Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

ውይይት ከግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ (፪)

ethiowaga.gif

አብርሃም ያየህ (ክፍል ሁለት)
ላንዳንድ ሰዎች፣ ወይንም ለበርካታ ሰዎች ማለት ይቻላል፣ ሀገር ማለት ጮማ የሚቆርጡበት፣ ጠጅ የሚጋቱበት፣ ለሽርሽር የሚሄዱበት፣ ወንዙን ተራራውን እየጠሩ በግጥምና በስድንባብ የሚመፃደቁበት፣ የሚጨፍሩበትና የሚዘሉበት፣ ወዘተ ብቻ ይመስላቸዋል። በጣም የሚገርመውና የሚያሳዝነው ደግሞ፤ ሌላው የፖለቲካ ሱስ ያለበት ይመስል፣ ከፖለቲካ ገለልተኛ ነኝ፣ ፖለቲካ አልወድም፣ ኃይማኖተኛ ነኝ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዋጋ የለውም ወዘተ. የሚሉ ጉዶች አሉ። አንዳንዶቹማ፣ መታገሉንና ላገር መቆርቆሩ ቀርቶ፤ ነብሳቸውን ሽጠው ከሚታገሉ ሰዎች ጋር ላለመታየት እንኳ ሲንጰረጰሩ ማየት ትውልዱ ምን ያህል እንደከሰረ የሚያመለክት ነው። ይቺን አጋጣሚ ተጠቅሜ፣ ባለፈው ዓመት እዚህ ከምኖርበት ዴንማርክ ያጋጠምኝን አብነታዊ ክስተት ላካፍል።

 

አንዲት Save the Children ብለው ፈረንጆቹ የሚቀልዱበት መያድ/NGO ሰራተኛ የሆነች እህት ካዲስ አበባ ወደዚህ ለሥራ ጉዳይ ስትመጣ ጓደኛዋ የሆነች ዘመዴ አስቂኙን የበረከት ስምኦን መጽሐፍ (የሁለት ምርጫዎች ወግ) ልካልኝ መጽሐፉን ለመውሰድ እሆቴሏ ድረስ እሄዳለሁ። ከናይሮቢ መጣሁ የሚለው የዚያው የፈረንጅ ገንዘብ መቃረሚያና መሰልያ መያድ ተቀጣሪ የሆነ አንድ ሰው እቦታው አብሯት ይቆየኛል። እኔም መልካም ሰው የሆነችውን እህት እና አብሯት የነበረውን ግለሰብ በኢትዮጵያዊ ባህላችን መሰረት እንግዶቼ በማድረግ ለመጋበዝ ጠየቅኩ። አብሯት የነበረው ሰው እኔ አብርሃም ያየህ መሆኔን ሲያውቅ ያደረበትን ጭንቀት ለመግለፅ ያዳግተኛል።

እኔም ጠበቅ አድርጌ ልጋብዛችሁ ስል ከጭንቀቱ ብዛት የተነሳ ሳይደብቅ “ካንተ ጋር መታየት ችግር ያመጣብናልና ይቅርታ ብታደርግልን” በማለት የቅጩን ሲነግረኝ፣ ትውልዱ ምንኛ እንደወደቀ ለመረዳት ጊዜ አልወሰደብኝም። እኔም፣ ምነው የምትኖረው ናይሮቢ ከሆነ ምን ያስጨንቅሃል? አዲስ አበባ የምትኖር ቢሆንምኮ ወያነ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አስፍኛለሁ ስለሚላችሁ ሥርዓቱ የምታሸተውን አየርና የምትገናኘውን ሰው ጭምር ሊመርጥልህ አይገባም አልኩት። ሆኖም የሰውየውን መረን የለቀቀ ጭንቀት በማየትና ልጅቷንም ከሱ ነጥየ ብቻዋን ከኔ ጋር እንድትሄድ ስላልፈለግሁ እዚያው ተሰነባብተን፤ እኔም ከወጪ ተገላግየ መጽሐፌንና ልጂቱ ያመጣቺልኝ ቆንጆ ስጦታ ተቀብየ በሰላም ተለያየን። የሰውየውን ስቃይ ግን ለኔ የሞት ሞት ነው። ይሁን እንጂ፣ ጨናቃው ሰውየ በግልፅ ጭንቁን መናገሩ ለኔ ትልቅ ትምህርት ነው። … (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)

http://www.ethiopiazare.com/

posted by Tseday Getachew

Single Post Navigation

Comments are closed.

%d bloggers like this: