Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

አንዳንድ ወሬዎች ከትግራይ (አብርሃ ደስታ -ከመቐለ እንደዘገበው)

ስኳር የገዙ ሁለት ካድሬዎች ታስረው ዋሉ!

በሑመራ አደባይ በሚባል ቦታ ነው። ባከባቢው ከፍተኛ የሆነ የዘይትና የስኳር እጥረት አለ። የንግድ ፍቃድ ያላቸው ነጋዴዎች የካድሬዎች ፖለቲካዊ ተልእኮ ካልፈፀሙ ስኳርና ዘይት አያገኙም። በስኳር እጥረት ምክንያት ብዙ ሻይ ቤቶች ችግር ላይ ወድቀዋል።

ሁለት የህወሓት ካድሬዎች (ሴቶች ናቸው) ከአደባይ ወደ ሑመራ ከተማ ተጉዘው የተወሰነ ስኳር አገኙና በዉድ ዋጋ ገዘተው ወደ ሰፈራቸው ሲመለሱ ‘ስኳር ገዝቷችኋል’ ተብለው ታስረው ዋሉ። የያዙት ስኳርም ተነጠቁ። ካድሬዎቹ አሁን አኩርፈው ይገኛሉ።
በመቀሌም ከፈተኛ የስኳር እጥረት መኖሩ ለመገንዘብ ችያለሁ።

———————————

ህዝብ እየጠየቀ ነው!
————————-

ዜጎች ይጠይቃሉ፤ መንግስት ያስራል። የመቀሌ ከተማ (የሰራዋት) ኗሪዎች የሰፈሩበት መሬት ለግሪን ኤርያ (Green Area) ይከለላል ተብሎው ከቀያቸው ተፈናቀሉ። አሁን ግን ለግሪን ኤርያ ይከለላል የተባለው ቦታ ካድሬዎች ለሃብታሞች እየሸጡት መሆናቸውን ተፈናቃዮቹ ስለሰሙ ተቃውሟቸው እያሰሙ ነው። ከመንግስት አካላት ጋር ባለመስማማታቸው ባከባቢው ዉጥረት ነግሷል። ህዝብን መሸወድ ካልቀረ እንዲህ በጠራራ ፀሐይ።

በተያያዘ ዜና የዓይናለም ከተማ ኗሪዎች በመሬት ጉዳይ ከክልል መንግስት አለመግባባት ተፈጥሯል። የዓይናለም ህዝብ የመሬት ባለቤትነትና የከተማነት ጉዳይ በተመለከተ የክልል መንግስት መፍትሔ እንዲሰጠው ጥያቄ ቢያቀርብም የመንግስት አካላት ግን ተገቢውን መልስ ከመስጠት ይልቅ ‘እኛ የምንላቹ ብቻ ፈፅሙ! ካልሆነ ግን መፍትሔ የሚሰጣቹ አካል ካለ እናያለን’ የሚል ማስፈራርያ ተሰጥቷቸዋል። የህዝቡ የተወካዮች ትናንት ወደ ፌደራል መንግስት (አዲስ አበባ) መሄዳቸው ተሰምቷል።

ዜጎች የፈለጉትን ጥያቄ የመጠየቅ ሙሉ መብት አላቸው፤ መንግስት ደግሞ ለተጠየቀው ጥያቄ ተገቢ መልስ የመስጠት ግዴታ አለበት። መንግስት ዜጎችን የማስፈራራት መብት የለውም።

————————–
ትንሽ ስለ Mekelle Institute of Technology (MIT)
————————-

የመቀሌ የቴክኖሎጂ ኢንስቲቱት (Mekelle Institute of Technology) ሲመሰረት ጎበዝ ተማሪዎችን በልዩ ስልጠና ለማብቃት ነበር። ድብቅ ዓላማውም ጎበዝ የትግራይ ልጆችን በቁሳዊ ነገር በመግዛት የህወሓት አገልጋዮች የሚሆኑበት መንገድ ለማመቻቸት ነበር፤ ተገዝተው ለስርዓቱ አገልጋዮች እንዲሆኑ ለማድረግ።

እንደዉጤቱም የMIT ወጪ በትግራይ ልማት ማህበር ይሸፈን ነበር። ቀጥሎም በትእምት ስፖንሰርሺፕ ነበር የሚማሩ። አብዛኞቹ ተማሪዎች በጥሩ ዉጤት (ብቃት) ሲመረቁ ነበር።

በቅርቡ ግን አንድ ችግር ተፈጠረ። ተቋሙ ብቁ ተማሪዎች ማፍራት ቢችልም ህወሓቶች የፈለጉት ዓላማ ግን ሊሳካ አልቻለም። ህወሓቶች የMIT ተማሪዎች ታማኝ የህወሓት አገልጋዮች እንዲሆኑ ይፈልጋሉ። ተማሪዎቹ ግን የራሳቸው ነፃ ሐሳብ ማራመድ ጀመሩ። ምክንያቱም በቀላሉ በሆዳቸው ሊሸመገሉ አልቻሉም፤ ጎበዞች ናቸዋ። ጎበዝ ሰው ደግሞ ለህሊናው እንጂ ለሆዱ አይኖርም።

የተማሪዎቹ ገለልተኛ እንቅስቃሴ በህወሓቶች አልተወደደም። ጉዳዩ በህወሓት መሪዎች ታየ። ተማሪዎቹ የህወሓት ታማኝ ካድሬዎች ሁነው ስለ ማገልገላቸው ወይ አለማገልገላቸው ጥናት እንዲደረግ ተወሰነ። ጥናቱ ተጠናቀቀ። ታማኝ ካድሬዎች አለመሆናቸው (የፈለጉትን ሐሳብ በነፃነት መናገር መጀመራቸው ተረጋገጠ)። ህወሓቶች ለMIT ተማሪዎች ስፖንሰር ማድረጋቸው እንደ ከባድ ኪሳራ ተመለከቱት። ‘እኛን ለማያገለግሉ ሰዎች ገንዘባችን በከንቱ ማፍሰስ የለብንም’ አሉ፤ ተስማሙ።

ህወሓቶች MITን ከትእምት ድጋፍ እንዳያገኝ ወሰኑ። ‘ታድያ ምን ይሁን?’ ለሚለው ጥያቄ ደግሞ የMIT ወጪ ከትእምት (የህወሓት ሃብት) ሳይሆን ከፌደራል መንግስት መሆን እንዳለበት ተስማሙ። የተቋሙ ወጪ ከፌደራል መንግስት ከሆነ ወደ መቀሌ ዩኒቨርስቲ መጠቃለል እንዳለበት ታመነበትና ተወሰነ። በዚሁ መሰረት MIT ወደ መቀሌ ዩኒቨርስቲ ገባ።

አሁን MIT አንድ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ አካል ነው። አሁንም ግን የMIT ተማሪዎችን ቅር ያሰኘ ጉዳይ አለ። MIT ወደ መቀሌ ዩኒቨርስቲ ቢገባም የግሬዲንግ ስርዓቱ (Grading System) ግን የተለየ ነው። እናም ጥያቄው ‘MIT ወደ መቀሌ ዩኒቨርስቲ መግባቱ ካልቀረ ለምን ሁሉም ነገር ተመሳሳይ አይሆንም?’ የሚል ነው።

ለሆዳችን ወይስ ለህሊናችን ተገዢ እንሁን???

EMF

posted by Tseday Getachew

 

Advertisements

Single Post Navigation

Comments are closed.

%d bloggers like this: