Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

ኮለኔል ጎሹ ወልዴ እና ዶር ታዬ ወ/ሰማያት ወዴት ገቡ?

https://i2.wp.com/www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2013/05/goshu-welde.jpg

ኮለኔል ጎሹ ወልዴ እና ዶር ታዬ ወ/ሰማያት ወዴት ገቡ?

ዛሬ ካልወጡሰ መቼ?        

ከሎሚ ተራ

ዝነኛውና የማይጠገበው ድምጻዊ (ዶ/ር) ጥላሁን ገሠሠ፤ ሲያንጎራጉር፤ እንዲህ ብሎ ነበር፤

“ጩኸቴን ብትሰሙኝ ፤ ይኸው አቤት አቤት እላለሁ በደል ደርሦብኝ እጮሃለሁ ብያለሁ”

ኮለኔል ጎሹ ወልዴ

እያለ ያንጎራጎረውን  እኔም አቤት አቤት የ ( የመሪ ያለህ!!! ) በዪ እኔም እጮሀለሁ። ምንም እንኳን ሰለኮነሬል ጎሹም ሆነ ሰለ ዶክተር ታዬ ታላቅ ሰራና አገር ወዳድነታቸው አገር የሚያወቀው ያደባባይ ሚሰጥር ቢሆንም  ቅሉ፤ ሰሞኑን ግን የተለያዩ የሀገርኛ ጉዳይን የሚያሳዩ ቪዲዩዎችን ሰመለከት ድንገት የኮነሬል ጎሹን ብዙዎችን ያሰደነቀና ያኮራ ሃገር አቀፍ የጥብቅና ንግግር (On the fate of Ethiopia and Eritrea’s Referendum) አየሁና  በቁጭት ምን ተብሎ፤ ማን አሰከፍቶት ይሆን ኮነሬሉ ጥግ የያዙት ? ዶክተር ታዬ ወልደሰማያትሰ ? የት ገቡ ? በማለት በቁጭት ለመጠየቅ ብዕሬን አነሳሁ።

መቼም እንዲህ ያለውን አንገብጋቢ ሃገራዊ ጥያቄ የሚጠይቁ በርካታዎች እንደሚሆኑ ባምንም ጥቂቶች ደግሞ  የ ምርጫ 97 ቱን ምሳሌ በማድረግ የሞተ ዘመድ የለውም ወይ?  ይኸ ሰው ምን ነካው የሚሉ እንደማይጠፉም አምናለሁ። መልሴ ግን የሞቱ ዘመዶች በርካቷች አሉኛ፤ ተሰፋዪ ግን አይሞትም።ተሰፋ ላንድም ሰከንድ አጥቼ አላውቅም ነው ።

እንዲህ አይነቱ ጥያቄ አገራችን የምትገኝበትን የፖሎቲካ ሂደትና ቀውሰ በሰፊው እንድንጠይቅና ከሰኸተታችንም ታርመን ይቅርም ተባብለን፤ በሃገር ጉዳይ እኔ ማን ነኝ ? ምንሰ ማድረግ ይጠበቅብኛል ? የሚለውን ጥያቄ በቅንነት በመጠየቅ አንተ ትብሰ፤ አንቺ ትብሸ በመባባል እንደገና እጅ ለእጅ ተያይዝን አገራችን እንድትገባበት ከተቆፈረላት ጥልቁ ጉድጓድ የማውጣት አገራዊ ግዴታ አለብን በዬ አምናለሁ።

ከገጠመን እና ከተጋረጠብን የፖሎቲካ ውጥንቅጥ አኳያሰ እባክህ፤ እባክሽ ያሰፈልጋል ወይ ? ብቃት ያላቸው የፖሎቲካ መሪዎችሰ እባካችሁ እሰኪባሉ መጠበቅ አለባችው ወይ ? በሚል የተለያዩ እሣት የሚተፉ እንጉርጉሮዎች ከየጎራው ሊነሱ እንደሚችሉ የሚጠበቅ ቢሆንም ከተጋረጠብን ከፍተኛ አደጋ ባሻገር ምንሰ ብናደርግ አገር ትዳን እንጂ ነው መልሴ።

ሥለዚህ  ሰለጠንካራ የፖሎቲካ አመራር ብቃታቸውና፤  ሰራቸው በርካታ አገር ወዳዶች የሚመሰክሩላቸውን ጠንካራ መሪዎች ዳግም ወደ ፈጠጠው የትግል ጎዳና እንዲመጡ የማይደረግበት ምክነያት ምንም ሊኖር አይችልም።  እነ ኮነሬል ጎሹንም እነ ዶክተር ታዬ ወ/ሰማያትንም ሌሎችም አሉ የሚባሉትን ከየ አካባቢያችን ውጡ፤ አገራችን ኢትዮጲያ ትጮሃለች፣ የመሪ የለኸ እያለችም ትጣራለች ብለን የማውጣት ሃገራዊ ግዴታ አለበን። እከሌ ከከሌ ሳንል ጩኸታችንን እናሰማና አገራችንን ተባብረን ከውድቀት እናድን።

“ይሄ – መሪ ትግሉ ይወልዳል የሚለውም ባዶ ጩኸታችን ለ 22 አመት ወልዶ አላሳየንም እና ሁላችንም ቆም ብለን እናስብ፡

የሚዲያ ክፍሎችም በሙሉ፤-  እነ ቪ. ኦ. ኤም፣ ዶቼ ቬሌም ፤ እሣትም፣ ሌሎች ሚዲያዎች ሁሉ ካሜራችሁን ወደ አራቱም ማዕዘናት አዟዙሩት ፤ምክነያታቸውንም አሰሙን እያልኩ ጩኸቴን ብትሰሙኛ እላለሁ። በቸር ይግጠመን!!

ሎሚ ተራ፦Tuesday, May-28-13

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=3754

posted by Tseday Getachew

Advertisements

Single Post Navigation

Comments are closed.

%d bloggers like this: