Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

Archive for the category “Uncategorized”

“በሽብር” ተከሶ ፍ/ቤት የቀረበው ወጣቱ ፖለቲከኛና መምህር አብርሃ ደስታ የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀበት

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

ወጣቱ መምህርና ፖለቲከኛ ዛሬ በግምት 9፡00 ሰዓት ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ ሲደርስ በግቢው የነበሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባሎች እንዲሁም የአብርሃ ደስታ ደጋፊዎች በጭብጨባ ያላቸውን አክብሮት የገለጹለት ሲሆን እሱም አጸፋውን መልሷል፡፡ ከማዕከላዊ አጅበውት የመጡት የፌዴራል ፖሊሶች ለምን አጨበጨባችሁ እያንዳንዳችሁ ትገባላችሁ በማለት እያስፈራሩ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ በማለት ከግቢ ለማስወጣት ሙከራ ያደረጉ ሲሆን ጉዳዩን ሊከታተል የመጣው ታዳሚም ለምን እንወጣለን አንወጣም እኛም ችሎት ተገኝተን ልንከታተል ሲገባ ግቢ ውስጥ መቆምም ልትከለክሉን ነው በማለት ተቃውሞ በማሰማቱ ችሎቱ እስኪጠናቀቅ በግቢው እንድንቆይ ተደረገ፡፡ የክሱ ጉዳይ የታየው በችሎት ሳይሆን በጽ/ቤት ነበር፣ ወጣቱ ፖለቲከኛ አብርሃ ደስታም ከጠበቃዬ ጋር ልገናኝ አልቻልኩም፣ ዘመድ አዝማድም ሊጠይቀኝ አልቻለም በማለት ለፍ/ቤቱ አስረድቷል፡፡

ዳኛውም ከጠበቃና ከቤተሰብ ጋር የማታገናኙ ከሆነ እርምጃ እወስዳለሁ በማለት ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡ ፖሊስ ተጨማሪ ማስረጃና ምስክር ለማሰባሰብ የጊዜ ቀጠሮ በመጠየቁ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮውን ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ተቃውመውታል ፖሊስ ደንበኛዬን ከመያዙ በፊት ማስረጃና ምስክሮችን ማዘጋጀት ነበረበት ነገር ግን አሁንም ደንበኛዬ ታስረው ማስረጃና ምስክር ሊባል አይገባም፣ እስራቱ ህገወጥ ነው በማለታቸው ዳኛው እንዳትሰራ አደርግሃለሁ ጥብቅናህን በፍትህ ሚ/ር አሳግድብሃለሁ በማለት እንዳስፈራሯቸው ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም ዳኛው ፖሊስ የጠየቀውን የጊዜ ቀጠሮው ፈቅደው ለመስከረም 22ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 እንድትገኙ በማለት ችሎቱ ተጠናቋል፡፡ አብርሃ ከችሎቱ ሲወጣም የሱን ጉዳይ ሊከታተል የመጣው ታዳሚ በጭብጨ ሸኝቶታል፡፡

posted by Tseday Getachew

http://satenaw.com

 

Advertisements

ሐሰን ሺፋ ከፌደራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነርነት ሥልጣናቸው ተነሱ

ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት ነባር ታጋዮች መካከል አንዱ የነበሩትና ሕወሓት በተከፋፈለበት ወቅት የነስዬ አብርሃ ወገንን ተቀላቅለው በኋላም ወደ አቶ መለስ ወገን ይቅርታ ጠይቀው የተመለሱት የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሐሰን ሺፋ ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉ አነጋጋሪ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመለከቱ።
hasen shifa
የፌዴራል ፖሊስ የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች እንደገለጹት አቶ ሐሰን ሽፋ በተለይ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ እንቅስቃሴን የሕወሓት መንግስት እንዳሰበው በተንኮል ሊቆጣጠረው ካለመቻሉና በስርዓቱ ባለስልጣናት ውስጥ በተነሳው ያለመተማመን ችግር ጋር ተያይዞ ካሉበት ቦታ እንዲነሱ ተደርገዋል። አቶ ሐሰን በምክትል ኮምሽነርነት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩን ከታች ሆነው ሲዘውሩ የቆዩ ሲሆን በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በጋምቤላ፣ በትግራይ፣ በአማራ ክልል፣ በደቡብና በሌሎችም ስፍራዎች ሥርዓቱ ለፈጸማቸው ጭፍጨፋዎች ተጠያቄ እንደሆኑ የሚናገሩት የዘ-ሐበሻ ምንጮች በድንገት ከዚህ ስልጣናቸው ተነስተው ወደ ፌደራል ጉዳዮች ሚ/ር መስሪያ ቤት ውስጥ እንዲሰሩ መላካቸው የስርዓቱን ደጋፊዎች ሳይቀር “ድርጅቱ በውስጡ ምን እየሆነ ነው?” በሚል እያነጋገረ ነው ብለዋል።

በሕወሓት/ኢሕአዴግ አገዛዝ ስር ያሉ ባለስልጣናት እርስበእርሳቸው አለመሰማማታቸው እንዲህ ያሉ ከስልጣን መነሳቶችና/ መዘዋወሮች በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ።

posted by Tseday Getachew

“ጉድ በል ጎጃም አለ ያገሬ ሰው!” የወያኔኢሕአዴግ ተላላኪው የዳላሱ ወጣት ኢብራሂም ሲራጅ ማን ነው?

በሚሊዮን ኢትዮጵያ(ከዳላስ)https://i2.wp.com/www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2014/09/dallas1.png

dallas1ወያኔ/ኢሕአዴግ በውጭ ሃገር የሚኖሩት ኢትዮጵያውያንን ለማደራጀት የሚያስችላቸውን የጥፋት ውጥን በመወጠን ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍል ተወልደውያደጉ ለሆዳቸው ያደሩ አደርባዮችን በመመልመል የቤት ስራውን እየሰራ ይገኛል። አያሌ ኢትዮጵያውያን የስርአቱን አስከፊነት በመገንዘብ ሳይወዱ በግድ የሚወዱት ሃደራቸውና ሕዝባቸውን ትተው ቢሰደዱም እንኳን እስካሉበት የስደት ሃገር በመከተል የከፋፍለህ ግዛ መሰሪ ፖሊሲያቸውን ለማስፈጸም በፖሊሲ ደረጃ በመንደፍ የጥፋት ተግባራቸውን ገፍተውበታል። በዚህም መሰረት ምንም እንኳን እዚህ ገቡ የሚባሉ ቁጥር ያላቸው አባላት ማፍራት ባይችሉም ጥቂት ርካሽ ተውዳጅነት ለማትረፍና የግል ንዋይ ፈላጎታቸውን ለማሟላት ከመራሹ መንግስት ጋር በመተባበር ህዝብን ለማወናበድና ለማታለል የሚተጉ ግን አልጠፉም። ኢብራሂም ሲራጅ ከእነዚህ በጥቅም ከተደለሉትና የመሰሪው የወያኔ መንግስት ተልእኮ ለመወጣት ሌት ተቀን ደፋ ቀና ከሚሉት አንዱ ነው።

ዳላስ በወያኔ መሰሪ ተባባሪዎች እጅ ወድቃለች ማለት ባይቻልም እነዚህ ጥቂት ርዝራዦት በኮሚኒቲ፣ በቤተክረስቲያንና በሌሎችም ኢትይጵያዊ በሆኑት ተቓማት እጃቸውን በማስገባት ቀላል የማይባል የጥፋት ተልዕኮአቸውን ለመወጣት ሌት ተቀን ደፋ ቀና እያሉ ለቱባ የወያኔ አለቆቻቸው ታማኝ ለመሆን ተግተው ይሰራሉ። ምንም እንኳን በኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አላማቸውን ማሳካት ባይችሉም። የጥፋቱ ሰለባ ከሆኑት ኢትዮጵያዊ ተቓማት ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያንና (http://www.stmichaeleoc.org/) በዳላስ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የጋራ መረዳጃ ማህበር (http://maaecdallas.org/) ዋና ተጠቃሽ ናቸው። በእነ አቶ ተፈራወርቅ (ጋሻው ኢንሹራንስ) የሚመራው የጥፋት ቡድን አማካኝነት ቤተክርቲያኒቷን ፍርድ ቤት ሶስት ጊዜ በመክሰስ በሺዎች የሚቆጠሩ ዶላሮች ወጪ ዳርገዋል። ኮሚኒቲውም ምርጫ በመጣ ቁጥር የወያኔ ጀሌዎቻቸውን ለማስረጽ ህዝብን በማወናበድ ላይ ይገኛሉ። ከወራት በኳላ የሚደረገውን የመራዳጃው ማህበር የቦርድ አባላት ምርጫ ላይ የወያኔ አባላትን ለማስገባት ተጽዕኖ ለመፍጠር የቤት ስራቸውን እየሰሩ ናቸው። ይህ እውነታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ሁሉም የኮሚኒቲው አባላት ኮሚኒቲው በወያኔ እጅ እንዳይወድቅ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ሊታደገው ይገባል።

እነዚህ የጥፋት ሃይሎች እራሳቸውን “ሰበቡ” የሚል ስያሜ በመስጠት በእነ ተኮላ፣ ደምመላሽ፣ ተፈራወርቅና ሌሎችም መሪ ተዋናይነት የሚመራ ሲሆን ሁሌም ምክንያት እየፈጠሩ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጉሮሮ በተነጠቀ በወያኔ በተመደበላቸው ባጀት ስጋዊ ፍላጎታቸውን የሚያስደስቱ ለሌላው ግድ የሌላቸው ህሊናቸው የሸጡ አገርና ሕዝብን የካዱ የግል ጥቅማቸውን ብቻ የሚያዩ ስንስቦች ናቸው። የማህበሩ አባላት ለሚሰሩት የጥፋት ተልዕኮ ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ በትውልድ ቀዬያቸው በህገ ወጥ መንገድ ከድሃው ምስኪን የሃገሬ ገበሬ መሬት እየተነጠቀ ለውለታቸው የመኖሪያና የንግድ ቦታ መስሪያ ይሰጣቸዋል። ኢብራሂም ሲራጅ የዚህ ማህበር ተላላኪ እንደመሆኑ መጠን የጽዋው ተቓዳሽ በመሆን በባህር ዳር ከተማ ሲኒማ ቤት መስሪያ ቦታ ለውለታው ተችሮታል። እነዚህ የጥፋት ሃይሎች ኢትዮጵያውያን በሚሳተፉበትና የገቢ ማሰባሰቢያ ቦታዎችን በመገኘት ወያኔኢሕአዴግ ለዚህ ተግባር በተመደበውብ ባጀት በመለገስ ሕዝብን ለማወናበድና የኮሚኒቲው ተቆርቓሪ ለመምሰል ይጥራሉ።

የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ፕላን(GTP) በተመለከተ የወያኔ/ኢሕአዴግ ቱባ ባለስልጣናት ወደ ሰሜን አሜሪካ በመጡበት ወቅት ምንም እንኳን ጥሪው ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚመለከት ቢሆንም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለመታደም ግን አልታደሉም። ስብሰባው ለመታደም የተዘጋጀበት ስፍራ ብሄድም ውይይቱን ለመካፈል ከተነፈጉት አንዱ ነኝ። የኢትዮጵያ ጉዳይ የሁሉም እንጂ የወያኔ አባላት ብቻ አለመሆኑን እይርታወቅ ስብሰባውን ለጥቂት አባሎቻቸው ብቻ በደብዳቤ በመጥራት ሐገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ደብዳቤ የላች ሁም በማለት ወደ ስብሰባ አዳራሹ እንዳይገቡ ተደርገው በፖሊስ እንዲባረሩ ተደርገዋል። በዚህ ወቅት እንዳይገቡ የተደረጉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ሲያሰሙ ለወያኔ የደህንነት አባላት የሚላክ ቪዲዮ በመቅረጽና ተቃውሞ እያሰሙ በነበሩት በመሳለቅ ኢብራኢም ሲራጅ ለወያኔ ታማኝነቱን አሳይቷል። ይህ ደግሞ ከሃገርና ህዝብ ክህደት በተጨማሪ ለዲያፖራው ማህበራሰብ ያለው ንቀት ምን ያህል እንደ ሆነ ያሳያል።

ኢብራሂም ሲራጅ በሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌደሬሽን(ESFNA) ዳላስን ወክለው ከሚጫወቱት ሁለት የስፖርት ክለቦች አንዱ በሆነው ኢትዮ ዳላስ ውስጥ እስከ ዛሬ ድረስ ላለፉት 11 አመታት ስጫወት ነበር ብሎ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሰጠው ቃለ መጠየቅ በፍጹም ከውነት የራቀ መሆኑን ቡድኑ ውስጥ ከሚጫወቱት አባላት ለመረዳት ችያለሁ። ለነገሩ መች ኢቲቪ እውነት አውርቶ ያውቅና። ወያኔ ማለት የውሸት ከረጢት መሆኑን ከታወቀ ውሎ ሰንብቷል። ነገር ግን ቡድኑ አባላት ውስጥ በተፈጠረው አለመግባባት እጁን በማስገባት ከጀርባ በመሆን ለሁለት እንዲከፈሉና ልዩነታቸው በሰላም እንዳይፈቱ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል። ወጣቶቹ ችግራቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ከማድረግ ይልቅ ከዋናው ቡድን እራሳቸውን ላገለሉት አባላት የቅርብ ጓደኞቹና ዘመዶቹ በመመልመል የጥፋት ሴራውን ሲሸርብ ነበር። ምንም እንኳን ያሰበው አላማ ባይሳካለትም የመጨረሻ ግቡ ግን ወጣቶቹን በጥቅም በመደለል የዛሬ ሁለት አመት ገደማ በአብነት ገመስቀል መሪ ተዋናይነትና በሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲን ሙሉ የገንዘብ ድጋፍ ለተቓቓመው የስፖርት ማህበር ለማስረከብ ነበር።

ኢብራሂም ሲራጅ በአሁን ሰአት ኢትዮጵያ የሚገኝ ሲሆን በኢትዮጵያ ቴሌቪሽን በእንግዳ ፓሮግራም በተደረገለት ቃለመጠየቅ ኢትዮጵያ ውስጥ የማይካድ ለውጥ አለ፣ በውጭ ኃገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስለ ልማቱ የሚናገሩትን አልሰማም፣ ወያኔኢሕአዴግ በሚያደርጋቸው ሁሉም ስብሰባዎች መሪ ተዋናይ ነኝ፣ የፖንድ ሽያጭና በቅርብ የማውቃቸው አቅም ያላቸው ኌደኞቼን በማስተባበር ላይ ግንባር ቀደም ነኝ ይለናል። በዚህም አንባገኑ የወያኔ ስርአትን ቀንደኛ ደጋፊ መሆኑና መራሹ ወያኔ ልማታዊነት ምስክርነት ይሰጣል። ውሸታሙን ኢቲቪንና ወያኔን እውነትነት አስረግጦ በመናገር የዲያስፖራውን ማህበረሰብ ውሸታም መሆኑን ይነግረናል። ይህ ደግሞ ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ያለው ንቀት ያሳያል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንባገነኑ ስርአት ለእስራት፣ ለስደት፣ ለሞት፣ ለረሃብ፣ ለእንግልትና ለስቃይ እየተዳረገ ባለበት ሁኔታ ወያኔን ማሞካሸትና ልማታዊነት መመስከር የህሊና ዳኝነት የጎደለው ከመሆን ውጪ ምን ይሉታል። ለመሆኑ ወያኔ የሚለውን የሚያስተጋባለትን እንጂ መች ሕሊና ያለው ሰው ይፈልግና።

ጀግናው በላይ ዘለቀ ያፈለቀችው ጎጃም ኢብራሂም ሲራጅ አሳድጋለች የናት ሆድ ዥንጉርጉር ይሉታል ይህ ነው። አንዱ የባህርዳር አንድ ክለብ የሚያሰነጥለው አብሮ አደጉ ስለ ኢብራሂም ሲራጅ ሲናገር ይህ ትልቅ ሃብታችን ነው ልንጠቀምበት ይገባል ብሎናል። ጀግናው በላይ ዘለቀ በተወለደበት ሃገር ሃገሩን ሽጦ ለሆዱ ያደረውን እንደ ሃብት ሲቆጠር ጉድ በል ጎጃም ማለት ይሄኔ ነው።

ውድ የሐገሬ ልጆች ሆይ ኢትዮጵያ ሃገራችን አንድነቷና ዳርድንበሯ ጠብቃ ልትቆይ የቻለችው ብዙ የደም መስዋዕትነት ተከፍሎባት እንድሆነ ሁሉም ጠንቀቆ የሚያውቀው ስለሆነ እኔ ልነግራች ሁ አልሻም ለቀባሪ ማርዳት እንዳይሆንብኝ። ዛሬ ግን ወያኔና ግብራበሮቹ ይህን ታሪክ ለማጥፋት የዘር ፖለቲካ በመከተል ህዝቡን አንድነቱን እንዳይጠብቅ በማድረግ፣ የገዛ መሬታችን ለጎረቤት ሀገራት አሳለፎ በመስጠት፣ ምስኪን ገበሬ በማፈናቀል ለውጭ ባለሃብት በመሽጥና ሌሎችም አያሌ መሰሪ ተግባራቸውን ገፍተውበታል። ወያኔ/ኢሕአዴግ ያለ ሕዝብ መልካም ፍቃድ ስልጣን በአፈሙዝ በማስፈራራት ቢቆናጠጥም ሕዝብ ያለመረጠው መንድስት ዘላቂነት ሊኖረው ስለማይችል ሰርጎገብ ከሆኑት የወያኔ ተላላኪዎች ሰላባ እንዳንሆን ነቅተን በመጠበቅ ማጋለጥ ይኖርብናል። የዚህ ጽሁፍም ዋናው አላማም ይህ ነው።

ኢብራሂም ሲራጅ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የእንግዳ ፕሮግራም ያደረገው ቃለመጠይቅ እዚህ በመጫን ይመልከቱ! http://www.diretube.com/engeda/ebrahim-serag

አንድ ሕዝብ!!!

አንድ ኢትዮጵያ!!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም አንድነቷን ጠብቃ ትኑር!!!
http://www.zehabesha.com

posted by Tseday Getachew

በተማሪዎች ላይ የኃይል እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ተገለጸ

በትምህርት በኢህአዴግ ጽ/ቤትና በትምህርት ሚኒስትር ትብብር ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሚሰጠው ስልጠና በተማሪዎች ላይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ተገልጾአል፡፡ በስልጠናው ሰነድ ላይም ተካትቷል፡፡ ‹‹የትምህርት ተቋማትን ወደ ትክክለኛው የትግል ስልት የመመለስ አስፈላነት›› በሚል አብይ ጉዳይ ላይ በተሳሳተ ስልት ይንቀሳቀሱ እንደነበር በመጥቀስ ‹‹ተማሪው ጥያቄውን የሚያቀርበው ትምህርቱን እየተማረ፣ የትምህርት ቤቱን ህግና ደንቦች እያከበረ ሊሆን ይገባል፡፡…..ህገ ወጥ ሆኖ ህጋዊ ምላሽ ማግኘት አይቻልም፡፡›› በሚል ‹‹ህገ ወጥ ከሆኑ›› ህገ ወጥ ምልሽ እንደሚጠብቃቸው ያስጠነቅቃል፡፡
UNiversity students

 

 

 

 

 

 

 

ሰንዱ አክሎም ‹‹በተማሪው ማህበረሰብ ውስጥ አፍራሽ አዝማሚያ ያላቸው ተማሪዎች ነውጥን ለማስፋፋት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በጥብቅ በመታልና የንብረት ውድመት እንዳይደርስ በጥብቅ መታል ይገባል፡፡ በቅድሚያ ራስን መነጠል እና ቀጥሎም የነውጥ ኃይል አራማጅና ደጋፊ የሆኑትን ማጋለጥና ትግል ማድረግ ይገባል›› በሚል በተማሪዎቹ ላይ ሊወሰድ የሚችለውን እርምጃ ይዘረዝራል፡፡

ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ

posted by Tseday Getachew

http://www.zehabesha.com

 

“ነብሰ ጡሯን አስገድደው ሲደፍሯት ሞተች..” – ፀጋ ኪዳኔ (ከሳዑዲ ተመላሽ ኢትዮጵያዊት – ቃለምልልስ)

ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከሳዑዲ አረቢያ ተመላሽ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን መካከል የተወሰኑትን በጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው በኩል አነጋግሯል። ዘ-ሐበሻ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ እንደወረደ አስተናግዳዋለች፦

ስምሽ ማን ነው?
ፀጋ ኪዳኔ ገብረኪዳን
ምን እየጠበቅሽ ነው?
ዘመድ አለችኝ አዲስ አበባ የምትኖር፤ እስዋ እስክትመጣ እየጠበቅሁ ነው፡፡
ሳኡዲ ምን ያህል ጊዜ ቆየሽ?
ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ነው ከሪያድ/ሞንፋ የመጣሁት፡፡ ከኢትዮጵያ ስሄድ በኮንትራት ቢሆንም በባህር ከሄዱት ስደተኞች የተለየ ክብር አላገኘሁም፡፡ ጭቅጭቅ፣ ስድብና ድብደባ ሲበዛብኝ ከተቀጠርኩበት ቤት በስምንተኛ ወሬ ወጥቼ ጠፋሁ፡፡ የሄድኩት ለአንድ ስራ ብቻ ተዋውዬ ነበር። የምተኛው ግን ከሁለት ሰዓት አይበልጥም ነበር፡፡ ሥራ ብቻ ነው 24 ሰዓት!
እስቲ ስለደረሰብሽ ችግር በዝርዝር ንገሪኝ..
በ700 ሪያድ ተቀጥሬ ነበር ከዚህ የሄድኩት፡፡ አሰሪዬ ቤት አራት ትላልቅ ወንድ ልጆች አሉዋት። የእህትዋ ልጆችም እዚያው ነው የሚኖሩት፡፡ ‹‹ወሲብ ካልፈፀምን..›› ብለው ያስቸግራሉ፡፡ በጣም ተሰቃየሁ፡፡ ከአቅሜ በላይ … ለህይወቴ በጣም አስፈሪ….ሲሆንብኝ ወጣሁ፡፡ ከአቅሜ በላይ ስትይ …
ልጆቹ ወሲብ ካልፈፀምን ብለው አሻፈረኝ ስላቸው፣ “በቢላ እናርድሻለን” እያሉ ያስፈራሩኝ ነበር፡፡ እምነቴን እንድቀይር ሁሉ ይፈልጋሉ። አፈር ድሜ በላሁ፡፡ ሰርቼ ለፍቼ … በዚያ ላይ ነፃነት አልነበረኝም፡፡ ወገቤ፣ ዓይኔ ታመመ፡፡ እነሱ እኮ ሃያ አራት ሰዓት እየበሉ እየጠጡ ነው፡፡ በዚያ ላይ በእጅሽ ላይ ስልክ ማየት አይፈልጉም፡፡ ሁሉ ነገር ሲያንገፈግፈኝ ሁለት ወር የሰራሁበትን ገንዘብ ጥዬ ወጣሁ፡፡ ከዛ ኤጀንሲው ለሌላ ሰው ሸጠኝ፤ በአስር ሺህ ሪያድ፡፡ እዚያም ግን አልተመቸኝም። ስራው ሃያ አራት ሰዓት ነበር፡፡ አምስት ሰው እንኳን የማይችለው ስራ ነበር፡፡ አንድ ኩንታል ሊጥ አብኩቼ፣ ለሱቅ የሚሸጡት ብስኩት ጠብሼ፣ ሰባት መቶ ሪያል ነበር የሚከፈለኝ፡፡ ሁለት ወር ሙሉ እንደምንም ድምጼን አጥፍቼ ሰራሁ… በእንቅልፍ እጦት ልወድቅ እየተንገታገትኩ፡፡ እፊታቸው ላይ ግን ደስተኛ እመስል ነበር፡፡ ሰውነቴ እየመነመነ መጣ፡፡ ይሄኔ ድጋሚ ለመጥፋት ተዘጋጀሁ፡፡
“ለሌላ ሰው ሸጠኝ” ያልሽው … ኢትዮጵያዊ ነው?
/እንባዋ እየፈሰሰ/አረብ ነው፡፡ ወደ ሳኡዲ ከላከኝ ኤጄንሲ ጋር አብሮ ይሰራል፡፡ የረመዳን ጊዜ ደግሞ ሱቃቸው ወሰዱኝ፤ የአንድ ሰዓት መንገድ ተጉዞ ሌላ ቤት አላቸው፡፡ እዛ ይዘውኝ ሲሄዱ ስራ ይቀልልኛል ብዬ ነበር፡፡ … ግን የባሰ ሆነብኝ፡፡ ለካ ጓደኞቻችን ወደው አይደለም ራሳቸውን የሚያጠፉት፤ አብደው ጨርቃቸውን ጥለው በየጎዳውና የወጡትና መንገዱ የወደቁት … የወገብና የአእምሮ በሽተኞች የሆኑት? “ምነው እናቴ ስትወልጅኝ በመሃፀንሽ ውስጥ ደም ሆኜ በቀረሁ? እናቴ እባክሽ መልሰሽ ዋጪኝ” አልኩኝ፡፡ ራሴንና ቤተሰቤን ልረዳ ስንገታገት ከፊታቸው ድፍት ብል እኮ … እንደሰው ከቆጠሩኝ … ሬሳዬን ለእናቴ ይልኩላት ይሆናል፡፡ ያለዚያ ግን የሀገራቸው መንግስት አውጥቶ ይቀብረኛል፡፡ ከዚያ ሁሉ በፊት ጠፍቼ መውጣት እንዳለብኝ አሰብኩ፡፡ አንድ ቀን ረመዳን ካፈጠሩ በኋላ ቤተሰቡ ተሰብስቦ ሊዝናኑ ወጡ፡፡ ደስ አለኝ፡፡ ቶሎ ብዬ የሴትየዋን ሙሉ ልብስ ለብሼ፣ ሽፍንፍን ብዬ ወጣሁ፡፡
ሻንጣ ምናምን ሳትይዢ?
ባዶ እጄን ነው የወጣሁት፡፡ የሰራሁበት ገንዘብ እንኳን በእጄ የለም፡፡ በቃ ዝም ብዬ ወጣሁ፡፡ ፓኪስታናዊ የታክሲ ሾፌር አገኘሁ፡፡ ‹‹ምን ሆንሽ?›› ብሎ ሲጠይቀኝ በዝርዝር ነገርኩት፤ አዘነ፡፡ ‹‹ሪያድ የሀበሻ ሃገር ነው፤ ብዙ ኢትዮጵያዊ አለ›› ብሎ እዛ (በነፃ) ወሰደኝ፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን አገኘሁ፡፡ እዚያ መኖር ጀመርሽ ማለት ነው?ሳያቸው በጣም ነው ያለቀስኩት፡፡ አገሬ የገባሁ ይመስል..መሬት ሁሉ ስሚያለሁ፡፡ ከኢትዮጵያ በባህር (በህገወጥ መንገድ) የመጡ ሴቶች ነበሩ። ከእነሱ ጋር አንድ ቤት በስድስት መቶ ሪያድ ለስድስት ወር ተከራይተን አብረን እየኖርን እንሰራ ጀመር፡፡
ቤቱን ለስንት ተከራያችሁ?
አስር ነበርን፡፡ ሁለት ወር እንደሰራሁ ግን በአካባቢው ግጭት ተነሳ፡፡ እግሬ አውጪኝ ብለን በየፊናችን ተበታተንን፡፡
ምን ዓይነት ግጭት?
መንግስት የሌለበት አገር ይመስል ጐረምሶች በር እያንኳኩ በሽጉጥ፣ በካራ፣ ሰው መግደል ጀመሩ፡፡ ስለዚህ ‹‹እጃችንን እንስጥ›› ብለን ተማከርን፡፡ ሌላው ችግር ፖሊስ፤ ትዳር መስርተው የሚኖሩትን የአበሻ ወንዶች እየወሰደ፣ ሴቶችን ለብቻቸው ይተዋቸው ነበር፡፡ በቤቱ ወንድ አለመኖሩን የተገነዘበ የአገሩ ዱርዬዎች (እንኳን ለአበሻው ለመንግስትም ልባቸው ያበጠ ነው) ሴትዋን ለአራትና ለአምስት እየሆኑ መድፈር ያዙ፡፡ ከእኛ ጎን የነበሩትን ሲያሰቃይዋቸው አይተናል፡፡ ወንዶቹን ፖሊስ ሲወስዳቸው ጎረምሶቹ ተከትለው ይገቡና ሴቶቹን መጫወቻ ያደርጓቸዋል/ለቅሶ/፡፡ አንድ ያየሁትን ልንገርሽ../ረጅም ትንፋሽ/ እነዚህ ጐረምሶች…ሶስት ሴቶች ያሉበት ክፍል ውስጥ ገብተው ለሰባት ደፈሯቸው፡፡ /ማውራት አልቻለችም፤ ሳግና እንባዋ እያቋረጣት/..ከሶስቱ አንዷ የሰባት ወር ነፍሰጡር ነበረች፤ ሲገናኝዋት ሞተች፡፡ አንዷን ደግሞ ለሰባት ደፈሯትና ገድለው ጥለዋት ሊወጡ ሲሉ ሽርጣ/ፖሊስ መጣ፡፡ ከፖሊስ ጋር ተኩስ ገጥመው እርስ በርስ ተገዳደሉ፡፡ የሀበሻ ወንድ ከእህቱ ወይንም ከሚስቱ ሊለዩት ሲመጡ አልለይም ይልና ይገደላል፤ ይደበደባል … በቃ እልቂት ይሆናል፡፡ አዲስ አበባ ብለሽ ካራ ቆሬ እንደምትይው..ሪያድ ብለሽ ሞንፋ የሚባል አካባቢ በርካታ አበሾች ይኖራሉ፡፡ እኔ እንኳን የማውቀው … ከአምስት በላይ ሴቶች እንደተገደሉ ነው፡፡ መላ አካላቸውን ቆራርጠው ነው የጣሏቸው፡፡ ግን ይሄ ሁሉ መከራ ምን አድርገን ነው?
አንቺ እንዴት መጣሽ ወደ አገርሽ?
እጄን ሰጠኋ፡፡ አሰሪዬ ‹‹የት ልትሄጂ ነው?›› ብላ ስትጠይቀኝ፡፡ ‹‹አንድ ጓደኛዬ ልትወልድ ነውና ልጠይቃት ..›› ብዬ የሰራሁበትንም ሳልቀበል ወጣሁ፡፡ ምክንያቱም ብትገለኝስ ብዬ ፈራሁ፡፡ አብዛኛው አበሻ ከስራ ወደቤቱ ሲሄድ እየተያዘ ነው የሚመጣው፡፡ የሰራበትን የለፋበትን ሳይዝ ባዶ እጁን፡፡ እና እኛም ነገሩ ስላስፈራን እጃችንን ሰጠን። በቃ እኔም ወደ እዚህ መጣሁ፡፡
ዛሬ ላይ ሆነሽ ስታስቢው ወደዛ በመሄድሽ ምን ይሰማሻል?
መጀመሪያ ከዚህ ስሄድ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር፤ የራሴንና የቤተሰቤን ህይወት ላሻሽል እንደሆነ ተስፋ በማድረግ፡፡ ከዛ በኋላ ግን ከስራው ብዛት የተነሳ ከጥቅም ውጪ ልሆን ነው ብዬ እጅግ አምርሬ አለቅስ ነበር፡፡ በጣም ስጋት ያዘኝ፡፡ ግን ከሞት ተርፌ ወደዚህ ስመጣ አምላኬን አመሰገንኩ፡፡
ቤተሰብሽ መምጣትሽን አውቀዋል?
አላወቁም፡፡ ምን እያሰቡ ይሆን? ይሄን ሁሉ ነገር እየሰሙ፡፡ እናቴ መንገድ መንገድ እያየች ይሆናል፡፡ ደሞ ከእኛ አካባቢ ልጆች ብዙ የሞቱ አሉ፡፡..አሁን እኔ ራሴ የሁለት ሰው መርዶ ይዤ መጥቻለሁ፡፡ እናቴም ሰው ሲመጣ ‹‹ልጄን አይታችኋል?›› ትል ይሆናል፡፡ እኔስ መጣሁ..በረሃ ላይ ተደፍተው ለመምጣት ወረፋ እየተጠባበቁ ያሉ ህጻናትና ሴቶች ብዙ ናቸው፡፡ እዚህ የመጣነው እኮ ግማሽ አንሞላም፡፡ በሳኡዲ የኢትዮጵያውያን እንባ ያሳዝንሻል፡፡ ብዙዎቹ በሃዘን ላይ ናቸው፤ ድረሱላቸው፡፡

http://www.zehabesha.com/

posted by Tseday Getachew

 

“እኔ ራሴ ስድስት ያበዱ ሴቶችን ይዤ መጥቻለሁ..” ራውዳ ጀማል – ከሳዑዲ ተመላሽ ኢትዮጵያዊት (ቃለ ምልልስ)

 

 

Image

ራውዳ ጀማል ትባላለች፡፡ የሃያ ዓመት ወጣት ናት፡፡ ስለራስዋም ሆነ በሳኡዲ ስላሉ ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ሁኔታ ስታወራ እያለቀሰችና እየተወራጨች ነው፡፡ ለማነጋገር ስቀርባት “ወንድ ከሆናችሁ ጋዜጠኞች ነን፣ የህዝብ አፍ ነን ካላችሁ፤ እዚህ ተቀምጣችሁ፣ “ሁለት ሰው ሞተ” እያላችሁ ከምታቅራሩ ሳኡዲ ሂዱና በየቀኑ ሁለት ሶስት ሰው የሚሞትበትን እልቂት ተመልከቱ፣ “ሰዎቹን ምን እየሰራችሁ ነው?” ብላችሁም ጠይቁልን” አለችኝ። መቅረፀ ድምፄን ሶስት አራት ጊዜ ያስጠፋችኝ ቢሆንም በመጨረሻ ግን ለቃለ ምልልስ ፈቃደኛ ሆነችልኝ፡፡
ስንት ዓመት ቆይተሽ መምጣትሽ ነው?
ከሁለት ዓመት በኋላ ነው የመጣሁት፡፡ እስከ አስረኛ ክፍል የተማርኩት አዲስ አበባ ቢሆንም፤ የኮምቦልቻ ልጅ ነኝ፡፡
እንዴት ነበር የሄድሽው?
በፓስፖርት… በኮንትራት ነበር የሄድኩት … ካላስ! የሰውየው ልጆች ግን “የማይሆን” ፊልም ተመልከቺ እያሉ ያስቸግሩኝ ነበር፡፡ ሲመረኝ ጠፍቼ ወጣሁ፡፡ ከዚያም ከጓደኞቼ ጋር በነፃነት ቤት ተከራይተን እየኖርን፣ በ1800 ሪያል ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩኝ፡፡ ቤተሰቤንም ገንዘብ እየላኩ እረዳ ነበር፡፡
ወደ አገርሽ እንዴት ተመለስሽ?
ውጡ ሲባል… ረብሻ ሲነሳ.. ጓደኞቻችን ሲሞቱ.. ሲደፈሩብን.. ‘ድሮም ስደተኛ ክብር የለውም’ ብዬ ተመልሼ መጣሁ..ከሚገሉኝ ከሚያበለሻሹኝ ብዬ እጄን ሰጠሁ፡፡ ብዙ ኢትዮጵውያኖች ችግር ላይ ናቸው.. እባካችሁ ድረሱላቸው፡፡ ብርዱም ፀሃዩም ሲፈራረቅባቸው.. ያሳዝናሉ፡፡ ብዙ ያልመጡ አሉ፤ መምጣት እየፈለጉ፡፡ ስቃይ ላይ ናቸው፡፡ እኔ አሁን አስራ ሶስት ቀን ታስሬ ነው የመጣሁት፡፡ እስቲ ስለ እስሩ ንገሪኝ … ሁለት ቀን ያለ ምግብ ያለ ውሃ ነው የታሰርነው። ከዛ በኋላ ግን ጥሩ ምግብ ሰጥተውናል፣ ጥሩ መኝታም አግኝተናል፡፡ ብዙዎቹ ግን ከእኛ የባሰ ችግር ላይ ናቸው፡፡ መጠለያ ያላገኙ አሉ… ኤምባሲያችንም አይሰማም እንጂ ስንት ጊዜ ደውለን ተናግረናል መሰለሽ፡፡ ግን የሚሰማ የለም፡፡ ከአገራችን ውጡ ካሉ በኋላ ትዕግስት ያጡና መልሰው ይዩዙናል፡፡ በዛን ጊዜ አበሻው፣ ሻንዛ/ጩቤ ይመዛል፡፡ ፖሊስ ራሱን ለማዳን ይተኩሳል። እኔ እንደውም ደህና ነኝ፤ እዛ ላሉት ድረሱላቸው። በምድረ ዱርዬ እየተደፈሩ ነው ያሉት /ለቅሶ/ ስንት ህፃናት አሉ የሚሞቱ፣ የሚታመሙ፡፡ ስንመጣ ደሞ፤ ሻንጣ አትያዙ ተብለን ተመናጭቀን…በጥፊ ተመትተን..መከራችንን በልተናል፡፡
ወንዶችና ሴቶች ለብቻ ነበር የተቀመጣችሁት?
የተቀመጣችሁት አትበይ! የታሰራችሁት በይ፡፡ … የሴት እስር ቤት ለብቻው ነው በሴቶችና በህፃናት ለቅሶ የተሞላ ነው፡፡ እኔ ራሴ ስድስት ያበዱ ሴቶችን ይዤ መጥቻለሁ…/ለቅሶ/
አሁን ቤተሰብ እየጠበቅሽ ነው?
ነበረ ግን ሻንጣዬ ጠፋብኝ፡፡ በርግጥ ጤነኛ ሆኖ መምጣትም ቀላል አይደለም፡፡ እዛ ያሉትን ጥለናቸው ስንመጣ እያለቀስን ነው፡፡ እስር ቤቱ ውስጥ አንድ እርጉዝ ሞታብናለች፡፡ እዛው እስር ቤት እያለን ምጥዋ መጣ፤ ግን የህክምና እርዳታ ባለማግኘትዋ ሞተች፡፡
እስር ቤት ያሉት ምን ያህል ይሆናሉ?
ሰማኒያ ክፍል አለ..በየክፍሉ ስልሳ አምስት ስልሳ አምስት ሰው ነው ያለው፡፡ መካሲመሺ እስር ቤት ይባላል፡፡ የወንድና የሴት እስር ቤት የተራራቀ ነው፡፡ በጣም ረጅም ከመሆኑ የተነሳ በመኪና እንጂ በእግር አይሞከርም፡፡ በአሁኑ ሰዓት በከተማው ያለው እስር ቤት ሞልቶ የመዝናኛና የስብሰባ አዳራሹን ሁሉ እስር
ቤት አድርገውታል፡፡ የተደፈሩት የሞቱት..ሴቶች ብዙ ናቸው፡፡ አንዷን እርጉዝ ለሶስት ሲደፍሯት ሞታለች፡፡
የሌሎች አገር ስደተኞችም እየወጡ ነው ተብሏል…
አዎ፡፡ ኢትዮጵያዊው ከበደሉ ብዛት የተነሳ እየተናነቀው እኮ ነው ግጭቱ የሚከረው፡፡
ሚስቱን እህቱን ከእጁ መንትፈው ሊወስዱበት ሲሉ ነው ጦርነት የሚነሳው፡፡ አበሻ ወንድ እየሞተ ያለው ‹‹ሴቶቻችንን አትንኩብን..›› ስለሚል እኮ ነው፡፡ ኤምባሲው ሊደርስላቸው ይገባል፡፡
አዲስ አድማስ ጋዜጣ

posted by Gheremew Araghaw

ሃበሻው ዶክተርና ልጁ – በአሜሪካ (አርአያ ተስፋማሪያም)

Robel

 

ዶ/ር ጳውሎስ ይባላል፤ ሃበሾችን ጨምሮ የሚያውቁት በርካታ ወገኖች ስለዶ/ር ጳውሎስ ተናግረው፣ አድናቆትና ምስጋናቸውን ሰጥተው አይጠግቡም። በዲሲ ከተዋወቅኳቸው እጅግ መልካም ሰዎች አንዱ ነው። ትብብር ለጠየቁት ሁሉ የነፃ ህክምና እርዳታ ያደርጋል። በተለይ የቁርጥማትና አጥንት ወዘተ ሕመም ለሚያሰቃያቸው በዘመናዊ መሳሪያ ፈውስ ይሰጣል። እረፍት በሆነ ቀን የህክምና መሳሪያውን እንደያዘ ነው የምታገኘው። « ገንዘብ እንክፈልህ..» የሚል ጥያቄ በጭራሽ መስማት አይፈልግም።..በአብዛኛው ከመናገር ይልቅ ማድመጥን ያዘወትራል። ለወገኖቹ አዛኝ፣ እንዲሁም አገሩን የሚወድ ሰው ነው። ንግግሩ ቁጥብ ነው፤ ከእርሱ ጋር ቁጭ ስትል ብዙ የህይወት ልምዶችን ትቀስማለህ።

ዶ/ር ጳውሎስ በመደበኛ ስራው ከአሜሪካ መንግስት ጥሩ ክፍያ ያገኛል። የተቸገሩ ወገኖችን በገንዘብ ጭምር ይረዳል። በደርግ ዘመን የኢህአፓ አባል ነበር። በትግል ተፈትኗል፣ እስርና ስቃይን ቀምሷል።…የዶ/ር ጳውሎስ ልጅ ሮቤል ይባላል፤ በትግል አብራው ከነበረች የቀድሞ ፍቅረኛው በአሜሪካ ተወልዶ ያደገው የ19 አመቱ ወጣት ሮቤል ከወላጅ እናቱ ጋር በቦስተን ይኖራል። …ከ6 ወር በፊት አፕሪል 15 ቀን 2013 በቦስተን ከተማ አስደንጋጭ ነገር ይከሰታል። በእለቱ ኢትዮጲያዊያን አትሌቶች በድል አድራጊነት ያጠናቀቁበት የማራቶን ውድድር ላይ ሁለት ወንድማማቾች ቦንብ በማጥመድ ንፁሃንን ገደሉ፣ በመቶዎች አቆሰሉ።..ድርጊቱ ከተፈፀመ ከሶስት ቀን በኋላ በርካታ የF.B.I አባላት መሳሪያ ወድረው፣በጎማ የሚንቀሳቀስ ታንክ አስከትለው የነሮቤልን መኖሪያ ይከባሉ። በር ሲቆረቆር… ወላጅ እናት ባየችው ነገር ክው ብላ ትደርቃለች።

ከተፈፀመው የሽብርተኝነት ድርጊት ጋር በተያያዘ ሮቤል ተጠርጥሮ እንደሚፈለግ ገልፀው ..ይዘውት ይሄዳሉ። አራት ቀን ለታሰረው ሮቤል ሶስት ታዋቂ ኢትዮጲያዊያን ጠበቆች ጥብቅና ሊቆሙለት ፈቃደኝነታቸውን አሳዩ። ..ከሁለቱ የድርጊቱ ፈፃሚ ወጣቶች አንዱ እነሮቤል መኖሪያ ቤት መጥቶ መፅሃፍ ሲቀበለው የሚያሳይ ቪዲዮ በምርመራው የቀረበ ቢሆንም፣ የሶስተኛ አመት ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነው ሮቤል ከዚህ ወጣት ጋር አብረው የሚማሩ የት/ቤት ጓደኛሞች መሆናቸውንና የሰጠውም መፅሐፍ የትምህርት እንደሆነ መፅሐፉን -ጭምር በማቅረብ ያስረዳል። ..የምርመራ ቢሮው ይህን ከተገነዘበ በኋላ ነበር – በ4ኛው ቀን እንዲፈታ ያደረገው።..ጉዳዩ በፍ/ቤት እየታየ በመሆኑ ሮቤል በመኖሪያ ቤቱ የቁም እስረኛ እንዲሆን ተደረገ።

በአንዱ እግር ብቻ (እንደ እጅ ሰአት የሚታሰር አይነት) “tether ankle monitor” የሚባል ኤሌክትሮኒክስ መቆጣጠሪያ ተጠልቆለታል። ይህ መሳሪያ የሚገጠምለት ሰው ከተፈቀደለት ክልል ውጭ አልፎ ከሄደ መሳሪያው ለፖሊስ ጥቆማ ይሰጣል፣ በደቂቃዎች ውስጥ ፖሊስ ይደርሳል።…ዛሬ አርብ ኦክቶበር 18 ቀን ሮቤል ፍ/ቤት ይቀርባል።….ዝርዝር ጉዳዩን ያጫወተኝ ወላጅ አባቱ ዶ/ር ጳውሎስ፣ በመከፋት ስሜት ቅዝዝ ብሎ ፥ « አልፎ…አልፎ ልጠይቀው እሄዳለሁ፤ ተሰናብቼው ስወጣ ከቤቱ በር ማለፍ ስለማይችል አይኖቹ ውስጥ ቅሬታ አነባለሁ።

እኔም ሆዴ እየተላወሰ ይከፋኛል። ትንሽ ይረብሻል። ..ሞራሉ ግን ጥሩ ነው፤ ቤት ሆኖ ትምህርቱን ያጠናል፣ ያነባል። ሮቤል ልጄ ስለሆነ ሳይሆን፣ የዚህ አይነት የሽብር ወንጀል ላለመፈፀም ኢትዮጲያዊ መሆን ብቻ በቂ ነው!! ሃበሻ አሸባሪ አይደለም!! » አለኝ።…

http://ecadforum.com/

posted by Tseday Getachew

 

አንድ ከሰዓት በመንበረ ፓትርያርክ

የመንበረ ፓትርያርክ 32ኛው ጉባኤ የረቡዕ ዕለት ከሰዓት ውሎ ካለፉት የተለየ ነበር፡፡ ዋና አጀንዳው ‹መቻቻልን› የተመለከተ ሲሆን አቅራቢዎቹም ከፌዴራል ጉዳዮች የተወከሉ አካላት መሆናቸውን በዕለቱ የመርሐ ግብር ዝርዝር ላይ ተገልጧል፡፡ ከሰኞ ጀምሮ ይቀርብ በነበረው የአህጉረ ስብከት ሪፖርቶች ላይ የመብት ጥሰትና ሥልጣንን ለግል ሃይማኖት ማስፋፊያ የመጠቀም አዝማሚያዎች መኖራቸውን፣ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠው እምነትን የመያዝ፣ የማስፋፋትና የአምልኮ ቦታ የማግኘት መብት እየተጣሰ መሆኑን የሚገልጡ ዘገባዎች ይሰሙ ነበር፡፡
በትናንትናው የከሰዓት ውሎ ስለ መቻቻል ገለጣ ከተሰጠ በኋላ ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳትና የጉባኤው ተሰብሳቢዎች የየአካባቢያቸውን ችግሮች በዝርዝር ነበር ያነሷቸው፡፡ ‹‹መቻቻል እስከ ምን ድረስ ነው›› ብለው ነበር ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ የጠየቁት፡፡ ‹‹አሁን በምዕራብ ወለጋ ያለው ሁኔታ መንግሥት በአገሩ ያለ ይመስላል ወይ? ሰው እግሩን እሳት እየበላው ቻል ይባላል እንዴ? እንድንቻቻል አድርጉን፣ እንችላለን›› ነበር ያሉት፡፡
የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሄኖክ ‹በነጆ ወረዳ በሕጋዊ መንገድ ተሠርቶ የነበረው ቤተ ክርስቲያን በአካባቢው ባለ ሥልጣናት ተጽዕኖ እንዲፈርስ መደረጉን፣ ለምን ታፈርሳላችሁ ብለው ድርጊቱን የተቃወሙ ስድሳ ምእመናን መታሠራቸውን›› በኀዘን ነበር የገለጡት፡፡ አያይዘውም ‹‹በባኮ ወረዳ የተመደቡ አንድ ካህን እያረሱ እያሉ የአካባቢው ባለ ሥልጣናት መጡ፤ ካህኑን በሰደፍ እየደበደቡ ‹ከዚህ ሀገር ልቀቁ፣ ይህ የነፍጠኛ መኖሪያ አይደለም› እያሉ አሰቃዩዋቸው፡፡ ካህኑን ሲደበድቧቸው አንበርክከው፣ ለ15 ደቂቃ አተኩረው ፀሐይዋን እንዲያዩ እያስገደዱ ነበር፡፡ ድብደባውን ሰምተው የወጡት ባለቤታቸው በድንጋጤ ታመው ከጥቂት ቀናት በኋላ ሕይወታቸው አለፈ››
‹‹በሰንበትና በቅዱስ ሚካኤል ቀን ምእመናን ሊያስቀድሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ ‹ለቅዳሴ ካህናቱ ይበቃሉ፤ እናንተ ውጡ›› እየተባሉ እንዳያስቀድሱ ይደረጋሉ፡፡ ከእኛ ቤተ ክርስቲያን 70 ሜትር ርቀት ላይ ሆን ተብሎ እርስ በርስ ለማጋጨት ለፕሮቴስታንቶች የጸሎት ቦታ ተሰጠ፡፡ ለምን ታጨቃጭቁናላችሁ፤ ይህ ቦታ ለእነርሱ አይሆንም ብሎ በመከራከሩ አንድ ዲያቆን ተደብድቦ ሞተ፡፡ የሕክምና ውጤቱም ሆን ተብሎ በወባ በሽታ ሞተ ተብሎ ተሠራ፡፡ ለሁለት ዓመት ያህል ተከራክረን አሁን ቦታው ለእኛ ተወሰነ፡፡
ጊምቢና መንዲ ላይ የምእመናን ልጆች ትምህርት ቤት ውስጥ በፖሊስ ማተባችሁን በጥሱ እየተባሉ ነው፡፡ ለምን ስንላቸው ከላይ የወረደ መመሪያ አለ ይሉናል፡፡››
ቀጥለው የሀገረ ስብከታቸውን ችግር ያቀረቡት የጋሞጎፋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤልያስ ነበሩ፡፡ ‹‹በጋሞ ጎፋ መቱ ወረዳ፣ ዋጁ ኡቆ ላይ የመስቀል ማክበሪያ ቦታችን ለሱቅ መሥሪያ ቦታ ተሰጠ፡፡ አቤት ብንል የሚሰማን በማጣታችን ዘንድሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መስቀል ሳናከብር ዋልን፡፡ ሀገሪቱ በችግር ላይ በነበረች ጊዜ እንኳን መስቀል ሳይከበር ቀርቶ አያውቅም ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያን የይዞታ ቦታ ለመንግሥት እየተሰጠ ነው፡፡ በአቡነ ጳውሎስ ዘመን በቅዱስነታቸው በኩል ለክልሉ ደብዳቤ ጻፍን፡፡ ክልሉ ወሰነልን፡፡ ነገር ግን እስካሁን አልተረከብንም፡፡››
ቀጥለው ሃሳባቸውን የሰጡት የባሰ ካልመጣ በቀር ድምጻቸው ማይሰማው ብጹዕ አቡነ ያሬድ የሶማሌ ክልል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ ‹‹በሶማሌ ክልል አምስት አብያተ ክርስቲያናት ብቻ ናቸው ያሉን፡፡ ምእመናኑ ብዙ ናቸው፡፡ ሲወልዱ የሚያስጠምቁበት፣ ሲያርፉ የሚቀበሩበት ቤተ ክርስቲያን እንትከል ብንል የሚሰማን አጥተናል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን የሚረዱ ምእመናን በግላቸው ጥቃት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ለዚህ መልሳችሁ ምንድን ነው›› ብለዋል፡፡
በገለጻው ላይ ኢትዮጵያ ክርስትናን የተቀበለችው በ4ኛው መክዘ ነው የሚለውን የተቃወሙት ብጹዕ አቡነ ማርቆስ ‹‹ታሪክ ክፉም ሆነ በጎ እንደ ታሪክነቱ መተረክ አለበት፤ አቅራቢው ወንድማችን በ4ኛው መክዘ ክርስትና ገባ ያልከው ተሳስተሃል፡፡ ለመሆኑ ይህንን ለማለት ‹ላይሰንስ አለህ?› አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል? ነገሥታቱን ወቀሳችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ነቀፋችሁ፤ ለመሆኑ ከማን ነው ይህቺን ሀገር የተረከባችሁት? ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው ጌታ ባረገ ዓመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8 ላይ አለ፡፡ ይህንን ዛሬ ‹ግራጁዌት አድርገው›፤ ልዑካኑ ስትመጡ ስለምትናገሩት ነገር ዕወቁ፤››
የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ እንድርያስም ‹‹በቤተ መንግሥት የወርቅ ዕቃ ብቻ አይኖርም፣ የእንጨትም፣ የድንጋይም ዕቃ አለ፡፡ በቤተ ክርስቲያንም ሁሉም ጥሩ አይሆንም፣ መጥፎም ይኖራል፡፡ ነገር ግን እስከ መጨረሻው የጸና ይድናል ብሏል፡፡ በእኔ ሀገረ ስብከት ስድስት አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፡፡ ሦስቱ በአንድ አካባቢ፣ ሦስቱ በሌላ ቦታ፡፡ ይህንን ለክልሉ መንግሥት ብናሳውቅ አልረዱንም፡፡ የተበደለ ሰው ይጮኻል፤ ሲጮህ ደግሞ ፖለቲካ ነው ይባላል፡፡ ድሮ ያስቸገረን የንዋያተ ቅድሳት ዘረፋ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ወደ ማቃጠል ተዛውሯል፡፡ አንዱ ባለ ሥልጣን እንዲያውም ችግሩን ሳቀርብለት ተቆጣኝ፤ ብዙ ብናገር ነፋስ ስለሚወስደው እዚህ ላይ ይብቃ››
ከብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳት ቀጥሎ የተናገሩት የወላይታ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ‹‹በበዴሳ ወረዳ ያለ አንድ የሌላ እመነት ተከታይ የሆነ ዳኛ ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጋር ቄራ አንካፈልም፤ በመኪና አብረን አንሄድም› ብሎ ዐወጀ፡፡ በጋራ በመቻቻል የኖርንበትን ዕድር ሁሉ ለዩ ብሏል፡፡ ታድያ እንዴት መቻቻል ሊመጣ ይችላል፡፡››
ከጉባኤው የቀረበውን ቅሬታና ሃሳብ ያዳመጡት የፌዴራል ጉዳዮች የሥራ ኃላፊዎች የቀረቡት ቅሬታዎች በሰነድ ተደግፈው ቢደርሷቸው እነርሱም በመፍትሔው ላይ መሥራት እንደሚችሉ፤ ኢትዮጵያ የሃይማኖቶች ጉባኤም ጉዳዩ በየደረጃው ቢቀርብለት መፍታት እንደሚችል፡፡ ቅሬታዎችን እንደዚህ ባለ መድረክ ከሚሆን በየጊዜው እየተገናኙ መፍታት ቢቻል›. የሚሉ ሃሳቦችን ሠንዝረዋል፡፡
የዘንድሮው የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ በአደረጃጀቱ ውበት፣ በተሳታፊዎቹ ብዛት፣ በአህጉረ ስብከቶች ቁጥር(50 ደርሰዋል)፣ በስብሰባው ቁም ነገረኛነት ካለፉት የተለየ ነበር፡፡ እነ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን በብርቱ እንደ ደከሙበት ያሳያል፡፡ በየዘገባዎቹ የተሰሙትን የመብት ጥሰቶች፣ ሥልጣንን ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ ጫናዎች፣ የአምልኮ ቦታ እጥረቶች፣ በካህናቱ ላይ የሚፈጸሙትን ግፎችና፣ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ የመንጠቅ ርምጃዎች ግን ሊገቱ ይገባቸዋል፡፡ ከአንዳንድ ክልሎች በቀር በብዙዎቹ የዞንና የክልል ባለ ሥልጣናት ችግሩን ተረድተው ለመፍታት እንደሚጥሩ ተገልጧል፡፡ በወረዳ ደረጃ የሚገኙት ግን ሥልጣንን ተገን በማድረግ የግል እምነታቸውን እያስፋፉ መሆኑን ያሳያል፡፡ በደቡብ ጎንደርና በምሥራቅ ጎጃም የተፈጸሙት የአብያተ ክርስቲያናትን የማቃጠል ርምጃዎች በጊዜው ተጣርተው መፍትሔ ካልተሰጣቸው ፍጻሜያቸው አያምርም፡፡
በየአካባቢው በሚገኙ ባለ ሥልጣናት የሚፈጸሙ ትንኮሳዎችም መቆም አለባቸው፡፡ ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳቱ ‹አታስቆጡን› እያሉ ደጋግመው የተናገሩት ነገር የዋዛ አይደለም፡፡ ኃላፊነት የማይሰማቸው አካላት የሚፈጽሙት ገደብ አልባ ትንኮሳና ጫና ወዴት እያመራ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱም አደረጃጀቷንና አሠራርዋን ይበልጥ የምትፈትሽበት፣ አሁን ለገጠማት ተግዳሮት ብቁ የሚሆን አሠራና አወቃቀር የምትይዝበት፣ ችግሮችን በስብሰባ ብቻ ሳይሆን በአካባቢያዊ ውይይት፣ በሕግ መሥመርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀራርቦ በመሥራት የምትፈታበት መንገድ ሊኖር ይገባል፡፡
ያለበለዚያ መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል የተረተው ተረት መድረሱ የማይቀር ነው፡፡
በጣልያን ጊዜ ነው አሉ፡፡ ጎንደር ላይ ጣልያን በድማሚት አንዱን ተራራ ያናውጠዋል፡፡ ተራራው ‹እድም› እያለ ይፈርሳል፡፡ አንዲት የከብት እረኛ ልጅ ፈርታ ወደ እናቷ ሄደችና ‹እማዬ ኧረ ጣልያን ተራራውን እያፈረሰው ነው›› አለቻት፡፡ እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡፡
posted by Tseday Getachew
 

መንገድ ወድቆ አየሁት (ክንፉ አሰፋ)

 

 

Sened Gebretsadik

Sened Gebretsadik, an account of a man who survived the Sahara desert and Mediteranean misery

ርሃብ፣ ድካም እና ሰቆቃው ለላፉት 12 ወራት ተፈራርቀውበታል። አንዴ በሰሃራ በረሃ ሌላ ግዜ ደግሞ በሜዲትራንያን ባህር የሰው አእምሮ ሊቀበለው የማይችል ስቃይ አልፎ እግሩ አውሮፓን ምድር ከረገጠ እነሆ አንድ ሌሊት አለፈ። ሰነድ ገብረጻድቅ ይባላል። ፊቱ እጅግ ተጎሳቅሏል። ከሰውነቱ ላይ አጥንቶቹ ይቆጠራሉ።

ወጣቱ  ተስፋ ወዳደረገባት የአውሮፓ ምድር ለመግባት የተነሳው ከአመት በፊት ነው። እንብርቱ የተቀበረችበትን ሃገር ተሰናብቶ ከወጣ ጀምሮ የደረሰበት መከራ ይህ ነው አይባልም። ሰነድን እመንገድ ወድቆ ነበር ያገኘሁት። ለጥቂት ደቂቃ አነጋገርኩት። ንግግሩ የሚረብሽ ነው። አጭር የቪዲዮ ቆይታችንን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።

EMF

posted by Tseday Getchew

 

ቴዲ የኩዋስ ሜዳ ልጅ ነው – (ሄኖክ የሽጥላ -ገጣሚው)

(ሄኖክ የሽጥላ -ገጣሚው)

ከምን ልጀምር? እንደው ይጨንቃል፤ ደሞ ዝም ቢሉት ያንቃል። አሁን ይሄን የምጥፈው ለማስተማር ነው ለማካረር? በልጅነቴ አንድ አብሮ አደጌ በጣም የሚወዳቸው እናቱና አባቱ እየተጋጩ ቢያስቸግሩት፥ ሄኒ አሁን አንተ በኔ ቦታ ብትሆን ማንን ትጠላለህ? ብሎ የጠየቀኝ ትዝ አለኝ። ማንን ልጥላ? ለማን አግዤስ ማንን ላውግዝ?
ማንንስ ልውቀስ? ማንንስ ልጥቀስ? ሲደብር።
በእውነትም ይደብራል። ለካ ያራዳ ልጆች ወደው አይደለም ድብርት የሚለውን ቃል የሚያዘወትሩት። እንደነሱ ፍቅር፤እንደነሱ መተሳሰብ፤ እንደነሱ ንጽህናን ማን አውቆት። ለካ ያም እንዳይጎዳ ፤ ይሄም እንዳይከፋው ፈልገው ነው፤ በቃ ተወው እሱ ደባሪ ነው፤ ብለው የሚያልፉት። ምነው ያራዳ ልጅ በሆንኩ።

በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

“አንድ ሄክታር መሬት በ1 ፓኮ ሲጋራ ዋጋ መቸብቸብ ራዕይ ነው?” – የተስፋዬ ገ/አብ ቃለ ምልልስ

life

(ይህ ቃለመጠይቅ አዲስአበባ ላይ በየ15 ቀኑ ከሚታተመው “ላይፍ” መፅሄት ጋር የተደረገ ሲሆን፤ ቃለመጠይቁ የተካሄደው ከመፅሄቱ ጋዜጠኛ ጋር በፌስቡክ በኩል በተደረገ ግንኙነት በፅሁፍ ነው። መፅሄቱ ለአገር ውስጥ አንባብያን ቅዳሜ መስከረም 28 ገበያ ላይ የሚውል በመሆኑ ግልባጩ በዚህ መልኩ ቀርቦአል።)

• አዲሱ “የስደተኛው ማስታወሻ” መጽሐፍህ ከ“የደራሲው ማስታወሻ” እና ከ“የጋዜጠኛው ማስታወሻ” በምን ይለያል?

 “የስደተኛው ማስታወሻ” ከቀዳሚዎቹ ማስታወሻዎች የቀጠለ ነው። በዚህ ቅፅ በተመሳሳይ ገጠመኞቼን ነው ያሰፈርኩት። በርግጥ እንደ ሰንሰለት የተያያዙ የአውሮፓ የስደት ገጠመኞቼ ተተርከውበታል። ይህ ቅፅ የማስታወሻዎቼ መደምደሚያ ሲሆን፣ ከዚህ በሁዋላ ወደ ስነፅሁፍ ስራዎች ነው የምገባው።

• “የስደተኛው ማስታወሻ” አሳታሚ ማነው? መቼ ለገበያ ይቀርባል?

 “ነፃነት አሳታሚ” ይባላል። ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኝ የኢትዮጵያውያን ንብረት የሆነ አሳታሚ ድርጅት ነው። ውል አድርገን መፅሃፉን አስረክቤያለሁ። የጀርባና የፊት ሽፋኑን ዲዛይን ሰርተው ልከውልኝ አፅድቄያለሁ። መፅሃፉ በህትመት ፕሮሰስ ላይ እንደሆነ መስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ነግረውኛል። ጥቅምት ገበያ ላይ ይውል ይሆናል። በትክክል ቀኑን አላውቅም። መረጃዎቹን በድረገፃቸው በኩል ይፋ ያደርጉታል።

• አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ስራዎችህ የሁለት የተለያዩ ሰዎች ተጽዕኖ ውጤት ነው ይላሉ፡፡ ከአሰፋ ጫቦ ሽሙጥን፣ ከበዓሉ ግርማ ጀብደኝነትን። ምን ትላለህ?

 አሰፋ ጫቦ አሽሟጣጭ ነው ብዬ አላስብም። በአሉ ግርማም ጀብደኛ አይመስለኝም። ስለሁለቱ ብእረኞች በዚህ መንገድ ማሰብ ስህተት ነው። የአሰፋ ጫቦን ብዕር አደንቃለሁ። አሽሟጣጭ ሳይሆን እውነታዎችን በቀጥታና በግልፅ የሚናገር ደፋር ብእረኛ ነው። በአሉም የሰከነ ብዕር የነበረው ደራሲ ነው። ጀብደኛ ሊያሰኘው የሚችለው ስራው የቱ ነው? ምናልባት “ኦሮማይ”ን በማሰብ ከሆነ፣ በአሉ ግርማ በዚህ መፅሃፍ ምክንያት ሊገደል እንደሚችል ቢገምት ኖሮ ከዚያ የተሻለ ስራ ይሰራ ነበር። ወደ ጥያቄው ስመለስ የበአሉና የአሰፋ ጫቦ ተፅእኖ የለብኝም ለማለት አልችልም። ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ግን የወርቃማው ዘመን የሩስያ ደራስያን ብእረኞች ይበልጥ ቀልቤን ይስቡታል። እንደምገምተው ማስታወሻዎቼ ይበልጥ የቱርጌኔቭ የህይወት ታሪክ ማስታወሻዎች ተፅእኖ ሳይኖርባቸው አይቀርም። ወደ ትረካው ጥበብ ስንመጣ ስብሃት ገብረእግዚአብሄርና ጎርኪይ ምንግዜም አብረውኝ አሉ። ዞረም ቀረ አንድ የብዕር ሰው በጊዜ ሂደት በተለያዩ ፀሃፊዎች የአፃፃፍ ስልት ሊገነባ ይችላል።

• በአሁን ጊዜ ለአማርኛ ስነ ጽሑፍ ምን ያህል ቅርብ ነህ? ከታተሙት መፃህፍት መካከል የምታደንቀው አለ? ‘አብሬው በሰራሁ’ ስለምትለው ወይም በልዩ ሁኔታ ስለምታስታውሳቸው ደራስያን የምትገልፀው ካለም እድሉን ልስጥህ?

 ለአማርኛ ስነፅሁፍ ቅርብ ነኝ ለማለት አልችልም። የሚታተሙ መፃህፍትን እንደልቤ ለማግኘት ስለምቸገር ስለታተሙ መፃህፍት በልበ ሙሉነት አስተያየት ለመስጠት እቸገራለሁ። በጥቅሉ ግን የአማርኛ ስነፅሁፍ አደጋ ላይ የወደቀ ሆኖ ይሰማኛል። አማርኛ በአዲሳባና በአማራ ክልል ቋንቋነት ብቻ ተወስኖ እንዲቀር ብዙ ተሰርቶበታል። ይህ ሁኔታ የአማርኛ ስነፅሁፍን ክፉኛ ጎድቶታል። አማርኛ ቋንቋ ጠላት ስለበዛበት ስነፅሁፉም ባለቤት አጥቶአል። ይህ አሳዛኝ እውነት ነው።

ስለ ደራስያን ወይም ስለ ብዕር ሰዎች የጠየቅኸኝ ጥያቄ ስሜታዊ የሚያደርግ ነው። በልጅነቴ ሳመልካቸው የኖርኩት አንዳንዶቹ የብዕር አማልክት ዛሬ በህይወት የሉም። ከጥቂቶቹ ጋር ከመተዋወቅ በላይ አብሬያቸው ለመስራት በቅቻለሁ። የቅርብ ጓደኞቼ የሆኑም አሉ። ከስብሃት ገብረእግዚአብሄር ጋር አብሬ በመስራቴ በምንም ነገር የማይለካ ልምድ አጊንቼያለሁ። የአርትኦትን ጥበብ ከአረፈአይኔ ሃጎስ ተምሬያለሁ። እሸቱ ተፈራ ቤተመፃህፍት ማለት ነበር። ማሞ ውድነህ ወዳጄ ነበሩ። “እነዚህ አለቆችህ” እያሉ ወያኔን ያሙልኝ ነበር። አበራ ለማ ወጣቶችን በማገዝ ሱስ የተለከፈ ደራሲ ነበር። የሺጥላ ኮከብ ምርጥ ደራሲ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ነካ ያደርገዋል። የእፎይታ መፅሄትን አንደኛ አመት ስናከብር መጣና እንዲህ አለኝ፣
“አንድ የማይረባ መፅሄት አንድ አመት ስለሞላው ምንድነው ይህ ሁሉ ቸበርቻቻ?”
የሺጥላ ይህን ሲናገር ነጋሶ ጊዳዳ እና አለምሰገድ ገብረአምላክ በአካባቢው ነበሩ።
“ሞቅ ስላለህ ወደ ቤትህ ሂድ” አልኩት።
መአዛ ብሩና አበበ ባልቻ የልብ ወዳጆቼ ነበሩ። ሃይስኩል እያለሁ ከመአዛ ብሩ ድምፅና ሳቅ ጋር ፍቅር ይዞኝ ነበር። አሁንም አልተወኝም። የመአዛን ሳቅ ለመስማት ስል የሸገር ሬድዮ ቁራኛ ነኝ። ተፈሪ አለሙና ማንያዘዋል እንደሻውን አልረሳቸውም። የማንያዘዋል ወንድም ይሁን እንደሻው ራሱ አሪፍ ፀሃፊ ነው። ከሳህለስላሴ ብርሃነ ማርያም እና ከአያልነህ ሙላቱ ጋር ባለመስራቴ በጣም ይቆጨኛል። ከተሰደድኩ በሁዋላ ግን ለአያልነህ ደወልኩለት። የማክሲም ጎርኪይን የትውልድ ቦታ ኒዥኒይ ኖቭጎሮድን ለመጎብኘት ፈልጌ ስለነበር አስጎብኚ እንዲያዘጋጅልኝ ለመጠየቅ ነበር የደወልኩለት። ሃይለመለኮት መዋእል ከኔ ጀግኖች አንዱ ነው።
በፍቃዱ ሞረዳን አልወደውም። ምክንያቱም ከመሬት ተነስቶ ነገር እየፈለገ ያበሳጨኛል። ተወኝ ብለው ሊተወኝ አልቻለም። 2009 ላይ ጦርነት ገጥመን ነበር። በቅርቡ ግን አሪፍ ግጥም ፅፎ ሳነብ ያናደደኝ ሁሉ ብን ብሎ ስለጠፋ አድናቆቴን በፅሁፍ ገለጥኩለት።
ምነው አብሬያቸው በሰራሁ የምላቸው በርካታ ወጣት የብእር ጀግኖች አሉ። በእውቀቱ ስዩም፣ ኑረዲን ኢሳ፣ ሲሳይ አጌና፣ ኤፍሬም ስዩም፣ አዳም ረታ፣ ይስማእከ ወርቁ፣ ማረፊያ በቀለ…እንዲህ እያልኩ ትዝታዬን ከቀጠልኩ መቶ ገፅ አይበቃኝም። ጥያቄህን መልሼልህ ይሆን?

• ለአንድ ጀማሪ ደራሲ በአንተ አስተውሎት መጠንና ጉልበት እንዲጽፍ ምን ትመክረዋለህ?

 በርግጥ በአስተውሎትና በብርታት እየፃፍኩ መሆኔን ካመንክ አመሰግናለሁ። ተሰጥኦ ያለው ጀማሪ ደራሲ ጥሩ የሚባሉ መፃህፍትን በጥንቃቄ መርጦ በዝግታ ያነብ ዘንድ እመክረዋለሁ። ብዙ ማንበብ ብቻውን ጥሩ ደራሲ አያደርግም። መምረጥና በጥልቀት ማንበብ ይገባል። በጥልቀትና በዝግታ ማንበብ ሲባል ታሪኩን ብቻ አይደለም። ቃላት አመራረጥ፣ አረፍተነገር አሰካክ፣ የአገላለፅ ዘዴዎችን በጥንቃቄ መመርመር ማለት ነው። ሌላው ጉዳይ ጀማሪ ደራስያን ያልኖሩበትን ህይወት ለመፃፍ እንዳይሞክሩ እመክራለሁ። ልጅ ያልወለደ ሰው ስለ ልጅ ፍቅር ሊያውቅና ሊፅፍ አይችልም። ቢፅፍም የተሳካለት አይሆንም። ስለ ገበሬ መፃፍ ከፈለጉ ጥቂት ቀናትን ከገበሬዎች ጎጆ ማሳለፍ መቻል አለባቸው። ይህን ጉዳይ ቼኾቭ አጥብቆ መክሮ ነበር። ስሞክረው ልክ እንደሆነ አወቅሁ። “በብርታት መፃፍ” የሚለው መቸም አከራካሪ ነው። እኔ በብርታት እየሰራሁ ያለሁት (በርግጥ ከሆነ) ሙሉ ጊዜዬን በፅሁፍ ስራ ላይ ስላዋልኩ ሊሆን ይችላል። ተሰጥኦ ያላቸው ሰዎች ሌላ ምንም ስራ ሳይሰሩ ፅሁፍ ላይ ብቻ የሚያተኩሩበት እድል ካገኙ በብርታት ብዙ ሊሰሩ ይችሉ ይሆናል። ኑሮውን ለመደጎም ሲል የማይወደው ስራ ላይ የሚባክን የብዕር ሰው የተሳካለት ስራ ለመስራት ይቸገር ይሆናል።

• ፖለቲካ ውስጥ ባይገባ ኖሮ “ስመጥር” ከሚባሉት ደራስያን መካከል አንዱ ይሆን ነበር ለሚሉት ምን ምላሽ አለህ?

 በአንድ ወቅት የኢህአዴግ አባል የሆንኩት ከፍላጎቴና ከእውቅናዬ ውጭ መሆኑን ተናግሬያለሁ። ከወያኔ ጋር በቆየሁበት ጊዜም ቢሆን ጋዜጠኛ ሆኜ ነው የሰራሁት። ከዚያ በሁዋላ ነፃ ሰው ነኝ። የማንም የፖለቲካ ፓርቲ አባል አይደለሁም። “ፖለቲካ ውስጥ ባይገባ” የሚለው አባባል የተጋነነ ነው። የኛ ዘመን ሰው እንዴት ከፖለቲካ መራቅ ይችላል? እንራቅህ ቢሉትስ መች ይሆናል? እንደ ጭስ ቀዳዳ ፈልጎ መኝታ ቤታችን ድረስ ይገባል። በአጋጣሚ ፖለቲካ ውስጥ ስለገባሁ እንደ ጋዜጠኛ እና እንደ ደራሲ የፖለቲካ ገጠመኞቼን ፅፌያለሁ። ይህን በማድረጌ ስህተቱ ምን ላይ እንደሆነ ሊገባኝ አይችልም። እርግጥ ነው፣ አምርረው የሚጠሉኝ ወገኖች አሉ። ከፖለቲካ አመለካከታቸው ተነስተው ሊሆን ይችላል። የምሰራው ስራ ዋጋ ካለው ክብር ያገኛል ብዬ አስባለሁ። እኔ ማድረግ ያለብኝ ልቤን መከተል ብቻ ነው።

• “የስደተኛው ማስታወሻ” መጽሐፍህ ሃገር ውስጥ እንዲነበብ ምን ጥረት ታደርጋለህ?

 ለአዲሱ ጠቅላይ ምኒስትር መልእክት ልኬ ነበር። ምላሽ አላገኘሁም። አንድ የኮክቴል ግብዣ ላይ በወሬ መካከል ስብሃት ነጋ፣ ለበረከት “ለምን አትተወውም? ያሳትም” ብሎት እንደነበር ሰምቻለሁ። በርግጥ ከዚህ አባባል ተነስቼ ችግሩ ያለው በረከት ስምኦን ጋር ብቻ ነው ለማለት አልችልም። በዚያም ሆነ በዚህ ግን ከመነበብ ሊያግዱት አይችሉም። ኮፒው በህገወጥ መንገድ ታትሞ መሰራጨቱ አይቀርም። የስርአት ለውጥ ሲደረግ ግን የታገዱትን መፃህፍት በድጋሚ አሳትማቸዋለሁ።

• ኢሕአፓዎች ይሔንንም መጽሐፍህ እንደማያባዙት ምን ዋስትና አለህ?

 መሞከራቸው አይቀርም። የሚያሰራጩባቸው ድረገፆችና የፊስቡክ ክፍሎች ስለሚታወቁ ህገወጡን ድርጊት ከፈፀሙ በህግ እንዲጠየቁ ጠበቆችን አዘጋጅተናል። በ’ርግጥ ኮፒ የማድረጉን ስራ የሚሰሩት የኢህአፓ ሰዎች ብቻ ናቸው ማለት አይቻልም። የምቀኝነት ህመም ያለባቸው አንዳንድ የአእምሮ በሽተኞችም ድርጊቱን ሊፈፅሙት ይችላሉ። በርግጠኛነት የምነግርህ ወያኔዎች ይህን ድርጊት እንደማይፈፅሙት ነው። የማይፈልጉትን መልእክት በማፈን እንጂ በማሰራጨት አይታወቁም። የኢህአፓ አመራር የኮሎኔል መንግስቱን መፅሃፍ ስካን አድርጎ ሲያሰራጭ መንግስቱ ሃይለማርያምን ገንዘብ ማሳጣት ነበር አላማቸው። የሚያስቅ ጅልነት ነው። መንግስቱ ገንዘብ አይፈልግም። ቀዳሚ አላማው መፅሃፉ እንዲነበብ ነው። ስለዚህ ኢህአፓ ማድረግ የነበረበት መፅሃፉን ገዝቶ ማቃጠል ነበር።

• ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ ዕድሉ ያለ ይመስልሃል?

 የሕወሓት ስርአት ከወደቀ እመለሳለሁ።

• አዲስ አበባ ውስጥ የሚናፍቅህ የትኛው ቦታ ነው? ቁጭ ብለህ ቡና ወይም ቢራ ለመጠጣት የምትመርጠው ቦታስ?

 አዲስአበባ ብዙም አይናፍቀኝ። ይልቁን ደብረዘይት እና የስምጥ ሸለቆ ከተሞች ይናፍቁኛል።ጋራቦሩ ኮረብታ ላይ ቆሜ የረር ተራራን በሩቅ ማየት በጣም ይናፍቀኛል። ቢሾፍቱ ሃይቅ ዳርቻ ከሚገኙ መሸታ ቤቶች ተቀምጬ ማምሸት እፈልጋለሁ። የባቦጋያና የሆራ አርሰዲ ዳርቻዎች በህልሜ እንኳ ይታዩኛል። ድፍን አድአ፣ እስከ ጨፌ ዶንሳ፣ እስከ ሎሜ፣ ያደግሁበት አገር ነው። በቢሾፍቱ ገደሎች ደረት ላይ እንደ ወፍ በረናል። ጋራቦሩን ጋልበንበታል። በህይወት ዘመኔ አንድ ጊዜ ወደነዚህ የአድአ ገጠሮች መሄድ እፈልጋለሁ። ርግጥ ነው፣ የወያኔ ስርአት ሲወድቅ በሚቀጥለው አይሮፕላን ቦሌ ከሚያርፉት መንገደኞች አንዱ እኔ ነኝ። እና ሽው ወደ ቢሾፍቱ!

• በቡርቃ ዝምታ እና በቢሾፍቱ ቆሪጦች መጽሃፍትህ የተጸጸትክበት አጋጣሚ አለ? አሁንም ያለህ አቋም የመጽሐፍቱ ነጸብራቅ ነው?

 በመፃህፍቱ የምፀፀትበት ምክንያት የለም። ይህ ማለት ድክመት የለባቸውም ማለት አይደለም። በ20ዎቹ መጨረሻ እድሜ ላይ ሆኜ የፃፍኳቸው መፃህፍት እንደመሆናቸው ድክመት ሊኖርባቸው ይችላል። የህይወት ልምድ ማጣት፣ ሊንፀባረቅባቸው ይችላል። የቢሾፍቱ ቆሪጦች ከስነፅሁፍ አንፃር ሊተች የሚችል ነው። ድክመት አለበት። እንዲህ ያለ ነገር ሊያጋጥም ይችላል። በአሉ ግርማ “የቀይ ኮከብ ጥሪ” ተበላሽቶበታል። ጥሩ አልነበረም። ብርሃኑ ዘርይሁን በወጣትነቱ የፃፋቸውን፣ “ጨረቃ ስትወጣ” አይነቶቹን ተመልሰህ ብታነብ ብርሃኑ ነው የፃፋቸው ለማለት ትቸገራለህ። ስነፅሁፋዊ ክህሎት እያደገ ስለሚሄድ በገፀባህርያት ቀረፃ ላይ ድክመት ሊታይ ይችላል። የሃያስያን መኖር አስፈላጊ የሚሆነው ለዚህ ነው። የቡርቃ ዝምታ መልእክቱ ላይ ችግር የለበትም። አሁንም የማምንበት ነው። የቡርቃ ዝምታን በመፃፌ እንደማልፀፀት ደጋግሜ ተናግሬያለሁ። የኦሮሞ ህዝብ ሰብእና ላይ የተፈፀመውን ግፍ የሚያሳዩ የጥበብ ስራዎች ወደፊትም መፃፍ አለባቸው። መሸፋፈን መፍትሄ አይሆንም። አብሮ ለመኖር ባለፈው ታሪክ ላይ መተማመን ይገባል። የቡርቃ ዝምታ የጭቆናውን ክብደት ለማሳየት የሞከረ መፅሃፍ ነው። የጭቆናውን ክብደት ማወቅ ተከባብሮ ለመኖር ያግዛል እንጅ የዘር ጦርነትን አይቀሰቅስም።

• ተስፋዬ ገብረአብ ጠቡ ከኢህአዴግ ጋር ሳይሆን ከኢትዮጵያ ነው የሚሉህ ሰዎች ለዚህ እንደ ማሳያ የሚያቀርቡት መጽሐፍህ በአማራ በትግሬ እና በኦሮሞ ህዝብ ቁርሾዎች ላይ ብቻ ያተኮሩ በመሆናቸው ነው ይላሉ? ምን ትላለህ?

 ስለ ዘር መነጋገር ወቅቱ ያመጣው አጀንዳ ነው። በየትኛውም የፖለቲካ ውይይቶች ላይ ቁርሾዎች የመወያያ አጀንዳ ሆነዋል። እኔ የጀመርኩት አይደለም። ክልላዊነትን ያስቀደመ የፖለቲካ ስርአት ነው ያለው። የማንነት ጥያቄ ቀዳሚ አጀንዳ ሆኖአል። አንድ የጥበብ ሰው የዘመኑን ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት አድርጎ መፃፍ ግዴታው ነው። “በአማራና በኦሮሞ መካከል ፀብ ለመፍጠር” የሚል አባባል እሰማለሁ። ይህ አባባል ከቡርቃ ዝምታ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው። የቡርቃ ዝምታ ታሪክ የኦሮሞ ህዝብ ስለ ራሱ ከሚያውቀው አንድ አራተኛውን እንኳ አልያዘም። ታሪኩን፣ አባባሎችን ቃላትን ያገኘሁት ከኦሮሞ ገበሬዎች እንጂ ከራሴ ፈጥሬው አይደለም። ያልተለመደ አቀራረብ ስለሆነ ሰዎች ሊሰጉ ይችላሉ። አዲሱ ወጣት ትውልድ መራራ ቢሆንም እንኳ እውነትን የመስማት ችሎታ አዳብሮአል። የሚደርሱኝ ደብዳቤዎች ይህን ጠቁመውኛል። በግልፅ በመነጋገር ችግሩ ይታወቃል። ችግሩ ከታወቀ ነው መፍትሄው የሚገኘው። በማድበስበስና በመሸፋፈን ግጭቶችን ማስቀረት አልተቻለም። ደርግም ሃይለስላሴም ሞክረውት አልተሳካም። ይልቁን ማፈን መፍትሄ እንዳልሆነ ማረጋገጫ ሰጡ። የታመቀ ስሜት ቢፈነዳ ይመረጣል።ቢነገር ይሻላል። ሲተነፍስ መፍትሄውም አብሮ ይመጣል።

• ከዚህ በፊት በአንተ ብሎግ ላይ ያሰፈርካቸው “የልዑሉ እናት”፣ “የመነን 4ተኛ ባል” እና “የንጉሱ ሴት ልጅ” መጣጥፎች ያነበቡ ሰዎች የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት ለመቀባት ሆን ብለህ ያደረግከው ነው ለሚሉት ምን ትላለህ?

 በ’ርግጥ የመሪዎች ደካማ ጎኖች ላይ የመፃፍ ፍላጎት አለኝ። ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ በጎ እና ጠንካራ ጎናቸው ብቻ ነው ተደጋግሞ የሚፃፈው። መፃህፍት መሪዎችን በማሞገስ የተሞሉ ናቸው። ደካማ ጎናቸው በግልፅ ቢፃፍ አንባቢ ብዙ ትምህርት ያገኛል ብዬ አምናለሁ። በተለይ ደ’ሞ መሪዎች እንደ ማንኛውም ሰው ተራ ሰዎች መሆናቸውን ማሳየት እፈልጋለሁ። በአካባቢያችን መሪዎችን የማምለክ ዝንባሌ አለ። ከወረዳ አስተዳዳሪ ጀምሮ ለተቀመጡ መሪዎች መስገድ ባህል ሆኖአል። መነሻዬ ይህ እንጂ ሌላ አይደለም። እንደ ደራሲ ታሪኩ እውነት እስከሆነ ድረስ በማንኛውም ርስሰ ጉዳይ ላይ እንደፈለግሁ አገላብጬ የመፃፍ መብት አለኝ። ታሪክ ቀመስ ልቦለድ ልሰራባቸውም እችላለሁ። ያም ሆኖ ተፈሪ መኮንን ለመነን 4ኛ ባሏ የመሆኑ መረጃ ስለ ፖለቲካዊ ጋብቻ ግንዛቤ ይሰጣል እንጂ ንጉሱን አያዋርድም። ደጃዝማች ተፈሪ 4 ልጆች ያላት ወይዘሮ በማግባቱ አደንቀዋለሁ። “ልጃገረድ ካልሆነች አናገባም” ለሚሉ አክራሪዎች ጥሩ አርአያነት ነው። መንግስቱ ሃይለማርያም ውባንቺ ቢሻው የተባለች ሚስቱን ያገባው አስገድዶ በጠለፋ ነው። ከዚህ ምንም ትምህርት አይገኝም። አዜብ መስፍን ለመለስ ዜናዊ ሻይ እንድታፈላ በድርጅቱ የተመደበችለት ታጋይ ነበረች። በዚያው ጠቀለላት። ይሄ ጥሩ ነው። እንዲህ ያሉ ታሪኮችን የመፃፍ ፍላጎት አለኝ። እንዳልኩት በመሪዎች ትከሻ ላይ የተቆለለውን የመኮፈስ ካባ ገፍፌ መጣል እፈልጋለሁ። “የልዑሉ እናት” የሚለውን ታሪክ የፃፍኩት የጳውሎስ ኞኞን መፅሃፍ መሰረት አድርጌ ነው። “የመነን 4ኛ ባል” ዘውዴ ረታ ከፃፉት የተወሰደ ነው። እኔ ስፅፈው የተለየ የሚሆንበት ምክንያት ምንድነው? እንዲህ የሚያስቡ ሰዎች ልባቸው ውስጥ የሸሸጉትን የዘረኛነት በሽታ ያክሙት ዘንድ እመክራቸዋለሁ። ሰዎች ስለኔ የሚያስቡትን ግምት ውስጥ እያስገባሁ ልፅፍ አልችልም። በማንኛውም ርእሰ ጉዳይ ላይ በራሴው እይታ እንዳሻኝ እፅፋለሁ። አንባቢዎቼን ለማስደሰት ወይም ለማናደድ ብዬ አይደለም የምፅፈው። ቢታተምም ባይታተምም የኔ ችግር አይደለም። ኳስ መጫወት የሚወዱ ሰዎች ኳስ ይጫወታሉ። እኔም መፃፍ ስለምወድ እፅፋለሁ። ሽማግሌው ቱርጌኔቭ እንደሚለው በጎ ከሰራን፣ ስራችንም ዋጋ ካለው፣ ያን ዋጋ ህዝብ ማስተዋል ከቻለ ለስራችን ክብር ይሰጠናል።

• በብዙ ጽሁፎችህ ለኦሮሞ መብት ጥብቅና የመቆም ዝንባሌ ታሳያለህ፡፡ ነጋሶ እንዳሉት ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ነኝ ማለትን ታበዛለህ ለሚባለው ምላሽህ ምንድን ነው?

 የነጋሶን አባባል ሰምቼዋለሁ። More catholic than the Pope የሚለውን አባባል ገልብጠው ሊጠቀሙበት ነው የሞከሩት። ነጋሶ ጭንቅላታቸውን ተናግረው አያውቁም። ሌሎችን ለማስደሰት በማሰብ የመናገር ልማድ አዳብረዋል። ነጋሶ አሁን የአንድነት ሊቀመንበር ናቸው። አራተኛ ድርጅታቸው መሆኑ ነው። ከኦነግ ወደ ወያኔ፣ ከወያኔ ወደ አንድነት ሲዘሉ ምንም አልተደናቀፉም። መርህ ያለው ሰው እንዲህ በቀላሉ ከአንድ ጫፍ ወደ ሌላ ጫፍ መዝለል አይቻለውም። ጨለንቆ ላይ ጉድጓድ አስቆፍረው አፅም እየሰበሰቡ “ነፍጠኛውን” ያወግዙ እንዳልነበር፣ አኖሌ ላይ ስለ “ጡት መቆረጥ” ታሪክ ሲያስተምሩ እንዳልነበር አሁን 180 ዲግሪ ተገልብጠው የራስ ጎበና ዳጪ ተከታይ ሆነዋል። እድሜ ከሰጣቸው የነገውን አናውቅም። በተቀረ ለኦሮሞ ህዝብ ጥብቅና መቆም ሃጢአት አይደለም። ሃጢአት ሊሆን የሚችለው ከተገፋና ካመፀ ህዝብ ጎን አለመቆም ነው። ለኦሮሞ ህዝብ መቆም ሲባል ሌላውን ህዝብ ማጥቃት ማለት አይደለም። ጥያቄው የክብርና የእውቅና ማግኘት ጥያቄ ነው። የኦሮሞን የሞጋሳ ባህል የሚያውቅ በነጋሶ አባባል በጣም ይገረማል። ያም ሆኖ እኔ በኦሮሞ ህዝብ መካከል ተወልጄ ያደግሁ፤ ራሴን ኦሮሞ ብዬ ለመጥራት የሞራል ብቃት ያለኝ ሰው ነኝ። ልጅ እያለን የኢብሳ ኦሮሞ የጠበል ጠላ ስንቀምስ፣ Ijollee warra Bishoftu ነበር ፉከራችን! በእነዚያ የልጅነት ዘመናት ጋራቦሩ ላይ እርጎ ጠጥተን ስናበቃ ከአህያ እስከ ፈረስ እየጋለብን ነው ያደግነው። ይህ ፖለቲካ አይደለም። ህይወት ነው። ማንነት የተገነባበት ንጥረነገር ነው።

• በጹህፎቸህ ውስጥ የበቀል ስሜት የለህም ወይ? ጹህፎችህ የኢትዮጵያን ህዝብ አንድ የሚያደርግ ገንቢ ሃሳብ ምንም ቦታ ላይ የለም ትባላለህ። ለምን?

 በግልባጩ የኔ ፅሁፎች ለአንድነት የቆሙ ናቸው። ችግሮችን በግልፅ አውጥቶ መፃፍ ለመፍትሄ ፈላጊዎች ግማሹን ስራ እንደሰራሁላቸው ነው የሚቆጠረው። በቀል የሚለው ቃል እኔን አይገልፀኝም። በግል የበደለኝ ሰው ወይም ህዝብ የለም። ለበቀል የሚያበቃ የማስታውሰው ጉዳት አልደረሰብኝም። በቀል ቀርቶ በጥላቻ የማስታውሰው ሰው እንኳ የለም። በቀል የሚኖረው ቂምና ጥላቻ ሲኖር ነው። በኔ ልብ ውስጥ ለቂምና ለጥላቻ ቦታ የለም…

• ከኢትዮጵያና ኤርትራ ስሜትህ ለየትኛው ቅርብ ነው?

 ኢትዮጵያ የትውልድ አገሬ ናት። በደም ኤርትራዊ ነኝ። ማንነት የብዙ ግብአቶች ውጤት እንደመሆኑ ለሁለቱም አገራት ስሜት አለኝ። ቋንቋ፣ ባህል፣ አስተዳደግ፣ ወላጆች እነዚህ ሁሉ ማንነትን የሚገነቡ ግብአቶች ናቸው። ጥያቄው ስለ ዜግነት ከሆነ ሆላንድ የዜግነት አገሬ ሆናለች። በቀሪው የህይወት ዘመን በዚሁ የዜግነት ሰነድ መንቀሳቀስ እችላለሁ።

• ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደፊት የመዋሃድ ዕድል ይኖራቸው ይሆን?

 ተመልሰው የሚዋሃዱ ቢሆኑ ኖሮ 30 አመት ትግል አይደረግም ነበር። በሰላሳ አመታቱ ጦርነት ከሁለቱም ወገን በአስር ሺዎች ተሰውተዋል። እንደገና በድንበር ጦርነት በተመሳሳይ የብዙ ሺዎች ህይወት ተቀጥፎአል። ከዚህ ሁሉ በሁዋላ ስለ አንድነትና ውህደት መነጋገር የሚቻል አይመስለኝም። ከመነሻውም የኤርትራ ጥያቄ የነፃነት ጥያቄ ነበር። ስለዚህ ሁለቱ አገራት ተከባብረው እንደ ጎረቤት በሰላም መኖር ከቻሉ እንኳ ትልቅ ድል ነው። እንደ አውሮፓውያን ድንበራቸውን አፍርሰው፣ የንግድ ህግ ደንግገው በሰላም መኖር ከቻሉ ትልቅ ስኬት ይሆናል። ሁለቱ አገራት የየራሳቸው ፀጋ አላቸው። ከመዋሃድ ባላነሰ ተግባራዊ ሊሆን በሚችል መልኩ በትብብር መስራት ይችላሉ። ኤርትራና ኢትዮጵያን በተመለከተ የኔ ምኞትና ፍላጎት በአዲሱ መፅሃፌ ላይ በግልፅ ተቀምጦአል። በአፍሪቃ ቀንድ ደረጃ በጋራ ለመስራት ከወዲሁ ጥርጊያ መንገዱን ቢያነጥፉ የአካባቢው 140 ሚሊዮን ህዝብ ተጠቃሚ ይሆናል። የአፍሪቃ ቀንድ ህዝቦች ከጦርነት የሚገኘውን ኪሳራ ከማንም በላይ ይገነዘቡታል። ስለዚህ ሰላማዊ አካባቢ ለመፍጠር በቁርጠኛነት መተባበር ብቻ ነው የሚያዋጣቸው።

• “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” የተባለው መጽሐፍህ ግነት እንደነበረበት ተናግረህ ነበር። በአሁኖቹ መጽሃፍት በሆነ ወቅት ‘ግነት ነበራቸው’ ላለማለትህ ምን ዋስትና አለ? ለሚሉ አስተያቶች ምላሽህ ምንድነው?

 “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” በነፃነት የተሰራ ስራ አልነበረም። መፅሃፉ የኔው ፕሮጀክት ቢሆንም በመካከሉ ድርጅታዊ ጣልቃ ገብነት መጣ። ሁዋላ ከፕሮጀክቱ ራሴን ያገለልኩት በትእዛዝ መፃፍ ስላልፈለግሁ ነው። በግሌ በሰራሁዋቸው ስራዎች ላይ ስለ ግነትም ሆነ ስለ መፀፀት ተናግሬ አላውቅም።

• እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ከመፃፍህ አንጻር ስለ ኤርትራ ምንም አለመጻፍህ ለብዙዎች እንቆቅልሽ ነው። ለምን?

 ገና ፅፌ መቼ አበቃሁ? የመሞቻዬ ጊዜም ገና አልደረሰም። የ45 አመት ሰው ነኝ። የመፃፊያ ጊዜዬ ገና መጀመሩ ነው። እነዚህ ማስታወሻዎች ወደ ስነፅሁፍ ስራ ለመግባት እንደመንደርደሪያ የተጠቀምኩባቸው ብቻ ናቸው። ከእንግዲህ ቢያንስ በየአመቱ አንድ መፅሃፍ ለማሳተም እቅድ አለኝ። በፕሮግራሜ መሰረት መቼ፣ ስለማን፣ ምን መፃፍ እንዳለብኝ መወሰን ያለብኝ እኔ ነኝ። ከዚህ ቀደም፣ “ስለ እዚህ ጉዳይ ለምን አልፃፍክም?” ተብሎ የተጠየቀ ደራሲ ያለ አይመስለኝም። ስለፃፍኩት እንጂ ስላልፃፍኩት ጉዳይ ልንነጋገር አይገባም። የሚገርመው “ለምን አልፃፍክም?” ተብዬ የምወቀሰው ስለማላውቀው ጉዳይ ነው። የምሰራው መፅሃፍ እንጂ ዜና አይደለም። በርግጥ ይህን ክስ የሚያራግቡት ወያኔዎች መሆናቸውን አውቃለሁ። ያቀረብኩትን መረጃ ማስተባበል ስላልቻሉ በዚህ ፕሮፓጋንዳ ከአንባቢ ሊነጥሉኝ ይሞክራሉ። ያም ሆኖ ባለፉት አመታት ወደ ኤርትራ የተጓዝኩ እንደመሆኑ የኤርትራ ጉዞዬን በአዲሱ መፅሃፌ ተርኬዋለሁ። ጀምሬያለሁ። እቀጥላለሁ…

• መለስ ራዕይ ነበራቸው በሚባለው ጉዳይ ብዙዎች ጥርጣሬ አላቸው። አንተስ? በቅርቡ በታተመ መጣጥፍህ፣ “መለስ ተመልሰው ቢመጡ አባይ ፀሐዬን እስር ቤት ያስገባው ነበር” ያልክበት ምክንያት ምንድነው?

 የመለስ ራእይ የሚባለውን የፕሮፓጋንዳ መፈክር መለስ ሲሞት በተደናበረ ሁኔታ የፈጠሩት ነው። መለስ ሲሞት እንደ ኢህአዴግ ማእከል ሆኖ ሊያሰባስባቸው የሚችል አይዲዮሎጂ አልነበራቸውም። አብዮታዊ ዴሞክራሲ ምን እንደሆነ ማንም ሳያውቀው አርጅቶ ሞቶ ነበርና አደጋ ላይ ወደቁ። “ምንድነው የመለስ ራእይ?” ብለህ ብትጠይቅ አንዳንዱ የዋህ ካድሬ፣ “የአባይ ግድብ”፣ “የባቡር ፕሮጀክት” ምናምን ይልሃል። የአባይ ግድብ ጥናት በጃንሆይ ዘመን የተጠና ነው። አቅም እና ምቹ ጊዜ እየተጠበቀ ነበር። ግብፅ ስትዳከም ምቹ ጊዜ ሆኖ ተገኘ። የባቡሩ ፕሮጅክት የሃይሉ ሻውል እቅድ ነው። ቅንጅት በ2005 ምርጫ ስልጣኑን ቢይዝ ሊፈፅመው ያቀደው ነው። ወያኔ ከአፍ እየቀለበ የመንጠቅ ልዩ ችሎታ አለው። “የመለስ ራእይ” የሚባል ነገር የለም። አሁን እንኳ ሽኩቻ ውስጥ ስለገቡ የራእዩ ከበሮ ረገብ ብሎአል። በመለስ ራእይ ስም መለስ የዘረጋውን መዋቅር በመበጣጠስ ላይ የሚገኘው አባይ ፀሃዬ ነው። አንዱ ጠንክሮ እስኪወጣ ድረስ ሽኩቻቸው ይቀጥላል።

• በመለስ ራእይ ስም መለስ የዘረጋውን መዋቅር በመጣጠስ ላይ የሚገኘው ዓባይ ፀሃዬ ነው ያልክበት ምክንያት ምንድነው?

 የሽኩቻው ድራማ ዋና አክተር አባይ ፀሃዬ ነው። በአፋቸው “የመለስ ራእይ” ይላሉ። በተጨባጭ ግን የመለስ ታማኞችን እየመነጠሩ ነው። መለስ ይዞት የነበረውን ብቸኛ አምባገነናዊ ሃይል ለመቆጣጠር እየሰራ ነው። ርግጥ ነው፣ አባይ ፀሃዬ በሚፈፅመው ድርጊት ተቃውሞ የለኝም። ለአገር ደህንነት ሲል አለመሆኑ ግን መታወቅ አለበት። አጤ ምኒልክ ሲሞቱ በደጃዝማች ተፈሪ እና በልጅ ኢያሱ መካከል የተፈጠረውን የስልጣን ሽኩቻ የሚያስታውስ ሁኔታ ላይ ነን። አባይ ወልዱ እንደ ወራሽ ልጅ እያሱ – አባይ ፀሃዬ እንደ ደጃዝማች ተፈሪ! በትክክል ተመሳሳይ የታሪክ ጊዜ ላይ ነን።

• እንደምታውቀው ኢሕአዴጎች “እዚህ ያለነው የመለስን ራዕይ ከግብ ለማድረስ ነው” ብለው ውሳኔ ላይ ደርሰው መንቀሳቀስ ከጀመሩ ዓመት አልፏቸዋል:: አንተ ደግሞ “የመለስ ራእይ” የሚባል ነገር የለም ብለሃልና ብታብራራው?

 መለስ ለመሞት አንድ ሳምንት ሲቀረው ነው ባለራእይ የሆነው? ምንድነው የሚያወሩት እነኚ ሰዎች? 20 አመታት ከመለስ አመራር የተገኘው ምንነበር? በዘር ከፋፍለው ህዝቡ እንዳይተማመን አደረጉት። ያልነበረበትን የሃይማኖት ግጭት ስር እንዲተክል ጥረት አደረጉ። በሰላም አስከባሪ ስም የዜጎችን ህይወት ቸበቸቡ። የምርጫ ኮሮጆ በመገልበጥ ህዝቡ በዴሞክራሲ ላይ ያለውን እምነት አሳጡት። ምንድነው የመለስ ራእይ የሚባለው ቀልድ? ጄኔራሎችን ከህወሃት ብቻ መሾም ራእይ ነው? ቡና ሲወቀጥ ግድግዳቸው የሚሰነጠቅ የኮንደሚንየም ቤቶችን መገንባት ራእይ ነው? ገበሬዎችን አፈናቅለህ ስታበቃ አንድ ሄክታር መሬት በአንድ ፓኮ ስጋራ ዋጋ መቸብቸብ ራእይ ነው? አንድ ፍሬ እህቶቻችንን ለአረብ ግርድና አሳልፎ መስጠት ነው ራእይ? በቀለ ገርባ፣ እስክንድር ነጋ፣ ርእዮት አለሙ፣ ኦልባና ሌሊሳ ለምን ታሰሩ? በመከላከያ ስም ሸቀጥ ያለቀረጥ በማስገባት የአገር ውስጥ ነጋዴዎችን መግደል ራእይ ነው? ምንድነው የመለስ ራእይ? ውሸትን በመደጋገም እውነት የማስመሰልን ጥበብ ተክነውበታል።

• በዚህ ወቅት ሕወኃት ለሁለት ተከፍሏል በሚባለው ትስማማለህ? ከሆነስ እነማን በአሸናፊነት የሚወጡ ይመስልሃል?

 በሁለቱ አባዮች (አባይ ፀሃዬ እና አባይ ወልዱ) መካከል ጦርነት መኖሩን እየሰማን ነው። መረጃው ግን የተረጋገጠ ነው ለማለት አልደፍርም። የምንሰማው እውነት ከሆነ ከመቀሌው አባይ በስተጀርባ ቴዎድሮስ ሃጎስ አለ። ከአዲሳባው አባይ ስር እነ ጌታቸው አሰፋ፣ እነ ደብረፅዮን መሰለፋቸው ይሰማል። ሳሞራ የአዲሳባውን አባይ ተቀላቅሎአል። አዜብ ‘አርፈሽ ቁጭ በይ! የመለስን ፋውንዴሽን ተከታተይ’ ተብላለች። እብድ ስለሆነች ያልተጠበቀ ነገር እንዳትፈፅም በመስጋት ሰንሰለቷን ሁሉ በጣጥሰውባታል። የዘረፋ ቀዳዳዎቿን እየዘጉባት ነው። ያም ሆኖ አዜብ አርፋ ትቀመጣለች ተብሎ አይታመንም። መሞከሯ አይቀርም። የግል አስተያየቴን ለመስጠት ያህል፣ የመቀሌ – አዲሳባ ሽኩቻ ይፋ ሳይወጣ ውስጥ ውስጡን ሊጠናቀቅ ይችላል። ሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች ሽጉጥ ከተኮሱ ቤተመንግስቷን ለዘልአለሙ እንደሚያጧት ያውቃሉና ሽጉጥ ወደ መምዘዝ የሚገቡ አይመስለኝም። ከሁለቱ ቡድኖች አንደኛው እስኪያሸንፍ ሃይለማርያም ወንበሩን በታማኝነት ይጠብቅላቸዋል። ማን በአሸናፊነት ሊወጣ እንደሚችል አብረን እናየዋለን። የአዲሳባው ቡድን የሚበረታ ይመስለኛል። ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከሁለቱም ቡድኖች ገለልተኛ ሆኖ የአስታራቂነት ሚና ለመጫወት እሞከረ ነው። ምናልባት እሱን በማንገስ ልዩነታቸውን ይፈቱ ይሆናል።

• ሕወኃት በምርጫ ስልጣን የሚለቅ ይመስልሃል?

 በግልፅ ተናግረዋል። “ጀርባችንን በእሳት ሰንሰለት እያስገረፍን ያገኘነውን ወንበር በምርጫ ካርድ ስም ሳምሶናይት ይዘው ለመጡ ሰዎች አናስረክብም” ብለዋል። በርግጥ የምኒልክን ወንበር በምርጫ አላገኙትም። ስለዚህ በምርጫ መልቀቅ አይፈልጉም። በምርጫ እንደማይለቁትም በ2005 ምርጫ አስመስክረዋል። በተመሳሳይ በ2010 ማንኛውንም አይነት የማጭበርበር ዘዴ በሙሉ ሃይላቸው ስለተጠቀሙበት 99.6 በመቶ በማሸነፍ ወንበሮቹን ሁሉ ያዙ። በምርጫ በኩል ይገኛል የተባለውን የዴሞክራሲ ጭላንጭልም ደፈኑት። ከዚህ በሁዋላ ምንድነው የሚጠበቀው?

• የሕወኃት በኃይል ስልጣን ላይ የመቆየት አባዜ የሚያዛልቅ ይመስልሃል?

 አዛልቆአቸው 22 አመት ሆኖአቸዋል። ሌላ 22 አመታት እንደማይገዙ ምንም ዋስትና የለም። ወያኔና ሻእቢያ በጠመንጃ ባይመጡበት ደርግ እስከዛሬ ስልጣን ላይ ሊቆይ ይችል ነበር። ሙጋቤ አሁንም አለ። ጋዳፊ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ነበረ። ስዩም መስፍን ቻይና የሚማሩትን የህወሃት የአመራር አባላት ልጆች እያሰለጠነ ነው። በቻይና መንግስት ድጋፍ ተተኪ የአገሪቱ መሪዎች ሊያደርጓቸው ይፈልጋሉ። ይህ ተረት አይደለም። እስከቻሉት ድረስ ይሞክራሉ። ከአንዳንዶቹ ጋር እንዲህ በስልክ ስናወራ “ከዚህ በሁዋላ 40 አመታት መቆየት እንችላለን” ብለው በቀልድ መልክ ጣል ያደርጋሉ። እየቀለዱ ግን አይደለም። “የ65ሺህ ጓዶቻችንን ህይወት የከፈልነው ዋጋው ውድ ነው” ይላሉ። በጨዋታ መሃል ከምኒልክ እስከ ሃይለስላሴ የነበረውን ዘመን ያሰሉታል። የንጉስ ሳህለስላሴ የልጅ ልጆች የቤተሰብ ጥል እየተጣሉም ቢሆን ስልጣን ከቤተሰባቸው ሳይወጣ እየተተካኩ ቆይተዋል። ህወሃት በተመሳሳይ መንገድ ልዩነት የፈጠሩትን እያስወገደ ሁለት ወይም ሶስት ትውልድ ከዚያም በላይ ለመግዛት ይችላል አይነት ወጎች አሏቸው። በአደባባይ ደግሞ፣ “እኛ በስልጣን መቀጠል ካልቻልን ኢትዮጵያ ትበታተናለች” ብለው መዛታቸውን ቀጥለዋል። ኢትዮጵያ እንዳትበታተን በመስጋት ህዝቡ ፀጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛላቸው ይመኛሉ።

• ሕወኃትን ለ22 ዓመታት በስልጣን እንዲቆይ ያስቻለው ምንድነው ትላለህ?

 ምስጢሩ ህዝቡን ከፋፍሎ መግዛት በመቻሉ ነው። የፌደራል አገዛዝ ስርአቱን ለስልጣን ማራዘሚያ ተጠቅሞበታል። ክርስትያኑን በሙስሊሙ ያስፈራራዋል። የአማራው ሃይል ሲበረታ በኦሮሞው እየመታ ዘልቆአል። ሌላ ምስጢር የለውም። ከፋፍሎ በመግዛት፣ የኢትዮጵያዊነት ብሄራዊ ስሜትን በማዳከም፣ ከተቻለ ጨርሶ በማጥፋት ዝንተ አለም መግዛት እንደሚችሉ አስልተው ጨርሰዋል። በርግጥ 95 በመቶ የመከላከያን አመራር ተቆጣጥረውታል። ደህንነቱ ሙሉ በሙሉ በእጃቸው ነው። ህዝቡ በዘር ተከፋፍሎአል። ለሃያላኑ አገራት ራሳቸውን በአገልጋይነት ስላቀረቡ በጫና ፈንታ እርዳታ እያገኙ ነው። የዚህ ሁሉ ድምር በስልጣን እንዲቆዩ አግዞአቸዋል።

• አሁን ያሉት ብዙዎቹ የሕወኃት ባለስልጣናት በአባት ወይም በእናት ኤርትራውያን ናቸው ይባላል:: የተባለው ትክክል ከሆነ ውሳኔዎቻቸው የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዳ ሊሆን አይችልም? ከዚሁ ጋር ተያይዞ የእነኚሁ ባለስልጣናት አያቶች ወይም ቅድመ አያቶች የጣሊያን ባለሟሎች የነበሩ ናቸው ስለሚባለው ምን መረጃ አለህ? የባንዳ ልጆች መሆናቸው የስነ ልቦና ቀውስ ውስጥ አይከታቸውም ?

 በአባት ወይም በእናት ኤርትራዊ መሆን የዘመናችን ዋና አጀንዳ መሆኑ ያሳዝነኛል። በረከት ስምኦን በእናቱም ሆነ በአባቱ ኤርትራዊ ነው። ለኤርትራ የፈፀመላት በጎ ነገር አለመኖሩን ግን አረጋግጥልሃለሁ። በረከት በኤርትራውያን ዘንድ እንደ ፖለቲከኛ እንኳ አይታይም። በኢትዮጵያውያንም አይታመንም። እድለኛ አይደለም። ይህ ሊሆን የቻለው በረከት የሚሰራው ለግሉ፣ ለዝናው፣ ለስልጣን ስለሆነ ነው። ግማሽ የኤርትራ ደም ያላቸው የህወሃት አመራር አባላት ለኤርትራ ያደላሉ ብዬ አስቤ አላውቅም። የተወለዱት እና ያደጉት ትግራይ ነው። ለትግራይ ነው የሚሰሩት። አንድን ሰው “ግማሽ ኤርትራዊ ነው” ብለን ከማሰባችን በፊት “ግማሽ ኢትዮጵያዊ ነው” የሚለውን ማስቀደም ለምን አልተቻለም? በአሉ ግርማ እኮ በአባቱ ህንዳዊ ነው። ገብሩ አስራት ግማሽ ጎጃሜ ነው። ጆሴፍ ስታሊን ሩስያዊ አልነበረም። ኦባማ በአባቱ ኬንያዊ ነው። ጥላሁን ግዛው የፊውዳል ቤተሰብ ነበር።ለኢትዮጵያዊነት ህይወታቸውን የከፈሉ ኤርትራውያንን ስም እንጥራ ብንል ሰአታት አይበቃንም። መለስ በአባቱ ኢትዮጵያዊ ነው። ለምንድነው ወደ እናቱ ጎሳ ያዘነብላል ተብሎ የሚታሰበው? ተወልዶ ያደገው ትግራይ ነው። መለስ ኢትዮጵያን ለመምራት ግማሽ ኢትዮጵያዊነቱ ከበቂ በላይ ነበር። እንደሚመስለኝ ችግሩ ግማሽ ኤርትራውያን መሆናቸው ሳይሆን መርህ አልባ፣ ወይም ስልጣናቸውን ብቻ የሚያስቀድሙ በመሆናቸው ሊሆን ይችላል። መለስ ዜናዊ የባንዳ ልጅ ስለመሆኑ ሲነገር የሰማሁት ከገብረመድህን አርአያ ነው። ገብረመድህን ስለሚያጋንን አይመቸኝም። የሆነው ሆኖ መለስ የባንዳ ልጅ ሊሆን ይችላል። የባንዳ ልጅ መሆኑ ግን እሱንም ባንዳ አያደርገውም። የመለስን ወላጆች እና ልጆች እንተዋቸው። መለስን ለመውቀስ የሚያበቃ በአገር ላይ የፈፀመው በርካታ ወንጀል አለ።

• መለስ ዜናዊ “የኤርትራ ህዝብ ከየት ወዴት“ የሚለውን መጽሐፍ መጻፋቸው፣ ኤርትራ ራስዋን ችላ ነፃ ሐገር ሆና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና እንድታገኝ ለዋና ጸሐፊው ቡትሮስ ጋሊ ደብዳቤ መጻፋቸው፣ ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብ ይገባኛል እንዳትል እንቅፋት መፍጠራቸውና ለኤርትራ ይገባል ማለታቸው ግማሽ ኤርትራዊ ባይሆኑ ኖሮ የሚሞክሩት ተግባር ነበር?

 ኤርትራን በተመለከተ በተወሰኑ ውሳኔዎች የኤርትራ ደም የሌለባቸውም ተሳትፈው አብረው ወስነዋል። የፖለቲካ አቋማቸውን ነው ያስፈፀሙት። ትግራይ ከኢትዮጵያ ጋር ስለመቀጠሏ እንኳ ሁለት ልብ ስለነበሩ የኤርትራን ነፃነት የማይቀበሉበት ሁኔታ ላይ አልነበሩም። ከዚያም ባሻገር አቋማቸውን ለመለወጥ ቢያስቡ ኖሮ እንኳ በወቅቱ ምንም ማድረግ አይችሉም ነበር። ተዋጊ የገበሬ ሰራዊትና ፖለቲካ የሚያንበለብሉ ሸምዳጅ ካድሬዎች እንጂ ሌላ አቅም አልነበራቸውም። አዲሳባን እንዴት እንደሚያስተዳድሩ አሳቡ እንኳ አልነበራቸውም። በርግጥ መለስ ዜናዊ ኤርትራን በተመለከተ ስሜቱ ስስ መሆኑ ብዙ የተባለበት ነው። ስለ መለስ የልብ ሚዛን የሚያውቀው ራሱ መለስ ብቻ ነበር። ሳይፅፈው ተሰናብቶአል።

• መለስና ጓደኞቻቸው ሽንጣቸውን ገትረው ለኤርትራ ነፃነት ሲዋጉ የነበሩት ለምን ይመስልሃል?

 እኔ እስከማውቀው ለኤርትራ ነፃነት የተዋጉት ኤርትራውያን ናቸው። መለስና ጓደኞቹ የራሳቸው አጀንዳና አላማ ነበራቸው። በቀይ ኮከብ ዘመቻ ወቅት ለስልጠና ኤርትራ ሄደው መስዋእትነት እንደገጠማቸው ሰምቻለሁ። የሻእቢያ ተዋጊዎችም በተመሳሳይ ህወሃትን በማገዝ ሂደት ውጊያ ላይ መስዋእትነትን ከፍለዋል። ይህ የጋራ ጠላትን ለመመከት ከተደረገ ታክቲካዊ ትብብር ያለፈ ስም ሊሰጠው አይችልም። የህወሃት እገዛ አንዳንድ ፀሃፊዎች አጋንነው እንደሚያቀርቡት አይመስለኝም።

• በኢትዮጵያ ባለጠመንጃ አስተዳዳሪ መሆኑ የሚቀርበት ጊዜ የሚመጣ ይመስልሃል?

 ተስፋ አደርጋለሁ።

• የሕወኃትን በኃይል ከስልጣኑ እናባርረዋለን የሚሉት ተቃዋሚዎች ሚሳካላቸው ይመስልሃል?

 ህዝቡ የወያኔን ስርአት ተንኮል ጠንቅቆ ተረድቶ አማፅያኑን በሙሉ አይኑ ማየትና ማመን ከጀመረ የሚሳካላቸው ይመስለኛል። በርግጥ እኔ በግሌ ጠመንጃ እንዲተኮስ አልፈልግም። ወጣቶች በጦርነት እንዲሞቱ አልመኝም። እኔ ራሴ የጦርነት ትራፊ በመሆኔ ህመሙ ይሰማኛል። ጠመንጃ ከማንሳት ባሻገር አማራጭ መጥፋቱ ግን ያሳዝነኛል።

ማለዳ ወግ …አምላክ ሆይ ! የአዲሱ አመት ተስፋና ምኞታችን አሳካው! – ነቢዩ ሲራክ መስከረም 1ቀን 2006 ዓ.ም

አንድየ ሆይ! ያላንተ እዚህ መድረስ አይታሰብምና ከሁሉ አስቀድሜ ለከበረው ስምህ ፣ ለማይደፈር ለማይገሰሰው ሰማያዊ ክብርህ ፣ ለቸርነት ፣ ምህረት ይቅርታህ ምስጋና ይድረሰው! አባታችን አዳም ትዕዛዝክህ ተላልፎ ታላቁን ስህተት ፈጸመ ፣ ከገነትም ተባረረ ! አባት ሆይ ! አዳም አጠፋ ብለህ አልተውከንም ! የምህረት አምላክ ነህና መንግስትህን እንወርስ ዘንድ በህግ ትዕዛዛትህ እንድንመራ አዘዝከን! ዳሩ ግን ትዕዛዛት ህግ ቀኖናህን ስንጥስ ኖርን … ይህ ሆነ ብለህም አልተውከንም …

ያለባላ በዘረጋህው ሰማይ ፣ ያለመሰረት ባነጠፍከው ምድር ፣ በእጹብ ስራህ የምድር መቀነት አድርገህ ባንሰራፋህው ውቅያኖስ እና ወንዝ ደምቀን ስታኖረን የምንበላው የምንጠጣውን የምንለብስ የምንጠለልበት በመለኮታዊ ስልጣን ከቸርነት እና ከምህረትህ ጋር ያልተውከን አንተው ብቻ ነህ ! እናም እናመሰግንሃለን ! ዘመን በዘመን ሲተካ ፣ ትውልድ በትውልድ ሲታደስ የዛሬ ባለተሮች ሆነናልና ለቀኖና ህግ የምንገዛ ለሰማያዊ ትዕዛዝህ የምናከብር አድርገን ! በይቅርታ ቸርነትህ ተጠብቀን አዲሱን አመት ስንቀበል የአዲሱ አመት ምኞታችን ብዙ ነው …ከሁሉም በላይ የሰው ልጅን ኢትዮጵያን እና ህዝቧን አንድነታችን ከሚያናጋ ፣ ህብረታችን ከሚንድ እኩይ ስራ ሁሉ ትጠብቃት ዘንድ ምኞቴ ነው ! በአዲሱ አመት መባቻ አሮጌው አመት ለመሸኘት ስንሰናዳ የሃገር የወገናችን ጉዳይ የሚያሳስበን የሚያስጨንቀን ተጠራርተን እንዲህ ብልን የህብረት ምኞት ተመኘን … አዲሱ ዓመት ሲጠባ፣ በአዲስ መንፈስ አዲስ ሕልም ለአገራችን ብሩህ እድገት ለወገኖቸቻችን ሰላም ጤና ህብረት ጥንካሬ የማለሙንቀዳሚ የምኞት ህልም ለማጠናከር ቃል ገባን። ኢትዮጵያ የብሔር፣ የሃይማኖት፣ የሃብት፣ የትምህርት፣ የፖለቲካ አመለካከት እና ሌሎችም ልዩነቶች አብሮነታችንን የማያደናቅፉባት፤ ከነልዩነታችን በጋራ እድገት የምንጠቀምባት፤ ለሁላችንም እኩል ዕድል እና ተጠቃሚነት የሚቀርብባት፤ ሁላችንም እንደ የችሎታችን ለጋራ ነጻነታችን፣ ደኅንነታችን እና ብልፅግናችን የምንሠራባት ሃገር ትሆን ዘንድ ተመኘን . …ለሃገራችን ብሩህ መጻኤ ህይዎት በጋራ ስኬታማ የምንሆንባት፤ እንዲሁም ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያፈቅራት፣ በዜግነቱ የሚደሰትባትና የሚኮራባት ኢትዮጵያ እንድትሆን በጋራ የአዲስ አመቱን አዲስ ምኞት ተመኘን ! አቤቱ የጭንቀት ምልጃ ልመናችን ተቀበለው ! ተስፋ ምኞታችን አሳካው !

ስደት ክፉ ነገር ነው … በስደት ረክሰናል ፣ በስደት ተዋርደናል ፣ በስደት መልካሙ ገጽታችን ከፍቷል ! ለስደቱ የከፋ መከራ አማኝ ለመሆኔ የአረብ አለም የገፋሁት ህይዎት አማኝ ምስክር መሆኔን በፊትህ ስመሰክር አንተ አታውቀውም ብየም አይደለም ! እናም ለቀሩው ትምህርት ቢሆን ደግሜ ደጋግሜ እናገረዋለሁ !

ለአመታት በከተምኩበት የአረቡ አለም የስደተኛ የከፋ መከራ የከፋ ነው ! የተሻለ ኑሮን ለመግፋት ከሚለው የተሻለ ኑሮ ፈላጊ ይልቅ የኑሮ ውድነት እና ድህነቱ አፈናቀሏቸው ወደ አረብ ሃገራት የሚሰደዱት ወገኖች ስቃይ በቃላት ሊገልጹት የሚቻል ያለመሆኑ ምስጥር ስደቱ ከሞት ጋር ተፋጦ የሚከወን ነው! ይህ በመኖርና አለመኖር መካከል በሚደረገው አሰቃቂ ስደት በሶማሌና በጅቡቲ እና በሳውዲ በቀይ ባህር ማዕበል እና ጭልጥ ባሉ በርሃዎች እልፍ አእላፍ ዜጎች ውሃውና በርሃው እየበላቸው በሃዘን ተለይተውናለል ! በራሳችን አዘዋዋሪ ዜጎች በንዋው ፍቅር ተለክፈው ጨክነው ጎድተውናል! ዜጎች በዘላን ሴሰኛ አረቦች እየተደፈሩ ሊናገሩት የሚሰቀጥጥ ግፍ እየተፈጸመባቸው እስከ ወዲያኛው አሸልበዋል ! ነፍሳቸውን ይማረው ! በባህር እና በበርሃዎች የቀሩትን ዜጎችስቃይ ህልፈት እያመመን ሲቀጥል በውል በማይታይ የማይጨበጥ የሃገራት የህግን ማዕቀፍ ወደ አረብ ሃገራት በኮንትራት ስራ ስም የሚሰደዱ ዜጎች ሰቆቃም ከህገወጡ ስደት ባልተለ የከፋ ሆኗል! ያሳለፍነው አሮጌ አመት ዜጎች ያለ ጠባቂ መብት አስከባሪ እንደጨው ሲበተኑ የሚሰደርስባቸው ፈተና ቀላል አልሆነም! ድህነትንና የኑሮ ውድነትን ሸሽተው የመጡ እድሜ ያልጠገቡ እህቶች እና ወንድሞች መሪር የመከራ ጩኸት ከፍ ብሎ ተሰምቷል ! ብዙዎች ድምጻቸው ሳይሰማ በግፍ ጠፍተዋል ፣ ከሞት የተረፉት በአካልና በመንፈስ ሁከት ደዌ ተሸብበው አብደውና ጨርቃቸውን በአደባባይ ጥለው ያየንበት አሰቃቂ ሰቆቃ ተስተናግዷል ! ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም ለመብት ማስጠበቁ የተሰየሙ ምስለኔዎቻችን የፈየዱልንን የመብት ጥበቃ ከማውሳት የበደሉንን በቁጭት ማዘከሩ ይቀላል ! ይህ ሆነ ብለን ግን አንተን ከማመስገን እና በጎ በጎውን ከመመኘት አንቦዝንም !

አቤቱ አምላክ ሆይ ! የምህረት የቸር አምላክ ነህና በአዲሱ አመት በስደት የተሰበረ ልባችን አጽናው ! ለሃገሩ ለወገኑ ቀናኢ መንግስት ስጠን ! ከተሰየሙለትና ከቆሙለት ሃገር ወገናዊ በጎ አላማ ይልቅ በቡድናዊ ስሜት ኑሯችን ያጨለሙትን ልብ አቅናው ! በመዋዕለ ንዋይ ታውረው በወገን ደም የሚበለጽጉትን አዘዋዋሪ ደላሎች በጭካኔ የታበለ ልብ አራራው !

ከህብረት ይልቅ መለያየትን ፣ ከሰላም ይልቅ ብጥብጥን ከመመኘት ሰውረን ! ክፉ ክፉ ከሚያሳስበን እኩይ ሰይጣናዊ ምግባር እቅበን ! ልዩነታችን ከፍቷልና በህብረት አንድነት ትስስር አሽረው ! አንድ አድርገን ! አዲሱን አመት በአዲስ ተስፋ እጀምረው ዘንድ በማወቅና ባለማዎቅ ያስቀየምኩ ፣ ያስከፋኋቸው ይቅርታየን ይቀበሉ ዘንድ ልባቸውን አራራው ! አቤቱ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ! አንተም በይቅርታህ ጎብኘን ! ዘመኑን የምህረትና የይቅርታ ዘመን አድርግልን !
አቤቱ ሁሉንም ማድረግ የማይሳንህ አምላክ ሆይ ! የአዲሱ አመት ተስፋና ምኞታችን አሳካው !

አሜን ! ! !

 posted by Tseday Getachew

የወገን ያለህ! (ከፌስቡክ የተወሰድ)

Girma Ayela

ግርማ አየለ ይባላል፡፡ ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ጉርድ ሾላ አካባቢ ነው፡፡ ከሰላም ቴክኒክና ሙያ ኮልጅ እንዲሁም ከተግባረ ዕድ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በጀነራል ሜካኒክስ በዲፕሎማ ተመርቋል፡፡ ሲንቴክ ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር (SINTEC ETHIOPIA PLC) በተባለው ድርጅት ውስጥ በቋሚ ሰራተኛነት ለአንድ ዓመት ከአስራ አንድ ወር ያህል በቴክኒሻንነት አገልግሏል፡፡

ግርማ ዛሬ ላለበት አሳዛኝ ህይወቱ መነሻ የሆነችውን ቀን ወደ ኋላ በማስታወስ ሲናገር አይኖቹ በእንባ ይሞላሉ፡፡ ጥቅምት 2 ቀን 2003 ዓ.ምን ‘በወጣትነት ጉልበቴ ሰርቼ እራሴንም ቤተሰቦቼንም እለውጣለሁ የሚለው ህልሜ የጨለመበት ቀን ነው’ ብሎ ይገልጸዋል፡፡

በሲንቴክ ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ውስጥ በቴክኒሻንነት ሲያገለግል የቆየው ግርማ አየለ እና ሌሎች ሁለት የስራ ባልደረቦቹ ከሙያቸው ውጪ የሆነ አንድ የስራ ግዴታ ተጣለባቸው፡፡ ‘የማላውቀውንና ልምዱም የሌለኝን ስራ አልሰራም የሚል ምላሽ በወቅቱ ብሰጥም ተቀባይነት አላገኘሁም’ የሚለው ግርማ የእንጀራ ነገር ነውና ስራው ወደሚከናወንበት ቦታ ከባልደረቦቹ ጋር አመራ፡፡ እንዲያከናውኑት የታዘዙት ስራ ደግሞ ድርጅቱ ከሸገር ሬድዮ ጣቢያ ጋር በተዋዋለው መሰረት የጣቢያውን ማሰራጫ ታወር መትከል ነበር፡፡

ግርማና ሁለቱ የስራ ባልደረቦቹ አዲስ አበባ ድልበር ተብሎ በሚጠራውና በጎጃም በር መውጫ በኩል በሚገኘው የመትከያ ቦታ ተገኝተው ስራውን ጀመሩ፡፡ አሁን ግርማና ሁለቱ የስራ ባልደረቦቹ የተከላ ስራው እየተከናወነ ባለው ታወር ከመሬት 65 ሜትር ከፍ ብለው እየሰሩ ነው፡፡ ድንገት የተሸከማቸው ብረት ተሰበረ፡፡ ሶስቱም እየተምዘገዘጉ ወርደው ከመሬት ተላተሙ፡፡ አንደኛው ወዲያውኑ ህይወቱ አለፈች፡፡ ሁለተኛው ሆስፒታል ቢደርስም የደረሰበት ጉዳት ህይወቱን ከአንድ ሳምንት በላይ የሚያስቀጥላት አልነበረምና አለፈ፡፡ በተዓምር የተረፈው ግርማ ብቻ ነበር፡፡

ግርማ ‘ለአደጋው መከሰት የብረቱ የጥራት ችግርና የሽቦ መወጠሪያዎቹ ማጠር ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው’ ይላል፡፡ አያይዞም ‘ለመከራከሪያነት እንዳይሆነን እንኳ እቃውን የት እንዳደረሱት አላውቅም’ ሲል ይገልጻል፡፡
ዛሬ ግርማ በኮሪያን ሆስፒታል ውስጥ ከ2 ዓመት ከ10 ወራት በላይ በተኛበት አልጋ ላይ አሁንም ይገኛል፡፡ የተደረገለት ህክምናም የአካል ጉዳቱን ሊጠግንለት ቀርቶ እስከ ዛሬ ድረስም ቁስሉ አልዳነለትም፡፡ ህግ የሚለውን አላውቅም፡፡

በህጉ በኩልም የሄደባቸውንም ሆነ የተሰጠውን ውሳኔ በዝርዝር አላውቅም፡፡ ይህንንም በዝርዝር የማወቅ ፍላጎቱም የለኝም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የወገን ጉዳት የኔም ጉዳት ነው የሚሉ፤ የሰብዓዊነት ስሜት ያላቸው የህግ ባለሙያዎች ቢያነጋግሩት ደስ ይለኛል፡፡ ደግሞም ነግ በኔ የሚለውን የሀገራችንን ብሂል ማስታወስ የሚገባ ይመስለኛል፡፡ ልጠይቀው በተኛበት ክፍል ውስጥ በተገኘሁበት ወቅት ግን እዚህ ሆስፒታል ከገባ በኋላ የሆነውን ሁሉ እንዲህ አጫውቶኛል፡፡

‘‘አደጋው እንደደረሰ ከጥቁር አንበሳ ሪፈር ተብሎ ቀጥታ ወደ ኮሪያን ሆስፒታል መጣን፡፡ እዚህም ስብራት ብቻ ስለሆነ ችግር የለውምና የነርቭ ችግር ካለ እናያለን ብለው ለአምስት ቀናት ያህል ያለ ምንም እርዳታ ቆየን፡፡ ከአምስት ቀን በኋላ ኤምአርአይ እንድነሳ ተደርጎ የነርቭ ችግር እንዳለ ታወቀ፡፡ ስብራቱን ግን የሰሩልኝ በአስራ ስምንተኛው ቀን ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ አስራ አራት ጊዜ ኦፕሬሽን ተደርጌአለሁ፡፡ ሰውነቴ ክፉኛ ቆሳሰለ፡፡

እስከዚህ ጊዜ ድረስ ማለትም ለአመት ከሰባት ወር ያህል ድርጅቱ የህክምና ወጪውን ይከፍል ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ አቅም የለኝም ብሎ ለሆስፒታሉ ማመልከቻ አስገባ፡፡ ቀጣይ ህክምና እንደሚያስፈልገኝ ለድርጅቱ ቢገለጽለትም እስካሁን በቆየባቸው ጊዜያት ውስጥ ተገቢ የሆነ ህክምና አልተደረገለትም የሚል መከራከሪያ ነጥብ አቀረበ፡፡ እንጊዲያውስ ሆስፒታል ልትቀይሩልኝ ይገባል ብዬ ብጠይቅም ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ህግም አያስገድደንም የሚል ምላሽም ሰጡኝ፡፡ ከዚህ በኋላ ኮሪያን ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት የሰጠሁበት ሂሳብ ይከፈለኝ በማለት ወደ ክስ ሄደ፡፡ እስከ አሁንም ሁለቱ ድርጅቶች በክስ ሂደት ውስጥ ናቸው፡፡

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ነርሶች ቁስሌን ይጠርጉልኛል እንጂ ምንም የህክምና እርዳታ እየተደረገልኝ አይደለም፡፡ ፊዚዮቴራፒ ያስፈልገኛል፣ የዶክተር ክትትልም ያስፈልገኛል፤ ሁለቱንም ከልክለውኛል፡፡ ሆኖም ግን ነርሶቹ በግል ለሚያሳዩኝ ፍቅርና ትህትና ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡ የኢንሹራንስ ካሳዬን ብጠይቅም ሆስፒታሉን ለቀህ ካልወጣህ አንሰጥህም አሉኝ፡፡ እንደ ተሸከርካሪ ወንበርና ሌሎች መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን አሟሉልኝ ብልም ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ አማራጭ ስለሌለኝ እስከ ዛሬ እዚሁ አለሁ፡፡

አሁን ከወገቤ በታች መንቀሳቀስ አልችልም፡፡ ምንም ህክምና ስለማይደረግልኝ ቁስሌ ይሸታል፡፡ ፈሳሹ እየጨመረ ሄዷል፡፡ ህክምና ማግኘት እንዳለብኝ ሆስፒታሉ ያምናል፡፡ ነገር ግን ገንዘብ ካልተከፈለኝ አላክምም ነው ያለው፡፡ ከገንዘብ በፊት ግን ምንጊዜም ቢሆን የሰው ህይወት መቅደም ያለበት ይመስለኛል፡፡

ኮርያን ሆስፒታል ክርስቲያናዊ የህክምና ማዕከል እንደመሆኑ መጠንና ከቆመለት ሰብዓዊና ሞራላዊ የበጎ አድራጎት ስራ አንጻር ተገቢውን ህክምናና ትብብር ሊያደርግልኝ ይገባ ነበር፡፡ ይሁንና ሆስፒታሉ ራሱ ሙያዊ ስህተት ፈጽሞብኛል፡፡ በኦፕሬሽን ወቅት ለፈሳሽ ማውጫ በሚል ምክንያት ውስጥ የቀረው ጓንት ጓንት ለ11 ቀናት ያህል ስለቆየ ስጋዬን አበሰበሰው፡፡ ቁስሌ እስከዛሬ ሊድን ያልቻለበት ምክንያትም ይሄ ነው፡፡

ዛሬ በዚህ እድሜዬ በበላሁበት አልጋ ላይ ስጸዳዳ የወጣትነት ህልሜ እንዲህ መና ሲቀር ሳይ ከባድ የሞራል ድቀት ይሰማኛል፡፡ እንደ ዜጋ የሚረዳኝ ሰው እፈልጋለሁ፡፡ የደረሰብኝን ሁሉ ህዝብ እንዲያውቅልኝ እፈልጋለሁ፡፡ በራሴ ልታከም የምችልበት አቅምም የለኝም፡፡ አባቴ ጡረተኛ ነው፤ እናቴ በህይወት የለችም፡፡ የሚረዳኝ የለም፡፡ ሁለቱ ድርጅቶች ሲካሰሱ እኔ ግን በመሃል ቤት እየማቀቅኩ ነውና የወገን ያለህ እላለሁ፡፡
http://ecadforum.com/

posted by Tseday Getachew

ኑሮ በካንጋሮ ምድር (ክፍል ፫)

እዚያው ፉትስክሬይ ቁጭ ብለን ወግ በመሰለቅ ላይ ነን፡፡ ባለፈው ወዳጄ ስለ ‹‹ኢምፖርት›› አንሥቶ ነበር ያቆመው፡፡ እስኪ ይቀጥል፡፡
‹‹ምንድን ነው ኢምፖርት የሚያደርጉት ኢትዮጵያ ሄደው››
‹‹ሚስት ነዋ››
‹‹እንዴት ነው ደግሞ ሚስት ኢምፖርት ማድረግ ማለት››
‹‹እዚህ ሀገር ያለ ሐበሻ በሦስት መንገድ ነው ሚስት የሚያገኘው››
‹‹በምን በምን››
‹‹በኢምፖርት፣ በኤክስፖርትና በባላንስ››
‹‹ይሄ ትርጓሜ ያስፈልገዋል››
‹‹ኦኬ፤ ኢምፖርት የሚባለው ሀገር ቤት ትሄድና ሚስት ወይም ባል ይዘህ ስትመጣ ነው፡፡ ኤክስፖርት የሚባለው ደግሞ የውጭ ሀገር ሰው በተለይም የዚህን ሀገር ሰዎች ስታገባ ነው፡፤ ባላንስ ሠራህ የሚባለው ደግሞ ሁለት አበሾች እዚሁ ተገናኝተው ሲጋቡ ነው፡፡››
‹‹ታድያ የትኛው ነው የሚሻለው››
‹‹ሁሉም የራሱ ጣጣ አለው፡፡ ኢምፖርት ስታደርግ ከታደልክ ትዳር የጠማትን ወይም የጠማውን ታገኘዋለህ ወይም ታገኛታለህ፡፡ ካልታደልክ ደግሞ እዚህ ከመጣች በኋላ አቢዩዝ አደረገኝ ብላ ልትፈነግልህ ትችላለች፡፡ ወንዱም ትቷት ሊሄድ ይችላል፡፡ ወይም ይፋታሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እዚህ ኢምፖርት ተደርገው ከመጡ በኋላ ስቃያቸውን ያዩም አሉ፡፡ ውጭ እንሄዳለን፣ ባል እናገኛለን፣ አለፈልን ብለው ሳያመዛዝኑ ውጭ ሀገር ስለተባለ ብቻ ይመጡና አበሳቸውን ያያሉ፡፡ በተለይ ስደት ላይ ብዙ ዘመን ኖረው፣ እድሜያቸውን ጨርሰው፣ ራሳቸውን መልጠው፣ ሁለት ጠጉር አውጥተው ከሀገር ቤት ዘልላ ያልጨረሰች ሚስት የሚያመጡ ፌንት ይገጫሉ፡፡››
እንዴት ነው የሚገጩት››
‹‹አየህ አንተ ሃያ ዓመቷን ሱዳንና ኬንያ ከጫርካት በኋላ አባባ የምትልህን ቆንጆ ልጅ ስታመጣ፤ እርሷ እያማረባት ሲሄድ አንተ ግን እድሜ ሲያናጭርብህ ቅናቱን አትችለውም፡፡ የነገር አባቷ እንጂ ባሏ ስለማትመስል ሥጋት እየገባህ ይሄዳል፡፡  ያም ያም አንተን ረስቶ የሚስትህን ቁንጅና ሲያወራ እርሷ ተጨዋች አንተ ተመልካች የሆንክ ይመስልሃል፡፡ ያን ጊዜ አበሻነትህ ይነሣብሃል፡፡ አውስትራልያ መሆንክን ትጠላውና መንዝና ሞላሌ፣ ወልቃይት ጠገዴ፣ ሽሬ እንዳ ሥላሴ መሆን ያምርሃል፡፡ መሳደብ፣ መጨቃጨቅ፣ ሲብስም መማታት፣ ሲያልፍም አካል መጉዳት፣ በመጨረሻም ሕይወት እስከ ማጥፋት ትሄዳለህ፡፡
እዚህ ሜልበርንኮ አንዱ እልኩና ቅናቱ አልወጣለት ሲል ከሕንድ ቤት ቀይ ቃርያ ገዝቶ ሚስቱን በበርበሬ አጥኗታል፡፡ ስንቱ ሚስቱን ገድሏል፤ ስንቶቹስ ተደብድበውና ተፈንክተው በሐኪም ጥረት ከሞት ተርፈዋል፡፡ ኢምፖርት ዕዳው ብዙ ነው፡፡
የዚህን ሀገር ሰዎች አግብተው የሚኖሩ ብዙ አበሾች አሉ፡፡ በተለይ ሴቶቹ በዚህ ጎበዞች ናቸው፡፡ እነርሱ ጋር እስካሁን የሰማሁት የከፋ ችግር የለም፡፡ ባይሆን ወንዶቹ ፈተና ይገጥማቸዋል፡፡ ፈረንጅ ወዳጄ ፍቅራዊ (ሮማንቲክ) ነገር ይወዳል፡፡ እኛ ደግሞ ሃኒ፣ ስዊት፣ ዳርሊንግ የሚል ነገር አልለመድነው፡፡ እኔ ሐኒ የማውቀው ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ ማር በእንግሊዝኛ ሐኒ መሆኑን ነው፡፡ ስዊት – ጣፋጭ ነው፤ በቃ፡፡ ዳርሊንግ እዚህ ነው የሰማሁት፡፡ እኛ ደግሞ ቆፍጠን ያልን ነን፡፡ ‹ሌቱን ለአራዊት ቀኑን ለሠራዊት› ነው ወዳጄ፡፡ የኛ አኗኗር ለእነርሱ መሥሪያ ቤት ይሆንባቸዋል፡፡ እንኳን እነርሱ እዚህ ሀገር ቆየት ያሉት ሴቶች እንኳን ‹‹የኛ ወንዶች አባወራነት እንጂ ፍቅረኛነት አይችሉም›› ይሉናል፡፡
ከቻልክ እዚህ ሀገር ባላንስ መሥራት ነው፡፡ ተዋውቀህ፣ ሀገሩንም ዐውቀህ መጋባት፡፡ ችግሩ እዚህ እንደ አሜሪካ ዲቪ የለ፣ እንደ አውሮፓ በመርከብ የሚገባ የለ፣ ከየት ታመጣለህ፡፡ ወይ እዚያው ስደት ላይ ተጋብተህ ካልመጣህ በቀር፡፡ ››
‹‹ይህን ችግርኮ ተባብራችሁ መፍታት ትችሉ ነበር››
‹‹አንዳንዱን አበሻ ተባበር ከምትለው ተሰባበር ብትለው ይሻለዋል፡፡ ሁሉም በየጎጡና በየሠፈሩ ነው፡፡ አብዛኞቹ ቤተ ክርስቲያኖች እንኳን ዘርን መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡ የአማራውን፣ የትግሬውን፣ የኦሮሞውን ቤተ ክርስቲያን ትለየዋለህ፡፡ ትግሬውም አንድ መሆን እያቃተው አድዋ፣ ሽሬ ሲል ታገኘዋለህ፡፡ አማራውም ወልቃይት፣ ጎንደር እየተባባለ ለብቻው ቸርች ይከፍትልሃል፡፡ ኮሙኒቲውም ለየብቻ ነው፡፡ እዚህ ሀገር የኦሮሞ፣ የሶማሌ፣ የሐረሪ፣ የትግራይ ኮሙኒቲዎች አሉ፡፡ አንደኛው ከአንደኛው ጋር የሚጠራጠሩ፣ የማይተባበሩ፡፡ ከትብብር ርቀው ንጽሕ ጠብቀው የሚኖሩ፡፡ በፍቅር የተጎዱ፣ ከኅብረት የጸዱ፡፡ አንዳንዶቹ ኢትዮጵያውያን ነን ይላሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ‹‹ምሥራቅ አፍሪካ›› የሚባል ሀገር ፈጥረውልሃል፡፡ …››
‹‹ኧረ እንዲያውም አዳሙ ተፈራ በጻፈው ‹‹ገመናችን በሰው ሀገር› የሚለው መጽሐፍ ላይ ሜልበርን የሚገኘው የኦሮሞ ኮሙኒቲ በ2010 እኤአ 25ኛ ዓመቱን ሲያከብር የጻፈውን አይቼ ገርሞኝ ነበር፡፡
‹‹The Oromo are indigenous African people from the north eastern ofAfrica.›› ይላል፡፤ ኢትዮጵያ ላለማለት አዲስ ሀገር ፈጥረዋል፡፡ ››
‹‹እይውልህ እንደዚያ ነው እንግዲህ፡፡ የሚገርምህኮ እዚህ ያለ ሰው መገንጠልን የሚጠላ ተገንጣይ መሆኑ ነው››
‹‹በዚህ ብቻ አይበቃም ትርጓሜ ያሻዋል – ብሏል ኪነ ጥበብ›› አልኩት፡፡
‹‹በውጭ ያለ ዳያስጶራ ስለ ኤርትራ መገንጠል ሁል ጊዜ እየተንገበገበ ያወራል፡፡ እርሱ ግን ራሱ በፈቃዱ ያለ ሪፈረንደም ተገነጣጥሏል፡፡ በምትቃወመው ነገር ውስጥ ራስህን እንደማግኘት ያለ አስነዋሪ አካሄድ የለም፡፡ በየስብሰባው ‹ዐንቀጽ 39› የምትባል ነገር ትነሣለች፡፡ ‹‹የብሔረሰቦች መብት እስከ መገንጠል›› የምትባለው፡፤ ይህች ዐንቀጽ እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ አልተደረገችም፡፡ እዚህ ግን ተግባራዊ ተደርጋለች፡፡ የተገበሯት ደግሞ የሚቃወሟት ሰዎች ናቸው፡፡ ለዚህ ነው ‹‹መገንጠልን የማይደግፍ ተገንጣይ›› ያልኩህ፡፡ አሁን ዘመን መለወጫ እየመጣ አይደለ? ሦስት ቦታ ነው ፕሮግራም የተዘጋጀው፡፡ ከዚያ መርጠህ እንደየብሔረሰብህ መሄድ ነው፡፡ ወዳጄ እዚህ ሀገር ጩኒ ይምጣብኝ››
‹‹ማነው ጩኒ ደግሞ››
‹‹ጩኒ ሰው አይደለም፤ ሕዝብ ነው››
‹‹ጩኒ የሚባል ሕዝብ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ መስማቴ ነው፡፡››
‹‹ጩኒ ማለት ቻይና ነው፡፡ እዚህ ሀገር ጩኒ ነው የምንላቸው፡፡ ጩኒ እርስ በርስ በመደጋገፍ ማንም አይችላቸውም፡፡ ብድር ይሰጡሃል፤ መረጃ ይሰጡሃል፡፡ ያቋቁሙሃል፡፡ ከዚያ ምርጥ ኢንቨስተር ትሆናለህ፡፡ ያለበለዚያ ደግሞ ወጥሬ እሠራለሁ ካልክ በቀላሉ የምትከራየው ቤት ይሰጡሃል፡፡ እንዲት ክፍል ተከራይተህ ኑሮ ሳይከብድህ ወጥረህ ትሠራና በዓመትህ ቀና ትላለህ፡፡ ወዳጄ ጩኒ አንገቱን ደፍቶ እየሠራ ልጁን ምርጥ ትምህርት ቤት ነው የሚልከው፡፡ ኮሙኒቲያቸው ልጆቹን በሚገባ ነው የሚረዳቸው፡፡ ስለዚህ ልጆቹ ውጤታማ ናቸው፡፡ እኛጋኮ ወላጆችና ልጆች አልጣጣም ብለዋል፡፡ ልጆቹን የቤት ሥራ ማን ያሳያቸው፡፡ ማን በትምህርት ያግዛቸው፡፡
አገርሽ ምንኛ መንደርሽ ምንኛ
አላውቅበት አልኩኝ ያንችን አማርኛ
ሲባል አልሰማህም፡፡ በምን ቋንቋ በምን ዕውቀት ከልጆቻችን ጋር እንግባባ፡፡ ልጆቻችን አያውቁም ብለው ንቀውናል፡፡ በዚህ የተነሣ ከትምህርት የሚያቋርጡት ብዙ ናቸው፡፡››
‹‹ቆይ ግን እዚህ መጥተው የተሳካላቸው የሉም››
‹‹ለዓይነት ያህልማ አሉ፡፡ መቼም ለስማችን መጠሪያ ቁና ሰፍተናል፡፡ ለአካባቢ ምርጫ እስከመወዳደር የደረሱ አሉ፡፡ ያው ከሆቴልና እንጀራ ቤት ባናልፍም ቢዝነስ ያላቸውም አሉ፡፡ በተማሩት ሞያ የሚሠሩም በመጠኑ አሉ፡፡ እኔ የሚገርመኝ ግን በኢሕአፓ፣ በኢሕአዴግ፣ በግንቦት ሰባት፣ በኢዲዩ፣ በቅንጅት ውስጥ ለመግባት እንጂ በምንኖርበት ሀገር በሚገኙ ፓርቲዎች ውስጥ ገብቶ፣ አባል ሆኖ፣ ተወዳድሮ ፓርላማ ለመግባት፣ የአካባቢ ተመራጭ ለመሆን የሚተጋ አበሻ ብዙ አናይም፡፡ አሜሪካ እንኳን ሚሊዮን የሚሞላ ኢትዮጵያዊ ተከማችቶ እስካሁን አንድ የአካባቢ ተወካይ እንኳን አለማግኘታቸው ይገርመኛል፡፡ እኛ በሀገራችን አምባሻ ነው የምንራኮተው፡፡ ለምሳሌ እዚህ አውስትራልያዊ ዜግነት ካለህ መምረጥ ግዴታህ ነው፡፡ እንደ አሜሪካ አይደለም፡፡ የመምረጥ ግዴታ አለብህ፡፡ ያለበለዚያ ቅጣት አለው፡፡ የፓርቲዎቹ አባል ስትሆንና ሳትሆን ዕድልህ ይለያያል፡፡ if you are not a member, you are a numberይሉሃል፡፡ ችግሩ ግን እዚህ ሀገር ተመልካች እንጂ ተጨዋች የለም፡››
‹‹ማለት››
‹‹ኳሱ ጉዳያችን ነው፡፡ ሜዳው አውስትራልያ ይባላል፡፡ ሕጉ የሀገሪቱ ሕግ ነው፡፡ ዳኛው ሲስተሙ ነው፡፡ ዋንጫው ውጤትህ ነው፡፡ እዚህ በሚገባ ተጫውተህ የስኬትን ዋንጫ መሳም ትችላለህ፡፡ ምን ያደርጋል ታድያ፡፡ በዙሪያህ ቆሞ ለምን ይህ አይሆንም? ለምን ይሄ አይደረግም? እገሌ ለምን እንዲህ ያደርጋል? እንዲህ በመሆኑ አኩርፌ ቀርቻለሁ፣ የሚል የዳር ተመልካች እንጂ ሜዳው ውስጥ ገብቶ ለመጫወት የሚፈልግ የለም፡፡ እዚህ ያለውን ሰው ‹‹ሰይጣን›› ከምትለው ‹ኮሙኒቲ› ብትለው ደንግጦ ያማትብብሃል፡፡ ተበላ፣ ተጠጣ፣ ተጣሉ፣ ተከፋፈሉ ብቻ ነው የምትሰማው፡፡ አንድ ወዳጄ ምን ይላል መሰለህ
የትልቅ ሰው ልጅ ቀረ በከንቱ
ሀገር ሳይገዛ ሳይባል አንቱ – እንዲህ ነው እንግዲህ፡፡
ካሮላይን ስፕሪንግስ፣ አውስትራልያ
posted by Tseday Getachew

ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ

  የETvው ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ ድብደባ እንደደረሰበት ሰማሁ፤ አዘንኩም። አንድ የዘነጋነው ነገር አለ። እውነት ነው፣ የገዢው ፓርቲ ተግባራት አንደግፍም። ገዢው ፓርቲ ስለማንደግፍ በመ

  ንግስት መስርያቤቶች ተቀጥረን አንሰራም ማለት ግን አይደለም። ልክ ነው፤ ኢቲቪ የመንግስት ሚድያ ሳይሆን የገዢው ፓርቲ የፕሮፓጋንዳ መሳርያ ነው።

  ብዙዎቻችን ድሆች ነን። ስራ እንፈልጋለን። የእንጀራ ጉዳይ ሁኖ በመንግስት ቢሮዎች እንሰራለን። በመንግስት ስንቀጠር መንግስትን ስለምንወድ ወይ ስለማንወድ አይደለም። ምግብ ስለሚያስፈልገን ነው። ምግብ ለማግኘት ሳንቲም ያስፈል…ጋል። ሳንቲም ለማግኘት ስራ ያስፈልጋል። የመንግስት ቢሮዎች ደግሞ ለብዙዎቻችን የስራ ምንጮች ናቸው።

  በመንግስት የተቀጠረ ሁሉ ገዢው ፓርቲ ይደግፋል ማለት አይደለም፤ ይቃወማል ማለትም አይደለም። የሚፈልገውን ገንዘብ ለማግኘት ግን እነሱ (ቀጣሪዎቹ) የፈለጉትን ነገር ወይ ስራ እንዲሰራ ግድ ይላል። የታዘዘውን ካላደረገ የሚፈልገውን አያገኝም። የሚፈልገውን ካላገኘ መኖር አይችልም። ስለዚህ የመንግስት ስራ የህይወት ጉዳይ ነው።

  ጋዜጠኛ ተመስገን የታዘዘውን ስላደረገ (የተፃፈለትን ስላነበበ) የድብደባ ሰለባ መሆን አልነበረበትም። የመንግስት ሰራተኞች ኮ ሓላፊዎች አሏቸው። የስራ ዕድገትና የደመወዝ ጭማሪ ለማግኘት የአለቆቻቸው ትእዛዝ ማክበር አለባቸው። ስለዚህ በመንግስት ሰራተኛ ላይ ጣት መቀሰር የመንግስት ሰራተኞች ሁኔታ ካለመረዳት የሚመነጭ ይመስለኛል።

  ስለዚህ ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች (እንደሚናገሩት ወይ እንደሚሰሩት) የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች አይደሉም። ደሞ … የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ቢሆኑስ? ኢህአዴግን የመደገፍ መብት የላቸውምን? የመንግስት ሰራተኞች እንደማንኛውም ዜጋ የፈለጉትን ድርጅት የመደገፍና የመቃወም መብት አላቸው።

  የምንታገለው ማንም ሰው በየፍላጎቱና በየምርጫው እንዲኖር እንጂ ከኛ ጋር ተመሳሳይ አመለካከት እንዲኖረው ለማስገደድ አይደለም።

  ስለዚህ በጋዜጠኛ ተመስገን በየነ ላይ የደረሰ ጥቃት እቃወማለሁ።

  It is so!!!See more

  posted by Tseday Getachew

Post Navigation

%d bloggers like this: