Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

ይድረስ ለሳኡዲው ባለሃብት ሼክ መሃመድ ሁሴን አላሙዲ “ዝምታን” ለምን መረጡ?

ከዘላለም ገብሬ (ጋዜጠኛ)

የተከበሩ ሼክ መሃመድ ሁሤን አላህሙዲ ክብረቴ ይድረስዎት እያልኩኝ በአሁን ወቅት ባለው አንገብጋቢ እና አሰቃቂ በሆነው ጉዳይ ላይ ምላሽዎን ቢሰጡኝ ብዬ ይህችን አጭር ደብዳቤ ለእርስዎ እና እንዲሁም ለወኪሎችዎ እንዲደርስዎ በማለት ከልቤ ያለውን ሃሳብ ልጠይቅዎት ወደድኩኝ ፣ እኔን በውል የሚያውቁኝ ሰው አይደለሁም ተራ ሰው እና ሳገኝ የውስጤን የምሞነጫጭር የእስኪርቢቶ ጓደኛ ስሆን እርስዎን የማግኘት እድል ከአንድም ሁለት ጊዜ ቢገጥመኝም የእጅ ሰላምታ ሰጥቶ የእግዜር ሰላምታ ከመስጠት ያለፈ ሂደት አላከናወንኩም ፣ ይሄ ማለት ደግሞ ትልቅ ነገር ሆኖ ለውጥ ያመጣል ብዬ አላስብም ግን ማነው ብለው የሚሉ ከሆነ አንድ
ተራ ብእርተኛ ብለው እንዲያስቡን እሻለሁ፣ እንዲህ ስልዎት ደግሞ ከሳቅዎ ጋር እየገነፈለ የሚወጣው ቁጣዎ መጥቶ እንዴት እኔን ይደፍረኛል ብለው እንዲሉ ሳይሆን እንዲያው ሃሳብን በሃሳብ ይረዱልኝ ዘንድ ቤዬ ችግሬን ላካፍልዎት ብዬ ወደድኩ ፤ ይሄውም በጣም በሚወዷቸው እና ዜግነትዎን ሁሉ ተናግረውለት በማይጠግቡት ሳኡዲዎች ፣በሌላ ወገንዎት (በትውልደ ኢትዮጵያውነትዎን በሚናገሩበት ዜጋዎት ላይ ፣)ደግሞ ከምንም በማይቆጥሩት እና ከመንግስት ጋር ባለዎት መልካም እና ጥብቅ ግንኙነት የሚጠቀሙበትን ህዝብ ፣ መንግስት እና እንዲሁም ሃገር ላይ ያለዎትን አስተያየት እና እንዲሁም አመለካከት እንዲነግሩኝ ሲሆን በአሁን ሰአት በዜጎችዎ የኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እንዴት እንዳዩት ልብ ሊሉልኝ ይገባል ።

በአሁን ሰአት ባሉበት ስውዲን ሆነው ይህችን ብጣሽ ደብዳቤዬን ሊያነቡልኝ እንደሚችሉ እርግጠኛ ነኝ እርስዎ ማንበብ ባይችሉ እና ጊዜ ቢያጡም አማካሪዎችዎ ከመናገር ወደ ኋላ አይሉምና ሊያገኝውት እደሚችሉ እርግጠኛ ነኝ ። እንደ ኢትዮጵያውያን የኑሮ ሁኔታ 85 በመቶ የሚኖረው ህዝብ ከገጠሪቱ የኢትዮጵያ ክፍል እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቁታል፣ከፍተኛው አርሶ አደር ነው ጥቂቱ ደግሞ አርብቶ አደር ፣የአርሶ አደሩ እና የአርብቶ አደሩን የገቢ ምንጭ ቁጥር ስናነጻጽረው የአርሶ አደሩ የተሻለ ህይወት አለው ሆኖም ግን 75 በመቶ የሚሆነው ህብረተሰብ በድህነት አለም ላይ ያለ ህብረተሰብ በመሆኑም የብዙ ቤተሰብ ጫንቃ በአንድ ሰው ትከሻ ላይ የሚጫንበት አገር እንደሆነች ብጠቅስልዎት ለእርስዎ ተረት ተረት ሊመስልዎት ይችላል ግን አይደለም ግልጽ ነው ።
ይህንን ስናገር እርስዎ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ ላይ እንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመሩ እረጅም ጊዜ እንዳስቆጠሩ በአንድ ወቅት ላይ በተናገሩት በራስዎት አንደበት ለመረዳት ችያለሁ ታዲያ በደሃ አገር በደሃ ህዝብ ላይ ሃብታም የሆነ አንድ ባለሃብት የደሃውን ጉሮሮ ለመድፈን ሳይሆን የራስን ጥቅም ለማሽከርከር ሲል ከአለው መንግስት ጋር ተጣብቶ የግል ፍላጎትን ለማሟላት የሚደረገው ጥረት ከእርስዎ ብቻ የመጣ ሳይሆን ታላላቅ ሃገሮች የሚባሉት አውሮጳ እና አሜሪካውያኖች በአፍሪካ ሪሶርስ ላይ ፈላጭ ቆራጭ በመሆን እጃቸውን አስገብተው እንደፈለጋቸው ለማሽከርከር በሚያመቹበት መልኩ እራሳቸውን አደላድለው ተቀምጠዋል ። ታዲያ እርስዎም በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና የንግድ ተቋም ላይ ለምን ገቡ ብዬ ልጠይቅዎት አልፈልግም በአንድ በኩል ትልቅ አስተዋጾ እያደረጉ መሆኑን ይገባኛል ይሄውም የዜግነት ግዴታዎን እየተወጡ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የደሃ ቤተሰቦችን ጉሮሮ እየደፈኑ እንደሆነ የሚታወቅ ስለሆነ ፣እንደዚያም ቢሆንም ከኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም ይልቅ እርስዎ የሚያገኙት ጥቅም 90% በላይ ሲሆን ሃገሪቱንም ጎድተው አንጡራ ሃብቶቿንም ተጠቅመው ሃብትዎንም አካብተው ዛሬ ላይ ደርሰዋል ፣ይሄን ሁሉ ለሆነልዎት ባለውለታ ለከፈለልዎት ህዝብ እና አገር ምላሽዎ ዝምታ ሆኖአል ።
ለምን ዝምታን መረጡ ? እንደዜግነትዎ የሁለት አገር ዜግነት እንዳለዎት እየተናገሩ ባለበት ወቅት ፣በሃገራችን ላይ የመጀመሪያውን ዘርዎን ለማስጠራት ሲሉ ሳኡዲ ስታር የሚለውን ኩባንያ ተክለው ፣ምርቶቹን ወደ ሳኡዲ እንዲሄድ እያደረጉ የሳኡዲ ዜግነት ያላቸውን ወገኖችዎን እየረዱ ባለበት በዚህ ሁኔታ ለምንስ ይሄን ያህል ዋጋ ለከፈለልዎት ህዝብ ደግሞ የውለታው ምላሽ አልሆኑለትም ? ከላይ እንደጠቀስኩልዎት ሃሳብ መሰረት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የገጠሩ ህዝብ እንደሆነ እና የገጠሩ ህብረተሰብ ደግሞ በድህነት አረንቋ የሚኖር እነመሆኑ መጠን እራሱን ለማሻሻል ቤተሰቡን ለመርዳት ብሎም ሃገሩንም ከችግር ለማውጣት ሲል በሌላ ዜግነት ባለዎት የሳኡዲ ምድር ላይ ስራ ሰርቶ እንዲኖር ያስችለው ዘንድ አገሩን ፣ ወገኑን ፣የትውልድ ቀዬውን እንዲሁም የልጅነት ናፍቆቱን ያሳለፈባቸው ጓደኛ ዘመድ አዝማዶቹን በእዝነ ህሊናው እየዳሰሰ በረሃን አቋርጦ ኑሮው ሲያሸንፈው ኑሮን ለማሸነፍ ደፋ ቀና ሲል “የሰው አገር ሰው ቢረግጡት አህያ ቢለጉሙት ፈረስ “ሆኖበት መከራ እና ስቃዩን ማየት ከጀመረ ከራርሞአል።

ታዲያ አገር እየገዛሁ ነው ያለው መንግስትም ምንም እርዳታውን በተገቢው መልኩ ሊያደርግ አልቻለም ፣የሳኡዲ ዜግነት እያለዎት በሳኡዲ መንግስት ላይ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ ሳይቻልዎ ቢቀር በደሃ አገሮች ላይ ክርንዎን ለማሳየት የሞከሩበት ዋነና ሁኔታ በማንቂያ ገንዘብ እያሳዩ በአካፋ መዛቅ የለመዱበት አገር ላይ ህዝቡ ዝምታን ስለመረጠልዎ ይመስለኛል ታዲያ እርስዎ ለዚያ ደሃ ገበሬ ፣ያፈራውን ምርት ነጥቀው ለሳኡዲዎች የሚሰጡበት ገበሬ ያ ደሃው ህዝብ ዛሬ የድረሱልኝ ጥሪ ሲያሰማ እርስዎስ የት ገቡ ።
ንጉስ አብደላንስ ለምን ለማማከር አልሞከሩም ። ነው ወይስ እንደ አቶ አይለማርያም ደሳለኝ ቅጥፈትዎን በአደባባይ ሊያሳዩን ፈለጉ?
በኢትዮጵያ ምድር እና ህዝብ ላይ ከ20 በላይ ትላልቅ የሆኑ ኩባንያዎችን መመስረትዎ የሚታወቅ ነው ጥቂቶቹን ብናነሳ ኤልፎራ ፣ኒያላ ኢንሱራንስ ፣ኒያላ ባንክ፣ሸራተን አዲስ፣ሳኡዲ ስታር ፣ሰን ላይት የኤሌትሪክ ኩባንያ ፥እንዲሁም የወርቅ ማእድን ቁፋሮ የሚያመርተው ትልቁ ኩባንያዎት
Managed under the parent MIDROC Group is MIDROC Ethiopia Technology Group with several further
companies under its management:
– MIDROC Gold Mine
– ELFORA Agro-Industries
– Huda Real Estate
– Kombolcha Steel Products Industry
– Modern Building Industries
– Trust Protection and Personnel Services
– Addis Home Depot
– Trans Nation Airways
– Addis Gas & Plastics Factory
– Wanza Furnishings Industry
– Daylight Applied Technologies
– Blue Nile P.P & Craft Paper Bags Manufacturing
– United Auto Maintenance Services
– Unity University
– Rainbow Exclusive Car Rental and Tour Services
– Summit Engineered Plastics
የሃገሪቱን አመታዊ በጀት በአንድ ቀን የሚያገኙበት ዋነኛው የንግድዎ ምንጭ እና እንዲሁም ሌሎች የአበባ ፣ሰሊጥ ፣እህል እና ትራጥሬ ምርት የሚሰበስቡበት ኩባንያዎት ትልቁን የሃገሬን ገበሬ ጉሮሮ እየነጠቀ ምንም የሚበላ ነገር ለማያመርቱት እና በግብርናው አለም ህይወታቸው አልፎ የማያወቀው ፣ በነዳጅ ምርት ብቻ እምሮአቸው ለተደፈነው ጥጋበኛ ባለ ሃብቶች ዝርያዎችዎ ምርታችንን በማከፋፈል ስራዎ መጠመድዎን አውቃለሁ ፣ታዲያ ለምንስ በእናትዎ ወገን ያሉትንስ ለማዳን አይጥሩም ?ሴት እህቶቻችን ሲደፈሩ ሲገደሉ ፣ወንዶችም ሲደፈሩ ፣ሲገደሉ ፣በርሃብ እና ውሃ ትም ሲሰቃዩ እናት ከእንጭጭ ልጆችዋ ጋር በሜዳ ላይ ያለ መጠለያ ስትወድቅ ሰው ያለ ሃገሩ በደል እና ስቃይ ሲደርስበት አስትዋሽ ሲያጣ መንግስትም ጉዳየ አይደለም ብሎ ህዝቡን በንቀት ሲመለከት እርስዎስ እንዴት አዩት ? ከ63 % በላይ መሬቱን ነጥቀው ምርት የሚያመርቱት የእርስዎ ዝርያ ያላቸው የሳኡዲ አረቦች መሆናቸውን ዘንግተውታልን ? በሃገራችን ገብተው እንደሚሰሩት ሁሉ ለምን የሌሎቹንም ዜጎች ክብር ሊጠብቁ እንዳልቻሉ ለምን አንደበትዎን ከፍተው አልተናገሩልንም ? ኢትዮጵያን እወዳለሁ እያሉ የሚደነፉት የግላዊ ጥቅምዎ እስኪከናወን ብቻ እንደሆነ ያየንበት እና የታዘብንበት ወቅት ዛሬ መሆኑን ገብቶናል እንጂ የንብ ቲሸርት ለብሰው እኔ ወያኔ ነኝ ባሉበት ወቅት አልነበረም ምክንያቱም ለኢትዮጵያ ህዝብ
ፖለቲካ ሳይሆን የቸገረው ዳቦ ፣ሰላም እና መልካም አስተዳደራዊ መንግስት ብቻ ነው ስለዚህ ያንን ሰላሙን በሃገሩ የነጠቀው መንግስት በሰው አገር እንዲሰደድ አደረገው በሰው አገርም ስደቱ አልበቃ ሲለው ስቃዩ እና መከራው በዛበት እንደርስዎ በገንዘብ የጠገበ ዲታ ሰው ማንንስ ደሃ ያስታውሳል ብቻ ድከም ብሎኝ እና የደሃ እህት እና ወንድሞቼ ደም ቢከሰኝ ጥያቄዬን ልጠይቅ ብዬ እንጂ መልስዎን ሊመልሱ እንደማይችሉ አውቃለሁ ፣ስለዚህ ምላሽ ካለዎት ምላሹን በዝግጅት ክፍላችን ልናስተናግድ ዝግጁዎች ነን ስለዚህ በኢሜል አድራሻችን ቢያቀርቡልን ለህዝብ ከማድረስ ወደ ኋላ አንልም ።ለዚህ ደግሞ ውድ ጊዜዎን ተሻምቼ ይህችን ስላነበቡልኝ ሳላመሰግን አላልፍም ፣ታዲያ እንዲህ ስልዎት ስም ያለውን ሰው እየፈለጉ ወይን ባለስልጣን እያሰሱ ብርዎን ከሚረጩ የድረሱልኝ ጩኸታቸውን እያሰሙ ያሉትን ዜጎቻችንን መፍትሄ ቢሰጡልኝ ደስታዬ እጅግ የላቀ ነው ።ከዚያም አልፎ ከስደት መልሳቸው በሃገራቸው ኮርተው ይኖሩ ዘንድ ስራንም ፈጥረው የስራ አጡን ቁጥር ቢቀንሱት የስደተኛው ቁጥር ሊቀንስ ይችላል እናልብ ሊሉት ይገባል በማለት የዛሬውን ሃሳቤን እቋጭልዎታልሁ ላደረጉት ነገሮች ሁሉ በድጋሚ እያመሰገንኩ በኢሜል አድራሻችን አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ቢልኩልን እንወዳለን እናስተናግዳለን zelalem@maledatimes.com ወይንም
editor@maledatimes.com አሁንም ለጊዜዎ ክብረትን ይስጥልኝ !

posted by Tseday Getachew

 

Advertisements

Single Post Navigation

Comments are closed.

%d bloggers like this: