Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

Archive for the month “December, 2013”

አድርባይነት (ለጥቅም ሕሊናን መሸጥ)

ከማርቆስ ዐብይ

ኢትዮዽያ ሀገሬ ሞኘ ነሸ ተላላ፣
የሞተልሸ ቀርቶ የገደለሸ በላ፣

The Ethiopian government spokesman Shimeles Kemal

እኚ ሰው የኮሚኒኬሸን ጉዳዮች ሚንስትር ዴእታ አቶ ሽመልሰ ከማል ይባላሉ…

አድርባይነት ቀለል ባለ አገላለጽ ማስመስል ወይም ለጥቅም ሲባል ሕሊናን መሸጥ እንደማለት ነው፣፣ ይህ እኩይ ባሕሪ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ቀላል የማይባል እድሜ አስቆጥሯል የሩቁን ትተን የቅርቡን ከጣሊያን ወረራ ቦኋላ ያለውን አሁን እስካለንበት ጊዜ ያለውን ለማየት ብንሞክር እንኳ በጣም ብዙ ነገሮችን መታዘብ እንችላለን።

ጣሊያን ኢትዮጵያን በግፍ በወረረበት ወቅት የክርስቶስን ወንጌል ይሰብኩ ከነበሩ የሐይማኖት አባቶች መካከል በጥቅማ ጥቅም የተደለሉ ጥቂት የሐይማኖት አባቶች በየአውደ ምሕረቱ ለምዕመናን ከመጽሃፍ ቅዱስ ላይ ኤሳው ለምስር ወጥ ሲል ብኩርናውን አሳልፎ ለወንድሙ ለያዕቆብ መሸጡን በመጥፎ ተምሳሌትነት እንዳላስተማሩ ሁሉ ራሳቸው ለቁራሽ እንጀራ ሲሉ ሕሊናቸውን በመሸጥ ከወራሪው ከጣሊያን ጎን በመሰለፍ ለምዕመናኑ በሃሰት በእግዚአብሔር ሃምሳል ኢትዮጵያን ለመታደግ የመጣ ነው በማለት ሕዝቡ ወራሪው ጣሊያንን አሜን ብሎ እንዲቀበል ያግባቡ ነበር።

በዚህ የወረራ ዘመን የንጉሠ ነገሥቱ የቅርብ ባልሙዋል ከነበሩ መኩዋንንቶች እና መሳፍንቶች መካከል ሳይቀር ለጣሊያን ያደሩ ነበሩ፣፣ እነዚህ ሹማምንቶች ህዝቡ ተቃውሞውን በማቆም ይዘውለት የመጡትን እውቀት እና ስልጣኔ በመቅሰም ሀገሩን ያለማ ዘንድ ሰዎቹን በትዕግሰት እንዲጠብቃቸወ በሀሰት ይሸነግሉት ነበር።

ታዋቂው ደራሲ አቤ ጎበኛ የረገፉ አበቦች በሚል ርዕሰ ያሳተሟት ልብ ወለድ መፅሃፍ ውስጥ ስለነዚህ ከዳተኞች የአድርባይነት መጠን ማሳያ የሚሆን አንድ ታሪከ ያሰነብቡናል፣ ይህውም በዚያ ዘመን የነበሩ በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ ትልቅ ስም ያላቸው አንድ ሰው ነበሩ እኚ ሰው ባለቤታቸው ሲወልዱ ትልቅ ግብዣ አዘጋጅተው ብዙ ሰው ይጋብዛሉ ከተጋባዡቹ መካከል የጣሊያን ወታደሮች የክብር ቦታ ተዘጋጅቶላቸዋል በግብዣው ሰፍራ ላይ ተገኝተዋል አሳላፊዎች ሰውን ለማስደሰት ከወዲህ ወዲይ ይራወጣሉ በዚህ መሀል ከክብር እንግዶች አጠገብ ተጎልተው የነበሩት ጋባዠ በእጅ ምልክት ሰውን ፀጥ እንዲል በማድረግ የልጃቸውን ሰም በታዳሚው ፊት ለማውጣት እንደሚፈልጉ ገለፁ በማሰከተልም ልጄን ሮማ (ROMA) ብያታለሁ አሉ አድናቆትና ጭብጨባ የክብር እንግዶች ካሉበት አካባቢ ብቻ ቀረበ የተቀረው ተጋባዠ እነሱን ተከትሎ አጨበጨበ እንጂ ሰለሰሙ የሚያውቀው ነገር ስለሌለ ነገሩ እሰከሚገለፅለት ድረሰ አላወቀም ነበር፣ በመቀጠልም ሮማ አሉ በአሰመሳይነት ኩራት የጌቶቻችን ሀገር ዋና ከተማ ነች ብለው ተቀመጡ፣ ሰው ሕሊናውን ሲሸጥ መቼም እራሱንብቻ ሳይሆን ቤተሰቡንም ለመሰዋትነት ያቀርባል።

መቼም እንዳያልፈው የለምና ያ የመከራ ጊዜ አለፈና በአርበኞች ፅናትና ተጋድሎ ዘመቻው በድል ተጠናቀቀ ፣ ወራሪው ጣሊያን በኩራት የተመላለሰባቸው እነዛ ጎዳናዎች በሃፍረት አንገቱን አቀርቅሮ የሞተው ሞቶ የተረፈው በደመነፍሰ ተራወጠባቸው በግፍ የወረራትን ሃገር በሃፍረት ጥሉዋት ፈረጠጠ ፣ እነዛ ወራሪውን አዝለው ህዝቡን ሲያሰጨንቁት የነበሩት ሆዳደሮች ግን ያዘሉትን ያህል እንኩዋን ሊያዝላቸው ቀርቶ እጃቸውን ይዞ የሸሸበት ያህል እንኩዋን ይዟቸው ሊሄድ አልወደደም እንደ ፓሰታ መቀቀያው ዕቃ የትም ጥሏቸው ሄደ እንጂ፣ እነዚ ከመጣው ጋር እንደ ሴተኛ አዳሪ ወዳጅ መሰለው መቅረብ እንደ መልካም በሐሪ የተጣባቸው ግለሰቦች አርበኞች ወደ ከተማ ሲገቡ ፀጉራቸውን አሳድገው ተቀላቀሉዋቸው እኛ ልጃቸውን ሮማ ብለው የሰየሙ ግለሰብም የልጃቸው ሰም ላይ ’ን’ በመጨመር ሮማን በማለት አይናቸውን በጨው አጥበው ከአርበኞች ጋር ላይ ታች ሲሉ ያያቸው የሀገሬው ሰው በትዝብት እጁን አፉ ላይ ጭኖ በመገረም ነበር የሚያያቸው ይሉናል አቤ ጎበኛ።

እሰካሁን ለመቃኝት የሞከርነው ህሊናቸውን ሸጠው ታሪክ አበላሸተው ወደማይቀረው ሞት ሰለነጎዱ ሰዎች ነው፣ አሁን ደግሞ በህይወት ያሉ ነገር ግን ህብረተሰቡ አፈር ካለበሳቸውና ሃውልታቸው ላይ ሆዳደር ብሎ ካተመባቸው ግለሰቦች መካከል ለናሙና አንዱን በመውሰድ እናወጋለን ከዛ አሰቀድመን ግን እንደመሸጋገሪያ ይሆነን ዘንድ ከጥቂት አመታት በፊት ጠቅላይ ምኒሰትር መለሰ ዜናዊ የሀገር ሸማግሌዎችን ሰብሰበው ሲያወያዩ አንድ የሃይማኖት አባት የተናገሩትን አሰገራሚ ንግግር እናሰቀድም እንዲህ ነበር ያሉት “በአባቶቻችን እሰከ አሁን ድረስ ሲነገር የቆየው ከወደ ሰሜን በመነሳት ኢትዮዽያን በጠነከረ አንድነት የሚያሰተዳድራት ንጉስ ይመጠል የተባለው ትንቢት ተፈፀመ ይህውም አንተ ነህ ብለው ጣታቸውን ወደሰብሳቢው ጠቆሙ” እሳቸውም በትዝብት ፈገግ ብለው ምላሸ ሰጡ፣ እኝህ አሰተያየት ሰጪግለሰብ ሀገሪቱ ቋንቋን መሰረት ባደረገ ክልል ተሸንሸና እንደባቢሎን ሰዎች እርስ በእርሰ መግባባት እንዳልተቻለ ሳያውቁ ቀርተው አይደለም ይህን ባሉበት ወቅት ሰዎች በዘመቻ መልክ ክልላችሁ አይደለም እየተባሉ የዘሩትን ሳይሰሰቡ ከየቦታው የሚፈናቀሉበት ውቅትም ነበር ይህንንም አሳምረው ያውቃሉ ነገር ግን እሳቸው እያሰሉ ያሉት ይህን መናገራቸው እንደውለታ ተቆጥሮላቸው ወደ ቅያቸው ሲመለሱ ስለሚደረግላቸው ከንቱ ውዳሴ ወይም ስልጣን ብቻ ነው፣ ይህን እዚህ ላይ ቋጭተን እሰኪ በአዲሰ መስመር ላይ እላይ ወደጀመርነው አንድ አስገራሚ ሰው እንመለስ።

እኚ ሰው የኮሚኒኬሸን ጉዳዮች ሚንስትር ዴእታ አቶ ሽመልሰ ከማል ይባላሉ፣ አቶ ሽመልሰ በመጀመሪያ ኒሻን የምትባል የግል ጋዜጣ በማቋቋም የመንግስትን ስህተት እየነቀሱ በጣም ጠንከር ባለ አገላለፅ ይተቹ ነበር ከዚህ ጎን ለጎን ሌላው የሚታወቁበት ደግሞ መንግስት በውሃ ቀጠነ የሀሰት ክሰ ጋዜጠኞችን ፍርድ ቤት ሲያቆማቸው እሳቸው ባላቸው የህግ እውቀት በነፃ ፍርድ ቤት በመቆም ለንፁሃን ጋዜጠኞች ሸንጣቸውን ገትረው በመከራከራከረቸው ነበር ፣ እኚህ ስው ታዲያ ትንሽ ጠፋ ብለው ከራርመና ሲመለሱ ባንዴ ጎፈር ሆነው ሲያወግዙት የነበረው መንግስት ባለስልጣን በመሆነ ከኔ በላይ ታማኝ የለም ብለው ቁጭ አሉ፣ ያኔ በደጉ ጊዜ ከህሊናቸው ጋር በነበሩ ሰአት ሲሟገቱላቸው የነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸውን ንፁሃን ጋዜጠኞችን መሰረተ ልማት ለማውደምና የመንግሰት ባለስልጣናት ለመግደል ከአሸባሪዎች ጋር ሲያሴሩ እጅ ከፍንጅ ያዝናቸው ብለው በአደባባይ ህጉን እያወቁት ከፍርድ ቤት ቀደመው ፍርድ አስተላለፉ፣ እነዚያ ንፁሃን ጋዜጠኞችም ያለጥፋታቸው የእድሜአቸውን እኩሌታ ዘብጥያ እንዲያሳልፉ የፖለቲካ ውሳኔ ተወሰነባቸው እናቃሊቲ ተወረወሩ፣ እኚህ ግለሰብ መንግስት እራሱን አሻሸሎ ነው የተቀላቀሉት እንኩዋን እንዳይባል እርሳቸው ስልጣን ላይ ከመውጣታቸው በፊት የነበረው የጋዜጠኞች የመሰራት ነፃነት አሁን ካለው ዘጠና በመቶ ይሻል ነበር ታዲያ ምን ነካቸው ከተባለ መልሱ ለጥቅም ሲባል ሕሊናቸውን ሸጡ ይሆናል።

ሰው ሕሊናውን በጥቅም ከተያዘ ዕውቀትና ስልጣን መጠሪያው ከመሆን የዘለለ ፋይዳ የለውም ፣ በጣም የሚገርመው እኚህ ሰው መንግስትን በመወከል በተደጋጋሚ የተናገሩዋቸውን ንግግሮች አለቆቻቸው ውድቅ በማድረግ ሸመልስ ያለው ውሸት ነው በማለት በአደባባይ ሲያዋርዱአቸው በፊት ለሎች ሲከራከሩ የነበሩ ሰው እንዳልነበሩ ሁሉ በጥቅም ስንሰለት እግር ተወርቸ ታሰረው እራሳቸውን እንኩዋን መከላከል አቅቷቸው ሲወራጩ በመታዘብ አይተናል።

ባጠቀላይ ህሊና ትንሹ እግዚአብሔር ነው ይባላል መልካም ስንሰራ የሚያበረታታን መጥፎ ሰንሰራ ደገሞ እንድንፀፀተና ዳግም እንዳንሰራ እረፍት የሚነሳን ታድያ ሰው ይህንን ትልቅ ነገር አጥቶ ሀብትና ዝናን ቢሰበሰብ እንዴት የዓይምሮ ሰላም ሊያገኝ ይችላል?

“ሰው እግዚአብሔርን አጥቶ አለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ምን ይጠቅመዋል” እንዳለው መፀሃፍ ቅዱስ፣

ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቅ!

posted by Tseday Getachew

Advertisements

ፍርድ ቤቱ አንድነት በኢቴቪ ላቀረበው ክስ ውሳኔ መስጠት ተስኖታል

ዳዊት ሰለሞን
መስከረም 3/2004 የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ የሆነውን አንዷለም አራጌ፣የብሄራዊ ምክር ቤት አባሉን ናትናኤል መኮንንና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በቁጥጥር ስር መዋላቸው አይዘነጋም፡፡መንግስት ተጠርጣሪዎቹን ካሰረ በኋላ አሁን በህይወት የሌሉት መለስ ዜናዊ በፓርላማ‹‹ማስረጃም መረጃም አለን››በማለት እነአንዷለም ሽብርተኞች ስለመሆናቸው በድፍረት መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ኢቴቪም ከጸረ ሽብር ግብረ ሀይል ጋር በመተባበር መለስ የፎከሩበትን መረጃና ማስረጃ ‹‹አኬልዳማ››በሚል ርዕስ ለማሳየት መዘጋጀቱን አታሞ መጎሰም ጀመረ፡፡አኬልዳማ ተጠርጣሪዎቹን ከፍርድ ቤት በፊት በሽብርተኝነት የወነጀለ፣ፓርቲውን ከሽብርተኛ ተቋማት ጋር ጋብቻ እንደፈጸመ አድርጎ በተራ ውንጀላ የፈረጀና የአንድነት አባላት ያልሆኑ ሰዎችን አባላት በማድረግ ያቀረበ የተለመደው ማጥላላት፣ሴራና ውሸት በመሆኑ ፓርቲው ለኢቴቪ አቤቱታ በማቅረብ እርምት እንዲወሰድ ይጠይቃል፡፡የኢቴቪ ቦርድ አመራሮች ግን ለዚህ ጆሮ አልነበራቸውምና፡፡በጥር 2004 ፓርቲው ክሱን አቀረበ፡፡
የፓርቲው ጠበቆች በቢፒአር መታየት ይገባዋል በማለት በፍጥነት እንዲታይላቸው ያቀረቡት ክስ እነሆ እስካሁን ድረስ ውሳኔ ሳያገኝ በድጋሜ ለጥር ወር ቀጠሮ ተሰጥቶታል፡፡ለ20ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበው ክሱ በጥር ወር ሁለተኛ አመቱን ይደፍናል፡፡

posted by Tseday Getachew

የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ መጽሐፍ ጻፉ

ከክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)
ፀሃይ አሳታሚ ድርጅት በታኅሣሥ 16, 2006 ዓ/ም (Dec. 25, 2013) የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን የሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስን ‘እኛና አብዮቱ’ የሚል መጽሃፍ ለገበያ እንደሚያበቃ አስታወቀ። ሻምበል ፍቅረሥላሴ እንደ ደርግ አባልነታቸው በጋራ ያመኑበትን፣ የተማከሩትን፣ የወሰኑትን፣ የሰሩትን፣ የገጠማቸውንና በቅርብ በዓይን ምስክርነት ያዩትን ተንትነው በ‘እኛና አብዮቱ’ ያስነብቡናል። የራሳቸውን ዕይታ ያካፍሉናል።

ልጅ ሆነን አንድ አባባል እሰማ ነበር።”አበላል እንደ ደርግ አባል። አለባበስ እንደ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ!” – የሚል። በተለይ በኔ ትውልድ ያለን ሰዎች፣ ከዚህ ውጭ ስለኝህ ሰው የምናውቀው ብዙም ነገር አልነበረም። ግና እኝህ ሰው በልባቸው መክሊት ለአመታት የቋጠሩትን መረጃ ጀባ ሲሉን፤”… አጻጻፍም እንደ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ” የሚያሰኝ ሆኖ አገኘሁት።

ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ለአስራ አምስት ዓመታት አብዮቱን ሲመሩ ቆይተው ወደ መጨረሻው ከሥልጣን በጡረታ ስም እንዲሰናበቱ ተደርገዋል። ደርግን በጣለው በወያኔ መንግሥትም ለ፳ ዓመታት ታስረው፣ የሞት ፍርድ የተበየነባቸውና በመጨረሻ ፍርዱ ወደ ዕድሜ ልክ ተዛውሮላቸው ከእሥር ቤት በአመክሮ የወጡ ግለሰብ ናቸው።

ጸሃፊው በድራማ መልክ በመጽሃፋቸው ካሰፈሩዋቸው እውነታዎችና ግለ-ሂሶች ውስጥ አንዳንዶቹን ለአንባቢያን ማካፈሉ አይከፋም። ደርጎች መፈንቅለ መንግስት አድርገው ሲያበቁ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘንድ ቀርበው ከንጉሱ የገጠማቸውን አስገራሚ ምላሽ ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ በመጽሃፋቸው እንዲህ ሲሉ አስፍረዋል።

የፖለቲካ እሥረኞች በሙሉ እንዲፊቱ የሚለው ጥያቄ እንደተነበበ ንጉሡ ጣልቃ ገብተው “ለመሆኑ የፖለቲካ እሥረኞቹ እነማን ናቸው?” የሚል ጥያቄ አቀረቡ። “በእርግጥ የምናውቃቸው የፖለቲካ እሥረኞች ባይኖሩም ማንኛውም የፖለቲካ እሥረኛ እንዲፈታ ነው የምንጠይቀው” አሉ ሻለቃ ተስፋዬ ገብረኪዳን። ንጉሡ ራሳቸውን ነቅነቅ አድርገው ጽሑፉን የሚያነበውን የደርግ አባል እየተመለከቱ “አልገባችሁም!” ብለው ዝም አሉ። በእርግጥም አልገባንም። ተማሪዎችና የተለየ ዓላማ የነበራቸው የተማሩ ሰዎች የሰነዘሩትን መፈክር ብቻ ነበር ይዘን ንጉሡ ፊት የቀረብነው። በፖለቲካ እሥረኝነት ስም በከፍተኛ ደረጃ ለጣሊያን ወራሪ መንግሥት በባንዳነት አድረው አገራችንን የወጉ፣ ለቅኝ ተገዥነትም የዳረጉትን እንደ ኃይለሥላሴ ጉግሳ ያሉ ወንጀለኞች የፖለቲካ እሥረኞች ተብለው ከግዞትና ከእሥር ቤት አስወጥተን እንደ ጀግና ራሳቸውን እንዲቆጥሩ አደረግናቸው።

የነ ጄነራል ተፈሪ በንቲ ጉዳይን አስመልክቶ የሰፈረው ታሪክ ደግሞ እንዲህ ይነበባል።

“በሊቀመንበርነት ስብሰባውን የሚመሩት ጄነራል ተፈሪ ‘የቋሚ ኮሚቴው’በዛሬው ቀን የሚወያይበትን ጉዳይ አስመልክቶ የመቶ አለቃ ዓለማየሁ የደርጉ ዋና ፀሐፊ ይገልጽልናል’ ብለው ስብሰባው መጀመሩን ካበሰሩ በኋላ ዓለማየሁ በአጀንዳው ላይ አጭር ገለጣ ማድረግ ሲጀምር ስልክ ተደወለ። ስልኩ ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱ አጠገብ ስለነበር ወዲያው ቅጭል እንዳለ መነጋገሪያውን በማንሳት ሃሎ አሉ። ከሌላው ጫፍ ማን እንደደወለ አላወቀንም። በኋላ እንደታወቀው ሌ/ኮሎኔል ዳንኤል ነበር የደወለው። ምን እንደተነጋገሩ አልተሰማም። ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱ ብቻ “እሺ እሺ” ብለው ስልኩን ዘጉት። ስልኩን እንደዘጉ “ይቅርታ ስልኩ የተደወለው ከጎንደር ነው። ጎንደር ውስጥ ችግር አለ። እናንተ ቀጥሉ” ብለው ከጀርባቸው ባለው በር በኩል ውልቅ አሉ። በዚህን ጊዜ ዓለማየሁና ሞገስ ጥርጣሬ የገባቸው መሰለ። ዓለማየሁ ንግግሩን አቋርጦ በመስኮት በኩል ውጭ ውጭዉን መመልከት ጀመረ። ዓይኖቹ አላርፍ አሉ። ግራና ቀኝ ይመለከታል። አጠገቡ ያሉትን ሰዎች ሁሉ በጥርጣሬ ተመለከተ። ሻምበል ሞገስም በር በሩን ይመለከታል። ከአሁን አሁን አንድ ችግር ይከሰታል የሚል ፍርሃት ያደረበት ይመስላል። ሁሉም የኢሕአፓ አባላትና ደጋፊዎች ፈርተዋል። እንደፈሩት አልቀረም ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱ ከወጡ ሁለት ደቂቃ እንኳን አልሞላም ከበስተጀርባ ባለው ኮሪደር የወታደሮችን እርምጃ ሰማን። ወታደሮች ሲንቀሳቀሱ በፊት ለፊታችን ባሉት መስኮቶች በኩል ተመለከትን። በዚህን ጊዜ ፍስሐ ደስታ “ተከብበናል” አለ። ወዲያው ሁለቱም በሮች በኃይል ተበረገዱ። ሁላችንም ደነገጥን፣ ቀልባችን ተገፈፈ፣ እጢአችንም የወደቀ መሰለን። ድርቅ ብለን በተቀመጥንበት ቀረን።…

ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ሰለ ልጅ ሚካኤልን አስተዋይነት ሲያስታውሱ እንዲህ የሚል ግለሂስም ያስነብቡናል።
እኛ በችኮላ ውሳኔ መስጠታችን፣ ሕዝቡን በደንብ አለማወቃችን፣ ሰፊ የሕዝብ አመራር ልምድ ማጣታችን፣ የአገርና የውጭውን ፖለቲካ ውስብሰባዊ ግንኙነት አለመገንዘባችን፣ የመንግሥትን አሠራር ደንብና ሥርዓት አለመረዳታችን፣ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ጥመርታዊ ግንኙነትን መመልከት አለመቻላችን፣ የተለያየ ገንቢም ሆነ አፍራሽ ተልዕኮ ያላቸው ኃይሎች ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩብ ያለማጤናችን፣ በየዋህነትና በቅንነት ብቻ እንደምንሠራ በመገንዘባቸው ሊሆን ይችላል ልጅ ሚካኤል ከእኛ ጋር መቆየት የሚችሉት ለአጭር ጊዜ ብቻ እንደሚሆን የጠቆሙት…

በወቅቱ ስለ ህዝቡ የእርስ በርስ መጨካከንና መወነጃጀል ባሰፈሩት ክፍል ውስጥ እንዲህ የሚል ታሪክ እናገኛለን።

..የሥራ ዕድገት የተከለከለ፣ በሌብነትም ሆነ በስካር ወይም በሌላ ጥፋት የተቀጣ፣ በግል ጉዳይም ሆነ በመንግሥት ሥራ ከአለቃው ጋር የተጣላ፣ በአጋጣሚው ተጠቅሞ አዲስ ሹመት ወይንም ዕድገት ለማግኘት የሚፈልግ ሁሉ ጠቋሚ፣ ወንጃይ፣ ከሳሽ፣ ተበዳይ ነው።

የተወሰነ ጥቅም ለማግኘት ወይም ሌላውን ለመጉዳት ብለው “ኢትዮጵያ ትቅደምን ይቃወማል፣ ከታሠሩት ባለሥልጣናት ወይም ሚኒስትሮች የቅርብ ዝምድና አለው። ስለሆነም ሥራ ይበድላል፣ ሠራተኛውን ያጉላላል፣ ውሳኔ አይሰጥም” በማለት አለቆቻቸውን የሚከሱ፣ የሚወነጅሉ በርካታ ናቸው። ለደርግ አባላት ቤታቸው ድረስ በመሄድ በማስረጃ የተደገፈ ቢሆንም ባይሆንም ተቆርቋሪ በመምሰል የክስ ማመልከቻ የሚያቀርቡም ነበሩ። እንታሠራለን ብለው በፍርሃት የተደበቁ ባለሥልጣናትን የቅርብ ዘመዶቻቸው ወይም አሽከሮቻቸው ወይም ጎረቤቶቻቸው ደርግ ጽሕፈት ቤት ድረስ በመምጣት ያጋልጧቸው ነበር። የመሥሪያ ቤቶችን ሰነዶች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ወይም ሰነዱን እንዳለ ከፋይሉ አውጥተው በማቅረብ “በመንግሥት ንብረት፣ ሀብት ወይንም ገንዘብ ላይ አላግባብ ተወስኗል” ብለው ጥቆማና መረጃ የሚያቀርቡም ነበሩ። ሠራተኞች አሠሪዎቻቸውን ይከሳሉ፣ ይወነጅላሉ። ገበሬዎች ለዘመናት በደል አደረሱብን የሚሏቸውን የአካባቢ ባለሥልጣናት ይወነጅላሉ። ውንጀላው በርካታ ነው።

አሽከሮች፣ ዘበኞች፣ ገረዶች… መረጃ ይሰጣሉ፣ ይጠቁማሉ። የተደበቀ የጦር መሣሪያ፣ የተደበቀ ገንዘብ፣ ወደሌላ ቦታ የተወሰደ ወይም የሸሸ ሀብት እንዳለም የሚጠቁሙን እነሱ ናቸው። በአንድ ቦታ በርከት ያሉ ሰዎች ተሰብስበው ምሽት ከአሳላፉ “ሲያድሙ ነበር” ብለው ከነስም ዝርዝራቸው መረጃውን ደርግ ጽሕፈት ቤት ድረስ ያመጣሉ። “እኛ እስከዛሬ የበይ ተመልካች ነበርን ዛሬ ዕድሜ ለእናንተ እንጀራ ሊወጣልን ነው! ከእናንተ ጎን ተሰልፈን አቆርቋዦቹን እንታገላለን! በማንኛውም ጊዜ ትዕዛዝ ብትሰጡን ለመፈጸም ዝግጁ ነን!” እያሉ ታማኝነታቸውንና ተባባሪነታቸውን የሚገልጡም ብዙዎች ነበሩ። በጣም የሚያስደንቀው አባቶቻቸውን፣ ልጆቻቸውን፣ ወንድሞቻቸውን፣ እህቶቻቸውን፣ ባሎቻቸውን፣ ሚስቶቻቸውን በመክሰስ፣ በመወንጀል፣ በማጋለጥ፣ በመጠቆም ብሎም በማሳሰር ጉዳት ያደረሱ በርካቶች መሆናቸው ነው።

እንግዲህ ስለ አዲሱ ‘እኛና አብዮቱ’ መጽሃፍ ይህንን ካልኩ ቀሪውን ለአንባቢ መተው ይበጃል። ሁሉም ሰው መጽሃፉን አንብቦ የራሱን ፍርድ ይስጥ።

ህይወት በሩጫ ትመሰላለች። የተፈጥሮ ህግጋት ነውና የሰው ልጅ እስትንፋሱ እስኪቋረጥ ይሮጣል። ከዚያም ሩጫውን ይጨርሳል። ሩጫውን ሳይጨርስ በልቡ ቋጥኝ የያዘውን እምቅ ቋጠሮ የሚተነፍስ ደግሞ እድለኛ ነው። በአንጻሩ ደግሞ በአእምሮው የቋጠረውን የእውቀት ምስጢር ሳያካፍል የሚያልፍ ሁሉ ያሳዝናል። ያለውን የወረወረ ንፉግ አይደለምና መንቀፍም ካለብን የሚወረውረውን ሳይሆን የማይወረውረውን ነው። መተቸት ካለብነም ሃሳቡን እንጂ ግለሰቡን ባይሆን ይመረጣል። በሃሳብ ላይ መወያየትና መተሻሸት ደግሞ አዋቂነት ነው።

በመጨረሻም የመጽሃፉ አርታኢ ኤልያስ ወንድሙ በመግቢያው ላይ ባሰፈረው መልእክት ጽሁፌን ልቋጭ።

የተማረ፣ ያወቀና ያደገ ትውልድና ዜጋ ምልክቱ የተጻፈን ማንበቡ፣ ያነበበውን ማብላላቱና ካነበበው ውስጥ ስንዴውን ከእንክርዳዱ መለየቱ ሲሆን፤ እራሱም አስተውሎና አገናዝቦ መጻፉ ደግሞ መማሩን ብቻ ሳይሆን መመራመሩንና ማወቁን የሚያሳይ ታላቅ ተግባር ነው። ለዚህም ደግሞ ግላዊ ነጻነት ያስፈልገዋልና ጫንቃው ላይ ያሉትን ግላዊና ታሪካዊ ቀንበሮች የሰበረ ነጻ ሰው መሆን ይጠበቅበታል። ትምህርትና ዕውቀት አስተዋይነትንና ጥልቀትን ከራስ በላይ ለትውልድ አሳቢነትን የሚያመለክት ታላቅ ኃላፊነት ነው። ለዚህም እንደ ትናንቱ ‘የተማረ ይግደለን’ ሳይሆን፤ የተማረ ያስተምረን፣ ያስተዳድረን ብሎም ይምራን በምንልበት ዘመን ከምናነብበው ውስጥ ያልተስማማንበትን በጨዋነት የመቃወም፣ የፈቀድነውን እንደ ስሜታችን የመደገፍና ተሳሳተ የምንለውን ለእርማት መጠቆም ግላዊ መብታችን ነው።…

* ፀሃይ አሳታሚ ድርጅት ከዚህ በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያምን፣ የቀድሞውን የህወሃት መሪ ዶ/ር አረጋዊ በርሄን፣ የቀድሞውን የኢህአፓን አመራር አባል የዶ/ር መላኩ ገኝን፣ የቀድሞው ሚንስትር የአቶ ተካልኝ ገዳሙን መጽሃፍትና ከስልሳ በላይ የሆኑ በኢትዮጵያ ታሪክና ጥናት ላይ ያተኮሩ መጽሃፍትን ማሳታሙ ይታወሳል። ‘እኛና አብዮቱ’ የሚለው ይህ አዲስ መጽሃፍ በwww.tsehaipublishers.com ድረገጽና በቀርቡ በየሱቁ አንደሚገኝ ከሎስ አንጀነሰ የደረሰን ዘገባ አስታውቋል። ሁላችንም ገዘተን እናንብብ።

መጽሃፉን አንብቤ እንደጨረስኩ በሂሳዊ ግምገማ እመለስበታለሁ።

posted by Tseday Getachew

በሳዑዲ አረቢያ 80ሺህ ኢትዮጵያውያን እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጠየቀ፤ ሳዑዲዎች አዲስ ዘመቻ ጀምረዋል (አዳዲስ መረጃዎች)

(ዜና ትንታኔ ኢትዮጵያ ሃገሬ ከጅዳ በዋዲ)

በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ አምባሳደር ዘነበ ከበደ የሚመሩት የመንግስት ሹማምንቶች ጅዳ ከተማ ውስጥ፡ መሽገዋል ያሏቸው 80 ሺህ ኢትዮጵያውያን እጃቸውን በሰላም ካልሰጡ የመንፉሃው አይነት እልቂት እንደሚጠብቃቸው ሲያሟርቱ! ሪያድ በኢትዮጵያው አምባሳደር መሃመድ ሃሰን የሚመራው ቡድን የሚያሰማው « ጅብ ከሄድ ውሻ ጮህ ጥሪ » ድብቅ አጀንዳ ያለው መሆኑ ተገለጸ::

ከ9 ሚልዮን በላይ የተለያዩ የውጭ፡ሃገር ዜጎች በጥገኝነት እንደሚኖሩባት የምትታወቀው ሳውዲ አረቢያ በህገወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ሃገር ዜጎች የመኖሪያ ፈቃዶቻቸውን እንዲያስተካከሉ የተሰጠ የ 7 ወር የግዜ ገደብ መጠናቀቅን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች ኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ ባነጣጠረ እርምጃ እስካሁን ቁጥሩ በወል ለማይታወቅ ወገናችን አሰቃቂ ህልፈተ ህይወት ስቃይ እና መከራ ምክንያት መሆኑ ይታወቃል። በተለይ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራ ሰፈር ሃገራቸው ለመግባት ጥያቄ ባቀረቡ ወገኖቻችን እና በሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች መሃከል በተነሳ ግጭት አያሌ እህቶቻችን በአረብ ጎረምሷች ተደፍረዋል እህቶቻቸውን እና ሚስቶቻቸውን ለመከላከል ጩሀታቸውን ያሰሙ ንጽሃን ወገኖች በአሰቃቂ ሁኔታ በሳንጃ እና በጓራዴ ተገድለዋል ፡፤

ይህንንም ተከትሎ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻች ከአሰቃቂው ጥቃት እርሳቸውን ለመታደግ ከዳር እስከዳር «ሆ »ብለው አደባባይ በመውጣት የሳውዲ አረቢያ አውራጎዳናዎችን በማጨናነቅ የአለምን መገናኛ ብዙን ሽፋን በማጝት በሳውዲ አረቢያ በጠራራ ፀሃይ እና በሌሊት በወገኖቻችን ላይ ሲፈጸም የነበረው ጭፍጨፋ ስቃይ እና በደል በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር የሚገኙ ወገኖቻቸውን ዘንድ ቁጣን በመቀስቀስ በሳውዲ መንግስት ላይ ባደረጉት ተጸዕኖ በማን አለብኝነት በወገኖቻችን ላይ ሲፈጸም የነረውን ኢሰባዊ ድርጊት ለግዜውም ቢሆን ጋብ እንዲል አስችሏል።

የኢትዮጵያኑ አለማቀፍ ቁጣ ያስደነገጠው የሳውዲ አረቢያን መንግስት በሚልዮን ለሚቆጠሩ የውጭ፡ሃገር ያወጣው ህግ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ እንዲያትኩር አስገድዶታል። ይህ በዚህ እንዳለ እስካሁን በመቶሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያ ውያን ስደተኞች የስውዲ አረቢያን ምድር በሰላም ለቀው ለሃገራቸው እንደብቁ የሚናገሩ ምንጮች አሁንም 80 ሺህ ህገወጥ ኢትዮጵያውያን ጅዳ ጣይፈ መካ መዲና ከተሞች ውስጥ መሸገዋል ተብሎ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት እይተሰጠ ያለው መግለጫ ቅንነት የጎደለው መሆኑንን ይገልጻሉ። በሃጂ እና ኡምራ አሊያም በባህር ወደ ሳውዲ ምድር ድንበር አቅርጠው ገብተውል ተብለው የሚነገርላቸው ኢትዮጵያውያን ያሉበትን ሁኔታ የማይዘረዘረው በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንላ የመንግስት ሹማምቶች መግለጫ ህገወጥ የተባሉት ወገኖች በግዜ እጃቸውን ሰጠተው ወደ ሃገር ካልተመልሱ በሪያድ መንፉሃ የተከሰተው አይነት አልቂት እንደሚገጥማቸው አስጠንቅቀዋል።

ይህ በቆንስል ዘነበ ከበደ የሚመራው ጽ/ቤት ሰሞኑንን እያሰማን ያለው ጩህት ወገናዊነት የጎደለው እና ሳውዲያኖቹ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ በማነጣጠር መኖሪያ ፈቃድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያን ጭምር ከሳውዲ ምድር ጠራርጎ ለማስወጣት የተያዘ እቅድ አንዱ አካል መሆኑንን የሚናገሩ የጅዳ ነዋሪዎች የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ወገኖች በሳውዲ ምድር በሰላም ሰርቶ የመኖር ህልውናቸው አስተማማኝ ባልሆነበት አጋጣሚ እንደዚህ አይነት መግለጫ ማውጣት ሃላፊነት የጎደለው መሆኑንን ይናገራሉ። እንዚህ ወገኖች የጅዳው ቆንስላ ጽ/ቤት እንደዚህ አይነት አስገራሚ መረጃ በአረብኛ እና በአማርኛ ቋንቋ በተዘጋጁ በራሪ ወረቅቶች ቅስቀሳ ማካሄዱ ትላንት ሪያድ ከተማ መንፉሃ ውስጥ፡ቆጨራ እና ሳንጃ ታጥቀዋል የሚል የተሳስተ መለዕክት በማስተላለፍ ወገኖቻቸውን ካስፈጁት በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አንባሳደር መሃመድ ሃሰን ከፈጸሙት ስህተት የማይለይ መሆኑንን ይገልጻሉ።

በሌላ በኩል ሰሞኑንን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ በየጥጋጥጉ ማስታወቂያዎችን በመለጠፍ እና በራሪ ወረቀቶች በመበትን እያሰማ ያለው የተለመደ የአዞ እንባ « ጅብ ከሄደ ውሻ ጮህ » መሆኑንን የሚገልጹ የአካባቢው ነዋሪዎች የምህረቱን አዋጅ ተከትሎ ጉዳዮቻቸውን እስካሁን ማስፈጸም ተስኗቸው በሳውዲ አረቢያ ውስጥ ለመኖር የሚያስችሏቸውን ማመዘኛ ያላሞሉ ወገኖች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ እየቀረቡ ምዝገባ እንዲያካሂዱ የሚለው መለዕክት ለኢትዮጵያውያኑ ታስቦ ሳይሆን ዲፕሎማቱ የተለመደውን ድብቅ አጀንዳቸውን በቀሪው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ላይ ለማስፈጸም እንደሆነ ይናገራሉ።

በተለያዩ አቅጣጫዎች ያለደረስኝ፡በወገኖቻችን ሽፋን በመቶሺ የሚቆጠሩ ሪያሎችን በመሰብሰብ ላይ የሚገኘው በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች ከተጠቀሱት ወገኖች ኪስ ለተለያዩ ገዳዮች ማስፈጸሚ የሚውል ገንዘብ ለመሰብሰብ እቀድ እንዳላቸው ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይገልጻሉ። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም በወገኖቻችን ላይ ለተፈጸመው አስቃቂ ግድያ ግፍ እና በደል ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ የገቡትን ቃል ከፖለቲካ ግብአትነት እንደማያልፍ የሚናገሩ ወገኖች የኢትዮጵያ መንግስት በሳውዲ አረቢያ መንግስት ላይ ያሳረፈው ምንም አይነት ዲፕሎማሲያዊ ተጽእኖ ባለመኖሩ ሳዑዲያኑ ለኢትዮጵያውያኑ ያላቸው ጥላቻ አገርሽቶ በሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን «በእስፖንሰሮቻቸው» የመኖሪያ ፈቃዳቻቸው በመሰረዙ አያሌ ወገኖች ለህገወጥነት እየተዳረጉ መሆናቸው ይነገራል።

posted by Tseday Getachew

የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን በማሰጠትና ለዜጎች ሞት የሚጠየቁት አቶ አያሌው ጎበዜ ስልጣናቸውን ለቀቁ

(ዘ-ሐበሻ) የአማራ ክልል መሬቶች ለሱዳን እንዲሰጡ ከገዢው ሕወሓት ጋር በመተባበር ወንጀል፣ እንዲሁም ከጉራፈርዳ ተባረው ወደ አማራ ክልል የመጡ ዜጎች የሚቀበላቸው የክልል መስተዳድር ጠፍቶ ለርሃብና ለሞት በመዳረጋቸው በዚህም ወንጀል እንደሚጠየቁ የሚነገርላቸው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አያሌው ጎበዜ ስልጣናቸውን አስረከቡ።

አቶ አያሌው ጎበዜ

መንግስታዊ ሚድያዎች አቶ አያሌው ጎበዜ “በመተካካት” ሂሳብ ስልጣኔን ተረክበውኛል ሲሉ ይዘግቡ እንጂ የአማራ ክልል ምክር ቤት በአስቸኳይ ተሰብስቦ ይሄን ውሳኔ ማጽደቁ ከበስተጀርባው የተደበቀ ምስጢር ሳይኖር እንዳልቀረ ብዙዎች ይገምታሉ። በተለይም አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ሰሞኑን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከሱዳን ጋር የኢትዮጵያን መሬቶች አሳልፈው ለመስጠት ከተፈራረሙ በኋላ የአቶ አያሌው ስልጣኔን ልልቀቅ ጥያቄ ምንልባትም ለሱዳን ከሚሰጠው የኢትዮጵያ መሬት ጋር በተያያዘ ሊሆን እንደሚችል አስተያየታቸውን ለዘ-ሐበሻ ሰጥተዋል።

የአማራ ክልል አስቸኳይ ስብሰባውን ከትናንት ምሽት ጀምሮ በባህር ዳር ያካሄደው የአማራ ክልል ምክር ቤት ክልሉን ላለፉት 8 ዓመት ተኩል የመሩትን የአቶ አያሌው ጎበዜን ጥያቄ ወዲያውኑ በመቀበል ከስልጣን ያወረዳቸው ሲሆን በምትካቸውም በሕወሓት ተላላኪነታቸው ከአቶ ደመቀ መኮንን አይተናነሱም የሚባሉት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተተክተው ተሾመዋል። አቶ ገዱ የአማራ ክልል ም/ል ፕሬዚዳንትና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን አቶ አያሌው አልፈጽምም ሲሉ የነበሩ ሥራዎችን ለሕወሓት በማደር ይሰሩ እንደነበር እርሳቸውን የሚያውቁ ወገኖች ለዘ-ሐበሻ ጠቁመዋል። በተለይም አምባገነንና እኔ ያልኩት ይድመጥ የሚል ባህሪይ እንዳላቸው የሚነገርላቸው አቶ ገዱ የአማራ ክልል ስር ያሉ የኢትዮጵያ መሬቶችን ለሱዳን በመስጠት ከሕወሓት ጋር አብረው እንደሚሰሩ ይጠበቃል።

አቤል የተባሉ በክልሉ የሚኖሩ በፌስቡክ ዘ-ሐበሻን የሚከታተሉ አንድ አስተያየት ሰጪ በሰጡት አስተያየት “ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ክቡር አቶ አያሌው ጎበዜ ዛሬ በአቶ ደጉ አንዳርጋቸው የተተኩበት አስቸኳይ ጉባኤ አንደምታው ምን ይሆን? ምን አልባት ከሠሞኑ የሚሠሙ ወሬዎችን እልባት ለመስጠት ይሆን? ያ ማለt ዐድርቃይን ለትግራይ፣ መተማን ለሱዳን፣ ጃዊ አካባቢ ያለ የአማራ ክልል ግዛቶችን ለመስጠት መሠናክሉን ከወዲሁ ለማቅለል ይሆን እንዴ? ያ ምርጫ፣  ዘመን ሣይጠናቀቅ ከስልጣን አቶ አያሌውን ማንሣት ምን ማለት ነው? እርሣቸው ለክልሉ ልዑላዊነት መከበር ጥብቅና የሚቆሙ ታማኝ መሪ ስለነበሩ ገለል ለማድረግ የታለመ ሹም ሽር ነው የሚል ግምት አለኝ” ብለዋል።

ሌላው የዘሐበሻ የፌስቡክ ተከታይም እንዲሁ “የአማራን ክልል መሬት ለሌላ አሳልፌ አልሰጥም በማለታቸው ስልጣናቸውን እንደለቀቁ ነው” የማምነው ሲሉ አስተያታቸውን ሰጥተውናል።

አንድ ቀን በኢትዮጵያ ነፃነት ሲመጣ ምንም እንኳ እርሳቸው አልፈረሙም፤ የፈረሙት አቶ ደመቀ መኮንን ናቸው የሚባል ወሬ ቢኖርም አቶ አያሌው ጎበዜ ለሱዳን በተሰጠው መሬት፣ በአማራ ክልል ለደረሱ ጭፍጨፋዎች፣ በዜጎች መፈናቀል ዙሪያ ላሳዩት ቸልተኝነት ለፍርድ ይቀርባሉ የሚሉ ወገኖች ብዙ ናቸው።

posted by Tseday Getachew

አቶ አያሌው ጎበዜም የድል አጥቢያ አርበኛ እንደ ውሃ ላይ ኩበት እመሀል ላይ እንደዋለሉ የማይቀረውን ስንብታቸውን ተሰናበተዋል

ዳዊት መላኩ(ከጀርመን)

አያሌው ጎበዜ

አቶ አያሌው ጎበዜም እንደምንም  የመምህርነት ስራቸውን ትተው የድል አጥቢያ አርበኛ በመሆን ገብተው ወይ ራሳቸውን ነፃ ሳያወጡ ወይ ህዝቡን በትክክል ሳያገለገሉ እንዲሁ እንደ ውሃ ላይ ኩበት  እመሀል ላይ እንደዋለሉ የማይቀረውን ስንብታቸውን ተሰናበተዋል፡፡ወያኔ እንደ ሸንኮራ ምጥጥ አድርጎ ተፋቸው፡፡እኔ እስከማውቃቸው አቶ አያሌው ከሌሎች የወያኔ ባለስልጣናት የሚለዮት በሙስና አለመጠርጠራቸው፤ብዙ ማውራት የማይወዱ ሲናገሩም ከባህል እና ከሞራል የማያፈነግጡ፤ለሚኖሩበት ማሀበረሰብ ክብር በመስጠት ሚስታቸው ሳይቀር አብረዋቸው ከሚኖሩት እድርተኞች እኩል መሳተፋቸው ነው፡፡ አቶ አያሌው እንደአባዱላ ገመዳ ብዙ ቤት ገንብተው ለትግሉ ስላስቸገረኝ ውሰዱልኝ ሲሉ አልተደመጡም፡፡እስካሁን ባለኝ መረጃ መሰረት አቶ አያሌው ባህርዳር ከተማ ውስጥ ቀበሌ 14 አካባቢ በማህበር ተደራጅተው በወሰዱት አንድ ቦታ ቤት እንደገነቡ ነው ፡፡ ዘመድ አዝማዳቸውን ስራ በማስገባት አይታሙም ፡፡የአቶ አያሌው ልጆች እንደ ሌሎች የባለስልጣን ልጆች አሜሪካ እና አውሮፓ ወይም አዲስ አበባ ውስጥ ባሉ ውድ የግል ትምህርት ቤቶች አይደለም  የሚማሩት፡፡እንደማንኛውም ደሃ ቤተሰብ ባህርዳር ውስጥ ባሉ የመንግስት ትምህርቤቶች ያስተምሩ ነበር፡፡

አቶ አያሌው እንግዲህ እነዚህ መልካም ነገር ቢኖራቸውም የተሰጣቸውን መክሊት አባክነው የክልሉ ህዝብ በየቦታው ሲፈናቀል የክልሉ መሬት እንደዳቦ እየተሸነሸነ ሲታደል የተቀመጡባትን ወንበር ላለማጣት በዝምታ ማለፍን መርጠዋል፡፡ይህ ደግሞ በምንም መልኩ ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ከሌባ ጋር አብሮ ስርቆት ሂዶ  በቅርብ ርቀት ሲሰርቁ እያዩ ዝም ማለት እና የሰረቀው አብሮኝ ያለው ሰው ነው አንጂ እኔ ነፃ ነኝ ቢሉ ከቅጣት አያመልጡም፡፡እንግዲህ እርሳቸው በስልጣን ላይ በቀዮበት ጊዜ ለጠፋው ሀይወት፤ለወደመው ንብረት፤ለተፈጠረው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ድቀት የድርሻቸውን ይወስዳሉ፡፡

መቼም በዘመኔ ወያኔ ስራና ሰራተኛ ተገናኝተው ባይውቁም እንደአማራ ክልል  ባለስልጣናት በእውቀት ድርቅ የተጠቃ የለም፡፡”ሰው ሢታጣ ይመለመላል ጎባጣ” ነው ነገሩ፡፡ሰው ሲታጣ ማለቴ ለወያኔ በታማኝነት የሚያገለግል ማለቴ ነው፡፡አቶ አያሌውን የተኩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በርቀት ትምህርት በማኔጅመት የመጀመሪያ ዲግሪ ሲኖራቸው በ1998 ዓ.ም የብአዴን ቢሮ ውስጥ ይሰሩ ነበር፡፡የተኛው የተምህርት ዝግጅት ተዛምዶ የክልሉየግብርና ቢሮ ኃላፊ ሁነው እንዲሰሩ እንዳበቃቸው የሚያውቀው ወያኔ ብቻ ነው፡፡ይባስ ብሎ ክልሉን የመምራት ሀላፊነት ለሳቸው መስጠት ከምጡ ወደ ዳጡ ነው፡፡ አቶ ገዱን የአማራ ወጣቶች ከከፍተኛ ትምህርቶች ተመርቀው የፓሪቲ አባል ካልሆኑ ስራ እንዳይሰጣቸው በክልሉ ላሉ ሁሉም ዞኖች ትእዛዝ ሲያስተላልፉ በተቃራኒው አባል ለሆኑት ስልክ ብቻ በመደወል እንዲቀበሉዋቸው ያል ምንም ውድድር እና ማስታወቂ  በደብዳቤ ብቻ ሲመድቡ እንደነበር ይታወቃል፡፡በተለይ በ1998ዓ.ም የንግድ እና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት በወረዳዎች መከፈትን ተከትሎ በሁሉም ወረዳዎች የተመደቡ ፈላፊዎች በዚህ አይነት የተመደቡ ነበሩ፡፡አቶ ገዱ የክልል ፕሬዚዳንት ቀርቶ ለቀበሌ አመራርነት ሚያበቃ ስብእና እንደሌላቸው ሚያወቁዋቸው ሁሉ የሚስማሙበት ሀቅ ነው፡፡ግን ምን ይደረግ ወያኔ በሚመራው ሀገር ውስጥ ለሀገር የሚጠቅም ነገር በነፃነት መስራት ስለማይቻል አንዴ አዲሱ ለገሰ፤አንዴ ደመቀ መኮነን፤አንዴ ገዱ አንዳርጋቸው እተፈራረቁ በህዝቡ ትክሻ ላይ ያለከልካይ ይጫናሉ፡፡

በመጽሀፍ ቅዱስ ታሪክ የምናውቀው ደጉ አብረሀም የተወለደው ያደገው ከጣኦት አምላኪ ቤተሰብ ነበር፡፡  እግዚያብሔርም አብርሀምን “አብርሀም አብርሀም ውጣ !እኔ ወደማሳህም ወደዚያ ተራራ ሂድ አለው”፡፡አብርሀምም ቤተሰቡ የሚያመልከው ጣኦት አይን እያለው የማያይ ጆሮ እያለው የማይሰማ “ልክ እንደ ኢህአዴግ”  ነበርና ከፈጣሪው የመጣለትን ትእዛዝ ሳያመነታ ተቀበለው ፡፡በሀጢያት ከረከሰው አካባቢውም ተለይቶ ወጣ፡፡አብርሀም ያደረገው ከሚወደው ቤተሰቡ  በባእድ አምልኮ አብሮ ላለመኖር የግድ መለየት ነበረበት ተለያም፡፡ዛሬ በተለያዮ የስልጣን እርከን በወታደራዊም ሆነ በሲቪል ተቋማት ከወያኔ ጋር እየሰራችሁ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ልክ እንደ አብረሀም በደም ከተበከለው ፤ህዝብን አፍኖ በችግር እየገደለ ካለው ስርኣት ራሳችሁ ለይታችሁ ውጡ፡፡አብርሀም ቅድስናን የተቀዳጀው ከባእድ አምልኮው ተለይቶ ነው፡ለጊዜያዊ ሥልጣን ጥቅም ወዘተ ራሳችህን እስካሁን አስገዛችሁ፡፡መጀመሪያ እውነት አለ መስሎአችሁ ገብታችሁ ይሆናል፡፡ግን ወያኔ ጋ ቀርቦ ያላየ የለም ደረጃው ይለያ እንጂ ፡፡ አንድም እውነት የለም ሁሉም ነገር የውሸት የማስመሰል ነው፡፡ወያኔ ጣኦት ነው፡፡ህገ-መንግስቱ፤የመለስ ራዕይ፤የብሄር መብት፤እድገት እና ትርናስፎርሜሽኑ፤የሚወራው ዲሞክራሲ ሁሉም ባእድ አምልኮዎች ጣኦቶች ናቸው፡፡እውነታውን ታውቁታላችሁ፡፡ስለገባችሁበት ነው እንጂ ሁሉም የህወአትን እድሜ ማራዘሚያ ነው፡፡ማንም ከወያኔ ጋር ሁኖ ህሌናው ያመነበትን እንደማይሰራ እናንተም ታውቁታላችሁ፡፡ፍርድቤቶች የሚፈርዱት በህሌናቸው ነው?ጋዜጠኞች እየሰራችሁ ያላችሁት እውነታውን ነው? ወታደሩ  የገንዛ ወንድሙን፣እህቱን  በቆመጥ የሚቀጠቅጠው አምኖበት ነው?፤የሚስኪኑዋ እናትክን ቤት እላይዋ ላይ የምታፈርሰው ህሌናህ ፈቅዶ በችግር ለተቆራመደው ወገናችን መርዳት ስንችል ለምን ተጨማሪ እዳ እንሆንባቸዋለን፡፡ከወያኔ ፍርፋሪ መጠበቅ ለጣኦት የተሰዋ መብላት ነው፡፡ ነው?ከወያኔ አገልጋይነት ተለዩ!ከወያኔ መንደር ውጡ!

http://www.zehabesha.com/

posted by Tseday Getachew

በህወሓት/ወያኔ መቃብር ላይ ብቻ ኢትዮጵያ በሰላምና በብልጽግና ትኖራለች!

ethiowaga.gif

አበራ ሽፈራው/ ከጀርመን/

የኢትዮጵያ ህዝብ ማናቸውም መብቶቹ ተነፍጎ የመኖርና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ ላይ እንገኛለን:: የህዝቡ የሰብዓዊ መብቶችበየትኛውም ዓለም በማይገኝ መልኩ ይጨፈለቃል ለዚህ ያበቃን ደግሞ ትልቁ ምክንያት የህወሓት/ወያኔን የወንበዴነት ጭካኔ ለመጋፈጥ ያለመፈለጋችን ወይም የጭካኔያቸውን መጠን የሚቋቋም ትግል ባለመኖሩና መስዋዕትነትን ለመክፈል ባለመቁረጣችን የመጣብን መከራ እንጂ ህወሓት/ወያኔ ምንም ስለሆነ አይደለም::  የተቃራነውን ጎራ የልብ ትርታ የተረዳው ህወሓት/ወያኔ ሲፈልገው ይገድላል፣ያስራል፣ ያዋክባል፣መሬትንና ንብረትን በሠበብ አስባቡ ይነጥቃል፣ ከስራ ያባርራል፣ የትምህርትና ሌሎች መብቶችን ገፎ ለመከራ ይዳርጋል ካልሆነም ከአገር ማሳደድን እንደትልቅ አማራጭ ተያይዞታል::

በኢትዮጵያ የመኖር መብት እንዳለንና አገራችን መሆኑን እያወቀ መብቶቻችንን የነፈገን ህወሓት/ወያኔ በማን አለብኝነት መቀጠላቸውን ይሁን ብለን ተቀብለን እኛም መስማማታችን ለዛሬው የባሰበት ችግር አድርጎናል:: እነሱ አገራችን አይደለችም ብለው በሚበዘብዟት አገር ላይ ተንደላቀው እየኖሩ ኢትዮጵያ አገሬ የሚሏት እየተዋከቡ ለችግርና ለመከራ መዳረጋችን እጅግ ያሳዝናል:: አሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያ ለውጥ ልታመጣ የምትችለው ህወሓት/ወያኔ ይዞት ከተነሳው  አገርን የማጥፋት እኩይ ተግባሩና አስተሳሰቦቹ ጋር ወደመቃብር ሲወርድ ብቻ ነው :: ህዝቡም ጨክኖ ለዚህ እውነት ሲነሳ ብቻ ነው::

ከመቼውም ጊዜያት በላይ ህዝባችንና አገራችን ለከፍተኛ ውርደት የተጋለጥንበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል:: በሃገራችን መኖር አልቻልንም፣ በሃገራችን ጉዳይ ላይ መወሰን አልቻልንም ፣በሃገራችን ላይ የበይ ተመልካች ሆነን እንገኛለን፣ በህወሓት/ወያኔ ቀኝ ገዥነት ህዝባችንና አገራችን ለከፍተኛ ብዝበዛ ተጋልጠናል፣ በከፍተኛ ሁኔታ በታጠቁ የህወሓት/ወያኔ በዝባዞች ቁጥጥር ውስጥ ወድቀናል፣ ከፍተኛ ህዝብ ከረሃብ አልፎ ለከፍተኛ ጠኔ ተጋልጦ ይገኛል፣ ይህ አልበቃ ብሎ የአገሪቷ ህዝብ ወደ ውጭ ወጥቶ እንኳን እንዳይሰራ ለከፍተኛ ውርደት ተዳርጎ ማንም እንደፈለገው የሚያደርገውና ተከላካይ የሌለው በዓለማችን ላይ የሚገኝ ህዝብ ለመሆን በቅተናል::

ህዝቡ በአገር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጦ ማንም እንደፈለግ የሚጫወትበት ህዝብ ከመሆኑም በላይ በየትኛውም ነገሩ ላይ ሃይማኖታዊ ጉዳዮቹን ጨምሮ በፈለገው መልኩ እንዳያከናውን መደረጉ ይታወቃል:: ከዚህም አልፎ ደግሞ የአገሪቷ መሬት በተለያዩ ጊዜያት ለተለይዩ ጎረቤት አገራትና ሃይሎች በመስጠትና በማካለል ትልቅ የታሪክ ውርደት ገጥሞናል:: ኢትዮጵያ መቼም ባልታየ መልኩ ለትልቅ ችግር ተጋልጣለች:: ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ትልቅ መስዋእትነትን የሚጠይቅ ትግል ከፊታችን ተጋርጦብናል ይኸውም በህወሓት መቃብር ላይ አገራችንን እንደገና ለማከም የሚያስገድድ ሁኔታ ገጥሞናል:: የህዝብ መብት ጉዳይ ሲነሳ ግድያ፣እስራትና ሞት ሆኗል እጣችን የአገሪቷን ወሰን ለማስጠበቅ የተወሰደው እርምጃም ምንም ባለመሆኑ ዛሬ ኢትዮጵያ መሬቷንና የግዛት ክልሎቿን እየተነተቀጭ ትገናለች::

በአባቶቻችን ተከብረው የነበሩ ድንበሮችን አሳልፎ ለመስጠት ዛሬ ለሱዳንና ለኤርትራም ጭምር እንደፈለገ የሚደራደረው ህወሓት/ወያኔ ገና ያልጨረሳቸው ኢትዮጵያን የማጥፋት አላማዎቹ አላለቁም እና እንዲሁም ቀደምት ወራሪዎቻችን  የፈለጉትን መሬት አባቶቻችን በትግላቸው ያቆዩትን አገር በባንዳዎች በእጅ አዙር ለማግኘት እየጣሩ መሆኑና ለዚህም ተፈጻሚነት ደግሞ የህወሓት/ወያኔ የባንዳ ቡድን ሃላፊነት ወስዶ እየሰራ መሆኑን ስንመለከት ያሳዝናል::

የእነዚህ ባንዳዎች አስተሳሰባቸው እና ድርጊታቸው በኢትዮጵያ ላይ መቀጠሉ እንዲያበቃ ዛሬ በህብረት ሆ ብለን መነሳት ካልቻልን ተግባራቸውም ከመፈጸም ሊያቆሙ የሚችሉ አይደሉም :: ህወሓት/ወያኔን ለማሸነፍ ሰዎች የተለያዩ የትግል አማራጮች አዋጭ ናቸው ብለው ባሰቡበት መንገድ ሊሄዱ ይችላሉ፣ ይሁንና አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ግን ህወሓት/ወያኔን በሰላማዊ ትግል እናሸንፋለን ለሚሉ ትግሉ ተገቢ ውጤት እንዲያመጣ ከተፈለገ ትግሉን ማቀጣጠልና በአጭር ጊዜ ወደውጤት እንዲመጣ ማድረግ ወይም ትግሉን ትቶ መውጣት ሌላኛው አማራጭ ይሆናል :: ምክንያቱም ህወሓት/ወያኔ በናንተ ስም የኢትዮጵያን ህዝብ እያታለለና ብልጭ ድርግም በሚለው የሰላማዊ ትግል ውስጥ አማራጭ እየመሰላችሁ እየገባችሁ የህዝቡን ተስፋ ሟሟጠጥና ከትግል ማራቅ በፍጹም አዋጭ የትግል ሥልት እንዳልሆነ ሁላችንንም እንረዳለን ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ ህወሓት/ወያኔ በአገሪቷ ታሪክ ውስጥ የፈጠራቸው ዘርን ከማጥፋት ጀምሮ እስከግለሰቦችና ቡድኖች ጭምር ለወሰዳቸው ግፎች  የሚፈለግ ቡድን ከመሆኑም በላይ በትግራይ ህዝብ ሳይቀር በተለያዩ ቡድኖችና ግለሰቦች የሚፈለጉ ሰዎች ስብስብ በመሆኑ ሰላማዊ ሽግግርን ይፈልጋሉ ብሎ ማሰብ በፍጹም የሚታሰብ አይደለምና ነው::

ለዚህም ምስክር ይሆን ዘንድ በቅርቡ በራያ በተደረገው ስብሰባ ለአቶ አብርሃ አንድ ተሰብሳቢ ያቀረቡላቸውን ጥያቄ መስማት ብቻ ይበቃል እሱም ህወሃት የሽፍታ ቡድን መሆኑን እና ከእነሱ የሚያላቅቋቸው መሆኑን በጥያቄ መልክ ማቅረባቸውን “ሽፍታ” ማለት ደግሞ ምን ማለት እንደሆነ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ የሚታወቅ በመሆኑ ነው::

 

ይህ ብቻ አይደለም በተለያዩ ጊዜያት አገርን በመክዳትና የአገሪቷንና የህዝቦቿን ጥቅሞች አሳልፎ በመስጠትም የሚፈለጉ ከመሆናቸውም በላይ በሠብዓዊ መብት ረገጣ በኩል አሁን ህወሓት/ወያኔን የሚመሩ ሃይሎች በአገራችን ውስጥ የተፈጸሙ የጅምላ ጭፍጨፋዎችን በማቀድ፣ በመተግበርና በማስተግበር በከፍተኛ ሁኔታ በአገር ውስጥና በውጭ ሃገራት የህግ አካላት እንደሚፈለጉ ጠንቅቀው የሚያውቁ መሆናቸውም ጭምር ነው::

ስለሆነም ይህ ችግራቸው ሊያመጣባቸው የሚችለውን አደጋ በማየት አገሪቷን ለመከላከል ሳይሆን ይህንን የራሳቸውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችላቸውን ሁሉ ለማድረግ እንደቆረጡና ይህንን ችግራቸውን ሊያቃልልላቸው የሚችልን ካልሆነም ጊዜ ሊያራዝምላቸው የሚችልን ሁኔታን ለመፍጠር ሲባል ማናቸውንም የአገሪቷን ጥቅሞች አሳልፈው ለመስጠት መቁረጣቸውን በቀላሉ መረዳት እንችላለን፣ በምንም መለኪያ ኢትዮጵያዊ እንዳልሆኑ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ከሚወስዱት አረመኔያዊ እርምጃ ልንመለከታቸው እንችላለን::

 

ከሁሉም በላይ ህወሓት/ወያኔ በተለያዩ ሰዓት የሚቀብራቸው በአንድ ወቅትና ወይም በተለያዩ ጊዜያት ሊፈነዱ የሚችሉ እምቅ ችግሮች በአገራችን ህዝቦች መካከል የፈጠራቸው እንዳሉ ሆነው አሁን ደግሞ ከጎረቤት አገራት በተለይም ከሱዳን ጋር ድንበር ለማካለል በሚል በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር ተጠንሥሶ የነበረውና አብሮት ያልተቀበረው አስተሳሰቡ ዛሬ በቀሪዎቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሊተገበር ከፍ ዝቅ እያሉ ያሉበት ጊዜ በመሆኑና በሌላ በኩል ከህወሓት/ወያኔ ማንነትና ይዞት ከተነሳው ዓላማው አንጻር ህወሓት/ወያኔ ሲፈልግ ኢትዮጵያዊ ይሆናል ሳይፈልግ ደግሞ ታላቋ ትግራይ ይሆናል  ስለሆነም ለመሆኑ የማንን መሬት ነው ህወሓት/ወያኔ የሚደራደርበት ? ህዝቦች ለተወሰነ ጊዜ ሊጨቆኑ ይችሉ ይሆናል ሁል ግዜ ግን እየተጨቆኑ ይኖራሉ ማለት ግን እንዳልሆነ አውቆ መረዳት ያልፈለገው ህወሓት/ወያኔ እራሱ ላይ ትልቅ ችግርን ሊያመጣ መቃረቡን በትክክል መገመት ይቻላል::

ህወሓት/ወያኔ በምንም መለኪያ ኢትዮጵያዊ እንዳልሆነና ኢትዮጵያዊነት ምኑም እንዳልሆነ የራሱ ታሪክ ያሳየናል:: ለዚህም ማስረጃ ለታላቋ ትግራይ ሲሆን አሰብ ይካለላል ለኢትዮጵያ ሲሆን አሰብ የኤርትራ ይሆናል ፣ ለህወሓት/ወያኔ ሲሆን ህገመንግስት ይጣሳል ለህዝብ ጥቅም ሲሆን ይኸው ህገመንግስት እንደፈለገ ይተረጎማል፣ የኢትዮጵያውያን ደም በሳውዲ ሲፈስ ህገወጥ ያሰኛል ለዚሁ ሰብዓዊ ግፍ ካሳን ከሳውዲ መጥየቅ ሲግባ 360 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት እቅዶች ለሳውዲዎች ያሸልማል፣ በኢትዮጵያ ላይ የመበታተን አደጋ ስትፈጥር የነበረችው ሱዳን በአምላክ እጅ መልሷን አግኝታ ስትበታተንና ደረቅ መሬቷን ስትታቀፍ ለህወሓት በታታኝ ቡድን ላደረገችው አስተዋጾ ከ1200 ኪ. ሜ በላይ በሚሸፍን መሬት ላይ እስከ 50 ኪ.ሜ ወደ ውስጥ የሚገባን መሬት ለመስጠት ሲሆን ሽንጡን ገትሮ ህወሓት/ወያኔ ሲንቀሳቀስ ምን ይባላል ? ህዝብን የሚያሸብርና ሽብርተኛ እራሱ ህወሓት/ወያኔ ሆኖ ሳለ የህዝብ ወገኖች የሆኑ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ታጋዮች ምንም ትጥቅ ሳይኖራቸው በሽብርተኝነት እየተፈረጁ በየዕስር ቤቶች የሚንገላቱ ለመሆን በቅተዋል::

በአጠቃላይ ህወሓት/ወያኔ የኢትዮጵያዊነት መለኪያም ሆነ ተግባር የሌላቸው ህይሎች ስብስብ የሆነና በኢትዮጵያውያን ደምና ላብ የራሳቸውን የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነት ጥማት ለማርካት በቋመጡ  ሃይሎች የተዋቀረ ቡድን በመሆኑና ይህንን የማፍያ ቡድንን እኩይ ተግባርን ለማገዝ በነዚሁ ዘረኞች በተዋቀረ ሠራዊት እየታገዙ አገራችንን ይዘው ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠናልና አገራችንን ለማዳን መቁረጥ ይኖርብናል:: ማንም ሊረዳን አይችልም ትግላችን ወደፊት ሲገፋ ግን ብዙዎች አቋማቸውን አስተካከለው ከኢትዮጵያውያን ጋር ይወግናሉ:: ምክንያቱም አገራችን በህወሓት/ወያኔዎች የባንዳ ሃይሎች ብቻ ሳይሆን በታሪካዊ ጠላቶችችንም እጅ ስር በመውደቃችንም ጭምር ነውና ::

ህወሓት/ወያኔ በወልቃይት ጥገዴ ህዝብ ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ በሰላም የተጠናቀቀ መስሎት ከሆነ ተሳስቷል:: የወልቃይት ጠግዴ ህዝብ፣ የሲዳሞ ህዝብ፣ የጋምቤላ ህዝብም ሆነ ሌሎች የህወሓት/ወያኔ የጅምላ ጭፍጨፋ ተጠቂዎች ሁሉ እንዳልተሸነፉ መታወቅ ይኖርበታል በእርግጥ መከራቸው ሁሌም የሚያደማ ቢሆንም :: ይልቁንም ህወሓት/ወያኔ አሁንም ሆነ ለወደፊትም ቢሆን በህዝብና በታሪክ ፊት በፍርድ ፊት ሊሆን የቀረበበት ጊዜ ነው:: ህወሓት/ወያኔ የሚቀብራቸው ፈንጂዎች ምን አልባትም በመጀመሪያ የሚያጠፉት እራሱን ህወሓትን/ወያኔን እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ:: ምክንያቱም ለህዝቦች መከፋፈልና እልቂት የቀበራቸው ፈንጂዎች አቅጣጫቸውን ወደ እራሱ  ወደ ህወሓት/ወያኔ እያደረጉ በመሆኑም ጭምር ነው:: ህወሓት/ወያኔና ባለሟሎቹ የኢህአዴግን ስም ተከናንበውና ተሸፋፍነው በህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን ደባ ለማስቆም በሚደረገው ትግል ውስጥ ተሳትፎአችንን እናጠናክር በህወሓት/ወያኔ መቃብርም ላይ አዲሲቷን ኢትዮጵያ በጋራ እንመስርት:: ካልሆነ ህወሓት/ወያኔ አገሪቷን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊበታትናት መቁረጡን ከድርጊቱ መመልከት እንችላለን:: ቸር ይግጠመን::

 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

 

http://aberashiferaw.wordpress.com/

posted by Tseday Getachew

ኦባንግ ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጋር ተነጋገሩ “በራችሁን ዘግታችሁ እርቅ አውርዱ”

 

ጎልጉል የድረ-ገጽ ጋዜጣ

“ባለውለታችሁ የኢትዮጵያ ህዝብ አዝኖባችኋል፣ አርቃችሁ እዩ”

“በትግሉ ወቅት ለነጻነት ስትዋደቁ ኢትዮጵያ በጋምቤላ አኙዋክ ምድር ላይ ሙሉ ከለላና ዋስትና በመስጠት ያበረከተችው አስተዋጽኦ የሚረሳ ነው? ከነጻነት ታጋዮችችሁ ጎን በመሰለፍ ብረት ያነሱ የአኙዋክ ኢትዮጵያውያን ልጆች መስዋዕትነት ይዘነጋችኋል? አሁን ድረስ የትግሉ የመስዋዕትነት ቁስላቸው ያልዳነ የአኙዋክ ልጆች እንዳሉ ትዘነጋላችሁ?” በማለት የተናገሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ /ጥቁሩ ሰው/ ናቸው።Obang Metho and South Sudan

በታላላቅ መድረኮችና በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተሰሚነታቸውና ስብዕናቸው እየጎላ የሄደው ጥቁሩ ሰው ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ ከላይ የተገለጸውን ህሊና የሚፈታተን ጥያቄ ያቀረቡት ለደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ባርናባ ማሪያል ቤንጃሚን ነው። ለረዥም ሰዓት ጊዜ ወስደው ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ የጎልጉል የአሜሪካ ዘጋቢ እንደዘገበው አቶ ኦባንግ ዶ/ር ባርናባን ያገኟቸው አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ነበር።

በጁባ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉ ይፋ ከተደረገበት አንድ ቀን በፊት አስቀድሞ በተያዘ የውይይት መርሃ ግብር የተገናኙት ዶ/ር ባርናባና አቶ ኦባንግ በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮችን አንስተው መነጋገራቸው ታውቋል። አቶ ኦባንግ የደቡብ ሱዳን የነጻነት ትግል ወቅት ኢትዮጵያ በመንግስት ደረጃ የሰጠችውን ሙሉ ድጋፍና፣ ድንበር ሳይከልላቸው በሁለቱም አገራት የሚገኙት የአኙዋክ ልጆች ትግሉን የነፍስ ዋጋ በመክፈል መደገፋቸውን በማስታወስ በውይይቱ ወቅት ያነሱት ያለ ምክንያት አልነበረም።

“በጆን ጋራንግ ይመራ የነበረው ትግል ፍሬ አፍርቶ ደቡብ ሱዳን ነጻ ስትወጣ የማይረሳ ውለታ ለሰራቸው ኢትዮጵያና የአኙዋክ ልጆች የተከፈላቸው ብድር አሳዛኝና የወደፊቱን ጊዜ ያላገናዘበ ነው” በማለት በውይይቱ ስለተነሱ ነጥቦች ማብራሪያ የሰጡት አቶ ኦባንግ፣ “ለህዝቦች ነጻነትና ለሰብአዊ መብት መከበር የታገለ ድርጅትና አመራሮች ለነጻነታቸው የተከፈለላቸውን የደም ዕዳ ያወራረዱትና እያወራረዱ ያሉት ከወያኔ መሪዎች ጋር በማበር ከለላ የጠየቁ ህጋዊ ስደተኞችን እያፈኑ ለወያኔ አሳልፎ በመስጠት መሆኑ አሳዝኖኛል። ኢትዮጵያዊያን አዝነዋል” በማለት ነበር።

ህጋዊ ከለላ የጠየቁ ስደተኞች ቶርቸር እንዲደረጉ፣ እንዲገደሉ፣ እንዲታሰሩና ኢሰብአዊ ግፍ እንዲፈጸምባቸው ለአምባገነኖች አሳልፎ መስጠት ዘግይቶም ቢሆን ዋጋ እንደሚያስከፍል አቶ ኦባንግ አስረግጠው ተናግረዋል። በ1993 የአኙዋክ ጄኖሳይድ /የጅምላ ጭፍጨፋ/ ሸሽተው በስደት ደቡብ ሱዳን የገቡ የአኙዋክ ልጆችን ለገዳዩ የወያኔ አንጋች ሃይል ማስረከብ መቆም እንዳለበት ያሳሰቡት አቶ ኦባንግ “ይህንን ተግባር የፈጸሙትም ቢያንስ ዓለም አቀፋዊውን ህግ ተላልፈዋልና ሊጠየቁ ይገባል። እርስዎም ይህንኑ የማስፈጸም ሃላፊነት ይኖርብዎታል” በማለት ለውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

የአኙዋክና የበኩር ልጆችና የደቡብ ሱዳን ግንኙነት ከድንበር ያለፈ የደም ትስስርና ኢትዮጵያ የማይረሳ ውለታ በመክፈል ያከበረችው ውህደት በመሆኑ መንግስታቸው ቆም ብሎ ሊያስብ እንደሚገባው አቶ ኦባንግ ምክር አዘል መልዕክት ማስተላለፋቸውን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ አስተማማኝ ከለላና ዋስትና በመስጠት የፈጸመችውን ሊዘነጋ የማይችል ተግባር አለማክበር ለወደፊቱ ወዳጅ የሚያሳጣ ብድር ለራስ የማስቀመጥ ያህል እንደሆነም በወጉ እንዲገነዘቡ ሚኒስትሩን ተማጽነዋል።

አምባገነኑና በህዝብ የሚጠላው የህወሃት አገዛዝ እድሜ አሁን ካለው ትውልድ እድሜ በላይ ዘሎ የሚሄድ ባለመሆኑ በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን ማቅረብ፣ መተዋወቅና መልካም ግንኙነት መመስረት ለወደፊቱ ጠቃሚ መሆኑንም አስረድተዋል። እርሳቸው በዋና ዳይሬክተርነት የሚመሩት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄም /አኢጋን/ ከተመሰረተበት ዓላማ አንጻር የደቡብ ሱዳን መንግሥት ህወሃት/ኢህአዴግን ለማስደሰት ሲል ኢትዮጵያዊያን ላይ ፈጸመውና እየፈጸመ ባለው ተግባር ያዘኑ ወገኖች የቀድሞውን የፍቅር መንገድ እንዲከተሉ አበክሮ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

ሕዝብ ያልወደደው መንግስትና ህዝብ ያልተቀበለው ኢንቨስትመንት መጨረሻው ኪሳራ በመሆኑ የደቡብ ሱዳን መንግስት ሊጠነቀቅ እንደሚገባው አቶ ኦባንግ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ነግረዋቸዋል። ከደቡብ ሱዳን ተነስቶ በጋምቤላ አድርጎ ወደ ኬኒያና ጅቡቲ ይዘረጋል የተባለው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ሕዝብን በመግፋትና በመበደል ከቶውንም ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል ያለማቅማማት ጠቁመዋል።

ህዋሀት በጋምቤላ ንጹሃንን ከቀያቸው በጠመንጃ ሃይል በማባረር፣ መሬታቸውን በሳንቲም ቸብችቦ፣ የህይወታቸው ዋስትና የሆነውን ደናቸውን አስጨፍጭፎ፣ ለምን በማለት የጠየቁትን አስሮና ገድሎ ያቋቋመው ኢንቨስትመንት በዜሮ መጣፋቱን ለአብነት ጠቅሰው ማስረዳታቸው የጠቆሙት ጥቁሩ ሰው “ኢንቨስትመንት መልካም ነው። ህዝብ ካልተቀበለው ተግባራዊ ሊሆን አይችልም። ህዝብ ይሁንታ የማይሰጠው ኢንቨስትመንት ፍሬ አያፈራም። ከውስጥም ከውጪም ያላችሁን ግንኙነት መርምሩ። ያዘኑባችሁ ተበራክተዋል” ሲሉ መክረዋል።

በአዲስ የምትቋቋመው “አዲሲቷ ኢትዮጵያ” ለደቡብ ሱዳን ወንድምና እህቶች ጭምር ቦታ በማዘጋጀት መሆኑንን አቶ ኦባንግ አረጋግጠው “በሌላ በኩል ደግሞ በአሁኑ ወቅት ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል። ለዲሞክራሲ መከበርና ለነጻነት በተከፈለው መስዋዕት የተገኘውን ድል የደቡብ ሱዳን መንግስት በአግባቡ እየተጠቀመበት አለመሆኑን አቶ ኦባንግ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገልጸውላቸዋል። አዲሲቷ ደቡብ ሱዳን ከድል በኋላ የትግሉን መሐላ ሙሉ በሙሉ ረግጣለች በማለት መሪዎቹን ወቅሰዋል።

ከድል በኋላ በደቡብ ሱዳን በርካታ ችግሮች መከሰታቸውን በመዘርዘር የማስጠንቀቂያ ምክር መሰንዘራቸውን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አሁን ባለው ሁኔታ በደቡብ ሱዳን ባሉ ሃያ አንድ ጎሳዎች መካከል ቀውስ መፈጠሩ አይቀርም። ስለዚህ በራችሁን ዘግታችሁ እርቅ አውርዱ። በቀደሙት ሰማዐታቶች ደምና አጥንት ላይ ዴሞክራሲን መስርቱ። ይህንን ካላደረጋችሁና አሁን በያዛችሁት የአምባገነንነትና የአንድ ሰው ወይም ጎሣ የበላይነት መንገድ ከቀጠላችሁ ጣጣው ወደኛም ያመራል” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን አስጠንቅቀዋቸዋል። አሁን ያለው የውስጥ ሽኩቻ መልኩን ሳይቀይር መፍጠን እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋቸዋል። (አቶ ኦባንግ ይህንን ለውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ የተናገሩት እሁድ መፈንቅለ መንግሥት ከመሞከሩና አሁን ደግሞ በዘር /ጎሣ/ መስመር ተከፋፍለው ደቡብ ሱዳናውያን መጫረስ ከመጀመራቸው አንድ ቀን በፊት ነበር)

በደቡብ ሱዳን እውነተኛ እርቅ ለማውረድ የአኙዋክ የፍትሕ ምክርቤት አንድ ግብረ ሃይል ወደ ጁባ እንደሚልክ መረጃ እንዳላቸው የጠቆሙት አቶ ኦባንግ በውይይቱ ወቅት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቀና ምላሽ ማግኘታቸውን አመልክተዋል። በመጨረሻም አቶ ኦባንግ የሚመሩት ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ የእርቅ ደጆች የሚከፈቱበት አግባብ ላይ ከሚመለከታቸው ተጽዕኖ አድጊራዎችና አቅሙ ካላቸው አካላት ጋር እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸውላቸዋል። በማያያዝም “እኛ ሩቅ እያየን እየሰራን ነው። እኛ በስፋት እያሰብን በመራመድ ላይ ነን።

በስፋት አስበን፣ ሩቅ እያየን ስንሰራ እናንተንም አንዘነጋም። በተቃራኒው እናንተ ለነጻነታችሁ የተዋደቁላችሁን የራሳችሁን ዜጎች እያነቃችሁ ለወያኔ አሳልፋችሁ ትሰጣላችሁ። ደም ያፈሰሱላችሁንና አጥንታቸውን የከሰከሱላችሁን ውድ ዜጎች ሳትታረቁ በምድራቸው ላይ ቱቦ ዘርግታችሁ ብር ልታመርቱ ታቅዳላችሁ። ይህ ከቶውንም ጤነኛ አካሄድ አይደለምና ህዝብን አስቀድሙ። አብረን እንስራ። ይህ መልካም ጅምር ነው” በማለት መሰናበታቸውን አቶ ኦባንግ ለጎልጉል ተናግረዋል።

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክትር አቶ ኦባንግ ሜቶ ከደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ባርናባ ማሪያል ጋር ለመወያየት የቻሉት ሚኒስትሩ አሜሪካ ከመምጣታቸው በፊት በኤምባሲያቸው አማካይነት አስቀድሞ በተያዘ መርሃ ግብር መሰረት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሩ ስለ ሰጡት አስተያየትና ምላሽ አቶ ኦባንግ በዝርዝር ለመናገር አልፈለጉም። አቶ ኦባንግ በትውልድ አኙዋክ ቢሆኑም እርሳቸው የሚመሩት ድርጅት /አኢጋን/ ኢትዮጵያውያን ከአገራቸው ውጭ በስደት በሚሰቃዩበት ቦታ ዘር፣ ቀለም፣ ጎሣ፣ ቋንቋ፣ ወዘተ ሳይለይ ፈጥኖ በመድረስ እርዳታ በማድረግ እርሳቸውም በተመሳሳይ ተግባር ተጠምደው በቅንነት በማገልገል እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የእርቅ ደጆች እንዲከፈቱ አግባብ ካላቸውና አቅሙ ካላቸው ክፍሎች ጋር እየሰራን ነው በማለት አቶ ኦባንግ ለሚኒስትሩ የገለጹላቸውን ሃሳብ እንዲያብራሩ ከጎልጉል ተጠይቀው “ሁሌም የእርቅ ደጆች እንዲከፈቱ እንሰራለን። ይህ የጋራ ንቅናቄውና አርቀው የሚመለከቱ ዜጎች ሁሉ እምነት ነው። ብዙ ስራ እየሰራን ነው። ስንጨብጠውና ለህዝብ ሪፖርት የምናቀርብበት አሳማኝ ጊዜ ላይ ስንደርስ ብቻ ይፋ እናደርጋለን። ስራው በባህሪው ከንግግር በመቆጠብ ተግባር ላይ ማተኮርን ስለሚጠይቅ እኛም ባናወራው ጊዜው ሲደርስ ሁሉም በየፊናው የሚገልጸው ይሆናል። ስራው ሳይሰራ ፕሮፓጋንዳው ከቀደመ በሁሉም ወገን ተዓማኒነትን የማጣትና የመጣል አደጋ አለው። የኢትዮጵያ ህዝብ ተግባር የናፈቀው ይመስለኛል” የሚል ድፍን መልስ ሰጥተዋል።

posted by Tseday Getachew

 

Ethnic segregation and fascism of TPLF the woyanes

December 18, 2013

by Nathnael Abate

Ethnic segregation idea was first sowed in the land of Ethiopia by fascist Italians. The country dividing and hate mongering ideology was defeated with the fascist Italians. Later on in 1991 this Ideology was re-introduced by TPLF the bandits of forest. The re-introduced language based segregation was been used by the regime past 23 years. The neo-fascist woyane successfully divided the country by language, culture and history. More over the hate mongering history lessons propaganda advanced to academic areas which teach completely false, clueless and evidence less lessons to the generation. This has created ethnic based racism aggression among the students, people and ethnics of Ethiopia.

The well-known dictator regime of Ethiopia is the post-messenger and follower of fascist Italians. There are many similarities between the Tigrian liberation front and the invaders of 1936- 1941. The fascist dictator of Italy, during its occupation of Ethiopia, it partitioned the country in to six governorates. The governorates were as follow

Governorate capital
Amhara Gondar
Tigre and Eritrea Asmara
Oromo-Sidama Jimma
Bale and Harari Harar
Shoa Addis Ababa
Somalia-Ogden Mogadishu

 

The Neo-fascist TPLF, Partitioned Ethiopia in to nine language based regions and two chartered cities. The regions are mainly based on the language and partially geographical regionalization. Language based includes Amhara,Ethiopia: EPRDF and Militarizing the Region

Tigray , Oromia ,Somalia, Benshangoul goumuz and Afar regions. The remaining regions seem to be divided according to their geographical location. Gambella region has more than one language. Anuak, Nuer OPO denka and Mezhengir are the languages of the region. In south Ethiopia there are many ethnicity and languages. So the regionalizers gave them the name SNNP and compressed them in to one region. The regions further divided in to zones, woredas (districts) and kebeles.

To identify the individual’s ethnicity, individuals are registered according to their region, language and ethnicity. Their identity card or any legal documents required to fulfill these standards. This documentation provides strong base for discrimination of individuals during employment and public benefits. For instance an individual from Amhara or Afar region cannot work in public offices in Oromia region or cannot be elected as a public officer. The employment opportunity, owning land and property rights of the individuals are limited to their regions. This method of discriminating citizens based on their ethnicity comes from non-Ethiopian origin.  The technique of limiting the right of individuals to their regions and ethnicity was first devised by the Apartheid leaders of South Africa

During the apartheid segregation of races in South Africa, the ruling white party segregated and tried to eliminate blacks’ from areas where whites live and the parliament. Blacks were deprived South African citizenship and limited to their Ethnic based regions called Bantustans. Blacks were forced to live In the Bantustans and forcibly removed from their homes and property. South Africa’s black population was subjected to a massive program of forced relocation. This brings us to the implementation of Apartheid Bantustans in Ethiopia. The recent eviction of Amharic speaking Ethiopians from south Ethiopia and Benshoungoul gomouz is strategic Bantustan system applied on Amhara’s by TPLF. Ever since, the Ethiopian Bantustan system created, citizens deprived their right to employment, residence, access to common benefits and the associated things. In turn this resulted in a massive flow of young men power out of the country. The ethnic politics, hatred between ethnics, tribalism and chaos between ethnics are the results of Woyane Bantustan system.

During the fascist Italian invasion Ethiopia was regionalized in to six governorates and in reign of TPLF the country is regionalized in to nine regions based on their ethnicity and languages. The chaos mongering regionalization of the country has created hatred between people, made a gap to misunderstand past political history of the country, reduced common sense, common value and caused underestimating unity in diversity.

The TPLFs government main scheme to elongate its life span is destroying the national sense of Ethiopians and the feeling of being Ethiopian from the people. For this purpose ethnic politics based on language has become the target instrument. The national feeling of young generation has decreasing over half percent in compare to the past generation. Now days in the most part of the country the idea of being Ethiopian and Ethiopia considered as a Neftegna system followers, especially in Oromia, Somalia and Afar regions. Followers of ethicized politics often get their history education from the worst writers of history and ethnocentric politicians. They have a mission of making battle grounds between the ethnics of the country. I know the fact that there has always been ethnic marginalization, injustice and inequality in Ethiopia. But what happened in the past should not be used as an excuse to cause division and hatred now.

The ruling regime intentionally reduced national feeling from the generation. The generation taught to not value their country but their ethnicity. The increased hatred stress among different ethnics has doubled many times in recent years that were never known before in the history of Ethiopia. The year 2012, conflict between Gharri and Borena ethnics in south Ethiopia caused over 20,000 people to flee. Several pastoral tribes in south Ethiopia get in to conflict every year. Tribal zone conflict of the Suri and Dizi and others were the fruits of the woyanes language based ethnic policy.

The separation of people is not only in a social and cultural area but also it is further penetrated in to spiritual environments too. Since recent years depending on the church language many different churches were built. Often it’s observed that members of churches with the same religion but different church language quarrel and fight with each other because of their language differences.

So far I have been comparing the ruling regime of Ethiopia with fascist Italians and racist apartheid government of South Africa. It’s obvious that woyane Government copied and implemented the policy of Apartheid and fascists. For these governments their policy was right and honored. The same is true for woyanes, their ethnic centered policy is holy and sanctified for them. The current segregation policy of woyane is daily fueled up to the people through media stating the segregation is for freedom, equality and justice which the people deprived in the former political systems. The repeated false propaganda of woyane brainwashed the people. The woyanes context of freedom, is sustaining its power and eradicating any opponent and Equality is dividing the country in to tribes and creating hatred among these ethnicities.

To continue divide and rule strategy, TPLF every year celebrates “ye bihereseboch qen”. Millions of dollars spent on the occasion and the main goal of the celebration is not to promote the unity in diversity or increase our bond but it’s aimed to pleasure the junta leaders. It’s illogical for woyane to celebrate the nations and nationalities day and make segregation among the people. Also it makes no sense since tens of thousands of our people killed and left on the land of Arab’s but back home the TPLF having party for diversities. Which comes first, saving lives of the abandoned citizens or having fake diversity party?

The confused government of Ethiopia with self-contradicting policy kept on ethnic apartheid leading system. Consequently, I cannot see unified peaceful country as long as TPLF exists. If the situation is left to continue in this manner, there is no doubt that soon or later civil war would occur or Ethiopians would be abandoned and become stateless people. To combat the woyane from act of country destruction, all Ethiopians should become patriots like their forefather who defeated fascists and turned them in to ashes.  As the South African blacks struggle was not a question of political power, our struggle is not an interest of political supremacy but it is a fight for survival of our country, keeping it or losing it forever. Our forefathers did not fight fascist for the sake of political power but it was a question of existence, sovereignty, keeping our land or losing it forever. That was the spirit which gave power to our forefathers and black South Africans to defeat their enemies. Our invincible Ethiopiansim power should come out of us. Our arms should be heavy up on woyane. There should be no more suppression, killing and segregation. We should stand together to build our country’s unity in diversity.

Writer could be reached by nathanialoret@gmail.com

Facebook- nathy de saint and Twitter @nathysaint

 

 posted by Tseday Getachew

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተመሰረተበትን አንደኛ አመት አስመልክቶ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ

Ginbot 7 Popular Force logo

ታህሳስ 7  2006 ዓም የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከተመሰረተ  አንድ አመት ሞላው። አንድ አመት  በጭንቅና  በአሳር  ለተያዘች የዛሬይቱ ኢትዮጵያና ህዝቧ እጅግ ረጅም ግዜ እንደሆነ ህዝባዊ ሃይሉ በሚገባ  ይገነዘባል። ባላፈው አንድ አመት ውስጥ የኢትዮጵያን ህዝብ የመከራ የአሳርና የውርደት ህይወት ይበልጥ እየሰፋ፣ የሚፈጸምበት ግፍ ይበልጥ እየገዘፈ መሄዱን አይተነዋል። በሃገርና በህዝብ ላይ እየወረደ ያለውን ወያኔ ወለድ የስቃይና የፍዳ ናዳ በቅጡ ላጤነው  ሃገሪቱና ህዝቧ የአዳዲስ የስቆቃና የመከራ አይነቶች መፈተኛ ቤተ ሙከራዎች እየተደረጉ ለመሆኑ ጥርጥር አይኖረውም። ለሚራበው ለሚረገጠው በግፍ ለታጎረው፣ በኑሮ ውድነት ለሚጠበሰው፣ ለተሰደደው ለተፈናቀለው ኢትዮጵያዊ እንድ አመት በሲኦል የቀናትና የወራት መቁጠሪያ እንደሚለካ ዘመን እጅግ የረዘመ የስቃይ ግዜ ነው።

የዋልድባ መነኩሳት ገዳማችን  አትድፈሩ አታፍረሱ በማለታቸው እየተገረፉ ለዘመናት ፈጣሪያቸውን ከሚማጸኑበት ለሃገርና  ለህዝብ ምልጃ ከቆሙበት ገዳም በዘር መመዘኛ እየተለዩ  እንደቆ ሻሻ ተጠርገው የተባረሩበት ፣ እምነታችን አትንኩ ያሉ የእስልምና እምነት ተከታዮችና  መሪዎቻቸው በሃሰት ክስ ተመስርቶባቸው  ወህኒ መውረዳቸው አንሶ  ወንድሞቻችን ይፈቱ በማለት  ሰላማዊ  ጥያቄ ያቀረቡ ወገኖቻቸን በወያኔ ነፍሰ- ገዳዮች  በአረመኔያዊ ጭካኔ የተጨፈጨፉት በዚሁ አመት ነው። ወያኔ በህዝብ መሃከል በዘራው የዘር መርዝ የተነሳ በሽዎች የሚቆጠሩ አማሮች ከጉራ ፈርዳና ከቤንሻንጉል፣ ኦሮሞዎች ለዘመናት ከኖሩበት ምስራቅ ሃረርጌ  አካባቢ  እንዲፈናቀሉና በገዛ ሃገራቸው መድረሻ ቢሶች  እንዲሆኑ የተደረገው በዚህ አንድ አመት ውስጥ ነው። ጋምቤላዎች ሙርሲዎች አፋሮችና ሌሎችም ብሄረሰቦችና ማህበረሰቦች የተጨፈጨፉበት፣በልማት ስም ለመጡ የውጭ ወራሪዎችና ወያኔ ለፈጠራቸው ቱጃሮች ቦታ እንዲለቁ ተደርጎ ቀደምቶቻቸው ለዘመናት ከኖሩባቸው ቀየዎች እንዲነቀሉ ተደርገው እንደ አልባሌ ነገር የትም እንዲበተኑ የማድረጉ ሂደት ከመቼውም በላይ ተጠናክሮ የቀጠለው በዚሁ አመት ነው። በዚሁ አንድ አመት በወያኔ የሃገሪቱ ገዥዎች በህዝብ ላይ የተፈጸመው  ጭካኔና ወንጀል ተዘርዝሮ  የሚያልቅ አይደለም።

ይህ ወያኔ  ሰራሽ ሃገር በቀል የውርደትና  የስቃይ ህይወት አልበቃ  ብሎ ወያኔ ከሳውዲ የጨለማ ዘመን ገዥዎች ጋር በመተባበር ወንድሞቻችን በሳውዲ አውራ ጎዳናዎች ላይ እንዲታረዱ እህቶቻችን በቡድን በተደራጁ የሳውዲ ጎረምሳዎች  እንዲደፈሩ ሁኔታዎችን አመቻችቶ  ለኢትዮጵያውያን ያለውን እጅግ የከረረ ጥላቻ በአደባባይ ያሳየበት አመት ነው። እንዲህ አይነቱ የጅምላ ግፍና  ውርደት ከመከሰቱ በፊት ህዝባዊ ሃይሉ በአረብ ሃገር በባርነትና  በስደት የሚገኙ እህትቶቻችንን ወንድሞችችን ስቃይ  ስቃዩ አድርጎ በመውሰድ “ላንቺ ነው” በሚለው ድርጅታዊ መዝሙሩ “በባለጌ  አረቦች መዳፍ ውድ ክብራቸው ለጎደፈው እህቶቻችን፣ በአረቦች የባርነት ቀንበር ጀርባቸው ለጎበጠው  ወገኖቻችን እንደርስላችኋለን፣ የተሰባሰብነው  ደማችን የሚፈሰው የመከራ ቀናችሁን ለማሳጠር ነው” የሚል ቃል ኪዳኑ ሰጥቶ  ነበር። የድርጅታችንን ምስረታ አንደኛ  አመት ስናከብር ልባችንን ደስታ ሳይሆን ሃዘን እንዲሞላ የሚያደርገው ይህ ቃል ኪዳናችን ለማክበር የጀመርነው ጉዞ ከድርጅት ምስረታና ከድርጅታዊ ዝግጅት አልፎ   በኢትዮጵያ ህዝብ ጥላቻና ንቀት  የተነፋውን የወያኔን እብሪት በማስተንፈስ የወሰዳቸው ተጨባጭ የአለኝታነት እርምጃዎች ባለመኖራቸው ነው።

ምንም እንኳን ግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል እራሱን እንደ ድርጅት አቁሞ  ኢትዮጵያውያንን አሰባስቦ  መራራው ትግል የሚጠይቀውን የፖለቲካ  የወታደራዊ ስልጠናና ትጥቅ አስታጥቆ  በወያኔ  ላይ ለመዝመት የጀመረውን ጉዞ የሚያስቆመው ምድራዊ ሃይል እንደሌለ ብናውቅም የህዝብ ስቃይ ለግዜው መቀጠሉ የህባዊ ሃይሉን አባላት ማሰቃየቱ አልቀረም። በወያኔ  ግፈኛ አገዛዝ የተንገፈገፈው ወገናችን ህዝባዊ ሃይሉ የወያኔን አገዛዝ እድሜ  የሚያሳጥሩ ፈጣን እርምጃዎችን እንዲወስድ በከፍተኛ  ጉጉት እየተጠባበቀ እንደሆነ  እናውቃለን። ህዝባዊ ሃይሉን ለመቀላቀል በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ የሃገሪቱ ዜጎች በተጠንቀቅ እንደቆሙ እናውቃለን። እነዚህ ዜጎች ከሁሉም የእምነት የቋንቋ  የጾታ የእድሜ  የኑሮና  የማህበረሰብ ስብጥር የሚያካተቱ  እንደሆኑ እናውቃለን። በሃገሪቱ ታሪክ ተሰምቶና  ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ  የወታደር ልብሱን  እየጣፈ እንዲለብስ፣  የወታደር ጫማውን መቀየሪያ አጥቶ  ሸበጥ እንዲያደርግ የተገደደውን፣  የወያኔ ጀነራሎች በስልጣንና  በዘረፋ ሲያብጡ በድህነት እንዲሟሽሽ የተፈረደበት የሃገሪቱ ሰራዊት በዘር በእምነት ሳይለያይ ከህዝባዊ ሃይሉ ጎን ለመቆም አሰፍስፎ  የቆመ  እንደሆነ  እናውቃለን። ይህ ሃገራዊ እውነታ ለህዝብ የገባነውን ቃልኪዳን የለምንም ጥርጣሬ  ማስከበር እንደምንችል በሙሉ ድፍረት እንድናውጅ የሚያስችለን ሃቅ ነው።

የወያኔ ጀንበር እየጠለቀች የኢትዮጵያ  ህዝብ ጀንበር እየፈካች የመሄዱ ጉዳይ እንደማይታጠፈው  የመንጋትና  የመምሸት የተፈጥሮ ህግ ነቅነቅ የማይል እንደሆነ ግንቦት7 ጠንቅቆ ያውቃል።  እውቀታችን ልዩ ጥበብ የሚጠይቅ ኣይደለም። ግፍ ፍትህን አሸንፎ፣ እውነት በሃሰት ተደፍቃ፣ ጥላቻ ፍቅርን፣ አድሎ እኩልነትን፣ ሃገራዊ ክህደት ሃገር መውደድን፣ ባንዳነት አርበኛናትን ለዘላላሙ ቀብረው የሄዱበት የሃገራችንና  የሰው ልጆች ታሪክ የለምና የወያኔን አይቀሬ ሞት ለመተንበይ  ልዩ ጥበብ አያሻንም። ይህን እኛ ብቻ ሳንሆን በዘረፋና በጥላቻ  የደነዘዘ ህሊና ያዳበሩት የወያኔ  ባለስልጣናትም ያውቁታል። ያለእኔ  ጀግና የለም፣ ያለእኔ  አልሞ  ተኳሽ የለም በሚል እብሪት በመጻደቅ የሚታወቁት ወያኔዎች በመቶ ሽዎች በሚቆጠሩ ወታደሮች ተከበው፣  በታንክ በአይሮፕላን በሚሳይል ታጅበው ከሚኖሩበት ቤተመንግስትና ቪላዎች ውስጥ ብርክ እንዲይዛቸው ያደረገው ለመሆኑ፣  ሳር ቅጠሉ ግንቦት ሰባት እየመሰላቸው ሲበረግጉ እንደሚያመሹ፣  የግንቦት ሰባት አባላት እያሉ ከድርጅታችን ጋር አንዳችም ግንኙነት የሌላቸውን ዜጎች እያሰሩ ሲያሰቃዩ ፣  ከምላሳቸው ላይ ግንቦት 7  የሚል ስም ተፈናጦባቸው  እንደሚውሉ በራሳቸው ሚድያ  ወያኔዎች ራሳቸው እያሳዩን እያስደመጡን ነው። ከዚህም አልፎ በዚህ አንድ አመት ውስጥ  የህዝባዊ ሃይሉን መሪዎች በመግደል ድርጅቱን ለማኮላሸት ይቻላል በሚል ወያኔ የላካቸው ነፍሰ ገዳዮችና ድርጅቱን ከውስጥ ለመቦርቦር ያሰማራቸው ሰርጎገቦች ተራ በተራ ተልእኳቸው እየከሸፈ በህዝባዊ ሃይሉ እጅ እየወደቁ ወይም ተልእኳቸው እንደማይሳካ ሲረዱ እየፈረጠጡ ወደ ወያኔ ሲመለሱ አይተናል።

ያለፈው አንድ አመት ተመክሯችን ስለወያኔ  ብቻ ሳይሆን ስለራሳችንም ጥንካሬና  ድክመት ብዙ ነገሮች ያስተማረን ኣመት ነው። የቀደምቶቻችን የጀግንነት የአርበኛነት ቅርስ በመላ ህዋሳቸው የተሸከሙ  ለኢትዮጵያ እና  ለህዝቧ ሲሉ ደማቸው ለማፍሰስ ውድ ህይወታቸውን ለመሰዋት ወደኋላ የማይሉ ቆራጥ ብቻ ሳይሆኑ አርቀው የሚያዩ  በርካታ ልጆች  ሃጋሪቷ ያሏት መሆኑን ያረጋገጥንበት አመት  ነው።  በሌላ በኩል ደግሞ  ድርጅታችን የኢትዮጵያን ህዝብ ብቸኛው የመንግስት ስልጣን ባላቤት የማድረጉን ታሪካዊ ራእዩን ለመሳካት የሚያደረገው ትግል ከወያኔ ጋር ብቻ ሳይሆን ከራሳችንም ጋር የሚደረግ እንደሆነ  በሚገባ  የተረዳነው  በዚሁ የአንድ አመት የድርጅታችን እድሜ  ነው። ከራሳችን ጋር የሚደረግ ትግል ወያኔ በማህበረሰባችን ውስጥ ከዘራቸውና የሃገሪቱን ዜጎች እንዲበክሉ ካደረጋቸው የዘረኛነት የአድሎ  ከህዝብና  ከሃገር ጥቅም በፊት የራስን ጥቅም ማስቀደም፣ የሱሰኛነትና የሙስናና ሌሎችም አደገኛ ባህሎች ጋር ነው።

ህዝባዊ ሃይሉ ደግሞ  ደጋግሞ  እንደገለጸው ትግላችን አንድ መንግስታዊ ስርአት ወድቆ ሌላው የመንግስት ስርአት በመጣ ቁጥር የህዝብ ተስፋ እየጨለመ  “አዲስ ከመጣው ስርአት ያላፈው ያረጀ ስርአት በግፈኛነቱ በዘራፊነቱ ያነሰ ነበር” የሚል የግፈኛና የዘራፊ ስርአቶች ንጽጽር ላይ የቆመ አሳዛኝ የህዝብ ህይወት እንዲያበቃ ነው። ደርግን ያየ የአጼውን ስርአት እንከኖች ረስቶ ንጉሱ ይሻሉን ነበር ያለበት፣ ወያኔን ያየ የደርግን አስከፊ ዘመን ረስቶ መንጌ በስንት ጣሙ ያለበት አሳዛኝ ሁኔታ ከወያኔ መውደቅ በኋላ በሃገራችን እንዳይደገም ነው ትግላችን። የኢትዮጵያ ህዝብ የውድ ልጆቹን ህይወት ገብሮ ወያኔን በማስወገድ የሚያመጣው ስርአት ከወያኔ ብሶ ህዝብ ወያኔ ማረኝ የሚልበትን ቅስም ሰባሪና አዋራጅ የታሪክ ቅጥልጥሎሽ  እንዳይቀጥል ማድረግ ህዝባዊ ሃይሉ የተመሰረተበት፣ አባላቱ መከራ ለመቀበልና መስዋእትነት ለመክፈል በረሃ የገቡበት ዋናውና ብቸናው ምክንያት ነው። ትግላችንን መራራ የሚያደርገው ከበሰበሰውና የአንድ ጀምበር የህዝብ ቁጣ ከታሪክ ቆሻሻ የመጠያ ስፍራ ከሚከምረው  የወያኔ ስርአት ጋር ብቻ ሳይሆን በወያኔ ቦታ የሚተካውን ስርአት ከአድሎና ከዘረኛነት ከዘረፋና ሃገራዊ ክህደት የጸዳ፣ ዳግም ለኢትዮጵያውያን ውርደትና እንግልት ምክንያት እንዳይሆን ለማድረግ ከራሳችን ጋር ሳይቀር የማያቋርጥ ትግልን ማድረግ የግድ ስለሚል ነው። ህዝባዊ ሃይሉ የአመጽ ትግል የሚያደርግ፣ የመሳሪያው ብዛትና  የሰራዊቱ ቁጥር እያደገ  የሚሄድ ሃይል መሆኑን ስለምንረዳ  ይህን ሃይል ገና ከጅምሩ ከብዙ እንከኖች እያጸዱ ማደራጀት ካልተቻለ  በሃገርና በህዝብ ላይ የሚመጣውን አደጋ  የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ጠንቅቀው የተረዱት ሃቅ ነው። ይህ ግንዛቤ የሰራዊቱን አባላት በጥንቃቄ መመልመልን፣ ማሰልጠንንና መገንባትን የግድ የሚል ነው።

ይህ ከራሳችን ጋር የሚደረግ ትግል እጅግ መራራ ነው። ታሪካዊ ስህተቶችን ላለመድገም የሚደረግ ትግል ነው። ይህ ትግል የአካልና የመንፈስ ጽናትን፣ ሃቀኛነትን፣ ታማኝነትን፣ ጀግንነትን የሚጠይቅ ትግል ነው። የወያኔ ስርአት ከሃገር ግድያው በተጨማሪ ትውልድን ለመግደል ሆን ብሎ ያስፋፋቸው እኩይና ጎጂ ባህሎችና ልምዶች ምን ያህል ማህበረሰባችንን እንደጎዱት ህዝባዊ ሃይሉ ባላፈው አንድ አመት እድሜው በሚገባ የተረዳው ጉዳይ ሆኗል። ህዝባዊ ሃይሉ የሚመኘውን የኢትዮጵያ ትንሳኤና ተሃድሶ እውን ለማድረግ እነኝህ  ወያኔ ሆን ብሎ  ያስፋፋቸውን የባህልና የሞራል ብክለት ማጽዳት የግድ እንደሆነ የተረዳ አካል ሆኗል።

ትግላችን መደፍረስን መጥራትን፣ መንተክተክን መስከንን የትግሉ ሂደት አካል አድርጎ  የሚጓዝ ነው።   ትግሉ የሚልመጠመጠውን እንደቀስት ቀጥ ብሎ ከሚራመደው፣ በካፊያው የሚንቀጠ ቀጠውን ለዶፉ ደንታ ከሌለው፣ ዝናር በቅፌን ከምሩ ተኳሽ  የሚለይ መራራ ትግል ነው። ያለፈው አንድ አመት ይህን አስተምሮናል። ህዝባዊ ሃይሉ ትግሉ ቀላል ነው የሚል ከእውነታ ጋር ያልተያያዘ ቃል ለህዝብም ሆነ ህዝባዊ ሃይሉን ሊቀላቀሉት ለተዘጋጁት ወገኖቹ አይናገርም። ህዝባዊ ሃይሉን ለመቀላቀል ለተሰለፉ በሽዎች ለሚቆጠሩ ወገኖቻችን ትግሉ የሚጠየቅውን የሞራል የስብእና ጥብቅነት፣ከፍተኛ  የሃገርና የወገን ፍቅር፣ ጥልቅ የሆነ የመስዋእትነት ፈቃደኛነት የሚጠይቅ መሆኑን ከማስረዳት አንቦዝንም። ህዝባዊ ሃይሉ ለህዝብ ቃል እንደገባው ከወያኔ  ጋር የምናደርገው ትግል በጥበብ በእውቀት በጥናት በጥንቃቄ የምናደርገደው ነው። ነጻነት ያለመስዋእትነት እንደማይሳካ ብናውቅም ለተራ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ስንል በቂ ዝግጅት ያልተደረገበት የሃገሪቱን ውድ ልጆች በከንቱ የሚማግድ ጀብደኛ እንቅስቃሴ  አናደርግም። የውሸት ተስፋ  ህዝብን አንመግብም።  አይናችንን ከዋናው የኢትዮጵያና  የህዝቧ  ጠላት ከሆነው ከወያኔ ላይ አንስተን በሌሎች  ወያኔን እቃወማለሁ በሚሉ ሃይሎች ላይ አንተክልም። ከወያኔ ሌላ ወደ ጎን የምንዋጋው፣ የምንጨቃጨው አታካራ የምንገጥመው ምንም ሃይል አይኖርም። ወያኔን ለመምታት ህዝባዊ ሃይሉ የጨበጠው  ቡጢ ወገኖቻችን በፍቅር ለመጨበጥ የሚዘረጉ ጣቶች  እንዳሉት በጸረ ወያኔ ዴሞክራሲያዊ ትግሉ  ከልባቸው ለመተባበር ለሚፈልጉ ሃይሎች ሁሉ ግልጽ እናደርጋለን።

ያለፈው አንድ አመት የመሰባሰብ የድርጅት ምስረታ  መሰረታዊ የሆኑ የፖለቲካና የወታደራዊ  ስልጠና የተሰጠበት፣ የድርጅት ማጠናከሪያና የማጥራት ሂደት የተካሄደበት ነው። በዚህ ረገድ የተሰራው ስራ አጥጋቢ ውጤት አስገኝቷል። ስልጠናው፣ ድርጅት ማጠናከሩና  ማጥራቱ ወደፊትም የሚቀጥል ነው። መጪውን አመት የተለየ የሚያደርገው ህዝባዊ ሃይሉ በህዝብ ላይ በሚደርሰው ግፍና ውርደት ከሚሰማው ከፍተኛ ብስጭትና ቁጭት አልፎ ባላፈው አመት ሊደርስላቸው ያልቻለውን የሃገራችንን ግፉአን ህዝቦች መታደግ የሚችልበትን እርምጃዎች መውሰድ የሚችልበት አመት መሆኑ ነው። በዚህ የህዝባዊ ሃይላችን የአንደኛ አመት ምስረታ  ክብረ በአል ወቅት ወገንም ጠላትም በግልጽ እንዲያውቀው የምንፈልገው ይህን ሃቅ ብቻ ነው።

ውድመት ለዋናውና  ለብቸኛው የኢትዮጵያ ህዝብና  የኢትዮጵያችን ጠላት ለሆነው የወያኔ ገዥ ጉጅሌ!

ድል በወያኔ ግፈኛ ስርአት አበሳውን ለሚያየው የመላው የኢትዮጵያ  ህዝብ!

የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል
Ginbot 7 Popular Force
http://www.ginbot7pf.org
Tel: +44 208 123 0056
email: pr@ginbot7pf.org

posted by Tseday Getachew 

የቀድሞው መብራት ኃይል ስራ አስፈፃሚ አቶ ምህረት ደበበ ከኃላፊነታቸው ተነሱ

(EMF) የቀድሞው መብራት ኃይል ለሁለት ተከፍሎ፤ አንደኛው አገልግሎት ሰጪ እንዲሆን ተብሎ ፓወር ግሪድ ለተባለ የህንድ ካምፓኒ በጨረታ ሲሰጥ፤ ሌላኛው ደግሞ የኤሌክትሪክ ኮንስትራክሽን ስራ ብቻ እንዲሰራ ተደርጓል። ይህ የህንድ ካምፓኒ በህንድ ውስጥ በሙስና ከሚታወቁት ድርጅቶች አንዱ ሲሆን፤ በዚህም ሳቢያ ባለፈው አመት ዋና ስራ አስኪያጁ Sushil Kumar Gupta በህንድ ፖሊሶች እጅ ከፍንጅ ተይዞ ሰባት አመት ተፈርዶበታል። እንግዲህ እንዲህ ያሉ ሰዎች የነበሩበትና በህንድ በሙስና የሚታወቅ ድርጅት ነው፤ የኢትዮጵያን የመብራት ኃይል የአገልግሎት ክፍል ሙሉ ለሙሉ የወሰደው።

በሌላ በኩል ደግሞ ከአገልግሎት ሰጪው የህንድ ካምፓኒ፤ እንዲለይ የተደረገው የኮንስትራክሽን ክፍል ቀደም ሲል በተለይ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ምህረት ደበበ ይመራል ተብሎ ሲጠበቅ፤ ጭራሹን አቶ ምህረት ደበበ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተደርጓልው። የቀድሞው የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ምህረት ደበበ ከኃላፊነታቸው የተነሱት፤ መብራት ኃይል ለሁለት መከፈሉን ወይም ለህንድ ካምፓኒ በመሰጠቱ ባለመስማማታቸው እንደሆነ በሰፊው ይነገራል። በሳቸው ምትክ ወ/ሮ አዜብ አስናቀ የተተኩ መሆናቸውን ምክትል ጠ/ሚ እና የኢህአዴጉ ተጠሪ ደብረጽዮን ያሳወቀ ሲሆን፤ አብዛኛው ነባር ሰራተኛ በዚህ ክፍፍል እና ሹም ሽር ደስተኛ አልሆነም። በሌላ በኩል ግን፤ የህወሃቱ ከፍተኛ አመራር ደብረጽዮን ከዚህ በተለየ፤ “አቶ ምህረት ደበበ የተነሱት በግምገማ ነው” ብለዋል። ዛሬ አዲስ አበባ ላይ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ በዚህ ጉዳይ የሚከተለውን ዘገባ አቅርቧል።

Mr. Meheret Debebe fired by Debretsion

Mr. Meheret Debebe fired by Debretsion

አቶ ምህረት ደበበ ከኃላፊነታቸው የተነሱት በግምገማ መሆኑን፤ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስ ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ገለፁ። በትላንትናው እለት የቀድሞ የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ለሁለት መከፈልን አስመልክተው በሂልተን ሆቴል መግለጫ የሰጡት ሚኒስትሩ፤ በኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት የስራ አፈፃፀም ላይ በሰራተኞቹም ሆነ በከፍተኛ ኃላፊዎች ላይ በተደረገ ግምገማ ዋና ስራ አስፈፃሚውን አቶ ምህረትን ጨምሮ ማኔጅመንቱ መስራት የሚገባውን ያህል ስላልሰራ በግምገማ ለውጥ የተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። አቶ ምህረት ከኃላፊነታቸው መነሳት ብዙዎችን ያስደነገጠ ቢመስልም በሰራተኛው በኩል ግን ሲጠበቅ የነበረ መሆኑ ኃላፊው አመልክተዋል። በማኔጅመንቱ በኩል ባሉት ችግሮች ላይ ከሰራተኛው ጋር ተነጋግሮ መስመር የማስያዝና ባለው አቅም ያለመስራት ችግሮች የነበሩ መሆኑን ዶ/ር ደብረፅዮን ጨምረው ገልፀዋል። አቶ ምህረት በነበራቸው አፈፃፀም ኮርፖሬሽኑ በተፈለገው ደረጃ ባለመመራቱ በነበራቸው የስራ ዘመን ያስመዘገቧቸው አዎንታዊ የስራ ውጤቶች እንደተጠበቁ ሆነው በተካሄደው ግምገማ ከነበሩበት ኃላፊነት ተነስተው በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ አማካሪ ሆነው እንዲሰሩ ተመድበዋል።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን በአዲሱ አደረጃጀት መሰረት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት በሚል ለሁለት መከፈሉን የገለፁት ዶ/ር ደብረፅዮን፤ አሁን ባለው አዲስ አደረጃጀት ኃይል አመንጪውና አገልግሎት ሰጪ የተለያየ ኩባንያ እንዲሆን የተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው በቅርቡ የተሾሙት የግልገል ጊቤ ሶስት ፕሮጀክት ዋና ሥራአስኪያጅ የነበሩት ኢንጅነር አዜብ አስናቀ መሆናቸው ታውቋል። ሁለተኛውን ማለትም የአገልግቱን ዘርፍ በማኔጅመንት ኮንትራት ደረጃ የሚመራው ፓወር ግሪድ የተባለው የህንድ ኩባንያ ነው።

EMF

posted by Tseday Getachew

 

የታሪክ ክህደት በማንዴላ የስንብት ፆሎት ላይ ሲደገም!! (አንተነህ ሽፈራው)

አንተነህ ሽፈራው – ታህሳስ 9/2006 ዓ.ም/Dec 18, 2013
በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት አገሮች ሁለንተናዊ ከፍተኛ ድጋፍ የወያኔ የጎጠኝነት ወታደራዊ ክንድ በመፈርጠሙና በኋላም በመንገድ መሪነት የወሎን፣ የጎንደርንና የጎጃምን ሕዝብ ትጥቅ ያለ ብዙ ወጣ ውረድ በማስፈታት ባገለገሉ በነ ታምራት ላይኔ ተዋናኝነት ወያኔ መላ አገሪቷን በግንቦት 1983 ዓ.ም በዚሁ ወታደራዊ ክንዱ መውረር መቻሉን ተከትሎ በተፈጠረው አዲስ ዓይነት የጎሣ/የቋንቋ/ ፖለቲካ አደረጃጀት እነ ሆድ- ባምላኩ ወዲያው ለዚሁ የወያኔ የጎሣ/የቋንቋ/ ፖለቲካ አደረጃጀት ሴራ ሰለባ በመሆን የጋራ ኢትዮጵያዊ ቤታችንን ለማፍረስ ከመሞከር አልፎ እርቆ በመሄድ ወያኔ በጠላትነት/በኢትዮጵያዊነት የፈረጀውን የሕብረተስብ ክፍል ለያቶ በመግደልና በማፈናቀል በታሪክ፣ በትውልድና በሕግ ፊት የሚያስጠይቅ ተደጋጋሚ ወንጀል እየፈጸሙ መሆናቸውን ላለፉት 23 ረጅም የመከራ ዓመታት በግልፅ እያየን ነው:: –– ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ—-

posted by Tseday Getachew

የፍርሃት ባህልን እያነገሰ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ፤(ያሬድ ኃይለማርያም)

አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት ወደ ኋላ
(ክፍል ሁለታ)

ያሬድ ኃይለማርያም
ከብራስልስ    
ታኅሣሥ 9፣ 2006

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት በኢትዮጵያዊያን ላይ እያሰፈነ ስላለው የፍርሃት ባህል ቀደም ሲል ባሰራጨሁት የዚህ ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ባለሙያዎች በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ለፍርሃት ባህል መስፈን መንሰዔዎች ያሏቸውን ነጥቦች ዘርዝሬ ነበር። በክፍል አንድ ጽሑፌ መግቢያ ላይ እንደገለጽኩት ምንም እንኳን ፍርሃት የግለሰቦች ባህሪ መገለጫዎች መካከል አንዱ ቢሆንም የዚህ ጽሑፍ ትኩረት በወል የምንጋራቸውና በማኅበረሰብ ደረጃም በሚንጸባረቁት የፍርሃት ምልክቶች ላይ ብቻ ያተኮረ ነው። በመሆኑም በዚህ ክፍል ውስጥ የህሊና እና የአካል ቁስልን ባስከተሉ ትላንቶች ውስጥ ማለፍ የሚፈጥረውን የፍርሃት ቆፈንና የሚያስከትለውን መዘዝ በመቃኘት ፅሑፌን ልደምድም።

በአለማችን ታሪክ ከሰው ልጅ አዕምሮ ተፍቀው የማይወጡና እጅግ አሰቃቂ በመሆናቸው ሲታወሱ የሚኖሩ በርካታ ጦርነቶችና የእርስ በርስ እልቂቶች ተከስተዋል። የመጀመሪያውና የሁለተኛው የአለም ጦርነቶች፣ የኦሽዊትዝ ጭፍጨፋ፣ የአፓርታይድ የግፍ አገዛዝ፣ የሩዋንዳው የዘር ማጥፋት እልቂት፣ እንዲሁም በተለያዩ የአፍሪቃ እና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ውስጥ የተከሰቱትና የሚሊዪኖችን ሕይወት የቀጠፉት እልቂቶች በዋነኝነት ተጠቃሾች ናቸው። እነኚህ በክፉ ክስተትነታቸው በታሪክ የሚወሱት አጋጣሚዎች ካስከተሉት እልቆ መሳፍርት የሌለው ሰብአዊ ቀውስ እና የንብረት ውድመት ባሻገር ከትውልድ ትውልድ የሚወራረስ ትምህርትንም አስተምረው አልፈዋል። በተለይም የምዕራቡ አለም በራሱም ሆነ በርቀት በሌሎች ላይም የተፈጸሙትን እነዚህን መሰል መጥፎ ክስተቶች በአግባቡ በመመርመር፣ መረጃዎችን ሰብስቦና አደራጅቶ በማስቀመጥ፣ በመጽሐፍ ከትቦና እና በፊልም ቀርጾ በማኖር ቀጣዩ ትውልድ እነኚህን መሰል አደጋዎችን ከሚያስከትሉ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ፣ ኃይማኖታዊና ኢኮኖሚያው ቀውሶችና ቅራኔዎች እራሱን በማራቅ ችግሮችን እጅግ በሰለጠነና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲፈታ ማድረግ ችለዋል። ዛሬ ላይ ያለው ትውልዳቸውም እነ ናዚ እና ሌሎች አንባገነኖች በታሪካቸው ውስጥ ያደረሱትን ሰቆቃና ግፍ እያሰብ የሚሸማቀቅ ወይም በፍርሃት የሚርድ ሳይሆን ታሪክን በታሪክነቱ ትቶ ሙሉ አቅሙንና ጊዜውን ከሳይንስና ተክኖሎጂ ጋር አዋህዶ በዚህ ምድር ላይ ያሻውን ሁሉ ለማድረግ የሚያስችል አቅም በመገንባት ላይ ይገኛል።

ወደ አገራችን ስንመለስ ኢትዮጵያም ዛሬ ያለችበትን ጂዮግራፊያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ሌሎች ገጽታዎች ለመላበስ ያበቋት እጅግ በርካታ ክፉ እና በጎ ተበለው የሚጠቀሱ የታሪክ ክስተቶችን አስተናግዳለች። ምንም እንኳን ከላይ ከተጠቀሱት የአለማችን አሰቃቂ ታሪኮች ጋር ባይወዳደርም አገራችንም ከውጭ ወራሪዎች በተሰነዘረባት ጥቃትም ሆነ በልጆቿ መካከል በተከሰቱ የእርስ በእርስ ግጭቶች በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ውድ ልጆቿን አጥታለች። ድህነትን ጠራርጎ ሊያስወግድ ይችል ከነበረው አቅም በላይ በብዙ እጥፍ የሚገመት አንጡራ ሃብቷን በጦርነቶች፣ በግጭቶችና በዘራፊዎች ተነጥቃለች። ይህ እና ሌሎች በርካታ ምክንያቶችም ተደራርበው አገሪቱን ከድሃም ድሃ ተብለው ከሚጠቀሱት አገሮች ተርታ አሰልፈዋታል። እንግዲህ ትልቁ ጥያቄ እኛስ እንደ ሌላው ዓለም ሕዝብ አገራችን ካለፈችበት የረዥም ዘመን ታሪክ እና በየወቅቱ ከተከሰቱ መጥፎና በጎ የታሪክ ክስተቶች ምን ተማርን? ተምረንስ ለዛሬ እኛነታችን ምን አተረፍን? በአያቶቻችን እና በእኛ መካከል በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ እና በፖለቲካ ተክለ አቋማችንም ሆነ አመለካከታችን ዙሪያ ለውጦች አሉ ወይ? ለውጣችን ቁልቁል ወይስ ካለፉት ወገኖቻችን የህይወት ተመክሮ ትምህርት ወስደን የደረስንበት የላቀ የአስተሳሰብና የኑሮ ደረጃ አለ? የታሪክ መዛግብቶቻችንስ ያለፉ ነገስታቶችን እና የጦር አበጋዞቻቸውን ከማወደስና ገድላቸውን ከመተረክ ባለፈ በቀጣዩ ትውልድ ሕይወት የጎላ ሚና ሊኖራቸ በሚችል መልኩ ተዘጋጅተዋል ወይ? ወይስ ‘እኔ የገሌ ዘር’ እያለ እንዲያዜምና በአያቶቹ ገድል እንዲያቅራራ ብቻ ተደርገው ነው የተዘከሩት? እንደ እኔ እምነት ከምዕራቡ አለም እኛንና ብዙዎች የአፍሪቃ አገራትን ከሚለዩን ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ ከነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ የሚመነጩ ይመስለኛል።

የዛሬ መቶ እና ሁለት መቶ አመት በፊት የተፈጠሩ የታሪክ ክስተቶችን ፍጹም በተዛባ መልኩ እያጣቀስን ልክ የእኛ የልፋት ውጤት አስመስለን እስኪያልበን የምንፎክርና የምንጨፍር እኛ ነን። ታሪክን እና ጀግኖችን ማወደስ ተገቢ ቢሆንም የኛን ድርሻ እነሱን በማወደስ ብቻ ስንገታው አደጋ ላይ ይጥለናል። እንደ አያቶቻችን ታሪክን መስራት ሲያቅተን ታሪክ ሰሪዎችን በማውሳትና በዜማና በግጥም ማወደስ ብቻ ብንኮፈስ የዛሬውን ማንነታችንን አይሸፍነውም። ይህ በአያቶቻችን ታሪክ ውስጥ ተደብቀን ‘በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ’ እያሉ ማዜም፣ መፎከር፣ ማቅራራትና ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ዛሬ ከተጣቡን የድህነት፣ የፖለቲካ ጭቆና እና ማኅበራዊ ቀውስ የማያስጥለን እና ነፃ የማያወጣን እሰከ ሆነ ድረስ ኩራታችን ከድንፋታ አያልፍም። አገሬን እወዳልሁ፣ በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ እያሉ ባንዲራ ለብሶ ማቅራራት በተግባር ካልታገዘ የውሸት ወይም ባዶ ኩራት (false pride) ነው የሚሆነው። እውነተኛ ኩራት የሚመነጨው ከራስ ነው፤ የራስን ማንነትን በማወቅና በመቀበል ላይ የሚመሰረት ነው። ማንነትን አምኖ መቀበል አቅማችንንም አብረን እንድፈትሽ ይረዳል። የዛሬ ባዶነታችንን በአያቶቻችን የታሪክ ገድል እንድንሞላ ወደሚያስገድድ የሞራል ክስረት ውስጥም እንዳንገባ ይረዳናል። የዛሬ ውርደታችንን በአድዋ ድል እና በሌሎች የአያቶቻችን ተጋድሎዎች በተገኙ ስኬቶችን ልንሸፍነው ከመጣር ይልቅ ታሪክ እንድንሰራ ብርታት ይሆነናል።

በሌላ በኩል የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ያሳቀፉንን የዘረኝነት መርዝ እያራባን በታሪክ ተፈጽመዋል የተባሉ አንዳንድ ክስተቶችን እየመነዘርን ‘ያንተ ቅም ቅም አያትህ የእኔን ቅም ቅም አይታቶች በድሎ ነበር፤ ስለዚህ በቅም ቅም አያቶቼ ላይ ያንተ ዘሮች ላደረሱት በደል ኃላፊነቱን አንተ ትወስዳለህ እያልን ድርጊቱን ዛሬ ላይ እንደተፈጠረ በመቁጠር የምንጋጭና ለመነጣጠል እንቅልፍ አጥተን የምናድርም አለን። እራስን እንደተበዳይ ሌላውን የኅብረተሰብ ክፍል እንደ በዳይ በመቁጥርና የተዛባን ታሪክ በመተንተን ለዛሬው በዘረኝነት መርዝ ለተለወሰው የፖለቲካ አጀንዳቸው ማሳኪያነት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ካፈር የሚለውሱ ኢትዮጵያዊያኖችም (እነሱ ኢትዮጵያዊ አይደለንም ቢሉም) ልብ ሊገዙ ይገባል። በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ጎሣዎች በገዛ አገራቸው እኩል መብትና ጥቅም እንዲረጋገጥላቸውና የሁሉም አገር እንድትሆን ከመጣር ይልቅ በዘረኝነት ስሜት ውስጥ ተወጥሮ ኢትዮጵያዊነትን መካድና ከራስ ጎሣ ውጭ ያለውን የኅብረተሰብ ክፍል እንደ ጠላት መቁጠር መዘዙ ብዙ ነው። ይህን ለመረዳት ብዙ ምርምር አያስፈልገውም። በቅርባችን ካለችው ከሩዋንዳ ትምህርት መውሰድ ይቻላል። ይህን የዘረኝነት እሳት እየተቀባበሉ የፖለቲካ መታገያቸው ያደረጉ ኃይሎችም ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ በስሙ የሚነግዱበት ሕዝብ ሊያወግዛቸው ይገባል።

እርቀን ሳንሄድ የቅርብ ጊዜ ታሪካችንን እንኳን ብንፈትሽ ዛሬ ለምንገኝባቸው እጅግ ውስብስብ እና ፈታኝ ችግሮች መንስዔ የሆኑትን ነገሮች በቀላሉ ልንገነዘብ እንችላለን። የችግሮቻችንን ምንጮች እና ያስከተሉብንን መዘዝ በቅጡ መረዳት ከቻልን ከተዘፈቅንበት አረንቋ ውስጥ ለመውጣት ጊዜ ላይወስድብ ይችላል። መወጣጫውም ላይርቀን ይችላል። ትልቁ ጥያቄ ችግሮቻችንን ከመዘርዘር ባለፈ ምንስዔዎቻቸውንም በቅጡ ተረድተነዋል ወይ? እንደ አንድ አገር ሕዝብ በችግሮቻችን እና በችግሮቹ ምንጭ ዙሪያ የጠራ የጋራ ግንዛቤ አለን ወይ? በፖለቲካ እና በሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ስንደራጅስ ከነዚህ ግንዛቤዎች ተነስተን ነው ወይ? የጋራ የሆኑ ችግሮች ሰዎችን ያስባስባሉ፣ ለድርጅቶች መፈጠርም መንስዔ ይሆናሉ፣ ችግሮቹንም ለመቋቋም እና ለማስወገድ “ከአንድ ብርቱ …” እንደሚባለው ኃይልን ይፈጥራሉ። ይሁንና ስብስቡ ወይም የተደራጀው ኃይል ፊት ለፊት ከተጋረጡት ችግሮች ጋር ከመፋለም ባለፈ በድጋሚ እንዳይከሰቱ ምንጮቻቸውን ለማድረቅ የሚያስችል እይታ ከሌለው እና አቅሙንም በዚያ ደረጃ ካላሳደገ ይህ አይነቱ ማኅበረሰብ ሁሌም ለተመሳሳይ አደጋዎች የተጋለጥ ነው። የችግሩን መንሰዔ አጥንቶ ምንጩን ለማንጠፍ ከሚያወጣው ጉልበት፣ ገንዘብና ጊዜ የበለጠ አዳዲስ ችግሮች በተከሰቱ ቁጥር ከተኛበት እየባነነ ተነስቶ ችግሮቹን ለመቋቋም የሚያስችሉ ድርጅቶችን ለመፍጠርና ለማፍረስ የሚያወጣው ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት እጅግ የላቀ ነው። በእንዲህ አይነት ማኅበረሰብ ውስጥ ጠንካራ የሆኑና ልምድ ያካበቱ ድርጅቶችን መፍጠር አይቻልም። ብዙዎቹ ድርጅቶች ሳይጎረምሱ፣ ሳይጎለምሱ እና ሳያረጁ በጨቅላነታቸው ይሞታሉ ወይም ደንዝዘው ስማቸውን ብቻ ይዘው ይቀራሉ። ይህ አይነቱ ማህበረሰብ አውራ የሚሆኑና በምሳሌነት ሊጠቀሱ የሚችሉም የፖለቲካ፣ የኃይማኖት እና የማኅበራዊ ህይወት መሪዎችን የመፍጠር አቅም የለውም፤ አይፈጥርምም፤ በራሳቸው ጥረት ቢፈጠሩም ጎልተው እንዲታዩ እድሉን አይሰጥም። ትላንት ያነገሳቸውን በማግስቱ አፈር ከድሜ ሲደባልቃቸው ምንም አመክንዮ አይፈልግም። ሲያከብርም፣ ሲሾምም፣ ሲያዋርድም ሆነ ሲኮንን በስሜት ነው። በተለይም እንደኛ በብዙ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ ተተብትቦ ግራ ለተጋባ ማኅበረሰብ ልምድና በእውቀት የጎለበቱና የሕዝብ አመኔታን ያገኙ ባለ ዕራይ ድርጅቶችና ግለሰቦች መኖር እጅግ ወሳኝ ነው።

የፖለቲካም ሆነ ሌሎች ልዩነቶቻችንን የምንይዝበት መንገድ ሊፈተሽ ይገባዋል። የቀዝቃዛው የአለም ጦርነት ማብቂያን ተከትሎ የፈረሰውና ጀርመንን ለሁለት ከፍሏት የነበረው ግንብ ሲናድ ምስራቅና ምዕራቡን ወደ አንድ አገር ከመለወጥ ባለፈ መላው አውሮፓን አንድ ያደረገ ክስተትን ፈጥሯል። የሰብአዊ መብቶች እና የዲሞክራሲ ጽንሰ ሃሳቦች የልዩነት ማጦዣ ምክንያቶች ከመሆን ወጥተው ጀርመንን ብቻ ሳይሆን አውሮፓን ያዋሃዱ ተጨባጭ እውነታዎችን ፈጥረዋል። ይህን ተከትሎም ከታሪክ ለመማር ዝግጁ በሆኑ በበርካታ የአለማችን አገራት በመሬት የተገነቡም ሆነ በሰዎች አዕምሮ ውስጥ የተካቡ የልዩነት ግንቦች ሁሉ ፈርሰው ዜጎች ለጋራ ራዕይ በጋራ የመቆም ጽናትን አሳይተዋል። ሕዝባቸውንም ነጻ አውጥተዋል። ሌሎች እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የተለያዩ አገሮች (አብላጫዎቹ የአፍሪቃ አገራት) የልዩነቶቻቸውን ግንቦች አጠንክረውና አዳዲስ ግንቦችን በአይምሯቸው ውስጥም ገንብተው የተሰበጣጠረና የሚፈራራ የኅብረተሰብ ክፍልን በመፍጠር ጉዞዋቸውን ቀጥለዋል። የጎሣ ግንቦች፣ የሥልጣን ግንቦች፣ የኃይማኖት ልዩነት ግንቦች፣ የድሃና የሃብታም ግንቦች፣ የጨቋንና የተጭቋኝ ግንቦች፣ ሌሎች ማኅበረሰቡን በአንድ ላይ እንዳይቆም እና ድህነትና አንባገነንነትን አሽቀንጥሮ እንዳይጥል አቅም የሚያሳጡ በርካታ የልዩነት ግንቦች ተገንብተዋል።

ድርጅቶችን እና መሪ የሚሆኑ ግለሰቦችን እየፈጠርንና መልሰን እየደፈጠጥን የመጣንበትን የ50 ዓመታት የፖለቲካ ጉዞ ወደ ኋላ መለስ ብለን ብንቃኝ ይህንን እውነታ ያረጋግጥልናል። ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ ለቁጥር የሚታክቱ የፖለቲካ፣ የሙያና በማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮሩ ድርጅቶች ተፈጥረው ብዙዎች ካለሙበት ሳይደርሱ ከስመዋል። ጥቂቶችም ባልሞት ባይ ተጋዳይነት በመኖርና ባለመኖር መካከል ሆነው ቀጥለዋል። በከሰሙትም እግር ሌሎች በርካቶች ተተክተው በተመሳሳይ አዙሪት ውስጥ ወድቀው የኅብረተሰቡን ቀልብ ለመሳብ ደፋ ቀና ሲሉ ይስተዋላል። እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባው በዚህ ዘመን ውስጥ ብቅ ብለው በከሰሙትም፣ ተውተርትረው ቆይተው በተዳከሙትም፣ አዳዲስ ስም እየያዙ በተፈጠሩትም ድርጅቶች ውስጥ ዋነኛ ተዋናዮቹና የድርጅቶቹ ፈጣሪዎችም ሆኑ አጥፊዎቹ አንድ አይነት ሰዎች መሆናቸው ነው። ትላንት በአንድ ድርጅት ጥላ ስር ሆነው ሌሎችን እንደ ጠላት ይፈርጁ የነበሩ ሰዎች ዛሬ የብዙ ድርጅቶች ፈጣሪዎች ሆነዋል። ትላንት በጠላትነት የሚፈራረጁ ድርጅቶች አባል የነበሩ ሰዎች ቂማቸውን እንዳረገዙ ዛሬ በአንድ ድርጅት ጥላ ሥር የተሰባሰቡበትንም ሁኔታ እናያለን። በድርጅቶቹ መካከል እጅግ ጠባብ የሆኑ የርዕዮታለም ልዩነቶች ከመኖራቸው ውጭ አብዛኛዎቹ የመጨረሻ ግባቸው አንድ እና አንድ ነው። ዲሞክራሲ የሰፈነባት፣ የሕግ ልዕልና የተረጋገጠባት፣ ሰብአዊ መብቶች የተከበሩባት እና ድህነትን ያሸነፈች ኢትዮጵያን ማየት፣ መፍጠር ነው። በነዚህ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ የሚለያዩ ድርጅቶች ያሉ አይመስለኝም፤ ሊኖርም አይችልም። ልዩነቱ እነዚህ ግቦች ላይ ለመድረስ ድርጅቶቹ በሚከተሉት አቅጣጫና መንገድ ቅየሳ ላይ ነው።

በዚህ የ50 ዓመት ጉዞ ውስጥ በሽብር መንፈስና በነውጥ ተግባራት የተሞላው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በድርጅቶች መካከል እርስ በርስ አለመተማመንንና መካካድን ፈጥሯል። ይህም አለመግባባቶቹ ከጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት አልፈው እልቂትን አስከትለዋል። በዚያም የተነሳ አገሪቷ በፍርሃት እንድትዋጥና ሕዝቧም በስጋት እንዲኖር፤ የፍርሃት ባህልም እንዲጎለብት ከፍ ያለ ሚና ተጫውቷል። ዛሬ በእያንዳንዳችን አዕምሮ ውስጥ በርካታ የልዩነት ግንቦች ተፈጥረዋል። በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በሲቪክ ማኅበራት፣ በኃይማኖት ተቋማት፣ በማኅበረሰብ ድርጅቶች መካከልም የበርሊን ግንብ አይነት ግዙፍ የልዩነት ግንቦች ተፈጥረዋል። የዛሬዎቹ ኃይሎች ከገዢው ፓርቲ በስተቀር በትጥቅ የተደራጁ ስላልሆኑ ነው እንጂ ለመጠፋፋት ቅርብ ናቸው። ትልቁና እያንዳንዳችን እራሳችንን ልንጠይቅ የሚገባን፤ እነዚህን ግንቦች ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዴት ንደን እና በላያቸው ላይ ተረማምደን ልብ ለልብ እንዋሃዳልን? እንዴት እንደ አንድ ሕዝብ የጋራ ዕራይ፣ የጋራ መዝሙር፣ የጋራ ህልም፣ የጋራ መፈክር፣ የጋራ መድረክና የጋራ አገር እንፈጥራለን? እንዴት ከቂም፣ ከበቀልና ከቁርሾ ሽረን ከታይታና ከቧልት ፖለቲካ ወደ እውነተኛ የፖለቲካ ሕይወት እንመለሳለን?

ለማጠቃለል ያህል በእኔ እምነት ከተተበተብንበት ውስብስብ ችግሮችና ከተጫነን የፍርሃት ድባብ ለመላቀቅ፤ አልፎም ጤናማ የሆነ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ሥርዓት ባለቤት የሆነ ማኅበረሰብ ለመፍጠር የሚከተሉት ተግዳሮቶች ቢቀድሙ ይበጃል እላለሁ::

–       ዛሬ ለፖለቲካ ንትርክና  እርስ በርስ መፈራራት እንደ ምክንያት የሚነሱት የታሪካችን ክፍሎች ከፖለቲካ፣ ከኃይማኖት እና ከሌሎች ወገንተኝነት ነጻ በሆኑ ምሁራን በአግባቡ የሚጠኑበት ማዕከል ቢኖረን። የመወዛገቢያ ነጥብ የሆኑትም ታሪካዊ ኩነቶችን በአግባቡ ቢጠኑ እና በተለያዩ መንገዶችም ተደግፈው ለማስተማሪያነት ቢውሉ በድንቁርና ላይ ከተመሰረቱት ታሪክ ጠቀስ የሆኑና በጥላቻ መንፈስ የተሞሉ ክርክሮች ወጥተን እውቀትን በዋጁ ውይይቶች ላይ እናተኩራልን።

–       የሩቁን ለታሪክ ምሁራን እንተወና ባለፉት አምሣ ዓመታት ከ1960 ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ በፖለቲካ ትግል ውስጥ ዋነኛ ተዋናይ የሆኑ ኃይሎች ዛሬም በአገሪቷ የለት ተዕለት የፖለቲካ ህይወት ውስጥ በግራና በቀኝ ሆነው እና በመቶ ድርጅቶች ጉያ ውስጥ መሽገው በአገሪቷና በድሃው ሕዝብ እጣፈንታ ላይ ወሳኞች ሆነው ቀጥለዋል። በተለይም ‘ያ ትውልድ’ በሚል የሚታወቀው የኅብረተሰብ ክፍል ከልጅነት እስከ አዋቂነት ክቡር ሕይወቱን፣ ጊዜውን፣ ገንዘቡን እና እውቀቱን ያለምንም ስስት የዛችን አገር እጣ ፈንታ ለማቅናት መስዋዕትነት ሲከፍል ቆይቷል፤ ዛሬም ዋነኛ ተዋናይና አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ ቀጥሏል። ይህ ትውልድ ትላንትናም ሆነ ዛሬ በገዢና በነጻ አውጪዎቻች ቡድኖች ተፈራርጆ እርስ በርሱ ተጨራርሷል፣ ቂምና ቁርሾም ተጋብቷል፣ ተሰዷል አሰድዷል። ዛሬም በልቡ ቂም ይዞና በቀልን አርግዞ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ መሽጎ የጎሪጥ ይተያያል። ባገኘው አጋጣሚም ሆሉ ይናቆራል። ‘ቂም ተይዞ ጉዞ’ እንዲሉ ትላንት በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ ሆነው በጠላትነት ይፈራረጁና ሊገዳደሉ ይፍላለጉ የነበሩ ሰዎች ይህን ሸክማቸውን በንስሃ እና በይቅር ባይነት ከላያቸው ላይ ሳያራግፉ ውስጥ ውስጡን እየተብሰከሰኩና እየተፈራሩ ገሚሶቹ በልጅነታቸው በቆረቡባቸው ድርጅቶች እየማሉ ቀሪዎቹም ዘመኑ በወለዳቸው አዳዲስ ድርጅቶች ውስጥ ሆነው የለበጣ ውህደት እየመሰረቱ በዋዜማው ይፈረካከሳሉ። እንደ እኔ እምነት ከዚህ የእርስ በርስ መፈራረጅ፣ መፈራራትና የቆየ ቂምና ጥላቻ ሳንሽር የምንክበው ካብ ሁሉ የእምቧ ካብ ነው የሚሆነው። እየሆነ ያለውም ይሄው ነው። ከዚህ አዙሪት ወጥተንና ከቂም ተላቀን የጋራ ራዕይ እንዲኖረን እያንዳንዱ ግለሰብ እራሱን ለይቅርታ ማዘጋጀት አለበት። ከልብ የበደላቸውን ይቅርታ ለመጠየቅና ይቅርታ ለመቀበል። ከድርጅታዊ ወገንተኝነትም እራሱን ነጻ አውጥቶ በሱና በድርጅቱ ላይ የተፈጸመውን በደል ብቻ ሳይሆን እሱም ጠላት ብሎ በፈረጃቸው ሰዎችና ድርጅቶች ላይ ያደረሰውን ግፍና በደል ለመናዘዝና ለደረሰውም ሁሉ አቀፍ ጥፋት ድርሻቸውን በድፍረት በማንሳት የተጠታቂነት ባህልን ‘ሀ’ ብለው ሊጀምር ይገባዋል።

–       ይህ ሁኔታም የደረሰውን የጉዳት መጠን በቅጡ እንድናውቅ ከማድረጉም ባሻገር እርስ በርስ የመወነጃጀሉን ታሪክ እንድንገታውና ልባችንንም በፖለቲካ ንስሃ አንጽተን የሚነገርለትን ያህል የተሳካ ባይሆንም እንኳ ልክ እንደ ደቡብ አፍሪቃው ‘በእውነት’ ላይ ወደ ተመሰረተ የእርቅ እና የሰላም መድረክ እንድቀርብ እድል ይፈጥርልናል።

–       የልጆቹን እርስ በርስ መጨራረስ እየተመለከት ፓለቲካ እንዲህ ከሆነ አርፎ መቀመጥ ይበጃል፤ እርም የፖለቲካ ነገር በሚል አይምሮውን ጥርቅም አድርጎ ዘግቶ የለት ጉርሱን ብቻ እየቃረመ የአገሩን የፖለቲካ እጣፈንታ ለእዝጌሩ ትቶ ደግ ቀንና መልካም አስተዳደርን እንደመና ከሰማይ እንዲወርድለት የሚጠባበቀውም የኅብረተሰብ ክፍል አይኑን ይገልጣል፤ ከመጠፋፋት ወደ ሰለጠነ የውይይት ባህል በሚሻገረው የፓለቲካ ኃይልም ላይ እምነት ያሳድራል፤ እራሱንም ከፍርሃት ነጻ አውጥቶ በሙሉ ልብ በአገሩ ጉዳይ ባለቤት ይሆናል።

–       ስለዚህም የገዢው ኃይል ወያኔ ካለበት ጥልቅ ፍርሃት እና የሥልጣን ጥም የተነሳ ለእንዲህ ያለው ለውጥም ሆነ የሰላምና የእርቅ ጎዳና ገና ዝግጁ ባይሆንም የተቀሩት የፖለቲካ ሃይሎች መንገዱን በመጀመር ለዘመናት በመካከላቸው የቆየውን ቁርሾና ቂም ከአዕምሯቸው በማውጣት ከልብ የመነጨ እርቅ በማድረግ የልዩነት ግንቦችን ማፈራረስ ይጠበቅባቸውል። የሰላም፣ የእርቅ እና የእውነት አፈላላፉ ጉባዔ ያስፈልገናል።

በእውነት ላይ ተመስርተው ተቃዋሚዎች በቅል ልቦና ከታረቁ አብረው ከሠሩ በኢትዮጵያዊና በኢትዮጵያዊያን ላይ ለዘመናት እንደ መዥገር ተጣብቀው ደማችንን የሚመጡትን፣ ክብራችንን ገፈው እርቃን ያስቀሩንን፤ ድኅነት፣ እርዛት፣ አንባገነናዊ ሥርዓትና ጭቆና፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ ጦርነትና የእርስ በርስ ግጭቶች፣ ድንቁርና፣ ጨለምተኝነት፣ ፍርሃት፣ ሙስና እና ጥላቻን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነቅለን መጣል እንችላለን። ቅን ልቦና ይኑረን! ለዘመናት የተጫነንን ሸክማችንንም እናራግፍ። ያኔ ለፍቅር በፍቅር፣ ለሰላም በሰላም፣ ለነጻነት በነጻነት፣ ለአንድነታችን በአንድነት የምንሰራበትና ታሪክ ዘካሪ ብቻ ሳንሆን ታሪክ ሰሪ የምንሆንበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም።

 

ቸር እንሰንብት!

ያሬድ ኃይለማርያም
ከብራስልስ

http://humanrightsinethiopia.wordpress.com/

posted by Tseday Getachew

በኢትዮጵያ በዲያስፖራው ከተያዙ 744 ፕሮጀክቶች ውስጥ ሩቡ እንኳን በአግባቡ ተግባራዊ አልሆኑም ተባለ፡፡

ethiowaga.gif

  ኢሳት ዜና :-ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳያስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ጀኔራል የተገኘ መረጃ  በግምት ከ2-3 ሚሊዮን የሚደርሱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የአለም ከፍሎች ቢኖሩም ለአገራቸው ያላቸው አስተዋጽኦ ግን አነስተኛ ነው ብሎአል።

አውሮፖና አሜሪካ የኢትዮጵያውያኑ ዳያስፖራዎች ዋነኛ መዳረሻዎች ሲሆኑ በርካታ የዳያስፖራው አባላትም በእነዚሁ አህጉራት ይገኛሉ ይላል።

እውቅና ያገኙ ተመራማሪዎች ፤ የጤና ባለሙያዎች ፤የዩንቨርስቲ መምህራን ፤በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚሰሩ ባለሙያዎች ፤ድርጅቶችን በመክፈትና በሌሎች መስኮች የተሰማሩ ኢንቨስትመንት ተቀጣሪዎችም መኖራቸውንም ሰነዱ ያወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት እንደ ህንድና ቻይና አገራት በአገራቸው ላይ ያላቸውን የልማት ተሳትፎ ለማጠናከር መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ቢሆንም በተለይ ከሜሊኒየም መባቻ ጀምሮ የዳያስፖራው ተሳትፎ እየጨመረ መጥቷል ቢባልም በተግባር የሚታየው የዚህ ተቃራኒ ነው ብሎአል።

‹‹የዲያስፖራ ተሳትፎ ዓለም አቀፋዊና የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታዎች›› በሚል ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው

 በ2005 ዓ.ም በተወሰኑ ከተማ አስተዳደሮች በተደረገ የዳሰሳ ጥናት በዲያስፖራው ስም ተመዝግበው ለመንቀሳቀስ ካመለከቱት 744 ኘሮጀክቶች መካከል በአሁኑ ሰዓት አገልግሎት ወይም ምርት መስጠት የጀመሩት 120 ኘሮጀክቶች ብቻ ናቸው።

ሁሉም ፕሮጀክቶች ወደስራ ከገቡ ለአንድ ሚልየን 82,972 ለሚሆኑ ዜጐች ቋሚ የሥራ እድል እንዲሁም ለ2 ሚልየን 131 ሺ 200 ዜጐች ጊዜያዊ የሥራ እድል ይፈጥራሉ ብሎ መንግስት ተስፋ ማድረጉም ተመልክቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳያስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ጀኔራል ዲያስፖራው በአገሩ ላይ የሚፈለገውን ሚና ለመጫወት ያልቻለባቸውን መንገዶች ዘርዝሮ አቅርቧል። በቅድሚያ የቀረበው ምክንያት  ዲያስፖራው በሀገሪቱ መንግስት ላይ ያለው አመለካከት የተዛባ መሆን የሚለው ይገኝበታል።

ዲያስፖራው በአሁኑ ስዓት ኢህአዴግን ከመደገፍ ይልቅ በኤርትራ ለሚንቀሳቀሱ የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ቡድኖች መደገፍ ይፈልጋል የሚለው ሰነዱ፤ ከመንግስትም ወይም ከተቃዋሚዎች ከመጎዳኘት ይልቅ መሃል ሰፋሪ መሆን የሚመርጡ የዲያስፖራ አባላት መኖራቸውን ይገልጻል።

በክልሎች ያለው የመልካም አሰተዳደር ችግር ፤ሙስና ፤ ዲፕሎማቶች ተገቢውን ስራ አለማከናወናቸው በመንግስት በኩል የሚታዩ ድክመቶች ናቸው በማለት የሚጠቅሰው  ሰነዱ፤ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ በሚመጡ የዲያስፖራው አባላት የሚታዩ ችግሮች በማለት ከዘረዘሩዋቸው መካከል ደግሞ ”

በተሠጣቸው የኢንቨስትመንት ቦታ ላይ ለማልማት ያላቸው አቅም አናሳ መሆን፣ የተቀበሉትን ቦታ ለሌላ አካል ለማስተላለፍ መሞከር፤ ፈጥኖ ወደ ስራ አለመግባትና አጥሮ ማስቀመጥ፣  የመሬት ሀብት ስለሚባክን ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ቅሬታ መነሳት ፤እነሱ በሚፈልጉበት ጊዜና መንገድ ጉዳያቸው ካልተፈፀመ መንግስትን የማማረርና የመልካም አስተዳደር ችግር እንደሆነ የማስመሰል ሁኔታዎች መኖር ፣

ከዳያስፖራዎቹ ከራሳቸው ምን እንደሚጠበቅና የኢንቨስትመንት አሠራር ህግን ያለማወቅ ፤ለጠየቁት ፕሮጀክቶች መሬት ማግኘታቸውን ሳያረጋግጡ ለፕሮጀክቶቻቸው አገልግሎት የሚውሉ ማሽነሪዎችን ግዥ ፈጽመው በወደብ የመጋዘን ኪራይ ያለአግባብ ወጭ እያወጣን ነው ብለው ማማረር ፤አብዛኛው ዳያስፖራ ወደ ክልሉ መጥቶ ለማልማት ሲፈልግ ቅድሚያ መረጃ የሚሰበስበው በየግለሰቡ መሆኑ” የሚሉት ይገኙበታል።

በአገር ውስጥ ያሉት የዳያስፖራ ተወካዮች ጉዳይ ለማስፈጸም ችግር ካጋጠማቸው ውጭ ለሚኖሩት ዳያስፖራዎች ችግሩን አጋኖ የመናገር ሁኔታ መኖር ፤በተወካዮቻቸው ድክመት ፕሮጀከቶቻቸው በሚፈልጉት መንገድ ካልተፈጸሙላቸው መንግስትን የማማረር ሁኔታ መኖር፣ በክልሉ  የተመዘገበውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ለውጥ አምኖ ለመቀበል ያላቸው ዝግጁነት አናሳ መሆን፤

ዳያስፖራው የኢንቨስትመንት ፈቃድ ካወጣ በኋላ ፕሮጀክቱ ወደ ተግባር እንዲገባ ለማድረግ የሚሰጠው ድጋፍና የሚደረገው ክትትል  አናሳ መሆን ፤ዳያስፖራው ለሚያቀርበው ጥያቄ አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ በመረጃና በአሰራር ላይ ተመስርቶ በወቅቱ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ

ነገ ዛሬ በማለት ስለሚያጉላላና ለአላስፈላጊ ወጭ ስለሚዳረግ መንግስትን ከማማረራቸውም በላይ ሌሎች ዳያስፖራዎችን ወደ በሀገራችን መጥተው በኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ለማድረግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ እየፈጠረ መሆኑ በሰነዱ ላይ ተዘርዝሮ ቀርቧል።

“ከፍተኛ አመራሮች ወደ ውጭ አገራት ሂደው ዳያስፖራውን ወደ ሀገሩ መጥቶ በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች እንዲሳተፍና ሀገሩን እንዲደግፍ ሲያወያዩት ‘ኑና አልሙ ትላላችሁ ወደ ክልላችን ስንሄድ ግን እንጉላላለን፤ተገቢውን አገልግሎት አናገኝም፤ የተሻሉ ሰዎችም ተስፋ ቆርጠውና ክልላቸውን ጠልተው ሲመለሱ እናያለን…’ በማለት እንደሚናገሩ ሰነዱ ይገልጻል።

ሰነዱ በትግራይ 95፣ በአማራ 120፣ በአፋር 60፣ በቤንሻንጉል 51፣ በኦሮምያ 114፣ በሀረሪ 96፣ በሶማሊ 83፣  በደቡብ 111 እንዲሁም በጋምቤላ 33 የዲያስፖራ ፕሮጀክቶች መመዝገባቸውን ያሳያል። ከህዝብ ብዛት አንጻር ሲነጻጸር በኦሮሚያ፣ በአማራና በደቡብ ክልሎች የዲያስፖራው ተሳትፎ እጅግ አነስተኛ ነው። አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በሚኖርባቸው በእነዚህ ክልሎች የመጣው ዲያስፖራ ተሳትፎ አነስተኛ መሆን ከፖለቲካው ጋር በቀጥታ የተያያዘ መሆን እና አለመሆኑ በሰነዱ ውስጥ አልተገለጸም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም የሚመሩት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከ120 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን አስከፊ በሆነ ሁኔታ እንዲባረሩ ቀሪዎቹም ተመሳሳይ እጣ እንዲገጥማቸው በማድረጉ በኩል ተጠያቂ መሆኑን አንዳንድ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ለኢሳት ገልጸዋል።

እነዚሁ ሰራተኞች እንደገለጹት የመንግስት የዲያስፖራ ፖሊሲ በአንቀጽ 5 ላይ ” ህጋዊ ወረቀት ለሌላቸው በውጭ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሚኒስቴሩ ህጋዊ የመታወቂያ ወረቀት  በመስጠት በችግራቸው ጊዜ ለመድረስና እና በአገሪቱ ልማት ተሳታፊ እንዲሆኑ ያበረታታል፣ ችግር ባጋጠማቸው ጊዜም አስፈላጊውን ክትትል፣ ድጋፍና እርዳታ ያደርጋል” የሚል ተደንግጎ ቢገኝም፣በሪያድ የሚገኘው ኢምባሲም ሆነ በጅዳ የሚገኘው ቆንስላ ለኢትዮጵያውያኑ ህጋዊ ወረቀት በመስጠት አሁን የተከሰተው አደጋ እንዳይከሰት ማድረግ ይችል ነበር፣

ለዚህም መንግስት ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ነው ሲሉ እነዚሁ ሰራተኞች ገልጸዋል። ከዚህ የበለጠ የከፋ አደጋ አልነበረም የሚሉት ሰራተኞች፣ መስሪያ ቤቱ ያሳየው ተነሳሽነት እና በሁዋላም ከተጠያቂነት ለማምለጥ በሚል ከስደተኞች ጋር ፎቶ ግራፎችን በመነሳት ችግሩን ለማድበስበስ ተሞክሯል ይላሉ።

ህጉ የወጣው ለይስሙላ ነው ካልተባለ በስተቀር በዲያስፖራ ፖሊሲ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው ለኢትዮጵያውያኑ ህጋዊ ወረቀት በጊዜው በመስጠት ችግሩን ማስቀረት ይቻል ነበር የሚሉት እነዚሁ ሰራተኞች በመካከለኛው ምስራቅ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ለአገራቸው ችግር ፈጥነው በመድረስ ያሳዩት ተሳትፎ በፖሊሲው ላይ ሳይቀር መገለጹን አውስተዋል።

በአንቀጽ አንድ ተራ ቁጥር 2 ላይ ” አብዛኞቹ ሙያ የሌላቸው ወይም በከፊል ሙያ ያላቸው በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስትና አገር ጥሪ ባቀረበላቸው ጊዜ በፍጥነት የሚደርሱ፣ በአገራቸው የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች የሚሳተፉና ለቤተሰቦቻቸው በየጊዜው ተቆራጭ ገንዘብ የሚልኩ ናቸው” ሲል ይገልጻቸዋል።

የአለም ባንክ ኢትዮጵያ በእየአመቱ በውጭ ከሚገኘው ኢትዮጵያዊ 3 ቢሊዮን 200 ሚሊየን ዶላር እንደምታገኝ የገለጸ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዙት በአረብ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ናቸው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ለኢትዮጵያውያን ስደተኞች ህጋዊ የመታወቂያ ወረቀት በማደል ችግሩ እንዳይከሰት ለማድረግ ለምን እንዳልቻለ እስካሁን አሳማኝ ማብራሪያ አልሰጠም።

ESAT

posted by Tseday Getachew

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተመሰረተበትን አንደኛ አመት አስመልክቶ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ

Ginbot 7 Popular Force logo

ታህሳስ 7  2006 ዓም የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከተመሰረተ  አንድ አመት ሞላው። አንድ አመት  በጭንቅና  በአሳር  ለተያዘች የዛሬይቱ ኢትዮጵያና ህዝቧ እጅግ ረጅም ግዜ እንደሆነ ህዝባዊ ሃይሉ በሚገባ  ይገነዘባል። ባላፈው አንድ አመት ውስጥ የኢትዮጵያን ህዝብ የመከራ የአሳርና የውርደት ህይወት ይበልጥ እየሰፋ፣ የሚፈጸምበት ግፍ ይበልጥ እየገዘፈ መሄዱን አይተነዋል። በሃገርና በህዝብ ላይ እየወረደ ያለውን ወያኔ ወለድ የስቃይና የፍዳ ናዳ በቅጡ ላጤነው  ሃገሪቱና ህዝቧ የአዳዲስ የስቆቃና የመከራ አይነቶች መፈተኛ ቤተ ሙከራዎች እየተደረጉ ለመሆኑ ጥርጥር አይኖረውም። ለሚራበው ለሚረገጠው በግፍ ለታጎረው፣ በኑሮ ውድነት ለሚጠበሰው፣ ለተሰደደው ለተፈናቀለው ኢትዮጵያዊ እንድ አመት በሲኦል የቀናትና የወራት መቁጠሪያ እንደሚለካ ዘመን እጅግ የረዘመ የስቃይ ግዜ ነው።

የዋልድባ መነኩሳት ገዳማችን  አትድፈሩ አታፍረሱ በማለታቸው እየተገረፉ ለዘመናት ፈጣሪያቸውን ከሚማጸኑበት ለሃገርና  ለህዝብ ምልጃ ከቆሙበት ገዳም በዘር መመዘኛ እየተለዩ  እንደቆ ሻሻ ተጠርገው የተባረሩበት ፣ እምነታችን አትንኩ ያሉ የእስልምና እምነት ተከታዮችና  መሪዎቻቸው በሃሰት ክስ ተመስርቶባቸው  ወህኒ መውረዳቸው አንሶ  ወንድሞቻችን ይፈቱ በማለት  ሰላማዊ  ጥያቄ ያቀረቡ ወገኖቻቸን በወያኔ ነፍሰ- ገዳዮች  በአረመኔያዊ ጭካኔ የተጨፈጨፉት በዚሁ አመት ነው። ወያኔ በህዝብ መሃከል በዘራው የዘር መርዝ የተነሳ በሽዎች የሚቆጠሩ አማሮች ከጉራ ፈርዳና ከቤንሻንጉል፣ ኦሮሞዎች ለዘመናት ከኖሩበት ምስራቅ ሃረርጌ  አካባቢ  እንዲፈናቀሉና በገዛ ሃገራቸው መድረሻ ቢሶች  እንዲሆኑ የተደረገው በዚህ አንድ አመት ውስጥ ነው። ጋምቤላዎች ሙርሲዎች አፋሮችና ሌሎችም ብሄረሰቦችና ማህበረሰቦች የተጨፈጨፉበት፣በልማት ስም ለመጡ የውጭ ወራሪዎችና ወያኔ ለፈጠራቸው ቱጃሮች ቦታ እንዲለቁ ተደርጎ ቀደምቶቻቸው ለዘመናት ከኖሩባቸው ቀየዎች እንዲነቀሉ ተደርገው እንደ አልባሌ ነገር የትም እንዲበተኑ የማድረጉ ሂደት ከመቼውም በላይ ተጠናክሮ የቀጠለው በዚሁ አመት ነው። በዚሁ አንድ አመት በወያኔ የሃገሪቱ ገዥዎች በህዝብ ላይ የተፈጸመው  ጭካኔና ወንጀል ተዘርዝሮ  የሚያልቅ አይደለም።

ይህ ወያኔ  ሰራሽ ሃገር በቀል የውርደትና  የስቃይ ህይወት አልበቃ  ብሎ ወያኔ ከሳውዲ የጨለማ ዘመን ገዥዎች ጋር በመተባበር ወንድሞቻችን በሳውዲ አውራ ጎዳናዎች ላይ እንዲታረዱ እህቶቻችን በቡድን በተደራጁ የሳውዲ ጎረምሳዎች  እንዲደፈሩ ሁኔታዎችን አመቻችቶ  ለኢትዮጵያውያን ያለውን እጅግ የከረረ ጥላቻ በአደባባይ ያሳየበት አመት ነው። እንዲህ አይነቱ የጅምላ ግፍና  ውርደት ከመከሰቱ በፊት ህዝባዊ ሃይሉ በአረብ ሃገር በባርነትና  በስደት የሚገኙ እህትቶቻችንን ወንድሞችችን ስቃይ  ስቃዩ አድርጎ በመውሰድ “ላንቺ ነው” በሚለው ድርጅታዊ መዝሙሩ “በባለጌ  አረቦች መዳፍ ውድ ክብራቸው ለጎደፈው እህቶቻችን፣ በአረቦች የባርነት ቀንበር ጀርባቸው ለጎበጠው  ወገኖቻችን እንደርስላችኋለን፣ የተሰባሰብነው  ደማችን የሚፈሰው የመከራ ቀናችሁን ለማሳጠር ነው” የሚል ቃል ኪዳኑ ሰጥቶ  ነበር። የድርጅታችንን ምስረታ አንደኛ  አመት ስናከብር ልባችንን ደስታ ሳይሆን ሃዘን እንዲሞላ የሚያደርገው ይህ ቃል ኪዳናችን ለማክበር የጀመርነው ጉዞ ከድርጅት ምስረታና ከድርጅታዊ ዝግጅት አልፎ   በኢትዮጵያ ህዝብ ጥላቻና ንቀት  የተነፋውን የወያኔን እብሪት በማስተንፈስ የወሰዳቸው ተጨባጭ የአለኝታነት እርምጃዎች ባለመኖራቸው ነው።

ምንም እንኳን ግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል እራሱን እንደ ድርጅት አቁሞ  ኢትዮጵያውያንን አሰባስቦ  መራራው ትግል የሚጠይቀውን የፖለቲካ  የወታደራዊ ስልጠናና ትጥቅ አስታጥቆ  በወያኔ  ላይ ለመዝመት የጀመረውን ጉዞ የሚያስቆመው ምድራዊ ሃይል እንደሌለ ብናውቅም የህዝብ ስቃይ ለግዜው መቀጠሉ የህባዊ ሃይሉን አባላት ማሰቃየቱ አልቀረም። በወያኔ  ግፈኛ አገዛዝ የተንገፈገፈው ወገናችን ህዝባዊ ሃይሉ የወያኔን አገዛዝ እድሜ  የሚያሳጥሩ ፈጣን እርምጃዎችን እንዲወስድ በከፍተኛ  ጉጉት እየተጠባበቀ እንደሆነ  እናውቃለን። ህዝባዊ ሃይሉን ለመቀላቀል በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ የሃገሪቱ ዜጎች በተጠንቀቅ እንደቆሙ እናውቃለን። እነዚህ ዜጎች ከሁሉም የእምነት የቋንቋ  የጾታ የእድሜ  የኑሮና  የማህበረሰብ ስብጥር የሚያካተቱ  እንደሆኑ እናውቃለን። በሃገሪቱ ታሪክ ተሰምቶና  ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ  የወታደር ልብሱን  እየጣፈ እንዲለብስ፣  የወታደር ጫማውን መቀየሪያ አጥቶ  ሸበጥ እንዲያደርግ የተገደደውን፣  የወያኔ ጀነራሎች በስልጣንና  በዘረፋ ሲያብጡ በድህነት እንዲሟሽሽ የተፈረደበት የሃገሪቱ ሰራዊት በዘር በእምነት ሳይለያይ ከህዝባዊ ሃይሉ ጎን ለመቆም አሰፍስፎ  የቆመ  እንደሆነ  እናውቃለን። ይህ ሃገራዊ እውነታ ለህዝብ የገባነውን ቃልኪዳን የለምንም ጥርጣሬ  ማስከበር እንደምንችል በሙሉ ድፍረት እንድናውጅ የሚያስችለን ሃቅ ነው።

የወያኔ ጀንበር እየጠለቀች የኢትዮጵያ  ህዝብ ጀንበር እየፈካች የመሄዱ ጉዳይ እንደማይታጠፈው  የመንጋትና  የመምሸት የተፈጥሮ ህግ ነቅነቅ የማይል እንደሆነ ግንቦት7 ጠንቅቆ ያውቃል።  እውቀታችን ልዩ ጥበብ የሚጠይቅ ኣይደለም። ግፍ ፍትህን አሸንፎ፣ እውነት በሃሰት ተደፍቃ፣ ጥላቻ ፍቅርን፣ አድሎ እኩልነትን፣ ሃገራዊ ክህደት ሃገር መውደድን፣ ባንዳነት አርበኛናትን ለዘላላሙ ቀብረው የሄዱበት የሃገራችንና  የሰው ልጆች ታሪክ የለምና የወያኔን አይቀሬ ሞት ለመተንበይ  ልዩ ጥበብ አያሻንም። ይህን እኛ ብቻ ሳንሆን በዘረፋና በጥላቻ  የደነዘዘ ህሊና ያዳበሩት የወያኔ  ባለስልጣናትም ያውቁታል። ያለእኔ  ጀግና የለም፣ ያለእኔ  አልሞ  ተኳሽ የለም በሚል እብሪት በመጻደቅ የሚታወቁት ወያኔዎች በመቶ ሽዎች በሚቆጠሩ ወታደሮች ተከበው፣  በታንክ በአይሮፕላን በሚሳይል ታጅበው ከሚኖሩበት ቤተመንግስትና ቪላዎች ውስጥ ብርክ እንዲይዛቸው ያደረገው ለመሆኑ፣  ሳር ቅጠሉ ግንቦት ሰባት እየመሰላቸው ሲበረግጉ እንደሚያመሹ፣  የግንቦት ሰባት አባላት እያሉ ከድርጅታችን ጋር አንዳችም ግንኙነት የሌላቸውን ዜጎች እያሰሩ ሲያሰቃዩ ፣  ከምላሳቸው ላይ ግንቦት 7  የሚል ስም ተፈናጦባቸው  እንደሚውሉ በራሳቸው ሚድያ  ወያኔዎች ራሳቸው እያሳዩን እያስደመጡን ነው። ከዚህም አልፎ በዚህ አንድ አመት ውስጥ  የህዝባዊ ሃይሉን መሪዎች በመግደል ድርጅቱን ለማኮላሸት ይቻላል በሚል ወያኔ የላካቸው ነፍሰ ገዳዮችና ድርጅቱን ከውስጥ ለመቦርቦር ያሰማራቸው ሰርጎገቦች ተራ በተራ ተልእኳቸው እየከሸፈ በህዝባዊ ሃይሉ እጅ እየወደቁ ወይም ተልእኳቸው እንደማይሳካ ሲረዱ እየፈረጠጡ ወደ ወያኔ ሲመለሱ አይተናል።

ያለፈው አንድ አመት ተመክሯችን ስለወያኔ  ብቻ ሳይሆን ስለራሳችንም ጥንካሬና  ድክመት ብዙ ነገሮች ያስተማረን ኣመት ነው። የቀደምቶቻችን የጀግንነት የአርበኛነት ቅርስ በመላ ህዋሳቸው የተሸከሙ  ለኢትዮጵያ እና  ለህዝቧ ሲሉ ደማቸው ለማፍሰስ ውድ ህይወታቸውን ለመሰዋት ወደኋላ የማይሉ ቆራጥ ብቻ ሳይሆኑ አርቀው የሚያዩ  በርካታ ልጆች  ሃጋሪቷ ያሏት መሆኑን ያረጋገጥንበት አመት  ነው።  በሌላ በኩል ደግሞ  ድርጅታችን የኢትዮጵያን ህዝብ ብቸኛው የመንግስት ስልጣን ባላቤት የማድረጉን ታሪካዊ ራእዩን ለመሳካት የሚያደረገው ትግል ከወያኔ ጋር ብቻ ሳይሆን ከራሳችንም ጋር የሚደረግ እንደሆነ  በሚገባ  የተረዳነው  በዚሁ የአንድ አመት የድርጅታችን እድሜ  ነው። ከራሳችን ጋር የሚደረግ ትግል ወያኔ በማህበረሰባችን ውስጥ ከዘራቸውና የሃገሪቱን ዜጎች እንዲበክሉ ካደረጋቸው የዘረኛነት የአድሎ  ከህዝብና  ከሃገር ጥቅም በፊት የራስን ጥቅም ማስቀደም፣ የሱሰኛነትና የሙስናና ሌሎችም አደገኛ ባህሎች ጋር ነው።

ህዝባዊ ሃይሉ ደግሞ  ደጋግሞ  እንደገለጸው ትግላችን አንድ መንግስታዊ ስርአት ወድቆ ሌላው የመንግስት ስርአት በመጣ ቁጥር የህዝብ ተስፋ እየጨለመ  “አዲስ ከመጣው ስርአት ያላፈው ያረጀ ስርአት በግፈኛነቱ በዘራፊነቱ ያነሰ ነበር” የሚል የግፈኛና የዘራፊ ስርአቶች ንጽጽር ላይ የቆመ አሳዛኝ የህዝብ ህይወት እንዲያበቃ ነው። ደርግን ያየ የአጼውን ስርአት እንከኖች ረስቶ ንጉሱ ይሻሉን ነበር ያለበት፣ ወያኔን ያየ የደርግን አስከፊ ዘመን ረስቶ መንጌ በስንት ጣሙ ያለበት አሳዛኝ ሁኔታ ከወያኔ መውደቅ በኋላ በሃገራችን እንዳይደገም ነው ትግላችን። የኢትዮጵያ ህዝብ የውድ ልጆቹን ህይወት ገብሮ ወያኔን በማስወገድ የሚያመጣው ስርአት ከወያኔ ብሶ ህዝብ ወያኔ ማረኝ የሚልበትን ቅስም ሰባሪና አዋራጅ የታሪክ ቅጥልጥሎሽ  እንዳይቀጥል ማድረግ ህዝባዊ ሃይሉ የተመሰረተበት፣ አባላቱ መከራ ለመቀበልና መስዋእትነት ለመክፈል በረሃ የገቡበት ዋናውና ብቸናው ምክንያት ነው። ትግላችንን መራራ የሚያደርገው ከበሰበሰውና የአንድ ጀምበር የህዝብ ቁጣ ከታሪክ ቆሻሻ የመጠያ ስፍራ ከሚከምረው  የወያኔ ስርአት ጋር ብቻ ሳይሆን በወያኔ ቦታ የሚተካውን ስርአት ከአድሎና ከዘረኛነት ከዘረፋና ሃገራዊ ክህደት የጸዳ፣ ዳግም ለኢትዮጵያውያን ውርደትና እንግልት ምክንያት እንዳይሆን ለማድረግ ከራሳችን ጋር ሳይቀር የማያቋርጥ ትግልን ማድረግ የግድ ስለሚል ነው። ህዝባዊ ሃይሉ የአመጽ ትግል የሚያደርግ፣ የመሳሪያው ብዛትና  የሰራዊቱ ቁጥር እያደገ  የሚሄድ ሃይል መሆኑን ስለምንረዳ  ይህን ሃይል ገና ከጅምሩ ከብዙ እንከኖች እያጸዱ ማደራጀት ካልተቻለ  በሃገርና በህዝብ ላይ የሚመጣውን አደጋ  የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ጠንቅቀው የተረዱት ሃቅ ነው። ይህ ግንዛቤ የሰራዊቱን አባላት በጥንቃቄ መመልመልን፣ ማሰልጠንንና መገንባትን የግድ የሚል ነው።

ይህ ከራሳችን ጋር የሚደረግ ትግል እጅግ መራራ ነው። ታሪካዊ ስህተቶችን ላለመድገም የሚደረግ ትግል ነው። ይህ ትግል የአካልና የመንፈስ ጽናትን፣ ሃቀኛነትን፣ ታማኝነትን፣ ጀግንነትን የሚጠይቅ ትግል ነው። የወያኔ ስርአት ከሃገር ግድያው በተጨማሪ ትውልድን ለመግደል ሆን ብሎ ያስፋፋቸው እኩይና ጎጂ ባህሎችና ልምዶች ምን ያህል ማህበረሰባችንን እንደጎዱት ህዝባዊ ሃይሉ ባላፈው አንድ አመት እድሜው በሚገባ የተረዳው ጉዳይ ሆኗል። ህዝባዊ ሃይሉ የሚመኘውን የኢትዮጵያ ትንሳኤና ተሃድሶ እውን ለማድረግ እነኝህ  ወያኔ ሆን ብሎ  ያስፋፋቸውን የባህልና የሞራል ብክለት ማጽዳት የግድ እንደሆነ የተረዳ አካል ሆኗል።

ትግላችን መደፍረስን መጥራትን፣ መንተክተክን መስከንን የትግሉ ሂደት አካል አድርጎ  የሚጓዝ ነው።   ትግሉ የሚልመጠመጠውን እንደቀስት ቀጥ ብሎ ከሚራመደው፣ በካፊያው የሚንቀጠ ቀጠውን ለዶፉ ደንታ ከሌለው፣ ዝናር በቅፌን ከምሩ ተኳሽ  የሚለይ መራራ ትግል ነው። ያለፈው አንድ አመት ይህን አስተምሮናል። ህዝባዊ ሃይሉ ትግሉ ቀላል ነው የሚል ከእውነታ ጋር ያልተያያዘ ቃል ለህዝብም ሆነ ህዝባዊ ሃይሉን ሊቀላቀሉት ለተዘጋጁት ወገኖቹ አይናገርም። ህዝባዊ ሃይሉን ለመቀላቀል ለተሰለፉ በሽዎች ለሚቆጠሩ ወገኖቻችን ትግሉ የሚጠየቅውን የሞራል የስብእና ጥብቅነት፣ከፍተኛ  የሃገርና የወገን ፍቅር፣ ጥልቅ የሆነ የመስዋእትነት ፈቃደኛነት የሚጠይቅ መሆኑን ከማስረዳት አንቦዝንም። ህዝባዊ ሃይሉ ለህዝብ ቃል እንደገባው ከወያኔ  ጋር የምናደርገው ትግል በጥበብ በእውቀት በጥናት በጥንቃቄ የምናደርገደው ነው። ነጻነት ያለመስዋእትነት እንደማይሳካ ብናውቅም ለተራ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ስንል በቂ ዝግጅት ያልተደረገበት የሃገሪቱን ውድ ልጆች በከንቱ የሚማግድ ጀብደኛ እንቅስቃሴ  አናደርግም። የውሸት ተስፋ  ህዝብን አንመግብም።  አይናችንን ከዋናው የኢትዮጵያና  የህዝቧ  ጠላት ከሆነው ከወያኔ ላይ አንስተን በሌሎች  ወያኔን እቃወማለሁ በሚሉ ሃይሎች ላይ አንተክልም። ከወያኔ ሌላ ወደ ጎን የምንዋጋው፣ የምንጨቃጨው አታካራ የምንገጥመው ምንም ሃይል አይኖርም። ወያኔን ለመምታት ህዝባዊ ሃይሉ የጨበጠው  ቡጢ ወገኖቻችን በፍቅር ለመጨበጥ የሚዘረጉ ጣቶች  እንዳሉት በጸረ ወያኔ ዴሞክራሲያዊ ትግሉ  ከልባቸው ለመተባበር ለሚፈልጉ ሃይሎች ሁሉ ግልጽ እናደርጋለን።

ያለፈው አንድ አመት የመሰባሰብ የድርጅት ምስረታ  መሰረታዊ የሆኑ የፖለቲካና የወታደራዊ  ስልጠና የተሰጠበት፣ የድርጅት ማጠናከሪያና የማጥራት ሂደት የተካሄደበት ነው። በዚህ ረገድ የተሰራው ስራ አጥጋቢ ውጤት አስገኝቷል። ስልጠናው፣ ድርጅት ማጠናከሩና  ማጥራቱ ወደፊትም የሚቀጥል ነው። መጪውን አመት የተለየ የሚያደርገው ህዝባዊ ሃይሉ በህዝብ ላይ በሚደርሰው ግፍና ውርደት ከሚሰማው ከፍተኛ ብስጭትና ቁጭት አልፎ ባላፈው አመት ሊደርስላቸው ያልቻለውን የሃገራችንን ግፉአን ህዝቦች መታደግ የሚችልበትን እርምጃዎች መውሰድ የሚችልበት አመት መሆኑ ነው። በዚህ የህዝባዊ ሃይላችን የአንደኛ አመት ምስረታ  ክብረ በአል ወቅት ወገንም ጠላትም በግልጽ እንዲያውቀው የምንፈልገው ይህን ሃቅ ብቻ ነው።

ውድመት ለዋናውና  ለብቸኛው የኢትዮጵያ ህዝብና  የኢትዮጵያችን ጠላት ለሆነው የወያኔ ገዥ ጉጅሌ!

ድል በወያኔ ግፈኛ ስርአት አበሳውን ለሚያየው የመላው የኢትዮጵያ  ህዝብ!

የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል
Ginbot 7 Popular Force
http://www.ginbot7pf.org
Tel: +44 208 123 0056
email: pr@ginbot7pf.org

posted by Tseday Getachew

Post Navigation

%d bloggers like this: