን!›› /ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል/
 • ‹‹እንኳን አይደለም ፕትርክናው ጵጵስናውም ከብዶኛል፤ እኔ እጠፋለኹ›› /ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ/
 • ‹‹እኛ መናጆ ተብለን ነው የገባነው፤ የሚመረጠው አባ ማትያስ ነው›› /ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ/
 • ‹‹ነገ በታሪክ የሚጠየቅና የሚወገዝ ሲኖዶስና አባት መኖር የለበትም›› /ብፁዕ አቡነ ገብርኤል/

ከላይ በዋናው ርእስ የተመለከተው÷ ቁጭት እንጂ አቅም ያነሳቸው ንግግሮች የተሰሙት ትላንት፣ የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም በፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴው በቀረቡት ዕጩዎች ላይ ለመወያየት የተሰበሰበው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውል ያለው ግልጽ ውሳኔ ላይ ሳይደርስ ከቀትር በኋላ በተጠናቀቀበት ወቅት ነው፡፡

በስብሰባው ሂደት÷ ለፕትርክናው የተሠየሙትን ብፁዕ አቡነ ማትያስን ጨምሮ ተሳትፎ በነበራቸው ብፁዓን አባቶች መካከል የነበረው የከረረ የቃላት ልውውጥ፣ ተሳትፎ ባልነበራቸው ብፁዓን አባቶች ላይ የታየው ስጋትና ድብታ፣ በኮሚቴው ዋና ጸሐፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ ምትክ የኮሚቴውን ሪፖርት ያቀረበው የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊው ለቅ/ሲኖዶሱ ጠረጴዛና ለአጀንዳው ታላቅነት የማይመጥን፣ ውክልናውና ያጸደቀለትን ማኅበር የሚያስንቅና የሚያስወቅስ ደርዝ የሌለው ንግግር፣ በዋናነትም ስብሰባው የተጠናቀቀበት ውል አልባ ኹኔታ ነው ይህን የሐዘን ንግግር ያናገረው፡፡ በዚህ ቃል ሲናገሩ ከተሰሙት አረጋውያኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጥቂቱን ለመጥቀስ÷ አቡነ አትናቴዎስ፣ አቡነ ኤርሚያስ፣ አቡነ አረጋዊ፣ አቡነ ኤፍሬም እና ከዕጩዎች አንዱ አቡነ ማቴዎስ ናቸው፡፡

ስብሰባው ጠዋት 3፡00 ላይ በውዳሴ ማርያም፣ መልክአ ኢየሱስ እና መልክአ ማርያም ጸሎት ከተከፈተ በኋላ ዐቃቤ መንበሩ የዕለቱን የስብሰባ አጀንዳ ሲያስተዋውቁ፣ ‹‹የአስመራጭ ኮሚቴውን ሪፖርት ሰምተን ለማጽደቅ ነው፤›› በሚል ነበር ያስጀመሩት፡፡ የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት ተጠርተው ገብተው በሕዝብ ግንኙነት ሓላፊው በኩል የዕጩዎች አመራረጥ፣ ዝርዝርና ማንነት በንባብ ከተሰማ በኋላ የነበረው የስብሰባው ድባብ ግን፣ ሰምቶ ማጽደቁ  ቀርቶ የተጋጋሉ ውይይቶችንና ትችቶችን ያስተናገደ፣ ከሕዝብ ግንኙነት ሓላፊው በቀር ብዙኀኑ የኮሚቴው አባላት አንዳች የውስጥ ክፍፍልን በሚያሳብቅ አኳኋን (በተለይም ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ) በእጅጉ አዝነውና ተክዘው የታዩበት፣ ኮሚቴው ከብፁዓን አባቶች ለቀረቡለት ጥያቄዎች የተረጋገጠ መልስ ሊሰጥ ያልቻለበት አሳዛኝ ኹኔታ ነበር፡፡

ኮሚቴው የተረጋገጠ ወይም በቂ ያልኾነ ምላሽ ሊሰጥባቸው ያልቻለባቸውና ለተካረረ መንሥኤ የኾኑ ዋነኛ ነጥቦች፣ የመጀመሪያው÷ ዕጩ ፓትርያሪኮች የቀረበቡበት መንገድ የምርጫ ሕገ ደንቡ ተሟልቶ ያልተፈጸመበት መኾኑ ነው፤ ሁለተኛው÷ የምርጫው ሂደትና ጠቅላላ ኹኔታ ለውጭ ኀይሎች ተጽዕኖ እና ለውስጥ ቡድኖች ፍላጎት የተጋለጠ  መኾኑ ነው፡፡ እኒህን አከራካሪ ነጥቦች በየጊዜው ባወጣናቸው ዘገባዎች እያጋለጠናቸው ቆይተናል፤ እስኵ አሁን ደግሞ በስብሰባው ሂደት ከተንሸራሸሩት ሐሳቦች አንጻር በመጠኑ እንመልከታቸው፡፡

በምልአተ ጉባኤው ስብሰባ ከዋነኛ አነጋጋሪ ነጥቦች አንዱ÷ የምርጫው ሂደትና ጠቅላላ ኹኔታ ለውጭ ኀይል ተጽዕኖ እና ለውስጥ ኀይሎች ጥቅማዊ ፍላጎት የተጋለጠ መኾኑ ነው፡፡ የውጭ ኀይል ሲባል ሌላ ማንም ሳይኾን የመንግሥት ተጽዕኖ ማለታችን ነው፡፡

ተጽዕኖው በግልጽ ሲቀመጥ÷ አቋም ያላቸውን የአስመራጭ ኮሚቴውን አባላት በተናጠል ማስፈራራት፤ በበርካታ አህጉረ ስብከት በተለይም በሐዋሳ፣ ናዝሬት፣ አሰበ ተፈሪ፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ አሶሳ፣ ባሕር ዳር እና ደሴ መራጮች ‹‹የመንግሥት ምርጫ ናቸው›› ለሚባሉት ብፁዕ አቡነ ማትያስ ድምፅ እንዲሰጡ፣ ድምፃቸውን ለብፁዕ አቡነ ማትያስ ለመስጠት ፈቃደኛ ካልኾኑ በሌሎች እንዲቀየሩ፣ ፈቃደኛ ኾኑም አልኾኑ ሰንበት ት/ቤቶችን በመወከል በመራጭነት የተመዘገቡ ወጣቶች የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ከኾኑ በአስቸኳይ ከዝርዝሩ እንዲወገዱና የማኅበሩ አባላት ባልኾኑ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች እንዲተኩ፤ ከፍተኛ የካህናትና ምእመናን ጥቆማ ያገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ራሳቸውን ማሸማቀቅና ‹‹ዐርፈው እንዲቀመጡ›› በዛቻ ማስፈራራት፣ በምትኩ እነርሱ በሚመሯቸው ሀ/ስብከት መንግሥት ለወደዳቸው ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኀይልና ሽብር በመንዛት የሚካሄደው የድጋፍ ቅስቀሳ እንዲጧጧፍ መርዳት በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

በምሳሌነት የቀረቡት እኒህ የመንግሥት ተጽዕኖ መልኮች በትላንቱ ስብሰባ ጥቂት በማይባሉ ሊቃነ ጳጳሳት ተረጋግጧል – ‹‹ሥራ አስኪያጆቻችን የደኅንነት ወከባና እንግልት ተፈጽሞባቸዋል›› በሚል፡፡ ከዚህ በመነሣት በትላንቱ ስብሰባ ለአስመራጭ ኮሚቴው ከቀረበሉት ጥያቄዎች አንዱ ‹‹መንግሥት ጣልቃ ገብቷል ወይስ አልገባም?›› የሚል መኾኑ ተገቢ ነው፡፡ ግና ምን ያደርጋል፤ ከአስመራጭ ኮሚቴው አባላት አንዳቸውም ለጥያቄው ምላሽ ሊሰጡ አልደፈሩም፡፡ [ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በምርጫው ወቅታዊ ኹኔታ ላይ ለመወያየት አስቸኳይ ስብሰባ በተጠራው የማኅበረ ቅዱሳን የአመራርና የአስፈጻሚ አባላት ጉባኤ ላይ ሪፖርት ያቀረበው የአስመራጭ ኮሚቴው ሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ ግን፣ የመንግሥትን ተጽዕኖ የሚቀርቡ ዜናዎች ፍጹም ሐሰት መኾናቸውን፣ በምትኩ ‹‹እኛ ሄድን እንጂ መንግሥት አልጠራንም›› በሚል በርካታ ዘገባዎችን አስተባብሎ ነበር፡፡]

ከዕለቱ የምልአተ ጉባኤው ስብሰባ ብርቱ ተናጋሪዎች አንዱ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ግን፣ ‹‹መንግሥት ፓትርያሪክ አይመርጥልንም›› ሲሉ በአጽንዖት አሳስበዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በበኩላቸው በአብዛኞቹ አህጉረ ስብከት የብፁዕ አቡነ ማትያስን አስቀድሞ መመረጥ የሚያሳዩ፣ ሕገ መንግሥቱን የሚጥሱ ያልተገቡ ተግባራት በመታየት ላይ መኾናቸውን አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ ብፁዕነታቸው ከዚህ በማያያዝ ሕጉ እንደኾን አንድያውን የተጣሰ በመኾኑ ከዚህ በኋላ የሽፋን ምርጫ ሳያስፈልግ አቡነ ማትያስን ለመሾም የፈለገው አካል በቀጥታ በደብዳቤ እንዲሾማቸው እንጂ ሂደቱ የምልአተ ጉባኤው ውሳኔ እንደማያስፈልገው፣ እንደማይገባውም አስታውቀዋል፤ አቋማቸውንም ሲያስረግጡ በውሳኔው ላይ ፊርማቸውን አስቀምጠው በምርጫው እንደማይሳተፉ ገልጠዋል፡፡

በዚሁ መንፈስ ከተናገሩትና ከብፁዕ አቡነ ማትያስ ዘኢየሩሳሌም ጋራ ቀጥተኛ ምልልስ ካደረጉት  ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አንዱ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ ሢመተ ፕትርክናው ከመንግሥት ተጽዕኖ ነጻ ካልኾነ በቀጣይ የሚኖረውን ኹኔታ የሚያመለክት ነው፡፡ ብፁዕነታቸው ለንግግራቸው መነሻ ያደረጉት በቂ ምላሽ ካልተሰጠባቸው የምልአተ ጉባኤው ጥያቄዎች አንዱ በኾነው የብፁዕ አቡነ ማትያስ ዜግነት ጉዳይ  ላይ ለሰጡት ምክር ብፁዕ አቡነ ማትያስ የሰጡት ምላሽ ነው፡፡

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፡- ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተሰጠ የተባለው ደብዳቤ (ብፁዕ አቡነ ማትያስ በሐምሌ 2004 ዓ.ም ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደተቀበሉት ተነግሯል) አሜሪካዊ ዜግነትዎን ለመመለስዎ ማረጋገጫ አይኾንም፡፡

ብፁዕ አቡነ ማትያስ፡- ከዚህ በላይ ምንድን ነው የምትፈልጉት?

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፡- ደብዳቤ ማረጋገጫ ሊኾን አይችልም፡፡ ደርግን አልፈልግም ብለው ዜግነትዎን ቀየሩ፡፡ አሁን ደግሞ አሜሪካዊ ዜግነቴን መልሻለኹ፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚሉ ከኾነ ማረጋገጫው ፓስፖርቱ ነው፤ ፓስፖርቱን ያምጡ?

ብፁዕ አቡነ አብርሃም፡- የውጭ ጉዳዩ ደብዳቤ ዜግነቱ እንደተመለሰ ይገልጻል፤ ሊመልስ አይችልም፤ ጉዳዩ ሊፈጸም የሚችለው በአሜሪካው እንጂ በዚህ አይደለም፤ ስለዚህ የውጭ ጉዳይ ደብዳቤ ማስረጃ ሊኾን አይችልም፤ ሰርቲፊኬቱን ያምጡ፡፡

ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፡- እንዴት ሊሰጥ አይችልም፤ ከዚህ በላይ ምን ይምጣ? ሌላ ተልእኮ አላችኹ?

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፡- እኔ ያን እስካላየሁ አልመርጥዎትም፣ ብፁዕ አባታችን፤ ይህን ይወቁት፡፡

ብፁዕ አቡነ ማትያስ፡- ቤተ ክርስቲያን ስትጠራኝ እምቢ እላለኹ ወይ?

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፡- ገና ዕጩ ነዎት፤ እርሱም ቢኾን በአበው ሥርዐት ሹመት ሲሰጥ አልኾንም፤ አይገባኝም ነው የሚባለው፡፡ ለኅሊናችንና ለቤተ ክርስቲያናችን መኖር መቻል አለብን፡፡ አለበለዚያ ቀድሞ በደርግ ጳጳሳቱና ካህናቱ እየተጠሩ አቡነ መርቆሬዎስን ምረጡ ብሎ እንዳደረገው የእርስዎም ሹመት እንደዚያ ነው የሚኾነው፡፡ ፓትርያሪክ በመንግሥት ተሾመ ተብሎ በሕዝቡ ዘንድ ጥላቻ መታየቱ በአራተኛው ፓትርያሪክም ያየነው ነው፡፡ ይህ ተቀባይነት የለውም፤ መደገምም የለበትም፤ ነገ የሚወገዝ፣ ነገ በታሪክ የሚጠየቅ አባትና ሲኖዶስ መኖር የለበትም፡፡ በሕገ መንግሥቱ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ እንደማይገባ ተደንግጓል፤ ስለዚህ ገብቶ ከኾነ እጁን እንዲያነሣ እንጠይቃለን፡፡

በአስመራጭ ኮሚቴው ምላሽ የተነፈገው የመንግሥት ተጽዕኖ ጉዳይ እንግዲህ ይህን ያህል አነጋግሯል፤ ‹‹የቀረበባቸውን ተቃውሞ በዝምታ አልፈውታል›› በሚል በአንዱ ጦማሪ ያልተጣራ ዘገባ የተሠራላቸው አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስም ይህን ያህል ተከራክረዋል፤ ‹ጥሪው›ም የተሰማቸው ከዕጩነት ባሻገር ጮኾና ጎልቶ እንደኾነ አረጋግጠውልናል፡፡ ከዕጩነት ባሻገር የተሰማው ጥሪ አቡነ ማትያስ ቀጣዩ ፓትርያሪክ እንደሚኾኑ ነው፡፡

ብፁዕነታቸውን ለማስመረጥ የተደረገው ሽርጉድ ግን በአስመራጭ ኮሚቴው የዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱትን ሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት ደስ አላሰኛቸውም፡፡ የኮሚቴው ሪፖርት በንባብ ተሰምቶ እንደተጠናቀቀ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ÷ ‹‹በአበው ገዳማዊ ሥርዐት በዕጩነት መመረጥ አይገባኝም፤ እንኳን አይደለም ፕትርክናው ጵጵስናውም ከብዶኛል፤ ይህን ነገር ከሰማኹ ጀምሮ ብርክ ይዞኛል፤ እኔን ተዉኝ፤ እኔ እጠፋለኹ፤›› ብለዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ  በበኩላቸው÷ ‹‹እኛ መናጆ ተብለን ነው የገባነው፤ የሚመረጠው አባ ማትያስ ነው፤ ይህ መንፈስ ቅዱስ የተለየው፣ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ያልጠበቀ ምርጫ ነው፤ ያኔ በዕጣ ይኹን ብዬ ተከራክሬ ነበር፤ የኾነ አካል አባ ማትያስን አምጥቶ ያስቀምጣል፤ እኔ መናጆ አይደለኹም፤ መናጆ አልኾንም፤›› በሚል አጽንዖት ተናግረዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል  ለየት በሚለው የአነጋገር ዘዬአቸው ‹‹ያው አጃቢ ነን፤ እናየዋለን›› በሚል ምፀታዊ መንፈስ መልሰዋል፡፡

አምስቱ ዕጩዎች የተመረጡት ብቃትን ዋና መነሻ በማድረግ አይደለም፡፡ ምርጫው የተመሠረተው በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የፓትርያሪክ ምርጫ አከፋፈል በትውልድ አካባቢ በተለዩ ዞኖች/ትግራይ፣ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ሸዋ እና ኦሮሚያ(?) መኾኑ ተገልጧል፡፡ ከትግራይ ብፁዕ አቡነ ማትያስ፣ ከጎንደር ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ ከወሎ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣ ከሸዋ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ እና ከኦሮሚያ(?) ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ መኾኑ ነው፡፡ የዕጩዎች ምርጫው ለቤተ ክርስቲያን ተገቢ ከኾነው መንፈሳዊ ብቃት ይልቅ የጎሳ/ትውልዳዊ ማንነትን የተከተለ፣ የጊዜው ፖሊቲካዊ አስተሳሰብና ስሜት የተጫነው መኾኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህም ኾኖ የኮሚቴው አሠራር ዕጩዎቹ ያላቸውን ስብጥር ያህል ሁሉንም በሁሉም አካባቢ በእኩልነት የሚያስተዋውቅ አልነበረም፤ የግል መረጃዎቻቸውን፣ ታሪካቸውንና ለዕጩነት ያበቃቸውን የሥራ ፍሬዎቻቸውን ከመመዘኛው አንጻር እኩል አጽንዖት ሰጥቶ በተሟላ ይዘት የቀረበበት አልነበረም፡፡

የጉባኤው የክርክር ማእከል የነበሩትን ብፁዕ አቡነ ማትያስ የግል መረጃና ታሪክ ሲታይ ዕድሜያቸው (ከ75 በላይ መኾን አለመኾኑ) በግልጽ ተረጋግጦ አልቀረበም፤ እንደ አንዳንድ ምንጮች ጥቆማ የነበራቸው የግል ማኅደርም እንዲጠፋ ተደርጓል፤ ዜግነታቸውን ስለመመለሳቸው ቤቱን ያሳመነ ምላሽ አልተሰጠም፡፡ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ‹‹ሁለት ማትያሶች አሉ፤ ኮሚቴው በማትያስ ላይ ማትያስ የተሾመበትን ታሪክ ለምን አልገለጸም?›› የሚል በሦስተኛው ፓትርያሪክ ዘመን ተላልፎባቸው የነበረውን ውግዘት የሚያስታውስ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀራቢው ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በተቃውሟቸው የብፁዕነታቸውን የዕርግናና የጤንነት ይዞታ  የተመለከተ ጉዳይ አንሥተዋል፡፡ ብዙዎቹ ነጥቦች ከፓትርያሪክ ምርጫው ሕገ ደንብ አንጻር በተለያየ ጊዜ ስለዳሠሣናቸው እንለፋቸውና ‹‹ሁለት ማትያሶች አሉ›› ለሚለውና የብፁዕ አቡነ አብርሃም ጥያቄ በስብሰባው ላይ ሳይናገሩ ዋሉ ተብሎ የተዘገበላቸው ብፁዕ አቡነ ማትያስ÷ ‹‹እርሱም የኾነብኝ ደርግን ስለተቃወምኹ ነበር፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤ ይልቅዬስ ጥያቄውን በዝምታ ያለፈው ኮሚቴው ነበር እንጂ እርሳቸውማ እንዴታ!

ትኩረት ሳቢ የኾኑ ሌሎች ሁለት ጥያቄዎች፡-

 • ‹‹በአምስቱ ዕጩዎች ተስማምታችኹ የተፈራረማችኹበት ቃለ ጉባኤ አለ ወይ?››
 • ‹‹ብፁዕ አቡነ ማትያስን የጠቆሙ ካህናትና ምእመናን አሉ ወይ? ካሉስ ብዛታቸው ምን ያህል ነው?››

ኮሚቴው በዕጩዎቹ ማንነት ላይ በአንድ ድምፅ፣ ያለልዩነት  የተፈራረመበት ቃለ ጉባኤ ስለመኖሩ ከኮሚቴው የተሰጠ ምላሽ ስለመኖሩ አልተዘገበም፡፡ ለነገሩ እንዴት ሊኖር ይችላል? በምልአተ ጉባኤው ስብሰባ ላይ ዋና ጸሐፊው ሊቀ ማእምራን ፈንታሁን ሙጩ አልታዩም፤ በሕመም ምክንያት ነው ቢባልም የሁሉ ገባሪ ኾኖ ከሚታየው የሕዝብ ግንኙነቱ ሓላፊ ጋራ እንዳልተስማሙ ተሰምቷል፤ ከታዋቂ ምእመናን የተወከሉት በተለይም ቀኝ አዝማች ኀይሉ እንዲያውም ራሳቸውን ስለማግለላቸውና በልዩነታቸው ምክንያት በሰበብ አስባቡ እንደሚጠፉ ነው የሚታወቀው፡፡ ኾኖም የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊው ቀደም ሲል በጠቀስነው የተወከለበት ማኅበር የአመራሮችና አስፈጻሚዎች የጋራ ስብሰባ ላይ÷ ‹‹ልዩነት አይደለም በድምፅ ብልጫ እንኳ የወሰነው ውሳኔ የለም፤ ሁሉንም በስምምነት ነው የወሰነው፤›› በማለት ተናግሯል፡፡

ብፁዕ አቡነ ማትያስን የጠቆሙ ካህናትና ምእመናን በቁጥር ቢያንሱም ቢበዙም ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል፤ ለብፁዕነታቸው የተሰጠውን ጥቆማ ጨምሮ ኮሚቴው ስለጥቆማው ለተጠየቀው ጥያቄ የሰጠው ምላሽ ስለመኖሩም አልተሰማም፤ ከዚህ ጋራ በተያያዘ የካህኑና ምእመኑ ጥቆማ ተገቢውን ዋጋ እንዳላገኘ ተነግሮታል፡፡

በትላንቱ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ በአስመራጭ ኮሚቴው ለቀረበው የዕጩዎች ዝርዝር ግልጽ ድጋፋቸውን በመስጠት ቅ/ሲኖዶሱ እንዲያጸደቀው ጠንካራ ድጋፍ ሲሰጡ የዋሉት÷ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ እና ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ናቸው፡፡ ከእኒህ ብፁዓን አባቶች መካከል በአንድ ወቅት ‹‹የደርጉ ጳጳሳት›› ተብለው ሲታሙ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ለብፁዕ አቡነ ማትያስ ስሜት የተቀላቀለበት ከፍተኛ ድጋፍ ሲሰጡ ተስተውለዋል፤ መብታቸው ነው፤ ወዳጅነታቸው፣ አባታዊ ውሳኔያቸው ሊከበር ይገባል፡፡ ቁም ነገሩ፣ ሥልጡንነቱ በአንጻሩ ሌላውን አባት በመደገፍ ተቃራኒ አቋም የያዙ አባቶችን መብትና ውሳኔ ማክበር ነው፡፡ ብፁዕ አቡነ ኤልያስም የመንግሥት ጣልቃ ገብነትን ሲኰንኑ የነበሩትን ብፁዕ አቡነ አብርሃምን÷ ‹‹መንግሥት፣ መንግሥት አትበል፤ ራስኽን ቻል፤›› ብለዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የተናገሩት ተግሣጽ÷ በደረቁ እውነት ነው፤ ተግሣጹ ግን ተግሣጽ ከመኾኑ በቀር ራሳችንን እንዳንችል ካደረጉን ምክንያቶች አንዱ የኾነውን የመንግሥት ተጽዕኖ እንዴት መግራት እንደምንችል /ሕገ መንግሥቱ ወይም ለብዙዎች እንደሚመስላቸው ጨርሶም ነጻ መኾን ስለማይቻል/ አያሳይም፡፡

ኮሚቴው ምላሽ ከሰጠባቸው ይልቅ ያልሰጠባቸው ጥያቄዎች በዝተው ዝምታው፣ አንገት መድፋቱ፣ መተከዙ፣ መቆዘሙ (በተለይ በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ እና በብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ላይ ጠንክሮ ታይቷል፤ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ የተቃውሞ/ልዩነት ቃል ቢናገሩ ምላሳቸው እንደሚቆረጥ የሚገልጽ ጽኑ የማስፈራሪያ ቃል ከአንድ ጎምቱ ባለሥልጣን እንደደረሳቸው ተዘግቧል፤) ጠንቶ በታየ ጊዜ የኮሚቴው ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ቢጨንቃቸው ሁሉንም ሥራ ለቅ/ሲኖዶሱ ምልአተ ጉባኤ አሳልፎ የመስጠት ንግግር ተናግረዋል፡- ‹‹የኮሚቴው አካሄድ ሕጉን ሥርዐቱን ካልጠበቀ የማስተካከል የማረም የመጨረሻ ሓላፊነቱ የምርጫው ባለቤት የኾነው ቅ/ሲኖዶሱ ነው፤ አስፈላጊውን ውሳኔ መስጠት ይችላል፤ እኛ ያልነው ይኾናል፤ ሌላ ነገር አንነጋገር፡፡››

የምልአተ ጉባኤው መጨረሻ ግን÷ በአንድ በኩል፣ አስመራጭ ኮሚቴው ያቀረበው ሥራ/ሪፖርት ምንም ዐይነት ውሳኔ መስጠት እንደማያስችል በመግለጽ የውሳኔውም የምርጫውም አካል እንደማይኾኑ  ግልጽ ያደረጉ ብፁዓን አባቶች የታዩበት ነው፡፡ እኒህ አባቶች አስመራጭ ኮሚቴው የሕግና የታሪክ ተጠያቂ እንደሚኾንም አስጠንቅቀዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹ነገሩ ከተበላሸ ቆይቷል፤ ከተበላሸ ስለቆየ እናጽድቀው›› የሚሉ አባቶች የታዩበት ነው፡፡ እኒህ አባቶች ውሳኔው አጽድቀው እንደወጡ ተናግረዋል፡፡ በሐተታችን መግቢያ እንዳመለከትነው ደግሞ÷ ‹‹ያሳዝናል! ያሳዝናል! ያሳዝናል! ቤተ ክርስቲያናችን እንዲህ ኹና አታውቅም፤ ይፋረደን፤ ይፋረደን!!›› የሚል ቁጭት ያሰሙ ሽማግሎች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ነበሩ፡፡

የኾነው ኾኖ ቃለ ጉባኤ በውል ያልተያዘበት፣ የተጨበጠ ውሳኔም ያልተላለፈበት የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ነበር፡፡ ቃለ ጉባኤው ገና ተጽፎ በነገው ዕለት ለፊርማ የሚቀርበው በአስመራጭ ኮሚቴው አባላት መኾኑ ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፡ ሐራ ዘተዋህዶ

http://ethioforum.org

posted by Tseday Getachew

የደህንነት መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ከአገር እንዳይወጡ አዘዘ

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ አየር መንገድ 15 የትኬት እና 30 የኤርፖርት ሰራተኞችን ከስራ ካባረረ በሁዋላ ከአገር እንዳይወጡ አገደ። ከአየር መንገድ የውስጥ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ሀብታሙ ጫኔ፣ ዳንኤል ገበየሁ፣ ኢማን ያሲን፣ ኤደን ካሳየ፣ ቤዛ ኤፍሬም፣ ይገርማል ታደሰ፣ ሰለሞን ይብራህ፣ ክንፈ ሚካኤል ሽጉጤን ጨምሮ በርካታ ሰራተኞች ከስራ የተባረሩ ሲሆን ፣ አየር መንገዱ ለደህንነት እና አሚግሬሽን መስሪያ ቤት በጻፈው ደብዳቤ ሰራተኞቹ ከአገር እንዳይወጡ አሳግዷል።

ሰራተኞቹ ከአገር እንዳይወጡ ሲታገዱ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች መካከል ለህዳሴው ግድብ ገንዘብ ለማዋጣት ፈቃደኛ አለመሆን፣ የድርጅቱን ሚስጢራዊ መረጃዎች የአገር ጠላት ለሆኑት የሽብርተኞች ሚዲያዎች ለኢሳት እና ለፍትህ ጋዜጣ መስጠታቸው፣ እንዲሁም የባለራእዩን መሪ የአቶ መለስ ዜናዊን ራእይ ለማሳካት በሚል የተነደፈውን የስድስት ቀን የነጻ የስራ አገልግሎት እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆን የሚሉት ይገኙበታል። የሰራተኞቹ ፓስፓርት ቁጥር ለኢሚግሬሽንና ደህንነት ክፍል በመላኩ ሰራተኞች ከአገር ለመውጣትና ራሳቸውን ለማዳን አልቻሉም።

ከዚህ ቀደም ከስራ ከተባረሩት መካከል ከሙስሊሙ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የታሰሩት ሰባ ማይልስ ስራ አስኪያጅ እስካሁን አልተፈቱም።

አካሉ አሰፋ፣ አንተሰናይ አማረ፣ ቤተልሄም ተፈራ፣ ቤተልሄም ጌታቸው፣ ኤደን በየነ፣ ኤደን ካሳየ፣ ኢማን ያሲን፣ ሳሙኤል እንዳለ፣ ሶሎሞን በቀለ፣ አይዳ ዘልኡል፣ አማኑኤል በልስቲ፣ አማኑኤል ነጋሽ፣ አማኑኤል ጸጋው፣ አንዱአለም ግርማ፣ ብርሀኑ ሰሎሞን፣ ቸርነት አለሙ፣ እኑ ገብረእግዚአብሄር፣ ሀይማኖት ንጉሴ፣ ሂሩት መለሰ፣ ቅድስት አበራ፣ ቅድስት ከበደ፣ ማትያስ አድማሱ፣ መቅደስ አበራ፣ ሜላት አስራት፣ ትንግርት ደምሴ፣ ሳምራዊት ገረመው፣ ሰሚራ አማን፣ ተዘራ ወርቁ፣ ወንዶሰን ሀብቴ፣ ዮሀንስ ፍሰሀ እና አልአዛር ተክለ ሚካኤል ከአገር እንዳይወጡ ትእዛዝ ከተላለፈባቸው መካከል ይገኛሉ።

የተባረሩ ሰራተኞችን በተመለከተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስኪያጅን ለማነጋገር ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። አየር መንገዱ ነባር ሰራተኞችን እያባረረ በታማኝ የኢህአዴግ አባላት እየተካ መሆኑን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።

posted by Tseday Getachew

የመናገር ነጻነት ዘመቻው ለህወሃት መራሹ መንግስት ምኑ ነው?

From Borkena blog/ ቦርከና

ሰሞኑን የዞን 9 አባላት የብሎጋቸውን በኢትዮጵያ መከልከል ተከትሎ ከክፈቱልን ያለፈ ፤ መሰረታዊ ሊባል የሚችል ዘመቻ በማህበራዊ ድህረ ገጾች ጀምረዋል፡፡ በዚህ ደረጃ ምላሽ መስጠቱ እና መጠቀም የሚቻለውን መድረክ ተጠቅሞ የችግሩን ጥልቀት ለማመላከት መሞከር ጥሩ ነው። ነገር ግን የመጻፍ እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እየተጠየቁ ያሉትን ቡድኖች(‘ፎርማሊ’ ካወራን መንግስት ናቸው -ያውም ፈላጭ ቆራጪ) ባህሪ  ግምት ውስጥ በማስገባት፤ ዘመቻው እነዚሁ ቡድኖች አምነትውበት በማናለብኝነት የወሰዱትን ርምጃ ከማስቀየር ይልቅ በስነ ልቦናቸው ለተቀረጸው የትምክህት እና የበላይነት አስተሳሰብ ሃሴት የሚሰጥ ሆኖ ስለተሰማኝ ለነሱ ትምክህት ሃሴት ላለማዋጣት ስል በዚህ በዘመቻ አልተሳተፉኩም።

እንኳንስ የመናገር ነጻነት አይደለም ለእምነት ነጻነት ጀርባቸውን ሰጥተው የክስርቲያኑን የእምነት ተቋማት በቁጥጥር ስር አድርገው ሙስሊሙንም እንዲሁ እምነቱን ለመንጠቅ ቤት ለቤት ጭምር አሰሳ የገቡ ሰዎች ናቸው፡፡ የመናገር እና ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ጋር በእጂጉ የተቆራኘ  የጋዜጣ ህትመት ማስቆም ሳያንሳቸው ዜጎችን –ያውም ኩሩ ሀገር ወዳድ ዜጎችን በሽብረተኛነት በመክሰስ ፣ብዙ እንግልት በማድረስ እና ክብራቸውን ጭምር ለማዋረድ በመሞከር ሌሌች ዜጎች የዜግነት ክብር እና ነጻነት  ጥያቄ ቅብጠት እና በህይወት መቀለድ እንዲመስላቸው በማድረግ የባርነትን እስተሳሰብ በደህንነት ተቋማት ፣በህግ ተቋማት እንዲሁም የማህበራዊ ድንዝዝነት በሚያስፋፉ ሌሎች ልማዶች የሚስፋፉበትን መንገድ በስውርም በግልጽም በማበረታታት  የባርነትን መስረት ለማጽናት ሌት ከቀን የሚሰሩ ለመሆናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ ያለ ብዙ ምርምር ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

የህገ-መንግስት ጉዳይ እና የዜጎች መብት ፋይዳ ሳይገባቸው ቀርቶ ነው እንዳይባል፤ ትግል ጀመርንም ጨረስንም የሚሉባቸውን ቀናቶች በብሔራዊ ደረጃ ጭምር እንዲከበርላቸው የሚፈልጉ ናቸው። እንዲያውም ያለባቸውን የስነ-ልቦና ችግር ከሚያመላክቱ ነገሮች  እንደኛው ይሄው ነው። ህወሃት ስልሳ ሺህ  ሰው ሰዋበት የሚሉትን በዓላቸውን የሚያዳንቁትን እና ሰው እንዲያዳንቅላቸው የሚፈልጉትን ያህል ለኢትዮጵያ ነጻነት ከጎጠኝነት በጸዳ በንጹህ የሃገር ፍቅር ስሜት የወደቁ በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያኖች ጉዳይ እንዲነሳም እንዲታወስም እይፈልጉም። ታሪኩ ሲነገር ያሳንሳቸዋላ!የሃሳብ ነጻነት ወደሚያፈኑበት ጉዳይ ስመለስ -የሚያፍኑበት እና ሃሳብ እንደጦር የሚፈሩበት ጉዳይ ምንድን ነው የተባለ እንደሆነ መሳሪያ እንቆ የተኮፈሰ የፓለቲካ ስብዕናቸውን የሚያኮስስ ስለሚመስላቸው። እደፊኛ የሚነፉትን ፕሮፓጋንዳ የሚያስተነፍስ ስለሚመስላቸው። የሃሳብ ልውውጥ ላይ ያለ ስለት ስለሚያስፈራቸው። አንግበው ለተነሱት የትምክህት እና የበላይነት ግንባታ ዓላማ እንቅፋት እንደሆነ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ይመስለኛል። የእምነት ነጻነትም እስከመንጠቅ የሄዱበት ምክንያት ከፍራቻ ውጭ ሌላ ሊሆን አይችልም። የፍርሃት ገጹ ይለያያል።  የህወሃት መራሹ መንግስት ፍርሃት በአንድ በኩል በጥጋብ እና በማናለብኝነት የተከናነበ ይመስላል በሌላ በኩል ደሞ በልማት ዲስኩር ተከልሎ ከዲስኩሩ በስከጀርባ በምናቡ የሚስላቸውን “ጸረ-ልማት ሃይሎች” (ኢትዮጵያውያኖች እኮ ናቸው የኢትዮጵያ ልማት ጠላቶች?) እንደምክንያት እየተጠቀመ የአፈና የሚጧጡፍበት የሞራል ፈቃድ አብረውት ክሚሰሩት “እህት ድርጂቶች”  ይወስዳል፡፡ በህወሃት “የማይበገር ጀግንነት” ውስጥ ያለው እውነታ (‘ሪያሊቲ’) ሃሳብን በነጻነት የመግልጽ መብትን እስከመፍራት የሚያደርስ ፍርሃት ነው። የደህንነት ተቋማቱም እወቃቀር የሚሰማቸውን የፍርሃት ደረጃ ግምት ውስጥ ያስገባ ይመስላል።ስለ ህወሃቶች እና ስለገነቡት የማፈኛ ተቋም የራሴም የሰዎችም ተሞክሮ አለኝ። ገና በልጂነት ባደኩባት የደሴ  ከተማ ፓሊስ(ህወሃት ለአፈና ተግባር ካሰለጠናቸው ውስጥ ነበር)   አንዱን ያለ እግባብ እያንገላታ ለማሰር ዱብ እንቅ ሲል (እንደዛ ይደረግ የነበረው ደሞ ለሃገሩ በብሄራዊ ውትድርና ዘምቶ የመጣ ዜጋ ነው-የገባው የሚመስለው የፖለቲካ ሁኔታ እንገቱን ባያስደፋው ኖሮ የዛን ለፍዳዳ ፖሊስ ጥርሱን የሚያራግፍ ጎበዝ ነበር። አውቀዋለሁ ) ነገሩ ከንክኖኝ ከፖሊሱ ጋር “የምን እደረገህ” ያደረገውም ነገር ካለ በስነ-ስርዐት ውሰደው የሚል ሙግት ውስጥ ገባሁ። ከዚያ በኋላ ፖሊሱ ልጁን ትቶ ወደኔ ዞረ። ዱላም ጀመረ። ታሳሪው እኔ ሆንኩ፡፡ እና ሂድ እልሄድም ውዝግብ ተጀመረ።  ጓደኛየ ታደሰ ባየ( ፌስ ቡክ ላይ አለ) በዛ በዝናብ ተንበርክኮ ሁሉ ለመነው ፓሊሱን፡፡ እኔ ደሞ እንኳን ልለምነው እንዴት ድንጋይ እንደሆነ በተጋጋሚ እነግረዋለሁ። የመምታት አቅሙን ተጠቅሞ ያ ሁሉ የፖሊስ ዱላ ወረደብኝ። በመጨረሻ ላለመታሰር ጨለማውን ምክንያት እድርገን ሁለታችንም አመለጥነው። የተመታሁት ብዙ እንደነበረ የገባኝ ግን በነገታው  መሄድ እቅቶኝ ቀኑን አልጋ ላይ ሳሳልፍ ነው።  ያኔ ተናድጄ ስለነበር ምንም አልተሰማኝም።   ሶስት ቀን ያህል ሳያስነክሰኝ አልቀረም።

Eskinderኮተቤ እያለሁ ደሞ ሮብ  ሮብ መብራት ይጠፋ ነበር። በዚያ ምክንያት ረቡዕ ማታ አካባቢ ጥናት የለም ። ወክ ነው የምናደርገው። ወደ ገደራ እየሄድን ስናወራ የነበረውን ከኋላ ይሰማ የነበረ አስቁሞን መታወቂያችንን ከጠየቀ በኋላ እዚያው እካባቢ ወደ ነበረ ፓሊስ ጣቢያ ተወስደን ተመዝግበን የሚጠይቁትን ጠይቀው ተመልሰናል።  ሌላ ጊዜ እንዲሁ አራት ኪሎ ላይ የከተማ አውቶብስ ይዞ የነበረ የትግሪኛ ተናጋሪ ሾፌር  በራሱ ስህተት እና ትክምህት ምክንያት ተሳፋሪውን ከአራት ኪሎ ይዞ ሚኒሊክ እካባቢ ወደነበረው ፓሊስ ጣቢያ ወሰደን። በትግሪኛ አወራ ከሰዎቹ ጋር። እኛ “ጥፋተኞች ሆንን።” የተማሪዎች ዲን ነው ጣልቃ ገብቶ ነገሩ ያለቀው።የሌሎችን ተሞክሮ በሚመለከት እዚያው ያደኩባት ደሴ ከተማ ላይ በጠራራ ጸሃይ አፉን በደንብ ያልፈታ የህወሃት ታጣቂ እንድ ባዶ እጁን የነበረ ወጣት አሯሩጦ ከደረሰበት በኋላ ሰው እየተጯጯኽ የክላሹን አፈሙዝ ደረቱ  ላይ አድርጎ ተኩሶ ከገደለው በኋላ ክላሹን እንቆ እንደያዘ  ሲሄድ ያስቆመው ፓሊስ አልነበረም። ሌሎች ታጣቂዎችም ያሉት ነገር የለም። (በነገራችን ላይ ያኔ እስከማውቀው ድረስ የልጁ ገዳይ ለፍርድ እልቀረበም)እንደዛ እይነቱ የህወሃት ጭራቅነት በርሃ ባልነበሩት ዘመድ እዝማዶቻቸው ላይ ተጋብቶ “ምክንያታዊ” በሚመስል ሁኔታ  ስለፍትህ በሚጮሁ ኢትዮጵያውያን የሚያሳዩትን ቅጥ ያጣ ንቀት ማየት እሁን የተጀመረው እይነት ዘመቻ በበታችነት ስሜት በሚናጥ ስብናቸው እና እስተሳሰባችው ላይ የበላይነት እና የገዠነት ካባ ከሚደርብላቸው በስተቀር ትርጉም ያለው ጩኽት ይሆናል የሚል እምነት የለኝም። የማስጮህ ስሜት እንዲሰማቸው አልፈልግም። ዛሬ ፌስ ብክ ላይ እንዲህ ያለ ዘመቻ ባለበት ሰዐት እዚሁ ፌስ ቡክ ላይ እስክንድር ነጋን በሚመለክት የነዚሁ የህወሃት ወገን የሚመስሉ ሰዎች ያደረጉትን ምልልስ ለአብነት እንዲሆን ያህል ከ’ሆም ፔጂ ላይ ስክሪን ሾት’ ወስጃለሁ፡፡

ከዚያ ውጭ የህግ ስርኦት ያለበት ሃገር ቢሆን ኖሮ እንደ ዳንኤል ብርሃነ ያሉ የህወሃት ደጋፊዎች ሃገር ውስጥ ያለው የሃሳብ ሙግት በጸጥታ ሃይል እና በ”ፍትህ አካላት” እየታፈነ ባዶ ሆኖ ሙግታቸውን እና የሃሳብ ክርክራቸውን ከውጭ ሃገራት ሰዎች ጋር ሲያደርጉ ማየት የህወሃት ደጋፊዎች እና ዘመዶች ባይሆኑ ኖሮ ሊያስገርም ይችል ነበር። ከታች በሊንክ ባስቀመጥኩት የዳንኤል ጽሁፍ የሂውማን ራይቱ ቤን ራውለንስ የእንግሊዝ መንግስት የዕርዳታ እሰጣጥ የሚተች የመጽሃፍ ሪቪው  አወጣ ብሎ  የእንግሊዝ መንግስት ትችት ሳይሆን ምስጋና ነው የሚገባው የሚል ጽህፍ አውጥቶ ብሎጉም ላይ ጭምር ለጥፎታል። የጽሁፉ ዓላማ ምን ነበር የሚለው ሌላ ጥያቄ ሆኖ መነሳት ያለበት መሰረታዊ ጥያቄ እንደ ዳንኤል ያለው የህወሃት ፖለቲካ ደጋፊ ስለሆነ ብቻ ሃገር ቤት በሚታተሙም ራሱ በፈጠረውም ብሎግ ላይ የመጻፍ ነጻነት ሲሰጠው ሌሎች ዜጎች (ለምሳሌ የዞን ዘጠኝ ብሎገር አባላት) የሚታፈኑበት ምክንያት ከላይ የገለጽኩት ነው። እፈናውን ተቃውሞ የሚደረገውን ተቃውሞ ያልተቀላቀልኩበት ምክንያት የሚጨምርላቸውን -ተዋጋን እያሉ ለሚያወሩት ብቻ ሳይሆን ያኔ ልጆች ለነበሩት እና የደም ትስስር በሚመስል ምክንያት ብቻ እፈናን በምክንያታዊነት ለማስተባባል እና ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ለሚሞክሩትም ጭምር- ለትምክህታቸው  የሚጨምረላቸውን ሃሴት ላለመስጠት ነው። የዳኤል ፓስት

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አምባገነናዊነት ሌላ ዓለም ከሚስተዋለው በመሰረታዊነት የሚለይ እንደሆነ እምኖ ተቀብሎ የሚደረገው ተቃውሞ የህወህትን እምባገነናዊ ባህሪ ግምት ውስጥ ያስገባ እና ህወሃቶች በመንፈስም በፖለቲካም የማይጠቀሙበት እና ትምክህት የማይጨምርላቸው መሆነ አለበት ብየ ስለማምን ነው፡፡  በሌላ አንጻር ደሞ የሚደረገው ዘመቻ መሬት ላይ ያለ እና ለህዝቡ ስነ-ልቦና እና አስተሳሰብ ቅርበት ያለው ፣ በቀላሉ የሚገባ ቢሆንም ጥሩ ነው። ምን ያህል ኢትዮጵያዊ ነው በፌስ ቡክ እና ትዊተር ላይ ያለው? ፌስ ቡክ ላይ ካለውስ የህወሃት ደጋፊ ከሆነው ውጭ ስለ ህወሃት መራሹ መንግስት አፈና እና ቅጥ ያጣ እምባገነናዊነት የማያውቀም ምን ያህሉ ነው? ለ “ዓለማቀፉ” ማህበረሰብ ነው እንዳይባል ለዚሁ አፈና ለሚያደርሰው መንግስት ትብብር እና ርዳታ የሚሰጡት እነዚሁ ወገኖች ናቸው። ዳንኤል የእንግሊዝን የእርዳታ አሰጣጥ በመደገፍ የእንግሊዝን መንግስት የሚከላከል ጽሁፍ መጻፍ ደረጃ ላይ የደረሰበት ”የዲፕሎማሲ” ልምምድ ሳይሆን የፖለቲካ ትስስርንም ጭምር የሚያመላክት ይመስለኛል። ለሃወሃት የጥጸጥታ ሃይሎች ስልጠና እና ሎጂስቲክ የሚያቀርበው ማን ነው? ብዙዎቹ የህወሃት ፖሊሲዎች በርግጥ ከህወህት ብቻ የመነጩ ናቸው? “የመለስ” ራዕይን ጨምሮ?

 

 

ስርአት አልባው የወያኔ ጋዜጠኛ ከብቸኛው ተቃዋሚ የፓርላማ አባል ጋር

ስርአት አልባው የወያኔ ጋዜጠኛ ከብቸኛው ተቃዋሚ የፓርላማ አባል ጋር ያደረገውን ቃለ-ምልልስ ያዳምጡ።

 http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/6286

 

posted by Tseday Getachew

 
 

 

Post Navigation

%d bloggers like this: