Fitih le Ethiopia

I wish democracy and unity for Ethiopia

ከጠቅላይ ፍ/ቤት እስከ ሚንስትሮች ም/ቤት

ተመስገን ደሳለኝ

መጋቢት 18/2005 ዓ.ም የእነ እስክንድር ነጋ ይግባኝ ለመጨረሻ ጊዜ ተብሎ ተቀጥሯል፡፡ በዚህ መዝገብ የተከሰሱት የህሊና እስረኞች ይግባኝ ከጠየቁ አምስት ወር አልፏቸዋል፡፡

ለምን? …በአዲስ መስመር እንነጋገርበት፡፡

የይግባኙን ውሳኔ ያዘገየው የፖለቲካ ተንታኝ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የተከሰሰው በሀሰት ስለሆነ ነው፡፡ በእርግጥ ይህንን ያልኩት እኔ አይደለሁም፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የመሀል ዳኛ የሆነው አቶ አማረ አሞኘ ነው፡፡ ባለፈው ወር ዳኛው አቃቢ ህጎቹን ሰበሰበና እንዲህ አላቸውከጠቅላይ ፍ/ቤት እስከ ሚንስትሮች ም/ቤት

፡-‹‹ይህን ሰው አሻባሪ ነው ብላችሁ ስትከሱት ያቀረባችሁት ማሰረጃ በተለያየ ጊዜ የፃፈውን ፅሆፎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ መድርክ ላይ ተናገረው ያላችሁትን ብቻ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ፅሁፉና ንግግሩ ያስከተለው አደጋ አልተገለፀም፤ ወይም ምንም አይነት አደጋ አላስከተለም ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተከሳሹ ላይ ቅጣት ለመጣል አያስችልም፡፡ ስለዚህም ሌላ ጥፋተኝነቱን የሚያረጋግጥ ማሰራጃ ካላችሁ አቅርቡ? አሊያም በሚቀጥለው ቀጠሮ ሲቀርብ በነፃ እለቀዋለሁ፡፡›

.አቃቢ ህጎቹ ምንም ማስረጃ አልነበራቸውምና በደፈናው ‹‹ሰውየው አሸባሪ ስለሆነ ዝም ብለህ፤ ይግባኙን ውድቅ አድርግና የከፍተኛው ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አፅናበት›› የሚል ይዘት ያለው ተመሳሳይ አቋም አንፀባረቁ፡፡ ዳኛው ምን አይነት መንፈሳዊ ኃይል ተጭኖበት እንደ ሆነ እንጃ! ‹‹በፍፁም ከህግ ውጪ አልሰራም፤ ህሊና አለኝ›› ብሎ ፍንክች ያባ ቢለዋ ልጅ ይላል፡፡ ይህን ጊዜም ነገሩ ቦግ ያደረገው አንድ አቃቢ ህግ

‹‹አንተ እስክንድርን እለቃለሁ የምትለው ያገርህ ልጅ ጎንደሬ ስለሆነ ነው!›› ይለዋል ቁጣ በተቀላቀለበት ድምፅ፡፡ ዳኛ አማረም ይበልጥ ተናዶ

‹‹እኔ እሰከ ዛሬ ድረስ ያገለገልኩት ሀገሬን ኢትዮጵያ እንጂ የትውልድ መንደሬን አይደለለም፡፡ ደግሞም ዘረኝነት የለብኝም›› ሲል መለሰለት፡፡

በእንዲህ አይነት ሁኔቴ መዋዘገቡ በመካረሩ መግባባት አልቻሉምና ጉዳዩ ሚንስትሮች ምክር ቤት ደረሰ፡፡ በሚንስትሮች ም/ቤትም ስብሰባውን የመራው ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ደመቀ መኮንን ሲሆን፣ ዳኛውም አብሮ ቀርቧል፡፡ አቶ ደመቀ መጀመሪያ ዳኛው ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠየቀ፡፡ ዳኛውም ስለክሱ አጠር አድርጎ ካብራራ በኋላ እንዲህ ሲል ደመደመ፡-

‹‹እስክንድር ነጋን ‹አሸባሪ› ብሎ ለመፍረድ የሚያስችል በቂ ማስረጃ ስላልቀረበ በሚቀጥለው ቀጠሮ በነፃ አሰናብተዋለሁ፤ እንዲህ ማድረግ አትችልም የምትሉኝ ከሆነ ግን ክቡራን ሚንስትሮች በዕለቱ በችሎት ለመሰየም ፍቃደኛ አለመሆኔን በትህትና ትረዱኛላችሁ ብዬ አስባለሁ!››

ከዚህ በኋላ ሚኒስትሮቹ መወያየት ጀመሩ፡፡ ተከራከሩ፤ በመጨረሻም አቶ ደመቀ እንዲህ አለ፡-

‹‹እኔም ከአቶ አማረ ጋር እስማማለሁ፡፡ ምክንያቱም በዚህ ሰውዬ /እስክንድር/ የተነሳ ከፍተኛ አለም አቀፍ ጫና እየደረሰብን ነው፡፡ ስለዚህም ብንፈታው ተጠቃሚዎቹ እኛው ነን ብዬ አስባለሁ፡፡›› አንድ ሚኒስትር ቀጠለ፡-

‹‹በመሰረተ ሃሳቡ ላይ እስማማለሁ፡፡ ነገር ግን እስከዛሬ አስረነው ‹ነፃ ነህ› ብለን ብንለቀው የፖለቲካ ኪሳራ ስልሚያስከትልብን፣ ከፍርዱ ላይ ቅንስናሽ አድርገን ይቅርታ ጠይቆ እንዲወጣ ብናደርግ የተሻለ ነው፡፡›› ሌላ ሚኒስትር ቀጠለ፡-

‹‹እስክንድርን እኔ አውቀዋለሁ፤ የአሜሪካን ሀገር መኖሪያ ፍቃድ እና ብዙ ሀብት እያለው እዚህ ነገር ውስጥ የገባ ሰው ነው፡፡ እናም በፍፁም ይቅርታ ለመጠየቅ ፍቃደኛ አይሆንም›› ሌላኛው ሚንስትር ቀጠለ፡-

‹‹ኧረ ለመሆኑ መለስ አለም አቀፍ ጫና እንደሚያስከትል እያወቀ ለፓርቲያችን ጥቅም ብሎ የገባበትን ጉዳይ፣ ዛሬ እርሱ አልፏል ብለን ጫና ይምንፈራበት ምክንያት ከየት የመጣ ነው? በቃ! መለስ አደገኛ ሰው ነው ብሎ አስሮቷል፡፡ አለቃ! እዛው ይበስብስ!›› የሚንስትሮች ምክር ቤትም ቢዚህ ጉዳይ ላይ መስማማት ሳይችል በመቅረቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት አቶ ተገኔ ቀርቦ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ቀጠሮ ይዘው ተለያዩ፡፡

…በእርግጥ ከአቶ ተገኔ ማብራሪያ በኋላ የሚኒስትሮች ም/ቤት ምን አይነት አቋም ላይ እንደደረሰ ለማወቅ ያደረኩት ጥረት ሊሳካ አልቻለም፡፡ መረጃውንም እስከ ዛሬ ያቆየሁት ለዚህ ነበር፡፡ አሁን ግን የቀጠሮ ቀን ሰለደረሰ ልነግራችሁ ተገደድኩ፡፡ እናም የፊታችን ረዕቡ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሚከተሉት አራት ነገሮች አንዱን እናያለን ብዬ አስባለሁ፡፡

1. የሚንስትሮች ም/ቤት ጫናው ስለከበደው በነፃ ይለቀዋል፣ 2. መለስ እያወቀ የገባበትን ጫና አንፈራም! (ራዕዩ እናስቀጥላለን እንደማለት ነው) በማለት የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ያፀናሉ፣ 3. ከተፈረደበት 18 ዓመት ላይ ቅንስናሽ አድርገው፣ ይቅርታ እንዲጠይቅ ወደ ማግባባቱ ይሄዳሉ፣ 4. ዳኛው አሞኘ እንደፎከረው ከችሎቱ ይቀርና አሁንም

‹‹የመጨረሻ›› ቀጠሮ ይሰጣል፡፡ የሆነ ሆኖ እንዲህ የሚል አንድ እውነት ‹‹በመሪዎቻችን›› ግንባር ላይ ተቸክችኳል፡፡ ‹‹ሲቪሉ ጀግና እስክንድር ነጋ እያርበደበደው ነው!››

አዎ! እኔም እላለሁ፣ የእስክንድር እና መሰሎቹ የግፍ እስር አርብድብዶ ብቻ አይተዋችሁም!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ! ውድቀት ለአምባገነኖች!!

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/6658

posted by Tseday Getachew

 

Advertisements

Single Post Navigation

Comments are closed.

%d bloggers like this: