Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

Archive for the month “October, 2012”

መለስ ማን ገደለው? ጌታቸው ረዳ

ተቃዋሚ ጋዜጠኞችም ሆኑ ምሁራን መለስ ዜናዊን የገደለው በሽታ ምን እንደሆነ እና መቸ ወር እና ቀን እንደሞተ ባሉት ዙርያዎች ለማወቅ እያብሰለሰሉ ጥያቆችን ማንሸራሸር እንጂ “መለስን የገደለ ሃይል ማነው?” የሚል ጠለቅ ያለ ሰውዬው ከነበረው ከኢትዮጵያዊ ባህል፤አገራዊ እና ሃይማኖታዊ የራቀ ሸካራ ግንኙነት ከፖለቲካው ትንተና ባሻገር እነኚህ የተጠቀሱ ሦስቱ የአገሪቱ አድባራዊ (ስፒሪት) ምሶሶሰዎች ባለው ዙርያ ሊያስከትሉበት የቻሉት መለኰታዊ ቅጣቶች ብዙም ትኩረት አልሰጡትም።

ዘመናዊ ጋዜጠኞችም ሆኑ የተማሩት ክፍሎች ትኩረታቸው ምድር ላይ ከሚታያቸው ጉዳይ ማያያዝ እንጂ የዓለም ሕዝቦች የሕይወት ታሪክ መዛግብቶቻቸው ከሚኖሩበት ከኢትዮጵያ ሰማዬ ሰማያት ማለትም ከምድሪቱ በላይ ያለው ሃይል መመርመር ዘመኑ ያለፈበት የቂሎች እምነት እንዳያስብላቸው ስለሚሰጉ፤ለመለስ መሞት እንደ ሽፋን ሆኖ ተከስቶ ከገደለው በሽታ በላይ ያለው ቀጪ ሃይል ማየት ስላልቻሉ ስለ ገደለው በሽታ እና የሞተበት ቀን እንደትልቅ ጉዳይ አድረገው ሲተነትኑ ይታያሉ።

ይህ እንደዋዛ የሚታይ እይታ ሳይሆን ፤ ለመለስ መሞት ምክንያቶች “ኢትዮጵያን እንደ አገር ተከብራ እንድትኖር፤ያቆዩዋትና የተከላከሉላት” *የባህል እና የሃይማኖት* ተቋማት በወያኔ ሓርነት ሕዝቢ ትግራይ መሪዎች በተለይም ድርጅቱን በመራው በመለስ ዜናዊ የስልጣን መማገጥ ተሰነጣጥቀዋል። መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ያነጣጠረው ጥቃት የምድርቱ ሕግ ሊገቱት አልቻሉም እና ኢትዮጵያን የፈጠረ ሃይል ገድሎታል።

ወያኔዎች ልብ ያላሉት ነገር፤ “ኢትዮጵያ” የምትባል አገር በውስጧ የሚኖሩት ፍጡራን ሳይሆኑ ባለቤቶቿ ፤በምድሪቱ ውስጥ ሰፍረው የሚገኙ እልፍ ኣእላፍ እንሰሳዎች እና ሕዝብ በጥበቡ ያሰፈራቸውና የፈጠራቸው ንብረቶቹ የእግዚአብሔር መሆናቸውን ልብ አላሉትም። ልብ ስላላሉትም መሬቱም ሕዝቡም እንሰሳዎቹም ወንዞቹም ተራሮቹን እያንቀጠቀጡ በቁጥጥራችን አስገብተናል በማለት በማን እህሎኝነት ብዙ ግፍ ፈጽመዋል። እነኚህ ግፎች በወያኔ ትግራይ የሃይማኖት መሪያቸው በአባ ጳውሎስ እና በፖለቲካ መሪያቸው በመለስ ዜናዊ እና በኪነት እና በባሕል መሪያቸው በእያሱ በርሔ  ላይ ባንድ ዓመት ውስጥ የወረደው የእግዚአብሔር ቅጣት በጣም አስገራሚ ተአምር መሆኑን ልብ እንድትሉት ደጋግሜ አደራ እላለሁ።

ይህ ትኩረት የተናገርኩት ዘሬ ሳይሆን ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ባደረጉበት ሴራ እና አልጀሪስ ስምምነት ከተደረገ በሗላ የጻፍኩበት ቦታ የት እንደሆነ አሁን ትዝ ባይለኝም” ያስታወሳችሁ ብትኖሩ የጻፍኩትን ልብ እንድትሉት ደግሜ አሳስባለሁ። “ ልጆቿ ከድተዋት ብቻዋ ቀርታ ሰንደቋ እና ሕዝቧ እየተዘለፈ ለውርደት የተዳረገቺው ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ ፈጣሪዋ ስታመለክት “ዓለም” ያላየቺው ቅጣት ይወርድባታል።” ብየ ነበር። በተለይ ሃያል ነን በሚሉ አገሮች አንደ አውሮጳ፤አሜሪካ እና አረቦች እንዲሁም ሶማሌ’፡ ቅጣት ይደርስባቸዋል ብዬ ነበር። አሜሪካን አገር የደረሰው እና እየደረሰ ያለው የመከራ ዘመን እያያችሁት ነው። እነ ሶርያ እነ ኢራቅ እነ ሊቢያ እነ ግብፅ እንዲሁም ምጢጧ ሶማሌ “ኢትዮጵያን” ለመበተን የኤርትራ ሽምቅ ተዋጊዎች እያስታጠቁ  ራዲዬ ጣቢያ ከየመዲኖቻቸው እያስተላለፉ እርስበርሳችን ያጋደሉንን ያህል፤ ዛሬ እነ ሶርያ እነ ኢራቅ ሊቢያ  ሶማሌ;…….ፍዳቸውን ከፈጣሪ እያገኙ መሆናቸው ስትመለከቱት ‘በእጁ ጠፍጥፎ የሰራትን ኢትዮጵያ’ የተጫወቱባትን ያህል ፈጣሪዋም በበኩሉ ጊዜውን ቆጥሮ ትእግስቱ ካሟጠጠ በሗላ አንድ ባንድ ሲቀጣቸው ምን ትታዘባላችሁ?።  ይህ ትንቢት ከመድረሱ በፊት  ጽፌዋለሁ። ምናልባትም ሃዋርያ ጋዜጣ ላይ ወይንም ኢንተርኔት ላይ። ያስታወሳችሁት ሰዎች ከላችሁ እርዱኝ።

በህይወት ያሉ ተመሳሳይ ሞኞቻቸውም የሚናገሩትን አንደበት ልብ ብንል ለፈጣሪ የሚፈሩ አይደሉም። ለምሳሌ “ስየ አብርሃ” ባንድ የክርክር መድረክ ከመለስ ካድሬዎች ጋር በፖለቲካ እንካ ስላንትያ ገጥሞ መልስ ሲሰጥ “አታስፈራሩን! ካስፈራራችሁን፤እስካሁን ድረስ ያልተናገርነውን (የደብቀን ያቆየነውን) ምስጢር እናወጣዋለን” ብሎ ነበር። እየሰማችሁኝ ነው? ሰዎች የሚፈሩት ምድር ላይ ያሉት “አስፈራሪዎች” እንጂ ጠረፍ ላይ በኢትዮጵያ ሰማይ በመስኮቱ ብቅ ብሎ ወደ ታች እየተመለከታቸው ያለውን የሰማዩ ንጉሥ የሚሰጣቸው ሕጎች እና ማስጠንቀቂያዎችን አያስፈራቸውም።ሰውን እንጂ ከነሱ በፊት የነበረ፤ከጊዜ በፊት የኖረ ለወደፊቱም የሚኖር እና ዓለምን እና እነሱን የፈጠረ አምላክ አይፈሩም። ለአምላክ ሕግ የማይፈራ ባለሥልጣን እራሱ ባጭር ቀጭቶ ምድሪቱንም ለአምላክ ቁጣ ይዳርጋል (ለዚህ ነው አልኩ ባልኩት ትንቢቴ ውስጥ እኛንም እንዳይጨምሩን እንጸልይ ያልኩት)። ሃይማኖት ለመስበክ አላማየ አይደለም። ልብ እንድትሉት ግን አሳስባለሁ።

የመለስ ሞት ምክንያቶች ሁለት ናቸው።

(1)  ባህል እና ሃይማኖት በማንኳሰስ የተፈጥሮ ሕጎችን ተጻሯል

(2) የሕዝብ ሃይል/ሥልጣን በጉልበት ይዞ ብሔራዊ ወንጀሎችን ፈጽሟል።

እነዚህ የተጠቀሱ 2 መሰረታዊ ክሮች ከምድር ጋር ሳይሆኑ እትብታቸው የተለቆመው ከተፈጥሮ እና ከፈጣሪ ስለነበሩ አላግባብ በጥሷቸዋል።እነዚህን የበጠሰ ሕግ ወጥነት ነውና በምድር የመኖር መብቱ ባጭሩ ይቀጠፋል።

መለስ ሲቀጠፍ ጎራው በሁለት ተከፍሏል።ደጋፊዎቹ “መለስ ለምን ሞተ፤ሞተ? ሲሉ ተቃዋሚዎቹ ደግሞ “መለስ እንኳን ሞተ!ሞተ!” በሚል መስመር ፍጥጫ ውስጥ ገብተዋል። አንዳንድ በጐልማሳነት ዕድሜ ያሉ የወያኔ ቄሶችም “መለስን ወደ ፈጣሪ በመለወጥ” “መለስ እውነት ነው” በማለት “እግዚአብሔር እውነት ነው” የሚለውን ሃይማኖታዊ መመሪያ በመለስ ዜናዊ በመተካት “ፍፁም” አምላክ ብለውታል።

ፈጣሪን ልሳን መልእክተኞች የምንላቸው ቄሶች ‘ሰውን’ ወደ “ፍጹምነት/እውነት” በመለወጥ ሲያመልኳቸው ፈጣሪን እያስቆጡ ለሃገር ውድቀት እና ቅጣት እየዳረጉን ነው። ይህንን አምልኮ “አምባገነኖች” በሚገባ ስለሚያውቁት ከኛ ይልቅ “ፍፁማን” ተብለው ከሚመለኩት ሰዎች አንደበት የተነገረውን መፈተሽ ያስፈልጋል። ከላይ ለጠቀስኳቸው ተፈጥሮአዊ እና ዓለማዊ መብቶች መፈረካከስ ምክንያቱና መነሻው የመለስ ለኢትዮጵያ አምላክ የነበረበው ንቀት እና የስልጣን አልጠግብ ባይነት ነው። መለስ ስልጣን ከመውደዱ የተነሳ ገደብ ያጣ አገርን እና ባህልን ያናጋ ግለሰብ ነበር።  ይህንን ልብ በሉ “አምባገነንነት የፈጠሪን ቅንድብ የሚያስቆም ከባድ ወንጀል ነው”። ፈጣሪን የማይፈሩ መሪዎች ስለ ሕገ ወጥነት ጉዳይ ሲነሳ አምባገነኖች  የውንጀላ ጣታቸውን የሚቀስሩት፤ ወደ እራሳቸው ሳይሆን፣ወደ ሌላ አምባገነን ነው። መረጃ ልስጥ። ለአፍሪካ ውድቀት ምክንያት መለስ ዜናዊ ምክንያቶች የሚባሉ ነገሮች ተጠይቆ ሲመልስ እንደሚከተለው ነበር የመለሰው።

“የአፍሪካ ውድቀት ሁሌም የግለሰቦች አምልኮ ነው።” ሲል አፍሪካን ለውድቀት የዳረጋት በመሪዎች ላይ  አምልኮ ማሳደር እንደሆነ አስምሮበት ነበር።እነኚህ የተመለኩ መሪዎችስ እነማን ናቸው? ሲባል መለስ እንዲህ ሲል ይመልሳል። “ስማቸውም ሁሌ በ “መ”  ፊደል ዘር የሚጀምር ይመስላል። በዚህ ረገድ ሞቡቱ እና መንግሥቱ ነበሩን።መለስን ግን ከዚህ ዝርዝር ውስጥ ማስገባት አልፈልግም” ሲል የመለሰውን መልስ “የአቶ መለስ ጥቅሶች” በሚል ርዕስ “መለስ ከልጅነት እስከ እውቀት” ተብሎ ‘በትኩእ ባሕታ’ የተጻፈ መጽሐፍ ተጠቅሷል።
እሱ ከሄደ በሗላም  መለስን “ወደ ፍፁም/እውነት (አምላክነት) በመለወጥ” አምልኮ የአሳደሩበት ያደራጃቸው ቀሳውስቶቹ ለኢትዮጵያ ወጣቶችና ለሃይማኖት መበስበሰስ ምከንያት ናቸው።በ‘መ’ ፊደል ዘር የሚጀምር የአምባገነኖች ስም ሲጠቅስ ራሱን ለምን አልጠቀሰም? የሚል ጥያቄ ቢያስከትልም፡ የህጻናት፤የወጣቶች እና አረጋዊያን ደም ያለ ሕግ እንዲፈስ ያደረገ መሆኑን እያወቁ፤የራሱ ቀሳውስቶች መለስን በፈጣሪነት እና በፍፁም እውነትነት በማመን ለምን ሰበኩለት? ስንል ፍካሬ እየሱስ ላይ የተጻፈውን ማቴ፤7፡15 እንዲሁም 23፡5-7 ዘዳ 32 ብንመለከት የክህነት ልብስ በመልበስ መርዝ የሚረጩ ተኩላዎች በመካካላችን እንደሚቀላቀሉ እና እንደሚያሳስቱን ያስጠነቀቀው ትንቢት እውነታውን እያየን ነው ይላሉ መንፈሳዊ ምሁራን።

 

መለስ ዜናዊ የራሱን ሃሳዊ መሲሆችን በመመልመል ከቄስ እስከ ሃኪም  ከአረጋዊ እስከ ጎልማሳ እና ታዳጊ ብላቴናዎች ድረስ የተፈጥሮ እና የሰው ልጆች ሕግ የሚጻረሩ ርዕዮተአለሞችን እንዲቀበሉት በማድረግ የኢትዮጵያ ሕዝብ “ፋሺስቶችና ጉልተኞች” የሚከተሉትን “የጎሳ እና የደም ጥራት” መለኪያ አድርጎ በቋንቋ ልሳን ተከልሎ እንዲተዳደር ቀይሶ ሕዝብን አናክሶ “በወንድማማቾች ማሃል ደም እንዲፈስ አድርጓል”።

 

(1)በባህል እና (2)በሃይማኖት እምነታችን የሕዝቡን እይታ እንዲበላሽ መለስ የሰራቸውን ስራዎቹ ለሞት ቅጣት ያደረሱት እንዴት እንደሆነ እንመለክት። ሕብረተሰብ እንደሚበሰብስ ባለፈው ገልጫለሁ። ሕብረተሰብ አይበሰብስም {“ሕዝቡ በስብሷል ከማለት ለዘብ ያለ ቃላት” ብትጠቀም ጥሩ ነበር} ብለው ስልክ የደወሉልኝ ወገኖቼ አሉ። መንፈሳቸው ይገባኛል። ክፋት የለውም።  ነግር ግን ‘ዘመነ ሎጥ’ የሰዶም እና የጎመራ ከተሞች ሕዝብ በስብሶ ለቅጣት እንደተዳረገው ሁሉ የኛ ሕዝብም ግስጋሴው ከዛው ያልተናነሰ የባህል እና የሃይማኖት ወረራ ተፈጽሞበት በምድሪቱ ላይ እንዲስፋፋ መለስ ዜናዊ አስተዋጽኦ አድርጓል። የሕዝቡ መንቀዝ (መበስበስ) መረጃው ወደ ሗላ አመጣዋለሁ።

 

(2) ‘በፍፁምነት’ በመልአክትነት ያመለኩት የራሱ ቀሳወስቶች ብቻ ሳይሆኑ የተማሩ አምላኪዎቹም “መለስ ዜናዊ” የተባለ “አዲስ ሃይሞኖት” መስርተናል በማለት ይፋ አድርገዋል።

ከዛሬ ጀምሮ ሃይማኖቴ “መለስ” ወደ እሚባል ሃይማኖት ለውጬአለሁ በማለት ምሁራን ዜጎችም መለስን ወደ ሃይማኖትነት ለውጠውታል። መረጃ ላቅርብ። በወያኔው “ዓይጋ ፎረም’ ድረገጽ “ዓዳል ኢሳው” በተባሉት ጸሐፊ የቀረበውን ጽሑፍ ይመልከቱ። “I am again a born believer & my religioun is Meles Zenawi (Adal Isaw September 2, 2012)  “ፍሪኪሽ ቢሄቭዮር” (ለማመን የሚቸግር ባህሪ)የሚሉት እንዲህ ዓይነት የባህል እና የሃይማኖት መዛባት እንዲታይ መለስ ዜናዊ እና ድርጅቱ ያካሄዱት የአእምሮ ጠለፋ ምሁሩንም ኩፉኛ ጠልፈውታል።

 

በዚህ በሁለተኛው (በሃይማኖት መዛባት) እየታየ ያለው የሃይማኖትና የሕብረተሰብ መበስበስ ጎዳና ልጀምር።

 

ከላይ የተጠቀሱት ጸሃፊ I am again a born believer & my religioun is Meles Zenawi” ብለው ፡መለስ ዜናዊ” የተባለ አዲስ ሃይማኖት ለመመስረት የተነሱት “መለስ ዜናዊ” የተባለ “ሃይማኖት” ተከታይ የተነተኑልንን እንስኪ አንዳንዱን ልጥቀስ።

 

“ I believe, Meles Zenawi was born for reasons other than the ordinary ones that you and I were born for” ይህ ሰው እየሱስ ነው፤ ከማንኛችንም በላይ የተለየ ተልእኮ እንዲፈጽም በምክንያት የተፈጠረ ከፈጣሪ የተላከልን ልዩ  ፍጡር/መልእክተኛ ነው። ነው እያሉን ያሉት። ይቀጥሉና የመለስ ዜናዊ ሃይማኖት ተከታይ እንዲህ ይላሉ “

 

“I have a reason to revert back to the religion that I have abandoned early in life. Things were trite and nothing was out of the ordinary then, and, I had to walk away from my religion as a result. But now, and after many years of abandoning my religious belief, I am a born-again believer and my religion is Meles Zenawi.” ……”I believe in Meles Zenawi and he is my religion from now on till the end of my time”….

“ Indeed; Meles Zenawi is my religion for he is a rarity—a gift from the Goddess of Ethiopia. And hence, he is the religion that I have now”. ((Adal Isaw September 2, 2012  adalisaw@yahoo.com)

 

እንግዲህ እንዳያችሁት ጸሃፊው መለስን የተመለከተው “አርበኛ፡ “አንበሳ”…የሚሉት ሙገሳዎች/መለኪያዎች ያንሱታል ነው የሚሉት። ለሱ የሚመጥነው “ለምክንያት የመጣ እኛን ተመስሎ ለማዳን ወደ እዚህ ምድር ከኢትዮጵያ አምላክ የተላከልን አዳኚያችን ነው” ብሏል በሰፊው ጸሐፊው ሲተንትኑ (ሊንኩን አንብቡት)። ይህ ጉድ እና በጣም አሳፋሪ የባህል፤የሃይማኖት መበስበስ እየታየ ያለው መነሻው የግዛቤ እጥረት እንደሆነ ምንም የሚያከራክር አይደለም። መለስ ዜናዊ የፈጸማቸው ወንጀሎች አምላክ እንዳትፈጽሙ ያላቸውን አብዛኛዎቹ በተለይም ትላልቆቹ (ትልቅ እና ትንሽ የሚባል የሕግ ጥሰት ካለ) አትግደል፤ አትዋሽ፤ በሕዝብ እና በአገር ክሕደት እንዳትፈጽም፤ ፈጣሪህን አክብር፤”ክረስትያን ወይንም እስላም” አማኝ ከሆንክ በምድሪቱ ውስጥ ግብረሰዶምነት አንዳይከናወኑ አጥብቀህ ኮንን/ተቆጣጠር፤ ከሌቦች፤ነብሰገዳዮች፤ከአመጸኞች ጋር አትመሳጠር፤ የአገሪቱን ዳር ድምበር ጠብቅ፤ አርበኞቿ እና ሰንደቅአላማዋን አክብር… የሚሉትን ትእዛዞች የጣሰ ክፉ ሰይጣን ነበር። መቸም በዚህ መረጃ ይታጣል የሚል ሰው ከተገኘ ሞኝ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ይህ “ፍፀም” ሆኖ ወደ አምላክነት እና ወደ ሃይማኖት የተለወጠ የወያኔ መለኰት “ፍፁም” ነው ብሎ ማለት አስቂኝ ብቻ ሳይሆን የወንጀሉ ተባባሪ እና በሕዝባችን፤በቤተሰባችን፤በጓደኞቻችን፤በአገራችን የፈሰሰው የሰው ልጆች ደም ደንታ ቢስነት መሆን ነው።

 

(2)መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያን ባህል እና አርበኞች ክብር አልነበረውም።

 

መለስ ዜናዊ ሰፊ አገር ያስገኙለት የድሮ የጦር አርበኞችና ነገሥታትን ሙገሳና ክብር መስጠቱ ይቅርና በአትሌቲክስ/ስፖርት አገራቸውን ያስጠሩ አርበኞች በተቻለው መጠን መንፈሳቸው እና ህይወታቸው እንዲሰበር ከማድረግ የቦዘነበት ጊዜ አልነበረም። መለስ ዜናዊ ስልጣን ሲቆጣጠር እሴቶቻችንን ነበር መልቀም የጀመረው። አርበኛው ማሞ ወልዴን ታስታውሳላችሁ? ዊክዴፒያ/ኢንሳይክሎፒዲያ የተባለው የታሪክ ማህደር እንዲህ ይላል፡ “In 1993, Wolde was arrested on the accusation that he participated in a Red Terror execution during the regime of the dictator Mengistu Haile Mariam. He argued that although he was present at the killing, he was not a direct participant. The IOC pressured the Ethiopian government to release him. In early 2002 he was convicted to six years of imprisonment, but released because he had spent nine years in detention already waiting for his trial.”

እየተከታተላችሁኝ ነው? አንደኛ በግድያው አልተሳተፍኩም፤ ሆኖም እዛው ቆሜ ነበር በማለት የተከራከረበት ክስ 6 አመት ሲያስፈርድበት፤ እሱ የታሰረው ግን 9 ዓመት ነበር። ይታያችሁ አንግዲህ፤ መለስ ዜናዊ የተባለ “ፍፁም አምላክ” እና “መለስ ዜናዊ የተባለ ሃይማኖት” በሚያስተዳድራት አገር 6 አመት የተፈረበት ሰው 9 አመት ፈጽሞ ወደ 10ኛው አመት እያመራ እንዳለ በ9ኝ አመቱ ፍርድ ስለተሰጠው፤ ከሚገባው በላይ ስለታሰረ አሰናብተውታል። ሲሰናበት የጉበት በሽታ ይዞ በመውጣቱ ወዲያውኑ ለሞት ተዳረገ።  ይህ “መለስ ዜናዊ የተባለ ከፈጣሪ የተላከ ልዩ መልአክ” 6 አመት የሚያስፈርድን ክስ 9 አመት እንዲበሰብስ የሚያደርግ መልአክ ከየትኛው ሰማይ እንደወረደ የዜናዊ ሃይማኖት  ተከታዮች እንዲያብራሩልን እንጠብቃለን።

የማሞ ወልዴ ባለቤት ወ/ሮ አበራሽ ከባድ የሕሊና እና የኑሮ ጫና ለማወቅ መሉ ንባኑን ለማግኘት ይህንን ይመልከቱ፤http://www.kennymoore.us/kcmarticles/woldehonolulu/woldestory.htm

“ፆታህንም መቀየር ትችላለህ”

መለስ ዜናዊ እና ፓርላማው ሹሟሙንቶቻቸውን ሲሾሙ በመጽሐፍ ቅዱስ ወይንም ቁርአንን ወይንም የኢትዮጵያ ሰንደቃላማን አስይዘው መሃላ አያስፈጽሟቸውም። ምክንያቱም መመሪያቸው ፋሺስታዊ እና ኮሚኒስታዊ ፈጣሪ አልባ መመሪያቸው በሞሆኑ። ለዚህም ግብረሰዶምን እንደነውር አይቆጥሩትም እና በአንደበታቸው ሲያበረታቱት ተደምጠዋል። “ፆታህን መቀየር ትችላልህ” በማለት ፃየፍ ይህ ብልግና የተሞላበት መልስ የሰጠ መሪ ማን ነው? መለስ ዜናዊ! ይህ ስብእናን እና አርበኛን የሚያቆሽሽ ኢትዮጵያዊ ባህል የሚጻረር የብልግና ስድብ ምላሽ የተናገረው ለማን ነበር? ታሪኩን እንመልከት።

መለስ ዜናዊ የስፖርት አርበኞችን ያከብራል፤ለሙዚቀኞችን፤ ለከያኒያንን አክብሮት ነበረው፤ እያሉ ከራሳቸው ከአፍቃሬ ወያኔ ባለሞያዎቹ አለቃቸው ሲሞት እያለቀሱ ሲያከብራቸው እንደነበረ አስደምጠውናል። እውነታው ግን ውርደትን እንደ ክብር እና ጀግንንት የተቀበሉት እነኚህ ካፍንጫቸው አካባቢ ውጭ አርቀው ማየት ያቃታቸው ሕሊናቸው በገንዘብ የተጭበረበረ የስፖርት ባለሞያዎች መለስ በህይወት እያለ ምን እያለ ክብራቸውን ይጋፋ እንደነበር ንግግሮቹ እና ቃለ ምልልሶቹ በመጽሐፍ መልክ ካድሬዎቹ ጠርዘው ባሳተሙለት መጽሐፍ ውስጥ ሲላቸው የነበረውን ነግረውናል። ይህንን እንመልከት፦

“አንድ ዝነኛ አርቲስት ክስ ተመስርቶበት ከታሰረ ትንሽ ቆየት ብሎ ነበር። በዚህን ወቅት አንድ ታዋቂ አትሌት በውጭ አገር አስደናቂ ድል ተቀዳጅቶ ወደ አገሩ ሲገባ ጠ/ሚኒስተር መለስ አድናቆታቸውን ለመግለፅ ኤየርፖርት ድረስ ሄደው ይቀበሉታል። አትሌቱም አንድ አንገብጋቢ ጥያቄ እንዳለው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይናገራል።

“ምን ችግር አለ ጠይቃ” አሉት ጠ/ሚኒሰትሩ።

“እከሌ የተባለ አርቲስት ካልተፈታ ዜግነቴን እቀይራለሁ”።” “አንኳን ዜግነትሀ ፆታህንም መቀየር ትችላለህ! አሉት ጠ/ቅላይሚኒስትሩ።

(መለስ ከልጅነት እስከ እውቀት- ደራሲ ትኩእ ባህታ)

እንዲህ ያለ ነውር፤ ያውም የዓለም አምበሶች የተባሉ ሯጮች ያስናቀ የወንዶች ወንድ “ሱሩህን ፈትትህ ከወንድ ጋር ተዳራ” የሚል በነውር የተሞላ አርበኛን የሚንቅ በትዕቢት የተሞላ መሪ አንኳን በተቀደሰቺው ኢትዮጵያ ይቅር፤ ነውር በሚያከብሩ ነውራም አገሮችም ለአንድ አርበኛቸው እንዲህ ያለ ሰብአዊ ጥያቄን ለጠየቀ አገር ያስጠራ አትሌት ነውር የመለሰ መሪ በታሪክ የለም። ግበረሰዶም እፈጽማለሁ ካልከኝም መብትህን አከብራለሁ የሚለው የግብረሰዶማዉያን መብት አስጠባቂ የነበረው መለስ ዜናዊ በንግግር ብቻ ሳይወሰን በግብርም ግብረሰዶም በኢትዮጵያ እንዲስፋፋ እሱ እና ተከታዮቹ የተቻላቸውን ጥረዋል። እስላም እና ክርስትያን በመጽሓፋቸው የኰነኑትን እኩይ ስነምግባር አገር እንዲበሰብስ አስተዋጽኦ አድርገዋል። በዚህም አምላክ ተቆጥቶ መለስን ባጭር ቀስፎታል።መረጃው እነሆ፤

ታዋቂው ጋዜጠኛ ኢየሩሳሌም አርአያ በኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ ድረገጽ ላይ “በኢትዮጵያ አስደንጋጩ የባሕል ወረርሽኝ” በሚል ርዕስ ለሕዝብ ያስነበበውን የግብረ ሰዶም መከሰት በኢትዮጵያ መለስ ዜናዊ እና ስርዓቱ ምን ያህል አስተዋጽኦ እንዳደረገ በሰፊው እንዳስነበበን ታስታውሳላችሁ። ከ10 እና 12 ዕደሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሃያ (20) ታዳጊ ሕፃናት በውጭ አገር ሰዎች እንደተደፈሩና ደፋሪውም ወደ አገሩ እስኪመለስ ደረስ ሆን ተብሎ መንግስት ቸል እንዳለው ዘገባዎች አመልክተዋል። ችግሩ ጠለቅ ብልን እንድንረዳው ጋዜጠኛ እየሩሳሌም ግበረሰዶማዉያን በደብቅ ሳይሆን በቡድን ወደ መደራጀት ደረጃ እንደደረሱ ሁኔታውን እንዲህ ይገልጸዋል፤-

“ግብረሰዶማዊያን ማሕበር (ቡድን) እስከ መደራጀት ደርሰዋል።ከላይ እንደጠቀስኩት የመለስ አስተዳደር ምን አቋም እንዳለዉናእንደሚከተል ጠንቅቀዉ የተረዱ ግብረሰዶማዊያን የ2000ዓ.ም.ሚሊኒየም በማስታከክ “ሕጋዊ ዕውቅና ይሰጠን” እስከማለትናየመለስ ዜናዊን በቀጥታ እስከመጠየቅ ደርሰዋል።ስለዚሁ ጉዳይወይም ጥያቄ “ሪፖርተር” ጋዜጣ የዜና ሽፋን በወቅቱ ሰጥቶታል።” ይላል ጋዜጠኛ አርአያ ተስፋማርያም (እየሩሳሌም አርአያ)።

ቀጥሎም፤

“በአገር ዉስጥ ከሚታተሙ የኪነጥበብና ማሕበራዊ ነክ የግልመጽሔቶች ሳይቀር ሕብረተሰቡን የሚንቁ ጽሑፎችን ማዉጣትይዘወል። አንድ “ቢኒያም” ነኝ ያለ ግበረሰዶማዊ ባወጣዉመጣጥፍ- በአዲስ አበባ ብቻ 7 ሺሕ (ልብ በሉ ሰባት ሺሕ ነዉ!)ግብረሰዶማዉያን በአንድነት እንደተሰባሰቡና ማሕበርእንደመሰረቱ፤ለሚመለከተዉ የመንግሥት አካል ሕጋዊ ዕዉቅናእንዲሰጣቸዉ ጥረት እያደረጉ መሆኑን (ግብረሰዶማዉያንን (Gay)ገይ በሚገልጽ ሁኔታ በአዲስ አበባ ዕምብርት (በስማቸዉ መሆኑነዉ) ትልቅ ናይት ክለብ ለመክፈት አስፈላጊዉ ዝግጅት መጠናቀቁናለዚህም የሚያስፈልገዉ ገንዘብ በበቂ ሁኔታ መመደቡን፤ አባላቱያቋቋሙት ማሕበር የፋይናንስ ችግር የሌለበት መሆኑን፤የበለጠለመደራጀት ሲሉ የአባላት ቁጥር በየፊናዉ እየመለመሉና እያበራከቱመሆኑን እዉቅና ካገኙ በሗላ በስማቸዉ ጋብቻ የሚፈፅሙበትየሃይማኖት ተቋማት (ቸርች) እንደሚመሰርቱ፤ በ2000 ዓ.ም.ጀርመን ከሚገኝ ወንድ ጓደኛዉ ጋር የጋብቻ ስነስርኣት አከናዉኖመምጣቱን…በሰፊዉ ከዘረዘረ በሗላ አያይዞም “ሕብረተሰቡንእያግለን፤ግብረሰዶማዉያንን ማግለል ይቁም” እያለ በጽሑፍዘላብዷል። ይኸዉ ግለሰብ በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ይዘት ያለዉመግብረሰዶማዊያን ማሕበር (ቡድን) እስከ መደራጀት ደርሰዋል።ከላይ እንደጠቀስኩት የመለስ አስተዳደር ምን አቋም እንዳለዉናእንደሚከተል ጠንቅቀዉ የተረዱ ግብረሰዶማዊያን የ2000ዓ.ም.ሚሊኒየም በማስታከክ “ሕጋዊ ዕዉቅና ይሰጠን” እስከማለትናየመለስ ዜናዊን በቀጥታ እስከመጠየቅ ደርሰዋል።ስለዚሁ ጉዳይወይም ጥያቄ “ሪፖርተር” ጋዜጣ የዜና ሽፋን በወቅቱሰጥቶታል።መጣጥፍ በመጽሔት ያቀረበ ሲሆን በዛው ጽሑፍያካተተዉ ተጨማሪ ጉዳይ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎችየመዝናኛ ክለቦች ተከፍተው በስራ ላይ እንዳሉና ግብረሰዶማውያንበአንድነት ተሰባስበው እንዲዝናኑ ሲባል ታስቦበት የተከፈቱመሆናቸውን አክሎ ገልጿል።”

ጋዜጠኛ አርአያ በግብረሰዶማውያኑ ዳንስ ቤት ድረስ በመሄድ ያተዘበው ዘገባ ሲያጠቃልል እንዲህ ይላል።

“ነበር።እንደተገለጸዉ አስኳሉ ሸራተን የሆነዉ ወረርሺኝ በይፋከከፈታቸዉ የምሽት መዝናኛ መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ። በአካልጭምር ተገኝቼ ያረጋገጥኳቸዉ ቦሌ ቴሌ መድሃኒያለም ተብሎበሚጠራዉ አካባቢ የሚገኘዉ “ሸገር“ ሕንፃ ሦስተኛ ፎቅ በሰፊአዳራሽ (ሁለት ቦታ ተከፍሎ) ተከፈተዉ “ሻምፒዮን” ወይምበሌላኛዉ መጠሪያዉ “ዲቫይን” የተባለዉ የግብረ ሰዶማዉያንመዝናኛ በዋናነት ይገኛል። የባሩ ባለቤት በአሜሪካ ለረጂም ዓመትየኖረና በ1999ዓ.ም. እንግሊዝ-ለንደን ከተማ ከወንድ ጓደኛዉ ጋር“ጋብቻ” መስርቶ እንደተመለሰ ተረጋግጧል፡፤ ለጋዜጠኛነት ስራየእንዲሁም ባሕላዊ ወረርሽኝ ለመከላከል ባለብኝ ግዴታ በመነሳትወደተጠቀሰዉ ባር በእኩለ ሌሊት አመራሁ። የገጠመኝ ሁኔታከሰማሁት የበለጠ ነበር! በምሽት ደብዛዛ የብርሃን ጨረር የተሞላዉይህ ባር እንደነገሩ ሁለት ቦታ ተከፍሏል። እንደ ዊስኪና ሌሎችየአልኮሆል መጠጦች በዉድ ዋጋ የሚቸበቸቡበትና በዲጄ በሚለቀቁየዉጭ ዘፈኖች ታጅበዉ የሚደነስበት ሲሆን፤ በሌላኛዉ ክፍልደግሞ እጅግ ከደበዘዙና ብዙም የብርሃን ጨረር ከማይፈነጥቁአምፑሎች በመታገዝ ግብረሰዶማዉያን የሚፈጽሙት የሚያቅለሸልሽአፀያፊ ተግባር የሚፈፅሙበት ነዉ። ከሰኞ በቀር በሁሉም የሳምንትቀናቶች ይህ ወራዳ ተግባር ይፈጸማል።በጣም የሚገርመዉፈረንጆች ወንድ ለወንድ ፤ሴት ለሴት ሆነዉ (ካፕል- ካፕል መሆኑነዉ) እየተላላሱ በሚያጠይፍ አኳሗን መመልከቴ ነበር። “ይሕችያልታደለች፤ተቆርቋሪ መንግሥት ያጣች አገር… ድሕነት አሳሯንየሚያሳያት አልበቃ ብሎ፤ የነርሱ ቆሻሻ ባሕል ማራገፊያ መሆኗስታይ ያቃጥላል” አልኩ በወቅቱ ለራሴ ። የእኔን ሃሳብና ቁጭትየሚጋራ ድፍን ሙሉ አገር እንደሆነ አልጠራጠርም። በሌላ ቀንጥቆማ ወደ ደረሰኝ መዝናኛ ስፍራ አመራሁ። ቦታዉ ከቦሌትምህርት ቤት ሽቅብ እንደተጓዘ “ቦሌ ኬክ ቤት”ን ያገኛሉ፡ ከኬክቤቱ በግምት 200 ሜትር ርቀት ላይ ከመንገዱ ግራና ቀኝ በመደዳከሚገኙ በርካታ ባር ቤቶች ከቀን በኩል ቅድሚያ የሚያገኙት“ላጌቶ” የተባለዉን የግብረሰዶማዉያን መናኻርያ ባር ነዉ።በሚታይ ጉልሕ ጽሑፍ የመዝናኛዉ ታፔላ ተሰቅሏል። በግራዉንዱአልፈዉ ባሩ ወደ ሚገኝበት አንደኛ ፎቅ ይደርሳሉ። ከእነሱ በቀርሌላ ተጨማሪ ሌላ ሕንጻ የለም። የባሩ ባለቤት አስመራ የቆየና“ላጌቶ” የሚል ተመሳሳይ መጠሪያ የሰጠዉ መዝናኛ ከፍቶ እስከዘጠናዎቹ አመታት አጋማሽ ሲሰራ እንደቆየ ከራሱና ከኤርትራዉያንጭምር ማረጋገጥ ተችሏል። አስመራ ያለዉ መንግስት በግብረሰዶምዙርያ ጠንካራ አቋም ያለዉ ሲሆን በዚህ ርካሽ ተግባር ተሰማርቶየተገኘ ማንኛዉም ግለሰብ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ በሞትእንዲቀጣ ይደረጋል። ይህ ግለሰብ ሻዕቢያ ሲደርስበት አምልጦበየመን በኩል አዲስ አበባ ይገባል። አስመራም አዲስ አበባምየሚታወቅበት መጠሪያ ስሙ “ላጌቶ” በባሩ ስያሜ ነዉ። ይህ ማለት( Gay-ጌይ) የሚለዉን ለማመላከት ነዉ የሚሉ አሉ።በየዕለቱ በዚህባር አካባቢ ፖሊሶች አይጠፉም። ግለሰቡ ኤርትራዊነቱን ሸሽጎ“ሻዕቢያ ሊገድለኝ ሲል ያመለጥኩ የትግራይ ተወላጅ ነኝ” እያለከማደናገሩ በተጨማሪ ሴት “ጥንዶች” ወይም ‘ሌዝቢያን’ በብዛትአይጠፉም። ለመግለጽ የሚቀፉ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የሚታየዉኤርትራዊዉ እና ግብረሰዶማዉያኑ አባላቶቹ በሚለቀቀዉ ዘፈን(ዘፈኖቹም የነጭ እና የሻዕቢያ ናቸዉ)ጣልቃም ከአየአቅጣጫዉ”አሞሬ”…አሞሬ” የሚሉት ቃላት ይወረዉራሉ።ትርጉሙን ስጠይቅ “ፍቅረኛየ” ማለት እንደሆነና የ“Gay”ዮቹ ቋንቋእንደሆነ ተረዳሁ። ሽንት ቤት ሳመራ ባየሁት ነገር አስታወኩ!ወዴት ያመራን ይሆን?” በማለት ደምድሞታል።

በዚህ የባህል ወረራ መበስበስ ጥቃት የደረሰባት ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር ቁጣ ወርዶ መለስ ዜናዊን  እንደ “ሎጥ” ዘመን ሕብረተሰብ ዋና አበስባሽ መሪው መለስ ዜናዊን በሞት ቀጥቶታል።

በአገራችን ውስጥ በጀርመን ፊልም ሰሪዎች ቅንብር አንድ የሃይማኖት ሴራ ለመፈጸም ሙከራ ተደርጎ ነበር።

 ማርያም መግደላዊት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የተለየ ፍቅርና ፆታዊ ግኢነኙነት እንደነበራት የሚገልፀው እየሱስ አልዓዛርን ከሞት በተአምር ማስነሳቱ ተጥሶ በአፉ -ለአፍ ሳይንሳዊ መፍትሔ ተጠቅሞ እንደሆነ ያሳያል። ይባስ ብሎ ሓዋርያት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ሲሰሩ ይገልጻል።

በፊልሙ ስክሪፕት ላይ ሳይጻፍ (በተንኮል ሰናሱሩን ለማሳለፍ) በልምምዱ (ተዋናዮቹ እንዲለማመዱት የተደረገው) ወቅት የተከሰተው አስደንጋጩ ክፍል ደግሞ እየሱስን አሳልፎ የሸጠው ይሁዳ ጋር ከንፈር ለከንፈር እንዲሳሳሙ የተደረገበት አስደንጋጭ ክስተት ለፊልሙ ተመርጠው በነበሩት በኢትዮጵያ ገዳማት እና በተክርስትያናት ቅጥር ግቢ ውስጥ ድርጊቱ እንዲቀረጽ ተደርጎ በጀርመንኛ እና በአማርኛ ቋንቛ አንዲሆን በተንኮለኞዩ በጀርመኖች እና ተባባሪ ኢትዮጵያዊያን ፊልሙ አንዲቀረጽ ተዶልቶልን እንደነበር መዲና የተባለው ጋዜጣ ታህሳስ 2004 ዓ.ም ዜናው አውጥቶት እንደነበረ ይታወሳል። ሆኖም በጠንካራ አገር ወዳድ እና ሃይማኖታቸውን በሚያከብሩ ወገኖች ሴራው ከሽፏል። ክርስቶስ ግብረሰዶም ፈጻሚ እንደነበረ እና ኢትዮጵያዊ ንም አጸያፊው ተግባር እንዲከተሉ የሚገፋፋ የሰይጣኖች ሴራ ነበር። የወያኔ ስርዓት የላመጣብን ጉድ የለም

 

በጣም የሚገርመው ደግሞ በዚህ አስጸያፊ ግብረሰዶም ስነ ምግባር የሚያበረታቱ ድረገጾች እና በግብረሰዶማዉያኖቹ የታተሙ መጽሐፍቶች ቢኖሩ ስፈልግ ፤ ይህንን አግኝቻለሁ።EthiopiaLGBT.com (GBT የሚለው ገይ፤ባይሴክሹዋል፤ እና ትራንስ ጀንደር ማለት ነው)እናEthiopiangay.com  እና ከዚህ ሌላ  “የሰዶም ነብሳት” የሚል የግብረሰዶም አበረታታች መጽሃፍ ታትሟል። መለስ ዜናዊ ሲሞት ከልብ ካለቀሱለት አልቃሾቹ እነኚህ ክፍሎች አንደኞቹ ክፍሎች ነበሩ። የዚህ ጉደኛ መጽሑፍ ደራሲ ቃለ መጠይቅ ለማንበብ አድራሻ ገብታችሁ አንብቡት። በጽሑፏ ላይ ወደ 500 የሚሆኑ የወንድ ሸርሞጦች አዲስ አባባ እንዳጣበቧት ይጠቁማል። “መሃረነ ክርስቶስ!!” http://www.ezega.com/news/NewsDetails.aspx?Page=news&NewsID=2805
መደምደሚያ፡
  አሁን በቅርቡ “ጎልጉል” በተባለ የህዋ ሰሌዳ ጋዜጣ “ቀጭኑ ዘቄራ” በተባለ የብዕር ስም የተዘገበ የዛሬቱ ኢትዮጵያ ወጣቶች እና የወያኔ ባለሥልጣናት እና ካድሬዎቻቸው የተላበሱት የበሰበሰ የመንፈስ እና የባህል ወረርሺኝ በየዝግ ቤቶች እየዞረ የታዘበው አስገራሚ ዘገባ እንድትመለከቱት ላስነብባችሁ እና ልደምድም። 

“በሬ ለምኔ” የፍየል ቁርጥና ጥብስ መለያ ማስታወቂያ ነው።ከኦሎምፒያ ወደ መስቀልፍላወር በሚወስደው መንገድ ላፓሬዚንአለፍ እንዳሉ ወደ ግራ ሲታጠፉ ያገኙታል። ለጉዳዬ የሚመቸኝንበሬ ለምኔ ላመላክት እንጂ ብዙ “በሬ ለምኔ” ቤቶች አዲስ አበባተከፍተዋል። ያዲሳባ ቀምጣላ ካድሬዎች፣ ልማታዊ ባለሀብቶች፣አቀባባዮችና ባለጊዜዎችና አጫፋሪዎቻቸው እድሜ ለማራዘም ፍየልይመገቡና ማታ ልቅ የግብረ ስጋ ለማድራት አይጨነቁም።

 

………እጠቆምኩት ቤት ስትገቡ ፍየል የሚያገላብጡት የሚታወቁባለሥልጣናትና ታዋቂ ካድሬዎች ናቸው።……አንዱን “ሮዚና” ዝግቤት ላስተዋውቃችሁ። ሮዚና ዝግ ቤት ማንም ዘው ብሎ አይገባም።ሮዚና ሲደርሱ እንደ መኖሪያ ቤት ጥሩምባ አሰምተው ከተንበሪውንየሚያስከፍቱ ደንበኞች ብቻ ናቸው። “ደንበኞች” ስል እንግባባለንብዬ አስባለሁ።

ሮዚና ወገቧ ሸንቃጣ፣ አንጀት የሚባል ነገር ያልሰራባት፣ ዳሌዋሰፊና ክብ፣ ሽክ ያለች፣ አንገቷ ውድ ነገሮች የሚቀመጡበት፣ ሽታዋየሚያውድ፣ ዓይነ ርግቧ በቀለም እንደ ስዕል የሚዋብ፣ ሳሳ ያለልብስ የምትለብስ፣ እንግዳዎቿን በምትዘጋባቸው ቤትእየተዘዋወረች የምትቀበል አራዳ ነች። አስተናጋጆቿ በጣም ትንንሽልጆች ሲሆኑ ጸሃይ አይነካቸውም። ስራቸው ለሮዚና እንግዶችመስተንግዶ ሳይስተጓጎል መስጠት ነው – የሚጠጣ ያቀርባሉ፤ ፍምእሳት አዘጋጅተው ቡና ያፈላሉ፤ ለማሟሟቂያ የቡናው ስነ ስርዓትበየክፍሎቹ ከተከናወነ በኋላ የጫቱ ሙቀት እየጨመረ ሲሄድ ሺሻይለኮሳል። ህጻናቱ ሺሻ እያሞቁ ደንበኞቹን ለማስተናገድ ከቡናማፍያው በርጩማ ተነስተው ፍራሹ ላይ ሲወርዱ ከአባታቸው ጋርበሰንበት የሚጫወቱ እንጂ የስራ ግንኙነት ያላቸው አይመስሉም።ጫት እየቀነጠሱ፣ ሺሻ እያሞቁ ደንበኛቸውን ባፍ ባፉ መከደም ዋናስራቸው ስለሆነ ተክነውበታል።……..ተጋብዤ የተመለከትኩት ክፍልየነበረችው ልጅ ሪታ ትባላለች። ንግግሯ የቀምጣላ ልጆች አይነትነው። ስትስቅ አማርኛ አይመስልም። ጠይም ቀለሟ የጸዳ፣ ለጋነች። እንደ ጋባዤ አገላለጽ “ጥፍሯ ይበላል”፤ ዕድሜዋ ከአስራአምስት አይበልጥም። ቡና እንደጨረሰች ስስ ነገር ለብሳ ደንበኛዬጎን ቁብ አለች። መቃም ትችልበታለች። ጫት ላኪዎች በትዕዛዝየሚልኩትን ጫት ትጠጣዋለች። ያለ ምንም ማጋነን የቅጠልአበላሏን ፍየል ብታየው በቅናት ምላሷን ትቆርጠዋለች። ምንአደከማችሁ ቅማ ታቃቅማለች። አልፎ አልፎ ሮዚና ለጉብኝት ብቅብላ ስትመለስ ቤቱን ታውደዋለች።ምርቃናው ሲጨምር ወዳጄ ቀስበቀስ ከልጅቷ ጋር ተጣበቀ። እጆቹም ሁለመናውም እሷ ላይ ሆነ።በቃ ደረቱ ላይ ጣላት። ደረቱ ላይ አንጋሏት ሺሻውን ይምጋል።ብቸኝነቱ ሊውጠኝ ሲደርስ መሄድ አለብኝ ብዬ ተነሳሁ። ፒኮክእንደምጠብቀው ነገርኩትና ተለየሁት። ህጻኗን ልጅ ደረቱ ላይአንጋሏት ስመለከት ልጄን አቅፌ ሳስገሳው ትዝ አለኝ። የሚያስገሳትእንጂ የሚዳራት አይመስልም። እንዲህ ያሉትን ትውልድ አምካኝቤቶች ማጥፋት ቀላል ነው። ግን ተጠቃሚዎቹ ህግ አስከባሪና ህግአወጪዎቹ በመሆናቸው አይታሰብም። አንዳንድ ዝግ ቤቶችበሲቪል ጠባቂዎች የሚጠበቁ ናቸው። አንዳንዴ ቤተመንግስቱንናሟቹን የቤተመንግስት ነዋሪ ይጠብቁ የነበሩት በፈረቃ ይታደማሉ።ዝግ ቤቶች…

“ያራዳ ልጅ” በማለት ሳንቲም የሚለምኑ፣ ሎተሪ የሚያዞሩ የጎጃምጉብሎች፣ የመንገድ ላይ ነዋሪዎች፣ ቀበሌና አድራሻ የሌላቸውወንድምና እህቶች፣ ኑሮ ያዞራቸው የኑሮ ሰለባዎች ይታያሉ። አዲስአበባ ሁሉን ተሸክማ እየመሸላት ይነጋል።

አፕሬቲቬን እየቀነደብኩ ስለ ሮዚ ቤት እያሰብኩ ቆዘምኩ። ቤቱውስጥ ያሉት ህጻናት የተመረጡ ናቸው። መልምሎየሚያመጣቸውና ስልጠና የሚሰጣቸው አለ። በህጻንነታቸውተከትበው ሺሻ ስር ሲርመጠመጡ በዛው ሱስ ይዟቸው ገደልየከተታቸው፣ ኖረውም ተስፋ ያጡ፣ ታመው የፈረደባት እናት እጅየወደቁ አሉ። አገሩ እንዲህ ሆኗል። የኢትዮጵያ ህዳሴና የኢኮኖሚእድገት ያተረፈው እንዲህ ያሉትን ዜጎች ነው። በርግጥ አገሪቱኢኮኖሚዋ አድጓል። ያደገው ግን ለዝግ ቤት ተጠቃሚዎች እንጂለሌሎች አይመስልም። እድገቱ የሚታያቸው በዝግ ቤትናቤታቸውን ለሌሎች ዘግተው አገሪቱን እያለቡ ላሉት ይመስላል።

በሃሳብ እየቀባጠርኩ፣ አፕሬቲቬን እየሳብኩ ቆየሁ። ወዳጄተመችቶታል መሰል አልመለስ አለኝ። ፒኮክ ስለሰለቸኝደወልኩለትና እንስራ እንገናኝ አለኝ። ወደ እንስራ አመራሁ።እንስራ ደግሞ ሌላ ትዕይንት አለ።

እንደምን ከረማችሁ… ። አሁን እንስራ ነኝ። እንስራ ለማታውቁላስተዋውቃችሁ። እንስራ ቦሌ ቴሌ አካባቢ የሚገኝ የምሽት ንዳድቤት ነው። በመለስ ሞት ምክንያት ተፋዞ ከርሞ ነበር። እንስራሲገቡ በጡንቸኞች ይዳብሳሉ። ፍተሻ መሆኑ ነው። እንስራ በር ላይተዳብሰው ሲዘልቁ ቀለሙ አይን ይወጋል። የደም ጢስየሚጨስበት ይመስላል። እንስራ ውስጡ በዲጄ ይናጋል፤ ይነዳል።በምድር ቤት ውስጥ የሚደለቀው ሙዚቃ ከተለያዩ አቅጣጫከሚፈሰው የተደበላለቀ ቀለም ጋር አንድ ላይ ተዳምሮ የሲኦል ቤተሙከራ ይመስላል። መድረኩ ላይ እየተገመዱ የሚላቀቁትተዋንያኖች እንግዳ ያስደነግጣሉ። ቁመታቸው ረጃጅም የሆኑእንስቶች የተጠና ዳንስ ይተውናሉ።

እርቃናቸውን ያለ ልብስ የሚናጡት እንስቶች ሃፍረታቸው ላይየቻይና ማራገቢያ የምትመስል አነፍናፊት ከመለጠፋቸው ውጪሁሉም ነገር እንደ አዳምና ሄዋን እንደ ድሮው፣ እንደ ጥንቱ ነው።እርቃን!! ዳንሱ “ብልግና ተኮር” ይባላል። ወገብና መቀመጫንበማላመጥ ሲወዘውዙት ማየት ይመስጣል። “ኮረኮንች” የሚባለውምንነቱ የማይታወቀውን አልኮል በሉት ዊስኪ እየተጋቱ አብረውየሚያውካኩትን ለተመለከተ አገራችን ውስጥ ችግር በቃል ደረጃምየሚታወቅ አይመስልም።

ከየአቅጣጫው የሚወርደው ባለቀለም ጨረር የሰውነታቸውን ቀለምእንደ እስስት ይቀያይረዋል። እየነደደ ወርዶ የሚቀንሰው ብርሃንውስጥ ኮሮኮንች ያሳበዳቸው ይዘላሉ። አንዳንዶች መድረኩ ላይሳያስቡት ደርሰውበት ዓይናቸውን ከእምብርት በታች ቸክለውይቅበዘበዛሉ። አንዳንዶች ጥንድ ሆነው መጥተው ብቻቸውን ያሉይመስል በሜዳ ላይ ወሲብ መሰል ዳንስ ተማርከው ዓይናቸውሲቅበዘበዝ አለመስማማት የሚፈጠርበት አጋጣሚ አለ።

ስድስት የሚሆኑት ዳንሰኞች አጎንብሰው መቀመጫቸውንሲወዘውዙት፣ ተሸብርከው “እንካ፣ አምጣ” ሲሉ፣ ሙዚቃውሲያቃጥር “የኮረኮንቹ” ኮታ ሳይታወቅ ይበረታል። ከቦሌ አካባቢናከዩኒቨርሲቲ መንደር የሚዝናኑ መስለው የሚነግዱ በተመሳሳይራቁታቸውን ከጊዜያዊ ጓደኞቻቸው ጋር ያስነኩታል። የዩኒቨርሲቲዳይ ካነሳሁ አንዴ ወደ አንጋፋው የዝሙት ገበያ ናዝሬት ፔንሲዮንላምራችሁ።

ናዝሬት ፔኒስዮን እንደ ዛሬው ሳይሆን “ሻሞ” የሚባልበት ለሞትመጣደፊያ አልኮል መቸርቸሪያ ባር ነው። ናዝሬት ፔንሲዮንአካባቢው የጫት መቃሚያና የድለላ ስራ እምብርት በመሆኑ ሰውስፍሩ ነው። ናዝሬት ፔንሲዮን በብዛት የንግድ ስራ ኮሌጅተማሪዎች እንደሚታደሙበት አንድ ወቅት መረጃዎች በይፋተሰራጭተው ነበር።

በተለይ ከክፍለሃገር የሚመጡ ተማሪዎች ከመንግስት የሚሰጣቸውወርሃዊ ድጎማ ለቀለብና ለማደሪያ ስለማይበቃቸው ናዝሬትፔንሲዮን ለስራ መሰማራታቸው ያደባባይ ወሬ ነበር። “ይሞታልወይ?” ያለች ተማሪም ነበረች። ውዱ መሪያችን፣ ነብሳቸውንይማረውና፣ ስጋቸውን እየሸጡ የሚማሩ ተማሪዎችንአስተዋውቀውናል። እኚህ መሪያችን ናቸው “ልማታዊ ሴቶችንአፈሩ፣ ለሴቶች ልዩ ትኩረት አዘነቡ” የሚባሉት፣ እየተባሉ ያሉት።የኮሜርስ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይ ወደ ሀዋሳናአርባ ምንጭ ችግሩ ያስከተለው ቀውስ ቤተሰብን አንገት ማስደፋትየደረሰበት ደረጃ ደርሷል።

ቤተሰብ ልጄ ተምራ ተመረቀች ብለው ሲጠብቁ አጅሬውየቀሰፋቸው ጥቂት አይደሉም። ሃዋሳ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የቡናቤት ኮማሪቶች በ”ገበያዬን” ወሰድሽብኝ ከፍተኛ ጸብ ውስጥ ሲገቡማየት የተለመደ እንደሆነ ሀዋሳ በነበርኩበት ወቅት ያስተዋልኩትናያረጋገጥኩት ጉዳይ ነው። አንዴ እኔው ራሴ አብራኝ እንድትጠጣለጋበዝኳት ልጅ ይህንን ጥያቄ አቅርቤላት “ገበያችንን ዘጉት”በማለት የስድብ ናዳ እያወረደች ነበር ሁሉንም ያጫወተችኝ –ተማሪዎቹን ማለቷ ነበር። የሴቶች ተሳታፊነት አደገ ይሏል እንዲህነው። ነብስ ይማር።

ወደ እንስራ ልመልሳችሁ። እንስራ ጥቂት እንደቆየሁ ወዳጄ ያችኑልጅ አንጠልጥሎ መጣ። መጨለጥ ቀጠለ። አስቀድሞም ሲጠጣስለቆየ ለመስማት ጊዜ አልወሰደም። እንደውም እንደ አዲስ ጀበናመንተክተክ ጀመረ። ህጻኗን ከፊትለፊቱ ወትፏት በቁሙ እንደውሻይቀነዝራል። መብራቱ ስለሚመች ስጋት የለም። በቁሟ በዳንስእያስመሰለ ፈትጎ ሊገላት ምንም አልቀረም። ይህ ሰው ያለውንኃላፊነት እዚህ ከሚያደርገው ተግባሩ ጋር በማገናዘብ ሳስበውአመመኝ። እንዲህ ያሉ ብዙ “ትልልቅ ሰዎች” ይመሩናል። በችጋርይጠብሱናል። ሲሞቱ በደቦ ያስለቀሱናል። በጀት ከልክለው በረሃብያቃጥሉናል። ሲሞቱ ደግሞ በጀት መድበው ደረት ያስመቱናል።“ያገራችሁን ህዳሴ ከእኛ ጠብቁ” እያሉ ያለ ሃፍረት ይሰብኩናል።አጽማቸውን እናመልክ ዘንድ ይመኛሉ። ከወዳጄ ጋር የትና እንዴትእንደተገናኘን አስታውቃለሁና ተረጋጉ። አሁን በፈጣሪ እጅ ላይ ሆኖእየኖረ እንደሆነ፣ ከቤቱም እንደማይወጣ ሰምቻለሁ። ሮዚ አራዳዋአለች እንዳማረባት። ህጻናቱ ግን … ። ሰላም እንሰንብትና ሳምንትእንገናኝ!!”

መለስን ከቀጣ የፈጣሪ ቁጣ ያድነን። አመሰግናለሁ።

 

 

Advertisements

ለመሆኑ ኢሕአዴግ አለ እንዴ? (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

ጤና ይስጥልኝ ክቡራትና ክቡራን አንባቢያን፤

በዚያኛው ሰሞን ስለብዙዎቹ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ከእግዚአብሔር መንገድ መራቅና ስለሕዝበ ክርስቲያን የመንፈስና የልብ መሸፈት አንዳንድ ነጥቦችን ተናግሬ ነበር፡፡ አንድ ሦስት ያህል የነጻው ሚዲያ ድረገጾች አስተናግደውታል፡፡ እግዚአብሔር ይባርክልኝ፤ መንግሥተ ሰማይንም ያውርስልኝ፡፡ ሙከራየ ጥቂቶችን ከገቡበት አረንቋ እንዲወጡ – እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ – ለማሳሰብ እንጂ ሃይማኖተኝነትን ለመክሰስ ወይ ለመውቀስ አይደለም፡፡ ሃይማኖት የሌለው ሰው ልጓም እንደሌለው የጋማ ከብት ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ እንደመኖሩ በዚያው መጠን ሃይማኖት አለኝ የሚልም ሰው ከለየለት ሃይማኖት የለሹ ሰው ባላነሰ ምናልባትም በከፋ ደረጃ አጥፊ ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ይስተዋላልና ያን መረዳትና ሲቻልም ማስቀረት እንዲቻለን በዚህ ረገድ የሚታዩብንን ማኅበረሰብኣዊ ህፀፆች በግልጽ መመልከቱ እንደጥፋት ሊወሰድ አይገባም፡፡ በግልጽ የሚታይንና ጥፋት የሚመስልን ነገር የማጋለጥ መብት ደግሞ ከማንም በችሮታ ሊሰጥ ወይ ሊከለከል የማይችል ሰው በመሆን ብቻ ሊገኝ የሚችል ሥልጣን ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ  የእረኛ ማጋጣ በጎችን ቀበሮ እንደሚያስበላ መጠቆምም ዋናው ዓላማየ ነው፡፡ ጋጣውና በረቱ በየትኛውም የሃይማኖት ክፍል(You may call it sect or denomination,) ይመራ ዋናው ጉዳይ ግን የራሱን ቀኖና በትክክል መከተሉ ላይ ነው፡፡ ወያኔን ብዙዎች የምንወቅሰውና የምንከሰው ሌላው ሁሉ ይቅርና ራሱ የሚያወጣቸውን ሕጎችና ካለሕዝብ ቀጥተኛ ተሣትፎ በሚመስሉት አፈንጋጮች ብቻ ተደግፎ የደነገገውን ሕገ መንግሥት እንኳን ማክበር ባለመቻሉ ነው፡፡ ራሱ ያቆመውን ሕግ ማክበር የማይችል ደግሞ ዕብድ ወይ ሕጻን ልጅ እንጂ ዐዋቂ ሊባል አይችልም፡፡ ‹ሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ› የሚባለውም ለዚህ ዓይነቱ አፄ በጉልበቱ ነው፡፡

ለማስተናገድ ድፍረት ያጡት አንድም ያልኩት ሊገባቸው አልፈለጉም አለበለዚያም የሀገራችን ችግር የዴሞክራሲ እንጂ የሃይማኖት አይደለም ብለው ተዘናግተው ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ እውነትን በጥሬው መናገር ለሺዎች ዘመናት በሕዝብ ጫንቃ ላይ ተጎብሮ በእግዚአብሔር ስም ሲያነሆልለን የባጀው ከማይምነትና ከባህላዊ ልማዶች ጋር የተዛነቀው ሃይማኖታዊ ይትበሃላችን በነሱም ላይ የፍርሀት ድሩን አድርቶ ላለመዳፈርና ጥርስ ውስጥም ላለመግባት ፈልገው ይሆናል – ግን ግን እኔ እላለሁ – መጠንቀቅስ ኅሊናን ከሚያስጨንቅ የእውነት ፍላጻ ነው፤ መጽሐፉም ‹ሥጋን የሚገድሉትን … ሣይሆን ነፍስን የሚገድለውን… ፍሩ› ይላልና፡፡ በየትኛውም መንገድ ይሁን ያን “ወርቅ ጽሑፍ” አለማስተናገዳቸው በዚህ ወይ በዚያ የሚያሳማቸው ነገር መኖሩን የሚያመላክት ብቻ ሳይሆን በሀገራችን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ባህል ገና (እ)ያልዳበረ እንደሆነና ዕዳ ጉዳችን  ተዝቆ የማያልቅ መሆኑን ጭምር የሚጠቁም ነው፡፡ እግዚአብሔር ይሁነን ከማለት ውጪ ምን ይባላል?

በዚያ ጽሐፍ በራሴ አጎት ላይ የደረሰ አሳዛኝ ታሪክ ወደፊት እገልጣለሁ ብዬ ነበር፡፡ ነገር ግን ቆይቼ ሳስበው ከዚያ በላይ መሄዱ ጥሩ እንዳልሆነ ስለተረዳሁ ያ የጠቀስኩት የአጎቴ የነፍስ አባት የትላልቅ ሴቶችና ወንዶች ልጆች እናት የነበረችውን አሮጊት ባለቤቱን ጣጥሎ የአጎቴ ዐርባ በቅጡ ሳይወጣ ጓዙን ጠቅልሎ መግባቱን ብቻ መጠቆሙ ከበቂ በላይ ነው፡፡ ይህ እንግዲህ የዛሬ 50 ዓመት ገደማና በገጠር ውስጥ ነው፡፡ በተለይ በዚህ ዘመነ መንሱት ውስጥ በከተማ እየተሠራ ያለውማ ከዚህ በስንት እጥፍ ይብስ? ይህን መሰል ጨዋታ ከጓደኞች ጋር አንስቼ በቀደም ዕለት ስናወራ አንዷ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሩቅ ሴት ጓደኛችን ያጫወተችን ገጠመኝ በእጅጉ አስደመመኝ – በእውነቱ የሚዘገንኑና እጅግ  የሚያስጨንቁ ብዙ ነገሮችን እንሰማለን፡፡ እናም እሷን ብቻ ተንፍሼ ወደጀመርኩት ሃሳብ እገባለሁ፡፡ ይቅርታችሁንና ትዕግስታችሁን ወዳጆቼ፤ የችግሮቻችንን ዙሪያ ገባ መረዳት ለመፍትሔው ሁለንተናዊ ፍለጋ ያመቻልና ነው በዚህ አቅጣጫ ትግስታችሁን መሻቴ፡፡ እንጂ የቄሣርን ለቄሣር በሚለው ነባር ብሂል የሃይማተኞችን ጉዳይ ለነርሱው ሰጥቶ ሥጋዊውን መንገድ ብቻ መንጎድ በተቻለ፡፡ ግና ያ ብቻውን አይበቃም፡፡ ሥጋና ነፍስ የተቆላለፉ ናቸው፡፡ የአንዱ መጎሳቆል ለሌላኛው መጎሳቆል ቀጥተኛ ተጠያቂ ነው፡፡ በተለይ ፍቅርንና ሰላምን የተጠማች ነፍስ ቂም በቀልንና ዐመፅን ካረገዘች ሥጋ ጋር ስትዋሃድ ምን ሊከሰት እንደሚችል ኢሕአዲጋውያንን የሚያውቅ ያውቃል፡፡ ስለዚህ የሃይማኖት በቅጡ መኖርና አለመኖር በአንድ ማኅበረሰብ ገጽታ ላይ ያለው ተፅዕኖ ቀላል ባለመሆኑ እነዚህን መሰል ማኅበራዊ ጉዳዮች አንዳንዴ መዳሰሱ ጉዳት የለውም ባይ ነኝ፡፡

ያቺ ጥሩ ክርስቲያን እንደሆነች የገመትኳት የሥራ ባልደረባችን እንዲህ አለችን፡- “የእህቴ ነፍስ አባት ጸሎት አድርገው ቤቷን ጠበል ረጭተው ሊሄዱ ሲሉ አንድ መቶ ብር ከቦርሣዋ አውጥታ ልትሰጣቸው ስትል ‹ አይይ…! ይችማ ምን አላት! ዛሬ መቶ ብር አንድ ብር ሆና ምን ትገዛለች ብለሽ ነው የኔ ልጅ?› ብለው ገንዘብ እንድትጨምርላቸው የሌሎች ነፍስ ልጆቻቸውን ትሩፋት እየጠቀሱ በቃላትና በዐይነ ውኃቸው ቢማጸኗትም ‹እንዴ አባ! እኛ እኮ ድሆች ነን፤ አቅማችን የቻለውን እንሰጣለን እንጂ ከሀብታሞቹ ጋር ለምን ያወዳድሩናል? ብላ ሸኘቻቸው፡፡” ይህን ስትነግረን የጠላታችሁ ዐመድ ቡን ይበል ሁላችን ዐመዳችን ቡን  አለ፡፡ እስከዚህ ወርደናል፡፡ ሃይማኖታችንን ሸቀጥና ውራጅ ልብስ አድርገውብናል፤ ክርስቶስ ይሄኔ ነበር ‹የአባቴን ቤት መሻቀጫ አደረጋችሁት!› ብሎ ድንብርብራቸውን ማውጣት የነበረበት – ታሪክ ተደገመ፡፡ መስቀል ከተሳለምክ በኋላ እጅ እጅህን የሚያየው ቄስ ብዙ ነው፤ ከነአካቴው ሀፍረቱን ሸጦም ‹ለመስቀሉ አምስት ብር ወዲህ በል!› የሚልህ ዐይኑን በጨው ያጠበ ደፋርም ያጋጥምሃል – በቅዳሤ ሰዓት ልብሰ ተክህኖውን ግጥም አድርጎ ለብሶ ንዋየ ቅድሣትን ይዞ በቡድንና በተናጠል በታቦት ስም የሚለምንህ ሞልቷል – እንደምክንያት ለታቦት ማሠሪያና ለዕድሳት ይበሉህ እንጂ በአብዛኛው ለግላቸው ነው – ማኅተምና ካርኒ እንደሆነ ዕድሜ ለጥቅም ሼሪኮችና ፎርጀሪ ችግር የለም – የትም ይገኛል፡፡ በዚህ ‹የቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ግንባታ› በሚሰኝ የዘመኑ ታላቅ ኢንቬስትመንት  የልመና ቢዝነስ ምክንያት ያለፈላቸው ካህናትና ምዕመናን በጣም ብዙ ናቸው ይባላል፡፡ በሥራ ከሚገኝ ገቢ ይህኛው ስንጥቅ ነው አሉ ልጄ፡፡ በገበያ ጥናት የኢኮኖሚክስ ሕግ መሠረት አንድ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ሰው ወደሌላ ሥፍራ እንዳይሄድ ብዙ ጽላት በመደራረብ የሚሸቅጡ ቄሶች አሉ – ‹እመብርሃን እዚሁ ካለችልኝ ለምን ወደሌላ ቦታ በመሄድ እለፋለሁ?› እንድትልና በዚያው ሁሉንም እንድታገኝ፡፡ በጠበል ሽያጭ የሚከብሩ አሉ – ደግነቱ በገንዘብ የሚገኝ ጠበል የፈዋሽነት ኃይሉ በፈጣሪ ይሰረዛል እንጂ፡፡ የደብር አለቃንና ቀዳሽ ወይ አወዳሽ ካህንን ደህና ገቢ ያለው ቦታ በጥሩ ደሞዝ ለመመደብ በሺዎች የሚገመት ጉቦ አስከፍለው በቀላሉ የሚከብሩ አለቆችና ሊቃነ ጳጳሣትን ጨምሮ ከፍተኛ የቤተ ክህነት ባለሥልጣናት ሞልተዋል፡፡ ጉቦ ካልከፈልክ – ለምሳሌ – የቅ. ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን አለቃ ሆነህ መሾም አትችልም ይሉሃል፡፡ በኪነ ጥበቡ ይታረቀን እንጂ በቁማችን ጠፍተናል፡፡ እረኛው የጠፋበት በግ እና መሪ የሌለው ሕዝብ ደግሞ ምን ሊገጥማቸው እንደሚችል በሀገራችን በግልጽ እየታዬ ነው፡፡ እነኚህን በክተው እያበከቱ ያሉ ሰው መሳይ በሸንጎዎችን መንካት ኃጢያት ከሆነ አሁኑኑ ልኮነን፡፡ ግን እንዳይመስለን – በዚህ የሚኮንን አምላክ የለም – እነሱው ናቸው እንዳናያቸው ያሳወሩን፡፡  ሀገርንና ሕዝብን ከመንግሥት ባልተናነሰ እንዲያውም በበለጠ ሁኔታ እንዴት አድርገው አሽመድምደዋት እንዳሉ ብዙ ነገር መናገር ይቻላል፡፡ አፄ ቴዎድሮስን የመሰለ ይላክባቸው!!

በነገራችን ላይ ትችቴ በኦርቶዶክስ ላይ ጠንከር ያለ እንደሚመስል አላጣሁትም፡፡ ይህ የሆነው የአነሳሴ ሚዛን ነው፡፡ እንጂ የተለያዩ ጥፋቶች በሌሎች እምነት ተከታዮችም እንደሚስተዋሉ ጠፍቶኝ አይምሰላችሁ፡፡ አብነቶችን ግን ሳልጠቁም ማለፍ አልፈልግም – ከወቅታዊው ልጀምር፡፡

ሀገራችን የጉድ መፍለቂያ ከሆነች ዋል አደር ማለቷ አይዘነጋም፡፡ ‹በሕይወትህ ምን የሚያሳዝንህ ነገር ይታወስሃል?› ተብሎ የተጠየቀ 85 ሚሊዮን ሕዝብ ‹የሚመራ› ሰው ‹በብዙ ነገሮች ደስተኛ ነኝ፤ ነገር ግን በእናቴ አለመዳን ሁልጊዜ አዝናለሁ› ብሎ መናሩን ስሰማ እኔም በዚህን መሰል ሰው ‹በመመራቴ› ክፉኛ ማዘኔን የምገልጽላችሁ ፈጣሪ ከዚህን መሰሉ ሞኝነት እንዲመልሰው በመማጸን  ነው፡፡ በእውነቱ ትልቅ ስህተት ነው፤  የሆዱን በሆዱ ይዞ ቢያንስ በአደባባይ እንዲህ ባይናገር ይመረጥ ነበር፡፡ የሰውዬው ሴክት በትልቅ ግምት 10 ሚሊዮን ተከታይ አለው ቢባል ቀሪው 75 ሚሊዮን ሕዝብ የሌላ እምነት ተከታይ ነው ማለት ነው – ‹የጠፋ›፡፡ ስለዚህ ይህ ሰው ‹የጠፋ› ወይም በርሱው አገላለጽ ‹ያልዳነ› 75 ሚሊዮን ሕዝብ ‹እየመራ› ነው ማለት ነው፡፡ ከዚህ በላይ ድንቁርና የለም፡፡ የኔን መዳንና አለመዳን እንኳን ሌላ ሰው እኔ ራሴም አላውቅም፡፡ ማን ነውና እሱ ስለኔ መዳን አለመዳን በአደባባይ አፉን ከፍቶ የሚናገር? ከዚህ ዓይነቱ አስነዋሪ ንግግር መታቀብ ያስፈልጋል፤ በዚህ የረቀቀ መለኮታዊ ሥራ አላግባብ እገቡ ብዙዎች ሲጃጃሉ አስተውላለሁ፡፡ እውነትን መናገር ካስፈለገ የጠፋውስ በሃይማኖቱ ምክንያት ሳይሆን በደም ባሕር ከሚዋኝና በሙስና ከተጨማለቀ ፓርቲ ውስጥ የሚገኘው ርሱ ራሱ  ነው፡፡ በመስትዋት ቤት ውስጥ የሚኖር ሰው ድንጋይ ለመወርወር የመጀመሪያው መሆን የለበትም መባሉ ይህን ዓይነቱን ዐላዋቂነት ለማለዘብ ነው፡፡ የእርሱ እናት ይዳኑ አይዳኑ የሚያውቀው አንድ አምላክ ሆኖ በዚህ ንግግሩ ግን መላውን የሌላ እምነት ተከታይ ሕዝብ አስቀይሟልና ንስሃ ይግባ፡፡

ማንኛችንም ይህን ነባራዊ እውነት በቅጡ ብንረዳ ለማኅበራዊ ተራክቦኣችን ስኬታማነት ይበልጥ ይጠቅመናል፡፡ ‹ከአንተ ሃይማኖት ይልቅ የኔ ትክክለኛው ነው› የሚሉት ፈሊጥ የከንቱዎች እንጂ የአስተዋዮች ሊሆን አይችልም፡፡ የሚያዋጣውን የሚያውቅ ባለቤቱ እንጂ ጎረቤቱ ሊሆን አይገባም፤ አይችልምም፡፡ ዕድሜው ለአካለ መጠን የደረሰን ሰው ይህን ተከተል ያን አትከተል ብሎ የሐኪም ማዘዣ ዓይነት ሃይማኖታዊ ትዕዛዝ ማውጣት የጤናማነት ምልክት አይደለም፡፡ ከዚህ አንጻር ብዙ ስህተቶችን ከየእምነት ተቋሙ እናያለን – በተለይ ተከታይን በማፍራት ረገድ፡፡ አስታውሳለሁ – አንድ ወቅት በአንድ ሴክት አንድ ፊልም ተሠርቶ ለዓለም ተሠራጭቶ ነበር፡፡ በጣም ነው ያስገረመኝ፡፡ ሆሊውድ እንኳን እንደዚያ ያለ አስደናቂ ፊልም ሊሠራ አይችልም፡፡ የፊልሙ ይዘት አንድ የሃይማኖት አባት ከአንድ ሴክት ወደሌላ ሴክት እንደኮበለሉ የሚያሳይ የቁጩና ፍጹም ያልተሳካ ሙከራ ነበር – ያን ጉድ የሸፋፈንኩት ሆን ብዬ ነው – እንኪያውስ ብዙ ስንክሳር ባጻፈኝ፡፡ ያሣፍራል፤ ነገርን ከሥሩ የሚመረምር ሰው ጠፍቶ እንጂ በዚያ መጥፎ ሥራቸው ምክንያት ሴክታቸው ምዕመናንን አጥቶ ባዶ በቀረ ነበር፡፡ ልብ አድርጉ! ሰውን ማታለል ቀላል ሊሆን ይችላል – አንዴም ሁለቴም ምናልባትም ከዚያም በላይ፤ ፈጣሪን ማታለል ግን በጭራሽ አይቻልም፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ማታለል ቢፈቀድልን እስከዘላለሙ ማታለል እንችላለን ማለት አይደለም፡፡ እናም የየትኛውም እምነት ተከታይ መጠንቀቅ የሚኖርበት ነገር አለ፤ ይሄውም በአንዱ ኪሣራ ሌላው ለማትረፍ የሚደረገው ሩጫ በፍጹም የማያዋጣ መሆኑን ተገንዝቦ ወደኅሊና መመለስና ፈጣሪን በትክክል መታዘዝ እንደሚገባ መረዳት ይገባል፣ ‹እንዳገርህ ቀድስ፣ እንዳገሬ እቀድሳለሁ› ይባላል፡፡ ጥሩ ብሂል ነው – ‹ሰው በወደደው ይቆርባል›ም እንላለን፤ እናም ሃይማኖትን ተመርኩዞ የሚፈጸምን በጉልኅ የሚታይ ህፀፅና ነውር ከመንቀስና ከማሳየት ባሻገር የሰውን የእምነት ነጻነት ባንጋፋ መልካም ነው፡፡ ይህ ሲባል ደግሞ ለእውነትና ስለእውነት ብለን በእውነት መንገድ እንመላለስ እንጂ ያለንበት ሴክት በግድ ከሌሎች የበለጠ ወይም ያነሰ ነው ለማለት እንዳልሆነ መገንዘብም ያሻል፡፡ ጣፋጭ ፍሬ ከዛፉ ላይ ያስታውቃል፤ መልካም ሥራና ጥሩ አረማመድም ከመንገዱ በበለጠ ወደጽድቅ ቦታ ያደርሳሉ፡፡ እናም ‹የኔ ካንተ ይበልጣል› የሚለውን የደናቁርት ዜማ እንተወው፡፡

 

የደርጉ ሊቀ መንበር ጓድ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አንድ ወቅት “በርግጥ አሁን ደርግ አለ?” ማለታቸው ይታወሳል፡፡ በርግጥም ያኔ ደርግ አልነበረም፤ ምክንያቱም መለዮውን አውልቆ ባለሱፍና ባለ ክራቫት የጠብደል ወርሃዊ ደሞወዝ ባለቤት ባለሥልጣን ሆኖ ነበርና፡፡ ያኔ የደናቁርቱ የደርግ መሪ መንግሥቱም ሌሎች ከየጎሣውና ከየብሔሩ – እንደሚመስለኝ – ታስቦበት ሳይሆን በአጋጣሚ የተውጣጡ የደርግ አባላትም ስማቸው ተቀየረ እንጂ በሕይወት ነበሩ፡፡  (‹ደርግ›ን ደብድብ፣ ርገጥ፣ ግዛ እንለው ነበር በምህጻረ ቃልነት)

ዛሬስ ኢሕአዴግ አለ?

እንተማመን ኢሕአዴግ የለም፡፡ ሰዎች ግን ያለ እየመሰላቸው ሲደነብሩ ይታያሉ – (ክፉ አውሬ ለምሳሌ እባብ ሞቶም ያስደነግጣል – አንበሣ ያላልኳቸው አክብሬው ነው – ለምን፣ አንበሣ ጀግና ነው – ጀግና ደግሞ መሐሪ ነው ፤ ማሸነፉን ሲያውቅ እንደወያኔ ቀብር ድረስ ገብቶ ‹እከሌን ገዳይ!› ብሎ አይፎክርም – ፈሪ ነው ማሸነፉን የማውቅና ዕድሜ ልኩን በጠላትነት የፈረጀውን አካል እንዳላሸነፈ እየተጠራጠረ ሬሣ የሚደበድብ – ለነገሩ ሞቶ የተቀበረስ ሲኖር አይደል – ወደፊት እናያለን)፡፡ ኢሕአዴግ አቶ መለስ ዜናዊ ሲሞት አብሮ ሞቷል፡፡ ነገር ግን አንዳንዴ እንደዚህ ያለ ነገር ያጋጥማል – ሞቶ ያለመሞት ወይም ያሉ መስሎ መሞት፡፡ ከታሪክ ለማስታወስ ያህል ደርግ የሞተው ግንቦት 8 ቀን 1983ዓ.ም መሆኑን ያጤኗል፡፡ ኮ/ል መንግሥቱ እነኚያን ሀገሪቱ በድህነት አቅሟ ለብዙ ዓመታት በሀገር ውስጥና በውጪ ያሠለጠነቻቸውን ‹ጥቂት/ጢኖ› የጦር መኮንኖች ብዙ የደከሙላትን ሀገራቸውን ለአፍታም ቢሆን ማሰብ አቅቷቸው ለአንዲት የሥልጣን ወንበራቸው ሲሉ ከረሸኗቸው ማግሥት ጀምሮ ሀገሪቱ ውቃቢ ራቃት፡፡ ‹በጊዜ የጮኸ ጅብ አያሳድረኝም› ያሉ ሌሎች የጦር አመራሮችና አጠቃላይ ማኅበረሰቡ ኮሎኔሉን ጅባት ብሎ በመጥላትና በመክዳት ብቻቸውን አስቀራቸው፡፡ እሳቸውም የሠሩትን መጥፎ ነገር ሁሉ እንደታላቅ ድል በመቁጠር በግትርነታቸው ገፉበት – ራሳቸውን ለመመርመር የአምባገነንነት ባሕርይ አልፈቀደላቸውም – በዚያ ላይ ሆድ አምላኪው አጨብጫቢና አንፋሽ አከንፋሹም በዙሪያቸው አለ፤ አምባገነኖች ደግሞ ሞተውም እንዳልሞቱ የሚቆጥሩ ጅላጅሎች ናቸው፡፡ ሕዝቡና ጦሩ ሌላ አማራጮች ቢዘጋጉበት በወቅቱ በለስ እየቀናቸው ለመጡት ለወያኔና ሻዕቢያ ያን ክፉ መሪ አጋልጦ ሰጣቸው፡፡ እሾህን በእሾህ ያስነቀሉት የመሰላቸው ጦሩና ሕዝቡ ግን ከአንዱ የመከራ አዙሪት ሲወጡ ወደባሰበት የመከራ አዙሪት ገቡና መለስ ዜናዊ የተባለ በቂም በቀል ተረግዞ ለጥፋትና ዕልቂት የተወለደ የባንዳ ልጅ ቁም ስቅላቸውን ያሳያቸው ጀመር፡፡ መራገም የሚያውቅበት የኢትዮጵያ ሕዝብ – ተሓት፣ተሓሕት፣ ማገብት፣ ሕወሓት፣ ማሌሊት፣ኢማሌኃ፣ ኢሕአዴግ፣… በሚሉ የክትና የሠርክ ስሞች የራሱን ድርጅት አባላትና ኤሊቶች ሳይቀር እያታለለና በሥልት እየጨፈጨፈ፣ እያሰደደና እያሳደደ የመጣውን ለገሠ ዜናዊን ላለፉት ሃያ አንድ ዓመታት አለቀሰበት – ይሄውና በውስጥ ዐዋቂዎች እንደተገለጸው ባለፈው ሐምሌ 7  ቀን 2004ዓ.ም ከሰንኮፉ ወልቆ ተገነደሰ፡፡ እሱም ብቻ አይደለም፡- ከገሚስ የሚያልፈውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሃይማኖቱ ገብተው እንዲያኮላሹለት ሃይማኖቱንም እንዲበርዙና እንዲከልሱ ከውጪ ሀገር አስመጥቶ ከሕግ አግባብ ውጪ ያስቀመጣቸውም አረማዊ ፓትርያርክ አብረው ተገነደሱ – ‹ሃሌ ሉያ› ይባላል እንጂ አይለቀስም፤ አይታዘንምም – ምክንያቱም እንደመጽሐፉ ‹ብንኖርም ለርሱ ባንኖርም ለርሱው› ነውና! የሕዝብ ጸሎት ሥምረት ከዚህ በላይ ታይቶም ሆነ ተሰምቶ አይታወቅም – የነዚህን ግለሰቦች የዐዋጅ ሞት ተከትሎ የተስተዋለውን የዕብደት መሰል ቲያትር ግን ለጊዜው በዝምታ ማለፉ ይመረጣል፡፡ ይህን መሰል ቲያትር ይነስም ይብዛም  ዱሮም ነበር ፤ አሁንም አለ፤ ወደፊትም ይኖራል፡፡ እውነት ግን ምን ጊዜም እውነት ናትና ብትሰለስል እንጂ አትበጠስም፡፡ ለሞተ ማዘን ተገቢ ቢሆንም ያን ያህል የተነረተው ድራማ ግን ለትዝብትና ለሥላቅ ከመዳረግ በስተቀር ማንንም አይጠቅምም፡፡ ‹ሲነጋ ለማፈር!› እንዲሉ ነው፡፡ ነገ ያፍሩበታል፡፡

‹ኢትዮጵያን አደራ፤ ጀግና አይሞትም፤ ባለራዕዩ መሪያችን፣ ….› ያልተባለ ነገር የለም፡፡ በጸሎት ብዛትና በኅሊና ጸሎት መዝጎድጎድ፣ በቢልቦርድና በአርቲፊሻል የሀዘን ጥብቀት ሰው ቢድን ኖሮ መለስን ቀድሞ የሚድን ባልነበረ፡፡ ግን ቂልነት ነው፡፡ ሳያምን የሞተን ለማጽደቅ የተደረገው ነገር ሁሉ ቤተ ክርስቲያንንም ሰዎቿም ለትዝብት ከመዳረግ ውጪ አንዳችም አይፈይድም፡፡ ያ ሁሉ ልፋት በጠቀመ እግዚአብሔርም እግዚአብሔርን ባልሆነ! ዜጎችም ዕንባቸውን በከንቱ እንዲያባክኑ ተገደዱ – ላይመልሰው ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲባል ብቻ ብዙ ነገር ታዘብን፡፡ ልድግመው – ‹ሲነጋ ለማፈር!›

በወፍ በረር ቅኝት ታሪካዊ ዳራውን በመጠኑ ከዳሰስን ኢሕአዴግ እንዴት ነው የሌለው ለምንስ ነው ኢሕአዲጋዉያን አሁን በሚገኙበት የተዘበራረቀ ሁኔታ ውስጥ ሊገኙ የቻሉት የሚሉትን ባጭሩ መመልከት ተገቢ ነው፡፡ ለዚህም ዓለማቀፋዊ መነሻ ታሪክ አናጣም፡፡

ሌኒን የዛሩን መንግሥት ለመጣል ሲታገል ‹ምን ነካህ? አብደሃል? ከዚህ እንደብረት ከጠነከረ ግድግዳ ጋር ታግለህ እንዴት ታሸንፋለህ?› የሚሉት ወገኖች ነበሩ፡፡ መልሱም ‹ግድግዳው የበሰበሰና ያረጀ ስለሆነ በትንሽ ኃይል ሲገፋ የሚወድቅ ነው› የሚል ነበር፡፡ እውነት ነው፡፡ ለድል ለመብቃት መስዋዕትነት መክፈል ያለ በመሆኑ ቦልሼቪኮች ትግሉ የጠየቀውን ከፍለው ለድል በቅተዋል፡፡

ወያኔም በሕዝብ መክዳትና በጦር የውጊያ ሞራል ማሽቆልቆል እንዲሁም በምዕራባውያን ሁለንተናዊ ድጋፍ በዚያም ላይ ለገንዘብ ባደሩ የጦር መኮንኖች ሻጥር ተደጋግፎ ካራ ምሽግን በማለፍ የሸዋ እምብርት ሸገር ላይ ጉብ አለ – በህልም ብቻም ሳይሆን በቅዠትም ዐይቶት የማያውቅ ድል በድንገት በእጆቹ መዳፍ ገባለት – በለስ ሲቀና እንዲያ ነው፡፡ በቁሙ በስብሶ የነበረው የደርግ ሥርዓት የሚገፋው አጥቶ ለሁለት ዓመታት ያህል በሰመመን እንቅልፍ በአለሁ የለሁም እየተንጠራወዘ ከቆዬ በኋላ የምናውቀውና በያመቱ እየዘገነነንም ቢሆን በጆሯችን ‹የሚንቆረቆረው› ‹ጀግናው የኢሕአዴግ ሠራዊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረው ሬዲዮ ጣቢያ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል…› የሚል አዲስ ቅንቅን ሊዘመርበት በቃ፡፡ ነገሩ የሎሚ ተራ ተራ ጉዳይ ነው፡፡ ያ መዝሙር ታድሶ ወደፊትና በቅርቡ በሌላ ቃናና ቅላጼ እንደሚዘመርበት በጣም ግልጽ ነው፡፡ ግን ለመልካም ይሁን ብሎ መጸለይ ወቅታዊ ምኞታችን ሊሆን የሚገባው ይመስለኛል፡፡

ኢሕአዴግ አልሞትኩም ብሎ ሌት ከቀን እንዲዋሽ የተገደደበት ምክንያት የመሞቱ ምሥጢር ፋታ ስላሳጣው ነው እንጂ ከሞተ ቆይቷል፡፡ በመሠረቱ ኢሕአዴግ የሞተው ዛሬ ሳይሆን ከሰባት ዓመታት በፊት በተደረገው የ97ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ነው፡፡ ይሁንና ዕድሜ ለመርዝ አቀባዮቹ ምዕራባውንና የሩቅ ምሥራቅ ሼሪኮቹ ሬሣውን በግብጽ የዘምዘም ውኃ አባብሰው(mummification)፣ በአይ ኤም ኤፍና በዓለም ባንክ ብድር እስትንፋሱን አጠናክረው በነጻ እንዲጋልበን ፈረስን ያለልጓም ሰጡትና በሜዳ በምንመሰለው ጭቁን ኢትዮጵያውያን ላይ ለቀቁብን – ያበደ ውሻን ጃዝ ብለው የመልቀቅ ያህል፤ የሥራቸውን ይስጣቸው፡፡ እኛም የሞተውን እንዳልሞተ ቆጥረን ተጋለብንለት – አሁን ድረስ፡፡ ቁጥጥሩን አጠበቀ፤ ሥቃዩን ጨመረ፤ በኑሮ ውድነቱ ሰንጎ ያዘን፤ እንኳንስ ለመንግሥት ተቃውሞ ለሽንት ማውጫም የሚሆን የወንድነት መግለጫ ሥነ ሕይወታዊ የሰውነት ክፍል አጣን፡፡ ግን ይህም የሚያልፍና ለበጎም ነው፡፡ እኛ ብቻ አይደለንም በዚህን ዐይነቱ ሸምቀቆ ውስጥ እያለፍን ያለነው – ብዙዎች ነበሩ – አሉም፡፡ ሂደት ነውና ወደፊትም ይኖራሉ፡፡ የኛን ግን አደራውን በቃችሁ ይበለን፡፡

የሥንግ የተያዘ ሕዝብ ደግሞ አይፈረድበትም፡፡ ጊዜ ጀግናን ይፈጥራል፡፡ ጊዜ ፈሪን ይፈጥራል፡፡ ጊዜ ጀግናን ፈሪ ያደርጋል፡፡ ጊዜ ፈሪንም ጀግና ያደርጋል፡፡ ‹የጊዜ እንጂ የሰው ጀግና የለውም › መባሉም ለዚህ ነው፡፡ ጀግንነት ደግሞ ከአመራርም ይወለዳል፡፡ ቁጥር ብቻውን ደግሞ የትም  አያደርስም፡፡ አንድ ነጥብ ሦስት ቢሊዮን የሚገመተው የቻይና ሕዝብ ሌላ አማራጭ እንዳይኖረው ተደርጎ በአንድ የኮሚኒስት ፓርቲ ብቻ የሚቀጠቀጠው ፈሪ ሆኖ አይደለም፡፡ 90 ሚሊዮኑ የግብጽ ሕዝብ ለ30 ዓመታት በሙባረክ የተቀጠቀጠው ፈሪ ሆኖ አይደለም፤ 6.5 ሚሊዮኑ የሊቢያ ሕዝብ ለ41ዓመታት በጋዳፊ የማሰነው፣ 23 ሚሊዮኑ የየመን ሕዝብ በአብደላ ሳለህ ለ33 ዓመታት የተቀጠቀጠው፣ ሃያ ሚሊዮኑ የሦርያ ሕዝብ ከ42 ዓመታት በላይ በአባትና ልጅ በዙር የሚቀጠቀጠው ፈሪ ሆነው አይደለም፤ 142 ሚሊዮን የሚሆነው የራሽያ ሕዝብ ለፑቲን የተመሳሳይ ጉልቻ መለዋወጥ የተንበረከከው ፈሪ ሆኖ አይደለም፤ 304 ሚሊዮን የሚደርሰው የሰሜን አሜሪካ ሕዝብ በዴሞክራሲ ስም የሚቀለድበትና ከራሱ ብዙዎቹ ሳያልፍላቸው የሀብታም ተመራጭ መሪዎቹና የጠብ ያለሽ በዳቦ መንግሥቱ ለፖለቲካዊ ጥቅም ሲባል አምባገነን መንግሥታትን ሲረዳና በሥልጣን ላይ እንዲቆዩ ሲያግዝ፣ በድንበር ዘለል ጣልቃ ገብነትም ጠላቶችን ሲያፈራና የገዛ ጥያራቸውን ወደነዲዳዊ ፍላፃነት ለውጠው በአሸባሪነት ንጹሓን ዜጎችን እንዲጨርሱ ሜዳና ፈረሱ ሲበጃጅላቸው በዝምታ የሚያልፈው ፈሪ ሆኖ አይደለም ፣ … ብዙ ነገሮችን መናገር ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ጉልበቱ ጸሎቱ፣ ተበቃዩም ፈጣሪው ነውና ከሰባት ዓመት በፊት የሞተውን የሀገሩን ጠላት በድጋሚ ገደለለት፤ሰው ሲሞት ጠላትም ቢሆን እልል ተብሎ አይቀበርምና በምርም ሆነ በለበጣ ተለቀሰለት፡፡ በሕይወት እየኖረ የጥፋት ዘመቻውን ከሚያካሂድ ሞቶልን አልቅሰን መቅበራችን በጣም የሚያንስበት ውለታው ነው፡፡ ዱርዬና የቤት ዕቃን ሸጦ የጨረሰ መጥፎ ልጅ ሲሞትስ ለደንቡ ያህል ተለቅሶ ይቀበር የለምን? እናም አንቅናበት፡፡ ተመልሶ ባለመምጣቱ ግን እርግጠኛ እንሁና ቢያንስ በዚያ እንደሰት፡፡ እንዳይመጣ ታዲያ ከወሬና ከአሉቧልታ ባለፈ ብዙ ነገር መሥራት ይጠበቅብናል፡፡ አመራር – አመራር – አመራር፤ ወሳኝ የወቅቱ ጥያቄ!!

ይህ ሁሉ ወያኔዊ ትርምስ ሞታቸውን ለመደበቅ ነው፡፡ ሞት ደግሞ አይደበቅም፡፡ ሬዲዮው ቲቪው ሁሉ መሞታቸውን በገሃድ እያሳበቀ ነው፡፡ እንደልማድ ሆኖ ብዙዎቻችን የወያኔን ሚዲያ የምንቀበለው ከሚናረው በተቃራኒው ነው፡፡ ወያኔ ደግሞ በተፈጥሮው እውነት እርሙ ነው፡፡ እውነትን መናገር አይችሉም ብቻ ሳይሆን ሥነ ተፈጥሯቸው አይፈቅድላቸውም፡፡ ስለዚህ ለምሳሌ በነሱ ጣቢያ ብዙ ተመረተ ከተባለ ምንም ምርት የለም ማለታቸው መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡ ያዝን ካሉ ለቀዋል፤ ተሸሎታል ካሉ ሞቷል፤ ተፈርዶልናል ካሉ ተፈርዶባቸዋል፤ ወጣ ካሉ ወርዷል፤ … በዚህ ሥሌት 11 በመቶ የሚሉት ተረት ተረቱ የሀገሪቱ ዕድገት -11(ኔጌቲቭ 11) በመቶ መሆኑን በግምት መገንዘብ ይቻላል፡፡ ዱሮውንስ የ30 ብር ጤፍ ሁለት ሺ ብር ሊገባ ዳር ዳር እያለ፤ የሃምሣ ሣንቲሙ አንድ ሊትር የምግብ ዘይት 60 ብር ገብቶ… የምን 11 በመቶ ዕድገት ነው? ለማንቻውም እንደዚህ ናቸው ወያኔዎች እንግዲህ፡፡ የውሸትና የክህደት አምባሳደሮች፡፡

ዐይን ያልገለጡ ቡችሎች እናታቸው ብትሞት እንዴት ሊያድጉ ይችላሉ? እንደምናውቀው መለስ ዜናዊ የወያኔዎች ሁለነገራቸው ነበር፡፡ እርግጥ ነው እርሱ ዐዋቂና አንባቢ ነበር፡፡ ይህን ማንም አይክድም፡፡ መለስ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ግሩም የዲፕሎማሲ ሰዎች፣ እጅግ ሊጠቅሙ ይችሉ ከነበሩ ብልሆች ዜጎች መካከል አንዱ ሊሆን በተቻለው ነበር – ፍጥረቱ ግራኝ ሆኖ አጥፍቶን ጠፋ እንጂ(በውነት እኮ – ሚስቱን ጎርፍ የወሰደበት ባል እንብላ ሲላት እንተኛ እያለች ስታውከው ኖራ  ‹ሚስቴን ከወንዙ ወደታች ሳይሆን ከወንዙ ወደ ላይ ነው የምትፈልጓት› ብሎ ነገረኝነቷን ባደባባይ እንደመሰከረባት ጠማማ ሴት ሆኖ ነው መለስ የሞተው – ‹ሢሠራው ለዚህ› አሉ?)፡፡ ለዚህም ነው እኮ ሌሎችን ረግጦ እንደተናጋሪ እንስሳት በመቁጠር እርሱ ብቻ ሊገን የቻለው፡፡  በመለስ ዐዋቂነትና ነገር ጎንጓኝነት ማንም ሊከራከር አይገባም፡፡ ነገር ግን ዋናው ጥያቄ ማንን ጠቀመበት? የሚለው ነው፡፡ ሰይጣንም እኮ እጅግ ዐዋቂና በመልክም – የመለስን እንተወውና – ከመላዕክት ሁሉ የሚበልጥ አብረቅራቂ ነበር ይባላል፡፡ እምብዝም ስለት የገዛ አፎትን መቅደዱ የነበረ ሆነና ይሄውና የመለስ አንጎል ሰይጣናዊ ቀለም በዝቶበት ሀገሩን እንጦርጦስ አውርዶ ድርጅቱንም ትንሣኤ ለሌለው ሞት አጋልጦ ሞተ፡፡ አሁን ምንም ተባለ ምን መለስን የሚተካ ሰው ከወያኔው መንደር በፍጹም ሊኖር አይችልም፡፡ ይህም የሆነው በፈጣሪ ጣልቃ ገብነት ይመስለኛል  – ካለሱ ባዶ ነበሩ – እሱም ተላላፊ ነው፤ እናም ከሞት ወደሞት ተላለፈ፡፡ በቁሙም አልኖረም፡፡ ሞቶም አይኖርም፡፡ የተሠራው የኛን ዕዳ ሊያስከፍል በመሆኑ እየገፈገፍን እንገናለን፡፡ አሁን ግን እንመለስ፡፡ የዕዳ ደብዳቤያችን እንዲቀደድ በርትተን እንጸልይ!

መንጫጫት ያለ ነው፡፡ እናታቸው የሞቱባቸው ጫጩቶችም ሆኑ የውሻ ቡችሎች መንጫጫታቸው ሲያንሳቸው ነው፡፡ ከቻሉና ዕድሉን ካገኙም አጠገባቸው የሚገኝን ምግብ አይለቁም፤ እስኪሞቱ ይበላሉ፡፡ የነጋበት ጅብም እንደዚሁ ነው፡፡ ያገኘውን እየጠራረገ ከቻለ ወደጎሬው ይዞ ይገባና ለማታ ግዳዩ ይሰማራል፤ ካልቻለም የያዘውን ይዞ ይጠፋል – ይሞታል፡፡ ስለዚህ በቀሪዎቹ ወያኔዎች ልቅ ንግግርም ሆነ ዕኩይ ድርጊት ብዙም ሳንጯጯህና ሳንደነጋገር መሥራት ያለብንን ነገር በብልሃት እንሥራ፡፡ በየሚናገሩት ጠያፍና ለዳፋ ንግግር ሁሉ ጊዜ ስናጠፋ ደስ ይላቸዋል፡፡ መናኛና ባለጌ ሰው ሰውን በመሳደብ ይረካል፤ መለስም እንዲሁ ነበር – ሰው ከቢሮው ገብቶ ሲወጣ እንደባለጌ ሕጻን ምላሱን የሚያወጣበት እስኪመስለኝ ድረስ በምናቤ እስለዋለሁ – መለስን፡፡ ከባለጌ ከዚህ በላይ እንጂ በታች አይጠበቅምና በነዘርፍጤ ‹አቦይ› ስብሃትና በመሀመድ የኑስ ብዙ አንናደድ፤ መናደዳችን ለተግባራዊ እንቅስቃሴያችን እንደማቀጣጠያ ሆኖ የሚያነሳሳን ከሆነ እሰዬው ይሁን ፣ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ጀምበራቸው የገባች ዋልጌዎች የአብሮነት ሕይወታችንን ሊያጠይሙና ከወንድሞቻችንም ጋር ሊያቀያይሙን አይገባምና ሰውነታቸውን ከደረጃ በታች አስቀምጠን ወቅቱ የሚጠብቅብንን የነጻነት ትግል በየፊናችንና በየምንችለው እናድርግ፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ የዘረኝነት አባዜ ከፈጣሪ ተቆርጦ የወደቀ ይመስለኛልና በዚያ ረገድ ባንሞክረው ይሻለናል፡፡ …

የመለስ ልቅሶ እስካሁን ድረስ እንዲሀ መግነኑም የሚደንቅ አይደለም፡፡ በመሠረቱ እንደእውነቱ ከሆነ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ‹ተመርጦ› ሥልጣን ከያዘ በኋላ የሞተው ባለሥልጣን ስም በካህናትና በቤተሰብ ይጠራ እንደሆነ እንጂ እስከዚህን የዓለም መሣቂያና መሣለቂያ እስኪሆኑ ድረስ በስሙ ሊዘባበቱበት ባልተገባ ነበር – በውነት እርሱም እንዳያርፍ አለመላው ወደው ላይወዱት ነፍሱን እያስጨነቋት ነውና ወዳጅ ካላቸው ይምከራቸው፤ ይረፍበት፡፡ ሚዲያውም የኢትዮጵያ እንጂ የአንድ ሰው ሊያውም የሞተ ሰው አይደለምና አይጫወቱበት – ለ30 ሴከንድ ማስታወቂያ ኅያውና ሀገር ጠቃሚ ዜጎችን ስንትና ስንት እያስከፈሉ ለአንድ በሞት ለተሰናበተ ሰው እንዲህ ሃያ አራት ሰዓት መብከንከን የጤና አይደለምና እባካችሁን ወደ አቅላችሁ ተመለሱ በሏቸው፡፡ ያ ተመረጠ የተባለው አዲስ ‹ጠ/ሚኒስትር›ም ለሥልጣኑ ቀናኢ ባለመሆኑና የሞተን ሰው እንደወከለ ስለሚቆጥር እንጂ – በራስ መተማመን ብሎ ነገር ስለሌለው – እኔ እሱን ብሆን ከተሾምኩ በኋላ የዱሮውን ቢያነሱብኝ ማቄን ጨርቄን ሳልል ‹ከቆረባችሁበት ከዱሮ ሰውዬኣችሁ ጋር ገደል ልትገቡ ትችላላችሁ!› ብየ ውልቅ እል ነበር፤ የአሁኑ ሰውዬ ግን ይህን ሊያደርግ አይችልም – ወኔና ድፍረት የማጣት ጉዳይ ብቻም  አይደለም – ከበፊቱኑ ‹ይህ ሥልጣን ለኔ የሚገባ ሳይሆን ጌቶቼ ሰው እስኪያፈላልጉ ድረስ በታዛዥነት ለማገልገል የገባሁበት ስለሆነ እንዲህ ዓይነት ቅብጠት ለኔ አይገባም› ብሎ የሚያምን ይመስለኛል – የምን ይመስለኛል ነው –  ነው እንጂ! ሚስትህ ሞታ ሌላ ሚስት አግብተህ በአዲሲቷ ሚስትህ ፊት ነጋ ጠባ በዕንባ ብትታጠብ ምን ሊሰማት እንደሚችል አስበው፡፡ ባልሽ ሞቶ ተቀብሮ ሌላ ባል አግብተሸ ባገባሽው ባል ደረት ላይ ተለጥፈሽ የዱሮውን ባልሽን ስምና ዝና እያነሳሽ በዕንባ ብትታጠቢ ጥፊና እርግጫው በዘመናዊ አስተሳሰብ ቅኝት ተዋዝቶ ከድምር ሒሳቡ ቢቀነስልሽ የፍቺው ጥያቄ ግን ጎሕ ሳይቀድ እንደሚቀርብልሽ አትጠራጠሪ – ደግሞም በኢትዮጵያ መሬት፡፡ ስለዚህ እነዚህ ወያኔዎች ከሰው ሠራሽ ሕግም ከተፈጥሮ ሕግም ከፈጣሪ ሕግም ከሞራልም ከልምድና ተሞክሮም ብቻ ምን አለፋን ከሁሉም የዚህች ምድር ሕግጋትና ሥርዓቶች በእጅጉ ያፈነገጡ ለምንም ነገር ደንታ የሌላቸው አረማውያን ወይም አሕዛብ ናቸው ማለት እንችላለን፡፡ ለነዚህ ሰዎች ስም ማውጣትም አይቻልም፡፡ ደግነቱ ሁሉም አንድ በመሆናቸው የአንዳቸው ግማት ለሌላኛቸው አይሰማቸውም፡፡ ሙትቻዎች! 85 ሚሊዮኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድ ሰው ይተኩት? እነሱ በቁማቸው ቢሞቱ ሌላውም የሞተ መሰላቸው? ወይ ጊዜ!!

ይህን የሞተ ሥርዓት አለ እያሉና ያልተገባ ክብደት እየሰጡ የበሬውን ቆለጥ ስትከተል እንደዋለችው ሞኝ ቀበሮ መሆን ለበለጠ ጥፋት ይዳርጋል፡፡ ወያዎች ከሞቱ በኋላ የሚልሱት ነገር እንዳላቸውም መረዳት ተገቢ ነው፡፡ እባብ ከሞተ በኋላ ይነሳል ይባላል – በመርዝ አቀባዮቹ አማካይነት፡፡ አሁን ግን የወያኔ ሞት እውነት ስለሆነ ሁሉም ዜጋ መተባበርና መነሳት ያስፈልጋል፡፡ እርግጥ ነው – ፈጣሪ የዚህችን ሀገር የመንግሥት ዛብ የሚሰጠው ለተመሳሳይ ዘረኛና የሃይማኖት አክራሪ እንደማይሆን በፍጹም ልባችን እናምናለን፡፡ የዚህችን ሀገር የመንግሥት አመራር የሚረከቡት ከዘውገኝነትና ከሃይማኖታዊ ጽንፈኝነት የተላቀቁ፣ የሁሉንም እንደሁሉም ሆነው የሚያከብሩ፣ በኢትዮጵያዊነት የአንድነት ጥላ ሥር ብቻ የሚንቀሰቀሱና ጥላቻን በፍቅር ግለኝነትን በወል የተኩ ወገኖች እንደሚሆኑ እንጠብቃለን፤ እምነታችንም ነው፡፡ አለበለዚያ ብድር ሲመላለሱ ማደር ሰልችቶናልና በተመሳሳይ ቅኝት የሚመጣ በአድልዖ የተመረዘ አስተዳደር በአፍንጫችን ይውጣ፡፡

እስካሁን እንደምንታዘበው የሕዝቡን ፍላጎት ለማጤን የሚተጉ ተቃዋሚዎች ከስንት አንድ ናቸው፡፡ ለዚህም ይመስላል በለስ እንዳይቀናቸውና በለመድነው የበሰበሰ ሥርዓት እንድንቆይ ፈጣሪ ምርጫው ሆኖ ያለው፡፡ ቆሻሻ ቆሻሻን ሊያጸዳ እንደማይችል መታወቅ አለበት – መጽሐፉም ‹ብዔል ዘቡል ብዔል ዘቡልን አያወጣም ይላል›፡፡ ሐጎስ ሄዶ ስንሻው ቢመጣና የሐጎስን መመሪያ ቀባብቶ ቢከተል ወይም ጎይቶም ቢሄድና ቶሎሣና ዘበርጋ ተተክተው በቀደመው ጠባብ መንገድ እየተጓዙ ተመሳሳይ ትርምስ እንፍጠር ቢሉ ሕዝቡ ቀርቶ ምድሪቱ አትቀበላቸውም፤ ይህ ዓይነቱ ነገር በእጅጉ ሰልችቶናል – ጋዝ ጋዝ ብሎናል፡፡ በቴዎድሮስ ካሳሁን የቅርብ ጊዜው የሙዚቃ ኮንሰርት ከሕዝቡ የተንጸባረቀውን ፍላጎት ማጠየን ይገባል፡፡ ፈጣሪ ደግሞ ልብንና ኩላሊትን ያያል፤ ይመረምራልም፡፡ በተመሳሳይ ቅኝት ለመዝፈን የአራት ኪሎን ቤተ መንግሥት የሚቀላውጥ ካለ ቁርጡን ይወቅ፤ ያ ዓይነቱ ሕዝብን ከሕዝብ፣ ጎሣን ከጎሣ፣ ቋንቋ ከቋንቋ፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት እያናካሱና አንዱን ከሌላው እያባሉ በሥልጣን ላይ መቆየት ከእንግዲህ ሊታሰብ አይገባውም፡፡ ይህ የሚሆነው ግን ትክክለኛው የፈጣሪ ሰው ወደ መንበሩ መምጣት ከቻለ ነው፡፡ ያ እንዲሆን ደግሞ ከኛም ብዙ ይጠበቃል፤ ‹እግዚአብሔር ይመስገን›ና ‹አልሃምዱሊላሂ ረቢንአለሚን›ም ትልቅ ጦር ናቸው – ካወቅንበት!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ ፤ ሕዝቧንም ከአረመኔዎች ግርፋት ያድን፡፡ አሜን፡፡

 

ብርሃንና ሰላም = ጽልመትና ሽብር ከሰሎሞን ተሰማ ጂ.

“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ ሳምንታዊውን የፍትሕ ጋዜጣ እንዳይሰራጭ አገደ፤”                 (www.fetehe.com እና በአዲስጉዳይ መጽሔት፣ ሐምሌ 2004 ዓ.ም)

“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ ሳምንታዊው የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንዳይታተም ከለከለ፡፡” (www.fnotenetsanet.com እና amharic.voanews.com October 02, 2012/ መስከረም 22 ቀን 2005 ዓ.ም))

“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ የሪፖርተር ጋዜጣን ገጽ ቁጥር ገደበ፡፡” (ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም)                             

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በሁሉም ዜናዎች በበጎ ጎኑ አልተነሳም፡፡ “እንዳይሰራጭ አገደ!” “እንዳይታተም ከለከለ!” እና “ቁጥር ገደበ!” የሚሉት ሃረጎች የማተሚያ ቤቱን ስምና ክብር የሚያጎድፉ ናቸው፡፡ ይህ ማተሚያ ተቋም፣ የዛሬዎቹ ሹመኞችና ባለሥላጣናቱ አወቁትም – አላወቁትም ትልቅ ራዕይና አላማዎችን አንግቦ የተነሳ ነበር፡፡ እነዚህን ተልዕኮዎቹን ለርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ሲባል መስዋዕት ማድረግ ግን ከተጠያቂነትና ከታሪክ-ሕሊና ተወቃሽነት አያድንም፡፡

“ብርሃንና ሰላም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ማተሚያ ቤት” በመስከረም 3 ቀን 1914 ዓ.ም በአልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ተቋቋመ፡፡ ይህ ማተሚያ ቤት በጥቃቅን ፔዳሎች ማለትም በእግር በመርገጥ በሚንቀሳቀሱ የማተሚያ መኪናዎች ሥራውን የጀመረው ስድስት ኪሎ በሚገኘው የዛሬው የቋንቋዎች አካዳሚ ሕንፃ ውስጥ ነበር፡፡ በዚያ ሁናቴ የተጀመረው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት  በ1958 ዓ.ም ሠላሳ ሺህ ጋዜጦችን በሰዓት ለማተም የሚችሉ ዘመናዊ የኦፍሴት ማተሚያ መኪናዎች ባለቤት ሆኗል (የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ ቅዳሜ ኅዳር 18 ቀን 1958 ዓ.ም፤ ገጽ 3 ይመልከቱ)፡፡

በወቅቱ፣ የማተሚያ ቤቱ የቴክኒክና ፕሮዳክሽን ክፍል ኃላፊ የነበሩት አቶ አክሊሉ እንዳሉት፣ “ማተሚያ ቤቱ እየተሻሻለ በመሔዱ ባለፈው ዓመት እንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ መጽሐፍትን (1,500,000)፣ ከአስር ሚሊዮን በላይ ጋዜጦችን  (10,000,000)፣ ሠላሳ ሚሊዮን (30,000,000) ቴምብሮችና ሃያ ሁለት ሚሊዮን (22,000,000) ሌብሎችን፣ አንድ ሚሊዮን ተኩል (1,500,000) የአውቶቡስ ካርኔና ቁጥራቸው ያልተገለጠ እጅግ ብዙ የምስጢር እትሞች እና የሎተሪ ትኬቶችንም አትሟል፡፡”

አቶ አክሊሉ ጨምረውም፣ “ማተሚያ ቤቱ ከሁለት ዓመታት በፊት ገዝቶ ያስመጣው ትልቁ ኦፍሴት፣ 32 ገጾች ያሉትን መጽሐፍ 18ሺ እትም በሰዓት፣ አጥፎና ቆርጦ ሲቆልላል፣ እንዲሁም በቀን አንድ መቶ ሺ ጋዜጦችን ለመሥራት እንደሚችል፣” አስታውቀዋል፡፡ ከሁለት ዓመት ወዲህም አድገቱ አርባ በመቶ (40%) ያህል ያደገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኃላፊው እንደገለጹት ከሆነ፣ በ1958 ዓ.ም እንኳን፣ ሮላንድ የተባለው ኦፍሴት መሳሪያ በልዩ ልዩ ሕብረ ቀለም አድርጎ ከሦስት ሺ እስከ አምስት ሺ ጋዜጦችን በአንድ ሰዓት ውስጥ ለማተም የሚችል ነበር፡፡ ትልቁ ኦፍሴት ደግሞ በሦስት ቀለማት አድርጎ በሰዓት ሠላሳ ሺ ጋዜጦችን ለማተም መቻሉን ገልጸዋል፡፡

“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት አምስት መቶ ስድሳ ሠራተኞች የሚሠሩ ሲሆን፣ አራቱ ብቻ የውጭ አገር ሰዎች ናቸው፡፡ ከጠቅላላው ሠራተኛ ውስጥ ስድሳ በመቶዎቹ (60%) ሴቶች ናቸው፡፡ ማተሚያ ቤቱ በሥራው ጥራትና በቀጠሮ አክባሪነቱ ብዙ ደንበኞችን ለመሳብ ይችላል፤” ይላሉ አቶ አክሊሉ፡፡

ዛሬ ደግሞ አቶ አክሊሉ ስለማተሚያ ቤቱ እንዲገልጹ ቢጠየቁ፣ እነዚህን ወርቃማ ቃላትና ሐሳቦች አፋቸውን ሞልተው እንደማይደግሙት እግጥ ነው፡፡ ዛሬ፣ ብርሃንና ሰላም በቀጠሮ አክባሪነቱና ደንበኞቹን በመሳብ በኩል ብዙ ርቀት ቁልቁለቱን ይዞ ተንሸራቷል፡፡ ይህ ቁልቁለት የተጀመረው ደግሞ የአራት ኪሎው ግርማ “ሽብር ነዝቶ” የማተሚያ ቤቱን ወዝአደሮች በ1970 ከፈጀና ካስፈጃቸው በኋላ እንደነበር ይታወሳል (ነበር፣ ቅጽ 1፣ ገጽ —)፡፡

ባለፈው ሰሞን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር በፓርላማ ስለብርሃንና ሰላም ሲጠየቁ የመለሱት ነገርም በማተሚያ ቤቱ ላይ ሕዝባዊ ትኩረትን ስቧል፡፡ “የወረቀት ችግር የለብንም፡፡ … ማተሚያ ቤቱ አስተዳደራዊ ርምጃ የመውሰድ” መብት አለው፤ አይነት ነበር ንግግራቸው፡፡ ንግግራቸውን ለማመን ግን ያስቸግራል፡፡ ምክንያቱም፣ ማተሚያ ቤቱ ነፃና ገለልተኛ የንግድ ተቋም አለመሆኑን ስለምናውቅ ነው፡፡ ማለትም፣ በኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የዕዝ ትዕዛዝ ሥር እንደሚሰራም ግልጽ ነውና፡፡ ሁለተኛውም ምክንያት፣ የውጭ ምንዛሪው እጥረት ምን ያህል መንግሥትንና ባንኮቹን እግር ተወርች አሳስሮ እንደሚኮረኩዳቸው አብጠርጥረን ስለምናውቅ ነው፡፡

********************************

በአገራችን የጽሕፈት መኪናዎች ከመምጣታቸው በፊት የነበረው ችግር ብዙ ህትመት እንዳይኖር አድርጓል፡፡ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሲቋቋም ጀምሮ ለበርካታ አመታት ያህል በቁም ጸኃፊነት የሠሩት አቶ ተክለ ጊዮርጊስ ናቄ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ሪፖርተር ጠይቋቸው ሲመልሱ እንዳሉት ከሆነ፣ “በአገራችን የቁም ጽሐፊ የሚባለው መንፈሳዊ መጽሐፍትንና ቁም ነገርነት ያላቸውን ጽሑፎች የሚጽፍ ፀሐፊ ናቸው፡፡ ክታቡን፣ አስማቱን፣ ድግምቱንና ሌላውን ተራ ነገር የሚጽፍ ቁም ጸሐፊ አይባልም፡፡ ሐዲሳትን፣ ድጓውን፣ ስንክሳሩን፣ መልኩን ለመጻፍ የሚያገለግለውን የኢትዮጵያውያን አበውን ከዚህኛው ለመለየት ጽሑፉ “ቁም ጽሕፈት” ተባለ፤” ሲሉ ስለሙያቸው ያስረዳሉ፡፡

አያይዘውም፣ “ቁም ጽሕፈትና ድርሰት በአገራችን ቀድሞ ያለ ቢሆንም፣ በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት በጣም ተስፋፍቶ እንደነበር ይነገራል፡፡ ከዚህም ወዲህ በጎንደር ነገሥታት ዘመነ መንግሥት በተለይም በአፄ አድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመነ መንግሥት መጽሐፍትን የሚጽፉና የሚያዘጋጁት ሊቃውንት ተመድበው ይሠሩ ነበር፡፡ እንዲያውም መለክዓ ፊደሉ የተጠነቀቀው በአፄ አድያም ሰገድ እያሱ ዘመን ነበር፡፡” ሆኖም፣ የጋዜጣና የኅትመት ጉዳይ ለብዙ ዘመናት ፈቅም አለማለቱን አቶ ተክል ጊዮርጊስ ያስረዳሉ (የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ ኅዳር 18 ቀን 1958 ዓ.ም፤ ገጽ–)፡፡

ይኼው፣ በኅዳር 18 ቀን 1958 ዓ.ም የወጣው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ በፊት ለፊት ገጹ ላይ ደግሞ እንዲህ የሚል ዜና አስነብቧል፡፡ “ግርማዊ ጃንሆይ 3,886,812 ብር የፈጀውን የብርሃንና ሰላም ሕንፃ መረቁ!” ከጋዜጣው ሐተታ ውስጥ የሚከተለው ዘገባ ቀልብን ይገዛል፡፡ እንዲህ ይላል ዝርዝሩ፡፡ “አዲሱ ማተሚያ ቤት ሕንፃ የፈጀው 1,385,581 ብር ከ36 ሳንቲም ሲሆን፣ ለሌሎች የሲቪል መሐንዲስ ሥራዎች 116,352 ብር ከ33 ሳንቲም ወጪ ሆኗል፡፡ እንዲሁም፣ ከፈረሳይ፣ ከእንግሊዝ፣ ከጀርመ፣ ከሲዊድንና ከጃፓን ተገዝተው የመጡት ለማተሚያ ቤቱ የሚያገለግሉ መሣሪያዎች ዋጋ 2,364,879 ብር ከ17 ሳንቲም ነው፡፡ በጠቅላላው ለሕንፃውና ለመሣሪያው የፈጀው 3,886,812 ብር ከ86 ሳንቲም መሆኑ ታውቋል፡፡” (በወቅቱ የነበረው የብር ምንዛሪ ከዶላር አንፃር ሲታይም አንድ ዶላር በሁለት የኢትዮጵያ ብር ነበር የሚመነዘረው፡፡ ስለዚህም፣ በወቅቱ የምንዛሬ ታሪፍ መሠረት $1,943,406.43 የአሜሪካን ዶላር ወጪ ተደርጎበታል፡፡)

በዕለቱ ተመርቆ ሥራውን የጀመረው ዌቭሴት የተባለው የማተሚያ መኪና፣ ባለ16 ገጽ የሆነውን A-2 size አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ በሰዓት 30,000 ኮፒ በስምንት ቀለማት አትሞና አጥፎ የሚያወጣ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አዲሱ ሕንፃ፣ 200,000 የተማሪዎች መማሪያ ደብተሮችን በ24 ሰዓት ውስጥ የሚያዘጋጅ መሣሪያ ያለው ሲሆን፤ 60,000 ኢንቨሎፖችን በአንድ ቀን አትመውና አዘጋጅተው የሚያወጡ መሳሪያዎችም አሉት፡፡  የተቀናጀው የኢንቨሎፖች መሥሪያ ክፍልም የተሟላ በመሆኑ፣ በልዩ ልዩ መጠንና ዓይነት በየቀኑ እስከ ስድሳ አምስት ሺ እንቨሎፖችን እያቀናበረ ያቀርባል፡፡ ባመት ሲታሰብም ደግሞ ከሠላሳ ሚሊዮን የማያንስ ኤንቨሎፖችን እያዘጋጀ  ያትማል፤” ሲሉ ኃላፊው አቶ አክሊሉ ገልጸው ነበር፡፡ የጋዜጣው ሪፖርተር እንዳለው ከሆነ፣ “ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት አሁን (በ1958 ዓ.ም) ባለው አቋሙ መሠረት መጽሐፍትንና ጋዜጦችን በብዛት በመላ ሀገሪቱ ውስጥ ለማሰራጨት የሚችል ታላቅ ድርጅት ሆኗል” (የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ ኅዳር 18 ቀን 1958 ዓ.ም፤ ገጽ–)፡፡

ከዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ መውጣት አንድ ቀን ቀደም ብሎ፣ በዕለተ ዓርብ ኅዳር 17 ቀን 1958 ዓ.ም የወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በበኩሉ፣ ጃንሆይ ማተሚያ ቤቱን ሲመርቁ ያደረጉትን ንግግር ሙሉ ቃል ይዞ ነበር፡፡ በዕለቱም ባደረጉት ንግግራቸው እንዳወሱት ከሆነ፣ በሁለት ቁም ነገሮች ላይ አተኩረው ነበር (በገጽ 1 እና 3 ላይ ይመልከቱ)፡፡ እንዲህ አሉ፤ “ማተሚያ ቤቱ ሥራውን የጀመረው፣ የመጀመሪያውን ማተሚያ መሣሪያ በግል ገንዘባችን ገዝተን በቤተ መንግሥታችን ቅጥር ግቢ ውስጥ፣ አሁን ለዩኒቨርሲቲነት በሰጠነው የአባታችን ቦታ ላይ ነው፡፡ እንደምናስታውሰው ቁጥራቸው ከ15 በማይበልጡ ሠራተኞች ስናቋቁም በሁለት ዓይነተኛ ምክንያቶች በመመራት ነበር፡፡

“አንደኛ፣ የመጻሕፍተ ብሉያትና የመጻሕፍተ ሐዲሳት ንባባቸውና ትርጓሜያቸው በኢትዮጵያ ውስጥ በየስፍራው እንዲገኙና ክርስቲያን የሆነ ሁሉ እየተመለከተ እንዲጠቀምባቸው ለማድረግ በእጅ ጽሑፍ ተጽፎ በየገዳማቱና በየአድባራቱ፣ እንደዚሁም በየአውራጃው ለኢትዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን ለማደል የሚቻል መሆኑን በማሰብና፤ ሁለተኛም፣ የአገራችን ሕዝብ በጽሑፎች ፍላጎት ረክቶ ርምጃው የተፋጠነ እንዲሆንና በዕለት ወሬም ያገሩንና የውጭውን ሁናቴ ማወቅ እንዲችል በመመኘት ነበር፤” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ጃንሆይ አክለውም፣ ሦስት አንኳር ጉዳዮች ላይ አጽንዖት ሰጥተው ነበር የተናገሩት፡፡ አንደኛ፣ “ማተሚያ ቤቱን በ1914 ዓ.ም ስናቋቁም በዚያን ጊዜ ከነበሩት ሰዎች መካከል አቶ ገብረ ክርስቶስ ተክለ ሃይማኖት ለስራው ሃሳባችንን ጥለንበት ስለነበር – የማቋቋም ሥራውን በእጅጉ ረድቷል፡፡ የመጀመሪያው ሥራ አስኪያጅም በመሆን ሠርቷል፡፡” ካሉ በኋላ፣ “ማተሚያ ቤቱ ሥራ እንዳይፈታም በማለት እንደብላቴን ጌታ ኅሩይ ያሉት ልዩ ልዩ ጽሑፎችን ለአገራችን በማበርከት ረገድ ረድተዋል፤” ሲሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ሁለተኛም፣ “ይህ ማተሚያ በልዩ ልዩ አውራጃዎች (ከተሞች) ‘ከሣቴ ብርሃን የልዑል ራስ መኮንን ማተሚያ ቤት’ ተብለው ሦስት ቅርንጫፎች በሐረር፣ በአሥመራና በጎንደር እንዲኖረው ማድረጋችንንም እናስታውሳለን፡፡ ፋሺስት ኢጣሊያ በግፍ ወረራዋ ጅምራችንን እስከምታደናቅፈን ድረስ ብዙ ጥረናል፡፡” በመጨረሻም አሉ ግርማዊነታቸው፣ “ከዚህ ማተሚያ ቤት የሚገኘውን ገቢ ሁሉ፣ ለቤተ ሳይዳ ሆስፒታል (የዛሬው የካቲት 12 ሆስፒታል ነው፤) እንዲረዳ ስለወሰንን፣ የተወዳጁ ሕዝባችንን ጤንነት በመጠበቅ በኩል እንዲያግዝልን ሰጥተናል፡፡ የማተሚያ ቤቱ ገቢ ለአካል ጉዳተኞች መርጃ እንዲሆንም አዘናል፤” በማለት ነበር ንግግራቸውን የቋጩት፡፡

ማሳረጊያ፤

ስለብርሃንና ሰላም አንድትና ጥምረት የሚያስረዱ አንድ ሦስት ጥቅሶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንጥቀስ፡፡ ነቢዩ ኢሳያስ በትንቢቱ እንደተናገረው፣ “ንባብዋ ውስተ ልባ” (ለኢየሩሳሌም የልቦናዋን ተናገሩዋት) ሲል ስለሕዝቡም የተናገረው ቃል ነው (ምዕራፍ 40፣2)፡፡ ነቢዩ ሲራክም በ(ምዕራፍ 30፣13) ላይ በተመሳሳይ መልኩ፣ “ናዝዛ ለልብከ” (ልብህን አጥናናው) ሲል ምክሩን የሰጣል፡፡ ለሰብዓዊ ባሕሪያት በሞላ፣ የልቦናን መናገርና ልብንም ማጽናናት አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ ሰው ብርሃንን ካገኘና ዕውቀትንም ከተመገበ፣ አእምሮውም እንደምኞቱ መጠን ይጎለብታል፡፡ አእምሮው የጎለበተም ሰው፣ ልቦናውን ስለሚያስደስት እዝነ-ልቡናው ዕረፍትንና መጽናናትን ያገኛል፡፡ ያን ጊዜም አእምሮው ሰላምን አገኘ ማለት ነው፡፡

በዮሐንስ ወንጌል (ምዕራፍ 4፣5) ላይ የተጠቀሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ኃይለ-ቃልም፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ!” ካለ በኋላ፣ ደቀመዛርቱን “እናንተም የዓለም ብርሃን ናችሁ!” ሲል ያውጃል፡፡ ይኼው የብርሃን አዋጅም ወደ ኦሪት ዘፍጥረት የመጀመሪያው ምዕራፍ ይወስደናል፡፡ ያኔ፣ ፈጣሪ “ብርሃን ይሁን” (ለይኩን ብርሃን) ነበር ያለው፡፡ ከምዕራፉ እንደምንማረው ከሆነ፣ የብርሃን ጉድለት (ጽልመት) የነገሰበት ወይም የሰፈነበት ዓለም፣ እርሱ ዕውቀት አልባም ነው፡፡ ያለብርሃን የመኖርን ባዶነት የምንረዳው፣ በብርሃነ-አእምሮአችን እንጂ በጽለመታዊው እእምሮአችን አይደለም፡፡ ብርሃን ሲጠፋ፣ ያኔ አእምሮም ወደ ጽልመቱ ተመልሶ ይገባል፡፡

ብርሃን ለሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ ፀጋ ነው፡፡ “ሕፃን ልጅ ልክ እንደተወለደ ዓይኖቹን ወደ ብርሃነ ቀላይ በአራቱም ማዕዘናት እያዟዟረ ያቁለጭልጫል” ይባላል፡፡ በብርሃን ውቅያኖስ ውስጥ እንደፈለገው ለመዋኘት ያለውን ሰብዓዊ ናፍቆት በሕፃኑ ውስጥ እናያለን፡፡ ጨቅላው በብርሃኑ አማካይነት የሚያየው ነገር ውሱን ነው፡፡ ወሰኑም በአድማሳት አጥር/ኬላ መጠን የተከለለ ነው፡፡

ስለዚህ ሰው በዐይኑ ብርሃን ከሚያየው የበለጠ ረቂቅ የሆነ ብርሃን በአእምሮው ዐይኖች ያያል፡፡ ማየት የተሳነው ሰው ቢሆን እንኳን፣ በአእምሮው ብርሃንን ያያል፡፡ የአድማስ ጥጋት ከማየት አይከለክሉትም፡፡ ብርሃኑ በተለይም በትምህርትና በዕውቀት ከጎለበተማ የባሕር መቀመቅ፣ የምድርም ጥልቅ ውስጥ ዘልቆ ይገባል፡፡ ረቂቅ አቅምን የሚጋርደው ግንብም ሆነ ድንበር ስለሌለ ነው፡፡

ከዚህ የአእምሮ ብርሃንም ሰላመ ይወለዳል፡፡ ስጋት፣ ፍርሃት፣ ጭንቀትና ሽብር እንዲሁም “ምን ይመጣብኝ ይሆን?” የሚል ስሜት ሁሉ በብርሃን ይወገዳል፡፡ የሽብር ምንጩ ጽልመት ነው፡፡ ምን ይመጣብኝ ይሆን ብሎ መስጋት ከጭለማ የሚወለድ ጋኔል ነው፡፡ ጽልመቱ በብርሃን ጮራዎች ከተወገደ በኋላ ግን፣ ልብ ሰላምን ያገኛል፡፡ ሰላምም፣ ሰላማዊ መንግሥት እንዲመሠረት ያደርጋል፡፡ ለሰው ልጅ ሰላምን ከመስጠት የበለጠ ምን በጎ ምግባር አለ?

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤትም የያዘው ስያሜ ሞላው ዓለም የሚስማማበት ምኞት ነው፡፡ የብርሃንና የሰላም ምኞት ነው፡፡ ብርሃን ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ ሰላምም ሰብዓዊ ነው፡፡  የመላው ዓለም ሕዝብ ለብርሃንና ለሰላም የጋለ መሻት፣ ጉጉትና ናፍቆት አለው፡፡ ዘላለማዊ መሻት ነው፡፡ ጊዜያዊ የፖለቲካ ሽቀላና ትርፍ አጋባሽነት ያንን ዘላለማዊ ናፍቆትና መሻት አያሰናክለውም፡፡ ከጽልመትና ከሽብር ይልቅ ብርሃንና ሰላም በመላው ዓለም እንዲነግስ፣ በተለይም በኢትዮጵያችን እንዲንሰራፋ ዘላለማዊ ጸሎታችንን እናድርስ!

 

የኢትዮጵያዋ፡ ርእዮት ‹‹የጥንካሬዬ ዋጋ››

ከፕሮፌሰር  ዓለማየሁ  ገብረማርያም
ትርጉም  ከነጻነት ለሃገሬ

ስለስልጣን ብልግና አለያም ስለ ስልጣንን በማንአለብኘነት አለ አግባብ ስለ ከመጠቀም ከመናገር ይበልጥ አስቸጋሪ የሆኑ bezu ነገሮች yelum፡፡ ለ31 ዓመቷ ወጣት ኢትዮጵያዊት አይበገሬ ርዕዮት ዓለሙ ግን፤ የመጻፍ ነጻነት፤ የመናገር ነጻነት፤ ሃሳብን በነጻ የማንሸራሸር ነጻነትን ድምጻቸው በመሳርያና በስለላ መዋቅር ለታፈነባቸው ድምጽ ከመሆን ምንም አይነት ጋሬጣ ቢደረደር ሊያደናቅፋት ጨርሶ አይችልም፡፡  አሁንም ቢሆን ባለችበት ክፉ ሁኔታም ሆና ስለግፍ ስልጣን ቁልጭ ያለ ሃቅን ትናገራለች፤ ‹‹ለጥንካሬዬ ዋጋ እንደምከፍል ብገነዘብም የሚቃጣብኝን ለመቋቋም ዝግጁ ነኝ››፡በማለት ካለችበት ገሃነማዊ የቃሊቲ ጉረኖ ባመለጠው የእጅ ጽሁፏ መልእክቷን  ለአለም አስተላልፋለች፡፡

“ጥንካሬ ለሁሉም ድርጊት ታላቅ ዋጋ አለው፡፡ ጥንካሬ ከሌለ ማንኛውንም አይነት ዋጋ ያለው ተግባር ማከናወንም ሆነ ማቀድ አይቻልም” ያለችው ታላቋ የአሜሪካ የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ጸሃፊ ማያ አንጀሉ ናት፡፡ ባለፈው ሳምንት የዓለም አቀፉ ሜዲያ ፋውንዴሽን (IWMF) የ2012ን  ታላቁን “የጋዜጠኝነት ጀግንነት” ሽልማቱን  ለአይበገሬዋ ርዕዮት ዓለሙ ሸልሟል፡፡ ባለፈው ሜይ ርዕዮትን ወደ ወህኒ ለመወርወርና ዝም ለማሰኘት ስለተከናወነው ሂደት ጽፌ ነበር፡፡

ለዚያ ማፈርያ ፍርድ ቤት ማስረጃ ተብሎም በርዕዮት ላይ የቀረበው ሰነድ፤ከሌሎች የሙያ ባልደረቦች ጋር በህገወጥነት የተሰበሰበ የኢሜይል ልውውጥ፤በስለላ መዋቅሩ የተጠለፈ የቴሌፎን ንግግር፤ሲሆን ከሁሉም ጋር ያደረገችው ልውውጥ ግን ሰላማዊ ትግልና ለማጠናከር ሊደረግ የሚገባውን የሚያመላክት ብቻ ነበር፡፡ ርዕዮት በፍትሕ ጋዜጣና በኢትዮጵያን ሪቪዩ ድህረገጽ ላይ ያወጣችው ጽሁፍም በማስረጃነት ቀርቧል፡፡ ከፍርድ ቤት መቅረብ አስቀድሞ ርዕዮትና ውብሸት ታዬ (የአውራምባ ጋዜጣ አዘጋጅ) ከጠበቃ ጋር የመገናኘት መብታቸው ታግዶባቸው ነበርና ጠበቃ ማነጋገር አልቻሉም፡፡ ቃለ መጠይቅም የሚባለው ስርአት ያጣ ሂደትም በሚካሄድበት ወቅት የጠበቃቸው ውክልና መብት እንደታገደ ነበር፡፡ በምርመራ ወቅት የደረሰባቸውን ወከባና ስቃይ፤ የህክምና መከልከልን አቤቱታቸውን፤ ያ አሳፋሪ ፍርድ ቤት ለመስማት እንኳ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡

ዛሬ ግን ርዕዮት ይህን ታላቅ እውቅናና ሽልማት ስትሰጥ ለማየት በመብቃቴ እጅጉን እኮራለሁ፡፡ በ2007ም ይህንኑ ሽልማት ሰርክዓለም ፋሲል ስትሞሸርበት ደስታዬ ወሰን አልነበረውም፡፡ ወጣት ኢትዮጵያዊያን ጀግኖች እጅጉን አስከፊ በሆነ ገዢ ባለስልጣን መንግስት ላይ እውነትን በመናገርና የሕዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ ቆርጠው በመነሳታቸው ሰበብ  ለእስርና ለግፍ ስቃይ የተዳረጉት ዓለም አቀፍ እውቅና፤ ክብርና ሞገስ ሲቸራቸው ከማየት የበለጠ ምን የሚያስደስት ነገርአለና!?

ርዕዮትና ሰርክዓለምን ለዚህ ክብር ያበቃቸው “ጥንካሬያቸው” ምነድን ነው? ጥንካሬ በተለያየ መልኩ ይከሰታል፡፡ እራሱን ለመስዋእትነት ለማሳለፍ ቆርጦ በጦር ግንባር የተሰለፈ ተዋጊ አደጋው ከፊትለፊቱ እንዳለ ቢያውቅም በጥንካሬው ይጋፈጠዋል፡፡ ወጣት የሆነች ሴት ‹‹ጭቆናና ድምጻቸው የታፈነባቸው ምትክ ለመሆንና ጩኸታቸውን ለመጮህ፤ እሮሯቸውን ለማሰማት፤ ለሕዝብ በመወገን፤ አቆማለሁ›› ለማለት መቁረጥ የሚጠይቀውን ዋጋም ለመክፈል ቆርጦ መነሳት ጥንካሬን ያሳያል፡፡ “ጥንካሬ” በራሱ ግን ምንድን ነው? ታላቁ ፈላስፋ እንደሚለው ‹‹ጥንካሬ  በውስጥ በህሊናችን በመንፈሳችን የሚገኝ ግፊት ነው፡፡ በመረረው አደጋ ውስጥ እንድንጋፈጠውና ገትረን እንድንቋቋመው ያስችለናል፡፡›› ሌሎች እንደሚሉት ደግሞ ጥንካሬ በፍርሃትና በጅልነት መሃል የሚገኝ ነው፡፡ ምናልባትም ጥንካሬ ሌሎችንም ዋጋዎችን ቆራጥነትን፤የዓላማ ጽናትን፤ፈቃደኝነትን፤ትእግስትን፤አሳቢነትን አመኔታን ያካተተ፤ ሊሆን ይችላል፡፡ ጥንካሬን ዓላማቸው ያደረጉ ርዕዮትና ሌሎችም መስሎቿ  በግል ለሚደርስባቸው ችግር፤መከራ ስቃይ ወይም እስርና እንግልት ጨርሶ አያስቡም አያስፈራቸውም፡፡ ስለዚህም እንደ ርዕዮትና ሰርክ ዓለም ያሉ ጠንካሮች እህቶችና እስክንድር ነጋንና ውብሸት ታዬን የመሰሉ ቆራጦች ስላሉን በእጅጉ ልንኮራ ይገባናል፡፡ እንደ ሰብአዊ ፍጡር  ከፍተኛውን የጥናካሬ ደረጃ ያመላከቱንን ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች በእስር በመማቀቅ ላይ ቢሆኑም መከራና ችግሩ፤ ግፉና ጭካኔው ግን ጨርሶ ከዓላማቸው ዝንፍ ጥንካሬያቸውንም ሸብረክ አላደረገውም፡፡

በኦክቶበር 24/2012 በሽልማቱ ስነ ስርአት ላይ የተነበበው የርዕዮት የእጅ ጽሁፍ መልእክት ለመጪው ትውልድ የጥንካሬ ማረጋገጫ ነው፡፡የታሪክ ነጻነት፤የፕሬስ ነጻነት፤በኢትዮጵያ በሚጻፍበት ጊዜ መጪው ትውልድ ይህን የርዕዮትንና ሌሎችንም እውነታዊ መልዕክቶች ያነባል፡፡ ጊዜያዊ ግፈኛ ገዢዎች  ሕዝቡን ለስቃይና ሚዛን ላጣው ግፍ በዳረገበት መራር ወቅት ርዕዮትና መሰሎቿ ሃሰትን በማጋለጥና ለግፍ እምቢታን በመምረጣቸው ለእስራት ቢበቁም ቀኑ ሲመጣ ግን በድርጊታቸው የሚኮሩ ይሆናሉ፡፡ ከዓላማዋ ሳታፈገፍግ፤ በዓለም ካሉት ወህኒዎች ሁሉ ያዘቀጠና ግፍ የበዛበት ቦታ ሆና( ወህኒው በኢትዮጵያ የገዢው መንግስት በከፍተኛ ገንዘብ የቀጠረው ኤክስፐርት እንደገለጸው) ለዓላማዋ በመቆም፤ በተራ መጻፊያና በብጭቅጫቂ ወረቀት ላይ በማቃሰት ላይ ያለውን አምባገነን መንግሥት ከወህኒ ቤት ሆና እየሞገተችውናእየሞጨረች እየተዋጋች ነው፡፡

በኢትዮጵያችን የተሻለሁኔታ እንዲመጣ ለማገዝ የበኩሌን አስተዋጽኦ ማድረግ አለብኝ፡፡ በርካታ ፍትሕ አልባነት፤ጭቆናዎች፤በኢትዮጵያ ውስጥ በየቀኑ በየሰአቱ በየደቂቃው በመፈጸም ላይ ናቸውና በጽሁፌ እንዚህን ሁኔታዎች እያነሳሁና እያጋለጥኩ መኮነን ይኖርብኛል፡፡ ንጹሃን ነጻነትንና ዴሞክራሲን ለመጠየቅ ባዶ እጃቸውን አለ የሚባለውን ሕገ መንግስት ላይ የሰፈረውን በማመን ሰልፍ በመውጣታቸው  መረሸናቸው፤የተቃዋሚ ፓርቲዎችን አመራሮች ማሸነፋቸው ወንጀል ሆኖባቸው፤ የነጻው ፕሬስ አባላት አመለካከታቸውና አቋማቸው ከጨቋኙ አገዛዝ የተለየ በመሆኑ፤ ስለመብት መነፈግ በመሟገታቸው፤ ብክንትን፤በተመለከተ ሁኔታዎች መለወጥ እንዳለባቸው በመናገራቸው ለወህኒ መዳረጋቸውን ቀድሞም የጻፍኩበት ነው፡፡ ያንን ሳደርግም ይህን ለማድረግ በረዳኝ ጥንካሬዬ የተነሳ ዋጋ እንደምከፍልበት ተረድቼ ነው፡፡ ሆኖም ግን ጋዜጠኝነት እኔ እራሴን የምሰዋለት ሙያ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ በሌላ አንጸር ደግሞ የኢህአዴግ ጋዜጠኞች የፕሮፓጋንዳና ቆርጦ ቀጥል አገልጋይ፤ የታዘዙትን እንጂ የታዘቡትን የማይጽፉ ጋዜጠኛ ናችሁ የተባሉ ግን ያልሆኑ የገዢው መደብ አገልጋዮች እንደሆኑም እረዳለሁ፡፡ለኔ ግን ጋዜጠኞች ድምጽ ላጡ ድምጽ ሆነው የሚሰዉ ቆራጥና ጥንካሬያቸው የማይገበር መሆናቸውን አውቃለሁ፡፡

ስለዚህም ነው በጭቆና መከራ ውስጥ ስላሉት እውነታውን በተመለከተ በርካታ ጽሁፎች ያቀረብኩት፡፡በዚህ ሳቢያ በርካታ ችግሮች ቢያጋጥሙኝም፤ እኔ ግን ለእምነቴ፤ ዓላማዬና ሙያዬ  በጥንካሬ እቆማለሁ፡፡በመጨረሻም ዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ስለ እውነቷ ኢትዮጵያ እንዲራደ አበክሬ እጠይቃለሁ፡፡እውነተኛዋ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንደምታይዋት አለያም የገዢው መደብ ባለስልጣናት ፈጥረውና የሌለውን እንዳለ፤ ያልተሞከረውን እንደተከናወነ፤ ያልታሰበውን እንደተፈጸመ አድርገው እንደሚያወሩላችሁም አይደለም፡፡በእውነተኛዋ ኢትዮጵያ ውስጥ ከመጠን ያለፈ ጭቆና እየተካሄደ ነው፡፡በነጻ በማሰባቸው ምክንያት ለእስር የተዳረጉት ኢትዮጵያውያን እኔ የምተርክላችሁ እውነት መሆኑን ያረጋግጡላችኋል፡፡እባካችሁ አቅማችሁ በፈቀደ መጠን ይህን ሁኔታ ለመለወጥ ሞክሩ፡፡

ማንም የጥንካሬን እውነተኛ ትርጓሜ ማወቅ ቢያሻው፤በፍልስፍና ጽሁፎችና አተረጓጎም ውስጥ አለያም በወታደራዊ ታሪኮች ውስጥ ለማግኘት አይሞክር፡፡ ከዚህ የርዕዮት ጽሁፍ በመማር ወደ ተግባር ይቀይሩት፡፡

ሌሎቻችን ጥቂት አለያም ጨርሶ ምንም ሳናደርግ እየኖርን ባለንበት እንደ ርዕዮት ያሉትን ግለሰቦች ጥንካሬን ተላብሰው ይህን እንዲያደርጉ የሚያተጋቸው ምንድን ነው እያልኩ ብዙ ጊዜ እገረማለሁ፡፡ ከጥንካሬና ከዓላማ ቁርጠኝነት ጋር አብረው ተወልደው ነው ወይስ በኋላ ያገኙት፤ከሆነስ የትና እንዴት ነው ያገኙት? ይህ ጥንካሬ በአጋጣሚ የተቀላቀላቸው ነው? ለርዕዮትና ለመሰሎቿ የሞራል ግዴታ የሆነባቸው ስልምንድን ነው? ይህ ሊሆን የሚገባው ሳይሆን በመቅረቱ ለምን? ብለው ሌሎቻችን ግን እንደሆነው ስንቀበል እነሱ ለምንን ዋነኛ መልስ ፈላጊ መብት አድርገው ማየት የቻሉት? ርዕዮትስ ሌሎችችን ከወህኒ ውጪ ሆነን በድሎት መኖርን ስንመርጥ ከዚያ የግፍ መጋዘን ከሆነው ወህኒ ቤት ‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ የተሸለ ሁኔታን ለማምጣት የበኩሌን አስተዋጽኦ ማድረግ አለብኝ ብዬ አምናለሁ›› ብላ ለምን መልእክቷን አስተላለፈች? ‹‹መቼም ቢሆን ለዓላማዬና ለሙያዬ በጥንካሬ እቆማለሁ››  በማለት በቆራጥነት ምን አናገራት? ‹‹ እባካችሁ አቅማችሁ በፈቀደ መጠን በኢትዮጵያ ይህን ሁኔታ ለመለወጥ ሞክሩ››፡፡ በማለትስ ለምን ተምጽኖ አሰማች? አብዛኛዎቻችን ለሃሞተቢስነታችን በበርካታው እንዲከፈለን ስንስማማ ርዕዮትን በተለይ ሁኔታው የሞራል ግዴታዋ እንዲሆን ምን አስገደዳት?

እንደ ርዕዮት ላሉት ወጣቶች እጅጉን ልዩ በሆነ መልኩ ብርታትንና ጥንካሬን ያላበሳቸው ምን እንደሆነ ማሰብ እንኳን መጀመር ያስቸግረኛል፡፡ምንልባትም ይህን መሰሉ ጥንካሬ ለተለዩ የዘመኑ ወጣቶች የተሰጠ ጸጋ ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባትም እኛ የዕድሜ ባለጸጎቹ ይህን የሚያላብሰን የደም ስራችን፤ ወኔያችን፤የአመለካከት ሚዛናችን ተዳክሞብን ይሆናል፡፡ ምናልባትም ለአንዳንዶቻችን ጥንካሬ ሽንፈት፤ ቅሌት ደግሞ ክብር፤ፍርሃትም ጀግንነት፤ መቀሳፈት እውነተኛነት ይመስለን እንደሁ አላውቅም፡፡ ነገር ግን ስንቶቹ በዚህ ‹‹በነጻው ዓለም ዋና ከተማ›› የሚኖሩ በብእር ስም፤ በስውር ስምና በሌላም መልኩ በርካታ ጦማሮችን መጠሪያ ስማቸውን በመደበቅ እንደሚከትቡ አውቃለሁ፡፡ ሌሎችም የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅና፤ ችሮታ ፍለጋና ቤተሰብነትን ለማግኘት በማለት የአምገነኑን ገዢ ስርአትና አገልጋዮቹን ለማስደሰት ያለውን እውነታ በመካድም እንደሚጽፉ አውቃለሁ፡፡ እንዲሁም በሃገር ውስጥ ስላለው መከራና ግፍ፤ የኑሮ ውድነትና ሌሎችም መብቶች ስለመገፈፋቸውና ሕዝቡ ለስቃይ መዳረጉን በዝምታ ማለፍን ምርጫቸው ያደረጉም አውቃለሁ፡፡ በግል ጨዋታ ግን ተቃውሟቸውን ያዥጎደጉዱታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንደርዕዮት ያሉት ጠንካሮች ለምን ለጥንካሬያቸው የሚፈለገውን ያህል ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ እንደሆኑና ሌሎቻችን ደግሞ ይህን ጥንካሬ እንዳጣነው ያስገርመኛል፡፡በአጭሩ ከጥንካሬ ጋር የተለያየነው ሃሞታችን ስለፈሰሰና ለጊዜው በሚገኝ ሽርፍራፊ ጥቅም ስንል ጥንካሬያችንን ጠቅልለን ለሃሰትና ለመስሎ መኖርነት በመሸጣችን ነው ልበል?

እኔ ርዕዮትን አላውቃትም:: የሞራል ብቃቷንና ጥንካሬዋን ግን በአድናቆት አከብራለሁ፡፡ርዕዮትና መሰሎቿ የሚኖሩት በሃሳባቸው ጸንተው፤በእምነታቸው ተማምነው  እነዚህ እሴቶቻቸው በሚፈጥሩላቸው ሁኔታ ነው፡፡ በዓላማቸው ጸንተው በሞራል ግዴታቸው ተማምነው ያላቸውንና መደረግ አለበት ብለው ለሚያምኑበት ሁሉ ችሮታቸውን ሳያጓድሉ ለዚያ ለቆሙለት እውነታ በማድረግ ነው፡፡ ምንግዜም በውስጠ ህሊናቸው ውስጥ የሞራል ግዴታቸውን የሚያነቃቃና የሚያስተገብራቸው ሃይል አላቸው፡፡ የተሸለ ዓለም፤ ሚዛናዊ የሆነ፤ሰዎች ሁሉ ያላንዳች ችግርና በደል ሊኖሩበት የሚችሉ ለማድረግ፤ ሊቆጣጠሩት የማይችሉት ፍላጎትና የተግባር ጽናት በውስጣቸው አለ፡፡ ዘወትር ጭንቀታቸውና ፍላጎታቸው የሰው ልጅ ደስታና የተደላደለ ሰላማዊ ኑሮ እንዲኖረው ማድረግ ነው፡፡ ፍትሕ ሲዛባ፤ሥልጣን አለአግባብ መጠቀሚያ ሲሆን፤አድልዎ ሲፈጸም ህሊናቸው በጣሙን ይጎዳና እረፍት ይነሳቸዋል:: ስለዚህም ያንን ተቋቁሞ እንዲስተካከል መታገልን ተቀዳሚ ግዴታቸው ያደርጋሉ፡፡ እንደ ርዕዮት ያሉ ዜጎች ለግል ፍላ ጎታቸውና ድሎታቸው ጨርሶ አይጨነቁም፡፡ እኔ የሚባል እራስን የማስቀደም በሽታ ሊይዛቸው ቀርቶ ባጠገባቸውም ደርሶ አያውቅም፡፡ እነሱ ለራሳቸው ሳይሆን ለሰብአዊ ፍጡራን መብትና ጥቅም ብቻ የቆሙ ናቸውና፡፡ ሌሎች ሰዎች ክንዋኔያቸውን እንዲያመሰግኑላቸው አለያም እንዲፈቅዱላቸው አይጠብቁም፡፡ የስብስብ አርቲ ቡርቲና የስብስብ ዋጋ ቢስ አስተሳሰብ ያማቸዋል፡፡ ለራሳቸው የጥንካሬ ብርታት ሊከፈል የሚገባው ዋጋ እንዳለና ያም የሚያስከትለውን እኩይ ሁኔታ ቢያውቁትም ያንን ሁሉ  ለመክፈል ፈቃደኛ ናቸው፡፡  የጥንካሬ ዋጋገው በመንፈሳቸው ጉዳት የሚከፈል መሆኑን ቢረዱም ያንንም ተቀብለውታል፡፡ እንዲህ ነው የአልበገሬዎች ሕይወትና ታሪካቸው!

ርዕዮት ከዚያ የጭቆናና የግፍ ማጎርያ ወህኒ በማንኛውም ጊዜ ልትወጣ ትችላለች፡፡ ለዚህም ማድረግ ያለባት በጉልበቷ ተንበርክካ እራሷን ዝቅ አድርጋ ከአሳሪዎቿ ይቅርታን መለመን ነው፡፡ ርዕዮት አንዳችም በደል አልፈጸመችም ስለዚህ ምንም በደል ባለመፈጸሟ ላልሰራችው ጥፋት ጨርሶ ይቅርታ መጠየቅ የሷ ስብእና አይደለም፡፡ በዚያ ማፈርያ ፍርድ ቤት ተብዬ መጋዘን ውስጥ በተላለፈው ፍትህ አልባ ፍርዳቸው ጋዜጠኛ አባቷን ልጃቸው ይቅርታ እንድትጠይቅ ይመክሯት እንደሆን ሲጠይቃቸው መልሳቸው፡-

ይህ ምናልባት አንድ ወላጅ ሊደርስበት የሚችል ግን አስቸጋሪ ጥያቄ ነው፡፡ ሁላችንም ወላጆች ሳናውቀው ከልጆቻችን ጋር የሚያስተሳስረን የደም ትስስር የሃሳብ ክር አለ፡፡ ሁል ጊዜ ለልጆቻችን መልካሙን ብቻ እንመኛለን፡፡ ከማንኛውም ጉዳት ፈጣሪ እንዲታደጋቸው እንጸልያለን፡፡ ያም ሆኖ ግን ይቅርታ መጠየቁን በተመለከተ ያ የራሷ የርዕዮት ውሳኔ ነው፤ እኔም ውሳኔዋ ምንም ይሁን ምን ያን አከብርላታለሁ፡፡ መሰረታዊ ጥያቄህን ለመመለስ፤እኔ አባቷ እንደመሆኔ ስለውሳኔዋ ያለኝና የሚኖረኝም አቋም አንዳችም ጎጂ ምግባር ያልፈጸመች ንጡህ በመሆኗ ይቅርታ ያውም ያለ ጥፋቷ እንድትጠይቅ አልፈልግም አልመክራትምም፡፡ ምንም ወንጀል አልፈጸመችምና፡፡

ስለሞራል ጥንካሬ በአንድ ወቅት ሮበርት ኬነዲ ሲናገሩ፤‹‹ይህን በመከራ የተጨናነቀ ዓለምን ለመለወጥ የሚፈቅዱ ሁሉ ያላቸው ልዩ ብቃት የሞራል ጥንካሬ ብቻ ነው፡፡ አንድ ሰው ለአዲስ ሃሳብ ሲነሳሳ ወይም የብዙዎችን ሃሳብ ሲመዝን፤ አለያም ፍትህ መዛባቱን ሲሞግት፤ እያንዳንዱ በየራሱ ትንንሽ አስተዋጽኦ በሚያደርግበት ወቅት እነዚህ ትንንሽ አስተዋጽኦዎች ተጠራቅመው ጠንካራ ጉልበት በመሆን ተኩራርቶና ማን ደፍሮኝ በሚል ከንቱ እምነት የተወጠረውን ያንን የመከራና የስቃይ ፋብሪካ የሆነውን ኃያል ነኝ ባይ ያኮራምተዋል::››  እህታችን ርዕዮትም በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጭቆናና የፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች እኩይ ምግባር ለመዋጋትና በሰላማዊ መንገድ ታግሎ ማሸነፍ መቻሉን የሚያመላክት ትንሽ ግን ወሳኝና ጠንካራ መልእክቷን ለ90 ሚሊዮን ደጋፊዎቿ አስተላልፋለች፡፡

በዚህ አጋጣሚ እኔም ርዕዮትን የጥንካሬን ትክክለኛ ገጽታ ስላስተማረችን አክብሮት የተመላበት ምስጋናዬን አቀርብላታለሁ፡፡(ምንም እንኳን የኔ ትውልድ ያንን ጠንካራና ግን ትንሽ መልእክቷን ማዳመጥ ቢሳነውም) እኔ ርዕዮት ለእራሷ ትውልድ ለላከቻት መልእክት አሁንም አመሰግናታለሁ፡፡ በብዕሯ ድጋፍና መሳርያነት ጭቆናን ለሕዝብ ለማልበስ በመጣር ላይ ያለውን ስርአት የጭቆናን ግርግዳ በብእሯና በብጫቂ ወረቀቷ ለመቦጫጨቅ በመነሳቷም አመሰግናታለሁ፡፡ እኛ ገሃድ የሆነውን የጭቆና ጫና አንሰማም አናይም ስለ እሱም አንናገርም ማለትን ስንመርጥ ርዕዮትና መሰሎቿ ግን በዚያ በአሰቃቂው ወህኒ ይማቅቃሉ፡፡ በጨቋኞችና በእኩይ አሳቢዎችና ፈጻሚዎች አመለካከት ላይ ሶስት ምርጫዎች አሉን፡፡ሃቁን ሸሽተነው በሃፍረት ሸማ ተሸፍነን መኖር፡፡ ምንም ጭቆና የለም በማለት ያለውን ክደን መኖር፡፡ አለያም ልክ እንደርዕዮት ሁሉ ያንን እኩይ ምግባር በጥንካሬ በመጋፈጥ ድምጻቸውን ለታፈኑ ድምጽ ለመሆንና ሰብአዊ ክብር ለመላበስ መወሰን፡፡ ድምጻቸው ለታፈነባቸው ድምጽ መሆንን ባንደፈርውም፤ ድምጻቸው ለታፈነባቸው ድምጽ በመሆናቸው ለእስር ለተዳረጉትስ ድምጽ መሆን ምርጫችን ሊሆን አይገባም?

እንደ ርዕዮት፤ሰርክዓለም፤እስክንድር ነጋ፤ውብሸት ታዬ፤ዳዊት ከበደ የመሳሰሉት ጀግኖቻችን በዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ሲከበሩና ለጥንካሬያቸው የሚገባቸውን ክብርና ሞገስ በያዓመቱ ሲሰጣቸው፤ እኛም ተግባራቸውን በቅርብ እያየንና እያወቅንም ዝምታችንን ብቻ መለገሳችን የሚያም: የሚያሳፍር የሚያሳዝን ሁኔታ ነው፡፡ ለምንድን ነው የማናከብራቸው? ማንነታቸውን የማናደንቅላቸው? የሚገባቸውን ክብርና ሞገስ በአደባባይ የማናውጅላቸው ለምን ይሆን? ለርዕዮቶቻችን፤ ለሰርካለሞቻችን፤ ለእስክንድሮቻችን፤……የዓለም ሕብረተሰብ ለምን ያከብራቸዋል?

‹‹በኢትዮጵያ የተሻለ ነገ እንዲመጣ የበኩሌን አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለብኝ አምናለሁ›› ርዕዮት ዓለሙ

የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):

መስማት የተሳነው፡ ስብሃት ነጋ፡( ከማተቤ መለሰ ተሰማ)

በአጼ ምኒልክ ዘመን፡ አንድ ኢትዮጵያዊ፡ በድንገት መስማት ይሳነዋል አሉ፡ ሰውየው እድሜ ጠግቦ እስከሚሞት፡ የምኒልክ፣ የእያሱ፣ የዘውዲቱ ንግስና አልፎ፡ ከሀይለ ስላሴ የግዛት ዘመን አጋማሽ ድረስ ቆይቶ ነበርና፡ ጆሮው መስማት ከማቆሙ በፊት የነበረው ሁሉ እንዳለ፡ የቀጠለ መስሎት፡ በምኒልክ አምላክ እንዳለ ነው የሞተው ይባላል። በአጠቃላይ ስነምግባሩ፡ ሲታይ ከሰው ተወልዶ ከእንስሳት ጋር እንዳደገ፡ በግልጽ የሚመሰክርበት፡ ስብሃት ነጋም፡ እንዳይሰማ ጆሮው የደነቆረው፣ እንዳያነብ አይኑ የታወረው፡ ደደቢት ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን የሚቀር አይመስለኝም። ምክናያቱም ዛሪ ሕዋሃት የማስመሰያ ካባውን አጥልቆ፡ ኢትዮጵያዊ ለመባል እየጣረ ባለበት ወቅት ስብሃት ከ21 አመት በሗላ የሚናገረው ሁሉ፡ በምኒልክ ሲል እንዳለፈው ሰው ደደቢት በነበረበት ጊዜ ሲሰበክ የነበረውን፡ የኢትዮጵያን ህዝብ ማዋረድንና አማራንና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን  ማጥላላት፣ ስለአከተመለት ስርአት ሰለደርግ ማውራትን ነው። ከዚህ አንጻር ሲታይ፡ በአሁኑ ወቅት ሰውየውን በጥሞና ለሚከታተለው ሰው፡ ዘመናት ጥለውት ከንፈው እሱ አንድ ቦታላይ ቆሞ ለብቻው እየቆዘመ እንዳለ ለመገንዘብ አያዳግተውም።

ለነገሩማ እርጅናም፡ በአንዳንድ ሰዎች ላይ የህሌና ሚዛንን ማዛባቱ ባይቀርም፡ ስብሃትን ግን ከእድሜው በላይ ያደነቆርው፡ ቀን ሲያኝከው የሚውለው ጫት፣ ማታ ተዘፍዝፎበት የሚያድረው አረቄ ነውና፡ እነዚህ ሁለት አድገኛ የሰው ልጅ የአካልም የአእምሮም ጠንቅ የሆኑና አቅልን የሚያስቱ ነገሮች፡ ማየትና መስማቱን ብቻ አይደለም፡ ህይወቱንም አለመንጠቃቸው የሚያስገርም ነው።

ውድ አንባብያን፡ በዚህ ጽሁፊ ስብሃት ነጋን አንተ እያልሁ የምገለጸው፡ የክብርን ዋጋ ለማያውቅና፡ በ90 ሚሊዮን የሚገመተውን ጭዋና አስተዋዩን የኢትዮጵያን ህዝብ በጠቅላላ ለሚዘልፍ ሰድ አክብሮት መስጠት፡ እራስን እንደማዋረድ ስለምቆጥረው መሆኑ ይታወቅልኝ። ለምን የሚል ካለ መልሴ፡ ሌላውን ትቸ 19/10/2012 የጀርመን ሶሻሊስት ፓርቲ ባዘጋጀው፡ የአፍሪካ የውይይት መድረክ ሰብሰባ ላይ ተገኝቶ በነበረበት ወቀት ከተናገረው 2ቱን ለአብነት ብጠቅስ በቂ ይመስለኛል። ስብሃት ነጋ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ መጻሂ እድልና የፓለቲካ ምህዳር እንዲያብራራ ለቀረበለት ጥያቄ፡ በተለመደውና ስነምግባር ባልገራው አንደበቱ የሰጠው ከጥያቄው ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው መልስ፡ 1ኛ/ ስነስራት የሌለውን የኢትዮጵያን ህዝብ ስራት ለማስተማርና፡ የደርግ እርዝራዦችን፡ ለመቆጣጠር በዙ ጊዜ አሳልፈናል። 2ኛ/ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሴ ብቁ አይደለም የሚል ነበር። ማን ይሆን፣

አውቃለሁ መራር ነው መራብ መጠማት፣

ቁስሉ አይጸናም እንጅ ደግሞ እንደ ውርደት

ያለው? እንዲህ ተዋረደ፡ ደጉ፣ እሩህሩሁ፣ ጭዋው፣ አትንኩኝ ባዩ፡ የኢትዮጵያ ህዝብ፡ ይገርማል፡ አርቆ በማሰቡ፣ በመታገሱ፣ ከወያኔና ጋጠወጥ መሪዎቹ፡ የተመለሰለት ይህ ነው። ለመሆኑ ስብሃት ነጋ ማነውና ነው የኢትዮጵያን ህዝብ ስራት የሚያስተምረው? እሱስ ስራት ለማስተማረ ቀድሞ ነገር ስራት አለው ወይ? ይህን ያህል በእብሪት የተወጠረበትስ ምክናያት ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳት የግድ ከሚልበት ደረጃ ላይ የደረስን ይመስለኛል። ከኤርትራዊ እናቱና ከአድዋው አባቱ የተወለደው፡ የዛሪው ስብሃት የትናንቱ ወልደ ስላሴ ነጋ፡ ወደትግል ከመግባቱ በፊት የሚያከብረውና የሚያፈቅረው፡ ከአባቱ ይልቅ እናቱን እንደነበርና፡ አሁንም ሆነ በትግሉ ወቅት፡ ከምር የሰራውና እየስራ ያለው ከኢትዮጵያ የልቅ ለኤርትራ እንደነበርና እንደሆነ በብዙ ማስረጃዎች እያስደገፉ ምስክርነታቸውን ሲሰጡ የኖሩ በቅርብ የሚያውቁት ሰዎች እነዳሉ አስታውሳለሁ።

ስብሃት ወይንም ወልደ ስላሴ፡ ለኢትዮጵያውያን የነበረውን ጥላቻ፡ በገቢር ማሳየት የጀመረውም፡ ሜዳ በነበረበት ጊዜ፡ ወደትግሉ የሚቀላቀሉ ሴት እህቶቻችንን አስገድዶ እየደፈረ፡ ሲያረግዙ እንዳያጋልጡት በመግደልም እንደነበር ብዙ ቀራቢው የነበሩ ሰዎች ተናግረውታል፡ ቀጥሎ ወያኔ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በሗላም፡ ከመለስ ዜናዊ በስተጀርባ ሆኖ ለ21 አመታት በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ ለተፈጸመው መለኪያ መስፈርት፡ መግለጫ ቃላት፡ ለማይገኝለት ግፍ፡ ቀላል ሚና አልነበረም፡፡ ሌባ ሲካፈል እንጅ፣ ሲሰርቅ አይጣላም፡ እንደሚባለው ሁሉ፣በቅርብ፡ ከአዜብ መስፍን ጋር፡ በጥቅም መጋጨት እስከጀመሩ ጊዜ ድረስ፡ መለስ ያለስብሃት ይሁንታ፡ የሰራውና የሚሰራው እንዳልነበር የታወቀ ነው።የዛሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ስራት የለውም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሴ ብቁ አይደለም ወ.ዘ.ተ. የሚለው ዘለፋው፡ የመነጨውም፡ከዚያ  ከቆየው የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን ጥላቻው ነው።

ያረጀ የልማድ ፈረስ ጋላቢውና፡ በክፋት፣ በቅናትና በምቀኝነት፡ ለተበከለ፣ በመንፈስም የታወረ፣ በአልኮል መጠጥ ብቻም ሳይሆን፡ በእርኩስ ምኞትም የሰከረ፡ አእምሮ ባለቤት የሆነው፣ እንዲሁም ከክዕደት ጋር ጡት የተጣባው፡ ስብሃት ነጋ፡ የበቀል ጥሙን ለማርካት የነደፈው መረሃግብር ተሳክቶለት፡ ኢትዮጵያ በጥፋት፣ ህዝቧ በፍርሀት እንዲዋጡ፣ ምድሯም ሲቃይ ተዘርቶ መከራ የሚበቅልባት፣ ምሪትና ዋይታ የሚታጨድባት፣ ሞት፣ በሽታ፣ እራብና እርዛት፣ በገፍ የሚመረትባት፣ የሰው ልጅ ስብናው፡ እየበሰበሰ፣ ማንነቱ ሰርዶ እየለበሰ ያለባት፡ ምድራዊ ጋነብ እንድተሆን፡ ካደረጓት ሰዎች ግንባር ቀደሙ ለመሆን በቅቷል።

ያንን ሁሉ በደል ሲፈጽም፡ ዝም በመባሉም ነው፡ እንደዚህ ለከት የለሽ፡ አፉን ለመክፈት የበቃው፡ እኛስ መቸይሆን ትግስታችን የሚያበቃው? መቸ ይሆን ውርደቱ የሚያመን? መቸይሆን በሌሎች ኪሳራ አትራፊ ለመሆን የፓለቲካ ሂሳብ መስራታችንን፡ አቁመን የተነጠቅነውን ማንንታችነን፡ ለማስመለስ የህይወት መሷዕትነት መክፈልን፡ ምርጫችን የምናደርገው? መቸይሆን እንደዚህ እየተዋረዱ፡ ቆሞ ሲሞቱ ከመኖር ይልቅ፡ ሞትን በሞት ሽሮ ማለፍ ሃያው እነት ነው፡ የሚለውን ብሂል ስራላይ የምናውለው? ውድ አንባብያን እስኪ ለአፍታ ቆም በማለት ውስጣችነን እንፈትሽ፡ እኔም፣ አንተም ሆንህ፣ አንች፡ ከስብሃት ነጋ የምናንስበት ምን ነገር አለ?????

ጥቅምት ወር 2012

 

የ“አዲሱ መንግስት” ተግዳሮት እና የአቶ ኃይለማሪያም አጣብቂኝ

ዘሪሁን ተስፋዬ
(የቀድሞ የአዲስ ነገር ጋዜጣ ባልደረባ)

አዲስ ታይምስ

mስከረም 2፤ 2005 ዓ.ም ሎንዶን። ከእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ የተወከሉ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተናል ከሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች፣ ጋዜጠኞች እና የምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተወካይ ግለሰቦች ጋር ለውይይት ተቀምጠዋል። ወቅቱ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ማን ይተካ ይኾን የሚለው ጉዳይ የሚብሰለሰልበት ነበር። በርግጥ ለእንግሊዝ ተወካዮች የሚያብሰለስል ጉዳይ አልነበረም፤ ምስጢራቸውን በልባቸው ሸሽገው ከባለሞያዎቹ ተጨማሪ ሃሳቦችን ይሰበስባሉ። ሁሉም ባለድርሻ የሚመስለውን እና ጥናቱ ያመላከተውን ሐሳብ ሰነዘረ። ተንታኞችን በሚያስማማ መልኩ የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ተተኪነት አነጋጋሪ አልነበረም። በጠቅላይ ሚኒስትር ተተኪ ማንነት ላይ ላይ ጥርጣሬ የነበረው ማንም አልነበረም። የድሕረ መለስ የፖለቲካ ኹኔታ እንዲሁ ትኩረት ያገኘ ነበር።የ“አዲሱ መንግስት” ተግዳሮት እና የአቶ ኃይለማሪያም አጣብቂኝ

የተለየ ጉዳይ የተከሰተው ግን ተሳታፊዎች ውይይታቸውን አጠናቀው በሻይ ሰዓት የግል ጭውውት ሲያደርጉ ነበር። የውጭ ጉዳይ ተወካዮቹ የያዟትን ምስጢር ለመተንፈስ እድል ያገኙ መሰለ። ከእንግሊዝ ተወካዮች መካከል አንዱ የምስራቅ አፍሪካን ፖለቲካ አብጠርጥሮ ያውቃል ብለው ወደገመቱት የፖለቲካ ባለሞያ ቀረብ ብለው “ስለ ደመቀ መኮንን የምታውቀውን ንገረኝ?” አሉት። ለዓመታት የምሥራቅ አፍሪካን የፖለቲካ ግለት ሲለካ ለነበረው ባለሞያ ጥያቄው ዱብ ዕዳ ብቻ ሳይኾን፤ በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ቀበሌ ስለሚኖር አንድ ተራ ግለሰብ ዝርዝር ጉዳይ የመጠየቅ ጉዳይ ኾኖ ተሰማው። ስለአቶ ደመቀ የሚያውቀው ጉዳይ ቢኖርም ለበሰለ የፖለቲካ ተዋስዖ የሚበቃ አልነበረም። መረጃ በሌለው ጉዳይ ላይ ዝምታን ቢመርጥም ጉዳዩ ከንክኖት ስለነበር በተራው ጠያቂ ኾነ፤ “ደመቀን በተመለከተ ምን አዲስ ነገር አለ?” ምላሹም በዲፕሎማሲያዊ ቃና የታሸ ነበር። “ [ደመቀ] ቦታ ሳይያዝለት አልቀረም”- አጠር ምጥን ያለ ምላሽ።

ባለሞያው ተጨማሪ ማብራሪያ አላሻውም። ይልቁንም ነገሮች ከጠበቀው ውጪ እየተራመዱ እንደኾኑ ይበልጥ ግልጽ ኾነው ታዩት። በእርግጥም የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደወትሮው ሁሉ ከግምት ውጪ የኾኑ ክስተቶችን እያስተናገደ ነበር። አቶ ደመቀን እንዲህ ላለ ከፍተኛ ስልጣን ማንም የገመተ አልነበረም። በአብዛኛው የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ከሕወሓት ወይም ከኦሕዴድ እጅ ያመልጣል የሚል ግምት አልነበረም። በተለይ ለአመታት ‹‹ከስልጣኑ ስገለል ኖሪያለሁ›› የሚለው ኦሕዴድ ከስልጣን ቅብብሎሹ ተጋሪ ይኾናል የሚል ዕምነት በብዙዎች ዘንድ ነበር።

ይኹንና የቅርብ ተንታኞችም ኾኑ የአገሬው ዜጋ ሳይሰማ የብአዴን ተወካይ አቶ ደመቀ ትልቁን የሥልጣን እርከን እንደሚቆጣጠሩ እንግሊዞች “ደርሰውበት” ኖሯል። ከቀናት በኋላም የኾነው ይህ ነበር። በእዛው ሣምንት ቅዳሜ ምሽት ኢህአዴግ አቶ ደመቀን የግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ “መረጠ”። በእለቱ የተሰራጨው ዜና ለብዙሃኑ የፖለቲካው ነፋስ አቅጣጫ ተንባዮች እና ዜጎች አዲስ ቢኾንም ቀመሩን ለሠሩት ለአሜሪካ፣ ለእንግሊዝ፣ ለአቶ ስዩም መስፍን እና ለአቶ በረከት ስምዖን ግን የቤት ሥራው በወጉ መጠናቀቁን “የሚያበስር” ነበር። “ቦታ ሳይያዝለት አልቀረም” የምትለዋ ዲፕሎማሲያዊ ሐረግም ፍቺዋን አገኘች።

ምስጢራዊነት ትልቁ የፖለቲካው ማቀንቀኛ መድረኩ የኾነ የፖለቲካ አመራር ሥፍራውን በተቆጣጠረበት አገር ግምቶች ሁሉ ፉርሽ ናቸው። ኢህአዴግ እና ምስጢረኝነት ደግሞ የዘመናት ቁርኝት አላቸው። ግንባሩ በትጥቅ ትግል ወቅት ስኬታማ ከኾነባቸው መንገዶች አንዱ የኾነውን ጥብቅ የምስጢር ጠባቂነት ወግ የመንግሥት ሥልጣንንም በእጁ ካስገባባት ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የሙጥኝ ብሎ ይዟል። የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አልጋ ላይ መዋልን ተከትሎም በተለያዩ የብዙሐን መገናኛ ዘዴዎች ሲወራ የነበረውን “ዜና እረፍት” በዚሁ የምስጢረኝነት ጠባዩ በመጽናት እስከመጨረሻዋ ሰዓት ድረስ ሲያስተባብል ቆይቷል። በማስተባበሉ ሂደትም ግንባሩ የሥልጣን ሽግግሩን ጉዳይ አፍኖ ቢይዝም ውስጥ ውስጡን ግን ከለጋሽ አገራት በተለይም ከእንግሊዝ እና አሜሪካ ጋር በመኾን ቀመሩን ሲያሰላ ነበር።

ምስጢራዊነቱ የተዋጣለት ለተባለ ግምት በሩን የከፈተ ስላልነበርም የቀመሩ ስሌት የሕ.ወ.ሓ.ትን የዓመታት የበላይነት ያስወገደ በሚመስል ሁኔታ ለአደባባይ ወሬ በቃ። የደ.ሕ.ዴ.ን ሊቀመንበር ኃይለማሪያም ደሳለኝን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሁም ፍጹም ቦታ አይኖረውም ተብሎ ተግመቶ የነበረው ብ.አ.ዴ.ን አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ በማሾም ቀመሩ የ.ሕወ.ሓ.ትን የበላይነት አደብዝዞ አሳየ። ይህም የተጭበረበረ ምስል የአንድ ብሔር ልሂቃን የበላይነት ለዘመናት ሠፍኖባት ለነበረባት አገር የፖለቲካውን አቅጣጫ ይለውጠው ይኾናል የሚል እምነት በነበራቸው ዜጎች እና በለጋሽ አገራት ዘንድ ትልቅ ስኬት ተደርጎ ተወሰደ። በርግጥም የበርካታ ቋንቋ ተናጋሪዎች ስብስብ የኾነው የደቡብ ክልል የሥልጣን ተቋዳሽ መኾኑ፤ እንዲሁም በሥልጣን ክፍፍሉ “ምንም ዓይነት” ሽራፊ ስልጣን ላይኖረው ይችላል ተብሎ ተገምቶ የነበረው የአማራ ክልል “ትልቁን” ድርሻ ማንሳቱ የስልጣን ሽግግሩ ከተገቢ ለውጥ ጋር ተካሂዷል ለሚሉት ሰዎች ማሳያ ሊኾን ይችላል።

በተለይ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ የሥልጣን ሽግግሩን በአዎንታዊ መልኩ እንዲወስድ ያስገደደው ብሔርን ያማከለው ፌዴራሊዝም አዳዲስ ፊቶችን ከተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች ማካተቱ ነው። ይኹንና የተለያየ የፖለቲካ ስብዕና የተላበሱ አመራሮች ወደ ሥልጣን መምጣታቸው እና የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ የሥልጣን ሽግግር ሰላማዊ መኾን የአገዛዙን መሠረታዊ መለያ ጠባያት የለወጠ አይደለም። ይልቁንም በግልጽ የሚታይ የአመራር ክፍተት እና ከሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር የተወረሱ ሕጸጾች የፖለቲካው መለያ ጠባያት ኾነው እንዲቀጥሉ አድርጓል። አቶ ሃይለማሪያምም በቀላሉ ለመፍታት ከሚቸግሯቸው ተግዳሮቶች ጋር መፋጠጣቸው የግድ ነው።

ስንኩል አመራር

የአቶ ኃይለማርያም አስተዳደር ከሚገመተው በላይ በጣም ደካማ ነው። ከመነሻውም ቢኾን የቀድሞ ዋነኛ የሕ.ወ.ሓ.ት እንዲሁም የኢሕአዴግ አመራር አባላትን ይኹንታ ያላገኙት የደቡቡ ሰው፤ ከስሙ በስተቀር የአመራር ብቃታቸውን የሚያሳዩበትን ስልጣን ከእጃቸው አላስገቡም። አቶ መለስ ዜናዊ ሞት ባይቀድማቸው ቃል እንደገቡት በቀጣዩ ምርጫ ሥልጣናቸውን የማስረከብ ዕድል ቢኖራቸው ኖሮ ምንአልባት ከሕወሓት አፈና መጠነኛ የኾነ መተንፈሻ ያገኙ እንደነበር የተነገረላቸው አቶ ኃይለማሪያም ነጻ የመኾንን ዕድል ተነፍገዋል። የደህንነት፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የአገሪቷን የደህንነት እና ስለላ ሥራ የሚያግዘው የቴሊኮሙኒኬሽን ክፍል አሁንም በሕወሓት እጅ የተያዙ እና ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቁጥጥር ውጪ የኾኑ ናቸው።

በተጨማሪም የውጭ ጉዳይ እንዲሁም የኢኮኖሚ የአማካሪነት ሥፍራዎች ዋነኛ እና ጠንካራ ትግራዋይነትን በሚያቀነቅኑ የሕወሓት አባላት አሁንም የተያዙ ናቸው። በጉምሩክ፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ቢሮዎች እና በመካከለኛ የሥልጣን ዕርከን በፌዴራል ቢሮዎች የሚሠሩ የፖለቲካ ሹመኞች በብዛት የሕወሓት አባላት ሲኾኑ የማይገሰስ የበላይነትን ያሰፈኑ ናቸው። ብዙዎቹም ሥርዓቱ የፈጠረላቸውን አጋጣሚ ተጠቅመው አግባብ ያልኾነ ሐብት ያካበቱ በመኾናቸው በቀላሉ ሥፋራውን ለአዲሱ አመራር ለመልቀቅ የተዘጋጁ አይደሉም። ከዚህም ባሻገር በአቶ መለስ ቀጥታ አመራር ሥር የነበረው እና ሙሉ ለሙሉ የሕወሓት ቅርጽ እና መልክ የተላበሰው አምስት ሺህ የሚገመተው አግዓዚ ኮማንዶ እጣው ፈንታው ያለየ ሌላው የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ራስምታት ነው። ይህም የአቶ ኃይለማሪያም መንግሥት አሁንም የሕወሓት የበላይነት የሰፈነበትን የፖለቲካ ሥርዓት ከለላ በመኾን ዕድሜ ከማራዘም ተሻግሮ ይህ ነው የሚባል ፋይዳ እንዳያስመዘግብ እንቅፋት ይኾናል።

ከግለሰብ አምባገነንነት ወደ ቡድን አምባገነንነት

አቶ መለስ ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወዲህ ሕወሓት የሚታወቅበትን “ዴሞክራሲያው ማዕከላዊነትን” አፈር አልብሰው ሲያበቁ በብቸኝነት አመራሩን ተቆናጠው ኖረዋል። ጠያቂ በሌለበት እንዳሻቸውም ገዝተዋል። ከትልቁ የፖለቲካ ሥልጣን እስከ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ያለው የሥልጣን ተዋረድ ከእርሳቸው ቁጥጥር ውጭ አልነበረም። ይህም ታዛዥ እና ተገዢ እንጂ በራሱ የሚተማመን አመራርን ለኢሕአዴግ አልፈጠረም። ከዚህም ባሻገር ሁሉም የኢሕአዴግ አመራር አባላት በሚባል ደረጃ የሕዝብ ተቀባይነት የሌላቸው ሲኾኑ አንዳንዶቹም መርጦናል ብለው ለሚደሰኩሩለት ማኅበረሰብ ባዕድ ናቸው።

አቶ መለስም ጥለው የሄዱት ኢሕአዴግ ገና ወደ ፖለቲካው መድረክ እንደተቀላቀለ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ በመዳህ ላይ ያለ ነው። ይህ ኹኔታም አደገኛ መዘዝን ይዞ ነው የመጣው። ለዘመናት በአንድ ግለሰብ አምባገነንነት ከሚመራ ግንባር የሥልጣን ሽኩቻ ወደበዛበት እና የግለሰቦች ፉክክር ወዳየለበት የአንጃዎች ጥርቅም የግንባሩን ቅርጽ ይለውጠዋል። “እኔ ከማን አንሼ” የሚለው የፉክክር መንፈስ የፖለቲካውን መድረክ ይቆጣጠረዋል። ይህ ዓይነቱ ለውጥ የግል ወይም የብሄር ጥቅማቸው ያስተሳሰራቸው በአንድነት ጥላ ሥር የተሰባሰቡ አባላት ብዛት መገለጫው ይኾናል። ግንባሩም የይስሙላ “አንድነት” ቢኖረውም ልል እና አማካይ የአመራር ሥፍራ እንዳይኖረው ያደርገዋል።

አማካይ ሥፍራ የሌለው አመራር ተጠያቂነትን የሚያዳፍን እና የቡድን አምባገነንነትን የሚያሰፍን ነው። አቶ ኃለማሪያምም እንዲተውኑ የተሰጣቸውን “ሥልጣን” በአንድ እርምጃ ለማራመድ ቁርጠኝነቱን ለማሳየት እስካሁን አልደፈሩም። ለመጥቀስ ያህል ሕገ መንግሥቱ የፈቀደላቸውን በቤተ መንግሥት የመኖር መብት እንኳ ለመጠየቅ ድፍረቱን አላገኙም። ከርሳቸው ይልቅ ከወይዘሮ አዜብ መስፍን ጋር ቅሬታ አላቸው የሚባሉት የሕወሓት አባላት እና አቶ በረከት ስምዖን እመቤቲቱን ለማስወጣት ደፋ ቀና ሲሉ ይስተዋላሉ። አቶ ኃይለማሪያም ለውሳኔ በዘገዩ እና የተተበተቡበትን ሠንሠለት ለመበጣጠስ በአቅማሙ እና በዘገዩ ቁጥር የአንጃዎቹ መበርታት የያዙትንም ቦታ ሊያሳጣቸው ይችላል።

በሌላ በኩል የግንባሩ መፍረክረክ ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ ባለበት አገር እንደ መልካም አጋጣሚ የሚቆጠር ነው። የተሻለ ታክቲክ በመንደፍ ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ለማድረግ አመቺ ነው። ይኹንና አሁን ባለው ኹኔታ በጥንካሬ የሚጠቀስ ተቃዋሚ በአገር ውስጥ የለም። የአማራጭ ሃይሎች በፖለቲካው መድረክ አለመታየት ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ ውስጥ ከሚታየው የሥልጣን ሽኩቻ ጋር ተደማምሮ አጠቃላይ አገራዊ የአመራር ቀውስ ሊፈጥር ይችላል።

ኦ.ሕ.ዴ.ድ- “ሲሞቅ በማንኪያ . . .”

የአቶ መለስ ዜናዊ አልጋ ላይ መዋልን ተከትሎ ከበሮ ይመታባቸው ከነበሩ ሥፍራዎች ሁለቱ ተጠቃሽ ናቸው- ጎረቤት ሶማሊያ እና የግንሩ አጋር ድርጅት ኦ.ሕ.ዴ.ድ። በተለይ የሶማሊያ ታጣቂዎች (ሽብርተኛውን አል-ሻባብን ጨምሮ) የመለስን መሞት በጉጉት ይጠብቁ ነበር። ከተለያዩ የሚዲያ ባለሞያዎች መረጃ ለመሰብሰብ የሚያደርጉትን ያላሰለሰ ጥረት የተመለከተ ጠባቸው ከአቶ መለስ ጋር ብቻ የኾነ ያህል እንዲሰማው ያደርጋል። የኦ.ሕ.ዴ.ድ ከበሮ ግን የአል-ሻባብን ያህል ባይደምቅም አጋጣሚውን ተጠቅሞ ሥልጣን ለመጋራት ያለውን ፍላጎት ያሳይ ነበር።

ከሁለት ወራት በፊት የመጀመሪያውን ሙከራ ያደረገው በኦሮሚያ ክልል ተቀባይነት አላቸው የሚባሉትን አቶ አባ ዱላ ገመዳን ለድርጅቱ ሊቀመንበርነት በማጨት ነበር። ወትሮውኑም ቀድሞ የነበራቸው ወጣ ያለ ተሳትፎ በኢሕዴግ ያልተወደደላቸው አባ ዱላ አፈ ጉባዔነቱን እንዲይዙ የተደረገው ኾን ተብሎ ከኦሮሚያ ክልል ለማራቅ መኾኑን ማንም አላጣውም። በወቅቱም ድርጅቱ እርሳቸውን ወደፊት ለማምጣት ፍላጎቱን ሲያሳይ ከፍተኛ ተቃውሞ የመጣው ከ.ሕ.ወ.ሓ.ት ነበር።

ኦ.ሕ.ዴ.ድ ለሕ.ወ.ሓ.ት “ቀኑን የሚጠብቅ ኦ.ነ.ግ” ማለት ነው። እምነት ሊጥሉበት አልቻሉም። ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የኦ.ነ.ግ አባላት መሰግሰጊያ ነው ሲሉ ይሟገታሉ። በመኾኑም ድርጅቱ በተሻለ ሰው እንዳይወከል የመንግሥት ከፍተኛ አመራር አካላት ሌት ተቀን ደክመዋል። ለዚህም ይመስላል በቅርቡ ድርጅቱ ባደረገው ስብሰባ አቶ አለማየሁ አቶምሳን ለድርጅቱ በከፍተኛ ሥልጣን ደረጃ አለመወከል ተጠያቂ በማድረግ የህወሓትን ሴራ ለማደፋፈን እየተሞከረ ያለው። “አቶ አለማየሁ ሁለቱንም ሥልጣን ደርቦ በመያዝ ኦሮሚያ ከፍተኛ ሥልጣን በፌደራል መንግሥቱ እንዳይኖረው አድርጓል” የሚል ወቀሳ ከአባሎቻቸው የደረሰባቸው። ነገሩ ግን ግልጽ ነው። የአቶ በረከት እና መሰሎቻቸው ሴራን ለመሸፈን እና ችግሩን ወደ ድርጅቱ ለማምጣት ነው።

ከኦሕዴድ ጋር ያለው ትግል በአጭሩ የሚቋጭ አይመስልም። በቀጣይ ከፍተኛ ሹም ሽር ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል። በርካታ የድርጅቱ አባላት ጥርስ የተነከሰባቸው እና በቅርቡ ከፓርቲው የሚሰናበቱ ናቸው። ይህ ሁሉ ሲሆን የሕወሓት ሙሉ ተሳትፎ እንጂ የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚና እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ከቀጥጥራቸው ውጪ የኾኑ ነገሮች እየተካሄዱ ነው። ከሁሉ በላይ ግን ኦሕዴድን ከከፍተኛ ሥልጣን ማግለሉ የአቶ ኃይለማሪያምን የሥልጣን ዘመን ተጨማሪ ፈተና ይሰጠዋል።

ከላይ የተጠቀሱት አንኳር ነጥቦች እና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች ወሳኝ አመራርን የሚጠይቁ ጉዳዮች ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለትክክለኛ ለውጥ የቆሙ ከኾነ ከፊታቸው የተጋረዱትን ፈተናዎች በብልሃት እና በትዕግስት መፍታት ይኖርባቸዋል። አዳዲስ ሰዎችን ወደ ሥልጣን ማምጣት፣ ለተቃዋሚዎች መድረኩን መክፈት፣ ለነጻው ፕሬስ አመቺ ሁኔታን መፍጠር እንዲሁም የፖለቲካ እሰረኞችን መፍታት የተግባሮቻቸው ሁሉ መጀመሪያ ሊኾኑ ይገባል።

 

ደቡብ ሱዳን ቀጣይቱ የኢትዮጵያ ፈተና – ከተመስገን ደሳለኝ

ከተመስገን ደሳለኝ
ደቡብ ሱዳን ከሰሜኑ ጋር እዚህ አዲስ አበባ ላይ ያደረጋቸው የሰላም ስምምነት ለኢትዮጵያ ከሚያስገኘው ጥቅምና ጉዳት አንፃር ምን አንድምታ አለው? የሚለው ለጊዜው በመወያያ አጀንዳነት ገና ወደ
አደባባይ አልመጣም፡፡ ኢትዮጵያ ለረጅም አመታት ሁለቱ አገራት በክብ ጠረጴዛ ዙሪያ ተገናኝተው እርቅ ያወርዱ ዘንድ ያደረገችው አስተዋፅኦ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ መቼም የኢትዮጵያ መንግስት
ይህንን ሁሉ ዋጋ የከፈለው ለፅድቅ ነው ብለን የምንመፃደቅ አይመስለኝም፡፡ የየትኛውም አገር የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የመጨረሻ ግቡ የራስን አገር ጥቅም ማስጠበቅ ነው፡፡ የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ወደ እርቅ መምጣት አገራችን ያሰላችው ፖለቲካዊም ይሁን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ይኖራል የሚል እምነት አለኝ፡፡ እነዚህ ስሌቶች አንዳንዴ መልካም ጐናቸው ሲያመዝን፤ በተቃራኒው ደግሞ ከተጠበቀው ይበልጥ የከፋ ቀውስ ይዘው የሚመጡባቸው አጋጣሚዎች ይኖራሉ፡፡ ደቡብ ሱዳን አሁን ላይ ሆነን ይሄንን በረከት ይዛ መጥታለች፤ አልያም ይህንን አይነት መርገምት አድርሳለች የምንልበት ወቅት ላይ ባንሆንም፤ ለወደፊቱ አገራችን እነዚህን ሁነቶች አስልታ የምትዘጋጅባቸውን አንዳንድ ነጥቦችን ማየት ተገቢ ነው፡፡
ሙላት ውብነህ እና ዮሐንስ አባተ በጋራ ባሳተሙት ‹‹Ethiopia transition and development in the horn of Africa›› በሚለው መጽሐፋቸው ከአጠቃላዩ የኢትዮጵያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መካከል የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደውና በዋቢነት ትኩረት የሚያደርገው አፍሪካን በሚመለከት የሰፈረው ሃሳብ ነው፡፡ በተደጋጋሚ እንደተገለጸው በአህጉሪቱ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዙሪያ የአገራችንን ንቁ ተሳትፎ ማድረግን ቀዳሚ ግቧ አድርጎ ማስቀመጡ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
1960 በፊትደከ1960ዎቹ በፊት ኢትዮጵያ አብዛኛውን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል ከጅቡቲ መንግስት ጋር የነበራት ግንኙነት ተጠቃሽ ነው፡፡ ለዚህም ዋነኛው የግንኙነቱ ምክንያት ሁለቱን ሀገሮች በኢኮኖሚ አስተሳስሮ የያዘው የጅቡቲ አዲስ አበባ የባቡር ሀዲድ መስመር ነው፡፡ ከዚህ ውጭ በጊዜው በቅኝ ግዛት ስር ከነበሩት የጐረቤት ሀገራት ጋር ይህ ነው ሊባል የሚችል አይነት ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አልነበራትም፡፡
ከ1960ዎቹ በኋላ ግን አገራችን ከነዚህ አገራት ጋር ከጉርብትና ባለፈ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ቀርፃ ከቀሩት የቀጠናው ሀገራት ጋር ጥብቅ ግንኙነት ልትመሰርት ችላለች፡፡ በጊዜው አገራችን ካከናወነቻቸው ተግባራት መካከል በእንግሊዝና ፈረንሳይ ቅኝ ግዛቶች ፣ በሰሜኑ አረብ አገራትና በተቀረው ጥቁር የአፍሪካ አገራት፣ እንዲሁም በካዛብላንካና በሞኖሮቪያ ቡድኖች መካከል የተነሱትን አምባጓሮዎች ለመፍታት የተጫወተችው ሚና ከፍተኛ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ለየትኛውም ቡድን ወገንተኛ አለመሆኗ የሁሉም አጋር እንድትሆን ከማስቻሉም በላይ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እ.ኤ.አ. በ1963 ዓ.ም ሲመሰረት ለመቀመጫነት ተመርጣ ሰፊ የሆነ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ለማግኘት ችላለች፡፡ ለዚህም እንደማሳያነት የሚጠቀሰው አፄ ኃ/ስላሴ በ1962 (እ.ኤ.አ) ዓ.ም. በሌጐስ ስብሰባ ላይ‹‹ኢትዮጵያ እራሷን እንደ አንድ ቡድን ብቻ ታያለች ይህም የአፍሪካ ቡድን ብቻ ነው›› ማለታቸው የሁሉም አይን ሀገሪቷ ላይ እንዲያርፍ አስችሏል፡፡

የኢትዮ-ሱዳን ግንኙነት የረጅሙ የኢትዮ-ሱዳን ታሪካዊ ግንኙነት አንዴ በጥላቻ ሌላ ጊዜ በወዳጅነት ረጅም አመታትን አሳልፏል፡፡ የአፄ ኃ/ስላሴ መንግስት መውደቅ፤ በተለይም በ1956 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ) የሱዳን መንግስት ነፃ መውጣትን ተከትሎ በሁለቱ አገራት ውስጥ የተገንጣይ ቡድኖች መስፋፋት፤ የድንበር ማካለልና የስደተኞች ጉዳይ ለግንኙነቱ እንደ ዋነኛ ችግር ፈጣሪ ተደርገው የሚቆጠሩ ነበሩ፡፡
በኢትዮጵያ የሰሜኑ የኤርትራ ክፍል የፌዴራል ስርዓቱ መጣስና የኃ/ስላሴን የውህደት ፖሊሲ በመቃወም የተነሳው የተገንጣይ ቡድን አንዱ ሲሆን፤ በሱዳን ደግሞ የደቡብ ክፍል ከሰሜኑ አረብ አስተዳደር ጋር ባለመስማማት ነፍጥ ማንሳቱ በሁለቱ አገራት ፖለቲካዊ ግንኙነት ላይ የራሱን አሻራ ሊያስቀምጥ ችሏል፡፡ የኤርትራ ገንጣይ ቡድን የነበረው የጀብሐ አመራር ክፍል በአብዛኛው ከእስልምና ሃይማኖት ጋር የተያያዘ በመሆኑ የአረብ አገራትን ቀልብ ለመግዛት አስችሎት ነበር፡፡ ለዚህም የ‹‹እስልምና ወንድማማችነት›› በሚለው የአጋርነት ፖሊሲ ምክንያት የሰሜኑ የሱዳን ክፍል የኤርትራ ተገንጣይ ቡድኖችን በከፍተኛ ሁኔታ መርዳት ጀመረ፡፡ ይህን አስመልክቶ አቢር ሞርደካይ “The continuous horn of Africa conflict” በሚለው መጽሐፋቸው ኢትዮጵያ ከአረቡ አገራት ጋር በመቆራረጥ በአዲስ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አቅጣጫ ፊቷን ወደ እስራኤል ማቅናቷን ያብራራሉ፡፡ ‹‹ከዚህ በኋላ ነበር የአረቡ ሀገራት አጋርነት ከሃይማኖት በተጨማሪም የፖለቲካዊ ግንኙነት መልክ እየያዘ የመጣው›› ሲሉ አክለው ያብራራሉ፡፡
ይህን ተከትሎ ነበር የኢትዮጵያ መንግስት የሰሜኑን አረብ አገዛዝ ለማዳከም የደቡብ ሱዳን ግዛት (በአብዛኛው ክርስቲያን እንደሆነ የሚታመነው) ያነሳውን የአኒያ-ኒያ (Anya-Nya) እንቅስቃሴ መደገፍ የጀመረው፡፡ ሁለቱም ሀገሮች የውክልና ጦርነት (Proxy war) በማድረግና ተቃራኒ ቡድኖችን በመደገፍ እልህ ውስጥ የገቡት እንዲህ ብለው ነው፡፡
ይህንንና የመሳሰሉትን ሸካራ ግንኙነቶች አልፈው አሁን ኢትዮጵያ ሱዳን ድረስ ዘልቃ የሀገሪቱን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋጋት የምታስፈልግበት ጊዜ ደረሰ፡፡ ደቡብ ሱዳንም ከሽምቅ ውጊያ ተላቃ ወደ አገር አደገች፡፡
ጋምቤላ-ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን ህዝቦች መካከል ወደፊት ሊፈጠር ስለሚችለው የሁለትዮሽ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትስስር ለመረዳት ሁለት መንገዶች አሉ፡፡ ቀዳሚው ሁለቱ አገራት ከዚህ ቀደም የነበራቸውን የፖለቲካ-ታሪክ (Political History) በሚመለከት አጭር ዳሰሳ ማድረግ ሲሆን፤ በሁለቱ አገራት ድንበር አካባቢ ያሉትን ህዝቦች ነባር
ግንኙነት መስመር ማጥናት ሌላኛው አማራጭ ነው፡፡
በማንኞቹም አገራት የሚኖሩ ድንበር ተጋሪ ህዝቦች የሚያመሳስላቸው አንድ እውነት አለ፡፡ ይህም የጋራ ቋንቋ፣ ባህል፣የአየር ንብረት፣ የኢኮኖሚ ምንጭና ተመጋጋቢ የህዝብ ለህዝብ ትስስሮሽ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በዙሪያዋ ከበዋት ካሉ የቀንዱ አባል አገራት ጋር ተመሳሳይ የሆነ ተሞክሮ አላት፡፡ ለምሳሌ በትግራይና ኤርትራ፣ በአፋርና ጅቡቲ፣ በኢትዮጵያ ሶማሌና በሱማሊያ፣ በኢትዮጵያ ሞያሌ እና ኬንያ ሞያሌ እያልን መዘርዘር እንችላለን፡፡
የደቡብ ሱዳንና የጋምቤላ ተሞክሮም ተመሳሳይ ነው፡፡ ስለአገራቱ ህዝቦች ቀጣይ እጣ ፋንታ ለመናገር አስቀድሞ በሁለቱ አገራት ህዝቦች መካከል ያለውን አንድነት እና ልዩነት በሚገባ መመርመር ተገቢ ነው፡፡ አሌክሳንደር ሜኬልበርግ “Changing Ethnic relations, a preliminary investigation of Gambella, south west Ethiopia”በሚለው ጥናታዊ ፅሁፋቸው የጋምቤላን ህዝቦች አሰፋፈር ከደቡብ ሱዳን አንፃር አስተያይተው ያቀርባሉ፡፡ በጥቅሉ በጋምቤላ ውስጥ ወደ አምስት የሚጠጉ ብሔሮች ይገኛሉ (አኙዋክ፣ ኑዌር፣ መጀንገር፣ ኦፓ እና ኮሞ)፡፡ ከነዚህ አምስቱ

ብሔሮች መካከል ኑዌር 40% የሚሆነውን አብዛኛውን ድርሻ ሲወስድ አኙዋክ 25%፣ መጀንገር 10% የሚሆነውን ይዘው በተከታይነት ተቀምጠዋል፡፡
በደቡብ ሱዳን ውስጥ ከሚገኙ ህዝቦች መካከል ኑዌር እና አኙዋክ ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ የእነዚህ ህዝቦች በሁለቱ አገራት ውስጥ ያላቸው ተዋፅኦ በተናጠል ማየት እንችላለን፡፡ አብዛኛው የኑዌር ተወላጆች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቁጥራቸው የበዛ ሲሆን የቀረው ደግሞ በደቡብ ሱዳን ውስጥ የሚገኘው ነው፡፡ በተቃራኒው አብዛኛው የአኙዋክ ቤተሰቦች በደቡብ ሱዳን ሲገኝ የተቀረው የብሔሩ አባላት በጋምቤላ ውስጥ የሚኖሩትን ይጠቀልላል፡፡ ይህ ማለት በሁለቱ አገራት መካከል ተመሳሳይ የሆኑ ህዝቦች በተለያየ መጠን፣ በተለያየ አስተዳደር ስር ይኖራሉ ማለት ነው፡፡
ሰማያዊ ወርቅን በጥቁር ወርቅ እንደ ተቀሩት የቀንዱ አገራት ሁሉ ደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያን የሚያመሳስላቸው ብዙ መለኪያዎችንም ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ ሁለቱም ለህዝባቸው ሊያሟሉ የሚገባቸው ነገር ግን ያልቻሏቸው በርካታ ጐደሎ ነገር አላቸው፡፡ ሁለቱም በመካከለኛው የአገራቸው ክፍልና በድንበር አካባቢ ያሉ ህዝቦቻቸው እጅግ የተራራቁ ከመሆናቸው በተጨማሪ ለተቀረው የአገሬው ነዋሪ የምግብና የኃይል አቅርቦትን በበቂ ሁናቴ ለማዳረስ የተሳናቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህን ችግሮቻቸውን ለማስታረቅ ሁለቱም የግድ ተቀራርበው ሊሰሩባቸው የሚገቡ መደላደሎች መኖራቸው እሙን ነው፡፡
ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ወደፊት ለሚኖራት የጠበቀ ትስስር ስትል የሰሜኑን ወዳጅነት ማበላሸት እንደሌለባት ይታመናል፡፡ ለዚህም አንዱ ምክንያት ከሰሜኑ የምናገኘው የወደብ አገልግሎትና እስከዛሬም ድረስ ጥገኛ የሆንበት የነዳጅ  ከዋነኞቹ መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ሃርይ ቬርሆቨን “The case of regional energy integration: gold for black gold” በሚለው ፅሁፋቸው ኢትዮጵያ በተለይ ከሱዳን ጋር ያላትን አዎንታዊ ቁርኝት በሰፊው ፡፡ እንደ እርሳቸው አገላለፅ ከሆነ በኢትዮጵያና ኤርትራ መንግስት መካከል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ  በኤርትራ ትገለገልበት የነበረው የወደብ አገልግሎት በመቋረጡ ምክንያት ፊቷን ወደ ጅቡቲና ሱዳን እንድታዞር ፡፡ ስለዚህ ፖርት ሱዳን ከጅቡቲ ቀጥሎ ሌላኛው የወጪና ገቢ ንግድ ማስተንፈሻ በመሆን እያገለገለ ይገኛል፡፡
ለዚህም ነው ደቡብ ሱዳንን ለማትረፍ በሚል የምንመርጠው አካሄድ ከሰሜን ሱዳን የምናገኘውን የወደብ አገልግሎት  መጠንቀቅ ይገባል የምለው፡፡
ሁለተኛው የኢትዮጵያና ሱዳን ጥብቅ ቁርኝት የሚስተዋለው ጥቁሩን ወርቅ (ነዳጅ) በሚመለከት ሁለቱ አገራት  መንገድ በማየት ነው፡፡ ምንአልባት መረጃዎቹ ተተንትነው የቀረቡበት መንገድ ይለያይ ይሆናል ሰእንጂ  ደረጃ ኢትዮጵያ ከ85-90% የሚሆነውን የነዳጅ ፍላጐት የምታሟላው በቀጥታ ከጐረቤት አገር ሱዳን ነው፡፡
ሁለቱ አገራት በደረሱበት ስምምነት መሰረት ሱዳን ለኢትዮጵያ የምታቀርበው ነዳጅ በዋጋ ደረጃ ከአለም መገበያያ አንፃር  ዝቅተኛ የሚባል ነው፡፡ ይህ ግብይት በዓመት ከ1.2 እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሲሆን፤አገራችን በጠቅላላው  ንግድ ከምታገኘው ገቢ ሃምሳ በመቶ (50%) የሚሆነውን ነዳጅ ለመግዛት ታውለዋለች፡፡
በቀጣይ የአገራችን ነዳጅ የማግኛ እጣ ፈንታ ወደ ደቡብ ሱዳን የሚያጋድል ይመስላል፡፡ ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን  ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርጋለች፡፡ ደቡብ ሱዳን በበኩሏ ኢትዮጵያ አባይን በተመለከተ በምትወስደው ማናቸውም  ቅር እንደማትሰኝ መሪዎቿ በተደጋጋሚ ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአባይ ዙሪያ የምታመነጨው የኤሌክትሪክ  (ተንታኞቹ ሰማያዊው ወርቅ የሚሉት) ተከትሎ ደቡብ ሱዳን ለህዝቦቿ ከአጭር ርቀት ገዝታ ለመጠቀም ካላት  አንፃር ሁለቱ አገራት በኃይል አቅርቦት ዙሪያ ተመጋጋቢ ግንኙነት ሊፈጥሩ የሚችሉባቸው አማራጮች እየታዩ ፡፡
አዲሱ ውል  ሱዳን ግዛቶች መካከል ዩኒቲ፣ የላይኛው አባይ (በደቡብ ሱዳን ድንበር ውስጥ የታጠሩ)፣ እና የአቢዬ ግዛት (የማን  ገና ውሉ ያለየለት) በነዳጅ ሀብታቸው የሚታወቁ ናቸው፡፡ ይሁንና ደቡብ ሱዳን የምታመርተውን ነዳጅ  አቀፍ ገበያ ለማቅረብ ይቻላት ዘንድ የምትጠቀመው ብቸኛው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ በሰሜን ሱዳን የሚገኘው ፡፡ በቅርቡ ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ እና ከጅቡቲ መንግስታት ጋር አዲስ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ለመዘርጋት በእቅድ  መሆኗን ይፋ አድርጋለች፡፡ የደቡብ ሱዳን ማዕድን ሚኒስትር የሆኑት ስቴፈን ዳዩ ዳኡ አዲሱን ፕሮጀክትና ፋይዳ  በቀረበላቸው ጥያቄ ስለጠቀሜታው የሰጡት መልስ ሲጠቃለል ሁለት እንዳምታዎች አሉት፡፡
የመጀመሪያው፤ የቀድሞ ነዳጅ ማስተላለፊያ ለመተው (ምንም እንኳን የሶስት አመት ቀሪ ኮንትራት ከሱዳን ጋር ያላቸው ) አዲሱ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሲሆን ለደቡብ ሱዳን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው በመታመኑ የሚነሳ ነው፡፡ ታሪካዊ ጠላት ከሆነችው ሱዳን ጋር በነዳጅ ማስተላለፍ ሂደት ውስጥ የተፈጠረው አለመተማመን  ነዳጁ ከሚመረትበት አንስቶ እስከ ጅቡቲ ወደብ ያለው እርቀት ከዚህ ቀደም ፓርት ሱዳን ካለበት አንፃር  አጭር የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሲሆን ኢትዮጵያ ነዳጅን በሚመለከት ያላት ከፍተኛ ጥገኝነት ሰየተሻለ ጠቀሜታን እንድታገኝ  ሁለተኛው ምክንያት ነው፡፡ በነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦው አማካኝነት የኢትዮጵያ መንግስት ግዛቱን በመፍቀዱ  የኪራይ ውል እንደተጠበቀ ሆኖ ፕሮጀክቱ በነዳጅ ላይ ያለንን መተማመኛ ከረጅም ዓመት እቅድ አኳያ  ያደርግልናል፡፡ እነዚህን አካሄዶች በስርዓት መያዝ ከተቻለ የደቡብ ሱዳን ወደ ቀጠናው መቀላቀል እውነትም  በረከትን ይዞ ይመጣል ብለን ተስፋ እንድናደርግ ይረዳናል፡፡

ስጋቶች
ጋምቤላንና ደቡብ ሱዳንን በሚያዋስነው የድንበር አካባቢ ያለው ቀጠና ከረጅም ጊዜያት አንስቶ በተለያዩ ምክንያቶች ብጥብጥ ያልተለየው እንደነበረ የተለያዩ ፀሐፊያን ባሰፈሯቸው ድርሳናት ላይ ገልፀዋል፡፡ በእዚህ አካባቢ  ላደረጉ ግጭቶች የተለያዩ ምክንያቶች ማቅረብ ቢቻልም በጥቅሉ መሰረታዊ ምክንያት የሚባሉትን አንዳንድ  በሦስት የተለያዩ ደረጃዎች ከፋፍለን ማስቀመጥ እንችላለን፡፡ ቀዳሚው ምክንያት በጋምቤላ ክልል ውስጥ  ግጭቶች እና አለመግባባቶች ብሎም የለየላቸው ጦርነቶች በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ብሔሮች መካከል መነሻውን  ሲሆን ሁለተኛው ምክንያት በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ብሔሮች ከማዕከላዊው የፌዴራል መንግሥት  የሚፈጥሩትን አለመግባባት ተከትሎ የሚከሰተው ግጭት ነው፡፡ ሶስተኛው የግጭት ምክንያት ድንበር ተሻጋሪ ምንጭ  ነው፡፡ ይኸውም የጋምቤላን ክልል ታኮ ባለው የደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢ የሚኖሩ የሌላኛዋ አገር ዜጎች የተፈጥሮ ሀብትን ከጋምቤላ ነዋሪዎች ጋር ለመጋራትና በሀገራቸው የሚቀሰቀሱ የተለያዩ ግጭቶችን በመሸሽ ድንበር
አቋርጠው የሚገቡ ስደተኞች ከነዋሪዎቹ ጋር የሚፈጥሩት ግጭት ነው፡፡ ደረጄ ፈይሳ የተባሉ በጋምቤላ ክልል ዙሪያ ሰፊ ጥናትና ምርምር ያደረጉ ፀሐፊ ከላይ የጠቀስኳቸውን ተለዋዋጭ የግጭት
ምክንያቶች ዘርዘር አድርገው ያስቀምጡታል፡፡ “A National perspective on the conflict in Gambella”በሚለው ጽሁፋቸው በተለያዩ ጊዜያት በጋምቤላ አካባቢና በደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢ የሚነሱ ግጭቶች አምስት መሰረታዊ መነሾ እንዳላቸው ያትታሉ፡፡
ቀዳሚው በጐሳዎች መካከል የሚነሳ የግጭት ነው፡፡ ይህ ትንተና በጋምቤላ ውስጥ በሚኖሩ የተለያዩ ብሔሮች መካከል የሚነሳውን ግጭት ይመለከታል፡፡ ለዚህ መሰሉ ግጭት ምክንያቶች የተለያዩ ቢሆኑም በተለይ የተፈጥሮ ሀብት ክፍፍል፣አንዱ ብሔር ሌላኛው ብሔር በሚኖርበት አካባቢ የሚያደርገው ሰፈራ፣ በብሔሮች መካከል የሚከሰቱ የእርስ በርስ አለመግባባቶች በዋነኝነት ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው፡፡ በክልሉ ከሚገኙት ብሔሮች መካከል ኑዌሮች እና አኙዋኮች በእንዲህ አይነት ግጭት በተደጋጋሚ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በጐሳ መካከል የሚነሳው ግጭት ሁለተኛው ምክንያት ነው፡፡ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ብሔሮች ከእርስ በርስ ግጭት አልፎ በውስጣቸው በያዟቸው ጐሳዎች መካከል የሚነሳው ግጭት ሌላኛው የቀውስ ምክንያት ነው፡፡ በጐሳ መካከል ለሚነሳው የእርስ በእርስ ግጭት በዋናነት ከሚቀመጡት ምክንያቶች መካከል የፖለቲካ ውክልና ለማግኘት የሚደረግ ፉክክር (በመጀንገር)፣ የተፈጥሮ ሀብትን በበላይነት ለመቆጣጠር ሲባል (በኑዌር)፣ ይጠቀሳሉ፡፡ሌላኛው አገር በቀልና ህዳጣን በሚባሉት ዜጎች መካከል የሚነሳው ግጭት ሦስተኛው ነው፡፡ ጋምቤላ በማዕከላዊው መንግስት የግዛት ማስፋፋት ፖሊሲ ስር ከመጠቃለሏ በፊት በአካባቢው የነበሩ ብሔሮች በአንድ ወገን አገር በቀል (Natives) የሚባል ስያሜ ሲሰጣቸው፤ ግዛት ማስፋፋቱን ተከትሎ የሰፈሩና በንግድና በኋለኛው ዘመን በተካሄደዱ
የሰፈራ ፕሮግራሞች አማካኝነት ወደ አካባቢው የመጡ ‹‹ሰፋሪዎች›› (Migrants) መካከል በቦታ ይዞታና የክልላዊ ማንነትን ጥያቄ መሰረት ያደረገው አለመግባባት ሌላው የግጭት መስመር ነው፡፡
ማዕከላዊ መንግስት በክልሉ ከሚገኙ ብሔሮች ጋር በሚፈጠረው አለመግባባት የሚከሰተው ግጭት አራተኛው ምክንያት ነው፡፡ ጋምቤላ ውስጥ ከሚገኙ ብሔሮች መካከል ማዕከላዊው መንግስት በተለይ በተደጋጋሚ የግጭት ሂደቶችን ያሳለፈው እና አሁንም እያሳለፈ ያለው ከአኙዋኮች ጋር ነው፡፡ የአኙዋኮች ጥያቄ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ቢሆንም በተደጋጋሚ ችግሩን ለመፍታት መንግስት የሄደበት መንገድ ለችግሩ ዘለቄታዊ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ይበልጥ እያጋጋለው ለመምጣቱ አሁንም ግጭቱ ላለመብረዱ ምስክር ነው፡፡
የመጨረሻው ምክንያት ድንበር ተሻጋሪ ግጭት የሚለው ነው፡፡በጋምቤላ ውስጥ ከሚነሱ ግጭቶች መካከል ድንበር ተሻጋሪው ግጭት ለየት ያለ ባህሪ አለው፡፡ ለዚህም ሁለት ምክንያቶችን ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አንደኛው በግጭቱ ተሳታፊ
የሚሆኑት ብሔሮች በሁለት የተለያየ ሉዓላዊ አገራት ውስጥ የሚገኙ የመሆናቸው ሁነት ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ለግጭቶቹ መፍትሄ ለመስጠት የሚወሰዱ እርምጃዎች ችግሩን በቀላሉ የሚፈቱ አለመሆናቸውን መጥቀስ እንችላለን፡፡
ከላይ የተጠቀሱት በጋምቤላ አካባቢ በምክንያትነት የሚቀርቡ የግጭት መስመሮች ከዚህ ቀደም ተለምዷዊ በሆኑ የግጭት አፈታት ስልቶች መፍትሄ ሲበጅላቸው ቆይቷል፡፡ የማዕከላዊውም ይሁን የክልሉ መንግስት በመሰረታዊ የክልሉ ህዝቦች  ቅሬታ በሚያቀርቡበት ወቅት ምላሽ ተደርገው የተወሰዱት ባልተመጣጠኑ የግጭት አፈታት እርምጃዎች ምክንያት የተለያየ ወቀሳ የደረሰባቸው ቢሆንም ለጉዳዩ እየሰጡ ያሉት ትኩረት ግን አሁም ድርስ እዚህ ግባ የሚባልና መፍትሄውም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እርምት መስጠት የሚችሉ አለመሆናቸው እስከዛሬም ድረስ እነዚህ ቀውሶች ተሸክመናቸው እንድንጓዝ ተገዳናል፡፡

ደቡብ ሱዳን ከግጭት ጀርባ
የደቡብ ሱዳን በምስራቅ አፍሪካ አካባቢ ተጨማሪ አገር ሆና ብቅ ካለች ገና ለጋ እድሜ ላይ ነች ቢባልም ለወደፊቱ ግን በተለይ ጋምቤላን ታከው ለሚነሱ ግጭቶች የደቡብ ሱዳን ሚና እንደ ከዚህ ቀደሙ ከኢትዮጵያ ያነስና በቸልታ የሚታይ ይሆናል የሚል እምነት የለኝም፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም የጋምቤላን የግጭት ምክንያቶች ተንተርሶ እርምት ለመውሰድ ብሎም ግጭቱን ለማስታረቅ በሚጠቀምበት መሰረታዊ አካሄድ ዙሪያ ዳግም የተሻለ እና ከዚህ ቀደም ከሚከተለው የተለየ አካሄድ ማየት እንደሚገባው አምናለሁ፡፡
በአካባቢው በሚነሱ ግጭቶች ዙሪያ ለወደፊቱ የደቡብ ሱዳን እየተጠናከረች መምጣት የተለየ ትርጓሜ እንደሚኖረው ከወዲሁ መገመት ከባድ አይሆንም፡፡ ወደፊትም ደቡብ ሱዳን በአካባቢው የሚኖራት አስተዋፅኦ አንዳድ መሰረታዊ ምክንያቶችን ይዞ የሚነሳ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ፡፡በሁለቱ አገራት (በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን) ውስጥ የሚኖሩ የድንበር ተጋሪ ህዝቦች መካከል በተደጋጋሚ ለሚነሱ
ግጭቶች መሰረታዊ ምክንያቶች ጠቅለል አድርገን ማስቀመጥ እንችላለን፡፡ በዚህ አካባቢ ያሉ ዜጐች ዋነኛ የኢኮኖሚ ገቢያቸው (መተዳደሪያቸው) በከብት ማርባት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ እነዚህ ህዝቦች ለከብቶቻቸው የግጦሽ መሬት እና ውኃ ፍለጋ ሲሉ የአንዱን ድንበር አቋርጠው በማለፍ የተፈጥሮ ሀብትን ለመጋራት የሚያደርጉት ሙከራ የግጭቱ አንዱ ምክንያት ሲሆን፤ ሁለተኛው ምክንያት በተለይም ከዚህ ቀደም እንደታየው ጋምቤላ ውሰጥ ባሉት ኑዌርና በደቡብ ሱዳን በሚገኙት የሙርኔ ህዝቦች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶች የሚያስከትሏቸው የሰው ህይወት መጥፋት ለግጭቶች
መባባስ ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው፡፡
ደቡብ ሱዳን ከዚህ ቀደም ለእንደዚህ አይነት ድንበር ዘለል አለመግባባቶች ትሰጠው የነበረው ትኩረት አናሳ ከመሆኑም በተጨማሪ ራሳቸውን ከሰሜኑ የሱዳን ክፍል ለመገንጠል ያደረጉ የነበረው መራራ ትግል ደቡብ ሱዳንን በድንበር አካባቢ ለሚነሱ አለመግባባቶች ዋጋ እንዳትሰጥ አድርጓታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ በታሪክ ደቡብ ሱዳን ነፃ አገር እንድትሆን ያደረገችውን አስተዋፅኦ ከግምት ስናስገባ ለግጭቶቹ ትኩረት ሰጥቶ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለመነታረክ የሚደረግ ማንኞቹም ሙከራዎች ከጥቅማቸው ይልቅ የሚያስከትሏቸው ኪሳራዎች መብዛታቸው ሌላኛው ለኢትዮጵያ
የጠቀመ የማሰሪያ ፖለቲካ ካርድ ነበር፡፡
ጥያቄው ይሄ የፖለቲካ ካርታ እስከመቼ ያጫውታል? የሚለው ነው፡፡ ደቡብ ሱዳን ከዛሬ ነገ እየጠነከረች ስትመጣ ለዜጐቿ የምትሰጠውም ትኩረት የዛኑ ያህል እየጨመረ መምጣቱ አይቀርም፡፡ ‹‹በፖለቲካ ዘላቂ ወዳጅም ይሁን ዘላቂ ጠላት የለም›› የሚለው መርህ ተግባራዊ መሆን ሲጀመር፤ አልፎም ‹‹አገራት በአለም አቀፍ መድረክ በማንኛውም የሉዓላዊነት መስፈርት እኩል ናቸው›› የሚለው መርህ በተግባር ሲተረጎም ደቡብ ሱዳን ለዜጐቿ ጥበቃ እና ከለላ ለማድረግ በሚል ከአገራችን ጋር የተካረረ ግጭት ውስጥ ልትገባ የምትችልባቸው አጋጣሚዎች ይፈጠራሉ፡፡
በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ድንበር በዘላቂነት ከተለያዩ ድንበር ዘለል አደጋዎች ለመጠበቅ ሊወሰዱ የሚገባቸው ቅድመ ጥንቃቄዎች መኖር እንደሚገባቸው ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ለዚህም ቀላል እና አፋጣኝ ወቅታዊ እርምጃዎች ሊሰጥባቸው የሚገቡ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ተገቢ ነው፡፡ የማዕከላዊውም ይሁን የክልሉ መንግስት አስቀድሞ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የድንበር ወሰን ጥርት ባለና ሁለቱንም ሊያግባባ በሚችል መልኩ ከደቡብ ሱዳን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መግባት ቀዳሚው ሲሆን (በሁለቱ አገራት መካከል ድንበርን በሚመለከት ያሉትን አንዳንድ መሠረታዊ ነጥቦች ለመረዳት ዶ/ር ወንደሰን ተሾመ የፃፉትን ‹‹colonial Boundaries of Africa the case of Ethiopia’s Boundry with suda›› የሚለው ፅሁፍ መመልከት በቂ ነው፡፡)፤ በሁለቱ አገራት አዋሳኝ ድንበር ላይ ባሉ ዜጐች መካከል የሚነሱትን አለመግባባቶች በባህላዊው የግጭት አፈታት መንገድ እልባት እንዲሰጣቸውና በቀጣይም ለግጭት የሚጋብዙ ምክንያቶችን ከምንጩ ለማድረቅ መስራት ይጋባል፡፡
በተጨማሪም በድንበሮች አካባቢ የሚኖሩ የሁለቱ አገራት ዜጎችን ኢኮኖሚ ከአርብቶ አደር ወደ ተረጋጋና የተሻለ ወደሚባለው የግብርና መር ኢኮኖሚ እንዲሻገሩ በማድረግ ግጦሽ መሬትን ፍለጋ በሚል ሰበብ ይከሰቱ የነበሩትን እንቅስቃሴዎች መግታት ከብዙ በጥቂቱ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም እንደከዚህ ቀደሙ ሳይሆን የጋምቤላን ክልል በሚመለከት አዲስና የተለየ የፖሊሲ አቅጣጫ ትግበራ ማድረግ ይገባዋል፡፡ አለበለዚያ አዲሲቱ አገር ደቡብ ሱዳን ከበረከት ይልቅ ለቀንዱ አካባቢ ተጨማሪ መርገምት መሆኗ አይቀርም፡፡
“Irredentism”
ደቡብ ሱዳን በተጠናከረ መልኩ ወደ ቀጠናው እጇን እያሳረፈች ስትመጣ በቀጣይ ስጋት ልትሆን ትችላለች ብዬ ከማስብባቸው ምክንያቶች መካከል ከዚህ በፊት የገጠመን የሱማሌያ ተሞክሮ ሌላው ነው፡፡ ሱማሊያውያን ለረጅም አመታት በኢትዮጵያ ከተፈራረቁ ወሪዎች ጋር ደም አፋሳሽ ጦርነቶችን አድርገዋል፡፡ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ከፍተኛ የታጠቀ ኃይል መኖሩ ዙሪያ ገባው አገራችን ክፍል ለተለያዩ ጥቃቶች እንድትጋለጥ አድርጓታል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት በአገራችን ላይ ከሶማሊያ መንግስት የተቃጡብን ጦርነቶች ምክንያታቸው ተመሳሳይ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ሶማሊያዊያኑ የግዛት ይገባኛል ጥያቄን በማንሳት በአገራችን ላይ ጦረነቶችን አውጀዋል፡፡ የግጭቶች መነሻ በኢትዮጵያ ስር ተጠልለው  የሚገኙትን ሶማሌዎች የሚኖሩበትን አካባቢ (ኦጋዴን) በኢትዮጵያ መንግስት በጉልበት ተነጥቀናል የሚል ታሪካዊ ጥያቄን በማንሳት ነው፡፡ እነዚህ ኃይሎች ይህንን ጥያቄ መነሻ ምክንያት በማድረግ ‹‹ህዝባችን እና መሬታችንን እስካልተመለሰልን ድረስ ትግላችንን እንቀጥላለን›› የሚል ወጥ የሆነ አቋም ያራምዳሉ፡፡ ይህ ተደጋጋሚ ጥያቄ ለሶማሌያውያኑ የአንድ ወቅትና የአንድ ትውልድ ብቻም ሳይሆን የዘመናትም እስከመሆን ደርሷል፡፡ ይሄ በሶማሌያውያኑ የተሰነዘረው የመሬት ይገባኛል ጥያቄ (Irredentism) በቀጣይም ከደቡብ ሱዳን ሊቃጣ እንደሚችል መጠርጠር ተገቢ ነው፡፡ ይህንን ጥያቄ በደቡብ ሱዳንም ዘንድ ሊያስነሳ የሚችል ተመሳሳይ አይነት ተሞክሮ በጋምቤላና መኖሩን ማየት እንችላለን፡፡

አብዛኞቹ በጋምቤላ አካባቢ የሚኖሩ ብሔሮች በአንድም ይሁን በሌላ ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያመሳስሏቸው የተለያዩ ነገሮች አሉ፡፡ በተለይ በህዝብ ለህዝቡ ግንኙነት ዙሪያ ኑዌሮች እና አኙዋኮች ቤተሰቦቻቸውን ደቡብ ሱዳን አስቀምጠው የመጡ ናቸው፡፡ ረጅም አመት ያስቆጠረው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ለብዙ የደቡብ ሱዳን ነዋሪዎች ከቀያቸው መፈናቀልና በጋምቤላ ቋሚ ኑሮ ለመጀመር አይነተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የደርግ መንግስት ለደቡብ ሱዳን ይሰጥ በነበረው ቀጥተኛ ወታደራዊ እርዳታ ምክንያት ከጋምቤላ ተቆርሶ በተሰጠው መሬት ላይ ደቡብ
ሱዳናውያኑ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ ከፍተው ይጠቀሙ እንደነበር ይታወቃል፡፡
እነዚህ ምክንያች በቀጣይ ምን መዘዝ ይዘው ሊመጡ ይችላሉ? የሚለውን ማየት ተገቢ ነው፡፡የደቡብ ሱዳን መንግስት ይነስም ይብዛም ጋምቤላ ውስጥ ባሉ ብሔሮች መካከል ይፈጠሩ በነበሩ አለመግባባቶች እና ግጭቶች ውስጥ እጁ እንዳለበት የተለያዩ ፀሐፊያን ይስማማሉ፡፡ በተለይ በኑዌሮች እና አኙዋኮች መካከል ሲነሱ ከነበሩ ግጭቶች ጀርባ የደቡብ ሱዳን ጦር ኑዌሮችን በመርዳት ግጭቱን ያባብስ እንደነበር እነዚሁ ፀሐፊያን ያትታሉ፡፡ በቀጣይም የኢትዮጵያ መንግስት በአካባቢው ላይ በሚወስዳቸው ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ እርምጃዎች ዙሪያ የደቡብ ሱዳን መንግሥት አንዳንድ አፀፋዊ እርምጃዎችን ሊወስድ ይችላል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ጆን ያንግ “Armed groups along sudan’s Eastern frontiees: An over view and analysis”በሚለው ፅሁፋቸው ሁለቱን አገራት በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ ለሚኖሩ ዜጐች አንዳንድ ማስተካከያዎች እስካልተደረጉ ድረስ ግጭቶቹ ተባብሰው ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ያስረዳሉ፡፡ በተለይ በጋምቤላ አካባቢ ያሉ ዜጐች ወደ ድንበር የተጠጉ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ከማዕከላዊ አስተዳደሩ እና ማህበረሰቡ ጋር ያላቸው ቁርኝት የላላ ነው፡፡ ከዚህ ውጭም በተለያዩ አጋጣሚዎች በክልሉ የተቀሰቀሱ ግጭቶችን ተከትሎ የተወሰዱባቸው እርምጃዎች ፊታቸውን
ከማዕከላዊው አስተዳደር እንዲያርቁ አስገድዷቸዋል፡፡ ይህንና ሌሎች መሰል አጋጣሚዎች በጋምቤላ አካባቢ መከሰታቸው ደቡብ ሱዳን በቀጣይ በአገሪቷ ላይ ያላትን ተፅዕኖ ለማስፋት ልትጠቀምበት እንደምትችል መገመት ይቻላል፡፡ ከነዚህ ተጠባቂ ስጋቶች መካከል አንደኛው እንደ ሶማሊያ ሁሉ የግዛት ይገባኛል ጥያቄ የማንሳቷ ሁነት ነው፡፡ አብዛኛው የጋምቤላ ነዋሪ በደቡብ ሱዳን ውስጥ ከሚኖሩ ዜጎች ጋር ተመሳሳይ የሆነ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ያለው ከመሆኑ አንፃር የደቡብ ሱዳን መንግስት በቀጣይ የጋምቤላን መሬት ከራሳቸው ጋር ይቀላቀል ዘንድ ሴራ ሊሸርብ ይችላል፡፡ ለዚህም ሲል በክልሉ
ውስጥ ከሚገኙ ህዝቦች መካከል ‹‹የተገፋው ማህበረሰብ›› በመንግስት ላይ እንዲያምፅ የማድረግ እንቅስቃሴ ውስጥ ሊገባ ይችላል የሚለው ቀዳሚው ሲሆን፤ ሌላኛው ስጋት የኢትዮጵያ መንግስት እንደከዚህ ቀደሙ በአኙዋኮች ላይ ወታደራዊ እርምጃ የሚወስድ ከሆነ ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ ውስጥ በሚኖሩ ዜጐች ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለመከላከል በሚል ድንበር ዘለል ድጋፍና ከለላ ልታደርግ ትችላለች የሚለው ስጋት ነው፡፡ይሄ ክስተትም ቀጣናውን ወዳልተፈለገ ብጥብጥ ይዞት ጭልጥ እንዲል ያደርገዋል፡፡
አዲሲቷን ደቡብ ሱዳን የምንመለከትበት የተለየ መነፅር ያስፈልገናል፡፡ ከመርገምቱ ይልቅ በረከቱን እንድንቋደስ የአገራችን መንግስት ብልጠት የተሞላበት ፖሊሲ ሊቀርፅ ይገባዋል፡፡

የኦሮሞ ፖለቲካ ጉዳይ (ከትናንት እስከ ዛሬ) – ከቡልቻ ደመቅሣ

ከቡልቻ ደመቅሣ የኦሮሞ የፖለቲካ ጉዳይ በየዘመኑ አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት እርምጃ ወደኋላ ሲመሏ ለዘመናት ቆይቷል፡፡ ይህ የሆነው ከአፄ ሚኒሊክ ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ ከዚያ በፊት፣የኢትዮጵያ ነገስታት ኦሮሞን ለማሸነፍ ስላልቻሉ በየጊዜው እየተጋጩ እንደምንም አብረው ይኖሩ ነበር፡፡ ፋዘር አልሜዳ የሚባለው የፖርቱጋል ቄስ በዚህ ጉዳይ በሰፊው ጽፏል፡፡ ነገር ግን አብሮነታቸው እንደ ገዥና ተገዥ አልነበረም፡፡ ከአጼ ልብነድንግል ጀምረው እስከ ንጉስ ሳህለ ስላሤ የነበሩት አፄዎች ሁሉ ኦሮሞን ለማሸነፍ እና ለመግዛት ያላደሩጉት ጥረት አልነበረም፡፡
ኦሮሞንና ሀገሩን አሸንፈው ለማስገበር የቻሉት አፄ ሚኒሊክ ብቻ ነበሩ፡፡ እሳቸውም ኦሮሞን ለማሸነፍ የቻሉት ከኦሮሞዎች ቀደም ብለው ከፈረንጆች የጦር መሳሪያ ስላገኙ ነበር፡፡ መሣሪያ ያገኙበትም ምክንያት ከእሳቸው ቀድሞ የነበሩት አንዳንድ አፄዎች ለአውሮፓ መንግስታት “ኢትዮጵያ ብቻዋን ክርስቲያን ሆና በአፍሪካ ውስጥ የምትኖር ሀገር ነች”ብለው የአውሮፓውያን መንግሥታትን ስለለመኑና ስላስረዱ የጦር መሣሪያ ማግኘት ቻሉ፡፡ በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አፄ ሚኒሊክ ሸዋን በሙሉ ለመቆጣጠር ሲነቃነቁ ደብረብርሃን አጠገብ በምትገኘው አብደላ በምትባል መንደር ውስጥ
ከጎበና ዳጬ ጋር ተገናኙ፡፡ ጎበና ዳጬም በዚያን ጊዜ በኦሮሞ ገዳ ሥርዓት የሉባና የነበዙ አባ ደክር ወዳጅ የነበሩ፡፡ ከአፄ ሚኒሊክ ለጎበና ዳጬ አንድ ነገር ተናገሩ፡፡ “ወደታች ወደደቡብ እንሂድ፡፡ ወደአቢቹ፣ ገላን፣ ጉለሌ፣ አርሲ አብረን እንዝመት፡፡ አንተ የጋላ ንጉስ ትሆናለህ፣ እኔ የኢትዮጵያ ንጉስ እሆናለሁ ተከተለኝ” አሏቸው፡፡ እንደተባባሉትም ወደታች ወደደቡብ መጥተው የኦሮሞን ጎሣዎች መውጋት ጀምሩ፡፡ ጎበናም ራስ ተባሉ፡፡ ነገር ግን አፄ ሚኒሊክ ለጎበና የገቡትን ቃል ሳይጠብቁ ቀሩ፡፡ ጎበናም ብዙ ጊዜ ከተዋጉ በኋላ እየተዳከሙ ሄዱ፡፡ ነገር ግን የሸዋን፣ የወለጋን (በሰላም የገቡ) እና የከፋን
(ከፋም በሰላም ገባ) ኦሮሞዎች ካሸነፉ በኋላ አፄ ሚኒሊክ እራሳቸው ጦርነቱን መምራት ጀመሩ፡፡ ራስ ጎበና በቀየሱት መንገድ ሄደው ሌሎች ያልተያዙትን ሀገሮች ያዙ፡፡ ለምሳሌ ሀረርን፣ ውጋዴንን፣ ሱማሌን፣ ቦረናን ያቀኑት ከዚያ በኋላ ነው፡፡ (እኔ አቀኑ እላለሁ አንዳንድ ሰዎች ግን “ኮሎናይዝ” አደረጉ ነው የሚሉት፡፡ እውነቱን ለታሪክ ተንታኞች እንተዋለን፡፡) ይህ ታሪክ አፈታሪክ ነው፡፡ የታሪክ ምሁራን እንደሚሉት አፈታሪክ የተፃፈ ታሪክ ያህል ዋጋ አለው፡፡ አሁን ልክ አይደለም ብሎ መከራከር ዋጋ ቢስ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ኦሮሞዎች ሁሉ ይህን ያምናሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ የታሪኩን
እርግጠኛነት የሚያረጋግጠው የራስ ጎበና ሕመም ነው፡፡ (በብስጭት እንደሆነ በእርግጠኝነት የሚናገሩ የእሳቸው ተወላጆች አሉ፡፡)
እኔ እንደብዙ ወገኖቼ ጎበናን አላብጠለጥልም ሰው ስራ መስራት አለበት፡፡ ቤተሰቡን የሚደግፈው የሰራ እንደሆነ ነው፡፡አለስራ መኖር አይቻልም፡፡ ስለዚህ ራስ ጎበና ስራ አግኝተው ቢሰሩም የፈለጉት ሳይሆን ቀርቶ ታመው ሞቱ፡፡ ይሄ ማንኛቸውም መሪ የሚያረገው ነገር ነው፡፡ አንዳንዱ አላደርግም ብሎ ይሞታል፡፡ ግን ብዙ ሰው ሞትን አይመርጥም፡፡ አፄ ሚኒሊክ ጎበናንም ባያገኙ ማሸነፋቸው አይቀሬ ነበር፡፡ ምክንያቱም በዚህ ጊዜ ከአውሮፓውያን ብዙ የጦር መሣሪያ አግኝተዋል፡፡
ራስ ጎበና ከሚኒሊክ ጋር ያደረጉት ስምምነት ለጊዜው ለኦሮሞ አንድ እርምጃ ወደፊት የሚሄድ መስሎ ነበር፡፡ ከዚያም በኋላ አፄ ሚኒሊክ ኦሮሞን የገዙበት የባሪያ አገዛዝ ሁለት እርምጃ ወደኋላ እንዲሄዱ አደረጋቸው፡፡ ኦሮሞ ደርግ ላይ ምንም ተስፋ ስላልነበረው የጀነራል ተፈሪ ባንቴ ፕሬዝዳንት መሆን ምንም አልመሰለውም፡፡ ዶክተር ነጋሶ ፕሬዝዳንት ሲሆኑ ለኦሮሞ የተሻለ መስሎ አልታየውም፡፡ ዶክተር ነጋሶም እራሳቸው በስርዓቱ ባለማመን ረግጠው ወጡ፡፡
ከዚያ በኋላ የአፄ ሚኒሊክን የጦር ኃይል መመከት ያልቻለው ኦሮሞ፣ ገባርነትን ለመቀበል ተገደደ፡፡ ሆኖም ግን አፄ ሚኒሊክ ከዚያ በፊት ኦሮሞ ይዞት የነበረውን መሬት ማስለቀቅ ስላልቻሉ ኦሮሞ በአፄ ልብነድንግል ጊዜ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ይዞት የነበረውን መሬት እንደያዘ ቀረ፡፡ እዚህ ላይ እናስታውስ፡፡ የወሎ አሮሞና ትግራይ ውስጥ ያሉት ራያና አዘቦ ኦሮምኛ ቋንቋቸውን እየረሱ አማርኛ ወይም ትግሪኛ መናገር ጀምረዋል፡፡ በአማራ ክልል ውስጥ ያለው ኦሮሞ ዞን ከተፈጠረለት ለምን የራያና አዘቦ ዞን በትግራይ ውስጥ አልተፈጠረም፡፡ ይኼ የሚያሳየው ሕገ መንግስቱ በተፃፈበት ጊዜ (በ1986 ዓ.ም) ህወሓት የነበረውን ፍጹም የበላይነት ነው፡፡ ዛሬ የኦሮሞ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ቢያንስ 35 በመቶ መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ሕዝቡም ወደ ሰላሳ ስድስት ሚሊዮን ይገመታል፡፡ የኦሮሞ መሬት ስፋቱ 387,000 ኪሎ ሜትር ይሆናል፡፡ ማለትም ጀርመንን ያክላል ማለት ነው፡፡ ኢህአዴግ በ1983 ዓ.ም. አዲስ አበባ በገባ ጊዜ ኦነግ አብሮት ስለነበረ ኦሮሞ አንድ እርምጃ ወደፊት እንደሄደ ሊገመት
ይችላል፡፡ ምክንያቱም ኦነግ አስራ ስድስት አመት ከታገለ በኋላ ከህወሓት/ኢህአዴግ ጋር አብሮ ሲመለስ አንድ የፀና ስምምነት ተፈራርሞ የመጣ መስሎ ለኦሮሞዎች ታየ፡፡ ስለዚህ ኦሮሞዎች ለጊዜውም ቢሆን ተረጋጉ፡፡ ነገር ግን ሳይቆይ ኦነግ ወደ ትግል ተመለሰ፡፡ በአገር ውስጥ ያሉ ኦሮሞዎች ኦነግ ፌደራሊዝምን የተቀበለ – መስሎአቸው ስለነበር ካገር በመውጣቱ አዘኑ፡፡ ከዚህ ይልቅ በሀገር ውስጥ ሆኖ ስለሰብዓዊ መብት፣ ስለእኩልነትና፣ ስለዲሞክራሲ መታገል ነበረበት ብዬ አስባለሁ፡፡
ኦነግ ተመልሶ ከአገር ሲወጣ “ኢህአዴግ ውስጥ ገብቼ አባል አልሆንም” የሚለውን ኦሮሞ ሁሉ ‹‹የኦነግ አባል ነህ›› እያሉ በጅምላ ማሰር፣ አንዳንዱን መግደል፣ የእለት ተዕለት ትእይንት ሆነ፡፡ በዚች አጭር ጽሑፍ ውስጥ የሞቱትን፣ የታሰሩትን መቁጠር አይቻልም፡፡ ነገር ግን እኔ የኦፌዴን መሪ በነበርኩበት ጊዜ ከትልልቆቹ ስራዎቼ መካከል ዋናው ስለኦሮሞ መሞት፣መታሰር እና መሰቃየት ለኦሮሚያና ለፌዴራል መንግስታቱ እድፍ ነበር፡፡ እንዲያውም አንድ ጊዜ ለማስመሰል የፌዴራል መንግስቱ፣ ኦፌዴንና ኦህዴድ የጋራ ኮሚቴ አቋቁመው ስለነኚህ ችግሮች ያጥኑና የጥናታቸውን ውጤት ያቅርቡ ተብሎ
አንድ ኮሚቴ ተቋቁሞ ነበር፡፡ መጀመሪያውኑ ከልብ ስላልሆነ ኮሚቴው ቶሎ ፈረሰ፡፡
ኦሮሞ የገዳን ሥርዓት ለመተው የተገደደው በመንግስት እና በዘመኑ የኢኮኖሚ ሥርዓት ለውጦች ምክንያት ነው፡፡ የገዳ ሥርዓት እንዳለ ሥራ ላይ መዋል በአሁኑ ዘመን አይቻልም፡፡ ምክንያቱም በአሁኑ ዘመን ወጣቶች ሁሉ በተወለዱበት ሥፍራ አይቆዩም፡፡ ለስራና ለትምህርት ከተወለዱበት ወጥተው ወደሌላ ስፍራ ይሄዳሉ፡፡ አንዱ ትውልድ ሌላውን ትውልድ በሙሉ ካልተካ የገዳ ሥርዓት አይሰራም፡፡
ብዙ የኦሮሞ ምሁራን የገዳን ሥርዓት የሚወዱበት ምክንያት ሥልጣን ላይ ያለው ትውልድ አዲሱ ትውልድ ለስራ ሲዘጋጅ ቦታውን ለቆ መሄዱ ለዲሞክራሲ ጥሩ አስተዋጽኦ ያደርጋል በማለት ነው፡፡ ለሁሉም በአሁኑ ጊዜ ማንም በተወለደበት ቦታ ለብዙ ጊዜ ቀጥሎ ስለማይኖር የገዳ ሥርዓት ሃሳቡ ሲፀነስ በሰራበት መልኩ አሁን ሊሰራ አይችልም፡፡
የኦሮሞ ጥንታዊ ሀይማኖት ዋቄፈታ ሲሆን፤ ይኼም ብዙ ሰዎች እንደሚሉት ወይም እንደሚመስላቸው ለፍጥረት መስገድ አይደለም፡፡ ወንዝ አጠገብ፣ ታላቅ ተራራ አጠገብ፣ ታላቅ ዛፍ ስር ዋቄፈታ ማድረግ እንደዚህ አይነት ታላቅ ፍጥረትን ለፈጠረው አምላክ መስገድ ነው፡፡ አማኞቹ እንደሚሉትም እግዚአብሔር ራሱን የሚገልፀው በታላላቅ ፍጥረቶች በኩል ነው፡፡ እዚህ ላይ ስለዋቄፈታ ያነሳሁት ባለፈው አስር ቀን ውስጥ ኦሮሞዎች ቢሾፍቱ ሀይቅ አጠገብ የተለመደውን ኢሬቻ ለማድረግ የተሰበሰበውን ህዝብ (ሶስት ሚሊየን ህዝብ ነበር ተብሏል) ፖሊስ በሀይል በህዝቡ መሃከል ለብሶ የለበሳችሁት ልብስ የኦነግ ባንዲራ ነው በማለት በመደብደብ፣ በመርገጥ እና ልብሳቸውን በማስወለቅ ጭምር ከባድ ጉዳት አደረሰባቸው፡፡ ይሄ አድራጎት በኦሮሞዎች ዘንድ እንደ ታላቅ ሀጢያት እና እግዚአብሔርን እንደ መዳፈር መስሎ ታየ፡፡ ይህ ሥርዓት በጠባዩ ለእነርሱ ሀይማኖታዊ ነው፡፡
የህዝብን ድምፅ የሚሻ፣ ሰላምን የሚፈልግ እና ትብብርን ከህዝብ የሚጠብቅ መንግስት እንዲህ አይነት ፀረ-ባህልና ፀረ-ህዝብ ወንጀል አይፈፅምም፡፡ ለጊዜው ለዚህ አድራጎት የምናየው ምላሽ ላይኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን ኦሮሞ ይሄንን አድራጎት ይረሳል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ ማንም ህዝብ ይህ ቢደርስበት ዝም የሚል አይመስለኝም፡፡ የፌደራሊዝም ፅንሰ-ሀሳብ የተዋወቀው ይህን መሰሉን በደል ለማስቀረት ነበር፡፡
ይህ ሁኔታ በፌዴራሊዝም ስርዓት የሚያምኑትን የኦሮሞ ምሁራን አቋም የሚፈታተን ነው፡፡ ምክንያቱም ኦሮሞ ከሌላው ህዝብ ሁሉ ተለይቶ እንደባእድና ጠላት እየታየ መኖር ቢመረውም ከቀሪዎቹ የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር ተስማምቶ በፍቅር መኖር ይፈልጋል፡፡ የኦሮሞ ጥንታዊ ሃይማኖት ዋቄፈታ ነበር፡፡ አሁንም በዋቄፈታ የሚያምኑ ኦሮሞዎች ቁጥራቸው በጣም ብዙ ነው፡፡ ዋቄፈታ ከክርስትናም ሆነ ከእስልምና የተለየ የኦሮሞ የጥንት እምነት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ልዩነቶች ቢኖሩም ብዙዎቻችን የኢትዮጵያ አካል ሆነን በፌዴራሊዝም ሥርዓት እንኖራለን ብለን በቆራጥነት ተነስተናል፡፡ እንዲህ የሚለው ወገን ግን ዛሬ ድምፁ እየተዳከመ ሄዷል፡፡ ህዝብ መናቅ እንደ ቀላል ነገር ሆኖ እየታየ ነው፡፡ ቢሾፍቱ ላይ ለኢሬቻ የመጡትን አማኞች የኦነግን ባንዲራ ለብሳችኋል በማለት ደብድበው ልብሳቸውን የነጠቋቸው ሰዎች ራቁታቸውን ከስፍራው ሲወጡ ታይተዋል፡፡ የኢሬቻን በዓል መንግስት ለምን እንደፈራው አይታወቅም፡፡ ከዚህ በፊት ለዘመናት በየዓመቱ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ አሁን የመንግስት የፀጥታ ሰራተኞች አንድ ቡድን ያደመው ወይም ያዘጋጀው ተንኮል ኖሮ የደረሱበት ነገር ኖሮ ይሆን? አናውቅም፡፡ ጨርሶ ኢሬቻን ለማጉላት አይመስለኝም፡፡ ሌላ የኦሮሞ ቅሬታ አለ፡፡ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ የመንግስት ብወዛ ተደርጎ ነበር፡፡ ለጊዜውም ቢሆን የመንግስትን አቅጣጫና ፕላን የሚያመላክቱ ብወዛዎች ተፈፅመዋል፡፡ እዚህ ውስጥ ኦሮሞዎች ምንም ሚና አለመጫወታቸው ብዙ ሰዎችን አስገርሟል፡፡ ከሃገሪቷ አጠቃላይ ህዝብ 35 በመቶ ከመሆናቸው ባለፈ ምድራቸው እጅግ በጣም ሰፊና ሀብታም ሆኖ ሳለ፤ ዛሬ ለኦሮሞ ህዝብ ዝቅ ያለ ግምት እየተሰጠው ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ለምንድን ነው? የጥያቄው መልስ
ያለው ኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ነው፡፡ ኦሮሞ ሙሉ የዴሞክራሲ መብቱን የሚጠይቅበት ጊዜ ቅርብ ነው፡፡ ኦሮሞንና የደቡብ ህዝቦችን ማጥቃትና መናቅ በምንም ዓይነት መንገድ ፍትሀዊ አይሆንም፡፡ የሚመጣው የኦሮሞ ትውልድ እንደዛሬው ትውልድ ዓይናፋርና ዝምተኛ አይሆንም፡፡
ፓርላማ ውስጥ እኔና ጓደኞቼ ለምንድን ነው ኦሮሞ የሚጠመደው? ለምንድን ነው ኦሮሞ እንደ ጠላትት የሚታየው? ብለን ስንጠይቅ መልስ አላገኘንም፡፡ ነገር ግን በሽብርተኝነት ህጉ መሠረት ኦነግን ትደግፋላችሁ በማለት በፍፁም ከኦነግ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ሰዎች በብዛት ታስረው ዛሬ እስር ቤት ውስጥ ይማቅቃሉ፡፡ ፍርድ ቤት የእነኚህን ሰዎች ጥፋት በጥልቀት ቢመረምር አንድም የሚያስከስስ ስራ አልሰሩም፡፡ አንዳንዶቹ የፖለቲካ ነፃነት ያለ መስሏቸው ህዝብን ለማደራጀት እንዲሁም የፖለቲካና የኢኮኖሚ ትምህርት ለመስጠት ሲሞክሩ ያለአንዳች ጥያቄ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው ብዙ ቀናት ከማቀቁ በኋላ ፍርድ ቤት ይቀርቡና ለረጅም ጊዜ እስር ቤት እንዲቆዩ ይደረጋል፡፡ በቀለ ገርባ የሚባል የኦፌዴን ም/ፕሬዝዳንት እነሆ ያለአንዳች ጥፋት ዛሬ ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ይማቅቃል፡፡ የተያዘው ስለ ሰብዓዊ መብት ኢትዮጵያን ሲጎበኙ የነበሩ ፈረንጆች ስለአነጋገሩት ነው፡፡ በሕገ መንግሥቱ የተፃፈው ታምኖበት ነው ወይንስ አንዳንድ ገር ሰዎችን ለማታለል ነው፡፡ ዜጋ የሚያዝበት ሁኔታ፣ ተይዞ ፖሊስ ጣቢያ የሚቆይበት ጊዜ፣ ፍርድ ቤት የሚቀርብበት ጊዜ፣ ፍርድ ቤትም ጉዳዩን በቀጠሮ የሚያቆይበት ጊዜ ሁሉ በሕገ መንግሥትና በሲቪልና ክሪሚናል ፕሮሲጀር ኮድ ተጽፏል፡፡ እነኚህ ሕጎች ሁሉ በየቀኑ እየተጣሉ ነው፤ በትንሹ ሳይሆን በብዛት ነው፡፡ ይህን ሁሉ አቶ መለስ ከዕረፍታቸው በፊት ያውቁ ነበር፡፡ እኔ ራሴ ከእኔ ቢሮ ስለሚሞቱት ሰዎች፣ ስለሚያዙ ሰዎች፣ ስለሚታሰሩ ሰዎች፣ ብዙ
ጊዜ ለክልሉ ፕሬዚዳንት እና ለጠቅላይ ሚ/ር ቢሮ ጽፌአለሁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬም በእሳቸው ቦታ የተተኩ ሰዎች በኦሮሞ ላይ የሚደርሰውን ግፍ ያውቃሉ፡፡ ነገር ግን የሕዝብ መብት እንዳይደፈር አንድ ወገን ለይቶ ማጥቃት ተገቢ አለመሆኑን የወጣ አዲስ ትዕዛዝ አላየንም፡፡ ለወደፊትም ላናይ ነው?
ማስታወሻ
ከዚህ አጭር ጽሁፍ ጋር አያይዤ ለአንባቢያን የማሳስበው ነገር አለ፡፡ አንዳንድ ወዳጆቼ አንድ ጥያቄ ሁልጊዜ ይጠይቁኛል፡፡ “ለምን ሁልጊዜ ስለ ኦሮሞ ብቻ ትጽፋለህ?” መልሶቼ ባያጠግቡም ሁልጊዜ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ “እኔ ደህና አድርጌ የማውቀው ስለ ኦሮሞዎች ስለሆነ ነው፡፡ የኢህአዴግ መንግስትም ኦሮሞን ለይቶ ስለሚያጠቃ ነው፡፡ ሌላውንም ህዝብ አጥቅቷል፡፡ ለምሳሌ ሲዳማና ጋምቤላ በጣም ተመቷል፡፡ ስለነሱ በዝርዝር የሚያውቁት መጻፍ ይገባቸዋል፡፡ እኔ ስለ ኦሮሞ ስጽፍ ኦሮሞ የኢትዮጵያ አካል አይደለችም በማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ህግና ሥርዓት ባለበት ሀገር ማንም
ቡድን፣ ብሔር ወይም ሌላ ስብስብ መጠቃት የለበትም፡፡  አመለካከት እና አያያዝ ለመከላከል ነበር፡፡ እኔ ለኦሮሞ የምፅፍበት ሌላ ምክንያት የለኝም፡፡ ግን ሌላም የኢትዮጵያ ጉዳይ ደጋግሜ እጽፋለሁ፡፡

ቅንጫቢ ፩ የሽብራዊ ያገዛዝ ታሪክ (ካልታተመ መፅሃፍ የተወሰደ በግደይ ገ/ኪዳን እና ተክሉ አስኳሉ)

የሽብራዊ ያገዛዝ ታሪክ

ሽብር ምንድ ነው? መንበረ ስልጣን የተቆጣጠረ ክፍል ሽብር ሊፈፅም ይችላል? በየትኛውም ስሌት ለበጎም ተባለ ለሌላ ሽብርን የሚደግፍ አይኖርም፡፡ አሸባሪዎች በምስልም ሆነ በታማኝ ምስክር ተረጋግጦባቸው እኩይ ተግባራቸው ቢጋለጥ የሚያስከፋው አይኖርም፡፡ የዛሬውን ውስብስብ ያሸባሪዎች ተግባር ለመፈተሽ በታሪክ ገዢዎች ዜጎቻቸው ላይ የፈፀሙትን ሽብር ማስታወስ ይኖርብናል፡፡ አሸባሪዎች ንፁሃን ናቸው ለማለት ሳይሆን እንደ አብዮታውያን መሳርያ ሁነዋል ወይ የሚለውን ለመመርመር ይረዳናል፡፡
 “ሰዎች አብዛኞቹ ማሰብ አይችሉም፣ የቀሩት ማሰብ አይፈልጉም፣ የሚያስቡት ከዚ የቀሩት እጅግ ጥቂቶቹ በደንብ አያስቡም፡፡ እጅግ በጣም ጥቂት የሆኑት በቋሚነት፣ በትክክል፣ በስልታዊ መንገድና እራሳቸውን ሳያታልሉ የሚያስቡት -በረዥም ግዜ ልኬት- እነዚህ ናቸው ፋይዳ የሚኖራቸው፡፡”
ሮበርት ኸይንለይን (Robert Heinlein) – Paul J. Watson: Order Out of Chaos ላይ፡፡
ፖል ኮሊንስ (Paul David Collins) መጣጥፎቹን ካልሆነ መፃህፍቱን ማግኘት የተሳነን ተመራማሪ The Hidden Face of Terrorism: The Dark Side of Social Engineering, From Antiquity to September 11 ከተሰኘው መፅሃፉ በተቀነጨበው ፅሁፍ ላይ በዚህ ባለንበት ዘመናዊ ዓለም የሚጎረብጥ እውነት ሲኖር በፈጠራ ይቀየራሉ ይላል፡፡ ከነዚህ ፈጠራዎች አንዱ ሽብር ማለት ያኮረፉ ቡድኖች ተገንጥለው የፋይናንስና ሌላ አቅማቸውን በራሳቸው በማሟላት የሚፈፅሙት ዘግናኝ ተግባር ነው የሚለው ነው፡፡ የሽብር የበላይ ጠባቂዎች ግን እንደ ጋርዮሻውያን ስፖንሰሮች ሌሎች ለማመን የሚከብዱ አካሎች ናቸው፡፡ የሽብር እውነተኛ ምንነትን ለመረዳት በታሪክ የሚከሰቱት ዓበይት ክንውኖች ያጋጣሚ ናቸው ከሚለው የኦፊሻል አተራረክ መውጣት ያስፈልጋል፡፡ የሽብር የመጀመርያው ወሳኝ ገፅታው በዓብዩ የሚፈፀመው የመንግስት ሽብር ነው፡፡ ሁለተኛ እንዲህ አይነቱ ሽብር መንግስት የነደፈውን የማህበረ-ፖለቲካዊ ፕሮጅክት ለማስፈፀም አብዝሃውን በማሸበር የጥቂቶችን ጥቅም ማስጠበቂያ አካል ነው፡፡ (Father Ignacio Martín-Baró “The Psychological Consequences of Political Terror” የላይኛው መፅሃፍ ላይ የተጠቀሰ፡፡)
“Fake Terror: The Road to Dictatorship” በሚለው መፅሃፉ ሚካኤል ሪቬሮ (Michael Rivero) ፡ “[ሽብር]በመፅሃፉ ያለ ጥንታዊው ዘዴ ነው፣ እስከ ሮም ግዜ ድረስ የሚመዘዝ፡ የሚያስፈልጉህን ጠላቶች መፍጠር፡፡” ነው ይለዋል ሽብርን፡፡ (የላይኛው መፅሃፍ) በዚህ ክፍል ይሄን መንግስታት ስፖንሰር የሚያደርጉትን ሽብር ታሪክ እንዳስሳለን፡፡ ይህን የምናደርገው ታሪክ እውነት መሆኑ ያረጋገጠው መንግታቱ ያመኑበትና ቅጥረኛ ታሪክ ፀሃፊዎቹ የፃፉትን ዋቢ በማድረግ ከተሰሩ ስራዎች ነው፡፡ መንግስት ያላመነበት የሽብር ጥቃት የመስከረም 11፣ 2001 ጥቃት ነው፣ ይህን ደሞ በሚቀጥሉ መእራፎች ማስተባበያቸው ደካማ ከመሆኑ የተነሳ ሳይንስ ተጠቅመን ቅጥፈቱን እናስነብባቹሃለን፡፡
ሮም ሲቃጠል ኒሮ ሲጫወት ነበር – Nero Fiddled While Rome Burned
“ፊድልድ” የሚለው የእንግሊዘኛ ቃል ቫዮሊን መጫወት ወይም ማጭበርበር ተብሎ እንዳገባቡ ይፈታል የሮማ ከተማ በእሳት በተያያዘችበት ግዜ እብዱ ንጉሷ ኒሮ ቫዮሊን ሲጫወት ነበር ይባላል፣ ለእንሊዘኛ ተናጋሪው የተረፈው አባባልም ሁለት ትርጓሜ አለው፡ ሮም ስትቃጠል ኒሮ ቫዮሊን ሲጫወት አልያም ሲያጭበረብር ነበር የሚል ነው፡፡ የፖል ዋትሰን (Paul J. Watson): Order Out of Chaosየሚለው መፅሃፍ ታሪኩን ይነግረናል፡፡
ኒሮ ከ54 እስከ 68 ዓ.ም የገዛ ንጉስ ሲሆን አማካሪዎቹ በሞት ሲለዩት የፀባይ ለውጥ አመጣ፡ የሞት ቅጣት በማስቀረት፣ ግብር በመቀነስ፣ ባሮች ጌቶቻቸውን እንዲከሱ በመፍቀድ የሚታወቀው ተወዳጅ ንጉስ ተቀየረ፡፡ ብቻውን ስልጣን ፍፁም መቆጣጠሩ ፍፁም ይመርዘው ጀመር፡፡ ሮም ከመቃጠሏ በፊት የጀመረው እብደቱ በክህደት የተጠረጠረ በሞት እንዲቀጣ የሚያዝ ህግ አስተላልፎም ነበር፣ በዚህም ፖለቲካዊ ተፎካካሪዎቹን፣ ሚስቱንና እናቱን ሳይቀሩ አስወግዷቸዋል፡፡ ሲያበሳጩት የነበሩት ክርስትያኖችን የሚያገኝበትን ሰበብ ሲፈልግም ነበር፡፡ ክርስትያኖቹ ግዛቲቱ የምትከተለውን የበሰበሰ ተግባራትና የባእድ አምልኮን ሲነቅፉ ነበር፡፡ የታሪክ ምሁራን እሳት አደጋው በሚጀምርበት ግዜ ኒሮ ሮማ ነበር ወይስ አልነበረም የሚለውን ይከራከሩበታል፣ በርግጠኝነት ግን እሳቱ ከፍተኛ ደረጃ በደረሰበት ግዜ ሮማ ውስጥ ነበር፡፡ ህዝቡ ሲሞት ቅኔ ሲፅፍና ሲዘፍን ነበር የሚያያቸው፡፡ አባባሉም ከዚህ ነው የመጣው፡፡
ኒሮ ሲጫወት ዘቦቹን ጎዳናዎቹን እንዲጠብቁና ቃጠሎውን ለመቆጣጠር የሚደረግ ሙከራ እንዲያጨናግፉ ትእዛዝ ሰጥቷቸው ነበር፡፡ ታዘን ነው በሚሉ ሰዎች እሳት የሚያዛምቱ ችቦዎች ቃጠሎው ላይ ሲጨምሩ ታይተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት እሳቱን ያስጀመረው ኒሮ እራሱ ነው የሚል ጭምጭምታ ሊሰማ ችሏል፡፡ በትክክል ያስጀምረው ወይም እንዲባባስ ይፍቀድ ሊያከራክር ይችላል፣ ውጤቶቹ ግን አያከራክሩም፡፡ ኒሮ ለእሳቱ ወድያውኑ ክርስትያኖችን አወገዘ፡፡ ብቸኛ ማስረጃው አንዳንድ ክርስትያኖች ሌሎች ክርስትያኖች ላይ መስክረዋል የሚለው ነው፡፡ ይህ ደሞ እንዲህ እንዲሉ ታስረው ከተሰቃዩ በውኋላ የመጣ ነው፡፡ በከተማው የድሆች መኖርያ አካባቢ እሳቱ እንደመጀመሩ በዚሁ አካባቢ የሚኖሩትን ክርስትያኖቹን መጠርጠር መሰረተ-እውነት (ሎጂክ) የተከተለ አይደለም፡፡ ዓላማ ከነበራቸው የኒሮን ቤተመንግስትን እንጂ የራሳቸውን መኖርያ ለምን ያቃጥላሉ? እርሱ ግን የሚጠላውን የተዘበራረቀውን ቦታ አጥፍቶ እንደገና እንደልቡ ምኞት መገንባት ይፈልግ ነበር፡፡ ቃጠሎ እንዳበቃ ከተማዋ እንደአዲስ ንድፍ ወቶላት መገንባት ጀመረች፣ ለኒሮ ክብር ከሚገቡ አዳዲስ ቤተመንግስቶች ጋር፡፡ ማምለጫ የተደረጉት ክርስትያኖች ግን እጅ እግራቸው ለሰርከስ (ለህዝብ መዝናኛ) እየታዩ ባንበሶች ተቦጫጭቀው የሰው ችቦ ሁነው ነበር፡፡ ከቃጠሎ ኒሮ ሁለት ነገሮችን አትርፏል፡፡ ከተማዋን ዳግም ያነፃት ሲሆን ለስልጣኑ ያሰጋውን እንቅስቃሴንም ወግቷል፡፡ ላጭር ግዜ መንበረ ስልጣኑን ቢያጠናክርም በረዥም ግዜ ግን ከፈጣሪ በቀል አላመለጠም፣ የደረሰባቸው ግፍ እንደነ ጴጥሮስ እና ጳውሎስን ወደ ሰማእትነት አስቀይሯቸዋል፡፡ የሮም ሰዎች ሃዘኔታ ይሰማቸው ጀመር፣ የኒሮ ዘመንም በ68 ዓ.ም እራሱን ካጠፋ በውኋላ አበቃለት፡፡
ዲዮክሊትያን – Diocletian
ዲዮክሊትያን በ284 ዓ.ም ነበር ስልጣን የያዘው፡፡ የወታደሮች ጀነራልም የነበር ሲሆን ጨቋን አያያዝ ይጠቀም ነበር ይለናል የፖል ዋትሰን (Paul J. Watson): Order Out of Chaos የሚለው መፅሃፍ፡፡ መንግስቱንም ሲያካሂድ የነበረው አንድ ጀነራል ወታደሮቹን እንደሚይዛቸው አድርጎ ነበር፡፡ ለግዛቲቱ (ኢምፓየር) ስርአት መምጣት የሚችለው የግለሰባዊ ነፃነት ክፉኛ በቁጥጥር ስር ከዋለ ነው ብሎ ያምን ነበር፡፡ በ301 ዓ.ም ከጀርመኖችና ከሳሳኒዶች ጋር የነበረው ውጊያ ሲገባደድ ለጨቋኝ አገዛዙ ሰበብም አብሮ ተቋጨበት፡፡ ጨቋኝ አገዛዙን ለማስቀጠል አዲስ ጠላት አስፈለገው፡፡ በግዜውም ኢኮኖሚው ቀውስ ውስጥ ገብቷል በማለት የተጋነነ ግብር ጫነ፡፡ ህዝቡም ማንገራገር ጀመረ፡፡ እንደ-ባርያ የሆኑት ዜጎቹን ድጋፍ ለማግኘት አዲስ ጠላት መገኘት ነበረት፡፡ በመጀመርያ በተሳካ መልኩ ማኒካውያንን ካሳደደ በውኋላ፣ አውራ ጣቱን ቁልቁል ዘቅዝቆ ፊቱን ወደ ክርስትያኖች አዞረ፡፡ ይህ የሆነው ላለፉት አስራ አምስት አመታት ከናካቴው ረስቷቸው/ትቷቸው ከነበር በኋላ ነው፡፡ ላለፉት 50 አመታት የክርስትያኖች ቁጥር በእጥፍ በመጨመር ከግዛቲቱ አስር መቶኛ ደርሰው ነበር፡፡ ሁለት ንጉሶች ተቀይረው ነበር፡ የሰሜን ምስራቅ ሚሰፖታምያ የምትገኘው የኦርሶኢኔ (Osroene) ንጉስና የአርመንያ ንጉስ፡፡ በሮም ወታደር ውስጥ ሲያገለግሉም ነበር፣ በአካባቢያዊ አስተዳዳሪዎች ስርም ሰራተኞች ነበሩ፣ በንጉሳዊው ሰራተኞች ዝቅተኛ ቦታ ላይም ነበሩ፡፡ ዲዮክሊቲያን ሰበብ ይታየው ጀመር፡፡
በ302 ዓ.ም በሶርያ አንቶይችን ለስራ በሚጎበኝበት ወቅት እንደልማዱ የጣኦት አምልኮው በሚጠይቀው መሰረት መስዋእትነት ሲያካሂዱ ነበር፡፡ ክርስትያኖቹም ዘወትር እንደሚያደርጉት ክፉ ተፅኖን ለማስራቅ እያማተቡ እንዲህ አይነት የጣኦት ተግባር መቃወም ጀመሩ፡ ከነዚህ ክርስትያኖች ሮማነስ የተባለ የሚታወቀው ነበረበት፡፡ ዲዮክሊቲያን ተበሳጨ፡፡ የተሰዋውን እንሰሳ ሰውነት አካሎች እያየ የሚተረጉመው በክርስትያኖቹ ተፅእኖ ምክንያት ሊታየው እንዳልቻለ ይናገራል፡፡ ዲዮክሊቲያን በመቆጣት በዘውዱ አካባቢ ያሉ ሁሉም መስዋእትነት ስርአት እንዲፈፅሙ ያዛል፡፡ በዚህም ትእዛዝ ማሳደዱን ለመጀመር ሰበብ አገኘ፡፡ ሮማነስ ምላሱ ተቆርጦ ለአንድ አመት በወህኒ ማቀቀ፡፡ በግዜውም ዲዮክሊቲያን ክርስትያነኖች ለመንግስት አማልክት መስዋእትነት እንዲፈፅሙ አልያ ቅጣት እንዲቀበሉ አዘዘ፡፡ የንጉሱ ምክትልም ጋሌሪየስ(Galerius) ቤተመንግስት ቢቃጠል ዘመቻው እንደሚጧጧፍለት ይመክረዋል፣ በ16 ቀናት ውስጥ እንዳጋጣሚ ሁለቴ ኒቆመድያ የሚገኘው ቤተመንግስቱ ቃጠሎ ደረሰበት፡፡ ወድያው ክርስትያኖቹ ተወቀሱ፡፡ ክርስትያኖች መሰባሰብ ተከለከሉ፡፡ መፅሀፍ ቅዱስ ተሰብስቦ ተቃጠለ፡፡ የክርስትያኖቹን ጥፋተኝነት ተታሎ ያመነ ህዝብ በሚገፋፋቸው አራዊቶች ተበሉ፡፡ ሌሎቹ ታስረው አንድ የጣኦት መስዋእትነት ስነስርአት ከፈፀሙ ትለቀቃላችሁ ተባሉ፡፡ አብዛኞቹ አልተቀበሉትም፣ ዲዮክሊቲያን ክርስትያኖቹን ለመከፋፈል ያላደረጉትን መስዋእትነት አደረጉ የሚል ምልክት ያደርግባቸው ጀመር፡፡ ይህ እስከ 305 ዓ.ም ድረስ ቀጠለ፣ በዚህን ግዜ ክርስቲያኖችን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት በማይቻል መልኩ በግዛቲቱ ተስፋፍተው ነበር፡፡ በ305 ዓ.ም አምባገነኑ ታሞ ሞተ፡፡ ምክትሉ ጋሌሪየስ ከምእራቡ ግዛት ምክትል ንጉስ ከነበረው ኮንስታንተይስ ጋር በመሆን መግዛት ጀመረ፡፡ በ306 ዓ.ም ኮንስታትየስ በጦር አውድማ ሞተ፣ ልጁም ኮንስታንታይን ተካው፡፡  በዲዮክሊቲያን የተጨፈጨፉት በሺዎች የሚቆጠሩ ክርስትያኖች በከንቱ አልሞቱም፡፡ ኮንስታንታይን የመጀመርያው ክርስትያን ንጉስ በመሆን ዓለምን ቀየረ፡፡
የባሩዱ ሴራ (Gunpowder Plot)
በእንግሊዛውያን ቀን መቁጠርያ ላይ እስከዛሬ ድረስ የጋይ ፋውከስ ቀን (Guy Fawkes’ Day) ተብሎ የሚታሰበው ህዳር 5፣1605 ላይ የተመዘገበው ለፖለቲካዊ ትርፍ የተቀነባበረው የሽብር ውሎን እናገኛለን፡፡ ዌብስተር ታርፕለይ /Webster Tarplay፡ 9/11 Synthetic Terror Made in USA በሚለው መፅሃፉ ታሪኩን ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ንጉስ የነበረው ቀዳማዊ ጀምስ ስትዋርት በስብእናው ስኮትላንድንና ኢንግላድን ያዋሃደ ፕሮቴስታንት ነበር፣ ቁንጮ የካቶሊክ ሃይል ከሆነችው ስፔን ጋር ስምምነት የሚያወርድበትን መንገድ ሲያፈላልግ ነበር፡፡ እንግሊዝ ውስጥ ካሉ ካቶሊኮች ጋርም የመቻቻል እርምጃዎችን ሲወስድ ነበር፣ በሰሜን የነበሩት ባላባቶች በግዜው ለሮማ ታማኝ ነበሩ፡፡ ለግላቸው ጥቅም እንደሚያገኙ ተስፋ ያደረጉ የቬኔሽያ ቁንጮዎች የላኳቸው ሰላዮች ጄምስን ከስፔን ጋር ሊያጋጩ መንቀሳቀስ ጀመሩ፡፡ ለነሱም ካቶሊኮች መንግስት ቢያሳድዳቸው እንደሚጠቀሙበት አሰሉ፡፡ ከነዚህ ጦር ናፋቂዎች ዋናው በዘውዳዊው ገዢ ስር ቻንስለር (ጠ/ሚኒስትር) የሆነው የሳሊስበሬ መኳንንት የነበረው ሎርድ ሮበርት ሴሲል (Lord Robert Cecil) ነው፡፡ ይህ ሰው እቅዶቹ ንጉሱ እንዲቀበል የተጠቀመበት ዘዴ ሽብር ነበር፡፡ ራሱን ከትእይንቱ በስተጀርባ በመደበቅ በህቡእ ካቶሊኮችን መቀስቀስ ጀመረ፣ ከነዚህ ዋናው ሎርድ ቶማስ ፐርሲን (Thomas Percy) ነበር የተንኮል ቀለበቱ ውስጥ የከተተው፡፡ ይህን ከፍተኛ የካቶሊክ ቤተሰብ በመጠቀም ፅንፈኛና ጀብደኛ የሆኑ ገራገር ካቶሊኮችን በተዘዋዋሪ በማሰባሰብ የሽብር ቡድን መጠንሰስ ጀመረ፡፡ ከነዚህ ሞኞች አንዱ ጋይ ፋውከስ ነው፡፡ ቶማስ ፐርሲ አክራሪ ካቶሊክ ነው ቢባልም እውነቱ ግን ሁለት ሚስቶች የነበሩት ሰው ነው፡፡
እኚህ ፅንፈኛ ካቶሊኮች ፓርላማው አካባቢ ካለ ቤት ምድር ለምድር በመቆፈር ከተከራዩት የፓርላማው ምድር ቤት በኩል በመውጣት ምድርቤቱን በተቀጣጣይ ባሩድ (ፈንጅ) በመሙላት ንጉሱ ህዳር ላይ ምክር ቤቱን ለማስጀመር በሚመጣበትና የባላባቶቹና የታችኛው ም/ቤቶች በሚሰባሰቡበት ወቅት ማፈንዳት የሚል ነበር፡፡ ሆኖም ጋይ ፋውከስ ወንጀሉን በቀጠሮው መሰረት እንደነገ ሊፈፅም ማታ ላይ ወደ ምድርቤቱ ሲገባ በቁጥጥር ስር ውሎ ከሸፈ፡፡ ፋውከስና ቡድኑ ተሰቃይተው በስቅላት ተገደሉ፣ ሌሎች የካቶሊክ ቀሳውስትም ሰለባ ሆኑ፡፡ ጄምስ ካቶሊኮችን መቻቻል የሚለውን እቅዱን ተወው፣ በመቀጠልም ከስፔንና ፖርቱጋል ግዛቶች ጋር ድፍን ክፍለ ዘመን የፈጀውን ጦርነት እንግሊዝ ጀመረች፣ ከዚህም የብሪታንያ ግዛት (ኢምፓየር) ውልደቱን አገኘ፡፡ የጋይ ፋውከስ ቀን “የእንቢ ለጳጳሱ” /“no popery”  እና ለስፔን ጥላቻ የሚታስብበት በዓል ሆነ፡፡
ይን የባሩዱን ሴራ በተመለከተ የሱሳዊው (ጀስዊት-የካቶሊክ ቀሳውስት ህቡእ ማህበር) የሆነው ጌራርድ እንደሚከተለው ብሎታል፡
“በግዜው የነበረው አስተዳደር (የሴሲል) ለዓላማው ሲል ሴረኞቹ እቅዳቸውን እንዲፈፅሙ የሚያነሳሳበትን መንገድ አግኝቷል ወይም ቢያንስ ከጅምሩ ጀምሮ የሚደረገውን እያወቁ ለራሳቸው ጥቅም የሚያገኙበት ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ ሴራውን ሲንከባከቡና ሲጠብቁት ነበር፡፡ ምንም እንኳ ትክክለኛ ባህርያቱን ለመረዳት የሚከብደን ቢሆንም ሴረኞቹ ወይም አብዛኞቹ ታላቅ ጉዳት ለማድረስ ብለው ከልብ ይሰሩ የነበሩ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም፤ ሆኖም ግን ከነሱ የረቀቁ ሴረኞች ባዘጋጁት ጨዋታ የተታለሉ ተሳታፊዎች መሆናቸው ቢረጋገጥ’ኳ ከጥፋተኝነት አይፀዱም፡፡” Gerard, John, S.J. What Was the Gunpowder Plot? The Traditional Story Tested by Original Evidence
ይህ የዛሬ 406 ዓመት ስለተስተናገደ ሴራ በ1897 የተፃፈ ዓ.ነገርን ደግመው ያንብቡት ዛሬ ላይ እየተሰራ ስላለው የዓለም አቀፋዊው የሽብር ትእይንት የሚለው ብዙ አለው፡፡ ይህ መንግስት አስተዳደር ስፖንሰር ስለሚደረግ ሽብር የተሰጠ ጥሩ ፍቺ ነው፡፡
እዚህ ላይ መጨመር ያለበት ቀዳማዊ ጄምስ ስለሴራው አስቀድሞ የሚያውቀው ነገር እንዳልነበረ ነው፡፡ ሴራው ያነጣጠረው ጄምስ ላይ ነበር፤ በአንድ በተፈለገ የፖሊሲ አቅጣጫ እንዲሄድ ነው ያደረጉት፡፡ ከድርጊቱ በውኋላ ንጉሱ የሴሲል እጅ ምን ያህል እንደነበረበት የተረዳ ይመስላል፡፡
የኦተስ የፈጠራ ሴራ
በ17ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ አውራ የካቶሊክ ሃይል ሆና የወጣችው ፈረንሳይ ነበረች፡፡ ዳግም የእንግሊዝ ፓርላማ አሁን በእንግሊዝ ካቶሊክን ዳግም ለማደስ እያሴረች ያለችው ፈረንሳይ መሆኗን መስረጃ እንዳገኘ በአንድ አጭበርባሪ ታይተስ ኦተስ (Titus Oates) የተባለ መስካሪ ተደርጎ ማስረጃ ቀረበ፡፡ እንግሊዝ ዳግም በፀረ ጳጳሱ እንቅስቃሴ ተናጠች ካቶሊኮች ተገደሉ ታሪክ እራሱን እየደገመ ቀጠለ፡፡ በ1678 መጨረሻ ሴራው ተቀባይነት ከማግኘትም በላይ ስለሴራው መኖር የማይቀበል እንደ አገር ከሃዲ ተደርጎ ይቆጠር ነበር፡፡ ይህ የኦተስ ሴራ እየተባለ የሚታወቀው ፈጠራ በእንግሊዝ ውስጥ ሰብአዊ ርህራሄ እንዲጠፋ ያደረገ ፈጠራ ነበር፡፡
የዚህ ታይተስ ኦተስ የተባለ አጭበርባሪ ሰው ፈጠራ ስፖንሰሮች የነበረው አንቶኒ አሽሊ ኩፐር፣ ሎርድ ሻፍትስበሪ፣ የዊግ ፓርቲ መስራች እና CABAL የሚባለው የቁንጮዎች ካቢኔ አባል የነበረው ነው፡፡ CABAL የስማቸው መጀመርያ ሲሆን አርሊግቶን፣ ባኪንግሃም፣ አሽሊ እና ላውደርዴል የነበሩበት ነው፡፡ ፈላስፋው ጆን ሎክ የአሽሊ ፀሃፊ ነበር፡፡ በ1679 ጫጫታው መብረድ ጀመረ፣ ታይተስ ኦተስም ውሸታምና አጭበርባሪ መሆኑ ተደረሰበት፡፡ በዚህን ግዜ ንጉሱ ቻርለስ 2 አሽሊ በክህደት ወንጀል ፍርድቤት እንዲቀርብ አደረገ፡፡ አሽሊ ብይን አምልጦ የሂወት ዘመኑን በጨረሰባት ሆላድ ተሰደደ፡፡
አዶልፍ ሂትለር
የዚህ ሰው ስም በክፉ የሚነሳበትን ያህል ሴራዎቹ ባግባቡ አይገለፁም፡፡ የስኬቱ ሚስጥር ፋይናንስ ያደረጉትን ምእራባውያን ቁንጮዎች በክፍል አንድ አይተነዋል፡፡ ባገር ውስጥ ዲሞክራሲውን ሰርዞ እራሱን ፉረር ማለትም “መሪ” ለማድረግ የተጠቀመበት ስልት ሽብር ነበር፡፡ የሽብሩ ሚስጥርም ለሃገሪቱ ሳይሆን ለሂትለር ታማኝ የሆኑ ፖሊሶች በኸርማን ጎሪንግ (Herman Goering) የፕረሽያ ፖሊስ ሃላፊ ሲሆን በሃገሪቱ ፖሊስ እንዲገቡ መደረጉ ነው፡፡ እነዚህ ፖሊሶች የመንግስት ጠላትን እንዲጠሉ ተደርገው የሚሰለጥኑ ናቸው፡፡
የፖል ዋትሰን (Paul J. Watson): Order Out of Chaos የሚለው መፅሃፍ እንደሚከተለው ያስነብበናል፡፡ በየካቲት 1933 ኸርማን ጎሪንግ፣ ጆሴፍ ጎቤልስ (ፕሮፖጋንዳ ሚኒስቴር) እና ሂትለር የፓርላማውን ህንፃ በእሳት የሚያነዱበት እቅዳቸውን አጠናቀቁ፡፡ ሶስቱም ከሺህ አመታት በፊት የፈፀመውን የኒሮን ተግባር አጥንተው ነበር ማለት ነው፡፡ በዚሁ ወር ማሪነስ ቫን ደር ሉቤ የተባለ የአይምሮ ችግር ያለበት የዳች ተወላጅ የመንግስት ህንፃዎችን የማቃጠል እቅድ አነግቦ በርሊን ውስጥ ሲዘዋወር ነበር፡፡ በሂትለር ቁጥጥር ስር የገባው ፖሊስ ሰውየውን ለማሰር ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ በመጨረሻ ቫን ደር ሉቤ ፓርላማ ጠባቂዎችን አስቶ በመግባት ሸሚዙን አቀጣጥሎ ፓርላማውን ለማጋየት ሞከረ፡፡ የጎሪንግ ክፍል ምድርቤት ከፓርላማው ምድርቤት ጋር የሚያገናኝ የምድርስር መተላለፍያ ተጠቅመው የሂትለር ፖሊሶች (SA) እና መሪያቸው ካርል ኧርነስት (Karl Ernst) ጋዝ በማርከፍከፍ እሳቱን አባብሰው በገቡበት ተመልሰው አመለጡ፡፡ ሂትለርና ፕሮፖጋንዳ ሚኒስትሩ ቶሎ ብለው ለዚህ ተጠያቂው ኮሚኒስቶች እንደሆኑ አሳወቁ፡፡ ሂትለር ለጋዜጠኞች፡ “አሁን በጀርመን ታሪክ የታላቅ ዘመን ጅማሮን እያያቹ ነው፡፡ …ይህ እሳት የመጀመርያው ነው፡፡” ብሏቸው ነበር፡፡ ከዚህ በውኋላ ይህ “የኮሚኒስቶች ሴራ” በመገናኛ ተደጋግሞ ተለፈፈ፡፡ ሂትለርም ከቃጠሎ በፊት የተዘጋጀበትን ሁሉ ፈፀመ፣ ተቃዋሚዎቹን ማሰር ጨምሮ፡፡
ከቃጠሎው በነጋታው ሂትለር ያስቸኳይ ግዜ አዋጅ አስተላለፈ፣ አንቀፅ 48ን ስራ ላይ አዋለ፡- የግለሰባዊ ነፃነቶችን፣ የመናገርና የመፃፍ ነፃነትን፣ የመሰብሰብ ነፃነት፣ የፖስታ፣ የቴሌግራፍና ቴሌፎን ግንኙነት ሚስጥርነትን፣ የቤት ፍተሻ ትእዛዝ፣ የንብረት መውረስና የአጠቃቀም ገደብ ትዛዝ ባንቀፁ እንደተጠቀሰው እስከተፈቀደ ድረስ እንዲጣሱ የሚያውጀውን አንቀፅ ወደትግበራ አስገባው፡፡ እንዲህም ሁኖ ሂትለር አምባገነን ፉረር ለመሆን የሚያስችለውን ሁለት ሶስተኛ ድምፅ ማግኘት አልተቻለውም፡፡ ለዚህም ሂተለር ፕሬዚደንቱ ሂንደንበርግ ከዚህም የባሱ አዋጆችን እንዲፈርም ጫና ይፈጥርበት ጀመር፡፡ በዚህም ስልት ናዚዎችን መውቀስ በህግ የሚያስቀጣ ተግባር በማስደረግና መከላከያ፣ ታዛቢ ፈራጆች (jury) እና የህግ አማካሪ የሌሉበት የወታደራዊ ፍርድ ቤቶች በማቆም የህዝብ ተወካዮችን በፍራቻ በማሸበር መቆጣጠር ጀመረ፡፡ አዲስ ፓርላማ በሚመረጥበት ወቅት ሂትለር የይሁንታ አዋጅን (Enabling Act) በፈጠረው የፍራቻ ምህዳር ስር ሁነው እንዲያፀድቁ በማድረግ ህጋዊ አምባገነን ለመሆን ቻለ፡፡ ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው በዛች እሳት አደጋ ተጀምሮ ነው፡፡
ዌብስተር ታርፕለይ /Webster Tarplay፡ 9/11 Synthetic Terror Made in USA የሚለው መፅሃፍ ሂትለር ሽብርን የተጠቀመበት ህጋዊ አምባገነን ለመሆን ብቻ አይደለም አብዛኛው ሰው ጦርነትን እንደማይደግፍ ስላወቀ ጦርነት የጀመረበት የፖላንድ ወረራውንም ሰበብ ባቀነባበረው ሽብር ውጤት ነበር ይለናል፡፡ በነሐሴ 1939 በጀርመን ማርሚያ ቤት የሚገኙ ወንጀለኞች ቡድን በማሰባሰብ የፖላንድ ወታደሮች መለዮ በማስለበስ ፖላንድ ድንበር አቅራቢያ ከሚገኝ ግሌዊትዝ ሬድዮ ጣብያ ወሰዳቸው፡፡ እነዚህ መከረኞች ወደ ሬድዮ ጣብያው ተወስደው ተረሸኑ፡፡ ሬሳቸውም በሬድዮ ጣብያው ዙርያ ጥቃት ሲሰነዝሩ እንደሞቱ እንዲመስል ተስተካከሎ ተበተነ፡፡ ከዛም የናዚ ሰዎች ሲተላለፍ የነበረውን ፕሮግራም አቋርጠው በፖሊሽ ቋንቋ ፀረ-ጀርመን ንግግር መለፈፍ ጀመሩ፡፡ ይህ ቀፋፊ ተውኔት በፕሮፖጋንዳ ሚኒስትሩ መቶ ግዜ ሲለፈፍ ህዝቡ ከፖላንድ ጋር የማይቀረውን ጦርነት እንዲቀበል አደረገው፡፡ መስከረም 1፣ 1939 ጦርነቱ ጀመረ፡፡
ዘመቻ ኖርዝዉድስ / Operation Northwoods
አሜሪካን ወደአንደኛና ሁለተኛ አለም ጦርነት ለማስገባት የተፈፀሙትን ሴራዎች ክፍል አንድ ላይ ተመልክተናቸዋል፣ እነሱን እያስታወስን እዚህ ደግሞ ሶስተኛ የዓለም ጦርነት ሊያስጀምር ብሎ የነበረውን እቅድ እናስነብባችኋለን፡፡ ይህ ዘመቻ ኖርዝዉድስ የተባለው ሰነድ የወታደራዊ የበላይ መኮንኖች ጥምረት ሊቀመንበር የሆነው ለይማን ሌሚንቲዘር አጋሮቹ መኮንኖች ካስትሮን ከኩባ ለማስወገድ ያለመ የሽብር ዘመቻ እቅድ የያዘ ሰነድ ነው፡፡ የመኮንኖቹ ትክክለኛ ፍላጎት በውል ለማወቅ ግልፅ አይደለም፡፡ ከካስትሮ ጋር ጦር መማዘዝ እንደፈለጉ ግን ግለፅ ነው፡፡ ይህ Body of Secrets ለሚለው መፅሃፉ ሲመረምር ይፋ ያደረገው ጄምስ ባምፎርድ (James Bamford) የተባለ የቀድሞ የኤቢሲ ጋዜጠኛ ነው፡፡ ይህ ሰነድ ጦርነቱን የአሜሪካ ህዝብ እንዲደግፈው አሜሪካ ላይ ሽብር መንዛትን እቅድ የያዘ ነበር፡፡ ዘመቻ ኖርዝዉድስ ያሉት እቅዳቸው በአሜሪካ ጎዳናዎች ላይ ንፁሃን ዜጎች እንዲገደሉ፣ ከኩባ የሚሰደዱ ባህር ላይ እንዲሰምጡ፣ በዋሽንግተን ዲሲ፣ ሚያሚና ሌሎች ቦታዎች የአሜሪካ ሰራዊት ከባድ የሽብር ማእበል እንዲነዛ የሚጠይቅ ሰነድ ነበር፡፡ ሰዎች ባልፈፀሙት የቦምብ ጥቃት እንዲጠየቁ፣ በተራቀቀ ቴክኖሎጂ አውሮፕላኖች እንዲጠለፉ ወይም ሰው አልባ አየሮች (በርቀት መቆጣጠርያ የሚነዱ) በማፈንዳት ኩባ ያደረገችው በማስመሰል ለጦርነት ምክንያት ማግኛ የታቀዱ ነበሩ፡፡ መኮንኖቹ በወታደሮቻቸው ላይም ሞት ከመሸረብ አልተመለሱም፡- ወዳጅ ኩባውያንን የካስትሮ ደንብ ልብስ በማልበስ ጓንታናሞ ቤይ የሚገኘውን የአሜሪካ ባህር ሃይል እንዲያጠቁ ማድረግም እንዳማራጭ ያቀርባል፡፡
ዘመቻ ኖርዝዉድስ ታሪክንም እንደማጣቀሻ በመጠቀም ለሽብር ፈጠራቸው ሃሳብ ያፈልቃሉ፡- በ1898 በሃቫና ወደብ ፍንዳታ የደረሰባት ማይኔ (Maine) የምትባለዋ የአሜሪካ የጦር መርከብ በማስታወስ በጓንታናሞ ቤይ የአሜሪካ መርከብን በማፈንዳት ኩባን መውቀስ እንችላለን ይላሉ፡፡ የማይኔ የጦር መርከብ በ1898 በፍንዳታ መስመጧ አሜሪካ የመጀመርያውን ኢምፐርያሊስት ጦርነት እንድታረግ ያረጋት ታሪክ ያስቀየረ ክስተት ነበር፡፡ ለዚች መርከብ መስመጥ ስፔኖች ቢወቀሱም ከአስርት አመታት በውኋላ በሰመጠችው መርከብ ቅሪት በተደረገው ምርበራ መርከቧ ከውስጥ በተነሳ ፍንዳታ መስመጧ ተረጋግጧል፡፡ በግዜው የነበረው የቁንጮዎች ጋዜጣ ስፔንን ወቅሶ ጦርነት ሲወተውት ነበር፡፡
ወደ ኖርዝዉድስ ስንመለስ በአሜሪካ ያሉ ቁንጮዎች መንግስት ስፖንሰር ያደረገው ሽብርን ከመጠቀም ወደኋላ እንደማይሉ ያሳየ ሰነድ ነው፡፡ ፕሬዚደንት ኬነዲ እቅዱን ውድቅ ባያደርገው ኑሮ መኮንኖቹ በዛ ቀዝቃዛው ጦርነት በጦፈበት የኩባ ሚሳይል ቀውስ ግዜ ሶስተኛ የዓለም ጦርነትን ከማስጀመር የሚገታቸው አይኖርም ነበር፡፡ አሁን የኬነዲ አሟሟት እየተረዳነው ያለን ይመስለናል፡፡
ሃማስና ሊኩድ ፓርቲ
ይህ የማይታመን ግን እውን የሆነ ጥምረት ነው፡፡ እስራኤል ለሃማስ ካደረገችለት ድጋፍ ተጠቃሹ፡ ፅንፈኝነቱ እየታወቀ ለሚያንቀሳቅሳቸው ምግብ ቤቶች፣ ክሊኒኮች፣ ት/ቤቶች፣ መዋእለ ህፃናት እውቅና በመስጠት የፋታህን አማራጭ አስተዳደር ስርአትን እንዲፎካከር ይደረግ ነበር፡፡ እነዚህ “የመንደር ሊጎች” – ‘Village Leagues’ በመባል ይታወቁ ነበር፣ የታወቁ የሃማስ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ አንቀሳቃሽ ሰዎች መሰረታቸውም ነበሩ፡፡ ይህ የተጀመረው ቀድሞ ራሱ አሸባሪ የነበረው የእስራኤል ጠ/ሚኒስቴር ሜናኬም ቤጊን(Menachem Begin) ሼክ አህመድ ያሲን የእስላማዊ ማህበር ለመመስረት የሚጠይቅ ማመልከቻ ሲያስገባ ፈቃድ በሚሰጠው ግዜ ነበር፡፡ ይህ ማህበር ነው በ1987 ወታደራዊ ክንፉን ሃማስ በማለት የከፈተው፡፡ የእስራኤል ፅንፈኛ ቀኝ ዘመሙ ሊኩድ ፓርቲ ፈቃዱን የሰጠው አንድ አይነት አጀንዳ ስለነበራቸው ነው፡ የያሲን አረፋትን ፋታህን ማወክ የሚል፡፡ የመንደር ሊጎቹ ለፍልስጤማውያን ስልጠና ለመስጠት ብቻ ሳይሆን የጠቀሙት በሺዎች የሚቆጠሩ ወሬ አቀባዮችንም አስገኝቷል፡፡ በ1993 የኦስሎ ስምምነት ከተደረገ በኋላም ድጋፉና ፈንዱ ሲሰጠው ነበር፡፡ ተቀናቃኝ ቡድን ማስገባቱ የፍልስጤም ነፃ አውጪ /ፒ.ኤል.ኦ/ ድርጅት እንዲሳሳ አድርጓል፡፡ በውኋላ ጠ/ሚ የሆነው ኤርያል ሻሮን የዚህ ፖሊሲ ዋና አስፈፃሚ ነበር፡፡ በ1994 የአጥፍቶ ማጥፋቱ ጥቃት ማእበል ከጀመረ በውኋላ እስራኤል ከፒ.ኤል.ኦ ጋር በማገናኘት ስሙን ታጎድፍ ነበር፡፡ ወግ አጥባቂው ሊኩድ ፓርቲም ከጨቋኝ ፖሊሲዎቹ ጋር ተቀባይነት እንዲኖረው ያስችላል፣ ባሸባሪ ፍልስጤማውያን ላይ አፀፋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ቃል በመግባት፡፡ በዌስት ባንክ የሚፈጠረው ግርግርና ስርአት አልበኝነት ለሊኩድ ፓርቲ ስርአት መዘርጊያ ይሆናል፡፡ ሃማስ ከእስራኤል ጋር ያለው ግንኙነት የአረቡ አለም ያደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ሃማስ እስራኤል የሚያሰጓትን የፒ.ኤል.ኦ አመራሮችንም ያስወግድላታል፡፡
በፍልስጤምና እስራኤል መካከል ሰላም ሊያወርድ ተቃርቦ የነበረውን የእስራኤል መሪ ይሳቅ ራቢንን የገደለው ዪጋል አሚር ያሰለጠነው የእስራኤል ሺን ቤት የተባለው ያገር ውስጥ ደህንነት ነው፡፡ ሺን ቤት መሪያቸው ይሳቅ ራቢን ሂወት ላይ ጥቃት እንደሚፈፀም ተደጋጋሚ ጥቆማ ደርሶት ነበር፡፡ ማንኛው የታጠቀ ሰው ሰልፍ ሰብሮ ሲገባ ወድያው እንዲተኩሱበት የሰለጠኑት የራቢን ጠባቂዎች ገዳዩ ከስድስት ጫማ ርቀት አጠገባቸው ሁኖ ሲተኩስበት ፀጥ ብለው ማየታቸው እንግዳ ነው፡፡ ኒው ዮርክ ታይምስ እንደዘገበው ከሆነ ራቢን ተነስቶ ወደ ሊሞዚን መኪናው እየሄደ “ያማል፣ ግን ያን ያህል አይደለም” እያለ ተሰምቶ ነበር ወደ ሆስፒታል የተወሰደው፡፡ እዛም ሲደርሱ ሹፌሩ ከመኪናው ወጥቶ የድረሱ ጥሪ ለማሰማት ተገዶ ነበር፡፡ የተጎዳውን ጠ/ሚኒስትር ለመርዳት በተጠንቀቅ ሲጠብቅ የነበረ የሕክምና ቡድን አለመኖሩ የማይጠበቅ ነው፡፡ እንዲሞት የፈለጉት ቡድኖች እንዲሞት እንዳረጉት የሚያሳይ ነው፡፡
የራቢን ባለቤት ለሞቱ በቀጥታ ተጠያቂ ያደረችው የሊኩድ ፓርቲን ሲሆን በተለይም ደም የተጠማው መሪውን ቤናሚን ኔታንያሁን ወቅሳለች፡፡ የራቢን ግድያ የሃማስ ሞኞች አልያም የራሳቸው የእስራኤል ኤጀንቶች እንደተገበሩት የሚያሳይ ሲሆን ስልቱና ዓላማው ሁሌም አንድ ነው፡፡ የእስራኤል የቀኝ ክንፍ ቁንጮዎችና ሉላዊ ጌቶቻቸው ከራቢን ሞት በፊት የነበረው የትኛውንም የሰላም ተስፋ ለማጨናገፍ የያዙትን እቅድ የሚያሳይ ነው፡፡
ለራቢን መሞት ሌላው ምክንያት እስራኤል ለሃማስ የምታደርገውን ድጋፍ መቃወሙ ነበር፡፡ በ1992 ወደ 400 የሚሆኑ የሃማስ ሰዎችን ከእስራኤል ያባረረ ሲሆን፣ ከመሞቱ በፊት ባሉ ወራቶች ደግሞ 4,000 የሚሆኑትን አስሯቸው ነበር፡፡ (በቅርቡ በኔታንያሁ የሚመራው አስተዳደር ከሃማስ ጋር የእስረኛ ልውውጥ አድርጓል፡፡) ሃማስ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ የሚል አቋም በመያዝ ከተቃዋሚ ፓርቲ የነበረው ሊኩድ ጋር ጥምረት ፈጠረ፡፡ እንዲህ አይነቱ መረጃ አረፋት ወይም ራቢን ያሰራጩት ፕሮፖጋንዳ ነው የሚለውን ከግምት በማስገባት የ Jerusalem Post  በርእሰ አንቀፁ የሃማስ-ሊኩድ አጋርነት የአምባጓሮ መፍጠርያ ፕሮፖጋንዳ ሳይሆን እንዲህ አይነቱ ጥምረት “የተለመደ እውቀት/ተግባር” (“conventional wisdom”) ነው ይለዋል፡፡ ‘The Hamas-Likud Pairing’ – Jerusalem Post – August 25 1995 – http://www.prisonplanet.com/news_alert_hamas4.html ከትእይንቱ በስተጀርባ ያልተለመደ የአገዛዝ ስልት የለም፡፡ በዚህ ላይ ይበልጥ ለማንበብ የፖል ዋትሰን (Paul J. Watson): Order Out of Chaos ይመልከቱ፡፡ በቀጣይ ምእራፎች ጠለቅ ብለን ስለ ምእራቡና የሙስሊም ፅንፈኞች ህቡእ ትስስር እንዳስሳለን፡፡
ጠላትህን መፍጠር፡ ኢራን፣ ሰሜን ኮርያ እና ቻይና
የሰሜን ኮርያ ገዥዎች ደጋግመው አለምን እንደሚያጠፉ በመዛት ይታወቃሉ፡፡ ሰሜን ኮርያ በጋርዮሻውያን ስርወ መንግስት የምትገዛ አገር ነች፡፡ ሰ.ኮርያ አንድ ሚሊዮን ሰራዊት፣ በሌሎች ግምት ደሞ 4 ሚሊዮን አላት የምትባል አገር ስትሆን፣ ገዢዎቿ ህዝቡን በማስራብና በሰፋፊ ማጎርያ ካምፖች በማከማቸት የስታሊን አርአያን የሚከተሉ ናቸው፡፡ የኢራቅ ገዢዎች ሰብአዊ መብት ጥሰትና ሌሎችም ጉዳዮች ተወንጅለው ሰራዊት ተዘምቶ ተወግደዋል፡፡ ከሰ.ኮርያ ጋር ሲነፃፀሩ ኢራቆቹ የመዋእለ ህፃናት ተማሪዎች ነው የሚሆኑት፡፡ ለሰ.ኮርያ ገዢዎች እንኳን ሊነኩ ቀርቶ በአሜሪካ የኒኩለር አቅማቸው እየተገነባላቸው ነው፡፡ በ1994 በክሊንተን አስተዳደር ስር በተደረገ ስምምነት አሜሪካ የሰ.ኮርያን የኒኩሌር ማብሰልሰያን ወደ ቀላል የውሃ ኒኩሌር ማብሰልሰያ ለመቀየር ተስማማታለች፡፡ መንግስት የከፈላቸው ሙያተኞች ይህ የውሃ ኒኩለር ማብሰልሰያ መሳርያ ለመስራት እንደማይሆን ተናግረዋል፡፡ ይህ አባባል የኒኩለር መሳርያ ያለማልማት ስምምነት ፖሊሲ ትምህርት ማእከል በዋሽንግተን ሃላፊ የሆነው ሄነሪ ሶኮልስኪ አይስማማበትም፡፡
“ቀላል ውሃ ማብሰልሰያዎች የመሳርያ ደረጃ ያለው ፕሉቶንየም በሰሜን ኮርያም ሆነ በኢራን ደርዘን ቦምቦችን ለመስራት ያስችላሉ፡፡ ይህ ለማንኛውንም የቀላል ውሃ ማብሰልሰያ የሚሰራ እውነት ነው፡- ይህ አሳዛኝ የሆነ እውነታን የዩ.ኤስ. ፖሊሲ አውጪዎች ሊሸሽጉት ችለዋል፡፡” (‘Nuclear Succor for North Korea’ – Matt Bivens – Moscow Times – Septemner 16 2002)
ሶኮሊስኪ በሌላ ግዜም የሚከተለውን ብሏል፡-
እኚህ ማብሰልሰያዎች እንደማንኛውም ማብሰልሰያዎች ናቸው፣ መሳርያ የመስራት አቅም አላቸው፡፡ እናም መጨረሻ ላይ እንዳይኖረው ለምንፈልገው አደገኛ የኒኩሌር ጥሰት ፈፃሚ ለሆነው የኒኩሌር መሳርያ የሚያገኝበትን መንገድ አቅራቢ ልንሆን እንችላለን፡፡ (‘US grants N Korea nuclear funds’ – BBC – April 3 2002)
የዩኤስ ውጭ ጉዳይ ቢሮም ጉዳዩን ያጠናክርልናል፣ የእምነት ቃሉን በመስጠት ሳይሆን ልክ በቲቪ እንደምናያቸው ቀሽም ዋሾዎቻቸው ቢሮውም ይቀባዥራል፡፡ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ቀላል የውሃ ማብሰልሰያዎች ቦምብ ለመስራት አይሆኑም የሚል አቋም የሚያራምድ ሲሆን በ2002 ራሽያ ከኢራን ጋር የምታደርገውነ የኒኩሌር ትብብር ኢራንን የኒኩሌር ማሳርያ ባለቤት እንዳያረጋት እንድታቆም ጠይቃለች፡፡ ራሽያ በኢራን የቀላል ውሃ ማብሰልሰያ ስትገነባ ነበር፡፡ ውጭ ጉዳይ በድረ-ገፁ ለራሽያ በተደጋጋሚ ከኢራን ጋር የምታደርገውን ማናቸውም የኒኩሌር ትብብር የቀለል ውሃ ማብሰልሰያን ጨምሮ እንድታቆም መጠየቁን ገልፅዋል፡፡ (‘State Department on Russia-Iran Nuclear Cooperation’– U.S. Department of State – January 31 2003 -http://usinfo.state.gov/topical/pol/arms/03020321.htm)
እንደቢሮው ከሆነ ቴክኖሎጂው በኢራን ለመሳርያ መስርያ የሚሆን ሲሆን በሰሜን ኮርያ ግን አይውልም፡፡ በዚህ ግን አሜሪካ ኢራን ጡንቻዋን አፈርጥማ ማስፈራርያ እድትሆን አይረዷትም ማለት አይደለም፡፡ ዝርዝሩን በቀጣይ ምእራፎች እናየዋለን አሁን ግን የአሜሪካ ቀኝ እጅ የሆነችው ብሪታንያ ለኢራን የቦምብ ደረጃ ያለው ግብአቶች መስጠቷን እንይ፡፡ አንድ የቢቢሲ ዘገባ እንደሚከተለው ብሎ ነበር፡-
ፕሮግራሙ እንደዘገበው ቃለመጠይቅ ያደረገለት በዩ.ኬ. ዋነኛ የኒኩሌር ጦር መሳርያ ሙያተኛ የንግድና ኢንዱስትሪ መስርያቤቱ ወደ ኢራን እንዲላክ ፈቃድ የተሰጠባቸው የቤሪሊየምና ሌሎች ዝርዝሮች በአጠቃላይ ለኒኩሌር ጦር መሳርያ ፕሮግራም የሚሆኑ ናቸው ይላል፡፡ (‘UK sells bomb material to Iran’ – BBC – September 23 2002)
የቤሪልየም ብረት ለኒኩሌር ጦር መሳርያ ስራ ከመዋል ውጪ ለሌላ ለምንም ነገር አይጠቅምም፡፡
ቻይናስ? ቻይናም ብትሆን ከፀጋው ተቋድሳለች፡፡ ታሊባኖችን ትደግፋለች፣ ከፓኪስታን ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላት፡፡ በዚህ ዙርያ አሜሪካ ምን አደረገች? በቡሽ አስተዳደር ግዜ ለብሄራዊ ደህንነት አስፈላጊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ሲያሸጋግሩላት ነበሩ፡፡ ብቸኛ ጥቅሙ የኒኩሌር ጦር መሳርያ መስራት የሆነ የኮምፒውተር ፕሮግራም ቻይና ተሰጧታል፡፡ (‘High-Tech Transfers To China Continue’ – Zoli Simon – Insight Magazine – July 8 2002) ለቻይና የሚደረግላት ድጋፍ አዲስ ክስተት አይደለም፡፡ ከስር ካልታተመው የአሜሪካ የሚስጥር ተቋም የትርጉም መፅሃፋችን የወስደነውን እናንብ፡-
ልክ የቡሽ ቤተሰቦች በመጀመርያ አካባቢ ሶቭየት ህብረትን ሲገነቡ፣ ከዛም ናዚዎችን ፋይናንስ ሲያረጉ፣ በብዥታ ደሞ ከአንጎላ በስተጀርባ እንዳገኘናቸው፣ አሁን ደሞ ቡሽ የሚለው ስም አዲስ ዲያሌክቲክ ክንድ ሲገነባ እናገኘዋለን፡ ኮሚውኒስት ቻይናን፡፡
ሚር. ኒክሰን ጆርጅ በ1971 “ፖፒ” (“Poppy”)  ቡሽን (ከኦርደሩ 1948) በተ.መ.ድ. የዩ.ኤስ. አምባደር አርጎ ሾመ፣ ከዛ በፊት ምንም የዲፐሎማሲያዊ ስራ ልምድ ባይኖረውም’ኳ፡፡ እንደዋና የዩ.ኤስ መልእክተኛነቱ ቡሽ የቻይና ሪፐብሊክን (መጀመርያ ነፃ የተ.መ.ድ. አባል የነበረችውን) ከኮሚውኒስት ቻይና ጥቃት መከላከል ይጠበቅበት ነበር፡፡ መጠቀም የሚችለውን ሰፊ የአሜሪካን ጉልበት ይዞ ቡሽ በሚያሳዝን አኳኋን ወድቋል፡፡ ሪፓብሊኳ ተባራ ኮሚውኒስት ቻይና ቦታዋን ተረከበች፡፡ ከዚህ ግዙፍ ውድቀት በውኋላ ቡሽ የተባበሩት መንግስታትን ትቶ የሪፐብሊካን ብሄራዊ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ሆነ፡፡
ይህ የአሜሪካ እጅ በቻይና ያለውን ጠቅላላ ታሪክ እሚነገርበት ቦታ አይደለም፡፡ የተጀመረው ዎል ስትሪት በ1911 የሰን ያት ሰን (Sun Yat Sen) አብዮት ጣልቃ ሲገባ ነው – እስካሁን ህዝብ በሚያውቀው መልኩ ያልተመዘገበ ታሪክ፡፡
በ2ዓ.ጦ. ግዜ ዩ. ኤስ. የቻይና ኮሚውኒስቶች ወደስልጣን እንዲመጡ ረዳቻቸው፡፡ አንድ የቻይና ጥናት ላይ በሚያተኩር ቺን-ተንግ ሊያንግ (Chin-tung Liang) የተባለ ስለ ጀነራል ጆሴፍ ደብሊው. ስቲልዌል (General Joseph W. Stilwell) ከ1942-1944 የዩ.ኤስ. ተወካይ በቻይና ስለሆነው እንደፃፈው ከሆነ፡ “ኮሚውኒዝምን ከመታገል አኳያ ከታየ…(ስቲልዌል) ለቻይና ታላቅኢ-አገልግሎትን አድርጎላታል፡፡” ይላል፡፡ (Chin-Tun Liang, General Stilwell In Chino, 1942-1944: The Full Story. St. John’s University 1972, p. 12.)
ስቲልዌል ከጀነራል ጆርጅ ሲ. ማርሻል ከዋሽንግተን የተላከለትን ትእዛዝ ብቻ ነበር የሚያንፀባርቀው፡፡ አድማይራል ኩክ ለኮንግረስ እንደተናገረው ከሆነ፣ “…በ1946 ጀነራል ማርሻል በስውር መልኩ ቻይናዎችን ትጥቅ አልባ ለማድረግ የጥይት መጓጓዝን እንዲቆም አድርጓል፡፡” ብሏል (Ibid., p. 278.)
ወደ ጀነራል ማርሻል ስንደርስ ግን ማወቅ ያለብን በዩ.ኤስ. የሲቪል ባለ ስልጣኑ በወታደራዊ ጉዳይ የመጨረሻው ቃል ያለው መሆኑንና ይህ ደሞ ወደጦር ሹሙ (ሚ/ሩ) ሄነሪ ስቲምሰን (Henry L. Stimson) ይወስደናል-የማርሻል የበላይና የኦርደሩ አባል (ከኦርደሩ1888)፡፡ በሚገርም መገጣጠም በ1911 በሰን ያት ሰን አብዮት ግዜ የጦር ሹም የነበረው እራሱ ስቲምሰን ነበር፡፡
ቻይናን የመካድ ታሪክና የኦርደሩ ሚና ሌላ ቅፅ መጠበቅ ሊኖርበት ነው፡፡ ለአሁን ግን የኮሚውኒስት ቻይናን እንደአዲስ የዲያሌክቲኩ ክንድ ለመገንባት የተወሰደውን ውሳኔ ብቻ ለማስመዝገብ እንፈልጋለን – በፕሬዚደንት ሪቻርድ ኒክሰን የተወሰደ እርምጃና ወደትግበራ የተገባው በሄነሪ ኪሲንጀር (ቼዝ ማንሃተን ባንክ) እና ጆርጅ “ፖፒ” ቡሽ (ከኦርደሩ) ነው፡፡
ይህ ስራ ወደ ህትመት እየተሄደ እያለ (በ1984 መጀመርያ) ባችቴል ኮርፖሬሽን አዲስ ባችቴል ቻይና ኢንክ. (Bechtel China, Inc.)የተባለ ካምፓኒን መስርቷል -ልማትን፣ ኢንጂነሪንግንና ኮንስትራክሽን ኮትራቶችን ለቻይና መንግስት ሊይዝ፡፡ የባችቴል ቻይና ኢንክ. አዲሱ ፕሬዚደንት ሲድኒ ቢ. ፎርድ ነው፣ ቀድሞ የባችቴል ሲቪልና ሚነራል ኢንክ. ማርኬቲንግ ማናጀር የነበረ፡፡ አሁን ባችቴል እየሰራ የሚገኘው ለቻይና ብሄራዊ ከሰል ልማት ኮርፖሬሽንና ለቻይና ኦፍሾር ኦይል ኮርፖሬሽን ጥናትን ነው- ያው ሁለቱም የቻይና ኮሚውኒስት ድርጅቶች ናቸው፡፡
ይህ እንግዲ የሚመስለው ምንድን ነው ዲትሮይት ከነበረው አልበርት ካን ኢንክ. (Albert Kahn, Inc) የተጫወተውን ሚና ሊጫወት ነው ማለት ነው – አልበርት ካን በ1928 ለሶቭየት ህብረት የመጀመርያውን አምስት አመት እቅድ ቅድመ ጥናት ያካሄደው ድርጅት ነው፡፡
በ2000 ዓ.ም. ኮሚውኒስት ቻይና “ልእለ-ሃያል” ሃገር ትሆናለች ማለት ነው፣ በአሜሪካ ቴክኖሎጂና ሙያ ተገንብታ፡፡ [ይህን ሲፅፍ1984 ላይ ሁኖ ነበር፣ በውነትም የኦርደሩን እንቅስቃሴ መተንበይ ችሏል፣ ዛሬ ቻይና ምን ላይ እንደምትገኝ እናውቃለንና፡፡] የኦርደሩ አላማ ነው ተብሎ አንደሚገመተው ይህን ሃይል ከሶቭየት ህብረት ጋር በግጭት መስመር ውስጥ እንደሚያስገባ ነው፡፡
ባችቴል ሃላፊነቱን እንደሚወጣ ጥርጥር የለውም፡፡ የቀድሞ የሲ.አይ.ኤ. ዳይሬክተር ሪቻርድ ሄልምስ ለባችቴል ይሰራል፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበረው ጆርጅ ሹልትዝና (George Shultz) መከላከያ ሚኒስቴር የነበረው ካስፓር ዌንበርገርም (Caspar Weinberger)ቢሆኑ ለባችቴል እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ አንዱ ከዋሽንግተን ያለ ከብሄራዊ ደህንነት ጋር የተያያዘ እቅድ አውጪ ከመስመር ወጥቶ ቢቃወም ይህ በቂ ሃይለኛ ተፅእኖ አድራጊ ጥምረት ይገጥመዋል፡፡
ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን ኦርደሩ የተሳሳተ ስሌት አድርጓል፡፡ ለዚህ ዲያሌክቲክ ለውጥ የሞስኮ ምላሽ ምን ሊሆን ይችላል? ከተለመደው የራሽያ የጥርጣሬ በሽታ ውጪም ቢሆን እዚህ ላይ ትንሽ ጭንቀት ቢያሳዩ ይቅር ሊባሉ ይገባል፡፡ ማን ነው የቻይና ኮሚውኒስቶች ከ2000 በውኋላ ከሞስኮ ጋር ሰላም ፈጥረው ልእለ-ልእለ-ሃያል የሆነች ዩ.ኤስ.ን ለማስወገድ አይጣመሩም ያለው?
ሌሎች የሽብር አገዛዝ ምሳሌዎች
የቬትናም ጦርነትን ያስጀመረው የቶንኪን ባህረ ሰላጤ ክስተት (The Gulf of Tonkin) በሁለት ገጠመኞች ላይ ተመስርቶ ነበር፡፡ ከኬነዲ መሞት በውኋላ የተተካው ሊንደን ቢ. ጆንሰን አስተዳደር ሰሜን ቪየትናም ላይ ጦርነት እንዲያውጅ ያደረገው፡- የመጀመርያው ትንኮሳ ሲሆን የአሜሪካ መርከብ ላይ ደረሰ የተባለው ጥቃት የአሜሪካ ጥፋት ነበር፡፡ (ያለ ቦታው ለስለላ የሄደ የአሜሪካ መርከብ ስለነበር ተንኳሿ እራሷ አሜሪካ ነች፡፡) ሁለተኛው ደግሞ ባዶ ሜዳ ላይ በመተኮስ ተጠቃን ተብሎ የተተወነ ፈጠራ/ውሸት ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡ በዚህ ጦርነት አንድ ሚሊዮን ቪየትናማውያንና 58,000 አሜሪካውያን ሂወታቸውን አጥተዋል፡፡
የኦክለሆማ ከተማ ፍንዳታ የቀኝ ዘመም ፅንፈኛ ሚሊሻዎች ያደረሱት ጥቃት ነው ተብሎ የተፈረጀው የሽብር ጥቃት ብዙ ክፍተቶች ያሉበት ነበር፡፡ በፍንዳታው የተጠቃው ህንፃ ሙራ ፌደራል ህንፃ (Murrah Federal Building) እንዲያፀዳው ስራው የተሰጠውControlled Demolition, Inc. ለተባለው ድርጅት ነበር፣ ይህ ድርጅት የዓለም ንግድ ማእከል ከፈረሰ በኋላም እንዲጠራርገው የተደረገው ነው፡፡ ፖሊስ በዚህ ህንፃ ፅንፈኞቹ የተባሉት በመኪና ደጅ ካስቀመጡት ውጪ ህንፃው ውስጥ የተጠመዱ ሁለት ፈንጆችን አግኝቶ ነበር፡፡ በወቅቱ ጋዜጠኞችም ዘግበውታል፡፡ ጡረታ የወጣው ብርጋዴር ጀነራል ቤንቶን ኬ. ፓርቲን (Benton K. Partin) በፍንዳታ ልዩ ሙያተኛና በዩ.ኤስ. አየር ሃይል የ31 ዓመት ልምድ ያለው ሙያተኛ በ1997 ለዩ.ኤስ. ምክርቤት ህንፃው ከደጅ መኪና ላይ በተጠመደ ሳይሆን ከውስጥ በተጠመዱ ፈንጆች እንደወደመ የሚያሳይ ማስረጃ ፅሁፉን አንብቦ ነበር፡፡ በዚሁ ዓመት ዩ.ኤስ. ኢንግሊን፣ ፍሎሪዳ ያለው አየር ሃይል በሙራ ህንፃ ፍንዳታ ላይ ያደረገውን የ56 ገፅ ጥናቱን ይፋ አድርጎ ነበር፡፡ የብርጋዴር ጀነራሉን ግኝት የሚደገፍ ነበር፡፡ አው – በነገራችን ላይ እንደሁልግዜው ባካባቢው የነበሩ የጥበቃ ምስል መቅረጫዎች የቀረፁት ምስል ለህዝብ ይፋ አልሆነም፣ እንደሁልግዜው አደረጉት ከተባሉት ውጪ ሌሎች ፊቶች ሲሰሩ እንዲታዩ አይፈለግምና፡፡ ምንጭ antiglobalconspiracy

ጠ/ሚኒስትሩ ንግግር ላይ ባይታሙም ቀልድና ተረብ ይጐድላቸዋልመቼም አንደበተ ርዕቱ ናቸው! (ከወንበሩ ይሆን እንዴ?)

እንዴት ናችሁ…ወዳጆቼ? ሰውም ጠፋ አትሉም እንዴ? ባትሉኝም ግን አልቀየማችሁም፡፡ እናንተን ተቀይሜ የት ልደርስ! (እኔ እንደ ኢህአዴግ ቅያሜ አላውቅም) ለማንኛውም የጠፋሁበትን ምክንያት ልናዘዝ (ግልጽነት እንዲለመድ ብዬ እኮ ነው!) የጠፋሁት ለምን መሰላችሁ? ነገሮች እስኪረጋጉ ድረስ ነው (እስኪለይለት!) ልክ ነዋ… አገሪቱን የሚመራው ማን እንደሆነ ሳይታወቅ ዝም ብሎ ይፃፋል እንዴ? የኢህአዴግ ሊ/መንበርና የአገሪቱ Prime minister እስኪታወቅ ድረስ ቫኬሽን ላይ ነበርኩ፡፡ ፈርቼ ግን እንዳይመስላችሁ፡፡ እንዴት እፈራለሁ…ኢህአዴግ እያለልኝ (ይቅርታ ህገመንግስቱ እያለልኝ ማለቴ ነው!)

በነገራችን ላይ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር እንዴት ናቸው? በቀደም ፓርላማ ውስጥ የምክር ቤቱ አባላት ለሰነዘሯቸው ጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ ሲሰጡ ይመቹ ነበር አይደል! መቼም አንደበተ ርዕቱ ናቸው! (ከወንበሩ ይሆን እንዴ?) ደሞም እኮ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር “ግርፍ” ናቸው ይባላል (ይባላል ነው!) ከመምህሩ ደቀመዝሙሩ እንዳይሆን እንጂ የተማረውን ልቅም አድርጎ የሚይዝ ተማሪ ሸጋ አይደለም እንዴ?! አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ምን ሲሉ ሰማኋቸው መሰላችሁ… “የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር መጥቀስ አበዙ” (ሌኒንን ይጥቀሱ እንዴ ታዲያ!) ለነገሩ ላለፉት ጠ/ሚኒስትር ያለቀስነው ከልባችን ከሆነ እሳቸውን የመሰለ ማግኘት ለምን ይከፋናል?!
እኔ የምለው … አቶ ሃይለማርያም ሥልጣን በቃኝ ብለው ወደ ትምህርታቸው ሊገቡ ሲሉ “ከትግሉ ማፈግፈግ የለም” ብለው የመለሷቸው የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ናቸው የሚባለው እውነት ነው እንዴ? (እንኳንም መለሷቸው!) ግንኮ ራሳቸውም በመጀመሪያ ንግግራቸው “ዳገቱ ወገብ ላይ ደርሶ መቆም አይቻልም!” ብለዋል፡፡
በነገራችን ላይ ኢህአዴግ፤ አባላቱ ሥልጣን “በቃን” ሲሉ “ከትግሉ ማፈግፈግ የለም” እያለ ችክ የሚለውን ነገር ቢተው ነው የሚሻለው (ዕድሜ ለመተካካት!) ምን የሚያሳስብ ነገር አለ? አንድ ጥያቄ አለኝ … ግን ለምንድነው ኢህአዴግ ሁሉን ነገር ትግል የሚያደርገው? እኔ ያልገባኝ ምን መሰላችሁ … “አገር መምራት እንዴት ትግል ሊሆን ይችላል?” የሚለው ነገር ነው፡፡ እኔማ ኢህአዴግ አዲስ አበባ ገብቶ ሥልጣን የያዘ ዕለት ትግል አብቅቷል ብዬ ነበር (ተሳስቻለሁ!) እንዴት ብትሉ … ይሄው ፓርቲው 21 ዓመት ሙሉ ከአፉ ላይ ትግል የሚለው ቃል ጠፍቶ አያውቅም፡፡ “ታጋይ ቢሞት ትግል አይሞትም”፣ “ያለመስዋዕትነት ድል የለም”፣ “በእነገሌ መቃብር ላይ ትግሉ ይለመልማል!” … እነዚህን መፈክሮች መቼም የምንተዋቸው አይመስለኝም!! (ማን ነበር “ላልከዳሽ ቃል አለብኝ” ያለው?) ኢህአዴግ እውነት ትግል ላይ ከሆነ ደግሞ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በሰላማዊ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ ለምን ያሳስባል? አንድ ጥርጣሬ ግን አለኝ፡፡ ይህች “ትግል” የምትባል ነገር የልማታዊ መንግስት ባህርይ ልትሆን ትችላለች እኮ!
አያችሁ…እኔም ራሴ ዋና ጉዳዬን ትቼ ትግል ውስጥ ገባሁ፡፡ ለነገሩ የእኔም እኮ ትግል ነው (ለጥቂት ሳምንት ከትግሉ ባፈገፍግም) አሁን ወደ ዋና ጉዳያችን እንመለስ፡፡ እንግዲህ ወጋችን በአዲሱ ጠ/ሚኒስትራችን ዙሪያም አይደል (መብታችን መሰለኝ!) በመጀመሪያ ግን “ሹመት ያዳብር” ብያለሁ – ለተከበሩ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ!! እንዴ የስንቱ ወዳጅ አገር መሪ “ሹመት ያዳብር” ሲላቸው እኛ እኮ ዝም አልን! የይገባናል ጥያቄ ወይም ቅሬታ ካለን (የሥልጣን ማለቴ ነው) የ2007 ምርጫ ጊዜ ያደርሰናል፡፡ እኔ የምለው … ተቃዋሚዎች አዲሱን ጠ/ሚኒስትር “Congra!” ብለዋል እንዴ? በአደባባይ ባይሆንም በምስጢር ካሉም በቂ ነው (ነግ በኔ እኮ ነው!) የተከበሩ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ገና ጠ/ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት በአዲስ አበባ መስተዳድር ቲቪ ቀርበው ስለአገራችን ተቃዋሚዎች ያሉትን ሰምታችኋል? “አይገቡኝም!” (ልብ በሉ “አይረቡም” አላሉም) ደሞ በደፈናው “አይገቡኝም” ብለው አላለፉም፡፡ “አማራጭ ፖሊሲ ሳይኖራቸው ኢህአዴግን ለመቃወም ብቻ የሚቃወሙ ናቸው” ሲሉ አስረድተዋል – ምክንያታቸውን፡፡ ሁሉንም ግን አላሉም፤ “ከጥቂቶች በቀር” የሚል ጨምረውበታል፡፡ እንደነገርኳችሁ ይሄን የተናገሩት የአገሪቱን ትልቁን ሥልጣን ከመያዛቸው በፊት ነው፡፡ አሁን ግን በደንብ ሊያውቋቸውና ሊገቧቸውም ይገባል – ተቃዋሚ ፓርቲዎች፡፡ (ካልገቧቸው ችግር ነዋ!)
እኔ የምለው ግን…የሰሞኑን የፓርላማ ማብራሪያቸውን እንዴት አያችሁት? እኔ በግሌ (እንደ ፓርቲ እንዳልል ፓርቲ የለኝም) ተመችተውኛል፡፡ “አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች” ጠ/ሚኒስትሩ ንግግር ላይ ባይታሙም ቀልድና ተረብ ይጐድላቸዋል የሚል ስጋት ያዘለ አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡ እኔም አስተያየታቸውን በከፊል እጋራቸዋለሁ፡፡ ግን ደግሞ ይሄን ያህል ስጋት ውስጥ የሚጥል አይደለም – ጉድለታቸው!! ሥልጣኑን በደንብ ሲለምዱትና ሲለምዳቸው ቀልድና ተረብ ብቻ ሳይሆን ሃይለቃልም ሌላ ሌላም መልመዳቸው አይቀርም (ለመሪነት አስፈላጊ ነው የተባለውን ሁሉ!) ለጊዜው ግን ፓርላማ የቀልድና የፌዝ ቦታ አይደለም ብለን ልናልፈው እንችላለን፡፡
አዲሱ ጠ/ሚኒስትር በዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት ተቃዋሚዎች የድርሻቸውን ማበርከት እንጂ ጣት መቀሰር ፋይዳ የለውም ያሉት ነገር ተስማምቶኛል፡፡ ችግሩ ግን ተቃዋሚዎች “ሜዳው የት አለ?” እያሉ ነው፡፡ ሜዳውም ኖሮ ኢህአዴግ ኳሷን አልሰጥም ካለ እኮ ዋጋ የለውም፡፡ (አጫዋቹስ የማነው?) አያችሁ … በትግሌ ያገኘኋት ኳስ ናት ብሎ ካሰበ ለብቻው ተጫውቶ ለብቻው ነው የሚያገባው – ራሱ ላይ፡፡ በሌላ ቋንቋ … ጨዋታም የለም፤ ግብም የለም ማለት ነው፡፡
ባለፈው ሳምንት እዚሁ ጋዜጣ ላይ፣ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ቤተመንግስት አለመግባታቸውን ሳነብ ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃላችሁ … የታምራት ደስታ “አይከብድም ወይ” የሚለው ዘፈን፡፡ ሸክሙ የቀለለኝ አንድ ካድሬ ወዳጄ አግኝቶኝ ነገሩን ሲያጫውተኝ ነው፡፡ እሱ እንዳለኝ ከሆነ እንግዲህ … ለኢህአዴግ ሁሉም ታጋይ ነው፤ ሥልጣን ራሱ መስዋዕትነት ነው አሉ – ለፓርቲው የሚከፈል፡፡ እናላችሁ … ለእኔና ለእናንተ ነው እንጂ ለኢህአዴግ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር አንድ ታጋይ ማለት ናቸው (ባይታገሉም) ስለዚህ ቤ/መንግስት መግባትና አለመግባት ለኢህአዴግ ቁምነገር አይደለም፡፡ የመብትና የፕሮቶኮል ጥያቄዎች ማንሳት ደግሞ ኪራይ ሰብሳቢነት ነው! (ካድሬው እንዳለኝ)
“ጠ/ሚኒስትሩ አገር የሚመሩት ከመካኒሳ እየተመላለሱ ነው የሚባለውስ?” ስል ጠየቅሁት – ካድሬ ወዳጄን፡፡
በረዥሙ ሳቀና “ትቀልዳለህ…እኛ እኮ ጫካ ሆነን ነበር ህዝቡን የምንመራው” አለኝና አረፈው፡፡ እኔ ግን አላረፍኩም፤ ሌላ ጥያቄ አስከተልኩ “ያኛው ትግል እኮ ነው፤ ይሄኛው አገር መምራት…” አልኩት፡፡
“ለእኛ ሁለቱም ያው ነው፤ ሁሉም ታጋይ ነው፤ ሁሉም መስዋዕትነት ይከፍላል!” አለና ፈገግ አሰኘኝ፡፡
“ግን እኮ መስዋዕትነቱንም ቢሆን ቤተመንግስት ሆነው ቢከፍሉት ይሻላል” ስል መለስኩለት፡፡ ካድሬው ወዳጄ ግን አልተዋጠለትም፡፡ “አልፈርድብህም፤ የኢህአዴግን ባህርይ ስለማታውቅ ነው” ብሎ እኔኑ ጥፋተኛ ሊያደርገኝ ፈለገ፡፡ ወዳጄን ምን ነካው! ራሱ የኢህአዴግን ባህርይ አያውቅም እንዴ? (ድብቅነቱን ማለቴ ነው)
የሆኖ ሆኖ ግን እንደምንም ቤ/መንግስት ቢገቡ ይሻላል – ጠ/ሚኒስትሩ፡፡ ሌላው ቢቀር ለወጉ እንኳ! (ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ እንዳትሉ) መቼም ከ2005 እስከ – ድረስ ጠ/ሚኒስትር ነበሩ መባሉ አይቀርም አይደል (ደሞዟ ባትረባም!) እኔ የምለው…የጠ/ሚኒስትር ደሞዝ ተሻሻለ ወይስ ያው ነው? የኬንያ የፓርላማ አባላት ደሞዝ ስንት እንደሆነ ሰምታችኋል አይደል… በወር 170 ሺ ብር!! የእኛ አገር ጠ/ሚኒስትር የወር ደሞዝ ደግሞ 6ሺ ምናምን ብር!! ለካስ ኢህአዴግ ሥልጣንን መስዋዕትነት ነው የሚለው ወዶ አይደለም!! (ተቃዋሚዎች ምን አሉኝ ይሆን?)

(ምንሊክ ሳልሳዊ)

ስርዓተ አልበኝነት የነገሰበት የግብይት ስርዓት ና የኑሮ ውድነት

የኑሮ ውድነት፣ የመግዛት አቅም መዳከም፣ የአቅርቦት መመናመን፣ የጥራት መጓደል፣ ስርዓተ አልበኝነት የነገሰበት የግብይይት ስርዓት አጅበውት የመጡት ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የኑሮአችን አካል ከሆኑ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ እነዚህ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ከስጋትነት አልፈው የእለት ተእለት መወያያ ርእሳችን ከሆኑም ሰነባብተዋል፡፡ መሽቶ በነጋ ቁጥር ኑሮአችንን መሸከም አቃተን፣ ቤተሰብ በቅጡ መምራት አዳገትን የሚሉት መሰረተ ሰፊ የሕዝብ ጥያቄዎችና ሮሮዎች መፍትሄ አጥተው በስፋት መሰማታቸውን ቀጥለዋል፡፡ መንግስትም ኢኮኖሚያዊ ቀውሱን በማመን መንስኤው በመካሄድ ላይ የሚገኘው ሰፋፊ የመሰረተ ልማት ግንባታ በመሆኑና ስርዓቱም የሚገለፀው በዚሁ ፍልስፋና በመሆኑ መፍትሄው አሁንም ልማቱን ማስቀጠል ብቻ እንደሆነ ተደጋግሞ እየተነገረን ይገኛል፡፡ መሰረታዊው ጥያቄ ግን የችግሩን መንስኤ በተዛባ መልኩም ቢሆን መቅረቡ ብቻ ሳይሆን መልስ አሰጣጡ ሸክሙን እስከመቼ መሸከም እንደሚገባና ሸክሙ ቀለል የሚልበት መዳረሻ የት ጋ እንደሆነ የሚጠቁም የመንግስት ባለሙያ ወይም ሹመኛ አለመኖሩ ጭምር ነው፡፡ ብቻ ነጋ ጠባ በትእግስት ጠብቅ ከሚል ፕሮፓጋንዳ ውጭ ጠብ የሚል መፍትሔ ማምጣት አልተቻለም፡፡

ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ የቱንም ያህል የገዘፈ ቢሆንም ቅሉ እንደመፍታሄ የሚቸረን ቀውሱን ያለጥያቄና ያለማንገራገር ተቀብልን፣ ከመሰረተ ልማት ግንባታው ጋር መትመም ብቻ ነው፡፡ ገቢያችን እንደ ግመል ሽንት ወደኋላ ይገሰግሳል፡፡ የኑሮ ውድነትና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅሉ ከመሰረተ ልማት ግንባታው እኩል በፍጥነት ሽቅብ ይተማል፡፡ መንግስት ስር ነቀል ለውጥ የሚያመጣ መፍትሄ ከመሻት ይልቅ፣ ከአስር ዓመት እልህ አስጨራሽ ኢኮኖሚያዊ ትንቅንቅ በኋላ ዛሬም ግድ የለም፣ እመኑኝ በሚል የማይቆረጠም መፈክር ስር ማብቂያ በሌለው የኑሮ ውድነትና ግሽበት ውስጥ ኑሮአችንን እንድንገፋ በማበረታታት ላይ ይገኛል፡፡
እስከአሁን ድረስ እንዴት እንደሆነ ማስረዳት ባይችሉም፣ ልማቱ ኢኮኖሚያዊ ቀውሱን አንድ ቀን ይፈታዋል በሚል ማስተማመኛ ቃል ኑሮን እየገፋን እንገኛለን፡፡ በምን መንገድ ልማቱ የኑሮ ውድነቱና ግሽበቱን መቼና እንዴት? በከፊል ወይም በሙሉ ሊፈታው እንደሚችል ፍንጭ ማግኘት ግን አልተቻለም፡፡ መኖር እያዳገተን ችግርን እንድናውልና እንድናሳድር ከመምከርና ቃል ከመግባት ገፋ ሲልም አፈጻጸምን ከመራገም በስተቀር አዙሮ ሊደፋን በተቃረበው የኑሮ ውድነት ላይ መንግስትም ሆነ አስፈጻሚዎቹ በግልም ሆነ በጋራ ኃላፊነት በመውስድ ከስህተታቸው ተምረው፣ አዲስ ስልት ሲቀይሱ ማየት አልተቻለም፡፡ ዛሬም ዜማው “ተው ቻለው ሆዴ!” ነው፡፡
ኢህአዴግ የኑሮ ውድነትና ግሽበትን ተቆጣጥሮ ልማትን ማስፈን የሚያስችል ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲ መቀየስ አለመቻሉን ተቀብሎ እውነታውን በመጋፈጥ፣ የተሻለ ፖሊሲ ከመቀየስ ውጭ አቋራጭ መንገድ እንደሌለው ለመረዳት እጅግ ዘግይቷል፡፡ ከሃያ አንድ ዓመት አስተዳደር በኋላ ዛሬም በድህነት ስለመማቀቃችንና ኑሮአችን የተመሰቃቀለበት ምክንያቱ የቀድሞው ስርዓት ያስረከበን ባዶ ካዝና ነው ከሚል ስንኩል ያረጀና ያፈጀ ምክንያት መላቀቅ አልቻለም፡፡ ለኢኮኖሚያዊ ቀውስ መነሻ የነበረውና ከሩብ ምዕተ ዓመት በፊት የፈረሰው ስርዓት አስተዋፅኦ ከጊዜና ከሂደት ጋር ሞቶ እየተቀበረ ነው፡፡ ዛሬ ለምንገኝበት ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ሃገርን በማስተዳድር ላይ ከሚገኘው መንግስት በላይ ሌላ ተጠያቂ ከየትም ሊፈበረክ አይችልም፡፡ ደርግ ለኢኮኖሚያችን ውድቀት የቆሰቆሰው ጦርነት ለኢኮኖሚያዊ ውድቀቱ ምክንያት የሆነውን ያህል ለኑሮአችን መመሳቀልና ለግሽበት ኢህአዴግ የሚከተለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ብቸኛ ተጠያቂ ነው፡፡ ኢህአዴግም ይህንን መቀበል አለበት፡፡ አራት ነጥብ፡፡
የአቅርቦት ችግር፣ የምርት እጥረት፣ ግሽበት፣ የኑሮ ውድነትና መሰል ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መንስኤያቸው የመንግስት ፖሊሲና እቅዶች ድክመት ከመሆን ውጭ ሌላ መጠርያ ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ግሽበትና የኑሮ ውድነት እንደ መንፈስ በድንገት የሚከሰቱና በትእግስት ስለጠበቅናቸው የሚሰወሩ አይደሉም፡፡ ለኑሮ ውድነት መንስኤ የሆነውን መሰረታዊ ችግር ከመፍታት ይልቅ የማያጠግቡ ፖሊሲዎችንና እቅዶችንም በመጣፍ ዘለቄታ ያለው መፍትሄ ማምጣት አይቻልም፡፡ ሰሞኑን የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለተከበረው ምክር ቤት በሰጡት ኢኮኖሚያዊ ትንታኔ ላይ፣ ከዚህ ቀደም ያልታዩ ትንታኔዎች ሰምተናል፡፡ አካፋን አካፋ ለማለት የሄዱት ርቀት የሚያስደስት ነው፡፡ ዘይትና ስንዴ ለዓመታት በድጎማ እያስመጡ መቀጠልን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንዴት ሊሸከመው እንደሚችልና የውጭ ምንዛሪው ከሌላ አስፈላጊ አቅርቦት ላይ እየተቀነሰ እንደሆነ ሊያስረዱን አልደፈሩም፡፡ በከፍተኛ ወጭ የሚሸመተውና የሚረጨው ስንዴም በኢህአዴግ ፖሊሲ ልዩ ጥበቃ የሚደረግለት አርሶ አደር ያመረታትንም ያህል ወደ ገበያ አላመጣ በማለቱ፣ የተከሰተውን የአቅርቦት መመናመንና የዋጋ ንረት ለማውረድና አርሶ አደሩ ምርቱን እንዲያወጣ ለማስገደድ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የኛም ጥያቄ ለአቅርቦት መመናመን ቀጥተኛው ምክንያቱ አርሶ አደሩ ቢመስልም ይህንን ስልጣን እንዲቀዳጅ የተደረገው የሃገሪቱ የምርት አቅርቦት ስርዓቱ አርሶ አደሩን ለመከላከል በሚል መፈክር ስር በገበያ ስርዓት እንዳይመራ በመደረጉ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ መለስተኛና መካከለኛ ሜካናይዝድ እርሻዎች በሃገር በቀል አራሾች አማካኝነት እንዳይስፋፉ ኢህአዴግ መፈለጉና የተፈቀደ ግን የማይተገበር እንዲሆን የተለያዩ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ መሰናክሎች በአስፈሚዎች መቀፍቀፋቸው ለዚህ ችግር መንስኤ ተጠቃሽ ምክንያት ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማርያ ደሳለኝ፤ ግሽበት ወደ 18 ፐርሰንት መውረዱንና እድገታችን በ11 ፐርሰንት እንደሚያድግ ተንብየዋል፡፡ እሰየው!! ትንቢታቸው እንዲሰምር ምኞቴ ነው፡፡ የሚያነጋግረን ቁም ነገር ግን ይህ ብቻ አይደለም፡፡ 18 ፐርሰንት ወርሃዊ ግሽበት ቋሚ ገቢ ባለውና ደሞዙ በማያድግ ሕዝብ ውስጥ መሆኑን በነካ እጃቸው ባስረዱን ደግ ነበር፡፡ የዛሬ አመት ከ800 እስከ 1000 ይጠራ ነበረው የጤፍ ዋጋ ዛሬ 1600 ብር ነው፡፡ ዛሬም የሰራተኛው ደሞዝና የአርሶአደሩ ገቢ እዛው የዛሬ አመት በነበረበት ላይ ነው፡፡ በአንድ አመት ውስጥ የጤፍ ዋጋ በአማካይ 60 ፐርሰንት ሲያድግ የማህበረሰቡ ገቢ ባለበት ይገኛል፡፡ ወይም በዚሁ ምርት ላይ የማህበረሰቡ የመግዛት አቅም በ60 ፐርሰንት አሽቆልቁሏል፡፡ እሳቸው እንዳሉት ካለፈው ወር ወደዚህ ወር ስንሸጋገር፣ አብዛኛው ምርት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ አልታየም ይሆናል፡፡ ጤፍም ምስርም ሽሮም በርበሬም ከዛሬ ወር በፊት በነበሩበት ዋጋ ላይ ተገኝተው ይሆናል፡፡
አንድም ከፍተኛ የዋጋ ንረት ቋሚ ገቢ ያለውንና የመግዛት አቅሙ ወትሮውንም የተመታው ከገበያ እያወጣው በመሆኑና ግብይይት በመቀነሱ ዋጋ ባለበት ቆሟል አሊያም በሁለቱ ወራት መካከል የተከሰተው የዋጋ ንረት እዚህ ግባ የሚባል ስላልሆነ ወርሃዊ ግሽበቱ እንዲቀንስ አንዱ ምክንያት ሆኖ ሊታሰብ ይችላል፡፡ ጥሬ እውነታው ያለው ግን ወዲህ ነው፡፡ አይኑ እያየ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሸቀጣ ሸቀጥ ዋጋ ከ45 እስከ 100 ፐርሰንት ለጨመረበት በስልትና በተጠና አቀራረብ የተነረገው የግሽበት ቅንስናሽ ሊቆረጠምለት አይችልም፡፡ ቋሚ ገቢው እዛው እየዳከረ፣ የአቅርቦቱ ዋጋ ሰማይ እንደወጣ ተሰቅሎ በቀረበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በሰቀቀን ዋጋዉን አንጋጦ እየተመለከተ ሳለ፣ በተቀመረ ስሌት ስለ ግሽበት መቀነሰ መናገር ቢቻልም ውጤቱ ከማሸማቀቅ አያልፍም፡፡
የማህበረሰቡን ችግር ለዘለቄታው ከመፍታት አኳያ እዚህ ግባ የሚባል ሚና ባይኖራቸውም ከሊቢያ ጀምሮ በርካታ የአፍሪካ መንግስታት የዓለም አቀፍ ማህበረሰብን ያስደመሙ ፖሊሲዎች፣ እቅዶችና ፕላኖችን ሲቀረጹ ማስተዋል ተችሏል፡፡ ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ውስብስብ ከሆኑ ፖሊሲ፣ እቅዶችና ጥናቶች በተጨማሪ ቅድመ ዝግጅት፣ ትኩረት፣ የእለተ ተእለት ክትትል፣ የማስፈጸም ብቃት፣ ቁርጠኝነት በተለይ ደግሞ በሕዝብ ሃብት እራሳቸውን ከሚያደልቡ አስፈጻሚዎች የጸዳ ንፁህ እጅ ይሻል የሚል ጽኑ እምነት አለኝ ፡፡
በዚህ ጽሁፌ የኢህአዴግን የልማታዊ መንግስት ኢኮኖሚ ፖሊሲዎችና ችግሮቻቸውን ለመፈተሽ አልሞክርም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በቂ ጊዜ ተወስዶ ውይይት ሲካሄድበት ኖሮአል፡፡ ካስፈለገም ወደፊት ልመለስበት እችላለሁ፡፡ ግሽበቱ ወደ ችግር እያዳፋ እየወሰደን እንደሆነ ለመረዳት ከተፈለገ ከኢኮኖሚ ፍልስፍና ትንተናዎች በላይ ያለንበት ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ፍንትው አድርገው የሚሳዩን እውነታዎች የእለት ተእለት ኑሮአችንን የምንገፋበትን ሁኔታን ነው፡፡
ከላይ ለማንሳት እንደሞከርኩት በልማትና (Economic Development) በእድገት (Economic growth) እንዲሁም በግሽበት (Unadjusted inflation) ዙርያ የሚጠቀሱ ቁጥሮችና ፐርሰንቶች አንዳንዴም ፈገግ የሚያስደርጉ፣ አንዳንዴም የሚያስደምሙ በመሆናቸው በቁጥሮቹ ላይ ክርክር ማካሄዱ የመፍትሄው አካል ለመሆን የሚያግዝ አይደሉም፡፡ ኢህአዴግ ከፍ ከፍ ያሉ አመላካች ቁጥሮችንና ፐርሰንቶችን አይ.ኤምኤፍና ወርልድ ባንክ ሲዘግቧቸው፤ ኢኮኖሚያዊ ትንታኔውና ምንጩ የኒዮሊበራሎች አስተሳሰብና የትንተና ውጤት ቢሆንም ስሌቱንም ሆነ ስልቱን እንደ መረጃና የዘገባ ማጠናከርያነት ከመጠቀም ወደ ኋላ አይልም፡፡ ውጤቱ ኢህአዴግ ከሚፈልገው አመላካች ቁጥርና ፐርሰንታይል ወጣ ካለ ግን አምና ምስክር የነበሩት ዓለም አቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች ዘንድሮ በልማት ምቀኝነት መፈረጃቸው የተለመደ ነው፡፡
ይህ ሁሉ በቁጥር፣ በስሌትና በሰንጠረዥ የማሳመንና የሌለ ዳቦ የማጉረስ አባዜ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በእኔ እምነት ዛሬም የሕዝቡ ጥያቄ በማያወላዳ መልኩ እየቀረበ ነው፡፡ ጥያቄውም ፈረንጆቹ እንደሚሉት (where is the beef?) ወይም “ስጋው ወይም ዳቦው የታለ?” የሚል ነው፡፡
ኢህአዴግ የተለየ መረጃ የሚጠቅሱትን ማሸማቀቁ የተለመደ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ዛሬ ኢትየጵያ ያለችበት ኢኮኖሚያዊ እውነታን በቁጥር ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ በተለይ አይ.ኤምኤፍ በተለያዩ ሃገራት ላይ ኢኮኖሚያዊ ትንታኔ የሚያደርጉ ድርጅቶች እ.ኤ.አ በሰኔ ወር 2012 ላይ ባወጡት ዘገባ መሰረት፤ የኢትየጵያ አጠቃላይ ሃገራዊ ምርት እድገት ወደ ስድስት ፐርሰንት እንደሚያሽቆለቁል ተንብየዋል፡፡ የሚያስደስት ዜና ባይሆንም በኢኮኖሚያዊ ትንታኔ ላይ የተመሰረተ ዜና ነው፡፡ የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ ደግሞ የ11 ፐርሰንት እድገትን ተንብየዋል፡፡ በወቅቱ በወጣው ዘገባ ላይ፣ ለሃገሪቱ እድገት ማሽቆልቆል በምክንያትነት ከተነሱት ነጥቦች መካከል በዋነኛነት የተወሳው ደግሞ ግሽበትና ከፍተኛ የሆነ መንግስት ከብሄራዊ ባንክ የሚወስደው የሃገር ውስጥ የገንዘብ ብድር ነው፡፡ አዙሪቱ ግልጽ ነው፡፡ የግሽበቱ አይነተኛ መንስኤ ዝቅተኛ የምርት እድገትና የምርት አቅርቦት፣ ከፍተኛ የገንዘብ ስርጭት፣ ዝውውርና ሕትመት ሲደመር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው ያልተረጋገጠ፣ ከፍተኛ የገንዘብ ወጭን የሚጠይቁ፣ ለሙስናና ለብክነት የተጋለጡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችንና የስራ እድል ፈጠራ በሚል ስም የሚተገበሩ ለእድገት አስተዋጽኦ የሌላቸው ስራዎችን ፋይናንስ ማድረግ ነው፡፡
አለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ዘገባውን ሲያቀርብ፣ ግሽበቱ 40 ፐርሰንት ደርሶ ነበር፡፡ በርካታ ዓለም አቀፍ የመረጃ አደራጅ ተቋማት፤ ኢትዮጵያ የምትገኝበት የድህነት ደረጃ ከታች ወደ ላይ ሲለካ ከአንድ እስከ አምስት በሚገኙ ሃገራት ተርታ የሚያስቀምጧት ሲሆን ግሽበቱን ደግሞ ከላይ ወደ ታች ሲለካ 52.4 ፐርሰንት ካስመዘገበችው ቤላሩስ ቀጥሎ በ33.2 ፐርሰንት በሁለተኛ ደረጃ ያስቀምጧታል፡፡ ይህንን ሪፖርት ተክትሎ በመንግስት በኩል የተሰጠው ማብራሪያ፤ ከኢኮኖሚያዊ መለኪያዎች አኳያ አፈጻጸሙ እንዴት እንደሆነ ማወቅ ባይቻልም የተባለውን አመታዊ እድገቱ ሳይታጠፍ ግሽበቱን በጥቂት ወራት ምናልባትም በሶስት ወራት ውስጥ ወደ አንድ ዲጂት እንደሚያወርደው ተገልጾ ነበር፡፡ ይህ እንግዲህ ከሆነ ዓመታት አልፎታል፡፡ ግሽበቱም አለ፤ የኑሮ ውድነቱም ቀጥሏል፡፡ ከላይ የቀረበውን ትንታኔ ላጤነውና እንደ ኢህአዴግ ፍላጎት ከሆነ በወቅቱ የታቀደው ግሽበቱን ወደ አንድ ዲጂት አውርዶ የመሰረተ ልማት ግንባታውን አሁን ባለበት መጠን ማስቀጠል መቻል ነበር፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ኬኩን በልቶ ኬኩን ለማቆየት ከመመኘት ያለፈ ትርጉም እንዳልነበረው ዛሬም ከግሽበቱ መቀጠል ጋር በማነጻጸር መተንተን ይቻላል፡፡
ስር ነቀል ኢኮኖሚያዊ ልማትን ብቻ ሳይሆን ስር ነቀል ኢኮኖሚያዊ እድገትን፣ በኑሮ መሻሻልን ለማረጋገጥ ስንጠብቅ ዓመታት አልፈውናል፡፡ ዛሬ ልማቱ እየተጓዘ ያለበት መንገድ በሌላ ወቅት የምመለስበት ይሆናል፡፡ አጠቃላይ የተስተካከለ ግሽበቱን (Adjusted inflation) ግን እንደተባለው ወደ አንድ ዲጂት መወረዱ ቢቀር እንኳን ባለበት ለማቆምም አልተቻለም፡፡ በስታትስቲክስ ቢሮ ዘገባ መሰረት፤ እ.ኤ.አ በሰኔ ወር 30 ፐርሰንት አካባቢ የነበረው ግሽበት በሀምሌ ወር ወደ 40 ፐርሰንት ገደማ አድጓል፡፡ የሰኔ ወር ግሽበት ከሐምሌ ወር ጋር ሲነጻጸር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ የመስከረሙ ወር ደግሞ ወደ 18 ፐርሰንት አሽቆልቁሏል፡፡ ለግሽበቱ ማሽቆልቆል ምክንያት የለኝም፡፡ የጥናቱም ባለቤት በቂ ትንታኔ አላቀረበም፡፡ መንስኤው እንቆቅልሽ ቢሆንም ከግሽበቱ መቀነስ በኋላም ቢሆን የምግብና የጤፍ አቅርቦቶች ዋጋ ንረት እንደቀጠለ ነው፡፡ የከብት ስጋ ዋጋ አልቀመስ ካለና የሽቅብ ጉዞውን ከተያያዘው ከርሟል፡፡
ሰሞኑን ደግሞ ተራው የጥራጥሬና የበግና ፍየል ሆኗል፡፡ ይህ የሚያሳየው ግሽበቱ አቅማችንን ከመፈታተን አልፎ የማርያም መንገድና መሸሸጊያ እያሳጠን መሆኑን ነው፡፡ አኗኗራችንን ማስተካከልም ሆነ ከስጋ ወደ ሽሮ፣ ከከብት ወደ በግ ማፈግፈግ አልተቻለም፡፡ ይህ ለምን ሊሆን እንደቻለና ይህንኑ ውጣ ውረድ እስከመቼ መታገስ እንዳለብን መልስ ሰጭ የለም፡፡ የስታትስቲክስ ቢሮም ቢሆን ስለፐርሰንቱ መጨመርና መቀነስ፣ አልፎ አልፎም የትኞቹ ምርቶች እንደጨመሩ ከመግለጽ ውጭ የጭማሪው መንስኤ ምን እንደሆነና እንዴት እንደሚቀለበስ መልስ የለውም፡፡
ሃገራችን ውስጥ ያለው የተዛባ የመረጃ አቅርቦትና እጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ነገር ቢኖር፣ ከሰኔ ወር ወደ ሀምሌ ወር ስንሸጋገር የገዢውና የተጠቃሚው ቁጥር በግሽበቱ ልክ አለመጨመሩንና ምርትም አለማሽቆልቆሉን ብቻ ነው፡፡ ታድያ ግሽበቱና ኑሮ ውድነቱ እለት ከእለት የሚያሻቅበው ለምን ይሆን? ይህ የሕዝብ ጥያቄ አግባብነት ያለውና በቅጡ በኢህአዴግ በኩል መመለስ ያለበት ይመስለኛል፡፡
ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ሲባል በርካታ ጊዜያዊ መፍትሄዎች፣ ነገር ግን በረጅም ጊዜ ውስጥ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ለውጥረት የሚዳርጉ በችግር ፈችነት ተግባር ላይ ውለዋል፡፡ እነዚህ መፍትሄዎች የትም አላደረሱንምና ምናልባትም ከታች ከዘረዘርኳቸው መካከል አንዱ በተናጠል ብቻውን ወይም አብዛኞቹ በድምር አሊያም ሁሉም በጥቅል ለአጠቃላይ ችግሮቻችን ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉና መፍትሔ ሊሰጣቸው ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ከመጀመርያ ረድፍ ውስጥ ከሚጠቀሱት መካከል፣ መንግስት የበጀት ጉድለቱን የሚደጎምበትን መንገድ ለማረም ቃል በገባው መሰረት፣ ከብሄራዊ ባንክ ገንዘብ መበደርን አለማቆሙ፤ በሙስናና በዘረፋ ኢኮኖሚው ውስጥ የሚፈሰው የገንዘብ መጠን የግብይይት ስርዓቱን እያዛባው መሆኑ፤ የሃገሪቱ የውጭ ብድር ኢኮኖሚው ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ስለተለጠጠ፤ የውጭ ብድሮች ወለድ ከፍተኛና የክፍያ ዘመናቸው አጭር መሆናቸው ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ የግብይይት ስርዓታችን ኋላ ቀር በመሆኑና “ስግብግብ ነጋዴዎች” መብዛታቸው፤ የአምራቾች ህብረት ስራ ማህበራት የአርሶ አደሩን የምርት አቅርቦት በብቸኝነት በመቆጣጠራቸውና ብቸኛ ዋጋ ተማኝ በመሆናቸው፤ በስራ እድል ፈጠራ ስም ለምርታማነትም ሆነ ለምርት እድገት ቀጥተኛ ጠቀሜታ የሌላቸው የስራ እድሎችን መንግስት በስፋት ፋይናንስ እያደረገ የመግዛት ፍላጎትንና አቅምን ብቻ ከሚገባው በላይ ማዳበሩ፤ ኢኮኖሚያዊና አትራፊ ባልሆነ መንገድ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረጉት ጥረቶች የምርት ዋጋ ላይ ከባድ ተጽእኖ እያሳደሩ መሆኑ፤ በሁለተኛነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው፡፡ በመጨረሻም አብዛኛዎቹ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ኢኮኖሚያዊ አቅምን፣ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን ከግምት ከማስገባት ይልቅ ቅድሚያ የሚሰጠው አጣዳፊነታቸው መሆኑና በዚህ ላይ ፖለቲካዊ ዝንባሌ መጨመሩ ሌላው ኢኮኖሚያዊ ወጥመድ ነው፡፡
በአጠቃላይ መፍትሔ ከመንግስት ሊገኝ ይችላል የሚል ትምኔታዊ ግለሰብ አይደለሁም፣ ነገር ግን መንግስት በቅድሚ የድርሻውን ማንሳትና ከሕዝብ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ዝግጁነቱን ማረጋገጥ አለበት፡፡ እንደሚታወቀው መንግስታት የገቡትን ቃል ማስፈጸም ሲያዳግታቸው ማየት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ መንግስታት ቃላቸውን መጠበቅ ያልቻሉበትን መሰረታዊ ምክንያት መግለጽ አለመቻላቸው ግን ዴሞክራሲያዊ ነን ከሚሉ መንግስታት የሚጠበቅ ተግባር አይደለም፡፡ የስልጣን ባለቤትና የችግሩ ተጠቂ የሆነውን ሕዝብ ማክበርም ሆነ መፍራት የዴሞክራሲያዊ መንግስታት አይነተኛ መግለጫ መሆኑ በኢህአዴግም በኩል ተደጋግሞ መረጋገጥ አለበት፡፡ መንግስት የዜጎችን ኑሮ እያመሰቃቀለ የሚገኘውን ችግር ወቅታዊና ቀልጣፋ መፍትሄ በመስጠት መፍታት ባይችል እንኳ መፍትሔ መስጠት ያልተቻለበትን ምክንያትና በቀጣይ ለመስራት ያቀደውን ያለማሳወቅ እንዲሁም ሕዝቡ ለሚከፋውም ሆነ ለሚበጀው መዘጋጀት እንዲችል አለማድረግ በምርጫ ስልጣንን አግኝቶ ለሚያስተዳድር መንግስት ሊያሳስብው ይገባል፡፡

ጉዋንታናሞ በኢትዮጵያ/ቃሊቲ/

ቃሊቲን በጨረፍታ – በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ተወዳጁ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና “የቃሊቲው መንግስት” በሚል ርዕስ በፃፈው መፅሐፍ እስረኞች በቃሊቲው ማረሚያ ቤት የሚኖራቸውን የህይወት ገፅታ ጨርፎ አሳይቶናል፡፡ ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገ/ኪዳን ደግሞ “የቃሊቲ ሚስጥሮች” በተሰኘው መፅሐፉ የቅንጅት አመራሮች በቃሊቲ እስር ቤት በታሰሩ ወቅት እርስ በእርስ ምን እየተባባሉ እንደሚጎናነጡ እንዲሁ ጨርፎልናል፡፡ መቼም የቃሊቲ ጉድ በእነዚህ ሁለት መጽሐፍት ብቻ የሚገደብ እንዳልሆነ ለደቂቃም ቢሆን ግቢውን የረገጠ ይገባዋል፡፡ እናም በአርኪዎሎጂ ጥበብ ከተገኙ ጥንታዊ ከተሞች አንዱን የመሰለ ገፅታ በተላበሰው እስር ቤት ከየትኛውም ብሔር እና የሀገሪቱ ድንበር ያልተወከለ የለም- በእስረኝነት ማለቴ ነው፡፡ አይንህ ኢትዮጵያዊ እስረኛ ማየት ቢደብረው የጃማይካ፤ የስዊድን፤ የስዊዘርላንድ፤ የአሜሪካ፤ የናይጄሪያ፤ የታንዛንያ፤ የኬንያ፤ የሶማሊያ፤ የኤርትራ… ሰዎችን እንደልብህ ታያለህ፡፡ ሌላው በቃሊቲ በመኖርህ የምታገኘው ጥቅም ምን መሰለህ? ዘባተሎ የለበሰ ፈረንጅ እስረኛ በብር ከስሙኒ ብቻ የሚሸጠውን የግቢውን ሻይ እንድትጋብዘው ይጠይቅሃል፤ ይህን ጊዜም ኩራትህ ተራራን ያክላል፤ ቃሊቲ ባትታሰር ግን ይህንን እድል አታገኝም፤ ምንአልባትም ይህንኑ ፈረንጅ አንተው ራስህ ደንበል ሕንፃ ጋ ቆመህ “ሚስተር…” እያልክ ገንዘብ ልትለምነው ትችል ነበር፡፡ ማን ያውቃል? እንግዲህ እነዚህ ሁሉ የተለያየ ታሪክ እና ወንጀል ከቃሊቲ ወንጀል ጋር የተጣቡ ናቸው፡፡
እመነኝ የቃሊቲ ታሪክ መቶ እና ሁለት መቶ መፅሐፍም ቅም የሚለው አይደለም፤ የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚ፤ የፍትህ፤ የብልጠት፤ የስግብግብነት፤ የጭካኔ፤ የሀሰተኝነት… ምሽግ ነውና፡፡ በአጠቃላይ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት “እግሩ የጣለው” ወይም “ወንጀሉ የጣለው” አልያም እንደ እኔ “አቃቤ ሕግ የጣለው” ፀሐፊ ሁሉ ተርኮ የማይጨርሰው አስገራሚ፤ አስደናቂ፤ አሳዛኝ፤ አማራሪ፤ አሸፋች … ትርክት ያገኛል፡፡ እነሆም በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለስድስት ቀን ያህል በአቃቤ ሕግ በተጣልኩበት ጊዜ ያየሁት እና የሰማሁትን እነግርህ ዘንድ ወደድኩ፡፡
በቅድሚያ – የ16ኛ ወንጀል ችሎት
“ፍትህ ጋዜጣን” መስርቼ በዋና አዘጋጅነት መምራት ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ በጋዜጣዋ ላይ በሚስተናገዱ ዘገባዎች እና ነፃ ሀሳቦች የተነሳ የሀገሬ መንግስት “ደመኛው” አድርጎኛል፡፡ (አቤት በገዛ መንግስት እንደክፉ ባላጋራ መታየት እንዴት ያሳቅቃል?) በዚህም የተነሳ ከጥቃቅን እስከ ግዙፍ ማስፈራሪያዎች ( ጥቃቅን ሲባል የመንግስት አነስተኛ የስራ ፈጠራ ዘርፍ ብቻም እንዳይመስልህ፤ ለጋዜጠኞች ተብሎ የሚዘጋጅ ጥቃቅን ሽብሮች አሉና) ወከባዎች፤ የሰላይ ጫናዎች፤ ተደራራቢ ክሶች… የዕለት ቀለቤ ሆነዋል፡፡ …ከዕለታት በአንዱ ቀንም (ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም) ከመአት ክሶቼ ሶስቱ ተመዘው በከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ለመቅረብ ተገደድኩ፡፡
በዕለቱ ፍርድ ቤት የተገኘሁት ከሁለት ጠበቆቼ ጋር ሶስተ ሆነን ሲሆን፤ ከሳሾቼ አቃቤያን ህግም በተመሳሳይ ቁጥር ሶስት ሆነው ነው የተገኙት፡፡ ከጠዋቱ አራት ሰዓት አካባቢም ችሎቱ ተሰየመ፡፡ ዳኛውም ቦታቸውን ያዙ፡፡ አስቀድሞ አቃቤ ህግ ላቀረበው ክስም መልስ እሰጥ ዘንድ ተጠየኩ፡፡ አንደኛው ጠበቃዬ ለቀረበው ክስ መቃወሚያ ያሉትን ሀሳብ አቀረቡ፡፡ አቃቤያን ህጉም የጠበቃዬን መቃወሚያ እንደኦርኬስትራ ተቀባብለው አጣጣሉት፡፡ ዳኛውም ተደረቡ- የቀረበውን የክስ መቃወሚያም ውድቅ በማድረግ፡፡ አስከትለውም አቃቤያን ህጉ ክሱን ያብራሩ ዘንድ ጠየቁ፡፡ “ሳተናዎቹ” አቃቤያን ህግም ለሶስት እየተቀባበሉ ሶስቱን ክሶች ተገን አድርገው የሀሰት ክሶች ደረደሩ፡፡ ድርዳሬውን ሲያበቁም በዳኛው የእምነት ክህደት ቃሌን ተጠየኩ፡፡ ክሱ ውሸት እንደሆነ እና ያጠፋሁትም ሆነ የጣስኩት ህግ እንደሌለ አስረዳሁ፡፡ ጠበቃዬም ቀጠሉና ከችሎት በዋስ ተለቅቄ የክስ ሂደቱን እከታተል ዘንድ ጠየቁ፡፡ ይህን ጊዜም አቃቤያነ ህግ ተቃውሞአቸውን በእሩምታ አሰሙ፡፡ የተቃውሞ ምክንያታችን ያሉትን ሲያብራሩ “ ተከሳሹ በዚህ ጉዳይ ተከሶ ለፖሊስ ቃል ከሰጠ በኋላ አሁንም የአመጽ ቅስቀሳውን አላቋረጠም” አሉና ሐምሌ 24 ቀን 2004 ዓ.ም. ከ”ፍኖተ-ነፃነት” ጋዜጣ ጋር ያደረኩትን ቃለ-መጠይቅ እንደ ማስረጃ አቀረቡ፡፡ በጣም ደነገጥኩኝ ምክንያቱም አቃቤያን ህግ የያዙት የክስ መዝገብ ራሱ ለፖሊስ ቃል የሰጠሁት ሐምሌ 25 ቀን 2004 ዓ.ም. እንደሆነ በግልጽ ይናገራልና፡፡ ሆኖም ደፋሮቹ አቃብያን ህግ የሐሰት ክርክራቸውን ቀጠሉ፡፡ ሐምሌ 28 ቀን 2004 ዓ.ም. ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረኩት ቃለ-መጠይቅ ሐምሌ 13 ቀን 2004 ዓ.ም. የታገደውን የፍትህ ጋዜጣ ህትመት “በሲዲ ስላለኝ እለቀዋለሁ” ብሎ ዝቷል አሉ፡፡ አሁን ዳኛው ማስረጃ የፈለጉ መሰሉ፡፡ እናም “ጋዜጣው የታለ?” ሲሉ ጠየቁ፡፡ አንደኛው አቃቤ ህግ ጋዜጣውን እንዳልያዙ ተናገሩ፡፡ ይህን ጊዜም እርግጠኛ ሆንኩ፤ ዳኛው “ያለማስረጃ ውንጀላውን አንቀበልም” እንደሚሉ፡፡ ግና! ምን ዋጋ አለው፤ ያለማስረጃ ክስ ቢቀርብም ለዳኛው ምንም ማለት አልነበረምና የችሎቱ ታዳሚ እስኪታዘብ ድረስ ዳኛውና አቃቤያነ ህግ “ሰምና ወርቅ” ሆነው መስራታቸውን አደሩት፡፡ በዚህ መሀል አንደኛው አቃቤ ህግ ከስነ-ስርዓት ውጪ በሆነ መልኩ አዲስ ክስ አቀረበ፡፡ “ይህ ጉዳይ እልባት እስኪያገኝ ድረስ ፍትህ ጋዜጣ ይታገድልን” የሚል፡፡ አሁን በችሎቱ ከተገኙት ውስጥ አብዛኛው ትእግስታቸው በማለቁ ከመገረም አልፈው ማጉረምረም ጀመሩ፡፡ እናም ዳኛው “ክስ በዚህ መልኩ እንደማይቀርብ” ተናግረው አቃቤ ህጉን ይገስፃሉ ብለው የጠበቁ ነበሩ፡፡ እሳቸው እቴ! ምንተዳቸው! ይልቁኑም በመንበራቸው ተመቻቹና ከህገ ደንብ ውጭ ድንገት የእኔ ጠበቆች መልስ እንዲሰጡ ጠየቁ፡፡ (እዚህ ጋር ከኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ጋር በተያያዘ የተነገረ አንድ ቀልድ ትዝ አለኝ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፤- በድህረ ምርጫ 97 የቅንጅት አመራሮች ተከሰው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡ ከተከሳሾቹም መካከል ከምስራቅ ጎጃም ተይዘው የመጡ ይገኙበታል፡፡ መንግስትም ለነዚህ ተከሳሾች ከዛው ከምስራቅ ጎጃም የሀሰት ምስክር አምጥቶ ስለነበ ምስክሩ መስክረው ሲጨርሱ ድንገት ከተከሳሾቹ መካከል ከመንደራቸው ወደ አዲስ አበባ ከመጣ አስር አመት ያለፈውን አንድ ጋዜጠኛ ያያሉ፡፡ ጋዜጠኛው የተከሰሰው በሚሰራበት ጋዜጣ ላይ በፃፈው ፅሑፍ መሆኑን የተረዱት አርሶ አደሩ የአቃቤ ህግ ምስክር ችሎቱን እንዲህ ሲሉ በትህትና ጠየቁ “ጌታው! ያያ እከሌ ልጅም እዚህ ስላለ መንግስት ሁለት ጊዜ የአበል እና የትንስፖርት ከሚያወጣ እሱም ላይ መስክሬበት ልሂድ?”)
ከመራራው ቀልድ እንፋታና ወደችሎቱ እንመለስ፡፡ ደህና! አዲስ ለቀረበው ክስም ጠበቆቼ መልስ ሰጡ፡፡ በዚህ መሀል እኔው እራሴ መናገር እንደምፈልግ ገልጬ እንዲፈቀድልኝ ጠየኩ፡፡ ለተከሰሰ የሚሰጥ መብት ነውና ተፈቀደልኝ፡፡ ፍኖተ-ነፃነት ጋዜጣ ላይ ቃለ-መጠይቅ የሰጠሁት ለፖሊስ ቃል ከመስጠቴ አንድ ቀን በፊት እንደሆነ፤ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይም አቃቤ ህጎች “ዝቷል” ያሉት ውሸት እንደሆነና ጋዜጣው መጠቶ እንዲታይ፤ እንዲሁም አንድ ጋዜጣ የሚታገደው ለብሄራዊ ደህንነት አስጊ ዘገባ መያዙ በማስረጃ ሲረጋገጥ ብቻ እነደሆነ የፕሬስ ህጉ በግልፅ የደነገገ መሆኑን ጠቅሼ፤ መታተም ከአቆመ ከአንድ ወር በላይ የሆነ ጋዜጣ፤ ያውም ምን አይነት ዘገባ ይዞ ሊወጣ እንደሚችል ያልታወቀ ጋዜጣን አዘጋጁ ድንገት እዚህ ስለተገኘ ብቻ ይታገድልኝ ማለት “ህገ-ወጥነት” እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ አስረዳሁ፡፡ በዚህ መሀል ዳኛው ተጨነቁ፡፡ ትንሽ አንሰላሰሉ እና “እየደበራቸው” መሆኑ በሚያስታውቅ መልኩ “የእገዳ ጥያቄውን ” ውድቅ አደረጉ፡፡ ነገር ግን የዋስትና ጥያቄዬን ከህግ ውጭ “ በልዩ ሁኔታ ከልክለናል” አሉ፡፡ ( ያ ልዩ ሁኔታ ምን ይሆን? ምንስ ማለት ነው? … ብቻ በችሎት ከተገኙት ውስጥ የገባው አንድም ሰው ያለ አልመሰለኝም) ከዚህ በኋላ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሆኜ እንድከራከር ተወሰነ፡፡ ችሎቱም ለነሐሴ 28 ቀን 2004 ዓ.ም ተቀጥሮ ተበተነ፡፡ እነሆም በእንደዚህ ባለ “ሚስጥራዊ”ሁኔታ በተካሄደ ችሎት ነበር ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለስድስት ቀናት ያህል ያሰለፍኩት፡፡
ከችሎቱ ውጭ
ችሎቱ ዋስትና ከልክሎኝ በመጠናቀቁ በጥቂት ፖሊሶች ተከብቤ፤ በበርካታ የፍትህ አንባቢዎች ታጅቤ በፍርድ ቤቱ ግቢ ወደሚገኘው “አንበሳ ቤት” አመራሁ፡፡ ይህን ጊዜም ከከበቡኝ ሰዎች መሀከል የማበረታቻ ድምፅ መሰማት ጀመረ፡፡ ቀስ በቀስም ድምፁ እየበረታ፤ ጭብጨባውም እየበዛ ሄደ፡፡ ባልተጠበቀ ሁኔታ እየተፈጠረ ባለው ነገር የተደናገጡት ፖሊሶች ህዝቡ ዝም እንዲል እና እንዲመለስ በቁጣ አዘዙ፡፡ ነገር ግን በችሎቱ ድራማ እልህ የተጋባው ሕዝብ የፖሊሶቹን ማስፈራሪያ ችላ ብሎ ጭብጨባውን እና ፉጨቱን ሳያቆም “አንበሳ ቤት” ደረስኩ፡፡ በተለምዶ “አንበሳ ቤት” የሚባለው በፍርድ ቤቱ ግቢ የሚገኝ ጣሪያው ላሜራ ሆኖ ዙሪያ ገባው በብረት ፍርግርግ የተዋቀረ ነው፡፡ የቤቱ አገልግሎት አብዛኛውን ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው ዋስትና የሚከለከሉ እና ሳይታሰሩ ሲከራከሩ ቆይተው የሚፈረድባቸው እስረኞች ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስኪላኩ ለሰአታት የሚቆዩበት ቤት ነው፡፡ ቤቱ አንዳንዴም ከወህኒ ቤት የመጡ እስረኞች ችሎት አስኪቀርቡ ለጥበቃ አመቺ ነው በሚል እሳቤ ለማቆያነት ያገለግላል፡፡ እናም ይህ ቤት ስያሜውን ያገኘው በአሰራሩ ስድስት ኪሎ አካባቢ ከሚገኘው “አንበሳ ግቢ” ጋር ሲለሚመሳሰል ይመስላኛል – አንበሳ ቤት፡፡
እኔም ከችሎቱ በቀጥታ ወደ አንበሳ ቤት እንድገባ ከተደረገ በኋላ ከአጀቡኝ ፖሊሶች መካከል አንዱ መዝጊያውን ከውጪ በኩል ቀረቀረውና በትልቅ ጓጉንቸር ቆለፈው፡፡ አሁንም ከፖሊሶች በላይ የተቆጡት የችሎቱ ታዳሚዎች ከውጭ በኩል የአንበሳ ቤቱን ከበው ማበረታታቸውን ቀጥለዋል፡፡ የፖሊሶቹ “ዞር በሉ” ማስፈራሪያም እንዲሁ እንደቀጠለ ነው፡፡ በዚህ መሀል ድንገት በቦታው የነበሩ ጥቂት ጋዜጠኞች ረጅም ጊዜ እስር ቤት ሊቆይ ይችላል ብለው ስለሰጉ ነው መሰለኝ “የምትናገረው የመጨረሻ ንግግር ካለህ ተናገር” አሉና መቅረጸ ድምፃቸውን ለስራ አዘጋጁ፡፡ ከህዝቡ መሀከል በርከት ያሉ ወጣቶች ሞባይላቸውን ደቅነው ጋዜጠኞቹን ተቀላቀሉ፡፡ ግራ ገባኝ፡፡ የምናገረውም ጠፋኝ፡፡ ውስጤን እልህ ተናንቆታል፡፡ የአንበሳ ቤቱን የከበቡት ጋዜጠኞች እና የፍትህ አንባቢዎች ደግሞ የምለውን ለመቅዳት እየወተወቱኝ ነው፡፡ ከጥቂት ማመንታት በኋላ እንዲህ አልኩ፡፡
“የዛሬው የችሎቱ ድራማ ከአምባገነኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ህልፈት በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡ እናም ድራማው አስቂኝም አሳዛኝም ነው፡፡ ግና! አንድ ነገር እርግጠኛ ሁኑ፤ ይኸውም የስርአቱ ግብአተ መሬት እየተቃረበ ለመሆኑ ከምልክቶቹ አንዱ ዛሬ ያያችሁት አይን ያወጣ እና ያፈጠጠ ዳኝነት መሆኑን፡፡”
ከዚህ በኋላ ፊቴን አዙሬ በአንበሳ ቤት ውስጥ ከተደረደሩት ወንበሮች በአንዱ ላይ ጀርባዬን ከቤቱ ባሻገር ለተሰበሰቡት ሰዎች ሰጥቼ ተቀመጥኩ፡፡ ይህን ጊዜም እስካሁን ድረስ ያላስተዋልኩት አንድ እስረኛ ከእኔው ጋር በዛች ቤት መኖሩን ተረዳው፡፡ እድሜው በግምት አርባዎቹ መጨረሻ ላይ ይሆናል፡፡ ቁመቱ እንደሸንበቆ የተመዘዘ ቢሆንም ኑሮ ደህና አድርጎ እንዳጎሳቆለው ያስታውቃል፡፡ ንትብ ያለ ውሃ ሰማያዊ ጃኬት እና አዳፋም ጥቁር ሱሪ ለብሷል፡፡ ጫማውም ቢሆን ብዙ ቦታ የተጣጠፈ፤ ቀለሙ ታይቶ የማይታወቅ አሮጌ እስኒከር ነው፡፡ ቀና ብዬ አየሁት፡፡ ፈገግ አለና የአንገት ሰላምታ ሰጠኝ፡፡ በርከት ያሉ ሰዎች አብረውኝ በመምጣታቸው ግራ የተጋባ ይመስላል፡፡ ፈጠን ብዬ ሰላምታውን ሞቅ ባለ ሁኔታ መለስኩለት፡፡ በሰላምተዬ ምላሽ ተበረታቶ ነው መሰለኝ “እነዚህ ሁሉ ጓደኞችህ ናቸው ?” የሚል ጥያቄ አቀረበልኝ፡፡ “አዎን” ስል መለስኩለት፡፡ “አይዞህ” አለኝ፡፡ (ይች “አይዞህ” ለእስረኛ እንዴት አይነት ስንቅ መሰለችህ?)
የሆኖ ሆኖ እኔና የአንበሳ ቤት ጓደኛዬም እንደዋዛ ወደ ጭውውት ገባን፡፡
“ምን አድርገህ ነው የመጣኸው?” ፊቱን አጨልሞ ባለቤቱ ከስሳው እንደሆነ ነገረኝ፡፡
“ለምን ከሰሰችህ?”
“አንድ ልጅ ወልደን ተለያይተናል፡፡ እናም ልጁን ማሳደጊያ ገንዘብ አይረዳኝም ብላ ነው የከሰሰችኝ”
“አንተ ለምን አትረዳትም?”
“ስራ የለኝም ነበር በቅርቡ ነው ስራ ያገኘሁት”
“ታዲያ ስራ ከጀመርክ ለምን አትረዳትም?”
“ከደሞዜ ላይ ተቆራጭ ላደርግላት ተስማምቼ ነበር፡፡ እነሱ ግን እንድሰጣት የወሰኑብኝ ብር ከአቅሜ በላይ ነው፡፡”
“ችሎት ቀርበህ ነበር እንዴ?”
“አዎን ቅድም ቀርቤ ለከሰአት ተቀጥሬአለሁ”
“ለምን?”
“ዳኛው የወሰኑት በወር መቶ ብር እንድሰጣት ነው፡፡ እኔ ደግሞ ያንን መስጠት አልቻልኩም፡፡ እናም ፍርድ ቤቱ እንድታሰር ወስኗል፡፡” (…እግዞ መቶ ብር የሌለው ሰው ወደ እስር ቤት የሚላክበት ሁኔታ ከዚህ ሀገር በቀር የት ይገኝ ይሆን? ኢትዮጵያ እጆቿን የምትዘረጋው ወዴት ይሆን? ወደ አሜሪካ ወይስ አረብ ሀገር?)
“እየሰራህ ከሆነ ለምንድነው መቶ ብር መስጠት ያቀተህ?”
“አልገባህም! እኔ ስራ ከጀመርኩ ገና 18 ቀኔ ነው፡፡ እነሱ ደግሞ ዛሬውኑ ገንዘቡን መስጠት እንድጀምር ወጥረው ያዙኝ፤ ደሞዝ እስክቀበል ታገሱኝ ብል ሊሰሙኝ አልቻሉም፡፡”
ይህን ጊዜ ትንሹ ወንድሜ በርገር እና የታሸገ ውሃ ይዞ ጠራኝ፡፡ የመጀመሪያውን የእስር ቤት ስንቅ እጄን በፍርግርጉ አሾልኬ ተቀበልኩ፡፡ ከመጀመሪያው እስረኛ ጓደኛዬም ጋር ተካፍለን መመገብ ጀመርን፡፡ ተመግበን እንደጨረስንም የተለያዩ ወዳጆቼ እና የማላውቃቸው የፍትህ አንባቢዎች በፍርግርጉ በኩል እየመጡ “ሞራል እና የስንብት ቃል” መስጠታቸውን ስለጀመሩ ከእስረኛው ጓደኛዬ ጋር የጀመርኩትን ወግ መጨረስ አልቻልኩም፡፡
በእንዲህ አይነት ሁኔታም በግምት ለሁለት ሰአት ተኩል ያህል ከቆየሁ በኋላ ፖሊሶቹ ጓጉንቸሩን ከፍተው ከአንበሳ ቤቱ እንድወጣ አድርገው ወደ ዋናው የፍርድ ቤቱ በር አካባቢ ከወሰዱኝ በኋላ ፊቷን ወደ መውጫው በር አዙራ የቆመች አንዲት የደከመች የፖሊስ ነጭ ሚኒባስ ውስጥ ከተቱኝ፡፡ ይህን ጊዜም ለአንዴ እና ለመጨረሻ ስንብት ፍርድ ቤት የተሰበሰቡትን ቤተሰቦቼን፤ ጓደኞቼን፤ ባልደረቦቼን እና የፍትህ አንባቢዎችን በሚኒባሱ መስኮት እጄን አውጥቼ ሰላምታ ሰጠዋቸው፡፡
መኪናዋ መንቀሳቀስ ጀመረች፡፡ በሶስት ፖሊሶች ታጅቤም ከፍተኛውን ፍርድ ቤት ለቀቅን፡፡ ሆኖም ሚኒባሷ ከልደታ ቤተ ክርስቲያን ከፍ ብሎ ከፍርድ ቤቱ ፊት ለፊት በሚገኘው አስፓልት ቁልቁል በመውረድ ሳር ቤት ከደረስን በኋላ በአቋራጭ ቃሊቲ የሚያደርሰንን መንገድ ከመያዝ ይልቅ ወደ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ አመራች፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች ጉዞ በኋላ ፖሊስ ጣቢያው በር ላይ ደረስን እና ከበር ላይ ቆምን፡፡ ጋቢናው የተቀመጠው ልጅ እግር ፖሊስም ከመኪናው ወርዶ ወደ ጣቢያው ገባ፡፡ ይህን ጊዜም በር ላይ የቆሙ የጣቢያው ፖሊሶች ለጥበቃ ካጀቡኝ ፖሊሶች ጋር የወዳጅነት ሰላምታ ተለዋወጡ፡፡ በዚህ መሀል አንዱ ፖሊስ አንገቴ ላይ በጠመጠምኩት “ስከርፍ” አማካኝነት ያወቀኝ መሰለ፡፡ ማንነቴንም ማወቁንም በፊት ገጽታው እየነገረኝ ወደ ተቀመጥኩበት ወንበር ተጠግቶ “አውቅሃለው! ተመስገን አይደለህ?” አለኝ ጓደኞቹ እንዳይሰሙት ድምጹን ዝቅ አድርጎ፤ አንገቴን በመነቅነቅ አረጋገጥኩለት፡፡ ምን አድርጌም እንደሆነ ጠየቀኝ፡፡ ወዴት እየሄድኩ እንደሆነም ገብቶታል፡፡ ነገርኩት፡፡ ጥቂት እንደመከፋት አለና ጣቱን ወደ ሰማይ ቀስሮ “አይዞህ እግዚአብሔር አለ” አለና አበረታታኝ፡፡ በዚህ መሀል ወደ ውስጥ የገባው ፖሊስ በሌሎች ሶስት ፖሊሶች የታጀቡ በግምት እድሜያቸው አሰራ ስምንት አመት የማይሞላቸውን ሶስት እስረኞችን ከእኔ ጋር ስለቀላቀሏቸው የአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ጉዳይ እንደተጠናቀቀ የገባው ጎልማሳው የሚኒባሱ ሹፌር ሞተሩን አስናሳ፡፡ ጉዞ ወደ ቃሊቲ ሆነ፡፡
ከፊት ለፊቴ ለተቀመጠው ፖሊስ ወንድሜ ልብስ ይዞ ክራውን ሆቴል አጠገብ ስለሚጠብቀኝ ስንደርስ እንድቀበለው መኪናውን በማቆም ይተባበሩኝ እንደሆነ ጠየኩት፡፡ የጠየኩት ፖሊስ ከመመለሱ በፊት ጋቢና የተቀመጡት ሁለቱ ፖሊሶች እና ሹፌሩ ምንም ችግር እንደሌለው እና እንደሚተባበሩኝ ተደራርበው መለሱልኝ፡፡ አመስግኜ ትኩረቴን ከመኪናው ውጪ አደረግኩ፡፡ በግምት ከሰላሳ ደቂቃ በኋላም ክራውን ሆቴል ደርሰን መኪናው በሩ ላይ ቆመ፡፡ ወንድሞቼ ከእኛ ቀድመው በመድረስ ፍራሽ፤ ብርድ ልብስ እና አንሶላ ይዘው እየጠበቁኝ ስለነበር ጊዜ ሳላጠፋ ተቀብያቸው ጉዟችንን ቀጠልን፡፡ ከጥቂት ደቂቃ በኋላም ከሀገሪቱ በስፋት ተስተካካይ ወደሌለው አስቀያሚ እስር ቤት በር ላይ ደርሰን ሹፌሩ ደጋግሞ ጡሩንባ ያሰማ ጀመር፡፡ የእስር ቤቱ ዋና በርም ከውስጥ ወደ ውጭ ወለል ብሎ ተከፈተና ሚኒባሷ ገባች፡፡ ከፍርድ ቤት አጅበው ያመጡኝ ፖሊሶችም ለቃሊቲ ፖሊሶች አስረክበውኝ ሲያበቁ ርክክቡን የሚያረጋግጥ ደረሰኝ ተቀብለው ሞቅ ባለ ፈገግታ ተሰናበቱኝ፡፡

እመነኝ የቃሊቲ ታሪክ መቶ እና ሁለት መቶ መፅሐፍም ቅም የሚለው አይደለም፤ የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚ፤ የፍትህ፤ የብልጠት፤ የስግብግብነት፤ የጭካኔ፤ የሀሰተኝነት… ምሽግ ነውና፡፡ በአጠቃላይ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት “እግሩ የጣለው” ወይም “ወንጀሉ የጣለው” አልያም እንደ እኔ “አቃቤ ሕግ የጣለው” ፀሐፊ ሁሉ ተርኮ የማይጨርሰው አስገራሚ፤ አስደናቂ፤ አሳዛኝ፤ አማራሪ፤ አሸፋች … ትርክት ያገኛል፡፡ እነሆም በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለስድስት ቀን ያህል በአቃቤ ሕግ በተጣልኩበት ጊዜ ያየሁት እና የሰማሁትን እነግርህ ዘንድ ወደድኩ፡፡

በቅድሚያ – የ16ኛ ወንጀል ችሎት

“ፍትህ ጋዜጣን” መስርቼ በዋና አዘጋጅነት መምራት ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ በጋዜጣዋ ላይ በሚስተናገዱ ዘገባዎች እና ነፃ ሀሳቦች የተነሳ የሀገሬ መንግስት “ደመኛው” አድርጎኛል፡፡ (አቤት በገዛ መንግስት እንደክፉ ባላጋራ መታየት እንዴት ያሳቅቃል?) በዚህም የተነሳ ከጥቃቅን እስከ ግዙፍ ማስፈራሪያዎች ( ጥቃቅን ሲባል የመንግስት አነስተኛ የስራ ፈጠራ ዘርፍ ብቻም እንዳይመስልህ፤ ለጋዜጠኞች ተብሎ የሚዘጋጅ ጥቃቅን ሽብሮች አሉና) ወከባዎች፤ የሰላይ ጫናዎች፤ ተደራራቢ ክሶች… የዕለት ቀለቤ ሆነዋል፡፡ …ከዕለታት በአንዱ ቀንም (ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም) ከመአት ክሶቼ ሶስቱ ተመዘው በከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ለመቅረብ ተገደድኩ፡፡

በዕለቱ ፍርድ ቤት የተገኘሁት ከሁለት ጠበቆቼ ጋር ሶስተ ሆነን ሲሆን፤ ከሳሾቼ አቃቤያን ህግም በተመሳሳይ ቁጥር ሶስት ሆነው ነው የተገኙት፡፡ ከጠዋቱ አራት ሰዓት አካባቢም ችሎቱ ተሰየመ፡፡ ዳኛውም ቦታቸውን ያዙ፡፡ አስቀድሞ አቃቤ ህግ ላቀረበው ክስም መልስ እሰጥ ዘንድ ተጠየኩ፡፡ አንደኛው ጠበቃዬ ለቀረበው ክስ መቃወሚያ ያሉትን ሀሳብ አቀረቡ፡፡ አቃቤያን ህጉም የጠበቃዬን መቃወሚያ እንደኦርኬስትራ ተቀባብለው አጣጣሉት፡፡ ዳኛውም ተደረቡ- የቀረበውን የክስ መቃወሚያም ውድቅ በማድረግ፡፡ አስከትለውም አቃቤያን ህጉ ክሱን ያብራሩ ዘንድ ጠየቁ፡፡ “ሳተናዎቹ” አቃቤያን ህግም ለሶስት እየተቀባበሉ ሶስቱን ክሶች ተገን አድርገው የሀሰት ክሶች ደረደሩ፡፡ ድርዳሬውን ሲያበቁም በዳኛው የእምነት ክህደት ቃሌን ተጠየኩ፡፡ ክሱ ውሸት እንደሆነ እና ያጠፋሁትም ሆነ የጣስኩት ህግ እንደሌለ አስረዳሁ፡፡ ጠበቃዬም ቀጠሉና ከችሎት በዋስ ተለቅቄ የክስ ሂደቱን እከታተል ዘንድ ጠየቁ፡፡ ይህን ጊዜም አቃቤያነ ህግ ተቃውሞአቸውን በእሩምታ አሰሙ፡፡ የተቃውሞ ምክንያታችን ያሉትን ሲያብራሩ “ ተከሳሹ በዚህ ጉዳይ ተከሶ ለፖሊስ ቃል ከሰጠ በኋላ አሁንም የአመጽ ቅስቀሳውን አላቋረጠም” አሉና ሐምሌ 24 ቀን 2004 ዓ.ም. ከ”ፍኖተ-ነፃነት” ጋዜጣ ጋር ያደረኩትን ቃለ-መጠይቅ እንደ ማስረጃ አቀረቡ፡፡ በጣም ደነገጥኩኝ ምክንያቱም አቃቤያን ህግ የያዙት የክስ መዝገብ ራሱ ለፖሊስ ቃል የሰጠሁት ሐምሌ 25 ቀን 2004 ዓ.ም. እንደሆነ በግልጽ ይናገራልና፡፡ ሆኖም ደፋሮቹ አቃብያን ህግ የሐሰት ክርክራቸውን ቀጠሉ፡፡ ሐምሌ 28 ቀን 2004 ዓ.ም. ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረኩት ቃለ-መጠይቅ ሐምሌ 13 ቀን 2004 ዓ.ም. የታገደውን የፍትህ ጋዜጣ ህትመት “በሲዲ ስላለኝ እለቀዋለሁ” ብሎ ዝቷል አሉ፡፡ አሁን ዳኛው ማስረጃ የፈለጉ መሰሉ፡፡ እናም “ጋዜጣው የታለ?” ሲሉ ጠየቁ፡፡ አንደኛው አቃቤ ህግ ጋዜጣውን እንዳልያዙ ተናገሩ፡፡ ይህን ጊዜም እርግጠኛ ሆንኩ፤ ዳኛው “ያለማስረጃ ውንጀላውን አንቀበልም” እንደሚሉ፡፡ ግና! ምን ዋጋ አለው፤ ያለማስረጃ ክስ ቢቀርብም ለዳኛው ምንም ማለት አልነበረምና የችሎቱ ታዳሚ እስኪታዘብ ድረስ ዳኛውና አቃቤያነ ህግ “ሰምና ወርቅ” ሆነው መስራታቸውን አደሩት፡፡ በዚህ መሀል አንደኛው አቃቤ ህግ ከስነ-ስርዓት ውጪ በሆነ መልኩ አዲስ ክስ አቀረበ፡፡ “ይህ ጉዳይ እልባት እስኪያገኝ ድረስ ፍትህ ጋዜጣ ይታገድልን” የሚል፡፡ አሁን በችሎቱ ከተገኙት ውስጥ አብዛኛው ትእግስታቸው በማለቁ ከመገረም አልፈው ማጉረምረም ጀመሩ፡፡ እናም ዳኛው “ክስ በዚህ መልኩ እንደማይቀርብ” ተናግረው አቃቤ ህጉን ይገስፃሉ ብለው የጠበቁ ነበሩ፡፡ እሳቸው እቴ! ምንተዳቸው! ይልቁኑም በመንበራቸው ተመቻቹና ከህገ ደንብ ውጭ ድንገት የእኔ ጠበቆች መልስ እንዲሰጡ ጠየቁ፡፡ (እዚህ ጋር ከኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ጋር በተያያዘ የተነገረ አንድ ቀልድ ትዝ አለኝ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፤- በድህረ ምርጫ 97 የቅንጅት አመራሮች ተከሰው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡ ከተከሳሾቹም መካከል ከምስራቅ ጎጃም ተይዘው የመጡ ይገኙበታል፡፡ መንግስትም ለነዚህ ተከሳሾች ከዛው ከምስራቅ ጎጃም የሀሰት ምስክር አምጥቶ ስለነበ ምስክሩ መስክረው ሲጨርሱ ድንገት ከተከሳሾቹ መካከል ከመንደራቸው ወደ አዲስ አበባ ከመጣ አስር አመት ያለፈውን አንድ ጋዜጠኛ ያያሉ፡፡ ጋዜጠኛው የተከሰሰው በሚሰራበት ጋዜጣ ላይ በፃፈው ፅሑፍ መሆኑን የተረዱት አርሶ አደሩ የአቃቤ ህግ ምስክር ችሎቱን እንዲህ ሲሉ በትህትና ጠየቁ “ጌታው! ያያ እከሌ ልጅም እዚህ ስላለ መንግስት ሁለት ጊዜ የአበል እና የትንስፖርት ከሚያወጣ እሱም ላይ መስክሬበት ልሂድ?”)

ከመራራው ቀልድ እንፋታና ወደችሎቱ እንመለስ፡፡ ደህና! አዲስ ለቀረበው ክስም ጠበቆቼ መልስ ሰጡ፡፡ በዚህ መሀል እኔው እራሴ መናገር እንደምፈልግ ገልጬ እንዲፈቀድልኝ ጠየኩ፡፡ ለተከሰሰ የሚሰጥ መብት ነውና ተፈቀደልኝ፡፡ ፍኖተ-ነፃነት ጋዜጣ ላይ ቃለ-መጠይቅ የሰጠሁት ለፖሊስ ቃል ከመስጠቴ አንድ ቀን በፊት እንደሆነ፤ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይም አቃቤ ህጎች “ዝቷል” ያሉት ውሸት እንደሆነና ጋዜጣው መጠቶ እንዲታይ፤ እንዲሁም አንድ ጋዜጣ የሚታገደው ለብሄራዊ ደህንነት አስጊ ዘገባ መያዙ በማስረጃ ሲረጋገጥ ብቻ እነደሆነ የፕሬስ ህጉ በግልፅ የደነገገ መሆኑን ጠቅሼ፤ መታተም ከአቆመ ከአንድ ወር በላይ የሆነ ጋዜጣ፤ ያውም ምን አይነት ዘገባ ይዞ ሊወጣ እንደሚችል ያልታወቀ ጋዜጣን አዘጋጁ ድንገት እዚህ ስለተገኘ ብቻ ይታገድልኝ ማለት “ህገ-ወጥነት” እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ አስረዳሁ፡፡ በዚህ መሀል ዳኛው ተጨነቁ፡፡ ትንሽ አንሰላሰሉ እና “እየደበራቸው” መሆኑ በሚያስታውቅ መልኩ “የእገዳ ጥያቄውን ” ውድቅ አደረጉ፡፡ ነገር ግን የዋስትና ጥያቄዬን ከህግ ውጭ “ በልዩ ሁኔታ ከልክለናል” አሉ፡፡ ( ያ ልዩ ሁኔታ ምን ይሆን? ምንስ ማለት ነው? … ብቻ በችሎት ከተገኙት ውስጥ የገባው አንድም ሰው ያለ አልመሰለኝም) ከዚህ በኋላ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሆኜ እንድከራከር ተወሰነ፡፡ ችሎቱም ለነሐሴ 28 ቀን 2004 ዓ.ም ተቀጥሮ ተበተነ፡፡ እነሆም በእንደዚህ ባለ “ሚስጥራዊ”ሁኔታ በተካሄደ ችሎት ነበር ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለስድስት ቀናት ያህል ያሰለፍኩት፡፡

ከችሎቱ ውጭ

ችሎቱ ዋስትና ከልክሎኝ በመጠናቀቁ በጥቂት ፖሊሶች ተከብቤ፤ በበርካታ የፍትህ አንባቢዎች ታጅቤ በፍርድ ቤቱ ግቢ ወደሚገኘው “አንበሳ ቤት” አመራሁ፡፡ ይህን ጊዜም ከከበቡኝ ሰዎች መሀከል የማበረታቻ ድምፅ መሰማት ጀመረ፡፡ ቀስ በቀስም ድምፁ እየበረታ፤ ጭብጨባውም እየበዛ ሄደ፡፡ ባልተጠበቀ ሁኔታ እየተፈጠረ ባለው ነገር የተደናገጡት ፖሊሶች ህዝቡ ዝም እንዲል እና እንዲመለስ በቁጣ አዘዙ፡፡ ነገር ግን በችሎቱ ድራማ እልህ የተጋባው ሕዝብ የፖሊሶቹን ማስፈራሪያ ችላ ብሎ ጭብጨባውን እና ፉጨቱን ሳያቆም “አንበሳ ቤት” ደረስኩ፡፡ በተለምዶ “አንበሳ ቤት” የሚባለው በፍርድ ቤቱ ግቢ የሚገኝ ጣሪያው ላሜራ ሆኖ ዙሪያ ገባው በብረት ፍርግርግ የተዋቀረ ነው፡፡ የቤቱ አገልግሎት አብዛኛውን ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው ዋስትና የሚከለከሉ እና ሳይታሰሩ ሲከራከሩ ቆይተው የሚፈረድባቸው እስረኞች ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስኪላኩ ለሰአታት የሚቆዩበት ቤት ነው፡፡ ቤቱ አንዳንዴም ከወህኒ ቤት የመጡ እስረኞች ችሎት አስኪቀርቡ ለጥበቃ አመቺ ነው በሚል እሳቤ ለማቆያነት ያገለግላል፡፡ እናም ይህ ቤት ስያሜውን ያገኘው በአሰራሩ ስድስት ኪሎ አካባቢ ከሚገኘው “አንበሳ ግቢ” ጋር ሲለሚመሳሰል ይመስላኛል – አንበሳ ቤት፡፡

እኔም ከችሎቱ በቀጥታ ወደ አንበሳ ቤት እንድገባ ከተደረገ በኋላ ከአጀቡኝ ፖሊሶች መካከል አንዱ መዝጊያውን ከውጪ በኩል ቀረቀረውና በትልቅ ጓጉንቸር ቆለፈው፡፡ አሁንም ከፖሊሶች በላይ የተቆጡት የችሎቱ ታዳሚዎች ከውጭ በኩል የአንበሳ ቤቱን ከበው ማበረታታቸውን ቀጥለዋል፡፡ የፖሊሶቹ “ዞር በሉ” ማስፈራሪያም እንዲሁ እንደቀጠለ ነው፡፡ በዚህ መሀል ድንገት በቦታው የነበሩ ጥቂት ጋዜጠኞች ረጅም ጊዜ እስር ቤት ሊቆይ ይችላል ብለው ስለሰጉ ነው መሰለኝ “የምትናገረው የመጨረሻ ንግግር ካለህ ተናገር” አሉና መቅረጸ ድምፃቸውን ለስራ አዘጋጁ፡፡ ከህዝቡ መሀከል በርከት ያሉ ወጣቶች ሞባይላቸውን ደቅነው ጋዜጠኞቹን ተቀላቀሉ፡፡ ግራ ገባኝ፡፡ የምናገረውም ጠፋኝ፡፡ ውስጤን እልህ ተናንቆታል፡፡ የአንበሳ ቤቱን የከበቡት ጋዜጠኞች እና የፍትህ አንባቢዎች ደግሞ የምለውን ለመቅዳት እየወተወቱኝ ነው፡፡ ከጥቂት ማመንታት በኋላ እንዲህ አልኩ፡፡

“የዛሬው የችሎቱ ድራማ ከአምባገነኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ህልፈት በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡ እናም ድራማው አስቂኝም አሳዛኝም ነው፡፡ ግና! አንድ ነገር እርግጠኛ ሁኑ፤ ይኸውም የስርአቱ ግብአተ መሬት እየተቃረበ ለመሆኑ ከምልክቶቹ አንዱ ዛሬ ያያችሁት አይን ያወጣ እና ያፈጠጠ ዳኝነት መሆኑን፡፡”

ከዚህ በኋላ ፊቴን አዙሬ በአንበሳ ቤት ውስጥ ከተደረደሩት ወንበሮች በአንዱ ላይ ጀርባዬን ከቤቱ ባሻገር ለተሰበሰቡት ሰዎች ሰጥቼ ተቀመጥኩ፡፡ ይህን ጊዜም እስካሁን ድረስ ያላስተዋልኩት አንድ እስረኛ ከእኔው ጋር በዛች ቤት መኖሩን ተረዳው፡፡ እድሜው በግምት አርባዎቹ መጨረሻ ላይ ይሆናል፡፡ ቁመቱ እንደሸንበቆ የተመዘዘ ቢሆንም ኑሮ ደህና አድርጎ እንዳጎሳቆለው ያስታውቃል፡፡ ንትብ ያለ ውሃ ሰማያዊ ጃኬት እና አዳፋም ጥቁር ሱሪ ለብሷል፡፡ ጫማውም ቢሆን ብዙ ቦታ የተጣጠፈ፤ ቀለሙ ታይቶ የማይታወቅ አሮጌ እስኒከር ነው፡፡ ቀና ብዬ አየሁት፡፡ ፈገግ አለና የአንገት ሰላምታ ሰጠኝ፡፡ በርከት ያሉ ሰዎች አብረውኝ በመምጣታቸው ግራ የተጋባ ይመስላል፡፡ ፈጠን ብዬ ሰላምታውን ሞቅ ባለ ሁኔታ መለስኩለት፡፡ በሰላምተዬ ምላሽ ተበረታቶ ነው መሰለኝ “እነዚህ ሁሉ ጓደኞችህ ናቸው ?” የሚል ጥያቄ አቀረበልኝ፡፡ “አዎን” ስል መለስኩለት፡፡ “አይዞህ” አለኝ፡፡ (ይች “አይዞህ” ለእስረኛ እንዴት አይነት ስንቅ መሰለችህ?)

የሆኖ ሆኖ እኔና የአንበሳ ቤት ጓደኛዬም እንደዋዛ ወደ ጭውውት ገባን፡፡

“ምን አድርገህ ነው የመጣኸው?” ፊቱን አጨልሞ ባለቤቱ ከስሳው እንደሆነ ነገረኝ፡፡

“ለምን ከሰሰችህ?”

“አንድ ልጅ ወልደን ተለያይተናል፡፡ እናም ልጁን ማሳደጊያ ገንዘብ አይረዳኝም ብላ ነው የከሰሰችኝ”

“አንተ ለምን አትረዳትም?”

“ስራ የለኝም ነበር በቅርቡ ነው ስራ ያገኘሁት”

“ታዲያ ስራ ከጀመርክ ለምን አትረዳትም?”

“ከደሞዜ ላይ ተቆራጭ ላደርግላት ተስማምቼ ነበር፡፡ እነሱ ግን እንድሰጣት የወሰኑብኝ ብር ከአቅሜ በላይ ነው፡፡”

“ችሎት ቀርበህ ነበር እንዴ?”

“አዎን ቅድም ቀርቤ ለከሰአት ተቀጥሬአለሁ”

“ለምን?”

“ዳኛው የወሰኑት በወር መቶ ብር እንድሰጣት ነው፡፡ እኔ ደግሞ ያንን መስጠት አልቻልኩም፡፡ እናም ፍርድ ቤቱ እንድታሰር ወስኗል፡፡” (…እግዞ መቶ ብር የሌለው ሰው ወደ እስር ቤት የሚላክበት ሁኔታ ከዚህ ሀገር በቀር የት ይገኝ ይሆን? ኢትዮጵያ እጆቿን የምትዘረጋው ወዴት ይሆን? ወደ አሜሪካ ወይስ አረብ ሀገር?)

“እየሰራህ ከሆነ ለምንድነው መቶ ብር መስጠት ያቀተህ?”

“አልገባህም! እኔ ስራ ከጀመርኩ ገና 18 ቀኔ ነው፡፡ እነሱ ደግሞ ዛሬውኑ ገንዘቡን መስጠት እንድጀምር ወጥረው ያዙኝ፤ ደሞዝ እስክቀበል ታገሱኝ ብል ሊሰሙኝ አልቻሉም፡፡”

ይህን ጊዜ ትንሹ ወንድሜ በርገር እና የታሸገ ውሃ ይዞ ጠራኝ፡፡ የመጀመሪያውን የእስር ቤት ስንቅ እጄን በፍርግርጉ አሾልኬ ተቀበልኩ፡፡ ከመጀመሪያው እስረኛ ጓደኛዬም ጋር ተካፍለን መመገብ ጀመርን፡፡ ተመግበን እንደጨረስንም የተለያዩ ወዳጆቼ እና የማላውቃቸው የፍትህ አንባቢዎች በፍርግርጉ በኩል እየመጡ “ሞራል እና የስንብት ቃል” መስጠታቸውን ስለጀመሩ ከእስረኛው ጓደኛዬ ጋር የጀመርኩትን ወግ መጨረስ አልቻልኩም፡፡

በእንዲህ አይነት ሁኔታም በግምት ለሁለት ሰአት ተኩል ያህል ከቆየሁ በኋላ ፖሊሶቹ ጓጉንቸሩን ከፍተው ከአንበሳ ቤቱ እንድወጣ አድርገው ወደ ዋናው የፍርድ ቤቱ በር አካባቢ ከወሰዱኝ በኋላ ፊቷን ወደ መውጫው በር አዙራ የቆመች አንዲት የደከመች የፖሊስ ነጭ ሚኒባስ ውስጥ ከተቱኝ፡፡ ይህን ጊዜም ለአንዴ እና ለመጨረሻ ስንብት ፍርድ ቤት የተሰበሰቡትን ቤተሰቦቼን፤ ጓደኞቼን፤ ባልደረቦቼን እና የፍትህ አንባቢዎችን በሚኒባሱ መስኮት እጄን አውጥቼ ሰላምታ ሰጠዋቸው፡፡

መኪናዋ መንቀሳቀስ ጀመረች፡፡ በሶስት ፖሊሶች ታጅቤም ከፍተኛውን ፍርድ ቤት ለቀቅን፡፡ ሆኖም ሚኒባሷ ከልደታ ቤተ ክርስቲያን ከፍ ብሎ ከፍርድ ቤቱ ፊት ለፊት በሚገኘው አስፓልት ቁልቁል በመውረድ ሳር ቤት ከደረስን በኋላ በአቋራጭ ቃሊቲ የሚያደርሰንን መንገድ ከመያዝ ይልቅ ወደ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ አመራች፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች ጉዞ በኋላ ፖሊስ ጣቢያው በር ላይ ደረስን እና ከበር ላይ ቆምን፡፡ ጋቢናው የተቀመጠው ልጅ እግር ፖሊስም ከመኪናው ወርዶ ወደ ጣቢያው ገባ፡፡ ይህን ጊዜም በር ላይ የቆሙ የጣቢያው ፖሊሶች ለጥበቃ ካጀቡኝ ፖሊሶች ጋር የወዳጅነት ሰላምታ ተለዋወጡ፡፡ በዚህ መሀል አንዱ ፖሊስ አንገቴ ላይ በጠመጠምኩት “ስከርፍ” አማካኝነት ያወቀኝ መሰለ፡፡ ማንነቴንም ማወቁንም በፊት ገጽታው እየነገረኝ ወደ ተቀመጥኩበት ወንበር ተጠግቶ “አውቅሃለው! ተመስገን አይደለህ?” አለኝ ጓደኞቹ እንዳይሰሙት ድምጹን ዝቅ አድርጎ፤ አንገቴን በመነቅነቅ አረጋገጥኩለት፡፡ ምን አድርጌም እንደሆነ ጠየቀኝ፡፡ ወዴት እየሄድኩ እንደሆነም ገብቶታል፡፡ ነገርኩት፡፡ ጥቂት እንደመከፋት አለና ጣቱን ወደ ሰማይ ቀስሮ “አይዞህ እግዚአብሔር አለ” አለና አበረታታኝ፡፡ በዚህ መሀል ወደ ውስጥ የገባው ፖሊስ በሌሎች ሶስት ፖሊሶች የታጀቡ በግምት እድሜያቸው አሰራ ስምንት አመት የማይሞላቸውን ሶስት እስረኞችን ከእኔ ጋር ስለቀላቀሏቸው የአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ጉዳይ እንደተጠናቀቀ የገባው ጎልማሳው የሚኒባሱ ሹፌር ሞተሩን አስናሳ፡፡ ጉዞ ወደ ቃሊቲ ሆነ፡፡

ከፊት ለፊቴ ለተቀመጠው ፖሊስ ወንድሜ ልብስ ይዞ ክራውን ሆቴል አጠገብ ስለሚጠብቀኝ ስንደርስ እንድቀበለው መኪናውን በማቆም ይተባበሩኝ እንደሆነ ጠየኩት፡፡ የጠየኩት ፖሊስ ከመመለሱ በፊት ጋቢና የተቀመጡት ሁለቱ ፖሊሶች እና ሹፌሩ ምንም ችግር እንደሌለው እና እንደሚተባበሩኝ ተደራርበው መለሱልኝ፡፡ አመስግኜ ትኩረቴን ከመኪናው ውጪ አደረግኩ፡፡ በግምት ከሰላሳ ደቂቃ በኋላም ክራውን ሆቴል ደርሰን መኪናው በሩ ላይ ቆመ፡፡ ወንድሞቼ ከእኛ ቀድመው በመድረስ ፍራሽ፤ ብርድ ልብስ እና አንሶላ ይዘው እየጠበቁኝ ስለነበር ጊዜ ሳላጠፋ ተቀብያቸው ጉዟችንን ቀጠልን፡፡ ከጥቂት ደቂቃ በኋላም ከሀገሪቱ በስፋት ተስተካካይ ወደሌለው አስቀያሚ እስር ቤት በር ላይ ደርሰን ሹፌሩ ደጋግሞ ጡሩንባ ያሰማ ጀመር፡፡ የእስር ቤቱ ዋና በርም ከውስጥ ወደ ውጭ ወለል ብሎ ተከፈተና ሚኒባሷ ገባች፡፡ ከፍርድ ቤት አጅበው ያመጡኝ ፖሊሶችም ለቃሊቲ ፖሊሶች አስረክበውኝ ሲያበቁ ርክክቡን የሚያረጋግጥ ደረሰኝ ተቀብለው ሞቅ ባለ ፈገግታ ተሰናበቱኝ፡፡

እራሱን ያልሆነው ጠ/ሚንስትር

ጌዲዮን ደሳለኝ ከኖርዎይ

ለሁለት  አስርተ አመታት በኢትዮጲያና  በህዝቦቿ ላይ ነግሶ በማን አለብኝነት አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ በሁሉም ያገሪቱ አቅጣጫዎች ሰላማዊውን ህዝብ ለሞትና ለስደት እንዲሁም ለእስር ሲዳርግ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በፈፀመው ግፍና ሰቆቃ ለምድራዊ ፍርድ ሳይበቃ ይችን አለም ሲሰናበታት የብዙዎቻችን ነፃነት ናፋቂዎች ተስፋ ቢለመልምም ስርዓቱ ካለው እኩይ ተፈጥሯዊ  ባህሪ አንፃር የናፈቅነውንና የተመኘነውን ነፃነትም ሆነ ለውጥ ሳይመጣ እነሆ ሌሎች ንፁሃን ሲገደሉና ሲሰደዱ እንዲሁም ሲታሰሩ አየን ሰማን፡፡ለብዙሃን ዜጎች ህይወት መጥፋት፣ መሰደድና በየእስር ቤቱ መታጎር ተጠያቂ የሆነው አምባገነኑ የወያኔ ቡድን እንዲሁም ስርዓቱ  በተለይ ሃገር ሲያፈርሱ፣ ሲመዘብሩና ደሃውን የህብረተሰብ ክፍል ሲየፈናቅሉና በችጋር ሲቆሉ የነበሩት የህወሃት መስራቾች በዘፈቀደ ባገኙት አጋጣሚ እዚህ ምስኪን ህዝብ ላይ አፋቸውን ያላቀቁበትና የተዘባበቱበት አውሬው መሪያቸው ከሞተ በሗላ መሆኑ አንድም ሰውየው በህዝብ ላይ ብቻ ሳይሆን ጋሻ ጃግሬዎቹም ጭምር  ስብህናቸውን ሸጠው ሲረገጡ መኖራቸውን የሚያሳይ ሲሆን፡ አልያም ህልውናቸውን በነበረበት ሁኔታ ለማቆየት በህዝብ ላይ የፍርሃት ድባብ ለማስፈን የእውር ድንብራቸውን  ዘርን ከዘር፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ለማጋጨት በነሱ መልካም ፈቃድ  የስልጣን ዝውውር የተደረገ ይመስል ስልጣን ከአማራና ከኦርቶዶክስ እጅ አውጣን እያሉ ውሃ የማይቋጥር ተራ ዲስኩር በአስተሳሰብ ከነሱ ቀድሞ ዘርና እምነት ሳይለየው በአንድነት ለጠላቸው ህዝብ ሲነግሩት ሰንብተዋል፡፡

ጥቂት የማይባል የህብረተሰብ ክፍል ለዝች ዘመናትን በግፍና በመከራ ላሳለፈ ሃገርና ህዝብ የመጣል ተብሎ በታሰበው ወይም በመጣው አዲሱ መሪ ላይ ጭላንጭል ተስፋ ሰንቆ ቢቆይም  ተስፋ አሰቆራጭ ሁኔታ የተፈጠረው ብዙም ግዜ ሳይፈጅ መሆኑ ተስፋ አድርጎ የነበረውን ተስፈኛ አሁንም የመከራው ቀንበር መፈታት ሳይሁን አለመላላቱን  ያየነው አዲሱ  ጠ/ሚንስትር  ሃ/ማርያም ደሳለኝ ከሀ እስከ ፐ የሟች  ቅጂ መሆናቸው እየተስተዋለ ሲመጣ ነው፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ሟች አምባገነን መለስ ዜናዊ በዙሪያው የሚሰበስባቸውና ወደ ስልጣን የሚያስጠጋቸው ሰዎች ምን አይነት አመለካከትና ስብእና ወይም ሀገራዊም ሆነ ህዝባዊ ስሜት አላቸው ? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ሊቅ ወይም ነብይ መሆን የሚጠበቅብን አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም ሰውየው(ሟች) ይችን ሃገር በገዛበት ሁለት አስርተ የግፍና የመከራ ዘመን ውስጥ በራሳቸው የሚተማመኑትን፣ በሃሳብ ደረጃ እሱን የሚሞግቱትን በተለይ ለሃገርና ለህዝብ የሚጠቅም ፅንሰ ሃሳብ የሚያንፀባርቁትን የሃገር ሃብት ምሁራን ሲገድል፣ ሲገፋና ሲያሳድድ በግፍ ሲያስር የስልጣን ዘመኑን ማሳለፉ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ በአመለካከት ከሱ የተለዩትን አብረውት በትግል ሜዳ የነበሩትንም ሁሉ  ሳይቀሩ  ሲያሶግድ፣ ሲያስርና ሲያሳድድ መኖሩ  በህይወት ያሉ የቀድሞ የህውሃት ሰዎች ምስክር ናቸው፡፡ ይህንን ከተረዳን አቶ ሃ/ማርያም ደሳለኝ  በመለስ ዜናዊ ተመርጠው  እንዴት እዚህ ደረሱ የሚለውን ለማወቅ ከላይ እንደጠቀስኩት ነብይ መሆን አይጠይቅም፡፡

በሁለተኛ ደረጃ አቶ ሃ/ማርያም በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ተፅእኖም  ይሁን ወያኔ የህዝብ ይሁንታ ለማግኘት ቁልፍ የሆኑ የስልጣን ቦታዎችን  ይዞ ከፊት አስቀድሞ መንበረ ስልጣኑን ቢሰጣቸውም  ምንም  የመወሰን አቅም  የሌላቸው ወያኔ ለሽፋን ያስቀመጣቸው መሆናቸውን ያየንባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው፡፡የሳቸውም በራስ ያለመተማመን መንፈስና የስብእናችው ጉዳይ ታክሎበት በይዘትም ሆነ በፅንሰ ሃሳብ የግፈኛውን የመለስ ቅኝት መሆናችው እያየን ያለነው ገና በጠዋቱ የስልጣን ግዜያቸው ነው፡፡ የእሳቸው እራሳቸውን ያለመሆን ችግር አንድም እርምጃ ወይም ውሳኔ ለይስሙላ በተሰጣቸው ስልጣን እንደማይፈፅሙ የሚያሳየን  የህዝብና የሃገር ሃብትን ንብረትን በመመዝበር በምትታወቀው በሟች ባለቤት አዜብ መስፍን  ከቤተ-መንግስት  መውጣት አሻፈረኝ በማለቷ ስልጣናቸውን በይፋ ከተቀበሉ በሗላ ከወር በላይ መኖሪያቸውን ተረክበው በቤተ-መንግስት አለመግባታቸው ሰውየው ሳይሆኑ ለሃያ አንድ አመታት  ኢትዮጲያንና ህዝቧን ያስነቡና ያሰቃዩ የነበሩት የህውሃት ሰዎች መዘውርን እንደጨበጡት አንዱ ማሳያ ነው፡፡

የአቶ ሃ/ማርያም ደሳለኝን  ሹመት በተመለከተ በተለያየ ጊዜ ብዙ ተብሏል፡፡ አብዛኛው እኔን ጨምሮ ከላይ  በጠቀስኳቸው ጉዳዮችና ከዚህ አፋኝና  አምባገነን ስርዓት  ተፈጥሯዊ ባህሪ  አንፃር  ሰውየው የግፈኛውና የአምባገነኑ መለስ ቅጂ (ግልባጭ) ናቸው፡፡  ስርዓቱ እስካልተወገደ ድረስ ለውጥ  መጠበቅ ከእባብ እንቁላል እርግብ እንደመጠበቅ ነው ስንል  በጣም ጥቂት የዋሆች ግን ጊዜ ይሰጣቸው ይሉ እንደነበር  ይታወሳል፡፡ብርቅዬው ገጣሚ ሄኖክ የሺጥላ ለማይነጥፈው ብእሩ ምስጋና የግባውና ለ አቶ ሃ/ማርያም  ጊዜ ይሰጣቸው ለሚሉ ተስፈኞች ግጥም ፅፎ ነበር፡፡ እሺ ጊዜ ይሰጥ ግን ስንት ገለው ይብቃቸው፣ ኮታቸው ስንት ነው  ስርዓቱ እያለ  መግደል አያቆሙምና ደግሞ እሳቸው ስንት እስኪገሉ እንያቸው  ነው ያለው ገጣሚው፡፡ እና ይህው ብዙም አላለፉንም የስልጣን ጊዜያቸው ወራት ሳያስቆጥር  አስፈፅማለሁ ያሉትን  የሟች አለቃቸውን እቅድ  በደቡብ ወሎ በደጋንና ገርባ ከተሞዎች መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ  የጠየቁ  ንጹሃን ዜጎችን በጠራራ ፀሃይ በመግደልና በማሰር የሟች አለቃችውን  እቅድ በመተግበር  በንጹሃን ደም  ታጠቡ፡፡

ሰውየው ኢትዮጲያንና ህዝቧን የሚመሩት  ከአለቃቸው በውርስ ባገኙት የሳቸው ባልሆን  ባህሪ ብቻ ሳይሆን ይችን ሃገር መዝብረው በደለቡና በሰቡ የህውሃት ሰዎች በርቀት መቆጣጠሪይ ስለሆነ  ከህዝብ ሳይሆን  ከነኚሁ የሃገርና የህዝብ ጠላቶች  ክብርና ሞገስ  ለማግኘት እንደ ሟች አለቃቸው  ሆዳምና ከራሱ ባለፈ ስንዝር  የማያስብ  ጥርቅም በሞላበት ፓርላማ ተብይ ውስጥ በሙት መንፈስ  እየተመሩ  መኮረጅ የቻሉትን  ያህል  ሲተውኑ፣  ተልኳቸውን በድል ለመወጣት ሲወራጩና  ሲሳደቡ፣ እንዲሁም ህዝብ  ክብር የሚሰጣቸውን የህሊና እስረኞችንና የነፃነት ታጋዮችን  ሲዘልፉ፣ ከቃላት አጠቃቀምና አስተያየት ጀምሮ የሳችው ባልሆነ ስብእና  የሚያደርጉት ትእይንት  በሳችው ደረጃ ካለ   ከተማረና  ከዚህ ዘመን ስልጡን ሰው የሚጠበቅ አይደለም፡፡

ላይ ላዩን ቅልም ዱባ ይመሰላል እንዲሉ  የአቶ ሃ/ማርያም ስልጣን ሳየቀመጡበት መነቃነቅ ጀምሯል፡፡ ሟችቹ መለስ ትቶት ሄደው ዘርፈ ብዙ ችግር ወትሮም  ቅንነት የጎደላቸውን አዲሱን ጠ/ሚንስትርም  ሆኑ የስርዓቱን አውራ  ገዳዮች  ይንጣቸው የዟል፡፡ ከመጀመሪያ ጀምሮ  በአለቃቸው  ሞት ልባቸው መራድ  የጀመረው  የወያኔ  ቱባ ባለስልጣናት  ሊፈጠር  ይችላል ብለው ያሰቡትን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማፈንና  በህዝቡም ላይ ፍርሃት ለማንገስ  ለአዲሱ ጠ/ሚንስትር እውቅና ከመስጠታቸው በፊት ከስርዓት ውጪ በሆነ መንገድ  በአብዛኛው ከህውሃት ለሆኑት የተሰጠው ወታደራዊ ሹመት(የማእረግ  እድገት) በውስጣቸው ያልሰከነ ነገር ለመኖሩ አመላካች ነው፡፡ ከዚም ባለፈ  አቶ ሃ/ማርያም  እስከ አሁን ካቢኔያቸውን አለማሳወቃቸውና  ሌሎችም በሰርዓቱ ላይ የሚታየው ሰፋፊ ክፍተት፣ እንዲሁም ገዢው ቡድን እንደ አሻንጉሊት  የሚጫወትባችው  አጋር  የብሄር ድርጅቶች ውስጥ  የሚታየው መተራመስ  ስርዓቱ  በደመነፍስ  እየተውተረተረ  እንዳለ የሚያሳይ ነው፡፡

ይህንን ስርዓት  ለመጣል  በቅን ልቦና  በመደማመጥና ለጋራ ጥቅም  በአንድነት  ከታገልን በትንሽ መስዋትነት ሃገራችንንና  ህዝባችንን ነፃ ማውጣት አይገደንም፡፡

ድል  ለኢትዮጲያ   ህዝብ !!  ሞት ለወያኔና  ለሆዳሞች!!!!

ይድረስ ለእስልምናና ክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች

ይሄይስ አእምሮ(yiheyisaemro@gmail.com)

ከሁሉ በፊት የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2005 የአረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤

ኢሣት ኢትዮጵያ ውስጥ በመዘጋቱ ምክንያት ስንት ነገር አምልጦኛል ለካንስ እባካችሁ? ይህችነን ማስታወሻ ለመጻፍ አስቤ ብዕሬን ከወረቀት ላዋድድ ስል ከዜናና ከዜና ትንታኔው በኋላ ትቼው የተለየሁትን ይህን የኢትዮጵያ የወቅቱ ብቸኛ መተንፈሻ የቴሌቪዥን ጣቢያ ተመልሼ እንድከታተል ባለቤቴ ስትጠራኝ “ተይኝ ባክሽ ሌላ ሥራ አለብኝ” ብላት ስሜቴን ስለምታውቅ “ታማኝ መጣልህ!” አለችኝና የመከታተል ወይ ያለመከታተል ምርጫውን ለኔው ትታ ወደሥራዋ ገባች፡፡ በዚህ ረገድ በደንብ ታውቀኛለችና እንድመለስ ሌላ ቃል አልጨመረችም፡፡ በዚህች አባባል ሌሎች በመንፈስ እንጂ በሥጋ እንዳትቀኑ አደራችሁን – “ወላድ በድባብ ትሂድ! የታማኝ እናት ደጋግመሽ ውለጂ! ቢስ አይይብን፡፡ የልጅ ዐዋቂ ነህና ከዐይን ይጠብቅህ፡፡” አሜን በል ወንድማለም፡፡ ከአሜን ይቀራል አሉ፡፡

ታማኝ – ወይ ጉድ ስም ይቀድሞ ለነገር አሉ – በኦነግና በግንቦት ሰባት ጥምረት በተደረገ ስብሰባ ተገኝቶ ያደረገውን ንግግርና ስብከተ ሀገር ነበር ኢሣቶች እያቀረቡ የነበረው – የቆዬ ዝግጅት ነው፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ የምንኖር ዘጎች ከተናጋሪ እንስሳነት እምብዝም የማንለይ – ኧረ እንዲያውም እነሱ ከእኛ የሚሻሉበት ብዙ ነገር አላቸው – በመሆናችን ሁሉም የዜና ማዕከላት ተጠርቅመው የወያኔን ቅርሻት ብቻ እንድንሰማና እንድናይ ስለተፈረደብን በወቅቱ አላየሁትም፡፡ አሁን ግን ዕድሜ ለዲያስፖራው የኢትዮጵያ ሕዝብ – በኢሣት ጥረት የተደበቁ ዜናዎችንና መረጃዎችን መከታተል ጀምረናል፡፡ ይህ የዜና ተቋም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁለንተናዊ አቅም ያላችሁ ዜጎች እባካችሁን አንድነታችሁንና ኃይላችሁን አስተባብራችሁ ታገሉ፤ ሁሉም ያልፋል፡፡ የማያልፈው ግን አጥርን ዘልሎ የሚሻገር የመልካም ወይም የክፉ ሥራ ውጤት ነው፡፡ የዚህ የተገፋ ሕዝብ የየጨለመ የመኖር ተስፋ ብታለመልሙ ፈጣሪ ወሮታውን ይከፍላችኋል፡፡ የአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር ጉዞ የሚጀመረው በአንድ ሜትር ነውና አንዳንድ ጨለምተኞች “ወሬ ምን ዋጋ አለው! በወሬ ሆድ አይሞላም…” ቢሉም ብዙም ጆሮ አንስጣቸው፡፡ መጽሐፉ “እስመበተስፋሁ ሀደረት ሥጋየ” ይላልና የነጻነታችን ፋናወጊ የመረጃ ምንጭ የሆነውን ኢሣትን በየአቅማችን እንርዳ – እርግጥ ነው ድረ ገፆቻችንንም ሳንዘነጋ፡፡ ምርጫም የለንም፡፡ ምርጫ ከተባለም ያለን ሌላውና ብቸኛው ምርጫ በቦሌም በባሌም ብለን ባከማቸነው ገንዘብ የተንደላቀቀ ኑሮ እየመራን እንደከብት እያመነዠክን እንደዓሣም ያገኘነውን መጠጥ እየማግን መኖር ነው፡፡ ይህ ደግሞ እንስሳነት ነው፡፡ ይህ ከጤናማ ሰውነት የወረደ ወያኔያዊ ባሕርይ ለታሪክ ፍርድ አመቻችቶ ይተወናል፤ ለኋላ ፀፀትም ይዳርገናል – ‹ኋላ› ለሚባል ነገር ለምንደርስ፡፡ አንዳንዴ ‹ፊተኛ›ን ብቻ ለሚያውቅ ግብዝ ፍጡር ‹ኋለኛ› የሚባል ነገር ስለመኖሩም አይገባውም፤ ሁለቱንም ኑባሬያት በነቢባዊና ተግባራዊ አንድምታቸው የሚያውቅ ሰው የተረጋጋና ለየትኛውም መቼት የሚያበቃ ሕይወትን መርቶ በፊተኛውም በኋለኛውም የመኖርና ያለመኖር የሕይወት ቅምብቦች ውስጥ ዘወትር እየተወደሰና በሠናይ ምግባሩ እንደ አብነት እየተወሳ ዘመድ አዝማድንና ሀገርን አኩርቶ እስመለዓለመ ዓለም ይኖራል፡፡ (ታማኝ በርቺ – ጀምረሻል – እንዳትንሸራተች የኢትዮጵያን አምላክ ጠበቅ አድርገሽ ያዢ!! በተንሸራታች ፋብሪካ ሀገር ጥንቃቄና ምርመራ ውስጠት ዘወትር ካልታከለ ችግር ማስከተሉ አይቀርምና ራስን በየወቅቱ መፈተሽ፣ ራስን ብቻ ሳይሆን ግራ ቀኝን – ባላንጣን ጭምር ማዳመጥ ይገባል፤ ትምክህትን በፈጣሪና በምስኪን ሕዝብ ያደረገ ወድቆ አይወድቅም፡፡ ብዙዎች የአሁን ኢትዮጵያውን ደግሞ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ፍጡራን መሆናችንን ለማወቅ ይህች ጦማር በአንዱ ድረገጽ እስክትለጠፍ መጠበቅ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ መንጌ ምን አለ? ‹ሀገሬን ለሰው አልሰጥም አለ› ብለህ እንዳትቀልድብኝ፤ ከርሱ ቀጥሎ ያለው ቁም ነገር አለ … ወርቅ ቢያነጥፉለት … ችግሩ እነሱ እንደሚሉን እየሆንላቸው የተግባራቸው ብቻም ሳይሆን ለትንቢቶቻቸውና ለዕብሪት ንግግሮቻቸው እውናዊነትና ተፈጻሚነት  አጋር መሆናችን ነው፡፡ ለሁሉም ግን ተስፋ መቁረጥን ራሱን ተስፋ እናስቆርጠውና ለእውነት ልዕልና ቆርጠን እንነሳ … የቀረበው የነጻነት ቀን ልደት በምንም መንገድ አይጨነግፍም የሚል ጽኑ እምነት አለኝ… ግን ጽንሱ ከታሪክ ማኅጸን በቅጡ እንዲወጣ ልምድና ዕውቀት ያላቸውን አዋላጆች ከዬአህጉሩ እየፈለግን በማሰባሰብ እንደስካሁኑ መደዴና ስድ አደግ ሁሉ እጁን ሳይታጠብና በቂ ችሎታ ሳይኖረው ማዋለጃ ክፍል ውስጥ እየገባ ችግር ከመፍጠሩ በፊት እውነተኞቹ ባለሙያዎች ዕድል እንዲያገኙ እናድርግ፡፡…)

ትናንት ማታ የዶክተር ብርሃኑንና የፋሲል የኔዓለምን ውይይት ተመለከትኩ – ግሩም ነበር፡፡ ግን ፋሲል ግማሹን ቃለ መጠይቅ በአንተ፣ ቀሪውን ደግሞ በአንቱ በማካሄዱ እንደመዝናኛም ቆጥሬ ፈገግ ብያለሁ፡፡ ወጥነት እንዲኖር ለማሳሰብ ፈልጌ ነበር ግን ቀላል ጉዳይ ስለሆነ ተውኩት፡፡ ለነገሩ ቀረቤታንና አክብሮትን በአንድ መድረክ በማሳየቱ በጨዋታነት ደረጃ ደስ ይላል፡፡ ይህችን ነቁጥ ነገር ለትችትም የሚያበቃት ሰው አይጠፋ ይሆናል እኮ፡፡ አደራ እኔ ለቀልድ ነው እያነሳሁ ያለሁት!

በነገራችን ላይ የ24 ሰዓት የዜናና የሀተታ አገልግሎት ዝግጅት በጣም ከባድ ነው፤ የሰው ኃይል አለ፤ የማቴርያልና የበጀት ጉዳይ አለ፤ ብዙ ተያያዥ ተግዳሮቶች አሉ፡፡ ስለዚህ ኢሣት በቢሊዮን ዶላሮችና በሺዎች ሠራተኞች እንደሚንቀሳቀሱት የአልጀዚራና ቢቢሲ ጣቢያዎች እንዲሆን መጠበቅ አይገባንም፡፡ በአቅም ውስጥ ግን የሚቻለውን ያህል መንቀሳቀስ ይቻላል፡፡ እናም በበኩሌና በዚህ አጋጣሚ ይህ ጣቢያ ወጣቶችን፣ ሴቶችን፣ ሕጻናትን፣ አረጋውያንን… በጥቅሉ አብዛኛውን የኅብረተሰብ ክፍል እንዲይዝ በብልሃት ቢመራ ጥሩ ነው እላለሁ፡፡ ለምሳሌ በቀደምለት ‹ፈረቃ› በሚል ርዕስ የነዶኪሌን ቀልድ ስመለከት በጣም ደስ ብሎኛል – ደስ የማይለው ደግሞ ሊኖር ይችላል፡፡ ግን ለኔ ሲል ይታገሳል ብዬ አምናለሁ፡፡ ስፖርት ለኔ ብዙም አይጥመኝም – ስሜቴ በአብዛኛው በሀገሬ ላይ ስላረፈ ከመዝናኛ ቀልዶችና ጭውውቶች ወጣ የሚሉ ሌሎች ዝግጅቶች እምብዝም አይስቡኝም፡፡ ለሌሎች ስል ግን እታገሳለሁ – እከታተላለሁም፤ የፖለቲካ ትንተና ሲጀመር ግን አፌን ከፍቼ ላነጋ እችላለሁ፡፡ በመሠረቱ ሁሉን ማስደሰት ከባድ ነው – በተለይ ሰውን፤ በተለዬ በተለይ ደግሞ የዘመኑ ኢትዮጵያውንን – እንዴ፣ ለይቶልን የጥንቶቹን ባቢሎንያውያንን ሆነናል እኮ፡፡ … ይሁንና በአስተያየት መስጫ መድረኮች የሚሰሙ ጥቆማና አስተያየቶችን በጥሞና ማዳመጥ ሲቻልም ለመቀበል መሞከር መልካም ነው፡፡ በኢንስትሩመንታል ሙዚቃ ብዙ ጊዜ ባይባክን፣ ከየብሔረሰቡ ማራኪ ዘፈኖችና ውዝዋዜዎች በፕሮግራም ማሸጋገሪያነት ቢገቡ፣ የነልመንህና አለባቸው፣ የነደረጀና ሀብቴ፣ የሌሎች ሀገሮች አርቲስቶች ቀልድና ጭውውቶችም ቢዘወተሩ… ጥሩ ነው፡፡ በተነሱበት ያልተነሱበትን መናገር በኔ አልተጀመረም፡፡

መነሻየን የሚከተል ሌላ ጉዳይ ላክልና ወደ ዋናው ጉዳይ ልንደርደር፡፡

እንደውነቱ ከሆነ ብዙ ጊዜ ልጻፍ እልና በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ የኢንተርኔት ተጠቃሚው ሰው ቁጥር ተስፋ አስቆራጭ በመሆኑ ማን ያነበኛል በሚል እተወዋለሁ፡፡ የሀገራችን ወጣትና ጎልማሣ አንዳች ጠበል ካልተረጨ ወይም በወያኔ የተራገፈብን አፍዝ አደንግዝ ካልተነሳልን የሀገር ውስጡ ነገር አሳሳቢ እየሆነ ነው፡፡ አብዛኛው ዜጋ በሚያሳፍር ሁኔታ ለሆዱና በሆዱ ምክንያት ታስሮ ቢኮረኩት እንኳን ለመሳቅ ጊዜ የሌለው ሆኗል፡፡ ኢንተርኔት ካፌዎች ብትገቡ ሰው ከአፍ እስከገደፋቸው ጢም ብሎ ሞልቶ ታገኛላችሁ – በተለይ ወጣቱ፡፡ ግና የሀገራችን ወጣት ምን ነካው ብለን እስክንገረም ድረስ ከሞላ ጎደል ሁሉም የሚፎሰቡከው ፆታዊ ግንኙነትን ማዕከል ያደረገ ትርኪ ምርኪ ነገር ላይ ነው፡፡ ሀገራዊ የፖለቲካ ጉዳይ ይቅርና የረባ ቁም ነገር የሚፎሰቡክ ለማየት አንገትህ እስኪቀነጠስ ዙሪያ ገባህን ብዙ ብታማትር ማግኘት ይሳንሃል፤ ተረግመናል፡፡  እኔ ብዙ ጊዜ በዚህ ጉዳይ ላይ ዳሰሳ ጥናት ለማድረግ ሞክሬያለሁ – በጨረፍታና በስለላ መልክ፡፡ ይሁንና ከዘመድ አዝማድና ጓደኛ  ተራ የኢሜል ግንኙነትና ከወሲባዊ የፍቅር ጨዋታ እንዲሁም ከዚሁ ያልወጡ ግትርና ተንቀሳቃሽ ምስሎች ምልከታ በስተቀር በፕሮክሲዎች ገብቶ የተቃውሞ ድረገጾችን ለመፈተሽ የሚደረግ ሙከራ አልታዘብኩም፤ እርግጥ ነው ፍርሀትና የግንዛቤ ዕጥረት በመንስኤነት ሊጠቀሱ ይችሉ ይሆናል፡፡ የግብጾችንና ሌሎች የአረቡ ዓለም ወጣቶችን ስታስብ ደግሞ ተስፋህ እንደጉም ሊበንብህ ይችላል – ስለዚህ መፍትሔው እነዚያን ሀገሮች አታስብ ብዬ ነው የምመክርህ፡፡ ወያኔና ተቃዋሚዎች እግዜር ይይላቸው – በተለይ ወጣቱን ስሜትየለሽ አደረጉት፤ ግዴለሽ ዜጋ በዛ፡፡ ሆዱ ከሞላ ለሌላ የማያስብና ለሀገር ቀርቶ ለራሱም የማይጨነቅ ነሁላላ ዜጋ እየተበራከተ መጣ፡፡ በጁ ቆንጨራና ጩቤ አታይም እንጂ ሰው በተለይ የንግዱ ማኅበረሰብ ድሆች ዜጎችን በጠራራ ጠሐይ እየከተፈ ይበላው ይዟል፤ በይውና ጠጪው አሥረሽ ምቺው ላይ ነው – ‹ነገ ዓለም ታልፋለች› የተባለ ይመስል፡፡ የቢሮ ሠራተኛው ሁላ በእጅህ ካልሆነ በእግርህ ሄደህ ጉዳይህን አይፈጽምልህም፡፡ የሚኖሩት በሚሞቱት ላይ እየጨፈሩ ሲታይ ሀገርና ሕዝብ ያሉ ይመስላሉ እንጂ ሁሉ ነገር አብቅቶልናል፡፡ እንደሕዝብም እንደሀገርም ትናጋችን ተዘግቶ ኅልውናችን ቀጥ ሊል የቀሩት ሐሙሶች ከሁለትና ከሦስት የሚበልጡ አይመስልም፡፡ ‹ፀጉራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል› እንዲሉ ሆኖ እንጂ በቁማችን ሞተናል ብንል አልዋሸንም፡፡ እንደዘመነ ሶዶምና ገሞራ ልንሆን ነው መሰለኝ፡፡ አንዱ አንዱን እየበላ ገንዘብ ከማካበትና ሌትና ቀን በየዝጉብኚው ዳንኪራና ጮቤ ከመርገጥ በስተቀር አቅልን ገዝቶ ስለሀገር ቆም ብሎ የሚያስብ ሰው እየጠፋ ነው – በሀገር ቤት ውስጥ በተለይ፡፡ ምሁር ተብዬውም በዬወረቀቱ ተሸጉጦ ለዕለታዊ ጉርስና ለዓመታዊ ልብስ የምትሆነውን ሶልዲ የሚያገኝበት “የጥናትና ምርምር” ሥራዎችን በከተፋ – በኮፒ ፔስት የዘመን አመጣሽ ‹ምሁራዊ› ልክፍት ተጠምዶ – ከማምረት በስተቀር ይህ ነው የሚባል የረባ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው ሥራ ሲሠራ አይታይም፡፡  ሀገሪቱ በርግጥም የወላድ መካን የሆነች ትመስላለች – ዛሬ! ስለነገው በአቤቶኪቻዊ አባባል በአዲስ መስመር እንገናኝ፡፡

የነገው ግን በርግጠኝነት ሌላ ነው፤ ከአሁኑ እንቅልፍና ስንፍና ብዙ የተማረ አዲስ ትውልድ ሲፈጠር ወይም የአሁኑ ከተኛበት ሲነቃ ኢትዮጵያ ልዩ ሀገር ትሆናለች፡፡ የቀኝ ኋላው ዙር ዐዋጅ ሲታወጅ በርግጠኝነት የመከራችን ደመናና ጭጋግ ይገፈፋል፤ ወያኔ የጀመረውን ጉዞ በቅርቡ ሲያጠናቅቅ ሁላችን ከየተሸጎጥንበት የጥፋት ጭምብልና ከየመሸግንበት የፍርሀት ዋሻ ስንወጣ – ማንና የት እንደምንገኝ ስንገነዘብ – ያኔ  ያለንን ሁሉ አቀናጅተን በምንፈጥራት አዲሲቷ ኢትዮጵያ አዲስና የተከበረ ስብዕና ይኖረናል፤ በወያኔው የተዋረደው አሮጌው ስብዕናችን ከነዘረኝነቱና ከነሃይማኖታዊ የቁርቋሶ ቱማታው እንክትክቱ ወጥቶ ወደመጣበት ወደ ሀገረ ሳጥናኤል ሲመለስ ያኔ ዐይናችን ይበራል፤ ድንቁርናችን በዕውቀትና በማስተዋል ይተካል፤ የግላዊ ብልጽግና የተናጠል ሩጫችን እንደአሁኑ በዘርና በጎሣ በተቀነበበ ይሉኝታቢስነት አንዲትን ሀገር የብቻ ቁጥጥርና ዐይን ያወጣ ዝርፊያ ላይ ሳይሆን የንግድም ሆነ አጠቃላዩ የኢኮኖሚ ግንኙነት ለሁሉም ምቹ ሁኔታን በሚፈጥር የተስተካከለ የውድድር ሜዳ  ላይ በሚከናወን የግልና የወል ሕጋዊና ሚዛናዊ ጥረት ላይ የሚመሠረት ይሆናል፡፡ የወደፊቷ ኢትዮጵያ በእኩልነትና በነጻነት የምንኖርባት የሁላችንንም የልብ ትርታ በሚያዳምጥና አንዳችም አድልዖ በማይኖረው ሀገራዊ የጋራ ሕግ ታስተዳድረናለች፡፡

አሁን በአዲስና ተለዋጭ ርዕስ ወደተነሳሁበት ጉዳይ ከእውነት ገባሁ፡፡

የፋሲካው በግ በገናው በግ ይስቃል

ሰሞኑን በሙስሊሙ  ማኅበረሰብና  በመለስ ዜናዊ የሙት መንፈስ በሚታዘዘው የወያኔው ሥውር(abstract) መንግሥት መካከል የጦፈ ግጭት እንዳለ ይወራል፡፡ ይህም የሚደመጠው ድረገጾቻችንን ጨምሮ ኢሣትን ከመሳሰሉ የውጭ የዜና ማዕከላት እንጂ የሀገር ቤቱ የወያኔ የውሸት ወፍጮማ ሁሉም ሰላም እንደሆነ ነው ሰርክ እየተደሰኮረ ያለው፡፡ ይህ ሃይማኖትን ተመርኩዞ የተቀሰቀሰ ግጭት ወዴት ሊያመራ እንደሚችል መጨረሻው ወደፊት የሚታይ ሆኖ በተለይ ስለእስልምናና ክርስትና ሃይማኖቶች (በኢትዮጵያ) ትንሽ ነገር መናገር እፈልጋለሁ፡፡ ግጭቱ የሃይማኖት ሳይሆን የመብት ረገጣ የወለደው የአትንኩኝ ባይነት ትግል መሆኑን አምናለሁ፡፡ ወያኔ ዜጎችንና ጦርነትን በቆረጣ መግጠሙ ዛሬ የጀመረው አይደለም፡፡ ጠላቶቹ ተቆጥረው አያልቁም፤ የሚገጥምበት ሥልት ግን በተራና በቆረጣ ነው፡፡ ይህን የተበላ ዕቁብ ሕዝበ ክርስቲያንና ሕዝበ ሙስሊም ካልነቃበት ራሱ ያልቅበታል፡፡ ወያኔ ተንኮለኛ ነው፡፡ ሃይማኖት የለውም፡፡ ሃይማኖት አለን የሚሉ ወገኖችን ግን እርስ በርስ ሊያባላቸው የአንዱ ዕንባ አባሽ መስሎ አንዱን ከሌላው ሊያጋጭ ይሞክራል፡፡ ሞኝ ካገኘ ይሳካለታል፡፡ ከተነቃበት ግን ራሱ ያልቅለታል፡፡ ይህን ነው ሁሉም ሕዝብ መረዳት ያለበት፡፡ በየተራ ማለቅ ነው የሚጠቅመው ዌንስ ተባብሮ የጋራ ጠላትን ልኩን እንዲያውቅና መብትን መርገጥን እንዲያቆም ማድረግ? ምርጫው የምዕመናን ነው፡፡

እንደደራሲ ሰርቫንቴስ የምናብ ፍጡር እንደዶን ኪሾት የሚመሰለው ወያኔ ይህን የሙስሊሞችን ጥያቄ በቀላሉ ሊመልሰው ሲችል ተፈጥሮው ከሁሉም ነገሮች ጋር(ሕይወት ካለውም ከሌለውም ጋር) የመጋጨት እንጂ ሰላምን የመፍጠር ባለመሆኑ ይሄውና የራሱን መቃብር እየቆፈረ ይገኛል፡፡ ወያኔ ሰዓት ስንት እንደሆነ እንኳ ቢጠየቅ – እንደተቋም – “ሰዓት መጠየቅ እንደአካሄድ ትክክል ሞሆን አለሞሆኑ አነጋጋሪነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን ማን ነው ሰዓት ጠያቂው? የግንቦት ሰባት አባል ነው ወይንስ የመድረክ?  ለምን ዓላማ? ሰዓት ጠያቂው ሰዓት መጠየቅ ከሽብርተኝነት ጋር ቁርኝት ሊኖረው እንደሚችል ያልተገነዘበበት ምኽኒያቱ ምንድነው? ሰዓት የተጠየቀው ለሽብር የሚጠመድን የ‹ሠ› ሰዓት ፈንጂ ለማስተካከል አለሞሆኑ እስኪረጋገጥ ሰዓት ጠያቂውና ዘመድ ወዳጆቹ በቁጥጥር ሥር ውለው ከተጣራ በኋላ ሰዓቱ ሊነገረውም ላይነገረውም ይችላል…” ሊል ይችላል፡፡ ስለዚህ ወያኔን ምንም ነገር መጠየቅ በሽብርተኝነት ሊያስጠረጥር፣ ሊያስከስስና በታዛዥ ዳኞች – በሰው መሰል የወያኔ ሮቦት ዳኞች – ዕድሜ ይፍታህ ወይም የስቅላት ሞት ሊያስበይን የሚችል አደገኛ ወንጀል ነው፤ ‹ራበኝ አጉርሱኝ፣ ጠማኝ አጠጡኝ፣ ታረዝኩ አልብሱኝ፣ መንገድ አሳዩኝ …› በወያኔ በአሸባሪነት ሊያስጠረጥሩ የሚችሉ ‹ወንጀሎች› ናቸው፤ ይህ ዓይነት ዕንቆቅልሽ ፍጡር ለግማሽ ምዕተ ዓመት በሕይወት መኖሩ በርግጥም ያስደንቃል – በድንቃድንቅ ታሪኮች መዝገብም ሊሠፍር ይገባዋል፡፡ ወያኔ እኮ በማሰብህም የሚከስህ የመጀመሪያው የዓለማችን ጉድ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሀገራቸው ደግሞ በነጻነት መናገር እንደቅንጦት የሚቆጠር ሆኖ እንዲሁ ማሰብም መብላት መጠጣትም የማይቻልባት የመጀመሪያዋ ሀገር ናት – ለኢ-ወያኔያዉያን ነው ታዲያ፡፡ ኢ-ወያኔነት ደግሞ በእውነተኛ ኢትዮጵያዊነት የሚያገኙት የሚከብድ ሸክም እንጂ በዘርና በሃይማኖት ተፈጥሯዊና የግል ጉዳዮች የሚወሰንና ለተመረጡ ብቻ የሚሰጥ ምንዳ አይደለም፡፡ ከዚህ አኳያ ሙስሊሙም፣ ክርስቲያኑም፣ አማራውም፣ ኦሮሞውም፣ አደብ ካልገዛና የወቅቱን በረከተ መርገም ከአሌታዊው(ዘረኛ) ሥርዓት ተለጥፌ ከርሴን አልሞላም ብሎ ከቆረጠ ትግሬውም ጭምር ከዚህ ወያኔያዊ የጭካኔ በትር አያመልጡም – አብዮት ልጆቿን የመብላቷ መዝሙር በደርግ ዘመን ብቻ ተዜሞ አልቀረም፡፡ ወያኔን ያልመሰለና ያልሆነ አሣር ይደርስበታል፡፡ በምንም ሁኔታ ተከፋፍሎ መገኘት ለወያኔው ዱላ ይበልጥ ምቹ መሆን ነው፡፡ አለመተባበር መሰባበርን እንደሚያስከትል ዶክተር መራራ አስቀድመው አስታውቀዋል- ለሚገባው፡፡ ግን ግን አፍዝ አንግዟን ማን ወንድ ይፍታት! ለነገሩ ከላይ የመጣው ከላይ ካሉት ፍትሃቱን ጀምሯልና ዋናው መታገስ ነው – ‹እናያለን ገና› ብሏል አቀንቃኙ፡፡ በጊዜ የተመለሰ ብቻ ይድናል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ ነው እንግዲህ ሙስሊሞች መብታችን ይከበር ሲሉ ክርስቲያኑ ፀጥ ረጭ ብሎ የሚታየው፡፡ ሁለቱም መታረዳቸው የማይቀር በጎች ናቸው – የገናና የፋሲካ በጎች፡፡ ነገር ግን የፋሲካው አንድ ሦስት ወሮች ያህል ዕድሜ ስላሉት እየታረደ ባለው የገናው በግ ይስቃል ይባላል – በምሳሌያዊ አነጋገሩ፡፡ ለነገሩ በግ ባኣኣ ይላል እንጂ አይስቅም፡፡ እኛም ክርስቲያን ነን የምንል ወገኖች እየሳቅን ሳይሆን ባኣኣ ባንልም ዕርዱ እንደማይቀርልን ተገንዝበን በማጉረምረም ላይ የምንገኝ የወያኔ ጭዳዎች ነን፡፡ ዝምታን ድጋፍን ሳይሆን በአብዛኛው ተቃውሞን እንደሚተቁም መገንዘብ ተገቢ ነውና የቁርጡ ሲመጣ ሙስሊሞች አጋዥ የለንም ብለው እንዳይሰጉ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ ይልቁናም ሁለቱም ሃይማኖቶች መጠንቀቅ የሚገባቸው በውስጣቸው የሚገኙ የሁለት ጫፍ አክራሪዎችን ነው – ትልቁ መጥፎ ነገር ዘመድ መስሎ የሚቀርብ ጠላት ነው፡፡ የአክራሪነት ምንጭ ደግሞ የተወሳሰበ ነው – ያንተ ‹አክራሪ›ና የኔ ‹አክራሪ› የኛ አለመሆናቸውን ምናልባትም ከጋራ ጠላታችን የተላኩና በውስጣችን የሠረጉ ምንደኞች መሆናቸውን የምናውቅበት መንገድ ለሰላምና ለብዙኃን ድምጽ አንገዛም ያሉ እንደሆነ ነው፤ ‹አጭበርባሪ አይተኛኝም› ያለችዋን የሴተኛ አዳሪዋን ምሳሌ መቀበል ከብዙ ጉዳት ይሠውራልና ጠንቀቅ እንበል ጎበዝ፡፡ አክራሪነት በየትኛውም ሁኔታ ጎጂና አፍራሽ ነው፡፡ አክራሪ ክርስቲያን ይጠንቀቅ፤ አክራሪ እስላምም ይጠንቀቅ፡፡ አለበለዚያ ያከረሩት ነገር ሲበጠስ ከነአክራሪው ነው ገደል የሚከተው፡፡ አክርሮ ዘወር የማይባልባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ ሁልጊዜ ጌትነት የለም፡፡ … ወያኔን ስለምናውቅ በሌሎች መጨፍጨፍ የምንደሰት ጤናማ ዜጎች በመካከላችን አንኖርም፡፡ ግን የወያኔ ፕሮፓጋንዳና ለዘመናት የተረጨብን ፍርሀትን የሚያነግሥ ፕሮፓጋንዳ እንዲሁም ከደርግ ጀምሮ የወረደብን የልጆቻችንን ሬሣ ሳይቀር ከመንግሥት የመግዛት አረመኔያዊ ድርጊት  ሰንገው ይዘውን አንዳችን የአንዳችንን መከፋት ተከትሎ ብቻም ሳይሆን እኛ ራሳችን እየተገረፍንም ቢሆን ላለመጮህና ተቃውሞኣችንን ላለማሰማት የማልን እንመስላለን፡፡ እንጂ ይህ ወቅት ሁላችን ሃይማኖትና ብሔር ሳንል ሁላችን በህብረት ‹ሆ› ብለን በመውጣት ይህን አናቱ ተቆርጦ የተጣለ የቀትር እባብ ወያኔ ቆራርጠን የምንጥልበት ዘመን ነበር፡፡ መቆራረጥ ሲባል ሥጋዊ ትርጉም ሳይሆን መንፈሳዊ ፍቺን እንዲይዝልኝ እወዳለሁ፡፡ መቆራረጥ ክፉ ሃሳብን ነው – አካልን አይደለም፡፡ አካል ቢቆረጥ አካልን ይተካል፡፡ ክፉ አስተሳሰብ ከተቆረጠና ከተወገደ ግን የወደፊቱ ትውልድ ከመሰል ዕኩይ ፍልስፍናና ጠማማ አስተሳሰብ ይድናል፡፡ መቆራረጥ የሚለያየንንና የሚከፋፍለንን የወያኔን የዘውገኛነት ልክፍት ነው፤ መቆራረጥ ሀገርንና ሕዝብን ለከፋ ችግር የሚዳርግ የወንድሞቻችንንና የእህቶቻችንን የሆድ አምላኪነት የአስተሳሰብ ደዌ ነው፡፡

በኢትዮጵያ እስልምናና ክርስትና በሰላም ኖረዋል፡፡ የሃይማኖቶች በሰላምና በፍቅር የመኖር አርአያ ኢትዮጵያ ናት፡፡ በአንዳንድ ወቅቶች በዚህ ወያ በዚያ ሃይማኖት ተከታይ ምክንያት አንዱ በሌላው ላይ የሚያደርስውን ጉዳት ከታሪክ ማኅደር ማስታወስ ይቻላል ፤ ግን የግጭትን ታሪክ እያስታወሱ የሻረ ቁስልን ከማንቆርና ቂም በቀልን ከማጫር  ይልቅ ያሳለፍናቸውን የፍቅርና የደስታ፣ የመተሳሰብና የመተዛዘን ገጽታዎችን እያወሱ ተንኮለኞች ከቀደዱልን የጥፋት ቦይ መውጣት ነው የሚበጀን፡፡

አንድ መታወቅ ያለበት ነገር አለ፡፡ የአንድን ሰው ወይም የአንድን ማኅበረሰብ ሃይማኖታዊና ዘውጋዊ ማንነት በተመለከተ በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ ንጹሕ ዘርና ንጹሕ ሃይማኖት የሚባል ነገር በጭራሽ የለም፡፡ በዘመናት የአብሮነት ሕይወት ምክንያት ሁሉም ተባዝቆ ተባዝቆ ተቀላቅሏል፤ አንዱን ከሌላው ለመለየት በሚያስቸግር ሁኔታ ተዋህዷል – የኔን ብነግራችሁ ትገረማላችሁ፡፡ አንድ ወቅት የአፋሩ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ አባት አሊሚራህ እንዲህ አደረጉ አሉ፡- ሁሉም ሰው በዬሽብራሩ ወተት እንዲያመጣ አደረጉ፡፡ ሁሉም ያመጣውን ወተት ወደ አንድ ትልቅ ማጋቢያ እንዲገለብጥ አዘዙ፡፡ በኋላም ሁሉም ሰው ከዚያ የወተት ጋን ውስጥ የራሱን ወተት እየለዬ ባመጣበት ሽብራር መልሶ እንዲወስድ አስታወቁ፡፡ ሰው ሁሉ በአግራሞት ተጨንቆ “እንዴ! እንዴት ይታወቃል? ተደበላለቆ የለም እንዴ አባታችን?” ብሎ ይጠይቃቸዋል፡፡ ያም ብልሁ የሀገር አባት “የኢትዮጵያ ሕዝብም እንደዚህ ነው! ሁላችንም ስለተዋሃድን አንዳችንን ከአንዳችን ለመነጠል አይቻልም” በማለት ሕዝባቸውን በጉልበትና በዐዋጅ ከጋጋታ ሳይሆን በጥበብ አስተማሩ፡፡ የኢትዮጵያን ባንዴራ እንኳን አፋሮች ግመሎቻቸው እንደሚያውቋት የመሰከሩትም ያን ጊዜ ነው፡፡

ዶክተር ብርሀኑ በትናንቱ ቃለ መጠይቅ (እንዴት ያለ ግሩም ቃለ መጠይቅ ነበር!) እንዳሉት ከሞላ ጎደል በሁላችንም ቤት እስልምናና ክርስትና አሉ – እንዲያውም ከነዚህም በላይ፡፡ የሃይማኖት ውርርሱ በጋብቻ ወይም በትውልድ ሐረግ ከአባት እናት የተወረሰ ወይም በማወቅና በይሁንታ ከአንዱ ወደ ሌላኛው በመዛወር የተገኘ ሊሆን ይችላል፡፡ በየትም ይምጣ ዋናው ነገር ግን የሃይማኖት ጉዳይ የግል እንጂ የሀገር አይደለም፡፡ ሁሌ እንደሚባለው ሀገር የጋራ ናት፡፡ ሃይማኖት ግን የግል ነው፡፡ በአንድ ቤት ውስጥ አምስትም አስርም ሃይማኖት ሊኖር ይችላል፡፡ በአንድ ቤት ውስጥ ግን አምስትም አስርም ሀገር ሊኖር  አይችልም፡፡ ስለዚህ የማይቀላቀልን ነገር ማቀላቀል ለብንም፡፡ ቅድሚያ መስጠት ላለብን ቅድሚያውን እንስጥ፡፡

ዋናው ነገር ሃይማኖትም ሆነ የራሳችን ኅልውና  ሊኖረን የሚችለው በቅድሚያ ሀገር ስትኖረን ነው፡፡ ሀገር ሊኖረን የሚችለው ደግሞ የግልና የቡድን ነጻነታችንን የሚያከብር ቢቻል በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ራሳችን የምንመርጠው ባይቻል እንኳን የልብ ትርታችንን የሚያዳምጥ ከእኛው የወጣ እኛኑ የመሰለ ሀገርና ዜጋ የማይሸጥ እንደመለስ ያለ ወፍዘራሽ  የርግማን ውጤት ሳይሆን ሀገር በቀል የሆነ መሪ ሲኖረን ነው – እንደኃይለማርያምም የራሱን ማንነት ለመናኛ ጥቅም ያልለወጠ – እንደኤሳውም በምሥር ብኩርናውን ያልሸጠ፡፡ ዴሞክራሲ እዬዬም ሲዳላ ነው እንዲሉ ነው፡፡ ቀድሞ የመቀመጫዬን ብላለች ዝንጀሮ፡፡ አሁን እኮ ብዙዎቻችን ጨካኙን መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን ሳይቀር እየናፈቅን ነው – አትታዘቡኝ እኔ መንግሥቱን መናፈቅ ከጀመርኩ ቢያንስ ሰባት ዓመት አልፎኛል፡፡ መንግሥቱ እኮ ሥልጣኑን አትይበት እንጂ ከመሬት ተነስቶ የ‹ዐይንህን ቀለም› እያየ ሞትና እሥራት ርሀብና ሥቃይ አያዝብህም ነበር – እንዴ፣ መንጌ እኮ በጭካኔው ካባ ሥር የነበረው የሀገር ፍቅርና የሕዝብ ወገናዊነት እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አልነበረም፤ ሰውን መጥላትም ሆነ ማፍቀር በፈርጅ በፈርጁ እንጂ ሕጻኑን ከነታጠበበት ቆሻሻ ውኃ መድፋት ተገቢ አይመስለኝም(አንድ የኦሮምኛ አባባል ትዝ አለኝ፡- ‹አህያ እረዱ ቢሉን አህያ አረድን፣ አይጠቅማችሁም ቢሉን ጠራርገን ጣልን፣ እንዴ – ይጠቅማችሁ ነበር እኮ ቢሉንና ሄደን ብንፈልገው አጣነው› ይላል ይህ ቆንጆ ብሂል፡፡ አሁን መንጌን የት እናግኘው?(አቤት – ብዙ ሰው ሲንጫጫብኝ ታየኝ!)፡፡ ሰው የሚመሰገነው አንድም ሲሞት አንድም ሲለይ የሚባለው አውነት ነው፡፡ የራሳችንን ጨካኝ እንደዋዛ ሸኝተን አሁን የሰው ዘመሚትና ተምች አንበጣና የዓሣማ ግሪሣ በላያችን ላይ አነገሥን፡፡ ሰበቡ እኛ አይደለንም፤ ደግሞም እኛው ነን፡፡ የዘመን ዕንቆቅልሽ፡፡

እስላምና ክርስቲያን አንድ ነን አንድ አይደለንም ቅብጥርሶ የሚለው ክርክር ለተመቸው ነው፡፡ እኛ እሾህ ላይ ቆመን፣ የሲዖል እሳት ላይ ተቀምጠን የምንገኝ ዜጎች በመሆናችን ቢያንስ በአንድ የሥቃይ ቋት ውስጥ ገብቶ እንደሚወቀጥ የጋራ ዕጣ ተቋዳሽ ራሳችንን በመቁጠር በተናጠል ላለማለቅ በጋራ የጋራ ጠላታችን ላይ እንነሳ እላለሁ፡፡ ወያኔ የዘራብንን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ከቁብ አንጣፈው፡፡ መጀመሪያ ሀገር ትኑረን፤ ሀገር እንዲኖረን በማድረጉ ሂደት ጎን ለጎን የዴሞክራሲያዊ መንግሥት ምሥረታ በሚመለከታቸው የሀገሪቱ ልሂቃን ይሠራ፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ቀጣፊና አጭበርባሪ ወደሥልጣን የማይመጣበት አስተማማኝ የሕግ መደላድል በሀገራችን እንዲፈጠር ሁሉም ወገን ከዘርና ከሃይማኖት ግላዊ ጉዳዮች ተቆጥቦ በጋራ የኅልውና ማስጠበቂያ አውታሮች ላይ ይረባረብ፡፡

ታማኝ በየነን ጆሮ እንስጠው፡፡ ዛሬ ጧት ያዳመጥኩት የዛሬ ዓመቱ ንግግሩ አንጀቴን ነው የበላው፡፡ ለመቃወም ሲባል የተፈጠረ ሰው ካልሆነ በስተቀር ያን ንግግሩን መቼም የሚቃወም ሰው የሚኖር አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ ድል ማለት አንዱት ትቶ ሌላውን አንስቶ ነውና ግላዊ ጉዳዮችን ወደጎን እየተውን አንድ በሚያደርጉን ነገሮች ብቻ እንሰባሰብ፡፡ ያን ባናደርግ ተጎጂዎቹ እኛ ስንሆን ተጠቃሚዎቹ የጋራ ጠላቶቻችን ወያኔና መሰል የሀገር ውስጥና የሀገር ውጪ ጠላቶቻችን ናቸው፡፡ ጨው የሚጣፍጠው በጨውነቱ እስከቆዬ ድረስ ነው፡፡ ጨው ድንጋይ ነበር፤ ድንጋይም ጨው ነበር፡፡ ምርጫው የጨውና የድንጋይ ነው፡፡ ይህን ነባራዊ እውነት ዕንወቅ – ወቅቱን ጠብቆ ጨውም ጨው ድንጋይም ድንጋይ ይሆናሉ፡፡ የጭንቅላት ሥጋ መብሰሉ ለማይቀረው እሳት ፈጃል ይባላል፤ የኢትዮጵያ ጠላቶችም መቸ(ሸ)ነፋቸው ለማይቀረው ብዙ ‹ትግስት›ን እየጨረሱብንና  ውድመትን እስያከተሉብን ተቸገርነ፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ይባርክ!

አላሁዋክበር! (እግዚአብሔር ታላቅ ይሁን)

ከሲና የተረፉት የሲኦል ነዋሪዎች ጩኸት!!

“ላለፉት ሶስት ዓመታት ማንም ሳያውቀን ታስረናል። አሁን ጉዳያችን ለዓለም መድረሱን ሰማን።የተፈታን መስሎናል” የሚሉት እስራኤል ራምሌ በሚባ እስርቤት ከሶስት ዓመት በላይ ታስረው ያሉት ወገኖች ናቸው። ይህ የሆነው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር በርዕስ ለእስራኤል ጠ/ሚኒስትር በግልባጭ ደግሞ ከጉዳዩ ጋር አግባብ ላላቸው ለተለያዩ የአገሪቱ ባለስልጣናት፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የመገናኛዎች አውታሮች ያሰራጩትን ደብዳቤ ተከትሎ በእስር ላይ ያሉት ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በመንቀሳቀሱ ነው።

በእስራኤል የኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማኅበር ሊቀመንበር አቶ ሳሙኤል አለባቸው አድማሱ ለጎልጉል እንዳስታወቁት ከእስር ቤት በስልክ ያነጋገሯቸው ወገኖች የደብዳቤውን መልዕክት ሰምተው አስታዋሽ በማግኘታቸው ደስታቸውን ገልጸዋል። አቶ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው “ማድረግ የሚገባንን ማከናወን ጀምረናል የሚሆነውን እናያለን” በማለት በቅርቡ ከእስራኤል መንግስት ባለስልጣናት ጋር ለመነጋገር ወደ ስፍራው እንደሚያመሩና እስር ላይ የሚገኙትን ወገኖቻቸውን እንደሚጎበኙ አስታውቀዋል።

ኦክቶበር 16 ቀን 2012ዓም በኢትዮጵያ ወቅታዊ የመወያያ (ECADF) የፓልቶክ መድረክ አንድ እንግዳ ቀርቦ ነበር። ጠያቂዋ ሙያዬ ምስክር መናገርና መጠየቅ ተስኗት አምላኳን እየተማጸነች ድምጿ ጠፋ። በሱዳን በኩል በስደት ካገራቸው የሚወጡ ኢትዮጵያዊያን በሲና በረሃ የደረሰባቸውን አሰቃቂ ግፍ የሚናገረው ወጣት ፍቅሩ፣ በረሃ ላይ ስለሚደርስባቸው ዘግናኝ ግፍ ሶስት ዓመት ከሶስት ወር ከታሰረበት እስር ቤት ውስጥ የኑዛዜ ያህል የወገኖቹን ስቃይ አስተጋባ።

በረሃ ውስጥ የሚያገኟቸው አረቦች ገንዘብ ሲያጡ ኩላሊታቸውን ይወስዳሉ። አንዳንዴም አራትና ሶስት በመሆን “የኔን ውሰደው እነሱን ተዋቸው” በማለት ራስን ለእርድ የሚያቀርቡ ወገኖች አሉ። ኩላሊትና ልብ ለመልቀም ከጎረቤት አካባቢ እንደሚመጡ የተቆሙት የህክምና ባለሙያዎች የአካል ክፍላቸውን አውልቀው የወሰዱባቸው ወገኖቻችንን አካላቸው ተወስዶ ሲያበቃ አምጥተው ይዘረግፏቸዋል። ከአስራ አራት እስከ አስራ ስድስት ዓመት የሚሆናቸውን ታዳጊ እህቶቻችንን ክብራቸውን በመከራ ውስጥ ተገስሰዋል። ከዚህ ሁሉ መከራና ሞት ተርፈው ከለላ ፍለጋ እስራኤል የገቡት ወገኖች የገጠማቸው ህይወት እጅግ አሳዛኝ ነው።አቶ ሳሙኤል እንደሚሉት የኢትዮጵያውያኑ መታሰር እንዲታወቅ አይፈለግም ነበር። ተገደው ማመልከቻ በመጻፍ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ከተደረጉት ውጪ በእናታቸው እቅፍ ላይ ያሉትን ጨምሮ ከሶስት መቶ በላይ ወገኖች በጠረፍ ድንኳን ውስጥ ከታሰሩ አራትና ሶስት ዓመታትን አስቆጥረዋል።

አቶ ኦባንግ ከሁሉም በፊት የሚያነሱት ነጥብ “ለኢትዮጵያዊያን አዲስ ኢትዮጵያ ትሰራለች።አሁን ስደት ላይ ያሉት ወገኖች የጠየቁት ጊዜያዊ ከለላ ነው። በ1997 የጄኔቫ ኮንቬንሽን መሰረት ጉዳያቸው ሊጣራ ይገባል” የሚል የህግ ጥያቄ ነው። አቶ ሳሙኤልም አቶ ኦባንግ የሚሉትን ይጋራሉ።

በእስር የሚማቅቁት ወገኖች ድምጽ ይፋ መሆኑን ተከትሎ አቶ ኦባንግ የጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ግልባጭ የተደረገላቸው ታዋቂ የሚዲያ አካላት ስፍራው ድረስ ይደርሳሉ፣ እስረኞቹን አነጋግረውና ጎብኝተው የደረሰባቸውን በደል ለዓለም ያጋልጣሉ የሚል ፍርሃት መፈጠሩን፣ ለዚህም አንዳንድ ምልክቶች መታየታቸውን አቶ ሳሙኤል አለባቸው ይናገራሉ። ለጉዳዩ ቅድሚያ የሰጡትን ሚዲያዎችና ተቋማት በማመስገን ጥሪ የሚያስተላልፉት አቶ ሳሙኤል “በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚሰሩ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ድርጅቶች፣ ተቋማት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ አገርና ወገን ወዳዶች…” ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ያሰራጨውን ግልጽ ደብዳቤ በመደገፍ ጫናውን እንዲያበረቱ ጥሪ አቅርበዋል። አቶ ኦባንግ በጋራ ንቅናቄው በኩል አቤቱታ (ፒቴሽን) እንዲያስፈርሙም ተጠይቀዋል። በግል መልዕክት የላኩላቸው ክፍሎች እንዳሉም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያዊ ስደተኞች በኬንያ፣ በጃፓን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ እስራኤል፣ ኖርዌይ፣ ስዊድን፣ … በመሳሰሉት አገሮች ለሚደርስባቸው በደል “አገራችሁ እንደ ሶማሊያና ኤርትራ አይደለችም እያሉ የተባበሩት መንግስታትን መመሪያ ይጠቅሳሉ” የሚሉት አቶ ኦባንግ ድርጅታቸው (አኢጋን) ወደ ጃፓን፣ ሜክሲኮ፣ ኖርዌይ፣ ማልታ፣ ስዊድን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ … የተጓዘውና መልዕክተኛ የላከው ይህንን የተዛባ አመለካከት ለመቀየር እንደሆነ አመልክተዋል።

በሌሎች የዓለም ክፍሎች እንዳደረጉት ሁሉ በቅርቡ የጋራ ንቅናቄው በአካባቢው ከሚገኙ ቅርንጫፍ (ቻፕተር) አመራሮች ጋር በመነጋገር ወደ እስራኤል በመጓዝ ከሚመለከታቸው የእስራኤል ባለስልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩ ያስታወቁት አቶ ኦባንግ “የትም ይሁን የትም፣ የየትኛውም ብሄር አባል ቢሆን፣ ህጻናትም ሆኑ አዋቂዎች ኢትዮጵያዊያን ሁላችንም አንድ አካል ነን። ከታሰሩ ሁላችንም ታስረናል፣ ከተገረፉ ሁላችም ያመናል፣ ከተራቡ ሁላችንም ይርበናል፣ ሲጠሙ ሁላችንም ይጠማናል። የአንድ ወገናችን ስቃይ የሁላችንም ስቃይ በመሆኑ አቅማችን በፈቀደ ሁሉ የሚቻለንን ለማድረግ ዝግጁ ነን” ብለዋል። ይህ አስተሳሰብ “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ነጻ አይወጣም” ከሚለው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መሰረታዊ መርህ የሚነሳ መሆኑንም አመልክተዋል።

በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ወገኖቻችን እየተሰቃዩ መሆኑን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ በቅርቡ ታላላቅ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት፤ ሂውማን ራይትስንም ጨምሮ ወደ እስራኤል፣ ሲና በረሃና ኬንያ እንደሚጓዙ አመልክተዋል፡፡ አቶ ኦባንግ ከተቋማቱ ጋር ድርጅታቸው በተለይ ስለሚሰራው ሥራ አላብራሩም።

የተጀመረውን ዘመቻ ተከትሎ “ትምህርት እናስተምራቸዋለን” በሚል ህጻናትን ወደ ሌላ ስፍራ ማዘዋወር መጀመሩን፣ የእስራኤል ባለስልጣናት የጉብኝት ቀጠሮ መያዛቸውን፣ ያመለከቱት አቶ ሳሙኤል፣ አቡነ መርቆሪዎስ ስደተኞቹን ባሉበት ቦታ በመገኘት ለመጎብኘት ጊዜ መያዛቸውን ተናግረዋል። በልዩ ሁኔታ ጉብኝታቸውን ለማዘጋጅት ሙከራ እያደረጉ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
“በፍርድ ቤት የተፈረደበት እስረኛ ፍርዱን ሲጨርስ እንደሚለቀቅ ስለሚያውቅ ቀኑን ይጠብቃል። የእኛ አይታወቅም። እኛ ያለነው መደበኛ እስር ቤት አይደለም። ዓለም በቃኝ ነው…” ፍቅሩ ከሙያዬ ምስክር ጋር ባደረገው አሳዛኝ ቃለ መጠይቅ ወቅት የተናገረው ቃል ነው። ከሲና በረሃ ስቃይ በኋላ ሌላ ሲኦል!! ኦባንግ ሜቶ “ለሁላችንም መፍትሄ የምትሰጥ አገር አለችን። እሷም አዲሲቷ ኢትዮጵያ ናት። መሰረቷም ቅድሚያ ለሰብዓዊነት ይሆናል። አዲሲቷ ኢትዮጵያ እስክትሰራ ባለንበት ልንከበርና ችግራችንን ተገንዝበው ሊያስተናግዱን ይገባል” ይላሉ።

በተመሳሳይ ዜና አቶ ኦባንግ በኖርዌይ ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ለመነጋገር ወደ ኦስሎ ያመራሉ። በኖርዌይ የሚገኙ ስደተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ በየጊዜው የሚደረግባቸው ጫና እንዲቆም በየአቅጣጫው ጥረት ሲደረግ መቆየቱ በተለያዩ መገናኛዎች መገለጹ አይዘነጋም።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Post Navigation

%d bloggers like this: