Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

ጃዋርና የቀቢጸ ተስፋ እርምጃዎቹ (ክፍል 5)

Jawar Mohamed Muslim fundamentalist

January 26, 2014

ዓለማየሁ መሀመድ (ክፍል 5)

እንደምን ከረማችሁ?

መረጃ 1

ኦሮሞ ፈርስት በሚል ጃዋርና ሸሪኮቹ የከፈቱት ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ሰንበቴ ቤትን በተመለከተ ከዚያው መንደር የደረሰኝ መረጃ ነው። ይህ ማህበር ከመቋቋሙ በፊት ጃዋር ያላንኳኳው በር; ያልረገጠው ደጃፍ የለም። ጃዋር የቢዝነስ ጭንቅላት ያለው ይመስላል። ነጋዴ ነገር ነው። ገንዘብ እንዴት እንደሚገኝ ያውቅበታል። በአቋራጭ እንዴት መበልጸግ እንደሚችል ቀን ከሌሊት ያውጠነጥናል። በእርግጥ ኦሮሞ ፈርስት ጥሩ ብልሃት ናት። የሀረሩ አብዲ ሙተቂ እንጋለጠው ጃዋር ኦሮሞ ፈርስት የተሰኘውን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለማቋቋም ደጅ ከጠኑት ሰዎች አንዱ አፈንዲ ሙተቂ ነው። አፈንዲ እንዲህ ዓይነቱ ጸበል ቅመሱ አላማረውም። የጃዋር የገንዘብ ስግብግብነት መጨረሻው ከወዴት እንደሆነ በጠዋቱ ነው የተገለጠለት። የኦሮሞን ህዝብ ትግል ለጨረታ ያቀረበው ጃዋር እንደ በግ ነጋዴ የኦነግን የከሰረ ፕሮጀክት ተሸክሞ ገበያ ወጣ። ፖለቲካ የምግብ ዓይነት ይሁን የኳስ ክለብ ምን እንደሆነ በውል ያላወቁ ጥቂት አክራሪዎችን ከጎኑ አሰልፎ ጃዋር ኦሮሞ ፈርስትን አስመረቀ።

ጃዋር ጥሩ የገቢ ምንጭ አግኝቷል። ኒውዮርክ ከአንድ አፓርታማ ተሸጎጦ ጫቱን እያመነዥገ፡ ጥላቻ የሚረጭበትን ዓላማ  ከዳር ለማድረስ የከፈተው ፕሮጀክት እያስገኘለት ያለው ገቢ ቀላል የሚባል አይደለም። በአንድ የኦሮሞ ፈርስት መድረክ 2ሺህ ዶላር ይከፈለዋል። ይሄ የተጣራው ኪሱ የሚገባው ነው። ከለንደኑ የኦሮሞ ፈርስት መድረክ የጀመረ ደግሞ ሚስቱንም አስገብቷታል። እሷም እንደ አንድ ፓናሊስት ትቀርባለች በሚል ጃዋር የቢዝነስ አድማሱን አስፍቷል። እናም በየኦሮሞ ፈርስት መድረክ ጃዋር ሚስቱን እያንጠለጠለ ይጓዛል። በዚህም እነ ጃዋር ቤት በአንድ የኦሮሞ ፈርስት መድረክ 4ሺህ ዶላር ይገባል። ከዚህ በላይ ቢዝነስ የት ነው ያለው?

በነገራችን ላይ ሚስቱ አርፋሴ የኢትዮጵያን ምድር ረግጣ አታውቅም። ወላጆቿ ኬኒያ የሚኖሩ እዚያው ኬኒያ የወለዷት የኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ናቸው። አርፋሴ የኢትዮጵያን አፈር አታውቃትም። ኬኒያ ተወለደች፡ እዚያው ቆየች፡ አሜሪካ መጣች። ጃዋር ከአክራሪም  ጽንፈኛ የሆነው በእሷ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። አርፋሴ ደሟ ውስጥ የተቀበረ የኢትዮጵያ ጥላቻ እንዳላት የቅርብ መረጃዎች ያሳያሉ። አንድ ጊዜ በኒውዮርክ የሆነ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ተካሄደ አሉ። የሁሉም ሀገራት ተወላጆች በፌስቲቫሉ ላይ የየሀገራቸውን ባንዲራ ይዘው በመቆም ለጎብኚዎች ስለመጡበት ሀገር ያስተዋውቃሉ። አርፋሴ የኦነግን ባንዲራ ይዛ ከመሀል ቆማለች። ጎብኚዎች ይጠጓትና ይጠይቋታል።

‘’የት ነው ይሄ ሀገር’’

‘’ኦሮሚያ ‘’   አርፋሴ ስትናገር ሀፍረት የሚባል ነገር የለም። ፈርጠም ብላ ነው የምትናገረው

‘’ኦሮሚያ የት ነው ያለው?’’

‘’…ከሶማሊያ ጎን….. ከአቢሲኒያ በታች፡…… ከኬኒያ በላይ….ሱዳን እግር ስር…..’’   አርፋሴ የትኛውን የዓለም ካርታ እያነበበች እንደሆነ ከሷ በቀር ማንም አያውቅም። ፈረንጆቹ ግራ ገባቸው።

ካርታ አውጥተው

‘’ኦሮሚያ የሚባል ሀገር እዚህ ካርታ ላይ የለም’’ ይሏታል። አርፋሴ የሌባ ዓይነ ደረቅ አይደለች?!

የማይነበብ ለእሷ እንጂ ለሌሎች የማይታየውን በመንግስታቱ ድርጅት የማይታወቀውን በእሷና በመሰሎቿ ምናብ ውስጥ የሳሏትን ኦሮሚያ የምትባል ሀገር ፈጥረው አደባባይ የወጡበትን የቅዥት ታሪክ ለፈረንጆችም ሊነግሩ ተነስተዋል። ፈረንጆቹ ግራ ገባቸው። ትተዋት ሄዱ። መቼም እብድ ናት ሳይሉ አይቀሩም።

ሴት የላከው ሞት አይፈራም። አርፋሴ ጃዋርን ጃስ ትለዋለች። ‘’ሉቡ ኪያ!’’ ስትለውማ ጃዋር ሜንጫ ፍለጋ አይኑ ይማትራል። ባልና ሚስት ከአንድ ወንዝ ይቀዳል ቢባል ከአርፋሴና ጃዋር በልጦ ምስክር የሚሆን ከየት ይገኝ ይሆን?

አሁን አርፋሴ ቢዝነስ ላይ ናት። ከባሏ ጋር 4ሺህ ዶላር በአንድ ስብሰባ እያፈሰች ናት። በ1ወር ሁለት የኦሮሞ ፈርስት መድረኮች ከተዘጋጁ እነጃዋር ቤት 8ሺህ ዶላር በወር ይገባል። በአመት ከ80ሺህ ዶላር በላይ። አሜሪካውያን 80k የሚሉት።

መረጃ 2

ጃዋር በስመጥሩ የስታንፈርድ ተቋም የስኮላር ሺፕ ትምህርቱን ተከታትሏል። መቼም ስታንፈርድ የተማረ አይደለም በአጠገቡ የተጠጋ የሚኖረው የእውቀት ደረጃ፡ ከአሁኗ ዓለም ጋር የሚፈጥረው ትስስር፡ በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም። ከራስ ጥረት በተጨማሪ ዕድልንም ይጠይቃል ስታንፈርድ ለመግባት። ጃዋር ይሄን እድል አግኝቷል። ትምህርቱንም አጠናቆ ወጥቷል። ይሄ በአደባባይ የሚታወቅ ዕውነታ ነው። ውስጡን ለቄስ ይላሉ አበው ሲተርቱ?! ጃዋር ከስታንፈርድ የተመረቀው በአካለ ስንኩል ደረጃ (disability status) ነው ቢባል አሁን ማን ያምናል?

አዎን! ሀቁ ከወዲህ ነው ያለው።ጃዋር ከጥይቶቹ የስታንፈርድ ተማሪዎች ጋር የሚፎካከርበት አቅም አልነበረውም። ለነገሩ ማንም ሰው እንዲሁም መገመት የሚችል ይመስለኛል። ገና ከመንደር የጎሳ ጭንቅላት ያልተላቀቀ ወጠጤ፡ ዓለምን ገልብጠውና ተልትለው ከሚረዱት ምጡቅ ተማሪዎች ጋር ተፎካክሮ ይወጣል ማለት የማይታሰብ ነው። እናም ጓድ ጃዋር መውጪያ ቀዳዳ ፍለጋ ብልሃት መጣለት። በኤትዮጵያ እያለ በደል ይደርስበት፡ ስቃይና መከራ ይፈራረቁበት እንደነበረ፡ ህይወቱን በሙሉ መንግስትና የአማራው ገዢ መደብ እንደሚያሰቃዩት በመዘርዘር የአይምሮ ጉዳት እንደገጠመው፡ ይህም በትምህርት የመቀበል አቅሙ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰበት በመተረክ ደብዳቤ ያስገባል። የስታንፈርድ ተቋምም ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ጃዋር ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በእኩል ደረጃ መመዘን የለበትም የሚል ውሳኔ ያስተላልፍና የተለየ ድጋፍ እንዲደረግለት ያዛል። ጃዋር የአካለጎዶሎ መብት ተሰጠው። በቃ! ፈተና ላይ የሚሰጠው ጊዜ ከሌሎቹ ተማሪዎች በእጥፍ የበለጠ ነው። በውጤት ደረጃም የጃዋር የማለፊያ ነጥብና የሌሎቹ የተለያየ ነው። በዚህ መልኩ ነው እንግዲህ ጃዋር ከስታንፈርድ የተመረቀው።

የደህንነት መስሪያ ቤት ዘመቻ

የወያኔ የደህንነት መስሪያ ቤት የወያኔ ዕድሜ ለማራዘም ከሰማይ በታች ያለውን ማንኛውንም እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅቷል። በዚህም የተለያዩ ዘመቻዎችን ከፍቷል። ምንጮች እንዳረጋገጡት እነጃዋር በሚኒሊክ ላይ የከፈቱት ዘመቻ የዚሁ የደህንነት መስሪያ ቤት ዕቅድ አንዱ አካል ነው። እነጃዋር ከወያኔ ጋር ጋብቻ ለመፈጸማቸው ማረጋገጫው ሆኖ ተወስዷል። ባለፈው የሀረሩ አፈንዲ ሙተቂ እንደጻፈው ጃዋር ከወያኔ ጋር ይሰራል። ምናልባት የሙተቂን ሀሳብ እብዳለ እዚህ ላስቀምጠው።

‘’ይህ ሰው በጣም አጭበርባሪ ነው፡፡ የውሸት ወሬ መፈብረክ ይችልበታል፡፡ ደግነቱ የሚፈበርካቸውን ወሬዎች ሀሠትነት ለማረጋገጥ ረጅም ጊዜ አይፈጅም፡፡ የዚህ ሰው ሌላኛው ባህሪ ደግሞ ለሁሉም የፖለቲካ ቡድኖችና ፓርቲዎች የሚሰራ መሆኑ ነው፡፡ ሰውዬው ከላይ ሲታይ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ይመስላል፡፡ ሆኖም አብዛኛው ሰው እንደሚያውቀው ከኦፒዲኦ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋርም የጠበቀ ግንኙነት አለው፡፡ አንድ ቀን ሳያስበው ይህንን ግንኙነቱን ግልጽ ያደረገበትን ጥያቄ ጠየቀኝ፡፡ እኔ በሰጠሁት ምላሽ ሳስደነግጠው ትንሽ እንደማፈር ብሎ ዘጋው (በወቅቱ የጠየቀኝን ጥያቄ ሌላ ጊዜ ብነግራችሁ ይሻላል)፡፡ በርሱ ቤት ነገሩን የማላውቅ መስሎታል፡፡ ይሁንና በፌስቡክም ጭምር በሰፊው ሲባል የነበረ ነገር በመሆኑ ብዙም አልደነቀኝም፡፡’’

የጃዋርንና የወያኔን ጋብቻ በተመለከተ ከዚህ በፊት ብዙ ስላልኩበት አሁን አልመለስበትም። አፈንዲ የተናገረው ከበቂም በላይ ነው። እንደዚህ ያለ ምስክርነት ለጃዋር የአደጋ ምልክት ነው። ጃዋር የወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚ ስለመሆኑ የማያምን ካለ እሱ ወይ ራሱ ወያኔ ነው አልያም ሳያላምጡ ከሚውጡት ጃዋራውያን አንዱ ነው ወይም ደግሞ አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም አይነት ነገር ነው።

ከደህንነት መስሪያ ቤት አከባቢ የተገኘው መረጃ እንደሚያረጋግጠው ገና በርካታ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ዘመቻዎች በወያኔ በኩል ይከፈታሉ። የእነጃዋር ቢባርቅም በተወሰነ ደረጃ የተንጠባጠቡትን ለቃቅመሞ ውዥንብርና ጫጫታ ለመፍጠር መሞከሩ የሚጠበቅ ነው። በእርግጥ የእነጃዋር ጫጫታ ከፌስ ቡክ መንደር ብዙም ርቀት መሄድ አልቻለም። የጃዋር ተከታዮች ልጆቻቸውን እዚህ በእንግሊዘኛ እያስተማሩ ኦሮምኛ ቋንቋ በልጆቻቸው አፍ ዝር እንዳይል እየተከላከሉ፡ ሀገር ቤት ያሉትን ምስኪኖች የቁቤ ትውልድ በተሰኘች መሸንገያ ከኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር ደም ለማቃባት መፍጨርጨራቸው በቀጣይም የሚጠበቅ ነው። ለዚህም የወያኔ የደህንነት መስሪያ ቤት መዋቅር ዘርግቶ እየሰራበት ነው።

የቀቢጸ ተስፋው ዘመቻ

አሁን ጫጫታው በርዷል። 21ኛው ክፍለ ዘመንን ያረከሱት እነጃዋር ጥጋቸውን ይዘው የመከላከል ስትራቴጂን የሙጥኝ ብለዋል። የተኮሱት ጥይት ዞሮ እነሱ ላይ እየተምዘገዘገ ነው። ባርቆባቸዋል። ለ40 ዓመት ኦነግን በርስትነት ይዘው የቆዩት እነ ሌንጮ ለታ ወደ ሀገር ቤት እንገባለን ብለው ማወጃቸው ለነጃዋር ግራ የሚያጋባ ሆኗል። ኦህዴድን ከኦነግ ጋር በመቀየጥ ወይም በማጋባት አዲስ ጽንፈኛ የኦሮሞ ድርጅት ለመፍጠር ከወያኔ ጋር እየሰራ ላለው ጃዋር የእነ ሌንጮ ለታ ወደ ሀገር ቤት እንገባለን ዜና አስደንጋጭ ነው። ወያኔ ምን እያደረገ ነው? ለጃዋር ጥሩ ጊዜ ከፊት እየመጣ አይመስልም። ወያኔ ጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ እያሰላ የሚንቀሳቀስ ማፊያ ድርጅት መሆኑን ጃዋር በእርግጥ አያውቅም ማለት ይከብዳል። ለነገሩ በአካለ ጎዶሎ መብት ለተመረቀ ወጠጤ አእምሮ ውስብስቡ የወያኔ ሴራ የሚከብደው ይመስላል።

አሁን ነገሮች ውል እየያዙ ነው። ጃዋርን ለፍርድ ለማቅረብ የተጀመረው ዘመቻ ተቀጣጥሏል። የህግ ባለሙያዎች እንዳረጋገጡት ጃዋርን ለዘር ማጥፋት ወንጀል ቅሰቀሳ በማድረግ በሚለው ክስ ችሎት ለመገተር የሚያስችሉ በቂ የድምጽ፡ የቪዲዮ እና የጽሁፍ ማስረጃዎች አሉ። የሚቀረው ፊርማ አሰባስቦ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ነው። ያም እየተሰራበት ነው። በሌላ በኩል በሰለጠነው የምዕራቡ ኣለም እየኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈጸም በሚቀሰቅሱት ጽንፈኛ ኦሮሞች ላይ የሚከፈተው ክስን በተመለከተ የህግ ምሁራን እየመከሩበት ሲሆን ጉዳዩ  ከተጀመረ ለእነጃዋርና መንጋዎቹ መጪው ጊዜ በጨለማ የተጋረደ እነደሆነ እየተነገረ ነው።

እናም የቀቢጸ ተስፋ እርምጃዎች በጃዋርና መንጋዎቹ በኩል እየተካሄደ ነው። ምን ያህል ርቀት ይወስዳቸው ይሆን? የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር በቅርቡ የሚረጋገጥ ይሆናል።

Advertisements

Single Post Navigation

Comments are closed.

%d bloggers like this: