Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

Archive for the month “March, 2013”

ኢህአዴግን “አድርባይ” አመራሮች አስግተውታል

አባላት “አድርባይነት የመመልመያ መስፈርት ነው” አሉ!!

ኢህአዴግ አመራሮቹን “አድርባይነት የተጠናወታቸው” ሲል ፈረጀ። የከፍተኛ አመራሮች የግምገማ ውጤት የሆነውን ፍረጃ የሰሙ “የኢህአዴግ አባል ለመሆን አንዱና ዋናው መስፈርት አድርባይነት ነው” በማለት አድርባይነትን የፈጠረውና ያስፋፋው ራሱ ኢህአዴግ፣ በተለይም ህወሃት እንደሆነ አመለከቱ።

በባህር ዳሩ የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ ተገኝቶ የነበረ ጋዜጠኛ በምሥጢር የላከው ዜና “አድርባይነት” ኢህአዴግን በሚፈታተን ደረጃ መስፋፋቱ መገለጹ አብዛኞችን የድርጅቱን አባላትን አስገርሟል።

ኢህአዴግን የፈጠረውና ከላይ ሆኖ የሚመራው ህወሃት “ነጻ” አመለካከት የማይወድ፣ የነጻ አስተሳሰብ ባህል የሌለው፣ ራሳቸውን የቻሉ ድርጅቶችን፣ ፓርቲዎችንና ማህበራትን አጥብቆ የሚጠላ፣ ሁሉም ለሱ እያጎበደዱ በሚሰፈርላቸው ቀለብ እንዲኖሩ ሌት ከቀን የሚሰራ መሆኑ እየታወቀ ማንን? ለምንና እንዴት አድርባይ በሚል እንደሚፈርጅ አብዛኞች ግራ መጋባታቸውን የደረሰን ዜና ያመለክታል።

ህወሃት በፈለፈላቸው ድርጅቶችና የአፈና ተቋማቱ አማካኝነት በሂደት የኢትዮጵያን አብዛኛውን ህዝብ “አጎብዳጅ” የማድረግና “አድርባይ” ሆነው የሚኖሩትን ቁጥር ማብዛት ዋናው ስትራቴጂው እንደሆነ እየታወቀ “አድርባይነት” እንዴት ለድርጅቱ በሽታ ሊሆን እንደቻለ ያልገባቸው እንዳሉት “አድርባይነት አስጊ ደረጃ ከደረሰ ህወሃት የለፋበትን ያገኘና በስኬት ጎዳና ላይ ለመሆኑ ማሳያ ነውና ስጋት ሊገባው አይገባም” የሚል የለበጣ አስተያየት መስጠታቸው ተጠቁሟል።

በስብሰባው ላይ በይፋ አስተያየት ከሰጡት መካከል አቶ አባይ ጸሐዬ ይጠቀሳሉ። በህወሃት የመከፋፈል ዘመን ቀደም ሲል ከውህዳኑ ጋር ያበሩ መስለው ሁለት ሳንጃ በመያዝ የተጫወቱት አቶ አባይ አሁን አድርባይ ተብሎ የተፈረጀው የኢህአዴግ አባል በሙሉ ወደ መካከለኛ አመራርነት ከተሸጋገረ አደጋው ከፍተኛ እንደሚሆን ተናግረዋል። ቀደም ሲል አባሉ በተመለመለበት ደረጃ ተግባሩን ሲያከናውን ባግባቡ አለመመዘኑ የአደጋው መነሻ ምክንያት እንደሆነ አመልክተዋል።

ኢህአዴግ አባሎቹ “አድርባይና አጎብዳጅ” እንደሆኑበት የገለጸው ስትራቴጂዎችን የመፈጸም ችግር ስላጋጠመው ነው። በጉባኤው ኢህአዴግን ያስደነገጠው ጉዳይ “አደገ” የተባለው የሰብል ምርት ሪፖርት ጉዳይ በዋናነት የሚጠቀስ ነው። አቶ በረከት በቀጥታ ተጠያቂ ያደረጉት ከፍተኛ ደረጃ ያለውን አመራር ነው። እንደሳቸው አባባል ታላቅ ንቅናቄ ሊፈጥር የሚችል የልማት ሰራዊት ያልተገነባበት ምክንያት ሊገመገም ይገባል።

በአሁኑ ወቅት ሰባት ሚሊዮን የሚጠጉ የተመዘገቡ አባላትን ያቀፈውና የቻይናን ኮሙኒስት ፓርቲ ሞዴል ወርሶ “በመለስ ውርስ ወደፊት” እያለ የሚጓዘው ኢህአዴግ አባላቱ “ፊት እያዩ የሚደፉ” መሆናቸው አደጋ መሆኑ ታምኖ መፍትሄ የተበጀለት ቢሆንም የቁርጠኛነትና በራስ ያለመተማመን ችግሩ ሰፊ ስለሆነ በቀላሉ ሊቀረፍ የሚችል እንዳልሆነ ተመልክቷል።

በተመሳሳይ ጉዳይ ሪፖርተር ባቀረበው ዜና አቶ ስዩም መስፍን “የራሱን የውስጥ ዲሞክራሲያዊ ሕይወት ያላስጠበቀ ካድሬ ወይም አመራር የሕዝቡን መብትና ዲሞክራሲ ሊያስጠብቅ አይችልም። ራሱ ነፃ ያልወጣና እየተሸማቀቀ የሚኖር ካድሬ ወይም አመራር የሕዝብን መብትና ጥቅም አስከብራለሁ ብሎ መንቀሳቀስ አይችልም” በማለት አድርባይነትን የፓርቲው አባላት እንዲታገሉ ማሳሰባቸውን አስነብቧል።

ወ/ሮ አዜብ በኢቲቪ አማካይነት በዚሁ ጉዳይ ሲነገሩ እንደተሰማው ችግሩ የቁርጠኛነት ጉዳይ እንደሆነ ገልጸዋል። “የሚባለው” በማለት የሰሙት መሆኑንን በመግለጽ ወ/ሮ አዜብ እንዳሉት “ለእንጀራና ለምደባ” ሲባል አድርባይነት መንገሱን ገልጸዋል። “ያሉት ክፍተቶች ቀላል አይደሉም” በማለት ማብራሪያቸው የሚያስከትሉት ወ/ሮ አዜብ፣ “ራሳችንን ማጽዳት፣ ግለኝነትን መታገል፣ ኪራይ ሰብሳቢነትን መዋጋት ያስፈልጋል” ካሉ በኋላ አስገራሚ አስተያየት ሰንዝረዋል።

“ቀናነት” እንደሚያስፈልግ በማሳሰብ “ስትራቴጂው አለ። ሲፈጸምም አይተነዋል” አሉ። በዚህ ንግግራቸው ባለቤታቸውን ያስታወሱት ወ/ሮ አዜብ “መቻቻልና አድርባይነት መጥፋት አለበት” የሚል መፈክር አሰምተዋል። በዚህ አላበቁም “እስከመጨረሻው፣ ከሁሉም ነገር ጽድት ብለን፣ በቁርጠኛነት የሚያደናቅፈንን መቻቻልና አድርባይነት ከመድረክ ላይ መጥለፍ መቻል አለብን” ብለዋል። “መድረክ” ሲሉ የጠሩትን ግን አላብራሩም።

የኢህአዴግ ጉባኤ ሲጠናቀቅ በተለይም የእህል ምርት በሚገባውና በተቀመጠበት ደረጃ ማደጉ ቀርቶ አፈጻጸሙ ደካማ መሆኑ እንዳሰጋው፤ ምናልባትም የከፋ ድርቅ ሊከሰት የሚችልበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል የሚለው ስጋት ህዝብን እንዳያነሳሳበት መፍራቱን ምንጮች አመልክተዋል።

የመላው ኢትዮጵያዊ ገቢ መጨመር እንዳለበት አቋም ቢያዝም በተለይም ጡረተኞችን፣ የቤት አበል የሚቀበሉ ቤተሰቦችን፣ እጅግ አነስተኛ በሆነ የደሞዝ ጣሪያ የተቀጠሩትንና በቀን ስራ የተሰማሩትን ስለማካተቱ በግልጽ የተባለ ነገር የለም። በኢትዮጵያ በደርግ ጊዜ ቤት ተወርሶባቸው በ30 እና 40 ብር አበል ላለፉት አርባ ዓመታት ተረስተው የኖሩ ዜጎች ቁጥር ቀልል የሚባል አይደለም። እነዚህ ወገኖች ለአፈር ግብር እንዲከፍሉ የሚጠየቁት ከሚያገኙት አበል በላይ መሆኑም ይታወቃል። አንዳንድ ቦታ ተከራዮች ከባለቤቶቹ (በውርስ ንብረታቸው ከተወሰደባቸው) በላይ ተከራይቶ በማከራየት ተጠቃሚ ናቸው። ዜናውን የላከልን እንዳለው ያገባናል የሚሉ ሁሉ አስቀድመው በዚህ ጉዳይ ላይ ከህዝብ ጋር በመነጋገር እንዲሰሩ አሳስበዋል። (ፎቶ: Ethiopian Herald)

http://www.goolgule.com/hustlers-in-eprdf/

posted by Tseday Getachew

Advertisements

ወ/ሮ አዜብ ተጨንቀዋል!

“ከሁሉም ነገር ጽድት ብለን እንታገል”

አቶ መለስ ከሞቱ ጀምሮ በተለያዩ መድረኮች ንግግርና መዕልክት የሚያስተላልፉት ወ/ሮ አዜብ መስፍን መረጋጋት እንደማይታይባቸው ተገለጠ። አሁንም በባለቤታቸው ስምና መንፈስ ሙግትና ማብራሪያ ከማቅረብ አልተላዘቡም። ይህን የሚያደርጉት ከጭንቀት የተነሳ እንደሆነ ተመልክቷል።

ሰሞኑንን በተጠናቀቀው የኢህአዴግ ጉባኤ አቶ መለስን አስመልክቶ ወ/ሮዋ የተናገሩት ንግግር በጭንቀት ውስጥ ስለመሆናቸው ማሳያ እንደሆነ የተናገሩት አብረዋቸው ባህር ዳር ስብሰባ የተቀመጡ የድርጅታቸው ኢህአዴግ “ባልደረቦቻቸው” ናቸው።

በጉባኤው ወቅት አቶ መለስ ዜናዊን በማወደስ የተዘጋጀው “ዝክረ – መውደስ” ታሪካዊ ሰነድ እንዲሆን ከመጽደቁ በፊት ወ/ሮ አዜብ በሰጡት አስተያየት “በፔሮል የሚከፈለው ብቸኛ መሪ መለስ ብቻ ነው” በማለት ራሳቸውን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በፔሮል በሚከፈላቸው ገንዘብ ብቻ እንደማይኖሩ የሚያመላክት ንግግር አድርገዋል።

መለስ ደመወዛቸው ስድስት ሺህ ብር እንደሆነ፣ ሁለት ሺህ ብር ሲቆረጥ አራት ሺህ እንደሚቀርና “ይህችኑ ገንዘብ” እየተቀበሉ ላገር ሲሰሩ ያለፉ መሪ መሆናቸውን ያወሱት ባለቤታቸው፣ ለመለስ ዝክረ-መወደስ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ይህ መካተት ይገባዋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

“መለስ ጭንቅላቱን ይዞ ወደዚህች ዓለም መጣ፣ ለዚህች ዓለም፣ አገር፣ ምድር፣ የምታገለግል ሃሳብ አመነጨ” ያሉት ወ/ሮ አዜብ፣ ባለቤታቸው ግለኝነት ሳይፈታተናቸው፣ ቤተሰቦቻቸውን በመርሳት፣ ላገራቸው የለፉና ድህነትን ሲዋጉ ኖረው ያለፉ መሪ መሆናቸው ሊረሳ እንደማይገባው አመልክተዋል። አያይዘውም ሊተኩ የሚችሉ መሪ እንዳልሆኑ በማሳሰብ ዝክረ-መወድሱ ከአቶ መለስ የሕይወት ጉዞ ብዙ ቁምነገሮችን የዘለለና ያልተሟላ ነው ብለውታል፡፡ እንዲሁም መለስ የኢትዮጵያ መሪም ብቻ ሳይሆኑ የአዲስ ራዕይ መጽሄት አዘጋጅ መሆናቸው አለመጠቆሙ አግባብ እንዳልሆነ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

በጉባኤው ላይ የተገኙ የድርጅት አባላት እርስ በርሳቸው ሲለዋወጡ የነበረውን የተከታተሉና በግልጽ ከስርዓቱ ባህርይ በመነሳት ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ እንዳሉት ወ/ሮ አዜብ የቀድሞው ስብዕናቸው አብሯቸው የለም። እንዲያውም በጭንቀት ውስጥ ያሉ ይመስላሉ ብለዋል።

በድርጅቱ አባላት ከላይ እስከታች የባለቤታቸውን ስልጣን ተገን በማድረግ በጣልቃ ገብነታቸውና ከፍተኛ የሚባል ንብረት በማካበት የሚታሙት ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ስም በመደጋገም የሚያነሱት የሚታሙበትን ጉዳይ ለማስረሳት እንደሆነ እርስ በርስ በእረፍት ሰዓት ይወራ እንደነበር እነዚሁ ክፍሎች ተናግረዋል።

“ሴትየዋ በግልጽ ስለሚነሳባት ጉዳይ ለምን አትናገርም” በማለት የጠየቁ እንዳሉ፣ ከዚህም በላይ በድርጅቱ ውስጥ ነግሷል የሚባለው ሙስና በግልጽ ለምን አጀንዳ ሆኖ እንደማይቀርብ አባሉ ውስጥ ውስጡን ሲያወራ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። በትክክለኛው መንግድ ለመታደስና ለመጥራት የሙስና ጉዳይ የድርጅቱ ቀዳሚ አጀንዳ መሆን እንዳለበት አስተያየት የሰጡም አሉ።

ወ/ሮ አዜብ ይህ ገብቷቸው ይሁን አይሁን ስለ ባለቤታቸው ድህነት ሲናገሩ “እንደሚባለው ሳይሆን እኛ እንኮራበታለን” ማለታቸው ከሙስና ጋር በተያያዘ ስጋት ስለገባቸው የአባሉን ልብ ለማራራት እንደሆነ አድርገው የወሰዱትም እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። በግልጽ ባያብራሩትም “እንደሚባለው” ብለው በመጥቀስ በይፋ እስከማስተባበል መድረሳቸው በባለቤታቸው ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ራሳቸውም የተረዱት አይመስልም፡፡

አቶ መለስ ከሞቱበት ጊዜ ጀምሮ በሚያገኙት መድረክ ስለ ባለቤታቸው ድህነትና ያለ እረፍት ያለፉ መሪ በማድረግ በስፋት የሚናገሩት ወ/ሮ አዜብ፤ ባለቤታቸውን ዴሞክራት መሪ አድርገው ቢስሉም ሪፖርተር በፖለቲካ አምዱ ያስነበበው እውነተኛ ታሪክ የስጋታቸውና የፍርሃታቸው መነሻ እንደሚሆን ከግምት በላይ የሚናገሩ አሉ። ሪፖርተር ወ/ሮ አዜብን በስም ባይጠቅስም፣ “መሐንዲስ አልባው መተካካት” በሚል ርዕስ በጻፈው “(መለስ) በተለያዩ ጊዜያቶች የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን ከፖለቲካ ጨዋታ ውጪ ማድረግ ቢችሉም፣ እስከ 1993 ዓ.ም. ድረስ ሥልጣን የግላቸው አልነበረም፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ላይ ሆነው የፈለጉትን ማድረግ የሚችሉ ሰውም አልነበሩም፡፡ በወቅቱ የሕወሓት መሰንጠቅን ተከትሎ የድርጅቱ ርዕዮተ ዓለም ቁንጮ (አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም) የወታደራዊ ስትራቴጂ ባለቤት (የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ስዬ አብርሃ)፣ የፕሮፓጋንዳ ኃላፊው (የቀድሞ የትግራይ ፕሬዚዳንት አቶ ገብሩ አስራት) እና ሌሎች የድርጅቱ ከ10 በላይ ከፍተኛ አመራሮች መወገድን አስከትሏል፡፡ የእነዚህ የድርጅቱ ወሳኝ ሰዎች መወገድን ተከትሎ በመንግሥትም ሆነ በፓርቲ ሥልጣናቸውን የተደላደለና ምንም የፖለቲካ ተቀናቃኝ የሌላቸው ሰው መሆን የቻሉበት ጊዜ ነበር፡፡ የፈለጉትን ሕግ ማውጣት ያልፈለጉትን የመደቆስ ሥልጣኑም ጉልበቱም ነበራቸው” ሲል ሪፖርተር የጻፈላቸው አቶ መለስን ተገን በማድረግ ወ/ሮ አዜብ በሃብት፣ በጣልቃገብነት፣ በተለያዩ ውሳኔዎች፣ ፈላጭ ቆራጭ ሆነው መቆየታቸው በርካታ ወዳጅ ያፈራላቸው ባለመሆኑ የስጋታቸው መጠን ሰፊና ጥልቅ እንደሆነ በስፋት አስተያየት እየተሰጠበት ነው።

http://www.goolgule.com/anxious-azeb/

posted by Tseday Getachew

ኢትዮጵያውያን ደቡብ አፍሪካ የኢሕአዴግን ስብሰባ በተኑ፤ ቴዎድሮስ አድሃኖም ተደብቀው አመለጡ

(ዘ-ሐበሻ) በደቡብ አፍሪካ ሮዝባንክ ከተማ የተጠራው የኢሕ አዴግ ሥብሰባ በኢትዮጵያውያን ብርቱ ትግል መቋረጡንና መበተኑን የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ሪፖርተር ከሥፍራው ዘገበ። በልማት ስም የተጠራውና በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የተጠራው ይኸው ስብሰባ የስር ዓቱ ደጋፊ የሆኑ ከ20 የማይበልጡ ሰዎች ቢገኙም ስብሰባው ይደረግበት የነበረውን ሃያት ሆቴል የስር ዓቱ ተቃዋሚዎች በመሙላት ስብሰባው እንዳይደረግ አድርገዋል።
የድምጻችን ይሰማ፣ የኦነግ፣ የግንቦት ሰባት እና የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላትና ደጋፊዎች በአንድነት የኢሕ አዴግን ስብሰባ እንዳይደረግ በማድረግ
– ከልማት በፊት የሕዝብ ነፃነት ይቅደም
– በቅድሚያ መገደብ ያለበት ወንዝ ሳይሆን የ ኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ነው በሚል ሕዝቡ ጩኸቱን በማሰማቱ ስብሰባው ተቋርጦ ደጋፊው ሕዝቡ ጥቃት ያደርስባቸዋል በሚል ፍራቻ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ደብቆ ከአዳራሹ አስመልጧል።
የኢሕአዴግ ስብሰባ እንዳይደረግ ያስተጓጎሉት ኢትዮጵያውያን ኢሕ አዴግ በከፈለበት የሃያት ሆቴል አድራሽ ስብሰባ በማድረግ በቀጣይ በአንድነት ስለሚያደርጉት የጋራ ትግል ዙሪያ መነጋገራቸውን፤ የተዘጋጀውን ውሃ እና መጠጥም የኛ ገንዘብ ነው በሚል እንደጠጡት የዘገበው የዘሐበሻ ሪፖርተር የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሃያት ሆቴል ስብሰባው ከተስተጓጎለበት በኋላ ደጋፊዎቹን በኢምባሲው ውስጥ መሰብሰቡ ታውቋል። ከኢትዮጵያ ኢምባሲ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው ከሮዝባንክ ከተማም ኢትዮጵያውያን ወደ ኢምባሲው በመሄድ ተቃውሟቸውን እንዳሰሙም ሪፖርተራችን ጨምሮ ዘገቧል።

http://www.zehabesha.com/

posted by Tseday Getachew

ባሁኑ ሰዓት በአማራው ወገናችን ላይ እየደረሰ ያለው አማራን የማጥፋት ሴራ፤ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የሚካሄደው ተግባር ዋናው አካል ነው።

በአሁኑ ሰዓት አማርኛ ተናጋሪው ወገናችን ላይ መለኪያ የሌለው ግፍ እየተፈፀመበት ነው። ይህ ግፍ፤ የአማራውን ወገናችን ለማጥፋት ከሚደረግ ወንጀል ሌላ፤ መገንዘቢያ ቀመር የለውም። የዛሬው እስከመቼ ይኼን ጉዳይ ይመለከታል።

http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2013/03/ESKEMECHE-101-1.pdf

http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2013/03/ESKEMECHE-No-102.pdf

posted by Tseday Getachew

Attempt to deport Ethiopian terror link man from UK fails

Home Secretary Theresa May has failed in a bid to deport a 33-year-old Ethiopian who had “thrown in his lot” with Islamist extremists “committed to terrorism”.
The Court of Appeal said there was a risk that the man – who was not named in a ruling – might be subjected to “ill treatment” if returned to Ethiopia.
Three appeal judges overturned a ruling by the Special Immigration Appeals Commission (Siac) – which had upheld Mrs May’s decision to deport the man, who has a wife and children in the UK.
They said Siac had “erred” in ruling that assurances given by the Ethiopian government were “sufficient” to prevent the man being “subjected to ill treatment” contrary to human rights legislation.
Lord Justice Jackson – the most senior of the three appeal judges – said he had reached his decision with “little enthusiasm”.
He said he had “no doubt” that Mrs May had been entitled to conclude that the man’s deportation was “conducive to the public interest on national security grounds”.
But he said “everyone within our shores” is entitled to protection under human rights legislation – “even those” involved or connected with terrorism.
The man – referred to as J1 in a written judgment handed down today after an appeal court hearing in London in February – had appealed against Siac’s decision to uphold Mrs May’s decision to deport him to Ethiopia.
He argued that Siac erred in holding that assurances given by the Ethiopian government were sufficient to prevent him from being subjected to ill treatment contrary to article 3 of the European Convention on Human Rights (ECHR), which prohibits torture and inhuman or degrading treatment or punishment.
The three appeal judges – Lord Justice Jackson, Lord Justice Elias and Lord Justice Treacy – agreed.
“The appellant succeeds in this appeal and the decision of Siac dismissing the appeal is reversed,” said Lord Justice Jackson.
“I should add that this is a decision which I reach with little enthusiasm. The appellant has been closely associating with Islamist extremists who are involved in terrorism. Such people show scant regard for the rights to life of others.
“I have no doubt that the Secretary of State was entitled to conclude that the appellant’s deportation was conducive to the public interest on national security grounds. The fact remains, however, that the UK is party to the ECHR and has incorporated its provisions into our domestic law.
“Everyone within our shores is entitled to protection under the ECHR, even those who are involved in or connected with terrorism. The courts are under a duty to uphold those rights and we do so in this case.”
Lord Justice Jackson said the man arrived in the UK with members of his family in 1990.
“Most of the family returned to Ethiopia in 1992, but the appellant and his sister remained in this country. Eventually, after various refusals of asylum and appeals, the appellant obtained indefinite leave to remain in the UK. He now has a wife and children in this country,” said the judge.
“Unfortunately the appellant has not lived peacefully in his host country. Instead he has thrown in his lot with a group of Islamist extremists who are committed to terrorism.”
Lord Justice Jackson said there were “hostile organisations” in Africa.
“The branch of Al Qaida which operates in the Horn of Africa is known as Al Qaida in East Africa (AQEA),” said the judge.
“Another Islamist extremist organisation in Africa is known as Al Shabaab. Al Shabaab has declared the ambition of establishing a caliphate in the Horn of Africa. The Ethiopian parliament has declared AQEA and Al Shabaab as terrorist organisations.”
Lord Justice Jackson gave a list of the man’s associates and outlined a series of terrorism connections, including links to a failed London bomb plot in 2005 and training camps in Cumbria and Scotland.
He said the man was “an important and significant member of a group of Islamist extremists in the UK”.
“The appellant has been associating with the following men: Dawit Semeneh, Joseph Kebide, Nathan Oqubay, Zulgai Popal, Elias Girma Eyassu, Bilal Berjawi, Mohammed Sakr, and Walla Eldin Rahman,” Lord Justice Jackson.
“In May 2004 Semeneh and Kebide attended a training camp in Cumbria which was run by a man called Hamid. Hamid was subsequently convicted of soliciting to murder and providing terrorism training.
“The training camp in May 2004 appears to have been a serious affair. Four men who were involved in the failed London bombings of 21st July 2005 attended Hamid’s training camp in May 2004.
“In December 2004 the appellant and three others were found by the police at Lanark. They were all wearing plastic gloves. They said that they were on their way to Fort William. At about this time Hamid was organising a training or bonding camp near Loch Ness.
“In May 2005 Semeneh, Oqubay, Popal, Eyassu and Kebide travelled to Somalia for purposes relating to terrorism. The appellant admits that he knew about this trip but claims he thought it was for religious purposes.
“On 21st July 2005 the appellant was in telephone contact with a man called Hussain Osman. Osman was one of five men who attempted to cause bomb explosions in London on that day. He is now serving a substantial prison sentence.”
Lord Justice Jackson added: “In October 2009 Berjawi, Sakr and Rahman travelled from the UK to Somalia for the purpose of terrorist training and terrorist activity in Somalia.
“The appellant knew in advance about the travel plans of those three men and the purpose of their expedition.
“During 2009 and 2010 the appellant was an important and significant member of a group of Islamist extremists in the UK who provided support to those three men in Somalia.
“Media reporting identifies Berjawi as a close associate of Harum Fazul. Until his death in June 2011 Fazul was a, if not the, leader of AQEA. Fazul was also a close associate of the leaders of Al Shabaab. On 11th July 2010 there were twin bombings in Kampala, for which Al Shabaab claimed responsibility. It is now generally thought that that claim is well founded.
“Perhaps unsurprisingly the Secretary of State came to the conclusion that the deportation of the appellant from the UK would be conducive to the public good for reasons of national security.
“Accordingly on 25th September 2010 the Secretary of State notified the appellant of her decision to make an order that the appellant be deported to Ethiopia. The appellant was taken into immigration detention on 25th September 2010.”
PA

posted by Tseday Getachew

Meles was a poor man who had no bank account – Azeb Mesfin

By Addis Fortune

Editor’s Note – Azeb Mesfin, the widow of Meles Zenawi, said her husband’s net salary was 4,000 Birr a month, too little money that he had no need for a bank account. Azeb was mad that such an important fact was missing from the minds of those who write flawless tributes in honor of her late husband. Eulogy writers should heed her advice before she gets hold of them: First, she is a member of the powerful TPLF politburo; second, if money is power, Azeb is uber-rich, perched like an eagle’s nest atop the mountain of gold called “EFFORT.”

Delegates of the ninth convention of the ruling EPRDF party have shown their dissatisfaction over a eulogy written for their late leader, Meles Zenawi, while some were critical of the quality of its writing and completeness of the content.

Translated from Tigrigna, the eulogy was first presented to the congress of the TPLF, held in Meqelle two weeks ago, before it was presented to over 1,000 delegates at the conclusion of the ruling coalition’s convention on Tuesday, held in Bahir Dar.

The first to voice such disappointment over the organisation of the eulogy and its content structure was Meles’s widow. Elected to the political bureau of the TPLF for the second time and to the all too powerful Executive Committee of the EPRDF, Azeb Mesfin was displeased to see the eulogy incomplete.

Some of the points she argued as missed are Meles’s place, role and the contributions he made as an Editor-in-Chief of the party’s ideological organ, Addis Ra’ey. Azeb feels that the contributions Meles had made in originating the idea of forming a training facility for the rank and file, now directed by Addisu Legesse, and the manual he develop ought to be forcefully underlined.

Azeb defended her late husband’s legacy in relations to how he had handled the conflict and the subsequent war with Eritrea. Despite condemnations from his political opponents due to his heritage, Azeb told delegates that Meles had never negotiated on the national interests of Ethiopia.

“Not even for a second,” Azeb told delegates rather emphatically.

Azeb described Meles’s conduct during the war with Eritrea in the late 1990s as “extraordinary” in not showing what he had felt of the accusations, but focused on defending his beliefs and political positions regardless.

She recalled her late husband as perhaps the only leader who had earned a little over 4,000 Br a month in net salary, but fought poverty with courage and resolve, while remaining selfless.

“Meles didn’t have a bank account,” Azeb said. “He had neither an ID card nor a driving licence.”

These parts, Azeb argued, were not given their proper place in the eulogy, which was read by Hailemariam Desalegn, re-elected to chair the EPRDF twice since the death of Meles in August 2012.

Hailemariam’s re-election was fait accompli, although he was made to pass the test of contest to the office. His deputy, Demeke Mekonnen of ANDM, and Alemayehu Atomsa of OPDO, were nominated by their respective parties for the chairmanship, while leaders of the TPLF have declined to nominate their leaders, Fortune learnt.

Hailemariam has won the chairmanship with a landslide, after bagging 176 votes of the 180 Council members of the ruling party, sources in the Council disclosed to Fortune.

Although the other two contenders have received two votes each against Hailemariam, Demeke too claimed the deputy chairmanship position with significant margin, claiming 146 votes against 25 given to his contender, Fortune learnt.

Emerging as uncontested non-combatant leader of the Revolutionary Democrats since the party’s formation in the late 1980s, Hailemariam was seen endorsing the conciliatory proposition made by Addisu, who remains one of the 13 political bureau members of the ANDM but left out from the EPRDF’s Executive Committee.

Addisu has argued that the eulogy is filled with repetition, is not well organised, and suffers from losses in translation, while its structure is weak. Addisu urged delegates to let the EPRDF’s Executive Committee rewrite the eulogy before it gets adopted as the party’s official document, a proposition Hailemariam had secured its adoption by the Congress unanimously.

http://www.ethiomedia.com/addis/5766.html

posted by Tseday Getachew

በአረመኔው የወያኔ አገዛዝ በግፍ እስር ቤት የታጎሩት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸው ታወቀ

 

ድምጻችን ይሰማ የሚል መፈክር አንግበው ላለፉት አስራ ሶስት ወራት አፋኙን የወያኔ አገዛዝ መቆሚያና መቀመጫ በማሳጣታቸው በጭካኔ እስር ቤት የተጣሉት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸውን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ሪፖርት ገለጸ፣ ፣ እንደዘጋቢያችን ሪፖርት በዘረኛውና አረመኔው የወያኔ አገዛዝ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ታፍሰውና ማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ በግፍ ታስረው የሚገኙት ሙስሊም የዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ፣ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ቦታ ባለማወቃቸው በቀለብ እና በልብስ እጦት እየተቸገሩ ነው ብሏል።

ዘጋቢያችን እንደገለጠው በአቃቂ እስር ቤት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ተማሪዎችና መምህራን እስር ቤቱን አጨናንቀው እንደሚገኙ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ፣ ከነኝህ ታሳሪዎች ውስጥ እጂግ በርካቶቹ ቶርቸር ( አሰቃቂ ድብደባ) ተፈጽሞባቸዋል። ይህም አልበቃ ብሎ ተማሪዎቹ በአሁኑ ጊዜ የረባ ምግብ አጥተው በመሰቃየት ላይ እንደሚገኙና ልብሶቻቸው በላያቸው ላይ እያለቁባቸው ለእርዛት እየተዳረጉ እንደሆነም ታውቋል።

አሁንም ጭካኔአዊ አሰራው አለማብቃቱና የተለያዩ ታማሪዎች በየጊዜው እየተያዙ መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን በማእከላዊ እስር ቤቶች ውስጥ ታስረው ከሚገኙት መካከል የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆኑት ኑርየ ካሲም እና ካሊድ ሙሀመድ፣ የጅማ ዩኒቨርስቲዎቹ ያሲን ፈይሞ፣ ሙሀመድ አሚን ከድር፣ እና ጁነዲን ሁሴን፣ የሚዛን ተፈሪው አብዱላኪም አህመድ፣ የወሎ ዩኒቨርስቲዎቹ ጣሂር ሙሀመድ ፣ ሙሀመድ አብዱራሂም እና ሰኢድ ሙሀዲን፣ የጎንደር ዩኒቨርስቲዎቹ ሰኢድ አብርሀም ፣ኦማር ሙሀመድ፣ እና ሊና ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው አብዱላዚዝ ሰኢድ እንዲሁም የአዋሳ ዩኒቨርስቲዎቹ አብደላ ሙሀመድ ይገኙበታል ብሏል።

የሙስሊም ጉዳይ አምደኛ የነበረው ሶሎሞን ከበደ፣ የከሚሴው ዳኢ ጀማል ከበደ፣ የሻሸመኔው ዳኢ አብዱረዛቅ ሼህ አህመድ፣ የከሚሴው ዳኢ ኢክርሀም አብዱ፣ የሀረርጌው ሁሴን ሮባ፣ የድሬዳዋው ሙሀመድ ሀሰን፣ የከምሴው ሁሴን አሊ እና አደም አህመድ አሊ በማእከላዊ እስር ቤት ከታሰሩትና ከፍተኛ ስቃይ ከደረሰባቸው መካከል ይገኙበታል።

የወያኔ ኢህአዴግ ፈረስ የሆነው ሀይለማርያም ደሳለኝ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እርምጃ እንወስዳለን በማለት ሰሞኑን በባህርዳር በመካሄድ ላይ ባለው የወያኔ ኢህአዴግ ጉባኤ ላይ መዛቱንም ተያይዞ የደረሰን ዘገባ አመልክቷል።

posted by Tseday Getachew

የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አብረን እንታገል የሚል የትግል ጥሪ አደረገ

 

የኢትዮጵያ ህዝብ ሃያ አንድ አመት ሙሉ ከቀለደበት  የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ እጅግ በጣም የተሻለ አማራጭ ኃይል እንዳለዉና ይህንን ለኢትዮጵያ አንድት፤ ለህዝቦቿ እኩልነትና ነፃነት በቆራጥነት የቆመዉን አማራጭ ኃይል የኢትዮጵያ ህዝብ በፍጥነት እንዲቀላቀልና የትግሉን የመጨረሻ ምዕራፍ እንዲጀምር የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አገራዊ ጥሪ አደረገ። የወያኔ ንቀት፤ጥላቻና ህዝብን ማሸበር ማብቃት አለበት ብለዉ አምርረዉ በተነሱ ወጣቶች፤ምሁራንና ወታደሮች በቅርቡ የተቋቋመዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል በላፈዉ ሳምንት እንዳሳወቀዉ በወያኔ ተራ ካድሬዎች መረገጥና እየተገፋ እስር ቤት መወርወር የሰለቸዉ ኢትዮጵያዊና በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ በህዝብ ነጻ ፍላጎት ተመስርቶ ህዝብን በታማኝነት የሚያገለግል ስርአት ለመመስረት ምትፈልጉ ኢትዮጵዉያን ሁሉ ወያኔ እስካለ ድረስ ይህንን ህዝባዊ ስርአት ካለመስዋዕትነት ማምጣት አይቻልምና ለድል ሊያበቃን የሚቸለዉን መስዋዕትነት ለመክፈል እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተጠንቀቅ እንዲቆም አገራዊ የአደራ ጥሪዉን አስተላልፏል። የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ይህንን ጥሪ ያደረገዉ የወያኔ ህወሀት ተሸካሚ ፈረስ የሆነዉ ኢህአዴግ ካለፈዉ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን እስከዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 17 ቀን ድረስ ባህርዳር ላይ ጌታዉን ተሸክሞ ያካሄደዉን ትርጉም የለሽ የወሬ ጉባኤ አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፈዉ መልዕክት ነዉ።

ዛሬ የኢትዮጵያን ህዝብ በዘረኝነት ገመድ አስሮ እየረገጠ የሚገዛዉ ወያኔ ለዚህ የበቃዉ በዘረኝነትና በጥላቻ አነሳስቶ ያሰታጠቃቸዉ ገበሬዎች በከፈሉት መስዋዕትነት ነዉ ያለዉ ይሄዉ ህዝባዊ ኃይል ሠላም ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱን ከእነዚህ የቀን ጅቦች ለማላቀቅና አገራችንን የእኩሎች አገር ለማድረግ ማንኛዉንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀት አለበት ብሏል። የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመረዉ የፍትህ፤የነጻነትና የዲሞክራሲ ትግል ግቡን እንዲመታ የመጀመሪያዉን እርምጃ የወሰደዉና ትግሉ የሚፈልገዉን የደም መስዋዕትነት ለመክፈል የትግሉ ግንባር የመጀመሪያዉ ደጃፍ ላይ የተሰለፈዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ካሁን በኋላ ኢትዮጵያ ዉስጥ የወያኔን ዘረኝነት፤ዝርፍያ፤ጥላቻና ንቀት ለማስቆም መፍትሄዉ ከአገር እየተሰደዱ በየባህሩና በየበረሀዉ መሞት ሳይሆን ለስደታችን፤ ለመዋረዳችንና ለመረገጣችን ቀንደኛ ምክንያት የሆነዉን የወያኔ ስርአት እዝያዉ አገር ቤት ዉስጥ ፊት ለፊት በመጋፈጥ ብቻ ነዉ ብሏል።

የወያኔ እህአዴግ ዘመን አብቅቷል፤ከአሁን በኋላ ዘመኑ የኛ የኢትዮጵያዉያን ነዉ ያለዉ የግንቦት ሰባት ዝብባዊ ኃይሎች ቃል አቀባይ ይህንን የኛ የሆነዉን ዘመን እዉን የምናደርገዉና የኢትዮጵያን ህዝብ ከዘረኝነት ነጻ የምናወጣዉ እንደአንድ ሰዉ ቆመን በጋራ ስንታገል ነዉ እንጂ የአገር ማዳኑንና የመስዋዕትነቱን አደራ ለተወሰኑ ወገኖች ብቻ በመተዉ አይደለም ብሏል። በመቀጠልም ወያኔን ፊት ለፊት ተፋልሞ ወንድሞቹንና እህቶቹን ከሁሉም በላይ ደግሞ ከአባቶቹ በአደራ የተረከባትን ኢትዮጵያን ለልጆቹ ለማስተላለፍ የሚናፍቅ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ከዛሬ በኋላ ዬት ሄጄ ወያኔን ልታገል የሚል ስጋት እንዳይሰማዉ አሳስቧል።ባለፈዉ ታህሳስ ወር እራሱን ለህዝብ ይፋ ይደረገዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ አያሌ ኢትዮጵያዉያን በየቀኑ እየተቀላቀሉት ሲሆን ይህንን የህዝብ ተገንና አለኝታ የሆነ ኃይል በመቀላቀል የአዲስቷ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ለመሆን የምትፈልጉ በአገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ አገራት የምትገኙ ኢትዮጵያዉያን ህዝባዊ ኃይሉ በተከታታይ ለሚያወጣቸዉ መግለጫዎችና ህዝባዊ ጥሪዎች ምላሽ በመስጠት እንዲትተባበሩ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ጥሪዉን ያስተላልፋል። 

posted by Tseday Getachew

“አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች ነበሩ”

ፍኖተ ነጻነት መጋቢት 15 ቀን 2005 ዓ.ም.

የዛሬው እንግዳችን አቶ ታዲዎስ ታንቱ ይባላሉ፡፡ አቶ ታዲዎስ የታሪክ ምሁርና በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ነፃ ፕሬስ ውስጥ ትልቅ ሚና ያላቸው ሲሆን በአሁን ወቅት “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ዋና ሰብሳቢ ናቸው ፡፡ በተለይ ለፋሺስቱ ግራዚያኒ ከተሰራው ሐውልት ጋር በተያያዘ አጭር ቆይታ አድርገናል ተከታተሉን፡፡

በጣሊያን የሩዶልፍ ግራዚያኒንን የሐውልት ለመቃወም የሐሳቡ ጠንሳሽ ማን ነው?

አቶ ታዲዎስ፡- የፋሽቱ ጣሊያን የኢትዮጵያውያን ዋና ጨፍጫፊ የነበረውን ሩዶልፍ ግራዚያኒ ሐውልት መሰራት ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞው የተጀመረው በውጭ ሀገር ባሉ

አቶ ታዲዎስ ታንቱ
ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት
ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ
ኢትዮጵያውያን ነው፡፡ በሀገር ውስጥ ግን የሐሳቡ ጠንሳሽ “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ነው፡፡ ከዛ በኋላ የባለዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር ሰልፉን ለማስተባበር ፈቃደኛ መሆኑን ገለፀልን፤ በዚህም ላይ ሰማያዊ ፓርቲ እንደሚተባበረን ከገለፀ በኋላ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ሰልፉን ለማካሄድmወሰንን፡፡

ተቃወቅሞውን ለማቅረብ ያነሳሳችሁ ዋነኛ ምክንያት ምን ነበር?

አቶ ታዲዎስ፡- ብዙውን ጊዜ እኔ በጋዜጦች ስለ አርበኞች ታሪክ ያነበብኩትንና ያወቅሁትን እፅፋለሁ፣ እመረምራለሁ፡፡ የጣሊያኑ ፋሽስት ግራዚያኒ ሀገራችንን በመውረር በአባቶቻችንና እናቶቻችን አርበኞች ላይ የፈፀሙት የግፍ ግድያ አሰቃቂ እንደነበር ስለተረዳሁ፤ ያ ሲቆጨኝ ደግሞ አሁን በጣሊያን ሀገር ለእሱ ሙዚየምና ሐውልት የመሰራቱን ወሬ ከኢንተርኔት ምንጮች ስላየሁ በጣም ተናድጄ እንደውም ተቃውሞ ማሰማት አለብን ብዬ ተነሳሁ፡፡ በኋላ ደግሞ እኛም የአንተ ዓይነት ሐሳብ ነበረን ብለው የባለ ዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር አነጋገሩን፡፡ ከዛ በመቀጠል ሰማያዊ ፓርቲ በጋራ እንስራ የሚል ጥያቄ አቀረበ፡፡ በዚህ ምክንያት ሶስቱ አካላት በጋራ ሰልፉን ለማድረግ ዝግጅት ማድረግ ጀመርን፡፡ ስለዚህ ለኢትዮጵያ ጠላት አይደለም ጣሊያን ሀገር ጨረቃም ላይ ቢሆን ሀውልት እንዲሰራ አንፈቅደም፡፡

በጊዜው ሩዶልፍ ግራዚያኒ ወንጀለኛ በመሆኑ የነበረው ፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተገፎ ከወታደርነቱ ተባሮ በጦር ወንጀል ተከሶ 19 ዓመት ተፈርዶበት ቅጣቱን ሳይጨርስ ከእስር ቢለቀቅም እ.አ.አ. በ1955 ዓ.ም. ሞቷል፡፡ ታዲያ ይህ በጊዜው ወንጀለኛ ለተባለው ሰው ሐውልትም ሆነ የመታሰቢያ ሙዚየም ማሰራት ኢትዮጵየውያንን መናቅና የአባቶቻችንን ክብር የሚነካ በመሆኑ ሊሰራለት አይገባም፤ እንደውም ለፈፀመው እልቂት ጣሊያን በቂ ካሳ ስላልከፈለች ካሳ መክፈልና በይፋ ይቅርታ መጠየቅ ይገባታል የሚል አቋም ይዘን ነው የወጣነው፡፡ ስለዚህ ግራዚያኒ ከነ አዳፋ ታሪኩ ሌላው እንዳይደግም ሲወሳ መኖር አለበት እንጂ እንደ ጀግና ሐውልት ሊሰራለት፣ሊወደስና ሊመሰገን አይገባም እንላለን፡፡

በወቅቱ የደረስው ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ ይቻላል?

አቶ ታዲዎስ፡- በወቅቱ ግራዚያኒ በፊርማው በግፍ ኢትዮጵያውያንን ያስጨፈጨፋቸው ሰዎች ስም ዝርዝር ከነደብዳቤው አለ፤ የዚህ ቅጂ እኔም ጋር አለ ይታወቃል፡፡ በተለይ የካቲት 12-14 ቀን 1929 ዓ.ም. ከ30 ሺህ በላይ ዜጎቻችንን በግፍ አዲስ አበባ ላይ እራሱ ግራዚያኒ አስጨፍጨፏል፡፡ ከ250 በላይ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ጨምሮ መነኮሳትን አስጨፍጭፏል፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት በ1938 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው አለም አቀፍ ጉባኤ ያቀረበው ሰነድ እንደሚያስረዳው 760,300 ሺህ ዜጎች ወዲያው ሲገደሉ 525,000 ደግሞ ከነቤት ንብረታቸው እንዲቃጠሉ ተደርጎ ህይወታቸው አልፏል፡፡ ከሁለት ሺህ በላይ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለው መነኮሳት ተገድለዋል፣ በርካታ ቅርሶች ተዘርፈው ተወስደዋል፡፡ በርግጥ ከተዘረፉ ቅርሶቻችን መካከል እስካሁን የተመለሰው የአክሱም ሐውልት ብቻ ነው፤ ሌሎቹ ግን አሁንም እዛው ናቸው፤ ሊመለሱልንም ይገባል፡፡ ከዛ ውጭ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የቀንድ ከብቶች በወቅቱ ተዘርፈው ተወስደዋል፤ 7 ሺህ ግመሎችም ተገድለውብናል፡፡ ይህም በሰነድ በተደገፈ ማስረጃ ለዓለም አቀፉ የሰላም ጉባዔ የቀረበ ነው፡፡ በወቅቱ ሰነድ ያልቀረበባቸውና ሰፊ ጥናቶች ሊደረግባቸው የሚገቡ በርካታ ጥፋቶች ተፈፅመዋል፡፡

ይህንን ተቃውሞ በዋነኝነት ማቅረብ የነበረበት መንግስት ነበር የሚሉ ወገኖች አሉ፤ እርስዎስ ምን ይላሉ?

አቶ ታዲዎስ፡- እኔም እስማማለሁ፤ ነገር ግን መንግስት ማዘጋጀት ካልቻለ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ማዘጋጀት ይችላል፡፡ እኔ እንደሚገባኝ መንግስት ተቃውሞ ያላቀረበው ከጣሊያን የሚያገኘው ዕርዳታ ይቀርብኛል በሚል ይመስለኛል፡፡ እኔ እስከማውቀው ይሄ መንግስት ዕለታዊና የፖለቲካ ገበያ ጥቅምን መሰረት ያደረገ እንጂ ወደፊት ትውልድ የሚኮራበትን ስራ የመስራት ዓላማ የለውም፡፡ ከዚህ በፊት የቀደሙ አባቶቻችን የሰሩትን በጎ ታሪኮች ሲያንቋሽሽ የኖረ መንግስት ስለሆነ እንዲህ ዓይነት የአባቶቻችንና እናቶቻችን አርበኞች ታሪክና ክብር የሚያስጠብቅ ስራ ይሰራል ብዬ አላስብም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያዊ ስሜት ያለው፣ ብሔራዊ ስሜትን የጠበቀ ህዝባዊ መንግስት ቢሆን ኖሮ ህዝቡን አስተባብሮ ይሄንን ስራ በቀዳሚነት መስራት የነበረበት እሱ ነበር፡፡ ስለዚህ መንግስት ባያደርግም ዜጎች ይህንን ሰልፍ የማድረግ መብት ስላላቸው እኛም ሰልፉን አድርገናል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የሀውልት ግንባታውን አለመቃወሙ ምን ያስረዳናል?

አቶ ታዲዎስ፡- ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ በእጅ አዙር ለሀውልት ግንባታው እውቅና እንደሰጠ ይቆጠራል፤ ይህንን እኔም አምናለሁ፡፡ ከዚህም በላይ አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች የነበሩ ናቸው፡፡ እንደውም ነፃነታችንን ባወጅንበት ሁለት ዓመት ሳይሞላ በአርበኞች ላይ ጦርነት የከፈቱ ናቸው፡፡ ስለዚህ ለግራዚያኒ የጀግና ሐውልት መሰራቱን ባይቃወሙ አይገርመኝም፤ ምክንያቱም እነሱ የማን ልጆች ናቸው? እስኪ በስልጣን ላይ ካሉት (ከኢህአዴግ) መካከል ለሀገሩ እና ለወገኑ ብሔራዊ ስሜት፣ ነፃነትና ክብር የተዋጋ የአርበኛ ልጅ አንድ ሰው ካለ ንገረኝ? አንድም ሰው የለም፡፡ ስለዚህ የባንዳ ልጅ ለጨፍጫፊው ግራዚያኒ በእጅ አዙርም ሆነ በቀጥታ እውቅና በመስጠት ድጋፍ ቢያደርጉ አያስደንቀኝም፡፡

እናንተ ሰላማዊ ሰልፉን ከማድረጋችሁ አንድ ቀን በፊት መጋቢት 7 ቀን 2005 ዓ.ም ስምንት ሰዎች መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ ይህ ክስተት በሰልፉ ወቅት እስር እንደሚኖር አልጠቆማችሁም?

አቶ ታዲዎስ፡- እሱን አውቀንም ነው ሰልፍ የወጣነው፡፡ አንድ ቀን አስቀድሞ ሌሎች ቢታሰሩም መውጣት አለብን ብለን ነው የወጣነው፤ እኛም ብንታሰር ሌሎችም እንደሚወጡ እናውቃለን፡፡ ችግር ይፈጠራል ብለን አልተውንም ፤መተውም የለብንም፡፡ ምክንያቱም ይሄ የሀገርና የወገን ጉዳይ ነውና፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሰልፉ ላይ የተገኙትን ላመሰግን እወዳለሁ፡፡

የታሰራችሁት ምን ወንጀል ሰርታችኋል ተብላችሁ ነው?

አቶ ታዲዎስ፡- ፍቃድ አልጠየቃችሁም ፣ አላስፈቀዳችሁም በሚል ነው፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ በነበሩ የአጼ ኃይለስላሴ፣ በደርግ ዘመንም ሆነ አሁንም በወያኔ አገዛዝ ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት ፈቃድ ይጠየቃል የሚል የተፃፈ ህገመንግስትም ሆነ አዋጅ አልነበረም፤የለምም፡፡ ዋናው ከእኛ የሚጠበቀው ሰላማዊ ሰልፍ እንደምናደርግ ማሳወቅና አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግ ማድረግ እንጂ ፈቃድ መጠየቅ አይደለም፡፡ ይህንንም ለእኛ ጥቅም እንጂ እነሱን ለማስደሰት አይደልም፡፡ እኛ ደግሞ የሀገሪቱን የተፃፈ ህግ ተከትለን ሰልፉን ከማድረጋችን 10 ቀናት አስቀድመን አሳውቀናል፡፡

ኢትዮጵያውያንን በግፍ ለጨፈጨፈው ግራዚያኒ የተሰራለትን ሐውልት በመቃወማችሁ በኢትዮጵያ መንግስት መታሰራችሁ ምን ስሜት ፈጠረባችሁ? ለእኛ የበለጠ የተነሳሽነት ስሜት ሰጥቶናል፡፡ ጉዳዩንም አጠናክረን እንድንሄድ ትልቅ የሞራል ድጋፍ ሆኖናል፡፡

ከእስር ሲለቋችሁ ምን ብለው ነው?

አቶ ታዲዎስ፡- ምንም ሳይሉን ለሁለት ሰው አንዳንድ ዋስ በማስጠራት ለቀውናል፡፡ ምክንያቱን ግን አልነገሩንም፤አላወቅንም፡፡ ከዛ ስትፈለጉ ትመጣላችሁ ብለው በዋስ ለቀውናል፡፡

በታሰራችሁበት ወቅትስ የገጠማችሁ ችግር አለ?

አቶ ታዲዎስ፡- በርግጥ እኔ ላይ ድብደባ አልፈፀሙም እንጂ ተመትተው ፊታቸው በተለይም አፋቸው አካባቢ የደማ ወጣት አይቻለሁ፡፡ ፊታቸው ያባበጠ ወጣቶችንም አይቻለሁ፡፡ ሌሎችንም ወጣቶች እንደደበደቧቸውም ሰምቻለሁ፡፡ በተለይ ደህንነቶች ማታ መጥተው በግል እያስጠሩ በቢሮ ያናግሩ ነበር፡፡ ስራው ግን የፖሊሶች እንጂ የደህንነቶች አልነበረም፡፡ በታሰርንበት ዕለት ያለምግብና ውሃ ቀን ሙሉ እንድንውል ተደርገናል፡፡ በተለይ እስር ቤቱን ስቃይ አራዳ ፖሊስ መምሪያና ጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ያለውን ስታይ ዕቃ ለማስቀመጥ ሆነ ለሌሎች እንሰሳቶች ለአንዲት ደቂቃ እንኳን እንዲቆዩበት አይመችም፡፡ እስር ቤቱን ስታይ በጣም ያሳዝናል፤ እዛ የገቡ እኮ ጤነኛ ሆነው የመውጣታቸው ዕድል እራሱ አነስተኛ ነው፤ለበሽታ የሚያጋልጡ ብዙ ነገሮች አሉ፤ ብቻ በጣም ያሳዝናል፡፡ ይሄ ደግሞ የወንበዴ ስራ ነው፤ ይሄንን መንግስት ማረም አለበት፡፡ ሌላው መርማሪ ፖሊሶችና ደህንነቶች ያልተገቡና ከእስሩ ጋር የማይገናኙ የግል ህይወትን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ፣ የኢ-ሜይል የይለፍ ቃል ይጠይቃሉ፣… ብቻ ብዙ ነው፡፡ በግል እኔን ደግሞ ፊታቸውን በኮፊያ የሸፈኑና ጥቁር መነፅር ያደረጉ ደህንነቶች ዋስ ጠርቼ ከወጣሁ በኋላ አንተ የአርበኞችን ታሪክ እያነሳሳህ ወጣቶችን እያነሳሳህ ስለሆነ ብታርፍ ይሻልሃል፤ በግል ልናናግርህ እንፈልጋለን እያሉ ለማስፈራራት ሞክረዋል፡፡ እኔ ግን በህጋዊ ደብዳቤ ያውም ያመንኩበት ካልሆነ ብትጠሩኝ አልመጣም፤ አላናግርም ብያለሁ፡፡

ከዚህ በኋለስ ይህን ተቃውሞ ለመቀጠልስ እቅዱ አላችሁ?

አቶ ታዲዎስ፡- አዎ አለን፡፡ ይህ ተቃውሞ ምላሽ አግኝቶ ያሰብነው እስኪሳካ እንቀጥላለን፡፡ ነገር ግን ዝርዝር ሁኔታውን በተመለከተ እያጠናን ስለሆነ ወደፊት ሀገር ውስጥ ያለነው ውጭ ካሉ ወገኖቻችን ጋር በመመካከር ምን መልክ መያዝ እንዳለበት ስንወስን ይፋ እናደርጋለን፡፡

በመጨረሻም የሚሉት ነገር ካለ ዕድሉን ልስጥዎት

አቶ ታዲዎስ፡- ህዝቡ ዓላማችን ከግብ እንዲደርስ የተለመደ ድጋፉን ከመስጠት ወደ ኋላ እንዳይል አደራ እላለሁ፡፡

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/6715

posted by Tseday Getachew

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ 60 የአማራ ተወላጆችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ መኪና ተገልብጦ 59 ሰዎች ሞቱ

ኢሳት ዜና:-ከአካባቢው ተፈናቃይ አርሶ አደሮች ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው አደጋው የተፈጠረው፣ ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረው መኪና ትክሻ በምትባል ቀበሌ ውስጥ ጀዴሳ በሚባል ወንዝ ውስጥ ገብቶ ነው።
ከትናንት ወዲያ በተፈጠረው አሰቃቂ አደጋ ለሞቱት ሰዎች የደረሰላቸው ሰው አለመኖሩን ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይገልጽ የፈለጉ ተፈናቃይ አርሶደሮች ተናግረዋል።
ከሞቱት መካከል ህጻናትና ሴቶችም ይገኙበታል። በአደጋው ዙሪያ የክልሉን ባለስልጣናት ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።
በተመሳሳይ ዜናም በዛሬው እለት በርካታ አርሶ አደሮች በክልሉ ልዩ ሚሊሺያ ጥቃት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።
የክልሉ ባለስልጣናት የሚፈናቀሉት ሰዎች በህገወጥ መንገድ ወደ ክልሉ የገቡ ናቸው ሲሉ ለአዲስ አድማስ መናገራቸው ይታወሳል።
የዜጐች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብትን በተለከተ አስተያየታቸውን የሰቱት የሕግ ባለሞያ አቶ ግዛው ለገሠ የሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 32 “የመዘዋወር ነፃነት” በሚል ርእስ ስር ‹‹ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ አገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ፤ በመረጠው የአገሪቱ አካባቢ የመኖርና የመኖሪያ ቦታ የመመስረት እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከአገር የመውጣት መብት እንዳለው መደንገጉን ለጋዜጣው ገልጸዋል።

posted by Tseday Getachew

ሳዑዲና ዓባይ ምን አገናኛቸው?

ሳዑዲ ዓረቢያንና አፍሪካን (ዓባይን) የከፈለውን ቀይ ባህርን ስናስብ እንዴት ሳዑዲ ዓረቢያ ከዓባይ ጋር ልትያያዝ የምትችለው ብለን ላናስብ እንችላለን፡፡ ምንም ዓይነት መቀራረብም ሆነ ጉርብትና የላቸውም፡፡ የሰውየውን መልዕክት አዘል ንግግር ስናስብ ደግሞ ሳዑዲ ዓረቢያ ለግብፅና ለሱዳን ጠበቃ ለመቆም የተናገረችው ሊመስለን ይችላል፡፡ ይህንንም ከተለያዩ መላምቶችና ምክንያቶች ብለን ከምናስባቸው ጉዳዮች እየተነሳን ልናትት እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን የዓባይ ውኃ ፖለቲካን ጠለቅ ብለን ስንመረምር የምናገኘው እውነት ሳዑዲ ዓረቢያ በአንድም በሌላም መልኩ በዓባይ ውኃ ፖለቲካ ውስጥ እጇን ለማስገባት መፈለጓን እንረዳለን፡፡ ይህንም ከኢትዮጵያው ባሮ (ጋምቤላ) በተከዜ አትባራ (ፖርት ሱዳን) እስከ ቶሽካ ፕሮጀክቶች እንደሚከተለው እንቃኛለን፡፡

ሳዑዲ ስታር የማንና ለማን ነው?
ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጥግ ብቻውን አገር ሆኖ የሚታየው ትልቁ የሚሊኒየም አዳራሽ በአንድ ወቅት በውጭ በኩል ባለው ግድግዳው እጅግ ትልቅ የሆነ ማስታወቂያ ሰቅሎ ነበር፡፡ ስለ “ሳዑዲ ስታር አግሪካልቸራል ዴቭሎፕመንት” ኩባንያ የሚለፍፈው ያ ማስታወቂያ እጅግ አረንጓዴ የሆነ የሩዝ ማሳ ያሳያል፡፡ ባለቤቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሳዑዲው ዜጋ ሼክ መሐመድ አል አሙዲ ናቸው፡፡ በምዕራብ ጋምቤላ ወደ 10,000 ሔክታር መሬት እጅግ ርካሽ በሆነ የሊዝ ኪራይ (158 ብር በዓመት ለአንድ ሔክታር) የተረከበው ይህ ድርጅት እስከ 2020 ድረስ ወደ 2.5 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ ያፈስበታል የተባለው ይህ ፕሮጀክት ዋና ምርቱ ሩዝ ሲሆን፣ በዋናነትም ለውጭ ገበያ የሚቀርብ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በምግብ ራሷን ያልቻለችው ኢትዮጵያ ለም መሬቶችን ለግዙፍ ኩባንያዎች እየሰጠች ሲሆን፣ በዋናነትም የውጭ ምንዛሪን ለማግኘት፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማምጣት እንደሆነ ይታመናል፡፡ ከዚህ አንፃር እሳቤው ባይከፋም ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ እንደሆነ ግን ሳንገልጽ አናልፍም፡፡

እንግዲህ ሳዑዲ ስታር የተባለው የሼክ አል አሙዲ ድርጅትም ምርቱን በዋናነት ለሳዑዲ ዓረቢያ ሊያቀርብ የታሰበ እንደሆነ የታመነና የተነገረ ነገር ነው፡፡ ባለሀብቱም ከሳዑዲ ንጉሣዊ ቤተሰቦች ጋር ባላቸው መቀራረብ ጋር ተነጋግረው የተጀመረ ግዙፍ ፕሮጀክት እንደሆነ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲናገሩ መስማቴን አስታውሳለሁ፡፡ ይህ የሚያሳየን ሳዑዲ ዓረቢያ በአንድም በሌላም መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የዓባይ ውኃ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የራሷ የሆነ የጥቅም ፍላጎት አላት ማለት ነው፡፡ ጋምቤላ ውስጥ ያሉ ወንዞች የዓባይ ገባር መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡

ዋናው ጥያቄ የሚሆነው ይህ ጥቅም እያለ እንዴት የሳዑዲው ምክትል መከላከያ ሚኒስትር በእንደዚያ ዓይነት አካሄድ “ኢትዮጵያ የዓረቡን ዓላም ከመጉዳት ቦዝና አታውቅም” ሊሉ ቻሉ? እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ አገሮች የተሻለ ነው የሚሉትን ጥቅማቸውን እንደሚያሳድዱ ግልጽ ሊሆንልን ይገባል፡፡ ይህ ጥቅማቸውም ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ባሕላዊ፣ ሃይማኖታዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህም በመነሳት ሚዛን ወደሚደፋው ጥቅማቸው ያጋድላሉ ማለት ነው፡፡ ሳዑዲ ዓረቢያም ያን እንዳደረገች የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ያምናል፡፡ ይህንም ለመረዳት በሳዑዲ ዓረቢያና በታችኞቹ የዓባይ ተፋሰስ አገሮች (ግብፅና ሱዳን) መካከል ያለውን ከዓባይ ውኃ ጋር የተያያዘ ግንኙነት ማጤን ይገባል፡፡

የግብፁ ቶሽካ ፕሮጀክትና ሳዑዲ ዓረቢያ
አሁን በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የግብፅ መሪ ሆስኒ ሙባረክ እ.ኤ.አ በ1997 “New Nile Valley Project” “የአዲሱ የናይል ሸለቆ ፕሮጀክት” በሚል ግዙፍ የሆነውን የሰሐራ በረሃን የማልማት ዕቅድ ነድፈው ያም ዕቅድ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል፡፡ በተያዘለት ዕቅድ ከተከናወነ ይህ ፕሮጀክት እ.ኤ.አ በ2017 ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ እየተጠበቀ ቢሆንም፣ በሌላ በኩል የማጠናቀቂያ ጊዜው እስከ 2020 ድረስ መሆኑን በቅርብ ጊዜ ከወደ ግብፅ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህ ፕሮጀክት በዋናነት ሁለት ምዕራፎች ሲኖሩት አንደኛው በሰሜን ምሥራቅ ግብፅ የሚገኘው የአል-ሰላም ቦይ (canal) ፕሮጀክት ነው፡፡ እሱም ውኃ ከዓባይ ግርጌ በመጥለፍ ወደ ሲና በረሃ ማሻገር ነው፡፡
በዘሪሁን አበበ ይግዛው
ይህን በማድረግ ብዙ መቶ ሺሕ ሔክታር መሬት በማልማት 750 ሺሕ ግብፃውያንን ለማስፈር ያለመ ነው፡፡ ዋናውና ትልቁ ፕሮጀክት ግን የቶሽካ ፕሮጀክት ሲሆን፣ ይህም የደቡብ ምዕራብ ግብፅ በረሃን ለማልማት ያቀደ ፕሮጀከት ነው፡፡ በግብፃውያኑ ዘንድ ይህ ፕሮጀክት አሁን ባለው ሁኔታ እ.ኤ.አ 2020 ያልቃል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ፕሮጀክቱ በዋናነት አዲስ ግብፅን በበረሃው ለመፍጠር ያቀደ ሲሆን፣ የተለያዩ በርካታ የውኃ ቦዮችንና የውኃ መምጠጫ ፓምፖዎችን በመገንባት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ይህን በማደረግ በረሃውን በማልማት ወደ ሦስት ሚሊዮን ግብፃውያንን የማስፈር ዕቅድ አላቸው፡፡ እንደ ግብፃውያኑ ከሆነ ይህ ፕሮጀክት ውኃውን የሚያገኘው በናይል ላይ ከተሠራው የአስዋን ግድብ ጀርባ ከሚገኘው የናስር ሐይቅ ነው፡፡ ግብፃውያኑ ይህን ሥራ የትኞቹንም የላይኛውን የተፋሰስ አገሮች ሳያናግሩ ሲሠሩት ውኃውን ከየት እንደሚያመጡት ያሰቡ አልመሰሉም፡፡ እነሱ እ.ኤ.አ በ1959 ከሱዳን ጋር የተፈራረሙት በሌሎቹ አገሮች ውድቅ የተደረገው “ስምምነት” ለራሳቸው በሰጡትና በመደቡት 55.5 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ራሽን/ኮታ መሠረት “ያላቸውን” ውኃ ለመጠቀም በማሰብ ነው፡፡
ሆኖም ግን ይህ ኮታ በሌሎቹ የላይኛው ተፋሰስ አገሮች ዘንድ ተቀባይነት ስለሌለው ግብፃውያኑ ውኃውን ከየት እንደሚያመጡት አሁንም ግልጽ አይደለም፡፡

እንግዲህ የሳዑዲ ዓረቢያ ሚና በዚህ ፕሮጀክት ላይ ምንድን ነው? ስንል ታላቅ ኢንቨስትመንትን እናገኛለን፡፡ የሳዑዲው ልዑል አል ዋሊድ ቢን ጣላል ቢን አብዱላዚዝ አልሳዑድ “ዘ ኪንግደም አግሪካልቸራል ዴቨሎፕመንት” የተሰኘ ኩባንያ ባለቤት ሲሆኑ፣ ግብፅ ውስጥ በጥቅሉ ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ካፒታል ያንቀሳቅሳሉ፡፡ በቶሽካ ፕሮጀክት ደግሞ ከ10 ሺሕ ሔክታር በላይ መሬት ተረክበው የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ለማምረት ከግብፅ የውኃና የመስኖ ልማት ሚኒስቴር ጋር ተፈራርመዋል፡፡ በየዓመቱም በሚሊዮኖች ለዚሁ የቶሽካ ፕሮጀክት አካል ለሆነው መሬት እንደሚያፈሱ ገልጸዋል፡፡ ስለዚህ እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ ግብፅ ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ ያሉት የሳዑዲ ቤተሰብ የሆኑት የንጉሡ ዘመድና ልዑሉ እንጂ ከኢትዮጵያዊ እናት የተገኙት ሼክ አል አሙዲ አይደሉም፡፡ ይህም ማለት ለሳዑዲ ዓረቢያ ቤተ መንግሥትም ሆነ ለምክትል መከላከያ ሚኒስትሩ የሚቀርቡት ሼክ አል አሙዲ ሳይሆኑ ልዑል አል ዋሊድ ቢን ጣላል ናቸው፡፡ ስለዚህ የምክትል መከላከያ ሚኒስትሩ ንግግር ከዚህ አንፃርም ሊታይ ይችላል፡፡

ዓባይ ኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ ከሚለው ፅሁፍ የተወሰደ
በዘሪሁን አበበ ይግዛው
ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው zerihun.yigzaw@graduateinstitute.ch ማግኘት ይቻላል፡፡

posted by Tseday Getachew

የትግራይ ህዝብ ‘ብኡ የሕልፎ’ በሚል የህወሓትን ጭቆና የተቀበለው ለምንድነው? (ኣብርሃ ደስታ ከመቐለ)

“… የትግራይ ህዝብ በሙሉ የህወሓት ደጋፊ ነው ማለት ኣይቻልም። ብዙ የሚቃወም ኣለ። ብዙ የሚጨቆን ኣለ። በትግራይ የሌለው ጭቆናን የሚያጋልጥ ሰው ነው። በሌሎች ኣከባቢዎች (ከትግራይ ውጭ) ሰው ሲታሰር ወይ ሲገደል የሚናገርለት ወይ የሚጮህለት ወገን ኣለው። በትግራይ ግን የለም። ኣንዱ ሲታፈን ሌላው ኣብሮ ዝም ይላል። ይሄ ነው ልዩነቱ እንጂ በትግራይ ጭቆና ስለሌለ ኣይደለም።”

ከዚህ በመነሳት Prof. Mesfin Wolde-Mariam እንዲህ ጠየቁ:

“አብርሃ ደስታ፤ ያልከውን አምናለሁ፤ ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህና አንተ በተመቸህ መንገድ መልስልኝ፤ በትግራይ ሰዎች ሲበደሉና ሲጠቁ ሌላው ሰው ዝም የሚለው በምን ምክንያት ነው?”

መልስ

ኣብዛኛው የትግራይ ሰው የህወሓት መንግስት በዜጎች በደል ሲያደርስ ከመቃወም ይልቅ “ብኡ የሕልፎ” የሚል ብሂል (ወይ ኣባባል) ተግባራዊ ያደርጋል። “ብኡ የሕልፎ” የትግርኛ ኣባባል ሲሆን Literally ‘በዛ ይለፍልን’ (ወይ ‘የባሰ ኣታምጣ’) ዓይነት ትርጉም ኣለው።

ለምንድነው የትግራይ ህዝብ ‘ብኡ የሕልፎ’ (የባሰ ኣታምጣ) በሚል የህወሓትን ጭቆና ‘ኣሜን’ ብሎ ለመቀበል የሚገደደው?

(1) ደርግ በትግራይ ህዝብ ብዙ ግፍ ያደረሰ ቢሆንም ህወሓት ከደርግ የባሰ ኣደገኛ ገዳይ መሆኑ የትግራይ ህዝብ በደምብ ያውቃል። የህወሓት የኣገዳደል ወይ ጭቆና ስልት በጣም የረቀቀ ነው። በዚህ የረቀቀ መንገድ ብዙ የትግራይ ተወላጆች ተገድለዋል ወይ እንዲጠፉ ተደርገዋል። ስለዚ የትግራይ ህዝብ ‘ህወሓት ከደርግ የባሰ ኣደገኛ ነው’ ብሎ ያስባል፤ ይፈራልም። ለምሳሌ እኔ ህወሓትን ፊት ለፊት ስቃወም ብዙ ጓደኞቼ ህወሓት ሊገድለኝ እንደሚችል ስጋታቸው ያካፍሉኛል። (የህወሓት ተግባር በደምብ ስለሚረዱ)። ይህም ሁኖ ግን በኣሁኑ ሰዓት ብዙ የሚቃወም ኣለ። (ፓርቲውም እየተዳከመ ነው)።

(2) የትግራይ ህዝብ: ህወሓት ደርግን ማሸነፍ በመቻሉ (ደርግ ኣስፈሪ ነበር) ‘ሃይለኛ ነው’ የሚል የሃሰት ግምት ተሰጥቶታል። በዚ መሰረት ህወሓት በሰለማዊ ተቃውሞ ስልጣን ሊለቅ ይችላል የሚል እምነት የለውም። የህወሓት ካድሬዎች (ፖሊት ቢሮ ኣባላትን ጨምሮ) ለህዝቡ የሚናገሩት ይሄንን ነው። “ጫካ ገብተን፣ ብዙ መስዋእት ከፍለን ያመጣነው ስልጣን በምላሳቸው ለሚቃወሙን የደርግ ርዝራዦች ስልጣን ኣሳልፈን ልንሰጥ ኣንችልም ይላሉ።

የትግራይ ህዝብ ታድያ እንዴት በሰለማዊ ተቃውሞ ስልጣን ሊለቅ የማይችልን ስርዓት ይቃወም? ህዝቡ ህወሓቶች ከስልጣን እንደማይወርዱ ኣምኖ ከተቀበለ ፣ መቃወም ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን መረዳቱ ኣይቀርም። መቃወማቸው ዉጤት ካላመጣ የሚቃወሙ ሰዎች ይገለላሉ፣ የባሰ በደል ይደርሳቸዋል። (የEDU ደጋፊዎች ነበሩ ተብለው የተፈረጁ ሰዎች እስከኣሁን ድረስ በመጥፎ ዓይን ይታያሉ)።

ከተቃወሙ ስራ ኣያገኙም ወይ ከስራቸው ይባረራሉ። የመንግስት ኣገልግሎት (መብታቸው ቢሆንም) ይነፈጋሉ። ለምሳሌ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የደገፉ ሰዎች፣ ከመንግስት ምንም ዓይነት ድጋፍ (የፖሊስ፣ ዳኝነት፣ የደህንነት ከለላ ባጠቃላይ) ‘ኣንፈልግም’ ብለው እንዲፈርሙ (መቃወምን ከመረጡ ማለት ነው) የሚያስገድድ ማስፈራርያ ይደርሳቸዋል (በተለይ በገጠር ኣከባቢ)።

ስለዚ በትግራይ መቃወም ማለት የመንግስት (ፓርቲ) ለውጥ ለማምጣት መታገል (ከተሳካም ገዢው ፓርቲ መቀየር) ማለት ሳይሆን የመንግስትን ኣገልግሎት ላለማግኘት መወሰን (በራስ ላይ ችግር መፍጠር) ማለት እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል። ከዚህ የምንረዳው ነገር ቢኖር በትግራይ መቃወም ክፉኛ እንደሚጎዳ ነው። ለዚህ ነው ኣንዱ ሲታፈን ሌላው ኣብሮ ዝም የሚለው።

(3) የህወሓት የጥላቻ ፖለቲካ ወይ ፕሮፓጋንዳ ሌላው ምክንያት ነው። ህወሓት ደርግን የፈፀመው ግፍ እንደ ጥሩ ኣጋጣሚ በመጠቀም “እኔ ከሌለሁ ጅብ ይበላችኋል” ይለናል። በደርግ ዘመን ደርግና ህወሓት ትግራይን ለመቆጣጠር ባደረጉት ጦርነት የትግራይ ህዝብ ብዙ ስቃይ ኣሳልፈዋል። በጦርነቱ ምክንያት ብዙ ግድያ ነበረ፣ ትምህርት ኣልነበረም፣ ሰላም (መረጋጋት ማለቴ ነው) ኣልነበረም፣ ገበሬው፣ ነጋዴው … በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት ኣልቻለም ነበር። ባጠቃላይ ያ ዘመን ለትግራይ ህዝብ (ለመላው የኢትዮዽያ ህዝብም ጭምር) መጥፎ ነበር። ህወሓት ታድያ (ደርግን በማባረሩና ጦርነቱ ጋብ ስላለ) ‘ከዚህ ሁሉ ችግር ያዳንኳቹ እኔ ነኝ። እኔ ባልኖር ኖሮ የደርግ ወታደር ይበላቹ ነበር። ህወሓቶች ከሌለን ደርግ መጥቶ ይገድላችኋል” ይለናል።

ይባስ ብሎ ደግሞ ህወሓት ከትግራይ ህዝብ ድጋፍ ለማግኘት የደርግን ኣስከፊነት ያስታውሳል፤ የተከፈለ መስዋእትነት 24 ሰዓት ይተርካል። ይህ የትግራይን ህዝብ ቁስል በመንካት ድጋፉን እንዲሰጥ የማስቻል ስትራተጂ ነው። ለዚህ ዓይነት ፕሮፓጋንዳ የሚነዙ ኣንድ ሬድዮ (ድምፂ ወያነ) ና ሦስት ኤፋኤም FM ሬድዮ ጣብያዎች ኣሉ።

ከዚህ በተያያዘ ህወሓት ህዝብን ሲሰብክ ደርግ ኣማራ ኣድርጎ ያቀርበዋል (የደርግን ዓይነት ጨቋኝ ስርዓት የመምጣት ዕድል እንዳለ ለማመልከት ተፈልጎ ነው)። ደርግ ላይመለስ ሞተዋል። ስጋት ሊሆን ኣይችልም፣ ተመልሶ ሊመጣ ኣይችልም። ህወሓት ግን ህዝቡን ለማጭበርበር እስከኣሁን ኣደጋው እንዳለ ለመጠቆምና የትግራይን ህዝብ ድጋፍ እንዳይለየው ለማድረግ ‘ፀረ ደርግ’ የነበረ ትግል ‘ፀረ ኣማራ’ እንደሆነ ኣድርጎ ኣቀረበልን። (በኣንደኛ ደረጃ ትምህርታችን ሳይቀር ተምረነዋል።)

በኣሁኑ ሰዓት ታድያ ሰው (ከትግራይ) ሲቃወም: “ከነዚህ የጠላት ቡድኖች (በብሄር ደረጃ ኣማራ ወይ ሸዋ) ወይ የደርግ ርዝራዦች (Remnants of the Derg Regime) ወግኖ ደርግን ወደ ስልጣን ለማስመለስ ህወሓትን ይቃወማል” በሚል ሰበብ ስሙ ይጠፋል። (እኔ ህወሓት ስለ ተቃወምኩ የሚሰጠኝን ስም መመልከት ይቻላል)። ይሄ ነገር ታድያ እየታፈንክ ዝም ኣያሰኝም???

(4) ደርግ የትግራይን ህዝብ ጠላት ተደርጎ ነው የሚወሰደው (በፈፀመው ግፍ)። የትግራይ ህዝብ ያን የደርግ ኣገዛዝ ኣይፈልግም። ‘ደርግ ይመለሳል’ ከተባለ ታድያ (ማመዛዘን ቢያስፈልግም) ህዝቡ ከደርግ ህወሓትን መምረጡ እንዴት ይቀራል?

የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ሲቃወም ከተቃዋሚዎች ጎራ እንደተሰለፈ ይቆጠራል። ተቃዋሚዎች ደግሞ ‘ደርጎች’ መሆናቸው ነው ለህዝቡ ሲነገር የቆየው። ስለዚ ኣንድ ሰው (ወይ ብዙ ሰዎች) ህወሓትን ከተቃወመ ከደርግ ጋር እንደተባበረ ነው የሚቆጠረው። በትግሉ ወቅት ከደርግ ጋር የተሰለፈ ሰው ምን ዓይነት ቅጣት ይሰጠው እንደ ነበር ህዝቡ በደምብ ያውቃል። ስለዚ የትግራይ ህዝብ ‘የመቃወም ቅጣት’ ይፈራል። ፈርቶም … ሲጨቆን ዝም ይላል (የባሰ ኣታምጣ ወይ ብኡ የሕልፎ ብሎ)።

(5) ኣብዛኛው የትግራይ ህዝብ ድሃ ነው። ድህነት በራስ የመተማመን ዓቅማችን ያሽመደምደዋል። ለመቃወም የኢኮኖሚ ነፃነት ወይ ዓቅም መገንባት ያስፈልጋል (ከገዢው መደብ ለሚደርሱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሽብሮች ለመቋቋም)። ድሃ ጭቆናውን ቢቃወም እንደውጤቱ የባሰውን ይጨቆናል። ለኣምባገነኖች; ጭቆና ተቃውሞን ለመቀነስ ይጠቀሙታል። ስለዚ የባሰውን ጭቆና ለማስቀረት ያለውን ጭቆና ‘ኣሜን’ ብሎ መቀበል (የትግራይ ህዝብ) እንደኣማራጭ የወሰደው ይመስለኛል።

ሌላው ችግር ደግሞ የትግራይ ህዝብ የመረጃ ዓፈና (ከሌሎች ክልሎች በባሰ ሁኔታ ሊባል በሚችል ሁኔታ) ይፈፀምበታል። የመረጃ ችግር ኣለ። ወደ ትግራይ የሚገባ መረጃና ከትግራይ የሚወጣ መረጃ በተቻለ መጠን ሳንሱር ይደረጋል። የትግራይ ህዝብ መረጃ እንዳያገኝ ይደረጋል። በመሆኑም የትግራይ ህዝብ ስለ የኢትዮዽያ ፖለቲካ በቂ መረጃ ኣለው ብዬ ኣላምንም።

በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ የሚፈፀሙ ችግሮች፣ በደሎች፣ ጭቆናዎች የሚዘግብና የሚያጋልጥ ሚድያ የለም። በፖለቲካዊ ተሳትፎ የሚድያ ሚና የማይናቅ ነው። በትግራይ ያሉ ችግሮች በኣግባቡ ስለማይዘገቡ ሰሚ ኣያገኙም። ሰሚ ካላገኙ (1) ሰዎቹ ተቃውመው ምንም ለውጥ ሊያመጡ እንደማይችሉ ስለሚረዱ እየተጨቆኑም ዝም ብለው ዝም ይላሉ፤ (2) ካልተዘገቡ በሌሎች ህዝቦች በትግራይ ችግር እንደሌለ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።

ስለዚህ ገዢው ፓርቲ ዓፈናን ለመሸፈን ዓፈናን (ራሱ) እንደመሳርያ ይጠቀመዋል። እንደውጤቱም በትግራይ ተቃውሞ እንኳ ቢኖር ስለማይዘገብ ግን ህዝቡ ህወሓትን እንደሚደግፍ ወይ እንደማይቃወም ተደርጎ ይወሰዳል። ትልቁ ችግር ይሄ ነው።

(6) የትግራይ ህዝብ የገዢው ፓርቲ ዓፈናን ተቋቁሞ ዝምታን የሚመርጥበት ዋናው ምክንያት ስለተቃዋሚዎች ትክክለኛና በቂ መረጃ ስለሌለውና ተቃዋሚዎችም ለህዝቡ ቀርበው በማነጋገር ዓላማቸውና ማንነታቸው በግልፅ ማስረዳት ባለመቻላቸው ነው።

ተቃዋሚዎች የትግራይን ህዝብ በሙሉ ህወሓትን እንደሚደግፍና ‘ጠላት’ እንደሆነ ኣስመስለው እንደሚያቀርቡ በብዙ የትግራይ ተወላጆች (በህወሓት ፕሮፓጋንዳ ምክንያት) ይታመናል። ይህንን እምነታቸው ህወሓትን የሚጠቀመው “ተቃዋሚዎች ደርጋውያን ናቸው፣ ደርግ ሙሉ በሙሉ ሞቶ ስላልተቀበረ ህወሓት እስከኣሁን ድረስ ከደርግ ጋር እየተዋጋ ነው ወዘተ” የሚል የማጭበርበር ፕርፓጋንዳ ለመቀበል ይገደዳሉ።

በዚ መሰረት ህወሓትን እየተቃወመም ቢሆን የተቃዋሚ ድርጅቶች ግን ከህወሓት ሊብሱ ይችላሉ ብሎ እንዲያስብ ስለሚገደድ ግራ ተጋብቶ ‘የባሰ ኣታምጣ’ ብሎ ኣብሮ ዝም ይላል።

ስለዚ ተቃዋሚዎች ከትግራይ ህዝብ ጋር መወያየትና መግባባት ያስፈልጋቸዋል። ምክንያቱም ሳያውቁት (በሚጠቀሙት የፖለቲካ ስትራተጂ) የትግራይን ህዝብ (target የሚያደርጉ ስለሚመስሉ) በህወሓት ቢጨቆን እንኳ ህወሓትን ላለመቃወም እንዲወስን (የባሰ እንዳይመጣ) ያደርጉታል። ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ዝምታ ምክንያት ኣለው (ህወሓት ስለሚደግፍ ግን ኣይደለም)።

“የትግራይ ህዝብ” የሚወክለው ኣብዛኛውን ህዝብ እንጂ ጥቂት የስርዓቱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ተጠቃሚዎችን ኣያጠቃልልም። ጥቂት የስርዓቱ ተጠቃሚዎች በሚሰሩት ተግባር ሁሉም የትግራይ ህዝብ ህወሓት እንደሚደግፍ ኣስመስለው ለማቅረብ ስለሚሞክሩ ሌሎች ሰዎች እውነት ሊመስላቸው ይችላል።

… ግን ዝምታ መፍትሔ ሊሆን ኣይችልም።

http://ethioforum.org

posted by Tseday Getachew

ነጋሶ ሞገቱ ወይስ ተሞገቱ?

 

“ኢህአዴግ በህዝብ (ያልተመረጠ) ስለሆነ እውቅና አንሰጠውም”

N G

“ … አንተም ሆንክ ማንም ኢትዮጵያዊ ውጪ ያሉትን ጨምሮ ቢደግፉን ደስ ይለናል። በዚህ መንገድ ሂዱ ብለው እንዲጠመዝዙን ግን አንፈልግም። … ሰላማዊ ትግል የምትሉት ለውጥ አያመጣም ይሉናል። እንደዚህ የምትሉ ከሆነ ከፈለጋችሁ ገንዘብ አትርዱን እንላቸዋለን … ኢህአዴግን እንደ መንግስት እውቅና አንሰጠውም” ከዶ/ር ነጋሶ የተመረጡ መልሶች መካከል የተጠቀሱ ናቸው። በዚህና በሌሎች ምክንያቶች ዶ/ር ነጋሶ ሊሞገቱ ሄደው ሞገቱ የሚል ርዕስ ለጽሁፌ መረጥኩ።

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አንድነትን በመወከል ሬዲዮ ፋና በሚያዘጋጀው የ”ሞጋች” ቃለ ምልልስ ክፍለ ጊዜ ላይ ተገኝተው ነበር። ቃለ ምልልሱ ከመጀመሩ በፊት “ጋዜጠኛው” ፕሮግራሙ ፈረንጆቹ እንደሚሉት “ሃርድ ቶክ አይነት ነው” አለ። ይህን ጊዜ ቀልቤን ሳበኝ። የቢቢሲው የሃርድ ቶክ ክፍለጊዜና የጠያቂው ጠልቆ የመግባት ችሎታ ታየኝና ዶ/ር ነጋሶ ሲዝረከረኩ ለመስማት ተዘጋጀሁ።

ጥያቄ ተጀመረ። ዶ/ር ነጋሶ መመለስ ቀጠሉ። የመጀመሪያዎቹ ጥያቄዎች የተለመዱ፣ የተረገጡ፣ የተሰለቹና በየመድረኩ ብዙ የተባለላቸው ሆኑብኝ። ዶ/ር ነጋሶም ሳይቸገሩ ከፈገግታ ጋር መለሱ። በመነሻው የቀረቡትን የተለመዱ ጉዳዮች በመዝለል በሶስት ጉዳዮች ላይ በማተኮር ሪፖርት ለማዘጋጀት ወሰንኩ።

ስለ ጠያቂው

አቶ ሴኩ ቱሬ ጌታቸው

ጠያቂው ጋዜጠኛ ነጋሶን ሲጠይቅ ላዳመጠ ጋዜጠኛ ሳይሆን ትክክለኛ ስሙ “ካድሬ” ነውና በዚህ ይስተካከል። መጀመሪያ ላይ “ይባላል፣ ይነገራል፣ ይደመጣል፣ አስተያየት ይሰጣል …” በማለት አግባብ ያለው አካሄድ ተከተለና በኋላ ላይ ግምገማ ፍርሃቻ ነው መሰል ነጋሶን አላናገር ብሎ ጭልጥ ያለ ክርክር ውስጥ ሲገባ ከኋላው አቶ ሴኩ ቱሬ ጌታቸው ምናምን የሚያሳዩት ይመስል ነበር። ያም ቢሆን “ገራም”፣ ቀስ ብሎ የሚናገርና በድርጅት ፍቅር የደረቀ አይመስልም።

የግራ ዘመም ስለመሆናቸው

ነጋሶ አሁን የሚመሩት አንድነት ፓርቲ የሊብራል ፖለቲካ እሳቤ አቀንቃኝ ነው። እሳቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ “የግራ ዘመም” ፖለቲካ አፍቃሪ ነበሩ። ኢህአዴግ ውስጥም ዋናው የልዩነታቸው መሰረት የግራውን መንገድ በትክክል መከተል ያለመቻልና የመበረዝ ችግር ነው። ዛሬ ምን ተገኘና ነው አዲስ አቋም የተያዘው በሚል ጠያቂው ያነሳው ሃሳብ የስሙን ያህል ባይሆንም ሙግት አስነስቶ ነበር። ጥያቄው ግን ምላሽ ያገኘው ውይይቱ ሲያልቅ ነው።

“ግራ ዘመም ምንድነው” አይነት ጥያቄ አንስተው ከዓለም ወቅታዊ ሁኔታ ጋር መመሳሰል አግባብ እንደሆነ በማስገንዘብ አስተያየታቸውን የሰጡት ነጋሶ፣ “ትክክለኛ” የሚሉትን ሶሻሊዝም እንደሚናፍቁ አልሸሸጉም። ይህ አስተሳሰባቸውና እምነታቸው አንድነት ከሚከተለው መንገድ ጋር እንዴት ሊጣጣም እንደሚችል የገለጹት ግን ዓለምን መምሰል በሚለው እሳቤ ነው። ጠያቂው በውይይቱ ማሳረጊያ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት በድጋሚ ይህንኑ ጉዳይ አንስቶ ነበር። ነጋሶ ግን “አንድ ሰው ድንጋይ አይደለም። አቋሙን መቀየር ወንጀል አይደለም” በሚል ዘጉት። አዎ፣ አቋም ለያውም በፖለቲካው ጎዳና የሚቀያየር፣ ዓለምን እያዩ የሚበውዙት የካርታ አይነት ጨዋታ ነው። እናም “እሰይ አበጀሁ” አይነት መልስ መልሰው ተሰነባበቱ።

የጣመኝ ፈርሙክርክር

የምርጫ የስነ ምግባር ኮድ ጉዳይ ለዚህ ሪፖርት አቅራቢ ምርጥ የተባለና የነጋሶ የህግ ግንዛቤ በቀላሉ ነገሮችን በማስረዳት ጎልቶ የወጣበት ነበር። እንዲህ ተባባሉ። ጠያቂው “የምርጫ ስነ ምግባር ኮዱን ብትፈርሙ ምን ትሆናላችሁ?” አለ። “አዋጅ በሆነ ጉዳይ ላይ ለምን እንፈርማለን። እንደዚህ ከሆነ ባገሪቱ በየጊዜው በሚወጡ ህጎች ላይ እንፈርማ?” የነጋሶ ውድ መልስ ነበር።

ጥያቄ፦ ብትፈርሙ ምን ይጎዳችሁዋል …?

ነጋሶ፦ ለምን እንፈርማለን? ለህዝብ ጥቅም ሁላችንም ስንሰራ ኢህአዴግ በሚለው ተንበርክከህ ኢህአዴግን በምርጫ በማጀብ አይደለም …

ጥያቄ፦ ጉዳት አለው ህዝቡ ይጎዳል? ህግ ሆኗል አይደለም?

ነጋሶ፦ የስነ ምግባር ኮዱ ብቻውን በቂ አይደለም፤…. የኢህአዴግ አዲሱ ሊቀመንበር በመጀመሪያው ንግግራቸው ያሉትን አልሰማህም?

ጥያቄ፦ … ምን ጉዳት ይደርስባችኋዋል?

ነጋሶ፦ እነሱ ቢወያዩና ችግራቸውን ቢያስወግዱ ምን ችግር አለው?

ጥያቄ፦ ፖለቲካ አብሮ የመኖር ጥበብ ነው። አብሮ መስራት ጥቅም አለው፤

ነጋሶ፦ ያ! ያ! አብሮ መስራት በእኩልነት ነው እኮ!! ኢህአዴግ አንድ የፖለቲካ ሃይል ነው ወይስ አይደለም? ለምን እንበረከካለን? ንግረኝ?

ጥያቄ፦ ለህጉ ትገዙ አይደል?

ነጋሶ፦ ያ!! እኮ፤ አዋጅ ሆኖ በወጣ በስንት ህግ ላይ እንፈርማለን? ይህ ከሆነ ፓርላማ ቢስማማም ባይስማማም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሁሉም ጉዳዮች ላይ መፈረም አለበት ማለት ነው፤

በቀጣይ ወደ ሌላ የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ አልፉ። ማጠቃያው ላይ አነሳዋለሁ፡፡

ለስደተኞችና ለስደተኛ አስተሳሰብ ትገዛላችሁ?

ጠያቂው ሊሞግት ያሰበበት ዋናው ጉዳይ መድረክም ሆነ አንድነት ከዲያስፖራው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በሚያውጣጣና በትጥቅ ትግል ከሚያምኑ ወገኖች ጋር ለመደመር ነበር። ከውጪ ሃይሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ እንደሚታሙና ለዚህም መረጃ እንዳለው አንስቶ ላቀረበው ጥያቄ ማሰሪያ ያደረገው “አገር ቤት ያለውን ህዝብ አክብሮት አትሰጡትም። ለስደተኛና ለስደተኛ አስተሳሰብ ልዩ አክብሮት አላችሁ” የሚል ነበር።

ነጋሶ ከወትሮው ለየት ብለው ፖለቲካኛ የሆኑበትን መልስ የሰጡት ዲያስፖራውም ሆነ ማንም፣ ጋዜጠኛውን ጨምሮ ቢደግፉዋቸው ደስተኛ መሆናቸውን በማመለካት መልስ ጀመሩ። አስከትለውም “በየኤምባሲው ደጅ አይታጡም” እንባላለን አሉ። ነጮቹ የሚሰጡት ድጋፍ ለተሰጠበት ዓላማ እንዳልሆነ ለምን አትናገሩ ይባላል? በማለት ጠየቁ።

ስለ ዲያስፖራውና “ስደተኛ አስተሳሰብ” ስለተባሉት ሲናገሩ የሰላማዊ ትግል መንገዱ አያዋጣም የሚሉዋቸው እንዳሉ አመለከቱ። ሲያጠቃልሉት ማንም ይሁን ማን “ሰላማዊ ትግል አያዋጣችሁም ለሚሉን ከፈለጋችሁ ገንዘባችሁን አትርዱን እንላቸዋለን” በማለት የራሳቸውን መንገድ እንደሚከተሉ ገልጸው ጥያቄውን ቆለፉት።

አገር ውስጥ ያለውን ህዝብ አታከብሩትም ለሚለው ግን “በርግጥ በሚፈለገው ደረጃ ህዝብ ውስጥ ላንቀሳቀስ እንችላለን” በማለት ራሳቸውን ጥፋተኛ አስመስለው ቢሮ ይታሸግብናል፣ እኛን የሚደግፉ ከስራ ይባረራሉ፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አይፈቀድልንም፣ ሰላማዊ ሰልፍ እንድናደርግ አይፈቀድም፣ መምህራን እኛን ስለደገፉ ይባረራሉ፣ … ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ኢህአዴግ እንደሆነ ተናገሩ።

ኢህአዴግን ተቀብለውና ደግፈው ከሚሰሩ ፓርቲዎች ጋር አብረው መስራት እንደማይችሉ ሲገልጹ “ኢህአዴግን ከሚደግፉት ጋር ተቀምጠን ምን አብረን ልንሰራ እንችላለን” ካሉ በኋላ “ኢህአዴግን እንደመንግስት እውቅና ሰጥተው ከሚንቀሳቀሱት መካከል ኢዴፓ በርካታ ልዩነቶች አሉት ግን ኢህአዴግን እንደ መንግስት እውቅና በመስጠት ይቀበላል። እናንተስ?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ “ኢህአዴግ በህዝብ፣ በምርጫ ገዢ ያልሆነ ፓርቲ ስለሆነ እውቅና አንሰጠውም” የሚል ግልጽ መልስ ሰንዝረዋል።

“ስለ አንቀጽ 39 ለምን አሁን ትጠይቀኛለህ?”

ነጋሶ ፓርቲያቸው አንቀጽ 39 እና የመሬት ጉዳይ ላይ ስላለው አቋም ግልጽ ያለ መልስ እንዲሰጡ በተደጋጋሚ ተጠይቀው ነበር። በግራም ሆነ በቀኝ፣ እሳቸው በጻፉት መጽሃፍ ላይ ካቀረቡት ሃሳብ ጋርና ቀደም ሲል ኢህአዴግ በነበሩበት ወቅት ሲያራምዱት ከነበረው ሃሳብ አንጻር የሃሳብ መንሸራተት እንዳጋጠማቸው በማስመሰል ጠያቂው ሊሞግታቸው ሞክሮ ነበር። በተደጋጋሚ ለማስረዳት ቢሞክሩም ሊቀበላቸው ባለመቻሉ “አንድ ሰው ድንጋይ አይደለም። የአቋም መቀያየር ወንጀል አይሆንም” በማለት አሳርገውታል።

በጥቅሉ ግን ካላይ የተነሱት ሁለት መሰረታዊ ሃሳቦች ህዝብ ውሳኔ ሊያሳልፋቸው እንደሚገባ አመልክተዋል። መገንጠል መብት ቢሆንም እርሳቸው እንደማይደግፉት በግልጽ አስቀምጠው ያለፉት ነጋሶ፣ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በመመስረት የሚመለሱ ጉዳዮች እንደሆኑ ግን አስምረውበታል። ምንም እንኳ ፓርቲያቸው የኒዎ ሊብራል ሃሳብ አራማጅ ቢሆንም በግላቸው በነጻ ኢኮኖሚ ስም መንግስት ከዋናና ህዝብን ከሚያገለግሉ ዋና ዋና የኢኮኖሚ አውታሮች መውጣት አለበት ብለው እንዳማያምኑ አስምረውበታል። በመድረክ ውስጥ ያሉት ፓርቲዎች ተመሳሳይ አቋም ባልያዙበት ሁኔታ ግንባር መመስረቱ ችግር እንዳለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነና ዋና የሚባሉት የልዩነት ቁልፍ ጉዳዮች ህዝብ ውሳኔ እንዲሰጥባቸው በመዘርዘር አልፈዋቸዋል።

ጠያቂው መሃል በመግባት አንቀጽ 39ን ትቀበላላችሁ? በሚል ላቀረበላቸው “አሁን ለምን ትጠይቀኛለህ” በማለት አስረግጠው መልስ ሰጥተዋል። በዚሁ የራዲዮ ፋናን ስቱዲዮ በስንብት ለቀው ወጥተዋል።

ነጋሶ እንደ ፖለቲከኛ ድርጅቱ ላይ ደረሱ የተባሉትን ችግሮች በየመካከሉ በማስገባት ጥያቄን በጥያቄ መመለስ ቢችሉ ኖሮ ይበልጥ አሸናፊ ሆነው መውጣት ይችሉ ነበር። ለምሳሌ ስለህጋዊነት ሲነሳ የራዲዮ ፋና አፈጣጠር ህጋዊ አለመሆኑንና ኤፈርት ስለተቆታጠረው የኢኮኖሚ የበላይነት፣ ስለ እስርና የሚዲአ አፈና … በየመልሶቻቸው መካከል በማስገባት ቢመልሱና ጥያቄ ቢሰነዝሩ ቢያንስ ሃሳባቸውን በአድማጭ ላይ አራግፈው መውጣት በቻሉ ነበር። እንዲህ ያለ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን ሲገኝ መሰረታዊ ብቻ ሳይሆን ራሳቸው የኢህአዴግ አባላት የሚያጉረመርሙትን ጉዳዮች በማንሳት የራሳቸውን ልምድና ተሞክሮ ማካፈል ይችሉ ነበር። ጠያቂው ከኢህአዴግ ስለተለዩበት ምክንያት በሰሚ ሰሚ ላነሳላቸው ጥያቄ “ቆቅ” ፖለቲከኛ ሆነው መረጃ ማስተላለፍ ሳይችሉ መቅረታቸው የዕለቱ ድክመታቸው ቢሆንም ሊሞገቱ ተጋብዘው ሞግተው ስለመውጣታቸው የዚህ ሪፖርት አቅራቢ ምስክራቸው ነው፡፡

http://www.goolgule.com/interview-negasso/

posted by Tseday Getachew

ከእሁድ እስከ እሁድ/(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)

አንድ ላስቲክ ውሃ 10 ብር!!
በአፋር የቡሬ ነዋሪዎች ለከፍተኛ የውሃ ችግር መዳረጋቸውን ውሃ የሚሸጥበትን ላስቲክ በፎቶ በማያያዝ የጎልጉል የአይን ምስክር ከስፍራው አስታውቋል። በክልሉ የጎልጉል ተከታታይ የሆኑ እንደገለጹት በመጠጥ ውሃ ችግር እየደረሰ ያለው ችግር ከፍተኛና ህይወትን የሚፈታተን ነው። አካባቢው የጦር ቀጠና ከመሆኑ አንጻርና የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር አሳሳቢ እንደሆነ ያስታወቀው የአይን ምስክር “እባካችሁ የሚሰማ ካለ ንገሩልን” ሲል ጥሪ አስተላልፏል።

የውሃ ችግር ጊዜ የሚሰጥ ባለመሆኑ አንድ ላስቲክ ውሃ 10 ብር ለመግዛት መገዳዳቸውን፣ በዚህም ቢሆን እንደ ልብ ማግኘት እንደማይቻል አመልክቷል። በስፍራው ያለውን የውሃ ችግር አስመልክቶ ሎጊያ የሚገኝ ጎልጉል የአይን ሪፖርተር አስተያየቱን እንዲሰጠን ጠይቀነው የበኩሉን ማጣራት ካደረገ በኋላ ችግሩ መኖሩን አረጋግጦልናል። ቡሬ አካባቢ ያለው ውሃ ችግር በዋናነት የሚጠቀስ ቢሆንም በተመሳሳይ የሚቸገሩና በድርቅ የተመቱ ቦታዎች እንዳሉ አመልክቷል። አንዳንድ የወታደር ተሽከርካሪዎች ውሃ እንደሚሸጡ መረጃ ማግኘቱንም ገልጿል።

“የልማት ሰራዊት” ያልተገነባበት ምክንያት ይገምገም ተባለ
ባህር ዳር ከተማ የአራት ቀን ጉባኤ ለማካሄድ የከተመው ኢህአዴግ በበቂ ሁኔታ የልማት ሰራዊት አለመገንባቱን፣ ከፍተኛ የሚባል የገንዘብ ችግር እንዳጋጠመው፣ ኢንዱስትሪው ግብርናውን ተረክቦ ያገሪቱን ኢኮኖሚ እንዲመራው የተያዘው እቅድ የተፋዘዘ መሆኑንና የግሉ ዘርፍ በሚገባ አለመንቀሳቀሱን በመግለጸ ጉባኤው ችግሮችን መርምሮ መፍትሄ እንዲፈልግ ተጠየቀ፡፡

የ2004 የግብርና ምርት አድገት ከተያዘለት መሰረታዊ የእድገት መጠን አማራጭ “አንሶ ማደጉን”፣ ለዚህም ምክንያቱ የልማት ሰራዊት ባግባቡ መፈጠር ባለመቻሉ ነው። በተፈጥሮ ጥበቃ የተሻለ የልማት ሰራዊት መገንባት ቢቻልም በሰብል ልማት ዘርፍ ግን ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር ያለፈ ስራ እንዳልተከናወነ ተጠቆመ። “ጓድ” ሃይለማርያም ደሳለኝ ዘጠነኛው የኢህአዴግ ጉባኤ የልማት ሰራዊት መገንባት ያልተቻለበትን ምክንያት ፈትሾ፣ የድርጅቱንና የህዝቡን የማስፈፀም አቅም በመገንባት ዘርፉን ወደፊት ለማሸጋገር የሚያስችል አቅጣጫ የማስቀመጥ ሀላፊነት እንዳለበት አመልክተዋል።

የፋና ብሮድ ካስቲንግን ጨምሮ የተለያዩ የኢህአዴግ መገናኛዎች እንዳሉት “ጓድ” ሀይለማርያም በንግግራቸው በአገሪቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ “የአክራሪነት አስተሳሰቦች” ብቅ ማለታቸውን አንስተዋል። እነዚህ የአክራሪነት አስተሳሰቦች ከመሰረታዊ የአገሪቱ ህገ መንግስት መርህዎች ጋር የሚጋጩ ናቸው ብለዋል። የህዝቡን ዲሞክራሲያዊ አንድነትና እኩልነት፣ የመንግስትን ከሀይማኖት ነፃ ሆኖ ሁሉንም በእኩልነት የማገልገል ሀላፊነቱን የሚፃረሩ በመሆናቸው ሁሉም ሊታገላቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል። በሃይማኖት ቤቶችና ደጆች አስተዳደራቸው ውስጥ ሙሉ በሙሉ የሚዋኘውን መንግሥታቸውን አቶ ሃይለማርያም በንግግራቸው “አሁንም መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም” ሲሉ ገልጸውታል።

አንደበት
“……አቶ መለስ ህወሓትን ከፊት አድርገው አዲስ አበባ ሲገቡ እውነተኛ ብሔራዊ እርቅ አድርገው ቢሆን ኖሮ ዛሬ ተገፍተን በስደት ያለን ሁላችን በየሙያችን አገራችንና ወገኖቻችንን እናግዝ ነበር። የሆነው ግን የተለየ ነው። መለስ “እነሱ” ብሎ ሌሎችን በመወንጀል ጥላቻን ማወጅ ጀመረ። ትውልድን የሚያንጽ ብሄራዊ ሚዲያ ሳይቀር የጥላቻና የቂም ስብከት እንዲያስተጋባ ተደረገ። የዚህ መዘዝ ዛሬ ላይ ጣለን። የጋራ ንቅናቄያችን “እነሱ” የሚል ቋንቋ የለውም። ስንጀምር “እኛ” ብለን ነው። ይህ ልዩ ያደርገናል። የሰው ልጆች ጥላቻን ለመሸከም አይመጥኑም። ጥላቻ የሚዘራብን እንደሰው ስለማንታይ ነው። እንደ ሰው ስላልተከበርን ነው። ሰው መልካም ነገር እንዲያደርግ ከፈጣሪ የተሰጠው ልዩ ስጦታ አለው፡፡ መለስ ግን ይህንን ረስቷል። በብሄር ብሄረሰብ ስም ሲምል ሁላችንንም ሳያሳፍር ነው። ብቻውን ወይም ጥቂት ሰዎች ይዞ ወደ ጥፋት ሄደ፤….”

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ November 16, 2012 ለጎልጉል ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ።

“በአፋር የከብት መኖ ለምግብነት እየዋለ ነው”
በአፋር ክልል ካለፉት አራት ወራት ጀምሮ የተከሰተው ከፍተኛ ረሀብና የውሀ እጥረት የበርካታ ህጻናትን ህይወት መቅጠፉን ነዋሪዎች እንደገለጹለት ጠቅሶ ኢሳት ዘገበ። ምንም እንኳ 60 በመቶ በሚሆነው የአፋር አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የምግብና የውሀ እጥረት ቢከሰተም፣ ችግሩ ከሁሉም ወረዳዎች አስከፊ በሆነበት የእዳ ወረዳ 6 ህጻናት በአንድ ወር ውስጥ ሞተዋል። ይህ አሀዝ በአንድ ሰፈር ብቻ የተጠናከረ እንጂ በአጠቃላይ በወረዳው በተከሰተው ረሀብና የውሀ እጥረት የሟቾች ቁጥር በብዙ መቶዎች ሊደርስ እንደሚችል ኢሳት ነዋሪዎችን ጠቅሶ አመልክቷል።

አንድ ጀሪካን ውሀ በ60 ብር ለመግዛት መገደዳቸውን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የእዳ ወረዳ ነዋሪ መናገራቸውን የገለጸው ኢሳት፣ የአካባቢው ነዋሪ ፍየሎቹና ግመሎቹ አልቀውበት ወደ አሳይታ ስደት መጀመራቸውን፣ አሳይታ በሰላም የደረሱት በህይወት ሲትረፉ ሌሎች ደግሞ በመንገድ ላይ ማለቃቸውን አትቷል።

የመንግስት እርዳታ እንዳልመጣላቸው የተናገሩት ነዋሪዎቹ ፣ አስቸኳይ እርዳታ ካልደረሰ አስከፊ እልቂት እንደሚከሰት መናገራቸውን ኢሳት አውስቷል። በአካባቢው የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ የሚገኘው የአፋር ጋድሌ (የአፋር ተቃዋሚ ድርጅት) ሊ/መንበር ኮሎኔል ሙሀመድ አህመድ ከፍተኛ ረሀብ በአካባቢው መግባቱን ድርጅታቸው እንደሚያውቅ ለኢሳት ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እሁድ ኢሣት ፍኖተ ነጻነትን ጠቅሶ ባሰራጨው ተመሳሳይ ዜና በአፋር ረሃብ ጠንቶ የሰዎችን ህይወት ማጥፋቱን አስታውቋል፡፡ የተረፉትም በዕርዳታ የመጣ የከብት መኖ እየጋገሩ ለመመገብ መገደዳቸውን አመልክቷል፡፡

ሚድሮክ ከ632 ሚሊዮን ብር የግብር ዕዳ አለበት
ሚድሮክ ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ከንግድ ትርፍ ግብርና ከተጨማሪ እሴት ታክስ ከ632 ሚሊዮን ብር በላይ ዕዳ በመንግሥት እንደሚፈለግበት ሪፖርተር ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል። በዜናው መሰረት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በቅርቡ ለሚድሮክ ኢትዮጵያ በላካቸው ሦስት የትርፍ ግብር ውሳኔ ማስታወቂያዎች የተጠቀሰው ገንዘብ እንዲከፈል ጠይቋል፡፡

ደብዳቤው አዋጅ ጠቅሶ ከማንኛውም ንግድ ትርፍ፣ ከተጨማሪ እሴት፣ ከተጨማሪ ግብር በመቶኛ በማስላት የተጠየቀውን ገንዘብ በ30 ቀናት ውስጥ ገቢ እንዲያደርግ መጠየቁን ያስረዳው የሪፖርተር ዘገባ ሚድሮክ ግዳጁን ካልተወጣ በህግ እንደሚጠየቅ እንደተገለጸለት ያስረዳል። በሌላም በኩል ቅሬታ ካለ አቤት ማለት እንደሚችሉ በደብዳቤው ላይ መጠቀሱን ለሪፖርተር የነገሩት የሚድሮክ ምንጮቹ ናቸው።

አልጀዚራ ከታነቀ በኋላ ጠንካራ ሪፖርት አቀረበ
የአልጀዚራ የቴሌቪዥን ስርጭት ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይተላለፍ መደረጉን አልጀዚራ ድርጊቱን በመቃወም ያስታወቀው በሳለፍነው ሳምንት ነበር። ጣቢያው ስርጭቱ የተቋረጠበትን ምክንያት እንዲገልጹለት ኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄ ቢያቀርብም መልስ እንዳልተሰጠው አስታውቋል። አልጀዚራ የቢቢሲ የስለላ ሪፖርት የኢትዮጵያን መንግስት ባጋለጠ ማግስት ማስተባበያ የሚመስል ስርጭት አስተላልፎ እንደነበር የሚያስታውሱ መንግስትን በመደገፍ መልኩ ሳይሆን አልጀዚራ ለበርካታ ጉዳዮች ሽፋን እንደማይሰጥ በመጥቀስ “የጁን አገኘ” ሲሉ ተጠምደዋል። አልጀዚራ በወቅቱ የምግብ እህል ርዳታ ለፖለቲካ አላማ ይውላል በተባለበት ቦታ አርሶ አደሮች ቤታቸው ድረስ በመግባት ነበር ሰፊ ከኢቲቪ የበለጠ ሪፖርት ያቀረበው።

የአልጃዚራ ድረገጾች እንዲታነቁ የተደረጉበት ዋናው ምክንያት የቴሌቪዥን ጣቢያው ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቃውሞ በሰጠው ሽፋን እንደሆነ አመልክቷል። እንደ ጉግል የመረጃ ትንተና በኢትዮጵያ ውስጥ የእንግሊዝኛው ድረገጽ ባለፈው ዓመት ሀምሌ ወር 50ሺ ተጠቃሚ የነበረው ሲሆን፣ በመስከረም ወር የተጠቃሚው ቁጥር ወደ 114 ወርዷል። የአረቢኛው ድረገጽም ከ5,371 ተጠቃሚዎች ወደ 2 መውረዱን ያሳያል። ይህንን መረጃ የዘረዘረው አልጀዚራ ይህ መረጃ የሚያሳየው ጣቢያው በነሃሴ ወር የኢትዮጵያ መንግስት በእምነት ጣልቃ እንደሚገባ ካስተላለፈ በኋላ በተወሰደው የእግድ ርምጃ መሆኑንን አመልክቷል። አልጀዚራ ከታገደ በኋላ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ሁኔታና የጋዜጠኞችን እስር በስፋት በዶክመንታሪ መልክ አቀናብሮ አስተላልፏል።

የኤሌክትሪክ መቋረጥ ማሽን እያቃጠለ ነው
በአዲስ አበባ ሰሞኑን በተደጋጋሚ ኤሌክትሪክ እየተቆራረጠ በመሆኑ ስራችንን በአግባቡ መስራት አልቻልንም ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን እያቀረቡ ነው። ከነዋሪዎች በተጨማሪ አንዳንድ ፋብሪካዎችና የተለያዩ ተቋማትም የሃይል መቆራረጡ ችግር እየፈጠረባቸና ማሽኖቻቸውን እያቃጠለባቸው መሆኑን በመግለጽ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ከአገር ውስጥ ተዘገበ።

በኮርፖሬሽኑ የዲስትሪቢዩሽን ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ መስፍን ብርሀነ እንዳሉት፥ የግንባታ ስራዎች በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የወሰን ማስከበር ስራ ሲሰራ በቦታው የነበሩ የኤሌክትሪክ መስመሮችን የማዛወር ስራ ስለሚሰራ ፤ በአንዳንድ አካባቢዎች በኔትዎርኮቹ ላይ የሚካሄደው ዝርፊያ እና የሚደርሰው የመኪና ግጭት ለችግሩ መንስኤ መሆናቸውን፣ ሰሞኑን እያጋጠመ ያለው ንፋስም ለችግሩ ምክንያት ሲሆን ፥ በዚህም የኤሌትሪክ መስመሮች ላይ ጉዳት ስለሚደርስና የኤሌትሪክ መስመሩን መልሶ መጠገን እስኪቻል የኤሌትሪክ ማቋረጡ ያጋጥማል ብለዋል። በዚህ ምክንያት በተለይ በኤሌክትሪክ እቃዎች ላይ ለሚፈጠረው መቃጠልና መሰል ችግሮች ፣ ኮርፖሬሽኑ አስፈላጊውን ካሳ እንደሚከፍል ሃላፊውን ገልጾ ፋና ዘግቧል። ሃላፊው ይህንን ቢሉም የችግሩ ሰለባ የሆኑ በተባለው መሰረት ካሣ እንደማያገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

http://www.goolgule.com/briefs-22/

posted by Tseday Getachew

የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው

-በቤተክህነቱ በዚሁ ጉዳይ ላይ ስብሰባ እየተደረገነው

ከመጋቢት 2 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ማቆም አድማ ላይ የነበሩት የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ስላሴ መንፈሰሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ እንደሆነ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፁ፡፡

የትምህርት ጥራት መጓደል፣ የአስተዳደራዊ ችግሮችና በምግብ ጥራት መጓደል ምክንያት ጥያቄያቸውን ለኮሌጁ አስተዳደር ቢያቀርቡም ምላሽ በማጣታቸው የትምህርት መቆም አድማ ለማድረግ የተገደዱት ቅድስት ስላሴ መንፈሰሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት በርሀብ ተጎድተው ራሳቸውን በመሳት በመጀመራቸው በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል መወሰድ መጀመራቸውን ስምቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ተማሪዎች ተናግረዋል፡፡ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኛም በቅድስት ስላሴና በየሆስፒታሎቹ ተዘዋውሮ እንደተመለከተው አባ እያሱ ሰብስቤ የተባሉ ተማሪ በየካቲት 12 ሆስፒታል እንዲሁም ደቀመዝሙር በኃይሉ ሰፊ ምኒሊክ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ መሆኑን አረጋጧል፡፡ አመሻሹ ላይም ገ/እግዚያብሄር የተባሉ ተማሪ በአምቡላንስ ከኮሌጁ ተወስደዋል፡፡ ተማሪዎቹ በደል አድርሰውብናል ከሚሉዋቸው የኮሌጁ ሀላፊዎች ውስጥ መምህር ፍስሀፂዮን ደሞዝ አካዳሚክ ዲን እና መምህር ዘላለም ረድዔት የቀን ተማሪዎች አስተባባሪ በዋነኝነት ተጠቅሰዋል፡፡

ደረሰ ስለተባለው ችግር ለማጣራት ጥያቄ ያቀረብንላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሀፊ ብፁዕ አቡነ ህዝቅኤል በኮሌጁ ጉዳይ ስብሰባ ላይ እንደሆኑ ተናግረው የነበረ ቢሆንም ተሰብሳቢ ባለመሟላቱ ስባሰባው እንዳልተደረገ ለፍኖተ ነፃነት የደረሱ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

http://www.fnotenetsanet.com/?p=3692

posted by Tseday Getachew

Post Navigation

%d bloggers like this: