Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

የአክራሪነት ውንጀላ የተሰነዘረበት ማኅበረ ቅዱሳን ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተቃውሞ ሪፖርት/ክሥ ማቅረቡ ተጠቆመ

  • የአክራሪነት ውንጀላው በ‹‹አገር አቀፍ የሰላም ዕሴት ማጎልበቻ ጉባኤ›› ወቅት ማኅበሩንና አገልግሎቱን ከተቀበረ ፈንጂ ጋራ ያመሳሰለውና በአቶ ስብሓት ነጋ አጽንዖት የተሰጠው የአባ ዮናስ ጥቆማ ነው፤ የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለቋሚ ሲኖዶስ በአጀንዳነት እንደሚያቀርበው ተመልክቷል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን

ማኅበረ ቅዱሳን

  • ከዋልድባ ገዳም፣ ከዕርቀ ሰላም እና ከ፮ው ፓትርያርክ ምርጫ ጋራ በተያያዘ በግል ፕሬሶችና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ላይ የተሳተፉ የማኅበሩ አባላትና አገልጋዮች ናቸው የተባሉ ግለሰቦች ‹‹ጽንፈኛ የፖሊቲካ ኀይሎች አካል በመኾን ሕዝቡን ለዐመፅና ሁከት አነሣስተዋል›› በሚል በአስረጅነት ተጠቅሰዋል፡፡
  • በማኅበሩ ውስጥ መሽገዋል የተባሉ የትምክህት ኀይሎችን ለማጋለጥና በሕግ ለመፋረድ ይካሄዳል የተባለው የ‹ፀረ አክራሪነት› እንቅስቃሴ የማኅበሩን ሕዝባዊ ተቀባይነት ለማሳጣትና የድጋፍ መሠረቱን ለማሸሽ የተወጠነ ሊኾን እንደሚችል ተጠርጥሯል፡፡
  • መንግሥት፡- የመንፈሳውያን ማኅበራትን የፋይናንስ ዝውውርና አጠቃቀም በምዝገባ ሕግ ከመቆጣጠር ጀምሮ ‹‹በማኅበራት ውስጥ ያሉኝን አባሎቼን [ኢሕአዴግ] በማንቀሳቀስ ቅኝታቸውን አስተካክላለኹ›› የሚል ዕቅድ መያዙ ተሰምቷል፡፡
  • በመንፈሳውያን ማኅበራቱ ውስጥ ያሉ የኢሕአዴግ አባሎችን በማንቀሳቀስ ‹‹የማኅበራቱን ቅኝት የማስተካከል›› እንቅስቃሴ በሁሉም ክልሎች የሚፈጸም ሲኾን በትግራይና በአማራ ክልሎች የግንባሩ አመራሮችና አባላት ላይ ልዩ ትኩረት ያደርጋል ተብሏል፡፡ በተለይ በክልል ትግራይ የማኅበረ ቅዱሳን ማእከላት የመንግሥት ሠራተኞች የኾኑ የማኅበሩ አባላት ከሥራቸውና ከአገልግሎታቸው እንዲመርጡ እንደሚገደዱ ተጠቁሟል፡፡
  • ማኅበረ ቅዱሳን ከሰሞኑ ‹‹የሰላም ዕሴት ማጎልበቻ ጉባኤ›› ሁለት ሳምንት በፊት ‹‹የአክራሪዎችና ትምክህተኞች ምሽግ›› በሚል ስለተፈረጀበት ኹኔታ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች ጋራ ለመወያየት በተለያዩ መንገዶች ያቀረበው ጥያቄ በሚኒስቴሩ ሓላፊዎች ፈቃደኝነት ማጣት ተቀባይነት አለማግኘቱ ተገልጧል፡፡
  • መንግሥት አካሂደዋለኹ የሚለው የፀረ አክራሪነት እንቅስቃሴ አሁን በሚታየው ስፋት ከመጀመሩ በፊት ማኅበሩ በኅትመት ውጤቶቹ የአክራሪነትንና አሸባሪነትን አደጋ የሚተነትኑ፣ ተከባብሮ የመኖር ባህላችን ጎልብቶ እንዲቀጥል የሚመክሩና የሚያሳስቡ ጽሑፎችን በተደጋጋሚና በጥልቀት ማቅረቡን የሚያስታውሱ አስተያየት ሰጭዎች÷ በፀረ – አክራሪነት/ጽንፈኝነት ሰበብ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከአገራዊ ሰላም አንጻር ብቻ ሳይኾን የቤተ ክርስቲያናችንን ኦርቶዶክሳዊ ማንነት፣ ተቋማዊ ህልውናና ነጻነት ከማስጠበቅ አንጻር በጥንቃቄ እንዲታይ በጥብቅ ያሳስባሉ፡፡

 

http://haratewahido.wordpress.com/

posted by TsedayGetachew

Advertisements

Single Post Navigation

Comments are closed.

%d bloggers like this: