Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

Archive for the month “October, 2013”

አንድነት ፓርቲ ስለ ብሄርተኝነት ያለውን አቋም ያውቃሉን?

የፓርተው የአምስት አመት ዕቅድና የስትራቴጂ መፅሀፍ የምከተለውን ይላል፡-

በብሄርተኝነት ዙርያ ያለ የተሳሳተ ግንዛቤና እንደምታዎቹ

ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች አገር እንደመሆንዋ የብሔር ብሔረሰቦች መብት መከበር በአገራችን ፖለቲካ ትልቅ ስፍራ እንደያዘ የሚኖር ጉዳይ ነው፡፡ የብሄር ብሄረ ሰብ መብት መከበር በቋንቋ የመናገር መብት ብቻ አይደለም’ በፖለቲካ የመወከልና የመደመጥ፤ በኢኮኖሚና በማሕበራዊ ዘርፍ አድልዎን የማጥፋትና ፍትሕንና እኩልነትን የማንገስ ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ስስ ጉዳይ በሚገባ ሊያዝ ይገባዋል፡፡

የብሄር ጉዳይ አያያዝን በሚመለከት በአገራችን ሁለት ጫፍ የረገጡ አዝማምያዎች ይታያሉ፡፡ አንዱ ጫፍ ለኢትዮጵያ አንድነት እንጨነቃለን ከሚሉ ግን የብሔር መብትን ለመቀበል ከሚቸገሩ ወገኖች የሚመጣ ሆኖ ጉዳዩን የማሳነስና የማጣጣል ብሎም የብሔር መብት ጥያቄ የሕዝብ መብት ጥያቄ መሆኑን የመካድ ዝንባሌን የሚያጠቃልል ነው፡፡ አንዳንድ ወገኖች የሕዝብና የአገራችን አንኳር ጉዳይ መሆኑን በመቀበል ፈንታ የየብሄሩ ልሂቃን የስልጣን ጥማቸውን ለማርካት ብለው የፈጠሩት ችግር አድርገው ያነብቡታል፡፡ ልሂቃኑ አይለጥጡትም ማለት አይቻልም፡፡ ሆኖም ግን የጉዳዩን ክብደትና በአገራችን ፖለቲካ ውስጥ ያለውን ስፍራ ለማሳነስ ምክንያት ሊሆን አይገባም፡፡

ሁለተኛው ጽንፍ የረገጠው አመለካከት የብሔር ብሔረ ሰብ መብትን ለማስጠበቅ እንታገላለን ከሚሉ ወገኖች የሚመጣና የብሄር መብት መከበርን ከአገር አንድነትና አብሮነት ነጥሎ የሚመለከት ዝንባሌ ነው፡፡ ከእነዚህ ወገኖች ውስጥ ጉዳዩን በማክረር ውጤቱ መገንጠል እንዲሆን የሚፈልጉ አሉ፤ በግልጽ መገንጠልን እንደ ዓላማ ያነገቡም አሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች እኛ ያልነው ካልሆነ በማለት አንድነትን በመያዣነት ያግቱታል (ሆስቴጅ ያደርጉታል)፡፡ ሁሉም የየራሱን መብት እያጠበቀና እያከረረ ከሄደ እያንዳንዱ ብሄረሰብ ከአጠገቡ ካለው ሌላ ብሄረሰብ እየተናከሰ እንደሚኖርና ከአንድነቱ መፍረስ ጋራ ሰላምም እንደሚደፈርስ ያለመገንዘብ ችግር አለባቸው፡፡

ሁለቱም አመለካከቶች በሃሳብ ብቻ ሳይሆን ልዩነታቸው በአደረጃጀትም መልክ ይታያል፡፡ የመጀመርያው ሕብረ ብሄራዊ አደረጃጀት የያዘ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ብሄራዊ ወይም ክልላዊ የአደረጃጀት መልክ ያያዘ ሆኖ አንዱ ከሌላው ጋር አብሮ መስራትና መኖርን የማይቀበሉ ናቸው፡፡

በአገራችን ፖለቲካ ውስጥ በብሄር/ብሔረሰብ መብት ማስከበር ዙርያ ያለውን ልዩነት ማጥፋት አይቻል ይሆናል፡፡ ጫፍ ከረገጡት ሁለቱ አመለካከቶች ወጣ ያለና የአገር አንድነትን እና የብሔርብሄረሰቦች እኩልነትን የሚያረጋግጥ አማካይ መስተጋብር መቅረጽና አብዛኛው ሕዝብ ወደዚህ አስተሳሰብ እንዲመጣ መስራት ያስፈልጋል፡፡ በአደረጃጀትም እንደዚሁ ሕብረ ብሄራዊውና ክልላዊ አደረጃጀቶችን (ያቀናጀ) ያስተሳሰረ አንድ አገር አቀፍ መዋቅር ለመፍጠር መስራት ይገባል፡፡ አሁን ያለው ሁኔታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተባብሮ በአንድ ድምጽ የኢህአዴግን አገዛዝ እንዳያስወግድ እንቅፋት እየሆነና ለቀጣይነቱ ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ነው።

ክልላዊና አካባብያዊውን ገጽታ እንዲሁም አገራዊ ገጽታዎችን ያጣመረ አንድ አገራዊ ስብስብ ወይም ፓርቲ እንዴት ይፈጠራል? ይህንን የሚያንጸባርቅ አደረጃጀትስ ምን መልክ ይኖረዋል? የሚሉትን ጥቄዎች መመለስ አንድነት ፓርቲ እንደ አንድ ትልቅ ፖለቲካዊ ተግዳሮት ይመለከተዋል፡፡

ከላይ የተዳሰሱት ሃሳቦች የያንዳንዱን የማህበረሰብ ክፍል የልብ ትርታ የማዳመጥን አስፈላጊነት አጉልተው ያሳያሉ፡፡ እንደዚሁም በተለያዩ የኢትዮጵያ ብሄርብሄርሰቦች የአስተሳሰብ አስኳል ጋር ተቀናጅቶ እንዲሄድ የሚያደርግ ስትራቴጂ የመቀየስ አስፈላጊነትን ያሳያሉ፡፡ ስትራቴጂው የእያንዳንዱን ብሄረሰብ ልዩ ሁኔታ/ስፍራ/ችግር መሰረት ያደረገ ይዘት እንዲኖረው የተቻለውን ሁሉ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

http://www.zehabesha.com/

posted by Tseday Getachew

 

 

Advertisements

ሰበር ሰሚ ችሎት የነ አቶ በቀለ ገርባን ይግባኝን እንደማያይ አስታወቀ

-እነ አንዱዓለም አራጌም የፊታችን ሰኞ ሰበር ሰሚ ችሎት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል

(ዘ-ሐበሻ)  የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የኦፌኮ-መድረክ ምክትል ሊቀመንበር እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ላይ እና የኦፌኮ ሌላው አመመራር ወጣት ኦልባና ሌሊሳ የጠየቁትን ይግባኝ ዛሬ ጥቅምት 21 ቀን 2006 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የህግ ስህተት የለውም በሚል ሰበር ሰሚ ችሎቱ ይግባኙን ውድቅ አድርጎታል፡፡ አቶ በቀለ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት በፌደራሉ አቃቤ ህግ በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል 8 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደባቸው ሲሆን ፤ ይህን በመቃወም ፈደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቀው ነበር፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተወሰነውን የ8 ዓመት እስራት ወደ 3 ዓመት ዝቅ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ አቶ ኦልባና ሌሊሳም በከፍተኛው ፍርድ ቤት 13 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደባቸውን በይግባኝ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ወደ 11 ዝቅ እንዲል አድርጓል፡፡ ይሁን እንጂ እነ አቶ በቀለ ገርባ የተከሰስነው በሐሰት የፈጠራ ወንጀል እንጂ ምንም የፈፀምነው ወንጀል ስለሌለ፤ አቃቤ ህግም በከሰሰን ወንጀል ያቀረበው ማስረጃ እርስ በርሱ የሚጣረስ በመሆኑ ሰበር ሰሚ ችሎቱ በነፃ ሊያሰናብተን ይገባል ሲሉ ይግባኝ ቢሉም ፤ሰበር ሰሚ ችሎቱ በዛሬው ጥቅምት 21 ቀን 2006 ዓ.ም. ውሎው የይግባኝ ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎታል፡፡

በተያያዘ ዜና የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር እና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አንዱዓለም አራጌ ፣ ሌላው የፓርቲው ምክር ቤት አባል አቶ ናትናኤል መኮንን፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፣ አቶ ክንፈሚካኤል ደበበ እና ሌሎች የአንድነት ፓርቲ አመራርና አባላት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተወሰነባቸውን የጥፋተኝነት ውሳኔ በመቃወም ለሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ ብለዋል፡፡ በዚሁ መሰረት የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2006 ዓ.ም. ከቀኑ 8 ሰዓት 6 ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀነ ቀጠሮ መሰጠቱን ጠበቃው አቶ አበበ ጉታ አስታውቀዋል፡፡

ይህም ለነ አቶ አንዱዓለም ቀጠሮ የመጀመሪያው የሰበር ሰሚ ችሎት ቀነ ቀጠሮ መሆኑ ታውቋል፡፡ አቶ አንዱዓለም አራጌ በከፍተኛው እና በጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕድሜ ልከል ፅኑ እስራት ሲፈረድበት ጋዜጠና እስክንድ ነጋ ደግሞ 18 ፅኑ እስራት ፍርድ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መፅናቱ ሲታወቅ የሌሎችም እንዲሁ መሆኑም አይዘነጋም፡፡

 

posted by Tseday Getachew

ኢትዮጵያዊቷን የማደጎ ልጅ በርሀብ የገደለችው አሜሪካዊት በ37 አመታት እስራት ተቀጣች

Hana’s parents broke down in tears as they get maximum sentences (+video)

 የ42 አመቷ ካሪ ዊሊያምስ የ13 አመቷን ታዳጊ ሐና ዊሊያምስን በረሀብና በብርድ በመቅጣት ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል።

የገዳዩዋ ባለቤት በ28 አመታት እንዲታሰር ተፈርዶበታል። ሌላው የ10 አመቱ የማደጎ ታዳጊ ኢትዮጵያዊም ለሌሎች አሳዳጊዎች እንዲሰጥ ተደርጓል። ፍርዱን የሰጡት ዳኛ ከፍተኛ የሚባለው ቅጣት ማስተላላፋቸውን ተናግረዋል። ሁለቱም ሰዎች ከሁለት አመታት በፊት መታሰራቸው ይታወሳል።

የስሚንቶ ፋብሪካዎች የገበያ ችግር እንዳጋጠማቸው ተዘገበ

ጥቅምት (ሃያ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :- ሪፖርተር ዛሬ ባወጣው ዘገባ በአገሪቱ የሚገኙ ሶስቱ ታላላቅ ስሚንቶ ፋብሪካዎች በአመት 12 ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ የማምረት አቅም ቢኖራቸውም በገበያ ውስጥ የሚገኘው ስሚንቶ ድምር ከ5 ሚሊዮን አይበልጥም።

አብዛኛውን ስሚንቶ የሚገዛው መንግስት ሲሆን፣ የግሉ ዘርፍ ድርሻ ቀዝቃዛ መሆኑ ተዘግቧል።

የሼክ ሙሀመድ አላሙዲን ንብረት የሆነው ደርባን ኩባንያ የዋጋ ቅናሽ በማድረግ በኩንታል 209 ብር እየሸጠ፣ ለደንበኞቹ ቤታቸው ድረስ እያደረሰ ነው። ሙገር ስሚንቶም በተመሳሳይ ለልዩ ደንበኞቹ ምርቶቹን ቤታቸው ድረስ እያደረሰ ነው።

ለሪፖርተር አስተያየታቸውን የገለጹ ባለሙያዎች ” ብዙም ግልጽ ባልሆነ ምክንያት የሲሚንቶ ገበያ እየተቀዛቀዘ መጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት በ2006 ዓ.ም 21 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን፣ በ2007 ዓ.ም. 27 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ አገሪቱ እንደምትፈልግ ከአራት ዓመት በፊት የወጣው ጥናት ጥያቄ ተነስቶበታል፡፡

‹‹ለሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ከፍተኛ የካፒታል ኢንቨስትመንት ፈሷል፤›› ሲሉ አስተያየታቸውን የሚሰጡት ባለሙያዎች፣ ጉዳዩን መንግሥት ከሥሩ ሊያጤነው እንደሚገባ አሳስበዋል።

በዚህ ሁሉ መሀል መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ 70 በመቶ የሚሆነውን ምርቱን ለአባይ ግድብ እና ለግልገል ጊቤ 3 የሀይል ማመንጫ ግድቦች በማቅረብ ላይ ነው። መሰቦ ሲሚንቶ በምን መስፈረት ለአባይ ግድብ ግንባታ አቅራቢ ሆኖ እንደተመረጠ አልታወቀም። ሙገር ስሚንቶ የመንግስት  ወይም የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት ሆኖ ሳለ፣ እንዲሁም ለአባይ ግድብ ማሰሪያ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ  በውድም በግድም ገንዘብ እንዲያዋጣ እየተደረገ ፣ ለድርጅቱ ስሚንቶ የሚያቀርበው ሙገር መሆን ሲገባው የህዝባዊ ወያን ሀርነት ትግራይ ኩባንያ የሆነው መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ እንዲሆን መደረጉ ” የኢትዮጵያ ህዝብ ያዋጣል፣ ገቢው ወደ ህወሀት ኪስ ይገባል” ሲል አስተያየቱን የተጠየቀው የኢሳት የአዲስ አበባ ዘጋቢ ገልጿል።

ህዝቡ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ገንዘብ እንዲያዋጣ ቢገደድም፣ ገንዘቡ በተዘዋዋሪ መንገድ ወደ ህወሀት ካዝና ነው የሚገባው የሚለው ዘጋቢያችን፣ መስፍን ኢንጂነሪንግና የወ/ሮ አዜብ መስፍን የእህት ልጅ ንብረት የሆነው ወርኪድ የተለያዩ የግንባታ እቃዎችንና የብረታ ብረት ውጤቶችን በማቅረብ ከግድቡ ከፍተኛ ገቢ እያገኙ ነው ብሎአል።

ሼክ ሙሀመድ አላሙዲን ለአባይ ግድብ ለማዋጣት 500 ሚሊዮን ብር  ቃል ቢገቡም በተለያዩ ሰበቦች እስካሁን አጠናቀው አልከፈሉም።  ዘጋቢያችን  ምናልባትም ኩባንያቸው ደርባን ለግድቡ ስሚንቶ እንዳያቀርብ በመከልከሉ ተበሳጭተው ሊሆን ይችላል ብሎአል።

የቆዳና ሌጦ አክስፖርት በችግር ላይ ነው

ጥቅምት (ሃያ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :- የጥሬ ቆዳና ሌጦ ኤክስፖርት ባለፉት አምስት ዓመታት የተሻለ ገቢ ያስገኘ ቢሆንም ግብይቱ ኃላቀር፣ሰንሰለቱ የተንዛዛና ከፍተኛ የግብይት ወጪዎች የሚታዩበት እንዲሁም በምርት ጥራት በኣለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱ እጅግ አነስተኛ መሆኑን ከንግድ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ አመለከተ፡፡

የጥሬ ቆዳና ሌጦ ኤክስፖርትን በማቆም እሴት የተጨመረባቸውን የተለያዩ የቆዳ ውጤቶች ለውጪ ገበያ በመላክ የተሻለ የውጪ ምንዛሪ ለማስገኘት ጥረት እየተደረገ መሆኑን መረጃው ጠቁሞ ዘርፉን ከብክነትና ከጥራት ጉድለት ግን መታደግ ባለመቻሉ አሁንም በብዙ ችግሮች ውስጥ የሚውተረተር ሆናል ይላል፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት ከዘርፉ 430 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን ጠቁሞ ይህ ግን ዘርፉ ማመንጨት ካለበት ገቢ ጋር ሲነጻጸር እጅግ አነስተኛ ገቢ ነው፡፡

የእንስሳት እርባታው ከውልደት ጀምሮ ኃላቀርና በባህላዊ ዘዴ በመከተል የሚከናወን በመሆኑ የቆዳና ሌጦ ጥራቱ ላይ ከፍተኛ ችግር መፍጠሩን፣በእርድ ወቅትና ከእርድ በኃላ የሚከሰቱ የተለያዩ የጥራት ጉድለቶች መኖራቸው ፣የግብይት
ሒደቱ ኃላቀር ፣የተንዛዛ፣ ቅብብሎሽ የበዛበትና እሴት የማይጨምሩ ግን ዋጋ የሚያንሩ ተዋንያን የበዙበት መሆኑ እንዲሁም ለንዑስ ዘርፉ ልማት እና ግብይት ጠንካራ አደረጃጀት አለመፈጠሩ እንደችግር ተጠቅሰዋል፡፡

በሌላ በኩል የጥራት ችግር እያመጣ ባለው የውጪ ጥገኛ በሽታ አምጪ ህዋሳት ላይ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በሽታዎቹ በሚያይሉባቸው በሰሜኑ የኢትዮጽያ ክፍል ማለትም በአማራ፣በትግራይና በአፋር ክልሎች የኬሚካል ርጭት ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በመካሄድ ላይ መሆኑን መረጃው ይጠቁማል፡፡ ይህም ሆኖ የኬሚካል ርጭቱ በአማራ ክልል መጠነኛ ለውጥ ያሳየ ቢሆንም በሌሎቹ ክልሎች ውጤቱ እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ያስረዳል፡፡ በዚህ ምክንያት በአሁኑ ጊዜ ተጨማሪ 25 ሚሊየን ብር በጀት ተይዞ በመላ አገሪቱ የኬሚካል ርጭቱ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

ወደ አዲስ አበባ የሚጎርፉ አረጋውያን ለማኞች ቁጥር ጨምሯል

ጥቅምት (ሃያ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :- የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት በልመና የሚተዳደሩ አረጋውያን ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል። አረጋውያኑም ከክልል ከተሞች ወደ አዲስ አበባ እንደሚጎርፉ ነዋሪዎች ይናገራሉ። መንግስት የገጽታ ግንባታ በሚል አረጋውያንን ሰብስቦ ወደ ክልል ቢበትናቸውም፣ አረጋውያኑ ተመልሰው በምጣት በልመናው ቀጥለዋል።

አንድ ነዋሪ እንዳሉት ቀድሞ ” አብያተ ክርስቲያናት ቅጥር ግቢ ውስጥ አይለመንም ነበር፣ አሁን ግን ልመናው ቤተክርስቲያን ውስጥ ሁሉ ሆኗል፣ ህዝቡ ጸሎት ማድረስ በማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ” ብለዋል፡፡ በአገሪቱ የሚታየው የኑሮ ውድነት መባባስ እንዲሁም አረጋውያኑን የሚንከባከብ ድርጅት መጥፋት ለአረጋውያኑ ስደት በምክንያትነት ይጠቀሳሉ።

በችግሩ ዙሪያ የአዲስ አበባን መስተዳድር ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

የስኳር ህመምተኞች መድሀኒት የለም ተባሉ

ጥቅምት (ሃያ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :- በዘውዲቱ ሆስቲታል መድሀኒቱን ለመቀበል ከሳምንታት በላይ ሲጠባበቁ የነበሩ የስኳር ህመምተኞች በመጨረሻ መድሀኒት የለም መባላቸውን ለኢሳት ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚሰጠው እርዳታ መቋረጥ ለችግሩ መፈጠር ምክንያት ነው ቢባልም፣ አንዳንድ ወገኖች ደግሞ የችግሩ ምንጭ መድሀኒቱ አየር ባየር ስለሚሸጥ ነው ብለዋል።

ህመምተኞች እንደሚሉት መድሀኒቱን በግላቸው ገዝተው ለመጠቀም ዋጋው የሚቀመስ አይደለም። ብዙዎቹ መድሀኒቱን ለማግኘት ባለመቻላቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን ገልጸዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

የቦሌ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን የድረሱልኝ ጥሪ አሰማች

 

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :- የቦሌ ለሚ ቅ/ሩፋኤል የጻዲቁ አቡነ ኤዎስጣቲዎስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት መልአከ ብርሀን ተከስተ ካሳሁን “የድረሱልን ጥሪን ይመለከታል” በሚል ርእስ ለለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ረዳትና የጅማ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ለሆኑት ለ ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ በጻፉት ደብዳቤ ላይ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ቤተክርስቲያኑዋን በ7 ቀናት እንዲያፈርሱ እንዳዘዙዋቸው ተናግረዋል።

ደብዳቤው ” ቤተከርስቲያኑ ከተመሰረተ 4 አመታትን አስቆጠረ ቢሆንም በ2001 ዓም እንደማንኛውም አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተነስቶ ካርታውን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን። በተለይም የመንግስት አካላት በተለያየ ወቅት  ቦታው ድረስ እየመጡ፣ ቦታው የኢንዱስትሪ ቦታ ስለሆነ አፍርሱ የሚል ትእዛዝ በተደጋጋሚ ደርሶናል። አሁንም በቀን 12/02/2006 ኣም በመ/ቁጥር ቦ/ክ/ከ/መዝ/9539/06 በተጻፈልን ደብዳቤ ቦታው ለልማት ስለሚፈለግ ቤተ ክርስቲያኑን በ7 ቀን እንድታፈርሱ ሲል በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳዳር የደምብ ማስከበር አገልግሎት ጽ/ቤት አሳውቆናል።” ይላል።

ደብዳቤው በማያያዝም “  የአካባቢው ህብረተሰብ አሁን በተረጋጋ መንፈስ የጸሎት ስነስርአትና አምልኮ ስነስርአት በሚፈጽምበት ወቅት በድጋሜ መጥተው በአስቸኳይ ቤተከርስቲያኑን እንድታነሱ የሚል ትእዛዝ ማስተላለፋቸው ምእመኑን እጅግ አሳዝናል ( አስቆጥቷል)። ስለሆነም ጉዳዩ ጊዜ የማይሰጥ ስለሆነ ለብጹእ ወቅዱስነታቸው ደብደቤ እንዲጻፍልንና ቅዱስነታቸውም ለክቡር አቶ ድሪባ ኩማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳደር ከንቲባ አስቸኳይ ደብዳቤ እንዲጽፉልን ስንል በቅድስት ቤተክርስያን  ስም እንጠይቃለን ብሎአል። ከደብዳቤው ጋርም የህዝቡን አቤቱታ የያዘ 10 ገጽ ወረቀት ተያይዞ ቀርቧል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ደንብ ማስከበር አገልግሎት ጽ/ቤት በ12/02/06 ለሩፋኤል ቤተከርስቲያን በጻፈው ደብዳቤ ፣ ትእዛዙን የሰጠው የቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት መሆኑን ጠቅሷል። በአቶ ጌታቸው አዲስ ፈለቀ የተጻፈው ደብዳቤ ቤተክርስቲያኑ በ7 ቀናት ውስጥ ካልተነሳ አስተዳደሩ ለሚወስደው እርምጃ ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን ይወስዷል ብሎአል።

የአዲስ አበባ ሀገረስብከትም ሆነ የፓትሪያርኩ ጽህፈት ቤት በጉዳዩ ላይ የሰጡት ምላሽ አልታወቀም።

የኦርቶዶክስ ሀይማኖት አንዳንድ አባቶች በቅርቡ መንግስት በቤተከርስቲያኑዋ ላይ እያደረሰ ያለውን ተጽእኖ መንቀፋቸው ይታወሳል።

 

በሁለት አመታት ብቻ ከ400 ሺ በላይ ዜጎች በህገ ወጥ መንገድ ተሰደዋል

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :- ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፉት 2 ዓመታት ብቻ ከ400 ሺ በላይ ዜጎች   ሲሆን፣ በህጋዊ መንገድ የተጓዙትን ሲጨምር አሀዙ በእጥፍ ሊጨምር ይችላል።

መንግስት በቅርቡ ለስራ በሚል ወደ ውጪ በሚጓዙት ላይ እገዳ መጣሉ ይታወቃል።  የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ስምሪት ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ አበበ ሀይሌ እንዳሉት ፥ እገዳው ከተጣለባቸው ሀገራት መካከል ሊባኖስ ፣ ኳታር ፣ ሳውዲ አረብያ ፣ ኩየት ፣ የመን ፣ ሱዳንና ደቡብ አፍሪካ ይገኙበታል።

በእገዳው መሰረት ካሁን ቀደም ቪዛ ያገኙትን ጨምሮ ቪዛ ለማግኘት እየተጣጣሩ ያሉትም ቢሆን ወደ ሀገራቱ መጓዝ አይችሉም።፤ እገዳው በቤት ሰራተኝነት ተቀጥሮ ለመስራት ከሚደረጉት ጉዞዎች ባሻገር አለም አቀፋዊ ተቀባይነት ባላቸው ሙያዎች ላይ የሚደረጉ ጉዞዎችን እንደማይመለክትም  ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በመንገድ የቀረው ቀርቶ ወደ መጨረሻ መዳረሻ ሀገር የገቡት ዜጎች እጣ ፈንታ አብዛኛውን ጊዜ ስቃይና እንግልት ቢሆንም ፥ ዛሬም በዚያ የሞት ጎዳና ላይ የሚተሙ ዜጎች ቁጥር ሊቀንስ አልቻለም።

ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር  በሰጠው መግለጫ  እገዳው ከስድስት እስከ ሰባት ወራት ይቆያል።

በአገሪቱ ውስጥ እየተስፋፋ የመጣው ድህነትና ስራ አጥነት ለስደቱ ዋና ምክንያቶች ናቸው። ከፖለቲካ ጋር በተያያዘም የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር በእየጊዜው እየጨመረ መሄዱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃዎች ያመለክታሉ።

 

መምህራንን ለመቆጣጠር መንግስት አዲስ አደረጃጀት ተግባራዊ አደረገ

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :- መምህራን ለኢሳት እንደገለጹት አደረጃጀቱ ተግባራዊ በሆነባቸው በጎንደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የኢህአዴግ አባላት ከሆኑ ከመምህራን አንድ፣ ከተማሪዎች አንድ ከፖሊስ አንድ እንዲሁም ከወላጆች አንድ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ መምህራንን የቀን ተቀን እንቅስቃሴ፣ ፖለቲካ አመለካከት እና ሌሎችንም ተያያዥ ጉዳዮች ይከታተላሉ።

መመሪያው በሁሉም ትምህርት ቤቶች የወረደ ሲሆን፣ በአብዛኛው ትምህርት ቤቶች የአንድ ለአምስት አደረጃጀቱ ተግባራዊ ሆኗል።

በዚህ ድርጅት ውስጥ የሚመደቡት የኢህአዴግ አባላት ከተራው መምህር በላይ ስልጣን ያላቸው ሲሆን፣ መምህራንም እነሱን በመፍራት ሀሳባቸውን በግልጽ ለመናገር እየተቸገሩ ነው።

ኢህአዴግ በመላው አገሪቱ እየገነባ ባለው የአንድ ለአምስት  አደረጃጀት ህዝቡን ለመቆጣጠር ሙከራ ቢያደርግም እስካሁን ውጤታማ አለመሆኑን ገንባሩ ከወራት በፊት ባደረገው ጉባኤ መግለጹ ይታወቃል።

 

በታች አርማጭ በደዊ ቀበሌ አንድ የጸጥታ ባለሙያ አንዱን ግለሰብ ከእስር ቤት በማውጣት መግደሉ ተሰማ

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :- ለኢሳት ከስፍራው የደረሰው ዘገባ እንዳመለከተው ጋሻው የቆየ የተባለው የጸጥታ አስከባሪ የ28 አመቱን  ጎሹ እያዩ የተባለውን አርሶ አደር  ከመጠጥ ቤት ውስጥ እንዲወጣ ካደረገ በሁዋላ፣ ወደ እስር ቤት ወስዶታል።

በመንግስት የተሾመው ታጣቂ ወጣት የጸጥታ ማስጠበቅ ስራ ለመስራት በሚል ለመስክ ስራ ተልኮ በነበረበት ወቅት ነው ወጣቱን ያለምክንያት ወደ እስር ቤት ካስገባው በሁዋላ፣ ከእስር ቤት አስወጥቶ የገደለው።

ገዳዩ በቁጥጥር ስር ውሎ እንደተመሰከረበት የአካባቢው ሰዎች ገለጸዋል።

 

 

የቀድሞው የፌዴራል ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በሙስና ተጠርጥረው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ጥቅምት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :- አቶ ተፈሪ ፍቅሬ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የፌዴራል ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ከ2002 እስከ 2005 ዓመተ ምህረት ያገለገሉት አቶ ተፈሪ ፍቅሬ የፌደራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና አቃቢ ህግ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ክስ እንደመሰረተባቸው የዘገበው ፋና ነው።

የስነ ምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ በክሱ ፣ ተከሳሹ ህግ እና አሰራርን በመጣስና በዜጎች መካከል ልዩነት በመፍጠርና የመንግስትን መብትና ጥቅም በሚጎዳ መንገድ በመስራት፤ በጥቅሉ ከ33 ቤቶች መንግስት ማግኘት የነበረበትን 370 ሺህ 446 ብር ተቀንሶ እንዲከራይ የማድረግ ስልጣን ሳይኖራቸው ከአሰራር ውጪ እየወሰኑ በመንግስት ላይ ጉዳይ ያደረሱና ግለሰቦችን ያለአግባብ ተጠቃሚ አድርገዋል ብሎአል።

ፍርድ ቤት የግለሰቡን የዋስትና መብት ማንሳቱም ተዘግባል።

ESAT

posted by Tseday Getachew

 

 

 

 

 

“ትግራይ ከአንድ ፋብሪካ እንደወጣ ሳሙና” አብርሃ ከመቀሌ

79232-images1

ዛሬ አንዴ ታሪክ ያስታወሰኝ አስተያየት አነበብኩ። በ97 ምርጫ ቅስቀሳ ወቅት በአዱስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩ። በኢህአዳጎችና ቅንጅቶች መካከል የነበረ ክርክር እከታተል ነበር።  የማናቸው ደጋፊ ወይ ተቃዋሚ አልነበርኩም። አንድ ሲኔራችን ነበር። ወደ ዶርማችን እየመጣ ስለነዚህ የቅንጅት መሪዎች መጥፎ ታሪክ ይነግረናል፤ የትግራይ ህዝብ መጥፎ አመለካከት እንዲላቸው ፣ …. ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ…

EMF

posted by Tseday Getachew

ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ፣ (ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት)

moresh

 

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት፣ ሕዝብ ያልተቀበላቸው አንቀጾች እንዳሉት ብንገነዘብም፣ዓለም የተቀበላቸውን የሰብአዊና የዲሞክራሲያዊ መብቶች ያካተተ ሙሆኑን እንረዳለን። በሕገ-መንግሥቱ ከተካተቱት አንቀጾች፣አንቀጽ 74 ከንዑስ አንቀጽ(1) እስከ (13) የተዘረዘሩት የእርሰዎ የጠቅላይ ሚነስትሩ ሥልጣንና ተግባሮች እንደሆኑ ያረጋግጣል ። ከሁሉም በላይ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 13 የተገለጸው ሕገ-መንግሥቱን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጠው ሥልጣን መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ተገልጿል። ይህም ማለት በአገሪቱ ውስጥ ለሚታይ የሕግ መከበርም ሆነ መጣስ ፣ሕግ ያከበሩትን የመሾምና የመሸለም፤ሕግ የጣሱትን ደግሞ ለፍርድ የማቅረብ ከፍተኛ ኃላፊነትና ተጠያቂነት ያለበዎ መሆኑን ሕገ-መንግሥቱ ያረጋግጣል። በአጠቃላይ፣በሕገ-መንግሥቱ የተጓደሉትንና የተዛቡትን ጉዳዮች በማጥናትና በማስጠናት እንዲሟሉና እንዲቃኑ የማድረግ፣በአግባቡ ያሉትን በሥራ እንዲውሉ የማድረግ ብቸኛው ኃላፊ እርሰዎ እንደሆኑ ሕገ-መንግሥቱ ያዛል። ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

posted by Tseday Getachew

ተስፍየገብረኣብየኢትዮጵያተስፋ! በገሪ ወዲ ሃገር

Tesfaye Gebreab

ገሪ ወዲ ሃገር
11/30/2013

በነጻ የመጻፍ መብት ላይ ሁላችን እንስማማለን። ችግሩ የሚመጣው እናንተ ኣትጻፉ እኛ የጻፍንላቹሁ ብቻ ተቀብላቹሁ ንሩ ነው ወይም በኛ ሳጥን ግቡና እኛን መስላቹሁ ኑሩ ኣለበላዝያ ኢትዮጵያውያን ኣይደላችሁም እንድያውም የኢትዮጵያ ጠላቶች፣ ኣፍራሶች፣ በታኞች፣ ጠባቦች፣ ተገንጣዮች፣ ወዘተ ናቹሁ ነው። ኣድበስብሰው ያለፉት በኣረም ይመለሱት!

በተስፋየ ኣጠቃላይ ድብደባው ከኣንድ ኣካባቢ ብቻ ነው፣ ከተወሰኑ የኣማራ ተወላጆች። ተስፋየ በጻፈው ድርጊት የሚክዱ ኣይመስለኝም፣ ማንሳቱን ላይ ይመስለኛል። ከዛ የባሰ በኣጼ ምንሊክ፣ በሃይለስላሰ፣ በደርግ እንደተፈጸመ እንዴት ይካዳል። በኦሮሞ፣ በትግራይ፣ በኤርትራ፣ በወሎ፣ በራያ፣ በቤጌምድር፣ በጎጃም፣ ወዘተ መፈጸሙ እንዴት ይካዳል። ኣታንሱት ደብቁት እና ወያኔ ብቻ እንደመሰረተው ይታወቅ፣ ይጻፍ ብቻ ነው ምኞታቸው። ወያኔ ንጽሁ ነው ማሌቴ ኣይደለም ቀደምት የጀመሩት ቀጠሉበት እንጂ ስለዚህ ሁሉም መንግስታት ይመዘኑ።

የሚገርመው ደግሞ በኣማርኛ የኣጻጻፍ ችሎታው ያደንቁታል፣ እና በርታ እንደማለት። ኣማራ/ ኣማርኛ ኣትንካ ከሆነ የማይነካበት ምንም ምክንያት የለም። እንድያውም ወደ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ ሌሆችም ቃንቃችን ተተርጉመው ተውያይተንበት ተምረንበት ተመኩሮ እንድናገኝበት መደረግ ኣለበት፣ ለዚህም በግሌ እንቀሳቀስበታለሁ ምክንያቱም ልንተዎው ልንረሳው ብንፈልግ፣ እምየ እያላቹሁ እምየ የፈጸሙት ድርጊት ግን መግላጽ ኣትፈልጉም፣ የሚመቻች ሁ ብቻ ቀንጭባቹሁ ለማቅረብና ለመቀባት ስለምትመኙ ብቻ ነው።

ኣሁን ወዳለንበት መከፋፈል ዋናው ምክንያት ኣጼ ምንሊክ፣ ሃይለስላሰ፣ ድርግ ብቻ ናቸው፣ ይህ ደግሞ ባብዛኛው የኣማራ ህዝብ ሳይሆን የኣማራ ባለስልጣናት የፈጸሙት ድርጊት ነው። ኣፓርታይድ የሳውዝ ኣፍሪካ ነጮች፣ ለጥቁር ኣመሪካውያን ነጮች፣ ለሳውዝ ሱዳን የሰሜን እስላሞች፣ የፈጸሙት ድርጊት ነው። ኢህወዴግ እድል ኣግኝቶ ስልጣን ያዘ ያን ሁሉ የእናንተው ክፋት፣ ብሶት፣ ኢሰብ ኣዊ ድርጊቶች ተጠቀመበት። ኢህወዴግን ተቃውመን ብነነሳ ኣንተማ ትግሪ ወያኔ፣ ኣንተማ ኣሮሞ ኦነግ፣ ኣንተማ ኤርትራዊ ሻእብያ እያላቸሁ የከፋፈላች ሁት እናተ የኣማር ሙሁራን ፕ/ር ለማ፣ ዶ/ር ጌታቸው፣ የሆላንዱ ዶ/ር ኣይደላችሁም እንዴ? የራሳችሁ ቤት ሳታጸዱ ምን ነው ወደ ተስፋየ?

በቤተ ክርስትያን ስር ተሁኖ ኣሰራሮችን እንዳይስተካከል፣ ምእመናኑ እንዳይበተንና ለውጭም ተጠቂዎች እንዳንሆን ሳታስቡ የግላቹሁ ጥቅም ብቻ ለማስጠበቅ ኣቡነ መርቆርዮስ ወደ ውጭ ስባቹሁ ቤተ ክርስትያን ለሁለት ከፈላቹ ሁ፣ በዘር፣ በቃንቃ መሰባሰብ ኣራመዳቹሁ፣ ኢህአዴግም ኣራመደው ኣቀጣጠለው፣ ሌሎችም ለህልውናቸው ሲሉ፣ የእናንተ ስድብ ከመስማት፣ መሰባሰብ ተጀመረ።

ኣብራሃም ያየህም ከተሞክሮው ከሱዳን ጀምሮ እስከ ኣዲስ ኣበባ ከዛም ወዳ ኣፍሪካ እንዲሁም ኤርትራ ያየው የሰማው የታዘበው ውስብስብ ሁኔታዎችን በማጤን ለማንም ሳይፈራ በግልጽ የመሰለውን ይሻላል ያለውን መፍትሄ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/8786 በማቅረቡ ጥቃታችሁን እንደ ተስፍየ ወረዳችሁበት። ችግራችሁ የሌሎችን ብሶት ምሪት መገናዘብ ኣለመፈለጋችሁ ነው። እናንተ ብቻ የምትሉትን እንዲፈጸም እንጂ ተመካክራችሁ ማእከላይ መፍሄ መሻት ከምታስቀድሙ ኢትዮጵያ ብትከፋፈል ደንታች ሁ ኣይደለም፤ ለዚህ ኣይደለምን ኣቡነ መርቆርዮስን ወደ ገዳም ሳይሆን ወደ ስደት በኬንያ ኣድርገው እንዲሰደዱ ያደረጋችሁት።

ጃዋር መሓመድም ቢሆን በቃለ መጠይቅ እንደገለጸው በተለይ በዲሲ ኣከባቢ ኣብሮ ለመስራት መኩሮ ግን ማህበራዊ እንቅስቃሴው የኣንድ ብሄር ብቻ ሁኖ እንዳገኘው ተከባብረህ መስራትም እንዳላየ ተናግሮ ሲያበቃ እናንተ ግን ኦሮሞኖቱ ኣስቀደመ ብላችሁ ወረዳችሁበት፣ መነሻውን መግለጽ ኣልፈለጋችሁም፣ ሌሎች ቅሪታዎች ላይ መጻፍ ኣልፈለጋችሁም፣ ብልህ ስለሆነ ለማቃለል ተነሳሳችሁ፣ ለተስፈየም ለኣብርሃምም ለሌሎችም እንደዛ ናችሁ።

እንድያውም የተስፈየን ጽሁፍ በድራማ ተሰርቶ ቢቀርብ ምን ኣዲስ ነገር ኣለው። የደረሰብን የተፈጸመብን ትውልድ እኮ ኣለን። በደርግ ወላጆቻችን ተረሽነውብን ያደግን ኣለን። በሀይለስላሰ የራያ ድብደባ የመቱብን ትውልድ እኮ ኣለን። የዓድዋ በጣልያን ድል እንደምን ኣስታውሰው፣ ኣጼ ምንሊክ መረብ ምላሽ ለጣልያን መሸጣቸው እኩል እናስታውሰዋለን፣ እናንተ ግን የመረብ ምላሽ እንዲነሳም ኣትፈልጉም፣ ታድያ እንዴት ብለን እንስማማለንና።

እናንተ ሌላውን ደብቃችሁ ያሰኛችሁን እንደምትጽፉ ተስፋየም የተፈጸመ ድርጊት የመጻፍ ሙሉ መብት ኣለው። እናትተ በዛን ግዜ እንደተፈጸ መኮንናችሁ መግለጽ ነው፣ ያኔ እኛም ይቅር ብለን ኣብረን ለምስራት እንችላለን። ወደ ኣባቱ ኤርትራ ዘመተ እያላችሁ እነ ጉንበት 7 ከኢሳያስ ጋር መተባበር ትደግፋላችሁ። በዚህም በዝያም የናንተ ግዜ ኣብቅተዋል ስለዚህ ተከባብረን እንኑር። ተከባብረን ስርዓት እንመስርት። ለህግ የበላይነት እንቁም። ሌላው እንደ ታሪኩ ይገለጻል, ይጻፈል, ይደረሳል, እናውቀዋልን እንማርበታለን እንዳይደገም ይኮነናል ይረጋገጥበታል።

 

posted by Tseday Getachew

ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በዚምባቡዌ

በዚምባቡዌ አቋርጠዉ ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለመሻገር የሞኮሩ 38 ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች የዚምባቡዌን ድንበር ሲያቋርጡ ተይዘዉ በመታሰራቸዉ ለከፋ ችግር መጋለጣቸዉ ተነገረ።

epa03809922 Zimbabweans check election results posted outside a polling station in Mbare, Harare, Zimbabwe, 01 August 2013. Prime Minister Morgan Tsvangirai on 01 August declared Zimbabwe's general election to be 'null and void' due to allegations of vote rigging and warned the country was on the brink of a crisis. The country's most important independent network of election observers announced it too doubted the legitimacy of the ballot. The 89-year-old Zimbabwean president, Robert Mugabe, who has been at the helm of the country since 1980, has vowed to step down if he is declared the loser in the election. EPA/AARON UFUMELI

ስደተኞች የተያዙት ከሞዛምቢክ ወደዚምባቡዌ ተሻግረዉ፥ ከዚምባቡዌ በአዉቶቡስ ወደደቡብ አፍሪቃ ሲጓዙ ነበር። የዚምባቡዌ ፖሊስ እንዳስታወቀዉ ኢትዮጵያዉያኑ ስደተኞች ከተያዙበት ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ ባይትስብሪጅ በተባለዉ መቆጣጠሪያ ኬላ ላይ እንደታሠሩ ነዉ። በሐራሬ- ዚምባቡዌ የዶቸ ቬለ ወኪል ኮሎምቦ ስማቭሁንጋ እንደሚለዉ ስደተኞቹ ምግብ የሚያቀብላቸዉ ካላገኙ በረሐብ ይጎዳሉ።

በዚምባብዌ ፖሊስ መግለጫ መሰረት እነዚ እድሜያቸው በ20 እና30 መካከልየሚገኙ 38 ኢትዮጵያውያን በሞዛምቢክ በኩል ኣድርገው ነው የዛሬ ሳምንት ወደዚምባብዌ የዘለቁት። በህገወጥ መተላለፊያዎች በኩል። የተያዙትም ቢሆን ከምስራቃዊትዋ የዚምባብዌ ከተማ ከሙታሬ ኣውቶቡስ ተሳፍረው በባይትብሪጅ የማቐረጫ ኬላ በኩል ወደደቡብ ኣፍሪካለ መሻገር ሲሞክሩ ነው ተብለዋል። የባይትብሪጅ ኬላ ጠባቂ ፖሊሶች ኣዛዥ እንደሚሉት እነዚህ ስደተኞች በእሳቸው ኣጠራር ህገወጥ ፈላሾች በህገወጥ መንገድ ወደኣገሪቱ በመግባታቸው ምርመራ እየተካሄደቸው ይገኛል። በዚሁ ወንጀልም ክስ ይጠብቃቸዋል። ከእነዚህ ኢትዮጵያውያን በተጨማሪም በተመሳሳይ ሁኔታ ወደኣገሪቱ የገቡ በርካታ ስደተኞች ኣሉ። የሁሉም ጉዳይ በኣገሪቱ ህግ መሰረት ይዳኛል ይላሉ የባይትብሪጅ ፖሊስ ኣዛዥ ላውሬን ሴቪንሄንጎ የዚህን ኣይነት ወንጀል ለማጣራት የማንፈነቅለው ድንጋይ የለም የሚሉት ላውሬንሴ እነዚህን ስደተኞች ኣሳፍሮ ድንበር ለማሻገር ሲጘዝ የተገኘው ኣውቶቡስ ደግሞ ንብረትነቱ የፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ዛኑ PF ፓርቲ

Zimbabwe's President Robert Mugabe addresses the crowd gathered to commemorate Heroes Day in Harare August 12, 2013. Mugabe told critics of his disputed re-election to go hang on Monday, dismissing his rivals as Western-sponsored stooges at a liberation war commemoration that was boycotted by his principal challenger. The Movement for Democratic Change (MDC) of Mugabe's rival Morgan Tsvangirai filed a court challenge on Friday against the announced landslide win of Mugabe and his ZANU-PF party in the July 31 vote, alleging widespread rigging and intimidation. REUTERS/Philimon Bulawayo (ZIMBABWE - Tags: POLITICS ELECTIONS HEADSHOT)

ሁነኛ አባል መሆኑም ሌላው ቅሌት ነው ሲሉም ኣክለዋል።

ንብረትነቱ የም/ቤት እንደራሴ በሆነ ኣውቶቡስ 38 ያህል ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መሳፈራቸውን በመረጃ ስናረጋግጥ ለመያዝ ኣላመነታንም ያሉት እኚሁ የፖሊስ ኣዛዥ የኢሚግሬሺን ባልደረቦችም ለዚሁ መተባበራቸውን ኣመስግነዋል። ባለስልጣናት ኣውቶቡሶችን ለህገወጥ ስደት እስከማመቻቸት ሲደርሱ ለመታገስ ኣይቻለንም ሲሉም ኣዛዡ ተናግረዋል።

በዚምባብዌ ኃራሬ የሚገኘው የዶቸ ቬሌ ባልደረባ ኮሎምበስ ማብሁንጋ እንደሚለው ደግሞ የእነዚህ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ በእርግጥ ለውሳኔ ማስቸገሩ ኣይቀርም። ምክኒያቱም በዚምባብዌ ህግ መሰረት ያለፈቃድ የገባማንኛውም ስደተኛ ተይዞ ወደኣገሩ እንዲመለስ ነው የሚደረገው። ኣሁን ግን ዚምባብዌ ይህንን ለማድረግ ኣቅሙም የላትም።

ኮሎምበስ እንደሚለው በርካታ ስደተኞች በተመሳሳይ ሁኔታ ከሩዋንዳ፣ ኤርትራ እና ኮንጎ እየመጡ ወደደቡብ ኣፍሪካ ይሻገራሉ። ድንበር ላይ ሲያዙ ግን የማጎሪያ ካምፑ ይዞታ ኣሁን ኢትዮጵያውያኑ የሚገኙበት ማለት ነው በጣም ኣስቸጋሪ ነው። ስንቅ የሚያቀብል ዘመድ ከሌላቸው በተለይ ለምግብም ሊቸገሩ ይችላሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ ኮሎምበስ እንደሚለው ኃራሬ የሚገኙት የኣፍሪካ ኣገሮች ኢምባሲዎች ደግሞ ለዜጎቻቸው ደንታ ያላቸው ኣይመሉም።

ዚምባብዌ ከደቡብ ኣፍሪካ ጋር ባላት ቀጥተኛ ድንበር የተነሳ በኣፍሪካ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ወደሆነችው ደቡብ ኣፍሪካ የበርካታ ኣገሮች ስደተኞች መሸጋገሪያ ሆና መቆየትዋ ይታወቃል። ሶስት ሚሊየን ያህል የራስዋ የዚምባብዌ ዜጎችም በደቡብ ኣፍሪካ እንደሚገኙ ሲታወቅ አብዛኞቹ ደግሞ በህገወጥ መንገድ የገቡ ናቸው። በየዓመቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደዚምባብዌ እንዲመለሱ ቢደረጉም ወዲያውኑ ግን በሌላ አቅጣጫ ተመልሰው እዚያው ደቡብ ኣፍሪካ ይገባሉ ተብለዋል።

ጃፈርአሊ

ነጋሽመሐመድ

AUDIO http://www.dw.de/popups/mediaplayer/contentId

_17195084_mediaId_17195313

posted by Tseday Getachew

ቅዱስ ሲኖዶስ ለ‹‹ገለልተኛ›› አብያተ ክርስቲያን ጥሪ ያደርጋል

 

የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከእናት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ወጥተው በገለልተኛ አስተዳደር ለሚመሩ አብያተ ክርስቲያን የአንድነት ጥሪ ሊያስተላልፍ ነው፡፡ ምልአተ ጉባኤው በትላንት፣ ጥቅምት ፲፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ውሎው የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና መዋቅር ከማጠናከር አንጻር በገለልተኛ አስተዳደር ለሚመሩ አብያተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ተግባራት መፈጸም እንደሚገባቸው መመሪያ ሰጥቷል፡፡

ቋሚ ቅ/ሲኖዶስ በቀጥታ ይከታተለዋል በተባለው በዚሁ የቤተ ክርስቲያንን ማእከላዊ መዋቅር የማጠናከር ተግባር፣ ለገለልተኛ አብያተ ክርስቲያን የአንድነት ጥሪ የሚተላለፍ ሲኾን ጥሪውን የተቀበሉት አብያተ ክርስቲያን በሚያነሧቸው ጉዳዮች ላይ የሚወያይ ራሱን የቻለ አካል እንደሚቋቋም ተጠቁሟል፡፡ በውይይቱ በሚደረስበት መግባባት አብያተ ክርስቲያኑ በውጭ አህጉረ ስብከት ጽ/ቤቶች አስተዳደር ሥር ተካተው የሚያስፈልጓቸው አገልግሎቶች ሁሉ በማእከል እንዲሟላላቸው መመሪያ መሰጠቱ ተገልጧል፡፡

ተጠሪነት ሳይኖር በራሳቸው ፈቃድ ቤተ ክርስቲያንን በገለልተኝነት የማቋቋም ኹኔታ ራሱን የቻለ መዋቅር መስሎ በይበልጥ የሚታየው በሰሜን አሜሪካ ነው፡፡ የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ጽ/ቤት በ፳፻፬ ዓ.ም. ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ያቀረበው ሪፖርት እንደሚያስረዳው፣ በአሜሪካ ባሉት ሦስቱ አህጉረ ስብከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚገኙት አብያተ ክርስቲያን ቁጥር 56 ያህል ብቻ ነው፡፡

በክፍለ አህጉሩ የተበተነውን ምእመን ለመሰብሰብ፣ መሠረታዊና እውነተኛ የኾነውን የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ለማስከበር ከባድ ውጣ ውረድ መታለፉን የገለጸው የሀ/ስብከቱ ሪፖርት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት በቀጣይነት ለማጎልበት÷ በመዋቅርና በገለልተኛ አብያተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ሰንበት ት/ቤቶች በራሳቸው አነሣሽነትና ተቆርቋሪነት በመሠረቱት የአንድነት ማኅበር አማካይነት የሚደረገውን የወጣቶች እንቅስቃሴ መደገፍ፣ የካህናትን የእርስ በርስ ግንኙነትና የጋራ የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብሮችን ማጠናከር፣ ከሀ/ስብከታቸው ውጭ እየመጡ ከመዋቅር ውጭ የኾኑ አብያተ ክርስቲያን የሚከፍቱና ክህነት የሚሰጡ ሊቃነ ጳጳሳት አንድነትን   ከሚያናጋና ገለልተኝነትን ከሚያበረታታ ኢ-ቀኖናዊ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማድረግን በመፍትሔነት አቅርቧል፡፡

በተያያዘ ዜና በሰሜን አሜሪካ በስደት ከሚገኙት አባቶች ሲካሄድ ቆይቶ የተስተጓጎለው የዕርቀ ሰላም ሂደት እንዲቀጥል በአጀንዳ የተነጋገረው ምልአተ ጉባኤው፣ በስደት ያሉት አባቶች ፈቃድ ተጠይቆና አስፈላጊው ነገር ተሟልቶ ውይይቱ የሚቀጥልበት ኹኔታ እንዲመቻች መመሪያ መስጠቱ ተዘግቧል፡፡

ምልአተ ጉባኤው ስለ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ወቅታዊ ኹኔታ በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ረዳት በንባብ የቀረበውን የአጣሪ አካል ሪፖርት አዳምጧል፡፡ ሪፖርቱ እንደተለመደው ከሥልጣናቸው እንዲገለሉ ቀደም ሲል ውሳኔ የተላለፈባቸውን የብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስን ጠቅላይነትና ዐምባገነንነት እንዲሁም ብልሹ አስተዳደራቸው በኮሌጁ መልካም ስምና ቀጣይ ዕድገት ላይ የጋረጣቸውን አደጋዎች ዳግም ያረጋገጠ ነበር፡፡

በቅጥር፣ ዝውውር፣ ዕድገትና ስንብት የአንድ – ሰውን – ሁሉን – ወሳኝነት አጉልቶ ያወጣው ሪፖርቱ ኮሌጁ በአስተዳደሩ የቤተ ክርስቲያን ሳይኾን የግለሰብ ድርጅት እንደሚመስል አስረድቷል፡፡ በሦስት ሰዎች መከናወን ለሚገባው ሥራ የዘጠኝ ሰዎች ቅጥር የተካሄደበት፣ ሁለቱም የኮሌጁ ተሸከርካሪዎች ለሊቀ ጳጳሱ የግል ተግባር የመዋላቸው ኹኔታ በምሳሌነት ተጠቅሰዋል፡፡ በደቀ መዛሙርት አቀባበል ስድሳ ያህል ተማሪዎች ያቀረቧቸው የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ (ESLCE) የትምህርት ማስረጃዎች ፎርጅድ መኾናቸው፣ ትምህርታቸውን ሳይጨርሱ‹‹ዲግሪ ተሠርቶ የሚሰጣቸው እንዳሉና ከእኒህም አንዳንዶቹ ከኢትዮጵያ ውጭ የሄዱ

መኖራቸው›› ለምልአተ ጉባኤው አስደንጋጭ ነበር፡፡

በቀድሞው ፓትርያርክ ትእዛዝ የመንበረ ፓትርያርኩ የቁጥጥር አገልግሎት በኮሌጁ አዲሱ ሕንጻ ላይ ባካሄደው የኦዲት ምርመራ የ21 ሚልዮን ብር ሙስና መፈጸሙን አረጋግጦ ሳለ ምንም ርምጃ አልተወሰደም፡፡ የመምህራኑ ቅጥር፣ አያያዝ(በመኖርያ ቤት) እና ደመወዝ ኹኔታ ብልሹ እንደኾነና በሥራ ላይ ሥልጠና አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ኮሌጁ የሠራው ሥራ አለመኖሩ በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡ በቅርቡ በሊቀ ጳጳሱ የተደረገውንና በቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ የተተቸውን የአካዳሚክ ምክትል ዲን ምደባ ሪፖርቱ ተቃውሟል፡፡

ሪፖርቱ የተጠቀሱትን ችግሮች በመሠረቱ ይፈታቸዋል ያላቸውን መፍትሔዎች በጠቆመበት ክፍሉ÷ የበላይ ሓላፊው ሊቀ ጳጳስ በበላይ ጠባቂነት ብቻ እንዲቀመጡ፣ በአስተዳደርና የፋይናንስ እንቅስቃሴ ጉዳዮች ላይ እንዳይወስኑ፣ በምትኩ የሽግግር ዋና ዲን እንዲመደብ፣ በሊቀ ጳጳሱ የተደረገው አዲስ የአካዳሚክ ምክትል ዲን ምደባ ተሸሮ በምትኩ ሌላ እንዲሾም ሐሳብ አቅርቧል፡፡ ተሟልቶና ጊዜውን ጠብቆ ከመሰብሰብ ጀምሮ ድክመት ያለበትና ለኮሌጁ የሚጠቅሙ ፖሊሲዎችንና ስትራተጂዎችን ከማውጣት ይልቅ በሊቀ ጳጳሱ ተጽዕኖ ሥር ወድቆ የአስተዳደር ሥራም የሚሠራው ሥራ አመራር ቦርዱም ዳግም እንዲዋቀር ተብሏል፡፡

ለበላይ ሓላፊው ሊቀ ጳጳስ ከልክ ያለፈ ወዳጅነት በማሳየት ውሳኔዎች እንዳይፈጸሙ አድርገዋል ተብለው የሚወቀሱት ፓትርያርኩ ‹‹ሊቀ ጳጳሱ በበላይ ጠባቂነት ይወሰኑ›› የሚለውን ሐሳብ መደገፋቸው ተነግሯል፡፡ ምልአተ ጉባኤው ከሌሎች ቦርዶች በተለየ በኮሌጁ አስተዳደር ሳይቀር እየገባ ይወስናል የተባለውን የሥራ አመራር ቦርድ በዛሬው ዕለት ለማብራሪያ ጠርቷል፡፡

በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ከምልአተ ጉባኤው ስብሰባ እንዲወጡ ተደርጎ (ከስብሰባው በሚወጡበት ወቅት ችግር የበዛባቸው ፮ው ፓትርያርክ ከተሾሙ ወዲህ መኾኑን በመጥቀስ ፓትርያርኩን፣ ብፁዕ ዋና ጸሐፊውንና ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁን በብስጭት ወቅሰዋል) የታየው የኮሌጁ አጀንዳ በዛሬው ውሎው በሪፖርቱ ከተጠቆሙት መፍትሔዎች አንጻር የሥራ አመራር ቦርዱ ማብራሪያ ከተሰማ በኋላ መቋጫ እንደሚሰጠው ይጠበቃል፡፡

His Grace Abune Timothy

http://haratewahido.wordpress.com/

posted by Tseday Getachew

ኢትዮጵያ:- የፖሊስ መንግስት ያንሰራፋባት ሀገር ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም

Prof. Al Mariam ፕ/ር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ህገመንግስት በህግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ዜጎችን አስመልክቶ የሚከተሉትን መብቶች ያጎናጽፋል፡፡“በህግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የዋለ ማንኛውም ሰው በህግ አግባብ መብቱ ተጠብቆ ይያዛል፡፡ ማንኛውም ሰው በሀሰት ለመረጃ ጠቀሜታ ተብሎ በማስገደድ እንዲያምን  ወይም የተባለውን እንዲቀበል አይገደድም፡፡ ማንኛውም በማስገደድ የተገኘ መረጃ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡“ ይላል አንቀጽ 19(2)(5)፡፡ እውነታው ሲታይ ግን ይህ የይስሙላ ሙበት የተጻፈበትን ወረቀት ዋጋ ያህል የለዉም፡፡

ባለፈው ሳምንት ሂዩማን ራይትስ ዎች “HRW“ የተባለው ዓለም ዓቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በኢትዮጵያ መንግስት “የፌዴራል ፖሊስ ማዕከላዊ ምርመራ” እየተባለ በሚጠራው የፖሊስ ጣቢያ የሚፈጸሙትን አስደንጋጭና አስከፊ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ዘገባ ሪፖርት አቅርቧል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው ይህ የፖሊስ ምርመራ ማዕከል በጥርጣሬ የተያዙ ዜጎችን በማሰቃየት ይታወቃል፡፡

እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ “በቁጥጥር ስር ባሉ እስረኞች ላይ በተለይም ያለው መንግስት ይቃወሙኛል በሚላቸው የፖለቲካ እስረኞች ላይ ማዕከላዊ ምርመራ እየተባለ የሚጠራው የምርመራ ተቋም እልህ አስጨራሽ የምርመራ ሂደት በማድረግ እስረኞችን በግድ ወንጀል ሰራን ብለው አንዲአምኑ በማስገድድ፣ እንደሚያሰቃይና ህገወጥ የእስረኞች አያያዝ“ እየፈጸመ እንደሆነ በማረጋገጥ በዘገባው ይፋ አድርጓል፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ በማያያዝም “ማዕከላዊ ምርመራ እየተባለ የሚጠራው ተቋም ብዙ የተቃዋሚ የፖለቲካ እስረኞች፣ ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች፣ መንግስት የብሄር ግጭት ተንኳሾች ናቸው በሚላቸውና ሌሎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በጅምላ ተይዘው የሚሰቃዩበት የምርመራ ማዕከል” ነው ብሎታል፡፡

ገጣሚው ዊሊያም ኤርነስትን አባባል በመዋስ “ማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል”  የሰቆቃ መደብር በለቅሶና በሰቃይ የታጠረ የጭለማ ቤት ነው :: የገዥው መንግስት ተቃዋሚዎች፣ አመጸኞች፣ የሚላቸዉን የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እና ሌሎች እስረኞች በሙሉ በምርመራ ጊዜ ሰቆቃ ተጠቅሞ አራሳቸዉን አንዲወነጅሉ ያስገደዳቸዋል:: እንዲሁም ብዙዎቹ ማሰቃየትን ጨምሮ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ይፈጸሙባቸዋል፡፡

እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች አባባል ማዕከላዊ እየተባለ የሚጠራው የምርመራ ተቋም “አስቀያሚው የአካልና የስነ ልቦና ማሰቃያ እንዲሁም አስገድዶ የማሰመኛ ምሽግ” መሆኑን በመጠቆም በማዕከሉ ከሚፈጸሙ የማሰቃየት ወንጀሎች እነዚህ ከብዙ ጥቂቶቹ መሆናቸውን በአጽንኦት ገልጿል፡፡ አኔም በግሌ  ከአስፈሪው ማአከላዊ ምርመራ መዳፍ የተረፉ የቀድሞ እስረኞችን አነጋገሬ አውቃለሁ::

እ.ኤ.አ. በ2011 የአሜሪካ መንግስት መምሪያ በዓመታዊ የሰብአዊ መብት አያያዝ ዘገባው በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ ለማሳየት የሚከተለውን ማጠቃለያ አስፍሯል፡፡

 ብዙ ተጨባጭ መረጃዎች እንደሚያረጋግጡት እ.ኤ.አ. በ2009 በአዲስ አበባ የሚገኘው ማዕከላዊ እየተባለ የሚጠራው የፖሊስ ምርመራ ማዕከል ፖሊስ ኃይልን በመጠቀም አስረኞችን አስገድዶ ለማሳመን የአካል ማሰቃየት ሰቆቃ ድርጊት ሲፈጽም ነበር፡፡ ይህ ዓይነት የማሰቃየት ዘዴ በአሁኑ ጊዜም በተግባር ላይ እየዋለ ያለ መሆኑን ዜጎች ያላቸውን ሰፊ እምነት አጽንኦት በመስጠት እየገለጹ ነው፡፡ ባለስልጣናቱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ ማዕከላዊ ምርመራን ለመጎብኘት የሚያቀርቡት ጥያቄ አሁንም በመንግስት በኩል አዎንታዊ ምላሽ እንዳላገኘ ይታወቃል፡፡“ በማለት ድርጅቱ ያለውን ሀሳብ ቋጭቷል፡፡

የ15ኛው ክፍለ ዘመን የሰቆቃ ስልት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ!

በአዲስ አበባ እምብርት ላይ የሚገኘው ማዕከላዊ እየተባለ የሚጠራው የማሰቃያ ምርመራ ተቋም በመካከለኛው (15ኛው) ዘመን በአውሮፓ የሰብአዊ መብት ረጋጮች በንጹሀን ዜጎች ላይ ይደረግ የነበረውን አስፈሪ፣ አስደንጋጭና ተስፋቢስ የማሰቃየት ስልት ገጽታ መለስ ብለን እንድናስታውስ ያስገድደናል፡፡ እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች መግለጫ “የማዕከላዊ ምርመራ ፖሊሶች በህግ ጥላ ስር የተያዙ የህግ አስረኞችን እነርሱ በሚፈልጉት መልኩ በግድ ለማሳመን፣ መግለጫ እንዲሰጡና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት ሲሉ በእስረኞች ላይ ማሰቃየትን ጨምሮ የተለያዩ የማስገደጃ  ዘዴዎችን እና ልዩ ልዩ ኢሰብአዊ ድርጊቶቸን ይፈጽማሉ፡፡ እንደ መካከለኛው የአውሮፓ ዘመን መብት ረጋጭ ተቋሞች ሁሉ የኢትዮጵያው የምርመራ ማዕከልም እንደመርማሪዎቹ ፍላጎትና አመችነት ሁኔታ እስረኞችን በአራት ዋና ዋና ክፍሎች መድቧቸዋል፡፡ የማዕከላዊ ምርመራ ማዕከል በተለያዩ የእስረኞች አያያዝና እያንዳንዳቸው ባላቸው ቅጽል ስም የሚታወቁ አራት አይነት የማጎሪያ እስር ቤቶች አሏቸው፡፡ እነርሱም፣ 1ኛ) ጨለማ ቤት፣ ይህ እስር ቤት በጣም አስቸጋሪና ብርሀን የማይገኝበት የማጎሪያ ክፍል ነው፡፡ በዚህ እስር ቤት እስረኞቹ የፀሐይ ብርሀን እና የመጸዳጃ ቤት የማግኘት ዕድላቸው በጣም ጠባብ ሲሆን አንዳንድ ጊዜም ለብቻ የመታሰር ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል፣ 2ኛ)ጣውላ ቤት፣ ይህ እስር ቤት በክፍል ውስጥ እንደልብ መዘዋወር የማያስችል ሲሆን ክፍሎቹም በቁንጫ ተባይ የተወረሩ ናቸው፡፡ 3ኛ) ሸራተን፣ በቅርብ ጊዜ ከእስር ቤት የማይለቀቁ ብዙዎቹ እስረኞች ወደዚህ የማጎሪያ ቤት እንዲዛወሩ ይፈልጋሉ፡፡ ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ባለው ሆቴል ስም የተሰየመው እስር ቤት እስረኞቹ የተሻለ የአካል እንቅስቃሴ የማድረግና በህግ አማካሪዎቻቸውና በዘመዶቻቸውም መጎብኘት እንዲችሉ የእስር ቤቱ ኃላፊዎች ፈቃድ የላላበት ነው፡፡ 4ኛ) የተፋፈገው የሴት እስረኞች ማጎሪያ፣ ይህ እስር ቤት በገፍ ሴት እስረኞችን አጭቆ የያዘ ነው፡፡”

ገዥው የኢትዮጵያ አስተዳደር ከተቃዋሚ የፖለቲካ እስረኞች መረጃዎችን፣ መግለጫዎችን እና ተገደው የእምነት ቃል እንዲሰጡ ለማድረግ የተለያዩ የማሰቃያ ዘዴዎችን ይጠቀማል፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች አንደጠቀሰው: “እስረኞች በተደጋጋሚ በጥፊ ይጠናገራሉ፣ በእርግጫ ይመታሉ፣ በቦክስ ይደለቃሉ፣ በዱላና በጠብመንጃ ሰደፍ ይደበደባሉ፡፡ አንዳንዶች እንደተናገሩት በሚያስጨንቅ ሁኔታ [በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ይደረግ እንደነበረው ‘እጅን በገመድ አስሮ ገልብጦ ከጣራ ወደ ታች በማንጠልጠል እንዲወድቁ በማድረግ የማሰቃየት’] ወይም ሁለት እጆችን ወደ ላይ ከእራስ በላይ ከፍ አድርጎ በገመድ አስሮ በማቆም ለበርካታ ሰዓታት በማቆየት በተደጋጋሚ ያሰቃዩ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ አሁንም [በመካከለኛው ዘመን ይደረግ እንደነበረው ሁሉ] በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ምርመራ ማዕከልም የእስረኞችን እጆች በካቴና በማስገባት ለበርካታ ጊዜ ታስረው እንደሚቆዩ እንዲያውም አንድ እስረኛ ከአምስት ተከታታይ ወራት በላይ እጁ በካቴና ታስሮ እንደቆየ እና ማቋረጫ በሌለው የቃል ጥያቄ ምርመራ በታሳሪዎቹ ዘንድ ፖሊስ ተደጋጋሚ ዛቻ እንደሚያደርግ ተረጋግጧል፡፡” በጥንት ጊዜ ‘በእስፓኞች ይደረግ እንደነበረው አሰቃቂ የምርመራ ሂደት‘ አንዳንዶቹ እስረኞች ለበርካታ ጊዜ ተገልለው ለብቻቸው እስራታቸውን እንዲገፉ ተበይኖባቸዋል፡፡ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን የእስር ቤት ማጎሪያዎች ይደረግ እንደነበረው ሁሉ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እስረኞቹ የፀሐይ ብርሃን የማግኘት መብታቸውን ይከለከላሉ፣ በደካማ የንጽህና አያያዝና በውሱን የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ይሰቃያሉ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች በተለይም በመጀመሪያ ለምርመራ  የቀርቡትን ተጠርጣሪዎች ላይ የበለጠ አሰቃቂ ይሆናሉ፡፡”

የእነዚህ ሁሉ የማሰቃየት ተግባራት ዋና ዓላማው በእስረኞች ላይ ታላቅ ጫና በመፍጠር ትክክል ይሁንም አይሁን ለቀረበባቸው የወንጀል ክስ ፈጻሚ መሆናቸውን እንዲያምኑ በማስገደድ መግለጫ፣ የእምነት ቃልና መረጃ እንዲሰጡ ለማድረግ ነው፡፡ እነዚህን በማስገደድ የተሰጡ መግለጫዎችና በግዳጅ የተገኙ የእምነት ቃሎችን አንዳንድ ጊዜ ተወንጃዮቹ ከእስር ቤት ከተለቀቁ በኋላ ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ ያለውን መንግስት ተገደው እንዲደግፉና ጉዳያቸው በፍርድ ቤቶች በሚታይበት ጊዜም መንግስት እንደ ማስረጃ ለመጠቀም ስለሚፈልጋቸው ነው፡፡

በማዕከላዊ እስር ቤት እስረኞች ለደረሱባቸው የአለአግባብ መታሰርና መንገላታት የሚጠየቅም ሆነ የሚገኝ ካሳ የለም፡፡ ፍርድ ቤቶች ከፖለቲካ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የማየት ነጻነት የላቸውም፡፡ ፍርድ ቤቶች የማዕካላዊ ምርመራ ፖሊስ በምርመራ ጊዜ በእስረኞች ላይ የማሰቃየትና ህገወጥ ድርጊቶችን ፈጽሟል የሚል ውንጀላ ለፍርድ ቤቶች ቢቀርብ ተገቢውን የማጣራት ሂደት በማከናውን እርምጃ ለመውሰድ አይችሉም፡፡ በሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ መሰረት የቀድሞ እስረኞች የማዕከላዊ ምርመራን የበቀል እርምጃ በመፍራት በምርመራ ወቅት የደረሱባቸውን በደሎች ለፍርድ ቤቶች ለማቅርብ ስለሚፈሩ ዝምታን እንደሚመርጡ ጠቁሟል፡፡ አንዳንዶቹም ከፍርድ ቤቶች ችሎት በፍጹም ደርሰው እንደማያውቁ ይናገራሉ፡፡

እ.ኤ.አ. በጁላይ 2008 በዓለም በደህንነት ሙያ ታዋቂ የሆኑት እንግሊዛዊው ጡረተኛ ኮሎኔል ሚካኤል ዴዋርስ የኢትዮጵያን የእስር ቤቶች አያያዝ ሁኔታ አጥንተው የመፍትሄ ሀሳቦችን እንዲያቀርቡ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተዋውለው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ እስር ቤቶችን ከጎበኙ በኋላ በተጨባጭ የተመለከቱትን የእስር ቤቶችን ሁኔታ እንደሚከተለው አቅርበዋል፡፡ እንደዚህም ይተርኩታል፡፡

“እስረኞቹ ወዳሉበት ግቢ ውስጥ እንድገባ ጥያቄ አቀረብኩ፣ ይህ ግቢ ረዥም የሆነ በአንድ ጎኑ በኩል መጠለያ ሊሆን የሚችል ዳስ ይዟል፣ ግቢው በግንብ አጥር የታጠረ ሲሆን ለአካባቢው ጥበቃ እንዲያመች ሆኖ የተሰራ የጥበቃ ማማና ጥበቃዎች አሉት፡፡ በግቢው ውስጥ ከ70 እስከ 80 የሚሆኑ እስረኞች በተጎሳቆለ ሁኔታ ይታያሉ፡፡ ለሁሉም እስረኞች በምንጣፍ ለመጋደም የሚያስችል በቂ ክፍል የለም፣ መብራት የሚባል ነገር የለም፣ ቦታው በአይነምድርና በሽንት በሚሰነፍጥ ሽታ ታውዷል፣ በግቢው ውስጥ ምንም ዓይነት ውኃም ሆነ የመጸዳጃ ፋሲሊቲ የለም፣ በግቢው ውስጥ ለሴት እስረኞች ተብሎ ትንሽ የሳር ጎጆ ተቀልሳ በቅርብ እርቀት ትታያለች፣ ሆኖም ግን ግቢውን ለማሻሻል ተብሎ በግቢው ውስጥ የተሰራ ምንም ነገር የለም፣ አብዛኞቹ እስረኞች በትናንሽ ወንጀሎች በተለይም በሌብነት ወንጀል እየተያዙ ወደ እስር ቤቱ በተደጋጋሚ የሚመጡ ናቸው፡፡ ጥቂቶቹ ለወራት በዚሁ እስር ቤት የቆዩ ናቸው…፡፡”

ኮሎኔል ዴዋርስ በእስር ቤቱ የተመለከቱትን በሚከተለው መልክ አጠቃለዋል፣ “የእስረኞቹ አያያዝ  በሚያሳፍር ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህም ሁኔታ ፌዴራል ፖሊስን ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ትችት እንዲጋለጥ አድርጎታል፣ ማንም ቢሆን እስር ቤቶች እንደ ሂልተን ሆቴል መሆን አለባቸው ብሎ ሀሳብ የሚያቀርብ የለም ነገር ግን ማንም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ላይ ተገኝቶ ቅኝት ቢያደርግ እኛ ያደረግነውን ጥረት የሚደግፉ መረጃዎችን ማውጣት ይችላል… የዚህ ሁሉ የመጨረሻ ውጤቱ ሁከት፣ የእስረኞች ፍትህ አልባነትና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብና በሰብአዊ መብት ተሟጋች ደርጅቶች መወገዝ ነው፡፡”

እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 2013 ሂዩማን ራይትስ ዎች ባቀረበው ዘገባ መሰረት “ባለፉት አስር ዓመታት ሂዩማን ራይትስ ዎች እና ሌሎች ዓለም አቀፋዊና የአገር ውስጥ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ማለትም በዘፈቀደ ማሰርና ማጋዝ፣ ህገወጥ የእስረኞች አያያዝ ድርጊት እና ማሰቃየት በተለያዩ ህጋዊና ህጋዊ ባልሆኑ እስር ቤቶች ውስጥ መፈጸማቸውን በተጨባጭ ማስረጃ አረጋግጠው ለህዝብ ይፋ አድርገዋል፡፡”

ማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል ቤት: ኢትዮጵያ እስር ቤት መሆኗን ይመሰላል  

ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ የእስር ቤቶችን አያያዝ ሁኔታዎች በተመለከተ ገንቢ ትችት ማቅረቤ ይታወሳል፡፡ እ.ኤ.አ. ፌብሯሪ 2012 ባቀረብኩት ትችት የኢትዮጵያ መንግስት በየፖለቲካ እስረኞች ማጎሪያዎች ላይ በዘፈቀደ የሚፈጽማቸውን የሰብአዊ መብት ረገጣዎችና ህገወጥ የእስረኞች አያያዝ ሁኔታ ለማጋለጥ ሞክሪያለሁ፡፡ እ.ኤ.አ. ፌብሯሪ 2013 ኢትዮጵያን “በአፍሪካ የፖሊስ ረጋጭ መንግሥት ተምሳሌትነት በመፈረጅ ጠንካራ ትችት አቅርቢያለሁ፡፡ የክርክር ጭብጤንም እንደሚከተለው አቅርቢያለሁ፡፡

“የሌባ ፖሊስ መንግስት ብቸኛ መለያው — ልዩ መታወቂያው — በማያቋርጥና በየቦታው የሚፈጽማቸው የዘፈቀደ እስሮች፣ ዜጎችን ማደንና ወደ እስር ቤት ማጋዝ ናቸው፡፡ ማንም ሰው በከፍተኛም ሆነ በዝቅተኛ የመንግስት ባለስልጣን ስሜታዊ ትዕዛዝ በቀጥጥር ስር ውሎ የሚታሰር ከሆነ ይኸ የፖሊስ መንግስት መገለጫ ነው፡፡ ከህግ አግባብ ውጭ የዜጎች መብት የሚጣስ ወይም የሚረገጥ ከሆነ ያ በጣም አስቀያሚ የፖሊስ መንግስት መገለጫ ነው፡፡ የህግ የበላይነት ከህግ በላይ በሆነ ፖሊስ አዛዥ የሚተካ ከሆነ ያ የሌባ ፖሊስ መንግስት ተምሳሌት ነው፡፡”

በዚያ ባቀረብኩት ትችት በአዲስ አበባ ከተማ በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ ከህግ አግባብ ውጭ የፍተሻ ወረቀት ሳይዙ በሌሊት በግልሰቦች ቤት በመሄድ በሚያካሂዱት ህገወጥ ፍተሻ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ በአንዱ ህገወጥ የቤት ፍተሻ ላይ የተደረገው የሚቆጠቁጥ ድርጊት ግን የፌዴራል ፖሊስ ኃላፊዎች በሙስሊም ዜጎች ቤቶች በመግባት የፈጸሙት የገንዘብ፣ የወርቅ ጌጣጌጥ፣ የተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ የሃይማኖት መጻህፍትና ሌሎች የግል ቁሳቁሶች ላይ የተደረገው ዝርፊያ ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ክፍለ ከተማ የፖሊስ አዛዥ ለሆነ ሰው የአሜሪካ ድምፅ የአማርኛው ፕሮግራም ጋዜጠኛ ጠንካራ ጥያቄዎችን በማንሳት ቃለመጠይቅ ሲያቀርብለት እንዲህ የሚል አሳፋሪ ማስፈራሪያ ሰጥቷል፣ “ዋሽንግተንም ሆነ በሰማይ ቤት ብትኖር ደንታዬ አይደለም፣ ከቁብ አልቆጥረውም፣ነገር ግን አዚያው ድረስ መጥቼ አንጠልጥልዬ አመጣሀለሁ፣ ይህን ልታውቅ ይገባል” ብሎ ዛተበት፡፡

እ.ኤ.አ. ጁላይ 2012 ኤርን በርኔት የተባለቸው የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ኢትዮጵያን ከጎበኘች በኋላ የሚከተለውን ምስክርነት ሰጥታለች፡፡

“ባለፈው ወር ኢትዮጵያ በነበርኩበት ጊዜ የፖሊስ መንግስት ምን እንደሚመስል ለመመልከት ችያለሁ… አውሮፕላን ማረፊያው በቆየሁበት ጊዜ የጉምሩክ የስራ ሂደቱን ለማጠናቀቅ አንድ ሰዓት ወስዶብኛል፣ ይህም በሰልፉ መብዛት ምክንያት አይደለም ነገር ግን በፍተሻና በሚቀርቡት ጥያቄዎች መንዛዛት ምክንያት ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣኖች ብዙ ጊዜ በመንግስት መኪናዎች እንድንንቀሳቀስ ይፈልጋሉ፣ ይህም ወዴት እንደምንሄድ ለማወቅ ስለሚፈልጉ ነው፡፡ በመቶሺዎች የሚቆጠር ዶላር ዋጋ ያላቸው የቴሌቪዥን መሣሪያዎች  በአውሮፕላን ማሪፊያው  ከተውን በኋላ ብቻ ነው ቁጥጥራቸው በመጠኑም ቢሆን መላላት የቻለው፡፡”

የፖሊስ መንግስት ቃለመጠይቅ አንዴት አይነት አንደሆነ በቪደኦ ማየት ይቻላል!?

ሂዩማን ራይትስ ዎች በተቃዋሚ ፖለቲካ እስረኞች ወይም መብታቸውን ለማስከበር በሚጠይቁ ዜጎች ላይ በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣ ዘገባ በማረጋገጥ በየጊዜው ዘገባዎችን እያዘጋጀ ያስቀምጣል፡፡ በዚህ ዓመት መጀመሪያ አካባቢ በአዲስ አበባ ከተማ የሙስሊሙን አመጽ መርቷል በሚል ውንጀላ ተከሶ የተያዘ ወጣት ግለሰብ ቃለ መጠይቅና የእምነት ቃሉን በቪዲዮ በመቅረጽ ህዝብ እንዲያየው ተደርጓል፡፡ በኢትዮጵያ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ከሁለት ዓመት በላይ ጀምሮ መንግስት በኃይማኖታችን ጣልቃ መግባቱን ያቁም በማለት ተቃውሞውን ሲያሰማ ቆይቷል፡፡

ከታወቁ የዜና ምንጮች መረዳት እንደተቻለው በቪዲዮ የተቀረጸው ቃለ መጠይቅ በማዕከላዊ ምርመራ በአንደ ፖሊስ ወይም ደህንነት ባለስልጣን ቢሮ ውስጥ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በቃለመጠይቅ መስጫው ክፍል ውስጥ ሌሎች ሰዎች የነበሩ ሲሆን የሚሰማው የዋናው ቃል  ጠያቂ ድምጽ ነበር፣ (የሌላ ሰው ድምጽ መስማማቱን ለመግለጽ ዋናውን ቃለ መጠይቅ አድራጊ ሲያቋርጠው ለተወሰነ ጊዜ ይሰማ ነበር፡፡)

የቃለ መጠይቅ ማድረጊያው ክፍል ባለመስታወትና ባለፋሽን በር ያለው ነው፡፡ በመሰረቱ ላይ ባለ ነጭ ቀለም መጋረጃ ይታያል፡፡ በጣም ውድ የሆኑ ከውጭ ኢምፖርት ተደርገው የገቡ ባለ ረዥም መደገፊያ በቆዳ የተለበዱ የባለስልጣን ወንበሮች እና ግማሹ የቃለ መጠይቅ ማድረጊያ ክፍል በሶፋዎች ተሞልቶ በካሜራ ሌንሱ ይታያል፡፡ ከተጠርጣሪው ጎን የኢትዮጵያ ካርታ ተሰቅሎ ይታያል፡፡ ቃለ መጠይቁ በጨለማው የማዕከላዊ ምርመራ ክፍል ውስጥ አለመደረጉን ያሳያል፡፡ እንደ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ከሆነ ቃለ መጠይቁ የተካሄደው በማዕከላዊ ፖሊስ ኮሚሽነሩ ቢሮ ውሰጥ እንደሆነ ይገመታል፡፡

በቪዲዮ ቴፑ እንደሚታየው ተጠርጣሪው ሰው ሁለት እጆቹን በካቴና ታስሮ ለጸሎት እንደሚተጋ ሰው መዳፎቹን ከወዲያ ወዲህ ሲያወራጭ ይታያል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ለወጣቱ ተጠርጣሪ ዝርዝር ቃለመጠይቅ ሰጠ፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው የሚያስጠላ አዛዣዊ ድምጽ የሚያስተላልፍ መሆኑን ያሳብቅበታል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ይደረግ እንደነበረው የማስገደድ ዝርዝር ቃለ መጠይቅ ሁኔታ ይታይበት ነበር፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው በፍርሀትና በለሆሳስ ድምጽ የሚናገረውን ተጠርጣሪ ስለእምነቱና ሌሎችም ጉዳዮች በጥያቄ ያዋክበው ነበር፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው በሚያስፈራ መልክ ስለሰለፊያ እምነት ምንነትና ስለእስላም አክራሪነት እንዲሁም በሌሎች ላይ ሰለሚኖረው መልካም አስተሳሰብ አደገኛነት ሲጠይቀው ተስተውሏል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ተጠርጣሪውን በአሽሙር በመሸንቆጥ ሲያስጨንቀው ታይቷል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ተጠርጣሪውን የሙስሊም ትምህርት ቤቶችን ሽፋን በማድረግ እሱ እና መሰሎቹ በኢትዮጵያ የእስላም መንግስት ለማቋቋም ጥረት እንደሚያደርጉ ወንጅሎታል፡፡ የተጠርጣሪው ድርጀት የገንዘብ ምንጩ ከየት እንደሆነ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ደጋግሞ በመጠየቅ ሲያባሳጨው ታይቷል፡፡ በቃለ መጠይቅ ሂደቱ ሁሉ ቃለ መጠይቅ አድራጊው በተጠርጣሪው ላይ ሲያፌዝ፣ ንቀት ሲያሳይ፣ ሲቀልድና በንቀት ሲሳለቅ ታይቷል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ተጠርጣሪው እንዲናገር ዕድሉን ከሰጠ በኋላ ተጠርጣሪው በማስተባበል መናገር ሲጀምር ቃለ መጠይቅ አድራጊው ወዲያውኑ በማቋረጥ ያስቆመዋል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ወጣቱ ተጠርጣሪ በተስፋቢስነት በረዥም የባለስልጣን ወንበር ላይ ተቀምጦ ሁለት እጆቹን በካቴና ታስሮ ቃለ መጠይቅ አድራጊውን በአክብሮት ዓይን እያየ በለሆሳስ ቅላጼና በጉልህ በማይሰማ ድምጽ በሚናገርበት ጊዜ የበላይነት ስሜት ያንጸባርቅበታል፣ ይረብሸዋል፣ እንዲሁም በተለየ መልኩ ያንቋሽሸዋል፡፡

እንደ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ከሆነ በቪዲዮው ላይ የተደበቀ ብዙ ነገር አለ፡፡ ለምሳሌ ያህል የተቀረጸው  የቪዲዮ ቃለ መጠይቅ ከመደረጉ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ለመደብደብ ወደ ኋላ በማይሉ ዝቅተኛ የፖሊስ ባለስልጣኖች በማለሳለስና ተገድዶ ላመነው የቪዲዮ ቀረጻ ተባባሪ እንዲሆን በማድረግ ሙሉ ቃለ መጠይቅ ተደርጎለት ነበር፡፡ የቪዲዮ ቀረጻ ቃለ መጠይቁ በሚደመጥበት ጊዜ ሌሎች የፖሊስ አባላትና የሲቪል ሰራተኞች እንዲገኙ ተደርጓል፡፡ እንዲገኙ የተደረገበት ዋና ዓላማም ጉዳዩ ለፍርድ ቤት በሚቀርብበት ጊዜ ተጠርጣሪው ግለሰብ ያለምንም ተጽዕኖ በእራሱ ፈቃድ አምኖ የተናገረው መሆኑን መመስከር እንዲችሉ ለማመቻቸት ነው፡፡ (በቪዲዮ የተቀረጸውን ቃለ መጠይቅ ቅጅ ለተከላካይ ጠበቆችም ሆነ ለፍርድ ቤቱ የተሰጠ ነገር የለም፡፡) ቃለ መጠይቁ የተቀረጸው የፖሊስ ማስፈራሪያነት በሌለበትና ከጣልገብነት ነጻ በሆነ መልኩ በተረጋጋና በጥሩ የንግግር ቅላጼ መሰረት ተደርጎ ነው፡፡ ጥያቄዎቹ በመስክ ላይ እንደሚፈነዳ ደማሚት ተደርገው በዘዴ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ጥያቄ አቅራቢው ተጠርጣሪው የየትኛው ድርጅት አባል እንደሆነ፣ ምን ፍልስፍና እንደሚከተል፣ እነማን ደጋፊዎቹ እንደሆኑ፣ የገንዝብ ምንጫቸው ከየት እንደሆነ፣ የተከሰሰበት ወንጀል ምን እንደሆነና የመሳሰሉት አጠቃላይ ጥያቄዎች ይቀርቡለታል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ተጠርጣሪው ድርጊቱን ለመፈጸሙ ሊያሳምን በሚችል መልኩ ተያያዥነት ያላቸው በሚመስል መልኩ ሌሎች ሁለተኛ ዙር ጥያቄዎች ይከተላሉ፡፡ ለምሳሌም ተጠርጣሪውን ለምንድን ነው የዚህ ድርጅት አባል የሆንከው? አባል ሆኖ ምን ሚና እንደተጫወተ እንዲሁም እነዚህን የተወነጀለባቸውን ድርጊቶች ለምን ሪፖርት እንዳላደረገና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ይጠየቃል፡፡ የቪዲዮ ቃለ መጠይቁ ተጠርጣሪው የወንጀል ድርጊቱን መፈጸሙን ለማመኑ ትክክለኛ መረጃና ለእራሱ መስቀያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ዋና የፖሊስ መርማሪዎች ጭካኔና አስገዳጅነት የተሞላበትን በቪዲዮ የተቀረጸ ቃለ መጠይቅ ያለበት የምርመራ ውጤት ማስቀረት አይፈልጉም፡፡ የውስጥ አዋቂ ምንጭች ተጠርጣሪው ወጣት እጆቹን በካቴና ታስሮ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ መደነቃቸውን ይገልጻሉ፡፡ እጁን በካቴና ታስሮ ለአንድ ከፍተኛ የፖሊስ ባለስልጣን ቃለመጠይቅ የሚሰጥ ተጠርጣሪ የጥያቄና መልስ ሂደት በቪዲዮ ቴፕ ተቀርጾ ማየት በጣም አስደንጋጭ ከመሆኑም በላይ እንደ አንዳንድ የውስጥ ምንጮች ተጠርጣሪውን ወጣት በካቴና አስሮ ቃለ መጠየቅ ማድረጉ ለምን እንዳስፈለገ ግልጽ እንዳልሆነ ይናገራሉ፡፡ እንዲሁም የቪዲዮ ቀረጻ ቃለ መጠይቁ መንግስት በተቃዋሚ የፖለቲካ ደርጅቶች ላይ የስነ ልቦና ጦርነት በማካሄድና በማስፈራራት ረገድ ጠቀሜታ ያስገኝለታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ይህ ሁኔታ ተጠርጣሪዎችን በማስፈራራትና በማሸማቀቅ ለተቃዋሚ ኃይሎችና ለአመጸኞች ማዳከሚያ እንዲሆን ታስቦ የተሰራ ነው፡፡ በጥንካሬና በጽናት የተሞሉ ወጣት የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች በማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል መዳፍ ስር ወይም መንጋጋ ከገቡ ፍርሀትና መደናገጥ አንደሚታይባቸው ለሕዝብ ለማሳየት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የተቃዋሚ ድርጀት መሪዎች ማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል ከደረሱ እንደሚሰባበሩ፣ እንደሚደቆሱ፣ እንደሚታኘኩና እንደሚበጣጠሱ የማያዳግም መልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴ ነው፡፡ እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ ከሆነ ተገዶ ማመን አንዳንድ ጊዜ ግለሰቦች ከእስር ቤት ከወጡ በኋላ ሳይወዱ በግድ መንግስትን እንዲደግፉ የሚደረጉበት ዘዴ ነው፡፡

ይህም ሆኖ በቪዲዮ የተቀረጸውን የቃለ መጠይቅ አድራጊውን ሙሉና የተጠርጣሪውን መብት በመጣስ ለእይታ የበቃውን ድራማ መመልከት “በህግ ከለላ በቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎች በፍርድ ቤት ወንጀለኛነታቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ ነጻ ናቸው፣ እንዲሁም ተገደው በእራሳቸው ላይ ምስክርነት አይሰጡም“ የሚለውን ህገመንግስታዊ መብት የጣሰ የማይታመንና አስደንጋጭ ሁኔታ ነው (አንቀጽ 20(3) ፡፡ ቃለ መጠይቅ  አድራጊው የወጣቱን ተጠርጣሪ ህገመንግስታዊ መብት በኮርማ እንደተናደ የሴራሚክ ቁልል ደፍጥጦታል፡፡ ወጣቱ ተጠርጣሪ “ያለመናገር መብት“ እንዳለው በግልጽ የተቀመጠውን ህገመንግስታዊ መብት ቃለ መጠይቅ አድራጊው ከቁብ የቆጠረው  አይመስልም (አንቀጽ 19(2)(5) ፡፡ “በህግ ከለላ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ያለመናገር መብት አላቸው፡፡ በህግ ከለላ በቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎች ተገደው የእምነት ቃል እንዲሰጡ አይደረግም ተገደው የሰጡትም ቃል ለማስረጃነት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በማስገደድ የተገኘ ማንኛውም ማስረጃ በህግ ፊት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡” ቃለ መጠይቁ በሚደረግበት ጊዜ የተጠርጣሪው የህግ ጠበቃ እንዲገኝ አለመደረጉ ቃለ መጠይቅ አድራጊውን የሚያሳስበው አይመስልም (አንቀጽ 20(5)፣ አንቀጽ 21(2) ፡፡ “የተከሰሱ ሰዎች የህግ ጠበቃቸው የመጎብኘትና… ከህግ ጠበቃቸው ጋር የመመካከር መብት አላቸው፡፡“  “ተጠርጥሮ በህግ ከለላ ጥላ ስር የዋለው ተጠርጣሪ ስለቀረበበት ክስ አስቀድሞ በቃለ መጠይቅ አድራጊው አልተገለጸለትም፡፡“ አንቀጽ 20(2) “የተከሰሱ ሰዎች ስለቀረበባቸው ክስ ዝርዝር መረጃ የማግኘት መብታቸው የተጠበቀና ይህም በጽሁፍ ሊደርሳቸው ይገባል፡፡“

ቃለ መጠይቅ አድራጊው ተጠርጣሪውን ከየትኛው የእስልምና እምነት ክፍል እንደሆነ በማስፈራራት መረጃ ለማግኘት ሞክሯል፣ ለማስረዳትም ጥረት አድርጓል፣ አክራሪነት የየትኛው የእስልምና አስተምህሮ እንደሆነና ተጠርጣሪው ይህንን አውግዞ መንግስት የሚፈልገውን እንዲመርጥ በመጠየቅ የተጠርጣሪውን መብት ደፍጥጦታል፡፡ አንቀጽ 27(1)(3) “እያንዳንዱ ሰው የራሱ የእምነት ነጻነት አለው… ይህ መብት ግለሰቡ የመረጠውን ኃይማኖት በግሉ ወይም ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ የመከተልና የማራመድ መብትን ጭምር ያጠቃልላል… (3) ማንም የመረጠውን የራሱን እምነት ለማራመድ የሚያግደው ወይም የሚከለክለው የለም፡፡“ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ለተጠርጣሪው ስለኃይማኖት እንቅስቃሴውና ስለእምነት ምርጫው ሲጠይቅ “ተጠርጣሪው በግል ወይም ከሌሎች ጋር በጋራ በመሆን የመሰብሰብ፣ የጦር መሳሪያ ሳይዙ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግና አቤቱታ የማቅረብ መብት” (አንቀጽ 30(1) እንዳለው የተረዳ አይመስልም፡፡ በአጭሩ ቃለ መጠይቅ አድራጊው የተጠርጣሪውን መብት የደፈጠጠው ህገመንግስቱ ያጎናጸፈውን የኢትዮጵያን ህገመንገስት በመጣስ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለቻቸውን ልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ ደንቦችን በመናድ ጭምር ነው፡፡

ጥፋተኝነትን ለመከላከል የአሜሪካ ህገመንግስት 5ኛ ማሻሻያ

ጥፋተኝነትን መከላከል ወይም ያለመናገር መብት የአሜሪካ ህገ መንግስት ለዜጎቹ ያጎናጸፋቸው ዋነኛ የመብት ስብስቦች ናቸው፡፡ ማንም ሰው “በማንኛውም የወንጀል ጉዳይ ተገዶ ምስክርነት እንዲሰጥ አይደረግም“ በማለት አምስተኛው የአሜሪካ ህገ መንግስት ማሻሻያ ይደነግጋል፡፡ ከእንግሊዝ ተሰደው አሜሪካንን በቅኝ ግዛትነት የያዟት የስነምግባር ሰዎች ናቸው ይህንን የተገበሩት፡፡ ምክንያቱም በእምነታቸው ሰዎች ሲጠየቁ ዝም የማለት ወይም በጌቶቻቸው ስቃይ ተገድደው መልስ ያለመስጠት መብት እንዳላቸው የጸና እምነት ስለነበራቸው ነው፡፡  የበላይ ጠያቂ ጌቶች ብዙውን ጊዜ ደጋጎቹን የእምነት ሰዎች የያዙት እምነት ምን እንደሆነ እንዲያምኑ ያስገድዷቸውና ያሰቃዩአቸው ነበር፡፡ ዝም ካሉና ካልተናገሩ ጥፋተኛ ብለው ይፈርጇቸው ነበር፡፡ የእንግሊዝ ህግ በ1600ዎቹ አጋማሽ ጥፋተኝነትን የመከላከል መብት ለዜጎቹ አጎናጽፏል፡፡

ይህ እራስን ከጥፋተኝነት የመከላከል የተቀደሰ መብት የአሜሪካ የወንጀል መከላከል ህግ መሰረት ነው – ማንም የተከሰሰ ሰው ጥፋተኝነቱ ባስተማማኝ ሁኔታ ከጥርጣሬ ባለፈ መልኩ በመንግስት እስካልተረጋገጠ ድረስ ነጻ ነው፡፡ ጥፋተኛ መሆን አለመሆኑን የማረጋገጡ ተግባር ደግሞ የመንግስት፣ የአቃቢያን ህግና የፖሊስ ነው፡፡ የተከሰሰን ሰው ጥፋተኝነት ለማረጋጥ የተከሰሰው ግለሰብ ምንም ነገር ማድረግ የለበትም፣ በተለይም ከፖሊስ ወይም ከአቃቤ ህግ ጋር መነጋገር ወይም መተባበር ግዴታ የለበትም፡፡ የአሜሪካ ኮንግረስ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የአሜሪካ ፕሬዚዳንትም ሆነ የአካባቢ ፖሊስ የአሜሪካንን ዜጋ በማስገደድ ለጥፋተኝነታቸው ማስረጃ የሚሆኑ መግለጫዎችን እንዲሰጥ/እንዳይሰጥ  ወይም እንዲያምን/እንዳያምን ማድረግ አይችሉም፡፡

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርደ ቤት የፖሊስን አስገዳጂ የምርመራ ቃለ መጠይቅ ተግባር ያቆመው እ.ኤ.አ. በ1966 ነው፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ “በፖሊስ ምርመራ ጊዜ የህግ መብት ማስጠንቀቂያ“ ለተባለ ቀላል የአሰራር ሂደት ኃላፊነት ሰጥቷል፡፡ በተግባር ሲታይ ይህ የፖሊስ ምርመራ የህግ መብት ፖሊስ ምርመራ ሊያደርግ በሚፈልግበት ጊዜ ተጠርጣሪውን/ዋን በቢሮው ወይም የተጠርጣሪውን/ዋን ነጻነት ሊያውክ በማይችል ሁኔታ መሆን እንዳለበት፣ ተከሳሹ/ሿ ዝም የማለት መብት እንዳላቸው፣ በተጠርጣሪው/ዋ የተሰጠው ምስክርነት ለተጠርጣሪው/ዋ ማስረጃነት ሊውል እንደሚችል፣ተጠርጣሪው/ዋ ከመጠየቁ/ቋ በፊት ከህግ አማካሪው/ዋ ጋር የመምከር መብት እንዳለው/ላት እና ተጠርጣሪው/ዋ የህግ ጠበቃ ለማቆም አቅም ከሌለው/ላት መንግስት ምርመራ ከመጀመሩ በፊት ጠበቃ እንደሚያቆም በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ ሆኖም ግን ድርጊቱ ሆን ተብሎ በማወቅ የተፈጸመ ከሆነ፣ ወይም ከስለላ ስራ ጋር የተያያዘ ከሆነ፣ ወይም አንድን ዓላማ ለማሳካት መሰረት አድርጎ የተፈጸመ ከሆነ ወይም በፖሊስ ህገወጥ የምርመራ ዘዴ የተገኘ መረጃ ከሆነ እራስን ከጥፋተኝነት የመከላከል መብት ወይም የህግ የምክር አግልግሎት የማግኘት መብትን ያስነሳል፡፡ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህን “ሚራንዳህ ወይም በፖሊስ ምርመራ ጊዜ የህግ መብት በቀን ተቀን የፖሊስ ምርመራ ተግባራት ሁሉ እንዲካተት አውጇል፣ ማስጠንቀቂያዎቹም አገር አቀፋዊ ባህል ሆነው እስኪሰርጹ ድረስ ይሰራል”፡፡

በአሜሪካ ህገ መንግስት አምስተኛ ማሻሻያ የተሰጠውን እራስን ከጥፋተኝነት የመከላከል መብት መከላከል እንድችል የህግ ባለሙያነቴ የሰጠኝ መብት በኩራት እንድሞላ አድል ደርሶኛል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1998 በህዝብና በፒቪ መካከል በነበረው ጉዳይ የሚራንዳህ የህግ ስርዓት ታስቦበትና ሆን ተብሎ የምስክርነት ማስረጃው (ጥፋተኝነትን አስገደድዶ መቀበል፣ በግዳጅ ማሳመን) በመጣሱ በካሊፎርኒያ ግዛት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቤ ሽንጤን ገትሬ በመከራከር ማስቀየር በመቻሌ ልዩ ክብርና ሞገስ ይሰማኛል፡፡ በዚያን ወቅት በካሊፎርኒያ ግዛት በሚገኙ የፖሊስ መምሪያዎች ተጠርጣሪዎች በምርመራ ጊዜ ያለመናገርና የህግ ባለሙያ የማናገር መብት እንዳላቸው እየታወቀ ፖሊስ አፋጥጦ በመጠየቅ መረጃን የማግኘት ጥረቱ በጊዜው በነበረው አሰራር ተቀባይነት ነበረው፡፡ ይህ በተወሰኑ የፖሊስና አቃብያነ ህጎች ክልል ወስጥ ይደረግ የነበረው ህገወጥ የአጠያየቅ ስርዓት “ከሚራንዳህ ህግ ውጭ” በመባል ይታወቅ ነበር፡፡

በካሊፎርኒያ ግዛት በፒቪ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት “ከሚራንዳህ ምርመራ ውጭ“ የሚደረግ የምርመራ አሰራር በፍፁም አንዲቆም ተደረገ፡፡ እ.ኤ.አ. በ2000 ዘጠነኛው የተዘዋዋሪ ችሎት በሲኤሲጀ እና በሳንታ ሞኒካ ከተማ ተካሂዶ ተጠርጣሪዎች በምርመራ ጊዜ ያለመናገር መብት እንዳላቸው እየታወቀ ይህንን ጥሰው ከሚራንዳህ የምርመራ ህግ ውጭ አስገድዶ ለማሳመን እና ጥፋተኝነትን እንዲቀበሉ ብለው የሚፈጽሙ ፖሊሶች በህገ መንግስቱና በሲቪል ህዝቡ ላይ ለሚያደርሱት ጉዳት በግል ተጠያቂና ተከሳሽ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡

በማስገደድና በማሰቃየት የተገኘ የእምነት ቃል ፍትሀዊም ተዓማኒነትም የለውም

በወንጀል መከላከል ህግ ተጠርጣሪውን/ዋን አስገድዶ በማሳመን ጥፋተኛ በማድረግ የተገኘ መረጃን ያህል ትኩረትን የሚስብ ነገር የለም፡፡ ፖሊስ ምርመራ የሚያደርግበት ዋና ዓላማ እውነታው ላይ ለመድረስ ወይም ተጠርጣሪው ነጻ መሆኑን ለማረጋገጥ አይደለም፡፡ ብቸኛውና ዋናው ዓላማ የጥፋተኝነት መግለጫዎችን እና የእምነት ቃል ከተጠርጣሪው አንደበት ለመስማትና ይህንን መሰረት በማድረግ በተከሳሹ/ሿ ላይ ክስ ለመመስረት እንዲቻል ነው፡፡ በማስገደድ የፖሊስ ምርመራ ሂደት ጊዜ ተጠርጣሪው ከጥፋተኝነት ነጻ መሆኑን በራሱ አንደበት መግለጽ ይጠበቅበታል፣ ወይም ደግሞ ጥፋተኛ ተብሎ እንዲወሰንበት መንግስትን በማገዝ መተባበር ይጠበቅበታል፡፡ “የፖሊስ የበላይነት” በተንሰራፋበት አካባቢ እራስን ጥፋተኛ አድርጎ ማቅረብ ሜዳውን ለእብሪተኛና ለመሰሪ ፖሊሶች ምርመራ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ዜጎችን ለፍትህ እጦት ሰለባ ያደርጋል፡፡

የተጠርጣሪው ወይም የተከሳሹ በፖሊስ ምርመራ ሂደት ዝም የማለት መብት የጥፋተኝነትና የቅጣት ሰለባ ለማድረግ ከሚደረገው ጥረት አንጻር ብዙ አሳማኝ ምክንያቶች አሉ፡፡ ዋናው ጠቃሚ ነገር ፍትሀዊነት ነው፡፡ በሙያው የሰለጠነ የምርመራ ፖሊስ የህግ ጥሰት ፈጽሟል ባለው ተጠርጣሪ ዜጋ ላይ ጥያቄዎችን እንዲያቀርብ በመፍቀድ የግዳጅ የእምነት ቃል ማግኘት በምንም መልኩ ፍተሀዊነትን አያሳይም፡፡ የማስገደድ የምርመራ ዘዴ ፍትሀዊነት በጎደለው መልኩ ሕገመንግስታዊ የማስረጃ ማቅረብን ግዴታ ከመንግስት ከሳሽ አጅ ወደ ተጠርጣሪው እንዲዞር ያደርጋል፡፡ ተጠርጣሪው ፍትህን በአግባቡ ማግኘት እንዲችል ከተፈለገ በፖሊስ የምርመራ ሂደት ጊዜ ተጠርጣሪው የምክር አግልግሎት እንዲያገኝ የህግ ባለሙያ እንዲያገኝ የማድረጉ ሂደት ጠቃሚነቱ የጎላ ነው፡፡ የተጠርጣሪውን የህግ ጉዳይ ፍሬ ነገሩን የተጠርጣሪው የህግ አማካሪ ሳያየው ተጠርጣሪውን ወይም ተከሳሹን በፖሊስ እንዲመረመር ማስገደድ ተገቢነት የለውም፡፡ ለማንኛውም የምርመራ ጥያቄ ተጠርጣሪው ምን መልስ መስጠት እንዳለበትና መልስ መስጠት የሌለባቸውን ጉዳዮች  የህግ ባለሙያው ካጠናው በኋላ  የተጠርጣሪው የህግ አማካሪ መንግስት ምን መረጃ እንደሚፈልግና ምን መከላከያ ማስረጃዎች እንዳሉ ማወቅ አለበት፡፡

በማሰቃየት ወይም ማንኛውንም የሰብአዊ መብት ረገጣ ዘዴዎች በመጠቀም የተገኘ የእምነት ቃል በምንም ዓይነት ሁኔታ አስተማማኝ መረጃ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ተጠርጣሪዎች በመርማሪ ፖሊሶች የሚደርስባቸውን የአካልና የአዕምሮ ስነ ልቦና ስቃይ ለማቆም ሲሉ ያልሰሩትን ነገር እንደሰሩ አድርገው የእምነት ቃል ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ምግብ፣ ውኃና የመኝታ አገልግሎት የተነፈጉ ተጠርጣሪዎች ግራ በመጋባትና ስቃዩን በማስቀረት መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት ሲሉ የእምነት ቃል ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ነጻ የሆኑ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ምርመራ ጊዜ ሲጠየቁ ከክሱ ነጻ የሚያወጣቸው እየመሰላቸው ስለእውነት ብቻ ይናገራሉ፡፡ በመሰሪ ፖሊሶች የሚዘረጉላቸውን አሽክላዎች አይገነዘቡም፡፡ እውነቱን መናገር ነጻ የሚያደርጋቸው ይመስላቸዋል፣ ሆኖም ግን ብዙውን ጊዜ እውነታው በተቃራኒው በሰለጠኑ የፖሊስ መርማሪዎች ተጠምዝዞና ተፐውዞ ተጠርጣሪውን ለማዳካም ሲባል ፖሊስ አደናጋሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ፣ በማስፈራራት፣ በመዛትና በማታለል ዓላማውን ለማሳካት ጥረት ያደርጋል፡፡ ነጻ የሆኑ ሰዎች የማያቋርጥ ለሰዓታት የዘለቀ የፖሊስ ምርመራ ከተደረገ በኋላ ያልሰሩትን ወንጀል እንደሰሩ (የሀሰት የእምነት ቃል) የሚያያረጋግጡ ብዙ ማህበራዊና ሳይንሳዊ ጥናቶች አሉ፡፡ በፖሊስ ምርመራ ጊዜ የተጠርጣሪው ዝምታ በዓለም ላይ ከወርቅ፣ ፕላቲኒየም፣ የተከበረ ድንጋይ ወይም አልማዝ የበለጠ ዋጋ አለው፡፡

ማስመሰል ለምን? ጨካኔንና ተያቂ አልባነትን መፍጠር

በ15ኛው ክፍለ ዘመን በእንግሊዝ አገር በተራ ፍርድ ቤቶች ሊከሰሱ የማይችሉና በጣም ታዋቂ የሆኑ ሰዎችን ጉዳይ የሚያይ ተጠያቂነት የሌለው ፍርድ ቤት (በፍርድ ቤቱ ጣሪያ ላይ የኮከብ ምልክት ያለበት) ተመሰረተ፡፡ ይህ ፍርድ ቤት በሚስጥርና የህግ ሂደትን ሳይከተል ምስክሮቸን ሳይሰማ ብይን ይሰጥ ነበር፡፡ በመጨረሻም ንጉሱ ይህን ተጠያቂነት የሌለው ፍርድ ቤት ተፎካካሪያቸውን፣ ተቃዋሚዎቻቸውን እና ትችት የሚያቀርቡባቸውን አካላት ጸጥ ለማድረግና ለማስወገድ ሲሉ ወደ ማጥቂያ ህጋዊ መሳሪያነት አሸጋገሩት፡፡ ገዥው የኢትዮጵያ አስተዳደርም እንደዚሁ በተመሳሳይ መልኩ የራሱን ተጠያቂ አልባ የፔንታጎን ቅርጽ ያለው ፍርድ ቤት በማቋቋምና በጣራው ላይ የኮከብ ምልክት ያለበትን ባንዲራ በመስቀል ስራውን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ 

ህግ የማያከብር መንግስት የማስገደድ እምነት፣ ለህግ ንቀትን የሚፈለፍል ገዥ

የራሱን ህገመንግስት መረን በለቀቀ አኳኋን የሚደፈጥጠውን አገዛዝ ሁኔታ ሁልጊዜ ባሰብኩ ቁጥር እንቆቅልሽ ይሆንብኛል፡፡ ሁልጊዜ ህገመንግስታችን እየተባለ በመንግስት መሪዎች የሚለፈፈው እርባናየለሽ ዲስኩር ከማሳቁም በላይ ምንም እውቀቱ ሳይኖረው ከቅዳሳን መጽሐፍት እየጠቀሰ የሚያነበንበውን የኃይማኖት ደቀመዝሙር እና  ምን እንደሚልና ምን እንደሚያደርግ ትርጉም ያለው እውቀት ሳይኖረው በዘልማድ ባህላዊ ባላትን ለማክበር ሽርጉድ የሚለውን ባተሌ እንዳስታውስ ያደርገኛል፡፡ “ሰይጣን ለዓላማው ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል“ የሚለውን የሸክስፒርን ስንኝ እንዳስታውስም ያደርገኛል፡፡ የስርዓቱ ገዥዎች ህገመንግስቱን ከአደጋና ከተቃዋሚዎች ጥቃት ለመጠበቅ ከነፋስ የፈጠኑ ናቸው፣ የራሳቸውን ህገመንግስት እራሳቸው በመጣስ ዋጋውን እንዲሚያሳንሱት በውል የተረዱት አይመስልም፡፡ ለዓመታት ደጋግሜ እንደተናገርኩት ለኢትዮጵያ መንግስት መሪዎች ስለህገ መንግስት ወይም የህግ የበላይነትን መስበክ ለተሰበሰቡ አረማውያን (አህዛብ) መጽሐፍ ቅዱስን እንደመስበክ ወይም በጥቁረር ባልጩት ድንጋይ ላይ ውኃ እንደማፍሰስ ይቆጠራል፡፡ በቅርቡ የወጣው የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ ገዥው ስርዓት ስለ የህግ የበላይነት ያለውን ጥልቅ ንቀት በጉልህ ያሳያል፡፡

በአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሚገኙ ታላላቅ የህግ ዳኞች አንዱ የሆኑት ሌውስ ብራንዴስ እንዳመለከቱት “ህግ ባለበት መንግስት አገር መንግስት ጥንቃቄ በተመላበት ሁኔታ የህግ ጥበቃ ካላደረግ የመንግስት ህልውና አደጋ ውስጥ ይወድቃል፡፡ መንግስታችን ጠንካራና በየትም ቦታ የሚገኝ መምህር ነው፡፡ ለጥሩም ሆነ ለመጥፎ ነገር እራሱን ምሳሌ አድርጎ ለህዝቡ ያስተምራል፡፡  ወንጅል ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ መንግስት እራሱ ህግ የሚጥስ ከሆነ ለህግ ያለውን ንቀት ይፈለፍላል፣ እያንዳንዱ ዜጋ እስከ እራሱ ድረስ ህግ እንዲጥስ ይጋብዘዋል፣ ስርዓተ አልበኝነት እንዲነግስ ይገፋፋል፡፡ የወንጀል ህግን ከማስተዳደር አንጻር ዓላማው ፍጻሜውን ሊያሳምር ይገባል፡፡ የግል ወንጀለኛን ለመዳኘት ሲል መንግስት እራሱ ወንጀልን የሚፈጽም ከሆነ አደገኛ በቀልተኝነት ይሆናል፡፡“ ብራንዴስ “በመንግስት በኩል የግል የስልክ መስመሮችን በመጥለፍ የስለላ ስራ በማካሄድ የእራስን የጥፋተኝነት መረጃ ለማቅረብ የሚደረግ አሰራር ህገወጥ ነው“ በማለት ሀሳባቸውን ቋጭተዋል፡፡

ገዥው አስተዳደር ህግን የሚጥስ ከሆነ ምን መደረግ አለበት? ህገመንግስት ደፍጣጭ ሲሆን? ገዥው አስተዳደር ለህግ የማይገዛ ወንበዴ ከሆነ ምን መደረግ አለበት? ህግን የማያከብርና የሚደፈጥጥ ገዥ አስተዳደር ህግን በሚያከብር መንግስት መተካት አለበት፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ መንግስት ይቃወሙኛል የሚላቸውን ከህግ ውጭ እያስገደደና እያሰቃየ በማሳመን የሚያገኘው የእምነት ቃል ሳያውቀውና ሳይገነዘበው ቀስ በቀስ እራሱ ህግ አልባ ለመሆኑ የእምነት ቃል መስጠቱን ይመሰክርበታል፡፡

“ጤናማ ሰው ሌሎቹን አያሰቃይም- በአጠቃላይ ሲሰቃዩ የነበሩ  ወደ  አሰቃይነት ይቀየራሉ፡፡”    ካርል ጁንግ

http://ethiopianreview.com/ethiopia/

posted by Tseday Getachew

 

 

የሌለውን ፍለጋ (ክፍል አንድ)

ዳንኤል ክብረት
ተስፋዬ ገብረአብ “የስደተኛው ማስታወሻ” የተሰኘ መጽሐፍ ማውጣቱንና ባነበው መልካም እንደሆነ ገልጦ አንድ ወዳጄ “ስስ ቅጅውን” ከሀገረ አሜሪካ ላከልኝ። ከዚህ በፊት ሌሎች መጻሕፍቱን አንብቤያቸዋለሁ፤ በአጻጻፍ ችሎታው የምደሰተውን ያህል እንደ አበሻ መድኃኒት ነገሩን ሁሉ እርሱ ብቻ የሚያውቀው ምስጢር ስለሚያደርገው፤ በአንዳንድ ጉዳዮችም ሆን ብሎም ሊያናጋቸው የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ እሴቶች ያሉ ስለሚመስለኝ፤ ተስፋዬ ለምን እንደዚህ ይጽፋል? እያልኩ የምጠይቃቸው ነገሮች ነበሩ።

 

በዚህ መጽሐፉ ውስጥም ያንን ጥርጣሬየን አጉልቶ ሥጋ ነሥቶ እንዳየው የሚያደርገኝ ነገር ገጠመኝ። ተስፋዬ በገጽ 306 ላይ “”የፍስሐ ጽዮን ፖለቲካ” በሚል ርእስ ስለ አቡነ ተክለ ኃይማኖት የማያውቀውን ነገር ጽፏል። ስለማያውቀው ነገር የጻፈው ባለማወቁ ብቻ አይመስለኝም። አንድም ለማወቅ ባለመፈለጉ፣ አለያም ሆን ብሎ የማፍረስ ዓላማ ይዞ ይመስለኛል።

ይህን የምለው በሁለት ምክንያት ነው። ተስፋዬ ስለ አቡነ ተክለ ኃይማኖት ለመጻፍ ሲፈልግ ሊያነባቸው የሚችላቸው መጻሕፍት በምድረ አውሮፓ እንደ ማክዶናልድ በዝተው ሞልተው ይገኛሉ። አብዛኞቹ ደግሞ ኢትዮጵያውያን ባልሆኑ ሰዎች የተጻፉ ናቸው። ሌላው ቢቀር ኤንሪኮ ቼሩሊ የደብረ ሊባኖስ አበ ምኔቶች ታሪክ (Gli Abbati di Dabra Libanos, 1945)፣ ኮንቲ ሮሲኒ ከሐተታ ጋር ያሳተመውን ገድለ አቡነ ተክለ ኃይማኖት፣በዋልድባ ቅጅ (Il Gadla Takla Haimanot secondo la redazione Waldebbana, 1896)፣ የዊልያም በጅን የአቡነ ተክለ ኃይማኖት ሕይወትና ተአምር (The Life and Miracles of Takla Haymanot, 1906)። ከኢትዮጵያውያን ጸሐፍትም ውስጥ የታደሰ ታምራትን Church and State in Ethiopia, ማንበብ በተገባው ነበር።

 

 

Share

የስደተኛው ማስታወሻ በተስፋዬ ገብረአብ Yesedetegnaw Mestawesha by Tesfaye Gebreab

ከዚህም ዘልሎ ጥልቅ ጥናት አድርጌ ደረቴን ነፍቼ እናገራለሁ ለሚል ደግሞ እንግሊዝ ምቹ ናትና ሎንዶን ወደሚገኘው ብሪቲሽ ሙዝየም ሄዶ በማይክሮ ፊልም የተነሡትንም ሆነ በአካል ያሉትን ብራናዎች ማየት ነው። እዚያም የማያደርሰው ከሆነ በዋና ከተማው በሆላንድ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙትን የጌታቸው ኃይሌን THE MONASTIC GENEALOGY OF THE LINE OF TÄKLÄ HAYMANOT OF SHOA, (Rassegna di Studi Etiopici, Vol. 29 (1982-1983), pp. 7-38)፤ የተስፋዬ ገብረ ማርያምን A Structural Analysis of Gädlä Täklä Haymanot (African Languages and Cultures, Vol. 10, No. 2 (1997), pp. 181-198)፤ የሐንቲንግ ፎርድን (G.W.B. Huntingford, “The Lives of Saint Takla Haymanot,” Journal of Ethiopian Studies, 4 (1966), 34-35.) የአሉላ ፓንክረስትን Dabra Libanos Pilgrimage Past and Present, The Mytery of the Bones and the Legend of Saint Takla Haymanot, (the sociology ethnology Bulletin) 1,3 (1994), P. 14-26 ጥናቶችን ማየት ይቻል ነበር። ያም ካልሆነ ወደ ቤልጅየም ሄዶ ፒተርስ አሳታሚ ከጥልቅ ጥናት ጋር የሚያሳትማቸውን የኢትዮጵያ ጥንታዊ መዛግብት ኅትመቶች ማገለባጥ ይቻል ነበር።

የገረመኝ ገድለ ተክለ ኃይማኖትን ያህል በኢትዮጵያ ታሪክ (History)ና የታሪክ አጻጻፍ (Historiography) ታላቅ ቦታ ያለው፣ በኢትዮጵያ ገድላት ጥናት (Hagiography) ቀዳሚ የሆነና በብዙ አጥኝዎች የተጠና ጉዳይ ያለ ምንም በቂ ማስረጃ አፈርሳለሁ ብሎ መነሣቱ ነው። ይኼ ደግሞ ከማይወጣበት የክርክር አዘቅት ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል።

 

ተስፋዬ ጽሑፉን የጀመረው በስድብ ነው። ኤርትራዊት እናቱ “ይዘምሩት ነበር” ብሎ ያቀረበው ጽሑፍ የራሱን ስድብ በእናቱ ያሳበበበት ነው። የኤርትራን ቤተ ክርስቲያንና ኤርትራውያን ክርስቲያን እናቶችን ከእርሱ በላይ አውቃቸዋለሁ። ተሰድደው በየሀገሩ ከተበተኑት ጋር አብረን ቋንቋና ድንበር ሳያግደን አገልግለናል። አሥመራ ከተማ ከሚገኙት ታላላቅ አድባራት አንዱም የአቡነ ተክለ ኃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ነው። በምንም መልኩ አንዲት ኤርትራዊት እናት ተስፋዬ በአቡነ ተክለ ኃይማኖት ላይ የተሳለቀውን “መዝሙር” አትዘምርም፤ አቡነ ተክለ ኃይማኖት ደማቸው የፈሰሰው ሰባት ዓመት ሙሉ ለጸሎት የቆሙበት እግራቸው በጸሎት ብዛት በመቆረጡ እንጂ ሰይጣን “ፈንግሏቸው” አለመሆኑን ኤርትራውያን እናቶች በሚገባ ያውቁታል። የሚገርመው ነገር ተስፋዬ በጆሮ ጠገብ የሆነ ቦታ የሰማውን መዝሙር አጣምሞት እንጂ መዝሙሩ እንዲህ አይደለም።

“ተክለ ኃይማኖት የዓለም ብርሃን ናቸው

ይኼው ለዘላለም ያበራል ገድላቸው” ነው የሚለው።

ተስፋዬ አቡነ ተክለ ኃይማኖትን በተመለከተ አነበብኳቸው የሚለን አምስት መጻሕፍትን ነው። የአባ ዮሐንስ ከማ፣ የኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ የጽጌ ስጦታው፣ የዳኛቸው ወርቁና የኢረይን ሙራይ። አባ ዮሐንስ ከማን እንደማያውቃቸው፣ የጻፉትንም ገድል እንዳላነበበ የሚያሳብቅበት “ደብተራ” ሲላቸው ነው። አባ ዮሐንስ ከማ ሰባተኛው የደብረ ሊባኖስ እጨጌ እንጂ ደብተራ አልነበሩም። በዚያ ዘመን “ደብተራ” ማለት የንጉሡን ደብር (ድንኳን) የሚያገለግሉት ካህናት ናቸው። አባ ዮሐንስ ከማ በዐፄ ይስሐቅ (1407-1423)ዘመንና በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ (1437-1461)የመጀመሪያዎቹ ዓመታት የነበሩ ደብረ ሊባኖስን እንደገና ያሳነጹ ገድለ ተክለ ኃይማኖትንም ያስጻፉ አባት ናቸው። ተስፋዬ አባ ዮሐንስ ከማ ከ200 ዓመታት ቆይታ በኋላ ስለ ጻፉ ተሳስተዋል ይላል። ባታውቀው ነው እንጂ ሙሴ ኦሪትን የጻፈው ዓለም ከተፈጠረ ከሺዎች ዓመታት በኋላ ነው። በቤተ ክርስቲያን ገድሎች ዘግይተው የሚጻፉት የአንድን ቅዱስ ቅድስና ለመመስከር ካረፈ ቢያንስ ግማሽ ምእተ ዓመት ስለሚያስፈልገው ነው። በመቃብሩ ላይ የሚሠሩት ተአምራት፣ በአማላጅነቱ የሚሠራቸው ተአምራትና ሌሎችም መታየት አለባቸው።

ተስፋዬ አላዋቂነቱን እንደ ዕውቀት ስለወሰደው እንጂ የአቡነ ዮሐንስ ከማ ገድል የመጀመሪያው የአቡነ ተክለ ኃይማኖት ገድል አይደለም። በነገራችን ላይ ስለ አቡነ ተክለ ኃይማኖት አራት ቀደምት ሰዎች ጽፈዋል። 1)በስንክሳር ተጽፎ የሚገኘው (በተለይም በፓሪሱ ስንክሳር) አጭር የአቡነ ተክለ ኃይማኖት ታሪክ፣ 2) የትግራይ ተወላጅ በሆነው በተክለ ጽዮን የተጻፈው የዋልድባው ገድለ ተክለ ኃይማኖት [አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ የአቡነ ተክለ ኃይማኖት (በቆብ) የልጅ ልጅ ናቸው። አቡነ ተክለ ኃይማኖት አቡነ መድኃኒነ እግዚእን ሲያመነኩሱ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደግሞ ሰባቱ ከዋክብት የተባሉትንና በጣና ዙሪያ የሰበኩትን (አቡነ ዮሐንስ ዘቁየጻ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘጣሬጣ፣ አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ዮሐንስ ዘጉራንቋ፣ አቡነ ታዴዎስ ዘባልተዋርና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን) ሲያመነኩሱ ነው ምንኩስናን ተቀብለው ለተልዕኮ የተሰማሩት። ለዚህም ነው የአቡነ ተክለ ኃይማኖትን ገድል ዋልድባዎች የጻፉት።] 3)ያልታወቀ ጸሐፊ አጭሩንና የሐይቅ እስጢፋኖስ ቅጅ የሚባለውን ጽፏል። ይኼኛው ገድል ቀዳሚ ሳይሆን አይቀርም፤ አንደኛ የተጻፈው ከሌሎች ቅዱሳን ገድሎች ጋር እስትግቡእ ሆኖ በስንክሳር መልክ ነው። ሁለተኛ የተጠቀማቸው አማርኛዎች በአሁኑ ጊዜ ጥቅም ላይ የሌሉ ዓይነት ናቸው፣ 4)አቡነ ዮሐንስ ከማ የጻፈው የደብረ ሊባኖስ ቅጅ ናቸው።

ይህ የአቡነ ዮሐንስ ከማ ገድል ምናልባት ከ1418-19 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ በዐፄ ይስሐቅ ዘመን የተጻፈ መሆኑ ይገመታል (Encyclopedia Aethiopica, Vol. IV, P. 832) በግብጽ ቤተ ክርስቲያን የሚገኘው ዐረብኛው ገድል በዐፄ ገላውዴዎስ ዘመን (1533-1551) የተጻፈ ይመስላል (Encyclopedia Aethiopica,Vol.IV, P.832)። ያልተመዘገቡ አያሌ ገድላት በየገዳማቱ መኖራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ 22 የብራና ገድሎች በአውሮፓ፣ 20 በኢትዮጵያ የማኑስክሪፕት ቤተ መጻፍት (EMML)፣ 3 በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት፣ 5 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም የአቡነ ተክለ ኃይማኖት ገድሎች ይገኛሉ። በአንድ ቅዱስ ላይ የተለያዩ ቅጅዎች መገኘታቸው መረጃዎችን ያሰፋቸዋል እንጂ ጉዳት የለውም። ስለ አንድ ክርስቶስ አራት ዓይነት ወንጌሎች መጻፋቸውን ማስታወስ ይበቃል።

አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በብዙ ሥራዎቻቸው የተከበሩና የተመሰገኑ ሊቅ ናቸው። አቡነ ተክለ ኃይማኖትን በተመለከተ ላነሡት ሃሳብ ግን ያቀረቡት ማስረጃ የላቸውም። ከኢትዮጵያ ገድሎች ሁሉ የአቡነ ተክለ ኃይማኖትን ገድል ያህል የሚታወቅና የተጠና የለም። ከሌሎች ጋር እየተነጻጸረም ሆነ በራሱ (Textual analysis) ገድለ ተክለ ኃይማኖት በአውሮፓውያንም ሆነ በኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ተጠንቷል። እስካሁን ግን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም ሆኑ ሌሎች የሚሉት “ሌላ ገድል” አልተገኘም። አለቃም ያነበቡት ከሆነ ያነበቡትን፣ ያገኙት ከሆነም ያገኙበትን አልነገሩንም። ምንጭ የላቸውምና ለታሪክ ክርክር ሊጠቀሱ አይችሉም።

ጽጌ ስጦታውም ቢሆን ምናቡንና አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌን ጠቀሰ እንጂ አለ የሚለውን “የዚያኛውን ተክለ ኃይማኖት” ገድል ሊያመጣልን አልቻለም። ዳኛቸው ወርቁ የጻፈው ልቦለድ እንጂ ታሪካዊ ዋጋ ያለው ነገር ስላልሆነ ለክርክር የሚቀርብ አይደለም። ይባስ ብሎ ተስፋዬ ኢለይን ሙራይ ለልጆች ብላ የጻፈችውን ተረት ጠቅሶልናል። ይህ ነገር የቦሩ ሜዳን ክርክር ነው ያስታወሰኝ።

በቦሩ ሜዳ ክርክር “ለኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ልደት አለው” የሚሉና “ሦስት ልደት አለው” የሚሉ ሊቃውንት ተከራክረው ነበር። በዚህ ክርክር የሁለት ልደትን ወክለው ከተከራከሩት መካከል የነበሩት መልከአ ብርሃን ወልደ ዮሐንስ “ነአምን ክልኤተ ልደታተ” የሚል ንባብ ከሊቃውንት መጽሐፍ ጠቅሰው ተከራከሩ። ዐፄ ዮሐንስም የሦስት ልደቶችን ተከራካሪ አለቃ ሥነ ጊዮርጊስን “በል አንተም እንደ እርሱ ከሊቃውንት መጽሐፍ ሦስት ልደት የሚል ንባብ አምጣ” አሉት በዚህ ጊዜ አለቃ ሥነ ጊዮርጊስ “በደብረ ብርሃን ተአምረ ማርያም ይገኛል” አሉ። በዚህ ጊዜ ንጉሡ “ከምታስተምረው ከአራቱ ጉባኤ አጣህና ነው ከተአምረ ማርያም ትጠቅሳለህ”” ቢሏቸው ” ከጉባኤው መጽሐፍስ የለም”” አሉ ይባላል።

የተስፋዬ አጠቃቀስ ከዚህም የወረደ ነው። አለቃ ሥነ ጊዮርጊስ የተወቀሱት ለእምነት ክርክር የማይጠቀስ የተአምር መጽሐፍ በመጥቀሳቸው ነው። ተስፋዬም ከዚያ ወርዶ ወርዶ ለታሪክ ክርክር የማይጠቀስ የተረትና የልቦለድ መጽሐፍ ሲጠቅስ ይገኛል።

ተስፋዬ ወግዳ የተሸሸገ ለሕዝብ የማይቀርብ ገድለ ተክለ ኃይማኖት አለ ይላል። በሀገራችን ጠንቋይ እንዳይጋለጥ ሲፈልግ የሌለ ነገር ያዝዛል ይባላል። ተስፋዬም ወግዳ የተደበቀ ገድል አለ አለ። ወግዳ በሰሜን ሸዋ በደብረ ብርሃን ዙሪያ ወረዳ ሥር የሚገኝ ቦታ ነው። የኢትዮጵያ የብራና መጻሕፍት በ1964 ዓም ማይክሮ ፊልም መነሣት ሲጀምሩ ከሰሜን ሸዋ ነበር የተጀመረው። እነ ሥርግው ሐብለ ሥላሴ (አጥንታቸውን ያለምልመው እንጂ) እያንዳንዷን ወረዳ ለቅመው አንሥተውታል። እንኳን በገዳማት አድባራት የሚገኙት በግለሰቦች እጅ የሚገኙትም አልቀሯቸውም። እንኳን የቤተ ክርስቲያኒቱ መጽሐፍ የሕንድ፣ የግሪክ መጻሕፍት አልቀራቸውም፤ እንኳን ገድልና ተአምር የቤተ ክርስቲያንን እምነት የሚቃረኑ መጻሕፍት በክብር ተጠብቀው ነው የተገኙት። ተስፋዬ ወግዳ የማይደረስበት መስሎት መደበቂያ ዋሻ አለ ይላል። ወግዳኮ ከአዲስ አበባ የ120 ኪሎ ሜትር ጉዳይ ነው።

በማይክሮ ፊልም ቀረጻው ወቅት በሥራ ላይ የተሠማሩት የሀገሬው ተወላጆች ነበሩና ያስቸገራቸው ነገር አልነበረም። በዚህ ጉዞ ውስጥ ይህ “የወግዳ ገድል” ይገኝ ነበር። ግን የለምና አልተገኘም። ይህ ዓይነት ፕሮፓጋንዳ ዛሬ አልተጀመረም። በትግራይ፣ በወሎ፣ በጎጃም በተክለ ኃይማኖት ስም ስለሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን የተጻፉ ገድሎች አሉ እየተባለ እንዲሁ በአፍ ታሪክ ይነገራል። እስካሁን ግን ማስረጃ አምጥቶ ያረጋገጠ አልተገኘም። የትግራይ ገዳማት የብራና መጻሕፍት በቅርቡ ዲጂታላይዝ ተደርገዋል። ግን የተባለው አልተገኘም። በመካከለኛው ዘመን ሌላው ቀርቶ ከማዕከላዊው መንግሥት ተጋጭተው ርቀው በነበሩት የደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ገዳም በጉንዳ ጉንዲ እንኳን የደብረ ሊባኖሱን ገድል የመሰለ ቅጅ ነው የተገኘው።

ማንኛውም ክርክር ሲቀርብ ለክርክሩ ብቁ የሆነ ማስረጃ መቅረብ አለበት። ልቦለዱንም፣ ቀልዱንም ለታሪክ ማስረጃ መጥቀስ ቧልት እንጂ ቁም ነገር አይሆንም።

ተስፋዬ ስለ አቡነ ተክለ ኃይማኖት የሚባለውን የታወቀ ታሪክ (official history) ለመቀበል አልፈለገም። ያ በራሱ ችግር አይደለም። አዲስ ማስረጃ አምጥቶ ወይም ነባሩን ማስረጃ በክርክር አፍርሶ ያላየነውን ካሳየን እናመሰግነው ነበር። እርሱ ግን ወይ የታወቀውን አልተቀበለ፣ አለያም አዲስ ማስረጃ አላመጣ፣ ከሁለት የወጣ ጎመን ሆነብን።

ሮማውያን የሕግ ሊቃውንት Argumentum ad Contrario የሚል መርሕ ነበራቸው። “አንድን ነገር የታመነውንና የታወቀውን ትተህ በተቃራኒው ያለውን አረጋግጥ” ማለት ነው። ለምሳሌ አቡነ ተክለ ኃይማኖትን በተመለከተ የሚባለውንና የሚታመነውን ተወውና ተቃራኒውን በማስረጃ፣ በተጠየቅና በትንታኔ አረጋግጥ ማለት ነው። ተስፋዬ ይህንን ለማረጋገጥ ዐቅም አላገኘም። እንዲሁ ቧልቱን ብቻ ነገረን።

ተስፋዬ የታሪክ ስሕተቱን የሚጀምረው በሰባተኛው መክዘ ዐፄ ዳዊት የሚባሉ ንጉሥ ኢትዮጵያ ውስጥ ነበሩ ሲለን ነው። ተስፋዬ በቀላሉ የሚገኘውን የሬኔ ባሴን ታሪከ ነገሥት፣ የሥርግው ሐብለ ሥላሴን የነገሥታት ዝርዝር፣ የተክለ ጻድቅ መኩሪያን መጻሕፍት አለያም የብላቴን ጌታ ኅሩይን “ዋዜማ”፣ የጌታቸው ኃይሌን ባሕረ ሐሳብ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1975 አሳትሞት የነበረውን The Dictionary of Ethiopian Biography, ብታይኮ እንዲህ ካለ ስሕተት ውስጥ አትወድቅም ነበር። በኢትዮጵያ ታሪክ ዳዊት በሚል ንጉሥ መጀመሪያ የነገሠው ዐፄ ዳዊት አንደኛ ከ1374-1406 ዓም ነው። ከየት አምጥተህ ነው በሰባተኛው መክዘ ያደረግከው።

እጂግ የሚገርመው ነገር የሀገራችን ሊቃውንት “ጨዋ ደፋር ነው” እንደሚሉት ተስፋዬም ያለ ምን ጥናት፣ ያለ ምንም ማስረጃ እርሱ ራሱም እንደሚለን “ኢትዮጵያ ሳለ የሰማቸውን አፈ ታሪኮች ሰብስቦ” (እኔ ግን አይመስለኝም፣ አሜሪካ ሆኖ ፈጥሮ እንጂ) በድፍረት “ሦስት ተክለ ኃይማኖቶች አሉ ይላል። ቢያንስ ለዕውቀት ክብር ሰጥቶ “ያሉ ይመስለኛል” ቢል እንኳን ምን አለበት። ለካስ እስከዛሬም በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት “የመንግሥት ምሥጢሮች” እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ማለት ነው?

ለመሆኑ ተስፋዬ እናዳለው ሦስት ተክለ ኃይማኖቶች አሉን? ሦስቱስ በገድለ ተክለ ኃይማኖት ተቀላቅለዋልን? ሳምንት እንመለሳለን።


© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ ላይ የወጣ ነው

 

posted by Tseday Getachaw

ተስፋዬ ገብረአብ እና የመከነ ብእሩ፡ ከቡርቃ ዝምታ እስከ የስደተኛው ማስታወሻ – መስፍን አማን (ከሃርለም፣ኔዘርላንድ)

Tesfaye Gebreab Ethiopian author and writer

ተስፋዬ ገብረአብ

ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድ ቅዳሜ ሻይ ቡና ለማለት አምስተርዳም ከወዳጆቼ ጋር በነበረኘ ቀጠሮ ላይ እንደአጋጣሚ ተስፋየም በመሃላችን ተገኝቶ ነበር።የባጥ የቆጡን ስናወራ፣ስለአዲሱ የተፋየ መጽሃፍ አንስቶ የውይይታችንን አቅጣጫ ቀየረው።በመሃሉ ተስፋየ፣ከመጽሃፉ ውስጥ አንዳንድ የማልወዳቸው ምእራፎች ቢኖሩ ትችቶቹን የምቀበል ስለመሆኔ አስረግጦ ጠየቀኝ?።እኔም መጽሃፋን ካነበብኩት በሁዋላ ለጥያቄው መልስ ብሰጥ እንደሚሻል ገልጨለት በዛው ተለያየን። አይደርስ የለም መጽሃፉን ለህዝብ ከመበተኑ በፊት ረቂቁን አነበብኩት። ረቂቁን አንብቤ እንደጨረስኩ ለተስፋየ ጥያቄ መልስ መመለስ እንዳለብ ወሰንኩኝ። ይሁንና በቀድሞው ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ተጽፎ የተሰራጨውን ጽሁፍ መውጣት ተከትሎ በዳያስፖራው አካባቢ አዋራው በመጨሱ ያዘጋጀሁትን ትችት በይደር ለማቆየት ወሰንኩ። በዚህ መሃል ተስፋየ ገብረአብ “የስደተኛው ማሰታወሻ” በማለት ያዘጋጀውን መጽሐፍ ባለፈው ሰሞን በነጻ አሰራጭቶልናል።

ወደ መጽሃፉ ትችት ስመለስ “በደራሲው ማስታወሻ” ውስጥ ያገኘሁት ደራሲ ኢህአዴግን ያገለግል ከነበረው ከቀድሞው ማንነቱ ያልተፋታውን ተስፋየ ገብረአብን ነበር። የእፎይታ መጽሄት ዋና አዘጋጅ እና የቡርቃ ዝምታ ደራሲን የድሮው ተስፋየን በዚህኛው የስነ-ጽሁፍ ስራ ውስጥም ዳግም አገኘሁት።የድሮው ተስፋየ ስል ታዲያ ስነጽሁፍን ለፍቅር፣ለመቻቻል፣እና ለእውቀት ሳይሆን የቆዩና የሻሩ ቁስሎችን መቆስቆሻ፣ያልነበሩትንም በመፍብረክ የእልቂት ነጋሪት መምቻ መሳሪያ አድርጎ የሚጠቀመውን ማለቴ እንደሆነ አንባቢ እንዲያስተውልእፈልጋለሁ።”የስደተኛው ማስታወሻ” የነዛ ስራዎች ቀጣይ እንጂ በይዘቱም ሆነ በመልእክቱ ጭብጥ አዲስ የስነ- ጽሁፍ ስራ ነው ለማለት የማያስደፍሩ የብዙ ምእራፎችን አካቶአል። ለዚህ የማቀርበው ምክንያት ሃያስያኑ እንደሚሉት የገጸ-ባህሪ አሳሳሉና የመልእክቱ ጭብጥ አመራረጥ እንዲሁም እንደ ደራሲ በዋነኝነት ማስተላለፍ በፈለገው መልእክት ላይ ነው።

በእርግጥም አንድ ፀሃፊ መፅሃፍ ሲፅፍ ብዙ አይነት አላማዎችን ይዞ ሊነሳ ይችላል፡፡የሚፈልገውን ሀሳብን እና ዓላማ በስነ-ጽሁፍ መልክ አንባቢውን በማስደመም የእኔ የሚለውን መልእክት ማስተላለፍ ዋነኛ አላማው ሊሆን ይችላል፡፡ሆኖም ከዓላማ ሁሉ ገዝፎ የሚታየውና የመፅሃፉን ዋጋ ከፍ የሚያደርገው ደግሞ መፅሃፉ በህብረተሰቡ ውስጥ ያሳደረው ወይንም ሊያሳድር የሚችለው ዘላቂ የሆነ በጎ ተፅዕኖ እና አዲስ ሃሳብ የማፍለቅ ችሎታው ነው፡፡ አንባቢውም መፅሃፉን ገዝቶ ሲያነብ ከደራሲው አንድ ቁም ነገር መጠበቁ አይቀርም፡፡ እናም የደራሲው ዋና ሚና የሚጠበቀውን አዎንታዊ ተፅእኖ ባማረና በተከሸነ ስነ-ጽሁፍ ለተደራሲው ማድረስ ነው፡፡የተስፋየ ገብረአብ የአሁኑን ስራ ከዚህ አንፃር ስንገመገም የምናገኘው መልእክት ሃሳዊነት እና ትንኮሳ አዘል ስነ-ጽሁፍ መሆኑን ብቻ ነው። በዚህ ፅሁፍ ለማየት የሞከርኩት በሁሉም አይነት መፅሃፍት ውስጥ ለኔ ገዝፈው የሚታዩኝን አውራ ጉዳዮችን
ነው፡፡ከዚህ አንፃር ተስፋየ ርእስ እየቀያየረ አዲስ መጽሃፍ ነው ይበለን እንጂ፣እንደ ደራሲ የሚያስተላልፍልን መልእክት ትላንትም ሆነ ዛሬ አንድና አንድብቻ ነው፣ጥላቻ እና መቃቃር። ተስፋየ ስነ-ጽሁፍን የሚጠቀመው በፍራቻ እና ጥላቻ የሚመለከተውን ማህብረተሰብ ማጥቂያ መሳሪያ በማድረግ ነው። ምናልባትም በዓለማችን የኖቤል ተቃራኒ የሆነ ሽልማት የሚሰጥ ድርጅት ቢኖር አጓዋጉል ነገሮችን በመጻፍ በሰውልጆች መሃከል ጥላቻን በማስፋፋም ተሰፋየን አለምንም ጥርጥር የዓመቱ ተሸላሚ ያደርገው ነበር።

ተስፋያዊ የገጸ-ባህያርት አሳሳል፤

በስነ-ጽሁፍ ስራዎቹ ወደሳላቸው ገጸ-ባህሪያት ስንመጣ ተስፋየ እነዚህን ልቦለዳዊ ባህሪያት ከአንዱ ወይንም ሌላው የሃገራችን ብሄርሰቦች ጋር በማዛመድ የሚፈልገውን ፖለቲካዊ መልእክት ለማስተላለፍ ሲጠቀምባቸው እናያለን። ካለትፉና ከአሁን ስራዎቹ አንድ ሁለት ብለን የተወሰኑ ምሳሌዎችን እያየን ብንመርምር የቡርቃ ዝምታው አኖሌ፣እና የስደተኛው ማስታወሻ ጫልቱ ለዚህ ተጠቃሽ ምሳሌዎች ይሆናሉ። ሁለቱንም የብሶት፣የጭቆና ሰለባዎች ያደርጋቸዋል። እንዳውም በቡርቃ ዝምታ ከሰዉ አልፎ ግኡዙን ወራጅ ውሃ (የቡርቃ ወንዝ) ቂመኛ በማድረግ የቁጭት ስሜት ለመቀስቀስ ተጠቅሞበታል።ተስፋዬ በሌላ አንጻር ከነአኖሌና ጫልቱ በተቃራኒ የሳላቸው ገጸ-ባህሪያት በቡርቃ ዝምታ ነፍጠኛው አስናቀ፣ በስደተኛው ማስታወሻ ሳምሶን ዘለቀን አንድ ማህበረሰብን ወክለው ግፍ ፈጻሚ እና የአጥቂነት ገጸ-ባህሪ ሚና እንዲጫወቱ አድርኋቸዋል።ይባሱኑ በደሎቹ በድንገት ወይንም በአጋጣሚ የተፈጠሩ ሳይሆኑ ሆነ ተብለው ታስቦባቸው መደረጋቸውን ከታሪኩ ጋር እያንደረደረ ወስዶ መደምደሚያው ላይ ይነግረናል። በዚህ “የስደተኛው ማስታወሻ” ላይ የተጠቀሰውን ብንመለከት ተስፋዮ የጫልቱን በደል አክርሮ በሚከተለውን መልኩ ይደመድመዋል፡

“እኔን የጨቆኑኝ እነማን ናቸው?” ብላ አጥብቃ ራሷን ጠይቃ ነበር። ሳምሶን ዘለቀ፣ ሽንኩርት ነጋዴው ወይስ አክስቷ? መልስ አልነበራትም። …………………….. የሆነችውን አፍርሶ፣ ያልሆነችውን እንድትሆን ያደረጋት ማነው? ይህ ስርአታዊ ሽብር (systemic Violence) ስለመሆኑ ጫልቱ ግንዛቤው አልነበራትም። የተቸገረችበት ሌላ አቢይ ጥያቄ ከፊቷ ተደቅኖባት ነበር። ሄለንነቷ እንዲህ በንኖ ከጠፋ፤ ወደ ጫልቱነትም መመለስ ካልቻለች ማንን ነው የምትሆነው? ወይም ምንድነው የምትሆነው?” ገጽ 99

ታዲያ የመጽሃፉ አንባቢ ተስፋየ እንዲህ አይነት ትረካዎች ላይ ለምን አጽንኦት ይሰጣል በማለት ጥያቄ ቢያነሳ መልሱ አንድና አንድ ነው።በብሔረሰቦች መካከል ፍርሃት እና ጥርጣሬን መፍጠር የሚለው አንደኛውና ዋንኛው መልስ ነው። ተስፋየ የሚተረካቸው ትረካዎች ችግሩን ሌላ መልክ በመስጠት ውጥንቅጡ የወጣ ማህበረሰብን የመፍጠር አላማ አድርገው የተነሱ መሆናቸውን የበዙ ምክንያቶችን በመደርደር ማሳየት ከባድ አይደለም። እንዳውም በደምሳሳው ስነ-ጽሁፎቹ ፈጽሞ መፍትሄ አማጪነት ባህሪ አይታይባቸውም። እናም እንዲህ አይነት
ሃላፊነት የጎደላቸው የፍብረካ ትረካዎች በአንዳንድ አንባቢያን ላይ የሚፈጥሩትን ስሜት ለመገመት ተመራማሪ መሆን አያሻም። የሚፈጥረው ስሜት በድርጊት ሲታገዝ ምን እንደሚከሰት መገመቱ ቀላል ነው። እዚህ ጋር መነሳት ያለበት ሌላው ጥያቄ ተስፋየ ይህን በብዙ ህዝብ ሊነበብ የሚችል ትረካ ፣ ጥሬ-ታሪክ ከየት አገኝ የሚል መሆን አለበት።በትረካው መጨረሻ ላይ እንደገለጸው የታሪኩ ምንጭ የእኔና የተስፋየ ወዳጅ ከሆነ የኦነግ አክቲቪስት ነው። ይሄ በራሱ የተስፋዬ ድርሰቶች ዓላማ ላይ ያለንን ጥርጣሬውን ውሃ እንዲያነሳ ያደርጉታል።የድርጅት
አክቲቪስት በነገረው ላይ የተስፋየ ስነ-ጽሁፍ ታክሎበት የሚቀርብ ታሪክ በአንባቢ ዘንድ፤ በተለይም ራሳቸውን እንደተጠቂ በሚቆጥሩ አንባቢዎች ዘንድ፤ ምን ስሜት እንደሚፈጥር ሁላችሁም መገመት ትችላላችሁ። በእሳት ላይ ቤንዚን እንደማርከፍከፍ ነው፡፡

ተስፋየን በሁሉም መጽሃፎቹ ውስጥ የቀረጻቸውን ገጸ-ባህሪያት ልብ ብሎ ለተከታተለ የሚያገኘው አንድ የጋራ ባህሪ አለ።እውናዊም ሆነ የፈጠራ በሆኑት እነዚህ የተስፋየ ገጸ-ባህሪያት በጨቁዋኝነት፣እና በግፈኛነት የሚሳል አንድ ማህበረሰብ አለ።በአንጻሩ ሁልግዜ ተበዳይ እና፣ብሶተኛ ገጸ-ባህሪን የሚወከል ማህበረሰብ፣ቁርሾውን እና ቂሙን እንዲወጣ በገደምዳሜ ምክር ብጤ ይሰጠዋል።ስለ ገጸ-ባህሪያቱ ካነሳን በሁሉም የተስፋየ ስራዎች ላይ የሚቀርቡ የኤርትራ (እርሱ እንደሚጠራቸው የአባት ሃገር) ሰዎች፣ ጀግንነትን እና ደፋርነትን የመሰሉ ባህሪያት አይነተኛ መለያቸው እንዲሆን ተደርገው ተስለዋልን። በተራራውን ያንቀጠቀጠው ትውልድ የአስመራ ልጆች በማለት የሚጠራቸው፣በየስደተኛው ማስታወሻ እንደ ኮለኔል እዮብ ያሉ መኮንኖችን የጀግንነት ወሰን ጥግ ላይ አድርሶ ለተደራሲው አቅርቧቸዋል። በገጽ 214-14 ላይ ሰለኮለኔሉ እንዲህ ብሎን ያልፋል፡-

“በርግጥ በቀጣዩ ቅዳሜ ከኮሎኔል እዮብ ጋር በሰፊው ተገናኘን። ለረጅም ጊዜ በተደጋጋሚ እየተገናኘን ታሪኩን አጫወተኝ።እዮብ ያወጋኝ ታሪክ በርግጥም አስደናቂ ሊባል የሚችል የኢንተሊጀንስ ታሪክ ሆኖ አገኘሁት። በቀይ ኮከብ ዘመቻ ወቅት መረጃዎች ወደ ሻእቢያ እንዴት ይተላለፉ እንደነበር በዝርዝር ሲተርክልኝ በመደነቅ ነበር ያዳመጥኩት። በዚህ ቅፅ ዝርዝር ታሪኩን ልፅፈው ግን አልቻልኩም። በሰማሁት ታሪክ ውስጥ ከደርግና ከሻእቢያ ባለስልጣናት በህይወት ያሉ በርካታ ሰዎች ስማቸው ይነሳል። ስማቸው የሚነሳ ሰዎችን በማነጋገር መረጃዎችን ማዳበር እና ማረጋገጥ እንዳለብኝ ስላወቅሁ፣ ዝርዝሩን ለማዘግየት ተገደድኩ። ወደፊት “የስለላ ስራ” በሚል ርእስ እተርከው ይሆናል…”

ገጽ214-15.

ከዚህ በመነሳት የሚቀጥለው የተስፋየ መጽሀፍ በሻእቢያ የስለላ ታሪክ ላይ ሊያተኩር እንደሚችል መገመት እንችላለን።ይህ የሚሆን ከሆነ አለምዓየሁ መሰለ በራሱ ተስፋዮ ገብርአብ ላይ የሰራውን አስደናቂ የስለላ ስራ የመጽሃፉ አካል ቢያደርገው የመጽሃፉን ውበት እና ሚዛናዊ ጸሃፊነቱን ያሳየናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ይህንን ካልሆነ ደግሞ ያው ተስፋየ ነው
ብለን እናልፈዋልን።

የስነ ስሁፍ ምሁራን እንደሚሉት፤ ገጸ-ባህሪያት አብዛኛውን ግዜ የደራሲው ፍላጎት እና ምኞት ነጸብራቆች ናቸው። ባህርያቸውን የሚወስዱት ከደራሲው ፈጣሪያቸው ነው።ደራሲው ገጸ-ባህሪያቱን የሚፈልገውን መልእክት ለመናገር ይጠቀምባቸዋልና።”የስደተኛው ማስታወሻ” ደራሲ ተስፋየም ያደረገው ይህንኑ ነው፡፡ የጫልቱን ታሪክ ያነበበ ማንም በቁጭት ስሜት እንዲነሳ መገፋፋቱ አይቀርም።ስነ-ጽሁፍ ከባድ የሆነ ሃይል አለውና።ምናልባትም ለዚያ ይሆናል ከታሪክ ነጋሪው የበለጠ አጡዞ በጫልቱ ውስጥ ብቅ እያለ የሚያስደምመን፡፡ ይህም በገጸ-ባህርያቱ በኩል የራሱን የደራሲውን ፖለቲካዊ መልእክት እንድናይ ያደርገናል።

በ“የስደተኛው ማስታወሻ”መጽሐፍ የተስፋየ ስደት ግለታሪክ፣ ሌሎች አጋጣሚዎች እና የአንዳንድ ሰዎች ትረካ ጭምር ተዳሷል። የስደት ተሞክሮዎችና ከስደት ህይወት ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ታሪኮች፣ በመጽሐፉ ተሸፍነዋል። እነዚህም ተስፋየ በተግባር የተሳተፈባቸው ድርጊቶች ብቻ ሳይሆኑ በሰሚ ሰሚ ያገኛቸውን መረጃዎችን ይጨምራል።ከዚያም ባሻገር በሰበብ አስባቡ ምክንያት እየፈለገ በመኮርኮም ታሪካቸውን በማኮስመን ስነ-ጽሁፍን ታሪክን የማዛባት ወይም የመደለዝ ተልእኮው መሳሪያ ሲያደርግ ይስተዋላል፡፡

የፍስሃጽዮን ፖለቲካ ወይስ የተስፋየ ገብረአብ ፖለቲካ፣

ተስፋዬ በመጽሐፉ ውስጥ “የፍስሃፅዮን ፖለቲካ”በተሰኘ ርእስ ስር የማይገናኙ ታሪኮችን በመጠቃቀስ ታሪክን የማጠልሸት ሙከራ ሲያደርግ ይታያል። ተስፋዬ በ”የስደተኛው ማስታወሻ” ውስጥ አለምንም አመክንዮ የፍስሃጽዮንን ገድል በዚህ አይነት ሁኔታ ልናምነው እንችላለን ወይ? እያለ ሲጠይቅ ይስተዋላል። አንባቢ የእርሱንም ሃሳዊ የሆኑ ታሪኮች እንዲህ ቢጠይቅ ተገቢ ሊሆንም ይችላል። ይህን የምልበት ምክንያት የፍስሃጽዮን (የአቡነ ተክለሃይማኖት) ታሪክ ከስደት ማስታወሻ ጋር ሊያናኘው የሚችል አንድም ምክንያት አልታይህ ስላለኘ
ነው።ያም ቢሆን ነገሩ ከታሪክ ግምገማነት አይን ይታይ ቢባል እንኳ፣ ተስፋየን በቅርብ የምናውቅ ሰዎች የታሪክ አጠናን ዘዴ ብቃቱ እንዲህ ላለ ስራ እንደማያበቃው አፍ ሞልቶ መናገር ይቻላል።ለዚህም በርካታ ምክንያቶች አሉን።አንደኛ ተስፋየ ሃሳዊ የፕሮፓጋንዳ ሰራተኛ እንጂ የታሪክ ተመራማሪ አይደለም ።ሁለተኛው በከዚህ ቀደሞቹ ስራዎቹ ሲገመገም ተስፋየ እንደ አጥኚ ሚዛናዊ በሆነ አይን ታሪክን ይመለከታል የሚለውን መከራከሪያ የሚያስተውን የበዙ ምክንያቶች አሉ። ሶስተኛው አንዳንድ ትረካዎቹ ላይ እንዳየነው የምንጭ አጠቃቀም ዘዴው መደዴ የሚባል አይነት ነው። ከነዚህ ምክንያቶች በመነሳት ተስፋየ ታሪክን የፈልገው ለመደለዝ ወይንም ማደፍረስ እንደሆነ እንረዳለን።

ከዛ ይልቅ ተሰፋየ ያተኮረው በታሪኩ ሂደት ላይ ሳይሆን አቡነ ተክለሃይማኖትን ጨምሮ አብዛኞቹ ሃገር በቀል ጻድቃን ለምን የአንድ አካባቢ ሰወች ሆኑ የሚለው ጉዳይ ነው ከመልእክቱ ጎልቶ የወጣው ክፍል። ለዚህ ደግሞ የዳኛቸው ወርቁ አደፍርስን በማናገር ምክንያቱን ለማጠናከር ሞክሮአል።ይቀጥልናም እራሱን ለመከላከል የሃገራችንን ደፋር ጸሃፍያንን ስም በማንሳት እነሱ የዛ አካባቢ ሰዎች ሰለሆኑ ዝም ተባሉ፣ሌላ ሰው ቢጽፈው ግን ሌላ ይባላል ለማለት ላይ ታቸ እያለ ምክንያት ፍለጋ ሲንከራተት ይታያል፡-

“ከዳኛቸው ወርቁ በመቀጠል አቡነ ተክለሃይማኖትን የተቹ ሁለት ብእረኞች ብቅ ብለው ነበር። ፅጌ ስጦታው እና በእውቀቱ ስዩም። በአጋጣሚ አሁንም ሁለቱም ብእረኞች አማራና ኦርቶዶክስ በመሆናቸው አጃንዳው እንዳይጋነን አድርጎታል።” ገጽ317

እርግጥ ነው፣ ተስፋየ እዚህ ጋር የሳተው ቁም ነገር በደፋር ጸሃፊና በሃሳዊ ጸሃፊ መሃከል ያለው ልዮነት የሰማይና
የምድር ያህል መሆኑን ነው።ደፋር ጸሃፈያን የሚጽፉት እውነትን ለመፈለግ፣ከተቻለም የተዛባውን ለማረም ነው። ሃሳዊ ወይንም ተንኳሽ ጸሃፍያን ግን ቁርሾን ለማስፋትና ታሪክ ላይ ውንብድና ለመፈጸም እስከሆነ ድረስ የመልእክታቸው ተቀባይነት ምን ግዜም በጥርጣሬ መተጽር ውስጥ መውደቁ አይቀርም።በኛ ሃገርም ታሪካዊና ታሪክ ቀመስ ልቦለዶችን ያስነበቡን ደራሲያን ጥቂት አይደሉም፡፡ በተለይ ደራሲ ብርሃኑ ዘርይሁን እና፣ ሃዲስ ዓለምአየሁ የስርአት ችግርን ነቅሰው በማውጣት ህብረተሰብ ወደፊት እንዲራመድ በስነ-ጽሁፋቸው ደፍረው አስተምረዋል።

ህብረተሰቡን አቅጣጫ በማሳየታቸው፣ስነ-ጽሁፋቸው የሃገራችን ዘመን አይሽሬ ስራ ለመባል በቅቷል። ሌላው ለአቡነ ተክለሃይማኖት የቅድስና ክብር የሰጠችው የግብጽ ቆፕት ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ እንጂ ሌላ አይደለም።እንዲህ ለማድረግ ደግሞ ቆብጦቹ ረጅም የሆነ የማጣራት ስነ-ስርአት አላቸው።ወደ አሌክሳንድርያ ብቅ ካልክ በስማቸው የተሰየመ ትልቅ ቤተክርስትያን ስላለ ኤዛ ቋሚ ምስክር ታገኛለህ።በኋላም አምስቱ የኦርየንታል (ምስራቃውያን) አብያተ ክርስቲያናት የቆፕጥ ቤተክርስቲያንን ውሳኔ ተቀብለው በክብረ በዐላቶቻቸው መዝገብ ውስጥ አሰገብተዋቸዋል።

ባለበት የእውቀት እጥረት ምክንያት ተስፋየ አላነበበ ይሆናል እንጂ ከደርዘን በላይ እውቅ አለማቀፍ የጥናት ስራዎች እና የዱክትርና መሟያ ምርምሮች በጠቀስከው የፍስሃጽዮን ታሪክ ላይ ተሰርተዋል።ሁሉም ባይሆኑ አንዳንዶቹ ምክንያታዊ የሆነ ሂሳዊ ግምማቸውን ከአሳማኝ መላምት ጋር አቅርበዋል።እንደነዚህ ያሉ ጥናቶችን ለምን በፈረንጅ፣ በተለይም ጣልያናዊ በሆኑ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ተጻፈ የሚል ትችት እስካሁን አልገጠመኝም።ልክ እንደ ፍስሃጽዮን ሁሉ አባት ሃገር ከምትለው ሰራዬ አካባቢ በወጡት አባ አውስጣቴዎስ (ቤተ- አውስጣቴዎስ) ላይም ብዙ ተጽፎአል። ታሪክ በባለሙያውና በትክክለኛው መንገድ ከተጠና ሁላችንም ያለፈ ጉዞአችንን እንድናይበት በር ይክፍታል እንጂ ጉዳት የለውም። በተስፋየ መጽሃፍ ውስጥ የሚገኙ ትረካዎች ግን አስፈላጊነታቸው እና ያላቸው የብቃት ደረጃ ጥያቄ ውስጥ የሚወድቁ ብቻ ሳይሆኑ የሃሳዊነት እና የትንኮሳ ባህሪ ስላላቸው ነው ከደፋር ጸሃፍያን ወይንም ከታሪክ ተመራማሪወች የሚለዩት።

ታሪክን በማዛባት ረገድ ተአማኒነት ይጎድላቸዋል ከምላቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ተስፋየ ስለ አጼ ቴወድሮስ አሟሟት እስካሁን ካነበብነውና ከሰማነው የተለየ አዲስ ታሪክ ይዞ ብቅ ማለቱ ነው፡፡ወርቂቱ የተባለች የወሎ ሴት ባላባት ገደለችው ከሚለው የታሪክ ውሽት በተለየ መልኩ፣ አሟሟታችው ላይ አዲስ ነገር ጭምሮ ብቅ ብሎአል። በይፋዊው ታሪክ ላይ የተዘገበው በገዛ እጃቸው ህይወታቸው ማጥፋታቸውን ሲሆን፣ይህንን በቦታው የነበሩ የናፔር ዘመቻ ተሳታፊ ወታደሮች ሳይቀሩ አረጋግጠዋል።እንዳውም አንዱ ወታደር በጻፈው ግለ-ታሪክ አስከሬናቸው በወራሪው የእንግሊዝ ጦር የክብር አቀባበር ተደርጎለት እንደነበረ የአይን ምስክርነቱን ሰጥቶአል። ይሁንና ተስፋየ የንጉሱን አሟሟት እንዲህ በማለት ጽፎታል፡-

“አጤ ቴዎድሮስ ራሱን ሲገድል አስተካክሎ ባለመተኮሱ ነፍሱ ሳትወጣ ጥቂት ተሰቃይቶአል። እንግሊዞች ደርሰው፣ መሬት ለመሬት እየጎተቱ ሲያንገላቱት ጭምር ቴዎድሮስ ህይወቱ ነበረች። ልብሱን አውልቀው ራቁቱን አድርገው በሚጠሉት ወገኖች ሲያስደበድቡት ግን የቋረኛው ንጉስ ህይወት አለፈች።”ገጽ390

ይህ ምን እንደሚባል አንባቢ የራሱን ፍርድ ቢሰጥ የሚሻል ይመስለኛል። ” የስደተኛው ማስታወሻ” እኩይ ለሆነ አላማ ታሪክን የማንጋደድ ስራ ጥሩ ማሳያ ነው የምለውም ከዚህ የተነሳ ነው።በእርግጥም ደራሲው በተራ ቋንቋ ሃሳቡን በቀላሉ በመግለጽ የታሪክ መሰረት የሌላቸውን ክስተቶች እዚህም እዛም በማስገባት ትውልድን የማሳሳት ሃሳዊ ስራውን ተወጥቶበታል ማለት ይቻላል፡፡

የተስፋየ ሃሳዊ ብዕር በአንድ በኩል የሃገራችንን ታሪክ ማደብዘዝ መደለዙን ስራየ ብሎ መያዙን እንዳየነው ሁሉ በሌላ በኩል አባት ሃገር ብሎ የሚጠራትን ኤርትራ፣ በአሁኑ ወቅት ያለው እውነታ እየታወቀ አንድም ነገር ለማለት አለመድፈሩ ሚዛናዊ ሃቀኛ የሰ-ነጽሁፍ ሰውነት ጥያቄ እንዲነሳበት በር ይከፍታል።ተስፋየ በሆላንድ የመኖሪያ ፈቃድ ካገኘ በሁዋላ ለበርካታ ግዜያት ወደ አባት ሃገር ኤርትራ ቢመላለስም የነገረን ከተገመተው በታች ነው። አስታውሳለሁ፣ በቀደምት ስራዎቹ ስለኤርትራ ለምን አንዳልጻፈ? ስጠይቀው፣የሰጠኝ ምክንያት ‘ስለኤርትራ ምንም የሚያውቀው ነገር ስለሌለ ነው’ የሚል የነበረ።ሆኖም ተስፋየ በዚህኛው “የስደተኛው ማስታወሻ” ጥቂት ምዕራፍ ሰጥቶ ስለ አባት ሃገር ኤርትራ አንዳንድ ነገሮችን ለማንሳት ሞክሯል።ይሁንና ስለኤርትራ ትንሽም ቢሆን በጻፈባቸው ምዕራፎች የተገለጸው፣ በዐለም መናኛ ብዙሃን ከምናውቃት ኤርትራ ጋር የማይመሳሰል ነው።ይህ ብቻ
ሳይሆን “የስደተኛው ማስታወሻን” በሻእቢያ የጦርነት ጅብዱዎች ገድል ዙሪያ እንዲያጠነጥን አድርጎታል። ይህ የኢትዮጵያን ፖለቲካ፣ ታሪክ እንዲሁም የህዝቦች ግንኙነት አሉታዎ ገጽታውን የማናር ትረካው፣ አባት ሃገር ኤርትራን ለመግለጽ ከተጠቀመበት ስልት ጋር ሲነጻጸር ጉልህ የሚዛናዊነት ችግር እንዳለበት ያሳያል።

ሲጠቃለል፣

“የስደተኛውን ማስታወሻ”ስራ ጥሩ መጽሃፍ እንዳይሆን ካደረጉ በርካታ ምክንያቶች አንዱና ዋነኛው የመልእክቱ ጭብጥ ሃሳዊነት እና ተንኩዋሸ ባህሪ ስነ-ጽሁፋዊ ፋይዳውን አሳጥቶታል።ይህ ብቻ ሳይሆን ጸሃፊው ባሳየው ሚዛኑን የሳተ የአጻጻፍ ስልት ስነ-ጽሁፉን አጠወልጎታል፡፡ በ”የስደተኛው ማስታወሻ” ላይ የተወሰነ ስነ-ጽሁፋዊ ውበት ብናይም ፣ጸሃፊው ለማስተላለፍ የሚፈልገው የፖለቲካ መልእክት፣ እንዲሁም ህዝብና ህዝብን አናካሽ በሆነው የአጻጻፍ ስልቱ ምክንያት የስደተኛው ማስታወሻ ከመከኑ የስነ-ጽሁፍ ስራዎች ተርታ እንዲመደብ አድርጎታል።

http://ecadforum.com

posted by Tseday Getachew

 

የሳዲቅ አህመድ ንግግር (ዋሽንግተን ዲሲ) የታሰሩት የሙሰሊም መሪዎች የሰላም አምባሳደሮች

ethiowaga.gif

 

የሳዲቅ አህመድ ንግግር (ዋሽንግተን ዲሲ)

የምንወዳት የምንሳሳላት እናት ሀገራችን ኢትዮጲያ ልጆቼን አያለች በምትጣራበት ወቅት ላይ እንገኛለን። የናት አገር ጥሪንም ሰምተን እዚህ  መገኘታችን ታላቅ ዋጋ አለው! በዚህም ሳቢያ የታደልን የኢትዮጲያ ለጆች ነን ለማለት እወዳለሁ።እርስ በርስ እንድንፈራራ አንዱ-አንዱን  እዲጠራጠር የተከፈተብን የስነ-ልቦና ጦርነት ቀላል አይደለም፤ ይህንን የስነ-ልቦና ጦርነት ለመርታትም እዚህ ተገኝተናል። የዜጎች ሁለንተናዊ አንድነትን ለመናድ የሚደረግ ሴራ እዉን  አይሆንም፤ ለምን ካላችሁ እኛ  ለዘመናት ያካበትነው ውዴታ፣ እኛ ለዘመናት በራሳችን ላይ አስርፀን ያቆየነው ፍቅር፣ አንድ ኣምባገነናዊ ስርአት ሊፈጥረው ከሚችለዉ ስነ-ለቦናዊ ጫና በጣሙን የላቀ ነውና በኢትዮጲያዊነታችን ሁሌም ልንኮራ ይገባል! በኢትዮጲያዊነት ፍቅር ሁለም ልንፀና ይገባል። አላሁ-አክብር!

የአለማችንን ታሪካዊና ወቅታዊ ሁኔታዎችን ከቃኘን በዘር ሃያልነት፣ በፖለቲካ አመለካከት፣ በሃይማኖት ልዩነት፣ በኢኮኖሚ የበላይንት፣ በተበደልኩ ባይነት ሰዎች አክራሪ አሸባሪ ሲሆኑ ይታያል፤ ብዙዎቻቹ ለዘመኑ ቴክኖሎጂና መገናኛ ብዙሃን ሩቅ አይደላቹምና የምትሰሟቸዉን  የዘር፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ የበላይነት ለመቀዳጀት የሚከሰቱ የአሸባሪነት ተግባራትን  እናቆይና የዛሬን የውይይት መድረክ የሚመለከቱን በተለያዩ መንግስታትና ህዝባዊ ተቋማት ብሎም አገራት አሸባሪ ተበለው የተሰየሙ ቡድኖችን እንጥራ። አልቃኢዳ፣ አልሸባብ፣ ቦኩ-ሃራም እና አንሷረል-ኢስላም፤ እነዚህ ቡድኖች በሽብር ፈጠራ ይታወቃሉ፤ ንፁህንን ሲቪሎችን ይገድላሉ፤ ንብረትን ያወድማሉ፤ በሃሳብ ልዩነት ተግባብተው ተቻችለው መኖርን የማይቀበሉ ከመሆናቸወም ባሻገር በመጀመርያ የጥቃታቸው ሰለባ የሚያደርጉት የራሳቸወን ወገን የሚቀርባቸውን ሙስሊሙን በመሆኑ ያለማችን አብዛኛው ሰላም ወዳድ ሙስሊም በጽኑ ይቃወማቸዋል፤ ይህን እዚህ ጋር ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።የአለማችን  አብዛኛው ሙስሊም ማህበረሰብ ቢቃወማቸወም፤ እኛም እንደ ኢትዮጲያዊና እንደ ኢትዮጲያዊ አሜሪካዊ በፅኑ የምንቃወማቸው መሆኑን ዳግም ላረጋግጠላችሁ እወዳለው።

ከላይ ስለተጠቀሱት አሸባሪ ቡደኖች በዙ ይባላል፤  አሸባሪ ተበሎ ለተሰየመ አሸባሪነቱ በገሃድ ስለሚተገበር እና ስለሚታይ    ስለቡድኑ ብዙ ከማለት ይልቅ በነዚህ አሸባሪ ቡድኖች ላይ ሰላም ወዳድ ሙስሊሞች ያላቸውን አቋም ማሳወቁ ግድ ይላል። የብዙ ኢስላማዊ ምሁራን ጥምረት የሆነው የሰሜን አሜሪካ የፊቅሂ ምክር ቤት  ይህንን ሃይማኖታዊ ብያኔ ወይም ፈትዋ ሰጥቶዋል።

1)     በሲቪሎች ላይ የሚደረግ ማንግኛውም ሽብር የመፍጠር ተግባር የተከለከለና ሃራም ነው ።

2)    በሽብር ፈጠራና ረብሻ/ሁካታ ከሚሰማሩ ቡደኖችሀና ግለሰቦች ጋር ማበር ብሎም መተባበር የተከለከለና ሃራም ነው።

3)    የንጹሃንን የሲቪሎችን ህይወት ለመጠበቅ ለማዳን ከህግ አስፈፃሚ አካላት ጋር መተባበሩ የበጎ ኣድርጎት ሃይማኖታዊ ተግባር ነው።

ከላይ የተጠቀሰው ሐይማኖታዊ አቋም በሰሜን አሜሪካም ይሁን በኣውሮፓ፤ እሴያም ይሁን በአፍሪካ ብሎም በመላው አለም የሚገኙ ሰላም ወዳድ የሆኑ ሙስሊሞች አቋም ነው። በሰላማዊ መንገድ ዲሞክራሲያዊና ህገመንግስታዊ መብታቸውን የሚጠይቁት ኢትዮጲያዊ ሙስሊሞች ከዚህ የተለየ አቋም እንዳላቸው አላሳዩምና የመንግስትን የማስፈራራት የማፈራራት የከፋፍለክ ግዛዉ ፕሮፓጋንዳና የስነ-ልቦና ጦርነት ውድቅ ማድረጉ አኩሪ ኢትዮጲያዊ ተግባር ነውና በጋራ ውድቅ ልናደርገው ይገባልነው። ኢንሻ አላህ!

ኢትዮጲያዊያን ሙስሊሞች ከአንድ አመት በላይ በጽናት በሰላማዊነት በጀግንነት መብታቸውን እየጠየቁ ነው ።ጀግና ስንል ‘መቼ ግዳይ ተጣለና?’ ትሉ ይሆናል፤ ትውልዱ ስለጀግንነት ያለውን አመለካከት በእስር ከሚገኘዉ  የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት  ክፍል ሃላፊ ከሆነው ወጣት አህመዲን ጀበል ልዋስ አህመዲንም እንዲህ አለ‹‹በተለያየመልኩግፈኞችሰዎችንየሚያሰቃዩትአካላቸውንለመጉዳትሳይሆንለሰውልጅእጅግወሳኝየሆነውንተስፋናወኔለመስበርነው።የነፃነትስሜትያላቸውንሰዎችበዳይለሆኑሰዎችሁሉእራስምታትናቸው።ተስፋእንዲቆርጡምወኔእንዲያጡምበቃልምበጉልበትምየሚችሉትንሁሉያደርጋሉ።ጀግናማለትእነዚህንየስነልቦናጦርነቶችተቋቁሞሊሰብሩትየፈለጉትንስነልቦናበተስፋሞልቶበፅናትየሚጓዝነው›› አህመዲን ጀበል ኢትዮጲያዊያን ሙስሊሞችም ይህን እያደረጉ ነው፤ኢትዮጲያዊያን  ክርስቲያኖችም ይህንን አድርገዋል አቡነ ጴጥሮስ አዲስ አበባ ላይ የተሰዉት በዚሁ የጀግንነት መንፈስ ነው  አቡነ ጴጥሮስ አዲስ አበባ ላይ ሲሰዉ ለክርስቲያን ብቻ አይደለም! ለሙስሊሙም ለክርስቲያንም ለዋቄፈታም ነው አቡነ ጥጴሮስ የተሰዉትና በኢትዮጲያዊነታችን ልንኮራ ይገባልአላሁ አክበር!

ውድ ኢትዮጲያዊያን ሆይ! ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎችን ተጠይቆ ለመመለስ የፈራው መንግስት ምንም ያድርግ ምን ከፈሪዎች ጎራ የሚመድብ ነዉ። ስለምን ካላችሁ ጀግናዉ ሰላም የሆንው ወጣቱ ትውልድ ነዉና! የዚህ ወጣት ወንድም እህት በመሆናችሁ ሙስሊመም ሁኑ ክርስቲያንም ሁኑ ዋቄፈታም ሁኑ ልትኮሩ ይግባልአላሁ አክበር!

ኢትዮጲያዊያን ሙስሊሞች ለሚያቀርቡት ጥያቄ መንግስቱ በፐሮፓጋንዳ እንደሚለው ኢስላማዊ መንግስትን ለመመስረት የሚደረግ የአሽባሪዎች ጉዞ ሳይሆን፤ እንደምን ሰላማዊና ፍጹም ሰላማዊ፤ ብሎም ህገመንግስታዊ ነው የሚለውን ለማመላከት  ከሃያ የሚበልጡ ነጥቦችን ይዣለሁ።ኢንሽ አላህ በሰአቱ ለመጨረስ ሞክራለሁ።

ከጥልቅ ዝምታ ወደ መንግስታዊ ብዥታ

የባሰውን አያምጣ በሚል አመለካከት ኢትዮጵያዉያን  ሙስሊሞች በደል ጭቆናውን ችለው በጥልቅ ዝመታ ውስጥ በመሆን እምነታቸውን እንደ ብርሃን እየተከተሉ ሳሉ፤ መንግስት በዚህ ብርሃን ላይ ብዥታ ለመፍጠር መጤ እምነትን ከሊባኖስ አምጥቶ ጫነባቸዉ…በእምነት ማስገደድ የለም በማለት ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ተነሱ… ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች እና መሪዎቻቸዉ በህገ-መንግስት የተረጋገጠውን መብት ለመተግበር የተነሱ ናቸው እንጂ አሽባሪዎች-አክራሪዎችም አይደሉም።

ከሁካታ ይልቅ ሰላማዊ ስሞታ

እምነት በግድ ሲጫን ህዝቡ ሆ…ብሎ ለረብሻ አልተነሳም፤ ሁካታም አልተፈጠረም፤ ምን እናድርግ በማለት ወጣቱ በአወሊያ ትምርት ቤት ቅጥር-ግቢ ዉስጥ ተሰባሰበ። በቀጣይም ሳምንት በድምጹና በፊርማው መፍትሄ ያፈላለጉ ዘንድ 17 ኮሚቴዎችን መረጠ፤ የተለያዩ ክለሎችም ተወካዮቻቸውን ወደ አዲስ አበባ በመላክ የተወከሉትን ወይም የተመረጡትን ወገኖች አረጋገጡ! መሪዎቻቸዉ አድርገዉ ተቀበሉ።እንግዲህ ኢትዮጲያ ውስጥ 10 ሰው መሰባሰብ በማይችልበት ሁናቴ ነው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ይህንን ባደባባይ እዉን ያደረጉት።

የተረጋጋ የሚያረጋጋ የህዝብን ቁጣ የሚያበርድ እንቅስቃሴ

የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ግብታዊነት (ስሜታዊነት)ያልታከለበት መሆኑን በገሃድ አስመስክሯል። ህዝብን ሊያስቆጡ የሚችሉ እስራቶች፣ድብደባና ግርፋት፣ብሎም በንጹሗን ላይ ግድያ ሲፈጽም የተቆጣውን ህዝብ ለማብረድ በአርቆ አሳቢንት የሚንቀሳቀስ የሰከነ አመራር ያለው እንቅስቃሴ በመሆኑ የአሽባሪዎች እንቅስቃሴ ሊሆን አይችልም። የዚህ ህዝባዊ እንቅስቃሴ የአመራር አካላት የአገሪቱን ህገ-መንግስት ተከትሎ መፍትሄ ለማምጣትብዙ ጥረዋል፤ ውይይትን እንደ መርህ በመከተል  ከተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በግል ተወያይተዋል፤ በባለስልጣናት አንደበትም ‘እናንተን አሸባሪ ናችሁ የሚል እራሱ አሸባሪ ነው’ ተበሎ ተመስክሮላቸዋል። ዛሬ ግን በውሸቱ ድራማቸዉ-በቅጥፈቱ ‘ጂሃዳዊ ሃረካታቸው’ አሸባሪ አድርገዉ ሊፈርጇቸዉ ቢሞክሩም የህዝብ አይን ሁሉንም እየተመለከተ ነዉና አይሳካላቸዉም።

ለአገር ሰላም ለህዝብ ደህንንነት ቅድሚያ የሰጠ እንቅስቃሴ

ትዕይንተ ህዝብ ሲደረግ የኢትዮጲያን ነባራዊ ሁናቴ ባጤነ መልኩ ነዉ። ጥምቀት ሲከበር  አንዋር መስጂድ የነበርው ትዕይንተ ህዝብ ጥምቀትን ለሚያከብሩ ክርስቲያን ወገኖች ክብር ሲባል ወደ ፒያሳ ወይም ሰፈር በኒ- ኑር መስጂድ ተዛውሯል። ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል በህይወት ቢኖሩ ተጠያቂ ይሆኑ የነበሩት ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ ሲሞቱ የሚደግፋቸውን ተከታይ እና ቤተሰብ በማክበር ብሎም የኢትዮያዊነትን  ባህላዊ ተሞክሮዎች  ከግምት ዉስጥ በማስገባት ለአንድ በወር ሙሉ በኢትዮጲያ ዉስጥ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ አልተደረገም ነበር። መለስ ዜናዊ ተጠያቂ ሆነዉ ሳለ እርሳቸዉ በመሞታቸዉ ለአንድ ወር  ተቃውሞ አልተደረገም! ታዲያ ይህ እንቅስቃሴ እንዴት የአሸባሪ ሊሆን ይችላል እህቶቼና ወንድሞቼ? ኢትዮጵያዊ ፍጹም ኢትዮጵያዊ የሆነ እንቅስቃሴ ነዉ።ይህ የመብት ጥያቄ በሌሎችአገራት ሊረዳ ቀርቶ ባህር ማዶ ያለውም ኢትዮጵያዊ በውሳኔ ደረጃ ተጽኖ የማድረግ አቅም የለውም፤ ሁላችንም የትግሉ ደጋፊዎች ነን፤ ትግሉ የሚመራው  ኢህአዴግ ስልጣን ሲጭብጥ ህጻን  በነበሩ ወይም ኢህአዴግ ስልጣን ሲጭብጥ ገና ጥርሳቸውን በነቀሉ ካልያም ኢህአዴግ ሰልጣን ሲጨብጥ ገና በተወለዱ  ወጣቶች ነው።  ይህ ሰላማዊ ትግል የውጭ ዕርዳታ፣ የሌሎችየሌሎች አገራት ጣልቃ ገብነት ቢኖርበት ኖሮ መንግስቱ አነፍንፎ ይፋ ባደረገ ነበር፤ ግን የለም! ትግሉ ኢትዮጵያዊ ነው! ትግሉ ፍጹምኢትዮጵያዊ  ነው።

ሰላማዊ ቃልኪዳን በአደባባይ የተገባበት ሰላማዊ ትግል

የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ኢትዮጵያ የተለያዩ እምነቶች ብሔር ብሔረሰቦች በጥምረት የሚኖሩባት አገር መሆኗን በጽኑ በማመን በፍጹም  በጭራሽ ለሌሎች ስጋት  አለመሆናቸዉን ለለማብሰር ሰላማዊና ሰላማዊ የሆነ ጎዳናን መርጠዋል።እስር፣ግርፋት፣ግድያ እና ሌላም የመብት ረገጣ ቢኖር በሰላማዊ የትግል መርህ ብቻ ለመታገል  በአንዋር መስጂድ ፊት ለፊት እጅ ለጅ በመያያዝ ከተከታዮቻቸዉ ጋር ቃል ገብተዋል።ታዲያ ይህ ትግል እንደምን የአክራሪዎች ወይም የ አሸባሪዎች ሊሆን ይችላል?

“የምንገልበት አላማ ባይኖረንም የምንሞትበት አላማ አለን”

ሌሎች ላይ ጥቃት በመፈጸም የሚመጣ ለውጥን ያልተቀበለ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ነው። ማንንም አናጠቃም ግን ይህንን ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ በመጠየቃችን የሚፈጽምብንን ጥቃት ለመቀብል ዝግጁ ነን። የሚል ጽኑ አላማ ያለው እንቅስቃሴ ነው። ተመሪዎች የጥቃት ሰለባ የሚሆኑበት ብቻ ሳይሆን መሪዎቹ እራሳቸውም መስዋትነትን በመክፈል አርአያ የሆኑበት እንቅስቃሴ ነው። መሪዎችሁ አልፈረጠጡም! መሪዎችሁ አገርን ጥለው አልኮበለሉም! መሪዎቹ በቃን አንታገልም አላሉም!እሰሩን ግደሉን የምንገልበት አላማ ባይኖረንም የምንሞትለት አላማ አለን ነው ያሉት…ይህ ህዝባዊ እንቅስቃሴ በፍጹም በጭራሽ የአክራሪዎች ወይም የአሸባሪዎች ሊሆን አይችልም ወገኖቼ።

 ከአገር መሰደድን መሰረት ያላደረገ እንቅስቃሴ

ዉድ ኢትዮጵያዊያን ሆይ! ይህንን ነዉ  አቡነ ጴጥሮስ ያደረጉት አውሮፓ ተንፈላሰው መኖር ይችሉ ነብር ግን አልፈለጉም። አገር ዉስጥ በመሆን  ሊመጣ የሚችለወን መከራና ስቃይ ተቀብሎ እንደሻማ ቀልጦ ብርሃን ሆኖ ለማለፍ አላማ ያለው ትግል በመሆኑ ነው መሪዎቹ በእስር እየተሰቃዩ የሚገኙት። መረጃዎች እንደሚያመላክቱት መንግስቱ በሽምግለናና በቤተሰብ በኩል ብሎም በማስፈራራት ወደ መረጡበት አገር እንድሚሸኛቸውና እንደሚገላግላቸው ቃል ገብቶ ነበር። ታጋዮችን ለሰደት በመዳርግ የሚታወቀው ስርአት የማያውቀው አይነት ትግል ገጥሞታል። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ ተቀናቃግኖች ተጽዕኖን በሚፈጥሩበት ወቅት አገርን ጥለው እንዲሰደዱ ግፊትን ይፈጥራል።የሙስሊም መሪዎች ግን አንሰደድም ‘የምንገልበት አላማ ባይኖረንም የምንሞትለት አላማ አለን’ ብለው በአሁን ሰአት እስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ ይገግኛሉ። ስለዚህ ምን ይበላቸው? አሸባሪዎች አክራሪዎች እያለ ነው።

የሌሎችን አመኔታ ያገኘ የመብት ጥያቄ

ሌሎች በፕሮፓጋንዳ ሳይሆን እውነታውን በራሳቸም ህሊና እንዲመዝኑ በማድርግ ተቀባይነትን በሌሎች ወገኖች ላይ ያሰረጸ ትግል ነው። ባህር-ማዶ ያለችው ቅዱስ ሲኖዶስ ድጋፏን ሰጥታዋለች፤ ኢትዮጲያ ውስጥ ያሉ ይ ሃይማኖት አባቶች በግልጽ ድጋፋቸውን መስጠት ባይችሉም ድጋፍ ከራጉኤል ቤተክርስቲያን መምጣቱ ተስተዉሏል። በአንዋር ተቃውሞ ሲደረግ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ምንም በድምጿ ድጋፍ መስጠት ባትችልም በቅዳሴ ወቅት የድምጽ ማጉያዋን (speaker) በማጥፋት ተባብራለች።’ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስቲያኑ ተዘነጋሽ እንዴ ኢትዮጵያ መሆኑ’ የሚባለዉ ለዚህ ነዉ። በአገርም በዉጭም ያሉ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች፣የሲቪክ ማህበራት፣የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ሌሎችም በዲፕሎማሲ ጫና ማሳደር የሚችሉ አለም አቀፍ አካላት ለዚህ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ድጋፍና እዉቅና ሰጥተዉታል።

ሴቶች የጀመሩት ሴቶች የተሳተፉብት እንቅስቃሴ

በደሉ ጭቆናዉ ሲበዛ ከአወሊያ ትምርት ቤት ቅጥር-ግቢ የነጻነት ድምጽ ተሰማ… አንዲት የአወሊያ ተማሪ ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ‘በአሁን ሰዓት ወንድ አጥተናል  እኛ እንታገል ስንል ወደ ጓዳ ግቡ ትሉናላችሁ የማትነሱ ከሆነ በቃ ተዉን እንሙትበት’ አለች…ቆራጥ የሆኑትም ሴቶች ለትግል ተነሱ።በኢትዮጲያ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ሴቶች በነቂስ የሚሳተፉብት ድጋፋቸውን የሚሰጡት እንቅስቃሴ ነው።እንግዲህ የአለማችንን ታሪክ እንቃኝ በየትኛዉ ቦታ ሴቶች ጥልቅ በሆነ የ አሸባሪነት ቦታ ሲሳተፉ ታይተዋል? ግን አንድ የሚታወቅ ነገር አለ ሴቶች የጀመሩት አብዮት ግቡን እንደሚመታ! ስለዚህ ለሴቶች ሞቅ ያለ ጭብጨባ እናድርግላቸዉ።

በሁሉም የእድሜ ክልል ያሉ ሙስሊም ኢትዮጲያዊያን የተሳተፉበት

ህጻን ልጅ በአንዋር መስጂድ አካባቢ እንባ በጉንጮቹ ላይ ኮለል ሲል የታየብት ፎቶ ልብን ይነካል…ከህጻናት እስከ አረጋዊያን ጾታን ሳይለይ ኢትዮጲያዊው ሙስሊም በነቂስ የሚሳተፍበት ድምጹን የሚያሰማብት  በኢትዮጲያዊያን ተወልዶ በኢትዮጲያዊያን ያደገ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ነው። ይህ የአሸባሪ የአክራሪ በፈጹም ሊሆን አይችልም!

ሁሉም ሙያዊ ግዴታውን እየተወጣ ያለበት ህዝባዊ ትግል

ሁሉም በሙያው መስክ ተሰማርቶ ለጋራ ስኬት የሚጥርበት ህዝባዊ እንቅስቃሴ ነው።ጸሃፍት በስነ-ፅሁፋዊ ቅኝት የቃኙት፣ከያኒያን የከየኑበት፣ድምጽዉያን ያንጎራጎሩበት፣የኮምፒተር ባለሙያዎች ሙያዊ ግዴታቸዉን የተወጡበት፣ነጋዴዎች የቸሩበት፣የእድሜ ባለጸጋዎች ምርቃታችዉን የሚለግሱበት ከላይ እስከትች መናበብ ያለበት በሰው ልቦና ውስጥ ሰርጾ የገባ ልዩ ህዝብዊ እንቅስቃሴ ነዉ።

ተመሪው ለመሪው ያለውን ታማኝነትና ጽናት ያረጋገጠበት

እንደለሎች የዲሞክራሲ ጥያቄዎች ተመሪው መሪውን አሳልፎ  ሰጥቶ ቤቱ የገባበትየገባበት ትግል አይደለም። ለመሪው ያለውን ታማኛነት እያስመሰከረ ትግሉን በሰላማዊ መንገድ ቀጥሏል።መሪዎቹ ቢታሰሩም ተከታያቸዉ እነርሱን  መከተሉን አላቆመም በእለት-ተእለት ኑሮው መሪዎቹን ሳይዘነጋ ለከፈሉት መስዋዕትነት አመስጋኝ በመሆን የመብት ትግሉን አፋፍሞት ይገኛል።

የእስር ቤትን አስፈሪነት ያመከነ ሰላማዊ ትግል

በኢትዮጲያ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቃሊቲ እስር ቤት ድረስ በመሄድ የቻሉትን ያህል ታሳሪዎች ጠይቀዋል። ታሳሪዎች ዉጪ ካሉ እጮኛዎቻቸዉ ጋር በእስር ቤት ዉስጥ ጋብቻ የፈጸሙበት ለጽናታዊ ተምሳሊትነት የበቁበት ልዩ ሰላማዊ ትግል ነዉ።

በህዝባዊ ድጋፍ ኢፍትሃዊ ችሎትን ያጋለጸ እንቅስቃሴ

በሺዎች በመሆን ፍርድ ቤት በመሄድና በአካባቢው በመገኛት ለመሪዎቻቸው ያላቸወን ጽናት አሳይተዋል።በካንጋሮዉ ፍርድ ቤት (kangaroo court)ኢፍትሃዊ ብያኔን ለመስጠት የተሳነዉ ፍርድ ቤትም ችሎቱ በዝግ እንዲሆንና ወደ ቃሊቲ እስር ቤት እንዲዛወር አድርጎ ነበር። ባለጉዳዮቹ እና ህዝቡ ችሎቱ ለጋዜጠኞችና ለዲፕሎማቶች ክፍት ይሁን እያሉ ሳሉ መንግስቱ ፍትሃዊነትን ማስፈን የሚፈልግ ከሆነ ለምን ችሎቱን በድብቅ ማረግ ፈለገ? ምን የሚደብቀዉ ነገር አለ? ምን አልባትም መንግስት መደበቅ የሚፈልገዉ የራሱን አሸባሪነት ይሆናል።ታዲያ ማነው አሸባሪ?…ማነው ተሸባሪ?

የስርአቱን አምባገነናዊ ጸብ አጫሪንት ጠንቅቆ ያወቀ ትግል

አውቶቢስን ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች እንዲሰብሩ ደህንነቶች ቢያመጡ ወጣቶቹ አንሰብርም እያሉ ድምጽ ያሰማሉ… እጅ ለእጅ ተያይዘው አውቶቢሱ የህዝብ ንብረት ነው በማለት ከለላ (human chain) ሲሰሩ ታይቷል ። ጸብ-አጫሪ ፈደራል ፖሊስ ታርጋ በሌለው ሞተር ሳይክል ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች መሃከል በፍጥነት ሲነዳ ገለል በማለት በጭብጨባ አስተናግደውታል።ደህንነቶች ድንጋይ (Cobblestones) እያመጡ የበተኑበት አጋጣሚ እንዳለ ተስተዉሏል፤ ጎረምሳ ወጣት ‘እባካችሁን ድንጋይ ወርውር ድንጋይ ወርውር ይለኛልና አጆቼን እሰሩልኝ’ እያለ የተንሰቀሰቀበት ሰላማዊ ትግል ነው። ይህ የመንግስትን ጸብ አጫሪነት የተቋቋመ ሰላማዊ ትግል በመሆኑ የአሸባሪዎች ሊሆን አይችልም።

በቤታችን ሰላም አጣን

ህዝብን ለማሸበር በወጣ የጸረ-ሽብር ህግን ከለላ በማድረግ ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ ያለ ፖሊስ ማዘዣ ጭንብል(mask) ለባሽ  ካድሬዎች፣ደህነቶችና ፖሊሶች በየሰው ቤት በመግባት ፍተሻ፣ማስፈራራት፣ማሸማቀቅ፣ማሸበር፤ ዝርፊያን ሲያከናዉኑ ትዉልዱ ከመሪዎቹ ባገኘዉ መመሪያ መሰረት ይህንን የማሸበር ተግባር በትእግስት ተቋቁሟል።በዚህም ፍተሻ ወቅት ገንዘብም ንብረት ተዘርፏል ፤የሴቶች ጌጣጌጧጦች ተሰርቀዋል፤ ያልተረጋገጡ ሪፖርቶችም እንደሚያመላከቱት በፍተሻው ወቅት ሴቶች በፖሊሰና በካድሬዎች (rape)ተደፍረዋል። በየሰዉ ቤት እየሄዱ በፍተሻ ስም ሽብርን ለምን የሚፈጽሙ ይመስላቹሃል? ወንዱ ቤቴን አላስደፍርም በማለት ከነርሱ ጋር እንዲፋለምና አሸባሪን አግኘን ብለው የሚፈልጉትን ለማድረግ ነዉ። በቤቱ ሰላም እያጣ ሰላምን ለማምጣት መስዋእትነትን እየከፈለ ያለዉ ትዉልድም ይሁን መሪዎቹ አሸባሪ ሊሆኑ አይችሉም! በዚህ ሰላማዊ የትግል ሂደት ዉስጥ አሸባሪነቱ የተረጋገጠዉ ግን መንግስት ነዉ።

ግልጽነት በእጅጉ የተሞላበት ትግል

የትግሉ ሂደት በሙሉ በቪዲዮ እየተቀረጸ ለአለሙ ማህበረሰብ ታይቷል።የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዉ ህጋዊ እንቅስቃሴዎች በመጽሃፍ መልኩ ተጠርዘው ሙስሊሙም ክርስቲያኑም ይመለክተው ዘንድ በአለም ላይ ተበትኖዋል። እያንዳንዱ የሄዱበት ጎዳና ፍንትዉ ብሎ ለህዝብም ለታሪክም ተቀምጧል ትግሉና ታጋዮች ግልጽነትን ተላብሰዋል ግን እራሳችዉን መንግስት በሚል ስያሜ ዉስጥ የሸጎጡ አሸባሪዎች ግልጽነትን በማመናመን ለሰሩት ኢፍትሃዊ ተግባር ከመጠየቅ አይድኑም።

በመንግስት የፕሮፓጋንዳ የስነልቦና ጫና ያልደረሰበት በመንግስት አመራርላይ  የስነልቦናጫና ያሳደረ እቅስቃሴ

መንግስት ህዝባዊ የመገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም የዉሸት አታሞዉን በመደለቅና ፕሮፓጋንዳዉን በመንዛት የስነ-ልቦና ጫናን ለመፍጠር ሞክሯል…የሙስሊሙ መሪዎችና ተከታዮቻቸዉ ግን ፍጹም የሆነን ሰላማዊ ወኔን ታጥቀዉ በመንግስት የአመራር አካላት ላይ ጫና ፍጥረዋል። የፖሊስ ሐይላት ዱላችውን ሲጥሉ ተሰተውለዋል፤ የኢህአዴግ አባላቶች በግልጽ በቪዲኦና በድምጽ እየተቅዱ ፓርቲያቸው ስተት ላይ መሆኑን በመናገር ፓርቲውን ጥለው እንደሚወጡ አስጠንቅቀዋል፤ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ቅዋሜያቸውን ገልፀዋል፤ ትዛዝ አንቅበልም ብለው ትጥቅ የፈቱ የፖሊስ ሃይላትም አሉ፤ባለሰልጣን ብቻም ሳይሆኑ ክርስቲያን ባለ ሰልጣኖችም ቅሬታቸውን እየገለጹነው፤ አንባገነናዊ ስርዓትም ዉስጥ ከፍተኛ መከፋፈል እንዳለም በይፋ ይነገራል፤ይህ ሰላማዊ እና ህዝባዊ እንቅስቃሴ ስርዓቱን ለመቦርቦር የበቃ በመሆኑ በስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የስነ-ልቦና ጫናም እየፈጠረ ይገኛል።

ስልጡን ትዉልድ የሰለጠነ ትግል

የዘመኑን ቴክኖሎጂ በአግባቡ የተጠቀመ ሰላማዊ ትግል ነው። መንግስት ሬዲዮ ቴሌቪዝንን በማፈን (Jamming) በማድረግ መረጃን ሲያፍን የማህበራዊ መገናኛ ዘዴን በተገቢዉ መልኩ በጥቅም ላይ ያዋለ ትውልድ ነው።በፌስቡክ፣በቲዊተር፣ በቴክስት፣ ድረ-ገጽና የእጅ ስልክ (cell phone) ብሎም መልክት በማስተላለፍ(word of mouth) መረጃን በማንሸራሸር የመንግስትን ሙሉ ለሙሉ የማፈን ሴራን ያከሸፈ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ነው ።

አለም አቅፋዊ እውቅናን ያተረፈ ሰላማዊ እንቅሰቃሴ 

የአለሙ ማህበረሰብ ያጣውን የፍትህ የዲሞክራሲ እጦትን በሰላማዊ መንገድ ማግኘት እንደሚቻል ያበሰረ፤ ከአፍሪካ ቀንድ የፈነጠቀ ብርሃን ነው። አምንስቲ ኢንተትርናችናል፣ ሂይውማን ራይትዎች ፣የአሜሪካ አለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን ፣ለጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሆነው ሲፒጄና ሌሎችም አገራዊና አለም-አቀፋዊ ተቋማት እውቅና የሰጡት ሰላማዊነቱን ያረጋገጡለት ሰላማዊ እንቅስቃሴ ነው።

ውድ ኢትዮጲያዊያን ሆይ!  አክራሪነትና አሸባሪነት በሌሎች ላይ የራሰን አመለካከት በሃይል ለመጫን የሚደረግ ተግባርና ጥረት ነው። ከላይ የጠቀስናቸውን እውነታዎችን ከቃኘን እራሱን መንግስት ነኝ ብሎ በሚጠራው የኢትዮጲያ መንግስት እንደ አክራሪና አሸባሪ እየተንቅሳቀሰ ነው። አክራሪዎች-አሸባሪዎች ፊታቸውን ይሸፈናሉ፤ ፊታቸውን የሸፈኑ ፖሊሶችና ካድሬዎች ጥቃትን በማታ እየሄዱ የፈፅማሉ። አክራሪዎችና አሸባሪዎች ይዘርፋሉ፤ መንግስት ነኝ የሚለው አካል እየዘረፈ ነው። አክራሪዎችና አሸባሪዎች ያፍናሉ፣ ያስራሉ፣ ይገድላሉ መንግስቱም ተመሳሳይ ድርጊትን በህዝቡ ላይ እየፈፀመ ነው።    አንባገነናዊዉ መንግስት የስልጣን እድሜዉን ለማራዘም በሙስሊሙናበክርስቲያኑ ላይ የሰነልቦና ጦርነት ከፍቷል።  እኛ ደግሞ በአልበገር ባይነትበኢትዮጲያዊ ጀግንነት እምቢኝ ለፍቅር እምቢኝ ለአንደነት ልነለው ይገባል።

ዉድ ኢትዮጵያዉያን ሆይ!  ብዙ የግፍ መዓት በእናት አገራችን ላይ ተስተዉሏል፤ ሴቶች እህቶቻችንን እና እናቶቻችንን በጎረምሳ ልጃቸው ወይም በጎረምሳ ወንድማቸው ፊት የፌዴራል ፖሊሶች በጥፊ ይመታሉ፤ ጎረምሳው ተናዶ እጁን እንዲሰነዝር…እናቶች አዛውንት አሮጊቶችን በከስክስ ጫማ ይረግጣሉ ጎረምሳው ልጃቸው ተነስቶ ድንጋይ እንዲወረወር እጁን እንዲሰነዘር …ይህን ሁሉ በመታገስ ከወራትም ባሻገር ወደ አመታት የዘለገዉ ሰላማዊ ትግል የሁሉም በመሆኑ በዘር በሐይማኖት ሳንለያይ ልንከባከበዉ ይገባል።

እናንተ የተስፋ ባለቤት የሆናችሁ ወገኖቼ! ይህ ትግል ልቦች የተጣመሩበት ነዉ። ልቦች የተጣመሩበትን ትግል መቀልበሱ የልምዣት በመሆኑ ልቦቻችን ሁሌም በተስፋ ይሞሉ። ልቡ በተስፋ የተሞላዉ ታዛዡ ትዉልድ ቁም ሲባል ይቆማል፣ተነስ ሲባል ይነሳል፣አፍህን ያዝ ሲባል ይይዛል፤ እንዲህ በግብረገባዊ ብቃት የታነጸን ትዉልድ የሙስሊሙም የክርስቲያኑም አምላክ ይጠብቀዋል። የልብ ባለቤት የሆነዉ ጥራትና ልዕልዕና የተገባዉ አላህ የምንወዳትን የምንሳሳላትን እናት አገራችን ኢትዮጵያን ይጠብቃት። አመሰግናለሁ…አላህ ይስጥልኝ! ልብ ያለዉ ልብ ይበል።

ድምጻችን ይሰማ እንበል በጋራ.. ድምጻችን ይሰማ… ድምጻችን ይሰማ…

ድሮ ባገራችን ሰላም አጣን ነበር የሚባለዉ አሁን ደግሞ በቤታችን ሰላም አጣን ስለሚባል ይህንኑ እዚህ አዳርሽ ዉስጥ ለማስታወስ በቤታችን ሰላም አጣን እንበል….በቤታችን ሰላም አጣን…በቤታችን ሰላም አጣን…

ልብ ያለዉ ልብ ይበል!

http://ecadforum.com/

posted by Tseday Getachew

የሁለት ኢትዮጵያውያን ሁለት አንቀጽ ወግ እና እኔ…(አቤ ቶኪቻው)

Tesafay Chemeda and Dawit kebed

የሁለት ኢትዮጵያውያን ሁለት አንቀጽ ወግ እና እኔ…

ዳዊት ከበደ እና ተስፋሁን ጫመዳ

ተስፋሁን ጫመዳ የተባለ አንድ ወጣት ኢትዮጳያዊ ነበር፡፡ የገዢው ግንባር ኢህአዴግ ነገረ ስራ አልመችህ ቢለው በተለያየ አጋጣሚ ተው ማለት ጀመረ፡፡ ኢህአዴግዬ ግን ተው ባይ አይወድምና በክፉ አይኑ ተመለከተው ይሄኔ ተስፋሁን የሚመጣበትን ጦስ ሸሽቶ መጪው ጊዜ መልካም እንደሚሆን ተስፋ አድርጎ እስኪያልፍ ያለፋል ብሎ ሀገሩን ትቶ ተሰደደ፡፡ ኢህአዴግ ግን ዝም አላለውም ከተሰደደበት ሀገር አፍኖ ወደ ሀገርቤት መለሰው፡፡ መመለስ ብቻም አይደለም እስር ቤት ዶለው፡፡ መዶል ብቻም አይደለም በቅርቡ ተስፋሁን በእስር ቤት በቂ ህክምና አጥቶ ህወቱን ተነጠቀ፡፡

ዳዊት ከበደ የተባለ ሌላ ኢትዮጵያዊ ወጣት ነበር፡፡ እርሱም የገዢው ግንባር ኢህአዴግ ነገረ ስራ አልጣመውም እና መምከር ጀመረ፡፡ ኢህአዴግዬ ግን በሚመክሩት ላይ መከራ የሚያበዛ ነውና በክፉ አይኑ ተመለከተው፡፡ ይሄኔ ዳዊት ከጎልያድ ጋር ይጋፈጥበት ወንጭፍ በእጁ አልነበረምና ቀን እስኪልፍ ብሎ ሀገሩን ትቶ ተሰደደ፡፡ ኋላ ላይ ግን እንደ ተስፋሁን አፍነው ሳይወስዱትም ራሱ “እንደውም አልፈራችሁም” ብሎ ወደ ሀገርቤት ተመለሰ፡፡ “ይገሉኝም እንደሁ ይሰቅሉኝም እንደሁ ይሄው መጣሁልዎ ያለምጣም ኢህአዴግ ብዬ ሰደብኩዎ” ብሎ ሁሉ ልክ ልካቸውን ነገሯቸዋል ነው የሚባለው… ነገር ግን እንደ ተስፋሁን እስር አልጠበቀውም፡፡ እንኳንስ ህወቱን ሻንጣውም አደጋ ላይ አልወደቀም፡፡

ሶስተኛ አንቀጽ እኔ

“አውቶብሱ መጣ ጎማው ሸተተኝ እኔም ከሰሞኑ ተሳፋሪ ነኝ” ብዬ ዥው ብዬ ወደ ሀገሬ ብሄድ የሚጠብቀኝ ምን ይሆን… እንደ ተስፋሁን ታስሮ ህይወት ማጣት፣ እንደ ውብሸት ታስሮ ይቅርታ ማጣት፣ እንደ ርዮት ታስሮ ጠያቂ ማጣት፣ እንደ እስክንድር ታስሮ ቤተሰብ ማጣት ወይስ እንደ ዳዊት ታስሮ አሳሪ ማጣት!? (በቅንፍም የሆነውስ ሆኖ ግን ስንት አመት ሰው ሀገር እቆያለሁ የሆነ ቀንማ ሄጄ መቀወጤ አይቀርም፡፡ (በሌላ ቅንፍም ደግሞ ሳላግጥ፤ ቢያንስ ግን ለጨዋታም ለቃለ ምልልስም እንዲመች የባቡር ግንባታው እንኳ ይለቅና እንተያያለን…!))

http://ecadforum.com/

posted by Tseday Getachew

 

የኢትዮሚዲያ ወቅታዊ መፈክር (ክፍሉ ሁሴን)

ethiowaga.gif

ክፍሉ ሁሴን

“ከ40 ግድብ አንድ የቀይ ባሕር ወደብ!”የኢትዮሚዲያ ድረገጽ የወቅቱ መፈክር ነው።ከመፈክሩ ጋር ወይም በመፈክሩ ላይ ምንም ችግር የለብኝም።ይልቁንም ወያኔ ከሌሎች ክፉ ነገሮች በተጨማሪ ወደባችንን አስበልቶ በምድር ብቻ ተቀርቅበን የቀረን አገር ስላደረገን እስከ ዛሬ ድረስ ከሚንገበገቡት ኢትዮጲያውያኖች አንዱ ነኝ።የባሕር በር ባለቤትነታችን በእኔ እድሜ እንኳ ባይመለስ ቢያንስ የባሕር በር እንድናጣ ባደረጉን ዋና ዋና ከሃዲዎች ላይ በአገር ክህደት ወንጀል ክስ ሲመሰረት በሕይወት ዘመኔ ለማየት ከፍተኛ ጉጉት አለኝ።በነገራችን ላይ በዚህ ክስ በቀንደኛነት እንዲካተቱ ከምፈልጋቸው ሰዎች ውስጥ አንዱ መንግስቱ ኃይለማሪያም ወልዴ ነው።ስለምን?በዋናነት የተበላነው እሱ የ”አብዮታዊ ጦር ጠቅላይ አዛዥ”በነበረ ጊዜ ነውና።

ከላይ የጠቀስኩትን የኢትዮሚዲያን ወቅታዊ መፈክር ተንትርሶ አንድ ራሱን ጋሻው አባተ ብሎ የሚጠራ አንባቢ ከፕሪቶሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ በጻፈው ደብዳቤ ኢትዮሚዲያን አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ ብሎ ካሞካሸና እነተስፋዬ ገብረአብን (ገብረ እባብ–ጋሻው እንዳሰቀመጠው) ጭምብላቸውን ገሽልጠሕ ስላጋለጥክልን እናመሰግናሃለን ገለመሌ ካለ በኋላ፤ ግን “ወደባችንንም አጥተን ግድብ አይኑራችሁ ነው ወይ የምትለው?” ብሎ መፈክሩ ችግር እንዳለበት በሻዕቢያዊ መሰሪነት ይሁን ወይም ስለ”ልማት” በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፕሮፓጋንዳ ሆዱ እንደተነፋ “ልማታዊ”ደንቆሮ ይሁን የመሰለውን ብሏል።

“Remove Assab! What? Reader vs Ethiomedia”በሚል ርዕስ ድረገጹ የለበደውን ፅሁፍ ይመልከቱ።

የኢትዮሚዲያ ዋና አዘጋጅ ለአስተያዬት ሰጪው “ጋሻው” ከሰጠው ምላሽ ውስጥ አንዳንዶቹ ነጥቦች ትኩረቴን በመሳብ ሌላ ቦታ ያነበብኩትን እንዲሁም በሕይወት ዘመኔ ያስተዋልኩትን እንዳስታውስ ስላደረጉኝ ይህን ለመጫር ተነሳሁ።ኢትዮሚዲያ በመፈክሩ ላይ የጸና አቋም እንዳለውና መፈክሩም በድረገጹ አናት ላይ ጎልቶ መታየቱን እንደሚቀጥል ካተተ በኋላ “በህዋሃት ውስጥ እውነተኛ ስልጣን በትግራይ ልጆች ሳይሆን እንደ መለስ ዜናዊ፣ስብሃት ነጋ ወዘተ በመሳሰሉ የለየላቸው ኤርትራውያን ቅጥረኞች እጅ”እንደነበረና ከሻዕቢያ ጋር የነበረውን መሞዳሞድ የተቃወሙ አንዳንድ የህዋሃት አባላት ምናልባትም እንደዋና አዘጋጁ አገላለጽ አንድምታ “ንጹህ የትግራይ ልጆች”በ”ለየላቸው ኤርትራዊያኖች”እጅ ተገድለዋል፤ወይም ተገልለዋል።

ትልቁ ችግሬ እዚህ ጋር ነው።ማነው ንጹሕ የትግራይ ልጅ? ማነው ንጹሕ የኤርትራ ልጅ?ሁለቱም ቡድኖች ወይም ከሁለቱም ክፍለሃገሮች ተወላጅ ነን የሚሉ የዚያን ጊዜ ልሂቃን በጎሳ ወይም በክፍለሃገር ጠባብ ስሜት ተከታትለው በመነሳትና በመደጋገፍ ጎሳን ወይም ክፍለሃገርን ብቻ “ነፃ” ሊያወጡ ነው የተነሱት እንጂ የኢትዮጲያን ሕዝብ በማስተባበር በኢትዮጲያ የግፍ ስርዓት እንዲቀር አልታገሉም።እነሱ የጀመሩትና የሰበኩት የክህደትና የጎሳ በሽታ ዛሬ ስር ሰዶ ከዘር ወይም መንደር ነፃ አውጪነት በላይ ማሰብ በኢትዮጲያ “ፖለቲካ” እጅግ አዳጋች ሆኗል።በበኩሌ ለኢትዮጲያ ባህር በር ማጣት ከሻዕቢያ እኩል ወያኔን እንዲሁም ላይ እንደጠቀስኩት የደርጉን ቁንጮ መንግስቱን ኃ/ማሪያምንም ጭምር በኃላፊነት እይዛለሁ።በእኔ መጽሃፍ በተለይ በዚያን ጊዜ በጎሳ “ነፃ አውጪነት”የተሰባሰቡት ሁሉ በአገር ክህደት የሚፈረጁ ናቸው።በተቀር ትግሪኛ ተናጋሪ ወገኖቻችንን በተመለከተ አንዱ የአገራችን ክፍል በፋሺስት ጥልያን ተቆርሶ ስለተወሰደብን ግማሾቹ ከኛ ጋር ሲቀሩ ሌሎቹ ከመረብ ወንዝ ወዲያ ማዶ በፈረንጅ ባላንጣ እጅ በመክረማቸውና በዚህና በሌላ ውሉ በደንብ ባልለየ ምክንያት እርስ በርስ ከሚናናቁ በቀር በመካከላቸው በደግም ሆነ በክፉ ብዙ ልዩነት በበኩሌ አይታየኝም።

በትግራይና በኤርትራ የሚገኙ ትግሪኛ ተናጋሪዎችን አንድ መሆንና ግራ የሚያጋባ ስር የሰደደ መናናቅ እና መጠላላት በአምባሳደር ዘውዴ ረታ ‘በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኤርትራ ጉዳይ ‘መፅሃፍ ላይ በገጽ 376-377 ላይ የሰፈረው የተድላ ባይሩና የወልደአብ ወልደማሪያም የከረረ ንግግር አመላካች ነው።ከብዙ በጥቂቱ ልጥቀሰው።

“አንድ ጊዜ በአስመራና በምፅዋ መካከል በሚገኘው “ቤተ ጊዮርጊስ”በተባለ ሥፍራ፤ጥቂቶች ያገር ፍቅር ማህበር መሪዎችና አባሎች ተሰብሰበው ሲወያዩ፣ተድላና ወልደአብ የተለዋወጧቸው ቃላቶች የሁለቱን ሰዎች በሀሳብ መራራቅ ብቻ ሳይሆን፣መጠላላታችውንም በትክክል ያሳያል።እንደተለመደው ወልደአብ ወልደማሪያም፣ኤርትራ ከኢትዮጲያ ጋር የምትቀላቀለው በሕግ በተደነገገ ውል መሆን አለበት፣የሚሉትን ሀሳብ እየደጋገሙ ይናገራሉ።የአንድነት ማህበር ዋና ጸሐፊ ደግሞ፣ተለያየተው የኖሩ እናትና ልጆች ብዙ እፍዳ ደርሶባቸው፣ከብዙ ዓመታት በኋላ ሲገናኙ ምን ውል ያስፈልጋቸዋል?በማለት ለማስረዳት ሲሞክሩ፣ወልደአብ ፊታቸውን አጥቁረው ለማዳመጥ የማይጥማቸው መሆኑን ያሳያሉ።በዚህ ጊዜ ተድላ ግልፍ ይላቸውና፣ኧረ ለመሆኑ መሠረተ ትውልድዎየት ነው?ብለው ይጠይቋቸዋል።ትውልዴ አክሱም አጠገብ ከምትገኝ “ዓዲ ክልተ”ከምትባል ቀበሌ ነው ብለው፣ወልደአብ ይመልሳሉ።አቶ ተድላ ቀጠል ያደርጉና፤ትውልድዎ አክሱም ከሆነ፣ታዲያ የኤርትራ ጉዳይ ምን ይመለከትዎታል?ይሏቸዋል።ወልደአብ በገነፈለ ስሜት “—–እንኳንእኔአክሱምአገሬ፤በኩረሎሚየሚሸተውትውልዴቀርቶ፤ከናይጄሪያየመጣጀዓሊ፣ከየመንየመጣጀቦሊ፣በኤርትራኖሬአለሁብሎ፣ስለኤርትራእድልለመናገርችሎየለምወይ?—ብለው መለሱላቸው።”

ወልደአብ ወልደማሪያም የመጀመሪያውና አንጋፋው የኤርትራ ግንጠላ አራማጅ እንደሚሉት “ንጹሕ”የአክሱም ተወላጅ ከሆኑ ኢትዮጲያን ያለ ባህር በር ባስቀረው የአገር ክህደት ወንጀል ላይ ከመረብ ወዲያ ማዶ ብቻ ተወለዱ የምንላቸውን “የለየላቸውን”የኤርትራ ልጆች ብቻ ለመወንጀል አይመችም።የጉዳዩ ውስብስብነት ሰለሞን ዴሬሳ እንዳለው የጦርነትና የፍልሰት ታሪክ ባጥለቀለቃት ኢትዮጲያ ውስጥ “የጠራሁ አማራ፤የጠራሁ ኦሮሞ፤የጠራሁ ትግሬ ማለት ጥጋብ ነው”ሲል የተናገረውንም ያስታውሰናል።ያውም ሰማይን በማሽቀንጠር እግዜሩን ካራቀብን የበቅሎ እርግጫ የባሰና አሁን በቀድሞ ኢትዮጲያውኖች ወይም በኤርትራውያኖች ላይ መዓት እንዳመጣው አይነት ሌላ መዓት የሚያስከትል ጥጋብ።

የመዋዠቅ መብት

የኢትዮሚዲያን የወቅቱን መፈክር ሳነሳ እስከ ቅርብ ጊዜ የነበረው የቀድሞ መፈክሩ ትክዝ አለኝ።ህዋሃት ሊታደስ አይችልም።ልክ እንደ አፓርታይድመፍረስ ነው ያለበት።የሚል ነበር።ታዲያ በቅርቡ ኢትዮሚዲያ ከዚህ መፈክሩ በተጻራሪ ሁኔታ ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ደብረፅዮን የመሳሰሉትን አይነት ሰዎች የህዋሃት አዳሽ አድርጎ በማቅረብ ወያኔዊው አገዛዝ የመታደስ ተስፋ እንዳለው በርዕሰ አንቀፅ መልክ በማስቀመጥ ያሳየው የአቋም መዋዠቅ አግራሞትን ፈጥሮም እንደነበር ትዝ ይለኛል።

ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው እጅግ አድርጎ መርገምት የተጠናወተው የኢትዮጲያ “ፖለቲካ” እንዲህ ያለ መዋዠቅ ቢያስከትል ሊያስገርመንም ሊያናድደንም እንደማይገባ፤ይልቁንም ኢትዮጲያ የተባለችውን መሰረታችንን እስካለቀቅን ድረስ በዚያው መሰረት ላይ ሆነን በተስፋ እና በተስፋ መቁረጥ መካከል ብንዋዥቅ ሊበረታታ እንደሚገባ፤መዋዠቃችንም ተስፋ ባደረግን ጊዜ እንደ ስዬ፣ብርሃኑ፤ነጋሶ፤ልደቱ፤እስክንድር፤ዳዊት ወዘተ የመሳሰሉ ግለሰቦችንም ጭምር እስከማምለክ ወይም ሰማይ ድረስ እስከ መቆለል ሊወስድን እንደሚችል፤ ተስፋ ስናጣ ደግሞ እርስ በርስም ሊያዘረጣጥንም እንደሚችልና ይህም በኛ ብቻ የሚታይ ሳይሆን በሌሎችም አገር ሕዝቦች ላይ የሚታይ መሆኑን በማወቅ የ”መዋዠቅ መብታችንን”ተጥቅመን ከስህተታችን ትምህርት እየወሰድን መቀጠል እንችላለን።ዋናው ቁም ነገር ግን መረጃ በመስጠት ተግባር ላይ ተሰማርተናል የምንል ሰዎች ከመዋዠቃችን በፊት–ምንም እንኳ ሰዎች እንደመሆናችን ባንዳንድ ጉዳይ እኛም ከመዋዠቅ ባናመልጥም—በጥንቃቄ ማሰብና መመርመር ይጠበቅብናል።ከዚህ አንጻር ኢትዮሚዲያ ልክ ህዋሃት ሊታደስ አይችልም ባለበት አንደበቱ በህዋሃቱ ውስጥ ጥርሳቸውን የነቀሉና ሌላ ሕይወት የማያውቁ ሰዎችን ከመለስ ሞት በኋላ ሊያድሱን ይችላሉ እንዳለው አይነት መዋዠቅ ነገ ተነስቶ ወደብ ባይኖረንም ግድብ ይበቃናል እንደማይል ተስፋ አለኝ።

እኔም ዋዠቁ መሰለኝ። መሰረታችን ኢትዮጲያ እስከሆነች ድረስ በኢትዮጲያ ጉዳይ  የመዋዠቅ መብት የማይጠበቅበት ምን ምክንያት አለ?ቅንነቱ እስካለ ድረስ ዋዥቀን ዋዥቀን ረግተን መቆማችን አይቀር።

Email;kiflukam@yahoo.com

Twitter;@Hussainkiflu

http://ecadforum.com/

posted by Tseday Getachew

የአቶ መለስ ዜናዊ “ያልተገለጡ ገፆች” – ከበትረ ያዕቆብ

ዉድ የሀገሬ ልጆች ከሁሉም በማስቀደም እንደምን ናችሁ ? ደህና ናችሁ ? 2006 እንዴት ይዟችኋል ? ስል የጠበቀ የወዳጅነት ሰላምታየን ማቅረብ እወዳለሁ፡፡ እዚህ ላይ ይህ ሰዉ ምን ነካዉ!? ባልተለመደ መክኩ ሰላምታ አበዛሳ !? ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ ሆኖም አትፍረዱብኝ፡፡ “አሸባሪ ፣ አክራሪ ፣ ጅሀዳዊ ፣ ተለጣፊ ፣ ነጭ ለባሽ”… ወዘተ የሚል ቅፅል ስም ለሀገር ወዳድና ለመብታቸዉ መከበር ድምፃቸዉን ለሚያሰሙ ሁሉ በጅምላ እየተሰጠ ዜጎች በሀሰት በሚወነጀሉበት ሀገር ፤ በእያንዳንዷ ቀን እንደ መልካም ተግባር መሰል ዜጎችን ጠልፎ ለመጣል የተንኮል ወጥመድ ሲጠመድ በሚዋልበት ጊዜ ፣ ንፁህ ዜጎች በግዳጅ ያልፈፀሙትን ኃጢያት እንዲናዘዙ በሚገደዱበት ዘመን ፤ በልቶ ማደር ፍፁም በከበደበት በዚህ የጭንቅ ወቅት አጥብቆ ደህንነትን መጠየቁ ተገቢ ሆኖ ስለታየኝ ነዉ፡፡ እንደዉም ከዚያም በላይ ብዙ ብል እንኳ የሚበዛ አይመስለኝም፡፡ የሆነ ሆኖ ለሰላምታ ያህል ይህን ካልኩ ወደ ዋናዉ ርዕሰ ጉዳየ በቀጥታ ልለፍ፡፡
እንደሚታወቀዉ ምንም እንኳን የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ህዝብ ከሰራቸዉ በጎ ስራዎች ይልቅ ያጠፋዉ ለሚዛን የከበደ ቢሆንም ህልፈቱን ተከትሎ በፓርቲዉና በዙሪያዉ በተሰባሰቡ ጥቂትጥቅመኛ የህብረተሰብ ክፍሎች እስከዛሬ ያለ እረፍት እየተወደሰ ይገኛል፡፡ ጀግና ፣ የልማት አርበኛ ፣ የዲሞክራሲ ዘብ ፣ የአፍሪካና የዓለም ምርጥና ድንቅ ባለራዕይ ፣ አስታራቂ አባት ፣ የሰላም ሰባኪ ፣ ብልህ ሽማግሌ ፣ ጥበበኛ ፣ መለኛ ፣ የደሀ ተቆርቋሪ ፣ የፍትህ ሰዉ ፣ ፈላስፋ ….ብዙ ብዙ እየተባለና በርካታ ከንቱ ዉዳሴ እየተዥጎደጎደለት ነዉ፡፡ ሀሰተኛ ታሪክ እንደ ልብ ወለድ እየተፃፈለትና እየተተረከለትም ይገኛል፡፡
ለምሳሌ በቅርቡ አንድ በየኢትዮጵያ ቴሌቭዥን “ያልተገለጡ ገፆች” በሚል በቀረበ ዘጋቢ ፊልም የሰዉየዉ ታሪክ እኛ ኢትዮጵያዊያን ከምንኮራባቸዉ የዘመነ አድዋ ጀግኖች ታሪክ ጋር ተነፃፅሮ የቀረበ ሲሆን ፤ “ኢትዮጵያን በብቃትና በታማኝነት ያገለገለ ተወዳዳሪ የማይገኝለት መሪ” ተብሏል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን አንድ ጉዳዮን የሚያዉቅ ወዳጄ ፊልሙ በተለያዩ የሀገር ዉስጥ ቋንቋዎች ሰፋ ባለ መልኩ ዳግም እየተዘጋጀ እንደሆነ ሹክ ብሎኛል፡፡ እንዳጫወተኝ እነዚህ ፊልሞች ለህዝብ እይታ በቅርቡ ይቀርባሉ፡፡
ኢህአዴግ/ህወሓት የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን እዉነተኛ ታሪክ በማድበስበስ ህዝብን ለማሳሳት እያደረገ ያለዉ ሙከራ መጠነ ሰፊ ነዉ፡፡ ከቴሌቭዥንና ራዲዮ ባሻገር ከእዉነት የራቁ አሳሳች ታሪኮች በተለያዩ ድህረ ገፆች አማካኝነትም ለህዝብ እየቀረቡ ይገኛል፡፡ ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪም በተለያዩ የዉጭ ቋንቋዎች መሰል ታሪኮች እንዲሰራጩ በመደረግ ላይ ነዉ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያየ አንድ የዉጭ ዜጋ የሆነ ወዳጄ በፕሮፖጋንዳዉ አለቅጥ መለጠጥና እየተሰራጩ ባሉት ታሪኮች ተደንቆ “መንግስታችሁ ስራ አጣ እንዴ!?..” ሲል በቅርቡ ተርቦኛል፡፡ አያይዞም “እንዴት ነዉ እኛ የማናዉቀዉ መለስ ዜናዊ የተባለ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበራችሁ?” ሲል ፈገግ አድርጎኛል፡፡ እንደማስበዉ ኢህአዴግ/ህወሓት ለምን የመለስን ታሪክ ማሰማመር እንደፈለገ ለብዙዎች ሚስጥር አይመስለኝም፡፡ እንደሚታወቀዉ ሰዉየዉ የዚህችን አገር የፖለቲካ መዘወሪያ ለ21 አመታት ያለተቀናቃኝ በጫንቃው የተሸከመና በሁሉም ነገር ላይ አራጊ ፈጣሪ የነበረ እንደመሆኑ የእርሱ ታሪክ የገዥዉ ፓርቲ እንዲሁም የሌሎች አመራሮች ታሪክ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነዉ፡፡ ስለሆነም ስልጣኑን ተቆጣጥሮ የቀጠለዉ ፓርቲና አመራር ለራሱ የተሻለ ገፅታ ለመስጠት የግድ የሰዉየዉን መልካም ያልሆነ ታሪክ ማስተካከል አለበት ማለት ነዉ፡፡ እንግዲህ አሁን እየተደረገ ያለዉም ይህ ይመስለኛል፡፡
ዉድ አንባብያን እንግዲህ እኔም ይህችን ፅሑፍ ለመፃፍ ምክንያት የሆነኝ ይህ ኢህአዴግ/ህወሓት የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን እዉነተኛ ታሪክ በማድበስበስ ህዝብን ለማሳሳት እያደረገ ያለዉ ሰፊ ሙከራ ሲሆን ፤ እዉነቱ ይፋ ወጦ የህዝብ መወያያ ሊሆን ይገባል የሚል ፅኑ እምነት አለኝ፡፡ ምክንያቱም የሰዉን እዉነተኛ ታሪክ (ያዉም ሀገርን ያህል ትልቅ ነገር ለረጅም ጊዜ የመራን ሰዉ) ሰርዞና ደልዞ ለህዝብ ማቅረብ በጣም አደገኛ ዉጤት የሚያስከትል ተግባር ነዉና፡፡ እንዲህ አይነት ተግባር ሰዎች በሰሯቸዉ ስህተቶች ተወቃሽ እንዳይሆኑና ትዉልድም ከታሪክ እንዳይማር የሚያደርግ ፣ ተተኪ ወጣቶች ትናንት አባቶቻቸዉ ባለፉበት የስህተት ጎዳና ደጋግመዉ እንዲያልፍ በር የሚከፍት ነዉ፡፡ ስለሆነም ሊደበቅ እየተሞከረ ያለዉን የአቶ መለስን ማንነት በዚች አጭር ፅሑፌ በትንሹም ቢሆን ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡ ሰዉየዉ በስልጣን ዘመኑ በማናለብኝነት በሀገርና በህዝብ ላይ የፈፀማቸዉን ወንጀሎች በመዘርዘር ለሕዝብ ዳኝነት እተወዋለሁ፡፡ ከዚህ ሁሉ በፊት ግን ለግንዛቤ ያህል የሰዉየዉን የህይወት ታሪክ ጠቅለል ባለ መልኩ አስቀምጨ ልለፍ፡፡
እንደሚታወቀዉ የትናንቱ ለገሰ ዜናዊ የዛሬዉ አቶ መለስ ዜናዊ በወርሃ ግንቦት 1947 ዓ.ም ነበር በአድዋ ከተማ የተወለደዉ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በአድዋ ንግስተ ሳባ ትምህርት ቤት የተከታተለ ሲሆን ፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በጀኔራል ዉንጌት አጠናቋል፡፡ ከዚያም ከፍተኛ ዉጤት በማስመዝገብ አዲስ በበባ ዩኒቨርስቲ ህክምና ለማጥናት መግባት የቻለ ቢሆንም ብዙም ሳይገፉበት ነበር ወታደራዊዉን አምባገነን የደርግ ስርዓት ለመታገል ወደ በረሀ የወረደዉ፡፡ በወቅቱ በኢትዮጵያ ያለዉ ጭቆና የብሔር ጭቆና ነዉ የሚል እምነት የነበረዉ ወጣቱ ታጋይ ፤ መፍትሄዉ ትግራይን ከቀረዉ የኢትዮጵያ ክፍል በመገንጠል የትግራይን ሪፐብሊክን መመስረት ነዉ የሚል ፅኑ እምነት ነበረዉ፡፡
በትግሉ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ በተለያዩ ከፍተኛ የሀላፊነት ደረጃዎች ህወሀትን በሙሉ አቅሙ ያገለገለ ሲሆን ፤ በድርጅቱ ዉስጥ ከነበረዉ ቁልፍ ሚና አኳያ የትግሉ አርክቴክት ነበር ማለት ይቻላል፡፡ አቶ መለስ በ1983 ትግሉ በድል ሲጠናቀቅ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት መሆን የቻለ ሲሆን ፤ ቆይቶም ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት በመሸጋገር እስከ እልፈተ ሞቱ ሀገሪቱን ያለአንዳች ተቀናቃኝ በማንአለብኝነት መምራት ችሏል፡፡
1. የኤርትራ መገንጠል
አቶ መለስ ዜናዊ 21 ዓመት መዝለቅ በቻለዉ ያስተዳደር ዘመኑ በሀገርና ህዝብ ላይ ከባድ ወንጀሎች ፈፅሟል ፤ እነርሱም በተለያዩ የታሪክ መፅሐፍት ላይ በዝርዝር ተጠቅሰዉ ይገኛል፡፡ ሰዉየዉ ከፈፀማቸዉ እነዚህ ወንጀሎች መካከል በዋነኝነት ተጠቃሹና በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥም ሁሌም የሚታወስበት በግብፅና በአንዳንድ የአረብ ሀገራት አጋዥነት ኤርትራን እንድትገነጠል ማድረጉ ነዉ፡፡ እዚህ ላይ ምንም እንኳን የበርካታ የህወሀት አመራሮች እጅ በዚህ ወንጀል ዉስጥ ቢኖርበትም የአንበሳዉን ሚና የተጫወተዉ እሱ ነበር ለማለት የሚያስደፍሩ በርካታ መረጃዎች አሉ፡፡
በርካታ የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት የኤርትራ መገንጠል ህግን እና ህጋዊ አካሄድን ያልተከተለ ከመሆኑም ባሻገር የኢትዮጵያን ጥቅም ከግምት ዉስጥ ያላስገባ ፤ የአረቦችን ፍላጎትና የኢሳያስን ገደብ የለሽ የስልጣን ጥም ለማሟላት ሲባል ብቻ ሆን ተብሎ የተደረገ ነበር፡፡ በወቅቱ በርካታ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን (ለቁጥር የሚታክቱ ኤርትራዉያንም ጭምር) ድርጊቱን በመቃወም ድምፃቸዉን ሲያሰሙ የነበረ ሲሆን ፤ ለነርሱ የአቶ መለስ ምላሽ ስድብ ነበር፡፡
በትግል ወቅት አቶ መለስ የኤርትራ ባለቤት ነን ከሚሉት የሻብያ መሪዎች በላይ ስለኤርትራ መገንጠል ያቀነቅን ነበር፡፡ ተስፋ ወደ መቁረጡ በተቃረቡበት ወቅትም “አይዟችሁ ኤርትራን በቅርቡ ከኢትዮጵያ ትገነጥላላችሁ ፣ በርቱ” እያለ ከመደገፉ ባሻገር ትግላቸዉን የሚያግዝ አስትራቴጅክ መፅሐፍም ፅፎ አበርክቶላቸዋል፡፡ ኤርትራ ከእናት ሀገሯ ከተገነጠለች በኋላም አለም እንደ ሀገር ይቀበላት ዘንድ እንደ መለስ ወዲያ ወዲህ ያለ የለም ማለት ይቻላል–ኢሳያስ አፈወርቂም ቢሆን እንኳ፡፡ በዚህም ምክንያት የወቅቱ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በነገሩ ግራ እስከመጋባት ደርሶ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ አንዳንዶችም የሰዉየዉን ኢትዮጵያዊነት እስከመጠራጠር ደርሰዉ ነበር፡፡
2. የኢትዮጵያ የባሕር በር (አሰብ)
አሰብ በታሪክና በህግ የኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ የበሀር በር የመሆኗ ጉዳይ አሌ የማይባል እዉነት ነዉ፡፡ ይህንንም በርካታ ምሁራን ሰነድ እያጣቀሱ ደግመዉ ደጋግመዉ በግልፅ አስረድተዋል፡፡ ሆኖም ግን አቶ መለስ ዜናዊ እዉነቱን እያወቀ (ለእርሱ ብቻ ግልፅ በሆነ ምክንያት) ይህንን ትልቅ ሀገራዊ ሀብታችንን ከእጃችን አይናችን እያየ እንዲያመልጥ አድርጓል፡፡ ይህም የብዙ ኢትዮጵያዉያንን ልብ የሰበረና እስካሁን እንቆቅልሹ ያልተፈታ ጉዳይ ነዉ፡፡
አቶ መለስ አሰብን በተመለከተ ጥፋት ያጠፋዉ ከአንድም ሁለት ሶስቴ ነዉ፡፡ የመጀመሪያዉ ጥፋት ኤርትራ ከኢትዮጵያ ስትገነጠል ወደቡ ወደ ኢትዮጵያ እንዲጠቃለል ማድረግ እየተቻለ (ህጉም እየፈቀደልን) ለኤርትራ መሰጠቱ ነዉ፡፡ በወቅቱ ለምን የሚል ተቃዉሞ ሲነሳ አቶ መለስ ይግረማችሁ ብሎ ለኤርትራ ሽንጡን ገትሮ በመከራከር ኢትዮጵያ ጥንታዊ የባህር በሯን በተመለከተ አንድም ጥያቄ እንዳታነሳ አድርጓል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በ1989ዓ.ም የኤርትራን ዉረራ ተከትሎ ኢትዮጵያ አሰብን በእጇ የምታስገባበት ሌላ እድል ተፈጠሮ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ያላደላት ሀገራችን የዚያን ሁሉ ልጆቿን ህይወት ገብራ ጦርነቱን በድል አድራጊነት ብትወጣም በአቶ መለስ ትዕዛዝ ወደ አሰብ ድርሽ እንዳትል ተደርጓል፡፡ ከዚህም በኋላ የአልጀርስን ድርድር ተከትሎ ብዙ ኢትዮጵያዊ ምሁራን ተስፋ ሳይቆርጡ መንግስት ወደቡን በተመለከተ ለአደራዳሪዉ አካል ጥያቄ እንዲያነሳ ከመማፀን ባሻገር ለድርድሩ የሚረዱ ጠቃሚ የታሪክ ፣ የህግና የፖለቲካ መረጃዎችን በዝርዝር ማቅረብ ችለዉ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ የፈየደዉ አልነበረም፡፡ የሆነዉ የብዙዎችን አንገት ያስደፋ ነበር፡፡ አቶ መለስና ግብር አበሮቻቸዉ ከኤርትራ ጎን ቆመዉ ለኤርትራ ጥቅም በመከራከር በገንዘብ የማይተመነዉን እጅግ ጠቃሚ የሀገር ሀብት ለኤርትራ አስረክበዉ ተመለሱ፡፡ እነዚህን በሀገርና ወገን ላይ የተፈፀሙ ክህደቶችና ወንጀሎችን በተመለከተ ዶክተር ያዕቆብ አሰብ የማናት በተሰኘዉ መፅሐፋቸዉ ላይ በደንብ አንድ ባንድ ያብራሩዋቸዉ በመሆኑ ዝርዝር መረጃ ማግኘት የሚፈልግ ሰዉ መፅሐፉን ማንበብ ይቻላል፡፡
ዛሬ ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም ወደብ ከሌላቸዉ ጥቂት ሀገራት ዉስጥ ትልቋና ብዙ ህዝብ ያላት ስትሆን ፤ በየቀኑ ከ4 ሚሊዩን ዶላር በላይ ለጅቡቲ የወደብ ክራይ እንድትከፍል ተገዳለች፡፡ ይህም የሁላችንን ኪስ የሚፈታተን ከፍተኛ የዋጋ ንረት እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ወደብ አልባ መሆናችን ሙሉ በሙሉ በሌላ አገር ላይ ጥገኛ እንድንሆን ምክንያት የሆነ ሲሆን ፤ የደህንነት አደጋም ጋርጦብናል፡፡ የአለማችን ዋና እስትራቴጅክ አካባቢ ከሆነዉ የቀይ ባህር አካባቢ መራቃችንን ተከትሎም በዲፕሎማሲዉ መስክ የነበረን ተፅዕኖ ፈጣሪነት እጅግ ተዳክሟል፡፡
3. የባድመ ጦርነት
ሻቢያ በ1989 ዓ.ም በድፍረት ድንበር ተሻግሮ ኢትዮጵያን መዉረሩ በተሰማ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ነበር በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵዉያን ለነፍሳቸዉ ሳይሳሱ የአገራቸዉን ዳር ድንበር ለማስከበር ወደ ጦር ግንባር የተመሙት፡፡ ይህንን ተከትሎ ኢትዮጵያ ጦርነቱን ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን እግረ መንገዷንም ሌሎች ጥቅሞቿን ታስጠብቃለች የሚል ግምት በብዙዎች ዘንድ ነበር፡፡ በተለይም አሰብ እንደገና በኢትዮጵያ ህዝብ እጅ የመግባቱ ጉዳይ ላይ ማንም አልተጠራጠረም፡፡ ሆኖም ግን በጣም ዘግናኝ ከሆነ ጦርነት በኋላ የመከላከያ ሰራዊታችን ወደ መሀል ኤርትራ መገስገስ ሲጀምር አቶ መለስ ዜናዊ በአስቸኳይ እንዲመለስ ትዕዛዝ በመስጠት ለወገኖቻችን ህይዎት መጥፋት ምክንያት የሆነዉን የሻብያ መንግስት ታደገ ፤ የዚያን ሁሉ ወጣት ኢትዮጵያዊ ህይወት ትርጉም አሳጣ ፣ ተሳለቀበት፡፡
በዚህም ያልተገታዉ አቶ መለስ ዜናዊ በአልጀርሱ ድርድር ላይ ሌላ አሳፋሪ ተግባር ፈፀመ፡፡ ተገቢነት የሌላቸዉና ፍርስ የሆኑ የ1900 እና የ1902 የቅኝ ግዛት ዉሎችን ለድርድር በመምረጥ የሻቢያን ህልም እዉን አደረገ፡፡ የዚያ ሁሉ ወጣት ደም የፈሰሰለትን ባድሜን ፣ ኢሮብን እና ፆረናን ለሻቢያ አስረክቦ በዶ እጁን ተመለሰ፡፡
4. የመተማ መሬት
አቶ መለስ ዜናዊ በስልጣን ዘመኑ በሀገር ላይ ከፈፀማቸዉ ወንጀሎች መካከል አንዱና የቅርብ ጊዜዉ የመተማ ጉዳይ ነዉ፡፡ ሰዉየዉ የተጠናወተዉ ሀገርን እየቆረሱ ለባዕዳን የመስጠት አባዜዉ አለቀዉ ብሎ ሰፊ የመተማን ለም መሬት ከኢትዮጵያ ህዝብ እዉቅና ዉጭ ሸንሽኖ ለሱዳን ያስረከበ ሲሆን ፤ ይህንን ተግባሩን በተቃዎሙት የአካባቢዉ አርሶ አደሮች ላይም ብዙ በደል ፈፅሟል፡፡ በቅርብ የወጡ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በአሁኑ ሰዓት መንግስት ለህዝብ በግልፅ ባላሳወቀበት ሁኔታ ኮሚቴ በማቋቋም አዲሱን ድንበር የማካለል ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡
5. ታሪክ ማጠልሸት
አቶ መለስ ዜናዊ ከሚታወስባቸዉ ተግባራቶቹ መካከል ከታሪክ ጋር የነበረዉ መረን አልባ ቅራኔ ነዉ፡፡ ይህ ሰዉ የ5 ሽህ ዓመት ታሪክ ባለቤት የሆነችዉን ሀገራችንን የመቶ ዓመት ዕድሜ ባለቤት ናት ከማለት ጀምሮ በርካታ የታሪክ ክህደት ፈፅሟል፡፡ ለእርሱ ሰንካላ የፖለቲካ ፍልስፍናና እረጅም የስልጣን እድሜ ያመቸዉ ዘንድ የፈለገዉን ታሪክ ሰርዟል ፣ ደልዟል፡፡ ያሻዉን ታሪካችን ነዉ ሲል ተከራክሯል፡፡ የአክሱም ታሪክ ለወላይታዉ ምኑ ነዉ …ወዘተ ሲል በሀገርና በህዝብ ላይ ቀልዷል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለማችን ከሚገኙ ጥቂት ቀደምት ታሪክ ካላቸዉ ሀገራት መካከል በግንባር ቀደምነት የምትጠቀስ ናት፡፡ ከዚህም ባለፈ የሰዉ ልጅ መገኛ መሆኗ ልዩ ያደርጋታል፡፡ የሚገርመዉ ይህን ታሪካችንን በርካታ ምሁራን የመሰከሩለትና በምርምር የተረጋገጠ በመሆኑ ጠላቶቻችን እንኳን የሚቀበሉት ነዉ፡፡ ሆኖም ይህ ሁሉ እዉነት ለአቶ መለስ አልሰራም፡፡
6. ኢትዮጵያዊ አንድነትን ማዳከም
ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች አገር ናት፡፡ እነዚህ የተለያየ ባህል ፣ ቋንቋና ሐይማኖት ያላቸዉ ህዝቦች ለበርካታ ዘመናት በአብሮነት ተከባብረዉና ተዋደዉ ኖረዋል፡፡ በአንድነት የደስታ ዘመናትን እንዳሳለፉ ሁሉ በርካታ አሳዛኝ ጊዚያትንም ተጋርተዋል፡፡ ተጋብተዉ ወልደዋል ፣ ከብደዋል፡፡ አብረዉ የዉጭ ጠላትን በደምና ባጥንታቸዉ ተከላክለዋል ፤ ደማቅ ታሪኮችን ሰርተዋል፡፡ ሆኖም የአቶ መለስን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ ይህ ኢትዮጵያዊ አንድነት ችግር ላይ የወደቀ ሲሆን ፤ ዛሬ እየተባባሰ መጦ በሀገሪቱ ሁለንተናዊ ደህንነት ላይ ጥላ አጥልቶበታል፡፡
አቶ መለስ ሲመቸዉ አንዱን ብሔር ጨቋኝ አንዱን ተጨቋኝ አድርጎ በማቅረብ እንዲሁም አንዳንድ በብሔር ብሔረሰቦች መካከል የተከሰቱ ያለፉ አለመግባባቶችን እየነቃቀሰ ህዝቦች በተለመደዉ አብሮነት እንዳይቀጥሉ በርካታ ጥረት አድርጓል፡፡ አንድ የሚያደርጉንን የጋራ እሴቶቻችንን በማደብዘዝ በመሀከላችን ልዩነት እንዲፈጠር ተግቶ ሰርቷል፡፡ ይህንን ሁሉ ያደርግ የነበረዉ ደግሞ ያን የሚሳሳለትን ስልጣን ለማስጠበቅ ብቻ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለሀገሪቱ ፍቱን ነዉ ሲል የፈለሰፈዉ ብሔር ተኮር ፌደራሊዝምም ቢሆን ከመስማማት ይልቅ አለመስማማትን እያጎለበተና ሌላ መዘዝ እያመጣብን ይገኛል፡፡
7. ምርጫ 97
እንደሚታወቀዉ ህወሀት/ኢህአዴግ ወደስልጣን ከመጣበት 1983ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ኢትዮጵያዉያን በአቶ መለስ ትእዛዝ በግፍ ተጨፍጭፈዋል ፣ በወጡበት ቀርተዋል፡፡ ለቁጥር የሚታክቱ ተደብድበዋል ፣ ታስረዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል በጋምቤላና በሶማሊያ ክልል የተፈፀሙትን መመልከት በቂ ነዉ፡፡
ምርጫ 97ን ተከትሎ ድምፃችን ይከበር በሚል አደባባይ በወጡ ንፁሐን ዜጎች ላይ የተፈፀመዉ ዘግናኝ ወንጀል አንዱ በአቶ መለስ ቀጥተኛ ትዕዛዝ የተፈፀመ የቅርብ ጊዜ ክስተት ነዉ፡፡ በወቅቱ ስልጣኔ ለምን ተነቀነቀ በሚል አዉሬ የሆነዉ አቶ መለስ የሀገሪቱን መከላከያ ሰራዊት በእርሱ እዝ ስር እንዲሆን በማድረግ በሰጠዉ መመሪያ መሰረት በአዲስ አበባ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ፣ ህፃናትና አዛዉንት የጥይት ሲሳይ ሆነዋል፡፡
እንደ ማጠቃለያ
አቶ መለስ ዜናዊ በሀገርና ህዝብ ላይ የፈፀመዉን ወንጀል ዘርዝሮ ለመጨረስ ይከብዳል፡፡ ሀገርን ከመካድና ከመናድ ባሻገር በርካታ ግፍ ፈፅሟል፡፡ ዜጎችን አስጨፍጭፏል ፤ በግፍ ንፁሀንን በእስር ቤት አሳጉሯል ፤ ምስኪን ደሀ ቤተሰቦችን ከቀያቸዉ አስፈናቅሏል ፤ የሀገርና የህዝብን ሀብት አስመዝብሯል ፣ መዝብሯል፡፡ እንግዲህ ይህ ነዉ የአቶ መለስ ዜናዊ ትክክለኛ ማንነት ፤ ይህ ነዉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለአፍታም ሊዘነጋዉ የማይገባዉ ነጥብ፡፡

http://ecadforum.com/

posted by Tseday Getachew

Post Navigation

%d bloggers like this: