Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

ህወሃት በሰሜኑ ግንባር ተጨናንቋል ም/መቶ አለቃ ደጀኔ እና ወታደር በኩር ይናገራሉ!

በልኡል አለም

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በምእራብ ትግራይ ሂሞራ በታች የማይካድራ ነዳጅ ማጠራቀሚያ አካባቢና እስከ ሰቲት ሁመራ እንዲሁም ጉናና ኡማህጂር ምስራቅ ትግራይና ዓዲ ግራት ድረስ የተሰማራዉ ከተለያዩ ክፍለ ጦሮችና ልዩ ኃይል እንዲሁም አካባቢ ሚሊሻዎች ተወጣቶ በስምሪት ላይ የሚገኘዉ የጸረ ሽብር ቡድን ወደ ግንባር እንዲሰማራ ባለመ መልኩ እየተበተነና እየተሰባጠረ እንደሚገኝ ታማኝ የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል።Ethiopian Soldiers

ይህዉ የጸረ ሽብር ቡድን በተለይም ከደረሰበትና እየደረሰበት ከሚገነዉ ድንገተኛ ጥቃት ምክንያት እጅግ በመመናመኑና በመዳከሙ ለስምሪት የአካባቢዉ ክፍለ/ጦሮች እንዲተኩ የተወሰነ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በአካባቢዉ ላይ ከሚደረገዉ ወታደራዊ መሯሯጥ የተነሳ ስጋት ስላደረባቸዉ አካባቢያቸዉን ወደ መልቀቁ ደረጃ ሊሸጋገሩ እንደሚችሉ እማኞች እየተናገሩ ይገኛሉ።

የህወሃት አዲስ ምልምልና ቅጥር ወታደሮች በመክዳት ምክንያት ከፍተኛ አደጋ እያስከተሉ በመምጣታቸዉ ወደ ደጀን ጦር በሚደረገዉ ዝዉዉር ከሰቲት ሁመራ ጀርባ ሲካተቱ ነባሮች ስምሪት እና ጸረ ሽብር ስምሪቱን እንደቆጣጠሩ ሆኗል።

በሰሜን ጎንደርና በምእራብ ትግራይ አካባቢ ተሰማርቶ የሚገኘው 24ተኛ ክ/ጦር ከ 25ተኛ ክ/ጦር ጋር ቅይጥ ብረት ለበስ ሜካናይዝድ በማደራጀት የጥምር ዉህድ የሚመስል ስልታዊ ክንዉን እያደረጉ ሲሆን ለዚህ ያለመረጋጋትና የመበታተን ጦስ ዋነኛዉ ምክንያት በየእለቱ በሰራዊቱ ላይ የሚደርሱ አነስተኛ ጥቃቶች እና የዉስጥ አርበኞች የፈጠሩት ጫና በአንኳርነት ተጠቃሽ ከመሆኑ በተጨማሪ የኢትዮ-ኤርትራ የጦርነት ስጋት የፈጠረዉ ትርምስ በራሱ የተያያዘ መጨናነቅ መፍጠሩን ባሳለፍነዉ ሳምንት ከሰሜኑ ግንባር ተነጥለዉ በጎረቤት ሐገር በተጠለሉ ም/መቶ አለቃ ደጀኔ ጥላሁን እና ወታደር በኩር ገ/ስላሴ ለታማኝ ምንጮቻችን ተናገረዋል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

ECADForum

posted by Tseday Getachew

 

 

Advertisements

“አርበኞች ግንቦት 7ትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ የደረግነው ጉዞ የሃገር ወዳድነት መለኪያ እንጂ ወንጀል አይደለም” ብርሃኑ ተክለያሬድና እየሩሳሌም ተስፋው

ወደ ኤርትራ ያደረግነው ጉዞ የሃገር ወዳድነት መለኪያ እንጂ ወንጀል አይደለም ሲሉ እነብርሃኑ ተክለያሬድ ለፍርድ ቤት የተከሳሽነት ቃላቸውን ሰጡ። አርበኞች ግንቦት 7ትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሊሻገሩ ሲሉ ተይዘው በወህኔ ቤት የሚገኙት የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባላት የነበሩ ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድና ወጣት እየሩሳሌም ተስፋው ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ይህንን ያቀረቡት በጽሁፍ ሲሆን፣ እንዳያነቡ መከልከላቸውም ተመልክቷል።Berhanu Tekleyared of Semayawi party

የሰላማዊ ትግል ጥረታቸው ባለመሳካቱ የመብትና የነጻነት ጥያቄ አንግበው ግንቦት 7ትን ለመቀላቀል ሲሉ መያዛቸውን የዘረዘሩት ብርሃኑ ተክለያሬድና እየሩሳሌም ተስፋው ወደዚህ ሁኔታ የገፋቸው የሃገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ ባቀረቡት ጽሁፍ ገምግመዋል። ከምርጫ 97 በፊት እንዲሁም በምርጫ 97 እና በኋላ ሰላማዊ ትግል በኢትዮጵያ ያለበትን ሁኔታ ገምግመው በውጤቱ 14 ጊዜያት ለእስር መዳረጋቸውን አስታውሰዋል።

በሃገሪቱ አሉ የተባሉ አፈናዎችን ዘርዝረው በዜጎች ላይ የሚደርሱ ሰቆቃዎችን አስታውሰው “ሰላማዊ ትግል ማድረግ ይቻላል ብለው የሚያምኑ የዋህ ወገኖቻችን ዕውነቱን ይገነዘቡት ዘንድ እንዲሁም ለከሳሾቻቸን ንጹህነታችንን እናስታውሳቸው ዘንድ ካደረሱብን ነገሮችን ጥቂቶችን ብቻ ለማንሳት እንሞክራለን” በማለት ለፍርድ ቤቱ በጽሁፍ ባቀረቡትና እንዳያነቡ በተከለከሉት የተከሳሽነት ቃላቸው ላይ ከራዕይ ወጣቶች ምስረታ ጀምሮ ያለፉበት ሂደትና እስከ 14 ጊዜያት የታሰሩበትን ዘርዝረዋል።

በሰላማዊ ትግል ያደርጉትን ጥረትና ያለፉበትን መሰናክል በተከሳሽነት ቃላቸው ላይ ያመለከቱት ብርሃኑ ተክለያሬድና እየሩሳሌም ተስፋው የመብትና የነጻነት ጥያቄዎች በጉልበት እየጨፈለቁ ያለው ስልጣን ላይ ያለው ቡድን ሌሎችን አሸባሪ ብሎ መፈረጅ አይልችልም፣ ይልቁንም በጸረሽብር ህጉ ለመጠየቅ የሚገባው እሱ ነው ሲሉ በጽሁፋቸው ተሟግተዋል።

ድምጻቸውን በጠመንጃ ተነጥቀው ሃገራቸውን ለማዳን ተገደው ነፍጥ ያነሱት የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ አባላት አሸባሪዎች አይደሉም ይልቁንም ሽብርተኛ ተብሎ ሊጠቀስ የሚገባው ህወሃት ነው ያሉት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ እየሩሳሌም ተስፋው “በዚህ ህዝባዊ ድርጅት አርበኞች ግንቦት 7 ሆነን ሽብርተኝነትን ለመከላከል የወሰንን ሽብርንና ሽብርተኝነትን የምንጸየፍ ንጹሃን ወጣቶችን ነን፣ በሽብር ቡድን አባል ለመሆንም ሆነ ሽብር ለመፈጸም አላሰብንም አልወሰንም አልተንቀሳቀስንም” ሲሉ ተከራክረዋል።

በሰላማዊ ትግል በኢትዮጵያ ለውጥ ማምጣት የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል በሚል አርበኞች ግንቦት 7ትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሲያቀኑ ተይዘው በወህኔ ቤት የሚገኙት ብርሃኑ ተክለያሬድ እየሩሳሌም ተስፋው ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት የተከሳሽነት ቃላቸው መጨረሻ ላይ “ለዚህ ችሎትና ለከሳሾቻችንን በአጽንዖት ልናስገነዝብ የምንፈልገው ነገር የፈጸምነው ድርጊት ከአንድ ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅ የሃገር ወዳጅነት መለኪያ እንጂ ወንጀል ሆኖ የሚያስከስሰን ባለመሆኑ በእስር ቤት ውስጥ ሆነን እንኳን ከምንጊዜውም በላይ ፍጹም ነጻነት ይሰማናል” ካሉ በኋላ አሳሪዎቻችንም ይኸው ነጻነት ይሰማቸው ዘንድ የቂም ፖለቲካን በመተው የታሰሩትን ፈትተው ለኢትዮጵያውያን ሁሉ የሰላም ጥሪ በማድረግ ስልጣን ለህዝብ እንዲያስረክቡ ጠይቀዋል። ይህን ካልፈጸሙ መጪውን ጊዜና ታሪክ ምላሽ ይሰጠዋል ሲሉ የተከሳሽነት ቃላቸውን አጠናቀዋል።

ESAT

Posted by Tseday Getachew

አቶ ሀብታሙ አያሌው አስቸኳይ የዉጭ አገር ሕክምና እንዲያገኙ ሰማያዊ ፓርቲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በላከው ደብዳቤ አሳሰበ

ሰማያዊ ፓርቲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በላከው ደብዳቤ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ሕዝብ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ወደ ውጭ ሀገር ሄደው ሕክምናHabtamu Ayalew is a former Public Relations Head of UDJ Party. እንዲያገኙና ከሀገር እንዳይወጡ የተጣለባቸው ማእቀብ በአስቸኳይ እንዲነሳ አሳስቧል። አያይዞም ሰማያዊ ፓርቲ በላከው ደብዳቢ እንዳሳሰበው “አቶ ሀብታሙ አያሌው በፍርድ ቤት ከሀገር እንዳይወጡ የተጣለባቸው እግድ ተነስቶ ወደ ውጭ ሀገር ሄደው ሳይታከሙ ቢቀሩ በግለሰቡ ሕይወት ላይ ለሚደርሰው አደጋ መንግስት (ሕወሃት) ሃላፊነቱን እንደሚወስድ እናሳስባለን ብሏል”።

አቶ ሀብታሙ አያሌው በድንገት እራሳቸውን ስተው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን እስካሁን ከሁለት በላይ ሆስፒታሎች ከአቅማቸው በላይ እንደሆነ በመግለጽ ወደ ሌሎች ሆስፒታሎች ልከዋቸዋል። አቶ ሀብታሙ አሁንም እራሳቸውን እንደሳቱ ይገኛሉ።

Letter from Semayawi (Blue) party

ECADForum

posted by Tseday Getachew

የኢትዮጵያ-ኤርትራ የጦርነት ጨዋታዎች (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

ይህን አስቂ ኝ (አስለቃሽ) ትአይንት  (ትያትር)  ፊልም ከዚህ ቀደም አላየነውምን?

Ethiopia and Eritrea war games

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2011 ዘ-ህወሀት የሕዝብን ስሜት ለማስቀየስ (ለማወናበድ ) ስለሚያካሂደው የጦርነት ጨዋታ  ትችት በጽሁፍ አቅርቤ ነበር፡፡

ዘ-ህወሀት ማለት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጦ የሚገኘው የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ በዓለም አቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት ስም ዝርዝር ውስጥ ስሙ ተመዝግቦ የሚገኝ አሸባሪ ድርጅት ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 አሁን በህይወት የሌለው የዘ-ህወሀት መሪ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመለኮስ እና ከግብጽ ጋር ደግሞ የውኃ ጦርነት ለማካሄድ የጦርነት ነጋሪት በመጎሰም ስለጦርነት አይቀሬነት ድምጹን ከፍ አድርጎ በማጉላት የወሬ ክኩን ይሰልቅ ነበር፡፡

በዚህም መሰረት ይኸው በአሁኑ ጊዜ እ.ኤ.አ ሰኔ 2016 ወደለመድነው የጦርነት አረንቋ ተመልሰን ለመዘፈቅ አሀዱ/አንድ በማለት ጀምረናል፡፡

ባለፉት ጥቂት ቀናት እንደገና በድጋሜ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ስለ”ጦርነት” ሰበካ፣ ስለጦርነት ሟርት እና ስለጦርነት ከበሮ ድለቃ ሌት ከቀን እየተለፈፈልን ሳንወድ በግድ እንድናዳምጥ በመደረግ ላይ እንገኛለን፡፡

እናም ይህንን የሕዝብ ስሜት/ቀልብ ማስቀየሻ ጦርነት እንደገና መመልከት ይኖርብናልን?

የዘ-ህወሀት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ጌታቸው “አፈ ጮሌው” ረዳ እንዲህ በሏል፣ “በሁለቱም ወገኖች በኩል ከፍተኛ የሆነ እልቂት ተፈጽሟል፣ በይበልጥ ደግሞ በኤርትራ በኩል ያለው ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እርምጃዎችን ስንወስድ ቆይተናል፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ እስከ አሁን ድረስ ስንወስዳቸው ከቆዩት እርምጃዎች በዓይነቱ እና በመጠኑ ከፍ ያለ እርምጃ መውሰድ በጣም ጠቃሚ ነገር ስለሆነ አስተማሪ የሆነ እርምጃ ወስደናል፡፡“

ኤርትራ በበኩሏ 200 የኢትዮጵያ ወታደሮችን በመግደል ከ300 በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ቁስለኛ አድርጊያለሁ የሚል መግለጫ ይፋ አድርጋለች፡፡

የካሊፎርኒያ ግዛት የዩኤስ አሜሪካ ታዋቂ የምክር ቤት አባል/ሴናተር የሆኑት ሂራም ጆሀንሰን ከብዙ ጊዜ በፊት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ጦርነት በሚመጣበት ጊዜ የመጀመሪያው የጥቃት ሰለባ የሚሆነው “እውነት” ነው፡፡“

ሁለት የጦርነት ተፋላሚ ቡድኖች በአንድ ዓይነት “እውነት” ላይ የጋራ ስምምነት ሲያደርጉ የምመለከት ከሆነ “እውነት” የመጀመሪያ እና ብቸኛ የጥቃት ሰለባ ሆኖ ስለመቆየቱ መገረም የምጀምር ይሆናል፡፡

እንደዚሁም ሁሉ የጠነባን ዓይጥ ማሽተት እጀምራለሁ፡፡ የጠነባን ዓይጥ ገና ከ10 ሺ ሜትሮች ርቀት ላይ ማሽተት እችላለሁ፡፡ ያ ሽታም  በኢትዮጵያ-ኤርትራን ጦርነት በሚባለው ላይ ተንሳፎ ይገኛል! (እፍ እፍ እፍ!!!)

በእርግጥ የጆሀንሰን ቁም ነገር የጦርነት ሰለባ መርህ አነጋገር  በጦርነት ተጫዋቾች ላይ አይሰራም፡፡

ለበርካታ ዓመታት ሳስተውለው እንደቆየሁት የዘ-ህወሀት አመራሮች ከሕዝብ ጋር መጥፎ የሆነ የግንኙነት አባዜ ላይ እንደወደቁ አድርገው እራሳቸውን በሚቆጥሩበት ጊዜ ለዚያ ማስቀየሻ ዘዴ ጦርነትን ያውጃሉ፡፡

ዘ-ህወሀት በህዝብ ላይ የሚፈጽመውን ሰብአዊ ወንጀል፣ ሙስና፣ ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀም እና ሰላማዊ ዜጎችን መጨቆንን ለመደበቅ ሲያስብ የአገር ውስጥ እና የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ስሜት ለማስቀየስ የሚያጋልጡትን መጥፎ ዜናዎችን ማፈን እና የሕዝብን ስሜት የማስቀየስ መንገድ እንደሚጠቀም እገምታለሁ፡፡

ያለፉት ጥቂት ሳምንታት ለዘ-ህወሀት መጥፎ ዜናዎች እንደነበሩ ምንም ዓይነት ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ አይደለም፡፡

ባለፈው ሳምንት የዩኤስ አሜሪካ የቦንድ እና የአክሲዮን ልውውጥ ኮሚሽን ዘ-ህወሀት ህገወጥ ወንጀለኛ በሆነ መልኩ ከደጋፊዎቹ እና ጥቅም አገኛለሁ ብለው ለቦንድ ግዥ ክፍያ ሲፈጽሙ ከቆዩት ኢትዮ-አሜሪካውያን 6.5 ሚሊዮን ዶላር በህገወጥ መልክ ዘርፎ በመገኘቱ ያወናበደዉን ገንዘብ ከነወለዱ እንዲመልስ ቅጣት ጥሎበታል፡፡ ዘ-ህወሀቶች ኮሚሽኑ ለሚያቋቁመው አስተዳዳሪ እ.ኤ.አ ሀምሌ 8/2016 ከማለፉ በፊት መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡

ይህ ድርጊት ለዘ-ህወሀት ትልቅ ውርደት እና የኢትዮጵያውያንን እና የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያንን ኪስ በማራቆት በአፍሪካ ታላቅ ግድብ እሰራለሁ በማለት መቋጫ የሌለው ዲስኩሩን ሲያሰማ በነበረው እና አሁን በህይወት በሌለው በወሮበላ ዘራፊው መሪ በአምባገነኑ መላስ ትውስታ ላይ ታላቅ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ የሚያልፍ ነገር ነው፡፡

ባልተመዘገበ እና ህገወጥ በሆነ የቦንድ ሽያጭ በማጭበርበር ግዙፍ የሆነ ግድብ በአፍሪካ እገነባለሁ ማለትን እስቲ አስቡት ጎበዝ! ቦንድ የማጭበርበር እኩይ ምግባሩን መከላከያ ዘዴ መሆኗ ነውን?

በዩኤስ አሜሪካ ሕግ መሰረት ያልተመዘገበ ቦንድ መሸጥ ሕገ ወጥ ነው በማለት ከሶስት ዓመታት ገደማ በፊት የተናገርኩ ሲሆን ከተናገርኩ ከሶስት ዓመታት በኋላ የዘ-ህወሀት መሪዎች የማጭበርበር አባዜ የተጠናወታቸው በመሆኑ ከማሰሮው ውስጥ እጃቸውን እንዳስገቡ እጅ ከፍንጅ እንደተያዙ ማሰብ እችላለሁ፡፡

የሚሰማ ጆሮ እና የሚያስተውል አእምሮ የላቸውም እንጅ እ.ኤ.አ ግንቦት 8/2013 ፊት ለፊት እና በቀጥታ ነግሪያቸው ነበር፡፡ ይህንን ነገር አታድርጉ! ያልተመዘገበ ቦንድ አትሽጡ! በዩናይትድ ስቴትስ የፌዴራል እና የአካባቢ መንግስታት ሕግ መሰረት ወንጀል ነው ብዬ ነግሪያቸው ነበር፡፡ ወንጀልን አትስሩ፣ ከጊዜ በኋላ አደጋው የሚያንዣብብ እና የሚያስጠይቃችሁ ይሆናል በማለት በግልጽ ተናግሬ ነበር፡፡

እንደተናገርኩት ከሶስት ዓመታት በኋላ ያልተመዘገበ ቦንድ ሽያጭ (ወንጀል ነው፣ የ1933 የቦንድ ድንጋጌ ክፍል 20 (b)ን ይመልከቱ) ወንጀል ስለሆነ ማጅራታችዉን ተያዙ፡፡

ሆኖም ግን የዘ-ህወሀት ያልተመዘገበ ቦንድ ዋና ሻጮች የወንጀል ቅጣቱን በማጭበርበር አንደተለመደው ሊያልፉት አልቻሉም፡፡

በእርግጥ አላለፉትምን?

የዘ-ህወሀት መሪዎች ለበርካታ ዓመታት ያህል ሰብአዊ መብቶችን እየደፈጠጡ ምንም ዓይነት ተጠያቂ ሳይሆኑ ደረታቸውን ነፍተው ተቀምጠው እንደሚገኙት ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ በአሜሪካ ሕጎች ላይም አፍንጫቸውን በመንፋት ከወንጀል ተጠያቂነት የሚያመልጡ መስሎ ታይቷቸዋል፡፡

በምንም ዓይነት መልኩ ሊሆንላቸው አልቻለም፡፡

ጉዳዩ በኮሚሽኑ (SEC) ግልጽ እና ይፋ ከሆነ በኋላ የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው ሂዩማን ራይትስ ዎች (ሂራዎ)/Human Rights Watch (HRW) “ጭካኔ የተመላበት እርምጃ፡ ለኢትዮጵያ ኦሮሞዎች ተቃውሞ የተሰጠ የግድያ እና እስራት ምላሽ“ በሚል ርዕስ ትልቅ ዘገባ አቅርቧል፡፡

ያ ዘገባ “ከመጠን ያለፈ እና አላስፈላጊ የሆነ የጥላቻ ኃይል መጠቀም እና ዜጎችን በጅምላ በቁጥጥር ስር የማዋል፣ መጥፎ የእስር ቤት አያያዝ፣ የሰላማዊ አመጽ እንቅስቃሴውን ለማኮላሸት የመረጃ ምንጮችን መቆጣጠር“ በማለት ዝርዝሩን አቅርቧል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ በማስመልከት የሂራዎ/HRW የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክር የሆኑት ሌዝሊ ሌፍኮው እንዲህ ብለው ነበር፣ “የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች የሰው ልጆችን ህይወት ከቁብ ሳይቆጥሩ የጭካኔ ተኩስ በመክፈት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን፣ አርሶ አደሮችን እና ሌሎችን ሰላማዊ ዜጎችን ገድለዋል፡፡“

ለሰው ልጆች ህይወት ምንም ዓይነት ቁብ ሳይሰጡ በሰላማዊ ተቃዋሚ ስብስብ ላይ የጭካኔ ተኩስ መክፈት በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ ሰብአዊ ወንጀል ነው፡፡ ይህንን የምለው ለታሪክ ምዝገባ ብዬ ነው፡፡

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 የዘ-ህወሀት ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ በአመጹ ላይ የተገደሉት ሕዝቦች “ሁከት እና ብጥብጥን ዓላማ ያደረገ የተደራጀ እና የታጠቀ አሸባሪ ኃይል በመፍጠር ሞዴል አርሰ አደሮችን፣ የህዝብ መሪዎችን እና ሌሎች በክልሉ የሚኖሩትን የጎሳ ቡድኖች መግደል በመጀመራቸው ነበር” ብሏል፡፡

የሚገርም ነገር እኮ ነው ጎበዝ! በመንገድ ላይ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ የሁለተኛ ደረጃ እምቦቃቅላ ተማሪዎች እና የኮሌጅ ተማሪዎች በምን መስፈርት እና መለኪያ ነው “የተደራጀ እና የታጠቀ አሸባሪ ኃይል” ሊባሉ የሚችሉት? ወያኔ በእራሱ የፍርሀት ምዕናብ እየፈጠረ በህዝብ ላይ የሚነዛው ሽብር ካልሆነ ሌላ ምን ሊባል ይችላል?

ውሸት እና ቅጥፈት በሚነገርባት ምድር ፑፍ የተባለው ድራጎን (ዘንዶ)፣ ሳንዲ እየተባለች የምትጠራውን ተንቀሳቃሽ ሲኒማ ልጃገረድ ውሸት እና ቅጥፈት ወደሚነገርባት ምድር የወሰደበትን ታሪክ  አስታወሰኝ፡፡ ሳንዲ እዚያ ከደረሰች በኋላ በሬ ወለደ እያለ የሚናገረውን ፕናክዮንን አገኘችው፡፡

ውሸት እና ቅጥፈት በሚነገርባት ምድር ፑፍ እና ሳንዲ ማንም አይቷቸው የማያውቅ ቀይ እና ሰማያዊ ላም እንዲሁም ቀይ እና ነጭ ዝሆንም አዩ፡፡

13 ወራት ሙሉ ውሸት እና ቅጥፈት በሚነገርባት በዘ-ህወሀት ቁጥጥር ስር ባለችው ኢትዮጵያ የትምህርት ቤት ልጆች እና የኮሌጅ ተማሪዎች ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር እንደተዘጋጀ ቡድን ተቆጥረው “የተደራጀ እና የታጠቀ አሸባሪ ኃይል” ሆነው ይታያሉ፡፡

ኢትዮጵያ 13 ወራት ሙሉ የፀሐይ ብርሀን የሚፈነጥቅባት ሀገር መሆኗን ነበር እኔ የማስታውሰው፡፡

በነገራችን ላይ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ሌሎች እ.ኤ.አ በ2007 በኬንያ ተደርጎ በነበረው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት ተከስቶ በነበረው ውዝግብ ወደ 2000 ገደማ በሚሆኑ ሰላማዊ ኬንያውያን ዜጎች እልቂት ላይ እጃቸው አለበት በሚል የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እ.ኤአ. በ2012 ክስ መስርቶባቸው ነበር፡፡

ሂራዎ/HRW በኦሮሞ ሰላማዊ አመጸኛ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው እልቂት እንዲጣራ ነጻ የሆነ አጣሪ አካል እንዲቋቋም ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሆኖም ግን ዘ-ህወሀት እንደተለመደው የዝሆን ጆሮ (የጅብ ሆድስ አለኝ) ይስጠኝ በማለት ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል፡፡

ዘ-ህወሀት ወደ 20 ሚሊዮን ገደማ የሚሆነውን ህዝብ እያሰቃየ ያለውን የረሀብ ሁኔታ አያያዝ በሚመለከት እያደረገ ስላለው ፍጹም የሆነ ብቃትየለሽነት እና ይኸ አውዳሚ የሆነ ረሀብ በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ሰቆቃ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እይታ ደብቆ ለማቆየት እያደረገ ባለው አሳፋሪ ጥረት የህዝብ ግንኙነት ስራው በመጥፎ ሁኔታ ተበላሽቶበታል፡፡

ከዩኤስኤአይዲ/USAID እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ የድህነት ወትዋች አቃጣሪዎች መጥፎ ሸፍጥ ጋር በመተባበር ዘ-ህወሀት ድርቁ ካጠቃቸው አካባቢዎች ምንም ዓይነት መረጃ እንዳይወጣ በማድረጉ እና ጋዜጠኞች ወደ አካባቢው በመንቀሳቀስ እውነታውን ለእራሳቸው እና ለህዝቡ ፈልፍለው እንዳያወጡ በመከልከሉ ደባ ተሳክቶላቸዋል፡፡

እስከ አሁን ድረስ ዘ-ህወሀት ስለረሀቡ ሁኔታ ስለጠቅላላ ተጠያቂነቱ እና ግዴለሽነቱ፣ ለብቃትየለሽነቱ እና ወንጀለኛነቱ ምንም ነገር ባለመሆኑ ስኬታማ ሆኗል፡፡ (ለዩኤስኤአይዲ/USAID አስተዳዳሪ ለጋይሌ ኢ. ስሚዝ የጻፍኩትን ደብዳቤ ይመልከቱ፡፡)

ዘ-ህወሀት ሁሉንም መጥፎ ዜናዎች ሁሉ ፍጹም በሆነ መልኩ ለምን እንደሚያፍን ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል፡፡

ዘ-ህወሀት የህዝብን ስሜት ለማስቀየስ መጥፎ ዜናዎችን በማፈን የጦርነት ወሬዎችን ከማምረት እና የጦርነት ነጋሪት ከመጎሰም የተሻለ ምን የተሻለ ስልት ሊኖረው ይችላል?

በዘ-ህወሀት እና በስተሰሜን በኩል ባሉት ጠላቶቹ መካከል የሚካሄደው ጦርነት በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ይደረግ እንደነበረው የጽጌረዳ ጦርነት ዓይነት ነው፡፡ የተለያዩ አባላት በሆኑት በአንድ ቤተሰብ መካከል የሚደረግ ጦርነት የውስጥ ጦርነት ነው፡፡

ዘ-ህወሀት እና ጠላቶቼ ናቸው እያለ የሚወነጅላቸው ኃይሎች በወንድማማችነት በአንድ ላይ ሆነው ለበርካታ ዓመታት በመዋጋት ወታደራዊውን አገዛዝ በማስወገድ ስልጣንን ተቆጣጠሩ፡፡ በወታደራዊ ኦፕሬሽን እና በህዝብ ግንኙት ስራ በአንድ ላይ ሆነው በመረዳዳት በወታደራዊ ጓደኝነት ሲታገሉ ቆይተው ነበር፡፡

በርካታ የዘ-ህወሀት አመራሮች ከጠላቶቻቸው ጋር የቤተሰብ እና የስጋ ዝምድና ትስስር እንዳላቸው ከበቂ በላይ ማስረጃ ሊቀርብበት የሚችል ጉዳይ ነው፡፡

ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ በ1991 ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ አሁን እየከሰሷቸው ካሉት ጋር አስቂኝ በሆነ የመድረክ ላይ ተውኔት በደስታ ስልጣንን ተካፍለው እንደ አበደ ውሻ ጭራቸውን በመቆለፍ ቆዩ፡፡ ያ ሁኑታ ግን እ.ኤ.አ በ1993-94 ላይ ተቋረጠ፡፡

እ.ኤ.አ ከ1998-2000 ባለው ጊዜ ውስጥ ሁለቱ የጦር ጓደኛሞች በድንበር ጦርነት ተጠመዱ፡፡ ኤርትራውያን የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት በመጣስ የኢትዮጵያን ግዛት ተቆጣጠሩ፡፡ ሆኖም ግን በግጭቱ ከ70 እስከ 120 ሺ የሚገመት የወታደሮች እና የሲቪል ዜጎች ህይወት ከተገበረ በኋላ ተቆጣጥረውት ከነበረው ግዛት በኃይል ተባረሩ፡፡

አሁን በህይወት የሌለው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስቡ አለቃ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ወዲያውኑ የድል ዜናን አወጀ፣ እናም በዓለም አቀፍ የሽምግልና እርቅ ሰበብ በተሰላ የፖለቲካ የሸፍጥ ስሌት እና በሀገር ክዳት ወረውት የነበረውን የሀገሪቱን አንጡራ ግዛት ተመልሶ ኤርትራውያኖች እንዲወስዱት በመፍቀድ የተንበርካኪነቱን የመድረክ ላይ ተውኔት አከናወነ፡፡

አምባገነኑ መለስ ጠንካራ የሕግ መከላከል ጥረትን ማድረግ ሲችል የሽምግልና የዕርቅ ስምምነቱ የተጻፈበትን ወረቀት ዋጋ አያወጣም በማለት የሀገርን ጉዳይ እንደተራ ነገር በመቁጠር ጉዳዩን አጣጣለው፡፡

በአሁኑ ጊዜ የቀድሞ የጦር ጓደኛሞች በጦርነት ላይ እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ የሌባ ጣቶቻቸውን አንዳቸው በአንዳቸው ላይ በመቀሰር የተለመደ ተራ ቅጥፈታቸውን በማራመድ ላይ ናቸው፡፡

ሆኖም ግን እነዚህ ውሸት እንጅ እውነት በአፋቸው የማይገባ ኃይሎች በእርግጠኝነት ጦርነት ያካሂዳሉ ወይስ ደግሞ የጦርነት ጨዋታ በመጫወት ላይ ነው የሚገኙት?

ሆኖም ግን ለምን እርስ በእርሳቸው እንደሚዋጉ ትክክለኛውን ነገር አይናገሩም፡፡

አንድ የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣን እንዳቀረበው ውንጀላ ከሆነ የኤርትራ መሪዎች በሰው ልጆች ላይ የመብት ረገጣ ማለትም ማሰቃየትን፣ ግድያ እና በባርነት መያዝን ጨምሮ የሰብአዊ መብትን ይደፈጥጣሉ የሚል ዘገባ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የምታቀርበው ኢትዮጵያ ናት የሚለው የመድረክ ላይ ትወና የተተወነው በኢትዮጵያ ነው በማለት በኢትዮጵያ ከምስክሮች የሚሰበሰበው መረጃ እንዳትረጋጋ ለማደረግ ጥረት ለምታደርገው ሀገር ለኤርትራ ጥሩ የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ እንድታገኝ አስችሏታል፡፡

የተመድ ዘገባ ለጦርነቱ መንስኤ መሆን ችሏልን?

“ሀገሮች ለምን እንደሚዋጉ“ በሚል ርዕስ ሪቻርድ ኔድ ሌቦው በ2010 በጻፉት መጽሐፋቸው ላይ አራት ታሪካዊ ዓላማዎች፡ ፍርሀት፣ ፍላጎት፣ ዝና እና በቀል በሚል መንግስታት ጦርነትን እንዲቀሰቅሱ ይመሯቸዋል በማለት የክርክር ጭብጣቸውን አቅርበዋል፡፡ አብዛኞቹ ጦርነቶች ለዝና እና ቀደም ሲል አንዱ መንግስት በጠላቱ ላይ ድልን በመቀዳጀት ግዛቱን ያስለቀቀው ከሆነ ያንን ለመበቀል ሲባል የሚደረጉ ናቸው በማለት ይሞግታሉ፡፡

በአሁኑ ጊዜ ዝና፣ በቀል እና ግዛትን ለመያዝ ሲባል በሁለቱ መንግስታት መካከል ለጦርነት መንስኤ ሊሆን ይችላልን?

እኔ የማደርጋቸው የአምባገነንነት እና ጦርነት ጥናቶች በእነዚህ ነገሮች የሚቀሰቀስ ሌላ የተለዋጭ ገለጸ ሀሳብ ያቀርባሉ፡፡

“የጦርነትን ካርድ” ማውጣት በአምባገነኖች የእጅ መጽሐፍ ውስጥ ያለ አሮጌው የማጭበርበር ዘዴ ነው፡፡

የእጅ መጽሐፉ እንዲህ ይላል፣ “የህዝብ ጥላቻ ሲመጣ ጦርነትን አውጅ፡፡ እውነተኛ ወይም ደግሞ የውሸት የማስመሰያ ጦርነት አውጅ፡፡ ምንም ዓይነት ችግር የለውም፡፡ ስለጦርነት አውራ፡፡ የጦርነት ቅስቀሳን ሆን ብለህ አሰራጭ፡፡ የጦርነት ከበሮ ምታ፡፡ የጦርነት ጨዋታዎችን ተጫወት፡፡“

ግን ለምን ጦርነት?

ምክንያቱም ጦርነት የተረጋገጠ እና በተግባር የተፈተነ የህዝብ ስሜት ማስቀዬሻ ፍቱን ዘዴ ነው!

ከሮማ ነገስታት ጀምሮ እስከ አሁን እስካለንበት ዘመን ድረስ የጦርነት ጌቶች እና ትናንሽ አምላኮች የጦርነት ካርድን ተጫውተዋል፣ እናም በስልጣን ኮርቻ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመቆየት የግዛት ዘመናቸውን ለማስቀጠል ሲሉ በህዝቡ ልብ ውስጥ የአርበኝነት ትኩሳትን ይቀሰቅሳሉ፡፡

በምዕተ ዓመታት የጦርነት ቴክኖሎጂው ሊቀየር ይችላል ሆኖም ግን የማታለል ማሽኑ፣ ማጭበርበሩ፣ ሸፍጡ እና የጦርነት ናፋቂዎች የከበሮ ድለቃ ዜማ እና አፈጻጸም እስከ አሁንም ድረስ ያው ነው፡፡

አምባገነኖች ሁልጊዜ በጦርነት ቃላት ይጀምራሉ፣ እናም ህዝቦቻቸውን በጦርነት ውሸት ፕሮፓጋንዳዎች፣ ፍብረካዎች እና ስለጦርነት ዝርዝር መረጃዎች የሌለው እና አሳሳች መረጃዎችን በማቅረብ በፕሮፓጋንዳ ጎርፍ እንዲጥለቀለቅ ድርጋሉ፡፡

አምባገነኖች በጦርነት መጀመሪያ አካባቢ ሊተነበይ የሚችል የአካሄድ ስርዓትን ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡ ስለጦርነቱ አስፈላጊነት ግዙፍ የሆነ መግለጫ ለህዝብ ያቀርባሉ፣ እንደዚሁም ሁሉ በሀገር ውስጥ ታላቅ ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ተስፋን በመሰነቅ በጠላታቸው ላይ ግዙፍ የሆነ ጥላሸት የመቀባት ዕኩይ ምግባርን ያራምዳሉ፡፡

ታምራዊ በሆነ መልኩ የእናት ሀገር ፍቅርን ከመቅጽበት ይለብሳሉ፣ በሰንደቅ ዓላማዎቻቸው ውስጥ ይጠቀለላሉ እናም ኃያል አርበኞች ይሆናሉ፡፡ አርበኝነትን ለማነሳሳት በመሞከር የተወሰዱ ግዛቶችንም እናስመልሳለን በማለት ቃል ይገባሉ፡፡

አምባገነኖች የህዝቡን ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ዓይን ባወጣ መልኩ በሀገር ወዳድ ብሄራዊነት እና የትምክህት እንቅስቃሴዎችን ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡ ስለማይቀረው የጦርነት ጥቃት፣ ስለማይታዩ ጠላቶች፣ ሳይታሰብ ስለሚመጡ አሸባሪዎች፣ ስለሀገር ሉዓላዊነት መደፈር እና ስለሌሎች ነገሮችም ሁሉ ገደብ የሌለው ፕሮፓጋንዳ እና ቅስቀሳ በማካሄድ በህዝቡ ዘንድ ፍርሀት እንዲነግስ ያደርጋሉ፡፡

በሚያገኙት በማንኛውም አጋጣሚ ሁሉ ህዝቡ ስሜታዊ ሆኖ በጠላቶቻቸው ላይ በቁጣ እንዲነሳ በመቀስቀስ የህዝብን ድጋፍ ለማግኘት አሳፋሪ እና የሌለ ታሪክ በመፍጠር እነርሱ አገር ወዳድ አርበኛ የእነርሱ ተቃዋሚዎች እና ጠላቶች ደግሞ ምንም ዓይነት የሀገር ወዳድነት አርበኛነት የሌላቸው አድርገው ይፈርጃሉ፡፡

ሁሉም ነገር ሲከሽፍ እና ሲወድቅ አምባገነኖች በህዝቡ ላይ ፍርሀት እና ስሜታዊነት እንዲነግሱ በማድረግ የህዝብን ስሜት በማስቀየስ እነርሱ ከተዘፈቁበት ሰብአዊ ወንጀል እና አምባገነናዊ አገዛዝ ለማምለጥ ጥረት ያደርጋሉ፡፡

አብዛኛውን ጊዜ የጦርነት ቃላት ስለአርበኝነት እና ስሜታዊነት በመቀስቀስ ከመክሰስ እና ጥላሸት ከመቀባት የበለጠ ኃይል የላቸውም፡፡ ወደ ሌላ ወደየትም ፈቀቅ ሳይሉ ስም በማጥፋት እና ጥላሸት በመቀባት ላይ ብቻ ተወስነው ይቀራሉ፡፡

ሆኖም ግን አምባገነኖች አብዛኛውን ጊዜ በጦር ሜዳ አውድ ውስጥ የጥይት ጭሆት ካቆመም በህዋላ ስለጦርነት ማውራት እና የጦርነት ነጋሪት መጎሰምን አጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡

ሆኖም ግን ጦርነት ለአምባገነኖች የማታለያ ሀሳብ ነው፡፡

የአምባገነኖች የመኖር ህልውና በጀመሩት ጦርነት የማሸነፍ ዝንባሌ የሚወሰን ይሆናል፡፡

በጦርነት የአምባገነኖች መሸነፍ ማለት የህልውናቸው ፍጻሜ ማለት ነው፡፡

የተሸነፉ አምባገነኖች አብዛኛውን ጊዜ በመፈንቅለ መንግስት ወይም ደግሞ በሌሎች ህዝባዊ አመጾች ሊወገዱ ይችላሉ፡፡ አምባገነኖች በሚሸነፉበት በእያንዳንዱ ጦርነት የመሰደድ፣ የመታሰር እና የመሞት ዕድላቸው እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡

ጥቂት የአፍሪካ አምባገነኖች ዓይን ባወጣ መልኩ ያለምንም ተጨባጭነት ሁኔታ በለኮሱት ጦርነት ቢሸነፉም ቅሉ ለበርካታ ጊዚያት በስልጣን ላይ ተጣብቀው ቆይተዋል፡፡ በእርግጥ ሽንፈታቸውን ለምክንያት እና ለይቅርታ በመጠቀም ህዝቦቻቸውን ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ ለመግዛት ይጠቀሙበታል፡፡ ጠላቶቻቸውን እንደ ጭራቅ በመቁጠር በእራሳቸው ህዝቦች ላይ እንደማስፈራሪያ በመጠቀም ህዝቡ ለጥ ገጥ ብሎ እንዲገዛላቸው ይጠቀሙበታል ፡፡

አምባገነኖች ስለሚጭሩት የጦርነት እሳት እውነታነት የሂትለር ቀኝ እጅ ከነበረው ከኸርማን ጎሪንግ የበለጠ እውነታውን ያረጋገጠ በዚህ ዓለም ላይ የለም፡፡ ኸርማን እ.ኤ.አ በ1945 ኑረምበርግ በተሰየመው የዓለም አቀፍ ችሎት ላይ ቆሞ ሲጠየቅ እንዲህ በማለት ተናግሮ ነበር፡

“በተፈጥሮ ተራው ህዝብ ጦርነትን አይፈልግም፡፡ ይኸ ነገር ግንዛቤ የተወሰደበት ጉዳይ ነው፡፡ ሆኖም ግን ከሁሉም በላይ የሀገሪቱ መሪዎች ናቸው ፖሊሲውን የሚወስኑት እናም በዚያ አቅጣጫ ህዝቡን የሚስቡት… ድምጽ ወይስ ድምጽ አልባ [ዴሞክራሲያዊ ወይስ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ያልሆነ መንግስት] ህዝቡ ምንጊዜም ቢሆን መሪዎች በሚያስቡት ነገር ላይ ሊመጣ ይችላል፡፡ ያ ቀላል ነገር ነው፡፡ ሁላችሁም ልትሰሩት የምትችሉት ነገር ቢኖር ጥቃት እየደረሰባቸው መሆናቸውን ንገሯቸው፣ እናም የአርበኝነት ጉዳይን ቸል በማለት ሀገሪቱን ለከፍተኛ አደጋ በሚጥሉት ሰላማዊ ሰዎች ላይ ውግዘት አካሂዱ፡፡ ይህ ጉዳይ በእያንዳንዱ ሀገር ሙሉ በሙሉ ይሰራል፡፡“

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2011 አሁን በህይወት የሌለው የወሮበላ ዘራፊው ሀዋሃት መሪ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የጎሪንግን አባባል እንዳለ በመውሰድ እንዲህ በማለት የገደል ማሚቶውን አሰምቶ ነበር፡

“አሁን በቅርቡ ኤርትራ አልሸባብን እና በሀገር ውስጥ የበቀሉትን አውዳሚ ኃይሎች በማሰልጠን በሀገራችን ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በዝግጅት ላይ ትገኛለች፡፡ ሆኖም ግን ግብጽ ለዚህ የሽብር ድርጊት በዋናነት ከጀርባ ቆማለች፡፡ እስከ አሁን ድረስ የነበረን ስልት ልማታችንን በማፋጠን የሀገራችንን ሉዓላዊነት ማስከበር ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን ዝም ብለን በቸልታ ቆመን ምንም ዓይነት መከላከል ሳናደርግ የምናይበት ሁኔታ የለም፡፡ ዝም ብሎ መከላከል የሌለው ድርጊትን እያራመድን መቆየትን እንደ ብቸኛ አማራጭ አድርገን ለመቀጠል አንችልም፡፡ ስለዚህ የኤርትራ ህዝብ አምባገነኑን አገዛዝ ለማስወገድ የሚያደርገው ትግል እንዲፋጠን መንገድ መቀየስ አለብን፡፡ ይህንን ስንል እንዲሁ ዘው ብለን በሀገራቸው ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ እንገባለን ማለት አይደለም፣ ሆኖም ግን ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነውን እጃችንን ረዘም አድርገን ወደዚያ መላክ ይኖርብናል፡፡ የኤርትራ መንግስት በእኛ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሚሞክር ከሆነ እኛም ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ እንሰጣለን“ ነበር ያለው አፈር ይቅለለውና፡፡

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2006 የእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረትን ከሶማሊያ ለማስወጣት እና አልሻባብን ለማጥፋት 843 ቀናት ያህል ጦሩን እዚያ ካቆየ በኋላ ስኬታማ ሳይሆን ሀፍረቱን ተከናንቦ ሰራዊቱን ከሶማሊያ በሚያስወጣበት ወቅት በተመሳሳይ መልኩ እንዲህ በማለት ነበር የጦርነት አመክንዮውን የገለጸው፡

“አካላዊ ጉዳትን በሚመለከት ወይም ደግሞ የወረራው አካላዊ ሁኔታን በሚመለከት ካለፈው የክረምት ወቅት ጀምሮ ምን እንደተደረገ ለመግለጽ የእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የታጠቁ ኃይሎችን በማሰልጠን፣ በማስታጠቅ እና ሰርገው እንዲገቡ በማድረግ ላይ ቆይቷል፡፡ እነዚህ ኃይሎች በኢትዮጵያ ውስጥ መረጋጋት እንዳይኖር ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩት እነዚህ ኃይሎች ወደ ኢትዮጵያ ሰርገው በመግባት ከደህንነት ኃይሎች ጋር ግብግብ በመግጠም ላይ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ያህልም የእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረት እነዚህን ሰርጎ ገብ ኃይሎች  አሰልጥኗል፣ አስታጥቋል፣ እስከ ድንበሩ ድረስ ለሰርጎ ገቦቹ የመጠለያ እና የትራንስፖርት አገልግሎትም አቅርቧል፡፡ በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ ላይ የጥቃት እርምጃ ለመውሰድ ቀጥተኛ በሆነ መንገድ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም ድርጊት ካለፈው የክረምት ወቅት ጀምሮ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ እስከ አሁንም ድረስ ቀጥሏል፡፡“ 

እ.ኤ.አ በ2009 ጭራውን በእግሮቹ መካከል በመወተፍ ከሶማሊያ ሲወጣ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የፈላስፋ ሸፍጡን በመያዝ እንዲህ በማለት ጉራውን ቸረቸረ፣ “ለኢትዮጵያ አዎንታዊ አመላካከት የሌለው የሶማሊያ ህዝብ መንግስት ቢኖርም እንኳ በአሁኑ ጊዜ ያለው ሁኔታ የተሻለ ነው፡፡ በሶማሊያ ውስጥ የተረጋጋ መንግስት እንዲኖር ማድረግ ብሄራዊ ፍላጎታችን ነው፡፡“        

ይኸው አምባገነን ሰው እ.ኤ.አ ታህሳስ 2006 አሸባሪዎችን ከሶማሊያ ውስጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ ድል በማድረግ አባርረን እንመለሳለን ብሎ ነበር፡፡

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የሰራው ነገር ቢኖር በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሲቪል ሶማሊያውያን ሞትና እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ደግሞ የጅምላ ተፈናቃይ የመሆናቸው ጉዳይ ነው፡፡

በሶማሊያ ውስጥ ሄደው የሞቱ የመለስ ዜናዊ የጦር ወታደሮች ብዛት ስንት ነው?

እ.ኤ.አ በ2009 አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከይስሙላው ፓርላማ ፊት በመቅረብ እንዲህ በማለት ተናገረ፣ “በሶማሊያ ውስጥ ስንት ወታደሮች እንደሞቱ ፓርላማው ማወቅ አስፈላጊው አይደለም፡፡“

አምባገነኖች ህዝቦቻቸውን የጦርነት እራት እንዲሆኑ በማድረግ በጦርነቱ ምን ያህል ወታደሮች እንደሞቱ ማወቅ የእናንተ ስራ አይደለም በማለት መናገር ይችላሉ፡፡

እንደዚሁም ሁሉ በአሁኑ ጊዜ ዘ-ሀወሀት እና ኤርትራ የጦርነት ከበሮ በመደለቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ በጦርነት ከበሮው የድምጽ ቅላጼ በመደነስ ላይ ይገኛሉ፡፡

በእርግጥ አስገዳጁ የጦርነት ማስጠንቀቂያ ሁልጊዜ ከሚጠበቁት ሲመጣ የቆየ ነው፡፡

የዩኤስ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “ጥላቻው በአስቸኳይ እንዲቆም” እና “ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሁለቱም መረጋጋትን ለማስፈን እንዲተባበሩ እና በቀጣናው ዘላቂ የሆነ ሰላም እንዲመጣ” በማለት የተለመደ የተዕማጽኖ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ባንኪሙን ኢትዮጵያ እና ኤርትራ “ከሰባት ዓመታት በፊት የድንበር ውዝግባቸውን በሰላም እንዲፈቱ የቋጨውን ሕግ በማክበር ከማንኛውም ጠብ አጫሪነትን ከሚቀሰቅሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል“ የሚል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዋና ጥያቄ ሆኖ መነሳት ያለበት ጉዳይ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለው ጦርነት ነው ወይስ ደግሞ የጦርነት ጨዋታዎች ናቸው የሚለው ነው፡፡

እኔ የማውቀው ነገር የለኝም!

ለእኔ የጦርነት ጨዋታዎችን እያካሄዱ ይመስለኛል፡፡

ሁለቱም ወገኖች በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ገደልን አቆሰልን እያሉ በመለፍለፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

ለእኔ ሁሉም ነገር አጠራጣሪ ነው፡፡

እኔ በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር ቢኖር ይህንን የሰርከስ ተውኔት ቀደም ሲል የተመለከትኩት መሆኑን ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 ዘ-ህወሀት ሲፈጽም የነበረውን የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ፣ ሙስና፣ ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀምን እና ሌሎችንም ዕኩይ ድርጊቶች መፈጸሙን በማስመልከት ለመደበቅ እና የኢትዮጵያን ህዝብ እና የዲያስፖራውን ማህበረሰብ ስሜት በማስቀየስ ላይ ዒላማ ያደረገ ባለሶስት ዙር የፖለቲካ ጦርነቶችን የፕሮፓጋንዳ ሰርከስ ተመልክቻለሁ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሁሉም ስለጦርነቱ እየተደረገ ያለው ንግግር እና የጦርነት ነጋሪት ጉሰማ ዘ-ህወሀትን ጥልቅ በሆነ መንገድ ሊያስወግድ የሚችል ድብቅ የህልውና ጦርነት ነውን?

በእኔ አስተያየት ግብታዊ በሆነ ህዝባዊ አመጽ ምክንያት ዘ-ህወሀት አእምሮው በማይቀረው ስልጣኑን እና ቁጥጥሩን የማጣት አባዜ ውስጥ ተዘፍቆ ስለሚገኝ የማስመሰያ የፍርሀት ጋጋታ ጨዋታ ነው፡፡ ሁሉም የጦርነት ዲስኩሮች በድብቅ አእምሮ ውስጥ ተሸብቦ ለሚገኘው አገዛዝ ጥልቅ ፍርሀት እና መሰረታዊ የሆነ የፖለቲካ ብስጭትን የሚገልጹ ናቸው፡፡

ፕሬዚዳንት ኬኔዲ በአንድ ወቅት እንዲህ የሚል ምልከታ አድርገው ነበር፣ “ቀደም ሲል  በቂልነት በነብር ጀርባ ላይ ሆነው መጋለብን ይፈልጉ የነበሩ ሰዎች መጨረሻቸው በነብሩ ሆድ ውስጥ ሆነው መገኘት ነው፡፡“

ወደፊት በተቆጣ እና በተራበ የነብር ሆድ ውስጥ ሆኖ የመገኘት ዕድል የዘ-ህወሀትን አመራሮች እና ደጋፊዎች ሌት ቀን እንቅልፍ ነስቶ ሁሉንም ቀናት የጦርነት ነጋሪትን በመጎሰም እንዲቆዩ አስገድዷቸዋል፡፡

ዘ-ህወሀት ስለጦርነት በጥልቅ በማሰብ ላይ ይገኛል፣ ሆኖም ግን ከኤርትራ ጋር ስለሚያካሂደው ጦርነት አይደለም፡፡

እያሳሰበው እና ሌት ቀን ረፍት ነስቶ እያሰጨነቀው ያለው ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ስለሚያደርገው ጦርነት ነው፡፡

እኔ ስለዘ-ህወሀት እውነቱን በመናገር ላይ ነው ያለሁት ምክንያቱም የዘ-ህወሀት አባላት እያንዳንዳቸው ሁልጊዜ እየተነጋገሩ ያሉበት ጉዳይ ስለሆነ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲህ ቢያድርግ ምን…? በማለት ብርክ ይዟቸዋል፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ 2016 የጦርነት ማቆሚያ ስለመሆኑ ወይም ደግሞ ቀደም ሲል ጀምሮ የሚተዋወቁት ወንድማማች ቡድኖች የህዝብን ስሜት ለማስቀየስ ሲሉ የጦርነት ጨዋታዎችን ሲያካሂዱ ለማየት ስለመቻሌ በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር የለም፡፡

በአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ላይ ያሉ ባሉ ቡድኖች መካከል ጦርነት ሊካሄድ ይችላልን? በማህጸን ውስጥ ያሉ አንድ ዓይነት መንትዮች በህይወት ለመቆየት የአንዱ መኖር ለሌላው ህልውና አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን በተመሳሳይ መልኩ ሁለቱ አሸባሪ ቡድኖች በስልጣናቸው ላይ ለመቆየት እያንዳንዳቸው እርስ በእርስ ይፈላለጋሉ፡፡ ያላንዱ ህልውና የሌላው ህልውና ሊቆይ እንደማይችል ያውቃሉና፡፡

በአሁኑ ጊዜ ጦርነት ማናቸውም ቢሆኑ የማይፈልጉት ነገር ነው፣ እናም ይህንን በሚገባ ያውቁታል፡፡

እ.ኤ.አ ጥቅምት 2015 የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ተግባራዊ እንዲሆን አጽድቋል፡፡ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ የተጣለበት ሀገር ጦርነትን አካሂዶ ስለማሸነፉ ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ነው፡፡

ጨካኝ እና አረመኔ የነበረው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔቪል ቻምበርላይን በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፣ “በጦርነት ጊዜ የትኛውም ወገን እራሱን አሸናፊ ነኝ በማለት ሊጠራ ይችላል፡፡ ማንም ቢሆን አሸናፊ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ሁለቱም ወገኖች ተሸናፊዎች ናቸው፡፡“

በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ማን ነው ተሸናፊ ሊሆን የሚችለው?

ስለጦርነት ሁለት ዝሆኖች በሚገጥሙ ጊዜ የሚጎዳው ሳሩ ነው የሚል የተለመደ አባባል አለ፡፡

በዝሆኖች መካከል በሚደረገው ጦርነት ሳሩ አሸናፊ ሆኖ ሊወጣ የማይችለው ለምንድን ነው?

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2011 እንዲህ በማለት ጽፌ ነበር፣ “ከኤርትራ ጋር ጦርነት ወይም ደግሞ ጣልቃገብነት ለማድረግ ስለመሞከሩ እና ከግብጽ ጋር የውኃ ጦርነት ስለመደረጉ ወደፊት ጊዜ የሚያሳየን ይሆናል… ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ በዚያ ዕጣ ፈንታ ላይ ማንም ቢሆን ዓይኑን ለአንድ አፍታም ቢሆን አይነቅልም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሊደረግ የሚችለው ብቸኛው የዜናዊ ጦርነት የህዝብን ስሜት የማስቀየስ ጦርነት ብቻ ነው“ ብዬ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ሚያዝ 2011 “የኤርትራ ህዝብ አምባገነኑን አገዛዝ ለማስወገድ ፈጣን መንገድ መከተል አለበት“ በማለት ዜናዊ አስፈራርቶ ነበር፡፡

ያለፉት አምስት ዓመታት እውነታ ለእራሳቸው ይናገራሉ፡፡

ምንም የማታውቅ ሞኝ ነህ ብላችሁ ጥሩኝ፡፡ ከዚህም በላይ ስለጅኦ ፖለቲካ ምንም ዓይነት ግንዛቤ የሌለኝ ትላንት እንደተወለድኩ አድርጎ መናገር ይቻላል፡፡

ምንም የማላውቅ እና ትላንት እንደተወለድኩ አድርጎ ማየቱ እውነት ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ትላንት ማታ አልተወለድኩም!

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2011 የተናገርኩትን እንደገና እ.ኤ.አ ሰኔ 2016ም እደግመዋለሁ፡፡ “የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የህዝብን ስሜት ለማስቀየስ የተደረገ የጦርነት ጨዋታ ነው፡፡”

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

ሰኔ 13 ቀን 2008 ዓ.ም

ECADFOURM

Posted by Tseday Getachew

 

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ በክብር አለመቀበራቸው በሶማሊ ክልል ከፍተኛ የስነልቦና ቀውስ እየፈጠረ ነው ተባለ

ሰኔ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በባይዶዋ፣ ሞቃዲሹና ሌሎችም የሶማሊያ ግዛቶች በአልሸባብ ተዋጊዎች የሚገደሉ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ፣ በመኪኖች እየተጫኑ በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር አካባቢ መጣላቸው በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ የስነ ልቦና ቀውስ ፈጥሯል።

የበርካታ ወታደሮች አስከሬን እንደ አልባሌ ሜዳ ላይ እየተጣለ በመሆኑ የአውሬ ራት እየሆኑ ነው የሚሉት ነዋሪዎች፣ የወዳደቀ እና በአውሬ የተበላ አስከሬን መመልከት የተመደ ነገር ሆኗል ይላሉ። ማንኛውም ሰው ቢሆን ከሞተ በሁዋላ በክብር ሊቀበር ይገባል፣ በእኛ አካባቢ የምናየው ነገር ግን እጅግ አሳዛኝ ነው የሚሉት ነዋሪዎች፣ ድርጊቱ በአካባቢው ነዋሪዎች ስነልቦና ላይ ትልቅ ተጽኖ እየፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

አንዳንድ ነዋሪዎች ችግሩ ትኩረት እንዲያገኝ በሚል የሟች ወታደሮችን ፎቶዎች በፌስ ቡክ  በመልቀቅ ላይ ናቸው።

በሌላ በኩል በደሴ ሰራዊት ለመመልመል የተደረገው ጥረት አለመሳካቱን ተከትሎ የወረዳው አመራሮች ከስልጣን እንደሚነሱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

ውትድርና ምልመላ መስፈርቱ ላይ 8ኛ ክፍል የጨረሰ የሚል መስፈረት የተቀመጠ ቢሆንም፣ የከተማዋ ፖሊሶችና ካድሬዎች ላልተማሩ ወጣቶች “ የትምህርት ማስረጃ እንሰራላችሁዋለን” በማለት እንዲመዘግቡ ለማግባባት ሲደክሙ መሰንበታቸው ታውቓል።

በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ጦርነት ከተነሳ  የኢህአዴግ መንግስት የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ሊያደርግ እንደሚችል ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ገልጸዋል።

 

ESAT

posted by Tseday Getachew

ወያኔ ከገባበት ውጥረት ለመውጣት በከፈተው ጦርነት ትኩረታችን አይቀለበስም !!!

office@ginbot7.org

ወያኔ ከገባበት ውጥረት ለመውጣት በከፈተው ጦርነት ትኩረታችን አይቀለበስም !!!

በጥጋብና እብሪት የተወጠረው የህወሃት አገዛዝ በትናንትናው ዕለት ዕሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008 በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በኩል ከኤርትራ ጋር በሚያዋስኑ የድንበር ቦታዎች ላይ ጦርነት ጀምራል፤ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም ይህን ዜና አረጋግጠው ዘግበዋል። ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ በወያኔ በኩል ስለጦርነቱ ምንም የተሰጠ መግለጫ ባይኖርም የኤርትራ መንግሥት በጾረና ግንባር በኩል ጥቃት እንደተፈጸመበት ትናንት ማምሻውን ይፋ ባደረገ መግለጫ አረጋግጦአል።

የህወሃት ዘረኝነት በፈጠረው ኢፍትሃዊነትና አፈና የተማረረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በአገዛዙ ላይ ተቃውሞውን እያጠናከረ ባለበት በዚህን ሰዓት በሙስና የተጨማለቁ የህወሃት የጦር ጀነራሎችና በሲቪል ማዕረግ አስተዳደሩን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩ ሃይሎች ለምን ይህንን ጦርነት መጫር እንደፈለጉ ግልጽ ነው። በኦሮሚያ የተነሳውን የመብት ጥያቄ ለማፈን ከ400 በላይ ሕዝብ መጨፍጨፉና በሺዎች የሚቆጠሩ እስር ቤት መታጎራቸው የህወሃትን ዕድሜ ለማራዘም እንደ አንድ መሣሪያ ሆኖ ላለፉት 25 አመታት ሲያገለግል በኖረው ኦህዲድ ውስጥ እንኳን ከከፍተኛ አመራር እስከ ተራ ካድሬ ያሉትን አስኮርፎአል። የወልቃይት ህዝብ ያነሳው የማንነት ጥያቄ ሌላኛው የህወሃት አጋር በሆነው ብአዴን ውስጥ የማያባራ ክፍፍል ፈጥሮአል። የነጻነት ታጋዮች በቅርቡ አርባምንጭ ከተማ አቅራቢያ የፈጸሙት የጀግንነት ገድል የደቡብ ኢትዮጵያን ሕዝብ የሚያንቃቃና ለትግል የሚያነሳሳ አርአያነት እንደፈጠረ የህወሃት አገዛዝ ተረድቶአል። በቤኔሻንጉል፣ በጋምቤላ ፣ በአፋርና በሱማሌ ከመሬት ንጥቂያ ጋር በተያያዘ ወንጀል ህወሃት ከህዝቡ ጋር አይጥና ድመት ድብብቆሽ ውስጥ ከገባ አመታትን አስቆጥሮአል። በአዲስ አበባና ሌሎች ትላልቅ ከተሞች ቀድሞውኑም የድጋፍ መሠረት እንደሌለው ማወቁ ብቻ ሳይሆን ይኩራራበት የነበረው የትግራይ ምሽግነትም ከእጁ ሙሉ በሙሉ እያፈተለከ መምጣቱን ተገንዝቧል። በዚህም ምክንያት ፊቱን ወደሰሜን በማዞር የሕዝቡን ትኩረት አስታለሁ ብሎ ወያኔ አምኖአል። አባይ ጸሃይዬና ሳሞራ ዩኑስ መቀሌ ላይ በቅርቡ ባደረጉት የህወሃት ስብሰባ ላይ “ህወሃት ከሌለ የትግራይ ህዝብ አይኖርም ፤ ኢህአደግ ከሌለ ኢትዮጵያ አትኖርም” ማለታቸው ኤርትራን በመውረር በተለይም የትግራይን ህዝብ ድጋፍ መልሶ ያስገኛል የሚል እምነት በአገዛዙ መሪዎች ውስጥ መፈጠሩን ያመለክታል።

ሌላው ህወሃትን ወደ ጦር አጫሪነት እየነዳው ያለው እብደት መለስ ዜናዊ ከሞተ ወዲህ ድርጅቱ ውስጥ የነገሰው የእርስ በርስ የሥልጣን ሹኩቻ የፈጠረው ውጥረት እንደሆነ መገመት አያዳግትም። አንዱን ውጥረት ለማርገብ ሌላ የውጥረት ግንባር በመክፈት ለሚታወቀው ህወሃት ይህ የተለመደ ስትራቴጂ ነው።

አርበኞች ግንቦት7 ህወሃት የኢትዮጵያን ሕዝብ ትኩረት ለመቀየር የሚያደርገው ማንኛውም አይነት ጥረት እንዳይሳካለትና የጀመረው ይህ የትኩረት ማስቀየሻ ስትራቴጂ የህወሃትን ውድቀት አፍጣኝ እንዲሆኑ ለማድረግ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። ካሁን ቀደም ለአገራችን ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም የሚሰጠው ፋይዳ ሳይመከርበትና ሕዝባዊ ስምምነት ሳይኖር ከአሥራ አንድ አመት በፊት ሱማሌ ውስጥ ዘፍ ተብሎ የተገባበት ጦርነት በየቀኑ የስንት ወንድሞቻችንን ህይወት እየቀጠፈ እንደሆነ እያየነው ነው። ቁጥራቸው ከ60 በላይ የሆኑ ወገኖቻችን ሰሞኑ በሽብርተኛው አልሸባብ ሲጨፈጨፉ የወያኔ መሪዎች አንዲትም ወፍ የሞተቺባቸው ያህል እንኳ አልተሰማቸውም ። ይህንን ሁሉም ያገራችን ህዝብ ያውቃል። እስከዛሬ በሰላም አስከባሪነት ስም ወደ ሰው አገር እየተላኩ ደመ ከልብ እየሆኑ ያሉ ወገኖቻችን ህይወት እያንገበገበን ባለበት በዚህን ሰዓት ለወያኔ የሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ እንደ አገር የምንዋጋው ሌላ ጦርነት እንደሌለ ሊታወቅ ይገባል። በ1998ቱ የባድሜ ጦርነት ወቅት ህዝባችን የከፈለው ዋጋና ከባድሜ ጦርነት መልስ ጉልበቱን አጠናክሮ ለመውጣት ዕድል ያገኘው የህወሃት በህዝባችንና በአገራችን ላይ እስከዛሬ እየፈጸመው ያለው አፈናና ጭፍጨፋ ተረስቶ ሌላ ዕድል ለመስጠት ዳግም መሳሪያ የምንሆንበት ምክንያት የለም ።

አርበኞች ግንቦት 7 ከአሁን ቦኋላ ወያኔ የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘምና የተዘፈቀበትን የሃብት ዘረፋ አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያደርገውን የሞት ሽረት ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ በምንም አይነት ሁኔታ ማስተናገድ የለበትም ብሎ ያምናል። በዚህም ምክንያት በመላው አገራችን የተጀመረው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ለፍትህ ለእኩልነትና ለነጻነት የሚደረገው ትግል ከግቡ እንዲደርስ የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ ትግሉን ለማጠናከር እንዲረባረብ አርበኞች ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያቀርባል ። በመካሄድ ላይ ያለውን የነጻነት ትግል አቅጣጫ ለማስለወጥ ወያኔ የሚያደርገውን የጦርነት እንቅስቃሴ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የነጻነት ቀናችንን እንድናፋጥን ሁላችንም እንነሳ ።

አርበኞች ግንቦት 7 ወያኔ በሰሜን በኩል የጀመረውን ትንኮሳ እየተከታተለ ለህዝባችን ወቅታዊ መረጃ ይሰጣል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

አርበኞች ግንቦት 7

posted by Tseday Getachew

በሊቦከምከም ወረዳ አንድ ታጣቂ 6 ፖሊሶችን ገደለ

ሰኔ (አሥራ  ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሊቦ ከምከም ወረዳ በደንጎሎ ቀበሌ አቶ አረጋ የተባለ ግለሰብ፣ እጁን ለመያዝ የሄዱትን 6 የፖሊስ አባላትን ገድሎ አንድ ስናይፐት ጠመንጃ መማረኩን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።

የፖሊስ አባላት በደረሳቸው መረጃ መሰረት እጁን ለመያዝ ሲንቀሳቀሱ፣ ታጣቂውም አስቀድሞ በደረሰው መረጃ መሰረት ራሱን አዘጋጅቶ በመጠበቅ በፖሊሶች ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል። አቶ አረጋ ጥቃቱን ካደረሰ በሁዋላ ለተወሰኑ ሰአታት ሌሎች ሃይሎች ይመጣሉ ብሎ ሲጠባበቅ መቆየቱንና በመጨረሻም ከአካባቢው መሰወሩን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

መንግስት አቶ አረጋን ለመያዝ ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ ቢቆይም፣ የአካባቢው ህዝብ አቶ አረጋን አሳልፎ ለመስጠት ባለመፈለጉ ከፍተኛ ችግር ሲደርስበት ቆይቷል። ምንም እንኳ ግለሰቡ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ጥቃቶችን ሲፈጽም መቆየቱ ቢታወቅም፣ በታጠቁ ፖሊሶች ላይ በዚህ መጠን ጉዳት ሲያደርስ ይህ የመጀመሪያው ነው።

ከአቶ አረጋ ጋር ሌሎች ሃይሎች መኖራቸው ወይም የሚደግፋቸው ሌላ ሃይል ይኑር አይኑር የታወቀ ነገር የለም። በጉዳዩ ዘሪያ የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም

sourecs esat

poated by Tseday Getachew

Egypt asks Israel to help solve Ethiopia’s Renaissance Dam crisis

Egyptian President Abdel Fattah al-Sisi is reported to have asked the Israeli Prime Minister Benjamin Netanyahu to intervene and help solve his country’s dispute with Ethiopia over the Renaissance Dam crisis.

The Al-Araby Al-Jadeed newspaper reported Arab diplomatic sources as saying on Monday: “Sisi has recently asked Netanyahu to help Egypt resolve its dispute with Ethiopia over the Renaissance Dam, due to Ethiopia’s intransigence and refusal to respond to the Egyptian calls to coordinate efforts during the construction and storage stages.”

The sources added that al-Sisi’s move came after Ethiopia rejected all pressures exerted by Arab parties, including Saudi Arabia and the UAE, because Addis Ababa believes “the national project will help lift its deteriorating economy”.

The sources said that Egypt has finally resorted to asking Israel for assistance, a strategic ally of Ethiopia and a number of Nile Basin countries.

Speaking to the newspaper, an Egyptian diplomat warned against al-Sisi’s move, saying it could lead to the transfer of the Nile water to Israel, explaining that current and former Israeli leaders have been calling for this since the signing of the Camp David agreement.

Addis Ababa and Tel Aviv enjoy close ties on the economic side, with Israel having provided a range of grants to Ethiopia over the past years.

sources ethiomedia.com

posted by Tseday Getachew


 


 

ሰበር ዜና… እስከ አፍናጫቸዉ የታጠቁ ከ20 እስከ 25 ሺ የሚጠጉ የአርበኞች ግንቦት7 እና የትህዴን ወታደሮች በጾረና ግንባር ነበሩ

በልኡል አለም

በህወሃት አመራር እና በሰሜኑ እዝ ዉስጥ በሚገኙ የወታደራዊ ደህንነት መረጃ ክንፎች በተለይም ወታደራዊ እግረኛ ቃኘዉ መረጃ፣ የቴሌስኮፕ ምልከታ ቃኘዉ መረጃ፣ የሬዲዮ ጠለፋ አገልግሎት መረጃ፣ የሳተላይት ቅኝት መረጃ፣ የአስተኳሽ አስተላለፍ መረጃ፣ የመግቢያና መዉጫ ኮድ ሚስጥር አሳላፊ አመራር መረጃ ምድቦች ባጠቃላይ ወደ ግምገማ እንዲገቡ ከመከላከያ ሚኒስቴር ቀጥታ ትእዛዝ ቢተላለፍም የወታደራዊ ደህንነቱ አጣብቂኝ ዉስጥ መግባቱን ታማኝ ምንጮች ጠቅሰዋል።Patriotic Ginbot7 attacked TPLF troops

ዋናዉ ምክንያት የተባለለት ጉዳይ በሰሞኑ የወያኔ መንግስት በኤርትራ ላይ የከፈተዉ ጦርነት ሲሆን መከላከያ ሚኒስቴሩ በጾረና ግንባር ኳ አቲት (Qua’ atit) ወይም አዲ ቀይህ (Adi keyh) አካባቢ ከ20 እስከ 25 ሺ የሚጠጉ የአርበኞች ግንቦት 7 እና የትህዴን ሰራዊት ሰፍሯል የሚል መረጃ ከወታደራዊ ደህነት ክፍሉ ማለትም ባጠቃላይ ከላይ ከተዘረዘሩት ምድቦች በመረጋገጡ መሆኑን ገልጾ ይህን እስከ አፍናጫዉ ድረስ የታጠቀን የአርበኞች ግንቦት 7 እና የትህዴንን ሰራዊት ለማጥቃት ከመከላከያ ሚኒስቴሩ በቀጥታ መመሪያ ወጥቷል፣ መመሪያዉን ተንተርሶ የትግራዩ ነጻ አዉጭ ቡድን መከላከያ አባላትን ለጦርነት ከመሰማራቱ ቀድሞ መረጃዎቹ ባጠቃላይ በኤርትራ ወታደራዊ ደህነቶች እጅ በመዉደቃቸዉ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ያልተገመተና ከፍተኛ አደጋ እንዲገጥመዉ ሆኗል።

በዚህ ምክንያት የወታደራዊ ደህንነቱ ከላይ የተዘረዘሩትን የመረጃ ምድብ ክንፎች ለግምገማ እንዲጠራ የተጠየቀ ሲሆን የሰሜኑ እዝ ደህንነት በበኩሉ የምድብ መረጃዎቹን በግሉ እንደሚገመግም እና ጠቅላይ ሪፖርትም እንደሚልክ አሳስቧል።

የዉስጥ አርበኞችን ተገን ያደረገ ምንጫችን እንደሚገልጸዉ የመረጃ ክፍሉ ምድብ አባላቶች የግምገማ ትእዛዙን በመቃወም የተወሰኑት መሰወራቸዉን አረጋግጧል።

(ወያኔ ማለት… ድመት በመስታወት እራሷን ስታይ ማለት ነዉ)

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

ecdaf

posted by Tseday Getachew

ሰበር ዜና… በደቡብ አፍሪካ በወያኔ ኢንባሲ አቀናባሪነት የተጠራዉ የኤርትራ መንግስት የመቃወም ሴራ ከሸፈ!

ልኡል አለም

የትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን በደቡብ አፍሪካ ለሚኖሩ ከወያኔ መንግስት ጋር በመተባበር የኤርትራንና የኢትዮጵያን ህዝብ በመሰለል እና በተለያየ ጥቅማ ጥቅም ለሚተዳደሩ ጥቂቶች ያመቻቸውና በዛሬዉ እለት ፕሪቶሪያ ከተማ ላይ የተባበሩት መንግስታት ቢሮ አካባቢ ሊደረግ የነበረዉ ተቃዉሞ ከሽፏል።

ወያኔ ይህንን ተቃዉሞ ሰልፍ ለማመቻት 70 ሺ ራንድ ወጪ ያደረገ ከመሆኑም ባሻገር የትራንስፖርትና የምግብ እንዲሁም የመጠጥ ወጪዎችን መድቦ ፈሰስ ያደረገ ከመሆኑ በተጨማሪ ከስብሰባዉ በሗላ በኢትዮጵያ ዉስጥ ልዩ የእራት ግብዛ ተቃዉሞዉ ላይ ለተሳተፉ ትዉልደ ኤርትራዊያንን በተለይም ንብረታቸዉ የተመለሰላቸዉ የሚባሉትን በጥቅምና በተስፋ ማነቆ የታሰሩ ግለሰቦችን ባጠቃላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አድርጎ ነበር።

ይህንን የተቃዉሞ ስብሰባ በማቀናጀቱ በኩል በደቡብ አፍሪካ ዉስጥ ነዋሪ ከሆኑ የወያኔ ጥቅም ተጋሪዎች መካከል ተስፉ ምስግና በቀለ ወይም አንክል የተባለ ትዉልደ ኤርትራዊ ከወያኔ ወንበዴዎች ጋር በጋር የባልትና ንግድ የሚሰራና በሐዋላ የገንዘብ ዝዉዉር የሚተዳደር ግለሰብ እና አማኑኤል ወልዱ የተባለ በትዉልድ ኤርትራዊ የሆነ ከወያኔ ኢንባሲ በስለላ ጉዳዮ በመተሳሰሩ ምክንያት በወር 10.000 ራንድ የሚከፈለዉና በዚሁ እኩይ ተግባር የሚተዳደር የህዝብ ጠላት ነዉ።

በመሆኑም የደቡብ አፍሪካ ሜትሮ ፖሊስ አገልግሎት ( Department Of Metro Police ) ህወሃታዊ ትዉልደ ኤርትራዊያን ዛሬ ዛሬ 06/23/2016 ሰልፍ እንዲወጡ ፈቅዶ የነበረ ሲሆን በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ይህንን የሰላማዊ ሰልፍ ያዘጋጀዉ የኢትዮጵያ ኢንባሲ መሆኑን ለሚመለከተዉ አካል በማሳወቅና በአሁን ወቅት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ ላይ በተቀሰቀሰዉ የህዝብ አመጽ ምክንያት ሰልፉ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳይሄድ በሚል ሁኔታ ለደቡብ አፍሪካ ሜትሮ ፖሊስ ዲፓርትመንት ማስጠንቀቂያ በመስጠታቸዉ ሰልፉ ተሰርዟል።

የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ አስከፊ ሁኔታ ላይ በሚገኝበትና መሪዎቻችን አለምን በልመና ባስጨነቁበት በዚህ ወቅት ላይ ህወሃት ኤርትራዊያን በመንግስታቸዉ ላይ እንዲያምጹ ከፍተኛ ወጪ በማዉጣት የህዝባችንና የሐገራችንን ሐብታና ንብረት ማባከኑን ተያይዞታል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

ECDAF

ማስተር ፕላኑ ይቁም ከተባለ፤ የታሰሩት ይፈቱ፣ገዳዮችም ለፍርድ ይቅረቡ!

 

በይድነቃቸው ከበደ
ምንጭ- ‎በኢትዮ ምኅዳር‬ ጋዜጣ

“….የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ንጹሃና ዜጎች በመንግሥት ታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን አስመልክቶ፣ መጽናናትን ለቤተሰቦቻቸው ከመመኘት ባለፈ ምንም አይነት ውሳኔ አለማሳለፉ ፣በእርግጥም ውሳኔው የኦህዴድ እንዳልነበረ የሚያሳብቅ ነው፡፡”

“የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን” የሚል ስያሜ የተሰጠው መንግሥታዊ ውንብድና ፣በአገራችን አለመረጋጋትን ፈጥሯል፤መተኪያ የሌለው የሰው ልጅ ሕይወት እንዲጠፋ፣ የንብረት ውድመትና ኪሳራ እንዲደርስ ምክንያት ሆኗል፡፡ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ማስተር ፕላኑን እንዲቆም እና ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ያላትን ጥቅሞች ተግባራዊ ለማድረግ ወስኛለው ማለቱ እየተሰማ ነው፡፡Yidnekachew Kebede of the Blue Party

የሕዝብ ጥቅም እና ፍላጎትን ያልጠበቀ ውሳኔ ማሳለፍ ከአንባገነን መንግሥት ሁሌም የሚጠበቅ ድርጊት ነው፡፡የፌደራል መንግሥትም ሆነ የኦሮሚያ ክልል አስተዳዳር “የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን”ን አስመልክቶ፤ የጉዳዮ ቀጥተኛ ባለቤት የሆነው የአካባቢ አርሶ አደሮች፣ የክልሉ ነዋሪዎችና የሚመለከታቸው ሁሉ በጋር በግልፅ ድርጊቱን ሲቃወሙ ነበር፡፡

ለሕዝብ አቤቱታና ተቋውሞ፣ ተገቢውን ክብርና ምላሽ የማይሰጠው የህውሓት/የኢህአዴግ አንባገነን መንግሥት፣ ይህ ነገር ለእኛ አይጠቅምም ያሉ፣ቅሬታቸውን በሠላማዊ መንግድ የገለጹ ፣በታጣቂ አይሎች በአደባባይ እንዲገደሉ ተደርጓል፣የአካል ጉዳትም የደረሰባቸው አሉ፣በመንግሥት የማሰቃያ እስር ቤቶች እየተሰቃዩ የሚገኙ ሰላማዊ ዜጎች እና የፖለቲካ አመራሮች እንዲሁም አባላት ይገኛሉ፡፡

ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ፣በህውሓት የሞግዚት አስተዳደር የሚመራው ፣የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ እንደ-ቀልድ ማስተር ፕላኑ ይቁም ማላቱ ፣ከውሳኔው ጆርባ ያለው ፓለቲካዊ አንድምታ ብዙ ርቀት ሄዶ ምርምርን የሚጠይቅ አይደለም፡፡የአፍንጫ ሥር ፖለቲካ ቁማር ነው ! ኦህዴድ ቀድሞ ነገር “የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን”ን አስመልክቶ የእቅዱ ባለቤት አልነበረም ፣ልሁንም ቢል የማይቻለው ነገር ነው፡፡ለዚህ እንደ-ማሳያ ብዙ ነገሮችን ማንሳት የሚቻል ቢሆንም ፣ከማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ፣ለሁለት ዓመት ያኸል ሕዝብ በይፋ ማስተር ፕላኑን ሲቃወም ነበር፤ኦህዴድ በሕዝብ የሚመራ ከሕዝብ የተመረጠ፣በራሱ ድርጅታዊ አቋም የሚጸና ቢሆን ኖሮ፣አሁን ላይ ሳይሆን ከሁለት ዓመት በፊት፣ የመሬት ወረራና ንጥቂያ በቆመ ነበር፡፡ግን አልሆነም፣መሆን ስለማይቻል!

በኢህአዴግ ውስጥ ያለው የሥልጣን ተዋረድ እንዲሁም የኃይል አሰላለፍ፣ በቁጠር ብዛት እንጂ በውሳኔ ሰጪነት ቦታ የማይኖራቸው እህት ድርጅቶች ፣ሁሌም ቢሆን ከሚወክሉት ሕዝብና አካባቢ ይልቅ፣ለበላይ ተጠሪያቸው ለህውሓት ማገልገል እና ታማኝ መሆን መገለጫ ባህሪያቸው ነው፡፡የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በተመለከተ የቀረበውን መሪ እቅድ በዋነኝነት ይደግፉ የነበሩት እንዲሁም ለተግባራዊነቱ ዘብ የቆሙት፣አቶ ሙክታር ከድርና አስቴር ማሞ በግንባር ቀደመ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

እነዚህ ሁለት የኦህዴድ ባለስልጣናት በመከተል ቁጥራቸው የበዛ የኦዴድ ካድሬዎች ፣ የወከላቸውን የኦሮም ሕዝብ ከማገልገል ይልቅ ፣የግል ጥቅማቸውን በማሰብ ለአሳድሪያቸው ገብረዋል፣አሁንም እየገበሩ ይገኛሉ!ጫና የበዛበት ፣የአስተዳደር በደል መሸከም ያቃተው የኦሮሞ ሕዝብ ፣ዓይን ባወጣ መልኩ ከቦታው በሃይል እንዲፈናቀል መደረጉን አምርሮ በመቃወሙ፣ይህም ተቃውሞ ዓይነቱና መጠኑ እየበዛ መምጣቱን ተከትሎ ፣ለአገዛዙ ሥርዓት አስጊ መሆኑን የተረዳው የህውሓት/ኢህአዴግ ገዢ መንግሥት “የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን”ን እቅድ እንዲቆም ወስኗአል፡፡

እቅዱ እንዲቆም መወሰንና እቅዱን መሠረዝ፣ የየራሳቸው ትርጉም እና እሱን ተከትሎ የሚመጣ ፖለቲካዊ መዘዙ ብዙ ነው፡፡የታሰበው የማስተር ፕላን እቅድ እንዲቆም መደረጉ ሳይሆን፣ መሠረዝ ወይም ማስቀረት ብቻ ነው፣ ለኦሮሞ ሕዝብ ለጥያቄው ትክክለኛ ምላሽ የሚያስገኝለት!!! ይህን በቅጡ ያልተረዱ ወይም ለመረዳት ያልፈለጉ የኦህዴድ ባለሥልጣናት “ሾላ በድፍኑ” አይነት ውሳኔ እንዲያሳልፉ በተሰጣቸው ትዝዛዝ መሠረት ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡

የተወሰነ ውሳኔ እንደሚያመለክተው “የውዝግቡ መንስኤ ሆኖ የቆየው የአዲስ አበባና በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ሙሉ በሙሉ እንዲቆም” በማለት ወስኗል፡፡ውሳኔው የመሬት ነጠቃና ወረራ ላወገዙ፣ተቃውማቸውን በአደባባይ ለገለጹ ኢትዮጵያዊን ሁሉ ትልቅ ድል ነው፡፡ ትንንሽ ድሎችን በመሰብሰብ ለተሻለ ደል መብቃት በእርግጥም ተጨማሪ ሥራ ይጠይቃል፡፡ነገር ግን የኢህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ንጹህና ዜጎች በመንግሥት ታጣቂ ሐይሎች መገደላቸውን አስመልክቶ፣ መጽናናትን ለቤተሰቦቻቸው ከመመኘት ባለፈ ምንም አይነት ውሳኔ አለማሳለፉ ፣በእርግጥም ውሳኔው የኦህዴድ እንዳልነበረ የሚያሳብቅ ነው፡፡

“በየትኛውም የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ሕዝብ የልማትና የግልፅነት ጥያቄዎችን ማቅረቡ ድርጅቱ ከሌሎች ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር በመሆን እየገነበ የሚገኘው ስርዓት ውጤት በመሆኑ በአድናቆት እንደሚመለከተውና ከፍተኛ ክብር እንዳለው” የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ ውስጥ ተካቶ ይገኛል ፡፡በሕዝብ ላይ ከዚህ በላይ መቀለድ ምን አለ ?! እነሱ እንደሚሉት ሕዝብ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄውን በማቅረቡ እና በመቃወሙ ብቻ ሕይወቱን እንዲያጣ ተደርጓል፡፡ኦህዴድ እወክለዋለው የሚለው ሕዝብ በጠራራ ፀሐይ ሙሉ ትጥቅ በታጠቁ ወታደሮች ሲገደል፣ይህን ድርጊት የፈጸሙ ግዳጁን እንደጣለ ጀግና በአደባባይ ሲዘባበቱ፤የሟች እና የገደይ ድርጊት ኦህዴድ “…..ከሌሎች ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር በመሆን እየገነበ የሚገኘው ስርዓት ውጤት በመሆኑ በአድናቆት እንደሚመለከተውና ከፍተኛ ክብር እንዳለው” ብቻ አይቶ ማለፉ፣ ድርጅቱ እውነትም የሕዝብ ውክልና አለው ወይ ብሎ የሚያስጠይቅ ነው፡፡
የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን በመቃወማቸው ብቻ፣የተገደሉ ዜጎቻችችን ደም ደመከልብ ሆኖ መቅረት የለበትም! የመግደል ትእዛዝ የሰጡ ፣ግድያውንም የፈጸሙ እና ያስተባበሩ ፣በእውነተኛ ፍርድ ቀርበው መዳኘት አለባቸው፡፡ይህ ሲሆን ብቻ ነው የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ የሚያገኘው፡፡ከዚህ ባነሰ “ሕይወታቸውን ላጡ እናዝናልን” ማለት ብቻ በቂ አይደለም፣ንጹሃንን የገደሉ እና ያስገደሉ ለፍርድ ይቅረቡ !!!

ይህም ብቻ አይደለም፣አሁን ላይ የፌደራል መንግሥትም እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል አስተዳዳር የሚመራው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ ስሕተት መሆኑ አውቆ ይቁም ስላለው ማስተር ፕላን ፤አስቀድመው ማስተረት ፕላኑን እንደማይጠቅም የተረዱ፣ መረዳታቸውንም በአደባባይ በመግለፃቸው ብቻ፣በተለያየ የአገዛዙ ሥርዓት የማሰቃያ እስር ቤቶች የሚገኙ፤ የኦሮሞ ተወላጆች፣ የፓለቲካ መሪዎችና አባላቶች እንዲሁም ማንኛውም ዜጋ ፣ከማጎሪያ እስር ቤት ሊፈቱ ይገባል፡፡እናም ማስተር ፕላኑ ይቁም ከተባለ፤ የታሰሩት ይፈቱ፣ ገዳዮችም ለፍርድ ይቅረቡ

ecadaf

posted by tseday getachew

በትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን ጸብ አጫሪነት የተቆሰቆሰዉ ጦርነት ከፈተኛ ዝግጅት እየተደረገበት ይገኛል!

በልኡል አለም

በኢትዮጵያ ወታደራዊ ደህንነት በኩል በከፍተኛ ሚስጥር እንዲያዝ በታቀደ ሁኔታ በሰሜኑ እዝ ዉስጥ ከተጠቃለሉት ክ/ጦሮች በተጨማሪ ከማእከላዊ እዝ ወታደሮችና ሜካናይዝድ ብረት ለበስ ሰራዊቶች እየተደራጁ ይገኛሉ።will not escalate clash with Eritrea

በጎንደር በኩል በተለየ ሁኔታ ከሁመራ እስከ ኡማህ ጅር እንዲሁም በሰሜን 14.718326 አየር ካርታ ዳር ዳሩን በምያዝ ከአፋር ዞን 1 እስከ አፋር ዞን 2 ብሎም እስከ አድዋ ከድዋ እስከ አዲ አቡን ድረስ ሰራዊት ለማሰማራት ታቅዶ የሐይል እጥረት መከሰቱን መከላከያ ምንጮች ጠቁመዋል።

በኤርትራ በኩል ከፍተኝ ጥበቃ እየተደረገ በመሆኑ ምክንያት እንዲሁም ኤርትራ ባደረገችዉ መልሶ ጥቃት ምክንያት ከፍተኛ አደጋ የደረሰበት የወያኔ ሰራዊት እንከን የገጠመው ከመሆኑ በተጨማሪ የሰራዊት ክዳት ከፍተኛ ችግር ማድረሱም ተረጋግጧል!

በሰሞን በተቀሰቀሰዉ ጦርነት ብቻ ከ140 በላይ ወታደሮች ከሰሜኑ እዝ በመኮብለል የተሰወሩ ሲሆን አንድ በጄኔራልነት ማእረግ ላይ የሚገኝ አመራር ብዛት ያላቸዉ ወታደሮችን ይዞ ወደ ኤርትራ ገብቷል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

ECADF

Posted by tseday getachew

ወያኔ፤ አንድም በብልሀት – አንድም በጉልበት (ይገረም አለሙ)

ይገረም አለሙ
ወያኔዎች ለትግል በርሀ ገባን የሚሉበት ግዜ የንጉሡ ሥርዓ ፈርሶ ኢትዮጵያ ወዴት አንደምትሄድ አይደለም የት ላይ እንደቆመች እንካን ብቅጡ ያልየበት ወቅት ስለነበር ለብሶት ዳርጎ ወደ ጫካ የሚያስኬድ ቀርቶ ከተማ ተቀምጦ ለማኩረፍ የሚያበቃ በደል ነበር ለማለት አይቻልም፡፡ ስለሆነም ወያኔዎች በዛን ወቅት ለትግል የተነሱት የአጼ ዮሐንስን ቤተ መንግሥት ይዘው የትግራይን መንግሥት የመመስረት ህልማቸውን ለማሳካት መንግሥት አልባው ወቅት ምቹ ሆኖ ስለታያቸው ነበር፡፡ ቢዘገይም ካሰቡት በላይ ተሳክቶላቸዋል፡፡
ወያኔዎች ሀ ብለው ትግል ሲጀምሩ በሰነድ ያሰፈሩት ዓላማቸውም ሆነ ፤አመሰረራታቸውን፣ እድገትና ሂደታቸውን በቅርብ የሚያውቁ ሰዎች የሚሰጡት ምስክርነት ከሁሉም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያን በጥቅል እየገዙ ነጻ አውጪ የሚለውን ስማቸውን መለወጥ አለመቻላቸውና ተግባራቸው ሁሉ ጫካ የገቡበትን ዓላማም ሆነ የረዥም ግዜ ዘላቂ ግባቸውን ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ፡፡
ንጉሳዊው ሥርዓት ፈርሶ የመጪው ምንነትና እንዴትነት ባልለየበት ሰዐት አጋጣማዊ በአጭር ግዜ ዓላማችንን ለማሳካት ያስችለናል በማለት ከከተማ ተጠራርተው በረሀ ቢወርዱም የአጭር ግዜ ዓላማቸውን ለማሳካትም ሆነ ወደ ረዥሙ ግዜ ግባቸው የሚያደርሳቸውን መንገድ ለማመቻት በጥልቀት አስበውና አቅደው የተነሱ ለመሆናቸው በብልሀትም በጉልበትም የፈጸሙዋቸው ተግባሮችና አሁንም ቀሪ ዓላማቸውን ለማሳካት እየሄዱበት ያለው መንገድ ይመሰክራል፡፡ሀያ አራት አመት አናሳዎቹ ብዙኃኑን ረግጠው እየገዙ ለመዝለቅ መቻላቸውም በራሱ ከመነሻው በጠንካራ መሰረት ላይ መቆማቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
ምንም እሰጥ አገባ የማያስከትለውና እነርሱም ሊክዱት የማይችሉት አነሳሳቸው ለትግራይ መንግስትነት ነበር፡፡ ነገር ግን አጋጣሚው ለኢትዮጵያ መንግሥትነት አበቃቸው፡፡ እነርሱ ግን መነሻ ዓላማቸውም ሆነ መድረሻ ግባቸው ይህ አይደለምና ሀያ አራት አመት በሥልጣን ላይ ሆነውም የኢትዮጵያ መንግሥት ለመሆን አልቻሉም፡፡ የኢትዮጵያን መንግስትነት በመያዛቸው ምክንያት የዘገየው ግን ሊተውት ያልቻሉትና መቼ ተግባራዊ እንደሚሆን እነርሱም ርግጠኛ ያልሆኑበትን ዓላማቸውን ማመቻቸቱን ግን አንድም ቀን ችላ ብለውት አያውቁም፡፡
ያ የደደቢት ጽንስ ዓላማቸው በአስተማማኝ ተግባራዊ እንዲሆን ሁለት አበይት ነገሮችን ይፈልጋል፡፡ አንድ ለሚመሰረተው የትግራይ መንግሥት ዘላቂነትና መረጋጋት ኢትዮጵያዊነት የሚባለው የእንድነት አስተሳሰብ መጥፋትና ኢትዮጵያ የተዳከመችና የተበታተነች ሀገር መሆን፡፡ ሁለት አዲሲቱ ሀገር በሁለንተናዊ መልኳ ራሱን እንድትችል የቆዳ ስፋቷን ማስፋት፤ መሰረተ ልማቷን ማስፋፋት የህዝቡን ስነ ልቦና መለወጥ፡፡ ወያኔዎች ይህንን በብልሀትም ሆነ በጉልበት ተግባራዊ ማድረግ የጀመሩት ትግሉን ሀ ብለው ሲጀምሩ ነው፡፡
ገና ትግላቸው ሳይጠነክርና አቅማቸው ሳይደረጅ ሀገራዊ ዓላማና አደረጃጀት የነበራቸውን ድርጅቶች ዒላማ ማድረጋቸው በኢትዮጵያዊነት ላይ ላላቸው አመለካከት አንዱና ዋናው ማሳያ ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞ በቀላሉ በኢህአፓና ኢዲዩ ላይ የፈጸሙትን ማስታወስ ይበቃል፡፡ ከዛም ከኢህአፓ በወጡ እንበለው በከዱ ወይንም ለወያኔ እጅ በሰጡ ሰዎች የተመሰረተውና የኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ይባል የነበረውን ፓርቲ ዓላማና ስም አስለውጠው ብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እንዲባል ሲያደርጉት ሀገራዊ አሰተሳሰብ ፈጽሞ አንዲጠፋ ታጥቀው የሚሰሩ ለመሆናቸው በቂ ማረጋገጫ ነበር፡፡ ልብ ያለው ብዙም አልነበረም እንጂ፡፡
ብሄር ብሄረሰቦች በአለፉት ሥርዓታት የተነፈጉትን የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ለማጎናጸፍ በሚል ልብ አማላይ ስብከት በየደረሱበት ምርኮኛውንም ወዶ ገቡንም እየሰበሰቡ አባልም አጋርም ያሉዋቸውን የጎሳ ድርጅቶች በመመስረት ለዓላማቸው ስኬት አንቅፋት ይሆናል ያሉትን ኢትዮጵያዊ አመለካከት የሚያጠፉበትን መንገድ ሲያመቻቹ ዓላማቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁና የመሪዎቹን እኩይ ተግባር የተረዱ ሰዎች ሊከተል የሚችለውን ጥፋት ለማመላከት ቢሞክሩም ብዙም ከቁብ የቆጠራቸው አልነበረም፡፡
ይልቁንም በየጎሳችሁ ተደራጁና የሽግግር መንግሥቱ አካል ሁኑ የሚለውን ጥሪ ተቀብለው አያሌ ኢትዮጵያውያን በአጭር ግዜ በርካታ የብሔር ብሄረሰብ /የጎሳ ድርጅቶች በመመስረት እያወቁም ይሁን ሳያውቁ የወያኔዎቹን መንገድ አመቻቹላቸው፡፡ (በደቡብ ብቻ በአንድ ግዜ ከ15 በላይ ድርጅቶች መፈጠራቸውን እናስታውሳለን፡፡) አስገራሚ የነበረው ነገር በብሄራዊ ስሜት አቀንቃኝነት በሀገራዊ መፈክር አንጋቢነት ከዛም በላይ በአለም አቀፋዊ አጀንዳ አራማጅነት ይታወቁ የነበሩ ትላልቅ የተባሉ ሰዎች ሳይቀሩ የጎሳ ድርጅት መስርተው የሽግግሩ ፓርላማ ውስጥ ለመታየት መብቃታቸው ነበር፡፡
ይህ የኢትዮጵያዊነትን ብሎኮ እየገፈፉ የየጎሳውን ነጠላ እያለበሱ የማስጨፈር መላው በብዙ መልኩ የሰመረለት ወያኔ የሚዘፍኑትን ዘፈን ግጥምና ዜማ ሳይቀር እየሰጠ ሁሉንም በተናጠል ማዘፈን ቻለ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ያለፈ ታሪክ እየመዘዘ ለእያንዳንዱ የቤት ስራ በመስጠት የኢትዮጵያ ልጆች ርስ በርስ አንዲወጋገዙና ሆድና ጀርባ እንዲሆኑ ለማድረግ ቻለ፡፡
ወያኔዎች ይህን በማድረግ ፖለቲካዊ ዓላማቸውን ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ መሰረታቸውን ለማጠናከር ያስቻላቸውን ኢኮኖሚያዊ እቅዳቸውንም አሳክተዋል፡፡ በድርጅት ከህውኃት በክልል ከትግራይ በስተቀር ሌሎቹ በተሰጣቸው አጀንዳ ተጠምደው በጎሳ ፖለቲካ ሰክረው እንወክለዋለን የሚሉትን አካባቢ እንኳን በንቃት ማየት ባለመቻላቸው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የነበሩና የወያኔን ቀልብ ያማለሉ ንብረቶች ያለምንም ተቃውሞና ሀይ ባይ የተቻለው በቀን በጠራራ ጸሀይ ሌላው በለሊት መብራት እያጠፋ ተጓጓዘ፡፡
በወያኔ የራስን እድል በራስ መወሰን ልብ አማላይ ስብከት ተታለውም ይሁን ከመጀመሪያው በውስጣቸው የነበረው የጎሰኝነት ስሜት አመች ግዜ ሲያገኝ ፈንቅሎአቸው ይሁን ባይታወቅም ድርጅት እየመሰረቱ በወያኔ የጎሰኝነት መስመር የገቡ ሰዎች እንዳንዶቹ ብዙም ሳይቆዩ ከሰሙ፤ እስከዛሬ የዘለቁትም ቢሆኑ ለወያኔ ከመጥቀማቸው ባሻገር ይህ ነው የሚባል ያስገኙት ፋይዳ የለም፡፡
ምንም ተባለ ምንም ተደረገ ግን ኢትዮጵያዊነት እንዲህ አንደ ዋዛ የሚጠፋ ባለመሆኑ ወያኔ አጠፋሁት ብሎ እፎይ ማለት በጀመረ ማግስት መልሶ እያንሰራራ ይሄው እስከ ዛሬ እንቅልፍ እንደነሳው ይገኛል፡፡ ወያኔ ከደደቢት ሲነሳ ካነገበውና ሀያ አራት አመታትም ለተግባራዊነቱ እየሰራ ካለው ዘላቂና የረዥም ግዜ ግቡ አንጻር ከኢትዮጵያዊነት ጋር ሊታረቅ የሚችል አይደለም፡፡ ኢትዮጵዊነትም በየዘመናቱ ከውስጥም ከውጪም የተቃጣበትን አደጋ ሁሉ ተቋቁሞ ለመዝለቅ የቻለ መቼም ሆነ በማን የሚጠፋ አይደለ እንደመሆኑ መቼም ሆነ በማን የሚጠፋ አይደለም፡፡ ይህም ሆኖ ወያኔ በበርሀ ታጋይነቱም ሆነ በከተማ መንግሥትነቱ ዘመን የፈጸማቸው ተግባራት ሁሉ ኢትጵያዊነትን ማጥፋት እንዳላስቻሉት ከራሱ ተሞክሮ ትምህርት አግኝቶ ከእኩይ ተግባሩ ሊገታ አልቻለም፡፡ በመሆኑም ግዜ እየጠበቀ ለደደቢቱ ዓላማው ስኬት ሲል በብልሀትም በጉልበትም በሚፈጸመው ተግባር ሕዝብ እየተጎዳ ነው፡፡ ከዚህ የማያባራ ጉዳት ለመዳን የ ህዝቡ ምርጫ የሌለው አማራጭ አንድ ነው፡፡ እሱም ከወያኔ አገዛዝ መገላገል አለያም ወያኔ መቼም በምንም ሊያጠፋው የማይችለውን ኢትዮጵያዊነት ለማጥፋት በየግዜው በሚፈጽማቸው ኢ- ሰብአዊ ተግባራት እየታሰሩ እየተደበደቡ እየተገደሉ በአንዱ ሲደርስ ሌላው እያለቀሰ ተራውን እየጠበቀ መኖር፡፡ ሁለተኛው የሚመረጥ ኣራች አይመስለኝም፡፡
ለኢትዮጵያ መንግስትነት መብቃቱ የደደቢት ዓላማውን ሊያስተወው ያልቻለው ወያኔ በኢትዮጵያ መንግሥትነት ስም የያዘውን ሥልጣን የተነሳበትን ዓላማ ለማሳካት የሚያስችለውን ምቹ ሁኔታ ለማመቻቸት መጠቀሚያ ማድረግ የጀመረው ገና ወንበሩ ሳይደላደል እንደነበረ አሌ የሚባል አይደለም፡፡ ይህንንም የቻለውን በብልሀት በዚህ መንገድ ያልሆነለትን ደግሞ በጉልበት ተግባራዊ እያደረገ ከዛሬ ደርሷል፡፡ አሁንም ቀጥሏል፡፡
ወያኔ የደደቢት ውጥኑን ለማሳካት ከተጠቀመባቸው ብልሀቶች አንዱና ዋናው በማር የተለወሰ መርዝ የሆነው ፌዴራላዊ አወቃቀር ነው፡፡ የፌዴራል የመንግሥት ሥርዓትም ሆነ የመሬት አከላለል የአሀዳዊ ሥርዓት ደጋፊ ከሆኑ ሰዎች በስተቀር በአብዛኛው ሰው የሚደገፍ በመሆኑ ወያኔ ከላይ ሲታይ ለሀገርና ለሕዝብ በማሰብ የመረጠው በሚመስል ሁኔታ በኢትዮጵያ ተግባራዊ አንዲሆን በህገ መንግስት እንዲሰፍር ያደረገው ብዙም ተቃውሞ ሳይገጥመው ነበር፡፡ ፌዴራል አወቃቀርን የፈለገው የተነሳበትን ዓላማ ገቢራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለማሟያነት ብሎም ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በማለም አንጂ ለሀገርና ለሕዝብ አስቦ ባለመሆኑ አከላለሉ በቋንቋንና በብሄረሰብ /በጎሳ ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚከናወን እንዲሆን የሚያደርግ ሕገ መንግሥት አጸደቀ፡፡ ይህ አዋቃቀር የወያኔን ፍላጎት የሚያሳካ አንጂ በኢትዮጵያ ተግባራዊ የማይሆን ለመሆኑ የደቡብ ክልል የሚባለውን ማየት ብቻ ይበቃል፡፡ ፌዴራላዊ መንግስትነትን ደግፈው ቋንቋና ብሄርን መስፈርት ያደረገውን አወቃቀር የተቃወሙ የመኖራቸውን ያህል ደጋፊዎችም ስላልታጡ የፌዴራል አወቃቀሩን በህገ መንግሥት ለማስፈርም ሆነ ተግባራዊ ለማድረግ ወያኔ ብዙ አልተቸገረም፡
በመሆኑም በፋኖነት ዘመኑ የትግራይን የቆዳ ስፋት ለማስፋት በሀይል የያዛቸውን የጎንደርና የወሎ ቦታዎች በዚህ የህገ መንግስቱ አንቀጽ መሰረት ከማጽናቱ በተጨማሪ ሲጎመዥባቸው የነበሩ ለም መሬቶችን በሙሉ የትግራይ ክልል ብሎ ወደሰየመው ለመጠቅለል ቻለ፡፡ እንዲህ በብልሀት በህገ መንግሥት ሽፋን ወደ ትግራይ የተከለሉ ዜጎች እኛ ጎንደሬ /አማራ አንጂ ትግሬ አይደለንም ብለው ትግሬ ናችሁ ለመባላቸው የተጠቀሰባቸውን ህገ መንግስት ራሱኑ ለመከራከሪያነት ጠቅሰው ይህን መሰል ጉዳይ የማየት ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን ለተሰጠው የፌዴሪሽን ምክር ቤት አቤት እስከ ማለት ቢደርሱም ጩኸታቸው በተኩላ አደባባይ የበግ አቤቱታ አንዲሉ ሆኗል፡፡ ሕገ መንግሥቱ ወያኔ ሲጠቀምበትና ህዝብ ጥያቄ ሲያነሳ አፈጻጸሙ የተለያየ በመሆኑ ሕግ አለ ብለው በህግ ተማምነው ከጎንደር አዲስ አበባ ዘልቀው አቤት ላሉ ወገኖች ለጥያቄአቸው መልስ ሊያገኝላቸው ቀርቶ ከጥቃት ሊታደጋቸው ባለመቻሉ ዓላማ ፍላጎቱን በብልሀት ካልሆነም በጉልበት ተግባራዊ በሚያደርገው ወያኔ እየታደኑ ነው፡፡ ህገ መንግሥቱ በተግባር የተጻፈበትን ወረቀትና ቀለም ያህል አንኳን ዋጋ የለውም የተባለውም አንዲህ በመሆኑ ነው፡፡
ወያኔ ዓላማውን ተፈጻሚ ለማድረግ አስቀድሞ በብልሀት ብልሀቱ ካላዋጣ በጉልበት ይሄ አልሆን ካለ ደግሞ በህግ መሳሪያነት ጉልበት ከሥርዓት ይሉት ዘዴ የሚጠቀም በመሆኑ ከመነሻው ነገሮችን ለዚሁ ያመቻቻል፡፡ በመሆኑም ወደ ትግራይ ሊጠቀልላቸው ያሰባቸውን ቦታዎች አስመልክቶ በብልሀትም በጉልበትም ምን ማድረግ እንዳለበት ገና ደደቢት ሳለ ነው ያሰበው ያቀደውና የተዘጋጀው፡፡ ይህ እቅዱንም ነው በፋኖነት ዘመኑም ሆነ በመንግሥትነት ግዜው ተግባራዊ ያደረገውና አሁንም እያደረገ ያለው፡፡
ከእነዚህ ስራዎች አንዱና ዋናው ከላይ የተጠቀሰው ቋንቋና ብሄርን መሰረት ያደረገው የፌዴራል አዋቃቀር ሲሆን ሌላው ተቀናሽ ያላቸውን ታጋይ ተጋዳላዮች ቦታው ላይ ማስፈር ነው፡፡ እነዚህ እነ መለስን ቤተመንግስት በማድረስ ተልእኮአቸው የተጠናቀቀና ከታጋይነት ወደ ቀደሞ አራሽነታቸው አንዲመለሱ የተደረጉ ዜጎች በቦታው የሰፈሩት ከነ ጠመንጃቸው በመሆኑ የተሰጣቸውን ለም መሬት አርሰው ከሚያገኙት ጥቅም በላይ ለወያኔ የሚሰጡት ጥቅም ብዙ ነው፡፡ ወሰናችን ተከዜ ነው በማለት የሚያስቸግሩትን እያስፈራሩ ጸጥ ማሰኘት፤ በፍራቻ ለማይበገሩት ደግሞ ጠመንጃቸውን ስራ ላይ ማዋል፡፡ ይህን ደግሞ ሰሞኑን በተካሄደ ሰልፍ ላይ የተሰሙት ታውቁናላችሁ እናሳያችኋላን ወዘተ መፈክሮች በቂ ገላጮች ናቸው፡፡ ሌላው የወያኔ ርምጃ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ሰዎችን በመውሰድ በወረራ በየዘው መሬት ላይ ማስፈሩ ነው፡፡ ተቃውሞ በርትቶ ትግሉ ገፍቶ በብልሀትም በጉልበትም የማይገታ ከሆነና ወያኔ በመጠባቢቂያነት ወደሚያስበውና አስቀድሞ የተዘጋጀበት ወደሚመስለው ህዝበ ውሳኔ ቢያመራ የተጋዳላዮቹም ሆነ የሰፋሪዎቹ ውሳኔ ምን እንደሚሆን የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
ከሀገር ጥቅም አንጻር ሳይሆን ከራሱ ዓላማ ስኬት አንጻር አርቆ የሚያስበውና የሚሰራው ወያኔ ልብ አማላዩን የፌዴራል ስርዓት ለራሱ ዓላማ ማመቻቻ የተጠቀመበት በመሬት አከላል ብቻም አይደለም፡፡ አንድ ቀን መንግሥት ሊሆንባት የሚያዘጋጃትን ክልል በቀሪው የኢትዮጵያ ሀብት በሁለንተናዊ መልክ ለማሳደግም ተጠቅሞበታል፡፡ የፌዴራል ስርዓት በሚፈቅደውና በህገ መንግስቱም ውስጥ በተጻፈው መሰረት ክልሎች ሙሉ ነጻነት ቢኖራቸው እቅዱን ገቢራዊ ማድረግ እንደማይችል ቀድሞውንም የተረዳውና የዘየደው ወያኔ በአደባባይ የብሄር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ራስን የማስተዳደር መብት እስከ መገንጠል ህገ መንግሥታዊ እውቅና እንዳገኘ እየለፈፈ በተግባር ግን የየክልሎቹ ሹማምንት ስሙንና ወንበሩን ከመያዝ የለፈ ሥልጣንም ነጻነትም እንዳይኖራቸው አድርጎ ያልተጻፈ አሀዳዊ ስርዐት እያራመደ የሁሉም ጠቅላይ ገዥ ራሱን አድርጎ ይሾማል ይሽራል ሀብት ይዘርፋል ፡፡
ወያኔ ፍላጎቱን በብልሀት ለመፈጸም እንዲያስችለው በማር የተለወሰ መርዝ ሲያቀርብልን መርዙን በለማየት ለእኩይ አላማው ስኬት ብዙዎች ተባባሪ ሆነዋል ብዙዎችም በዝምታ ተመልክተዋል፡፡ ነገሮች ካለፉ በኋላ መርዙን በማየት የሚሰሙ ጩኸቶችም ሆኑ የሚደረጉ ትግሎች በብልሀት ያሳካውን በጉልበት ለማስጠበቅ በሚወስደው ርምጃ መስዋእትነት እንጂ ድል ሊያስገኙ አልቻሉም፡፡
ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን የተለየ የሚመስል ነገር ይታያል፡፡ ወያኔ በማስተር ፕላን ስም በብልሀት ያሰበው የመሬት ወረራ የገጠመውን ተቃውሞ በጉልበት ሰጥ ለማድረግ ኢሰብአዊ ተግባር ፈጽሞ አልሳካ ሲለው የለመደውን በህግ ሽፋን ጉልበት ከሥርዓት የመጠቀም አካሄድም ሞክሮ ውጤት ባለማግኘቱ ማስተር ፕላኑን ሰርዣለሁ ብሏል፡፡ ይህን ብሎ ግን በባልስልጣኖች አንደበት የሚነገረውም ሆነ በነብሰ ገዳዮቻቸው የሚፈጸመው ድርጊት እንዲሁም ኦህዴድን በወያኔ ታማኞች ለማጠናከር የተያዘው ርምጃ ወያኔዎች እንዴት ያሰብነውን ማሳካት ያቅተናል በሚል አልህ ውስጥ ያሉ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ታክሲ አሽከርካሪዎች ባካሄዱት የአንድ ቀን ስራ ማቆም መንገድ ትራንስፖርት ያወጣውን ደንብ ለሶሰስት ወር አዘግይተነዋል የሚል ምላሽ ተሰምቷል፡፡
ጫካ ሆኖም ሆነ ቤተመንግሥት ተቀምጦ የደደቢት ህልሙን በብልሀትም በጉልበትም ተግባራዊ ሲያደርግ ለኖረው ወያኔ ማስተር ፕላኑን ሰርዣለሁ ማለቱ የመንገድ ሥነ ሥርዓት ደንቡንም ተግባራዊነት ለሶስት ወር አራዝሜአለሁ ማለቱ የህዝብ ትግል ውጤት መሆኑ ባይካድም ወያኔ የባህርይ ለውጥ አምጥቶ ነው ማለት ግን አይቻልም፡፡ እንዲህ በማሰብ መዘናጋት ከተፈጠረ ይህን ውጤት ያስገኘውን ትግል ማክሸፍ ታጋዮችንም ማስበላት ይሆናል፡፡
ወያኔ ከዓላማው ፍንክች ያለበት ግዜ የለም፡፡ቅንጅቶችን ከጸሀይ በታች ባለ ማናቸውም ጉዳይ ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ ብሎ ትጥቃቸውን (የህዝብ ሀይል ) ካስፈታ በኋላ እኔ በመረጥኩት አጀንዳና በምለው መንገድ ብቻ ነው መነጋገር የሚቻለው ማለቱ የሚዘነጋ አይመስለኝም፡፡ ስለሆነም በብልሀትም በጉልበትም ያሰበውን ከማሳካት ወደ ኋላ የማይለው ወያኔ ሸብረክ ያለ የሚመስለው ግዜ ለመግዛት ሁኔታዎችን ለማመቻቸትና ወጥመዱን ለማጥበቅ እንደሆነ በመረዳት በማስመሰያ ድርጊቶች ሳይታለሉና ሳይዘናጉ ለተጨባጭ ለውጥ መታገል ያስፈልጋል፡፡
ወያኔ የደደቢት ህልሙን ለማሳካት ብልሀትን ጉልበትን ጉልበት ከሥርዓትን እንደ ሁኔታው እያማረጠም እያደባለቀም አንደሚጠቀመው ሁሉ በለውጥ ሀይሉ በኩል ለትግሉ ከግብ መድረስ አንድና አንድ መንገድና አማራጭ ብቻ የሚጠቀም ሳይሆን መስዋዕትነቱን ቀላል ድሉን ቅርብ ሊያደርጉ የሚችሉ ግንባር ቀደም ታጋይ አታጋዮችን ከአደጋ የሚከልሉ ወያኔ ጉያ ውስጥ እሳት ማቀጣጠል የሚያስችሉ አማራጭ ስልቶችንና ተግባራዊ የማድረጊያ መንገዶችን መተለም ያስፈልጋል፡፡ በወያኔ ብልሀት መበለጥ፤ በጉልበት ለሚያደርገው መንበርከክ፤ በህግ ሽፋን በሚፈጽመው ውንብድና መታለል እንግዲህ ያበቃ ይመስላል፡፡ቢሆንም ግን ወያኔ እስካሁን ካጠፋው ይልቅ ወደፊት ሊያጠፋው የሚችለው ለበለጠ ተጠያቂነት እንደሚዳርገው ተረድቶ እርቅ የሚፈልግ፤ አድራጎቴን ህዝብ አልወደደውም ብሎ ከደደቢት ህልሙ የሚላቀቅ ሳይሆን ሸብረክ ያለ እየመሰለ የህዝብን ጥያቄ ተቀብያለሁ እያለ በብልሀትም በጉልበትም ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ ከጥፋት የማይመለስ በመሆኑ ከነጻነት ወዲህ ማዶ የሚኖር መዘናጋት ተራ በተራ መበላትን ያስከትላል ፡፡

posted by Tseday Getachew

http://abbaymedia.com/

 

የታገደው ድፍረት ፊልም የይገባኛል ጥያቄ አስነሳ

አንጀሊና ጆሊ ኤግዚኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር የሆነችበትና ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ዲፕሎማቶችና የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት በብሔራዊ ቴአትር ሊመረቅ የነበረው ድፍረት ፊልም፣ በፍርድ ቤት እግድ ከተቋረጠ በኋላ የይገባኛል ጥያቄ ማስነሳቱ ታወቀ፡፡

ፊልሙ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ የሚያጠነጥነው አስገድዶ የደፈራትን የ29 ዓመት ወጣት በገደለችው የ14 ዓመት ታዳጊ አበራሽ በቀለ (በፊልሙ ሒሩት) ሕይወት ዙሪያ ነው፡፡ ደፋሪዋ ሕፃኗን በጠለፋ ሊያገባትም ሙከራ አድርጐ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር መሥራች የሆኑት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ጉዳዩን ሰምተው ጥብቅና ቆመውላት ራስን ለመከላከል በሚል በነፃ እስከተለቀቀችበት ጊዜ ድረስ፣ አበራሽ በግድያ ክስ ተመሥርቶባት ማረሚያ ቤት ነበረች፡፡

በአቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ መሐሪ የተጻፈውና ዳይሬክት የተደረገው ይህ ፊልም በዚህ ዓመት በሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫል ተሸላሚ መሆኑን ተከትሎ፣ የታሪኩ ባለቤት በሆነችውና ፈቃደኝነቷን እንዳልተጠየቀች በምትናገረው ወ/ሪት አበራሽና የወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ወንድምና የታሪኩ ጸሐፊ ነኝ በሚሉት አቶ ፍቅሩ አሸናፊ ጥያቄ ተነስቶበታል፡፡

የፍርድ ቤት እግዱ እንደሚያሳየው በከሳሽነት የቀረቡት አቶ ፍቅሩ አሸናፊና ወ/ሪት አበራሽ በቀለ ሲሆኑ፣ ተከሳሾቹ ደግሞ አቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ፣ ኃይሌ አዲስ ሥዕሎች ድርጅትና ትሩዝ ኤይድ ሚዲያ ድርጅት ናቸው፡፡

ክሱ እንደሚያስረዳው ድፍረት የተሰኘው ፊልም ተመርቆ ለሕዝብ ዕይታ ቢውል በከሳሾች ሞራላዊና ኢኮኖሚያዊ መብት ላይ የማይተካ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል በመገንዘብ፣ ፍርድ ቤቱ ፊልሙ ለሕዝብ ዕይታ እንዳይውል ወይም እንዳይመረቅ ጭምር እገዳ ጥሏል፡፡ በተጨማሪም በተከሳሾች ላይ ሊደርስ ለሚችል ኪሳራ ከሳሾች 50 ሺሕ ብር በዋስትና አስይዘዋል፡፡

ወ/ት አበራሽ እንደምትለው ፊልሙ በርሊን እስከተመረቀበት ጊዜ ድረስ ምንም ዓይነት መረጃ አልነበራትም፡፡ ከሰባት ወራት በፊት ግን አቶ ዘረሠናይን አግኝታው በፊልሙ ላይ ዕውቅና እንዲሰጣት፣ የተወሰነ ገንዘብም እንዲከፍላት እንደምትፈልግ ገልጻለት የነበረ ቢሆንም ይህ ሳይሆን ቀርቷል፡፡

የፊልሙ ሥራ የእሷን ደኅንነት ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ አይደለም በማለት የምትወቅሰው ወ/ት አበራሽ፣ ምንም እንኳ ሁኔታውን ለማስረዳት ብትሞክርም ከአቶ ዘረሠናይ በመጨረሻ ያገኘችው መልስ አዎንታዊ አለመሆኑን ትናገራለች፡፡ ‹‹ከተፈጠረው ነገር ጋር በተያያዘ የምኖረው ተደብቄ ነበር፡፡ ይኼ ፊልም ግን ታሪኩን እንደ አዲስ ቀስቅሶ የእኔንም የቤተሰቦቼንም ሕይወት አደጋ ላይ ጥሎታል፤›› ትላለች፡፡

ወ/ት አበራሽ የደፈራትን ሰው ከገደለች በኋላ በኦሮሞ የእርቅ ባህል ጉማ መሠረት ቤተሰቦቿ ካሳ ከፍለው ነገሩ ተቋጭቶ ነበር፡፡ በስምምነቱ መሠረት እሷም ቀዬዋን ጥላ ለመውጣት ተስማምታ እንደነበር የምትናገረው አበራሽ፣ ‹‹በባህሉ መሠረት ሴት ገድላ ካሳ መክፈል አትችልም፡፡ ስለዚህም ወደ አካባቢዬ እንዳልመለስ የሟች ቤተሰቦች ያስጠነቀቁኝን በመስማትና ለቤተሰቦቼ ደኅንነት ስል ለዓመታት እዚያ ሳልደርስ ቀረሁ፤›› ብላለች፡፡

በአሁኑ ወቅት ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችን ለማገዝ የሚሠራ ሀረም በተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ በመሥራት ላይ የምትገኘው ወ/ት አበራሽ፣ በሕይወቷ ብዙ ውጣ ውረዶችን እንዳሳለፈች ትናገራለች፡፡ የትውልድ ቦታዋ ቀርሳ አርሲን የለቀቀችው ወ/ት አበራሽ ሁለተኛ ደረጃ እስክትደርስ የኖረችው ቀጨኔ ሕፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ነበር፡፡ ታሪኳ ተካትቶ በተሠራ ዘጋቢ ፊልም አማካይነት ታገኝ የነበረው ገንዘብ ኮሌጅ ስትገባ መቋረጡን ታስታውሳለች፡፡ ስለዚህም በነበረባት የገንዘብ ችግር የኮሌጅ ትምህርቷን ለማቋረጥ መገደዷን፣ ከዚያም ወደ ዱባይ እስከሄደችበት ጊዜ ድረስ በአንድ ትንሽ የፊልም ሲዲ ማከራያ ሱቅ ውስጥ መሥራቷን ለሪፖርተር ገልጻለች፡፡

አቶ ዘረሠናይ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ላይ እንደተናገረውና አቶ ፍቅሩ እንደሚሉት ስለታሪኩ መጀመሪያ አቶ ዘረሠናይ የነገረው ለእርሳቸው ነው፡፡ ይህ የሆነው እ.ኤ.አ. በ2005 ሲሆን፣ አቶ ፍቅሩ እንደሚሉት የፊልሙ ሐሳብ የተወሰደው ከእሳቸው በመሆኑ ፊልሙን በጋራ ለመሥራት አስበው ነበር፡፡ ‹‹ከ2008 በኋላ አቶ ዘረሠናይ እኔን ለማናገር አልፈለገም፡፡ እንዲያውም ይደበቀኝ ጀመር፤›› ይላሉ፡፡

የፊልሙን መሠራት ሲጠባበቁና ነገሮችን ሲከታተሉ እንደነበር፣ የአበራሽን ይሁንታም እንዳገኙ አቶ ፍቅሩ ይናገራሉ፡፡ አቶ ዘረሠናይ ግን ለእሷም ለእሱም የታሪኩ ሐሳብ ባለቤት እንደመሆኑ ዕውቅና ሳይሰጥ መቅረቱን ያስረዳሉ፡፡ ‹‹ያለሷ ታሪክ ፊልሙ አይሠራም ነበር፡፡ ባትደፈር፣ በጥንካሬ ደፋሪዋን ባትገድለው ኖሮ ታሪክ አይኖርም ነበር፤›› ይላሉ አቶ ፍቅሩ፡፡

በፊልሙ ውስጥ ሌላ ባለታሪክ የሆኑትና በወቅቱ የ14 ዓመቷ ታዳጊ ጠበቃ የነበሩት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ለፊልሙ ዳይሬክተር ታሪካቸው በፊልሙ እንዲካተት ፈቃድ መስጠታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ይህንንም ያደረጉት ታሪኩ በፊልም መሠራቱ የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ጥያቄን ያራምዳል፣ ስለጠለፋና ስለጥቃት ግንዛቤ ለመፍጠር ያስችላል በሚል እንጂ ‹‹የእኔ ታሪክ ይነገር›› በሚል እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

ለአበራሽ ጥብቅና በቆሙላት ጊዜ ከዚያም በኋላ አበራሽ በመኖሪያ ቤታቸው ተቀምጣ እንደነበር ቅርበትም እንደነበራቸው የሚያስታውሱት ወ/ሮ መዓዛ፣ ለረዥም ዓመታት ግን ከአበራሽ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሳይኖራቸው እንደቆዩም ይናገራሉ፡፡

ከፊልሙ መሠራት በኋላ ግን የታሪካቸው በፊልም መሠራት ለአበራሽ የሚከፍተው የዕድል በር ይኖራል በሚል ማፈላለግ መጀመራቸው የሚናገሩት ወ/ሮ መዓዛ፣ ስለጉዳዩ በነገሯት መሠረት በመጨረሻ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኗ ደራርቱ ቱሉ የአበራሽን ስልክ ቁጥር እንደሰጠቻቸውና እንዳገኙዋት ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

‹‹ደውዬ ወደ አዲስ አበባ አስመጣኋት፡፡ አሁንም ያለችው እናቴ ቤት ነው፡፡ የእኔ ቤት ወጣ ስለሚል ነው እዚያ እንድትቀመጥ ያደረግኩት፡፡ ከመጣች ወደ ሰባት ወራት ገደማ ሆኗል፤›› የሚሉት ወ/ሮ መዓዛ፣ ወ/ት አበራሽን አሁን እየሠራችበት ያለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እንድትቀጠር ያደረጉት እሳቸው እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡

ወ/ሮ መዓዛ እንደገለጹት ወ/ት አበራሽ ወደ አዲስ አበባ እንድትመጣ ያደረጉት ፊልሙ ጀርመን በርሊን ውስጥ ሊመረቅ በተቃረበበት ጊዜ ነበር፡፡

ለታሪኳ ባለቤት ወ/ት አበራሽ በፊልሙ ሥራ ተሳታፊ ከሆኑት ግለሰቦች ሁሉ ቅርበት ያላት እርሷ እንደመሆኗ የታሪኳ ባለቤት ተጠቃሚነትን በሚመለከት ለወ/ሮ መዓዛ ጥያቄ ቀርቦላቸው በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹መጠቀም እንዳለባት አምናለሁ፡፡ አቶ ዘረሠናይም በዚህ ያምናል፡፡ ይህን ለማድረግም በጣም ፈቃደኛ ነው፡፡ እሷም የምትጠብቀው ነገር አለ፡፡ ችግር የፈጠረው እንዴት በሚለው ላይ አለመነጋገር ነው፤›› ብለዋል፡፡

ወንድማቸው አቶ ፍቅሩ አሸናፊም ፊልሙ ላይ ጥያቄ ማንሳታቸውን በሚመለከት፣ ወንድማቸውና የድፍረት ፊልም ዳይሬክተርና ከፕሮዲዩሰሮቹ መካከል አንዱ የሆነው አቶ ዘረሠናይ ምንም እንኳ የጓደኝነታቸውን ደረጃ መናገር ባይችሉም፣ ጓደኛማቾች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ ወንድማቸው ስለ እርሳቸው ለጓደኛው አቶ ዘረሠናይ ሲያወሩ የፊልም ባለሙያ የሆነው አቶ ዘረሠናይም ታሪኩን ወደ ፊልም ለመቀየር ትልቅ ፍላጐት እንዳደረበትና የፊልሙ መነሻ እንዲህ እንደነበር፣ ከዚህ ውጪ ግን በወንድማቸውና በአቶ ዘረሠናይ መካከል ሌላ ጉዳይ ይኑር አይኑር የሚያውቁት እንደሌለ አስረድተዋል፡፡ ግጭቱ ቀላል እንደሆነ ስለዚህም በጣት በሚቆጠሩ ቀናት ውስጥ ይፈታል የሚል እምነት እንዳላቸው አክለዋል፡፡

የፊልሙ ዳይሬክተር አቶ ዘረሠናይ ብርሃኔ በእጁ ላይ ያለው የፍርድ ቤት እግድ ብቻ በመሆኑ ስለክሱ ዝርዝር ነገር ሳያውቅ በጉዳዩ ላይ ምንም ዓይነት አስተያየት መስጠት እንደማይፈልግ ለሪፖርተር አስታውቋል፡፡ የባለታሪኳ ወ/ሮ አበራሽ ፈቃድን ማግኘት አለማግኘቱን በተመለከተም አቶ ዘረሠናይ ምንም ማለት አለመፈለጉን ገልጿል፡፡ ጠበቃው ዓርብ ነሐሴ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ የክሱን ቻርጅ ለማግኘት ፍርድ ቤት እንደነበሩና የክሱን ዝርዝር እንዳወቁ ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጥ ገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ዓርብ እኩለ ሌሊት ድረስ ከእሱ በኩል የተሰማ ነገር አልነበረም፡፡

የፊልሙ እግድ ለብሔራዊ ቴአትር ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. አሥራ አንድ ሰዓት ላይ መድረሱን ከሳሾች ቢጠቁሙም፣ የቴአትር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሽመልስ እግዱ የደረሰው አሥራ አንድ ሰዓት ከሃያ አምስት ላይ እንደነበር ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

እሳቸው እንዳሉት እግዱ በደረሰበት ወቅት 1,200 ያህል እንግዶች አዳራሹ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አሥር ያህሉ አምባሳደሮችና ባለሥልጣናት ነበሩ፡፡ በአሳጋጆቹ በኩል የነበረው አቀራረብ አስቸጋሪ ስለነበርና በሌላኛውም በኩል ፊልሙን ለማቋረጥ ያለመፈለግ ነገር ስለነበር፣ በአጋጣሚው የአገር ገጽታ እንዳይበላሽ በጥንቃቄ ለመያዝ ቴአትር ቤቱ የተለያዩ ጥረቶችን አድርጓል ብለዋል፡፡

‹‹የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይከበራል፡፡ ይህ ምንም ዓይነት ጥያቄ የለውም፡፡ ነገር ግን በሁሉቱም በኩል የነበረው ነገር ወደ ግጭት የሚያመራ ዓይነት ስለነበር ነገሩ በሰላም እንዲፈታ ፖሊስ ጠርተናል፡፡ ምክንያቱም እኛ ያለን የፀጥታ ኃይል ያን ማድረግ አይችልም ነበር፤›› ሲሉ አቶ ተስፋዬ የነበረውን ሁኔታ አስረድተዋል፡፡

posted by Tseday  Getachew

http://satenaw.com

“በሽብር” ተከሶ ፍ/ቤት የቀረበው ወጣቱ ፖለቲከኛና መምህር አብርሃ ደስታ የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀበት

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

ወጣቱ መምህርና ፖለቲከኛ ዛሬ በግምት 9፡00 ሰዓት ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ ሲደርስ በግቢው የነበሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባሎች እንዲሁም የአብርሃ ደስታ ደጋፊዎች በጭብጨባ ያላቸውን አክብሮት የገለጹለት ሲሆን እሱም አጸፋውን መልሷል፡፡ ከማዕከላዊ አጅበውት የመጡት የፌዴራል ፖሊሶች ለምን አጨበጨባችሁ እያንዳንዳችሁ ትገባላችሁ በማለት እያስፈራሩ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ በማለት ከግቢ ለማስወጣት ሙከራ ያደረጉ ሲሆን ጉዳዩን ሊከታተል የመጣው ታዳሚም ለምን እንወጣለን አንወጣም እኛም ችሎት ተገኝተን ልንከታተል ሲገባ ግቢ ውስጥ መቆምም ልትከለክሉን ነው በማለት ተቃውሞ በማሰማቱ ችሎቱ እስኪጠናቀቅ በግቢው እንድንቆይ ተደረገ፡፡ የክሱ ጉዳይ የታየው በችሎት ሳይሆን በጽ/ቤት ነበር፣ ወጣቱ ፖለቲከኛ አብርሃ ደስታም ከጠበቃዬ ጋር ልገናኝ አልቻልኩም፣ ዘመድ አዝማድም ሊጠይቀኝ አልቻለም በማለት ለፍ/ቤቱ አስረድቷል፡፡

ዳኛውም ከጠበቃና ከቤተሰብ ጋር የማታገናኙ ከሆነ እርምጃ እወስዳለሁ በማለት ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡ ፖሊስ ተጨማሪ ማስረጃና ምስክር ለማሰባሰብ የጊዜ ቀጠሮ በመጠየቁ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮውን ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ተቃውመውታል ፖሊስ ደንበኛዬን ከመያዙ በፊት ማስረጃና ምስክሮችን ማዘጋጀት ነበረበት ነገር ግን አሁንም ደንበኛዬ ታስረው ማስረጃና ምስክር ሊባል አይገባም፣ እስራቱ ህገወጥ ነው በማለታቸው ዳኛው እንዳትሰራ አደርግሃለሁ ጥብቅናህን በፍትህ ሚ/ር አሳግድብሃለሁ በማለት እንዳስፈራሯቸው ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም ዳኛው ፖሊስ የጠየቀውን የጊዜ ቀጠሮው ፈቅደው ለመስከረም 22ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 እንድትገኙ በማለት ችሎቱ ተጠናቋል፡፡ አብርሃ ከችሎቱ ሲወጣም የሱን ጉዳይ ሊከታተል የመጣው ታዳሚ በጭብጨ ሸኝቶታል፡፡

posted by Tseday Getachew

http://satenaw.com

 

Post Navigation

%d bloggers like this: