Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

Archive for the month “April, 2013”

ህዝቡ በወያኔ ላይ ያለውን ምሬትና ጥላቻ መግለጽ ጀምሯል!

የኢትዮጵያ ህዝብ እውነተኛ ምርጫና የቀልድ ምርጫ ምን ማለት እንደ ሆነ ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑን በ1997 አም ባደረገው አለምን ባስደመመ ሂደት አስመስክርዋል::

Ginbot 7 weekly editorial ወያኔና ጀሌዎቹ ግን ዛሬም ሊማሩ አይችሉምና ደግመው ደጋግመው ህዝባችን ሊያሞኙት ይሻሉ በ2002 አ.ም ምርጫ ቦርድ ከሚባለው ሎሊያችው ጋር ሆነው ድምጹን ሰርቀውና አሰርቀው አሽንፍዋል አሽነፍን ብለው አይናቸውን በጨው አጠበው ጨፍር ብለው አደባባይ አስወጡት፤ በጥቃቅን ስም ባደራጁቸው እበላ ባዮች ታጅበውም በአደባባይ አላገጡ በህዝብ ቁስልም ላይ ጨው ነሰነሱ ህዝብም ታዝቦ ዝም አለ ዘንድሮስ?

ዘንድሮ የተለየው ነገር ተቃዋሚዎች ተባብረው 33 የሚሆኑት በአንድ ላይ ቆሙ ከምርጫው በፊት ጥያቄዎችን አንስተው እንደራደርም ብለው ጠየቁ ትእቢተኛው ወያኔም እንደልማዱ አሻፈርኝ የት ልትደርሱ አላቸው ትኩረታቸውን በሙሉ በየቤቱ እየዞሩ ካርድ እንዲወስድ ያስፈራሩት ጀመር የፈራ ወሰደ ያልፈራም ሳይወስድ ቀረ ይህንንም ህዝብ በትዝብት ተመለከተ ፤ካድሬዎቹም ሆነ አለቆቻቸው ወያኔዎች እሁንም ህዝቡን ንቀውታል ምን ያመጣል በሚል ትእቢት ከ99.6 % ወደ 100፥ በመለወጥ ለማሸነፍና ለመጨፈርና ለማስጨፈር ዝግጅታቸውን ማጠናቅቅ ላይ ብቻ አደረጉ።

ተቃዋሚዎችም በአንድ ድምጽ በመሆን የወያኔ የምርጫ አሻንጉሊት ሆነን ለእሱ ፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያ አንሆንም ብለው በውሳኔያቸው በመጽናታቸው ወያኔን በእጅጉ አበሳጭቶታል፤ ይሁን እንጅ አጨብጫቢ የሆኑ ፓርቲዎችን መፈለጉ ግን አልቀረም ለምርጫ ጨዋታው አዳማቂነት። የምርጫ ዴሞክራሲያዊነት ከሚለካበት አንዱና ዋናው ፤ ህዝብ የሚፈልጋቸውን መሪዎቹ ያለማንም አስገዳጅነት መርጦ እንደሚሾሙና እንደሚሽር ማመን ሲጀምር መሆኑ ዛሬም ሊዋጥላቸው አልቻለም። ይሁን እንጅ ህዝብ ዛሬ ሳይሆን ከ97 ምርጫ ጀምሮ ወያኔን በህዝብ ድምጽ ተሸንፎ እንደማይወርድ የተገነዘበው አሁን ላይ ሆኖ ሳይሆን ትላንት መሆኑን ወያኔዎች አልተረዱትም ቢረዱትም ለህዝብ ድምጽ ደንታ አልሰጣቸውም።

ስለዚህም የህዝብ የበላይነት ማረጋገጫ የሆነውን ምርጫ ሂደት ወደ ልጆች መጫዎቻነትና ማላገጫ በመቀየር መሬት ላይ የሌለውን ምርጫ በቲቢ ምርጫ እንዳለ ለማስመሰል በኢቲቪ ተወዳድሮ የማሸነፍ ምኞታቸውን መራጭ በሌለበት ምርጫ ለማሳየት ሞክረዋል። ይህም የማስመሰል እና የማጭበርበር አመላቸው ሱስ ሆንባቸው የውድቀታቸውን፣ የሽንፈታቸውን ጽዋ እየተጋቱ እልል ሲሉ ያሳዩናል “በቀሎ እያረረ ይስቃል እንዲሉ”።

የሀገሪቱን ዜጎች በደልና ጥቃት የፍትህ ስርአት የነጻነት ጥያቄ በማፈን የአማራውን መፈናቀል ያልዘገበ ሚዲያና ጋዜጠኞቹ፤ እውን ምርጫ ስላልሆነ ተውኔት የአለቆቻቸውንና የስልጣን ጥመኞችን ውሸት እውነት አድርጎ በማቅረብ አለቆቻቸውን ሲደስቷቸው ሌሎችን ደግሞ አሳዝኗል።

ሚዲያ በታፈነባት ሀገረ-ኢትዮጵያ እንደ ኢቲቪ ያሉ ያዩትን ሳይሆን በወያኔ የተነገሩትን፣ የተዘጋጀላቸውን ሀተታዊ ድራማ በሚዘግቡ፤ እውነታን በማይናገሩ ቡችሎች ስለምርጫ ሲዘምሩ ይታያሉ። ካድሬዎቻቸው እንኳ ወጥተው ባልተሳተፉበት መራጭ የሌለውን፤ ውጤቱ የዜሮዎች ድምር ዜሮ የሆነውን የምርጫ ድራማ ተውኔትና ውርደታቸውን ሲያሳዩ በአንጻሩ ህዝብ እየተፈናቀለ እያዩ እንዳላዩ በመሆን ለማስመሰያ ጭዋታ የሀገሪቱን ንብረትና ሀብት ያባክናሉ።

ይህን ሁሉ ፈተና አልፎና ተገድዶ የሄደው ህዝብም ቢሆን ያገኘውን እድል በመጠቀም ወያኔዎችን ውረዱ፣ በቃችሁ፣ወንጀለኞች ናችሁ፣ የፖለቲካና የሃይማኖት እስረኞችን ፍቱ እና ሌሎችንም የወያኔ ባዶነትን ለመግለጽ ባዶ ወረቀቶችን በመስጠት ጥላቻቸውን በድጋሜ አረጋግጠውላቸዋል። ግንቦት 7 ህዝቡ ያሳየውን እምባይነት እያደነቀ ነገር ግን የወያኔዎችን ጭቆና ተቋቁሞ ትግሉን ከዚህም በላይ በመውሰድ በየአካባቢው በማፋፋም መቀጠልና ነጻ አውጪዎችን ሳይጠብቅ በራሱ ጎበዝ አለቃዎች በመደራጀት አልገዛም ባይነቱን እንዲቀጥል ጥሪውን በዚህ አጋጣሚ ማስተላለፍ ይወዳል።

ንቅናቂያችን ዛሬም ትክክለኛና ህዝብ በነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ተሳትፎ የሚመርጠው አካል፣ እንዲሁም ለህዝብ ተጠያቂ የሆነና ህዝብን የሚፈራ መንግስት፣ በህዝብ የሚሾም፣ የሚሻር አካል ለመፍጠር በቅድሚያ ወያኔን በማስወገድ ብቻ ነው ብሎ ያምናል።

ነጻነትን ለማግኘት ዝም ብለን ስለተመኘነው የሚመጣ አይደለም፣ ዝም ብሎም በራሱ ታምር ሆኖ አይከሰትም፤ ሁሉም ዜጎች ከወያኔ የምርጫ ማጭበርበሪያ ካርድ ወጥተው ተደራጅተውና አደራጅተው በተናጥልም ሆነ በቡድን ወያኔን አስወግዶ በሀገራችን ሁሉም ዜጎች በእኩልነት ተከብረው የሁሉም መሰረታዊ መብቶች ባለቤት ሲሆኑ ነው። ይህ የሚሆነው ደግሞ ወያኔ እንደ ምጽዋት እስጣችኋለሁ በሚለው መንገድ ሳይሆን ፣ ብቸኛው ምርጫ በሆነው ነጻነታችንን ለማስከበርና የሀገራችንን ህልውና ለመታደግ ማናቸውንም አይነት የትግል ስልቶችን ተጠቅመን ደማችንን አፍሰን አጥንታችንንም ከስክሰን በሚከፈል ዋጋ መሆኑን አምነን ትግሉን በማፋፋም በመሆኑ በተለይም ወጣቶች ትግሉን እንድትቀላቀሉን ጥሪያችን ይድረሳቹሁ እንላለን።

በዚህም አጋጣሚ ግንቦት 7 ለወያኔ አባላት የሚያስተላልፈው መልእክት በፍላጎታችሁ እና በምርጫችሁ የመስራትና የመኖር ሰብአዊ ነጻነታችሁ በወያኔ የፖለቲካ ፓርቲ አሽከር አደግዳጊና ጉዳይ ፈጻሚ በመሆን ብቻ የምታገኙት እርጥባን ሳይሆን በዜግነታችሁና በሰውነታችሁ የተሰጣችሁ መብት በመሆኑ ከፍርሃት ወጥታችሁ ንጹህ ህሊናን ተጥቅማችሁ ወያኔን በማስወገድ በሚደረገው ህዝባዊ ትግል ውስጥ ጊዜው ሳይይረፍድ ከታጋይ ሀይሎች ጋር በመቀላቀል የበኩላችሁን አስተዋጽኦ በማድረግ ኢትዮጵያዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

http://www.ecadforum.com

posted by Tseday Getachew

Advertisements

ነጋሶ እና የከሸፈው የቤተመንግስት እቅድ

Written by ናፍቆት ዮሴፍ

ነጋሶ እና የከሸፈው የቤተመንግስት እቅድ

 ከኢህአዴግ የሽግግር መንግስት በኋላ እስከ 1994 ዓ.ም ድረስ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ያገለገሉት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በሥልጣን ዘመናቸው ለማከናወን አስበው ካልተሳኩላቸው የቤተ-መንግስት እቅዶች መካከል አንዱን አጫውተውኛል። ዶ/ር ነጋሶ ርዕሠ-ብሄር ሆነው ወደ ብሄራዊ (ኢዮቤልዮ) ቤተመንግስት ከገቡ በኋላ የቤተመንግስቱን የተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውረው ተመለከቱ፡፡ ብዙ ለዓይን የሚስቡና ለጐብኚዎች አይን ማረፊያ የሚሆኑ ነገሮችን ያስተዋሉት ፕሬዚዳንቱ፤ አንድ ሃሳብ ብልጭ ይልላቸዋል። ቤተመንግስቱን በሰለጠኑት አገራት የጥራት ደረጃ ለማሰራት ነበር ያሰቡት፡፡ ይሄንን ዕውን ለማድረግም የሌላው ዓለም ቤተ-መንግስቶች ምን አይነት አሠራርና አካሄድ እንዳላቸው ያጠኑላቸው ዘንድ በወቅቱ የቤተ መንግስቱ አስተዳዳሪ የነበሩትን ጀነራል ፍሬ ሠንበት ወደ እንግሊዝና አሜሪካ ላኩ፡፡ ጀነራሉ ባመጡት መረጃ መሠረት፤ የአሜሪካው ኋይት ሀውስም ሆነ የእንግሊዙ ቤኪንግሀም በቱሪስቶች ይጐበኛል፡፡

ኋይት ሀውስ ፕሬዚዳንት ኦባማ ስራቸውን እያከናወኑም ቢሆን አልፎ አልፎ ክፍት እየሆነ በውስጡ ያሉ ቅርሶችና ታሪኮች እንደሚጐበኙ፣ የንግስት ኤልሳቤት መቀመጫ የሆነው የእንግሊዙ ቤኪንግሀምም ለጐብኚዎች ክፍት እየተደረገ የአገሩ ህዝብ መሪዎቹ የሚኖሩበትን ቤተ-መንግስት፣ ቅርሶች፣ የቀደሙ መሪዎችን ታሪክ ይጐበኛል፡፡ ስለሀገሩም በቂ ግንዛቤ ያገኛል። ይህን የሠሙት ዶ/ር ነጋሶ፤ “በዚህ አይነትማ የሀገሬ ቤተመንግስት ብዙ ሊጐበኙ የሚችሉ ነገሮች ሞልተውታል” በማለት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መምከር ይጀምራሉ፡፡ (ልብ በሉ! በወቅቱ ዶ/ር ነጋሶ የሚኖሩበት ቤተመንግስት ጣሪያ ያፈስ ነበር።) “ጀነራል ፍሬ ሠንበትን ልኬ ባስጠናሁት መሠረት የእኛንም ቤተመንግስት ለቱሪስት ክፍት ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀመርኩ” ይላሉ ዶ/ር ነጋሶ፡፡

በተለይ አሁን ፕሬዚዳንት ወ/ጊዮርጊስ የሚኖሩበት ብሄራዊ ቤተመንግስት ከንግስት ዘውዲቱ፣ ከልጅ እያሱና ከሀይለ ስላሴ እስከ መንግስቱ ኃ/ማሪያም የአገዛዝ ዘመን ድረስ ያሉ በርካታ ቅርሶችን የያዘ በመሆኑ ለሙዚየምነት ከበቂ በላይ ነው፡፡ የኃይለስላሴ እና ሌሎች የልዑላን ቤተሠቦች ያገኟቸው ሽልማቶች፣ የጦር ሜዳ መሣሪያዎች፣ አልባሣት፣ የቤት እቃዎችና መሠል በርካታ ቅርሶች በቤተመንግስቱ ውስጥ ቢኖሩም የሀገሬው ህዝብ ግን ሊያያቸው ቀርቶ ከነመኖራቸው ማወቁንም ይጠራጠራሉ – ዶ/ር ነጋሶ፡፡ “ሌላውን ተይው ኃይለ ስላሴ ሊታሠሩ ሲያዙ ከአልጋ ላይ የወረዱበት ነጠላ ጫማና ፒጃማ ሳይቀር በቤተመንግስት ይገኛል” የሚሉት ዶ/ር ነጋሶ፤ መታጠቢያ ቤት ሲገባ የጢም መላጫቸው፣ ሳሙና፣ ፎጣና ሌሎች ነገሮች እንደሚገኙም ነው ያጫወቱኝ። ዶ/ር ነጋሶ እንደሚሉት፤ ይህንን ሁሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያየው ይገባል፡፡ “እኛ አገር ስለ ቱሪዝም ሲወራ ቶሎ ወደ አዕምሯችን የሚመጣው የፈረንጅ ጐብኚ ነው፡፡ ሀገሬው ሊጐበኛቸው የሚገቡ በርካታ ቅርሶች እንዳሉን ግን እንዘነጋዋለን” ይላሉ፡፡ የሆኖ ሆኖ እቅድ ወጣ፡፡

እቅዱም በብሔራዊም ሆነ በታላቁም ቤተ መንግስት ያሉ ቅርሶችን ለህዝብ ክፍት አድርጐ ለማሣየት፣ በታላቁ ቤተ መንግስት ግቢ ውስጥ አንድ ሙዚየም መገንባት ነው፡፡ ይህን እዉን ለማድረግ ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ተነስቶ በሒልተንና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፊት ለፊት በሚገኘውና ሼክ መሀመድ አሊ አላሙዲን ባሠሩት “አፍሪካ ፓርክ” አናት ላይ በድልድይ መልክ አልፎ ታላቁ ቤተ-መንግስት ድረስ የሚሄድ መንገድ መገንባትና ለጐብኚ ክፍት ማድረግ ነበር። የመንገዱ ዋና አላማ ብሄራዊ ቤተመንግስቱ ውስጥ ያሉትን ቅርሶች የሚጐበኙ ሠዎች፤ ከዚያ ወጥተው ላይኛው (ታላቁ) ቤተመንግስት ሙዚየም ለመግባት እንዳይቸገሩ ለማድረግ እንደነበር ዶ/ር ነጋሶ ይናገራሉ፡፡ በታላቁ ቤተ መንግስት ውስጥ አዲስ ከሚገነባው ሙዚየም በተጨማሪም የአፄ ምኒሊክ ቤተ መንግስት ስለሚገኝ እግረ-መንገዱን መጐብኘት ይችላል የሚል ሀሣብ መካተቱን የሚናገሩት ዶ/ር ነጋሶ፤ ይህም የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ወጣቱ ስለሀገሩ እያወቀና እየተገነዘበ እንዲሄድ በማሰብ ዝግጅት መጀመሩን ያስታውሳሉ፡፡

የሙዚየም ዕቅዱን እውን ለማድረግ ዲዛይን ሁሉ ተዘጋጀ፡፡ በጀትም ተመደበ፡፡ ወደ ስራ ሊገባ በዝግጅት ላይ እንዳለ የ1993 ዓ.ም የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት መጣና በነጋሶ የሞቀ እቅድ ላይ ውሀ ቸለሠበት፡፡ ሁሉም ትኩረቱን ወደ ጦርነቱ ከማድረጉም በተጨማሪ “የሙዚየሙን ጉዳይ እውን የምናደርግበት ገንዘብ የለንም” ተባሉ፡፡ ይህን የመሠለ የነጋሶ ድንቅ ዕቅድም በሀሣብ ብቻ መቅረቱን ያስታውሳሉ – ዶ/ር ነጋሶ። ይህንን ነግረውኝ ሲጨርሱ ትዝ ያለኝ የፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” የተሰኘ መፅሃፍ ነው፡፡ እኔም መክሸፍ እንደ ነጋሶ ሃሳብ” አልኩኝ ለራሴ፡፡ ዶ/ር ነጋሶ የሙዚየሙ ጉዳይ እንዲሣካ ከፍተኛ ፍላጐት እንደነበራቸው ይናገራሉ፡፡ ሙዚየሙን ለማስገንባት የቦታ ጥያቄ እንዳይነሳ በመፍራት “ፕሬዚዳንቱ በህገ-መንግስቱ እንደተቀመጠው ብዙ የአስተዳደር ስራ ላይ አልተቀመጠም፤ ለመኖሪያ የሚያገለግል አነስተኛ ቤትና ትንሽ ፅ/ቤት ብቻ ይበቃዋል፤ ሌላው ለጉብኝት ክፍት ይሁን” የሚል ሀሣብ አቅርበው እንደነበርም ያስታውሳሉ፡፡ አልተሳካም፡፡ የክሽፈት ታሪካችንን አያችሁልኝ!!

http://www.addisadmassnews.com

posted by Tseday Getachew

በተለያዩ የአለም ክፍሎች መንግስት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው

ሚያዚያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ለባይ ግድብ መዋጪ ለማሰባሰብ በኖርዌይ ኦስሎ የተጠራው ስብሰባ ለሁለተኛ ጊዜ በአገሪቷ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲቋረጥ ተደርጓል።

በተመሳሳይ ሁኔታም በካልፎሪኒያ ሳንዲያጎ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ተብሎ የተጠራው ስብሰባ በአካባቢው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ ሰብሰባው እንዲቋረጥ ተደርጓል።

በሌላ በኩል ደግሞ በኔዘርላንድስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመውን የማፈናቀል ዘመቻ አውግዘዋል። ። የኢትዮጵያውያን ማህበር በሆላንድ  ትናንት በአምስተርዳም ከተማ በጠራው ስብሰባ የህወሀት ኢህአዴግ አገዛዝ በቤንሻንጉል ጉሙዝና እና በሌሎችም  የአገሪቱ ክፍሎች በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ግፍ ፣ በእስር ቤት ውስጥ በሚገኙ የህሊና እስረኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እንዲሁም በሙስሊሙና በክርስቲያኑ ላይ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት  ለአውሮፓ መንግስታት ለማሳወቅ ሜይ 15፣ 2013 በአውሮፓ ህብረት መቀመጫ በሆነችው ብራሰልስ የተቃውሞ ሰልፍ  ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

በሌላ ዜና ደግሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት የጠራው ስብሰባ በጀርመን  ተካሂዷል።

posted by Tseday Getachew

በመተማ ወረዳ አርሶ አደሮች ከመፈናቀላቸውም፡በላይ ድረንበር ጥሰዋል ተብለው ሦስት ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ

 

ሚያዚያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በሰሜን ጐንደር ዞን በመተማ ወረዳ ከዮሐንስ ከተማ በስተሰሜን <<ደለሎ>> ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ ለረዥም ዓመታት መሬት  ወስደው በሕጋዊ መንገድ  ግብር ሲከፍሉ፡የቆዩ አርሶ አደሮች፣ አካባቢውን ጥለው እንዲሄዱ በወረዳው ውሳኔ መተላለፉን  የሪፖርተር ዘገበ፡፡

ጋዜጣው ምንጮቹን በመጥቀስ  እንደዘገበው፤ድንበር አልፈዋል በሚል ሦስት አርሶ አደሮችም በሱዳን ታጣቂዎች ተገድለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን በፓርላማ ሪፖርት ሲያቀርቡ በቤንሻንጉል ክልል የተፈፀመው ማፈናቀል በመንግስት ተቀባይነት እንደሌለውና ከ፡እንግዲህ ምንም አይነት ማፈናቀል እንደማይኖር ቃል፡መግባታቸው ይታወሳል።

የክልሉ አካባቢ ጥበቃና መሬት አስተዳደር ባለሥልጣን -ከወረዳው አስተዳደር ጋር በመተባበር አርሶ አደሮቹ የእርሻ ቦታቸውን ጥለው እንዲወጡ ማድረጋቸው አግባብ አለመሆኑን የሚናገሩት ምንጮቹ፣ አርሶ አደሮቹ መሬታቸውን በማለስለስ ለዘር ዝግጁ አድርገው እየተጠባበቁ ባሉበት ሁኔታ ውሳኔው መተላለፉ ፤ተስፋ አስቆራጭ እንደሆነባቸው ገልጸዋል፡፡

የክልሉ አካባቢ ባለሥልጣን የመሬት አያያዝ ብሎክ ፤ አርሶ አደሮችና -ባለሀብቶች ድንበራቸውን የመለየት ሥራ በሚል ሰበብ፣ ቀደም ብሎ በጂፒኤስ ተለክቶ የተሰጠን መሬት፣ ከ15 ዓመታት በኋላ ኋላቀር በሆነና ለማዳላት በሚያመች መንገድ በገመድ እየለካ መሆኑንም ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡

ባለሥልጣኑ እየሠራ ባለው ኋላቀር አሠራር፤ ለአስተዳደሩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች የሚፈልጉት ተጨማሪ ቦታ እየተመቻቸላቸው መሆኑን የሚናገሩት ምንጮቹ፤ አቅም የሌላቸው፣ አነስተኛ አርሶ አደሮችና ለአስተዳደሩ አመራሮች ቅርበት የሌላቸው አልሚዎች ተጐጂ መሆናቸውንም  አክለዋል፡፡

የገመድ ልኬቱ፤ የድንበርን ወሰንን በትክክለኛው ሊያስቀምጥ ባለመቻሉ እና አልፎ አልፎ ወደ ሱዳን ድንበር እየገባ በመሆኑ፤ በሱዳን አርሶ አደሮች በኩል አላስፈላጊ እንቅስቃሴ እየፈጠረ እና አካባቢውን ወደ አለመረጋጋት እየወሰደው መሆኑን ምንጮቹ  ተናግረዋል፡፡

ስለጉዳዩ የተጠየቁት የአማራ ክልል የአካባቢ ጥበቃና መሬት አስተዳደር ባለሥልጣን ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ባይህ ጥሩነህ  የተፈናቀለ አርሶ አደር እንደሌለ በመጥቀስ፤ በ አካባቢው ዘመናዊና ሥርዓት የያዘ  የመሬት አስተዳደር እንዲኖር በሰሜን ጐንደር መተማ ወረዳ ደለሎ አካባቢ  የባለሀብቶችንና የአርሶ አደሮችን ድንበር የመለካት ሥራ እየተሠራ  መሆኑን ተናግረዋል።

<<ደለሎ>> ተብሎ በሚጠራው አካባቢ  ሁለት ዓይነት ይዞታ አለ የሚሉት ኃላፊው፣ በ አንድ በኩል  በሕገወጥ መንገድ መሬት በመያዝ ግብር ሳይከፍሉ የሚኖሩ ከሌላ ቦታ የመጡ  አርሶአደሮች ሲኖሩ በሌላ በኩል   ሕጋዊ የሆኑ አርሶ አደሮች አሉ ብለዋል።

‹‹ተፈናቀልን›› የሚሉትም ሕጋዊ ሰነድ እንዲያቀርቡና ሕጋዊ እንዲሆኑ ተጠይቀው፣ ማቅረብ ያልቻሉ ሊሆኑ እንደሚችሉ ሀላፊው ግምታቸውን ጠቅሰው፤ ወደ ቢሮውም ቢመጡ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆናቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ቀደም ሲል ከደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳም ሆነ አሁን በቅርቡ ከቤንሻንጉል ለተፈናቀሉት አርሶአደሮች ለመፈናቀላቸው የሚቀርበው ምክንያት እንዳሁን<<ከሌላ ቦታ የመጡ ህገ-ወጦች ናቸው>.የሚል መሆኑ ይታወቃል።

አርሶ አደሮቹ  እንደሚሉትም፣ ዘር ለመዝራት ያዘጋጁት መሬት መወሰዱ ኢፍትሐዊ መሆኑን ለወረዳው አስተዳደርና ለዞኑ ቅሬታ ቢያቀርቡም፣ ማንም ሊያነጋግራቸው ፈቃደኛ አልሆነም።

በቀጥታ ለክልሉ መንግሥት ቅሬታ ሲያቀርቡም፤ ከወረዳ እስከ ዞን ባለው የቅሬታ አቀራረብ ሰንሰለት እንዳልመጡ በመግለጽ እንዳልተቀበላቸው ጠቁመዋል፡፡

ክልሉ ባለው መዋቅር መሠረት ሰንሰለቱን ጠብቀው ቅሬታቸውን ለማድረስ የሚወስደው ጊዜ ረጅም በመሆኑ፣ ለዓመታት ሲያለሙት የኖሩትን መሬት ለቀው ለመውጣት መገደዳቸውን ምንጮቹ አክለዋል፡፡

የአቶ መለስን ሌጋሲ በማስቀጠል ስም የሚነግዱና ለኢንቨስትመንት መዘጋጀት  የሚችልን መሬት ለግል ጥቅማቸው ለማዋል የሚፈልጉ የወረዳና የዞን አመራሮች እንዳሉ የሚገልጹት ምንጮቹ፣ መንግስት አንዳንድ ከእነሱ ጋር ግንኙነት የመሠረቱ ባለሀብቶችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርግ አሠራር መኖሩን  ተገንዝቦ ክትትል እንዲያደርግ እንዲሁም የ አርሶአደሮችን መፈናቀል እና  ከጐረቤት አገሮች ጋር ግጭት ውስጥ የሚጥል የልኬት ሥራን እንዲያስቆም ጠይቀዋል፡፡

በተመሣሳይ  ከድንበር ልኬት ጋር በተገናኘ ከመተማ ዮሐንስ ከተማ በስተደቡብ በኩል <<ቱመት-ቲያ>> ተብሎ በሚጠራው የኢንቨስትመንት አካባቢ ሦስት አርሶ አደሮች፣ ‹‹ድንበራችንን አልፋችሁ ገብታችኋል›› በሚል ሰበብ በሱዳን ታጣቂዎች መገደላቸውንም ሪፖርተር ምንጮቹን በመጥቀስ ጨምሮ ዘግቧል።

የመተማ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ተስፋ መኮንን አርሶ አደሮቹ በሱዳን ታጣቂዎች ተገድለዋል መባሉ እውነት መሆኑን ቢያረጋግጡም፣ ምክንያቱ ግን ከድንበር ልኬትና ከእርሻ ጋር የተገናኘ አይደለም ባይ ናቸው።

አንዳንድ ጊዜ የመተማ አርሶ አደሮች ድንበር ተሻግረው የመስፈር ሁኔታ መኖሩንና ከሱዳኖቹም በኩል ተመሳሳይ ባህሪ እንደሚታይ የገለጹት አቶ ተስፋ፣በዚህ ሳቢያ  ከሱዳኖች በኩል አንድ ታጣቂ ተገድሎ እንደነበርና ሱዳኖቹም በዚያ ድርጊት ቂም ይዘው ግድያውን ሳይፈጽሙ እንዳልቀሩ ግምታቸውን ገልጸዋል፡፡

የዜናው ምንጮች ግን ለ አርሶአደሮቹ ሞት ምክንያት የሆነው የመሬት ልኬቱ ድንበር እያለፈ ግጭት በመፍጠሩ እንደሆነ በመጥቀስ የ አካባቢውን አስተዳደር ተጠያቂ ያደርጋሉ።

ጠ/ሚ/ር ሀይለማርም ፦<<ዳግም መፈናቀል አይኖርም>>ብለው ቃል በገቡ ማግስት ይህን ዜና ያነበቡ ሰዎች፦<<ድርጊቱ አቶ መለስ ካለፉ በሁዋላ በ ኢህአዴግ ውስጥ መርህ፣ መደማመጥና መከባበር መጥፋቱን የሚያመለክት ነው”ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

posted by Tseday Getachew

የጠ/ሚኒስትር ሀይለማርያም ፓርላማ ዉሎ የፓርላማዉን አባላት ጭምር ማስቆጣቱ ታወቀ

የወያኔ ታማኝ ሎሌ የሆነዉ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈዉ ሳምንት የፓርላማ ዉሎዉ 40 በ 60 የተባለውን የቤቶች ልማት ፕሮጀክት አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠዉ ምላሽ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ ከዚህ ቀደም ከሳቅና ጭብጨባ ዉጭ ሌላ መቃወም የሚባል ነገር የማያዉቀዉን የወያኔ ፓርላማ ማስቆጣቱ ተሰማ፡፡ ኃይለማርያም ደሳለኝ ይህ እንግዳ የሆነ ተቃዉሞ የገጠመዉ የ2005 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ሲሆን  የፓርላማዉ አባላት 40 በ 60 የሚባለው የቤት ልማት መቶ በመቶ የመክፈል አቅም ላላቸው ሰዎች ቅድሚያ ይሰጣል የመባሉን ጉዳይ እርግጠኛ ስለመሆኑ ለጠየቀዉ ጥያቄ አዎንታዊ መልስ በመስጠቱ ወይም  መቶ በመቶ የመክፈል አቅም ላላቸው ቅድሚያ እንደሚሰጥ በማረጋገጡ  ፓርላማዉ በተቃዉሞ ድምፅ ሲሞላ ተስተዉሏል።

ለወያኔ ፓርላማ ቅርበት ያላቸው ምንጮች የፓርላማዉ አባላት ለምን አለወትሯቸዉ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ላይ እንዳልጎመጎሙ ተጠይቀው በሰጡት መልስ ቀደም ሲል ፕሮግራሙን በተመለከተ ለፓርላማው በቀረበዉ ሪፖርት 40 በ60 የሚባለው ፕሮግራም መካከለኛ ገቢ ያለውን በተለይም በደሞዝ የሚተዳደረውን የህብረተሰብ ክፍል ይጠቅማል ተብሎ መነገሩንና ሆኖም በዕቅድ ደረጃ  ለባለአንድ ክፍል መኝታ ቤት 857 ብር፣ለባለሁለት መኝታ ቤት 1 ሺ 337 ብር፣ ለባለሶስት ምኝታ ቤት ደግሞ 2 ሺ133 ብር ለአምስት ተከታታይ ዓመታት በየወሩ መቆጠብ እንዳለበት መታቀዱ የመካከኛ ገቢ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል አቅም ያገናዘበ አይደለም የሚል ቅሬታ በፓርላመዉ አባላት ዘንድ በቅሬታ መልክ በተደጋጋሚ ይነሳ እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ መካከለኛ ገቢ አለው የሚባለው በተለይም የመንግስት ሰራተኞች አማካይ ወርሃዊ መካከለኛ ገቢ ከ2 ሺ 500 ብር እንደማይበልጥ ምንጫችን ጠቅሶ ከዚህ ደመወዝ ላይ ዝቅተኛውን በወር 857 ብር መቆጠብ እንዴት ይቻላል ሲል የወያኔን ግራ የሚያጋባ አሰራር  ገና ሳይጀመር ጥያቄ ዉስጥ የገባ አሰራር ነዉ ብሎታል፡፡ በዚህ ምክንያት የ40 በ60 የቤት ልማት ፕሮግራም መካከለኛ ገቢ ላላቸዉ ሰዎች ይዘጋጅ እንጂ እካሁን ድረስ እየጠቀመ ያለዉ ከፍተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ነዉ፤ ይህንን ደግሞ ኃ/ማሪያም ደሳለኝም ፓርላማ ዉስጥ ባደረገዉ ንግግር አረገግጦታል ብሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ  ጠ/ሚኒስተር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ቢሮ አማካይነት በተደረገው ጥናት ለውጪ ኩባንያዎች ዝግየሆነውን የሸቀጦች ችርቻሮ ንግድ ስራ ለመፍቀድ ወይ ሌሎች አማራጮችን ለማየት መሞከሩን የኢሳት ቴሌቭዥንና ሬድዮ ዘጋቢ ጠቅሶ ይህ ነገር ግን ትልልቆቹ ኩባንያዎች በሸቀጦች የችርቻሮ ንግድ እንዲሰማሩ ቢደረግ የአገር ውስጥ አስመጪዎች በአጭር ጊዜያት ውስጥ ከገበያ ውጪ በማድረግ መንግስት ሊቆጣጠረው የማይችለው ገበያ ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት በመኖሩ በመንግስት ቁጥጥር ስር ሆኖ ዋጋ የማረጋጋትና አነስተኛ ዋጋ ካላቸው ገበያዎች ሸቀጦችን በመግዛት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርብ ኢንተርፕራይዝ እንዲቋቋም ውሳኔ ላይ ተደርሶአል፡፡

http://www.ethiosun.com

posted by Tseday Getachew

የዘረፋ ውሎ በእንዳማሪያም (ገብረመድህን አርዓያ)

ስብሃት ነጋ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ በሚታተመው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ አነበብኩት:: ስብሃት ነጋ “ኢህዴግን የመሰለ ፓርቲ በአፍሪካ የለም” እና ሌላም ብዙ ፣ ብዙ ይላል:: ይዘብታል ፣ ይፎክራል ፣ ይሸመጥጣል ፣ ያቀረሻል ፣በህዝብ ሞራል ላይም ያላግጣል:: ብዙም አልደነቀኝም:: ስብሃትም ሆኑ የዚህ ፋሺስታዊ ስርዓት አንቀሳቃሾች በብዙሃን ደም ላለፉት አርባ አመታት ታጥበዋል ፣ ታሪክ አውድመዋል፣ እጅግ ከፍተኛ ዘረፋ ፈጽመዋል ፣ አገር ቆርሰው ሸጠዋል:: በጣም ከፍተኛ ወንጀል የሰሩ ሰዎች እንደመሆናቸው በአገሪቷ የፖለቲካ ለውጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ መቀጣጠሉ እንቅልፍ እንደነሳቸው እያየን ነው:: አዎን ስብሃት ገና ፣ ገና ከዚህም በላይ ብዙ ይናገራል ፤ ቁጣው እያየለ በሄደ ቁጥር ብዙ ወንጀሎችም ይሰራል::

Sebhat Nega

Sebhat Nega

ዛሬ ወያኔ ኢህአዴግ ከመቼውም ጊዜ በበዛ ፍጥነት እና ማን አለብኝነት ኢትዮጵያዊ የሆኑ መሰረቶችን የመናዱን ስራ አጠናክሮ እየሰራ ለመሆኑ በየእለቱ የምንሰማቸው ዜናዎች እና ዘገባዎች ያሳያሉ:: እንደ እኔ ፣ እንደ እኔ የወያኔ የጥፋት ስራ ሳይሆን የጨመረው ይልቁንስ ረጅም እድሜ ለኢሳት ይስጠውና የዜና ዘገባ ብዛት እና አይነቱ መጨመሩ ይመስለኛል:: ወያኔ ሲፈጠር ጀምሮ ኢትዮጵያዊ መሰረት ያላቸውን እሴቶችን የማጥቃት ስራን እንደ መጨረሻ ግብ(strategic goal) አስቀምጦ የሚንቀሳቀስ ድርጅት መሆኑን ቀድመን ላወቅን እና ለተረዳን ሰዎች ግን እምብዛም አዲስ ነገር አይደለም:: ዛሬ ላይ ከኢትዮጵያ ከሚወጡ ዜናዎች በብዛት የምንሰማው ብዙዎች ሲያለቅሱ እና ጥቂት ዘረኞች ደግሞ ያለ ይሉኝታ ሲዘርፉ ፣ ሰዎችን አስረው ሲያሰቃዩ፣ እና ኢትዮጵያውያንን ዘር ቆጥረው ከቀያቸው ሲያፈናቅሉ ሆኗል::

የኢትዮጵያውያን ገበሬዎች ዋይታ በቤኒሻንጉል እና ጉራፈርዳ፣ የባህታውያን ለቅሶ በዋልድባ ፣ የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን የፍትህ ጥያቄ በመላ ሃገሪቱ ፣ ሌላም ፣ ሌላም:: ወያኔ ኢህአዴግ በአገር እና በወገን ላይ የሚያደርሰው ጥቃት በግብ ደረጃ የተያዘ በመሆኑ ይብሱን ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል:: ዛሬ ላይ ከዳር ቆመው የሚመለከቱ ሰዎችም ሆነ በስርዓቱ ውስጥ ያሉ ካድሬዎች እና አገልጋዮች ይህንን ሃቅ በደንብ ልብ ብለው ሊመለከቱት ይገባል:: የጥቃት ዱላው በአንድ ወይም በሌላ በኩል አይደርስ የሚመስልበት ቦታ ሁላ ይደርሳል::

ኢትዮጵያውያን ከምንም ነገር በላይ ለሃይማኖት እና የእምነት ተቋሟት ታላቅ ክብር ይሰጣሉ:: በዛሬ ጽሁፌ ለማንሳት የፈለግኩት ጉዳይ በአንድ ወቅት በወያኔ ኢህአዴግ ውስጥ ታጋይ በነበርኩበት ወቅት በዘመቻ ከስብሃት ነጋ እና ከሃለቃ ጸጋይ በርሄ ጋር ሌሎች ሁለት ታጋዮችም ተጨምረውበትአንድ ገዳም እንዴት እንደፈርን እና እንደዘረፍን በማሳየት ስብሃትም ሆነ ድርጅቱ እንዴት ለአገራዊ እና ሃይማኖታዊ ተቋማት ያላቸውን ንቀት ለማሳየት ነው:: ጊዜው ሕዳር ወር 1971ዓ.ም. እና የተ.ሓ.ህ.ት. 1ኛ ጉባኤ እየተቃረበ የመጣበት ወቅት ነበር። ድርጅቱ ለጉባኤው ማካሄጃ በሚል ሰበብ የትግራይ ደሃ ገበሬዎችን ንብረት እና ገንዘብ በስፋት መቀማቱን በዘመቻ ተያይዞታል:: ሃብትና ንብረታቸው የተዘረፈ ንጹሃን የትግራይ ገበሬዎችንም ሃለዋ ወያኔ በማስገባት መፍጀቱ ተጧጡፏል፤ በወቅቱ የተ.ሓ.ህ.ት. ቤዝ በለሳ፤ እገላ ወረዳ ውስጥ ይገኛል። ብዙ ክፍሎች፤ ማለትም 02 ወታደራዊ ማሰልጠኛ፤03 ህክምና፤ 04 ፖለቲካ ጽ/ቤት፤ 05 ክፍሊ ኢኮኖሚ፤ 09 መሳሪያ ግምጃ ቤትና 06 ሃለዋ ወያነ ተበለው ተከፋፍለው እዚሁ ቦታ ላይ በተለያየ አቀማመጥ ሆነው ይሰራሉ። አቦይ ስብሃት በ04 ፖለቲካ ጽ/ቤት በሚታዘዙ እና በአዲ ጨጓር እና በለሳ ምይ ሃማቶ ላይ በሚገኙ ሁለት ሃለዋ ወያኔዎች(እስር ቤቶች) ንጹሃንን አሳስሮ ያስገርፋል፣ ያስገድላል:: እኔ በወቅቱ የህክምናው ክፍል ሃላፊ ነበርኩኝ::እና ታዲያ በዚሁ አንድ የህዳር ቀን በስብሃት የተጻፈ ቀጭን ደብዳቤ በምሰራበት የህክምና ክፍል ደረሰኝ:: ደብዳቤው እንዲህ ይላል: ነገ ጠዋት ልክ በ2 ሰዓት መሬቶ እንድትጠብቀኝ፤ ወደ ሽራሮ ለሥራ ጉዳይ አብረን እንሄዳለን:: ለምን ፣ እንዴት ፣ በምን ተብሎ አይጠየቅም፤

በነጋታው እንደታዘዝኩት በተባለው ሰዓት መሬቶ ቁሽት ቀድሜ ደረሼ ቆየሁት። እሱም በሰዓቱ መጣ። ተያይዘን ጉዞአችንን ወደ ጭላ ወረዳ ቀጠልን። ቀኑን ሙሉ ስንጓዝ ውለን በመሃልም ግርማይ ጀብር የሚመራት አንድ ሃይል ተቀብላን አንድ ቦታ አደርን። ከአስመራ ወደ አድዋ የሚወስደውን መንገድ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ አሻገሩን። ይህ መንገድ ሁልጊዜ የኢትዮጵያ ጦር አይለየውምና ለመሻገር ጥንቃቄ ይሻል::

ጭላ ከጥዋቱ 2 ሰዓት ገባን። እዛ የቆዩን ሃለቃ ፀጋይ በርሄ–የላይ አድያቦ ሕዝብ ግንኙነት፤ አጽብሃ ሀ/ማርያም–የአንከረ ሕዝብ ግንኙነት፤ ቀሺ ታደሰ–የክርቢት ነውጠኛ መሪ ነበሩ። እኔና ስብሃት ተደምረን አምስታችን ጭላ ውለን ስብሃት ቀድሞ ለወጠነውና አስቅድሞ መረጃው ለሌለኝ የዘረፋ ስራ ወደ እንዳማርያም ገዳም ጉዞ ጀመርን:: ሃለቃ ፀጋይ በርሄ በስብሃት በታዘዘው መሰረት አስቀድሞ ጥናቱን ጨርሶ ስለነበር፤ የቤት ክርስትያኑን አቃቤ ግምጃ ቤት ባህታዊ ማን መሆናቸውን እና የት አካባቢ እንደሚኖሩ አውቋል። ሌሎቻችን ታጣፊ ክላሽንኮቭ ስብሃት ነጋ ደፍሞ ሽጉጥ ታጥቋል። ለምን እና ወዴት እንደምንሄድ ቀሺ ታደሰ፤ አጽብሃ ሃይለማርያምም ሆነ እኔ አናውቅም። ኋላም ተጉዘን እንዳማርያም ቤተ ክርስቲያን ገባን። ቤተ ክርስቲያኑ በጥንት ዘመን በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነመንግሥት የተሰራ፤ በጣም ሰፊና ብዙ የአትክልት እና ፍራፍሬ እርሻ የሚለማበት ገዳም ነው:: በመነኮሳት ጉልበት በመስኖ የለማ ሎሚ፤ ሙዝ፤ ብርቱካን፤ ትርንጎ፤ መንደሪን ገዳሙን ከቦታል። መቼም አካባቢው ውብ እና ለመንፈሳዊ ህይወት የተመቸ ነው:: በእድሜ የበለጸጉ ባህታውያን፤ ቀሳውስት፤ መናንያን እና ዲያቆናት በገዳሙ ዙሪያ መንፈሳዊ ህይወታቸውን ይመራሉ። ውስጥ ለውስጥ ብዙ ከሄድን በኋላ ከፊታችን አንድ ዲያቆን አገኘን። ሃለቃ ፀጋይ ዲያቆኑን ለብቻ ነጥሎ አናገረው፤ ምን እንደተነጋገሩ እኔ ካለሁበት ብዙም አይሰማም ብቻ ሁለቱ ተያይዘው ከፊት እየመሩ ወደ አንድ ቤት ውስጥ አስገቡን። ቀጥሎም ስብሃት ነጋ እንዲህ አለ፤ ሌሎቻችሁ እዚሁ ቆዩ:: እኔ ፣ ገ/መድህን እና ሃለቃ ፀጋይ ብቻ የገዳሙን አስተዳዳሪ ለማናገር እንሄዳለን::ከዚያም ሶስታችንም ተያይዘን ከነትጥቃችን ወደ ገዳሙ አስተዳዳሪ ቤት አቀናን:: የገዳሙንም አስተዳዳሪ ከቤታቸው አገኘናቸው:: ለአፍ ያህል ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ስብሃት ጊዜ ሳያጠፋ “የመጣነው ገንዘብ እንዲሰጡን ስለሆነ ያለዎትን ሁሉ ይስጡን!”አላቸው። ለመነኩሴው ግር የሚል ትዕዛዝ ነበር:: ብዙም ሳያቅማሙ “እኔ አልሰጥም፤ የእመቤቴ ብርሃን ንብረትና ሃብት ላይ የማዘዝ መብት የለኝም:: አልሰጥም::” በማለት እቅጩን በግልጽ አማርኛ ተናገሩ:: ስብሃትም አይኑን እያጉረጠረጠ ድምጹን ከፍ አድርጎ አምጡ ማለቱን ቀጠለ:: ስብሃት በቀላሉ እንደማይመለስ በድምጽም ፊቱን በመቀያየርም እንዲረዱ አደረገ ፣ ምስኪኑ አባትም አማራጭ እንደሌላቸው ተረዱ::ትንሽ አስብ አደረጉና ወደውስጥ ገብተው የተቋጠረ ከረጢት ተሸክመው መጡ።

ባዘነ አንደበት እንዲህም ሲሉ ተናገሩ ፤ “የቤተ ክርስቲያን ሃብት ወድጄ ፈቅጄ ሳይሆን የሰጠኋችሁ አስገድዳችሁ እና አንቃችሁ እንደወሰዳችሁ እወቁት::” ከዚያም ከረጢቱን አልሰጥም በማለት ብር 50,000 የታሰረ ገንዘብ ከፊቱ ዘረገፉለት። ስብሃትም በፍጥነት ይዘነው በመጣነው ‘ሃቨር ሳክ’ በሚባል ወታደራዊ ሻንጣ ሞልተን ተሸክመን እንድንወጣ አዘዘ:: እኛም የተባልነውን አደረግን::ባህታዊውም በመውጫችን ላይ እንዲህ አሉ፤ “ነገ ጠዋት ለሕዝበ ክርስቲያኑ የሆነውን ሁሉ እናገራለሁ::” የተዘረፈውን ገንዘብ እኔና ስብሃት ተሸክመን ተመልሰን በለሳ ማይሃምቶ ገባን።

የተፈጸመውን የዘረፋ እና የገዳም ደፈራ የአካባቢው ሕዝብ ሁሉ ሰማው፤ በተሰራው ስራም ክፉኛ አዘነ፤ አወገዘውም። ስብሃት ድርጊቱ የየግል ምስጢራችን ሆኖ መጠበቅ እንዳለበት አስጠነቀቀን። ለዘረፋው ስራም ባለን ድርጅታዊ ታማኝነት እንደተመረጥን ገለጸልን። እንግዲህ ይህ አንድ ገጠመኝ ብቻ ነው:: ዘረፋ፣ ማውደም ፣ ታሪክ እና ቅርስ ማጥፋት ፣ የእስላምም ይሁን የክርስቲያን ቤተ እምነቶችን መድፈር እና ማበላሸት ለህወሃት የሰርክ ስራዎች ናቸው::

በአለቃ ገበረ ሃና ስም የሚነገር አንድ ታሪክ አለ:: ልጅቷ አለቃ ጋር ሄዳ “ጎረምሶቹ ሁሉ ድንቼ ፣ ድንቼ እያሉ ይጠሩኛል:: ለምን ይመስልዎታል::” ብትላቸው አለቃም እንዲህ አሉ:: ” ሊልጡሽ ፈልገው ነዋ!”:: ትናንትና በዘር እና በሃይማኖት እየመረጠ የአንድን አገር ወንድማማቾችን አንዱን ለአንዱ ታሪካዊ ጠላትህ ነው ፤ ላንተ ህልውና ከኔ በላይ ላሳር እያለ ሲመጻድቅባቸው የነበሩ የሃይማኖትም ሆነ የብሄር ቡድኖችን ከነጠለ በኋላ ያለ ሃይ ባይ ሲያጠቃ እያየን ነው:: ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች አስር ሺህ በሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ታጭቀዋል:: በቃሊቲ ፣ በጨለንቆ ፣ በዝዋይ ፣ በሸዋ ሮቢት ፣ እና በሌሎችም በይፋ ባልተመዘገቡ የወያኔ ማጎሪያዎች ውስጥ ዜጎች ያለሃጥያታቸው ታስረው ይሰቃያሉ::

ስርዓቱ ዛሬ ላይ በሰፊው በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የመጨረሻውን ዱላ ከማንሳቱ በፊት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የማጥቃቱን ስራ ሙሉ አቅሙን አሳርፎ ሰርቷል:: ከኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በቀር በጉዳዩ ብዙም ግድ ያለው አልነበረም:: ነገ ደግሞ ተረኛ የካቶሊካዊት ወይም የሌላ ወንጌላውያን ቤተክርስቲያናት ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት አይከብድም:: ይህን ዘረኛ እና ከፋፋይ ስርዓት በመታገስ እና በማስታመም የትኛውም የህብረተሰብ ክፍል ነገ ጥቃት ተቀባይ ሊሆን አይገባም::

ስለወያኔ ማንነት ይኸው ለአመታት የተናገርኩት አንድ በአንድ ጊዜውን እየጠበቀ ሲፈጸም አየን:: አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ ኢትዮጵያውያን በአንድ ድምጽ በቃ የሚሉበት ጊዜ ላይ ደርሰናል:: የለውጥ ጊዜ እየቀረበ ነው:: ኢትዮጵያውያን አይን ለአይን ተያይተው ፤ ልብ ለልብ ተግባብተው ይህንን ዘረኛ እና ፋሺስታዊ ስርዓት ከዚያች ቅዱስ አገር የሚያጠፉበት ጊዜ በእውነትም እየቀረበ ነው:: ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሲሰሩ ምን ማድረግ እንደሚችሉ እስከ አፍንጫው በታጠቀው የወራሪው የፋሺስት ኢጣልያ ጦር ላይ የተቀዳጁትን የአድዋውን ድል ማስታወሱ ብቻ በቂ ነው::በአዲስ ተስፋ ለህልውናቸው እና ለቀጣይ ትውልድም የምትበቃ አገር እና መንግስት ለማቆም ሊሰሩ የሚገባበት ወቅት እየመጣ ነው:: በመጨረሻም ከሰሜን እስከ ደቡብ ፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ:: እስላም እና ክርስቲያን ሳይሉ ፤ ኦሮሞ ፣ አማራ ፣ ትግሬ ፣ ጉራጌ ፣ ወላይታ ፣ አገው ፣ አፋር ፣ ቤኒሻንጉል ፣ ስልጤ ፣ አደሬ ነኝ ብለው ወያኔ በሰፋላቸው የዘረኝነት ወጥመድ ውስጥ ሳይወድቁ እጅ ለእጅ ተያይዘው ለወሳኝ የፖለቲካ ለውጥ እንዲሰሩ ጥሪዬን አስተላልፋለሁኝ::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

ገብረመድህን አርዓያ

ፕርዝ፣ አውስትራሊያ

http://ethioforum.org

posted by Tseday Getachew

ግጭቱን ማን ለኮሰው? (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ቀኑ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 22 1998 ዓ.ም፤ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ገደማ… አንድ የከተማ አንበሳ አውቶብስ ተሳፋሪ ሳይጭን ከመርካቶ ተነስቶ ወደ ጎማ ቁጠባ አቅጣጫ በባዶ እየከነፈ ቁልቁል ወርዶ ..ተ/ሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን አደባባይን ከዞረ በኋላ ጥግ ይዞ ቆመ። ሹፌሩ አውቶብሱን ገትሮ ወዲያው ከአካባቢው ጠፋ። ለሁለት ሰዓት ገደማ አውቶብሱ እንደተገሸረ ቆየ።…በዚህ ቅፅበት አንዲት ነጭ ቶዮታ ፒካፕ (ታርጋ የሌላት ወይም ያለጠፈች) ከሱማሌ ተራ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየከነፈች ከመጣች በኋላ < በላይ ተክሉ ኬክ> ቤትን አለፍ ብላ ቆመች። ከሹፌሩ ጎን ሲቪል የለበሰና ኮፍያ ያጠለቀ ሰው የተቀመጠ ሲሆን ከመኪናው ጋር ከተገጠመው ሬዲዮ መገናኛ በተጨማሪ ሁለት ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ይዟል።… 25 ወጠምሻዎች፣ ሁሉም ረዘም- ወፈር ያሉ ዱላዎችን፣ ገሚሶቹ ደግሞ ገጀራ እንደጨበጡ እንዲሁም ከመካከላቸው ሁለቱ አነስተኛ ጀሪካን እንደያዙ…ከመኪናዋ ዘለው ወረዱ። ሁሉም የተቀዳደ ተመሳሳይ ድሪቶ አጥልቀዋል፤ « አደገኛ ቦዘኔ» መሆናቸው ነው። ነገር ግን « ሆን ተብሎ » የተዘጋጀ ድሪቶ እንደሆነ የሚያሳብቀው ….በግልፅ የሚታየው የሁሉም ፈርጣማ ጡንቻ ከጥሩ እንክብካቤ ጋር በስፖርት የዳበረና ወታደራዊ አቋም እንዲይዝ ተደርጎ የተገነባ መሆኑ ነበር።
ከመኪናዋ ዘለው ከወረዱ በኋላ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ « አትነሳም ወይ…አትነሳም ወይ …ወያኔ…ወያኔ..» እያሉ በመጮህ አንበሳ አውቶብሱን ተጠጉ። በያዙት የብረት ዱላና ስለታማ ገጀራ አውቶብሱን እንክትክቱን ካወጡ በኋላ በያዙት ነዳጅ አርከፍክፈው አቃጠሉት፤…ተመሳሳይ ጩኸትና ቅስቀሳ እያሰሙ ሽቅብ ወደ ሲኒማ ራስ አመሩ። ነጯ መኪና ከኋላ ደርሳ ሁሉንም ጫነች…ከዛም ወደፊት በፍጥነት እየካለበች አዲስ ከተማ ት/ቤት አካባቢ ደረሰች። ወጠምሻዎቹ ..የ <አትነሳም ወይ…> ቅስቀሳቸውን ሲቀጥሉ..እግረመንገዳቸውን በቅርብ ርቀት የሚገኘው የቴሌ መ/ቤት ላይ ድንጋይ በመወርወርና ከደጃፍ ቆመው የነበሩ ሁለት መኪኖችን መሰባበር ይዘዋል። ከዚሁ ጐን ለጎን በመ/ቤቱ ግቢ የታጠቁ ፌደራል ፖሊሶች ከድራማው መጀመር ቀደም ብሎ እንዲገቡ ተደርጎ ነበር። ያ ድርጊት ወይም ድራማ ሲፈፀም አይተው እንዳላዩ በማለፍ ቀጣዩን ይጠብቁ እንደነበረ በሰአታት ልዩነት አፈሙዝ በንፁሃን ላይ ሰድረው ይወስዱት የነበረው የጭካኔ እርምጃ በቂ ማመላከቻ ነበር፤ ዘግይቶ የሆነውም ይኸው ነው።..
በሰኔ ወር ግድያ ሲፈፀም በመጀመሪያ ኢላማ የነበረው ይህ ት/ቤት ነበር፤ በዛ ድርጊት ገና ያልሻረ ቁስል አለ። በሌሎች አካባቢዎችና ከተሞች የነበረው የተዳፈነ የተቃውሞ ቁስል ከዚህ የተለየ አልነበረም። በሕወሐት/ኢህአዴግ አስተዳደር የተንገሸገሸው ሕዝብ..እንኳን ቀዳዳ አግኝቶ ቀርቶ እንዲሁም፥ ትንሽ ነገር ቁጣውን እንደሚያገነፍለው ግልፅ ነበር። የተሰረቀ ድምፁን ለማስከበረም በፅኑ ይፈልጋል። ..በዚሁ መሰረት በአዲስ ከተማ ተማሪው ከአካባቢው ህዝብ ጋር በአንድነት ሆኖ ..<በተለኮሰው> ተቃውሞ ውስጥ ሰተት ብሎ ገባበት።..የተዳፈነው የሕዝብ እሳት በተለያዩ አቅጣጫዎች እየተዛመተ ሔደ።…..
ያቺ ነጭ መኪና <ሴራዋን> ከውና በጎጃም በረንዳ በኩል ወደ ግራ ታጥፋ እየከነፈች…አባኮራን ሰፈርን እያሳበረች በዮሃንስ ቤ/ክ አድርጋ ወደ ሰሜን ሆቴል አመራች።.. <ቅልቦቹ> ተመሳሳይ የተቃውሞ ድራማ አቀጣጠሉ። ከዚህ በተጨማሪ መንግስት በቦዘኔነት <ሽፋን> ያሰማራቸው ቅልብ ሃይሎች በኮልፌ ቀራንዮ አካባቢ አሰማርቶ ተመሳሳይ <ድራማ> እያቀጣጠለ ነበር። ..የተቃውሞ እሳት የጫረችው ነጯ ቶዮታ ..የማሳረጊያ ግዳጇን በሰሜን ሆ/ል አካባቢ ከተወጣች በኋላ ወጠምሻዎቹን ጭና ቁልቁል በመውረድ ወደ ማእከላዊ ወንጀል ፖሊስ መምሪያ ቅጥር ግቢ ነበር ሰተት ብላ የገባችው። በዚች መኪና ከፊት ተቀምጦ ትእዛዝ በመስጠትና ከበላይ አለቆቹ ጋር መረጃ ልውውጥ በማድረግ ሴራውን ሲመራና ሲያከናውን የነበረው ግርማይ (በቅፅል ስሙ ማንጁስ) የተባለ የሕወሐት አባልና በፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ የደህንነት ሃላፊ እንደሆነ በወቅቱ ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ከዚህ ባሻገር በአንዱ ስልክ ከጠ/ሚ/ሩ ጋር በቀጥታ ይገናኝ እንደነበረ ተረጋግጦዋል። (በነገርራችን ላይ ስለዚህ ጉዳይ መረጃው ለህዝብ ሳይደርስ ጋዜጦች ወዲያው ተዘጉ)
Ethiopian-Police-2005-flickr-aheavens-590x394
…ባጠቃላይ በዚህ መልክ በገዢዎቹ ሆነ ተብሎ በተለኮሰው የጥፋት <ሴራ> በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን በአደባባይ በጥይት እንዲቀጠፉ ሲደረግ፣ በ10ሺህ የሚቆጠሩ ደግሞ እስር ቤት ተጋዙ። የነመለስ/በረከት ቀጣዩ <ኢላማ>  የቅንጅት አመራሮችንና ደጋፊዎችን፣ጋዜጠኞችን እንዲሁም ሌሎች ወገኖችን ማሰርና ማሰቃየት ስለነበር፥ ያሰቡትን ተግባራዊ አድርገዋል። ከትግራይ ሃውዜን የጀመሩት ህዝብን በጅምላ የማስፈጀት አረመኒያዊ የሴራ ተግባራቸው፥ በአርባባ ጉጉ፣ በበደኖ፣ ትግራይ ሆቴል(ፒያሳ)፣ ጋምቤላ …እያለ በመቀጠል የ97/98 ምርጫን ተራምዶ እነሆ በህዝበ ሙስሊሙና በአማራ ተወላጆች ላይ ቀጥሎ ይገኛል። ከቤኒሻንጉል እንዲፈናቀሉ የተደረጉት የአማራ ተወላጆች በተራ የወረዳ ካድሬዎችና ሹሞች ትእዛዝ እንደማይፈፀም በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል። ለዚህ ማስረጃው በጋምቤላ አሰቃቂ ፍጅት እንዲደርስ የተደረገው በወቅቱ የፌደራል ጉዳዮች ሹማምንት በነበሩት አባይ ፀሃዬና በምክትላቸው ዶ/ር ገብረአብ ባርናባስ ቀጥተኛ ትእዛዝ ሰጪነት እንደሆነ የተረጋገጠና በወቅቱም የሁለቱ የሕወሐት ሹሞች ስም ጭምር ተጠቅሶ በኢትኦጵ ጋዜጣ ይፋ መደረጉ ነበር። እንዲያውም አባይ ፀሃዬ በግምገማ ላይ ዶ/ር ገ/አብን ጥፋተኛ ከማድረጋቸው በተጨማሪ < አብሬው መስራት አልችልም፤ ስለዚህ በአስቸኳይ ይነሳልኝ> በማለት የጋምቤላውን ፍጅት በዶክተሩ ላይ ከመደፍደፋቸው ባሻፈር ለ/ጠ/ሚሩ ጥያቄ አቅርበው ይኸው ተፈፀሚ ሆኗል። …ይህ በሆነበት ሁኔታ በቤኒሻንጉል በወገኖቻችን ላይ የደረሰውና ሆን ተብሎ እንዲደርስ የተደረገው መሰሪ ተግባር ከሕወሐት/ኢህአዴግ ቱባ ሹማምንት እውቅና ውጭ ብቻ ሳይሆን የነርሱ ቀጥተኛ ትእዝዛ ያለበት እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል።
በመጨረሻም ፥ በህዝበ ሙስሊሙ እየተካሄደ ባለው ሰላማዊ የመብት ጥያቄና ተቃውሞ ውስጥ የተስተዋለው ጉዳይ፥ ህዝብ ምን ያክል ገዢዎቹን በአስተሳሰብ በልጦ እንደሄደ የሚያመላክት ጭምር ነው። ይኸውም በአንዋር መስጊድና ሰላማዊ ተቃውሞ በሚሰማባቸው አካባቢዎች አንበሳ አውቶብሶችን ሆን ተብሎ በማቆም ሙስሊሙ እንዲሰብራቸው በገዢዎቹ ሲሞከር ታይቶዋል፤ ገዚዎቹ እንዳቀዱት አውቶብሶቹ ሲሰባበሩ… የ97/98 ድራማ ለመድገምና በለመዱት ጭካኔ በጥይት የጅምላ ግድያቸውን ለመተገበር ነው። የሃይማኖቱ ተከታዮች ግን « አንሰብርም….አንሰብርም…» እየሉ በአንድ ድምፅ የነበረከትን የሴራ ድራማ በማክሸፍ ለመብታቸው መቆምንና ሰላምዊ ጥያቄ ማቅረብን ነው የቀጠሉት። ህዝብ ምን ያክል ቀድሟቸው እንደሄደ ጥሩ ማሳያ ነው።
posted by Tseday Getachew

ESAT Abay bond Protest in Norway April 2013 video

http://ethsat.com/video/esat-abay-bond-protest-in-norway-april-2013/

posted by Tseday Getachew

በአባይ ስም ዶላር ለመሰብሰብ በሲውዲን የወያኔ አምባሳደር ወደ ኖርዌይ ተጉዛ ለ ሁለተኛ ጊዜ በ ኦስሎ ውርደት ተከና… watch video

posted by Tseday Getachew

ኦባማ አርፍደው ወደ ኢትዮጵያ?

“በአፍሪካ ብዙ ስራ አለን” ጆን ኬሪ
africa-china-us

በአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ከሚገኙት የተለያዩ እንግዶችና ባለስልጣናት በተጨማሪ አራት ታላላቅ መሪዎች እንደሚገኙ እየተነገረ ነው። በዋናነት የሚጠቀሱት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ኦባማ ሲሆኑ፣ የቻይና አቻቸውም ዋናውና ታላቁ እንግዳ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ባለፈው ረቡዕ ለአሜሪካ ኮንግረንስ ኮሚቴ የተናገሩትን በመጥቀስ ዜናውን የላኩልን ክፍሎች እንዳሉት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ሊያመሩ ይችላሉ።

ውጪ ጉዳይ ሚ/ሩ ኦባማ ኢትዮጵያ ስለመሄዳቸው ፍንጭ ቢሰጡም ስለጉዞው ዝርዝር አለመናገራቸው ታውቋል። የቻይና በአፍሪካ ሚና መጉላት ውሎ አድሮ የጠዘጠዛት አሜሪካ፣ በመጪው ወር በሚካሔደው የአህጉሩ 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ በፕሬዚዳንቷ ለመወከል መወሰኗ “ጉባኤ አድማቂ” አሰኝቷታል።

“በአፍሪካ ብዙ የምንሰራው ስራ አለን” ሲሉ የተናገሩት ኬሪ “በድግሱ” ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል። እየተጣጣመ የመጣው የአፍሪካና የቻይና ፍቅር እንዲሁም ቻይና በአፍሪካ ያላት ሰፋ ያለ ኢንቨስትመንት ለአሜሪካ አሳሳቢ ከመሆኑ ባሻገር ቻይና የምትከተለው የንግድ ስልት በአጠቃላዩ ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ውጪ ጉዳይ ሚ/ር ኬሪ አልሸሸጉም፡፡ ዝርዝር ከመስጠት ቢቆጠቡም ጉቦ፣ ሙስና፣ አምባገነኖችን መርዳት በማለት የተወሰኑትን በግልጽ ከመጥቀስ አላለፉም፡፡

ኦባማም ወደ ኢትዮጵያ የሚያቀኑበት ጉዳይ አሜሪካ በአፍሪካ ለምትከተለው አዲስ እቅድ ማጠናከሪያ ካስማ ለመቸንከር እንደሆነ አብዛኞች ይስማሙበታል። “ቻይናን በቅርብ ሆኖ መቆጣጠር” በሚለው መርህ  የአፍሪካን አምባገነኖች ወታደራዊ ድጋፍ በመስጠት ልቡናቸውን የመስለብ እቅድ ይዛ እየሰራች ያለችው አሜሪካ፣ የቻይናና የአፍሪካ ግንኙነት “የፓለቲካ እባጭ” የሆነባት ቻይና ድፍን የአፍሪካ መሪዎችን ቤጂንግ ጋብዛ ወዳጅነቷን አደባባይ በማውጣት ጸሐይ ካስመታቸው በኋላ ነበር። በርካታ መረጃዎችም በዚሁ ዙሪያ ቀርበዋል።

በቤጂንጉ ጉባኤ ቻይና ዶላር ለሚናፍቁት የአፍሪካ መሪዎች ብድር ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ፣ የንግድ፣ የኢንቨስትመንት፣ የቴክኖሎጂ፣ የመንገድ ግንባታ፣ የተለያዩ ርዳታዎች ለማድረግ፣ ከዚህም በላይ አምባገነኖች የስለላ መዋቅራቸውን እንዲያደራጁ የሚያስችላቸው በገሃድ እንዳይሰራጩ የተከለከሉ የአፈና መሳሪያዎችን ጭምር ለመስጠት ቃል ገብታ አፍሪካን የገበያዋ ሳሎን ስታደርግ አሜሪካና አውሮፓውያኖቹ ደነገጡ፤ ታመሙ።

በተመሳሳይ ቻይና ዘይትና የተለያዩ ማዕድኖችን ከአፍሪካ በመዛቅ የገበያ ድሯን ዘርግታ አፍሪካን ተጣባቻት። ዜጎቿንና የንግድ ተቋሞቿን አፍሪካ ምድር በትና ከላይም ከታችም ተቆጣጠረቻት። ከዚህ በኋላ ነበር መቀደሟ ያሳሰባት አሜሪካ ቻይናን በቅርብ መከታተል በሚል አዲስ ስልት የነደፈችው።

ባለሙያዎችና የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት አሜሪካ በኢኮኖሚና በገንዘብ ድጋፍ የአፍሪካን ሆዳም መሪዎች በማባበል ቻይናን ለመፎካከር በዛሬው ጊዜ አይቻላትም፤ በገሃድ እከተለዋለሁ የምትለውን ግብዝ ፖለቲካ ያበላሽባታል። እንደውም አታስበውም። ለዚህ ይመስላል የአፍሪካ አገሮችን ወታደራዊ ሃይል በማሰልጠን፣ በማደራጀት፣ በማስታጠቅ፣ የየአገራቱን ወታደራዊ እዝ ከበላይ ሆኖ በመምራት የቻይናን እንቅስቃሴ ለመበርበር የተንቀሳቀሰቸው። (ከዚህ በፊት “የኦባማ አስተዳደር መጪው የአፍሪካ ዕቅድ” በሚል የጻፍነውን እዚህ ላይ ይመልከቱ)

አምባገነኖች የመከላከያ ኃይላቸውን እንደ ብረት ለማጥበቅ ካላቸው የጸና ፍላጎት አንጻር አሜሪካ የነደፈችው ስልት የተዋጣለት እንደሆነ የሚናገሩ ክፍሎች “አሁን አሜሪካ ወታደራዊ ሃይልን ለማጠናከር በሚል ወደ አፍሪካ የገባችበት ስልት፤ ከአፍሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች እውቅና ውጪ የሚፈጸም ተግባር ስለሌለ መረጃ የማግኘት አቅሟ የቻይናን መስኮት በርግዳ ሳሎኗን የማየት ያህል ነው” ይላሉ፡፡

አሜሪካ አሁን ባለችበት ደረጃ አፍሪካ 50ኛ ዓመት በዓል ስታከብር በይፋ ባይረጋገጥም ኦባማ የመገኘታቸው ሚስጥር ከፖሊሲያቸውና ቻይናን በቅርብ ሆኖ ከመቆጣጠር አዲሱ ስልታቸው በመነሳት እንደሆነ የማያሻማ ነው። በጉባኤው ላይ አራት ከፍተኛ የአገር መሪዎች እንደሚገኙ የኢህአዴግ አንደበት ፋና ጠቁሟል ግን ዝርዝር አላቀረበም። ጆን ኬሪ “ከአፍሪካ ጋር ባለን ግንኙነት ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመሙላት ከአህጉሪቷ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማሻሻል እንሰራለን” ማለታቸውን ፋና ምንጭ ሳይጠቅስ አስፍሯል።

ፋናም ሆነ ሌሎች የመንግስት ሚዲያዎች ይፋ ባያደርጉትም የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ባለስልጣናትና የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የስብሰባው ታላቅ እንግዳ እንደሚሆኑ ፖለቲከኞች ቅድመ ግምታቸውን አኑረዋል። በኢህአዴግ ጉባኤዎች ላይ የክልል አንድ ልዩ ዞን ተወካይ እስኪመስል ልዑክ በመላክና የቻይንኛ ቀረርቶ በማሰማት ተሳትፎ ያላት ቻይና ለአፍሪካ ህብረት ታላቅ ስጦታ ማቅረቧ የሚታወስ ነው።

የአፍሪካ ኅብረትን ዘመናዊ ህንጻ በራስዋ ወጪ ያስገነባቸው ቻይና በቤቷ፤ ኦባማም ከተገኙ በእንግድነት የኅብረቱን የምስረታ ዘመን አስመልክቶ ቻይና በነጻ ገንብታ ባስረከበችው ህንጻ ውስጥ ሆነው ህንጻውን እያደነቁ ይደሰኩራሉ።

http://www.goolgule.com/obama-in-africa/

posted by Tseday Getachew

አባይ ወልዱ እና በደል በትግራይ

ኣባይ ወልዱ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በህዝብ ላይ ጨካኝ እና ዘግናኝ እርምጃ እየወሰዱ የልማት ሰራዊት በማደራጀት የ 5 ኣመት እድገት እና ትራንስፎርሜሽን ግቡ እንዲመታ እናደርጋለን፤ የሚሊኒየም ግብ ካስቀመጥነው ጊዜ ገደብ ኣስቀድመን እንፈፅማለን ብለውናል:: ኣባይ ወልዱ ኣለቃ ፀጋይ በርሀን አስወገደው ስልጣኑን ከተቆጣጠሩ በኋላ በክልሉ እጅግ ብዙ ፀረ ዲሞክራሲ የሆኑ ድርጊቶችን ፈፅመዋል። እንደ ኣብነት ለመጥቀስ በሚያዚያ26/27/2005 ዓ/ም በትግራይ ደቡባዊ ዞን ወረዳ ሞኮኒ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ 7000 ኣባዎራዎች ከ ኣፂ ሃይለስላሴ እስከ ዘመነ ኣገዛዝ ኢህአደግ ሲኖርበት የነበሩ ከ 3 ትውልድ በላይ ጊዜ የኖሩበት ተተኪ

Read more  http://www.ethiomedia.com/abc_text/tigrai_under_abai_woldu.pdf

posted by Tseday Getachew

የኦነግ ግልብጥ የሌንጮ ለታ ፀረ_ ኢትዮጵያ ሕዝብ ሸፍጥና የለበጣ አቋም

 

ሌንጮ ለታ፥ የተባለው አንጋፋ የኦነግ ግልብጥ ዩሃንስ ለታ ተብሎ የሚታወቅ የወለጋ ወይም የዳሞት ክፍለ ሃገር ሰው ነው። (ወለጋ የጥንት ስሙ ዳሞት ነበር የሚባለው)። ይህ ሰው የፖለቲካ ክላውት ወይም ወታደራዊ ጉልበት ፈጽሞ የሌለው እንደ ስብሃት ነጋ እንደፈለገው የሚቀደድና የሚናቆር ችግር ፈጣሪ ልግመኛ ደማጐግ ነው።

Read more:  http://www.ethiolion.com/Pdf/04242013Doc1.pdf

posted by Tseday Getachew

የህወሀት ደህንነቶችን ጤና የነሳው የፌስቡክ ጦማር

 

 

 Ethiopian blogger Abraha Desta from Tigry, Mekele
 
በህወሀት/ኢህአዴግ ውስጥ መግባባት ጠፍቷል፣ የወያኔ ቁንጮዎች ወዴት እንደሚሄዱ አያውቁም። እንደው በደፈናው “የመለስ ዜናዊ ራዕይ” ይበሉ እንጂ ራዕዩን እነርሱም አያውቁትም። ካድሬውም ሹማምንቱም እርስ በርስ ተናንቋል። በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ሁኔታቸውን ህዝብ እንዳያውቅባቸው እያደረጉ ያሉት ጥረት እምብዛም የሰራ አይመስልም። የሙስሊሞች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው፣ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ግፍ ህዝቡን ከዳር እስከዳር አስተባብሯል/ቀስቅሷል፣ ምርጫውን ምርጫ ለማስመሰል ያደረጉት ጥረት አልተሳካም፣ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ አለማቀፉ ማህበረሰብ እና ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጫና ፈጥረዋል። ለዚህም ይመስላል የወያኔ የደህንነት ሹሞች የሀሰት ዜናዎችን በፌስቡክ እያሰራጩ ፋታ ለማግኘት የሚጣጣሩት። ከዚህ በታች አብረሃ ደስታ ከመቀሌ በፌስቡክ የለቀቀውን ጦማር፣ የህወሃት/ኢህአዴግን ወቅታዊ አቋቋም እንደወረደ አቅርበነዋል። በህወሓት የጉባኤ ኣጀንዳ ዙርያ ስብሰባ ሊጠራ ነው

አብረሃ ደስታ፣ ከመቀሌ

ከኢህኣዴግ ጉባኤ በኋላ መሪዎቻችን (ከበፊቱ ብሶባቸው) መግባባት ኣቅቷቸዋል። በፌደራል ደረጃ የሚደረጉ ስብሰባዎች ያለ ዉጤት ይጠናቀቃሉ። ለምን ኣይግባቡም? (‘ቀሽም ጥያቄ’)። የሚያግባባ ነጥብ የላቸውማ። ድሮ (ከ‘ባለራእዩ መሪ’ ዕረፍት በፊት) ሁሉም ነገር እሳቸው ይሰሩት ስለነበር) በመሪያቸው ነበር ‘የሚግባቡት’ (አብረው የሚጓዙ)። በሰው ‘ይግባባሉ’ (ሌላ ሊያግባባቸው የሚችል ሓሳብ ወይ መርህ አልነበራቸውም፣ የላቸውም)። አሁን ታድያ እንዴት ይግባቡ?
‘ባለራእዩ’ ሰውዬ መመርያ ይሰጣል፣ ‘ፖሊሲ ነው ተግብሩት’ ይላቸዋል፣ እነሱም እሱ የተናገረውን ‘ቃል’ እየደገሙ (ከላይ እስከ ታች) ይዘምራሉ። ስሕተት መሆኑ (ሊተገበር የማይችል መሆኑ) ሲረዱ ‘ስሕተቱ ያለው አፈፃፀም ላይ ነው’ ብለው ራሳቸው ያፅናናሉ። ህዝቡ በማይፈፀሙ ፖሊሲዎች ተስፋ እንዳይቆርጥ መሪዎቻችን ሁሌ ስለ አዲስ ፖሊሲ ወይ አሰራር ይሰብካሉ። ሁሌ ስለ ‘አዲስ ኣሰራር’ ወይ ዕቅድ ሲወራልን ለውጥ የመጣ ያህል እንዲሰማን ለማድረግ ያህል ነው።
አሁን ሰውየው ‘አርፈዋል’። ለተከታዮቻቸው የተውት መርህ መሰረት ያደረገ የፖለቲካ አቅጣጫ የለም። የኢህኣዴግ ካድሬዎች ታድያ አሁን የሚግባቡበት ቋንቋ የላቸውም። የኣምስት አመቱ ‘የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን አቅድ’ ይዘት ወይ መሰረታዊ ፅንሰ ሓሳብ ምን እንደሆነ የሚያውቀው የለም። በዚህ ጉዳይ ተደጋጋሚ ውይይት ተደርጎ ያለ ዉጤት ተበትነዋል። (ዕቅዱ ግን ድሮውም ቢሆን ምንም የሚጨበጥ ሓሳብ አልነበረውም ….. የሚሰማን አጣን እንጂ)። ዕቅዱ ‘Ambitious’ ብለን በተደጋጋሚ አሳስበን ነበር (‘ሊተገበር የሚችል ዕቅድ አሳዩን’ ብለን ተማፅነን ነበር)። አሁን ግን ካድሬዎቹ ራሳቸው (በተለያዩ ስብሰባዎች) ‘የተለጠጠው (ዝተለጠጠ)’ ዕቅድ ማለት ጀምረዋል።
በኢህኣዴግ ደረጃ ያለው ችግር የስልጣን ሽኩቻ ነው (የባለስልጣናቱ ዓላማ ስልጣን ነው)። ህወሓቶች በኢህኣዴግ የነበራቸው ሚና ማጣት አይፈልጉም። ግን ይህንን ሚና ሊጫወት የሚችል ደህና ሰው የላቸውም። (ዓቅም የነበራቸው የፓርቲው ሰዎች በተለያየ ምክንያት እንዲጠፉ ተደርገዋል ) ። ራሳቸው በራሳቸው ችግር ፈጥረው (በሁለት ተከፍለው፣ ጓደኞቻቸው ኣባረው) ተዳክመዋል (አሁን ትግራይ እንኳ መቆጣጠር በሚችሉበት ሁኔታ ኣይገኙም)።
በኣሁኑ ግዜ በኢህኣዴግ ዉስጥ የተሻለ የስልጣን ተፎካካሪ ብአዴን ነው። ግን ብአዴን ከሌሎች ሦስቴ የኢህኣዴግ አባል ድርጅቶች ተቀባይነት የለውም። የህዝብ ድጋፍም በሰፊው የለውም። የሚጠበቀው ያህል (ኢህኣዴግ ለመቆጣጠር የሚያስችል) ጠንካራ አባላትም የሉትም። ግን በኢህኣዴግ ስርወ መንግስት የህወሓት አልጋ ወራሽ ብአዴን ይመስላል። በህወሓትና ብኣዴን ከፍተኛ ውዝግብ አለ።
ኦህዴድ በኢህኣዴግ ዉስጥ በጣም ያኮረፈ ቡድን ነው። የተለያዩ ምክንያቶች እየደረደረ ስልጣን ለኦህዴድ መሰጠት እንዳለበት ይወተውታል። ግን ኦህዴድ ሁለት ችግሮች ተደቅነውታል። (አንድ) በኦህዴድ ውስጥ መግባባት ብሎ ነገር የለም። (ሁለት) በሌሎቹ የኢህኣዴግ አባል ድርጅቶች እምነት ባለፈው የኦህዴድ ጉባኤ ወደ ሓላፊነት የወጡ ሰዎች ከኦነግ ጋር ግንኙነት አላቸው። በነሱ እምነት ኦነግ የኦህዴድ መዋቅር ተቆጣጥሮታል። ስለዚ ለኦህዴድ ስልጣን መስጠት እጅግ ያስፈራቸዋል።
ሌላው ደኢህዴን ነው። ደኢህዴን ጠንካራ ኣይደለም። በሁለት ቡድኖች ተከፍሎ ትርምስ ላይ ነው። ከቡድኖቹ አንዱ ከህወሓት ጎን መሰለፍ ይፈልጋል። ብቻውን (ህወሓት ከዚህ በፊት እንዳደረገው) የኢህኣዴግ ስልጣን መቆጣጠር የሚችልበት ዕድል የለውም። ህወሓትም ቢሆን ደካማ ሁነዋል። ዶር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በኢህኣዴግ ጉባኤ ሲናገር “በቃ ወድቀናል” ብሎ ነበር። ይሄ ከህወሓት ጋር መጠጋት ለሚፈልግ ቡድን ራስ ምታት ነው።
ህወሓቶች ጉዳዩ ኣስጨንቋቸዋል። የነ አባይ ወልዱ ቡድን የነ አርከበ ዕቁባይ ቡድን ካባረሩ ወዲህ የባሰ ንትርክ ዉስጥ ገብተዋል። እርስበርሳቸው አይግባቡም፣ ይናናቃሉ። የኣሁኑ መሪዎች ማንም አያከብራቸውም። በህወሓት ጉባኤ የተሳተፉ አባላት በነ ኣባይ ወልዱ የተመለመሉ ቢሆኑም በጉባኤው ወቅት በነኣርከበ የተወሰደው እርምጃ ግራ አጋብታቸዋል። ጉባኤተኞቹ ‘እነ ኣርከበ ከውጡ ህወሓት ከማን ጋ ትቀራለች?’ የሚል ጥያቄ ነበራቸው።
የፓርቲው ሊቀመንበር የሚመረጠው (በፓርቲው ደንብ መሰረት) በጠቅላላ ጉባኤ ነው (በቀጥታ ግን አይደለም)። እንዲህ ነው። ጉባኤተኞቹ አርባ አምስት የፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ይመርጣሉ። በውጤቱ (ባገኙት ድምፅ) መሰረት በቅደም ተከተል (የተመረጡት ሰዎች) ስማቸው ይገለፃል። የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት የፓርቲው ስራ ኣስፈፃሚ (ፖሊት ቢሮ) ይመርጣል። ፖሊት ቢሮ አባላት ደግሞ የፓርቲው ሊቀመንበርና ምክትል ይመርጣሉ።
በምርጫው ከፍተኛ ስልጣን ያለው (በመርህ ደረጃ) ጉባኤተኛው ስለሆነ ከፍተኛ ድምፅ ያለው (By Default) የፓርቲው ሊቀመንበር ይሆናል። የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ይሄንን አውቀው ባገኙት ድምፅ መሰረት ዘጠኙ (Top Nine) ለፖሊት ቢሮ ይመርጣሉ። ፖሊት ቢሮ አባላትም በተሰጠው ድምፅ መሰረት ከፍተኛውን ያገኘ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርገው ይመርጣሉ።
በጉባኤው የተሳተፉ አባላት ሊቀመንበር (ከተሰጣቸው አማራጭ) አድርገው የመረጡት ዶር ደብረፅዮን ነበር። ዶር ደብረትፅዮን የኣንደኛነት ድምፅ ሲያገኝ አባይ ወልዱ ሁለተኛ ነበር። (ደብረፅዮን ለኣባይ በ23 ድምፅ ይበልጠዋል)። ውጤቱ ግን ጉባኤተኞቹ እንደጠበቁት ኣልሆነም። የፖሊት ቢሮ አባላት ሁነው የተመረጡት (top nine) ዘጠኙ ኣልነበሩም። በውጤቱ መሰረት የህወሓት ሊቀመንበር መሆን የነበረት ዶር ደብረፅዮን ሲሆን ዉጤቱ ተገልብጦ አቶ ኣባይ ተመረጠ። ይሄ የሆነው የኣቶ አባይ ቡድን አብዛኛው የማእከላዊ ኮሚቴ ወንበር መያዝ በመቻሉ ነበር። (ጉባኤተኞቹ የነኣባይ ቡድን ደጋፊዎች ሲሆኑ አባይ ፓርቲው ይመረዋል ብለው ግን አያምኑም። ስለዚህ ጉባኤተኞቹ ደብረፅዮን ሊቀመንበር አድረገው መርጠው እንደሄዱ ነው የሚያውቁ)።
ይሄን ዉሳኔያቸው ታድያ በጉባኤተኞቹ ጥሩ ስሜት አልፈጠረም። የኣሁኑ መሪዎች የህዝብ አመኔታም የላቸውም። ይሄን ችግር ለመፍታት ሲሉ ከነገ እሮብ (ሚያዝያ 16, 2005 ዓም) ጀምሮ ጉባኤው በተመለከተ በመላው ትግራይ (በየደረጃው ከከፍተኛ የክልል ቢሮዎች ጀምሮ እስከ ቀበሌ አስተዳደር ድረስ) ስብሰባ እንደሚደረግ ታውቋል። ለስብሰባው ማስኬጃ ብዙ ሚልዮን ብር ተመድበዋል (ከመንግስት ካዝና መሆኑ ነው)።
ኣየ ህወሓት! በቃ ስብሰባ ነው። እኔ ደግሞ ስብሰባ ስጠላ! (እንኳን የህወሓት አባል አልሆንኩ)።
 
posted by Tseday Getachew

Zambia court ordered stiff penalties against 50 Ethiopian refugees

(PostZambia) – A Zambian court has fined 50 Ethiopians KR400.00 each or in default serve a one and half year imprisonment with hard labor for failing to report to an immigration officer.

Appearing before magistrate Shadreck Chanda for judgment on Friday were Sisay Asefa and 49 others aged between 11 to 37 who stood charged with one count of failing to report to an Immigration officer at Nakonde Border Post contrary to section 12(1) and 51(1) of the immigration and deportation Act number 18 of the Laws of Zambia.

It was alleged that on March 29 this year, 50 immigrants jointly and whilst acting together, being persons entering Zambia through Nakonde border, failed to report to the Immigration officer as required by law.

The court found the 50 prohibited immigrants guilty upon their own admission of guilty and convicted them accordingly.

Passing judgment, magistrate Chanda said the court took note of what the 50 had said in their mitigation, adding that he would have only deported them to their country of origin but that the offence committed was serious as it borders on national security.

He said the illegal immigrants knew very well that entering any country without legal documentation and failing to report to an Immigration officer is an offence saying he was therefore ordering them to pay a fine of KR400.00 each or in default serve an 18 months imprisonment with hard labour.
Magistrate Chanda said the government of Zambia would not allow or tolerate people entering the country without proper papers and warned the 50 prohibited immigrants that if they repeat the same offence, the court would not be lenient towards them.

In mitigation, the 50 asked the court to exercise maximum lenience on them saying they were wrong to have entered Zambia without first reporting to an Immigration officer at the border post.
They told the court that they have suffered a lot and that they wanted to go back to their country to be reunited with their families.

http://www.ethiopianreview.net/

posted by Tseday Getachew

የዕለቱ ዜናዎች » በቤንች ማጂ በተነሳ ግጭት ሶስት ተማሪዎች ቆሰሉ

በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን በሚገኘው ሚዛን 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት በተነሳው ግጭት ሶስት ተማሪዎች መቁሰላቸውና ከሚያዚያ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ ፡፡

እንደ ፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፃ ከሆነ ከሚያዚያ 7 ቀን 2005ዓ.ም. ጀምሮ በትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና አስተዳደር አካላት በተነሳ አለመግባባት ከፍተኛ እረብሻ በመፈጠሩ እንደሆነ ተገልጧል፡፡ ለረብሻው መንስኤው ለትምህርት ቤቱ  ከአሜሪካ በተሰጠው የትምህርት ዕድል የ12ኛ ክፍል የመሰናዶ ተማሪዎች መካከል በተደረገው ውድድር ከሴቶች ተማሪ መድኃኒት ስታሸንፍ ከወንዶች ደግሞ በጀመሪያ ተማሪ ጌታመሳይ ማሸነፉ ከተጠቆመ በኋዋላ በተደረገ የውጤት ማጣራት ሂደት ተማሪ ዮሐንስ ማለፉ መለጠፉ ነው፡፡ ይህንንም ተከትሎ በተለይ የውድድሩ አዘ
ጋጅ ኮሚቴ በወንዶች ተማሪ ዮሐንስና ተማሪ ጌታመሳይ ውድድር ላይ የውጤት አሰራር  ስህተት በመኖሩን  በተማሪዎችና  በትምህርት ቤቱ መምህራንና አስተዳደር አካላት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት መማር ማስተማሩ ሂደት መቋረጡ ተጠቁሟል፡፡

በመጨረሻም በተደረገው የውጤት ማጣራት መሰረት በውድድሩ ያለፈው ተማሪ ዮሐንስ መሆኑንም ምንጮቻችን አስታውሰዋል፡፡

ከረብሻው ጋር በተያያዘ ሚያዚያ 11 ቀን 2005ዓ.ም. በትምህርት ቤቱ አካባቢ ተኩስ መከፈቱና  በተፈጠረ ግጭትም 3 ተማሪዎች ቆስለው ወደ ህክምና ጣቢያ መወሰዳቸው ተረጋግጧል፡፡ ይህን ዜና እስከዘገብንበት ድረስም ትምህርት ቤቱ በፌደራል ፖሊስ መከበቡ ተጠቁሟል፡፡

ይህንንም በሚመለከት የትምህርት ቤቱ ዋና ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ አብዱ ካሣ ስለጉዳዩ ስናነሳላቸው አሁን ስለማልችል ከ30 ደቂቃ በኋላ መልሳችሁ ደውሉ ካሉ በኋዋላ ስልካቸውን በመዝጋታቸው  ምላሻቸውን  ማካተት አልቻልንም፡፡

ምክትላቸው አቶ አበራ ጉልማንም ለማናገር ጥረት ብናደርግም ስልካቸውን ጆሯችን ላይ ዘግተዋል፡፡

http://www.fnotenetsanet.com/?p=4123

posted by Tseday Getachew

Post Navigation

%d bloggers like this: