Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

“አንድ ላይ በመዋሐድ የትጥቅ ትግሉን በጋራ እያካሄድን ነው” – ት.ህ.ዴ.ን እና ኢ.ህ.ፍ.እ.ግ

ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ት.ህ.ዴ.ን) እና ከኢትዮጵያ ህዝቦች ለፍትህና እኩልነት ግንባር (ኢ.ህ.ፍ.እ.ግ) የተሰጠ የጋራ መግለጫ

የኢትዮጵያ ህዝብ ከሚደርስበት ጭቅናና ስቃይ እራሱን ነጻ ለማውጣትና መብቱን ለማስከበር ለዓያሌ አመታት ያካደው እልህ አስጨራሽ ትግል በህዝብ ስም በሚነግዱና በሃገሪቱ እየተፈራረቁ ወደ ስልጣን በሚመጡ አምባገነኖች መብቱ እየተረገጠ ምኞቱ ሳይሰምርለት አሁንም በአስከፊ ሁኔታ ላይ ይገኛል፣
በተለይም የህዝብን ጥያቄን መነሻ በማድረግ የተነሳው የኢህአዴግ ስርዓት፤ የአገሪቱ ጭቁን ህዝቦች ነጻነታቸውንና መብታቸውን ለማስጠበቅ ያካሄዱት ወደር የለሽ መራራ የትጥቅ ትግል፤ የተከፈለው መስዋእትነት፤ የተነሳለት ህዝባዊ ዓላማና የሰማእታትን አደራ በመካድ ከደርግ ስርዓት በከፋ መልኩ ህዝቡን በማፈን፤ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶችን በመርገጥና የሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ ትግል አማራጮችን ሁሉ በመዝጋት እራሱን አውራ ፓርቲ ብሎ በመሰየም በማን አለብኝነት አምባገነናዊ አገዛዙን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፣
ከአንድ አምባገነናዊ ፈላጭ ቆራጭ ስርዓት እንደ ህዝብ ነጻ ለመውጣት እርግጠኛው መንገድ ህዝባዊና ህዝባዊ ትግል ብቻ መሆኑ አሌ የሚባል አይደለም፣ በአገራችን ኢትዮጵያም አገሪቱንና ህዝቧን ከአምባገነኑ የኢህአዴግ ስርዓት ለመታደግ በየአቅጣጫው የትጥቅ ትግልን ጨምሮ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል እየተካሄደ ነው ፣ የትግሉ ዓላማም በሃገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን እዳይኖር ጋሬጣ የሆነውን የኢህአዴግ ስርዓትን በማስወገድ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን በህዝብ ተሳትፎ ማረጋገጥ ነው፣
በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶች ጸረ-ዴሞክራሲውን ስርዓት በመቃወም መታገላችን የሚደገፍ ቢሆንም በየአቅጣጫው በተናጠል እያካሄድነው ያለ ትግል ግን አንድ የተዋሃደ ሃይል ፈጥሮ መንቀሳቀስ ባልመቻሉ እንደ ሃገር የሚፈለገውን ውጤት ሊያስገኝልን አልቻለም፣
በዚህ ረገድ የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ከሚገኙት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲ ንቅናቄ/ትህዴንና የኢትዮጵያ ህዝቦች ለፍትህና እኩልነት ግንባር (ኢህፍእግ) ከኣመታት በፊት ማለት የአሁኑ ኢ.ህ.ፍ.እ.ግ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ለፍትህና እኩልነት (ደ.ኢ.ህ.ፍ.እ.ግ) ግንባር ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ሁለቱም ድርጅቶች የህዝብን ጥያቄ አንግበው ለዘመናት ምላሽ ያላገኘውን የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ በህብረት እየሰራን በተለያዩ አውደ ውጊያዎችም በመሳተፍም በጋራ መስዋእትነት በመክፈል የድርሻችን እየተወጣን መጥተናል፣
አሁንም የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በጥልቀት በመገምገም የህዝባችን አንገብጋቢ ጥያቄ ወቅቱን የጠበቀ ምላሽ እንዲያገኝ በተናጠል ከሚካሄየድ ትግል ይልቅ ውህደት ፈጥሮ ተቀናጅቶ በጋራ መታገል ወሳኝ እና ተገቢ መሆኑን በማመን ውህደታችንን አጠናክረን የትግላችን አላማ ግቡ እስኪመታ አስፈላጊውን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናችንን ለጭቁን የኢትዮጵያ ህዝብና ወዳጆቹ እናበስራለን፣

በሁለቱም የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የዓላማም ሆነ የፕሮግራም መሰረታዊ ልዩነት ስለሌለ እስካሁን ድረስም በመተባበር እየሰራን ቆይተናል። ይበልጥ እየተቀራረብንና የህብረት ስራ ውጤትን በተግባር እያየንና እየተገነዘብን የመጣን በመሆናችን በሁለቱም ድርጅቶች መካከል እየተጠናከረ የመጣውን ግኝነትና ህብረት ከመስከረም 18 ቀን 2006 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ውህደት በማሸጋገር አንድ አካል ሆነን ለመንቀሳቀስ ወስነናል፣
በዚህ አጋጣሚ ሁሉም የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የኛን ፈለግ እንዲከተሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፣
እያካሄድን ባለው የትጥቅ ትግል ሁለንተናዊ ድጋፉን ያልነፈገን መላው የኢትዮጵያ ህዝብም የተለመደው ድጋፉን ይበልጥ አጠናክሮ እንዲቀጥልበት ጥሪያችንን እናቀርባለን፣
ድል ለጭቁኖች!!
መስከረም 2006 ዓ/ም

ትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ከኢትዮጵያ ህዝቦች ለፍትህና እኩልነት ግንባር (ት.ህ.ዴ.ን) (ኢ.ህ.ፍ.እ.ግ)

http://www.zehabesha.com/

posted by Tseday Getachew

 

Advertisements

Single Post Navigation

Comments are closed.

%d bloggers like this: