Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

ዳንኤል ክብረት በአርቲስት ጀማነሽ ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴ ዙሪያ ያቀረበው ጽሁፍ ስንቶቻችሁ እንዳነበባችሁት አላውቅም፡፡ እኔ ግን…

የኢትዮጵያዊነት ድምጽ-Ethiopiawinet

ዳንኤል ክብረት በአርቲስት ጀማነሽ ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴ ዙሪያ ያቀረበው ጽሁፍ ስንቶቻችሁ እንዳነበባችሁት አላውቅም፡፡ እኔ ግን በጣም ተገርሜበታለሁ፡፡መጀመሪያም ከፕሮፌሰር መስፍን ጋ እንደዛ ያጠማመደው ለካ ይህ ኖራል?ቀጥታ ወደ ዲያቆናችን ከመግባቴ በፊት ትንሽ ስለ እነ ታምራት ነገራ የሆነ ነገር ብል ደስ ይለኛል፡፡ ታምራት የት እንደ ተወለደ አላውቅም ግን ልክ እንደ መስፍን ነጋሽ እንደ አብርሀም ደቦጭም ሀገር ያለው አይመስልም፡፡እሱ ኢትዮጵያም ውስጥ ኖረ ከኢትዮጵያ ውጪ ያው ልክ እንደ ጓደኞቹ የሰው ሀገር ሰው ነው፡፡ምናልባት እድሉ ካጋጠመው አሁን በሚኖርበት ሀገር እንደምንም የመኖሪያ ፈቃድ አግኝቶ እንዲህ ከማያውቃትና ከአፈጣጠሯ ጀምሮ እንከንና ብክነት ከሞላባት ሀገር እንዲገላገል በጣም የዘወትር ጸሎቴ ነው፡፡ግን አንድ ነገር እንዳይረሳ ልጆች ካሉ ወደ ኢትዮጵያ ይላካቸው ፣ የኢትዮጵያ አፈር ብቻ ሳይሆን አለትም መሰረትም ጭምር ካባት ካያቶቻቸው እንደ ተሰራች እንደምንም እናስተምራቸዋለን፡፡ በዚህ አመሉ እሱ ካስተማራቸው ነገ አድገው ተመንድገው በተንሻፈፈ ተረትተረት ሀገር ፍለጋ ጫካ እንዳይገቡ ያሰጋልና፡፡አበርሃም ደቦጭ ..ታሪክና..ተመራማሪ ..የሚሉ ትልልቅ የሰማይ ስፋት ያህል የእውቀት ይዘት ያላቸው ስሞችን ተሸክሞ የአንድ ነገር ምንነት ከግል አስተያየት በውጣ መልኩ ሙያና ስርአት ባለው መንገድ የአንድን ነገር መግለጽ አለመቻሉ ይገርመኛል፡፡ስም ተጭኖ አይገለም የሚባለው ተረት በሙሉ አካል ምን እንደሆነ ያሳየኝ ሰው ስለሆነ ባመሰግነው አይከፋኝም፡፡ግን ይህን አካል የያዘው አካለ ቢስ ስለሆነ አይደለም ትክከለኛ አካሉ ለነጮች ተረት ተረት አሳልፎ ሰጥቶ እነሱ በሱ ማንነት ወርቅ አውጥተው ማር ቆርጠው ካለ ማንነታቸው ባገኙት ነገር ሲደሰቱ እሱ ግን የነሱን ኩበት ተሸክሞ አገሪጻን ኩበት በኩበት ከብትበከብት ለማድረግ በወዶ ገብነት በመሰለፉ ነው፡፡ በተለይ ቢትል ኢንቲሞሎጂ.. የምትለው አስተሳሰብ ጎትቶ ጎትቶ የጎጠኝነት ቅርጫት ስላደረጋትና ፕሮፌስር መስፍንንም በዛ አንተልልጥሎ ለመሄድ በማሰቡ በጣም አዝኛንቶኛል፡፡የመጨረሻ ጥይት ..የምትለው ነገር ደግሞ ግሩም ናት፡፡ ሰውዬው ተኩሰው ተኩሰው የቀራቸው አንድ ወይም ሁለት ብቻ ነው በቃ አበቃላቸው አባባሉ ማለቴ ነው፡፡እንዲገባው ግን አንድ ነገር ብነግረው እሱ የመጨረሻ ያለውም ሆነ ከዛ በፊት የተተኮሱት ትይቶች ሁሉ ብዙዎችን የገደሉ ሳይሆኑ ብዙዎችን ያፈሩ ናቸው፡፡የወለዱትን ደግሞ የሚያሳድጉበት ጥሩ ቀለብ ፡፡ለምን እንዲህ እንደ ተናደድኩኝ ታውቃላችሁ ? በተለይ ታምራት ነገራ የኢትዮጵያ አፈጣጠር ይላል.. ከዛም ይቀጥልና ግብር ምናምን ..ይሄ ጠጋጠጋ ማንንና መቼን ለማንሳት ነው ነው ጥያቄው፡፡ ኢትዮጵያ ስትፈጠር ግብር ስለመሰብሰቡ እንዴት አወቀ ወይንስ መቼ እንደተፈጠረች የእሱ ቀን መቁጠሪያ ስላለ ነው? ኢትዮጵያ የትና መቼ ነው የተፈጠረችው? አብርሀም የሚባለው ደግሞ ..የእሳቸው ኢትዮጵያ.. የሚለው ነገሩ ቢመረመር ትርጉሙ ወይ እንደ እነ ዳንኤል ክብረት የኢትዮጵያ ስልጣኔምንቹ አረቦች ናቸው ማለት ነው አልያም ስትፈጠር አውቃታለሁ ገና ከጅምሯ የአስገባሪና የገባሪ ስርአት የተጫናት ነበር ሚል ነው፡፡ በጣም ይቅርታ ያለ ርእሴ ገባሁ፡፡ ተመስገን ደሳለኝ፡፡ ተው እንጂ፡፡ የቃሊቲ ጨረፍታ ብለህ ያ መሪ ጌታ ያልከው ሰው ማነው ?እግዚሀብሄር ኢትዮጵያን የወዳታል ሲል ሳቅህ ለምን ፈነዳ? አባባልህ ብዙ ጉድ አለሁ እነ አብርሀም ደቦጭ የጋገሩት የፈረንጅ ኬክ ደረሰህ እንዴ? የኢትዮጵያዊያን አንባሻ ሰለቸህ ?ፈረንጅነት ናፈቀህ ?ያሳዝናል አስብበት አይባልም አያስቅም ፡፡ የኢትዮጵያ እና የእግዚአብሄር ፍቅር ከባልና ከሚሲት እንደሚበልጥም አስብ!!! አሁን ግዴለም ቀጥታ ወደ ዳንኤል ክብረት ልግባ፡፡ የሆነ ጊዜ ኢቲቪ ላይ ቁጭት ..የሚል ዝግጅት የተከታተላችሁ ታስታውሱታላቹ፣ ያኔ ትዝ ካላችሁ ..እቺ ታላቅ ሀገር ከተመሰረተች 25000 አመቷ ነው .. የሚል ነገር ጋዜጠኛዋ ስትተርክ ሰምታቿል፡፡ዳንኤል ክብረትም የዛ ታሪክ ማጀቢያ ነበር፡፡በመገራችን ላይ ያ አባባል ተወሰደው..ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ ..ተብሎ ባማርኛ ከተተረጎመው መጽሀፍ ይመስላል.. ወይም እንደእሱ አይነት ፈረንጅ ከጻፈው ጽሁፍ . ምክንቱም ያንን ልክ ዶክመንተሪ ሲዘጋጅ እያነበብኩት ነበር፡፡ ለምን ዳንኤል ክብረት ያንን አመተ ምህረት አላስተባበለም ነው ጥያቄ፡፡የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከመጽሀፍ ቅዱስም ሆነ ከሌላ አንጻር ኢትዮጵያ የ25000 አመት ባለ ታሪክ ናት ሚል ነገር አንብቤም ሰምቼም አላውቅም፡፡የኢትዮጵያ ታሪክ ቢያንስ ቢያንስ ከኖህ ጊዜ ነው ብላ ነው የምታስተምረው፡፡እንዳውም ንቡረእድ ኤርምስ የተባለው ሰው የኢትዮጵያ ታሪክ ከአዳምና ከሄዋን ነው መጀምረው ገነትም ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ብሎ ማመን ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊም ሆነ ታሪካዎ መረጃ ያቀርባል፡፡እኔ ያኔ ማስተካከያም ሆነ ማስተባበያ ያልሰጠው በኢቲቪ ዝግጅት ላይ እንደ እነ መለስ ዜናዊ ያሉ ሰዎች ስለ ነበሩ ቀደም ቀደም ላለማለት ትህትናውን ለማሳየት ነው በማለት አስቤ ነበር፡፡ ግን አይደለም ማህበረ ክዱሳን ያሳተመው መጽሀፍ.. የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ከክርስቶስ ልደት እስከ 2000 ዓ.ም. … የሚል መጽሀፍ ገዛሁና አነበብኩት፡፡ ልክ በኢቲቪ ያለው የ2500አመት ታሪክ ነው ያለው፡፡የኢትዮጵያ ስልጣኔም ምንጭ ከአረቡ አለም በጡ ብለው ለሚያምኗቸው ሙሉ ለሙሉ አሳልፎ በመስጠት ኢትዮጵያ የጥቁሮች ስልጣኔ መሰረትም ሆነ እድገት ዋጋ ለማሳጣት በሚከጅሉ ትንታኔዎች ይቀጥላል፡፡ እና ዳንኤል ክብረት ምን አገባው ማለታችሁ አይቀርም፡፡ ዳንኤል ክብረት የማህበረ ክዱሳን ጉልላት ነው፤ ከነ ሙሉ ሰውነቱ የሰፈረው በዛ ተቋም ላይ ነው፡፡በመጽሀፉ ስራ ላይ በግልጽ ስሙ ሰፍሮ ባይታየይም የእሱ እግ አስተያየትና ድጋፍ የለውም ማለት ሞኝነት ነው፡፡ከዛ ለብቻ ማሰብ ጀመርኩኝ..ለካ ማህበረ ቅዱሳን .. የሚባለው ስብስብ ዳንኤል ክብረት የመሰረታት አዲሲቷ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ናት…በማለት፡፡የዳንኤል ክብረት ፍልስፍናና ክህደት የሚጋገርባት፡፡ ግን አንዳንድ ሰዎችን ደግሞ አውቃለሁ ማህበሩ ውስጥ በጣም ዋጋ የሚያወጡና ለኢትዮጵያ ዋጋ የሚሰጡ፡፡ግን ምን ያደርጋል የኢትዮጵያ ታሪክ ከፈረንጅ ተረት በተቀዳ ቀመር ሲሰራ ዝም ብለው መያ ከሆነ ያው የዳንኤልን መስቀል ከመሳለም አላመለጡምና ያው ናቸው ብዬ ደመደምኩኝ፡፡ድምዳሜዬ ሁሉንም ባያጠቃልልም ማህበረ ቅዱሳን ኦርቶዶክሳዊ ወኔ እንጂ መንፈስ እንደሌለው ከታተመው መጽሀፍ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ዝም ብላቹ እራሱ ስትጠይቁ .. ርእሱ አስቡት ፡፡የትኛዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ታሪክ፡፡ የዳንኤል ክብረትና የማህበረ ቅዱሳኗ ባለ 2500፣ ወይስ ከአክሱም ፈቅ ተብሎ የሚነገረው የ3000 አመት ወይንስ የሴም የካምም ሆነ የያፌት ዝርያዎች ተባብረወር የፈጠሯት አሁንም እንደ ነብር ከነ ተዥጎረጎረ ቀለማቸው አሉባት፣ የምትለዋ ፣የትኛዋ ነው?የማን ታሪክ ነው የተጻፈው? ግርም ነው የሚለው፡፡ ዛሬ ዳንኤል ክብረት ከፕሮፌሰር ጋር እስጣ ገባ ያበዛው..በእኔ እይታ በዚህ አካሄዱ ነው፡፡ የኢጥዮጵያን ታሪክ ከዚህ በፊት እንደ ነበሩት አንዳንድ ተንኮለኞች ደብተራዎች እየሰረዘና እየደለዘ ታሪክ ማጨማለቁን የወደዱለት አልመሰለኝም፡፡ ይህ አዲሱ መጽሀፋቸው ከማሳተማቸው በፊት በዚህ ነገር ላይ ጉዳይ አልነበራቸውም ማለት በጣም ይገርማል፡፡ አንድ ጊዜ ፍትህ ጋዜጣ ላይ የፕሮፌሰር መስፍንና የአቦይ ሰብሀት ነጋ ክርክር ልብ ብሎ የተከታተለ አንድ ነገር ያስታውሳል፡፡አቦይ ስብሀት ነጋ ፕሮፌሰር መስፍንን በማህበረ ቅዱሳን ጉዳይ አንዳንድ ነትብ አንስተውባቸው ነበር፡፡ ፕሮፌሰርም ለዛ መልስ ነገር ሰሲስጡ ለማህበሩ ትንሽ ምክር ነገር ለመሥጠት ፍላጎት እንደነበራቸው ገልጸዋል፡፡ ምክሩ ምን ነበር ማንስ አገዳቸው ብሎ መጠየቅ አይከፋም፡፡ያኔ በእነ አቦይስባሀት መካከል ይደረግ የነበረው ክርክር በታሪክ ዙሪያ የነበረ ሲሆን እንዳውም አቦይ የኢትዮጵያ ታሪክ እንደ ገና መጻፍ አለበት ሚል መንፈስ ያለው ሀሳብ ሁሉ አንስተዋል፡፡ እኔ ሳስበው ፕሮፌሰር መስፍን ለማህበረ ቅዱሳን ሊያካፍሉት ፈለጉት የቤተክርስቲያኗ የቆየ ታሪክ ሳይደልዙና ሳይበርዝ አደራ ማለት ይመስለኛል፡፡ዳንኤል ክብረት ግን እነደዛ በማለታቸው በተዘዋዋሪም ቢሆን የተገላመጣቸውና ፌት የነሳቸው ሳይሆን አይቀርም፡፡ለምን ቢባል አንደና ይሄሰው የኢትዮጵያ ታሪክ እና ስልጣኔ መሰረቱ ከአረብ ፈልሰው በመቱ የሴም ነገዶች ናቸው ብሎ ያምናል፡፡ ይህንን በተጻፈው መጻፍም ሆነ በኢቲቪ ባቀረበው ነገር ላይ መረዳት ይቻላል፡፡ እንዳውም መጨረሻላይ ጥሩ ምሳሌ አለኝ፡፡የዳንኤል አስተሳሰብ ም የጥቂቶች ካልሆነ በስተቀር የአብዛኞቹ የህወአት አመራር እምነመትም ነው፡፡ያኔ መለስ ለጋዳፌ የመናዊ ነኝ ያለውን ማስታውስ ጥሩ ነው፡፡ ዛሬ በፕሮፌስር መስፍን መጽሀፍ ላይ እየተኝጫጩ ያሉት አንዳንድ ታሪክ አዋቂ ነን እና የንግስት ሳባ ዘሮች ነን ፣ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ምንጩ የሳባ ዝርያ ነው ያም የዛሬው የትግራይ ህዝብ ነው በማለት ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ከመነሻው የኢትዮጵያ መሰረት የለውም ያሉት የኢትዮጵያን የታሪክም ሆነ የስልጣኔ ያስከፋቸው ፈረንጆች እንደሆኑ ማንም ያውቃል፡፡ እናም ፕሮፌሰር መስፍን ህዝባችን ከፈረንጅ ተረት ነጋሪ ተጠንቀቁ ተነሱና ንቁና እራሳችሁን እወቁ ማለታቸው አቃጥሏቸዋል፡፡የኢጥዮጵያ ምሁራንም ተማርን ካላችሁ የፈረንጅ ተረትተረት እየገለመጣችሁ ህዝቡን አትበርዝት ፣እስቲ በዚህ በዚህ በኩል ኢትዮጵያን ፈልጓት ብለው ብዙ የሚረባ ነገር ጠቁመዋል፡፡አፈታሪክና ስነቃሎች ኢትዮጵያን ታሪክና ማንነት ላለመሸከማቸው አጥኑና አረጋግጡ ፣ የኢትዮጵያን ታሪክ ለማትናት የፈረንጅ መነጽር ብቻ አድረጋችሁ ዝምብላችሁ በክደት፣እና አውቀው በሚሰሩት ሸር አትንጎዱ የሚለው አስተሳሰባቸው ልብ ያለው ልብ ይለዋል፡፡ እንደ እነ ዳንኤል ክብረቱ በማህበረ ቅዱሳን በጀት ማርስ ላይ ብቻ መሄድ ለቀረው ሰው ንቀትና ያለመሰልጠን ምልክት ተደርጎ ሳይታሰብ አልቀረም፡፡ በዘረኝነት የተወጣጠሩት የሳባ ዘር እኛ ነን እያሉ ያሉ ሞኞችም ማንነታቸው ማወቅ ክብር መስሎ አልታወቃቸውም፡፡ ከፖለቲካ ጋር እየቀላቀሉ ሲያወሩ ከስር የሚያስቡት ያልታወቀባቸው መስሏቸው ሌትተቀን ፣ጠንቅቀው የማያውቁትን ከዘረኝነት ጋር በማኘክና በማላመጥ መከራቸውን ይበላሉ፡ ያሳዝናል፡ ሌላው በዚህ ሰሞን የዳንል ክብረት ነገር የገረመኝ በአርቲስት ገማነሽ ላይ ባቀረበው ሀሳብ ነው ፡፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም .. በተመለከተ፡፡ ያለውን ሀሳብ እንዳለ ላስፍረው እንዲህ ይላል፡፡…. የኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ከሀገራዊ እሴትነቱ፣ መሥዋዕትነትንና ነጻነትን ከማንጸባረቁ፣ ለኢትዮጵያውያንም ከደማቸው ጋር የተዋሐደ ልዩ ምልክት ከመሆን አልፎ ግን ጽድቅና ኩነኔ ውስጥ የሚገባ፣ እርሱን ያልተቀበለና ያላደረገ ሰማያዊ ዋጋ የሚቀርበት፣ ከእርሱ ውጭ ቀለም ያለው ነገር የለበሰና ማተብ ያሠረ ኃጢአት እንደሠራ ተቆጥሮ ንስሐ የሚገባበት ግን አይደለም፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ ያለ ዜጋ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል ለመሆን የቤተ ክርስቲያኒቱን ዶግማና ቀኖና መቀበልን እንጂ አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ባንዲራን መቀበል ግዴታው አይደለም፡፡ በኡጋንዳ ባንዴራ፣ በአሜሪካ ባንዴራ፣ በግብጽ ባንዴራ፣ በሶማልያ ባንዴራ አሸብርቆም ቢሆን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጅ መሆን ይችላል፡፡ እስካሁን ስለ ቀኖና በሚደነግጉት መጽሐፎቻችን ውስጥ ሰንደቅ ዓለማን የተመለከተ ቀኖና የለንም፡፡በመሆኑም ሰንደቅ ዓላማችን ከኢትዮጵያዊነታችን ጋር እንጂ ከኦርቶዶክሳዊ እምነታችን ጋር የታሪክ እንጂ የድኅነት ተዛምዶ የለውም፡፡ እንደዚህ ዓይነት አመለካከቶች የሚያይሉት እንዲሁ አይደለም፡፡ በሕዝቡ ዘንድ ኢትዮጵዊ ስሜት ደብዝዟል፣ ለሰንደቅ ዓላማና ለሀገራዊ እሴቶች የሚሰጠው ዋጋ ቀንሷል ተብሎ ሲታሰብ ሰንደቅ ዓላማን የመሰሉ ሀገራዊ እሴቶች ጉልበት ያገኙ ዘንድ ተጨማሪ ሃይማኖታዊ ኃይል ይሰጣቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሰንደቅ ዓላማን ክብርና ትርጉም ማስተማርዋና በትውልዱ ውስጥ ማሥረጽዋ ባልከፋ፡፡ አስተምህሮው ግን ከሀገራዊ ግዴታ የሚመጣ እንጂ ከሃይማኖታዊ ግዴታ የሚመጣ መሆን የለበትም፡፡ ከሕዝብ እሴቶች እንደ አንዱ ሆኖ እንጂ ከጽድቅና ኩነኔ ጋር ተያይዞ መሆን የለበትም፡፡:.. ቅድም ዳንኤል ክብረት ኢትዮጵያዊነት የሳባ ዘር ነን እንደሚሉት እና ኢቲቪ እንዳቀረበው የ25000 አመት ታሪክ ያላት ብቻ ብሎ ነው የሚያምነውም እዚህ እንደሚገልጸውም የሚያስተምረው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ዲያቆንነት ችግር ውስት ገብቷል ማለት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ስ ተዋህ ቤተክርስቲን በገጠርም ሆነ በከተማ በጣም ከምትታወቅበት ነገር አንዱ ..ባረንጓዴ -ቢጫ-ቀይ ቀለም ማጌጧና እንዳውም መንፈሳዊ ስእሎቿሳይወሩ በዚህ ቀለም ማሸብረቁ ነው፡፡ ለምን ፖለቲካ ስለ ምታራምድ ነው? አይደለም!! የኢትዮጵያ ንጉሳዊ ስርአት ይህንን ቀለም ከቤተክርስቲያን ወሰደ እንጂ ቤተክርስቲያ ከቤተመንግስት የወሰደቸው አይደለም፡፡፡ ኢትዮጵያዊነት ትርጉሙ መንፈሳዊ እንጂ ፖለቲካዊ አይደለም፡፡፡ምናልባት ይህ መንፈሳዊነትና ኢትዮጵያዊነት የሚገናኙበት ገመድ ዳንኤል ክብረት ባሰላው የኢትዮጵያ እድሜ ውስት ስለ ማይገኝና የሚዋጋውም ነገር ስለሆነ ለምን እንደዛ አለ ማለት ተገቢ ላሆን ይችላል!!እሱ እንዳለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያ ከሀገራዊ ነገር ጋር የተያያዙ ነገሮች አቅም ሲያጡ ቤተክርስቲያ እገዛ ታደርጋለች ይህም ስታደርገው የነበረ ነው የሚል አይነት የግሉ አስተያየት የቤተክርስቲያኗ አቋም አስመስሎ አቅርቧል፡፡ ስህተት ነው፡፡ ማንም ያውቃል የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የታቦትን ስርአት አንድ አካሏ ያደረገችው ክርስቶስ እንደዛ ስላላት አይደለም፡፡ከክርስትን በፊት እግዚአብሀር የሚገለጥባቸውን መንገዶች አሁንም አክብራ የእግዚአብሄር ኪዳን አድርጋ ስለ ምትቀበል ነው፡፡ ከታቦት በፊት የነበሩ እግዚአብሄር ህዝቤ ከሚላቸው ጋር የተገናኘባቸው ብዙ የኪዳን ምልክቶች አሉ፡፡ ከነዛም ወስት ለኖህ የተሰጠው.. ከእንግዲህ በኋላ የሰው ልጅን በውሃ አላተፋም የ..ሚለው ነው፡፡ የዚህ ምልክት ስሙ ባንዲራ አይደለም ሰንደቅ አላማም ኤደለም የዜግነት ምልክትም አይደለም ..እግዚአብሄር ለሰው ልጅ ሰጠው የቃል ኪዳን ምልክት ነው፡፡የምር የምትታወቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ደግሞ ይህ ነገር የምታስተምረውና የምትከራከርለት ነገር ነው፡፡ ኖህ ከነ ልጆቹ ኢትዮጵያ ነበረ፡፡ ልጆቹም ተወልደው በዝተው ወደ ሌላ ሰፈሩት ከዚህ ነው ፡፡ የኖህ መንግስትም ተመሰረተው ይህንን የቃልኪዳን ምልክት እንደ አርማ አድርጎ ነው .. እንዲህ ብላ ነው የምታስተምረው፡፡ ዳንኤል ግን .. አረንጓዴ ቢቻ ቀይ.. የፖለቲካ ልብ ብቻ አድርጎ ከመንፈሳዊ ው አለምና ትርጓሜ ጋር ያለውን ዝምድና በጥሶ የሞኝነት መግለጫ አድርጎ አቅርቦታል፡፡ እዚህ ጋ ጀማነሽ ..ኤልስ አራት ኪሎ ነው.. ብላ ትነሳም አትነሳም አረንጓዴ ቢጫ ወይ.. እንደ መንፈሳዊ መሳሪያ መጠቀሟ.. በጣም ትክክል ናት፡፡ በጣም አልተሳሳተጭም፡፡እንዳውም ኤልስ በአራት ኪሎ አለ ከምትል ኖህ ተመልሶ ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል ብትል ኖሮ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስም አሪፍ ተሀድሶ ነበር፡፡እነ ዳንኤል ክብረት ያሉ ግማሽ በጽሀፍ አንባቢ አዲስ የሌለ ታሪክ ፈጣሪወችን ችያበጠረ ያስወግድ ነበር፡፡ ግን ዳንኤል አነድ ትያቄ ብጠይቀው ደስ ይለኝ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ ከኖህ አረንጓዴ.. ቢጫ .. ቀይ ቀለም ጋር ግንኑነተረት የለውም አለው ማለትም ክህደት ነው የሚል ከሆነ መጽሀፈ ሄኖክ ..ኢትዮጵያዊ መሰረት የለውም ማለት አይደለምን? ቢሆንስ ሊል ይችላል፡፡ ታዲያ ያንተ ድቁና የትኛዋን ቤተክርስቲያን የሚወክል ነው፡፡እን ሳስበው የራስህ ቤተክርስቲያ ፈጥረሀል ብል ይሻለኛል፡፡ በጣም የገረመኝ ደግሞ ጀማነሽ እያካሄደቸው ካለው ተሳሳተ ሀይማኖት ህዝብ ለመጠበቅ የቀረበው የመፍትሄ ሀሳብ ነው፡፡ ማስተማር ሳይቀደሙ መቅደም አይነት ነው፡፡ ሀዝቡ ምን እየተባለ ነው የሚማረው ? ኢትዮጵያ 2500 አመት ነው እድሜዋ ብሎ፤ አረንጓዴ ቢጫ፣ ቀይ . ቤተክርስቲያ ከቤተመነረግስት የተዋሰችው ነው ምንም መጽሀፍቅዱሳዊም ሆነ ከኢትዮጵያ ጋር ግንኑነት የለውም በማለት፣ ኢትዮጵያን ስልታኔ የፈኘጠቁበት ሰዎች መሰረታቸው ከአረብ ነው በማለት? ማን ቀበልሃል? ማንም፡፡ እራስ እና ያንተን ትንፋሽ ሚያምራቸው የዋህ ቲፎዞችህ ልትቀባበሉ ትችላላችሁ፡፡ እንዲህ ስል ግን ጀማነሥ ፍልስፍና እያበረታታሁ አይደለም ለበጎ ከሆነ እነደ እነ አጼ ዘርዓ ያቆብ ቤተክርስቲያኗን በስእላ ስእል ሚከድን ሳይሆን ከጥንታዊ ገመዷጋ የሚያስተሳስር ከሆነ በርቺ ቀጥዪበት ነው፡፡ መፈላሰፍ በሷአልተጀመረምና፡፡ እንኳን ሀገር ሰውተፈላስፍ ሥንት ወንዝ አቋርጦ የመጣ ሰው በየቀኑ አሳራችን እያበላን አይደለም፡፤ እንድ ነግ ብቻ ጠቅሼ ላብቃ፡፡ ዳንኤል ክብረት ፡ ቢያንስ ከላይ የጠቀስኳቸው ነገሮች ከእይታ ችግር የተነሳ አልፈውት ይሆናል ግንእያየ የሚያልፋቸው እየሰማ የሚዘጋቸው ድምጾች አአሉ፡፡ የቅድስተ ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች፡፡ እሱ ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆር ከሆነ/ አዛኝ ከሆነ፣ በመንፈሳዊ ቅንነትና አክብሮት ለዚህች ቤተክርስቲያን እሰራለሁ ካለ ለምን ደቀ መዛሙርቷ ሲጮሁ ከሌሎች ጋር አብሮ ያፍናል? እርግጠና ነኝ የሁሉም ነገር መቃጫ ነው፡፡ ዳንኤል ክብረት ብዙ ልሳን፣ ድምጽ ፣ ብዙም ጆሮ ያለው ሰው መሆኑ እርግጥ ነው ::ግን የምስኪኖች ፣ የተበደሉ የተገፉ ሰዎች ልሳን ድምጸም ሲሆን አይቼው አላውቅም፡፡በሌሎች ጩሀት ቀልድ ሲሰራና ሲያሽጥጥ እንጂ!!በእነዛ ሁሉ ግን የራሱን ሞኞትና አስተሳሰበብ ፣ባርትና ጭቆና እንጂ አንድም ቀን በተለይ ከባለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ ለሰውም ሆነ ለእግዚአብሄር የሚሆን ዘር ዘርቶባቸው አያውቅም ብል ስሰተኛ አልባልም ፡፡የዳንኤል እይታዎች ብሎ ፡ ሌሎች እንዲያጡት እንጂ ማኝንም አይቶበት አያውቅም፡፡ልማታዊ ሰባኪ፣ ልማታ ዲያቆን ስለሆነ ነው፣ ቤተክርስቲያኗን በአብዮታዊ አስተሳሰብ የተቃኘ ኦርቶዶክስ መፍጠርና አረንጓዴ ቢጫ ቢጫ ቀይ ቀለም አትፍቶ በልማታዊው ቀለም መተካት፡፡ አንተ የዚህ ደቀመዝሙር የዚህ አገልጋይ ዲያቆን እንጂ ሌላ የማንነት ገጽ የለህም፡፡ አበቃሁ፡፡ የቅድስ ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ጉዳይ

የኢትዮጵያዊነት ድምጽ-Ethiopiawinet

posted by Tseday Getachew

Advertisements

Single Post Navigation

Comments are closed.

%d bloggers like this: